#ባለመኖር_ስጋት
አብሬሽ እስካለሁ ''ፈልገሽ አትጪኝ''
ከሚል ምኞት በቀር ሌላ ሐቅ አላውቅም፣ በተፈለጉበት አለመኖር እንጂ
የሚፈልጉትን ማጣት ብዙ አይጨንቅም፡፡
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

YouTube
አትሮኖስ_ Tube
Share your videos with friends, family, and the world
👍6❤2
አንድ የመስታወት ቁራጭ ከእንብርቷ በታች ሆዷ ላይ ተሸጦባት ነበር….ትንፋሿን ሳዳምጥ ትንሽ ትንሽ ብን ብን ይላል፡፡በደመነፍስ ስልኬን አውጥቼ ለአባዬ ደወልኩለት… ከዛ በኃላ የሆነውን እኔ አላውቅም….እራሴን ስቼ ቤት ክፍሌ ውስጥ ተዘግቶብኝ በሶስተኛው ቀን ነው የነቃሁት፡፡እና አውቄም ሆነ በድንገት አደጋ እናትሽን የገደልኳት እኔ ነኝ…ነገ ጥዋት ወደከተማ እንደተመለስን አሁን ለአንቺ የነገርኩሽን ጠቅላላ ቃሌን ሰጥቼ ፍርዴን እቀበላለው..በወላጆቼና በሌሎች ሰዎች ላይ የያዝሽውን ቂም ግን በቃ አዚህ ላይ አቁሚ፡፡››አለና በረጅሙ በመተንፈስ ወደኩርሲው ተመልሶ ተቀመጠ፡፡
አለም የጂኒዬርን ኑዛዜ በጥሞና ነው ያዳመጠችው….አንድም ቃል አላሳለፈችም…. እናቷ እንዴት እንደሞተች አሁን በግልፅ አውቃለች….ግን አሁንም ታሪኩ ሙሉ አልሆነላትም…‹‹በምንም አይነት ወንጀለኛውማ ጂኒዬር ብቻ አይሆንም››ስትል በውስጧ አሰበች…እሷ የሆነ ነገር ከማለቷ በፊት….እናቱ ሳራ በድንገት መናገር ጀመረች፡፡
‹‹ልጄ አንተ እንዲሁ ሰበብ ሆናብህ እንጂ ሰሎሜን የገደልካት አንተ አይደለህም››አለችው፡፡
‹‹እማዬ አሁን በቃሽ …ባበቃለት ጉዳይ ላይ ምንም ለውጥ ላታመጪ አትድከሚ››
‹‹አይደለም..ሰሎሜን የገደልናለት እኔና ስርጉት ተባብረን ነው.››
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አለም የጂኒዬርን ኑዛዜ በጥሞና ነው ያዳመጠችው….አንድም ቃል አላሳለፈችም…. እናቷ እንዴት እንደሞተች አሁን በግልፅ አውቃለች….ግን አሁንም ታሪኩ ሙሉ አልሆነላትም…‹‹በምንም አይነት ወንጀለኛውማ ጂኒዬር ብቻ አይሆንም››ስትል በውስጧ አሰበች…እሷ የሆነ ነገር ከማለቷ በፊት….እናቱ ሳራ በድንገት መናገር ጀመረች፡፡
‹‹ልጄ አንተ እንዲሁ ሰበብ ሆናብህ እንጂ ሰሎሜን የገደልካት አንተ አይደለህም››አለችው፡፡
‹‹እማዬ አሁን በቃሽ …ባበቃለት ጉዳይ ላይ ምንም ለውጥ ላታመጪ አትድከሚ››
‹‹አይደለም..ሰሎሜን የገደልናለት እኔና ስርጉት ተባብረን ነው.››
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍82❤29😱23
ጁኒዬር ከተቀመጠበት ተነሳ፣ ወደኩማንደሩ ቀረበና እየተንዘረዘረ ማውራት ጀመር‹‹ከዛ እኔ ጅሉን አባቷ የሰራሀውን ወንጀል እንዲደብቅልህ እና ወደእስር ቤት እንዳትገባ ልጁን ማግባትና መዛመድ አለብህ ብላችሁ አስፋፈራራችሁኝና..በሰሎሜ ሞት ከደረሰብኝ ሀዘን እንኳን በቅጡ ሳላገግም አግለብልባችሁ ስርጉትን እንዳገባት አደረጋችሁ››ብሎ አፈጠጠበት፡፡
ኩማንደሩ አንገቱን ከማቀርቀር ውጭ ምንም አልመለሰለትም፡፡
‹‹ምን አይነት ጅል ኖሬያለው…አባቴና የልብ ጓደኛዬ እድሜዬን ሙሉ እንደጅል ሲጫወቱብኝ የማላውቅ ሞኝ ››ተንሰቅስቆ አለቀሰ…እናትዬው ከተቀመጠችበት ተነሳችና አቅፋ እያባበለች ወደመቀመጫው መለሰችው፡፡
ከተወሰነ የውጥረት ዝምታ በኃላ‹‹አንድ የመጨረሻ ነገር አለ…››አለ አቶ ፍሰሀ፡፡ የሁሉም አይኖች ወደእሱ ዞረ..
‹‹ከዚህ በላይ ምን ቀረ? አለቀ እኮ… ለመስማት ሳልመው የነበረውን ነገር ሁሉ በዝርዝር አስረዳችሁኝ፡፡››
‹‹ይሄንን ለሁላችሁም ነው የምናገረው..ልጄ ጁኒዬር በዛን ቀን እናትህንና ስርጉትን ሸኝተህ ስትመጣ ከሰሎሜ ጋር ስናወራ እና ስንጨቃጨቅ የነበረው. ልጄን አታገቢውማ
..አገባዋለው በሚለው ጉዳይ አይደለም››
‹‹እና ታዲያ በምንድነው?››ጁኒዬር በመገረም ጠየቀ፡፡
‹‹ይሄንን እውነት ስነግራችሁ ሁላችሁም ከህይወታችሁ አንቅራችሁ እንደምትተፉኝ አውቃለው …ይሁን እንጂ በዚህ ለሊት እግዚያብሄር ሁለቴ ከሞት ደጃፍ አድርሶ የመለሰኝ እውነቱን ተናግሬ ንሰሀ እንድገባ ነው….ስለዚህ ነግራችኃላው…የሚያምም ቢሆን ስሙኝ፡፡አለም አንቺ የጎበና ልጅ አይደለሽም…››በቤቱ ሌላ ድንጋጤ..ተበተነ፡፡
‹‹ከዚህ በፊት ዲቃላ ነሽ አላችሁኝ ..አሁን ደግሞ ያንኑ ዲቃላነቴን ልትነጥቁኝ ነው?ይሄስ ምን ማለት ነው?››
‹‹ገመዶ ትዝ ይልህ እንደሆነ አንጃ እሷ በዛን ክረምት ለአንተም ሆነ ለማንም ሳትናገር ወደኮፈሌ ድንገት ብን ብላ ነው የሄደችው…ምክያቱም በማታውቀው ሰው ተደፍራ ነበር፡፡››
‹‹ምን? ማለት?››ዜናው ቤቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ የሚያደነዝዝ ነበር፡፡
‹‹አዎ እኛ ቤት የጁኒዬር የ19 ዓመት የልደት በዓል ዝግጅት ነበር…ትልቅ ድግስ ነበር…ወጣቶች ሲጠጡና ሲጨፍሩ ውለው ሲጨፍሩ ነበር ያመሹት…..እሷ ቤታችን እቤቷ ስለሆነ ጓዲያ ጎድጓዳውን ታውቀዋለች…ለሊት ሰባት ሰዓት አካባቢ ሁኔታው እንዴት እንደሆነ እና የለማና አየጠፋ ነገር እንዳለ ለማየት ከመኝታ ቤቴ ወጣሁና ሳሎን ሄጂ ነገሮችን ተመልክቼ ስመለስ ከእንግዳ ክፍሎች መካከል አንዱን ገርበብ ብሎ ተከፍቷል
..የሆነ ነገር ትኩረቴን ሳበውና ተጠግቼ ገፋ ሳደርገው ተከፈተ፡፡ አልጋው ላይ ከላይ ሰሎሜ ተዘርራ ተኝታ ነበር…በጣም እንደሰከረች ከሁኔታዋ ማየት ይቻላል..ቀሚሷ ወደላይ ተገልቦ ጭኗ ክፉኛ ተጋልጧል…፡፡መልሼ በራፉን ዘጋሁና ወደመኝታ ቤቴ ሄድኩ .የዛን ጊዜ ሳራ ያማት ስለነበረ ለብቻዋ ነበር የምትተኛው፡፡ከዛ የተጋለጠ ጭኖ ከህሊናዬ ሊጠፋ አልቻለም…ስጋለበጥ ከቆየው በኃላ ተመልሼ ሄድኩና ሰው በኮሪደር ላይ አለመኖሩን አረጋግጬ ወደክፍሉ ገባው፣ ከውስጥ ቀረቀርኩት መብራቱን አጠፋው… ከዛ በኃላ
ያለውን ዝርዝሩል ልነግራችሁ አልችልም…ብቻ ማን እንደደፈራት ባታውቅም መደፈራን ግን አውቃ ስለነበረ በብስጭትና በእፍረት በማግስቱ ከተማውን ለቃ ወደኮፈሌ እንደሄደች ሰማው…በእውነቱ ከፊቴ ዞር ስላለች እፎይ ነበር ያልኩት….ከሁለት ነው ከሶስት ወር በኃላ መልሳ መጣች….አሁንም ትንሽ ቆይታ መሄዷን ሳማው..ከዛ ማርገዞን እና ልታገባ መሆኑን ተወራ…ቀኑ ተጠብቆ አንቺ ተወለድሽ ..ቀኑን እስልቼ ስቆጥረው ትክክል ነበር ..የእኔ ልጅ መሆንሽን ባውቅም ለማንም መናገር የምችለው ነገር አልነበረም፡፡የዛን ቀን ልጄ ቀለበት ሊያስርላት መሆኑን ሲነግረኝ ግድ እሷን ከዛ ጋብቻ ላስቆም ብዬ የልጅሽ አባት ጎባና እንዳልሆነ ታውቂያለሽ አይደል?››ስላት
‹‹እኔስ አዎ እናት ስለሆንኩ አውቃለው..አንተ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?›› አለችኝ፡፡
‹‹እኔም አባት ስለሆንኩ ነው ላውቅ የቻልኩት ብዬ ታሪኩን በዝርዝር ስነግራት አበደች…በዛ እየተጨቃጨቅን እያለ ጁኒዬር ተመልሶ መጣ ..እንግዲህ ከጠጣችው መርዝ ጋር ከእኔ የሰማችው ዜና ምን ያህል አእምሮዋን እንደሚያስታት መገመት ቀላል ነው…እና እዚህ ዋናው ወንጀለኛ እኔ ነኝ…››
‹‹እና አንተ ..አባቴ…››አለም በተጎተተ ቃላት ከአደበቷ በግድ አወጣች፡፡
‹‹አዎ እኔ አባትሽ….ይሄንንም አሁን ወደእዚህ ከመጣሽ በኃላ በሚስጥር ሳታውቂ እኛ ቤት መጥተሸ የጠጣሽበትን ብርጭቆ በመውሰድ ዲኤንኤ በማሰራት አረጋግጬለው፡፡ እና…››ብሎ ሊቀጥል ሲል አለም ዥው ብላ በተቀመጠችበት እራሷን ስታ ወደኃላዋ ተዘረረች፡፡
‹‹ወይኔ ልጄን..አቶ ፍሰሀ ተስፈንጥሮ ስሯ ደርሶ ደገፋት….ጁኒዬር ተከተለው፡፡ገመዶ ግን ከአቶ ፍሰሀ በሰማው ነገር ደንዝዞ ሰውነቱ ሁሉ እየተንቀጠቀጠበት ነው…‹‹እጅህን ወደጎንህ ላክና ሽጉጥህን መዥረጥ አድርገህ ከአለም በስተቀር እዚህ ቤት ያሉትን ሀጥያተኞች ሁሉ ግንባር ግንባራቸውን በልና ከዛ ራስህንም ገላግለህ ለዚህች ሚስኪን ልጅ ፍትህ አስገኝላት›› የሚል ስሜት ይታናነቀው ነበር፡፡ወዲያው ከጎኑ የነበረችው ሳራ ልክ እንደአለም የሰማችውን ዜና መቋቋም አቅቷት እራሷን በመሳት ከመቀመጫዋ ተንሸራተተችና እላዩ ላይ ተዘረገፈችበት፡፡
✨ተፈፀመ✨

❤59👎27🤔11👍9🔥1
ዳግመኛ ለማናገር፣ ይቅርታ ለመጠየቅ ፊቷ መቆም ብፈልግም ፈራኋት። ሳያት የሆነ ሰው በደሌን ተነቅሶ፣ ነውሬን የሚለፍፍ ዓይነት ድብርት ይዳበለኛል። በቀን ብዛት ይሄ ስሜት ድል ይነሳል ብልም አልሆነም። ሁሌም ሳያት የሚሰማኝ ስሜት ትኩስ ድብርት ነው። እኔ ከሚሰማኝ ስሜት እሷን ስበድላት የተሰማት እና ከሚሰማት አይበልጥም ብዬ መደበቴን ታገልኩት። አንዳንድ ቀን ያበድኩት እኔ የበደለችኝ እሷ ብትሆን እያልኩ እስክመኝ ድረስ እረፍት አጣሁ። ትግሌ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ከሃኒቾ ጋር የነበረኝን ትዝታ፣ የበደልኳትን በደል፣ ፊት መንሳቷን፣ ለማምለጥ እሷም ትዝታዋም አይደርሱበትም ብዬ ወዳሰብኩት ቦታ ለሚስቴ አሳማኝ የሚመስል ሰበብ ደርድሬ ቤታችንን አከራይተን ያን ሰፈር ለቀን ሄድን።
በሽሽት የበዳይነት ሕመሜን ድል አደረገው ከሆነ አየዋለሁ!
🔘አድኀኖም ምትኩ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
በሽሽት የበዳይነት ሕመሜን ድል አደረገው ከሆነ አየዋለሁ!
🔘አድኀኖም ምትኩ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢39❤19👍2🔥1
#ውርስ_ሕይወት
አባቴ ለብዙ ዓመታት ታስሮ ነበር። አስራ አራት ዓመቴ አካባቢ ተፈታ፤ የተወለድኩት ያን ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፤ አባቴ ሲፈታ እኔም ተፈታሁ። አባቴ አስራ አራት ዓመት ድረስ ሳስብ የነበረውን ቀስ እያደረገ ዳመጠው።
አባቴ የላላ፣ የተቆጠበ ማኅበራዊ ግንኙነት ያለው፣ ረጋ፣ ጀንተል፣ ኮስተር ያለ ግለሰብ ነው። ብዙ ሰዓት ዝም ይላል፤ የስሜት መለዋወጥ አይታይበትም፤ ጺሙ በብዙ ሲያድግ በመቀስ በትንሹ ይከረክመዋል፤ ልብሶቹ፣ የሚጠቀምባቸው እቃዎች ስትር ያሉ ናቸው።
ከእስር እንደተፈታ እኖር ከነበረበት ከእናቴ ቤተሰቦች ቤት ወስዶ ተከራይቶ ከነበረው ሰፊ ግቢ ውስጥ መኖር ጀመርን።
ቤታችን ቅዝቅዝ ያለ ነው። ቅዝቅዝ ያለው ብዙ ወንድም እና እህት ስለሌለን ነው ወይስ እናት ስለሌለኝ ነው፣ አልያም ደግሞ አባቴ ከሰው ጋ በደማቁ ስለማይግባባ፤ ምክንያቱን እርግጠኛ ባልሆንም ውጤቱ ግን ቀዝቃዛ ሰፊ ትልቅ ግቢ ውስጥ ነው የኖርነው።
መቀዝቀዙ የገባኝ፣ በየአገጣሚ የትምርት ቤት ጓደኞቼ ጋ ቤታቸው ስሄድ ይሳሳቃሉ፣ ይጨቃጨቃሉ፣ ይካሰሳሉ፤ በዚህም እቀና ነበር። እጦታችን ያወቅነው ዕለት ጉድለት ይሰማን የለ?!
ስሜ ዋሲሁን ቢሆንም አባቴ ዋሴ ነው የሚለኝ፤ ምንም ነገር ሲያስደርገኝ ሆነ ሳደርግ አምኜበት እንዲሆን አድርጎ ሠርቶኛል። ከፍቶኝ ለምቦጬን ከዘረገፍኩ "ዋሴ ማኩረፍ የአቅመቢስነት ማሳያ ነው፤ መጀመርያ የከፋህን፣ ቅር ያለህን በእርጋታ አስረዳ" እያለ የውይይት ባሕል ልቤ ውስጥ እያኖረ ነው ያሳደገኝ።ያምንብኛል። እንደመታመን አበርቺ እጽ እንደሌለ ያወቅኩት ለራሴ ያለኝ በጎ እና የእችላለሁ ወኔ ከብዙ አቻዎቼ መለየቱን እና ምንጩን ስረዳ እና ሲገባኝ ነው።
በጨዋታ መሀል
“ይሄውልህ ዋሴ ሁልጊዜ እሮሮ የሚዘበዝቡ፣ ሁልጊዜ ሰው ማጣጣል ላይ የተመሰጡ ሰዎች፣ ሁልጊዜም አልተሳካልን ዓይነት ደረት የሚመቱ፤ ለውድቀታቸው ሰው የሚወቅሱ ሰዎች፣ ለመውደቃቸው ኃላፊነት ከማይወስዱ ጋ አትወዳጅ" ይላል።
ይሄ ሰውዬ ጓደኛ የሌለው ለውድቀታቸው ኃላፊነት የሚወስዱ አጥቶ ይሆን እላለሁ አንዳንዴ።
ደግሞ በሌላ ቀን እጅግ ብዙ ቆይቶ
“ዋሴ" ይላል። ልገልጸው የማልችለው አጠራር አለው። ሁሉም ሰው ዋሴ ብሎ ቢጠራኝም በእሱ ዓይነት መንገድ የሚጠራኝ ሰው አልገጠመኝም። የሆነ አለኝታዬ ዋስትናዬ የሚለኝ ነው የሚመስለኝ፤ እወድሃለሁ የሚለኝ በአጠራሩ ውስጥ ባለው ድምጸት በኩል ነው።
"ይሄውልህ ዋሴ ሰው አንተ ላይ ስለሚይዘው . አቋም እንዳትጨነቅ፤ ሰው ለማስደሰት ከዳከርክ የራስህ እውነት ሳይኖርህ ታልፋለህ" ይላል።
አባቴ ጥንቅቅ ያለ ሰውዬ ነው፤ ነፍስ እያወቅኩ ስሄድ ነው ለእሱ ያለኝ ፍቅር እና አክብሮት ያየለው።
ብዙ ዝም ስለሚል ሲያወራ ተስገብግቤ ነው የምሰማው፤ እጦትን የመሰለ ነገሮችን ተፈላጊ አድራጊ ያለ አይመስለኝም እኮ::
"ይሄውልህ ዋሴ"
ወዬ አባቴ
“ስንት ዓመት መቀመቅ ያወረደኝ ሐቀኝነቴ ነው፤ ኃላፊነቴን በአግባቡ ለመወጣት ስዳክር፤ ብልሹ ካልኩት አሠራር ጋ ስታገል፣ መደለያቸውን በጄ ስላላልኩ መቀመቅ ውስጥ ወረወሩኝ።
ብቻዬን ቆምኩ!
በእርግጥ እኔ ቆምኩ ልበል እንጂ ለብዙ ሰው ወድቄያለሁ፤ የወደቀ ከሚለው ጋ ማበር የሚፈልግ ማን አለ? ወደቀ ብለው ተዘባበቱብኝ፤ ስንት ዓመት ለመኖር ነው ግን እንዲህ የከፉት እላለሁ፤ ስለ ተቻለ ብቻ አሳማም ጅብም እንዴት ይኮናል?!
ይኸውልህ ዋሴ
ለእራስህ እውነተኛን መሆን የመሰለ የሕሊና እረፍት የለም፤ ከራስ ጋ ሰላም ከመሆን በላይ ምን ሽልማት አለ? ወድቋል ብለው ሲዘባበቱ እኔ ያልሠራሁት መጥፎ ተግባር ምቹ ትራስ ሆኖኝ ከሰላሜ ጋ ነበርኩ።
አንተ እንዲህ የምትወደኝ እኮ፣ አንተ እንዲህ የጎበዝክልኝ'ኮ ለእውነቴ የተሰጠኝ ሽልማት ነው፤ በዚህ ዕድሜ ጤነኛ የሆንኩት እኮ አምላክ ለመታመኔ የሰጠኝ ስጦታ ነው፤ ሰው ሽልማት ጥሬ ገንዘብ ብቻ ይመስለዋል" ይል'ና በስሱ እንደሁሌው ጥርሱን ገለጥ አድርጎ ፈገግ ይላል፤ አሳሳቁ ሞገስ አለው!!
“እኔን ያሳቀሉኝ እኮ በእስተርጅና የሚመታቸው ልጅ፣ የማይወዳቸው ልጅ ኖሯቸዋል፤ ያመኑት ክዷቸዋል፡፡
“እግዚሃር በሚደግሱት ዝክር የሚሸወድ መስሏቸዋል" እያለ አፉን በትንሹ ከፍቶ ጥርሱን እያሳየኝ ፈገግ ይላል።
አባቴ የሚለኝን ሁሉ እየሆነ ያሳየኝ መምህሬ ነው።
“ይኸውልህ ዋሴ ጥቃቅን ነገር ላይ አታተኩር፤ የምትኖርለት መርሕ ይኑርህ፤ እመቀመቅ ድረስ የምትሄድለት ሕልም እና መርሕ ይኑርህ።"
የሚኖርን እውነት ከመስማት በላይ ምን ሐሴት አለ??
ብቻዬን መቆም አስተምሮኝ፣ ጥቂት ቀን ታሞ ጥቂት ቀን አስታምሜው አለፈ። ብዙ ቆይቼ እስር ቤት ሳለ የጻፋቸውን ሐሳቦችን እና ገጠመኞቹን ሳነብ ከዕድሜዬ በላይ አበሰለኝ።
ሕይወቴ ላይ የብስለቱ ዳና ያረፈብኝ የአባቴ ልጅ እኔ ዋሴ ነኝ!!!

❤49👏19
#ሊያብብ_ሲል
ሱስ ሳይበላው፣ ሲጋራ መግዣ መለመን ሳይጀምር፤ ጉስቁልና ሳያፈዘው፤ ለልብሱ መቆሸሽ ደንታ ቢስ ከመሆኑ በፊት፤ ሰዎችም ሲጣራ ባልሰማ መሄድ ሳይጀምሩ፤ ቃል አባይ ከመሆኑ በፊት፤ ክብሬ ማለት ሳያቆም፤ ለትንሽ ለትልቁ መላክ ሳይጀምር በፊት… ቆንጆ፣ ተወዳጅ፣ ዘናጭ ነበር። ከጓደኞቹ በላይ ድምቅ ያለ ልጅ ነበር፤ ቆንጆ አማርጦ ይሰክስ ነበር፤ የጸጉሩን ፍሪዝ በመሰታወት አስር ጊዜ እያየ አስር ጊዜ ያስተካክል ነበር።
ሕልመኛ ነበር። እንደ ሁሉም ወጣት ሀብታም መሆን፤ አዋቂ መሆን፤ ቤተሰቦቹን የመርዳት ሕልም ነበረው። የተንሸዋረረ አራድነት አሳስቶት የለኮሳት ሲጋራ፤ ለሳቅ ብሎ የተጎነጫት አረቄ፣ ለሙድ ብሎ የቀነጠሳት የጫት ቅጠል ስትደጋገም አፈዘዘችው፤ ሕልሙን ወጣትነቱን ክብሩን አረገፈችው።
ማንም ብርቱ ነኝ ቢል ታግሎ የማያስመልሳትን ወጣትነቱን ለማያቀው ጣዖት እየሰዋት ነው።
ጥግ ላይ ተቀምጦ ዘመን ሂዶ ዘመን ፤ በመጣ ቁጥር የሚመጡ ለውጦችን ከዳር በትዝብት እየተመለከተ ጊዜው እንዴት ነው የሚሮጠው? የሚል ይመስለኛል።

❤14👍5🔥3
#ባል_ተመኘሁ
አስተዳደጌ ነው የገደለኝ። አስተዳደጌ መጠበቅ እና ማግኘት ነበረበት። አባቴ ሁሌ ቃል ይገባልኛል፣ የሆነ ነገር በጥሩ መልኩ ሳደርግ ይሸልመኛል፣ እናቴ የቤት ሥራ ስሠራ ታመሰግነኛለች፣ ትመርቀኛለች። በምስጋና እና በስጦታ ተንበሽብሼ ነው ያደግኩት፤ ለዛ ነው የጠበቅኩትን ሳጣ የምታመመው ብዬ ሁላ አውቃለሁ፤ ግን በእሱ ብቻም አይደለም!
የማያቸው ሮማንቲክ ፊልሞች እና የማነባቸው መጻሕፍት ናቸው፤ ከፍቅር የሚገኘውን ደስታ እና ሁኔታ ከሚገባው በላይ አጋነው፣ ከቅዱስ የማገኘውን ነገር ሁሉ ያሳነሱብኝ ብዬም አምኜ አውቃለሁ።
ግን እሱ ብቻ አይደለም!
ቅዱስ ራሱ ነው ፍቅረኛሞች እያለን አባቴን መስሎ እና ሆኖ ተንከባክቦ ኑሮ ስንጀምር እርግፍ አድርጎ ትቶኝ የተፈላጊነት ስሜቴን የገደለው።
ኖ በእሱ ብቻም አይደለም!
ገመናዬን፣ ሚስጥሬን፣ ስሜቴን ለሰው ስለማልናገር ነው መፍትሔ ያጣሁት፤ የማይቀለኝ! የሚያብከነክነኝ!
ግን ዋናው ምክንያት ይሄም አይደለም!
ራሴን ከዋናው የሕመሜ ምክንያት፣ የድባቴዬን ምንጭ ለራሴ አልነግር ብዬ ነው።
ቅዱስ አይፈልገኝም። ሲመጣ ባዶ ቤት ቢቆየው ቅር አይለውም። ለስሜቴ ደንታ የለውም። ቆይ ስንት ወራቶች ሞላን ወሲብ እንኳን ከፈጸምን? አልጋ ከለየን ስንት ጊዜ ሆነን? ስንቴ ተዘገጃጅቼ ሊወጣ ሲል፣ ሲገባም ላነሳሳው በሚል አጋጣሚ አስመስዬ ራቁቴን የታየሁት፣ ቀስቃሽ አለባበስ ስንቴ ነው የለበስኩት?
እሱ ግን አያየኝም።
እንዲያዝንልኝ ታመምኩ፤ ኡኡ ነደድኩ፣ ጠዘጠዘኝ፣ ወጋኝ አልኩ፤ ታከሚ ይላል እንጂ አይደነግጥም። ወጣ ብሎ ስልክ ረጅም ሰዓት ያወራል።
መሀላችን ያለው ችግር ቀላል ነው ብዬ አስመሰልኩ... እውነቱ ግን እሱ አይወደኝም።
በመጨረሻ አልፈለግነት ሲጫወትብኝ፣ የድሮ ቦይፍሬንዴ ጋ ሄጄ ተልከሰከስኩ!
እሰይ!! እንኳን ተልከሰከስኩ።
ለሴት ልጅ የአለመፈለግነት ስሜት፣ ለዛውም በእንክብካቤ ላደገች፤ ለዛውም ተለማምጦ፣ ልዕልቴ ናት ብሎ ላገባት፣ ለዛውም መፈለግ እና መውደድ ለምታውቅ ሴት የሚሰማትን የሕመም ስሜት የት ያውቀዋል?!
የምን ጉዝጓዝ፣ ሰበብ፣ ድሪቶ፣ ዝባዝንኬ ነው?!
አለመፈለግ ብቻውን ቀላል ነው?!
ብቻውን ትዳርን መፍታት ብቻ አማራጭ አድርጎ ማሰብ ቀላል ነው?
ብቻውን ወሲብ ማድረግ መፈለግ እና ባል እያለ በፍትወት መቸንከር ቀላል ነው?
ብቻውን ላወራው እየፈለግኩ፣ ስደውልለት ሳያነሳልኝ ሲቀር አያከብረኝም፣ ከምንም አይቆጥረኝም ዓይነት ስሜትስ ቀላል ነው?!
ብቻውን እንዲህ እለዋለሁ ብዬ የሰበሰብኩትን ዓረፍተ ነገር፣ እንዲያዝንልኝ ያጠናሁትን ንግግር፣ እንዲታረቀኝ ያጠራቀምኩትን ቃላት፣ እንዲሳሳልኝ ያከማቸሁትን ሰበብ፣ እንዲረዳኝ የተዘጋጀሁበትን ቃል ፊት ነስቶ ሲያጠፋብኝ ስሜቱ ልብ አይሰብርም??!
ከድሮ ቦይፍሬንዴ ጋር ተንገብግበን፣ ተጠማጥመን ተዋሰብን። ቆንጆ ነኝ ወይ ስለው "ከድሮ በበለጠ” እያለኝ፤ ምኔን ትወድልኛለህ ስለው እያንዳንዱ አካሌን . እየሳመ እያሳየኝ። እየተዟዟርን፣ ቦታ እያማረጥን ተዋሰብን።
ደስስስ አለኝ!!
ለመለምኩ! እየጠወለግኩኝ ነበር።
ያደረግኩት ተግባር ለሌላው፣ ለመንገደኛው፣ ለመርሕ ሰው ሁሉ፣ ለጨዋው ሁሉ፣ ለአማኙ ሁሉ፣ ከዳር ሆኖ ላየኝ ሁሉ፣ ለፈራጅ ሁሉ፣ ለሌባው ሳይቀር ዝሙት ነው!.
ወሲብ ውስጥ ያለውን እፈልግሻለሁ፣ ታምሪያለሽ፣ እወድሻለሁ ሽንገላን መስማት ናፍቆኝ ነበር።
አመሰግንሃለሁ ብዬ አንገቱ ውስጥ ተወሽቄ ሳምኩት። ስለተኛኸኝ አመሰግናለሁ ይባላል? ትዳሬ ላይ ከባለግኩኝ በኋላ ማመስገን ነበረብኝ?
እኔ ግን አመሰገንኩት!
ተሰናብቼው ሳይመሽብኝ ወደ ቤቴ ፈጠን ፈጠን እያልኩ መሄድ ጀመርኩ፤ ቀስ እያልኩ ፍጥነቴን ቀነስኩ፤ እዛ ዱካክ፣ አልፈለግነት የሚበላኝ ቤት መሄድ ፈራሁ። የማይፈልገኝን ባሌን ማየት ሲዖልን የማየት ዓይነት ሆነብኝ፣ የማይናፍቀኝን፣ የማይንከባከበኝ ባሌ ያለበት ቤት መሄድ ጠላሁ፣ ወስልቼበት እንኳን ጸጸት ያልተሰማኝ ባሌ ጋ መሄድ አስጠላኝ።
ለመጀመርያ ጊዜ ልቤን ሰማሁት።
ከእኔ ካልሆነ ሰው ጋር እንድተኛ ያደረገኝ ሰውዬ ጋ ምን አደርጋለሁ??
መሳም እስክናፍቅ ድረስ የገፋኝን፣ መታቀፍን ብርቅ ያደረገብኝን፣ መወደድ እንደሚገባኝ ያሰረሳኝ ሰው ጋ ምን አደርጋለሁ?!
ምን አጠፋሁ? ይቅርታ ለማለት፣ ምን ላድርግልህ እንድለው ትንሽዬ እንኳን ፊት የማይሰጠኝ ሰው ጋ ለመኖር ለምን ወደኋላ ተመለስኩ።

❤38👍4😢1
#ምሶሶ_እና_ማገር
ሸክሜን ሳላስተያየው፣ ፍላጎቴን ቸል እያልኩ ከኔ በቀር ማን አለው ለምለው ቤተሰቤ ስል ፍላጎቴን አቀዝቅዤ መናገር የምፈለገውን ሁሉ ሳልናገር እንደ ጓደኞቼ ፋሽን ልከትል ሳልል ኑሮን ለማሸነፍ ስለምባትል ...
የቤታችን ምሶሶ እኔ ነኝ ባይ ነበረኩ!!
ድንገት እናቴ በአስር ቀን ሕመም ተለየችን። ቤታችን በፍጥነት ቀዘቀዘ።
እናታችን የአባቴን ስኳር፣ ደምብዛት እና ኮሌስትሮሉን ያማከለ ምግብ አቀናብራ አቅራቢ ነበረች። ተኝቶ ሳለ ከውጪ ሆነ ከቤት ውስጥ የሚረብሽ የመሰላት ድምጽ ከተተነፈሰ ቀስስ ቀስ ገረመው ተኝቷል ትላለች ድምጿን ለምልክት በቀረበ ማንሻካሾክ። አባታችንም እንዳይረበሽ ድምጽ ቀንስ ለምትለውም ሰው እንዳይቀየም እየተጨነቀች። አባታችን እናታችን ከሌለች ቤት ውስጥ ያገኘውን ሰው 'አልሚ የት ሄዳ ነው? በቃ አንዴ ከወጣች አትመለስም?' እያለ በስሱ ይነጫነጫል። ምቾቱ ሲሰወርበት ማን ዝም ይላል?
የታናሽ ወንድሜ ሱስ ያመጣበትን ግትልትል ብልግና የምትደበቅለት፣ የምትሸሽግለት፣ ብላ እንጂ ገንዘብ የለህ እንደው አንዱ ቦታ ገባ ብለህ የምትጎርስበት፤ እነዛ ጓደኞች እንደሆኑ ሊያጠጡህ ነው የሚፈልጉህ... ደግሞ ሰውነትህ እየቀነሰ ነው... ወይ እንደ ጎረምሳ ጎረስ ጎረስ አድርገህ አትበላ፣ በየትኛው አንጀትህ መጠጡን እንደምትችለው... እያለች ሳትሰለች ግሳጼ እና ምክር እያቀላቀለች ትኩረቷን የማትነግፈው፣ የምትቆረቆርለት፣ ከብልግናው መሀል መልካምነትን አነፍንፋ የምትመሰክርለት እሷ ብቻ ናት።
“ምዕራፌ እኛን እኛን እያልሽ ራስሽን አየበደልሽ እኮ ነው። ጸጉርሽን ተሰሪ እንጂ ደግሞ አማረልኝ እያልሽ ትጎምጂው እና ትጣይኛለሸ! ሴት ልጅ ጸጉሯ ነው ውበቷ..."
ውጪ ስትንገላታ ነው የምትውለው እያለች ታቀብጠኛለች፣ ትመክረኛለች፣ ገመናዬን ትሰማኛለች፣ ትገስጸኛለች፣ ጠዋት ማታ መግባት እና መውጣቴን፣ ሁኔታዬን፣” ገጼን፣ እንቅስሰቃሴን ትከታተላለች።
አደራህን ጌታዬ ከልጆቼ በፊት አድረገኝ፣ የልጅ ሐዘን አታሳየኝ፤ ከጓደኛ በታች አታውላቸው፣ ከክፉ ነገር ጋርዳቸው፤ ለኔ ያደረከውን ለማን አደረክ? ተመስገን፤ ተመስገን አያለች ስታጉተመትም ለሚሰማት ከአምላኳ ጋር የምታወራ አትመስልም፤ ከወዳጇ ጋር እንጂ!! በርግጥ ለታመነ ካምላክ በላይ ወዳጅ ማን አለ!
ምዕራፌ በርቺልን፣ ካላንቺ ማን አለን? አያለች መኖርያ ምክንያት ትለግሰኛለች። ለመመረቅ ሽራፊ. ምክንያት የምትፈልግ ይመስል ላደረኩት ትንሽ ነገር ስትመርቀኝ ትውላለች።
ለውሻችን ቦቸራ እንኳን በሰዓቱ ምግብ የምትወረውርለት፤ አሞታል እንዴ? ፈዘዘሳ ብላ የምታስተውለው እናቴ ብቻ ናት።
ዘመዶቻችን እንዲመጡ ወትዋች፣ ጠፋችሁ ብላ ወቃሽ፤ ሲመጡ ተንከባካቢ፤ ካልበላችሁ፣ ካልጨመራችሁ፣ ካልቆያችሁ፣ ካላደራችሁ እያለች የምትለማመጥ፤ ሰፈራችን ውስጥ ለቅሶ ሲኖር፣ ሰርግ ሲሰረግ፣ ዝክር ሲዘከር ግንባር ቀደም አጋዥና አድማቂ እናታችን ናት። ለሚውል መዋል፣ ለደግ ደግ መሆን ስለማይከብድ ቤታችን ጉዳይ ሲኖር የሚያግዘን፣ ስንታመም የሚጠይቀን፣ መንገድ ላይ ሰላምተኛችን ብዙ ነው።
ስናጣት ልካችን ተገለጠልን!! እንዴት ይሄን ሁሉ ስትሸከም በዚህ መጠን አላስተዋልኳትም? ተሸክሞ ሸክምን አለማሳየት ምን ዓይነት ጥበብ ነው?? እናቴን ያሳረፍኳት መስሎኝ ነበር፤ ለካ አሳርፋኝ ነው።
እናቴ ስንት ቀን ፍቅሯ እውነቷን ሲያስደብቃት፤ በድዬ ለእኔ ስታደላ አይቻታለሁ። ልጅ ሳለሁ በንዴት ከገረፈችኝ በኋላ ሲቃ እየተናነቀኝ ጉያዋ ስወሸቅ፣ ተንሰፍስፋ ያባበለችኝ ዕለት ትውስታ ልቤ ውስጥ አለ።
ድከመቴን የማታጎላብኝ፤ መውደዷ · የማይወላውል፣ እንደምወዳት ማስረጃ የማታስስ፤ ተዝረክርኬ ዝንጥ እንዳልኩ የምታሰማኝ፤ ሕመሜ የሚያማት፤ ስኬቴ ከሁሉ በላይ የሚያስፈነድቃት፣ ነገሬን ሁሉ ጉዳዬ ነው የምትል፤ እንደምወደድ እስትንፋሴ ዓለም ላይ ካረፈ ጀምሮ እያሳየች
የመሰከረችልኝ። እምወደድ እንደሆንኩ ልቤ ላይዐያሰረጸችልኝ፤ መወደድን የሚያክል ምንም በረከት እንደሌለ በምርቃት እና በጸሎቷ ያሰማችኝ።
ጥንካሬዋን ፈተና የማይበግረው፣ በደል ሆነ መከፋት የማይሽረሽረው፤ ትሕትና የተላበሰች፣ በየቀኑ ስለ ልጇ ከአምላኳ ጋ የምታወራ አመስጋኝ፣ ስጉ : ፍጥረት : ናት። እስክንጠግብ የማይርባት፤ አሟት በድካም የምታሳብብ፤ እየረገመችን የምትጸልይልን፣ አንደበቷ ከእውነቷ ጋ የማይገጣጠም ድብቅ ፍጡር ናት። ፍላጎቷን አሽሻ፣ የምትፈልገውን አጣጥላ ለምንወድው ነገር ፍላጎቷን የሰዋች፣ ለልጆቿ ቸር፣ ለራሷ ስስታም ናት።
የልጇን ፊት እንደ ዳዊት ዘወትር የምታነብ፤ ስትናፍቅ፣ ስናረፍድ በስጋት የምትቃዥ እናት፤ የፍጡር ፍቅር ጥግ ናት።
ዋርካችን ሲገነደስ የከለለልን ገበና ገለጠን!
ሞቷ ከእንባ በላይ ነው። አልቅሼ ላውጣው ብል አይወጣም። አንዳንድ ጊዜ አጠገቤ ያለች ይመስለኛል፤ ባትመልስልኝም የልቤን እንዲህ እያልኩ አወራታለሁ።
ለምን የሚወዱሽ ሲያለቅሱ፣ ደረታቸው ሲደቁ፣ ጸጉራቸውን ሲነጩ ዝም ብዬ ፈዝዤ ተመለከትኳቸው? አቅፈውኝ፣ አዝነውልኝ፣ እያለቀሱ ሲያባብሉኝ ለምን ደነዘዝኩኝ?
ግድ የለም አብሬሽ ሞቼ ነው የሚሆነው። አብሬሽ ሞቼ ባይሆን ድንኳኑ ውስጥ ወዳጅ አዝማድ ተስብስቦ ሲጨዋወት፣ ሲያጽናና እኔ ለምን ብቻዬን ዲዳ ሆንኩኝ?
አብሬሽ ሞቼ ባይሆን
የሚቀርበኝ ጉድሽ ፈላ እያለ ሲመለከተኝ፤ በርቺ አይዞሽ እያለ ማጽናኛ የቃላት ጋጋታ ሲያንጋጋ እንዴት በዚህ ሁሉ መሀል የእንባ ቋቴ አልተረታም? ከሩቅ፣ ከቅርብ ቀዬ ሐዘኔን በአካል ሊጋሩኝ መጥተው አይኔን እያዩ ሲያጨዋውቱኝ፤ ሊያበረቱኝ ሲታገሉ እንዴት ሆድ አይብሰኝም?
አብሬሽ ሞቼ ባይሆን
ቆሌ፣ ቅስሜ፣ ደመነፍሴ፣ ትውስታዬ፣ መጓጓቴ፣ ሕልሜ አብሮ ከአንቺ ጋ ባይቀበር እንዳሁኑ መች እሆን ነበር?
ከዚህ በኋላ አለመኖርሽ አንዴት አያባባኝም?
አንቺ ሞተሽ እኔ አብሬሽ ሞቼ ባይሆን አንድ ዘለላ እንባ እንዴት አልወጣኝም?
ይሁን ሁሉም... አብሬሽ ሞቼ ባይሆን ለምን ምሳዬ አይርበኝም? እንደሁሌው ውሃ ጥሜ ለምን አይታወቀኝም? ቆይ እሺ ለምን አትናፍቂኝም? አብሬሽ ሞቼ ባይሆን፣ ዋርካዬ ሲገነደስ እንዴት ዝም እላለሁ?
ነገሩ ምሰሶው ሲወድቅ ነው ማገር ማንነቱን የሚያውቀው።

❤23😢16👍1
“ምድር ከሰጠችኝ ገጸ በረከት እሷ ዋነኛዋ ነች። ምድር ላይ መቆየት ካማረኝ የሚያምረኝ በእሷ ምክንያት ነው። የሕይወት ተጋድሎዬን ያህል ነው ትርጉም የምትሰጠኝ፤ በዚህ በዝባዥ ስርዓት፣ በእዚህ አምባገነን ስርዓት፤ ሕዝብ ከቁጥር በቀር ትርጉም በማይሰጠው ይህን በዝባዥ አገዛዝ እታገለው ዘንድ እሷ የምትሰጠኝ ተስፋ እና ፍቅር ግዙፍ ነው።
'Socialism እና Karl Marx' እንደማይነጣጠሉ ሁሉ የኖረኝ ክብር እና ዝና ከእሷ ከሚስቴ ጋር ሊነጣጠል እና ካለ እሷ የሚቻል አልነበረም። አይኔን አይታ የምትታዘዘኝ እና የምታዝንልኝ የእኩለ ሌሊት ብርሃኔ እሷ ናት።
እሷ ጠይም የደስታ መግቢያ በሬ ናት። እሷ ሳትኖረኝ ምንስ ቢኖረኝ ምን ያደርግልኛል? ስንት ቀን እሱን ያየ፤ ከእሱ ጋ የቆመ እንደሎጥ ሚስት የጨው ሐውልት ይሆናል ተብሎ ታውጆ እንኳን ምን ቢመጣ ካላንተ ስሆን ከሚሰማኝ አይበልጥም ብላ አብራኝ ነበረች፤ ስንቴስ መቀመቅ ሲያወርዱኝ ከእሷ በቀር ማን አብሮኝ ቆመ?
እሷ የነፍስ ምግብ ጸዳሌ ናት። ምንም ብሆን፤ ምንም ባጣ የማይደንቀኝ ልበ ደንዳና እንደሆንኩ ያለፍኩበት ጨለማ ይመሰክራል፤ እሷ ብቻ ከእኔ ጋ ትሁንልኝ እንጂ።
እሷ ከቀደመችብኝ ያን ዕለት ነው ኩራባቸው መንፈሱ የሚታወከው፤ እሷ ካለችማ ኩራባቸው ልቡ ላይ ሐሴት እንደተመላለሰ የተሰፈረለትን ዘመን ይጨርሳል ..
እሷ የልቤ ብርሃን ናት። ግፍን እቋቋም ዘንድ የተቸረችኝ ጫንቃዬ ናት፤ በንፅሕና ከእውነት ጋ እንድቆም፤ አቋሜ እንዳይሸረሸር፤ መንገዴን፣ አቋሜን በፍቅር ከመንገዴ እንዳልሰናከል በትልቁ አቅም ሆናኛለች።
በጠላት፣ በአሰናካይ፣ በቀለብተኛ ተከብቤ : ሳለሁ እንዳላፈገፍግ የምታበረታኝ የደስታዬ ፍላጽ መዓዙን የዓላማዬ ያህል ነው የምወዳት... ይላል። .
ሌላ ገጽ ገለጥኩ
'I will not quit until I make my dreams come true. tius. ኣ"ደምን እንደምን ድምጽ ለመሆን መጥቼ ዝም እላለሁ?
በዜጎች መሀል ግጭትን የሚቸረችር አገዛዝ፤ የማንነታችንን ግንብ የሚሸረሸር ትርክት የሚያንሸረሽሩ ቀለብተኞች ባሉበት፤ ግፍ ባራኪ፣ ሞራል አልባ አሸከር፣ ፈሪ፣ መርሕ አልባ አለቅላቂ ልሒቃን በተሰባሰቡበት ምድር ተገኝቼ እስክሞት ዝም አልልም። ደግሞስ ላለመሞት አልመጣሁ፣ ይግደሉኝ እንጂ መቼም እንደማልደለል እኔም፣ መዓዙም፣ እነሱም ያውቃሉ።
እኔ ኩራባቸው ዓለሙ አገር እንድታብብ ከማለም በቀር፤ መነሻ አልባ ትርክት ከማጋለጥ በቀር አንድም ስውር ሕልም እና ግብ ኖሮኝ እንደማያውቅ የልቤን እውነት የምታውቀው መዓዚ እና ሕያው አምላኬ ምስክር ነው እንጂማ ስንቴ በስልጣን ሊደልሉኝ ታከውኝ የለ! እንጂማ በጉቦ ሊጥሉኝስ አላሴሩም? እኔ ኩራባቸው ሳንቲም ግድ የሚሰጠኝ መስሏቸው… ሃሃሃሃሃ የሚታገሉትን ኩራባቸውን አያውቁትም ::
ሌላ ገጽ ገለጥኩ
“አንቺ ግዙፍ ሕልሜን የምታክይ፤ አይበገሬው ልቤን የበገርሽ፣ ኮስታራ ግንባሬን ገንብረሽ ለፈገግታ የራቀውን ፊቴን የምታፈኪ ሚስቴ ሆይ የሕይወት ዘመን ንዑዴ ነሽ። በትንሽ ቀልድ፣ በትንሽ ጨዋታ የምትደሰችልኝ፤ በወደኩበት
በታመምኩበት በታሰርኩበት ሰው ሁሉ ፈርቶ ከእኔ ሲርቅ፣ ከእኔ ጋ ላለመተያየት ሲደበቀኝ በኩራት ፈቅደሽ መርጠሽ ከእኔ ጋ የሆንሽ የእኔ መዓዚ ሕልሜን ልቤ ውስጥ ካስቀመጠው በረከቴ እኩል ባንቺም ተባርኬያለሁ። ባንቺ ምክንያት የምድር ቆይታዬ ከሕልሜ ያላስበለጥኩት የእኔን ያህል መርሄን ስለምትወጅልኝ መስሎኝ...
ጽሑፎቹ እንኳን ለጉዳዩ ባለቤት ለማንም መንገደኛ ትርጉም ይሰጣሉ፤ አጀንዳውን ከተቀመጠበት አኖርኩት፡፡
ጋሼ ታዋቂ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ፣ መንግሥት እንቅስቃሴውን የሚያጠናው፣ መንግሥትም ሆነ መንግሥት የሚቃወሙ አካላት በዛቻ እና በንዋይ ሊደልሉት እንደሚሞክሩ በርካታ ጸሐፊያን በማስረጃ ከትበው አንብቤያለሁ፡፡ እንዲህ እየወደዳት፣ እንዲህ እየተመካባት፣ እንዲህ እየተንሰፈሰፈላት ሲቀጭባት፣ ሜዳ ላይ ሲሞትባት የገዳዩን ማንነት ከመላምት በቀር ገላጭ ሲጠፋ አረቄ ውስጥ ባትደበቅ ከማዘን ውጪ ማጠንከሪያ አቅም እና ሞራል ከየት በኩል ይወለዳል?
ብዙ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ሰዎች ስለ ኩራባቸው ዓለሙ ቃለ መጠይቅ እንድትሰጥ ይለምኗታል። አንድም ቀን ግን እሽ ብላ አታውቅም። አንድ ዕለት ስለ ሌላ የባጥ የቆጡን እያወራሁ ሳለ ...
እኔ የምልሽ አታቲ ለምንድን ነው ግን ስለ ጋሼ ምስክርነት፣ እውነት እና የሕይወት ዘመን እንቅስቃሴው የማትናገሪው? ካንቺ በቀርስ ስለሱ ሊያወራ የሚችል ማን ይኖራል? አልኳት...
አታቲ አይኗን ቦዘዝ አድርጋ ጠረጴዛው ላይ ከተቀመጠው ትልቅ ጉርድ ፎቶ ላይ በትካዜ ተክላ
“ይሄውልሽ ዕድሌ ኩራባቸው ምስክርነት አያስፈልገውም። የራሱን ሐውልት ገንብቶ ነው ያለፈው፤ ስለ እሱ ከሥራዎቹ በላይ መናገር የሚቻለው አንድም የለም። ሥራዎቹን መመርመር እና ሥራዎቹን መሞገት ይችላሉ፤ ሕልሙን ጽፎ
አቋሙን ተንትኖ ታግሎ የተሰዋ ሕያው ነው፡፡ ከጻፈው ውጭ የምናገረው፣ ማለት ፈልጎ ያላለው አንድም እውነት የለውም። ከእኔ ጋ ያሳለፍነውን በየሜዳው፣ በየስፍራው ለማንም አላወራም፤ ይነፍስበታል፣ ይቀልብኛል፤ ቀስ እያልኩ እየተረኩ እያዋዛው፣ እያስታወስኩ ራሴ ጋ የማስቀምጠው የሕይወት ዶሴዬ ነው..."
አታቲ ትንሽ ስትቀማምስ ጀግና እንዳላገባ የምትመክረኝ ምክሯ አልሠራም። ከቢልልኝ ጋ ተፋቀርን፤ ቢልልኝ እውነት፣ ከስሜትም፣ ከፍቅርም ይበልጣል የሚል የዘመኑ የማይናወጥ ጀግና ነው።
አታቲ ሞቅ ባላት ቁጥር “ጀግና እንዳትወጂ” ብትለኝም ልቤ ግን ጀግና፣ ባለ ራዕይ፣ ትጉህ እያየ ስላደገ ጀግና ከማፍቀር የታደገው የለም።
ቢልልኝ ኩራባቸው ዓለሙ አሳዳጊ አባቴ እንደሆነ ሲያውቅ የተሰማው ሐሴት ልዩ ነበር። የሰው ማንነት፣ እውነት የተወሸቀው እያየ ባደገው የተበጃጀ ፍጡር ነው ስለሚል የደስታው ምክንያት አልጠፋኝም።
ቢልልኝን አንድ አርብ ዕለት አመሻሽ ላይ ከአታቲ ጋር አስተዋወቅኳቸው። በጋራ እየተጫወትን ሳለ ጨዋታችን ሀገር፤ ትግል፤ እውነት፤ ታሪክ ሆነ። አታቲ የቢልልኝ ሐተታ ምቾት የሰጣት አልመሰለኝም። ስትሰማው ቆየች እና ተቆርቆሪነትህ እና አቋምህ ዋጋ እንደሚያስከፍል ታውቃለህ አይደል? አለችው በፍጹም እናትነት በስስት እያየችው።
ቢልልኝ ትንሽ ዝም ካለ በኋላ እኔ እንደምጠራት “አታቲ" አላት ፊቷ ሐዘን እንደተላበሰ በቀጥልልኝ ዓይነት አየችው
"ክብር አይደለምን ለሚያማኑበት ጉዳይ ዋጋ መክፈል?” ኣላት። ትክዝ ብላ እኔንም እሱንም አፈራርቃ ካየችን በኋላ አቅም አልባነት ፊት እያሳየችን መርዶ እንደሰማ ሰው በእንባ ታጅባ “አዬ መረገሜ” አለች፡፡

❤43
#እንባ_አዳሽ_ነፍሶች
አብረውኝ ከሚሰሩት ለየት ይልብኛል፤ ግሬይ፣ አመድማ፣ ሽሮ ከለር ልብሶች ያዘወትራል። አይዘንጥም፣ ጸጉሩን ስለማይንከባከብ የብርድልብስ ብናኝ በተለይ ጠዋት ላይ ከጸጉሩ አይጠፋም። ጺሙን በቶሎ አያነሳውም፣ ከሰው ጋ አይተራረብም፣ ሰው ሲተረብም አይስቅም። ፖለቲካ ይከታተላል፣ አንባቢ ነው፤ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅን ይወደዋል፤ ጆን ሎክን ይተነትናል፤ አረቄ ነፍሱ ነው።
አንዳንድ ጠዋት የተመሳቀለ ፊት ይዞ ይመጣል። ፊቱ አልኮል ያመሳቀለው ይመስለኛል። ስለ ራሱ አያብራራም፣ ሰው እሱ ላይ ሰለሚይዘው አቋም አይጨንቀውም።
የሚረዳው የለም ብዬ ዋስ ጠበቃ ለመሆን እጋጋጣለሁ፣ ግን ነገሮችን ስለሚመረምር ለራሱ አያንስም።
ሲያወራ፣ ሲሰማ፣ ሐሳብ ሲሰጥ ጥድፍ ጥድፍ አይልም። የዋዛ አንቅስቃሴዎቹ ላይ እንኳን እመለከታለሁ። አስተውሎትን
ሰኞ ዕለት ያሳደገው፣ ያስተማረው አንድ ወንድሙ በመኪና አደጋ ሞተበት። የቢሮ ሰዎች ተሰባስበን ቀብር ላይ ተገኘን። ብሩክ ፍልስፍናው፣ መጀናተሉ ቀሰስ ማለቱ ከእሱ በኖ ጠፋ። መሬት እየተንከባለለ ሲያለቅስ ሳየው አንጀቴ ተንሰፈሰፈ። እንባዬ አካላቴን ሳላወናጭፍ፣ ድምጽ ሳላወጣ ወለል እያለ ወረደ። ብሩክ አቅም አልባነት ሲያጥመለምለው፣ ለብዙ ሰው አለኝታ የነበረውም ወንድሙ ተጀቡኖ ወደ ጉድጎድ ሲወረወር ከንቱነት በላኝ።
በነጋታው ጠዋት ከእነ ዱካኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ተጣጥቤ፣ ቁርሴን በልቼ ከሥራ መልስ ብሩክ ጋ ለመሄድ ጥቁር ሻርፔን ቦርሳዬ ውስጥ ከትቼ ወደ ቢሮዬ ሄድኩ።
አይኔን አላመንኩትም፤ ብሩክ ወንበሩ ላይ ፋይል ከምሮ አንገቱን ደፍቶ ይሠራል። ሳየው ደነገጥኩ፤ በደመ ነፍሴ ብሩኬ ስለው ኮስተር እንዳለ በማያቀርብ አስተያየት እያየኝ "ሰላም ሊዲያ” አለኝ።
ሁላችንንም ፊት ነሳን። በሌሊት ሥራ ይገባል፣ አምሽቶ ይወጣል፣ ምሳ ብቻውን ይበላል። አይኑ አባብጦ እንባ ያሸበረው ፊት አይበታለሁ፤ ማንም እንዳያጽናናው መንገዱን ዘጋጋው። አለቃችን እንኳን በረታህ ብሎ ሲጀምር አዎ ይልና ከአጠገቡ እብስ ይላል፣ ወይ ደግሞ ወሬ ይቀይራል።
ወንድሙ ካለፈ በአስራ አራተኛው ቀን ላይ ብሩኬ ደህና ነህ? ግን ምነው እራቅከኝ? አልኩት።
"ትንሽ ቀን ነው የምፈልገው ደህና እሆናለሁ፤ ሁሉም ደህና ይሆናል" ብሎኝ ጭጭ አለ።
በቅጡ አንዳላጽናናህ እኮ መንገዱን ዘጋኸው፤ : ሰው በሚያስፈልግህ ጊዜ ነው ከሰው የራቅከው አልኩት። አየኝ፣ አጎነበሰ ቀስ ብሎ ቀና ብሎ እያየኝ ከትንሽ ዝምታ በኋላ...
“ይሄውልሽ ሊዱ ማጽናኛችን የጎደፈ ነው፤ አንዳንዱ ቤትሽ የሚመጣው ለወጉ ነው፤ አይኑ ላይ ምንም እንባ ሳይታይ ወንድሜ፣ ወንድሜ እያለ ድንኳን ውስጥ ይገባል። አጠገብሽ ይመጣና ምን አገኘው? ገጪው ተያዘን ወንድሜ፣ ሰላምተኛዬ፣ ጥሩ ሰው፣ መከታዬ ይላል። ሐኪም ቤት አልወሰዳችሁትም? ጥያቄ በጥያቄ። የሚያስቆጭ፣ ሐዘን የሚፈጥር ጥያቄ፣ የሚያጎላ ጥያቄ። እንዳልታዘበው፣ እንዳልቀየመው ሐዘንህን መጥቻለሁ ፊቶች፣ ፊታቸውን ለማሳየት የሚጋጋጡ ሰዎችን ጋቢ ለብሶ መታዘብ ሕመም ነው።
በጣም ከባድ ነው ሊዱ፤ ሁሉም የሚጽናናበት መንገድ ሊሆን ይችላል እኔ ግን አልቻልኩም፤ የአጽናኞቼን መንገድ የዘጋጋሁት ሆን ብዬ ነው። ለማጽናናት ስለጉዳዩ ማተት የግድ አይደለም እኮ፤ አብሮ መሆን በቂ ነው፤ ማቀፍ በቂ ነው። ጊዜ ኃያል ነው፤ የማያዶለዱመው ሕመም የለም።
ወንድሜ ጋሽዬ ለእኔ ብዙ ነበር። እሱ ነው ያሳደገኝ፤ የምምለው እንኳን በእሱ አይደል? ለቁም ነገር እንድደርሰ ያልሆነልኝ አልነበረም፤ ኃላፊነቱ ነበርኩ፤ የበኩር ልጄ ነው የሚለኝን ወንድሜን ነው ያጣሁት።
ጉዳዬ ከእግዜር ጋ ነው።
እሱ ነው የተመሳቀለውን እጦቴን በመልክ በመልኩ በእግዜርኛ የሚያበጃጅልኝ፤ እንጂማ በፍጡር ሊያውም ማብሸቅ በሚመስል ማጽናኛ አልድንም። ለዚህ ነው ከቀብር ጀምሮ ቤተክርስትያን የማድረው። ከአማኝ ጥቅማጥቅማችን አንደኛው ከአቅማችን በላይ የሆነ ሁነት ሲጋረጥብን እግዜርላይ ሙጥኝ ማለት አይደል? ከትናንት ዛሬ በደንብ እየበረታሁ ነው፤ የታመንኩት አምላክ እያጽናናኝ እያጸናኝም ነው።"
የብሩኬ አወራር፣ ሁኔታው፣ ሕመሙ አንጀቴን አላወሰው። አይኔ ላይ ያቀረረው እንባ አለመውረድ አልቻለም። አንድ ነገር ብቻ አልኩት
እግዜር ያበርታህ ወዳጄ።

❤19👏17😢4