አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ

እድላችን ነው: አሁን መነሳት ያለበት ጥያቂ አይደለም።
መልሉ የተሰጠ ጥያቄ ጥያቂ ሊሆን አይችልም
ይልቅስ ሁሉንም በፀጋ ተቀብሎ መኖር ነው" ለምን በምን. ላይ ያተኮረ
ሃሳብ  ሃሳብ እንዳላት ሊገባው  አልቻለም  ስለዚህ ደስታው እየኮለመነ ግራ መጋባቱ እያየለ ሄደ።

“ልታነጋግሪኝ የፈለግሽው ምንድን ነው? ፈገግ ለማለት
እየሞከረ በጥሞና ጠየቃት:

“...እንደውሻ ቢያላዝኑ ሰሚ በሌለባት ምድር ለምን
ተወለድሁ! መወለዴን ሳስበው ይቆጨኛል! መሞቴም ያበሽቀኛል፤
ለምን ተወለድኩና ለምንስ ደግሞ እሞታለሁ። ስወለድም ለሞት
የምኖረውም ለሞት... አይኖችዋ ድንገት በእንባ ተጥለቀለቁና ቁልቁል ተደፋ: ያን ጊዜ ጨነቀው፡
የሚለበልበው እንባዋ
የማያውቃት ልጅ ድንገት እቤቱ መምጣቷ ብቻ አንሷት እንደበደላት ሁሉ ስታለቅስበት የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፋው።

“የኔ እህት የሶራ ገልቻ ቤት የብሶት መወጫ የበደል
ማራገፊያ ነው ያለሽ ማን ነው?... ደግሞስ እንዲህ ስታለቅሺ ሰው ቢመጣ ምን ይላል? ልቅሶ ካማረሽ ብሶትሽን ማካፈል ከፈለግሽ...”ብሎ በውስጡ የተፈጠረውን ሃሳብ በአእምሮ አዘጋጅቶ ከመቋጨቱ በፊት አናጠባቸው:

“ወኔ ቢስ! ይህን ስትል አታፍርም አይደል! እልህ
ውስጥህ አይንጠውም አይደል!  እዚች ሃገር መወለዴ እድሌ መሆኑ ጠፍቶኝ የጠየቅህ ይመስልሃል?  እንዴት ያስጨነቀኝ ጥያቂ መለስህልኝ ባክህ ጅል!" ብላ በእልክ እያለቀሰች በስርዓት የተጠቀለለ ፀጉሯን ነጨችው።

“ቆይ እስኪ እንዴ
እኔ አልበደልኩሽ የኔ እህት: አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዲሉ ካለበደሌ..."

ዝም በል! ደሞ አልበደልኩሽ ይላል”  በለባጣ ሳቅ ተፍለቀለቀች። ጥርሶችዋ ያምራሉ! እያለቀሰች እንኳን አይኖችዋ
ያንፀባርቃሉ በጣቶችዋ
የምትበትነውኀፀጉሯም ውበቷን አላጎደለውም:

“ጤነኛ ነሽ? ለመሆኑ ከማን ጋር ለምን እንደምትነጋገሪ
ታውቂያለሽ?" አላት ትንሽ መረር ኮስተር ብሎ።

እሷ ግን “እብድ  መሰልኩህ? እልኸኛ በመሆኔ በማስመሰያ ግብረገባዊነት በውስጤ የሚንተከተከውን ሃሳቤን ሳላፍን እንደ እሳተ ጎሞራ ፈንድቶ ሲወጣ እየለበለበኝ የሚፈሰው እንባዬን,
ስሜቴን በማካፈሌ እብድ በለኛ! ለነገሩ ማን መርምሮኝ ጤንነቴን
አውቀዋለሁ። አመመኝ ስል አውልቂ እባላለሁ... በሽታዬ ይገኛል እፈወሳለሁ ስል ጭኖቼ ተበርግደው ቆሻሻ ይደፉብኛል”  ብላ
በትዝብትና ጥላቻ አየችው።

ከሴት ልጅ የምትፈልጉት ይህን ነው አይደል?!" ቀሚሷን ወደ ላይ ገለበችው:: ፈጣን አይኑ በለስላሳ ጭኖችዋ አልፎ
በለበሰችው ስስ ፓንት ያለውን ነገር ተመለከተ:

“...ይህን እንካ ብልህ እብድ ነሽ! አትለኝም ነበር። ከሃሣቤ ይልቅ ሳያስረዱህ የምታውቀው የስሜት ለሃጭህን የምታዝረከርከው
የሴት ልጅ ጭን ስታይ ነው አይደል!... ብሽቅ! አለችውና
ጭንቅላቷን ያዘች

“..እኔ ምንህም አይደለሁም. የአንተ እህት ግን ጓደኛዬ ናት። እንደ ሎሚ ተመጣ የምትጣል! ጭኖችዋን ለስሜት ሳይሆን ለገንዘብ የምትከፍት! የማታውቀውን ጠረን የምትታጠን... ለመሆኑ ስለእሷና ስለጓደኞችዋ አስበህ አዝነህ... ታውቃለህ? እህትህ ለተጠማው ወንድ ሁሉ በገንዘብ ተገዝታ የምትጠጣ መጠጥ
ተመልሳ ደግሞ እንደ ሽንት ቆሻሻ ላይ የምትሸና ጉድፍ መሆኗን ታውቃለህ?"

እህትህ' ስትል ነደደውና
ሶራ በጥሞና ሲያዳምጣት እንዳልቆዬ ሁሉ እህትህ
“የማን እህት?... የኔ... የኔ እህት?…" አፈጠጠባት: በንቀት እያየችው ቆየችና ረጋ ብላ፦

“ጠባብ በአብራh ክፋይ የምታምን ቂል. ሸርሙጣ እህት የለኝም እያልክ ያን የበከተ እምነትህን በመግለፅ ልትኮፈስ ይሆናል።''

“የኔ እህት ልትሰድቢኝ'ኮ…"

“ዝም በል  አንተ?” ባረቀችበት።

“የተማርከው! እንደ ባንዲራ እየዘመራችሁ ወደላይ ስቀሉኝና አየሩ ላይ ልውለብለብ ንፁህ አየር ነፍሴን ያስደስታት የነዳያንን
ጩኸት ወደማልሰማበት ፉከታቸውን ወደማላይበት! ወደላይ ሽቅብ ልውጣ... ባይ ነህ አይደል! እንደ ብዙዎቹ ምስኪን ያገራችን
ምሁራን፡

“የኛ መማር ከድሃው Uዝብ በተለየ ደሴት ውስጥ ለመኖር ነው። የተማርነውን
ንድፈ ሃሳብ ኮሯጆችን ውስጥ ከተን አንጨምርበት አኝከን አንትፋው ስንውጠው አንታይ!... ብቻ
ተሸክመነው እላይ ወጥተን መውለብለብ  ንግግሯን ገታ አድርጋ አየችው አያት፡ ተያዩ ምን እንደሚላት ጠፋው: ውጭልኝ ለማለትም ወኔ አጣ: እሷ ግን ቤቱን ደግማ አማተረች:: አይኗ
ከምኝታው ራስጌ ካለው ኮመዲኖ ባለው የሚማርh ፍሬም ላይ አረፈ።

“ምንድን ነው ይሄ?” ብላ ፈገግ እያለች በንቀት አየችው:

“የቱ?” አላት ወደራስጌው እየተመለከተ

"ዲግሪ ስትቀበል የተነሳኸው ፎቶ! አለችና ሳቀችበት።

“አያምርም! አየ አስተያየት አየ መልክ... አቤት ኩራት!
አሁንም የምፀት ሣቋን ለቀቀችው።

“...ምን ሰራሁበት ብለህ ነው ከራስጌህ ያስቀመጥከው?
መካኒክ የመካኒክነት ሙያ ንድፈ ሃሳብ በመማሩ መፍቻዎቹን ደረቱ
ላይ ደርድሮ ፎቶ ቢነሳ ምንድነው ትርጉሙ?  ጉራ ብቻ! ሥራበት አዲስ ቅርፅ አዲስ ምርት አምርትበት  ጠቅመህ ተጠቀምበት
የተባለውን መፍቻ እንደሰራው ሁሉ ደረቱ ላይ ደርድሮ ፎቶውን ገጭ አድርጎ ግድግዳው ላይ ቢሰቅለው ወይንም እንዳንተ ኮሚዲኖው ላይ ቢያስቀምጠው ፍችው ምንድነው?

ሶራ ተቁነጠነጠ ቀዝቃዛ ላብ በጆሮ ግንዱ ስር ተንቆረቆረ: “...ሌሎች የፈጠሩትን ለማወቅህ  ሌሎች ያሉትን ለመስማትህ የተቀበልከውን መተማመኛ
የደረሰህን ለማዳረስ ቃለ መሃላ የፈፀምክበትን ጥቁር ጨርቅና ወረቀት ለሰራኸው ቁም ነገር ለፈፀምከው የስው ልጅ መልካም ተግባር እንደተሰጠህ ሁሉ ቀለሙ በሚጮህ ፍሬም ውስጥ ከተህ ለእይታ ዳረግኸው፡

“ማንነትህ እንዲታወቅ... ያልተማረ እንዳትባል... በሃሣብህ ጨቅላነት የናቀህ ፎቶህን አይቶ እንዲያከብርህ እንደ ፋሲካ ዶሮ አልጋህ ላይ ልታርዳት የምታመጣት ሴት ኧረ የተማረ ይግደለኝ
ብላ በንድፈ ሃሳብ ሞረድ በተሳለው ምላስህ ሳትፈራገጥ
እንድትታረድልህ... ነው አይደል! ዲግሪ የተቀበልክበትን ፎቶ ራስጌህ ያስቀመጥኸው:

“ስትሰራ ህዝቡን ስትረዳ.. የተነሳኸውማ ምን ማስታወሻ አለህ? ማረሻ የያዘና ባዶ እጁን የቆመ ሁለቱም አንዳች ሥራ
እስካልሰሩ ድረስ ምን ለውጥ አላቸው?

“ለመሆኑ ለምን እዚች አገር ተወለድሁ? ከኬንያ
ከታንዛንያ... ያነሰች ደሃ ተብላ በምትናቅ፤ እምትኮራበት ታሪክ
አንጂ ቤሳ ቤስቲኒ ስልጣኔ በሌለባት ሃገር ለምን ተፈጠርሁ ብለህ
ቀንተህ ታውቃለህ  ከርሳም ጀብ ድሮ ጅብ ሆዱ ከሞላ በየት አገር ነው የሚቀናው: ሆዱ ከሞላ ባገኘው የቀበሮ ጉድጓድ ገብቶ መጋደም ነው: ክርፋቱ አይሸተው ጥንብ ነው ብሎ አይጠየፍ ስለ ማደሪያው አያስብ…

“በእንዳንተና እኔ አይነት ግዴለሾች ግን ችግር ችግር
እየተከመረ ዋጠን በህሊናና እጆቻችን ሰርተን ከመጠቀም ይልቅ
የህይወት ከርፋት ውስጥ ተጠቅልለን ማልቀስ መጮህ... እጣ ፈንታችን ሆነ" አላችና በሐዘን አንገቷን አቀረቀረች᎓ እንባዋ ዱብ
ዱብ ሲል ታየው: የመጣችበት ጉዳይና የምትናገርበት ምክንያት
👍372
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አራት
////

እንዳትሰማኝ ድምፄን ዝቅ አድርጌ‹‹የእውነት አድናቂሽ ነኝ"አልኩ  ..እውነቴን ነው ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ብቻዋን ገልብጣ ገድገድ ሳትል ...እኔ ገና በግማሽ ብርጭቆ ጉልበቴ  እየተብረከረከ ነው።

ተነሳሁና የተከፈቱ መስኮቶችን መዘጋጋት ጀመርኩ..ማብራቶችን አጠፍሁ፡፡ የሴትዬዎን ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ይዤ ወጣሁና የሆቴሉን በራፍ ቆልፌ ቁልፉን በጥንቃቄ ሚስጥር ኪሴ ውስጥ ሽጉጬ  ወደ አልጋ ክፍል አመራሁ...አቀብያት በዛው ወደ ቤቴ ሄዳለሁ ሞባይሌን አውጥቼ ሰዓት ሳይ 7፡40 ይላል።
ደረስኩና አንኳኳሁ...

‹‹ግባ ክፍት ነው››

የሚል ድምፅ ስሰማ ቀስ ብዬ በራፍን ወደ ውስጥ ገፋ አደረኩትና  ውስኪ ጠርሙስ የያዘ እጄን አስቀድሜ አንገቴን አሰገግኩ፡ መሀል ወለል ላይ ቆማ ተበትኖ ጀርባዋ ላይ የተኛውን ፀጉሯን አንድ ላይ ጠቅልላ እያሰረችው ነው..ቅድም ለብሳ የነበረውን ጅንስ ሱሪ አውልቃ ስስ የለሊት ቢጃማ ቀሚስ ለብሳለች...፡፡ ቢጃማው ሮዝ ቀለም ሲኖረው አጭር እና በቀላሉ አይን ውስጥ የሚመሰግ ነው...አስተውሎ ላየው ቀሚስ ሳይሆን ቁምጣ ነው የሚመስለው..እና ያ የሚንቀጠቀጥ እና ሊፈርጥ የደረሰ ዳሌዋ በከፊል እርቃን ነው...፡፡

"በራፍ ላይ ተገትረህ ታድራለህ ወይስ ትገባለህ ?"

"እ እሺ ገባለሁ ››አልኩና ወደውስጥ ገብቼ ጠርሙሱን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጬ ለመውጣት ዞር ስል  እሷ ከቦታዋ ተንቀሳቅሳ ወደበራፍ እያመራች ነው፡፡

‹‹...ብርድ አስመታሀኝ ››"በሚል ሰበብ  ክፍት ጥዬ የመጣሁትን በራፍ ዘጋችና ቆለፈችው፡፡

"ቆይ እኔ ሳልወጣ?"አልኩ ደንግጬ፡፡

"ትንሽ አጣጣኝ እና ትሄዳለህ.. ያውልህ ብርጭቆ…

"ቅዳልኝ" የንግግሯ ቃና ወደ ትዕዛዝ ያዘነበለ ነው.፡፡
ግራ በመጋባትና በመርበትበት  እንዳለቺኝ አደረኩና እዛው ጠረጴዛ ጎን ያለ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ..፡፡እሷም ወደእኔ መጣችና ብርጭቆዋን አንስታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች ...፡፡አቀማመጧ በእኔ ትክክል ነው...፡፡አይኔ ወደታች ወደተጋለጠው ጭኗ እየተንሸራተተ አስቸገረኝ ፡፡...እሷ የእኔን ሁኔታ ከቁብም የቆጠረች አይመስልም፡፡ጭኗ እንደሴቶች ጭን ልል እና ለስላሳ አይደለም…፡፡እንደስፖርተኛ የዳበረ እና ፈርጣማ ነው፡፡ሲነኩት ትንቡክ የሚል አይነት ሳይሆን ሲነካ ጭፍልቅ  የሚያደርግ አይነት፡፡

"አሁን ጋሼ እንዲህ ከእንግዳ ጋር በውድቅት ለሊት ቤርጎ ውስጥ  ገብቼ ዘና ስል  ቢያየኝ ምን ይለኛል? ጓደኞቼስ ቢያዩ ተረባቸውን እችለዋለሁ?››

በዝምታ ውስጥ ሆና የቀዳሁላትን  ጠጥታ  ጨረሰችና ከተቀመጠችበት ተነስታ እራሷ ለራሷ ቀዳች ፡፡..ልትቀዳ ስትል ታከከቺኝ..እናም ደግሞ የተቀባችው ሽቶ ያለፍላጎቴ በአፍንጫዬ ሰርጎ ገባ...እና እየጠጣሁ ካለሁት መጠጥ ጋር ተጋግዞ አነቃቃኝ...፡፡

ወደቦታዋ ተመልሳ ተቀመጠች ፡፡አቀማመጧ ግን እንደቅድሙ እግሮቿን አጣምራ ሳይሆን ፈርክክ አድርጋ ከፍታ ነው፡፡ ...እና በክፍተቱ አይንን ሚያጥበረብር ቀይ ፓንት አየሁ..፡፡ለምን አየህ ?ብላ ተነስታ የምታንቀኝ መስሎኝ  ከመርበትበቴ የተነሳ ብርጭቆ ውስጥ ያለችውን መጠጥ በአንድ ትንፍሽ ገርገጭ አድርጌ አጋባኋት፡፡

"በቃ እግዜር ይስጥልኝ አሁን  መሸብኝ ልሂድ..›› ለማለት አስቤ ገና አፌን ሳልከፋት ከተቀመጠችበት ተነስታ በድጋሚ ቀዳችልኝ፡፡ ..ለመናገር የተከፈተ አፌን ቀስ ብዬ ዘጋሁትና  አንዴ መጠጡን አንዴ እሷን እያፈራረቅኩ ማየት ጀመርኩ።"አሁን ብዥ እያለብኝ ነው..፡፡ሞባይሌን አወጣሁና ሰዓት ተመለከትኩ...8:18 ይላል።

"ምነው መሸብህ እንዴ?"

"አይ አንቺን እንቅልፍ ነሳሁሽ ብዬ ነው"

"ጥሩ አስመሳይ ነህ"አለችኝ.፡፡

‹‹እስቲ በጌታ አሁን እንዲህ ይባላል?››አንገቴን በእፍረት ከማቀርቀር ውጭ ምንም መልስ አልሰጠኋትም፡፡ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደሻንጣዋ በመሄድ መጎርጎር ጀመረች‹‹...ምን ልትሰጠኝ ነው?"ብዬ ሳሰላስል  ክሬም ቅባት አወጣችና አልጋ ላይ ወረወረች..መቀመጫዋን ወደ እኔ ፊቷን በተቃራኒው ወደግድግዳው አዞረችና በቆመችበት አጭሩን የለሊት ቀሚሷን ሞሽልቃ አወለቀች።አይኖቼን ጨፈንኩ..ገለጥኩ...መልሼ ጨፈንኩ...ቅድም በስሱ ካየሁት  ቀይ  ፓንት በስተቀር ምንም የጨርቅ ዘር በሰውነቷ አልቀረም....፡፡ጡቶቾ እንደሩሲያ አስፈሪ ሚሳዬሎች ጫፋቸውን ወደእኔ   ቀስረው ልቤን አራዷት ብላችሁ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን እየታዩኝ አይደለም፡፡ፐ!! ከኃላዋ የሚታየው የሰውነቷ  ቅርፅ  ግን ከአንገቷ በላይ ያለውን መልኳን በሁለት ሶስት እጥፍ ይበልጣል።

ዘለህ ተጠምጠምባት የሚል ስሜት  ከሁሉም የስሜት ህዎሳቶቼ ተሰባስቦ ጉሮሮዬ ላይ ተወተፈብኝ... እጇቼ ገላዋን ለመዳሰስ አይኖቼ ከግራ ወደቀኝ እያገላበጠ  መላ ሰውነቷን በምስጠት ለመመልከት፤ አፍንጫዬ አንገቷ ስር ተደፍቶ ጠረኗን ወደውስጥ መማግ፤ጆሮዎቼ አፍ አካባቢ ተለጥፈው ከአንደበቷ የሚወጣውን ሹክሹክታ በፅሞና ለማዳመጥ እና እንትኔ ደግሞ ጭኖቾን ፈልቅቆ ወደ ውስጠቷ መስመጥ ፈለገ(ውይ እንትኔ ለካ የስሜት ህዋሳቴ አይደለም...ነው እንዴ?)

ዘፍ ብላ በሆዷ አልጋው ላይ ተኛች...አሁን በህይወቴ በአካልም በፊልምም ጭምር ካየኋቸው ባለ እርቃን ሴቶች ሁሉ ተወዳዳሪ የሌላት ፍፅም አማላይ ሆና ታየችኝ፡፡.. ፀጉሯ ብትን ብሎ ከፊል ጀርባዋን እና የተንተራሰችበትን ትራስ ሸፍኖታል..፡፡ከዛ ወረድ ስንል ልምጥ  ብሎ የሚታየው ወገቧ  የሩብ ጨረቃን ቅርፅ ይዞ አይንን ያፈዛል ፡፡..ከዛ ሽቅብ ወደላይ ስንወጣ መቀመጫዋ ቀይ ፅጌረዳ አበባ የሸፈናቸው ግዙፍ መንታ ተራሮች ይመስላሉ፡፡..ከዛ በመነሳት ለሁለት ተከፍለው የተዘረጉት እግሮቾ ለምለም መስክ ላይ የተዘረጋ የአክሱም ሀውልትን ይመስላሉ...እጣቶቾ ደግሞ....

"ትንሽ እሸኝና ትሄዳለህ.."የሚለው ንግግሯ ስለውበቷ ተቀኝቼ ሳልጨርስ ከሀሳቤ አናጠበኝ።

" ሎሺኑን ተጠቀምና እሸኝ.."ደገመችልኝ።

"እሸኝ ማለት ምን ማለት ነው..?እንዴት ነው የማሻት..?የሚታሽና የማይታሽ የሠውነት ክፍል ይኖራት  ይሆን ?ካሸዋትስ በኃላ የሚከተል ነገር ይኖራል..?በሰከንድ ውስጥ በምናቤ  ብልጭ ድርግም ያሉ  ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው..፡፡እጆቼን ሰበሰብኩና ወደአልጋው ተራመድኩ፡፡ ጠርዝ ላይ ተመቻችቼ ተቀመጥኩ..፡፡ጃርባዋን ያለበሰውን ፀጉሯን ሰበሰብኩና ወደትራሱ አሻገርኩት...እና ሎሺኑን አነሳሁና ጨመቅ ጨመቅ አድርጌ እጄ ላይ አፈሰስኩና   ከትከሻዋ ጀመርኩ...፡፡ይህ ሰውነት ከዚህ በፊት እንደማውቃቸው የሴት ገላዎች የሀር ጨርቅ አይነት ልስላሴ የለውም..፡፡በዳበሩ ጡንቻዎች የተገነባና በጠንካራ ቆዳ የተሸፈነ ልዩ አይነት ሰውነት ነው፡፡ቢሆንም ሲያሹት እጅን ሙልጭ ሙልጭ እያደረገ ቢፈታተንም ደስ ይላል፡፡ ‹‹ አዎ ትግስት ካለኝ  ተገልብጣ በጀርባዋ ስትተኛና ከፊት ለፊቷ ያለውን የሰውነት ክፍሏን እንዳሻት ስትመቻችልኝ ቀስ ብዬ ልክ እንደዚህ ሎሺን ጡቶቾን አሸት አሸት እያደረኩ ከውስጣቸው ፍቅር እንዲያመነጩ አስገድዳቸዋለሁ፡፡›› ስል በአይነ ህሊናዬ በመሳል ጎመዣሁ..ምራቄን ገርገጭ እያደረግኩ ዋጥኩ ።
👍541
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_አራት

ዘርሲዎች ግማሽ ክብ ሰርተው ከመንደሩ ራቅ ብላ ዙሪያ ገቡን ከምታሳየው
የግራር ዛፍ ስርቁጭ ብለዋል ጩሉሌዎች
አንገታቸውን ቁልቁል ደፋ አድርገው በዛ ዙሪያ ያንዣብባሉ: ነፋሱ
ቅጠሎችን ጎንበስ ቀና እያደረገ ይነፍሳል 
ከፊት ለፊታቸው ርጥብ
ቅጠል ተነጥፏል  መሃል ላይ ጎረምሶች የተጠበሰውን የፍየል ስጋ እየቆራረጡ የፍሪንባውን ሥጋ በእድሜ ለገፉትና በጀግንነታደው ለሚታወቁት ለሌሎች ደግሞ ከተለያየውደ የስጋ አይነት እፊት ለፊታቸው ካለው ቅጠል አስቀመጡ" ህፃናት ጨዋታቸውን አቁመው ራቅ ብለው ሲቁለጨለጩ ቆይተው እደላው አልቆ መብሉ ሲጀመር ወደየአባቶቻቸው ጉያ ተሸጉጠው ዳረጎታቸውን እየተቀበሉ ከአጥንት ጋር መታገል ጀመሩ በመጨረሻ የሚበላው ከተበላ: ቀሪውን ደግሞ ጎረምሶቹ ካቀለጣጠፉት በኋላ ወጣቶቹ ቅጠሉን ሰብስበው ጥለው
ከስብሰባው አካባቢ ርቀው ሄዱ።

የሽማግሎች አለቃ ጦራቸውን ይዘው ከተቀመጡበት ተነስተው
ከፈርሱ እግራቸውን ቀባ አድርገው ወዲህ ወዲያ ወዲያ ወዲህ አሉና፣
"የአባት ደንብ ጥሩ ነው" በልክ መብላት የአባቶቻችን ባህል ነው አባቶቻችን የራበውና የጠገበ ትክክል ፍርድ አይሰጥም ይሉ
ነበር" የጠገበ ወንድ ሴት ማለት ነው መሳቅ ቧልት ይወዳል ከብቶችን አይፈቅድም ጫካውን አይቃኝም ከጓደኞቹ ጋር
አይመክርም መዝለል አይችልም መቀመጥና ማንጎላጀት ይወዳል
ትክክለኛ ፍርድ በዚህ ምክንያት አይሰጥም ይሉ ነበር አባቶቻችን" ሽማግሌው እቱፍ: እቱፍ
ብለው የጦሩን ዘንግ በምራቃቸው ቀባ ቀባ እያደረጉ ሽማግሎችን:
የአባታቸውን አገር አድማስ እየተዟዟሩ አይተው

አባቶቼ የራበውም ከጠገበ አይሻልም ይሉ ነበር የራበው ሰው ሰነፍ ነው
ሲኖረው አያውቅበትም
የወደቀችው ጀንበር:
የጠፋችው ጨረቃ ተመልሰው  የሚመጡ
አይመስሉትም እንደ
አጋሰስ ፈረስ ዘመዶቹ ለመቋቋሚያ የሰጡትን ፍየሉንም፥ በጉንም
ከብቱንም: እህሉንም ብቻውን እየበላ ነገን ዘንግቶ: ልጆቼ: የአባቴ
ምክር ሳይል ሁሉን ያሟጥጥና የሚያልበው ሲያጣ የሚበላው
ሲቸግረው ሰውን: መሬቷን: ቦርጆን: አባቶቹን ይራገማል" ሆዱን
ለመሙላት ይቀማል ይዋሻል … ፍቅር አያውቅም ዘመድ ወገን አይለይም
አያስተውልም፤ ጨካኝ ነው
በዚህ ምክንያት
አባቶቻችን የራበው ሰው ትክክል አይፈርድም ይሉ ነበር አባቶቻችን ትክክል ናቸው ወንድሞቼ ጥጋብ ልቦናን ያዛባል ረሃብ ደግሞ ተስፋ መቁረጥንና ጥላቻን ያመጣል ከሁሉም የሚከፋው ደግሞ ሁለቱም ያስዋሻሉ" ብለው በርኮታቸው ላይ ቁጭ አሉ
ዝምታው ቀጠለ ሐመር ላይ ተረትን ሽማግሌ ለሌላው ማስታወስ እንጂ አይጨርሰውም የሰሙት እኩል: የፈፀሙት እኩል … ስለሆነ ተረት ጨራሽ አዳማጭ የለውም"

"በሉ ተናገሩ?" አሉ ሽማግሌው ከጥቂት ቆይታ በኋላ ጥሩ ነው! ከወደ መሃል አንዱ ድምፅ አሰሙ ገልመጥ ብሎ ያዬ የለም ሁሉም ግን አባባላቸውን በጆሮው ቀልቧል።

"ጥሩ ነው!- በአካል ተለይተውን ነፍሶቻቸው ደንቡን ጥበቃ አብረውን ላሉት ወንድሞቻችን ተገቢው ደንብ የሚሰራበት
ቀን ይመረጥ ልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው በየበረሃው የአሉትን ተባት በግና ፍየሎች ከብቶችን ያስመጡ" በየመንደሩ ለሚኖሩት ዘመድ ጓደኞችም ጥሪ ይላክ ለዚያ ደሞ ዛሬ ቀኑ ተቆርጦ ቋጠሮ ይዘጋጅ አሉ።

የሽማግሎች አለቃ ሌላ ኃሳብ አለመኖሩን በዝምታደ ጠበቁና አንድ ጎረምሳ ጠርተው ልጥ አምጣ አንተ" አሉት ልጡ መጣ
"ስንት ላይ ይቋጠር?"

"መከን ተቢ" አሉ አንድ ሽማግሌ በስተግራ በኩል
ከተቀመጡት ሰላሳ ለማለት ልጡ ሰላሳ ላይ ተቋጥሮ ለሟቹ ታናሽ ወንድም
ተሰጠው" የሽማግሎች አለቃ አንዱን ችግር
በመቋጨታቸው
"ባይሮ ኢሜ" አሉ ሽማግሎችን እግዜር
ይስጣችሁ ለማለት

"በሉ ቀጥሉ?" አሉ የስብሰባው መሪ

"ጥሩ ነው!" አለ ልጅ እግሩና የአባቱን ጠላት ገሎ በቅርቡ
ከሽማግሌዎች ጋር ለመቀመጥ እድል ያገኘው ሰለምቤ፤ "ጥሩ ነው!
ታለውሻ በቀር አባቶቻችን ከአውሬ ጋር አልኖሩም እና ካርለቴ ይዛብን የመጣችውን አውሬ በጥይት አጉኖ ራቅ አድርጎ መቅበር ነው "አለ ገና የጎረምሳነት ባህሪው ሙሉ በሙሉ ያልቀዘቀዘለት ወጣቱ ሽማግሌ አለመብሰሉ በአነጋገሩ ፍጥጥ ብሎ እየታየበት።

"ጥሩ ነው! አውሬ ማለት ከብት የሚበላ ችግር የሚፈጥር ነው የነጯ ሐመር  የካርለቴ አራት እግር አውሬ ሳይሆን መሂና
ነው የሚባል አባቶቻችን ደሞ መሂና የሚባል አውሬ አለ አላሉንም ደሞስ የካርለቴ መሂና እንደ ፈረስ እየጫነን ገበያ እያመላለሰን ነው እና መኖሩ ምን ጎዳ! አሉ ግራሯን የተደገፉት አንድ ዐይና

የአባት ደንብ እየሻርን ያ ይጎዳል ይሄ ይጠቅማል
ካልንማ ይህች አገርና ይህ ህዝብ መዓት ይመጣበታል" በነሱ ጊዜ ያልነበረ አውሬ አሁንም መኖር የለበትም " አሉ አገጫቸውን በግራ
እጃቸው ደግፈው የቆዩት ሽማግሌ ከዚያ ክርክሩ ከተለያዬ አቅጣጫ
መቅረቡ ቀጠለ

በአባቶቻችን ደንብ ፍየል ቢመጣ ፍየል ጋጥ: ከብት
ቢመጣ ከብቶች በረት ሰው ቢመጣ  ወደ ሰዎች መኖሪያ ጎጆ ይገባል እህ እንዲህ እስተሆነ ድረስ የካርለቴ መሂና የሚገባ
ፍየሎች ጋጥ ነው? ከከብቶች በረት ነው? ወይንስ ከሰዎች ጋር ጎጆ
ውስጥ! መቼም ተውሾች ጋር እየተሯሯጠ አውሬና ጠላት ይከላከላል
አይባል ይኑር ከተባለ ወገኑ ከማን ነው?  ተከብቶቹ ወይንስ ከእኛ! አሉ ከወደመሀል መፋቂያቸውን ሲያኝኩ የቆዩት ሽማግሌ

"ጥሩ ነው የሁላችሁም አስተያየት አዲስ ነገር መምጣቱ ይኸው ሁለት ሶስት ቦታ ከፋፍሎ አጨቃጨቀን ያልነበረ ነገር
ሲመጣ ያልነበረ ችግር ይፈጥራል ነጯ ሐመር የእኛ የሆነች እንግዳ ናት መሂና ያለችውን አውሬ ዱካውን ለማጥፋት በጥይትና ጦር
ደብድበን እንቅበረው ብንል እሷን እናሳዝናት ይሆናል"
ባይሆን አውሬሽን ካመጣሽበት ጫካ ጥለሽ ነይ ብንላት አይሻልም
ወንድሞቼ!" አሉ። አንተነህ ይመር  ጋልታምቤ ጎን የተቀመጡት ሽማግሌ

ተው! ተው! ይህችን ሰው ተማበራችን አታውጧት! እሷ
ሐመር ናት  የሐመር  ልጃገረድ ተቀብላማ እንደ እህቶችዋ የፍየል ቆዳ ለብሳ ለዘመዷ ለከሎ ከብት
የአባቷን ትክክለኛ ደንብ
ዝላይ ተገርፋ … እንዴት እንዴት ነው  እንደውጭ ሰው ይከፋታል ማለት! ከአባትሽ ባህልና ደንብ ውጭ ያመጣሽው አውሬ ቦርጆን ያስከፋል የአባቶቻችንንም ነፍስ ያሳዝናል እነሱ ተቆጥተው ዝናብ ከሚያጠፉብን በሽታ ከሚልኩብን አውሬሽን ቀብረነው እንረፍ
ብንላት በፍጡም አይከፋትም  ወዲያውስ ከሽማግሌ ቃል ወጥታ የት ልትደርስ ኧረ አይከፋትም!" አሉ የዘርሲዎች አለቃ ከዚያ ለረጅም ጊዜ ዝምታ ሰፍኖ ቆየ

"ጥሩ ነው! እንዳላችሁትም
ነጯ ሐመር የእኛ ናት, የእኛ
ያልሆነውን ግን ዝም ብለን ብንለቀው ምን እንደሚያመጣ አናውቅም ሲቆይ ልጆቻችንን  እሷን ጨምሮ: እኛን ይተናኮስ
አይተናኮስ ሳናውቅ እናጥፋው እስከተባባልን
ድረስ በኋላ ለቀን
ከምናሳድድ እዚሁ ገራም መስሎ አጠገባችን እንዳለ አድብቶ በጥይት ማጎን ነው የሚበጀው ካለበለዚያ
እኮ አስተውላችሁት እንደሁ
አላውቅም እንጂ አጉረምርሞ አጉረምርሞ ሰውነቱ የጋለ እንደሆን
እንደ ጥይት ከተፈተለከ
ድንጋይ አይል ውሃ ... ማን ጀግና   ያቆመዋል! ስለዚህ ሳይደነብር አዋዝተው ጎረምሶች በክላሽ ጥይት
ሆድቃውን እንዲነድሉት ማድረግ ነው"" እንዳሉ

"ይህስ እውነት ነው! በቀደም ሳላየው ሩም … ብሎ ባጠገቤ ቢያልፍ የድምፁ ወላፈን እንዴት አሽቀንጥሮ ወረወረኝ መሰላችሁ ተዚያ ንዴቱ ይሁን ድንጋጤው ሰማይ እሆን ምድር ጠፋኝ!" አሉ ሌላው አዛውንት
👍21
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ስንት ሰዓት   እንደተኛች አታውቅም፡፡ ፍፁም ሰላማዊና ህልም አልባ እንቅልፍ ነበር። ነቃች።ከአልጋ ወረደች።ቀለል ብሏታል። ወደፊት ለፊተኛው ክፍል ስትገባ ባዶ ነው፡፡ እንደውም ተዘግቷል። ‹‹ባዶ ቤት ጥሎኝ የት ሄደ...?፡፡››ቅር አለት፡፡የቤቱን ዙሪያ ገባ ስትቃኝ መሀል ጠረጴዛ ላይ ወረቀት አየች፡፡ ወደእዛ ሄደችና አነሳችው… አነበበችው"
                         

ይቅርታ ስምሽን አላወቅኩትም ለማንኛውም
አስቸኮይ ስራ ስላጋጠመኝ ወጥቼያለሁ..
ሳልመጣ የምትሄጂ ከሆነ መኝታ ቤት ኮመዲኖ ላይ የታክሲ ብር አስቀምጪልሻለሁ።
ቤቱን ቆልፊና ፊት ለፊት ለአከራዮ ስጪልኝ።
በይ እግዜር ይማርሽ...አመሰግናለሁ።

አንብባ ስትጨርስ‹‹በቃ..? ››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹አይ እስክትመጣ አልሄድም..››ስትል ቃል አውጥታ ተናገረች… .አጠገቧ ያገኘችው ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡

‹‹ስሜ ልዩ ነው፡፡››ይሰማት ይመስል  በድጋሚ ጮክ ብላ ተናገረች፡፡

"ደግሞ እንዴት ይሄን ሁሉ ነገር አድርጎልኝ ሳላመሰግነው እሄዳለሁ..?እንደውም ጥሩ ምክንያት አገኘሁ ለእማዬ ደውዬ እንግራተና እዚሁ አድራለሁ..ከዛ የሚፈጠረውን አያለሁ››አለች ድንገት ከመቀመጫዋ ተነሳችና….ወደመኝታ ቤት ተመልሳ ገባች.. እንዳለው ኮመዲኖው ላይ ብር አስቀምጦላታል…አነሳችውና ቆጠረችው፡፡ ሶስት መቶ ብር ነው። ኮመዲኖ የታችኛው ቁልፍ እላዩ ላይ እንደተንጠለጠለ ነው፡፡ የምታውቀወ ግን የምትጠላውና የመትጠየፈው ቢሆንም ደግሞ ልትቆጣጠረው የማትችለው ኃይል በውስጧ ሲሰርግ ታወቃት.... የተጣባት የሌብነት መንፈስ አንበረከካት፡፡ ቁልፉን አሽከረከረችው… ተከፈተላት፡፡ ውስጡ ብዙ ሰነዶችና አንድ ላፕቶፕ አለ."ያለምንም ማቅማማት ላፕቶፑን አነሳችውና ፤300ብር በእጇ ጨምድዳ ይዛ መኝታ ቤቱን ለቃ ወጣች….እንዳለት ቤቱን ቆለፈችና ቁልፉን ለአሮጊቷ ሰጥታቸው ሰፈሩን በላዳ ለቃ ወጣች፡፡

መሄድ የነበረባ ወደጦር ኃይሎች ነበር ..ከዛ ወደትምህርት ቤቷ ሄዳ ግቢው ወስጥ ያቆመቻትን መኪና ይዛ ነበር ወደሳሪስ መሄድ የሚገባት ግን አሁን እንደዛ ማድረግ አልቻለችም ቀጥታ…ላፕቶፑን በደረቷ ላይ ለጥፋ ከካሳንቺስ እስከሳሪስ እያለቀስች ነበር የደረስችው...ልክ ላፕቶፕ ካልሰረቅሽ ህይወትሽን ታጪያለሽ ብለው በግዳጅ እንዳሰረቋት ነገር ነው ሁኔታዋ የሚመስለው፡፡

‹‹አሁን ለዚህ ልጅ በዚህ ደግነቱ እንዲህ መዘረፍ ይገበዋል…?.እኔስ ዘራፊና ሌባ መሆን ይገባኝ ነበር…?አረ ጌታ ሆይ እውነት በመንበርህ ካለህ አንድ ነገር አድርግ..ነው ወይስ የሌባ ፀሎት አንተ ጋር ምንም እርባን የለውም…ምንም ሌባ ብሆነ እኮ ያው አንተው ነህ የፈጠርከኝ››ስትል አምርራ ወደፈጣሪዋ አጉረመረመች፡፡
///
እቤት እንደደረሰች በራፍን የከፈተላት ዘበኛ በድንጋጤ ጭንቅላቱን ያዘ፡፡ በረንዳ ስታፀዳ የነበረችው የቤት ሰራተኛም  መወልወያዋን በቁማ ጥላ‹‹  እትዬ..ልዩ ተጎድታለች..እትዬ ልዩ ተፈንክታልሽ መጣች....››እያላች ወደግዙፍ ባለሁለት ፎቅ ህንፃ ገባች..እሷ የሳሎን በረንዳ ላይ ስደርስ እቤት ውስጥ የነበሩት ቤተሰቦቾ በጠቅላላ በእናቷ ፊት መሪነት እየተንጋጉ ዙሪያዋን ከበቧት፡፡
…እናቷ እሪታዋን ለቀቀችው..‹‹ወይኔ ልጄን ይሄው ገደሏት…ወይኔ ምነው እመቤቴ ..?ምነው አንቺም ልጅ አለሽ …የአንድ ብቸኛ ልጅ እናት መሆን ፈተናውና መሳቀቁ ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ካንቺ በላይ የሚያውቀው የለም… ታዲያ ምን አለ ብትሰሚኝ   ››ልክ የሞተችና  ሬሳዋን ተሸክመውላቸው የመጡ ነው ያስመሰሉት፡፡
አዛኙም አሽቃባጩም በአንድነት ከበቧትና  አፋፍሰው ልክ መራመድ እንደማትችል ወደውስጥ ይዘዋት ገቡ፡፡ እሷም ሲደጋግፏት ያልነበረ ህመሟ ከያለበት ተሰብሰቦ ሰፈረባት፡፡ ጭንቅላቷ ላይ የሆነ ቋጥኝ የተጫነባት  ይመስል ውጥርጥር አድርጓታል፡፤ የጭንቅላቷ እብጠት ጥዝጣዜ ነርቯን ነካት
‹‹….እዛ ልጅ ጋር ይሄን ያህል ያለመመኝ እቤቴ ስገባ ለምን ተደበላለቀብኝ፡፡››እራሷን ጠየቀች፡፡
‹‹በሉ እዛ ደክተር ጋ ደውሉለት….በአስቸኮይ መጥቶ ይያተና ካልሆነ ሆስፒታል እንወስዳታለን.››እናቷ ናቸው በለቅሶ የታጀበ ትዕዛዝ የሚየዥጎደጉዱት፡፡
አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የተንጣለለው መኝታ ቤቷ አስገቧት
….‹‹.ዞር በሉላት በቃ አታጨናንቋት….››ብለው አስተኞት፡፡
‹‹ለመሆኑ መንግስት ባለበት ሀገር ከማን ተጣልተሸ ነው..?››በቀጣይ የጠየቋት ጥያቄ ነው
‹ግን በአሁኑ ወቅት ኢትዬጵያ ውስጥ እንዲህ አይነት ጥያቄ ይጠየቃል..? መንግስት እያለ ምን የማይደረግ ነገር አለ..?ግድያ ፣አስገድዶ መድፈር፣ከገዛ መንደር መፈናቀል…ነገሩ እንዚህ ሁሉ ወንጀሎች መንግስት ባለባቸው በማንኘኛቸውም ሀገሮች ይፈፀማሉ… በአሜሪካም ጭመር….አንዳንዴ እንደውም መንግስት እራሱ በእጅ አዙር ያስፈፅማቸዋል  …አንተ እያለህልን እንዴት እንዲባል?እናቴ ግን ምን ታደርግ  ሳሪስ  ላይ ተቀምጣ ስለእነዚህ ነገሮች በወሬ እንኳን ብትሰማ ከምታየው የቱርክ ፊልም ጋር ስለሚምታታባት እውነት ይሁን ውሸት ትዝም አይሏት….ለነገሩ እኔም እንደእሷው ነኝ…አሁን እራሱ ስለእንደዚህ አይነት ጠንከር ያለ ነገር እንዴት ማሰብ እንደቻልኩ አላውቅም...ምን አልባት ጭንቅላቴን ሲነርቱት  የሆኑ አንቀላፍተው የነበሩ ነርቮችን አነቁብኝ ይሆን እንዴ…?ኸረ አያድርገው…ጌታ ሆይ ስለፖለቲካና ዲሞክራሲ ሚበሉ ህልሞች የሚያስብ የእምሮዬን ክፍሎችን መቼም ንቁ እንዳይሆኑ እማፀንሀለሁ›› ስትል ፀለየች..መቼስ ይሄንንንም እንደሌሎች ፀሎቶቿ ችላ እንደማይልባ አየተማመነች፡፡
እናቷ እሷን መጨቅጨቃቸውን ቀጥለዋል‹‹ዩኒቨርሲቲ አመፅ ተነስቶ ነው…? ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተሸ ነበር እንዴ?ምን  ተከስቷ ነው?›
እናቷ የማትመልሳቸውን አያሌ ጥያቄዎች ያዥጎደጉድባታል…. ዩኒቨርሲቲ ያሏት.. ጥዋት ከቤት ቁርስ በልታ ዩኒቨርሲቲ ክላስ አለኝ ብላ በመውጣቷ ነው ፡፡ደግሞም ሄዳ ነበር….ልዩ የምትማረው ዪኒቲ ዪኒቨርሲቲ ነው..መኪናዋን ይዛ ወደእዛ ነበር የተጎዘችው..አንድ ክላስ እንደተማረች ግን የተለመደ ድብርቷ ተቀሰቀሰባትና መኪናዋን እዛው ግቢ ውስጥ እንዳቆመች፤ስልኳን እንኳን እዛው መኪናዋ ውስጥ ቻርጅ እንደሰካች  በእግሯ ከግቢው ወጣች ፡፡
በተክሲ ስትዲዬም ድረስ ከስቴዲዬም ደግሞ መገናኛ ሄዳ ነው እንግዲህ ያ ታክሲ ላይ ያጋጠማት ታሪክ የተፈጠረው..እንደዛም ስለሆነ ከወትሮ በተለየ ፀፀትና  ንዴት አልተሰማትም ነበር፡፡በጣም ልዩ በሆነ አጋጣሚ ከተለየ እና ተአምራዊ ከሆነ ልጅ ጋር ነበር ያገናኛት.. ምን ያደርጋል? አፈፃፀሙን አበላሸችው… የማትፈልገውን ላፕቶፕ ሰርቃ ያንን የመሰለ አጋጣሚ በማጨመላለቋ እራሷን ተጠይፋለች፡፡አሁን በሰውነቷ ካለው ቁስል በላይ ክፉኛ እየጠዘጠዛት ያለው ይሄ ነው፡፡
..‹‹ግን ወድጄ ነው እንዴ  እንደዛ ያደረኩት?››ስትል እራሷን ለማፅናናት ሞከረች፡፡
ሁሉም መኝታ ቤቷን ለቀው እንዲወጡ ተደረገና በክፍሉ እናቷና እሷ ብቻ ቀሩ፡፡
👍80🥰43🔥1
#ህያብ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በኤርሚ

ነሀሴ መጨረሻ ላይ ውጤት መጣ ተባለና አየን ጥሩ ውጤት ነው ያመጣሁት ግን ሩቅ ሀገር ነው የመደቡኝ ጎንደር ዩንቨርስቲ በምፈልገው ዲፓርትመንት(ህክምና)

እናቴን እና ልጄን ትቼ እንዴት ችዬ ይህን ያክል እርቃለሁ.. ትምህርቴን መተው እናቴን እንደመቅበር ነው። ሁላችንም ቢከብደንም ግዴታ ሄጄ መማር አለብኝ።
.....
ስራ ቦታዋ ሄጄ ለእናቴ ስነግራት እልልታዋን አቀለጠችው። ደንበኞቿ ምን እንደተፈጠረ ሲጠይቁኝ ነገርኳቸው እንኳን ደስ ያለሽ እያሉ እናቴን አቀፏት..... ከሁኔታቸው እኔ ሳልሆን እናቴ ውጤት የመጣላት ነበር የሚመስለው....
......
ቤት ውስጥ ጎረቤቶቻችንና አንዳንድ የእናቴ ወዳጆች በተገኙበት መጠነኛ የሽኝት ዝግጅት ተደረገልኝ። ልለያት እንደሆነ ያላወቀችው ልጄም ከኔ እኩል ፍንድቅድቅ ብላለች። እንግዶች በልተው ማዕዱ ከፍ ካለ በኋላ እናቴ ወደ መሀል ወጣችና
"አንዴ ፀጥታ...." ብላ ጨብጨብ ስታደርግ ሁሉም ሰው ባንዴ ዝምምም አለ።

"በህይወቴ እንደዛሬ የተደሰትኩበት ቀን የለም ... ልጄ ዩንቨርስቲ ገባችልኝ። ይሄ ከምንም በላይ ትልቁ ህልሜ ነው። እዛ ሄዳ በስኬት እንደምትመለስ እተማመንባታለሁ። ትልቅ ነገርም ባይሆን ይሄን ስጦታ በእናንተ ፊት እሰጣታለሁ" ወደኔ መጥታ ጉንጬን አገላብጣ ከሳመችኝ በኋላ የተጠቀለለውን ስጦታ ሰጠችኝና"ክፈቺው..." አለችኝ። የተጠቀለለበትን ወረቀት ስከፍተው ሞባይል ከነ ቻርጀሩ ብቅ አለ። አላመንኩም እናቴ ለኔ የእጅ ስልክ ገዛችልኝ... በዚያን ጊዜ አብዛኛው ሰው ባለ ሞባይል እየሆነ ቢሆንም እኔ ይኖረኛል ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"አመሰግናለሁ እናቴ.... ደግሞ ቃል እገባልሻለሁ... አኮራሻለሁ"

"እተማመንብሻለሁ የኔ ጀግና.... ሳትሳቀቂ በናፈቅሺን ሰዓት መደወል ብቻ ነው...."ወደ ደረቷ ወስዳ ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ። ይሄን እቅፍ እኮ ስወደው..............
ቃል ባትናገር እንኳን በእቅፏ ብቻ ብዙ መልዕክት የምታስተላልፍልኝ ይመስለኛል።
"በርቺ....
ባንቺ እተማመናለሁ....
እኔ አለሁልሽ...
እወድሻለሁ......." ብቻ ስታቅፈኝ ከዚህም በላይ ብዙ የምትለኝ ይመስለኛል።
..............

የምወዳት ልጄን እና እናቴን ተሰናብቼ ወደ አፄ ፋሲል ሀገር ጥንታዊቷ ጎንደር ተጓዝኩ ።
..........

ምዝገባ እና ሌሎች ፕሮሰሶች አልቀው ትምህርት የምንጀምርበት ቀን ደረሰ...... የመጀመሪያ ቀን እንደመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ቀድሞ ክፍል ተገኝቷል ከነኛ መሀል አንዷ እኔ ነኝ።
.....
ከደቂቃዎች በኋላ
"ይሄ ሸበላ ብቻ እንዳይሆን የሚያስተምረን" ከኋላዬ ያለችው ልጅ ወደ ጆሮዬ ተጠግታ አንሾካሾከችልኝ። ከንግግሯ እኩል ቀና ብዬ ወደ ፊት ለፊቴ አየሁ..... " ዋው ውበት ..... ዋው ቁመና.... ዋው ደረት...." ብዙ ዋው የሚያስብሉ ነገሮችን ያሟላ ሸበላ ሰው.....
......
"እሺ ዛሬ ብዙም የምንማረው ነገር አይኖረንም እርስ በርሳችን እንተዋወቅና ኮርስ አውትላይን እሰጣችኋለሁ...... እምም ከፊት ልጀምር ስምሽን አስተዋውቂን እስኪ...." ምኑ ነው ምን አለ እስከምረጋጋ እንኳን ሌላ ሰው ቢጠይቅ

"ህያብ በዛብህ እባላለሁ የመጣሁት ከአዲስ አበባ" ጣቱን ከኔ ቀጥሎ ወዳለችው ልጅ ጠቆመ

"መቅደስ ገዛህኝ..... ከሀዋሳ
ተፈሪ ይልማ...... ከደሴ
አብሳላት አበበ.... ከአዳማ
የትናዬት ዘመረ..... ከአዲስ አበባ......" ሁሉም ስማቸውን እና የመጡበትን ከተማ ተናገሩ ሁላችንንም ከሰማ በኋላ

" የኔ ስም ደግሞ ዮናታን ይባላል የ...." ከዚህ በኋላ ያለውን አልሰማሁትም .... ዮናታን.... ዮኒ ስሙ ደስ ይላል መልኩም ደስ ይላል። ሳላውቀው ስለሱ ብዙ አሰብኩ.... እጄ ላይ ያረፈ ወረቀት ከሀሳቤ አነቃኝ

"ያልኩትን ሰምተሽኛል ህያብ" ድንብርብሬ ወቶ አይን አይኑን አየው ጀመር እሱም ትንሽ ካየኝ በኋላ

" ተወካይ እስክትመርጡ ድረስ አንቺ ተወካይ ሆነሽ እነኝህን ወረቀቶች ለሁሉም አዳርሺ...." መልሴን ሳይጠብቅ ክፍሉን ለቆ ወጣ። እንዴ ቆይ ደግሞ ስሜን እንዴት ባንዴ ያዘው..... ይገርማል
........
" እና እኔንም አፈዘዘኝ እያልሽኝ ነው" አለችኝ ከፊት ለፊቴ መጥታ

"ይቅርታ እህቴ ምን......"

."ቅድም አልሰማሽኝም የትናየት.... የትናዬት ነው ስሜ"

"እሺ የትናዬት የምትይው አልገባኝም"

"ቀስ ብሎ ይገባሻል ለማንኛውም የራሴን ልውሰድ." አንዱን ወረቀት አንስታ እየተቆናጠረች ከክፍሉ ወጣች።

"ወይ አምላኬ ስንት አይነት ሰው አለ" ብዬ ስዞር ሁሉም አፍጠው የሚያዩኝ እኔን ነው።

ህይወት ልክ በምኞታችን ውስጥ እንዳሰብናት ቀላልና ጣፋጭ አይደለችም። ልንመራት ያወጣነውን እቅድ አስጥላ በራሷ ምህዋር ላይ ታሽከረክረናለች። እምቢ ብለን ብናስቸግራት እንኳን ወይ ከራሳችን እቅድ ወይም ሽክርክሪቱ ከሚያመጣው ነገር ሳንቋደስ ሜዳ ላይ እንቀራለን።

ዩንቨርስቲ መግባትን ሳስብ የሚታየኝ ጠንክሮ መማርና መማር ብቻ ነበር። ግቢ ውስጥ ሆኜ ከትምህርቴ የበለጠ ቦታ እሰጠዋለሁ ብዬ የማስበው ምንም ነገር አልነበረም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ ሰው መጥቶ ይህን ጥያቄ ቢጠይቀኝ በመጠየቁ ልናደድበት እችል ነበር። ዛሬ ግን ያን እምነቴን የትላንት እቅዴን ሊያከሽፍ የሚችል ፍቅር ያዘኝ። ያውም ውድድር የበዛበት ፍቅር.....
አብሬው ልሁን ብዬ ባስብ እንኳን ከሱ እኔን አለማፍቀር ውጪ ከደርዘን በላይ ሴቶች ጋር መጋፈጥ ይኖርብኛል..... ያውም እኔ የማውቃቸው ብቻ።

ያለኝ አማራጭ አንድ ብቻ ነው ቢከብደኝም ስሜቴን አምቄ መያዝ እና በሰላም ትምህርቴን መቀጠል። ምንም ሳይተነፍሱ ሁሉንም በልብ መያዝ ከምንም በላይ ህመም ነው.... በተለይ ደግሞ ፍቅር ሲሆን...

ብዙ ጊዜ ይሄን አስባለሁ ለእናቴ ይሄ አይገባትም አይደል? ... ስኬቴን ለምትናፍቅ እናቴ ስል ከመጋፈጥ ይልቅ መሸሽን መርጫለሁ። የምሸሽበት ምክንያት ዋናው ቁም ነገሩ እኮ ማፍቀሬ አይደለም ፍቅር በየትኛውም ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ስሜት ነው። ችግሩ ለዚህ ፍቅር ስል ብፋለም ለትምህርት የሚሆን ነፃ አይምሮ ላገኝ እችላለው ወይ? የበለጠው ችግር ደግሞ ያፈቀርኩት ሰው ሁሉንም ቀማሽ መሆኑ ነው።
፧፧፧፧፧፧
ከዛን ቀን ጀምሮ ማለትም ከመጀመሪያ የትምህርት ቀናችን ጀምሮ በዮኒ ፍቅር ተለክፊያለሁ። ፍቅር እንደያዘኝ እንኳን እያወኩ ላለማመን ከራሴ ጋር ለወራት ተከራክሪያለሁ። የትናዬት በየቀኑ እኔን ማስበርገግ ስራዬ ብላ ከያዘች ቆይታለች። በተለይ ዮናታን አስተምሮን ሲወጣ ወይ ከጎኔ ናት ወይም ከፊት ለፊቴ.... እልፍ ጊዜ እኮ አብረው አይቻቸዋለሁ... ብዙ ጊዜ ቢሮው ስትገባ ያዩዋት ነግረውኛል...... እኔ ደግሞ በተቃራኒው ከሱ ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ሁላ ላፈርስ የምሞክር ሰው ነኝ። ለምን ይሄን ያክል የቤት ስራ እንደሆንኩባት አላውቅም። አሁን ግን መሮኛል ፀብ ላለመፍጠር እያልኩ እንደፈሪ መታየት መሮኛል።

ዛሬም እንደለመደችው ከጥሩ ትወና ጋር የአሽሙር ንግግሯን ተናግራኝ ከክፍሉ ወጣች። ብሽቅ ብዬ ወረቀቶቼን ሰብስቤ ተከትያት እየወጣሁ እያለ አንድ ሰው ከኋላዬ ያዘኝ። ዞር ስል ቢኒ ነው ከተማሪዎች ሁሉ የተለየው ዝምተኛ ልጅ።

"አቤት ቢኒ" አልኩት ኮስተር ብዬ... ግንባሬን አይቶ እጁን ከክንዴ ላይ አነሳ እና

"ይቅርታ ህያብ.... ጣልቃ ልገባ ፈልጌ አይደለም ግን እኔ የታየኝን አንድ ነገር ልበልሽ..."

"ምን"
👍4910👏3🥰1🤔1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አራት


///

የሚሰቀጥጥ የድንጋጤ ጩኸት…‹እስቲ ምን  መሆኔ ነው..…?ይሄ እንደሚከሰት እንዴት ቀድሜ ሳላስብ ……?ወንዙ ውስጥ ዘልዬ ስገባ እሱን ፍለጋ አይደለ እንዴ ….? እና ላገኘው እንደምችል  እና ሊያዝለኝ ወይም ሊያቅፈኝ እንደሚችል  እንዴት ሳልገምት…..…? ገምቼስ ከሆነ አሁን እንዲህ ለገዛ እራሴ እስኪሰቀጥጠኝ  ድረስ መጮኼ  ምን የሚሉት ቅብጠት ነው……? ››
ብላ እሯሷን በሯሷ ታዘበች፡፡ 

እንግዳው ሰው ግን ጩኸቷን  ከቁብ አልቆጠረም ..እንደዛው በጀርባው እንዳዘላት  ወንዙን መሀል  በቁመቱ በመሰንጠቅ ከነበሩበት ሁለት መቶ ሜትር ያህል  ርቀት  ይዞት ተሰፈነጠረ ….ከፍራቻ ይሁን ከፍቅር አታውቅም ጥምጥም አለችበት….ዞሮ ተመለሰና ልብሷ  ያለበት ቦታ ሲደርስ ወደዳር በመጠጋት  ድንጋዩን  በእጁ ይዞ እረፍት ወሰደ… ከዛው ከውሀ ውስጥ ሳይወጡ  እሷም አንገቱ ላይ ተንጠልጥላ  እንደተጣበቀችበት ማውራት ጀመሩ

‹‹ምን አይነት ሰይጣን ነህ….…?››

‹‹ቆንጆ ሰይጣን…?››መለሰላት፡፡

‹‹ሂድ ከዚህ …እንዴት እንዲህ ታስደነግጠኛለህ ?››የኩርፊያ በሚመስል የድምጽ ቅላፄ ገሰፀችው፡፡

‹‹ደነገጥሽ እንዴ የእኔ ፍቅር..…?ደግሞ እንዲህ ድንቅ የዋና ችሎታ እያለሽ ነው ሳምንት ሙሉ ስትግደረደሪ የነበረው…?››

‹‹መዋኛት አልችልም መች አልኩህ..…? አልፈልግም እንጂ ፡፡››

‹‹ ዛሬ ታዲያ  ምን ተገኘ…?››

‹‹ውሀ ልቀዳ ነዋ…››

መልሷን እንደሰማ ሳቁን ለቀቀው፡፡ ..ደነገጠች‹‹ ..ምን ተሳሳትኩ..…?››መለስ ብላ ከአንደበቷ የወጣውን ንግግር አሰበች…‹‹ውይ ምን አይነት ቀሺም ነኝ…?፡፡››አለች 

ጄሪካኗን እዛ ዳር ጥላ ልብሷን አውልቃ  ወንዙ መሀከል ገብታ  ውስጥ ለውስጥ እየተሹለከለከች  እየዋኘች  አግኝቷት  ዉሀ ልቀዳ ነው ብላ መመለሷ እንኳን ለእሱ ለእሷም አስቂኝ ነው፡፡

‹‹የቀረው መስሎሽ ደነግጠሽ  ነው አይደል….…?ከአንደበትሽ መስማት ደስ ስለሚለኝ ነው እንጂ እኮ ከፈለግኩ ከልብሽ ማንበብ እችላለሁ…ያው ስለማፈቅርሽ ልብሽን ሰርስሬ በመግባት ልሰልልሽ አልፈልግም….››

‹‹ምን ታስፈራራኛለህ…ከቻልክ አድርገው››ፎከረችበት፡

‹‹እንግዴያው ገባሁ… ወንዙ ውስጥ የገባሽው መዋኘት ፈልገሽ ሳይሆን ስለቀረሁብሽ ደንግጠሸ ነው… እኔን ፍለጋ ነው ሳታስቢበት በደመነፍስ   የገባሽው››

‹‹እንዴ ጥንቅር ብለህ ቅራ ….ምንድነው ሚያስደነግጠኝ…?›››

‹‹ብታምኚ ምን አለበት… እኔ እንደወደድኩሽ አንቺም ወደሺኛል…›› 

‹‹አሁን ወሬ አታብዛ..እንዴት አድርጌ ነው አንተን ልወድህ  የምችለው……?››

‹‹ምን ማለት ነው…?››

‹‹ሰው ሁን ሰይጣን እንኳን መለየት አልቻልኩም፡፡ወይ ምን ይታወቃል ብዙ ሰው ጨፍጭፈህ በወንጀል የምትፈለገ የመንግሰት ታዳኝ ልትሆንም ትችላለህ፡ አይ እንደዛ አይደለም ብለህ እራስህን መከላከል የምትፈልግ ከሆነ እስኪ   ከተማ ውስጥ አግኘኝና ልደነቅ…ወይንም  ደግሞ ቤትህ ውሰደኝ…››

‹‹እስኪ ምን ማለቴ ነው ለሳምንት የማውቀውን ሰው ከታማ አግኘኝ ምለው....?እሺ አግኝቶኝ ምን ያድርገኝ….…?እቤትህ ውሰደኝ ማለትስ… …?ይሄኛውማ  ባስ  ያለ ዕብደት  ነው›ሥትል በውስጧ
በእፍረትን በቁጭት ተብሰለሰለች፡

እሱ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹እንደዛ ካደረግኩ ብቻ ነው እዳማፈቀርሺኝ የምታምኚው…?››

‹‹ማምነው ሳይሆን..ምን አልባት ላፈቅርህ የምሞክረው››አለችው ..፡
እውነቱ ግን ከተማ ባያገኛትም ወይም  እቤቱ ፍቃደኛ ሆኗ ባይወስዳትም ..አንዴ በመጨራሻው አቅሟ አፍቅራዋለች…. ምንም ሚቀንስ ምንም ሚጨምር ነገር የለም….፡፡
እሱ ግን  አላሳፈራትም ..ውስጧን አንብቦ ይመስላል ‹‹እሺ ሰሞኑን እቤቴ ወስድሻለሁ...አሁን ግን አንቺን ማዘሉ ከበደኝ ….ውረጂልኝ››አላት…

በጣም ነው  የደነገጠችው፡፡.ለካ ይሄን ሁሉ የምትቀደው አጆቾን በአንገቱ ዙሬያ ጠምጥማ በጀርባው በኩል ከእርቃን ሰውነቱ ላይ እንደተጣበቀች ነበር…በርግጋ  እጆቾን ከአንገቱ  አላቀቀችና በጀርባዋ  ወደኃላ ወንዙ ላይ ተዘረረች….፡፡

‹‹ለዚህ እኮ ነው ምወድሽ…ፐ በተለይ እርቃንሽን ውብ ነሽ››ብሏት  ጭርሽ አሳፈራት፡፡

እዛው ወንዝ ውስጥ ጥላው  ወጣችና ጀሪካኑን ወደወንዙ መሀል ወረወረችለት…‹‹ወሬውን ተውና ልብሴን እስክለብስ ድረስ ሙላልኝ…››አለችው፡፡

‹‹ታዛዥ ነኝ የእኔ እመቤት ..››…..ብሎ ተስፈንጥሮ ጄሪካኑን ቀለበና ይቀዳላት ጀመረ ..እሷም ብስብስ ያለውን ቀሚሷን ካስቀመጠችበት ቦታ አነሳችና ለበሰችው፡፡

ተንዘፈዘፈች..፡፡በለሊት መዋኘት ውሀ ውስጥ ይሞቃል….ችግሩ ከወንዙ ውስጥ ሲወጡ ነው፡፡አየሩ ቀዝቃዛ ስለሆነ እንኳን እርጥብ ልብስ ደርበውበት ይቅርና ደረቅም ልብስ ቢለብሱበት መብረዱ አይቀርም ነበር….፡፡

ጄሪካኑን ሞልቶ ወደ ዳር አወጣላትና አቀበላት…ተቀበለችውና አንጠልጥላ ከፍ ያለ የግንድ ጉማጅ ላይ በማስቀመጥ  ዞራ  በጀርባዋ    በፎጣው  አዘለችና ስትጨርስ‹‹በል ቻው››አለችው
በቀዝቃዛው አየርና በረጠበቅ ልብሷ ምክንያት ሰውነቷ ሲንዘፈዘፍ ታዝቦፈኲ ‹‹ከቀሚስሽ ላይ ውሀው እኮ እየተንጠፈጠፈ ነው››አላት፡፡

‹‹ቅድም አንሸራቶኝ እኮ ወንዙ ውስጥ ከነ ልብሴ ገባሁ…...ለዛ እኮ ነው መግባቴ ካልቀረ ልዋኝ ብዬ የቀጠልኩበት..››አለችው  እፍረት እየተሰማት፡፡
‹‹ግን እኮ ተንሸራተሽ ሳይሆን ዘለሽ ስትገቢ ነው ያየሁት››ብሎት እርፍ
‹‹እና እንኳን ዘለልኳ…. በራሴ ቀሚስ ምን አገባህ?››

የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ ቢጤ ሆነችበት…እንደውሸታምና ቀልማዳ ሴት ሆና በእሱ መገመት አትፈልግም..እሱ ደግሞ ካለ ባህሪው ምንም አይነት ሽራፊ ውሸት ሰምቶ እንዳልሰማ አውቆ እንዳላወቀ ማለፍ አይሆንለትም፡፡

‹‹አትበሳጪ …ባይሆን ቀሚስሽን ላድረቅልሽ››

‹‹እንዴት አድርገህ ነው የምታደርቅልኝ…?  ››

‹‹እስኪ ጠጋ በይ››

‹‹ለምንድነው የምጠጋው..››

‹‹ግድ የለሽም እኔ ከወንዙ ከምወጣ አንቼ ጠጋ በይ››

‹‹…ምን ታማጣለህ?›› በሚል እልክ ተጠጋችለት ….እጁን ሰነዘረና ውሀ የሚንጠፈጠፍበትን የቀሚሷን ጠርዝ  ጨበጠው…. ማመን አልቻለችም ….ችስስስስስ በማለት እየተነነ  ፍም የሞላበት ጊርጊራ ውስጥ እጣን ሲጨመር የሚወጣ  አይነት ጭስ ለአንድ ደቂቃ ያህል  ከልብሷ  ተነነ  …. እናም  ኩርምት እስኪል ድረስ  ቀሚሷ ደረቀ ..አፏን በአድናቆት ከፍታ ምን እንደምትናገር ግራ ገብቷኝ እያለ ተስፈንጥሮ ውሀ ውስጥ ሰምጦ እንደወትሮው  ተሰወረባት…..


ይቀጥላል
👍171🥰2118
#ትንግርት


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


.....‹‹ሁላችንስ ሸርሙጦች አይደለን? እሷ ሸርሙጣ መሆኗን በአዋጅ ያስነገረች የአደባባይ ሸርሙጣ ስትሆን እኔ እና አንቺ ደግሞ ጓሮ ለጓሮ ከሠው ተሸሽገን በሚሥጥ የምንወሰብ ሸርሙጦች ነን፡፡ አሁንም እኮ የመጣሽው እንድንሸረሙጥ ፈልገሽ መሠለኝ >>

ሠውነቷ ተንቀጠቀጠባት፣የጨጓራዋ ቁስለት ሲለበልባት ይሰማታል፡፡ በትንግርት ጉዳይ ብዙ ጊዜ ተጨቃጭቀዋል፡፡ ለቀናቶች በተደጋጋሚ ተኮራርፈውም ያውቃሉ እስከአሁ የተለወጠ ነገር ባይኖርም፡፡ ብዙ ጊዜ እርግፍ አድርጋ ልትተወው ታስብና መሸነፍ ደግሞ ያስጠላታል.... እልህ ትገባለች፡፡‹‹እና ተመልስ እንድሄድልህ ትፈልጋለህ?››

‹‹እንደፈለግሽ፡፡››...

መሄድ አልፈለገችም፡፡ የምትወደውን ገላ፣በፍቅር የምትሰቃይለትን ሠውነት፣የምትራብለትን ትንፋሽ አይኗ እያየ አለሌ ለምትላት ትንግርት አስረክባ ወደ ቤት ሄዳ የሠላም እንቅልፍ እንደማትተኛ ስለገባት እዚሁ ቆይታ እውነታውን በመጋፈጥ ለመፋለም ወሰነች፡፡በዚህ ቅፅበት ነበር መለስ ብሎ የነበረው የሳሎን በር በድንገት ተበርግዶ የተከፈተው፡፡

እንደመንገዳገድ ብላ ቆመች ትንግርት ነች፡፡ ከላይ ከደረቷ እስከ እምብርቷ  ከስር ደግሞ ከመቀመጫዋ ብዙም የማይረዝም እራፊ ጨርቅ እላይዋ ላይ ጣል አድርጋለች፣ ከትከሻዋ አልፎ ወደ መቀመጫዋ የሚጠጋውን እንደ ሀር የሚጠቁረ ፀጉሯን በትግሬዎች ባህላዊ ሹሩባ አሰራር ተሰርታ አሽሞንሙናዋለች፡፡ ጎላ ጎላ ያሉ አይኖቿን በኩል ይበልጥ ደምቀዋል፡፡ በተረፈ ፊቷ ንፁህ ነው፡፡ በሜካፕ አልተጨማለቀም፡፡ በአጠቃላይ እርቃኗን የቀረች ክንፍ አልባ በሰው አካል ውስጥ ሰርጋ የምትንቀሳቀስ መንፈስ መስላለች፡፡

ሁሴን አስተውሏት ምራቁን ዋጠ፡፡ ትንግርት ሁለቱንም በደከሙ አይኖቿ እያፈራረቀች አየችና ፍርፍር ብላ ሳቀች፡፡ ‹‹ኪ.ኪ.. ኪ...
እንደምንም ተረጋግታ መናገር ጀመረ፡፡‹‹ጋሼ ጋዜ..ጠኛው፤ ዛሬ ደግሞ ሁለታ..ችንም በአንድ ጊዜ አሠኘንህ?›› አለች በተኮለታተፈ አንደበት፡፡

ከዚህ በፊት ሁለቱ በአካል ተገናኝተው ባያውቁም አንደኛዋ ስለሌላዋ ታሪክ በደንብ ያውቃሉ፡፡ ትንግርት ኤደንን በሩቅ አይታት ታውቃለች፡፡ ኤደን ግን የትንግርትን መልክ ስታይ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው፡፡ ደነገጠች..ዘወትር ሸርሙጣ ብላ የምታንቋሽሻት ጣውንቷ የዚህን ያህል አፍዛዥ ውበት አላት ብላ ገምታ አታውቅም ነበር፡፡

ሁሴን‹‹ቁጭ በይ›› አላት፡፡ተንደርድራ ከጎኑ ሄዳ ተቀመጠችና ጉንጩን ሳመችው፡፡ ኤደን ላለማየት ፊቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞረች፤

እራሷን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ

‹‹እሺ እህት... ደህና ነሽ?›› ትንግርት ነበረች የሽሙጥ ይሁን የትህትና ባለየለት ቃና ሠላምታ ለኤደን የሠነዘረችው፡፡ አልመለሠችላትም፡፡

የኋላ በር ተከፈተና ፎዚያ ገባች፡፡ ግራ በተጋባ ሁኔታ እንግዶቹን እያፈራረቀች ከቃኘች በኋላ በመርበትበት ለሁለቱም ሠላምታ አቀረበች፡፡ ሁለቱ በአንድ ቀን በአንድ ላይ ሲመጡ ስትመለከት ይሄ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኟ ነው፡፡

‹‹ሃይ..›› አለቻት ትንግርት፡፡ ኤደን በዝምታዋ እንደቀጠለች ነው፡፡

ፎዚያ‹‹እራት ላቅርብ?››ብላ ወደ ሁሴን በመዞር ጠየቀች፡፡

‹‹አቅርቢ፡፡›› መለሰላት፡፡

‹‹ጋዜጠኛው.... ሳልጠግብ ነው የመጣሁት፤ መጠጥ እፈልጋለሁ፡፡›› ትንግርት ነች ጠያቂዋ፡፡

‹‹ኦኬ›› በማለት ከተቀመጠበት ተነሳና ሙሉ የውስኪ ጠርሙስ ከሦስት ብርጭቆ ጋር ይዞ በመምጣት በየተራ ለሁሉም እስከ ድርበብ ቀዳላቸው፡፡ ለሁለቱ ሴቶች አድሎ ለራሱም ይዞ ወደ መቀመጫው ተመለሰ፡፡ ቀድማ መጠጣት የጀመረችው ኤደን ነበረች፡፡ በአንድ ትንፋሽ ግማሹን ማገችው፡፡

ትንግርት በመገረም‹‹እንዴ...?››. አለች፡፡

‹‹ምን ሆነሻል?›› በግልምጫ ጠየቀች ኤደን፡፡

‹‹የቤት ልጆችም እንዲህ ትጠጣላችሁ እንዴ?››

‹‹ከሸርሙጦች ነው የተማርኩት፡፡›› የመልስ ምት ሠነዘረች፡፡

‹‹ሠካራምነቱ ብቻ ነው… ወይስ ሽርሙጥናውንም? ፡፡››

ኤደን ሌላ መልስ ለመመለስ ስታሞጠሙጥ ፎዚያ የምግብ ሠሀኖችን ይዛ ገባችና ጠረጴዛ ላይ ኮለኮለችው፡፡ ትንግርትም ከተቀመጠችበት ሶፋ ተንደርድራ በመነሳት ወደ ምግብ ጠረጴዛው እየሄደች ‹‹ጋዜጣኛው... ካልበላሁ ለሊቱን በደንብ ላስደስትህ አቅም አይኖረኝም›› አለችው፡፡

ምንም አልመለሰላትም፡፡ የእንካ ሠላምታው ተሳታፊ ላለመሆን ወስኖ በዝምታ እንደተሸበበ ወደ ምግብ ጠረጴዛው ቀረበ፡፡

‹‹እመቤት እንብላ እንጂ፡፡›› አለቻት ትንግርት ወደ ኤደን በፈገግታ እየተመለከተች፡፡

ከግልምጫ ውጪ መልስ አልመለሰችላትም፡፡ ይልቅስ መጠጡን ከብርጭቆ አጋባችና ሁለተኛውን ሞልታ ቀዳች፡፡

‹‹እራት አትበይም እንዴ?›› ሁሴን ጠየቃት፡፡

‹‹ነገር አጥግቦኛል›› መለሠችለት፡፡

‹‹የእኔ እህት አንድ ምክር ልለግስሽ.. ለዘመኑ ወንድ እንዲህ በግነሽ አትችይም፡፡ ወንዱ ሁሉ ንፋስ ሆኗል፡፡ እንደ አነፋፈሱ አብረሽ ካልነፈስሽ ዕድሜሽ አጭር ይሆናል፡፡ የሠብለወንጌልና የበዛብህ አይነት በድንግልና እስከ መቃብር ድረስ ተማምኖ የመዝለቅን አይነት ፍቅር በዚህ ዘመን እየፈለግሽ ከሆነ በእውነት አንቺ ገና ከእንቅልፍሽ ያልነቃሽ ህልመኛ ነሸ፡፡››

‹‹ይሄንን ፍልስፍና…ማስተርስሽን በሽርሙጥና ስትሰሪ ነው ያስተማሩሽ?››

‹‹ይሆናል .. አንቺን ከማስረዳት በእርግማን የፈራረሰችውን ባቢሎን መልሶ መገንባት ይቀላል፤አርፌ እራቴን ብበላ ይበጀኛል፡፡›› በማለት መብላቱ ላይ አተኮረች፡፡

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኃላ ሁሴንና ትንግርት ምግባቸውን ተመግበው ወደ በፊት መቀመጫቸው በመመለስ መጠጡን
ተያያዙት፡፡ ትንግርትና ኤደን በመጠጥ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሚፎካከሩ ይመስላል፡፡ ሁሴንም በተመስጦ እየኮመኮመ ይመለከታቸዋል፡፡ በመሀከል ኤደን መተኛት እንደምትፈልግ መጠጥ ባሠከረውና በተኮላተፈ አፏ ተናገረች፡፡

‹‹ያው ግቢና ተኚ ››በማለት ከሱ መኝታ ክፍል ቀጥሎ ያለውን ሌላ መኝታ ክፍል ጠቆማት፡፡

‹‹ምን ማለትህ ነው?››

‹‹እንዴት ምን ማለት?››

ትንግርት ሳቅ አፈናትና እጆቿን አደራርባ አፏን ከደነች፡፡

‹‹አንተስ?››ኤደን ነች አሁንም ጠያቂዋ፡፡

‹‹እኔማ መኝታ ክፍሌ ተኛለሁ፡፡››

‹‹እንዴ ነችና ልጅት! ... እሷስ?››

‹‹እሷ ደግሞ ካንቺ ፊት ለፊት ካለው መኝታ ቤት ትተኛለች፡፡››

ትንግርት ጣልቃ ገባች፡፡ ‹‹ብሬን ግን ከች ነው፡፡››

እጁን ወደ ኪሱ ሠደደና ድፍን አምስት የመቶ ብር ወረቀቶች አውጥቶ ሠጣት፡፡

‹‹እግዜር ይስጥልኝ የእኔ እህት፡፡ ማታ አንዱ ጎረምሳ ስብርብሬን አውጥቶኝ ስለነበር ድክም ብሎኝ ነበር፡፡ አንቺ ባትመጪ ደግሞ ጋሼ ጋዜጠኛው በእዛ በምታውቂው ጠንካራ ዕቃው ሲሠነጣጥቀኝ ነበር የሚያድረው፡፡››
በማለት የሠጣትን ብር ጨምድዳ ቦርሳዋ ውስጥ ከታ እየተወላገደች ወደ ተመደበላት መኝታ ክፍል አመራች፡፡ በራፉ ላይ እንደደረሰች የረሳችው ነገር እንዳለ ፊቷን መልሳ ‹‹አንተ ጋዜጠኛ… ለምን ግን ያቺ ደራሲህንም ሳትጠራት? ሦስት ብንሆን ደግሞ ቤትህ ይበልጥ ይደምቅልህ ነበር!››
‹‹ጠርቼያታለሁ...እሷ እዚህ ውስጥ ነው ያለችው፡፡›› አላት በጣቱ ወደ ልቡ እየጠቆመ፡፡

‹‹ታድላለች....ልብህ ውስጥ ካለችማ እሷ ነች ማለት ነው አብራህ የምታድረው፡፡ እመቤት ኤደን አየሽ.. እኔ እና አንቺ ስንፎካከር ሌላዋ ጩልሌ ቀማችን፡፡ ለምን ግን ተስማምተን ለሁለት አናገባውም?››
👍10214😁11🥰3👏3👎1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለሀለቃዋ ትብለጥ ፍቅረኛዋ መሞቱ ድብርት ውስጥ እንደከታት  ተናግራ  የአንድ  ወር ፍቃድ ወሰደች፡፡እረፍቷን ጨርሳ ተመልሳ ከመግባቷ በፊት መጽሀፉም አልቆ እስከወዲያኛው ይገላግላት ይሆናል፡፡አዎ ተስፋዋ ያ ነው፡፡
ሳባ እረፍት ከወሰደች በኋላ ቤት መዋል ጀመረች፡፡ራሷን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስም ኃይለኛ መደበትና ጭንቀት ውስጥ ገባች፡፡እርግጥ ይሄ
የመደበት ችግር አሁን ፍቅረኛዋ ስለሞተ ወይም እሷ ራሷ ስላስገደለችው ድንገት የተከሰተባት በሽታ አይደለም…ከእሷ ጋር ሶስት አራት አመት በደባልነት ኖሯል…ቢያንስ በስድስት ወር አንዴ የሆነ ምክንያት  ፈልጎ ይቀሰቀስባታል፡፡
ይተወኛል ብላ ለ15 ቀን ከቤቷ ሳትወጣ እረፍት ለማድረግ ብትሞክርም ነገሮች ግን እየባሱባት መጡ..በዚህም ምክንያት የስነ-ልቦና ባለሞያ እንድታናግር አንድ  ወዳጇ  ጨቀጨቃትና  በሀሳቡ  ተሰማምታ  የጠቆማት ሆስፒታል ሄደች፡፡
በተቻላት መጠን ጥሩ አለባበስ ለብሳ ፤ከወትሮዋ በተሻለ ነቃ ለማለት፤ የተቻላትን ጥረት አድርጋ በጠዋት ተነስታ መኪናዋን አስነስታ በተሰጣት አድራሻ ሄደች፡፡ቀድማ ደውላ ቀጠሮ አስይዛ ስለነበረ.እንደሄደች ነበር ነርሷ የተወሰኑ ፎርሞችን እንድትሞላ በማድረግ ወደ ዶክተሩ እንድትገባ ያደረገቻት፡፡

ብዙ ጊዜ ለህክምና ወደተለያዩ የከተማዋ ስመጥር ሆስፒታሎች ሄዳ አገልግሎት አግኝታ ታውቃለች…አሁንም የገባችበት የዶክተሩ ምርመራ ክፍል ከዚህ በፊት ከምታውቃቸውና ከጎበኘቻቸው ብዙም የተለየ አይደለም…ግን በራፉን ከፍታ ወደውስጥ እንደገባች ፈዛለች፡፡ለውስጧ ጥልቅ ድረስ እስኪሰማት   ድረስ ደንዝዛለች፡፡

‹‹ጤና ይስጥልኝ አረፍ በይ›› ሲላት ሁሉ አልሰማችውም.አይኗን አይኖቹ ላይ ተክላ በቆመችበት ቅዝዝ ብላ እየተመለከተችው ነው፡፡

እጁ ላይ ያለውን የእሷን ካርድ እየተመለከተ ‹‹ወይዘሪት ሳባ….አረፍ በይ››ሲላት እንደምንም ከመደንዘዝ ለመንቃት እየሞከረች እግሯን የመጎተት ያህል አንቀሳቀሰችና እንድትቀመጥ በተነገራት ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹እሺ ሳባ ዶ/ር ጀማል እባላለሁ.››ሲል ራሱን አስተዋወቃት፡፡

ዝም አለችው

‹‹እስኪ ስለራስሽ ጥቂት ንገሪኝ›› አላት፡፡

‹‹ግራ ገባት..ሀኪም ቤት ለስነ-ልቦና ህክምና የመጣች ሳይሆን የሆነ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላ የሆነ አማላይ ወንድ  ወንበሯን ተጋርቶ ሊጀነጅናት ሙከራ እያደረገ እሷ ደግሞ እየተግደረደረችና እየተሸኮረመመች ያለች ነው የመሰላት፡፡

‹‹ስለእኔ ምን?››

‹‹ስለ ማንኛውም ነገር….ሳባ ማን ነች?ምንድነው የምትወደው? ምንድነው የምትሰራው? ፡፡››

‹‹ስራዬ የሆነ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ ነው ምሰራው…ተቀጥሬ   እንኳን ማለት ይከብዳል…በኮሚሽን ነው የምሰራው፡፡የምኖረው ብቻዬን   ነው…ማለት አንድ ዘበኛ እና ተመላላሽ የቤት ሰራተኛ አለኝ... ጥሩ ኑሮ እኖራለው፡፡ግን ደግሞ ብቸኛ እና ደስታ የራቀኝ ሰው ነኝ..ሁሉ ነገር እየሰለቸኝ ነው…ለምን እንደምኖር እራሱ ግራ እየጋባኝ ነው፡፡››ሁሉን ነገር ተወችና ቀጥታ ወደ መደምደሚያው በመሻገር አሁን ሰላለችበት ሁኔታ ወደማብራራቱ ተስፈነጠረች፡፡

‹‹ጥሩ…. እንዲህ አይነት ስሜት ይሰማሽ የጀመረው ከመቼ ጀምሮ ነው?››

‹‹ሶስት አራት አመት..ግን የከፋ የሆነው ከሀያ ቀን በፊት ጀምሮ ነው፡፡፡››

‹‹በቅርብ በህይወትሽ የተከሰተ ጠንከር ያለ ነገር ነበር?››

‹‹አዎ ለአንድ አመት ፍቅረኛዬ የነበረ  ሰው  ቀለበት  እያሰረልኝ  ሳለ  እኔ የማላውቃት ልጅ ፍቅረኛው ሆና በጠርሙስ ጭንቅላቱን ከፈለችውና ሞተ…ከዛ ወዲህ ይመስለኛል ነገሮች እየባሱ የሄዱት፡፡››የታሪኩን ግማሽ እውነት ነገረችው፡፡

‹‹ገባኝ….ግን የትኛው ነው በጣም ያመመሽ…?››ሲል ጠየቃት

‹‹ከምንና ከምኑ?››

‹‹ከፍቅረኛሽ ሞትና….ከመከዳትሽ?››
ደነገጠች…እንዲህ ፈፅሞ አስባ አታውቅም..‹‹መከዳት…ስለፍቅረኛው ማለትህ ነው?››

‹‹አዎ››

ዝም አለች..ምን እንደምትመልስ ግራ ገባት፡፡ሳባ ልክ እንደጓደኛሽ ቁጠሪኝ ….ነፃ ሁኚ፡፡

‹‹አይ ፋሲልን .ማለቴ ፍቅረኛዬን በተመለከተ የሚሰማኝ ስሜት ግራ የተጋባ ነው…ሞቱ ይሄን ያህል ይረብሸኛል ብዬ ፈፅሞ አስቤ አላውቅም  ነበር….የእኔና የእሱ ግንኙነት በተወሰኑ የጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ ነበር…ፍቅረኛውን በተመለከተ ምንም የሚሰማኝ ነገር የለም..በእርግጥ እስከመጨረሻው ቀን ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም..ባውቅም በእኔ ላይ ማግጦብኛል ብዬ የምበሳጭበት ምክንያት አይታየኝም...እኔም ታምኜለት አላውቅም እሱም ይታመንልኛል የሚል እምነት አልነበረኝም..እውነቱን ለመናገር እንዲታመንልኝም ፍላጎቱ አልነበረኝም.. በአጠቃላይ ስለፍቅረኛው ማወቄ ምንም ትርጉም የሰጠኝ አይመስለኝም፡፡››

‹‹ምን አልባት ትዳሩን ትፈልጊው ነበር…?በእሱ ሞት ምክንያት በመበላሸቱ ተበሳጭተሻል?››

‹‹በተአምር እንደዛ አይነት ፍላጎት አልነበረኝም...ቀለበቱን ሲያደርግልኝ ድንገት ሳያማክረኝ ነበር ያደረገው...ማማከር ሳይሆን ስለወደፊታችን አውርተን እንኳን አናውቅም...እንዳገባው ሲጠይቀኝ በጣም ብዙ በሚያውቁት ሰዎች ፊት ስለሆነ እሱን ላለማሸማቀቅ እና ግርግር ላለመፍጠር ነበር  ጣቴን  የዘረጋሁለት..እና መቼም ላገባው እቅድ አልነበረኝም፡፡ግን የገረመኝ በመሞቱ በውስጤ ቅሬታ ተፈጥሯል …ፈፅሞ ልረሳው አልቻልኩም…ከእሱ የማጣው  አንድ  ብቸኛ  ነገር ወሲብ ነው….ያንን ደግሞ ካሰብኩበት ከሌላ ሰው በቀላሉ ማግኘት እችላለሁ…ያው የእሱን ያህል ሊሆን ባይችልም ማለቴ ነው..እና ለምን ከአዕምሮዬ ላወጣው እንዳልቻልኩ አልገባኝም፡››

‹‹ግን እሱ ብቻ ነው የሚያስጨንቅሽ? ማለቴ እሱ በህይወት እያለስ ሌላ ምቾት የሚነሳሽ ጉዳይ ነበር?››

‹‹እየተጠነቀቀች እራሷን ከመጠን በላይ ላለማጋለጥ እየጣረች ከሁለት ሰዓት በላይ ከዶ/ሩ ጋር አወራች….በጊዜያዊነት የሚያረጋጓትን ሁለት መድሀኒቶችን መውሰድ ከሚገባት የተወሰነ ምክር ጋር ለግሷት ለሳምንት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷት አሰናበታት….

በመምጣቷ ተደስታለች …በዶ/ሩ መስተንግዶ ተደስታለች..ልቧ ለምን እንደደነገጠባት አልገባትም…ያምራል…ከአይኖቹ የሚረጫቸው ብርሀን የሰውን ልብ በቀላሉ ይሰረስራሉ፡፡ንግግሩ እርጋታ የተለባሰና እንዲያወሩ የሚያበረታታ ነው፡፡ በዛ የተነሳ በቆይታዋ ተደስታለችም…የተወሰነ ቀለል የማለት ስሜትም እየተሰማት ነው..ትንሽ ቅር ያላት ቀጠሮ ከሳምንት በኋላ መሆኑ ነው፡፡ ከሁለት ወይም ከሶስት ቀን በኋላ መልሳ ብታገኘው ደስ ይላት ነበር.ደግነቱ ችግር ካለና የተለየ ስሜት ከተሰማት እንድትደውልለት ነግሯት ቁጥሩን ሰጥቷታል፡፡መኪናዋን ራሷ እያሽረከረች ቀጥታ ወደቤቷ ሄደች..አዲሱ ዘበኛዋ በራፉን ከፈተና ወደ ውስጥ አስገባት..፡፡ይሄንን ዘበኛ ከቀጠረች አስር ቀን ቢሆነው ነው፡፡የመጀመሪያውን ዘበኛ ያሰናበተችው የመጀመሪየውን ዘበኛ ከእሷ ጋር አስተዋውቋት ያስቀጠረው ፋሲል ስለነበረ ነው፡፡ከእሱ ጋር የሚያገናኛት ምንም አይነት ትዝታ አትፈልግም፡፡ደግሞ ምን አይነት ሚስጥራዊ ግንኙነት እንዳላቸው ስለማታውቅና በዛም ጥርጣሬ ስለነበራት ያልሰራበትን የሶስት ወር ደሞዙን ሰጥታ አሰናበተችው፡፡

ከዛም እንደተለመደው መኝታ ቤቷ ገባችና ራሷን ሸሸገች..


💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8915🤔3👏1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
:
:
#ክፍል_አራት
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ፔሩ/ኢኩኤቶስ

ኑሀሚ በተኛችበት አጨንቁራ በመስታወቱ አሻግራ እያየችው ነው፡፡የህይወት አዙሪት ከየት ወስዶ የት ላይ እንደወረወራት አሰበችና እጅግ ተገረመች፡፡ስለእሱ እና ስለገጠመኞቾ እያመላለሰች በማሰብ ላይ ሳለች ድንገት ወደሀገር ቤት የሚያበር የሀሳብ ሀዲድ በአእምሮዋ ተዘረጋ….ጭንቅሏቷን ትራሷ ላይ አመቻቸችና በተዝናኖት ተኝታ በተዘረጋው ሀዲድ ወደሀገር ቤት በትዝታ ፍስስ አለች፡፡ ኑሀሚ የተደላደለ እና የተረጋጋ የሚባል ህይወት የኖረችው እስከ 9 ዓመቷ ድረስ ብቻ ነበር፡፡ ከዛ በጥምቀት ሰሞን በእለተ ከተራ የዘጠኝ አመቷን የልደት በአል ሊከበርላት ድግስ ተደግሶ፤ ኬክ ታዞ፤ ሻማ ተገዝቶና ፤እቤቱ በዲኮሬሽን አሸብርቆ ባለበት ቀን እናትና አባቷ ተቃቅፈው በተኙበት ሞተው ተገኙ፡፡በምትወዳት የልደት ቀኗ በጥምቀት ቀን ጥር 11 በህይወቷ በጣም ልብ ሰባሪው ሀዘን ደረሰባት፡፡ከዛ በኃላ ህይወት ለእሷ ቀላል ሆና አታውቅም፡፡ከዛ በኃላ በአለም ላይ በ10 ደቂቃ ታላቋ ከሆነ ከመንትያ ወንድሟ በስተቀር ምንም ነገር አልነበራትም….ከዛ በኋላ አመት በመጣ ቁጥር በጥምቀት ወቅት ህዝበ- ክርስቲያኑ በየጎዳናው ተቦት ተከትለው ሲዘምሩና ሲጨፍሩ የወላጆቾን ሬሳ ተከትለው ሙሾ የሚያወርዱ ለቀስተኞች ነው የሚመስሏት…በቃ ከዛ በኃላ ሕይወት በአጠቃላይ ሁሉ ነገር አስከፊ ሁሉ ነገር አስጠዩ ነበር የሆነባት፡፡ይህ በጥልቅ ሀዘንና ብቸኝነት አጥንት የሚሰነጣጥቅ ችግር ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለወንድሟም ጭምር ነበር፡፡ስለወንድሟ ትዝ ሲላት ከተጋደመችበት ተስፈንጥራ ተነሳችና ስልኳን በማንሳት ወደ ሀገር ቤት ደወለች…ወንድሟ ጋር፡፡
‹‹ሄሎ ናኦል…እንዴት ነህ?››

‹‹አለሁልሽ እህቴ…እንዴት ነሽ…?.ሁሉ ነገር አሪፍ ነው?፡፡››

‹‹ሰላም ነኝ.. ዛሬ ከፔሩ አንተ ወደምትወዳት ብራዚል እየበረርኩ ነበር… ግን የአየር ፀባዩ ተበላሸና ሳንደርስ አንድ የምታምር ለብራዚል ድንበር ቅርብ የሆነች የፔሩ ከተማ ለማረፍ ተገደድን፡፡››
ወንድሟ በሰማው ዜና በጣም ደነገጠ‹‹እንዴት ….?ምን አይነት ቦታ ነው ያረፋችሁት ..?ፕሌኑ ሰላም ነው?››

‹‹አረ ሁሉ ነገር አሪፍ ነው…፡፡››

‹‹እና እንዴት ልትሆኑ ነው?››

‹‹በቃ ምን እንሆናለን..አሁን ቤርጎ ይዤ አረፍ ብዬ ነው እየደወልኩልህ ያለሁት፡፡ነገ የአየር ፀባዩ ከተሻሻለ እንቀጥላለን፡፡ከለበለዚያ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሚሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የምናደርገውን እናያለን፡፡››
‹‹አህቴ እራስሽን ጠብቂ ደግሞ በጣም ናፍቀሺኛል….ጨርሰሽ እስክትመጪ ቸኩያለሁ፡፡..ሶስት ወር እንደዚህ ረጂም መሆኑን አላውቅም ነበር››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹ለምን ይዋሻል..ከዚህ በፊት እኮ ሶስት አመት ሙሉ ተለያይተን ነበር››

‹‹የዛን ጊዜ እኮ እኔ ራሴ ሀይለኛ ወከባ ላይ ነበርኩ…የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት አለ..በዛ ላይ በምታውቂው ስራ ሀለቃችን ምስራቅ ከወዲህ ወዲያ ታሽከረክረኝ ነበር…ከዚህ ሁሉ መዋከብ በተረፈቺኝ ብጣቂ ጊዜ ብቻ ነበር አንቺን መናፈቅ የምችለው፡፡አሁን ግን ስለአንቺ ከማሰብ ውጭ ሌላ ምን ስራ አለኝ?››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹ስለናፈቅኩህ ደሰስ ብሎኛ፤ቻለው ከአንድ ወር በታች ነው የቀረኝ…እና ደግሞ እንዲህ ዞር ስል የምናፍቅህ ከሆነ ስርህ እያለው አታበሳጨኝም ማለት ነው፡፡››
‹‹አረ አንቺ ብቻ ነይልኝ እንጂ ቀና ብዬም አላይሽም፡፡››ሲል ቃል ገባላት፡፡

‹‹ነግሬሀለው… አሁን የተናገርከውን ሪከርድ አድርጌዋለው፡፡››

‹‹ችግር የለውም እውነቴ ነው፡፡››

‹‹ምስራቅ ደህና ነች..?››ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹ያው ታውቂያለሽ ..እሷ ካልፈለገች አላገኛትም..ግን ደህና መሆኗን አውቃለሁ፡፡››ሲል እሷ ብቻ ሳትሆን ምስራቅም እንደናፈቀችው በሚያሳብቅ የድምፅ ቅላፄ መለሰላት፡፡ምስራቅ ማለት በሁለቱም ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላት…የደህንነት መስራቤት ውስጥ የምትሰራ ሲኒዬር ሰላይና ለአመታት ሀለቃቸው የነበረች የ43 ዓመት ሴት ነች፡፡
‹‹በል ቸው ..ልተኛ ደክሞኛል ነገ ደውልልሀለው፡፡››አለችው፡፡
‹‹ቸው እህቴ …ውድድ ነው የማደርግሽ››ስልኩ ተዘጋ፡፡
አልጋውን ለቃ ወረደችና ወደ ፍሪጁ በመሄድ ሌላ የቆርቆሮ መጠጥ አወጣችና ከፍታ እየተጎነጨች ወደውጭ ወጣች፡፡ዳግላስ አሁንም ላፕቶፑ ላይ አቀርቅሮ ውዝግብ ውስጥ እንደገባ ነው፡፡የአማዞን ወንዝ ከበረንዳው አሻግረው ሲያያዩ  እንደእባብ ተጠምዝዞ ሽብልል እያለ ሲፈስ ይታያል፡፡ትኩረቷን ወደዳግላስ መለሰችና‹‹እሺ አዲስ ነገር አለ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹የተወሰነ ነገር እየገባኝ ነው፡፡ሳይንቲስት ነኝ፡፡አዎ ኬሚስት ነኝ፡፡እዚህ አማዞን ጫካ ውስጥ በሚገኝ የኮኬይ መቀመሚያ ላብ ውስጥ እሰራ ነበር፡፡አሁንም እንዴት እንደሚቀመም ፕሮሰሱን ሁሉም ትዝ ብሎኛል፡፡ግን ከዛ በፊት የት ነበርኩ..?የት ነው የተማርኩት? ቤተሰቦቼ የት ናቸው…?ሚስትና ልጆች አሉኝ…?እንዴት እዚህ ነገር ውስጥ ልገባ ቻልኩ?አሁንስ ፔሩ ምን ስሰራ ነበር..?የተሸከምኩትን ሻንጣ ሙሉ ዶላር ከየት አመጣሁት? ለምንስ ተሸከምኩት?አሁንስ ወደብራዚል ለምንድነው እየሄድኩ ያለሁት?ቀደም ብለሽ አንቺ ለጠይቅሺኝ ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ሚሆን መልስ ግን እስከአሁን አላገኘሁም፡፡››
‹‹በቃ ላፕቶፑን ዝጋና ተነስ… ወደ ውስጥ እንግባ …ምን አልባት ለጠየቅካቸው ጥያቄዎች ሁሉ የሚሆኑ መልሶችን አረፍ ብለህ እንቅልፍ ከተኛህ በኃላ ትዝ ሊሉህ ይችላሉ፡፡ዶላሩ ላልከው ግን ምን አልባት ለአመታት ለሰራህላቸው ስራ የከፈሉህ ደሞዝ ሊሆን ይችላል፡፡ምን አልባት ከእነሱ ጋር በሰላም ተለያይተህ ሰላማዊና ኖርማል ህይወት ለመኖር ወደ ሀገርህና ቤተሰቦች በመጓዝ ላይ ትሆናለህ፡፡በል አሁን እኩለ ለሊት ሆነ ፤አረፍ እንበልና ነገ ከነገወዲያ የሚሆነውን እናያለን..ምን አልባትም እኮ ለእነዚህ ሁሉ ጥቄዎችህ መልስ የሚሰጥህ ሰው አየር ማረፊያ ቆሞ እየጠበቀህ ሊሆንም ይችላል፡፡››
‹‹አዎ እኔም ተስፋ ማደርገው እንደዛ ነው፡፡››አለና እንዳለችው ላፕቶፑን በመዝጋት መቀመጫውን ለቆ ተነሳ፡፡ ..ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡን ወደበረንዳ የሚያስወጣውን በራፍ በመዝጋት በየአልጋቸው ላይ ተቀመጡ፡፡
‹‹ታውቂያለሽ ከሌላ ፕላኔት ድንገት ተንሸራትቼ የወደቅኩና ያለቦታዬ ከማላውቃቸውና ከማይመስሉኝ ፍጡሮች ጋር የተቀላቀልኩ እየመሰለኝ ነው፡፡››አላት
በንግግሩ አሳዘናት‹‹አይዞኝ…..እንዳልኩህ አሁን መጨነቁን አቁምና ለማረፍ ሞክር…ጥዋት የሚሆነውን እናደርጋለን፡፡›› ብላ አልጋዋ ላይ ወጣችና ተሸፋፍና ለመተኛት መከረች፡፡ፈፅሞ እንቅልፍ ይወስደኛል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡ግን ወዲያው ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰዳት፡፡ማለዳ 12፡40 አካባቢ ከእንቅልፏ ባና አይኗን ስትገልጥ ዳግላስ ስትተኛ ተቀምጦበት በነበረበት ቦታ ተቀምጦ ነው ያገኘችው፡፡
‹‹ምነው አልተኛህም እንዴ?››ስትል በመገረም ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ አልተኛሁም፡››

‹‹እና እዛው የተቀመጥክበት ቦታ አነጋኸው …. ?››
👍888
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በፀሎት ከጠፋች ከአንድ ሰዓት በኃላ ነበር አባትዬው ዜናውን የሰሙት፡፡በመጀመሪያ የቤቱ ሰው ሁሉ ያሰበው የተለመደው የልብ በሽተዋ ተነስቷባት ተዝለፍልፋ የሆነ ቦታ ወድቃ ይሆናል ተብሎ ነበር ፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ጋርዶቹ ፤ ዘበኞቹና አስተናጋጆቹ ሳይቀር የቤቱ ጥጋጥግ ከ50 በላይ ክፍሎች አንድ በአንድ እየከፈቱ አንድም ቦታ ሳይቀር ፈልገው ጅባት ካሉ በኃላ ነበር የጋርዶቹ ሀላቃ ፈራ ተባ እያለ የአቶ ኃይለመለኮትን መኝታ ቤት ያንኳኳው….በለሊት ልብሳቸው ሆነው የልጃቸውን የልደት በዓል ምክንያት በድካም የዛለ ሰውነታቸውን አልጋ ላይ አሳርፈው ገና እንቅልፍ እንዳሸለባቸው ነበር በራፋቸው የተንኳኳው…በመጀመሪያ በህልማቸው መስሏቸው ነበር፡፡ በኋላ ግን የምርም ክፍላቸው እየተንኳኳ መኆኑን ገባቸውና እየተነጫነጩ አልጋቸውን ለቀው በንዴት ውስጥ ሆነው በራፉ ሊከፍቱ እየሄዱ ባሉበት ቅፅበት ከመኝታ ቤታቸው ቀጥሎ ካለው ከፍል ውስጥ ያሉት ወ.ሮ ስንዱ ድምፅ ሰምተውና ደንግጠው ክፍላቸውን ከፍተው እየወጡ ነበር፡፡ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እያንኳኳ ያለው ጋርድ ላይ አፈጠጡበት፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››

‹‹ጋሼ..እንዴት እንደሆነ አናውቅም…..ልጆቹ እየተከታተሏት ነበር….››ለማስረዳት አስቦ መንተባተብ ጀመረ..፡፡

‹‹ምን እያወራህ ነው?››

‹‹በፀሎት..››

‹‹በፀሎት ..ልጄ ምን ሆነች..?አመማት እንዴ…?የልብ ህመሟ ተቀሰቀሰባት?››እናትዬው በመርበትበት በጥያቄ አጣደፉት፡፡

‹‹አይ አላመማትም…ላለፉት አንድ ሰዓት ውስጥ ስንፈልጋት ነበር…የለችም…››

‹‹የለችም ማለት…….?››

‹‹ጓደኞቾ ደብቀው ይዘዋት ሄደው መሰለኝ…. ግቢው ውስጥ የለችም፡፡››

‹‹እንዴ ..ይሄ ምን ማለት ነው..?ያን ሁሉ ጠብደል ጎረምሳ በጠባቂነት የቀጠርኩት እንዲህ አይነት ነገር እንዲከሰት ነው እንዴ…?ሰውዬ የእያንዳንዳችሁን ግንባር በሽጉጥ ሳልነድልላችሁ ልጄን ካለችበት ፈልጉና አስረክቡኝ…፡፡››በመራር ንግግር ቀድሞም የደነገጠውን ሰውዬ ይበልጥ ፍርሀት ለቀቁበት፡፡

‹‹እሺ ጌታዬ… ሁሉም ሰው እየፈለጋት ነው፣ይሄንን ነገር እርሶም በሰዓቱ መስማት አለቦት ብዬ ነው ቀድሜ ያሳወቅኳት…››

‹‹ወይኔ ልጄን..ይሄ የእነሱ ሳይሆን ያንተ ጥፋት ነው…››እናትዬው ቁጣቸውን ወደባላቸው አዞሩት፡፡

‹‹ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?››ባልና ሚስቶች የተለመደውን ጭቅጭቃቸውን ቀጠሉ፡፡

‹‹ልጄን እንደከብት እረኛ ቀጥረህባት ስታጨናንቃት ነው ለዚህ ያበቃችው፡፡››

‹‹ሴትዬ እስኪ አሁን ተይኝ….እኔ ለራሴ ግራ ገብቶኛል ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ.››አሉን ፊት ለፊት እየሄደ ያለውን ጋርድ ተከትለው ኮሪደሩን አቆርጠው መሄድ ጀመሩ..፡፡ወ.ሮ ስንዱም ማጉረምረማቸውን በለቅሶ አጅበው የለበሱትን ቢጃማ እንኳን ሳይቀይሩ ከኋላ መከተል ጀመሩ…፡፡በፀሎት ግን ለሊቱን ሙሉ ብትፈለግ ..በየወዳጅ ዘመድ ቤት ቢደወል…በከተማ አውራ ጎዳናዎች ከሰላሳ በላይ መኪኖችን ተሰማርቶ ብትፈለግ ድኩዋን ለማግኘት አልተቻለም…

በስተመጨረሻ የግቢው ካሜራ ቅጂ ለሁለተኛ ጊዜ በዝግታ ሲታይ ነው እራሷን በአለባበሶ ቀይራ ብቻዋን በሞተር ሳይክል ግቢውን ለቃ እንደወጣች የታወቀው፡፡ይሄ ደግሞ በቤተሰቡ ላይ የነበረውን ድንጋጤና ፍራቻ ይበልጥ አናረው..ምክንቱም አወጣጧ አስባባት መሆኑን ስለተረዱ….፡፡ከዛ አባትዬው አቶ ኃይለመለኮት ያላቸውን ተሰሚነትና ከመንግስት ሰዎች ጋር ያላቸውን ትስስር በመጠቀም ለእያንዳንዱ ፖሊስና ትራፊክ ፖሊስ ፎቶዋና የሞተር አይነትና ታርጋ ቁጥሩ ተበትኖ እንድትፈለግ መመሪያ እንዲተላለፍ ተደረገ ፡፡

በማግስቱም ምንም ፍንጭ ሳይገኝ በመንጋቱ እቤቱ ሁሉ በወዳጅ ዘመድ ተጨናነቀ፡፡..ወላጆቹ በስጋትና ፍራቻ ብቻ ሳይሆን በሰው ትንፋሽም መፈናፈኛ አጣ…አቶ ኃይለመለኮት ሲጨንቃቸው ከአጀቡ ተነጥለው ቀጥታ ወደልጃቸው መኝታ ቤት ገቡና ከውስጥ ዘግታው አልጋዋ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብለው ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ግዙፍ የልጃቸውን ፎቶ እየተመለከቱ በትካዜ መንሳፈፍ ጀመሩ....እንባቸው መቆጣጠር አልተቻላቸውም…እንደህፃን ልጅ ነው ተንሰቅስቀው ያለቀሱት….በህይወታቸው እንዲህ አይነት ለቅሶ መቼ እንዳለቀሱ ፍጹም ትዝ አይላቸውም….አዎ ልጃቸው የልብ ንቅለተከላ በተደረገላት ጊዜ በህይወታቸው በጣም ያዘኑበትና የተጨናነቁበት ጊዜ ነበር…በቀሪ ህይወታቸውም መቼም ተመሳሳይ ሀዘን ውስጥ እገባለሁ የሚል ግምት አልነበራቸውም….ግን ተሳስተው ነበረ..አሁን ያሉበት ጭንቀትና ስጋት ከዛን ጊዜም ከፍ ያለ ነው…. ፡፡ልጃቸው አንድ ነገር ብትሆን ምን እንደሚሆኑ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም..፡፡ግን በእርግጠኝነት ሌላ ኃይለመለኮት እንደሚሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው..ምን አልባት አብደው ጨርቃቸውን ሊጥሉ ይችሉ ይሆናል...ወይንም ንዴታምና አውሬ አይነት ሰው ሊሆኑ ይችላሉ ….ልባቸው ፍስስ እያለባቸው ነው….አይናቸውን ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከሩ የልጃቸውን እቃዎች በስስት ሲቃኙ አይናቸው አንድ ፖስታ ላይ አረፈ..በድንጋጤ ተነሱና ወደእዛው ተራመድ፡፡ አነሱት… ሁለት ነው…፡፡ከላዩ ላይ የተፀፈውን አነበቡት..፣አንደኛው ለአባዬ ይላል…ሁለተኛውን አዩት ለእማዬ ይላል…እሱን ጠረጴዛው ላይ መልሰው አስቀመጡና ለእሷቸው የተጻፈውን ይዘው ወደአልጋ ጠርዝ ተመላሱና ፖስታውን ቀደው ወረቀቱን በማውጣት ማንበብ ጀመሩ፡፡

አባዬ….እንዴት እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል? በጣም ነው የምወድህ..ግን ሁሌ ትናፍቀኛለህ…፡፡ሁሌ እሩቅ ውጭ ሀገር ያለህ ነው የሚመስለኝ….እቤት እያለህ እራሱ የሌለህ መስሎ ነው የሚሰማኝ…እርግጥ አንተ ሁሉ ነገር ተሟልቶልኝ በቅምጥል የምኖር ደስተኛ
ልጅ ነው የምመስልህ…እየቀያየርኩ ምነዳችወ ከሶስት በላይ ዘማናዊ መኪናዎች አሉኝ፣በወር ከመቶ ሺ ብር በላይ በእጄ ይሰጠኛል….በየሄድኩበት እየሄዱ የሚጠብቁኝ ቁጥራቸውን የማላውቃቸው ጋርዶች አሉኝ……በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ የፈለኩትን ውጭ ሀገር ሄጂ እዝናናለሁ…በአጠቃላይ ኑሮዬ ለአብዛኛው ኢትዬጵያዊ በተረት አለም እንኳን ሰምቶት የማያውቀው የህልም አለም አይነት ነው…ግን እኔ በእድሜዬ እናትና አባቴ ሲሳሳሙ አይቼ የማላውቅ ልጅ እንደሆኑክ ማንም አያውቅም..አረ መሳሳሙ ይቅር አንድ መኝታ ቤት ውስጥ አብረው ሲያድሩ አይቼ አላውቅም… አይገርምም…..፡፡

አባዬ ልጅ ሆኜ እርግቤ እያልክ ነበር የምትጠራኝ..እርግቤ ስትልኝ እንዴት እንደምደሰት አታውቅም ፡፡የእውነትም ያንተ ነጭ እርግብ ሆኜ አድማሱን ሰንጥቄ በሰማይ መብረር የምችልና ጨረቃ ጋር ደርሼ ከዋክብቶችን ጨብጬ ምጫወትባቸው ይመስለኝ ነበር…በቃ ትንሽ መልአክ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ነበር የምታደርገው..ግን አባዬ አንተ ያልተረዳኸውነ ነገር እኔ ከ19 ዓመቴ በኋላ ማለቴ የሌላ ሴት ከሰውነቴ ካወሀድኩ ጀምሮ እኔ እኔን አይደለሁም…..ትዝ ይልሀል እርግቤ አትበለኝ በስሜ ጥራኝ ብዬ ያስተውኩህ እራሴው ነኝ..ለምን ብለህ ጠይቀኸኝ ግን አታውቅም..ምን አልባት ዝም ብዬ እርግቤ የሚለው ሰም ደስ ስለማይለኝ መስሎህ ሊሆን ይችላል እንደዛ ግን አይደለም….ከልብ ነቅለ-ተከላ ከተደረገልኝ በኃላ ክንፏ የተሰበረባት መብረር የማትችል እና በየጓሮ የምትንፏቀቅ እርግብ እንደሆንኩ እየተሰማኝ ስለመጣ ነው ያስቆምኩህ..ለአንድ ልጅ እኮ በሰማይ እንዳሻት እንድትበር የሚያደርጋት የአባቷ ፍቅር ቀኝ ክንፍ እና የእናቷ ፍቅር ግራ ክንፍ ሲሆናት ነው….የወላጆቾ ፍቅር ነው እንድትበር የሚያደርጋት….ያ እንደሌለኝ ስረዳ ነው ስሙ ያስጠላኝ፡፡ለምን
👍928👏4😁1
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ


ተመስገን

ከጠፋች በኋላ፤ ብቻ ሳይሆን ከእድላዊት ጋርም ከትምህርት ቤት መጥተው ምሳቸውን ከበሉበት ቀን አንስቶ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አይደለም አስቦትም አያውቅም፡፡

ወደ ትምህርት ቤትም አልሄደም፡፡ ትዳር የሚባል ሳያስብ እናት አባቱን እየረዳ የግብርና ስራውን ሌት ከቀን እየተጋ መዋሉን ተያይዞታል፡፡

ከሚወዳት እህቱ እድላዊት ውጪ የቅርብ ጓደኛዬ የሚለው ሴትም ይሁን ወንድ ለግዜው አልነበረውም፡፡ አንድ ቀን በስራ ምክንያት ከሰፈሩ ልጅ ያሬድ ጋር ይገናኛል፡፡ ታዲያ ተመስገንና ያሬድ ከዚህ በፊት ከእግዚአብሔር ሰላምታ በስተቀር የጠበቀ ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡

ያሬድ ተመስገንንም ይሁን ቤተሰቦቹን በደንብ ጠንቅቆ ያውቃቸዋል፡፡ በጥሩ ቤተሰብ ያደገና ከቤተሰቦቹ ጋር የሚኖር ገና ታዳጊ ወጣት ሆኖ በራሱ ፈቃድ
ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ግብርናው ከተሰማራ ሰንበትበት ብሏል፡፡

ከተመስገን ጋር ግንኙነታቸው ከእግዚአብሔር ሰላምታ አልፎ ወደ መቀራረብ ደረሰ ፤ አልፎ አልፎም ስራ በመተጋገዝ መረዳዳት ጀምረዋል፡፡

ተመስገን እንደ እህቱ የሚሆንለት ባያገኝም ለእሱ የሚሆንና የሚያበረታታው የቅርብ ጓደኛ በማግኘቱ ደስተኛ አድርጎታል፡፡

ከእለታት አንድ ቀን እነያሬድ ቤት የሽንብራ ቆሎ እየፈጩ ፤ ከስንዴው ጠላ ጎንጨት እያሉ የወደፊት ምኞታቸውና አላማቸውን ይጫወታሉ፡፡

"ለወደፊት ምን ለመስራት አስበሃል?" ብሎ ጠየቀው ተመስገን፡፡

"እኔ ለቀጣይ ያስብኩት አሁን የጀመርኩትን ቤት ስጨርስ ቤተሰቦቼ ትምህርትህን ከተወህ ማግባት አለብህ እያሉኝ ስለሆነ ለማግባት አቅጃለሁ፡፡ ብሎት አንተስ ምን አስበሃል? አለው ያሬድ፡፡

ተመስገን የወደፊት ምኞትና እቅዱ ከጓደኛው ያሬድ የተለየና ተቃራኒ ነው፡፡ "እኔ እንኳን እህቴን እስከማገኝ ድረስ ትዳር የመያዝ ሃሳብና ፍላጎት የለኝም"፡፡

ቤተሰቦቸን እየረዳሁ ለራሴም ትንሽ እያጠራቀምኩ ለመኖር ነው የማስበው አለ፡፡

ያሬድ የተመስገንን እቅድ ሲሰማ እህቱን በፊትም እደሚወዳት ስለሚያቅ ለምን አታገባም ብሎም አልጠይቀውም..፡፡

አርምዴ

ባለቤታቸው ከሞተ በኋላ፤ ሌላ ባል አላገቡም፡፡ ወደ ውጭ ወጥተው ጎንበስ ቀና ብለው መስራት አይችሉም፡፡

ልጃቸው ሰርቶ የሚሰጣቸውን እህል አብስለው ለመብላት ያልተቸገሩ የስልሳ ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው፡፡ የአርምዴ እናት ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

ቀኑ እንደመምሸት ብሎ ለዓይን ያዝ አድርጓል፡፡ ኩራዝ ለመለኮስ ከምድጃቸው እሳት ለማቀጣጠል ይታገላሉ፡፡

አይናቸው ተርገበገበባቸው፡፡ ዛሬ ደግሞ በምሽት ምን ሊያሳየኝ ነው ፡፡ አይኔ የሚርገበገበው እያሉ የውጭ በር ተንኳኳ

እሳት ማቀጣጠሉን ተወት አርገው ወደ ውጭ ወጡ፡፡ ልጃቸው አርምዴ እድላዊትን አዝሎ ገባ፡፡ ደነገጡ፡፡

"ውይ! በሞትኩት ልጄ ምን ሆና ነው? ብለው ጠየቁት፡፡

እረኞች ጫካ ውስጥ መሬት ለመሬት ጎትተዋት ነው፡፡

"እና በጣም ጎድተዋታል" ?

"አዎ! ይዣትም ስመጣ ለማናገር ብሞክርም ማናገር አልቻለችም"፡፡

"ታዲያ ከየት እንደመጣችም አልነገረችህም"?

"አልነገረችኝም ፡፡ ጩኸት ሰምቼ እየሮጥሁ ሲሄድ ጥለዋት ተበታተኑ፡፡ እሷም ተጎድታ ስለነበር አላናገረችኝም፡፡ እንዴው እግዚአብሔር ድረስላት ሲለኝ ነው እንጂ ዛሬ አደን የሔድኩት ይገሏት ነበር፡፡

"አሁን ምን እንስጣት? ነው ትንሽ ትተኛ? ድካሟ እስከ ሚያልፍላት አሉ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

ወደ አስተኛት ፍራሽ ላይ ተጠጋ፡፡ እድላዊት አይኖቿን አንከራተተች፡፡ ግራና ቀኝ ተቁለጨለጨች፡፡

አርምዴ የእድላዊትን አይኖች መንከራተትና በእንባ መሞላት አየ፡፡ እሱም ከየት መጣ ሳይባል አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡

እድላዊት አርምዴን የምትመለከተው ውሃ ስጠኝ ለማለት ነበር፡፡ ግን መናገር አቅቷታል፡፡

አቶ አርምዴ ውሃ መፈለጓን የተረዳት አይመስልም፡፡ አንጀቱ እንደነብሰጡር ተላወሰ፡፡ እንባ እየተናነቀው "ምን ልስጥሽ " አላት፡፡

እድላዊት መናገር አልቻለችም፡፡ በእጇ ውሃ እንደ ጠማት አመለከተችው፡፡

አቶ አርምዴ በምልክት የገለፀችውን ሳያደናግረው ተረዳት፡፡ ውሃ ቀድቶ ሰጣት፡፡

ውሃው ወደ ውስጥ መግባቱን ትቶ ግራና ቀኝ በአፏ ወደ ውጭ ፈሰሰ፡፡

እድላዊት በውሃ ጥም የተነሳ ቶንሲሏ ወርዷል፡፡ አቶ አርምዴ የባሰ ተጨነቀ

"ውይ በሞትኩት ልጄን ውሃ አልወርድላት አለ ? ቶንሲሏ ወርዶ ይሆናል አሉ፤ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

"እና ምን ይሻላል? መድሃኒት በቅርብ አይገኝም? አለ ፤ አቶ አርምዴ፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ የሃበሻ መድሃኒት ሊያቀምሷት መድሃኒቱን እንዲያመጣላቸው ልጃቸውን እንዳይልኩት መድሃኒቱ ሲቆረጥ ስሙ መጠራት የለበትም፡፡ እራሳቸው ለመቁረጥ ቆይ እስቲ መጣሁ ብለው ወደ ጓሮ ሄዱ፡፡

ለቶንሲል መድሃኒት የሚሆነውን ሰባት የጌሾ ቀንበጥ ቆርጠው አመጡ፡፡ ለእድላዊት እንድታኝከው ሰጧት፡፡

እድላዊት መናገር ቢያቅታትም መስማት ትችላለች፡፡ የተሰጠችውን የቶንሲል መድሃኒት አኝኪው ስለተባለች ብቻ

እየመረራት ቢሆንም ጨክና አኘከችው፡፡

በውሃ ጥም ምራቋ ደርቋል፡፡ ከንፈሮቿም ኩበት መስለዋል፡፡ ምላሷ ብቻ ብቅ ጥልቅ ይላል፡፡ ነብሷ ልትወጣ ደረሰች፡፡ ሰውነቷ በላብ ተዘፈቀ፡፡ ልቧ ተጨነቀች፡፡ በጀመረችው የምልክት ቋንቋ ውሃ ስጡኝ ብላ በእጇ አመለከተች፡፡

አቶ አርምዴ የእድላዊት ነገር አሁንም ግራ ገባው፡፡ ከሸንበቆ ላይ ቀጭን ሸንበቆ ተከርክሞ እድላዊት በሸንበቆው አማካኝነት ውሃ እንድትቀምስ ተደረገ፡፡

ለእድላዊት እንጀራ እንዳይሰጧት ችላ አትበላም፡፡ ምን እንደሚሰጧት ጨነቃቸው፡፡ የእድላዊት ነገር አንጀታቸውን በላው፡፡

በደከመ አቅማቸውም ቢሆን ትንሽ ገንፎ አገንፍተው እንድትቀምስ አደረጉ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

እድላዊት የተሰራላትን ገንፎ ለመድሃኒት ያህል ቀመሰች፡፡ ወ/ሮ በሰልፏ ለቶንሲሏ ሌላ መዳኒት ዝንጅብል እንድታኝክበት ሰጧት፡፡

"ለቶንሲል ጥሩ ነው፡፡ ለነገ በደንብ ይሻልሻል፡፡ አይዞሽ እያሉ ልጃቸው ያሰረላትን ጨርቅ ከቁስሏ ላይ ፈቱላት፡፡ ለብ ባለ ውሃ አጠቡላት፡፡ ያበጠውን እግርና እጇንም በቅባት አሹላት፡፡ የተላላጠውን ቁስሏንም በነጠላ ጨርቅ ተኩሰው መኝታ ላይ ጋደም እንድትል አደረጉ፡፡

አቶ አርምዴ የሚደረግላትን ካደረገ በኋላ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ አድሮ በነጋታው ጥዋት እድላዊት እንዴት እንዳደረች ለመጠየቅ ከመኝታው ተነስቶ ሲመጣ እናቱ የቤቱን በር ከፍተው ሲወጡ ደረሰ፡፡

የእግዚአብሔር ሰላምታ ተለዋውጠው "ደግሞ ማታ እመለሳለሁ ብለህ ሳትመጣ ቀረህ በሰላም ነው ያልተመለስከው? አሉት ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

"ለመምጣት አስቤ ነበር፡፡ ግን ቤቱንና ከብቶቹን ትቼ እንዳልመጣ አውሬ እንኳን ቢገባ የሚሰማ ስላልነበረ ቀረሁ"፡፡ እንዴት አደረች ልጅቷ?ተሸሏት አላደረችም? አለ፡፡

የእድላዊት ስቃይና መከራ ከአንጀቱ ገብቶ ሳይወጣ አንጀቱ እያለቀሰላት እህል እንኳን አልወርድ ብሎት ለአደን ሲሄድ በቀመሰው ቁራሽ እንጀራ ነበር፡፡ እራት ሳይቀምስ ያደረው፡፡

ከአሁን አሁን ያማት ይሆን ? እያሉ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ሳይወስዳቸው አይደለም በዓይናቸው ሳይዞር ነበር ያደሩት ወ/ሮ በሰልፏም፡፡

"ሰላም አድራለች፡፡ ብቻ ሌሊቱን ሲያቃዧት ነው ያደረው፡፡ አሟት ይሆን ብየ ሌሊት ተነስቼ ሳያት ከቅዠት በስተቀር ምንም አላየሁባትም፡፡ ከነጋም አልቀሰቀስኳትም፡፡ ቅዝቃዜ ስላለ ትንሽ ትተኛ ብየ ነው፡፡ እስኪ አሁን አንተ ከመጣህ ቀስቅሳትና እንዴት እንዳደረች ጠይቃት አሉ፡፡ ቤታቸውን ለመጥረግ የቤት መጥረጊያ ቅጠል ለማምጣት ወደ ውጭ እየወጡ፡፡
👍8813🥰3👎1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አለማየሁ ልቡ ላይ አዲስ እና ያልተጠበቀ ፍቅር በቅሏል…የአስካለ ምስልም በተለይ ወሬዋና ሳቋ  ከምናቡ ለደቂቃም ሊሰወር አልቻለም፡፡ለዘላለም ከሰሎሜ ውጭ ሌላ ሰው ሊያፍቀር ሚችል አይመስለውም ነበር…ግን ሆነ፡፡እርግጥ ለሁለቱ ያለው ፍቅር ፍፅም ተመሳሳይ አይደለም….ይሄኛው አዲሱ ፍቅሩ የሚያንቀዠቅዝ አይነት ነው፡፡የወሲብ ርሀብ ያለበት የተክለፈለፈ ፍቅር፡፡የሰሎሜ ግን የተረጋጋና ጥልቅ ነው፡፡ስስትና እና ተስፋ ያቆሙት  ዘላለማዊ መሳይ ነው፡፡
ከአስካለ ጋር ባሳለፈ በሁለተኛው ቀን ወደአላዛር ሄደና‹‹አባትህ እንዴት ናቸው?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ያው ድኖ አይደል ወደቤት የገባው…ምን ይሆናል?››ሲል ድርቅ ያለ መልስ መለሰለት፡፡
‹‹አሁን እንዴት እንደሆኑ ደውለህ ጠየቅክ?››
‹‹ለምን ብዬ ጠይቃለሁ?››
‹‹በትክክል መጠየቅ ይገባሀል…›››
‹‹የትናንቱንም እንዴት እንዳደረኩት ግራ እየገባኝ ነው››
‹‹እንደውም ተነስ እንሂድና አይተናቸው እንምጣ፡፡››
አላዛር ግራ በመጋባት አፍጥጦ ሲያየው ከቆየ በኃላ፡፡‹‹ሰላም ነህ ግን?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ምነው…ምኔ ነው ሰላም አልመስል ያለህ ?››ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡
‹‹ የምናገረው አይገባህም እንዴ? ትናንት በዛ ለሊት ለእሱ ስል ራሴም ተንከራትቼ እናንተንም ሳንከራተት ማደሬ እራሱ እየቆጨኝ ነው ..ጭራሽ ዛሬም ደግሜ ቤት ሄጄ እንድጠይቀው ትፈልጋለህ?፡፡››
‹‹ተወው በኃላ እንዳትፀፀት …ላንተው ብዬ ነው፡፡እኔ አባቴ ጠጪም ሌባም ፤ቁማርተኛም ..ምንም ሆኖ ምንም በህይወት ቢኖርልኝ እንዴት እንደምደሰት ልትገምት አትችልም፡፡በዚህ አለም ላይ እንደቤተሰብ ወሳኝ ነገር የለም፡፡ከፋም ለማም በጨለማ ቀናቶችህ አብረውህ የሚንከራተቱት እነሱ ናቸው፡፡..ቤተሰብ በህይወት መንገድ ወሳኙ አጋር እንደሆነ አውቃለው፡፡የገንዘብ ችግር ቢኖርብህ ቤተሰብ ካለህ ታልፈዋለ…ክፉኛ ብትታመም ቤተሰብ ካለህ ህመምህን ቻል አድርገህ በቀላሉ ማገገም ትችላለህ …ሀገርህ ፈርሳ ስደት ላይ ብትሆን እራሱ ቤተሰብህ ከጎንህ ካለ እንደምንም እየተደጋገፍክ ያንን ክፉ ቀን ታልፈዋለህ፡፡››
‹‹ገባኝ…የእኔ ቤተሰብ እናቴና እህቶቼ ናቸው፡፡በተጨማሪ ደግሞ እናንተ ወንድሞቼ አላችሁልኝ…እርግጥ እናቴ የለችም….ሁለት እህቶቼ ግን አሁንም አሉልኝ..እነሱ በቂዬ ናቸው፡፡ለእኔ አባቴ ከእናቴ ቀድሞ ነው የሞተው…አሁን እሱን ሳይ በድን አካሉ ብቻ ነው ሲንቀሳቀስ የማየው..ነፍሱ ውስጡ የለችም፡፡››
አለማየሁ ሊያሳምነው ስላልቻለ ተበሳጨ‹‹በቃ ቸው..ድሮም አንተ ከጠመምክ  መመለሻ የለህም››አለውና ፊቱን አዙሮ መራመድ ጀመረ፡፡
‹‹ቆይ አትሂድ..ና እንካ››አለና እጁን ወደባንኮኒው በመስደድ ብር በእጁ አስጨበጠው፡፡
‹‹ምንድነው?››
‹‹ማኪያቶ ልጋብዝህ ነበር …መውጣት አልቻልኩም..ስለዚህ ብቻህን ጠጣ››አለው፡፡
አለማየሁም‹‹አመሰግናለሁ፡፡››ብሎት የሰጠውን ብር በእጁ እያሻሸ አካባቢውን ለቆ ሄደ ..የእሱ ሀሳብ አላዛርን አሳምኖ አባቱ ቤት አብሮት መሄድ ነበር፡፡፡ያንን የፈለገው ያችን ውብ የጓደኛውን አባት ሚስት ዳግመኛ ለማየት ነው፡፡ከትናንትናው ምሽት ጀምሮ ፈፅሞ ከምናቡ ሊያሸሻት አልተቻለውም፡፡የአላዛር መገገም ግን እቅዱን ሁሉ ገደል ከተተበት፡፡
ከአላዛር ሱቅ ከራቀ በኃላ መዳፉን ፈልቅቆ ሲያየው ድፍን መቶ ብር ነው፡፡ስልኩን አወጣ ..ሰሎሜ ጋር ለመደወል ነው የፈለገው፡፡መቶ ብር ካለው ወይ ይዟት ሲኒማ ቤት ይገባል ወይ ደግሞ አንድ ካፌ ቁጭ ብለው ማኪያቶ እየተጎነጩ  ዘና ይላሉ፡፡እቅዱ እንደዛ ነው፡፡
‹‹ሄሎ ››
‹‹ምነው? አሁን ተለይተሀኝ ሄደህ አሁን ናፈቅኩህ እንዴ?››
‹‹ውይ ሰው ጠፍቶ አንቺ ትናፍቂኛለሽ…..?ጉረኛ ነሽ››
‹‹እመን …..››
‹‹ለምን ብዬ ነው የማምነው?››
‹‹እሺ ለምን ፈለከኝ?››
‹‹ምን እየሰራሽ ነው…?አመድ በኪሴ ስላለ ዘና ላድርግሽ ብዬ ነው…››
‹‹አንድ ጥብስ የማይገዛ ብር ይዘህ..ዘና ላድርግሽ ብዬ ነው ስትል ትንሽ አይሸምምህም?››
‹‹አንቺ ምስጋና ቢስ…ይሄኔ በኪስሽ አምስት ብር የለም…አሁን ትወጪያለሽ ወይስ አትወጪም?››
‹‹አዝናለሁ እቴቴ...ዘመዶቾ ጋር እንሂድ ብላኝ ለመሄድ እየተዘጋጀን ነው፡፡››
‹‹የት ?ሰንዳፋ?››
‹‹አዎ…ምነው መሄድ ትፈልጋለህ እንዴ?››
‹‹አይ ይለፈኝ…ግን ታድራላችሁ እንዴ?››
‹‹አዎ… ነገ ነው ምንመጣው፡፡››
‹‹እሺ መልካም መንገድ፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ በጊዜ ወደቤት ግባ …እቴቴ እንዳታዘርፈኝ እያለች ነው ፡፡››
‹‹እሺ …አታስቢ በያት፡፡››ብሎ ስልኩን ዘጋውና ተቀያሪ ሀሳብ ማብላላት ጀመረ…ወዲያው ነው መሳጭ የሆነ ሀሳብ ብልጭ ያለለት‹‹ መንገድ ተሻገረና ወደአትክልት መሸጫ ሱቅ ሄደ ..አንድ ኪሎ ሙዝ ገዛ፡፡ ታክሲ ውስጥ ገባ ፡፡ቀጥታ ወደአላዛር አባት ሰፈር ነው የሄደው፡፡ደረሰና የውጪውን በራፍ አንኳኳ…፡፡
ከተወሰነ ጥበቃ በኃላ ተከፈተለት…
ይህቺን ሴት ለሁለተኛ ጊዜ ሲያያት ይበልጥ አምራና ውብ ሆና ነው የታየችው፡፡አስካለ ፈፅሞ አየዋለሁ ብላ ያልጠበቀችው ስለሆነ በጣም ነው የደነገጠችው፡፡
በዝምታ አፍጥጣ ስታየው ግራ ተጋባና ‹‹ምነው አላወቅሺኝም እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡
በራፉን ጋርዳ እንደቆመች‹‹ይቅርታ እንዲህ በቅርቡ ደግሜ አይሀለው ብዬ ስላልገመትኩ ነው…እንጂማ አንተን እንዴት እረሳሀለው፡››አለችው ፡፡
በጥቁር ፔስታል የያዘውን ሙዝ እንድታይ እያወዛወዘ፡፡‹‹ጋሼን ለመጠየቅ ነው የመጣሁት››አላት፡፡
‹‹ግባ…ና ግባ››አለችና በራፉን ለቀቀችለትና ቀድማው ወደውስጥ መራመድ ጀመረች ፡፡ከኃላዋ ተከተላት፡፡ገቡ፡፡
‹‹ቁጭ በል፡፡››ሙዙን አቀበላትና ፈራ ተባ እያለ ቁጭ አለ፡፡
‹‹አሁን የእውነት ሰውዬው እሷቸውን ልጠይቅ እንደመጣው ያምኑኛል?››ሲል ከዚህ በፊት ያላሰበውን ነገር አሰበ‹‹አይ አላዛር ነው የላከኝ ..ስራ ላይ ስለሆንኩ ሰላም መሆኑን እይልኝ ሳለለኝ ነው የመጣሁት፡፡››እለዋለው ሲል ወሰና ተረጋጋ፡፡ሙዙን ተቀበለችውና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ..ከፊት ለፊቱ ሄዳ ተቀመጠች፡፡
‹‹ጋሼ ተኝተዋል እንዴ?››ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡
‹‹‹የሉም ስራ ገብተዋል››
በረጅሙ ተነፈሰ‹‹እንደዛ ነው…በደንብ ተሻሏቸዋል ማለት ነው?››
‹‹አዎ በደንብ ተሽሏቸዋል፡፡አተነፋፈስህ ግን ባለመኖራቸው ደስ ያለህ ይመስላል››አለችው፡፡ የውስጡን ስላነበበችበት አፈረ፡፡
‹‹አይ..ያው አለ አይደለ..ከድሮም ጀምሮ እፈራቸዋለው…ለዛ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ ይሄን ያህል የሚያጨናንቅህ ከሆነ ለምን መጣህ?››ብላ ሲፈራው የቆየውን ከባድ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው አላዛር ስራ ላይ ስለሆነ መጥቶ ሊጠይቃቸው አልቻለም…እይልኝ ብሎ ስላስቸገረኝ ነው››ከደቂቃ በፊት ያቀናበረውን ምክንያት ነገራት፡፡
ፈገግ አለች….
‹‹ምነው?››
‹‹አይ …እኔ ደግሞ እኔን ለማየት የመጣህ መስሎኝ ደስ ብሎኝ ነበር?››ስትል ያልጠበቀውን አማላይ አይነት መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹እሱማ ..ያው እግረመንገዴን አንቺንም ማየትና እንዴት እንደሆንሽ ማወቅ ስለፈለኩ ነው የመጣሁት፡፡››ሲል በከፊል  አመነላት፡፡
‹‹ስለመጣህ ደስ ብሎኛል…መጣው ተጫወት›› ብላ ወደውስጥ ገባችና ..ሻይ ጥዳ….ተመለሰች፡፡
ሞባይሉን አወጣና ሰዓቱን ተመለከተ..5፡20 ይላል፡፡‹‹ምሳ ሰዓት እየቀረበ ነው….››አላት፡፡
‹‹አዎ ..ምነው እርቦሀል ላቅርብ እንዴ?››
‹‹አይ!! ማለቴ ጋሼ  አሁን ለምሳ ይመጣሉ ለማለት ነው፡፡››
👍5614
#አላገባህም


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

ዘሚካኤል  ተገትሮ በቆመበት የክፍሉ መሀከላዊ ስፍራ እንደደነዘዘ ነው፡፡ልጅቱ አስር ለማይሞሉ ደቂቃዎች ብቻ አብራው ብታሳልፍም….ግን ደግሞ ለቀናት ያህል ያቀፋትና ለሳዕታት ሲስማት የቆየ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው…‹‹.ለምን ጉዳይ መጣች ምን ሰርታ ሄደች?››ብሎ ሲያስብ ሳይወድ ፈገግ አለ…ከቆመበት ተንቀሳቀሰና እጁ ላይ ያለውን የሰርግ የጥሪ ካርድ የያዘውን ፖስታ በራፉ አጠገብ በሚገኘው ቆሻሻ ማጠረቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ጨምድዶ ወረወረው፡፡

ለዛች ስሟን እንኳን ላልነገረችው ሴት ልጅ እንደነገራት በዚህ አለም ምንም አይነት  ወንድም ሆነ ቤተሰብ አያስፈልገውም እና ወደ የትኛውም ሰርግ የመሄድ ፍላጎት የለውም። እንደውም ከተቻለው ስለቤተሰብ በውስጡ የቀረውን እንጥፍጣፊ ትዝታ ከልቡ አሟጦ መሰረዝ ነው ፍላጎቱ፡፡

ከወገብ በላይ ራቁቱን መሆኑን ትዝ ሲለው ወደጠረጴዛው ሄደና ያወለቀውን ልብስ መልሶ ለበሰው..መጀመሪያ እቅዱ ቀጣይ የሙዚቃ ማቅረቢያ ሰዓቱ እስኪደርስ ድረስ ሻወር ገብቶ ከተለቃለቀ በኃላ 30 ወይም 40 ደቂቃ መተኛትና እረፍት መውሰድ ነበር፡፡አሁን ግን ሻወር የመውሰድም ሆነ የመተኛት ፍላጎቱ ከውስጡ በኖ ጠፍቷል…ቀጥታ ሶፋው ላይ ሄደና ተቀመጠ፡፡ፊትለፊት ካለው ጠረጴዛ ላይ ያለውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳና ከፍቶ በብርጭቆ ቀድቶ እየተጎነጨ ማሰላሰል ጀመረ….

‹‹ይህቺ ልጅ ምኑን ነክታ እንዴት ስሜቱን ድፍርስርስ አድርጋ እንደሄደች አያውቅም…ወንድሙ ላይ የያዘበት ቂምና የተበሳጨበት ብስጭት አሁንም ትኩስ ነው፡፡

‹‹ግን የዛን ጊዜ ፈቅዶልኝ አባቴን በዛ ቢላዋ ጨቅጭቄ ብገድለው ኖሮስ…?››ሁል ጊዜ እራሱን የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡

አዎ ወንድሙ በድብድብ እና በትግል ባያስቆመው ኖሮ እሱም ይሄን ጊዜ የእድሜ ልክ ፍርድ ተፈርዶበት በአባቱ ምትክ እስር ቤት ውስጥ ተቆልፎበት ተስፋ የሌለው ህይወት ይኖር እንደነበረ…እርግጠኛ ነው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ ሚካኤል ወንድምህ የእድሜ ልክ ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም?››አለው አእምሮው፡፡

‹‹ለምን..ያማ እውነት አይደለም….እሱ እኮ  እንደዛ ያደረገው እኔን ከመከራ ለማትረፍ አስቦ ሳይሆን ለዛ ጨካኝ እና ገዳይ አባቱ ለማገዝ ፈልጎ ነው››

‹‹አይ እሱ የአንተ አእምሮ አንሻፎ የተረጎመው ትርጉም ነው…እንደዛም ቢሆን እንኳን በዛ  ታሪክ ውስጥ ዋናው ተጠቃሚ አንተ ነህ፡፡በወቅቱ ዝም ብሎህ ያሰብከውን እንድታደርግ ቢፈቅድልህ ኖሮ ዛሬ በዚህ ጊዜ ዝነኛው ድምፃዊና ተዋናዩ ዘሚካኤል የለም ነበር…ሀመር መኪና የሚነዳው…የተንጣለለ ውድና ውብ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖረው…ከአደባባይ እስከቤተመንግስት የሚታወቀውና የሚጋበዘው የመገናኛ ብዙሀኖች የዜና ማጣፈጫ የሆነው ዘሚካኤል አይኖርም ነበር፡፡››ሲል እራሱን በራሱ በዝርዝር አስረዳ፡፡
የአእምሮው የእርስ በርስ ጭቅጭቅ ከዚህ በላይ ማስቀጠል አልቻለም..ምክንያቱም በንዴትና በቁጭት አእምሮው ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቱ እየጋለበት ነው፡፡ጠረጴዛው ላይ ያለውን ብርጭቆ አነሳና ጠቀም አድርጎ ተጎነጨለት እና መልሶ አስቀመጠው፡፡
ከዛ ስለሌላ ነገር ለማሰብ ሞከረ ..ግን አሁንም አእምሮውን የሞላችው ያቺ ከደቂቃዎች በፊት ከሰውነቱ ለጥፎ ያቀፋትና ለሁለት ሰከንድ ሲስማት የነበረችው ሴት ነች፡፡‹‹ቆይ ይህቺ ልጅ ምን የተለየ ነገር ቢኖራት ነው ከአእምሮዬ ልትወጣ ያልቻለችው ?››እራሱን ጠየቀ…‹‹ከንፈሯ ላይ አስማት አለ መሰለኝ…››አለና ፈገግ አለ….‹‹ምን አለ ስሟን እና  የሞባይል ቁጥሯን ብጠይቃት ኖሮ…?››በጣም ተቆጨ፡፡
ደግሞ እሷም እሱን በምንም አይነት ሁኔታ ደግማ  የማግኘት ፍላጎት እንደሌላት በሚያሳይ ሁኔታ ነው የመጣችበትን ጉዳይ ተናግራ የጥሪ ካርድን እጁ ላይ አስቀምጣ ነው ውልቅ ብላ የሄደችው፡፡

‹‹ባለትዳር ትሆን እንዴ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡
ሀሳብን መቋጫ ሳያበጅለት በራፉ በስሱ ተቆረቆረ…ብርጭቆ ውስጥ የቀረችውን ውስኪ ጨለጠና ሶፋውን ለቆ ወደበራፉ ሄደ ..ቀጣይ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜ መድረሱን ለማሳወቅ በራፉን እንደቆረቆሩ ያውቀል..በራፉን ከፍቶ ሲወጣ ንቁ ሆነው የሚጠብቁት ሁለት ወጠምሻ ጋርዶች ከግራና ከቀኝ ከበቡት፡፡ ሁለት እርምጃ ከተራመደ በኃላ የሆነ ነገር ወደኃላ ሳበው…መልሶ ፊቱን ዞረና ወደክፍሉ ተመለሰ….ከውስጥ በኩል ከበራፉ በስተቀኝ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ባስኬት አጎነበሰና አጣጥፎ የጣለውን የሰርግ ጥሪ ወረቀት አነሳ ፡፡የሱሪ ኋላ ኪስ ውስጥ ጨመረውና መልሶ ወጣ..ለምን እንዲህ እንዳደረገ ቢጠየቅ ምንም አይነት መልስ የለውም …እንዲሁ በደመነፍስ ያደረገው ነገር ነው፡፡
////
አሁን የዘሚካኤል ምስል ከሙሉ አቋሙ ጋር በአእምሯዋ እየተራወጠ ነው፡፡ሁለቱ ወንድማማቾች ከቁመትና ከፀባይ ውጭ በሌላው ነገር በሚያስደንቅ ሁኔታ ይመሳሰላሉ። የሚካኤል  ባህሪያት ከዘሚካኤል ትንሽ ደብዘዝ ያሉ ነበሩ እና የዓይኑ ቀለም ንፁህ ፣ ጠንከር ያለ ሰማያዊ ነበረ ፣ ግን ሁለቱም ሰዎች ተመሳሳይ ውብ ፈገግታ፣ ክብ የፊት ቅርፅ እና ሰልካካ አፍንጫ.. ወተት ከመሰሉ ነጫጭ ድርድር ጥርሶች ጋር አላቸው፤››
እየሾፈረች ያለችውን ቪታራ መኪና ኤክስፐረስ መንገድ ውስጥ አስገብታ ወደ አዳማ እያሽከረከረች   ሲሆን አሁንም ስለዛ ዘ-ሚካኤል ስለሚባለው ድምጻዊ ነው የምታሰላስለው፡፡ለሊት 8 ሰዓት ላይ ከእሱ ተለይታ እዛው በአቅራቢያው ወደተከራየችው ፕንሲዬን ሄዳ ለመተኛት ብትሞክርም ምንም እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር እንዲሁ ስትበሳጭና ስትገላበጥ ነው ያደረችው፡፡
ስለእሱ ማሰብ   የጀመረችው ቀደም ብላ ታሪኩን ከየጋዜጦችና ከዪቲዩብ ቻናሎች እየሰበሰበች በምታዳምጥበት ጊዜ ነው፡፡እርግጥ ታውቀለች በዩቲዩቭ የቀረበ ዜና ሁሉ በተለይ ስለፍቅርና ፃታዊ ግንኙነት የሚነዙት አብዛኞቹ ተመልካች ለማግኘት የታስቡ…በውሸት የሚፈበረኩ እንደሚሆን ታምናለች..ግን ቢሆንም‹‹ እሳት በሌለበት ጭስ አይጨስም….››በማለት ለሰው ስሜት የማይጨነቅ ጋጠወጥ ወሲባም አድርጋ ስላው ነበር፡፡እና ደግሞ ለሊት እንዳየችው አልተሳሳተችም…በዛ ለሊት እዛ ክፍል ውስጥ ሲያገኛት መጀመሪያ ያደረገው ወደራሱ ስቦ ከንፈሯ ላይ መጣበቅ ነው…..ስለዛች ቅፅበት ስታስብ ከንፈሯ  ተንቀጠቀጠባት….የሚያበሳጨው ደግሞ ለማንም ሴት ግርማ ሞገሱንና ውበቱን ለመቋቋም አስቸጋሪ የሆነ ሰው መሆኑን በራሷ ማረጋገጧ ነው…ባለፉት ስድስት አመታት በጣም ብዙ ከሆኑ ወንዶች በብዙ የተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈታተኗት ሞክረው ሾልካና አሳስቃ ..አንዳንዱንም ተኮሳትራና አስፈራርታ እራሷን ማትረፍ ችላለች..ከእሱ ጋር ግን በአንድ እይታ ነው ተዝለፍልፋ እቅፉ ውስጥ የወደቀችው፡፡
እንደምንም ከእቅፉ ወጥታ ለማምለጥ ወደበራፉ  በምትራመድበት ጊዜ እንኳን ተንደርድሮ መጥቶ እጇን ይዞ  ጎትቶ እንዲያስቀራት እና ተሸክሞ ሶፋው ላይ እንዲጥላት በውስጧ እየተመኘች ነበር፡፡ግን በተመሳሳይ ጊዜ እንደዛ በመመኘቷ እራሷን ስትወቅስና ስትራገም ነበር፡፡
👍6113👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


እሁድ የእረፍት ቀን ስለሆነ ኤልያስ ከወንድሙና ከጓደኛው ጋር ካፌ ቁጭ ብለው ቁምነገሩንም ቀልዱንም ሲጫወቱ አረፈድና ሌላ የሚሄዱበት ቦታ ስለነበር ተያይዘው ወጡ፡፡ሶስቱም የቢኒያም መኪና ወዳቆመችበት ቦታ እየተለፉ እየሄዱ ሳለ ድንገት ኤልያስ ከወንድሙ ከቢኒያም ጉሽሚያ ለማምለጥ ወደኃላው ሲሸሽ ከአንድ ውብ ሴት ጋር ተላተመ ፡፡ሴትዬዋ በእጇ የያዘችው ወረቀቶቿ ከእጆቿ ተንሸራተው ወደቁ  እና ቦርሳዋ ከተከሻዋ  ተንሸራቶ ሊወድቅባት ነበር…እሷም ተነገዳግዳ ሚዛኗን ለመሳት ስትጥር  ኤልያስ በፍጥነት ተስፈነጠረና ክንዷን ያዛት  ። ተረጋግቶ ሲያያት አይኖቹን ማመን ነው ያቃተው ።፡ራሄል ነች፡፡ ሞባይል ስልኳ አንድ ጆሮዋ ላይ ተጣብቆል…ስልክ እያወራች እንደነበር ተገነዘበ፡፡

አቀርቅራ የተበተኑ ወረቀቷቾን እያየች‹‹ምንድነው…አይንህ አያይም እንዴ? አብደሃል?››ስትል ጮኸችበት ።ከዚያም ቀና ብሎ አያት።ሀዘን  ያረበባቸው አይኖቿ እሱን ሲያዩት ፣ ንዴቷ በጥልቀት ወደ ውስጡ ዘልቆ ሲገባ ተሰማው። በልቡ ክልል ውስጥ የሆነ ቦታ ላይ የብርሃን ብልጭታ ፈነጠቀ።ድንገት ወደጎን ዞር ብላ እሱ መሆኑን ስታውቅ በንግግሯ አፈረች፡፡‹‹እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ››ብላ አጉተመተመች፣ክንዷን ወደኋላ ጎተተች። አሁንም እንደያዛት ረስቶት ነበር። ፈጠን ብሎ  ለቀቃት። ርቀቱን ጠብቆ  በጉጉት እያዩ ወደነበሩት ወንድሙ እና ጓደኛው  እየተመለከተ። ‹‹ይቅርታ አላየሁሽም….ከወንድሜ ቢኒ ጡጫ እራሴን ለማራቅ   እየሞከርኩ ነበር.››አላት፡፡

‹‹ምንም አይደለም፣ እኔም ቀልቤ  የማወራው ስልክ ላይ ስለነበር መጠንቀቅ አልቻልኩም ።›› በማለት ወረቀቶቿን ለማንሳት ጎንበስ አለች።

‹‹ቆይ እኔ ላንሳልሽ›› ብሎ እሱም ጎንበስ አለ… ሁለቱም በአንድነት እጇቸውን ወደወረቀቱ ሲሰዱ እርስ በርስ ተነካኩ ፡፡በመሀከላቸው የኤሌክትሪክ ንዝረት አይነት ቅፅበታዊ ብልጭታ ተፈጠረ፡፡

‹‹እባክህ አትጨነቅ››  የውስጥ ስሜቱን  የሚቆሰቁስ  አይነት እንደገና የሚያነቃቃ ፈጣን ፈገግታ ሰጠችው።

ወረቀቶቹን ሰብስበው ከተነሱ በኋላ‹‹ለመሆኑ እዚህ ሰፈር ምን እግር ጣለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ለስራ ጉዳይ››ስትል አፏ ላይ የመጣላትን ምክንያት ሰጠችው፡፡

‹‹ በእረፍት ቀን ትሰሪያለሽ እንዴ?››

ራሄል ፊቷን አኮሳትራ‹‹ስራ እስካለኝ ድረስ ቀን ሳልመርጥ ነው የምሰራው..ታውቃለህ  …ሥራዬ በጣም አስፈላጊ ነው።››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹ደህና፣ በቃ እንገናኛለን።››

‹‹ተስፋ አደርጋለው።›› አለችና መንገዷን ቀጠለች ፡፡

‹‹አሁንም አለሽ ራሄል?›› ከያዘችው የሞባይል ስልክ የአንድ ወንድ ድምፅ ተሰማ። እናም ራሄል እስከአሁን ስልኳ እንዳልተቆረጠ ስትረዳ  ‹‹ ሮቤል በቃ ቆይቼ ደውልሀለው … መንገድ ላይ ያልሆነ ነገር አጋጥሞኝ ነው›› ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡

ከዛም እርምጃዋን ሳታቋርጥ  ወደ ዔሊያስ ዞር ብላ ተመለከተች …በተገተረበት ቆሞ እያያት ነበር ..የሆነ ውርር የሚያደርግ ስሜት ተሰማት ፡፡መንገዱን አቋርጣ ወደካፌው ታጠፈችና ከእይታው ተሰወረች፡፡

ሁኔታውን በትኩረት ሲከታተሉ የቆዩት  ቢንያም እና ጓደኛው ወደ እሱ  ሮጠው ከጎኑ ቆመ

‹‹በቀጣዬቹ አመታት ውስጥ ያለህ የሕይወት እቅድ ውስጥ  ሴት እንደሌለችበት ደጋግመህ ነግረኸኝ ነበር? ››አለው ቢኒያም፡፡

‹‹እና ታዲያ?››

‹‹እናማ ይህቺ ሴት ማን ነች?።››

ዔሊያስ  ለወንድሙ  ‹‹የህይወት እቅዴ ላይ ምንም ማስተካከያ አልተደረገበትም..ያንን ካወቅክ ይበቃል።››ብሎት ወደመኪናው ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ወንድሙም ከኋላው ተከትሎት‹‹እቅድህን ማስተካከል ትችላለህ …በቅድሚያ ግን ብድርህን ክፈል፣ ሞተርህን ሽጥና ትክክለኛ መኪና ግዛ፣ ከዛ  ኑሮህን የምትጋራ ሴት መፈለግ ትችላለህ››አለው

ዔሊያስ ሕይወት ሁል ጊዜ እንደማይተነበይ ከግል ተሞክሮ ያውቃል ።  ዔሊ በስድስት ዓመቱ ወደ ማደጎ ቤት ለመግባት ተገዶ ነበር፡፡   በወቅቱ ጮርቃ  ልጅ ነበር  እና ስለ ተፈጥሮ ወላጆቹ የሚያውቀው ብቸኛው ነገር አባቱ ሉቃስ እናቱ ደግሞ ትእግስት እንደምትባል ብቻ ነው፡፡ስለ እነሱ ያለው የመጨረሻ ትዝታ ቤተሰቡ በአንድ ላይ ሆነው እየተጓዙ እያለ አባቱ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖት ሲጯጯሁ  ነበር፡፡አንድ አመት ሙሉ በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ተጣለ፡፡በዛን ተመሳሳይ ወቅት ቢኒያምም የአንድ አመት ህፃን ሆኖ በወላጇቹ ተጥሎ እዛ ማደጎ ቤት ከእሱ ጋር ነበር፣ እንደእድል ሆኖ አሳዳጊዎቻቸው ለሁለቱም ልባቸው ራራና አንድ ላይ ወደቤታቸው ወስደው እንደገዛ ልጇቻቸው ተንከባክበው አሳደጓቸው..እነሱም እርስ በርስ የሚዋደዱና የሚደጋገፉ ወንድማማቾች ሆነው አደጉ፡፡ አሳዳጊ ወላጆቻቸው ሁለቱንም በፍፁም ፍቅር እና  …በስርዓት አስተምረው ለዚህ ደረጃ አበቁዋቸው፡፡

ቀጥታ ጓደኖቾ ይጠብቋት ወደነበረው ካፌ ገባች፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ እየተጨዋወቱ እና እየሳቁ  ካሉት ከጓደኞቿ ጋር ተቀላቀለች፡፡

‹‹ደህና ናችሁ ፣ ውድ ጓደኞቼ››

እንዴት ነሽ ንግስቲቷ›› ሜሮን ነች ቀድማ ለሰላምታዋ መልስ  የሰጠቻት፡፡ከዛ ያሬድና ሌንሳ ተከተሉ፡፡እነዚህ ሶስቱ የልጅነት የትምህርት ቤት  ጓደኞቾ ናቸው፡፡ራሄል ልጅ ሆና  ፈጣን እና ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በዚህ ምክንያት ሁለት ክፍል በመዝለሏ ትምህርት ቤት ከገባችባቸው ልጆች ትንሿ ነበረች።   አንድ ቀን በክፍሏ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ልጃገረዶች በመጫወቻ ስፍራው ላይ ወደ  ጥግ ወስደው  ይሳለቁባት ጀመር። እንደአጋጣሚ ሶስቱ ጓደኛሞች በአካባቢው ሲያልፉ ሁኔታውን ተመለከቱ ..ዝም ብለው ሊያልፉ አልፈለጉም…ጣልቃ ገብተው  ራሄልን በክንፋቸው ስር ከልለው ታደጓት። ከዛን በኃላ ቋሚ ጓደኞቾ ሆኑ..ይሄው እስከዛሬ በህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ፣ የእርሷ ምስጢረኞች አማካሪዎች እና ውድ ጓደኞቿ ሆነዋል።እና  ከአራት አመት በፊት ሌንሳና ያሬድ የጓደኝነት ግንኙነታቸውን ወደፍቅር ቀይረው በመጋባት  መንታ ልጆችን ለመውለድ ችለዋል፡፡

ያሬድ  የራሄልን የተዘበራረቀ ሸሚዞን እና የተበታተነ ወረቀቷን ተመለከተና ‹‹ደህና ነሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹አዎ..ደህና ነኝ››

‹‹ቆይ ምን ሆንሽ?››ሜሮን ተቀበለችው፡፡

‹‹ከመኪናዬ ወርጄ ወደእዚህ ስመጣ ..፣ከአንድ ጓረምሳ ዶ/ር ጋር ተጋጨው ››

‹‹ምን…!ከጎረምሳ…?ወይስ ከዶክተር?››ሌንሳ ጠየቀቻት፡፡

‹‹ጓረምሳ የሆነ ዶ/ር ..ምነው ግልፅ አይለም እንዴ?››

‹‹እኔ ያልገባኝ..ጎረምሳ መሆኑን በእይታ አወቅሽ እንበል..ዶክተር መሆኑንስ?››ሜሮን ጠየቀች፡፡

‹‹ባክሽ የማውቀው ሰው ነው …የእህቴ የፀጋ  ዶክተር ነው፡፡››ሸሚዙ እንደተከፈተ፣ እና ፀጉሩ በግንባሩ ላይ ተደፍቶ  እንደነበረ  ላለማሰብ ታገለች።

ሁሉም በአንድ ላይ አስካኩባት፡፡

‹‹ስሙ ማን ነበር?››ሌንሳ በማሾፍ ጠየቀች፡፡

ራሄል ግን ጥያቄዋን በቁም ነገር ወስዳ‹‹ዓሊ››ስትል መለሰች፡፡

‹‹ኤሊ ማለት?››ያሬድ በገረሜታ ጠየቀ፡፡

‹‹ማለቴ ኤልያስ….ዶ/ር ኤልያስ››
ሌላ የህብረት ሳቅ ተከተለ፡፡

‹‹ተመልከቷት ነገሩ ስር የሰደደ ይመስላል ። የዔሊን ስም ሲነሳ  መልኳ በደቂቃ ተለወጠ›› ሜሮን  ጮኸች።

‹‹እንዴት ነው ግን…?››ለሊሴ ጠየቀቻት፡፡

‹‹ እሱ ቆንጆ ነው ማለት ይቻላል...›› ቡድኑን ዞር ብላ ተመለከተች እና በራሷ ሳቀች።‹‹እንደ ያሬድ ወንዳ ወንድ ነው›› ስትል አከለችበት፡፡
ሁሉም ሳቃቸውን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡
63👍3
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////

አለም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቷ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ  አያቷ የህግ ሙያ እንድታጠና አጥብቃ ትገፋፋት ነበር..በወቅቱ ምክንያቱ አይገባትም ነበር…እንዲሁ ሰዎች.. የልጅ ልጅሽ ጠበቃ ነች ወይም ዳኛ ነች እንዲሏት ካላት ምኞት ተነስታ የምትገፋፋት ይመስላት ነበር..አሁን ነው ነገሮችን ስታገጣጥም ምክንያቱ ፍንትው ብሎ የተገለፀላት፡፡

አለም በትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በመጨረሻ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልም ወርቅ ሜዳሊያ አጥልቃ ነበር የተመርቀችው። የህግ ትምህርት አያቷ የመረጠችለት እና በእሷ ዘንድ በልጅነቷ ያላገኘችውን ሞገስ ለማግኘት ስትል የገባችበት ሙያ ነበር፣ ግን ከተማረችው በኋላ አያቷን ደጋግማ አመሰግናታለች… ምክንያቱም በጣም የሳባት እና ያስደሰታት መስክ ነው። የማወቅ ጉጉት ያለው አእምሮዋ ወደ ውስጡ የህግ ዕውቀቷቹን መጦ ሲያስገባ በደስታ ነው፡፡ ወደስራም ስትሰማራ በሙሉ የራስ መተማመንና በከፍተኛ የስራ ንቃት ነበር፡፡

አቃቢ ህጉ የእጅ ሰዓቱን ተመለከተ.. ከዚያም ሲጋራውን በከንፈሮቹ መካከል አስገብቶ ቆመና ኮቱን ከመስቀያው አነሳ "ያለ በቂ ማስረጃ የግድያ ክስ እንደገና መክፈት አልችልም። ታውቂለሽ። ከሀያአምስት አመት በፊት ተፈፅሞ የነበረ ወንጀልን ወደኋላ ተጉዞ መረጃ ማሰባሰብ ብራንድ ልብሶችን ለብሶ በመዘነጥ የአዳም ዘርን እንደማማለል ቀላል ስራ አይደለም…..እና መጀመሪያ እኔን አሳምኚኝ..ምን አልባት ከዛ በኋላ ስለክሱ ሁኔታ መልሰን እንንጋገርበት ይሆናል››
ልቅ የሆነ ንግግሩን ችላ ብላ በብስጭት ተመለከተችው፡አጠያየቋ በጣም ድፋረት የታከለበትና እና ቅንነት የጎደለው መሆኑን ታውቃለች።እሷ በእሱ ቦታ ብትሆን ከረጂም ደቂቃ በፊት ክፍሉን ለቃ ትወጣ ነበር፡፡

"አየሽ አለም፣ ይህ የምትጠይቀኝ ጉዳይ እንደምትይው ቀላል አይደለም…እነዚህ ሰዎች በደቂቃ ውስጥ ይህንን ቢሮ ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ መቀየር የሚችሉ ናቸው። አንገቴን ልታስቀነጥሺኝ ካልፈለግሽ በስተቀር ይሄንን የአያትሽን ከንቱ ጥርጣሬ መልሰሽ ታነሺብኛለሽ ብዬ አልጠብቅም››ብሎ መንገዱን ቀጠለ፡፡ወደ ቢሮው ደጃፍ ሲያመራ ተከተለችው

"ክቡር አቃቢ ህግ ይሄ ለእኔ ጥልቅ ትርጉም ያለው ጉዳይ ነው። እንዴት እምቢ ትለኛለህ..የምታስበው ስለራስህ ብቻ ነው?።"

"እውነትሽን ነው እኔ እራስ ወዳድ ነኝ።
"ሲል መለሠላት።

"በሌሎች ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጌን እንዳለ ሆኖ ይህን ግድያ እንዳጣራ ፍቃድ ስጠኝ።"ሙጭጭ አለችበት፡፡

"እኛ ምን አይነት ውዝግብ እንዳለብን ታውቂያለሽ? መአት አንገብጋቢ ጉዳዮች እጃችን ላይ አሉ ፤ሀያ ምናምን አመት የተረሳ...መዝገብ እራሱ በአቧራ የተበላ ጉዳይን በቀላሉ ለፍርድ ማቅረብ አንችልም።"

"እሺ በትርፍ ሰዓቴ እሰራለሁ፣ ሌሎች ኃላፊነቶቼ ላይ በምንም አይነት ተፅዕኖ እንዲያሳድር እላደርግም፣ለዛ ቃል ገባልሀለው ።"

"አለም"

"እባክህ … ግርማ በቅርቡ አንድ ተጫባጭ ፍንጭ ከላገኘሁ ..ጉዳዩን እርግፍ አድርጌ ተወዋለሁ...ከዚያ በኋላ ስለ ጉዳዩ በጭራሽ ከእኔ አትሰማም.››

በትኩረት ተመለከታት እና ፊቷን አጠና ። "ለምን እንዲህ አይነት ውስብስብ ነገር ውስጥ ራስሽን ታስገቢያለሽ ..እንደማንኛውም ወጣት ዘመናዊ ሴት .ዘና ያለ የህይወት መንገድን አትመርጪም፡፡ ።"

ፊቷን አኮስታተረችበት ።

"እሺ፣ እሺ፣ ምርመራውን መጀመር ትችያለሽ፣ ነገር ግን በትርፍ ጊዜሽ ብቻ ነው። ተጨባጭ የሆነ ነገር ይዘሽ ነይ። አለበለዛ ውሳኔዬን ታውቂዎለሽ .አሁን ከቀጠሮዬ አዘግይተሽብኛል።››ብሎ በቆመችበት ጥሏት ሄደ፡፡

በእርካታ ተነፈሰች፡፡ሸክሟ ከባድ ነበር ፡፡ እያቷ በእናቷ ግድያ ላይ ያላት መረጃ የተወሰነ ነበር። በጋዜጣ ላይ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ እናቷን በመግደል የተወነጀለው ሰው የአእምሮ ብቻ ሳይሆን የመስማትም ችግር እንዳለበት ነው፡  ።እነሱ መሠረታዊ እና ቀላል ችግሮች ነበሩ. የአእምሮ ዝግመት ችግር የነበረው ሊቁ የተባለው ሰው በግድያው ቦታ በተያዘበት ጊዜ የሟቾ እናቷን ደም በጠቅላላ ልብሱ ላይ ተነክሮ እንደነበረ ተዘግቦ ነበር።በተጨማሪም በተያዘበት ወቅት ተጎጂዋን ገድሎበታል የተባለበትን የቀዶ ጥገና መሳሪያ በእጁ ይዞ ነበር።በዛ ምክንያት ወዲያው በቁጥጥር ስር ውሎ ታስሯል፣ ተጠየቋል
እና ተከሷል። በቀናት ውስጥ ነበር ችሎት የቀረበው። ወዲያው ዳኛው ካለበት የጤና እክል የተነሳ ለፍርድ የመቅረብ ብቃት እንደሌለው አውጀው በመንግስት የአእምሮ ሆስፒታል ውስጥ አንዲታሰር ትዕዛዝ አስተላለፉ።ተጠርጣሪው ግን ወደአእምሮ ሆስፒታል ተመዘዋወሮ ብዙም ሳይቆይ እራሱን አጠፋ ተባለ፡፡ በውቅቱ ወንጀለኛውን አሳዶ ለመያዝ
..ከዛም ፍርድ ለማስተላለፍና ፋይሉን ለመዝጋት የነበረው ጥድፊያ ያስደነግጣል፡፡ እናም ከፍተኛ ጥርጣሬም በአለም አእምሮ ውስጥ ጭሯል፡፡
በሶስተኛው ቀን ያገኘችውን ተጨማሪ መረጃ ይዛ ዋና አቃቢ ህጉ ፊት ለፊት ቀረበች፡፡መረጃዎቹን ካቀበለችው በኃላ

‹‹የእረፍት ቀን እንዴት ነበር?›››ስትል ለጫወታ መጀመሪያ ጠየቀችው፡፡

"ድንቅ ነበር. ካንቺ የበለጠ ውጤታማ ቀናቶችን አሳልፌለሁ ብዬ አስባለው። ብዙ ነገሮችን የማንበብ እድል ነበረኝ።"
ፋይሉን ገልጦ ይዘቱን መቃኘት ጀመረ። "እህም" የመጀመሪያ ንባቡ ትኩረቱን ለመሳብ በቂ ነበር። ወንበሩ ላይ ተደግፎ በጥንቃቄ በድጋሚ አነበበው።

"ይህ ዶ/ር ታደሰ የተባለው … ሊቁ የታሰረበት የነበረበት የአእምሮ ሆስፒታል ሐኪም ነው?"

‹‹አዎ ነው››

‹‹ታዲያ አግኝተሸ ማነጋገር አልቻልሺም?››

"አልቻልኩም እንዳለመታደል ሆኖ ከጥቂት ወራት በፊት ሞቷል." "አስደሳች ነው."
"አስደሳች?" አለም በንግግሩ ተበሳጨች። ወንበሯን ትታ ዞረች እና ከኋላው ቆመች
"ይሄ ታደሰ የተባለው ዶክተር ሊቁ የግድያ ወንጀል ለመፈፀም ብቃቱ እንዳለው ሙያዊ ውሳኔ ላይ ሲደርስ ለመጨረሻ ጊዜ የተከታተለው ሌላ የስነ አእምሮ ሃኪም ግን ሊቁ የተባለው ግለሰብ የአእምሮ በሽተኛ ቢሆንም ምንም አይነት ሰውን የማጥቃት ዝንባሌ አሳይቶ እንደማያውቅ በሪፖርቱ አስፍሯል.. ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት እንደሌለው እና
አመፀኝነትም ታይቶበት እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡ እና በዶክተሩ ሞያዊ አስተያየት መሠረት እሱ እኔን ዋጋ እንዳስከፈለኝ አይነት የግድያ ወንጀል መስራት እንደማይችል ነው ያረጋገጠው።ገደለ በተባለው ሰው ላይ ሁለቱ ባለሞያዎች የተለያ አይነት ምልከታ ነበራቸው…ይሄም ከመዝገቡ ጋር ተያይዞል..ዳኛው የባለሞያዎቹን ውሳኔ ሚዛናዊነት ለመጠበቅ የሶስተኛ ባለሞያ አስተያየት መጠየቅ ሲገባቸው ባልታወቀ ምክንያት የአንደኛውን አስተያየት ውድቅ አድርገው የሌለኛውን ተቀብለዋል፡፡በአጠቃላይ…ሊቁ የተባለው ሰው እናቴን አልገደላትም የሚል በጣም ጠንካራ እምነት አለኝ።›› አቃቢ ህጉ ሌሎች በርካታ አጭር መግለጫዎችን አነበበ፣ ከዚያም አጉተመተመ፡-

"በአጭር ቀናት ከዚህ የበለጠ ተአምራዊ የሆነ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አልችልም። ጉዳዩ ሃያ አምስት አመት ያስቆጠረ ነው። ተስፋ የማደርገው ይሄ ጉዳዩን በ ዳኞች ፊት ለማቅረብ በቂ ምክንያት ነው። በተጨማሪም የዓይን እማኝ የማግኘትም ትንሽም ቢሆን እድል አለኝ
።"
አቀቢ ህጉ‹‹አለም.››ሲል ተጣራ "አቤት"
44👍5