#የደም_ቀን #የካቲት_12 ፡
፡
አገር ተቃጠለ ፣
እሳተ ጎመራ ወረደ ከሰለ፣
ጭስ አመድ አዋራ ሰማዪን ሸፈነው ፣
ጥቁር ሰማይ ጥቁር !
ሸፈነው ጨለማ በሞት በእናት ቅድስት ሃገር፣
በጀግናው ህዝብ ላይ የጠላት ግፍ ቀንበር፣
ፋሺስት አስተጋባ ፋስ ተሰነዘረ ፣
ባካፋ መዶሻ ህዝቡ ተወገረ፣
የሰው ጭንቅላት ኳስ
አባቶች ታረዱ፣
እናቶች ታረዱ፣
ቤት ንብረት ፈረሰ ከብቶቹ ተነዱ፣
ዓለም መና ቀረ .. ...
🔘በገብረክስቶስ ደስታ
🔘