#ጫፍ_አልባ_ቁልቁለት
፡
፡
የያዙትን ይዞ ካልተጠላጠሉ
ወደ ላይ ካላሉ
ወ
ደ
ታ
ች
እ
ያ
ዩ
መውደቂያ ካሰሉ
ከውድቀት ዳርዳሩ ከተንደረደሩ
መውደቅ ከጀመሩ
ውድቀት ጫፍ የለውም
ሜዳዉ ቁልቁለት ነው ውድቀት ዳር የለውም
በውድቀት ላይ ውድቀት እየተያያዘ እየተዋዋለ
ከውድቀትም በታች ሌላ ውድቀት አለ።
፡
፡
የያዙትን ይዞ ካልተጠላጠሉ
ወደ ላይ ካላሉ
ወ
ደ
ታ
ች
እ
ያ
ዩ
መውደቂያ ካሰሉ
ከውድቀት ዳርዳሩ ከተንደረደሩ
መውደቅ ከጀመሩ
ውድቀት ጫፍ የለውም
ሜዳዉ ቁልቁለት ነው ውድቀት ዳር የለውም
በውድቀት ላይ ውድቀት እየተያያዘ እየተዋዋለ
ከውድቀትም በታች ሌላ ውድቀት አለ።
👍1
#ብሌን 🇪🇹
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#በዮርዳኖስ
ቤቱን የሞላውን ሁካታ ጩኸት ለማስቆም ሁለተኛው ጥይት ተተኮሰ ተኩሱን ተከትሎም ሁሉም ዝም አለ ቤቱን እንደገና ፀጥታ ወረሰው።
ፊትለ ፊታችን ከተጋደመው እሬሳ ትኩስ ደም እየተምዘገዘገ ወደስራችን ቁልቁል ይወርዳል።ግን ሁላችንም በፍራቻና በድንጋጤ ትንፋሻችን እንኳ እንዳይሰማ ሆኖ ዝም አልን ማንም አያለቅስም
መጮህ አይታሰብም ምክንያቱም በተነፈሰው ሁለት ቃል ምክንያት ወደ ሞት የተሸኘውን ሁሉም ስላየ ስቅስቅታ የለም የሚቆራረጡ ትንፋሾች እንጂ ተጨንቆ በተለይም ሰሚም ሆነ ደራሽ እንደሌለ አውቆ ተስፋ እንደመቁረጥ ፈርቶ መሽሽና ማምለጥ እንዳለመቻል ሞትን እያሰቡና ፊት ለፊት እየተጋፈጡት ማልቀስ እየፈለጉ አንዳለማልቀስ መጮህ እየፈለጉ አንዳለመጮህ ምንም ማለትና መደረግ እንዳለመቻል እሚያም ነገር የለም።
የሚከተለውን በማሰብ ማንም ደሙን ለመሸሽ ንቅንቅ አላለም።
ለመዳን መፀለይ ይኑርብኝ ንሰሀ መግባት አላወኩም ግን ሁለመናዬ ይንቀጠቀጣል ልብ ምቴ ለሁሉ እሚሰማ እስኪመስለኝ ድረስ በፍጥነት ይመታል ትንሽ ቆይቶ ግን መቆሙ እማይቀር ይመስላል እየሆነ ያለው እና የማየውን በህለሜ ይሁን በውን እንጃ ግን በህሌሜ ከሆነ ለምን አልባነንኩም ስል አሰብኩ በውኔ ከሆነ ደግሞስ እንዴት ተቋቋምኩት?
አጋቾቻችን አና ገዳያችን እርስ በእርሳቸው መነጋገርና መጯጯህ ጀመሩ።እኛ ብቻ ሳንሆን እነሱም መጠነኛ ድንጋጤ የደነገጡ ይመስላል።እኛን ትተው እርስ በእርስ ጭቅጭቅ ጀመሩ "ለምን?" የሚል ጥያቄና ቁጣም እያቀረቡበት ይመስላል። እሱም ሳይፈራ "እንኳን!"የሚል በሚመስል ልበሙሉነትና ቁጣ በጩኸት ይመልስላቸዋል።ከዚ በላይ ግን የሚሉትን ለመረዳት አልቻልኩም።
ድንገት ያለንባት በረት መሳይ ትንሽዬ ቤት በር ከፍተኛ ድምፅ አሰምቶ ተከፈተ።
እንደገና ጩኸት።
እኛን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ያስደነገጠ ክስተት ሆነ።
"አንዳትንቀሳቀስ...! እንዳትንቀሳቀስ ብያለው እንዳትበላሽ ዋ...!!"አለ ከውጭ የሚመጣ ድምፅ። ጠመንጃውን አስቀድሞ በቀስታ ወደ ውስጥ ዘልቆ ብቅ እንዳለ "ልጆች እዚ ምን እየተካሄደ ነው.."አሉ በዕድሜ ጠና ያሉት ሽማግሌ ሁሉንም በጥንቃቄ እያዮ።የመጀመሪያው አማረኛ ተናጋሪ ናቸው አይናቸው ውስጥም ክፋት ወይምን ጭካኔ አይታይም እንደውም ገፅታቸው ርህራሄ ይነበብበታል።ከሰማይ የመጣ አዳኝ መለዓክ ይሆን እንዴ..?አልያም አምላክ አዝኖ እኛን ለማስመለጥ የላከልን ታዳጊያችን ሰው ይሆኑ?! ብቻ ግን ውስጤ እንደገና በተስፋና ዳንኩ በምትል ትንሽ የደስታ መንፈስ ሲወራጭ ተሰማኝ።እኔን ብቻ ሳይሆን ሁሉም እንደዛ ያሰበ ይመስለኛል።
ግን ድንገት ከመካከላቸው አንድ ተነስቶ "እንዴ....ጋሽ ሽመልስ...! እርሶ ኖት እንዴ...?"አለ ለሰላምታ እቀፉን እያዘጋጀ።አማረኛው ጥርት ያለ ነው ግን እስካሁን አንዲትም የአማረኛ ቃል አልተነፈሰም ነበር።
"እህ...ሙሴ ጎረምሳው አንተም አለህ እንዴ...?ታድያ ምን አያደረጋችሁ ነው?"የፊት ገፅታቸውን ወደ ቁጣ ቀይረው ጠየቁት።
"ኧረ ሰላም ነው ምንም አይደል አጎቴ..."አለ
እንዳሰብነው ሳይሆን ቀረና ሔዶ ተጠመጠመበት ተቃቀፉ ያብቻ አይደለም ሌላ በእድሜ ተለቅ የሚለውና ዋናው አዛዥ የሚመስለውም ተነስቶ በክብር ሰላም አላቸው ና ማውራት ጀመሩ።ሁሉም የሚያውቋቸው ና የተከበሩ የአከባቢው ነዋሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሁኔታቸው መገመት ይቻላል። ግን ተወላጄ እንዳልሆኑ ግለፅ ነው።ባዩት ነገር እንደደነገጡና እንዳዘኑም የፊት ገፅታና አስተያየታቸው ያሳብቃል።በርግጥም ሊያድኑን ፈልገዋል ሆኖም ምንም ያህል ደግ ቢሆኑም አና ሀዘኔታ ቢኖራቸውም ግን እነሱን መቃወም ሆነ እንዲለቁን ማድረግ እንዳልቻሉ ግልፅ ሆኖልን ነበር። አይናቸው ላየ ሀዘኔታ ይነበባል ጥለው ለመሄድ አልፈለጉም። እሳቸውም የማይችሉት ነገር እንደሆነ ተረድተዋል ቢሆንም እርዳታን እሚማፀኑና የሚያለቅሱ አይኖች በተስፋ እሳቸው ከማየትና ከመጠበቅ አልቦዘኑም።
"አይ እንደዛ ከሆነማ እሺ እኔ ደሞ ምን ተፈጠረ ብዬ እኮ ነው።እንዲያ ከሆነማ..."ለአፍ ይበሉ እንጂ ከልባቸው አይደለም የሚናገሩት።
"አይ እርሶን አያሳስቦት ቀላል ነገር ነው ያው እንዳለኮት ነው አንጎዳቸውም ታውቁ የለ..."ይላል ከመጀመሪያው ተነስቶ ያቀፋቸው ሰው።
ፊታቸው ቅራኔን እንደተሞላ ደጋግመው አየተዟዛሩ ካዮን በበሗላ ለአራጆቻችን ጥለውን ወጡ።ግን ውስጤ ተስፋ አልቆረጠም ከሁኔታቸው አንዳየሁት ሰዎችን ይዘው ተመልሰው መተውም ቢሆን ከማዳን ወደ ሗላ እንደማይሉ እርግጠኛ ሆኜባቸው ነበር።
"ምንም ችግር አይፈጠርም..?"አለ አንደኛው ሰው
"የዚው አከባቢ ሰው ናቸው አሳልፈው አይሰጡንም"አለ አጎቴ ሲል የነበረው።
"አይ አይመስለኝም"አለ አዛዡ በአይን ምልክት አንዲከተሉት ትዕዛዝ እየሰጠ።
ወዲያው ሁለት ሰዎች በፍጥነት ተከታትለው ወጡ።
እንደገና ቋንቋቸውን ቀይረው መጨቃጨቅ ጀመሩ መጀመሪያውም ያልተስማሙት አጋቾች እንደገና በነዚ ሰው ምክንያት አለመግባባት የተፈጠረባቸው ይመስላል።ቋንቋውን በፍፁም ሰምቼው አላውቅም ምናልባት ብዙ እማይነገር የአንዱ ብሔር ቋንቋ ሊሆን ይችላል አልያም ደግሞ እዚው ለመግባቢያ የፈጠሩት ሌላ የኮድ ቋንቋ ሊሆን ይችላል።ሁለተኛውን የመሆን እድሉ ግን ሰፊ ይመስለኛል።
እኛ ታዳጊ መልክተኛችኝ አባት ምን ሆነው ይሆን...? አምልጠው ያድኑን ይሆን ወይስ እነሱም ተይዘው እዚው እኛው ጋር ይቀላቀሉ....? በሚል ሀሳብ ውስጥ እንደተዋጥኩ ቀጥሎ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመርኩ።
በግምት 3 ደቂቃ ያህል ይሆናል ምንም የለም እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የሚሆነውን በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቀ ይመስለኛል።ምክንያቱም ከነኚያ ሰው ጋር ተስፋችንን አብረን ልከናል የመሞትና የመዳን ዕድላችን በሳቸው የሚወሰን ሆኗል በሳቸው ምክንያት ተስፋ አልያም ሞት ይቀጥላል በቃ።
ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ። ቢያመልጡ እንጂ ቢያዙ መቼም ይሄ ሁሉ ደቂቃ አይቆዮም ብዬ ደመደምኩ። ምናልባት እስከ ነገ ቢፈጅባቸው ነው ከዛም መተው ያድኑናል ብዬ ሙሉ ለሙሉ ተስፋ አደረኩ ደስም ያለኝ መሰለኝ።አሁን እግዚአብሔርን የምለምነው እስከ ጠዋት በህይወት እንዲያቆየን ብቻ ነው ግን እስኪነጋ ማን ይሙት ማን ይትረፍ የምናውቀው ነገር የለም ምናልባት ሁላችንም በአንድ ሽጉት ቀላሀ ብቻ ልናልቅ እንችል ይሆናል አልያም ሁላችንንም አንተርፋለን።ወይም ምን ይታወቃል እዚሁ በጭድ በተሞላው ቤት ውስጥ እንዳለን ቤንዚን አርከፍክፈው ያነዱን ይሆናል
ብቻ ቀጥሎ የሚሆነውን ማንም መገመትም ሆነ ማወቅ አይችልም።
በቃ የሚመጣውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለም።
ግን አሁን ትንሽም ቢሆን ተስፋ አለን።
ከአስራዎቹ ደቂቃ ቡሓላ የሄዱት ሰዎች ኮቴና ድምፅ ተሰማን።ባዶዋቸውን እንደተመለሱም እርግጠኛ ሆንኩ።
ግን ሳይሆን ቀረና ያ ተስፋዬን አብሬ የላኩበት ሰው ተስፋዬን ጥሎብኝ አብሯቸው መቶ ነበር
"እህሳ ፈልገኸኝ ነበር? ከመንድ ሲያስመልሱኝ ጊዜኮ ችግር የተፈጠረ መስለኝ"አሉ ድንጋጤያቸውን ለመደበቅ እየጣሩ እንዳሉ በሚያሳብቅ ንግግር።
"አይ ችግር የለም እንደው አግረመንገዶን ከመጡ አይቀር ለምን አንድ ነገር አላሳይዎትምና አላማክሮትም ብዬ እኮ ነው"አለ ዋናቸው ሰው እጁን ትክሻቸው ላይ አስደግፎ ይዟቸው እየወጣ በድጋሜ በዛ ርህራሄ በሞላበት አይናቸው ቃኘት አድርገውን ነበር የወጡት ነገሩ ግራ አጋባኝ ቢሆንም ከኛ ጋር አለመቀላቀላቸውን ወይም መንገድ ላይ አለመገደላቸውን ተስፋ አድርጌ መጠበቅ እንደጀገመርኩ በዛው ቅስፈት ከወደውጪ ተኩስ ተሰማ ልቤ ከልባቸው እኩል አብሮ ምቱን ያቆመ መሰለኝ

ተስፋዬም አብሮ አከተመ።ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጼን አውጥቼ ተንሰቀስኩ ግን እሚሰማ አልመሰለኝም የምችለውን ያህል ጮህኬ አለቀስኩ ግን ድምፄ ሀይል አልነበረውም።ተከትሎኝ ሁሉም መንሰቅሰቅ ጀመረ። በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልቤ አምርሬ አለቀስኩ።በቃ በሕይወት ለመጨረሻ ጊዜ ተስፋ የቆረጥኩ መሰለኝ። ማንም ሆነ ምንም ነገር እንደዚ አስከፍቶኝ አያውቅም ግን ይሄ ከመከፋትም ያልፋል።ጩኸቴም ለቅሶዬም ወደ ውስጥ እንጂ ወደ ውጭ አልሰማልሽ አለኝ።ሰሚ የሌለው ዋይታ ሆነ ባነባው እማያልቅ እማይወጣ ህመም።
ከእንቅልፌ ስነቃ በእንባ ርሼ ነበር።ብድግ ብዬ ተነሳው ገና ሌሊት ነው በተለመደው ሰዓት ነበር የነቃሁት።አልጋዬ ላይ ቁጭ አንዳልኩ እጅና እግሬን አጣምሬ አንገቴን ቀብሬ ማልቀስ ጀመርኩ።ምክንያቱም ዛሬም እዛው ስሜት ውስጥ ነኝ።እስኪ ወጣልኝ አነባው ተነሰቀሰኩ።አሁንም እንደታመምኩ ነኝ ሊያውም ሰው የማያወቀውንና ፍፁም ሊረዳው እማይችለውን ህመም።
ለደቂቃዎች ካነባው ቡሗላ ተነስቼ ደብተርና ወረቀቴን እንደለመድኩት ይዤ ቁጭ አልኩ።
"የነፃነትን ዋጋ የምንረዳው ባጣናት ቅስፈት ብቻ ነው ማንም ሰው ግን ያቺን ቅስበት እስካላየ ድረስ የነፃነት ሙሉ ዋጋ ና የነፃነት ጥጉን መቼም ሊረዳው ሆነ ሊያጣጥመው አይችልም ግን ያቺን ቅስበት ያየ የነፃነት ዋጋዋ እና ውድነቷን ከማንም በላይ ይረዳዋል እና ለመጀመሪያ ጊዜ ይናፍቃታል ሊያገኛትም ሩቅ እኝደሆነ ይሰማዋል ነብሱም ድምጿን ከፍ አድርጋ ነፃነትን ትጣራለች ግን ሰሚ አታገኝም እናም ይህ ሰው እድለኛ ከሆነ ዳግም ነፃነትን አግኝቶ ዋጋዋን ተረድቶ ያጣጥማታል።ያንን ያላየው ግን እንዲያው ትርጉሟ ሳይገባው ይመላለስባታል።ይሔ ሰው ታድያ ነፃነትን ስላጡ ሰዎች ምንም ላይመስለው ይችላል ይሆናል ግን ያቺን ቅስፈትና የነፃነት ዋጋን የተረዳው ግን ግድ ይለዋል ልክ እንደኔ! ለዛም ነው ዝም የማልልው "
ለመጀመሪያ ጊዜ መፃፍ የቻልኩት ይሄንን ብቻ ነው።
፡
፡
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየታችሁ እንዲሁም ማስተካከል ያሐባት ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት።
ፈጣሪ ሁሉንም በያሉበት ይጠብቅልን እናም በሰላም ያገናኘን ።
"ሕመማቹ ህመማችን ነው!!!!"

#አድዋ
የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፤
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣
እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ…
የድል ታሪክሽን አውሪ።
#እጅጋየሁ_ሽባባው
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፤
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣
እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ…
የድል ታሪክሽን አውሪ።
#እጅጋየሁ_ሽባባው
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#ሙግት_ወይስ_እውነት?
፡
፡
በፍላጎት መንገድ...
በምኞት ጎዳና ፣ ስመጣ ተጉዤ
ገንዘብ እየፈለግሁ...
"ፍቅር ይበልጣል" የሚል ፣ ከንቱ ሙግት ይዤ
እኔም ልክ እንዳንቺ...
ከገንዘብ ወዳጅ ጋር ፣ ተከራክሪያለሁ
ገንዘብ የማይገዛው...
ብዙ ደስታ አለ ፣ ስል አስረድቻለሁ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ግን ደሞ ግን ደሞ...
በማስረዳቴ ውስጥ ፣ አለ የሚያስረዳኝ
ከፍቅር ከገንዘብ...
ከምንም የሚበልጥ ፣ "እውነት " ይሉት አዳኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡
እናም እውነት ማለት...
በጭራሽ አይደለም!
አንድድ እውነት ለማቆም ፣ አንዱን እውነት መጣል
አትጠራጠሪ!!!
አንዱ ገንዘብ ሲመርጥ ፣ አንዱ ፍቅር ይመርጣልተ
ሒጅ ወደ ፈለግሽው!!!
ከፍቅር ከገንዘብ ፣ ፍላጎት ይበልጣል፡፡
⚫️በላይ በቀለ ወያ⚫️
፡
፡
በፍላጎት መንገድ...
በምኞት ጎዳና ፣ ስመጣ ተጉዤ
ገንዘብ እየፈለግሁ...
"ፍቅር ይበልጣል" የሚል ፣ ከንቱ ሙግት ይዤ
እኔም ልክ እንዳንቺ...
ከገንዘብ ወዳጅ ጋር ፣ ተከራክሪያለሁ
ገንዘብ የማይገዛው...
ብዙ ደስታ አለ ፣ ስል አስረድቻለሁ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ግን ደሞ ግን ደሞ...
በማስረዳቴ ውስጥ ፣ አለ የሚያስረዳኝ
ከፍቅር ከገንዘብ...
ከምንም የሚበልጥ ፣ "እውነት " ይሉት አዳኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡
እናም እውነት ማለት...
በጭራሽ አይደለም!
አንድድ እውነት ለማቆም ፣ አንዱን እውነት መጣል
አትጠራጠሪ!!!
አንዱ ገንዘብ ሲመርጥ ፣ አንዱ ፍቅር ይመርጣልተ
ሒጅ ወደ ፈለግሽው!!!
ከፍቅር ከገንዘብ ፣ ፍላጎት ይበልጣል፡፡
⚫️በላይ በቀለ ወያ⚫️
#ፍቅርና_በቀል
፡
፡
#ክፍል_አንድ
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
‹እሱ….እሷ…እሳቸው›
"ኪስህ በብር ተሞልቶ ካዝናህ በወርቅ ቢታጨቅም ..ከልብህ ፍቅር ከነጠፈ አንተ በጣም ሊታዘንልህ የሚገባ ደስታ የራበህ ደሀ ሰው ነህ ፡፡"
#እሱ…
እሱ ኃይሌ ይባላል…የአርባ አመት ጎልማሳ ነው፡፡እዚሁ አዲስ
አበባ ተክላኃይማኖት መሀል ላይ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ ባለቤት ነው፡፡ከህንጻው ኪራይ ብቻ በወር ከሁለት መቶ ሺ ብር በላይ
ገቢ ያገኛል…በዛ ላይ የፎቁ የመጀመሪያው ግራውንድ ፍሎር
ላይ የሚገኘው ሆቴል የእሱ ነው፡፡እራሱ የሚሰራበት
መኖሪያ ቤቱ ሳር ቤት ብስረተ ገብርኤል አካባቢ ሲሆን ቤተመንግስት መሳይ የተንጣለለ ቢላ ነው፡፡ግን እዛ ግቢ
ውስጥ …ሚስት የለችም…እዛ ግቢ ውስጥ ልጆች
አይሯሯጡበትም….እዛ ግቢ ውስጥ ዘመድ አዝማድ ዝር
አይልበትም…..ከአንድ ሽማግሌ ዘበኛ እና ከአንድ የ65 ዓመት
አሮጊት የቤት ሰራተኛ በስተቀር …ከመኖሪያ ቤትነት ይልቅ
የገዳምነት ድባብ ያረበበበት ነው፡፡
ኃይሌ እንዲህ የሞላው ሀብታም ሆኖ …ሁሉ ነገር
የተትረፈረፈለት ሰው ሆኖ ለምን አላገባም ?ይሄ ጥያቄ
በቀላሉ የሚመለስ አይደለም :ለጊዜው ይሄን ጥያቄ
እናቆየው….::ኃይሌ ማግባቱን እሺ አያግባ ለምን እንደዚህ
ብቸኛና ዝምተኛ ሰው ሆነ…?ለምን እንደዚህ ውስጡን ደስታ
የራቀው …ጥርሱን እንደዚህ ሳቅ የናፈቀው ሆነ….? ፡፡ምን
አልባት አንድ ጉድለት ይኖርበት ይሆናል ብላችሁ ገምታችሁ
ይሆናል…የጤና ችግር::ፈጽሞ አታስቡ… የሀኪም ቤትን
ደጃፍ ከረገጠ ከስንት አመት በፊት እንደነበር እሱም
አያስታውስም…::
መልከ ጥፉ ስለሆነ…? ፍጽም አይደለም::…እስኪ ስለኃይሌ
አካላዊ ቁመና በመጠኑ ላውራችሁ..ቁመቱ ሜትር ከሰማንያ
ሁለት ነው፡፡ክብዳቱ ሰባ ዘጠኝ፡፡ አፍንጫው ስገግ ያለ….ክብ
የፊት ቅርጽ ያለው..ጥቁር ሉጫ ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ድፍት
ያለ…ፂሙ ከፀጉሩ አንስቶ አገጩ ላይ ተንዠርግጎ ፈላስፋ
ያስመሰለው… ቀይ ሞዴል መሳይ ሰው ነው፡፡ሲራመድ
በቄንጥ እና በእርጋታ ስለሆነ ዘወትር እየቀያየረ
ከሚለብሳቸው ውድ ሱፍ ልብሶች ጋር ግርማ ሞገሱ
የሚያስፈዝ አይነት ነው፡፡በቃ ማንም ሴት የእኔ በሆነ ብላ
የምትመኘው አይነት ሁሉን አሞልቶ የሰጠው የሚባል አይነት
ወንድ….፡፡ግን እሱ ብቻ ነው የጎደለውን የሚያውቀው….እሱ
ብቻ ነው ከአገኘው ነገር ይልቅ የተነጠቀው እንደሚበልጥ
የተረዳው……አዎ ይህቺ አለም ለእሱ ሳቅ ሳይሆን ለቅሶ ነው
የሸለመችው…፡፡ ፍቅርን ሳይሆን በጥላቻ እሳት መለብለብን…
በበቀል በትር መወገርን ነው የሸለመችው……..
#እሷ……
ሩት የሰላሳ ሁለት አመት ሴት ነች…ጠይም ድንቡሽብሽ ያለ
ፊት በደም ግባት የወረዛ ስዕል መሳይ ባይባልም ማራኪ
መልክ የታደለች ከቁመቷ መዘዝ ፤ከወደ ወገቧ ቀጠን፤ ከወደ
መቀመጫዋ ትንሽ ሰፋ ያለች..እግሮቾ ለብቻቸው ውበትን
የሚዘምሩ ቄንጠኛ ወጣት ነች፡፡
ሩት ቀን እቤቷ ተኝታ ታረፍዳለች፡፡ከሰዓት ለባብሳና ዘንጣ
ትወጣለች….ከዛ ወደ ተክለኃይማኖት ታመራለች…ሆቴል
ትገባለች …ወንበር ይዛ ቁጭ ትላለች፡፡ የፈለገችውን
ታዛለች…እሲኪመሽ እዛው ትቀመጣለች..፡፡በዛ ቆይታዋ…
አምስት እና ስድስት ቢራ ልትጠጣ ትችላለች፡፡ወይም ሁለት
ጠርሙስ ወይን ልትጠጣ ትችላለች…ከፈለገች ደግሞ ሶስት
ጠርሙስ ሚርንዳ እያረፈች ልትጠጣ ትችላለች… ይሄንን
ማድረግ ከጀመረች አንድ ሳምንቷ አይደለም ..አንድ ወሯም
እንዳይመስላችሁ …ያለፉንትን አራት አመታት ተኩል
ያለማቆረጥ እንዲህ አድርጋለች..፡፡
ደግሞ ዘወትር የምትቀመጠው አንድ አይነት ቦታ ነው…የእሷ
መቀመጫ ላይ ማንንም አይቀመጥበትም….፡፡ ሁሌ ሪዘርቭድ
ነው፡፡ለእሷ ብቻ የተፈቀደ ማንም የማይደፍረው መንበር፡፡
ከዛ ሲመሽ ሰክራ እየተወላገደች ወደቤቷ ትገባለች ..አይ
እንደዛማ አታደርግም እሷና ስካር እንዲህ በቀላሉ
አይደፋፈሩም…ሁለት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ከመቀመጫዋ
ተነስታ ትቆማለች፡፡ቦርሳዋን ይዛ በሆቴሉ የጀርባ በር አልፋ
ትወጣለች…፡፡ከዛ አንድ ክፍል ትገባለች፡፡የለበሰችውን ረጅም
ቀሚስ ወይም ጅንስ ሱር በብጣቂ ጉርድ ቀሚስ ትቀይርና
ከንፈሯን ሊፕስቲክ.. አይኖቾን ኩል ትቀባባና ወደ ሆቴሉ
ትመለሳለች፡፡ ስትጠጣ የዋለችበትን ትከፍላለች ወይም
አትከፍልም..እንዳሰኛት ነው፡፡…ከዛ ሆቴሉን ለቃ ትወጥና
እዛው የሆቴሉ መውጫ በራፍ ጋር ካለ የመብራት ፖል ጋር
ተደግፋ ትቆማለች…..፡፡ወንድ ጥበቃ…፡፡የሰከረ እግረኛ
መጥቶ ያነጋራታል…የቀነዘረበት ባለ አሽከርካሪ አቁሞ
ያዋራታል….፡፡
ሩት የፈለገ ቢከፈላት አምስት ሰዓት ሳያልፍ ከዛች ሆቴል
በራፍ ንቅንቅ አትልም…፡፡አሷን የሚፈልጉ ቋሚ ደንበኞቾ
ይሄንን ስለሚያውቁ ሆቴል ገብተው እየጠጡ የእሷ ሰዓት
እስኪደርስ ጠብቀው ነው ሊያነጋግሯት የሚወጡት…፡፡
ለምን እንዲህ እንደምታደርግ ብዙ ሰው ግራ ይገባው ይሆናል
…እሷ ግን በቂ ምክንያት አላት…ወይም አለኝ ብላ ታምናለች፡፡
እንዲህ ስታደርግ ሆቴሉ በረንዳ ላይ ጥጉን ይዞ በመቆዘም
የሚመለከታት አንድ ሰው አለ…..ውስኪውን
እያንቆረቆረ..ሮዝማኑን እያቦነነ….ፀጉሩን በጣቶቹ
እያፍተለተለ፡፡የእሷ ድርጊት የዘወትር እና የማያቋርጥ እንደሆነ
ሁሉ የሰውዬው በረንዳ ላይ በአጭሩ የግንብ ከለላ ተሸሽጎ
እሷኑ እያጮለቀ ማየት የማያቆርጥ ተግባሩ ነው፡፡
ስትደራደር ..ስትሰዳደብ ይታዘባታል.፣አይ መታዘብ እንኳን
አይታዘባትም ግን በውስጡ ቁስል ጥዝጣዜ ይሰቃያል፡፡
አንዳንዴም ባለ መኪኖች መኪናቸውን ጭለማውን አሲዘው
ሲጠሯት እየተውረገረገች ስትሄድ… የመኪናውን በራፍ ከፍታ
ወደ ውስጥ ስትገባ…መኪናዋ ስትርገፈገፍ …ይሄ ሰውዬ
እዛው በረንዳ ላይ ኩርምት ብሎ እንባውን እያንጠባጠበ
..የሲጋራውን ጭስ እያትጎለጎለ ይመለከታታል….
ሰዓቷ ሲደርስ ከመረጠችው ጋር ትሄዳለች…አዎ በሳምንት
ሶስት ወይም አራት ቀን እንደዛ ታደርጋለች….ሌላውን ቀን
ደግሞ….ልደታ ወደሚገኘው ቤቷ ታመራለች፡፡ቤቷ ስላችሁ
ወደ ተከራየችው ቤት አይምሰላችሁ…ወደ ገዛ ቤቷ ነው፡፡
እሰኪ ስለ ቤቷ ትንሽ ላውራችሁ፡፡ምትኖረው ስድስት ክፍል
ያለውና ሁሉ ነገሩ የተሞለለት የድሮ ስሪት ቢላ ቤት ውስጥ
ነው ፡፡ብቻዋን ነው የምትኖረው…..ግቢዋ 1500 ካሬ ሜትር
ስፋት ሲኖረው ውስጡ 15 ክፍል ሚከራይ ቤት አለው…
ፔንሲዬን ነው፡፡ፔንሲዬን በቅርብ የተገነባ ነው ፡፡ቢያንስ በቀን
ከሁለት ሺ ብር በላይ ገቢ ያስገባላታል፡፡ይሄ ሁኔታውን
ይበልጥ አስገራሚና ግራ አጋቢ ያደርገዋል፡፡አንዳንዴም ታዲያ
ከወንዶቹ ጋርም ሆነ ወደ ቤቷ መሄድ ያስጠላታል…::እና
እንዳዛ ዘንጣ…እንደዛ የሚያጓጓ የተገላለጠ ሰውነት ይዛ
እዛው ሆቴል አጥር ስር ቁጭ ትላለች….፡፡እንዲህ
ምታደርገው ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ወይም ሰባት ሰዓት ላይ
ነው፡፡
ከዛም ሸርተት ብላ ኩርምትምት ብላ ትተኛለች፡፡ያ በረንዳ
ቁጭ ብሎ የሚከታተላት ወንድ ኮንፎርት ብርድልብስ አምጥቶ
ያለብሳታል..ትራስ አምጥቶ ጭንቅላቷን ቀና በማድረግ
አመቻችቶ ትራሱ ላይ ያስተኛታል….ከዛም ከጎኗ ኩርምት ብሎ
ቁጭ ይላል….፡፡እሱ ልብስ አያስፈልገውም..እሱ እንቅልፍ
አያምረውም …ሲጠብቃት ያድራል….፡፡
ድርዬ መጥቶ እንዳይደፍራት አይደለም…ሌባም
እንዳይዘርፋት አይደለም... በቃ ትንፋሿን ለማዳመጥ ..በቃ
ከአጠገቧ ብቻ ለመሆን..፡፡እንጂማ አይደለም የእሷን
የእሱንም ደህንነት ከማንኛውም ጥቃት የሚጠብቁ ሁለት
ጋርዶች ከእነሱ በስድስት ሜትር ርቀት ላይ በተጠንቀቅ
ቆመው በንቃት ፈጠው ያድራሉ…ይሄ ሁሌ እሷ እዛ ውጭ
በረንዳ ላይ መተኛት በፈለገች ቀን የሚታይ ትዕይንት ነው፡፡
ከዛ ሲነጋጋ እና ወፎች መንጫጫት
ሲጀምሩ ሩት

👍2❤1
ከእንቅልፏ
ትባንናለች…..ትንጠራራለች
ቀስ ብላ ዓይኖቾን ትገልጥና
አካባቢውና ትቃኛለች…፡፡ያለበሳትን ብርድልብስ ከላዮ ላይ
ትገፍና ትጥላለች..ከዛ ትቆምና ቀሚሷ ላይ ያለውን አቧራ
ለማራገፍ ትሞክራለች..ኩርምት ብሎ ከጎኗ የተቀመጠውን
ሰው ለሰከንድ አፍጥጣ ታየዋለች..ከዛ ፈገግ ትልና ቦርሳዋን
አንጠልጥላ መንገዷን ትቀጥላለች..፡፡ወደቤቷ..፡፡ ..ልብሷን
ልትቀይር…የተሸለ እንቅልፍ ልትተኛ…፡፡
ወንድዪውም የእሷን ከአካባቢው መራቅ አረጋግጦ
ከበረንዳው ተነስቶ ይቆማል..የደነዘዙ እግሮቹን
ያፍታታል..ወደ ሆቴሉ ጓሮ ይሄድና ያቆማት መኪና ውስጥ
ገብቶ ሞተሩን ያስነሳል …..ሞተሩ እስኪሞቅለት በድካም
የዛለ ጭንቅላቱን መሪው ላይ አስደግፎ ትንሽ ያሸልባል…
ከዛም ይባንናል …መኪናዋን ያንቀሳቅሳል ፡፡የሆቴሉን ግቢ ለቆ
ወደ መኖሪያ ቤቱ….ሊተኛ..
እኚ ናቸው ሁለት ፍቅር እና በቀል ያጣበቃቸው ሚስኪን
ነፍሶች…እሷ ና እሱ….ሩት እና ኃይሌ……
#እሷቸው…..
እሷቸው በሁለቱ መሀከል ያሉ ብቸኛው ድልድይ ናቸው፡፡
የማንኛቸው ትክክለኛ አጎት እንደሆኑ ባላውቅም ሁለቱም
በፍቅር አጎቴ እያሉ ነው የሚጠሮቸው፡፡
እኚ አዛውንት ከ8 ዓመት በፊት አውቃቸዋለው፡፡አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ሁለት ኮርስ
አስተምረውኛል፡፡ፕሮፌሰር አብረሀም ይመር ይባላሉ፡፡
….የራሳቸው የማስተማር ጥበብ የሚከተሉ በጥልቅ ዕውቀት
እና በራሳቸው ፍልስፍናዊ መርህ የሚመሩ ሙሉ ምሁር
ነበሩ፡፡እርግጥ አሁን ጡረታ ወጥተዋል፡፡ ሚገርመው ግን
እኚን አዛውንት መምህሬ ስለሆኑ ብቻ አይደለም
የማውቃቸው፡፡ ከንባብ ጋር ቁርኝት ያለው አብዛኛው
ኢትዬጵያዊ ቢያንስ በስም ያውቃቸዋል፡፡
በጻፎቸው በቁጥር ከ8 በላይ በሚሆኑ የፍልስፍና እና የልብ-
ወለድ መጻሀፎች አንቱታን ያተረፉ ጉምቱ ደራሲ ናቸው፡፡
እንደውም ዝም ብዬ ስለ እሳቸው ሳስብ ከዕድሜ መግፋት
በላይ ዕውቀት እና ንባብ ተጋግዘው ያጎበጣቸው
ይመስለኛል፡፡ ለማንኛውም ከእኚ እጅግ ከማደንቃቸው ምሁር
ጋር ህይወት አዙራ ለሁለተኛ ጊዜ አገጣጥማናለች፡፡
ባልታሰበ ሁኔታ የሩት እና የኃይሌ አጎት የሆኑት ፕሮፌሰር
የእዚህ ታሪክ ድር ናቸው..አንድን ከአንዱ የሚያስተሳስሩ .. ፡፡
እኚ ፕሮፌሰር ብዙውን ጊዜ ፂማቸውን አንዠርግገው
ትከሸሻቸውን አጉብጠው ቦርሳቸውን የሚንቀጠቀጠው
ትከሻቸው ላይ አንጠልጥለው በተጎተተ አርምጃ ወደ ትሁት
ሆቴል ይመጣሉ..ሩት ጎን ይቀመጣሉ…እዛ ሆቴል ውስጥ
ከእሷ ጎን ለመቀመጥ ሚፈቀድላችው ብቸኛው ሰው እሳቸው
ብቻ ናቸው፡፡..ከጎኗ ይቀመጡና አሷ የምትጠጣውን
ይጠጣሉ ፡፡ ከቦርሳቸው ውስጥ አንድ መጻሀፍ ያወጡና
ያነባሉ፡፡ እያነበቡም ይጠጣሉ…..ቆይተው ከመጠጡም
ከንባቡም እረፍት ይወስዱና ከእሷ ጋር ማውራት ይጀምራሉ፡፡
ሲያወሯት በፍቀር እና በስስት ነው፡፡እሷም መፍለቅለቅ
ምትጀምረው እሳቸው ሲያወሯት ብቻ ነው፡፡ ምትረጋጋው
አጠጋቧ ሲቀመጡ ብቻ ነው፡፡ሚገርም ቁርኝት ነው ያላቸው፡፡
በፊት በፊት እንደውም አባቷ ይመስሉኝ ነበር፡፡ቆይቼ ነው
አንዳልሆኑ ያወቅኩት፡፡እኚ ፕሮፌሰር ከሩት ጋር ያላቸውን
አይነት ተመሳሳይ ቁርኝት ከኃይሌ ጋርም አላቸው፡፡እሷን
በሚያዩበት ዓይናቸው ነው እሱንም የሚያዩት… እሷን
በሚዳስሱበት ፍቅራዊ መንገድ ነው እሱንም የሚዳስሱት፡፡
ለዚህ ነው ይሄ ትረካ በዋናነት የእነዚህ ሶስት ሰዎች ነው
የምላችሁ፡፡አንዱ በአንድ ህይወት ውስጥ ስር ሰዶ በቅሏል
አንዱ በሌላው ህይወት ውስጥ ተዘረጋግቶ ተኝቷል፡፡
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

#የሴት_ክብር_በአፍሪካ
፧
ሴት ስትንኳሰስ
ሴት ስትዋረድ ~ ሴት ስትደፈር፣
በምትኖርባት
አፍሪካ በሚሏት ~ አህጉር፣
የሴቶችን ክብር
በፍትህ ዓይን ~ መዝና ስትሰፍር፣
አመት ሴትን ረስታ
አንዱን ቀን መርጣ ትኖራለች ማርች8ን ስታከብር።
፡
አይ አፍሪካ!!!!
፧
ሴት ስትንኳሰስ
ሴት ስትዋረድ ~ ሴት ስትደፈር፣
በምትኖርባት
አፍሪካ በሚሏት ~ አህጉር፣
የሴቶችን ክብር
በፍትህ ዓይን ~ መዝና ስትሰፍር፣
አመት ሴትን ረስታ
አንዱን ቀን መርጣ ትኖራለች ማርች8ን ስታከብር።
፡
አይ አፍሪካ!!!!
#ብሌን 🇪🇹
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በዮርዳኖስ
ቀሪውን ሰዓት መተኛት እማይታሰብ ስለሆነ እንዲሁ ክፍሌ ውስጥ ስንጎራደድ አነጋው።
ከአባቴ ቀድማ የምትነሳው ቡርቴ ስለሆነች እሷ እስክትነቃ ነው የምጠብቀው።
አባቴ ትናንት ስላደረግነው ነገርም ሆነ ስለሄድኩበት እና ስላደረኩት ነገር አንዳያውቅ ስለተነጋገርን እኔም ሆንኩ ቡርቴም አልነገርነውም።
ከወደ ውጭ ድምፅ ስለሰማው በሬን በቀስታ ከፍቼ ወጣው።እንዳሰብኩትም ቡርቴ ተነስታ ኩሽና ውስጥ ነበረች።
"ምነው በጠዋት?"አለች። እንዳየችኝ ምጣድ ልታሰማ እንደሆነ ያስታውቃል።
"ዝም ብዬ ነው አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ስለፈለኩ ነው"አልኳት
"አንቺ ልጅ ብቻ እንደትናንትናው ልታረጊኝ አንዳይሆን...!"
"አይ እሱን እንዳልተፈጠረ አርገሽ እርሺው የትናንትና ውሎዬን አልረሳሁትም የነገርሽኝንም እንደዛው ግን ሌላ ጥያቄ ነው"
"እውነት በይ ከምርሽን ነው እየተሻለሽ ነው ማለት ነው የኔ ቆንጆ ጠይቂኝ ምንድነው...?"አለች ሰፍ ብላ
"እ....ብ..ሌ..ንስ...?"ሌሊቱ እስኪነጋ ያስቸኮለኝን ጥያቄ ነገርኳት።ፊቷ በቅስፈት ልውጥውጥ ሲል አስተዋልኩ።
"አሁን የትናንት ውሎዬን አስታውሳለው ብለሽ ነበር እኮ በቃ እስከዚ ነው ምታስታውሺው?"
ማለት? አልኩኝ በውስጤ
ቀጥላ "ትናንት እኮ ነግሬሽ ነበር?"አለች
"እና ምን?"ጠየኳት
በረጅሙ ተንፍሳ"ሔዊ ብሌን እዚ የለችም ያው ት/ት እንደሔደች ነው ግኝ እባክሽ መልሰሽ ይሄን ጥያቄ እንዳጠይቂኝ"አለች።ልክ ያልሆነነገር እንዳለ አነጋገሯና ገፅታዋ ሳይደብቁ ይነግሩኛል በተፈጥሮዋ ምንም መደበቅ አትችልም።ቢሆንም በአሁን ሰዓት ማፋጠጡ ሞኝነት መስሎ ስለታየኝ ብዙ አልተከራከርኳትም ምክንያቱም በቀላሉ ማወቅ የምፈልገውን ሁሉ እንድትነግረኝ ለማድረግ ሌላ ዘዴ መጠቀም አለብኝ ካልሆነ ግን ለአባቴ ተናግራ ልታስቆመኝም ትችላለች ምክንያቱም ከአባቴ ትዕዛዝ እንደደረሳት ግልፅ ነው።እንዳለችው ዶክተሩ ባለው ምክንያት ይሆን ወይም በሌላ ባላወኩት አንድ ምክንያት ብቻ ከብዙ ነገር እንድከለከል ተደርጓል።ስለዚ አባቴ ሳያውቅ እሷ እንድትረዳኝ በጥንቃቄ መያዝ እንዳለብኝ ገባኝ።
ግን ስለ ብሌን ውስጤን ሰላም አይሰማውም ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘንበትን ወይም ያወራነውን ባላስታውስም ግን ውስጤ ያውከኛል።ምናልባት ከነሙሉ ማንነቷም አላስታውሳትም ይሆናል።ግን አይምሮዬን ሞልታዋለች።አለ አይደል አንዳንዴ እንዴትና ምን እንደጎደለን ሳናውቅ ጎዶሎነት ወይም የማጣት ስሜት ወይም ባላወቅነው ምክንያት ውስጣችን ሲከፋ እና ሲያዝን የሚሰማን አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ።በትክክል ባይገባኝም ግን ካላንዳች ምክንያት ውስጤ ይሄንን አያሰማኝም።
የምትማርበትን ብቻ ልጠይቃት አሰብኩ ቢሆንም ትንሽ ማረሳሳት ስለነበረብኝ ቁርስ በልተን አባቴ ስራ እስክሄድ ጠበኩ።
"ቡርቴ እባክሽ አንዴ ብቻ አንድ ነገር ልጠይቅሽ ደግሜ አልጠይቅሽም..."አልኳት በልምምጥ እያየኋት
"እሺ...ምንድነው? "አለች በረጅሙ ተንፍሳ
"የምትማርበትን ንገሪኝ እና ስልክ...."አላስጨረሰችኝም
"ውይይ ሔዊ ...ለማንኛውም ነይ ተከተይኝ "ተነስታ ከሳሎኑ እየወጣች።እኔም ተከትያት ወጣው "ይመስለኛል አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ አንቺን ይረዳሻል ብዬ በማሰብ እንጂ ጋሼ ቢያውቅ የሚፈቅድ አይመስለኝም ግን ደም መጥፎ ነገር አይመስለኝም"አለች ወደ አንዱ ክፍል ይዛኝ እየገባች።ምን ልታደርግ እንደሆነ ለማወቅ ጓጓው።
"ምን መሰለሽ አሁን እንደተረዳሁት ነገሮችን በጥልቀት ለማስታወስ ነው የቸገረሽ እንጂ ምንም አልረሳሽም ስለዚ ለምን የቀድሞ ማስታወሻ እና ደብተሮችሽ አታይም በጣም መፃፍ ትወጂ ስለነበር ብዙ ነገሮችን በተለይም ለየት ያለ ነገር ስታይ በትኩረት ስለዛ ነገር ትፅፊና በጥልቀት ስለዛ ነገር ለማወቅ ትጥሪና ትጠይቂ ነበር አው ትዝ ይለኛል የኔና የናቴን ታሪክም ትጠይቂኝና ትፅፊ ነበር ምን ላይ አድርሰሽ እንደተውሺው ባላውቅም ስለዚ እርግጠኛ ነኝ ስለብዙ ነገሮች ፅፈሻል።"አለች አንድ ተለቅ ያለ በደብተርና መፅሀፍ የተሞላ ካርቶን እያቃበለችኝ።
ያለችን እስታወስኩ ልክ ነች ብዙ ጊዜ በነገሮቸ እሳባለው በነዛ ነገሮችም መደነቅ በጣም እወዳለው እና የሳበኝን ነገር እስከመጨረሻው ማወቅና መመራመር ተፈጥሮዬ ነው ደሞም ፀሀፊ ነኝ አው ሕይወት እንደገባችኝ መጠን እና ባስተማረችኝ ልክ ማስታወሻ የምፅፍላት ፀሀፊ።
"እሺ ቡርቴ በጣም አመሰግናለው ምርጥ እኮ ነሽ!"ካርቶኒውን ከጇ የመመንተፍ ያህል ተቀበልኳት ክበደቱ እንደጠበኩት ሳይሆን በጣም ከባድ ነበር።
"በጣም ጥሩ ነው ያደረግሽው ይሔ በጣም ይረዳኛል ቢሆንም ግን አባዬ ማወቅ የለበትም ነይ ከዚ ቶሎ እንውጣ!"ይዣት ወጣው።
እርግጠኛ ነኝ አባቴ ይሔንን አይፈልግም ባይሆን ኖሮ ደብተርና መፀሀፍቶቼ ከክፍሌ ውጭ እንዲቀመጡ አይሆንም ነበር።ምክንያቱም አደገኛ ነው።በፍፁም ነገሮችን እስከመጨረሻው ጥግ ካልደረስኩባቸው እንደማልተው እና እንደማላርፍ ውዱ አባቴ አሳምሮ ያውቃል እና አደገኛ የሚያደርገውም ይሔ ነው።ስለ ብሌን መጠየቄን ከጀመርኩ ስላለችበትና ስለሁኔታዋ መጠየቄን ቀጥዬ ያለችበት ድረስ መፈለጌን እሰከመጨረሻው መታገሌን እንደማላቆም ያውቃል ካለዚያ አይምሮዬ አያርፍም የፈለኩትን ነገር ከማድረግ ደግሞ ምንም ማንም እንዲያስቆመኝ እማልፈቅድ ጠማማ እና ደረቅ ነኝ ስለዚ አባቴ ሊያደርግ የሚችለው በተቻለው አቅም ስለ እገታዬም ሆነ ላጋራ ስለምችለው ስለመጥፎ ነገሮች እንዳላውቅ መጣር ነው።ካልሆነና ጫፍ ከያዝኩ ግን በጭራሽ አላቆምም ለዚም ይሆናል እንዳላስታውስ የተደረኩበት ምክንያት ምናልባት በቀጥታ አባቴ እንዳላስታውስ አድርጎ ወይም ፈልጎ ላይሆን ይችላል ግን የሌላ ሰው እጅ ሊኖርበት ይችላል ምክንያቱም በዚን ሰዓት ማንንም አላምንም ጠላቴ ማን ይሁን ወዳጄ ማን ይሁን የማወቀው ነገር የለም ግን መጠርጥሩ አይከፋም ከዚ ቡኃላ ጥንቁቅ መሆን ያለብኝ ይመስለኛል ።ቢሆንም አባቴ ካወቀ ግን ለማስቆም መሞከሩ የማይቀር ስለሆነ በሚስጥር ለመያዝ እና ለመቀጠል እገደዳለው።
ክፍሌ ገብቼ በሩን ከወደ ወስጥ በላዬ ላይ ቆለፍኩት።ቁልፍ መሆኑን ካረጋገጥኩ ቡኃላ መኝታዬ ላይ ከዘረጋኃቸው ማስታወሻና መፅሐፍቶች ምፈልገው ለማግኘት አገላብጠው ገባው።
"ትህትና... 1987"
የሚል ፅሁፍ አገኘሁ ስሙን በትክክል አውቀዋለው።ቀጥዬ ገለፅ ገለፅ አደረኩና ማየት ጀመርኩ።
"በቅስፈት ከሰውነት ወደ አውሬነት የተቀየረ መሰለኝ ከሌሎቹ ቀናት በተለየ ተናዶና በጭካኔ ነበር የመታኝ እና አጠገቤ ባገኘሁት ዘነዘና ያገኘሁት ቦታ ዝም ብዬ መታሁት እና እግሬ ስር ተዘረረ።እንደመደንገጥ አልኩ ምኑን እንደመታሁት በውል ስላላወኩ የገደልኩትም መሰለኝ።ብቻ ግን በድንጋጤ ውስጥ እንዳለሁ በደመነፍሴ ሮጬ ከቤት ወጣው አላመንኩትም የሚከተለኝ ነው የመሰለኝ የምችለውን ያህል ሮጥኩ ኋላ የመታኝ ቦታ ሕመሙ ብሶ ሲሰማኝ ላፍታ ጨለማ ውስጥ ቆም ብዬ አሰብኩ።ይሄም ሁሉ ለብሌን ለናቴ ና ለወንድሜ ለቤተሰቤ ስል ያደረኩት ነበር።እነሱ ጥሩ ትዳር እንዳለኝ እንዲያሰቡ ስለፈለኩ አልነግራቸውም ነበር እና በድነገት ተጣላው ብዬ እነሱ ጋር መሔድ እንደሌለብኝ ስላሰብኩ መግቢያዬን አስብ ጀመር።"
ይላል የብሌን እህት እንደሆነች ስላወኩ ለጊዜው ደብተር ዘጋሁ እና ቀጣዮን ተመሳሳይ ደበተር አነስቼ ከፈትኩት።
"የሕይወት ምሳሌየፍቅር የአንድነት እና የተስፋ ማሳያ፦ብ...ሌ...ን" ይላል።
ቀጣዮን በሚስጥር ስለፃፍኩት እርሳርስ ማግኘት ነበረብኝ እና እሱን አውጥቼ ሌሎቹን በአንድ ላይ ሰብስቤ ወደካርቶኑ ከመልሰኳቸው

👍3
👍1
#የውጊያ_ስልት
፡
፡
ሙሴ በበትሩ
ፈርኦን በጦሩ
ኤርትራ ባሕር ላይ ፣ ጦርነት ጀመሩ፡፡
፡
ሙሴ በበትሩ…
ግዙፍ ባህር ከፍሎ ፣ ህዝቡን አሻገረ
ፈርኦን በጦሩ
ከነ ወታደሩ
ባሕር ሰጥሞ ቀረ፡፡
፡
ውጊያ የማይችል ሕዝብ
ግዙፍ ባሕር ከፍሎ ፣ በተዓምር ሲሻገር
ሌላ የውጊያ ስልት
ቀይሮ ይመጣል ፣ ቢሰምጥም ወታደር፡፡
እ
ን
ደ
ዚ
ህ
፡
የተሻገረ ህዝብ
ለቀሪ መንገዱ
አሳ እያጠመደ ፣ ከባህር ሲያወጣ
የፈርኦን ወታደር
ሞቶ ለመዋጋት
በአሳ ገላ ላይ ፣ እሾህ ሆኖ መጣ!!!
።።።።
"አሳን መብላት
እንዳይወጋህ ፣ በብልሃት!"
🌑በላይ በቀለ ወያ🌑
፡
፡
ሙሴ በበትሩ
ፈርኦን በጦሩ
ኤርትራ ባሕር ላይ ፣ ጦርነት ጀመሩ፡፡
፡
ሙሴ በበትሩ…
ግዙፍ ባህር ከፍሎ ፣ ህዝቡን አሻገረ
ፈርኦን በጦሩ
ከነ ወታደሩ
ባሕር ሰጥሞ ቀረ፡፡
፡
ውጊያ የማይችል ሕዝብ
ግዙፍ ባሕር ከፍሎ ፣ በተዓምር ሲሻገር
ሌላ የውጊያ ስልት
ቀይሮ ይመጣል ፣ ቢሰምጥም ወታደር፡፡
እ
ን
ደ
ዚ
ህ
፡
የተሻገረ ህዝብ
ለቀሪ መንገዱ
አሳ እያጠመደ ፣ ከባህር ሲያወጣ
የፈርኦን ወታደር
ሞቶ ለመዋጋት
በአሳ ገላ ላይ ፣ እሾህ ሆኖ መጣ!!!
።።።።
"አሳን መብላት
እንዳይወጋህ ፣ በብልሃት!"
🌑በላይ በቀለ ወያ🌑
#ፍቅርና_በቀል
፡
፡
✍ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
ስለሚንቀለቀል እሳት ሁለንተናዊ ባህሪ ሙሉውን እውነታ
ለማወቅ… አውቆም ለማስረዳት… እሳቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ
መግባት ይጠይቃል፡፡እሳቱ ውስጥ ደፍሮ መግባት ደግሞ
መቅለጥ እና ከስሎ ከእሳቱ ህልውና ጋር መዋሀድን ያስከለትላል፡፡
የእነዚህ ሁለት ሰዎች ታሪክ ይበልጥ ለማወቅ በጥልቀት
ለማጥናት ወሰንኩ፡፡ ልፅፈው፡፡እርግጥ የግለሰቦችን ግለ-
ታሪክ ስፅፍ.. ፅፌም በመፅሀፍ መልክ ሳሳትም ይሄ
የመጀመሪያ ሙከራዬ አይደለም…፡፡ቀደም ብዬ ሶስት ተመሳሳይ መጻፍ አበርክቼያለው፡፡ ልዩነቱ ከዚህ በፊት
የተፃፉት መፅሀፎቼ በፖለቲካውና በጥበብ ዓለም አንቱ
ስለተባሉ ግለሰቦች የሚያወሱ ነበሩ፡፡
ዝነኛ የሆኑትን ይበልጥ ዝና ለማጎናፀፍ በእኔ ፍላጎት ብቻ
ሳይሆን በራሳቸው በግለሰቦቹ ጎትጎችነት እና የገንዘብ ድጋፍ
የተፃፉ ነበሩ…..ይሄኛው ግን ጥቅም ላይ መሰረት ያደረገ
አይደለም..የተለየ ታሪክ ፍለጋ በራሴ ብቻ ተነሳሽነት በፍቅር
ልሰራው የወሰንኩት ታሪክ ነው፡፡ቀድሜ የሄድኩት ወደ ኃይሌ
ነበር ፡፡ያንን የተቋጠረ ገጽን ይበልጥ አጨማደደና
‹‹ለምን የእኛን ታሪክ ለማወቅ ፈለግክ?››
‹‹ከውስጣችሁ በጥልቀት እርቆ የተቀበረ እውነት ያለ ስለመሰለኝ››
‹‹እንዴት እንደዛ አሰብክ?››
‹‹ስለሁለታችሁ የምሰማውና አይኖቻችሁ ውስጥ የምመለከተው የተለየ ነገር ስለሆነብኝ....››
‹‹በፍጽም …ስለእኔ እና እሷ ምንም ነገር እንደበቴ ተላቆ
መናገር አልችልም››
‹‹እሷ እሺ ካለችኝስ?››
‹‹ከዛ ቡኃላ ጠይቀኝ ››ሲለኝ ተስማምቼ ወደ እሷ ሄድኩ፡፡
#እሷ
ከእሱ የበለጠች አስቸጋሪ ነበረች፡፡አንደኛ እንደእሱ የተረጋጋች
አልነበረችም፡፡ እሺታዋንም ሆነ እንቢታዋን ደርዝ ባለው
መልኩ ማስረዳት አይሆንላትም፡፡ፀባዮ በየሰከንድ ተቀያያሪና
ግራ አጋቢ ነው፡፡ የአዕምሮዋ ሚዛን በየሰከንድ ከፍ ዝቅ
እንደሚልም ማንም ለ10 ደቂቃ ከእሷ ጋር የማውራት ዕድሉ
ያጋጠመው ሰው ማወቅ ይችላል፡፡
‹‹ስለ አንቺና ስለኃይሌ ታሪክ አንድ መፃፍ ልጽፍ ፈልጌ ነበር››
‹‹የቱ ኃይሌ››አለችኝ…ጭራሽ ስሙን እንኳን ለመጀመሪያ ቀን
እንደሰማ ሰው ግራ ተጋብታ
‹‹ኃይሌ የትሁት ሆቴል ባለቤት››ርዕሱን ወደ አላሰብኩበት
አቅጣጫ ለውጣው‹‹ለመሆኑ ትሁት ማን እንደሆነች
ታውቃለህ…..?››ስትል ጠየቀችኝ፡፡
‹‹አረ አላውቅም…በፈጠረሽ ልወቃት… .?ማን ነች..? ገምት
ካልሺኝ ግን የኃይሌ እናት ወይም እህት ስም ይመስለኛል›››
‹‹ አይደለም…ትሁት ልጄ ነች..››
‹‹ያንቺ ልጅ››
‹‹አዎ የእኔ ልጅ ነች…የእኔ ቆንጅዬ ልጅ…ቆይ እንደውም
ፎቶዋን ላሳይህ›› አለችና አይፎን ሞባይሏን ከቦርሳዋ
አውጥታ በመክፈት በአማላይ እጣቷ ገልበጥ ገልበጥ አድርጋ
ትሁት የተባለችውን ልጅ ፎቶ አሳየችኝ…ከሰላሳ በለይ ፎቶ
ነው ያየውት…. ትሁት ከአራስነቷ አሁን እስካለችበት ዕድሜ
ድረስ በተላያየ ጊዜ የተነሳችው ፎቶ ነው፡፡ እውነትም እሷ
እንዳለችው ትሁት እንደስሟ ትሁት የሆነች የምታምር መልአክ
መሳይ ልጅ ነች፡፡ የመጨራሻ ትልቁ ፎቶዋ የ8 ዓመት ልጅ
እንደሆነች መገመት ያስችላል ፡፡ግን የገረመኝ ሰላሳውም ፎቶ
ውስጥ አንድም ከእሷ ጋር የተነሳችው ፎቶ የለበትም..ይህ
ደግሞ ወዲያውኑ ነው‹እንዴት..?› የሚል ጥያቄ በውስጤ
የፈጠረብኝ…ደግሞ ልጅቷ ከመልኳ በስተቀር ምኗም የሀበሻን
አይመስልም……››
‹‹ታድለሽ ቆንጅዬ ልጅ አለችሽ…አሁን ካንቺ ጋር ነች?››ጥርጣርዬን ለማረጋገጥ የሰነዘርኩት ጥያቄ ነበር፡፡
‹‹አይደለችም… ነጥቀውኛል..››እንባዋ ያለፍቃዷ ተንጠባጠበ
‹‹ነጥቀውኛል ስትይ…?››
‹‹በቃ ያለፍቃዴ ከጉያዬ መንጭቀው ወስደውብኛል፡፡
የሚገርምህ አንድም ቀን ፊቷን በአካል አይቼት አላውቅም
...እርጉዝ እንደነበርኩ በደንብ አስታውሳለው …ስምንት ወር
እስኪሞላኝ ድረስ አስታውሳለው ከዛ ለተወሰነ ጊዜ ጠፍቼ ነበር..ማለቴ አዕምሮዬ አንቀላፍቶ ነበር መሰለኝ ፡፡ስነቃ
ሆዴ ባዶ ነበር…እቅፌ ላይም የሚያለቅስ ልጅ አላገኘውም….ስጠይቅ የትሁቴን አንድ ውር ሲሆናል ያነሷትን
ፎቶ ነው የሰጡኝ፡፡ ብጮህ መንግስት አለ ብዬ ብከስ …ሰሚ
አለገኘውም፡፡ ማንም ልጄን ሊያስመልስልኝ
አልቻለም….የእኔን ልጅ በመንጠቅ ጉዳይ ላይ አለም
ጠቅላላ በአንድ ድምፅ ነው ያደመብኝ…፡፡ለዛ ነው ሰው ሁሉ
የሚያስጠላኝ…በተለይ ወንዶችን ሳጥናኤል አባቴ ቢሆን እና
ሲኦልን ቢያወርሰኝ የጠቅላላ ወንዶች ማሰቃያ ቦታ ነበር
የማደርገው…. ይገርምሀል ያን ጊዜ እንኳን እሺ ስለሚያመኝ
ነበር ልጄን ከስሬ ያሸሹብኝ ….አሁንስ…..? አይገርምም!!!
አሁንም ልጄን ብዬ ስጠይቅ ፎቶዋን ብቻ ነው የሚልኩልኝ…
እስቲ አንተ ፍረድ አሁን እኔ የገዛ ብቸኛ ልጄን ለማሳደግ እና
ለመንከባከብ የማልችል ዕብድ እመስልሀለው?››አስደንጋጭ
ጥያቄ ነው የጠየቀችኝ፡፡
‹አዎ ትመስይኛለሽ› ብዬ መቼስ አልመልስላትም…ዝም
አልኳት‹‹አየህ ..አንተም እንኳን በእነሱ ሀሳብ ትስማማለህ…
ዓለም ጠቅላላ እኔ መውለድ እንጂ ማሳደግ የማልችል …
በፍቅር አቅሌን የሳትኩ ዕብድ ሴት እንደሆነኩ ነው
የሚያስብት›
‹‹ኸረ እንደዛ አይደለም.. ››አለኳት
‹‹ተወው በቃ››
‹‹ለመሆኑ ማነው ልጅሽን የነጠቀሽ?››
‹‹እሱንማ አልነግርህም? ››
‹‹እሺ ትሁት ያንቺ ልጅ ከሆነች ኃይሌ ታዲያ ይሄን ሆቴል
ለምን በስሟ ሰየመ.?.››
‹‹እሱን እራሱን ጠይቀው? ››
‹‹እሺ እንዳልሽ ….ስለአንቺ እና ስለኃይሌስ?››
‹‹ ስለእኔና ስለእሱ ምን?››
‹‹ማለቴ ስለ ድሯችሁ?››
‹‹ሰማህ ወንድም እኔ ከምትለው ሰው ጋር ምንም አይነት ድሮ
የለኝም ..ከእሱ ጋር ብቻም ሳይሆን ከሌላ ከማንም ጋር
ምንም ዓይነት ያለፈ ወይም የተጠራቀመ ታሪክ የለኝ፡፡እኔ
በየቀኑ ተወልጄ በየቀኑ የምሞት የንጋት ጤዛ ነኝ፡፡እንዲህ
አይነት ሰው ታውቃለህ ፡፡ጥዋት ከእንቅልፌ ነቅቼ ከአልጋዬ
ላይ ስወርድ ከእናቴ መሀጽን ገና የወጣው ነው መስሎ
የሚሰማኝ፡፡ማታ ወይም እኩለ ለሊት ላይ ለመተኛት ወደ
አልጋዬ ስሄድ ወደ ሞት እየተጓዝኩ ያለው መስሎ ነው
የሚሰማኝ፡፡በቃ ህይወት ለእኔ እንደዛ ነች፡፡ስለዚህ ተወኝ ፡፡…
መቼስ የየእለት ታሪኬን ለመቃረም አትፈልግም አይደል.? ›.
‹‹አረ ፈልጋለው… ለምሳሌ በቀን የ10 ደቂቃ ጊዜ ብትሰጪኝ
እና በዛች ደቂቃ ስለሚሰማሽ ነገር ብቻ ብታጫውቺኝ ለእኔ
በቂዬ ነው››ብዙ ለፈለፍኩ ….ብዙ ቀባጠርኩ...እሺታዋን
ለማግኘት ግን ከአንድ ወር በላይ ተስፋ ሳልቆርጥ መወትወት
ነበረብኝ…. ይገርማል በየቀኑ እንቢ ባለችኝ ቁጥር ይበልጥ
የሚስጥራቸው ረሀብተኛ
እየሆንኩ መጣው፡፡ ተስፋ ሳልቆርጥ ዳከርኩ
….በስተመጨረሻ ተሳካልኝ፡፡…..እሺ ያለችኝ በእኔ ስብከት
ተማርካ አይደለም… እኛ አዛውን አጎቷ ናቸው እሺ ያስባሉልኝ፡፡
እሷን ለማሳመን እንደ እኔ አንድ ወር መለፍለፍ
አላስፈለጋቸውም በሁለት ደቂቃ ውስጥ ከአምስት ያልበለጡ
ምጥን ዓ/ነገር ነው ከአንደበታቸው ያወጡት፡፡እሺ
አለቻቸው..እሺ አለቸኝ፡፡ድሮ መምህሬ በነበሩበት ወቅት
እወዳቸው ነበር ..አሁንም ደግሞ ይበልጥ ወደድኳቸው፡፡ከነገ
ጀምሮ ከሰዓት ቡኃላ በተመቻት ሰዓት ለ30 ደቂቃ ያህል ልታወረኝ፡፡
‹‹እሺ እግዜረ ይስጥልኝ››አልኳት ..እሺታዋን ካገኘው ቡኃላ በደስታ ተውጬ
‹‹እግዜር ምንም ሰጥቶኝ አያውቅም.. እንዲሰጠኝም
አልፈልግም››ብላ አሳቀቀችኝ፡፡
‹‹እሺ ይሁን አመሰግናለው››
‹‹እንድታመሰግነኝም አልፈልግም…አጎቴ እሺ በይ ስላለኝ ነው
እሺ ያልኩህ››
‹‹እሺ እዳልሽ… ግን የት ነው ሚመችሽ ማለቴ የት ነው
የምንገናኘው››
‹‹ከሰዓት ቡኃላ ብዬሀለው አይደል?›

👍3❤1
<<አዎ...ማለቴ>> ቦታውን ነው የጠየቅኩሽ››
‹‹እኮ ከሰአት የት አንደምገኝ አታውቅም?››
‹‹ትሁት ሆቴል ነዋ…?››
‹‹ታዲያ ለምን ትጠይቀኛለህ…?››አለችኝ፡፡ሀሳቧን
እንዳትቀይር በመስጋት በፍንደቃ ቶሎ ብዬ ከእሷ ተለየውና
ወደ እሱ ሮጥኩ….
‹‹እሺ አለችኝ እኮ››በቅጡ ሰላም ሳልለው እንኳን ነገርኩት
‹‹አለም እሺ አለችህ..?››
‹‹አረ የምን አለም ..ሩት እሺ አለችኝ እኮ ነው ምልህ››
‹‹ገብቶኛል.. ለእኔ ሩት ሳትሆን ሰላሜ ነች››ተጀመረ አልኩ በሆዴ
‹‹እንደዛ ነው ..ለማንኛወም እሺ ብላኛለች››ደገምኩለት
መልሶ ወደ መብረዱ እየገባ‹‹አይ ጥሩ ነው›› አለኝ
‹‹ስለዚህ አንተም እሺ ብለኸኛል››
‹‹አላደርገውም›› ብሎ ነገሩን ከንደገና እንጭጭ አደረገብኝ
‹‹አረ ተው አቶ ኃይሌ እሷን ለማሳመን ምን ያህል እንደለፋው
ታውቃለህ… ሁለታችሁም ካልተባበራችሁኝ ተደብቋል ብዬ
ማስበውን ንጽህ እውነት አንዴት አደርጌ ፈልፍዬ ማውጣት
እችላለው…››
‹‹ንፅህ እና ቆሻሻ የሚባል እውነት የለም፣እውነት ያው
እውነት ነው፡፡››በማለት በተቀመጥኩበት መቀመጫ ጎልቶኝ
ጥሎኝ ሄደ፡፡ግን አሁንም ተስፋ አልቆረጥኩም፡፡ከሳምንት
መመላለስ ቡኃላ በከፊል ተስማማልኝ፡፡በየቀኑ እሷ
የምትተርክልኝን ታሪክ ከጻፍኩ ቡኃላ ላስነብበው..ከዛ
ባነበበው ታሪክ ላይ በመመርኮዝ በእሱ በኩል ያለውን
እምነት እና እውነት ሊነግረኝ፡፡ምርጫ ስለሌለኝ በእሱ
መንገድ ተስማማው፡፡ከዛ ፕሮፌሰር ጋር ሄድኩ… ላመሰግናቸው፡፡
‹‹ጋሼ ሩት በጥያቄዬ እንድትስማማ ስላሳመኑልኝ በጣም
አመሰግናለው..ይሄ ስራ ለእኔ በጣም አስፈላጊ
ነበር›..ለመሆኑ እኔ አንድ ወር ለምኜት ማሳመን ያልቻልኩትን
እርሶ በደቂቃዎች ያሳመኗት ምን ብለው ነው?››
‹‹እሱን አልነግርህም››
‹‹ይሁን….. ለማንኛውም አመሰግናለው…በምጽፈው
መጽሀፍ ጠቃሚነት አምነውበት እሷንም ስላሳመኑልኝ በጣም
አመሰግናለው፡፡
‹‹አይ በምትጽፈው መጽሀፍ ጠቀሜታ ስላመንኩበት
አይደለም››
‹‹እና ታዲያ ለምንድነው?››
‹‹አየህ እንደምታየው ሩት ችግር ላይ ነች፡፡የእሷ ችግር ደግሞ
እሷ ላይ ብቻ ያበቃ አይደለም… ለኃይሌም የተረፈ ነው፡፡
ለእንደዚህ አይነት ችግር ደግሞ ማውራት እና መተንፈስ
ዋናው ፍቱን መድሀኒት ይመስለኛል፡፡በሁለቱ መሀከል ያለ
ፍቅር ለኒዩክሌር መስሪያ ታስቦ እየተብላላ ለዘመናት የቆየ
ዩራኒዬም አይነት ነው፤ የተመቀ እና በቁጭት የታጨቀ
ኃይል፡፡ይሄንን መጽሀፍ ስታዘጋጅ እርግጠኛ ነኝ ከልጅነታቸው
ጀመሮ ያለውን የረሱትን፤ የዘነጉትን እና የሸሸጓቸውን ታሪኮች
እንዲያወሩልህ ስታደርጋቸው… ያጡትን ነገር እያስታወሱ
ይመጣሉ፡፡የጥላቻቸው መንሴ እርባነ-ቢስ የፍቅራቸው
ጥልቀት ወሰን-አልባ እንደሆነ ሊገለጽላቸው ይችል ይሆናል
..በሂደት ..አንተ ምክንያት ትሆናቸውና እራሳቸውን በራሳቸው
እያከሙ አንዳቸው ስለአንዳቸው መልካምነት ይበልጥ እያሰቡ
ይመጣሉ፡፡ያ ደግሞ በተለይ ለሩት በአማኑኤልም በፀበልም
ነቅሎ ሊወጣላት ያልቻለው የአእምሮ መናጋት
ሊያስተካክልላት ይችላል..ያንን ተስፋ ስላደረግኩ ነው
ያሰመንኳት፡፡
‹‹አመሰግናለው… ግን ሩት ህክምና ሞክራ ነበር እንዴ?››
‹‹አዎ ሁለት አመት አማኑኤል ስድስት ወር ፀበል አሳልፋለች፡፡
ያው አብረው አሳልፈዋል ብልህ ይቀላል፡፡እሷ ስትታመም
እሱም ይታመማል…ሲሻላት ይሻለዋል፡፡ስታዝን ያለቅሳል….ስትደሰት ይፈጋል፡፡
‹‹የሚያስቀ ና ፍቅር ነው›› ከልቤ ያላሰብኩበትን አፌ ላይ
የመጣልኝን አድናቆት ተናገርኩ
‹‹የሚያስቀና አልከው ..ይሄ ምኑም አያስቀና ..የእነሱን ታሪክ
ይበልጥ ጠልቀህ ስታውቀው እንደማያስቀና እና ፍቅር
ሳይሆን መርገምት እንደሆነ ይገባሀል፡አየህ ፍቀር ጥቅል
ትርጉም ያለው ቃል ነው፡፡የወሲብ አምሮት ያነሆለለው
ጎረምሳም አፍቅሬያለው ይላል፡፡ልቡ በውበት ድማሚት
የተሰነጠቀበትም ያው ሌላ ስም የለውም አፍቅሬያለው
ይላል፡፡ልቡ በመውደዱ የተነሳ ቀልጣ ባፈቀረው ነገር መላ
አዕምሮው ተነጥቆ ወደ ዕብደት ወይም ወደ አምልኮ
የተሸጋገረውም ያው አፈቀርኩ ብቻ ነው ማለት የሚችለው፡፡
ፍቅር እንደትምህርት በደረጃ አይከፋፈልም፡፡ፍቀር እንደ
ጠጣር ቁስ በኪሎ ተመዝኖ የእከሌ ፍቅር ይሄን ያህል ኪሎ
ነው…የዛኛው ደግሞ ይሄን ያህል ኪሎ ይመዝናል አይባልም፡፡
ፍቅር በፊልም እና በልብ ወለድ አሰማምረን እና አሽሞንሙነን
ለመግለፅ እንሞክራለን …ግን ማሳየት የምንችለው የፍቅርን
ከፊል እውነት ብቻ ነው፡፡
ፍቅር እየተንቀለቀለ የሚነድ እሳት ማለት ነው፡፡ስለእሳት
ለማሰረዳት የነበልባሉን ቀለም ወይንም ሰውነታችን
ስለሚለበልበን ነበልባል ሙቀት በመግለጽ ለማስረዳት
እንሞክር ይሆናል፡፡ግን ይሄ የእሳትን ሁለንተናዊ ተፈጥሮ
ለማወቅ ..አውቆም ለማስረዳት በቂ አይደለም፡፡ስለእሳቱ
ሁለንተናዊ ባህሪ ሙሉውን እውነታ ለማወቅ እሳቱ ውስጥ
ሙሉ በሙሉ መግባት ይጠይቃል፡፡እሷቱ ውስጥ ከተገባ
ደግሞ መቅለጥ እና ከስሎ ከእሷቱ ህልውና ጋር መዋሀድን
ያስከለትላል፡፡ከእሳቱ ህልውና ጋር መዋሀድ ማለት ደግሞ
ያው እሳት መሆን እና ስለ እሳት ለመሳረዳት አንደበትም
አፍላጎትንም ማጣት ማለት ነው፡፡
እና በዚህ ስሌት መሰረት በሩቴ እና በኃይልዬ መሀከል ያለው
ፍቅር ሙሉ እውነት ለማወቅ ለማንም የሚቻል
አይደለም..ምን አልባት እነሱ በተነከሩበት ደረጃ ፍቅር ውስጥ
ለገባ ካልሆነ በስተቀር፡፡ በእነሱ መጠን ፍቀር ውስጥ መነከር
ደግሞ ያው እንደምታየው በመንፈስ መጥፋትን ያስከትላል፡፡

👍2
#ፍቅርና_በቀል
፡
፡
#ምእራፍ_ሦስት
፡
✍ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
"የዕድሜ እርጅና ነፍስህ ከነንቃቷ እና ብቃቷ ማደሪያዋ
የሆነውን የደከመ አካልህን ተለይታ ወደ ዘላለማዊው እሷነቷ
መነጠቂያ ወቅቷ መቃረቡን ማስጠንቀቂያ ምልክት ብቻ
ሲሆን…የአዕምሮ እርጅና ግን በአካልህ ውስጥ በጊዜያዊነት
ያደረችው ህያዊቷ ነፍስህ ኃይሏ ከስሞ በሚንቀሳቀሰው አካልህ ውስጥ በድንዛዜና በፍዘት ላይ የመገኘቷ ማሳያ
ነው.፡፡"
ከቀጠሮዬ 30 ደቂቃ ቀድሜ ነው ትሁት ሆቴል የተገኘሁት፡፡
ከአስር የማይበልጡ ደንበኞች እዚህም እዛም ፈንጠርጠር
ብለው ሲሰተናገዱ ይታያሉ፡፡አይኔ ቀድሞ የተመለከተው ሩትን
ነው፡፡ተመስገን ነው ቦታዋ ላይ ትገኛለች፡፡መቼስ ቦታዋ የብቸዋ ግዛት እንደሆነች ነግሬያችሆለው፡፡
ሌላ ተስተናጋጅ ወደ እሷ በቀላሉ እንዳይሄድ እንደ ካሻሪ ቤት
ከወገብ በታች በሆነ በመስታወት የተከለለ እና ሁለት
መለስተኛና ምቹ ሶፋዎች የተቀመጡበት ቦታ ነው፡፡አሁን
ይሄንን የማወራው በራፉ ጋር ቆሜ ከመስታወቱ አሻግሬ በሩቅ
እያየኋት ነው፡፡ስለተቀመጠች የለበሰችው ቀሚስ አጭር
ይሁን ረጅም ለመለየት ቢያዳግተኝም ሰማያዊ ቀለም ያለውና
ውብቷን ያጎላ እንደሆነ እየታየኝ ነው፡፡ፀጉሯን ዝም ብላ
ጀርባዋ ላይ በትናዋለች፡፡ያ እንደመቃ የተመዘዘ አንገቷን ወደ
ግራ 45 ዲግሪ ያህል ዘንበል ብሏል፡፡አንድ ከሚላት
ጠርሙስ ግምሽ ድረስ ከተሞላ ብርጭቆ ጋር ከፊት ለፊቷ
ካለ ጠረጵዛ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ወደ እሷ አላመራውም በራፍ
አካባቢ ወንበር ፈልጌ ተቀመጥኩ፡፡ ኃይሌን ከተቀመጥኩ
ቡኃላ ነው ያየሁት …..ከሩት መቀመጫ በተቃራኒ ኮርነር ላይ
ካለ የካሻሪ ወንበር ላይ ተቀምጧል፡፡እንደሁል ጊዜው ፊቱ
እንደተጨማደደ ሲሆን እንደወትሮው በሱፍ ሽክ እንዳለ
ነው….የቀጠሮዬ ሰዓት አስኪደርስ መጠበቅ አለብኝ፡፡
እስከዛው ማኪያቶ አዘዝኩ.. እንዲያነቃቃኝም፤
እንዲያረጋጋኝም፡፡ይህ ነገር እንዲበላሽብኝ አልፈልግም፡፡
የስራ ዘመኔን ሙሉ ታወቂ ሰዎችን እና ባለስልጣኖችን ቃለ
መጠየቅ ሳደርግ እና ሳናዝዝ ነው የኖርኩት…. እንደዛሬው ቀን
ግን የተጨናነቅኩበትን ቀን አላስታውስም፡፡
አይደርስ የለ ደረሰና በምልክት ወደእሷ እንድጠጋ
ፈቀደችልኝ..ማስታወሻ ደብተሬን እና መቅረጫ ቴፔን ያዝኩና
መቀመጫዬን በመልቀቅ ወደ እሷ አመራው… የመስታወት
ከለላው ጋር ልደርስ ሁለት ሜትር ያህል ሲቀረኝ አንድ ከእሷ
በቅርብ ርቀት ላይ ተገትሮ የነበረ ወጠምሻ ተንደርድሮ መጣና
ፊቴ ተጋርዶ አስቆመኝ፡፡
‹‹ጌታዬ ወደየት ነው››
‹‹ሩት ጋር ››
‹‹ወደ እሷ መሄድ አይችሉም››
‹‹እራሷ እኮ ነች እንድንገናኝ የፈቀደችልኝ››
‹‹ይቅርታ ጌታዬ… ማጣራት አለብኝ..እዚሁ ቆመው
ይጠብቁኝ ››ብሎ ልክ ቤተመቅደስ እንደሚገባ ትሁት አማኝ
በአውራ ጣቱ ብቻ ወለሉን እየረገጠ ወደ እሷ ተጠጋ
ቀረባት፡፡እጆቹን ወደኃላ አጣመረና አጎነበሰ…፡፡
ከዛም ለሹክሹክታ በቀረበና ለኔ ሊሰማ በማይችል ድምፅ ነው
የነገራት፡፡የእሷ ጀርባ ብቻ ስለሚታየኝ ምን እንዳለችው
አላወቅኩም…ብቻ ነሸጥ አድርጎት‹ ዞር አድርግልኝ› ብላ
ትዕዛዝ እንዳትሰጠው ፈራው፡፡ ልጁ እንደአካሄዱ ተመለሰና
መጣ
ፊቱን ወደኃይሌ አዞረ …አይኖቹን ተከትዬ አንገቴን
አሽከረከርኩት..ኃይሌ አንገቱን ከፍ ዝቅ በማድረግ የይሁንታ
ምልክት ሲሠጠው አየው..እንግዲህ ወደ እሩት ለመጠጋት
የእሷ ፍቃድ ብቻ ሳይሆን የኃይሌ ፍቃድም የግድ ነበር ማለት
ነው፡፡››
‹‹ይግቡ…›› ‹‹በዝግታ ገባውና በፀጥታ ከፊት ለፊቷ የተዘረጋ
ክፍቱ ሶፋ ላይ ተቀመጥኩ…፡፡ዝም አልኩ ..ዝም አለቺኝ ..፡፡
5 ደቂቃ አለፈ፡፡ አቤት እንዲህ አይነት ዝምታ እንዴት
ያስጨንቃል…‹ዝምታ ወርቅ ነው› የሚሉ ሰዎች ምን አለ አሁን
በእኔ ቦታ ተቀምጠው ወርቅ ምን ምን እንደሚል ባጣጣሙ››
‹‹እሺ ደራሲ ነህ ፀሀፊው.. ወይን ትሞክራለህ?››አለችኝ ?
‹‹አይ ይቅርብኝ››
ጉዳዬ ምን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ እንደማያውቅ ሰው‹‹እሺ
ምን ነበር?››አለችኝ
‹‹መጀመር እንችላለን?››
‹‹ጀመርን እኮ ››ማስታወሻዬን ገለጥኩና ብዕሬን
ቀሰርኩ..ድምጽ መቅረጫዬን አስተካክዬ‹‹….ድምጽሽን
ብቀዳው ቅር ይልሻል?››
‹‹እንደፈለግክ››አለችኝ ግድ የለሽ ሆና
‹‹አመሰግናለው››
‹‹ምስጋና አልወድም››
‹‹እሺ ይቅርታ››
‹‹አቦ ይቅርታም አልወድም››ድንግርግሬ ወጣ
‹‹እሺ ወደ መጀመሪያ ጥያቁዬ ልግባ››
‹‹ኡፍ… ጥያቄም አልወድም››ብስጭትጭት
አለችብኝ….‹‹ታዲያ ምን ይሆን የምትወደው?›› ስል እራሴን
ጠየቅኩ፡፡
‹‹ታዲያ እንዴት ይሁን?››አልኳት
‹‹አውሪኝ አይደል ያልከኝ …በቃ ዝም ብለን እናውራ››
‹‹እሺ እዚሁ አዲስ አበባ ነው የተወለድሽው
አይደል….?››ሳላስበው አልወድም ያለችኝን ጥያቄ ነው
የጠየቅኮት..እሷ ግን ስላላስተዋለችው ትመልስልኝ
ጀመር‹‹አዎ እዚሁ ልደታ አሁን የምኖርበት ቤት ውስጥ ነው
የተወለድኩትም ያደግኩትም..እንደዚህ እንደምታየኝ እስካረጅ
ድረስም እዛው ነው እየኖርኩ ያለውት፡፡
ስለወላጆቼ ላውራህ መሰለኝ…..፡፡አባቴ ቀላል ሰው
አይምሰልህ …የተፈራ እና የተከበረ የሀይለስላሴ ዘመን
ባላአባት ነበር ፡፡ባላምብራስ ሞገስ ይመር ይባላሉ፡፡ያው
አባቴ ቢሆኑም ባጣም ትልቅ ሰው ስለሆኑ አንተ ማለት
ይከብዳኛል፡፡እንዳልኩህ በንጉሱ ዘመን የሲዳሞ ባላባት ነበሩ፡፡
በዚህም የተነሳ ግማሽ የሲዳሞ መሬት የእሷቸው የግል ይዞታ
እደነበር ሲያወሩ ሰምቼያለው...በዛ መሬታቸው ተለክቶ
የማያልቅ ቦሎቄ እና ቡና ያመርቱ ነበር፡፡ እዚህ አዲስ አበባም
ከሶስት በላይ ምን የመሳሰሉ የንግድ ቤቶች ነበሯቸው፡፡ይሄ
ሁሉ ግን ከንጉሱ መንግስት መገርሰስ ጋር አብሮ ወድሞባቸዋል፡፡
አባቴ ሲዳሞ ንብረት ብቻ አልነበረም ሙሉ ቤተሰብም
ነበራቸው፡፡የመጀመሪያ ሚስታቸው እና ከእሷ የወለዷቸው
ሶስት ልጆች ጋር ይርጋጨፊ በተንጣለለ ሙሉ ቤት ውስጥ
ይኖሩ ነበር፡፡ግን ልክ የለውጡንፋስ እንደተሰማ በለሊት
እንደተኙ ቤታቸው ከውጭ ተቀርቅሮ እሳት ተለቀቀበት…፡፡
ንብረታቸው፤ ልጆቻቸው ሆኑ በወቅቱ እቤት ውስጥ የነበሩ
አገልጋዬቻቸው በሙሉ በእሳቱ ተበልተው ከሰል ነበር የሆኑት፡፡
ያንን ያደረገው ሰውዬ ዋና አላማው ቤተሰቡን መግደል
ሳይሆን አባቴን ማጥፋት ነበር..፡፡ያው እንደአጋጣሚ ሆኖ
እሳቸው በተፈጥሮቸው ተጠራጣሪ ስለነበሩ ገና የለውጡን
ጭምጭምታ እንደሰሙ ሹልክ ብለው ወደአዲስ አበባ መጥተው ነበር፡፡
ያንን ሚስጥር ደግሞ ጥፋቱን ያደረሰው ጠላታቸውም ሆነ
ብዙ ወዳጆቻቸው አያውቁም ነበር…ስለዚህ ቡዙው ሰው
እሳቸውም አብረው እንደሞቱ በማሰብ አልቅሰውላቸው ነበር፡፡
ያንን ጥቃት ማን እንደፈፀመባቸው አይታወቅም.. እሳቸው
እንደሚሉት ግን ጊዜ ሲጠብቅላቸው የነበረ ከድሮ በርካታ
ጠላቶቻቸው መካከል አንድ ጊዜ ሲጥላቸው ጠብቆ
እንደተበቀላቸው ያምናሉ፡፡..ያ ማለት ደግሞ ሚስጥሩን
በሆዳቸው ቀብረውት እንጂ ማንነቱንም በደንብ ያውቁ ነበር
ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም እሳቸው እዚሁ አዲስ አበባ
እርማቸውን አውጥተው እንደወጡ ቀሩ.. በለውጡ ምክንያት
ሙሉ ቤተሰባቸውን ብቻ አልነበረም ..ሙሉ ንብረታቸውንም
ነበር የተነጠቁ…፡፡
እና ከውርስ በተረፈላቸው አሁን እኔ በምኖርበት የልደታው
ቤት ኑሮቸውን እንደአዲስ መኖር ጀመሩ፡ሌላ ሰው ቢሆን
ይሄንን እጦትና በደል ማን ሊቋቋመው ይችላል?፡፡ አባቴ ግን
ፅኑና ቆፍጣና ሰው ናቸው..ለምንም ነገር ፊት አይሰጡም
ማንም ሰው ምንም ነገር ሊነጥቃቸው ይችላል…አንገታቸውን
ግን ሊያስደፋቸው አይችልም ››አለችኝ ››ለአባቷ ያላትን
ትምክህት እና ኩራት በሚገልፅ ስሜት፡፡
‹‹ታዲያ የዛን ጊዜ
እናትሽ አልነበረችም

👍1🥰1
‹<በርግጥ ጉዳዩን በጥልቀት አላውቅም… ግን አባቴ
ቤተሰባቸውን ካጡ ቡኃላ በገረድ ብቻ ከአስር ዓመታት በላይ
በላጤነት ኖረው ነበር..ከዛ ወዳጅ ዘመዶች ሽማግሌው
ተጎዱ..ጭናቸውን የምታሞቅ ልጃገረድ ፈልገን እንዳራቸው
ብለው..እናቴን አጋቧቸው…፡፡
አባቴ እናቴን ሲያገቧት ቢያንስ በ50 ዓመት የሚበልጧት
ይመስለኛል፡፡››
‹‹ኦ!!! ትልቅ ልዩነት ነው››
‹‹አዎ ትልቅ ልዩነት ነው….ግን ልዩነቱ ግራ ያጋባል፡፡ለእናቴ
እኔ ሁለተኛ ልጅ ነኝ፡፡እኔን ስትወልድ ዕድሜዋ 20 ብቻ
ነበር..ግን ልጅ ሆኜ እንኳን እናቴ አሮጊት አባቴ ደግሞ ጎረምሳ
ነበር የሚመስሉኝ፡፡እናቴ ሁለ ነገሯ ቅርፍፍ ያለ ነበር፡፡አካሄዷ
የተጎተተ..ንግግሯ የቀሰሰ..ፈሪ እና ድንጉጥ… ሁሌ ጎዲያ
የምትወሸቅ ..በዛ ላይ ሁሌ በሽተኛ የሆነች ሴት ነበረች….፡፡
የዕድሜ እርጅና ነፍስህ ከነ ንቃቷ እና ብቃቷ ማደሪያዋ
የሆነውን የደከመ አካልህን ተለይታ ወደ ዘላለማዊው እሷነቷ
መነጠቂያ ወቅቷ መቃረቡን ማስጠንቀቂያ ምልክት ብቻ
ሲሆን…የአዕምሮ እርጅና ግን በአካልህ ውስጥ በጊዜያዊነት
ያደረችው ህያዊቷ ነፍስህ ኃይሏ ከስሞ በሚንቀሳቀሰው
አካልህ ውስጥ በድንዛዜና በፍዘት ላይ የመገኘቷ ማሳያ
ነው…..፡፡
ምን ለማለት ፈልጌ ነው …አባቴ በዕድሜ ሲያረጁ እናቴ
በአዕምሮ አርጅታ ነበር፡፡ አላሳዝንም ከሁለት ሽማግሌዋች
መወለዴ…በነገራችን ላይ እናቴ ታላቅ ወንድሜን ብቻ ነው
ለአንድ አመት ጡት ያጠባቸው..፡፡ እኔ እና ታናሽ እህቴ ግን
ለዛ አልታደልንም….ምክንያቱም በወቅቱ ነቀረሳ ሚባል በሽታ
ታማ ጡቷ ተቆርጦ ነበር..፡፡
ቡኃላ ሄዳ ሄዳ የአስር ዓመት ልጅ ሳለው እስከመጨረሻው
አሸለበች.. ሞተች፡፡ በመሞቷ አላዘንኩም.፡፡እንደውም
በጣም ነው የተበሳጨውባት….፡፡ ዕድሜ ጠገብ ሽማግሌ
አባቴ እንዲያ በጥንካሬ ሕይወትን እየኖረ ሳለ እሷ እንዴት
ጥላኝ ትሞታለች…፡፡ የተናደድኩባት በወቅቱ ልጅ ስለሆንኩ
አይደለም… አሁንም ስለእሷ ሳሰብ ተመሳሳይ ንዴት ነው
የሚሰማኝ… ከተወለድኩ አንስቶ አንድም ቀን እንደምፈልገው
ተንከባክባኝ አታውቅም..
‹‹አባትሽ አሁን በህይወት አሉ?››
‹‹አይ የለም …እሱም ሞቷል››
‹‹እሳቸውም ታመው ነው?››
‹‹አይ እሷቸውን እንኳን እኔው ነኝ የገደልኳቸው››
‹‹የገደልኳቸው ስትይ …?ግድል ግድል››
..ያለምንም ማወላወል ቋፍጠን ብላ፡፡‹‹አዎ ግድል››አለችኝ
‹‹ደነገጥኩ‹‹እስቲ ትንሽ አባርሪልኝ ..እንዴት አድርገሽ…
ለምንስ ብለሽ ገደልሻቸው….…?አሁንስ…?››ይቺ ልጅ
የምትናገረውንም የእውነት ነው ብዬ መቀበል እየከበደኝ ነው
፡፡
‹‹ይሄንን ለዛሬ እንዝለለው….ምን አልባት ሌላ ቀን እነግርህ
ይሆናል፡፡›› ሰዓቱን ተመለከትኩ…...8 ደቂቃዎች አለኝ፡፡
‹‹እህትና ወንድምሽስ አሉ?››
‹‹እህቴ የእናቴ ቢጤ ደካማ ስለነበረች 15 ዓመቷ ላይ ነው
ድንገት የሞተችው..፡፡ ወንድሜ ግን አለ ..ግን አይቼው
አላውቅም…ማለቴ ካየውት ቆየው፡፡ እንግሊዝ ነው ያለው..፡፡
አንተ የረሳውትን አስታወስክኝ ብታይ በጣም ናፍቆኛል፡፡
ወንድሜ ለእኔ በጣም ጥሩ ሰው ነው፡፡ግን ለእኔ ጥሩ ነው
ማለት ለሌላውም ጥሩ ነው ማለት አይደለም..ራስ ወዳድ እና
ጨካኝ ቢጤ ነው.. ብታይ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ
ጉርምስናቸው ጊዜ ድረስ ዘወትር እንደተጣላን እና
እንደተደባደብን ነበር፡፡ይገርምሀል ሁሌ የምንጣለው ደግሞ
በኃይልዬ ምክንያት ነው..፡፡ እሱን ሲያስከፋብኝ አልወድም…
እሱን ሲተናኮሰው አያስችለኝም..፡፡ታላቄ ነው… እነደሚያሸንፈኝም አነደሚጠልዘኝም እየወቅኩ ዘልዬ
አንቀዋለው..፡፡ ማንም በኃይልዬ ሲመጣብኝ
አልወድም…››ዝም አለች.. ለመጀመሪያ ጊዜ ዐይኖቾ በእንባ
ተሞሉ …አንገቷን ቀና አደረገችና እይኖቾን ወደ ተቃራኒው
ኮርነር ወረወረች… አይኞቾን ተከትዬ በአይኖቼ ተጎዝኩ ኃይሌ
ላይ አረፉ…. እሱም ወደ እኛ ሲያይ ነበረ መሰለኝ ድንገት
ስንገጣጠም እንደመርበትበት አለና አንገቱን ወደተቃራኒው
አቅጣጫ አዞረው….‹‹የእኔ ጌታ…››አለችና ትኩረቷን ወደ እኔ
መለሰች…..እኔ ደግሞ ግራ ግብት ብሎኝ ነበር… ግራ ግብት
አለኝ ስላችሁ የምታወራውን ነገርም እውነትነት
እየተጠራጠርኩ ነው እያልኳችሁ ነው፡፡…ቢሆንም መቀጠል
አለብኝ…፡፡
‹‹ኃይሌ እና ወንድምሽ ይታዋወቁ ነበር እንዴ?››
‹‹አንድ ቤት እኮ ነው ያደግነው…ኃይልሻ እና ወንድሜ ደግሞ
በ10 ወር ብቻ የሚበላለጡ እኩያሞች ነበሩ፡፡አባቴ ከሲዳሞ
መጥተው ልደታ መኖር እንደጀመሩ ትንከባከባቸውና
ትቀልባቸው የነበረችው እቴቴ ነበረች… ማለቴ የኃይልዬ
እናት….፡፡አባቴ እናቴን ሲያገባ እቴቴ የአራት ወር እርጉዝ
ነበረች..ከዛ ኃይልዬን ወለደች..፡፡እናቴም ልክ እንደእህቷ
አረሰቻት…፡፡ከዛ እናቴም በ10 ወር ልዩነት ወንድሜን
ስትወልድ እቴቴ በተራዋ አረሰቻት.፡፡እና ወንድሜ ደረጄና
ኃይልሻ እኩያሞች እና ጎደኛሞች ነበሩ፡፡
ግን ከልጅነት እሰከ ጎረምስ ድረስ ደረጄ ኃይልሻን
እንደቀጠቀጠውና እንዳመናጨቀው ነበር..እኔ ደግሞ
ለኃይልሻ ተደርቤ ከእሱ እንደተጣላው፡፡ ኃይልሻ በጉልበት
ከእሱ አንሶ አይደለም ….እንደውም ደረጄን ሌሎች የሰፈር
ልጆች ሲቀጠቅጡት የሚበቀልለት እና የሚያስጥለው
ኃይልሻ ነበር፡፡ ከእሱ የበለጠ ጉልበትም ድፍረትም ነበረው፡፡
ግን አባቴን እጅግ ሲበዛ ይፈራቸው ነበር..እሳቸው ደግሞ
ለደረጄ ያለቸው ፍቅር የተለየ ነበር…በዛም የተነሳ ቀና ብሎ
ሊያየው እንኳን ይሸማቀቅ ነበር….
‹‹የሚገርም ነገር ነው….››
‹‹…ሌላ የሚገርም ነገር ደግሞ ልንገርህ ….እኔ ከወለደችኝ
እናቴ በላይ እናቴ መስላ የምትታየኝ እቴቴ ነች..፡፡እቴቴ
የኃይልሻ እናት..እርግጥ የቤታችን ገረድ እንደሆነች ነው
የሚታወቀው …ለእኔ ግን ያ ትርጉም ሰጥቶኝ አያውቅም፡፡
ይገርምሀል …ሀይልሻን ጡት ያስጣልኩት እኔ ነኝ፡፡ያው እናቴ
በሽተኛ ነበረች ብዬሀለው አይደል…ልክ ከእናቴ ማህፀን
እንደወጣው ወደ እቴቴ እቅፍ ነው የተሸጋገርኩት፡፡ከዛ
ከኃይልዬ አፈ ውስጥ የእቴቴን ጡት መንጭቄ እኔ አፍ ውስጥ
ከተትኩት እናም እሱ በሁለት አመቱ ጡት ሲጥል..እኔ ቀጣዩን
ሶስት አመት የእቴቴን ጉያ ውስጥ ተወሽቄ ጡቷን ጠባው፡፡
ጡቷን ብቻ ሳይሆን ፍቀሯንም ዕድሜ ልኬን ጠብቼያለው፡፡
የእኔ ወላጆች በአካባቢው በጣም የተከበሩ በምቾት
ተንደላቀው ቢላ ቤት ውስጥ ጮማ እየቆረጡ የሚኖሩ
ነበሩ…. የኃልዬ እናት እቴቴ ደግሞ አባቴ ፈቅዶ በሰጣት
ከኩሽናችን ቀጥሎ ባለች ጠባብና የፈራረሰች ጭቃ ቤት
ውስጥ ነበር የምትኖረው…ሁል ጊዜ ግን እግዚያብሄርን
ጠይቀው የነበረው ‹ምን አለ እኔንም እንደኃይሌ ከእቴቴ
እንድወለድ ብታደረገኝ ›› ብዬ ነበር.. የእቴቴ የፈራረሰው እና
የሚያፈሰው ቤቷ የታደሰላት እራሱ በእኔ ምክንያት ነው..እኔ
ከእሷ ጉያ ውስጥ እዛው ፍርስራሽ ቤት ውስጥ አድር
ስለነበረ… ‹‹አባቴ ልጄ በሸታ ላይ ትወድቅብኛለች›› ብለው
ስለሰጉ ቤቱን አሳደሱላት፡፡ ›› አለችና ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ
ፈልጌ አፌን እንደከፈትኩ ‹‹…በል ቸው››ብላኝ ድንገት
ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከመቀመጫዋ በመነሳት በኃለኛው
በር ወጥታ ተሰወረችብኝ..፡፡ ምርጫ አልነበረኝም..፡፡በፊት
ለነበሩኝ ጥያቄች መልስ ለማግኘት መጥቼ ጭራሽ በብዙ
አዳዲስ ጥያቄዎች አዕምሮዬን ጠቅጥቄ ዕቃዎችን ሰብስቤ
ተነሳው፡፡ኃይሌን በዓይኖቼ ተሰናብቼ ሆቴሉን ለቅቄ
ወጣው…..፡፡
ነገ ጥዋት ከእሱ ጋር ቀጠሮ አለኝ……አሁን ሩት የተረከችልኝ
ተረት መሳይ ታሪክ የእውነት ነው ወይስ የአዕምሮዋ
መቀባዠር የፈጠረው ብዣታ …? ይሄንን ከኃይሌ ነው
ማረጋገጥ የምችለው፡፡… ሩት ያወራችልንን ታሪክ መሰረት
በማድረግ
ለኃይሌ