አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አንድ ሰዓት የቤቱ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ጠባቧን ሳሎን ሞሏት…መጨረሻ ላይ የመጣው ፊራኦል ነበር…በእጁ አንድ ኪሎ ሙዝ ይዞ ነበር፡፡
ለሊሴ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከእጁ መንጭቃ ተቀበለችው እና‹‹..ወንድሜ ሙዝ ገዛኸልኝ….!!! ደሞዝ ደረሰ እንዴ?››ስትል በፈገግታ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ እንደምታውቂው ቀኑ ገና 18 ነው….በ18 ደግሞ ደሞዝ የለም…ስለዚህ ሙዙ ላንቺ አይደለም››ሲል መለሰላት፡፡

ለሊሴ ግራ ገብቷት‹‹ እና››ስትል አይኖቾን በማፍጠጥ ጠየቀችው፡፡
‹‹ለበሽተኛዋ ማለቴ… ለእንግዳዋ ነው››ሲል ያልጠበቀችውን መልስ ሰጣት፡፡

‹‹እ ነው…እሺ…››አለችና ፔስታሉን ወደበፀሎት ወስዳ ስሯ አስቀመጠችላት…፡፡

በሳቅና በጫወታ በደመቀ ምሽታ እራት ተበላ… ቡና ተፈልቶ ተጠጣ….ከጓዲያ የተጠቀለለ የጥጥ ፍራሽ ወጣና ወንበሮቹ ተሰብስበው ከእሷ ጎን ተነጠፈ…ለሊሴ ከጎኗ በተነጠፈው የጥጥ ፍራሽ ላይ ስትተኛ ፊራኦል ደግሞ ከእነሱ ራቅ ብሎ ግድግዳውን ተደግፎ ካለ አሮጌ ሶፋ ላይ አንድ አልጋ ልብስ ተከናንቦ ተኛ…
‹‹ለሊሴ ታዲያ ስትበራገጂ እግሯን እንድትነኪባት››

‹‹አረ አታስቢ እማዬ …እጠነቀቃለሁ፡፡››

ለሊሴ በፀሎትን ‹‹ለሊት የሆነ ነገር ከፈለግሽ ቀስቅሺኝ››አለችትና የለበሰችውን አልጋ ልብስ ተከናነበች፡፡

‹‹እሺ ቀሰቅስሻለሁ..ደህና እደሩ ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ደህና እደሪ….ወንድሜ ደህና እደር››

‹‹ምኑን ደህና አደርኩት ….ዛሬ ደግሞ ምን አልባት ሴኖ ትራክ ይሆናል ቤታችን ላይ የሚወጣው…. ››

‹‹ወንድሜ ደግሞ.. አሽሙራም ነገር ነህ››
‹‹እሺ መብራቱን ላጥፋው?››ፊራኦል ጠየቀ፡፡

‹‹አጥፋው››በፀሎት መለሰች፡፡

መብራቱ ጠፋ፡፡ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ሁሉም ፀጥ ያለና በእንቅልፍ የተዋጠ ይመስል ነበር..በፀሎት ግን ፈፅሞ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለም...ጨለማው ውስጥ አይኗን አፍጥጣ በጭንቀት እያሰላሰለች ነበር..ይሄኔ የአባቷ ቅጥረኞች ድፍን አዲስ አበባን እየገለባበጦት እንደሚሆን እርግጠኛ ነች..

‹‹የፈለገ ቢገለባብጡ የፈለገ ያህል ቢሞክሩ አያገኙኝም….››ስትል እርግጠኛ ሆነች፡፡ስልኳን ከቤት ይዛ አለመውጣቷ አሁን ነው ያስደሰታት….እንደዛ ባታደርግ ኖሮ ያንን ተከትለው ያለችበትን ለማግኘት ይሞክሩ ነበር አሁን ግ ምንም እድል የላቸውም…አዎ አሁን ባልና ሚስቶቹ እየተናቆሩም ቢሆን እሷን በመፈለጉ አንድ ላይ ለማውራትና ለመተባበር ይገደዳሉ…ምን  አልባትም  ወደቀልባቸው  እንዲመለሱ  ምክንያት  ሊሆናቸው  ይችል
ይሆናል… ይሄ የእሷ ምኞት ነው፡፡ካለበለዚያም ይለይላቸውና እርስ በርስ ይገዳደሉ ይሆናል፡፡ ‹‹እንደዛ ከሆነ እስከወዲያኛው እገላገላቸዋለው››አለችና በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ እንዲሁ ስትገላበጥና ስትተክዝ እኩለ ለሊት ሆነ፡፡ በአእምሮዋ የሚጉላላው ሀሳብ ብቻ አይደለም እቅልፍ የነሳት… የእግሯም ጥዝጣዜ ጭምር ነው ፡፡በዛ ላይ ሽንቷን ወጥሯታል….‹‹እንዴት ነው የማደርገው.?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡.እንደምንም ተቆጣጥራው እስከንጊት ለማቆየት ብትጥርም አልቻለችም..አምልጧት ከመዋረዷ በፊት ከጎኗ ድብን ያለ እንቅል የተኛችውን ሊሊሴን መጣራት ጀመረች‹፡፡

‹‹ሌሊሴ….ሌሊሴ››
ያልጠበቀችው ሻካራ ድምጽ መልስ ሰጣት..‹‹አትልፊ እህቴን እንኳን በጥሪ በመድፍም ልትቀሰቅሻት አትችይም››
ግራ ተጋብታ ምን እንደምትመልስ እያሰላሰለች ሳለ መብርቱ በራ…በቁምጣና በጃፖኒ ቲሸርት ውጥርጥር ያለ ሰውነቱን በከፊል አጋልጦ ካለችበት በሶስት እርምጃ ርቀት ቆሟል…

‹‹ምን ልስጥሽ?››ሲል ጠየቃት

‹‹አይ..ሽንት ቤት መሄድ ፈልጌ ነበር››ፈራ ተባ እያለች መለሰችለት፡፡

‹‹ምን ፖፖ ላምጣልሽ?››
ፖፖ ቢያመጣላት እዚህ እፍንፍን ያለ ቤት ይሄ ሁሉ ሰው ባለበት እንዴት አድርጋ እንደምትሸና አሰበችና‹‹ አይ ሽንት ቤት ነው መሄድ የፈለኩት›› በማለት መለሰችለት፡፡

‹‹እንግዲያው እሺ›› አለና ወደበራፍ በመሄድ የተቀረቀረውን በራፍ ወለል አድርጎ ከፈተና ተመልሶ ወደእሷ መጣ …ምን ሊያደርግ ነው ብላ አፍጥጣ እያየችው ሳለ በርከክ ብሎ ስሯ ተቀመጠና የለበሰችውን ብርድ ልብስ ከላዮ ላይ ገፈፈ፡፡ እጆችን በትከሻዋና በእጆቾ መካከል አሰቅስቆ አስገባ..

‹‹ምን እያደረክ ነው?››ግራ በተጋባ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹መቼስ እንዲህ ተሰባብረሽ ልራመድ አትይም….እንደፈረደብኝ አቅፌ ሽንት ቤት እየወሰድኩሽ ነው››

‹‹አረ ተው ..እነጋሼ ብያዩን ምን ይሉናል?››
‹‹አይዞሽ እነጋሼ ልጃቸው ምን አይነት ልጅ እንደሆነና እንዴት አድርገው እንዳሳደጉት ስለሚያውቁ ምንም አይሉም…..ምን አልባት ግን ይመርቁኝ ይሆናል››አለና አንከብክቦ አቅፎ ከቤት ይዟት ወጣ፡፡የልጁ ድርጊት ፍጽም ያልጠበቀችው ስለሆን በጣም ነው የተደመመችው፡፡

እንደተሸከማት ከሰርቢስ ቤቱ ጫፍ በኩል ክፍቱን ካለ አንድ ክፍል ወስዶ ወደውስጥ ደፉን አሳለፈና ደግፎ አቆማት…ከዛ ቀኝ እጁን ዘረጋና በቀይ የኤሌክትርክ ገመድ ጫፍ ላይ የተንጠለጠለውን ማብሪያ ማጥፊያ ሲጫናው የሽንት ቤቱ መብራት ቦግ ብሎ በራና በክፍሉና በአካባቢው ያለው እይታ ወለል ብሎ አንዲታየ አደረገ …
ደረቱ ላይ ተደግፋ እንደቆመች ሽንት ቤቱን ቃኘችው..ስፋቱ ሁለት ካሬ እንኳን አይሞላም
…በዛ ላይ ከለመደችው አይነት መፀዳጃ ቤት ፍፅም የተለየና የማይነፃፀር አይነት ነው….ይህን መሰል አይነት ሽንት ቤት በምስል አንኳን አይታው የማታውቀው አይነት ነው፡፡እርግጥ ፅዳቱ የተጠበቀ በመሆን ዝግንን የሚል የመቅፈፍ አይነት ስሜት እንዲሰማት የሚያደርግ አይነት አይደለም…ቢሆንም በምቾት ዘና ብላ የምትቀመጥበት አይነት አይደለም…‹‹በቃ እንደምንም ግድግዳውን ተደግፈሽ ቁሚ..››ትዕዛዙን ስትሰማ እንደምንም የተበታተነ ሀሳቧን ሰበሰበች፡፡

እስከአሁን ደረቱን ተደግፋ መቆሟን ትዝ ሲላት እንደመደንገጥ አለችና ግራና ቀኝ እጇን የሽንት ቤቱን በራፍ ግራና ቀኝ ጉበን ይዛ ቆመች…ትቷት ወደኃላ ሸሸና መራመድ ሲጀምር
በመደንገጥና በመገረም ስሜት‹‹እንዴ? ጥለኸኝ ልትሄድ እንዳይሆን?››ስትል ጠየቀችው፡፡
እርምጃውን ሳያቋርጥ ‹‹መጣሁ..››አለና ከበራፉ አካባቢ አንድ ባዶ ሀይላንድ ላስቲክ ይዞ ወደ ቧንቧው በመሄድ ውሀ ቀድቶ ከሞላበት በኃላ ..ወደእሷ ተመለሰና እጁን አንጠራርቶ ከሽንት ቤቱ ቀዳዳ አጠገብ አስቀመጠላትና …‹‹..ግቢና እንደምንም ተቀመጪ››አላት፡፡
ወደውስጥ ዘልቃ ገባች‹‹በራፍ የለውም እንዴ?››ሌላ ያስጨነቃትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይዞሽ….ምንም አትሆኚም››አለና ወደላይ ተሰብስቦ የተጠቀለለ ጨርቅ ነገር አላቀቀና እንደመጋራጃ ወደታች ለቆ ጋረደላት…..የእግሯን ጥዝጣዞ እንደምንም ችላ በአንድ አይኗ አጨንቁራ በማየትና ነገሮችን በመቆጣጠር እደምንም ተቀምጣ ለመተንፈስ ቻለች..ጨርሳ ስትወጣ ተንደርድሮ ከበራፍ ተቀበላትን ሰቅስቆ አቀፋት፡፡

‹‹ካላስቸገርኩህ ጨረቃዋ ደስ ትላለች ..ትንሽ ውጭ መቀመጥ እንችላለን?››ስትል በልመና ቃና ጠየቀችው፡፡
‹‹እንደፈለግሽ.. ››አለና ግድግዳውን አስደግፎ አቆማትና ትቷት ወደውስጥ ሊገባ መራመድ ጀመረ…
‹‹እንዴ ብቻዬን ልቆይ እኮ አይደለም ያልኩህ ..አንተ ምትገባ ከሆነማ እኔ ብቻዬን ፈራለሁ››

‹‹በለሊት ሞተር ስትጋልቢ እንዴት ሳትፈሪ…?ለማንኛውም ወንበር ላመጣልሽ ነው››አለና ወደቤት ገባና አንድ ባለመደገፊያ ወንበር በማምጣት አደላድሎ ወስዶ አስቀመጣትና ከጎኗ ጠፍጣፋ ድንጋይ አስቀምጦ ተቀመጠ፡፡
👍5513
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ስራው "የፍቅርና የጋብቻ አማካሪነት ነው።የተማረው ፍልስፍና ነው።ሁለተኛ ዲግሪውን ግን አሜሪካ ሄዶ በስነልቦና መስራት ችሏል፡፡በፍቅርና ጋብቻ አማካሪነት የሰራውም እዛው አሜሪካ ነው….ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ሶስት አመት ተቀጥሮ ሰርቶል፡፡አሜሪካዊያኑ በፍቅርና በጋብቻ ጉዳይ ችግር ሲያጋጥማቸው ባለሞያ ጋር መሄድና ድጋፍ ማግኘት ባህላቸው ነው፡፡በመጀመሪያ ወደትዳር ከመግባታቸው በፊት ማድረግ ስለሚገባቸው ስነልቦናዊ ቅድመ ዝግጅት ለማወቅ ባለሞያው ጋር ይሄዳሉ..ትዳር ውስጥ ገብተው ችግር ሲያጋጥማቸው…እርስ በርስ ያለው ተግባቦታቸው አመርቂ ካልሆነ…የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት የሚያጨቃጭቃቸው ከሆነ…የወሲብ አለመጣጣም በመሀከላቸው ካለ ብቻ ማንኛውንም ችግር በመሀከላቸው ከተፈጠረ ወደ ጋብቻ አማካሪ ሄዶ ሞያዊ ምክር መጠየቅና ከዛም የሚሰጣቸውን ምክርና ትዕዛዝ ለየብቻም ሆነ አንድላይ በመተግበር ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርጉት ጥረት ያስቀናል፤ሌላው ይቅር ጋብቻቸው እንደማይሰራ እርግጠኛ ከሆኑ እንኳን ጤናማና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዴት መለያየትና ጓደኛሞች ሆኖ መቀጠል እንደሚችሉ ምክር ለማግኘት ተያይዘው ወደ ጋብቻ አማካሪ ቢሮ ይሄዳሉ..ይህ ጉዳይ በጣም ነበር የሚያስገርመው፡፡በተለይ በመሀከላቸው ልጆች ካሉ ለየብቻ ሆነው እራሱ
የልጆቻቸውን ስነልቦና ጠብቀው እንዴት ተግባባተው ማሳደግ እንዳለባቸው ዝርዝር መመሪያ ከአማካሪዎች በመስማት ያንን ሳያዛንፉ በመተግበር የልጆቻቸውን ደስታ ሆነ የእነሱን ሰላም ይጠብቃሉ፡፡ያም ሆኖ ግን ምንም እንኳን በስራው በጣም ደስተኛና ጥሩ ገቢ የሚያገኝበት ቢሆንም ከአምስት አመት በኃላ ጠቅልሎ ወደሀገሩ ተመለሰ….ሲሄድ መቼም ላይመለስ ነበር…..ሀገር ቤት ባሉ ነገሮች ጠቅላላ ተስፋ ቆርጦ ነበር…ግን እንዲመለስ የሚያስገድደው ቁራጭ ምክንያት አገኘ……እና ተመለሰ፡፡

ሰለሞን ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሰ መጀመሪያ ተቀጥሮ ለመስራት  ስራ ለማፈላለግ ሞክሮ ነበር….።አስቴር ግን የራሱን ስራ መጀመር እንዳለበት በተደጋጋሚ ጊዜ ግፊት ስታደርግበት እራሱን ከተበታተንበት ሰበሰበና እና መኝታ ቤቱ ውስጥ ገብቶ በላዩ ላይ ዘጋና ስብሰባ ተቀመጠ።አስቴር የልጅነት ጓደኛው እናም ደግሞ ፍቅሩ ነች…ወጣት ሲሆኑ ደግሞ እህቱ ሆነች…እስከአሁንም እህቱ ሆና ቀረች..እሱ በልቡ ተመልሳ ፍቅሩ እንድትሆን ነው የሚመኘው….አላማውም እቅዱም ያ ነው..እሷ ግን ያንንን መስመር ጠርቅማ ዘግታበት አባቱን አባቷ እናቱን እናቷ አድርጋ ለእሱ ደግሞ እህቱ ሆናለች፡፡

ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የሚያውቃት፡፡ ገና ሰባት ወይ ስምንት አመቱ ላይ…የእናቷን ጠርዙ የነተበ የቀሚስ ጫፍ በትናንሽና ለስላሳ እጆቾ ጨምድዳ ይዛ ስርስሯ ኩስ ኩስ እያለች ስትመጣ ነበር የሚያውቃት…የዛን ጊዜውን የልጅነት መልኳን አሁንም በአእምሮው ሰሌዳ ላይ በጉልህ ተስሎ ይገኛል..በአጭሩ ተቆርጦ እርስ በርሱ ተጠቅልሎ የተንጨፈረረ ወርቃማ ፀጉር…ጎላ ጎላ ብላው በፍርሀት የሚንካባለሉ አይኖች…በእንባና በአቧራ ብራብሬ የሆነ አሳዛኝ ፊት….ልክ የግቢው አጥር ተከፍቶላቸው የፊትለፊቱን ትልቁን የሳሎን በራፍ አልፈው ወደጓሮ ሲዞሩ ከኃላ ተከትሎቸው ይሄዳል…እናትዬውን ተከትላ ማድቤት ስትገባ ተከትሏቸው ይገባል…
‹‹የእኔ ልጅ፣ እስኪ እኔ ስራዬን ልስራበት አንቺ ከሰሎሞን ጋር አብራችሁ ተጫወቱ››እያለች እናትዬው ታባብላታለች…እሷም የእናትዬውን ልመና ተቀብላ ከእሱ ጋር ለመጫወት ፍቃደኛ እንድትሆን በአይኖቹ ጭምር ይለማመጣታል….የተቋጠረ ግንባሯን ሳትፈታ በቀሰስተኛ እርምጃ ወደእሱ ትጠጋለች…በደስታ አጇን አፈፍ አድርጎ ይይዛትና እየጎተተ ወደትልቁ ቤት ይዞት ይሄዳል…ከታላቅ እህቱ ጋር በጋራ ወደሚኖርበት መኝታ ክፍላችው ይዞት ይገባል፣..ያሉትን መጫወቻዎች ሁሉ ከየመደርደሪያዎቹን ከየአልጋ ስሩ እየጎተተ ያወጣና  ፊት ለፊቷ  ወለሉ  ላይ  ይቆልላል፣ለእሱ  የሰለቹትን  መጫወቻዎች  ለእሷ  ብርቅ  ነበሩ….እናትዬው እነሱ ቤት በተመላላሽነት በሳምንት ሶስት ቀን ትሰራለች፡፡እና እነዛን ሶስት ቀናት በናፍቆትና በፍቅር ነበር የሚወዳቸው… ሳምንቱን ሙሉ ለምን እንዳማይመጡ ይገርመው ነበር..ከዛ አባቱ እሱን አንደኛ ክፍል አስመዝግቦ ትምህርት ሲያስጀምረው ለእሷም እንደዛው ደብተርና ዩኒፎርም ገዝቶ እሱ የሚማርበት ትምህርት ቤት እናቷ እንድታስመዘግባት አደረገ…አንድ ትምህርት ቤት አንድ ክፍል መማር ጀመሩ…ይሄ ደግሞ የሚገናኙበትን የቀን ብዛትና አጋጣሚ አሰፋው…..ጓደኝነታቸው አብሮ ዕቃ ዕቃ ከመጫወት የተጀመረ ….ከዛ ኤለመንተሪ ጀምረው እስከ ሀይ እስኩል በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ነው የተማሩት።

የተወሰኑ ክፍሎችን አንድ ክፍል ጥቂት ክፍሎችን ደግሞ አንድ መቀመጫ ላይም አብረው ተቀምጠው የመማር አጋጣሚዋች ነበሯቸው።ስለዚህ እሷ ልክ አብረውት እንደተወለድ ወንድሞቹ እና እህቱ እድሜ ልኩን ነው የሚያውቃት፡፡
ፍቅር የጀመሩት 8ተኛ ክፍል ሲማሩ ነው።በወቅቱ እሱ 8ተኛ ቢ ሲማር እሷ ደግሞ 8ተኛ ኤፍ ክፍል ነበረች።ግን ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ወደት/ቤት ሲሄድና ወደሰፈር ሲመለሱ ተጠራርተውና ተጠባብቀው ነበር።እና አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲወጡ እየጠበቀችው ነበር።አብረው ወደቤት መመለስ ቢጀምሩም ግን አንደበቷ እንደተቆለፈና እንደተበሳጨች ነበር...ምን እንደሆነች ቢጠይቃትም በቀላሉ ልትነግረው አልቻለችም..በኋላ በስንት ጭቅጭቅ ከቦርሳዋ አንድ ወረቀት አውጥታ ሰጠችው።ምንድነው? ብሎ በጉጉት ተቀብሎ አነበበው።
አስቴርዬ የእኔ ቆንጆ..የፍቅርሽ ፍላፃ ልቤ ላይ ነው የተሰካው….እስካሁን ሰንኮፉን
አልነቀልኩትም…ያልነቀልኩት ሲሰካብኝ ከነበረው ጊዜ በላይ ስነቅለው ያመኝ ይሁን በሚል ስጋት ነው…….ምን አልባት አንቺው በትንፋሽሽ አዘናግተሸ በልስልስ እጆችሽ ቀስ ብለሽ ብትነቅይልኝ መልካም ይሆን ይመስለኛል፡፡፡አንቺ እኮ ከአለም ሴቶች ጭምር ተወዳዳሪ
የሌለሽ ውብ ነሽ።እኔ አፍቃሪሽ በአንቺ ፍቅር መንገላታት ከጀመርኩ አመታት አልፈዋል።ግን እስከዛሬ ስቃዬን በውስጤ አፍኜ ህመሜን የቻልኩት ከጓደኛዬ ከሰለሞን ጋር ግንኙነት ያላችሁ ስለሚመስለኝ ነበር።ግን በቀደም ወኔዬን አሰባስቤ ስጠይቀው ጓደኛሞች ብቻ እንደሆናችሁ ነገረኝና ነፍሴን በሀሴት አስጨፈራት።እና ውዴ አንቺስ ምን ትያለሽ...
?መልስሽን በጉጉት እጠብቃለሁ... የአንቺው አፍቃሪ መስፍን ጋዲሳ›› ይል ነበር።

አነበበውና ግራ የመጋባትና የመደነጋገር ስሜት ተሠማው..በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው በቀደም በብዙ ጓደኞቻቸው መካከል ስለፍቅር አንስተው ሲያወሩ መስፍን እንደቀልድ ‹‹አስቴርና ሰለሞን ፍቅረኛሞች ናቸው›› አለ ወዲያው ሰለሞን ከአፉ ተቀበለና
‹‹እውነት አይደለም እኔና አስቴር ፍቅረኛሞች ሳንሆን ጓደኛሞች ነን ››ብሎ መልስ ሰጠ ።ነገሩ በዚህ ተደመደመ።ደብዳቤውን ባነበበበት ወቅት ግን መሠፍን ሆነ ብሎ ለገዛ የግል ጥቅሙ ጥያቄውን ጠይቆት እንደነበረና እሱንም ማኖ እንዳስነካው ገባውና በጅልነቱ ተበሳጨ።

ግን ደግሞ የአስቴር ወቅታዊ ኩርፊያ አልገባውም ነበር።‹‹መስፍን ደብዳቤ ለፃፈላት እኔን ለምን ልታኮርፈኝ ቻለች?››እራሱን ጠየቀ
"እና እኔ ምን አጠፋው..የምታኮርፊኝ?"ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡
👍6813🔥2
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞን ለዚህ ነው ከውጭ ከተመለሰ በኃላ ለመደላደል ስራ መጀመር እንዳለበት የወሰነው
‹‹ምንድነው መስራት ያለብኝ?ምን አይነት ዕውቀት ነው ያለኝ?ምን አይነት ጥሪትስ አለኝ?ህብረተሠብስ ምን አይነት ሸቀጥ ወይም አገልግሎት ነው መግዛት የሚፈልገው?። መልሶቹ ቀላል አልነበሩም...ወደ አእምሮው የሚመጣው መልስ ወደግል ስራ የሚያስገባው ሳይሆን እንደውም በተቃራኒው የሚያርቀ ነው የሆነበት።

1/ይሄ የምኖርበት ህብረተሠብ በዚህ ሰአት ግዙፍ ችግሩ ምንድነው...?ወረቀትና እስኪሪብቶ ያዘና ዘርዝሮ መፅፍ ጀመረ

1/ኑሮ ውድነት
2/የሠላም እጦት
3/የፍቅር እጦት
4/ቴክኖሎጂ ቅኝ ግዛት
5/...!!የአየር ፀባይ መዛባት
የፃፈውን መለስ ብሎ አየው ...ለደቂቃዎች ብቻውን ተንከትክቶ ሳቅ ። ዝርዝሩን አንድ አነስተኛ የግል ቢዝነስ ለመክፈት ሳይሆን አዲስ ጠቅላይ ሚንስቴር ሆኖ ተሹሞ በሀገሪቱ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጡ የፓሊሲ አማራጮችን ለማርቀቅ መነሻ ሀሳቧችን እያሰላ ያለ ፓለቲከኛ ነው  የሚመስለው።

‹‹እስቲ የህብረተሠብም የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ ምን አይነት ቢዝነስ ነው የሚኖረው...?ኑሮ ውድነቱ እንኳን ግለሠብ መንግስትስ ለማስተካከል አቅም አለው...?የመለኮት ጣልቃ ገብነት ከሌለስ  መፍትሄ ይኖረዋል?።››ሲል አሰበና በራሱ ድርጊት ዳግመኛ ሳቀ፡፡ ከዘረዘራቸው ሀሳቦች የ3 ተኛው ሀሳቡን ገዛው።‹‹ፍቅር እጦት የእኔም የማህበረሰብም የጋራ ችግር ነው።የፍቅር እጦት ደግሞ የሌሎች ችግሮች ሁሉ መነሻ ምክንያት ነው።ደግሞ በሙሉ አቅሜ መስራት የምችለው ስራ እሱን ነው …ሞያዬም ችሎታዬም እሱ ላይ ነው››ሲል አሰበና ወሰነ፡፡

አሜሪካ እያለ ተቀጥሮ የሚሰረባትን የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ድርጅት እዚህ ሀገሩ መሀል አዲስ አበባ ላይ በራሱ ለመክፍት ወሰነ…‹‹የራስህን ቢዝነስ ጀምር›› ብላ ስትጨቀጭቀው ለነበረችው አስቴር ነገራት፡፡፡አንገቱ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመች በሀሳብ በጣም መደሰቷንና በማንኛውም ነገር ከጓኑ እንደሆነች አበሰረችው…እሷ የተደሰተችበት ነገር ደግሞ በእሱ ህይወት ትልቅ ቦታ ስላለው ወዲያውኑ በደስታ ወደእንቅስቃሴ ገባ……ፍቃድ ለማውጣት ቢሮ ለመከራየትና አስፈላጊ የቢሮ እቃዎችን አሞልቶ ለመክፈት 40 ቀን ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡

ይሁን እንጂ ለአንድ ወር ያህል በሰአት ቢሮ እየገባ በሰዓት ቢወጣም አንድም ደንበኛ ማግኘት አልቻለም…ሁሉ ነገር ተስፋ አስቆራጭ የሆነበት፡፡ግራ ገባው ፣በመጀመሪያውም ዝግና ድብቅ ባህል ባለበት ሀገር የጋብቻና የፍቅር አማካሪ ድርጅት ከፍቶ ውጤታማ ሆናለው ብሎ በማሰብ በራሱ ጅልነት ተበሳጨ…የስድስት ወር የቢሮ ኪራይ ባይከፍልና ለፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎችን ለማሟላት ከመቶ ሺ ብሮች በላይ ባያወጣ ኖሮ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ዘጋግቶ ሌላ የቅጥር ስራ ይፈልግ ነበር..ግን ለጊዜው እንደዛ ማድረግ አይችልም…‹‹አዎ ለአስቴር ምን እላታለሁ….?እንድታፍርብኝማ አላደርግም…እሷ ከምታፍርብኝ አለም ጠቅላላ ብትገለባበጥ እመርጣለሁ….ስለዚህ የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ››በማለት ወሰነና ቀኑን ሙሉ ሲያሰላስል ዋለ… የሆነ ነገር ብልጭ አለለት፡ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡
ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ሄሎ ወንድሜ….›››የሚል ድምፅ በስልኩ እስፒከር አቆርጦ ጆሮው ውስጥ ተሰነቀረ…

‹‹አለሁልሽ››

‹‹ምነው ድምፅህ?››

‹‹ደህና ነኝ….የሆነ ነገር ላማክርሽ ነበር?››

‹‹ይቻላል..ግን ስራ አሪፍ ነው እንዴ?….››

‹‹አሪፍ ነው …አሁን አንድ ደምበኛዬን ወደትዳር ከመግባቷ በፊት ማድረግ ስለሚገባት ቅድመ ዝግጅት ማወቅ ፈልጋ ነበር.. እሷን እንደሸኘሁ ነው የደወልኩልሽ››ዋሻት፡፡

‹‹ደስ ይላል ወንድሜ …ህልምህን መኖር ጀምረሀል ማለት ነው….››

‹‹አንቺ ከጎኔ ሆነሽ እስከደገፍሺኝ ድረስ ምንም ማላሳከው ነገር የለም…..አሁን ለምን መሰለሽ የደወልኩልሽ…ፀሀፊ ብቀጥር ብዬ አሰብኩ…››ያሰበውን ነገራት፡፡

‹‹አዎ አንተ ….እስከዛሬ እንዴት አላሰብንበትም…?ለፕሮቶኮሉ እራሱ አስፈጊ ነው…ባለጉዳዬች እንደመጡ አንተን ማግኘት የለባቸውም በፀሀፊህ በኩል ቀጠሮ ይዘውና ተገቢውን ቅድመ ማሟላት ያለባቸውን ነገር አሟልተው መሆን አለነበት…አሪፍ ነው…››

‹‹እና እንዴት ላደርርግ ?ማስታወቂያ ላውጣ….?››

‹‹አይ እኔ በሶስት ቀን ውስጥ ምርጥ ፀሀፊህ ቀጥርልሀለው….አንተ በዚህ ጉዳይ ምንም አትጨነቅ…..ሶስት ቀን ብቻ ስጠኝ››

‹‹እሺ ማታ እቤት እንገናኝ››

‹‹እሺ ቻው ..ወንድሜ››

‹‹ቻው..››

ወንድሜ የሚለው ቃል ከአንደበቷ በወጣ ቁጥር በአንገቱ የተንጠለጠለ የብረት ሰንሰለት ነው የሚታየው….ሆነ ብላ እሱን ለማጥቃት አስባ ከአንደበቷ የምታወጣው ነው የሚመስለው….‹‹አደራ እኔ እህትህ ባልሆንም ልክ እንደእህትህ ነኝና ሌላ ነገር በአእምሮህ እንዳይበቅል››የሚል ማስጠንቀቂያ ነው የሚመስለው፡፡
የእናትና አባቱ ልጆች የሆኑት እህቱ ወንድሜ የሚለውን ስም በአመት አንዴ እንኳን ሲጠቀሙ አልሰማም….ትዝም የሚላቸው አይመስለውም…እሷ ግን ልክ እንደዘወትር ፀሎት እንደውዳሴ ማርዬም ነው በየእለቱ የምትደግመው፡፡
///.....////...../////

በፀሎት ጥዋት ከእንቅልፏ ስትባንን እቤት ውስጥ ከወ.ሮ እልፍነሽ በስተቀር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም፡፡

‹‹እማዬ ሰው ሁሉ የት ሄደ?››እማዬ ብላ መጣራቷን ለራሷም እየገረማት ነው…ደግሞ አፏ ላይ አልከበዳትም…ወላጅ እናቷ…ሌላ ሴት እናቴ እያለች መጥራት መጀመሯን ብትሰማ ልብ ድካም ይዟት ፀጥ እንደምትል እርግጠኛ ነች፡፡

‹‹ወይ ልጄ… ነቃሽ…ልቀስቅሳት ወይስ ትንሽ ትተኛ እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ነበር፡፡ በረሀብ ሞትሽ እኮ››ብለው  ወደ ጓዲያ ገብና የእጅ  ማስታጠቢያ  ይዘው መጥተው,ሊያስታጥቧት ጎንበስ አሉ…እንደምንም ከአንገቷ ቀና ብላ ተነሳችና ‹‹ያስቀምጡት እኔ እታጠባለው››

‹‹አረ ችግር የለውም ልጄ ..ችግር የለውም››

‹‹ግድ የሎትም….››.

‹‹እንግዲያው ታጠቢ …ቁርስሽን ላቅርብ ›› ብለው ማስታጠቢያው ስሯ አስጠግተው አስቀመጡላትና ተመልሰው ወደ ጓዲያ ሔድ

…….እግሯ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ጥዝጣዜው ነፍሶ ድረስ ይሰማታል…..ፊቷ ላይ አሁንም ተራራ የሚያህል ቁስል የተሸከመች እየመሰላት ነው…እንደምንም ተንፏቀቀችና እጇን ታጥባ የሚመጣላትን ቁርስ መጠበቅ ጀመረች…ጩኮ ከእርጎ ጋር ነበር የመጣላት…ጩኮ መች በልታ እንደምታውቅ አታስታውስም….ቤቷ ቁርስ ሲቀርብ አስር …አስራአምስት አይነት ምግብ ጠረጴዛ ሞልቶ ነው….ከዛ ውስጥ ሶስት ወይም አራት አይነቱን አፕታይቷ የፈቀደላትን መርጣ በልታ ሌላውን ትተዋለች..አሁን የቀረበላት ምግብ ይህን ያህል ግን አስደሳች አልነበረም…….እርቧት ስለነበረ እየተስገበገበች በላች…
ያጋባችውን ሰሀንና ብርጭቆ መልሳ…እጇን ታጠበችና…..‹‹እማዬ ማንም የለም እንዴ?››ስትል ደግማ ጠየቀች፡፡

‹‹ልጄ ለሊሴ ስራ ፍለጋ ብላ ወጥታለች…ፊራኦል ስራ ነው ..አባትሽም እንደዛው››መለሱላት፡፡

‹‹ለሊሴ ምን አይነት ስራ ነው የምትፈልገው?››
👍5513
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አቶ ኃይለ መለኮት እቤታቸው ባለ የገዛ ቢሯቸው ውስጥ ተሸከርካሪ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠዋል…በቀኝ እጃቸው የሚያብረቀርቅ ማካሮብ ሽጉጣቸውን ይዘው ፊታለፊታቸው ያሉት ሶስት ግለሰቦች ላይ በየተራ እያነጣጠሩ ምላጩን በስሱ እየዳበሱ ይናገራሉ

‹‹በመጀመሪያ ማንን ልግደል?››

‹‹ጌታዬ ይቅር ይበሉን…አጥፍተናል….››

‹‹አጥፍተናል….ጥፋት እኮ በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ስህተት የሆነ ድርጊት ስታደርግ ነው፡፡ለምሳሌ እዚህ መኖሪያ ቤቴ ላይ ጋዝ አርከፍክፈህ ክብሪት በመለኮስ ግማሹን ህንፃ ብታወድመው ጥፋት አጥፍተሀል ብዬ የጠየቅከውን ይቅርታ ልቀበልህ እችላለው፡፡ ምክንያቱም እቤቱን አሁን ካለበት ይዘት ይበልጥ አስውቤ ከእንደገና ላስገነባው እችላለሁ…ወይም ከፋብሪካዎቼ ትልቁን መርጠህ ሙሉ በሙሉ ብታወድመው እንደጥፋት ቆጥሬ ይቅርታህን ልቀበል እችላለው…ወይንም ሽጉጥህ ባርቆብህ ቀኝ እጄን ብትመታኝና በዛ የተነሳ እጄ ቢቆረጥ አዎ ይቅርታህን ልቀበል እችላለው፡፡ግን አሁን ምንም አላስቀረህልኝም፡፡ልጄ ሁለ ነገሬ ነች…ምንም መተኪያ ምንም ማካካሻ የላትም…ያ ማለት ይቅርታ ላደርግላችሁ ፈፅሞ አልችልም.››

‹‹ጌታዬ ይገባናል፣ አንተ ትክክል ነህ..ግን ቢያንስ በፍለጋው ላይ ጠንክረን እየሰራን ነው….የሆነ ትንሽ ቀን ጨምርልንና አቅማችንን አሟጠን እንፈልጋት… የሆነ ያህል ጊዜ ስጠን… ካልተሳካልን ያሰብከኸውን ታደርጋለህ፡፡››

‹‹አዎ እሱማ አደርጋለው….ዋጋማ ትከፍላላችሁ….አሁን የምናደርገው…..››ንግግራቸውን ሳያጠናቅቁ ስልካቸው ጠራ…የደቀኑትን ሽጉጥ ሳያወርድ ስልኩን አንስተው ማውራት ጀመሩ፡፡

‹‹እሺ…ጥሩ …ሶስቱም ነው እይደል… በጥንቃቄ ጠብቋቸው››
ስልኩን ከዘጉ በኃላ ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹ስልኩ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ…?የእናንተ የሁለታችሁን አንዳንድ ልጃችሁን ያንተን ደግሞ ምትወዳትን ሚስትህን አሳግቼቸዋለው…ልጄ በሚቀጥሉት ሶስት ቀን ውስጥ ተገኝታ ወደቤቷ ካልተመለሰች ያው የምወዳትን ልጄን ስላሳጣችሁኝ ለዛ ክፍያ የምትወዱትን ሰው ታጣላችሁ ማለት ነው፡፡››ሲል ሰቅጣጭ መርዶ አረዷቸው፡፡

ሶስቱም ሰዎች ላይ የታየው ድንጋጤ ሲእላዊ ነበር፡፡፡አቶ ኃይለልኡል ሰዎቹን ከቢሮቸው አሰናብተው ሽጉጡን ወደመሳቢያው ውስጥ መልሰው በማስቀመጥ ቆለፉበትና ወጥታው ወደ ባለቤታቸው ወ.ሮ ስንዱ መኝታ ቤት ሄዱ
….ሚስታቸው አልጋው ላይ ተሰትረው ጉልኮስ ክንዳቸው ላይ ተሰክቶ እህህ እያሉ ነው..ለዘመናት ወደዋቸው የማያውቁት ባላቸውን ድምፅ ሲሰሙ የከደኑትን አይን ገለጡ እና በመከራም ቢሆን ከንፈራቸውን አነቃነቀው ማውራት ጀመሩ

‹‹ኃይሌ…ልጃችን አልተገኘችም?››

‹‹አይዞሽ አታስቢ ..ትገኛለች….አንቺ ምንም አትጨነቂ››ሊያፅናኗቸው ሞከሩ፡፡

‹‹እንዴት አልጨነቅ…?በዚህ አለም ላይ ያለቺኝ እሷ ብቻ ነች..በህይወቴ ሙሉ የበደልከኝን በደል እንድረሳልህ…የሰራህብኝን ስራ ይቅር እንድልህ ከፈለክ ልጄን አግኝልኝ….ልጄን ካገኘህልኝ ያልከኸውን ሁሉ አደርግልሀለው….እንደውም ምንም ሀብት ሳልካፈልህ እፈታሀለው…እፈታህና ገዳም እገባለው..አዎ ልጄ ሰላም መሆኗን ካረጋገጥኩ ከህይወትህ ዞር እልልሀለው›

‹‹አረ ተይ …ለእኔም ልጄ እኮ ነች…እሷን ለማግኘትና ወደቤቷ ለመመለስ ከአንቺ ጋር ይሄንን አድርጊልኝ እያልኩ የምደራደር ጭራቅ ነገር እመስልሻለው….?ተይ እንጂ..አሁን ወጣ ብዬ ፖሊሶቹ ምን ላይ እንደደረሱ መጠየቅ አለብኝ..ሀኪሞቹ ሚሉሽን ስሚና ጤናሽን ተነክባከቢ..ልጃችን ስትመጣ እንደዚህ ሆነሽ እንደታገኚሽ አልፈልግም…እናቴ በእኔ ምክንያት ሽባ ሆነች ብለ መፀፀት የለባትም››ብሎ ወጥቶ ሄደ…..
///
በፀሎት ከእንቅልፏ የባነነችው በቤቱ ውስጥ ግርግር እና የብዙ ሰው ድምፅ ስትሰማ ነበር..አይኖቾን ስትገልጥ ግን ያሰበችውን ያህል ብዙ ሰው አልነበረም ነበር…ወ.ሮ እልፌ
፤አቶ ለሜቻና አንድ ሙሉ ሱፍ የለበሰ ጎልማሳ ሰው ነበር በቤቱ ያሉት….ግን ያ ጎልማሳ ሰው ሲያወራ ድምጹ መመጠኛው እንደተበላሸበት ማይክራፎን ከጣሪያ በላይ ይጮኸ ስለነበረ የብዙ ሰው ድምጽ ይመስላል….
አይኗን ስትገልጥ አየና ወደእሷ ተጠጋ.‹‹ልጄ ተነሳሽ..?ጥሩ …ይሄ ዶክተር ታፈሰ ይባላል..የጓደኛዬ ልጅ ነው….አንቺን እንዲያይልኝ አስቸግሬው ነው፡፡›››አቶ ለሜቻ ናቸው ተናጋሪው፡፡

‹‹አባቴ ዝም ብለህ ነው እኮ የተቸገርከው..ደህና ነኝ እኮ››
ከወ.ሮ እልፍነሽ ጋር በተስማማችው መሰረት ቢሻክራትም አንቱታውን በአንተ ቀይራ ማውራት ጀመረች…

‹‹ደህና መሆንሽና አለመሆንሽን እኔ ሀኪሙ አይቼ ብወስን አይሻልም›› ዝም አለችው….
ወደእሷ ተጠጋና  አያት…ግንባሯና ከፊል ፊቷ በስነስርአት መታሸጉን አረጋገጠና  ..አንድ መርፌ በክንዷ ወግቷት መድሀኒት አዘዘላት…
‹‹በቃ ጋሼ..የወንድሞት ልጅ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች..ቁስሉ ጊዜውን ጠብቆ ፋሻው ተነስቶ በደንብ ፀድቶ ከእንደገና መታሸግ አለበት…›››

‹‹ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም እያልከኝ ነው?››

‹‹አይ የለም ሰላም ትሆናለች..ግን ምን አልባት ፊቷ ላይ ጠባሳ ሊሆንባት ይችላል፡፡››

‹‹ያንን ማስቀረት አይቻልም?››አቶ ለሜቻ ጠየቁ፡፡

‹‹ያው የቆዳ ስፔሻሊስቶች ያስተካከሉታል..በአሁኑ ጊዜ ብር ካለ የማይስተካከል ነገር የለም..ዋናው በህይወት መትረፏና አካለ ጎዶሎ አለመሆኗ ነው…የጠባሳው ነገር የገንዘብ ጉዳይ ነው… ይስተካከላል፡፡››

‹‹ይሁን እንግዲህ…….አንተንም አስቸገርኩህ››

‹‹አረ ጋሼ…ለርሶ ባልታዘዝ አባቴ አያናግረኝም….በማንኛውም ሰዓት ካመማት ደውሉልኝ..አሁን ልሂድ….፡፡እግዜር ይማርሽ እህቴ››

‹‹አመሰግናለው ዶ/ር፡፡››

‹‹ዶ/ር አቶ ለሜቻን አስከትሎ ቤቱን ለቆ ወጣ ..ክፍል ውስጥ ወ.ሮ.እልፍነሽና በፀሎት ብቻ ቀሩ፡፡

‹‹ጋሼ ዝም ብሎ እኮ ነው የሚጨነቀው?››

‹‹እሱ..እንዲሁ ነው….ታያለሽ ነገ ደግሞ ሌላ ዶክተር ለምኖ ይዞ ይመጣል..እስክትድኚ እረፍት አይኖረውም››

አቶ ለሜቻ ተመልሰው ከመምጣታቸው በፊት ለሊሴ ከሄደችበት ተመልሳ መጣች፡፡ ይዛ የመጣችው ዕቃ ግን የሳሎኑን ግማሽ የሸፈነ ነበር….ከአምስት በላይ ፔስታል ከባለታክሲው
ጋር እየተጋገዙ ወደውስጥ አስገቡ….ከገዛችው ዕቃዎች ውስጥ ለበፀሎት አዲስ አንሶላዎች
…ምቾት ያለው ብርድልብስ ፣ቢጃማ ..ሸበጥ ጫማ..ቅባት…ፓንቶች..ብቻ ያስፈልጋታል ያለችውን እና በእይታዋ የገባላትን ዕቃ ሁሉ ገዝታ ነበር..ከዛ የቤት አስቤዛ አትክልቱን..ፍራፍሬውን..ፓስታ ..መኮሮኒ..ስጋና የመሳሰሉትን እልክ የታጋባች ይመስል ቤቱን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በቁሳቁስ ሞላችው…፡፡
አቶ  ለሜቻ  ዶክተሩን  ሸኝተው  ሲመለሱ  ትተው  የሄዱት  ሳሎን  ሌላ  መልክ  ይዞ ሲጠብቃቸው ከመደንገጣችው ብዛት ባሉበት ደርቀው ቆሙ….

‹‹ሊሊሴ ምንድነው ይሄ ሁሉ?››
‹‹አየህ አባዬ አንሶላው አያምርም…

ብርድ.ልብሱስ….?.እሄው ቢጃማም ገዛሁላት…››

‹‹ጥሩ አደረግሽ…ብሩን ከየት አመጣሽው?››

‹‹እኔማ ከየት አመጣለው….እራሶ ሰጥታኝ ነው፡››አለች ወደበፀሎት እየጠቆመች፡፡

‹‹ይሄንን ካሮት፤ ቆስጣ ፤ስጋ ፤መኮሮን ይሄን ሁሉ በእሷብር ነው የጋዛሽው ››

‹‹አዎ አባዬ››

‹‹እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ለሊሴ…?ችግር ላይ ካለች ልጅ እንዴት? ››
👍7812🤔2
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስር


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሀሳቧን ሳትጨርስ ፊራኦል ከውጭ ስልኩን እየጎረጎረ መጥቶ ፊት ለፊቷ ቁጭ አለ…ለረጅም ደቂቃዎች አላናገራትም …

‹‹ይሄን ያህል ምን ቢመስጥህ ነው?››

‹‹ባክሽ የድሮ መስሪያ ቤቴ..ማለቴ ቆርቆሮ ፋብሪካ ምናምን ብዬ አውርቼሽ ነበር አይደል?››

‹‹እ..ስለምትናፍቅህ ልጅ እያወራኸኝ ነው?››

‹‹አዎ ..ትክክክል?››
‹‹እና እሷ ምን ሆነች?››

‹‹እባክሽ ጠፋች…አንድ ብቸኛ ልጃቸው ጠፋችባቸው…ከዛሬ ነገ አገኛታለሁ ብዬ ስቃትት የእህቴንም ልብ ይዛ ጠፋች››

‹‹ጠፋች ማለት?››

‹‹እኔ እንጃ ..ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ነው…ማህበራዊ ሚዲያው ሁሉ ስለእሷ ነው የሚያወራው››

‹‹ስለጠፋች ብቻ?››

‹‹አዎ አባትዬው ያለችበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዬን ብር በሽልማት መልክ እክፍላለሁ ብሎ ስላሳወጀ ምድረ ዱርዬ ጠቅላላ መንገድ ላይ ያገኞትን ወጣት ሴት ሁሉ እያስቆሙ ከእሷ ፎቶ ጋር ማስተያያት ጀመረዋል፡፡››

‹‹እየቀለድክ መሆን አለበት?››
‹‹እውነቴን ነው…አታይውም እንዴ..?››ብሎ ስልኩን አቀበላት… ማህበራዊ ሚዲያውን የተቆጣጠረውን ሁለት ሶስት ፎቶዋን አየች…ውስጧን በረዳት…ግማሽ ፊቷ በፋሻ የተሸፈነ ቢሆንም አስተውሎ ያያት ሰው ሊለያት ይችላል…ፊቷ የተቀመጠው ፊራኦል እስከአሁን እንዴት እንዳለያት ተደንቃለች፡፡
ስልኩን መለሰችለት‹‹ምን ሆና ይሆን …..?የሀብታም ልጅ ነገር ይሄኔ ቀብጣ ሊሆን ይችላል?››ስትል አፏ ላይ እንደመጠላት ተናገረች፡፡

‹‹አይ እንደዛ እንኳን ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም…እሷ የሀብታም ልጅ ስለሆነች ነገሩ ጮኸ እንጂ በየቀኑ እኳ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች እዚህም እዛም ከያሉበት ተወስደው የሚጠለፉበት…በሰው ሚሊዬን ብር የሚጠየቅበት ሀገር ነው እኮ ያለነው….ስንቶች የተጠለፈባቸውን ልጃቸውን ወይም ባላቸውን ለማስመለስ ቤታቸውን ሸጠዋል…?ስንቶች የመኪናቸውን ሊቭሬ አስይዘው አራጣ ተበድረዋል….?.ንብረቱን አሟጦ ሸጦ ከከፈለስ በኋላ ስንቱ ሬሳ ተልኮለታለል…….እዚህ አገር በዚህ ጊዜ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች እንኳን ለማውራት ለማሰብም ይከብዳ…እና ይህቺ ልጅ ምን እንደገጠማት ማንም የሚያውቅ የለም….፡፡››

‹‹እንዲህ አይነት ነገር መኖሩን አላውቅም››

‹‹እንዴ!! ሀገር ውስጥ እየኖርሽ አልነበረም እንዴ…..?ክፍለሀገር ያለች የእናቱን ሞት ሰምቶ ሄዶ መቅበር ያልቻለ ስንት አለ….?ዘመድ ከዘመድ ከተቆራረጠ እኮ ቆየ፣ስንቱ የትውልድ አካባቢውን ሄዶ ለማየት ልክ እንደአውሮፓና አሜሪካ እንደመሄድ ከባድና የማይቻል ሆኖበታል…እና የዚህች ልጅ ቤተሰብ ጭንቀታቸውን ተመልከቺ…ስንቱን ያስባሉ… እህቴ ብትሆንስ ብዬ ሳስብ ዝግንን ይለኛል…እንደውም በቀደም የሰማሁትን ታሪክ ላጫውትሽ…››
በጉጉት ትኩረቷን ወደእሱ አቅንታ‹‹እሺ እየሰማሁህ ነው..››አለች ፡፡

ከአስር ወራት በፊት አዳማ አካባቢ ካለ አንድ የጠበል ቦታ ታጣቂዎቹ ድንገት ይመጡና የተወሰኑ ሰዎች አፍነው ይወስዳሉ፡፡ከተወሰዱት ውስጥ አንዱ ከአርሲ አካባቢ ነው የመጣው…የተጠየቀውን ብር ወላጆቹ በቀላሉ ማሟላት አይችሉም ቢሆንም ተለምኖና ከየሰው ተለቃቅሞ ከተጠየቀው ሩቡን ያህል ብር ለታጣቂዎች ይላክና የልጁ መለቀቅ ይጠበቃል..ግን ከዛሬ ነገ ይመጣል ሲባል ወራቶች ያልፋሉ፣..እናት እንቅልፍ ታጣለች…ቀንና ለሊት ማልቀስ ይሆናል ስራዋ…ልጇ ይኑር ይሙት የምትጠይቀው ሰውና የምታጣራበት መንገድ አልነበራትም…በመጨረሻ ሰው መፍትሔ ያለውን ይነግሯታል…የሞተ ሰው ነፍስ ጠርተው የሚያናግሩ ሰዎች ጋር ይዘዋት ይሄዳሉ…እንደተባለውም የልጇ ነፍስ ሲጠራ ይመጣል..‹‹አዎ እማዬ እኔ ልጅሽ ከሞትኩ 6 ወር አልፎኛል….እርምሽን አውጪ ይላታል››እናትም ወደቤቷ ተመልሳ ድንኳን ጥላ የልጇን እርም ታወጣለች…ዘመድ አዝማድ ሁሉ ለቅሶ ደርሶ እርማቸውን ያወጣሉ..በጣም የሚገርመው ምፀት ደግሞ ምን መሰለሽ እሷን ለቅሶ ለመድረስ ከሚመጡት የቅርብ ዘመዶቾ ውስጥ ሶስቱ ዳግመኛ በታጣቂዎች ተጠልፈው አረፉት፡፡››

ንግግሩ ይበልጥ ሆድ እንዲብሳት አደረጋት..እንባዋን ሊዘረገፍ ሲተናነቃት ተሰማት..
እሱ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹አባዬ ይሄንን ባይሰማ ደስ ይለኛል…ከሰማ በጣም ነው የሚያዝነው….እሷን ሰፈራቸው ድረስ እየሄደ ከመኪና ስትወርድና ከቤት ስትወጣ እንደሚያያት አውቃለው…ልጄን በውስጧ ይዛለች..እሷን ሳያት ልጄ በከፊልም ቢሆን በህይወት እንዳለች ይሰማኝና እፅናናለው ይላል…ይገርምሻል እኔ እራሱ እንዲዚህ እንዳስብ ተፃዕኖ ያደረገብኝ እሱ ነው››

‹‹ይገርማል ….ግን ጋሼ ምን በሩቅ አሳያቸው ማለቴ እቤት ገብተው ቢያዮት እኮ ሰዎቹ የሚቃወሙ አይመስለኝም፡››

አዎ እንዳልሽው አይቃሙም ይሆናል..ግን አባዬ እኛን ፊት ለፊታቸው ካዩ ይሳቀቃሉ…ልጅቷ ፊት ከቀረብን ማልቀሳችን አይቀርም.. እሷ ፊት ማልቀስ ማለት ደግሞ ልጅቷ ልክ በሌላ ሰው ህይወት እንደምትኖር እንድታስብ ማድረግና ልጅቷን መጉዳት ነው….ሁላችንም ከእሷም ሆነ ከቤተሰቡ በስህተት እንኳን መገናኘት የለብንም ብሎ ቁርጥ ያለ ትዕዛዝ ለሁሉም አስተላልፏል…እኔንም ከዛ ፋብሪካ ስራዬን ጥዬ እንድወጣ ያስገደደኝ በዛ ምክንያት ነው፡፡አሁን አሁን ግን ያንን የእሱን ትዕዛዝ ለመጠበቅ እየተቸገርኩ ባለሁበት ሰዓት ነው…ይሄው አንደምታይው ልጅቷ የጠፋችው…››

‹‹‹በቃ ደከመኝ መሰለኝ ትንሽ ልተኛ ››ብላ አልጋ ልብሱን ወደላይ ሳበችና ሙሉ በሙሉ ተሸፈነችና ..በፀጥታ እንባዋን ዘረገፈች…አባትና እናቷ አሳዘኗት….ቢሆንም ለአመታ ያበሳጮትን ብስጭት ልትረሳላቸው አልቻለችም….በውሳኔዋ ፀንታ እስከመጨረሻው መቆየት እንዳለባት ዳግመኛ ወሰነች፡፡‹‹አዎ አሁን እያዩት ያሉት ስቃይ ይገባቸዋል››በማለት በረጅሙ ተነፈሰች፡፡

////
ሰለሞን በሶስተኛው ቀን አርፍዶ ሶስት ሰዓት አካባቢ ወደቢሮ እየሄደ ሳለ ስልኩ ጠራ…የማያውቀው አዲስ ቁጥር ነው…አነሳው፡፡

‹‹ኪያ የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ነው፡፡››ድርጅቱን ኪያ ብሎ የሰየመው አስቴርን ለማስደሰት ስለፈለገ ነበር…አስቴር እናቷ ከመሞታቸው በፊት ‹‹ኪያ ›› እያሉ ነበር የሚጠሯት እሱም አልፎ አልፎ ይሄንን ስም ይጠቀማል…ድርጅት ለመመስረት ሲያስብ ግን ወዲያው በምናብ የመጣለት ስም ይህ ኪያ የሚለው ስም ነው፡፡እንደምንም ብሎ አግብቶ ከእሷ ጋር አንድ ቤት መኖር ሲጀምሩ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በወጥነት ኪያ የሚለውን ስም ይጠቃማል..ሚስቱም ሆነ ድርጅቱ በአንድ ስም ይጠራሉ…ይህ ነው እቅዱ፡፡

ሴሎቹ ሁሉ ተነቃቁ…‹‹በስተመጨረሻ ተሳካ…በስተመጨረሻ የመጀመሪያ ደንበኛዬን አገኘሁ….‹‹ሰሎሞን ጀግና ነህ፣›››ብሎ ተደሰተና ድምፁን ጎርነንና ሻከር አድርጎ፡፡‹‹አዎ ትክክል ኖት..ምን ልታዘዝ?፡፡››ሲል መለሰ፡፡
‹‹እባኮት የቢሮዎትን ትክክለኛ አድርሻ ላስቸግሮት…?››

‹‹ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 3ተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 ፡››

‹‹አመሰግናለው ..ከ15 ደቂቃ በኃላ ደርሳለሁ›› ስልኩ ተዘጋ፡፡
እሱ ደግሞ ቢሮ ለመደርረስ 5 ደቂቃ ብቻ ነው የሚቀረው..
👍819
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ይህቺን ፀሀፊ ልጅ ወዶታል…እሷ እራሷ የመጀመሪያ ደንበኛው ከመሆኗም በላይ ሌላ ደንበኛ አገኝታለታለች፡፡ስልኩን አወጣና ደወለ……አስቴር ጋር…

‹‹እሺ ወንድሜ ደህና ነህ?››

‹‹አለሁልሽ…የላክሻት ልጅ መታለች ልልሽ ነው፡፡››

‹‹እንዴት ነው …ተስማማችሁ?››

‹‹አዎ ጎበዝ ልጅ ትመስላለች››

‹‹ጎበዝ?››

‹‹አዎ ምነው?››

‹‹አይ በአንድ ቀን እንዴት ጎበዝ መሆኗን አወቅክ ?ብዬ ገርሞኝ ነዋ››

‹‹ማለቴ እንዲሁ  ሳያት ተግባቢና ቀልጣፍ ነገር ነች ልልሽ ነው››

‹‹ወንድሜ ፍቅር እንዳይዝህና እንዳትጎዳብኝ…ልጅቷ ፍቀረኛ አላት››

‹‹አይዞሽ አታስቢ አውቃለው፣በዛ ላይ እኔ ማፈቀሪያ ጭንቅላቴ የተበላሸብኝ ሰው ነኝ….››

‹‹ምኑ ነው ምታውቀው?››

‹‹እንዳላት ነዋ››

‹‹ከምኔው?››

‹‹ውይ ኪያ ደግሞ ….በቃ ቻው ማታ ቤት እንገናኝ››

‹‹እሺ ቻው ወንድሜ››በተንከትካች ሳቅ አጅባ ስልኩን ዘጋችው፡፡

////
ወላጇቾ ብቻ ሳይሆኑ ያደገችበትና የእድሜዋን ግማሽ የኖረችበት እቤቷም ጭምር ናፈቃት‹‹ ቤት ማለት..ግን ምን ማለት ነው?ስትል እራሷን ጠየቀችና መልሱን ከአእምሮዋ ውስጥ በርብራ ለማግኘት አይኖቾን ጨፍና ማሰላሰል ጀመረች

‹‹አዎ እቤት ከድንጋይ ወይም ከእንጨት የሚታነፅ የሰው ልጅ መጠለያ ነው።ያንን ህንፃ ከመጠለያነት ወደ ቤትነት የሚቀይረው ግን የታነፀበት ማቴሪያል ጥራትና ውበት አይደለም...ውስጡ ያሉት  ዘመናዊ የቤት እቃዎች እና ውድነትም አይደለም። ህንፃው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነትና የፍቅር ትስስር መጠን ነው ህንፃውን እቤት የሚያደርገው።ለዚህ ነው ከኖርኩበት የተንጣለለ ቪላ ይልቅ አሁን እየኖርኩበት ያለሁት ባለ ሁለት ክፍል ጎስቋላ ቤት የተሻለ የሚሞቀውና የሚደምቀው
››መልሱን ለራሷ ሰጠች፡፡ ቀኑን እንዲሁ በሀሳብና በትካዜ ጊዜውን ብታሳልፍም ሲመሽ ግን ሁሉ ነገር የተለየ ሆነ፡፡

ማታ የቤተሰቡ አባል ጠቅላላ ተሰብስበው በሞቅ ደስታ ከወትሮ በተለየ ድግስ መሰል እራት ቀርቦ በመጎራረስ ከበሉና ቡናም ተጠጥቶ ከተነሳ በኃላ በፀሎት ሽንት ቤት ለመሄድ እንድምትፈልግ ለለሊሴ ነገረቻት…ያሰበችው እሷ ደግፋ እንድትወስዳት ነበር…በተቀራራቢ እድሜ ስለሚገኙ እቤት ውስጥ ካሉ ሰዎች ሁሉ እሷን ማዘዝ ወይም ትብብር መጠየቅ ቀላል ይላታል፡ ….ለሊሴ ግን እንዳሰበችው አላደረገችም….
‹‹ወንድሜ በፀሎትን ሽንት ቤት ትወስዳታላህ?››ብላ ስትጠይቀው ክው ነበር ያለችው….እሱ አንደበት አውጥቶ ፍቃደኝነቱን ሳይናገር በቀጥታ ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳና ወደእሷ በመሄድ ልክ ትናንት ለሊት እንዳደረገው ከስር ሰቅስቆ ልክ እንደህፃን ልጅ አቀፋት….እንዲህ አይነት ሁኔታ በህይወቷ ገጥሞት ስለማያውቅ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እፍረትም ተሰማት…‹‹.ወላጆቹ እንዲህ ሲያቅፈኝ ምን ይላሉ ?››የሚለው ሀሳብ አእምሮዋ ተሰነቀረና ያንን ለማጣራት እይታዋን በቤቱ ዙሪያ ስትሽከረከር ሁሉም በራሳቸው ጫወታ ተመስጠው እርስ በርስ እያወሩ እየተሳሳቁ ነው……አንከብክቦ እንዳቀፋት ይዟት ወጣ
..ቀጥታ ሽንት ቤት ወሰዳና ወደውስጥ አስገብቶ አቆማት…ልክ እንደሌሊቱ ውሀ በሀይላንድ ከቧንቧው ቀድቶ አመጣላትና የሽንት ቤቱን መጋረጃ ወደታች መልሶ ‹‹ስትጨርሺ ጥሪኝ
››ብሎ ከአካባቢው ዞር አለ፡፡

የሽንት ቤት ጣጣዋን ከጨረሰች በኋላ ቀጥታ ወደቤት አይደለም ይዞት የገባው፡፡ልክ እንደለሊቱ ወንበር አመቻችቶ ስለነበር ተሸክሞ ወስዶ አስቀመጣት….‹‹ቀኑን ሙሉ ተኝተሸ ስለዋልሽ አሁን ትንሽ ንፍስ ይንካሽ››

‹‹አዎ ትክክል ነህ፣በዛ ላይ ጨረቃዋም ናፍቃኝ ነበር፡፡››
እሱም ለራሱ መቀመጫ አምቻችቶ ከፊት ለፊቷ እየተቀመጠ‹‹ከጨራቃዋ ጋር ወዳጅ ናችሁ እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አዎ ለዛውም የእድሜ ልክ››

‹‹ያን ያህል ብቸኛ ነሽ ማለት ነው?››

‹‹እንዴት ከጨረቃ ጋር ለመወዳጀጀት ብቸኛ መሆን የግድ ነው እንዴ?››

‹‹አይ የግድ ባይሆንም ከልምዴ ስነሳ ብዙውን ጊዜ ከጨረቃዋ ጋር ለረጅም ጊዜ የማውጋት ልምድ ያላችው እንቅልፍ አልባ ብቸኛ ሰዎች ናቸው……በተለይ በፍቅር የተሰበሩ››

‹‹እንዴ በፍቅር የተሰበሩ ነው ያልከው..አይ እንደዛ እንኳን አይደለም…..ባይሆን እንዳልከው ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ በሚፈጠር ብቸኝነት ብንለው የተሻለ ነው..የፍቅር ጉዳይማ ቢሆን በምን እድሌ..ፍቅር እኮ በጣም ምርጥ ነገር ነው፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ… ፍቅር በጣም ወሳኝ ስሜት ነው….አንድ ሰው ሩሚን ‹‹ፍቅር ምንድነው?››ብሎ ጠየቀ።ሩሚም ..‹‹ፍቅር ምን እንደሆነ ትክክለኛ ትርጉሙን ልታውቅ የምትችለው ውስጡ መጥፋት ስትችል ነው።›› ብሎ መለሰለት…..፡፡

‹‹አዎ ትክክለኛ አባባል ይመስለኛል….ፍቅር የምትተነትነውና የምታወራው ነገር አይደለም፣ፍቅር ኖረህ የምታጣጥመው የተቀደሰ ስሜት ነው….በፍቅር መጥፋት ጥሩ አባባል ነው››

‹‹አይ ጥሩ…ለማንኛውም ለደቂቃም ቢሆን እስቲ ከጨረቃዋ ጋር ብቻችሁን ልተዋችሁ…. መጣሁ›› ብሎ ተነስቶ ወደቤት ገባ..እሷ አይኖቾን ወደላይ አንጋጠጠች…ሰማዩ ጥርት ብሎ ይታያል ፡፡ጨረቃዋ ሙሉ ክብ ሆና ደፍናለች..ዙሪያዋን የተበተኑና ከዋክብቶች ብልጭ ድርግም እያሉ ይታያሉ…አናትና አባቷ ትዝ አሏት..ይሄኔ የእሷን መጥፋት ምክንያት በማድረግ የመጨረሻውን ጥል እየተጣሉና የመጨረሻ የተባለውን አንጀት በጣሽ ስድብ
እየተደሰዳደብ እንደሆነ በምናቧ አሰበችና ሙሉ ሰውነቷ ሽምቅቅ አለባት..ሰውነቷ ሲሸማቀቅ ደግሞ የእግሯ ሆነ የፊቷ ጥዝጣዜ ህመም ተቀሰቀሰባት….
ድንገት የሰማችው ድምፅ ነው ከሀሳቧ ያባነናት…..ያልገመተችውን ነገር ነው እያየች ያለችው..ፊራኦል ፊት ለፊቷ ቅድም የነበረበት ቦታ ቁጭ ብሎ ክራር እየከረከረ የሙሀመድ አህመድን የትዝታ ሙዚቃ ያንቆረቁራል….ፍዝዝ ብላ በፍፁም ተመስጦ ታዳምጠው ጀመር፡፡
ስንቱን አስታወስኩት…ስንቱን አስብኩት ልቤን በትዝታ ወዲያ እየላኩት
አንዴ በመከራ …አንዴ በደስታዬ ስንቱን ያሳየኛል ..ይሄ ትዝታዬ

በድምፁ ድንዝዝ ብላ ጠፋች………… የትናንቱ ፍቅር ….ጣሙ ቁም ነገሩ ምነው ያስተዋሉት ያዩት በነገሩ
ሁሉም እንደገና ኑሮን ቢያሰላስል አይገኝም ጊዜ ያኔን የሚመስል፡፡

ዘፈኑን ሲጨርስ‹‹አንተ..አንድ ሺ አመት በዚህ ምድር ላይ ኖረህ ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ያለውን ጊዜ ናፍቀህ የምትተክዝ እድሜ ጠገብ አዛውንት ነው የምትመስለው፡፡››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡

‹‹ያን ያህል?››

‹‹አዎ …ድምፅህ በጣም ግሩም ነው….ሙዚቃ ትሰራለህ እንዴ?››

‹‹አይ ያን ያህል እንኳን ሰራለሁ ማለት አልችልም …በፊት በፊት ቀበሌ ኪነት ከጓደኞቼ ጋር እሞክር ነበር አሁን ከህይወት ሩጫ ጋር አብሮ አልሄድ አለኝና ተውኩት፣እንዲህ አንደዛሬው ጨረቃዋ ሙሉ ስትሆን እንዲህ እቀመጥና ለእሷ አዜምለታለው፡፡››

‹‹እንዴ..ለእኔ የዘፈንክልኝ መስሎኝ ውስጤ በደስታ ተፍነክንኮ ነበር ..ለካ ለጨረቃዋ የተዘፈነውን ዘፈን ነው ሳይፈቀድልኝ የሰማሁት…..››

‹‹አይ እንደዛ አንኳን ለማለት አልችልም…የዛሬው ዘፈን ቀጥታ ላንቺ ነው..ምስጋናና ይቅርታ ለመጠየቅ፡ ብዬ ነው የዘፈንኩት፡፡››

‹‹አልገባኝም..ይቅርታውስ ለምን ?ምስጋናውስ?፡፡››

‹‹ይቅርታው ገና ስትመጪ ጀምሮ በሙሉ ልቤ ስላልተቀበልኩሽና ለእኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ እንደሸክም ስለቆጠርኩሽ…ምስጋናው ዛሬ እናቴንም ሆና መላ ቤተሰብን አንበሽብሸሽ በማስደሰትሽ…..››
👍7918😱1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አቶ ለሜቻ ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ነው..፡፡የቤቱ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ተሸብሯል…፡፡በፀሎት የምትገባበት ጠፍቷት አብራቸው እንባዋን እያረገፈች ነው፡፡፡ልጃቸው ፊራኦል ላጠፋው ጥፋት አባትዬው ይቅር እንዲሉት በጉልበቱ ተንበርክኮ እየለመናቸው ነው፡፡

‹‹ልጄ ይቅር የምልህ..እያንዳንዱን የገዘኸውን ዕቃ ወይ በየገዛበት መልሰህ ካልሆነም ለሌላ በመሸጥ ገንዘቡን አንድም ሳታጎድል ለልጅቷ ስትመልስ ነው፡፡››

‹‹እሺ አባዬ እንዳልክ አደርጋለው፡፡››

‹‹እኮ ተነስና አድርግ››

‹‹አሁን እኮ መሽቷል….ነገ በጥዋት ተነስቼ እንዳልከው አደርጋለው››

‹‹እስከዛው ላይህ አልፈልግም፣ወይ ቤቱን ለቀህ ውጣ ወይ እኔ ልልቀቅልህ››

‹‹አረ አባዬ… አንተ ምን በወጣህ እኔ ወጣለሁ….››ብሎ ከተቀመጠበት ሲነሳ በፀሎት ከተቀመጠችበት ሆና ጣልቃ ገባች…ጋሼ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ሀሳብ ነው….ቆርቆሮውም..ሲሚንቶውም ሁሉም የተገዛው በእኔ ሀሳብ ነው፡፡በወቅቱ እሱ እንደማይሆን ነገሮኝ ተቃውሞኝ ነበር..እኔ ነኝ ያስገደድኩት…ስለዚህ ወቀሳውም ቅጣቱም የሚገባው ለእኔ ነው…ለሊሴ ታክሲ ልትጠሪልኝ ትችያለሽ?››

ጥያቄዋ ሁሉንም ሰው አስደነገጠ፡፡

‹‹እንዴ ታክሲ ምን ሊያደርግልሽ?››ለሊሴ ጠየቀች፡፡

‹‹የጋሼን ቅጣት ተግባራዊ ለማድረግ ነዋ…ሆቴል ድረስ የሚወስደኝ ታክሲ ጥሪልኝ…ከቤት መባረር ያለብኝ እኔ ነኝ››

‹‹ተይ እንጂ ልጄ..ለምን ጡር ውስጥ ታስገቢኛለሽ?››አቶ ለሜቻ ለዘብ ብለው ተናገሩ

‹‹ጋሼ ..ይሄ ምንም ጡር አይደለም…ይሄንን እቃ ያስገዛሁት ለራሴ ስል ነው….ያው እንደምታዩት በዚህ አያያዜ ለመዳን ሁለትና ሶስት ወር ይፈጅብኛል ..ከዳንኩ በኋላም ቶሎ የምሄድበት ቦታ ስለሌለኝ ከእናንተ ጋር ቢያንስ ስድስት ወር ኖራለው..ስድስት ወር ሙሉ ደግሞ እንዲህ የለሊሴን መኝታ አስለቅቄ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ከባድ ስለሆነ ነው

ሀሳብን ያመጣሁት..እኔ እንደውም ቤቱን ተረባርበን በአንድ ወር ውስጥ አልቆ እኔ ከእነለሊሴ ጋር እኖርበታለው ብዬ ነው››ስትል አብራራች፡፡

‹‹ልጄ ቢሆንም አግባብ አይለም..በእኛ ላይ ይሄን ሁሉ ብር መከስከስ እኛም አሜን ብለን መቀበል ነውር ነው…ሰውን ተይው …እግዚያብሄሩስ ምን ይለናል?››
‹‹አሁን ልጅህ ለሊሴ ብር አግኝታ እንዲህ ብታደርግ ይሄን ያህል ትበሳጭባታለህ?›› ዝም አሉ
‹‹ገባኝ አትበሳጭባትም….እኔንም እንደልጅህ አድርገህ ከምር ብትቀበለኝ ኖሮ ይሄን ያህል ቅር አትሰኝም ነበር..በቃ ለሊሴ ደውለሽ ታክሲውን ጥሪልኝ››
ለሊሴ  ፈራ  ተባ  እለች…  ስልኳን  ከተቀመጠበት  አነሳችና  ለመደወል  ስትዘጋጅ  ጋሽ ለሜቻ‹‹ልጄ ስልኩን አስቀምጪው..እስኪ ሁላችሁም ተቀመጡና እንረጋጋ…››

‹‹አዎ  ልጆች  ሁላችሁም  ተቀምጡ….ለሊሴ  እስኪ  ሲኒውን  አቀራርቢና  ቢና እናፍላ››እናትዬው ውጥረቱ ረገብ ስላለ ተደስተው የተናገሩት ነበር፡፡
////
በማግስቱ

‹‹…አየሩ በጥላቻ ጥላሸት ጠቁሯል፡፡ከፍቅር ዕጦት በሚመጣ የፍራቻ ግንብ ተከልያለው….በንዴቴ አጥር ስር ተሸሽጌ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡ይበርደኛል..አዎ በጠራራ ፀሀይ ይበርደኛል…ይርበኛል..እየበላው ሁሉ ይረበኛል….፡፡ጉሮሮዬ በጥማት ተሰነጣጥቆል….ግን ከዛ ከጥማቴ የሚፈውሰኝ ውሀም ሆነ ምድራዊ ወይን የለም፡፡››በፀሎት ነች የምታወራው…ፊራኦል ግን ምንም አልገባውም

‹‹አንዳንዴ እንደፈላስፋ ነው የምታወሪው?››

‹‹እንደእኔ ህይወትህን ሙሉ በብቸኝነት በራፍ ዘግተህ ለብዙ ሰዓታት በትካዜና በቁዘማ የምታሳልፍ ከሆነ ወደፈላስፋነት መቀየርህ የግድ ነው፡፡ከሞት ደጃፍ ደርሶ..በቃ አበቃልኝ ብሎ ተስፋ ከቆረጠ በኃላ ወደህይወት ተመልሶ ሁለተኛ እድል የተሰጠው እደእኔ አይነት ሰው ነገሮችን በተለየ መልክ ባያይ ነው የሚገርመው፡፡›››

‹‹አልገባኝም የሞት አፋፍ ላይ መድረስ ስትይ?››

ደነገጠች..አንደበቷን አንሸራቷት ሚስጥር ልታወጣ በመድረሶ እራሷን ወቀሰችና‹‹ማለቴ በዛ ለሊት በሞተሬ ከእዚህ በራፍ ጋር ስለ መጋጨቴ እያወራው ነው…የሞትኩ ማስሎኝ ነበር እኮ››

‹‹እ..እሱ እንኳን እውነትሽን ነው….ግን አሁን ፊትሽ ቁስሉ ደርቆል እኮ …ለምን ቀንና ለሊት በሻርፕ ትሸፍኚዋለሽ…››

‹‹እርግጥ እንዳልከው ድኗል ግን ጠባሳው ያስጠላል..እንዲህ ሆኜ ሰው እንዲያየኝ አልፈልግም ..በተለይ ወንዶች ››
ፈገግ አለ….‹‹ዝም ብለሽ እያካበድሽው ነው እንጂ እርግጠኛ ነኝ ከነጠባሳሽ በጣም ቆንጆ ልጅ ነሽ…እንደውም እንዲሁ አቋምሽን ሳየው የት እንደሆነ የማውቃት አርቲስት ወይም ሞዴል ነገር እየመሰልሽኝ ደነግጣለው፡፡››

‹‹አየህ አንደውም ለዚህ ነው ፊቴን ዘወትር በሻርፕ ምጆብነው››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ሙሉ በሙሉ ገልጬልህ ፊቴን በደንብ ካየኸው የትኛዋ ሞዴል ወይ አርቲስት እንደሆንኩ ወዲያው ስለምትለየኝ፣እንደዛ እንዳይሆን ስለፈለኩ ነው››

‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››

‹‹ምን ላድርግ ብለህ ነው….በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ እንደእኔ አይነት ሰው ባይቀልድ ነው የሚገርመው››

‹‹እስኪ እርእሱን እንቀይር ፣ሌላው ስለአንቺ የሚገርመኝ  እስከአሁን ሞባይል ይዘሽ አለማየቴ ነው››

‹‹የለኝም…..ማለቴ ከቤቴ ስወጣ ይዤ መውጣት አልቻልኩም፡፡››

‹‹ታዲያ  ልግዛልሽ…ማለቴ  በራስሽው  ብር  የምትፈልጊውን  አይነት  ስልክ  ልገዛልሽ እችላለሁ፡፡››

ፈገግ አለችና‹‹በራስህ ብር ብትገዛልኝ አይሻልም?››

‹‹ደስ ይለኝ ነበር..ግን አቅሜ ላንቺ የሚመጥን ስልክ ለመግዛት በቂ አይመስለኝም…››

‹‹የእኔ አቅም ምን ያህል ነው..?በምንስ ሚዛን ለካሀው…?ለማንኛውም ለጊዜው አያስፈልገኝም…ስፈልግ ግን ነግርሀለው፡፡››

‹‹ይገርማል… በአንቺ እድሜ ያለች ሴት ስልክ አያስፈልገኝም ስትል አጃኢብ ነው፡፡››

‹‹ምኑ ይገርማል..?ለጊዜው ማንም ጋር ለመደወል እቅድ የለኝም..››

‹‹ሶሻል ሚዲያስ….እንዴት ያስችልሻል፡፡››

‹‹ዕድሜዬን ሙሉ ስልክና ላፕቶፕ ላይ አረ አንቺ ልጅ አይንሽ ይጠፋል እየተባልኩ እስክሪን ላይ አፍጥቼ ነው የኖርኩት…ሶሻል ሚዲያ ከጨለማ ሀሳቦቼ እና ከድብርቶቼ መሸሺጊያ እና መደበቂያ ዋሻዬ  ነበር…አሁን  ግን ችግሮቼን ፊት ለፊት መጋፈጥ  ነው የምፈልገው

….እስከአሁን ከኖሩኩት ህይወት በተቃራኒ ነው መኖር የምፈልገው፡፡ይልቅ ከቻልክ ነገ መፅሀፎች ገዝተህልኝ ትመጣለህ፡፡››

‹‹እሺ ምን ምን መፅሀፍ እንደምትፈልጊ ትንግሪኝና ገዝቼልሽ መጣለው፡፡››

‹‹ጥሩ አሁን ደግሞ ምርጥ አንድ ሙዚቃ ብትጋብዘኝ በጣም ደስተኛ እሆናለው…››
‹‹ጥሩ …አለና ከአጠገቡ ያለውን ክራር አንስቶ ክሮቹን በእጁ እያጠበቀ እና እያላላ ቅኝቱን አስተካከለና‹‹ምን አይነት ዘፈን ይሁንልሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹መቼስ በዚህ ውድቅት ለሊት ስለሀገር ዝፈንልኝ አልልህም…የፍቅር ዘፈን ይሁንልኝ፡፡›› እንደማሰብ አለና ክራሩን መገዝገዝ ጀመረ ..አፏን ከፍታ ነበር የምታዳምጠው…
የነገን ማወቅ ፈለኩኝ … መጪውን አሁን ናፈቅኩኝ.. የፍቅር ምርጫዬ አንቺ ነሽ…ልቤንም መንፈሴን የገዛሽ ወሰንኩኝ ልረታ አስቤ፣አካሌን መንፈሴን ሰብስቤ

በፍቅር ህይወቴን ላኖረው..ላልመኝ ፍፁም ሌላ ሰው የፍቅርን ትርጉም ገልፀሸ አስተማርሺኝ
ካንቺ ደስታ ፣እኔን እያስቀደምሺልኝ ፍቅር ለካ ለራስ …ማለት እንዳልሆነ ስታደርጊው አይቶ… ልቤ በቃ አመነ ከነገርሽ…. ባህሪሽ ማርኮኛል…
👍6321🥰1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

እለቱ እሁድ ነው፡፡ከፊራኦል ጋር ለመውጣት ስለተነጋገሩ እየተዘጋጀች ነው፡፡ለሊሴ እየረዳቻት ነው፡፡
ሰው ከለገመ ከሻማ በላይ በቀላሉ ቀልጦ የሚጠፋ ከጠነከረ ደግሞ ከአልማዝም በላይ ማይቆረጥና ማይሸረፋ ተአምራዊ ፍጡር መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡በፀሎትም የማያልፍ የመሰላት አሰቃይ ህመም በጥቂት ቀናት ውስጥ ጥሏት ሄዶ ንፅህና ጤነኛ ልጅ ሆናለች፡፡የእግሯን ስብራት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ድኗል…የፊቷ ቁስል ግን ምንም እንኳን ቢድንም ጣባሳውና ቁስለቱ አሁንም በግልጽ ፊቷ ላይ ይታያል… በዚህ ምክንያት አሳባ ከፊል ፊቷን ሁሌ በሻርፕ እንደሸፈነችው ነው፡፡ዋና ምክንያቷ ግን ማንነቷ በቀላሉ እንዳይለይ በማሰብ ነው፡፡አሁንም ተመሳሳይ አለባበስ አድርጋ በዛ ላይ ጥቁር መነፅር አይኗ ላይ ሰክታ ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ግን እህቴ ለምንድነው እኔን የማታስከትሉት?››ለሊሴ ተነጫነጨች፡፡

‹‹አይ …መጀመሪያ ከወንድሜ ጋር የምንሄድበት ቦታ አለ…ባይሆን ከዛ ቶሎ ከጨረስን እንደውልልሽና ትቀላቀይናለሽ››

‹‹ይሁንላች ግን ታበሳጭቼባችኋለሁ››

በታክሲ ከሰፈር ሁለት ፌርማታ ያህል ርቀው ከሄዱ በኃላ ‹‹ደርሰናል እንውረድ›› አላት፡፡ያን ያህል ቅርብ ይሆናል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡እንደወረዱ ቀጥታ ፊት ለፊት የሚገኝ በፅድና በባህርዛፍ አፅድ የደመቀ ሰፊ መናፈሻ ውስጥ ነው ይዞት የገባው…ቀጥታ ከሰው ነጠል ያለ ቦታ ይዞት ሄደና ቁጭ እንድትል መቀመጫ አመቻችቶላት ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ‹‹እሺ ምን ትጠቀሚያለሽ?››

‹‹ቆይ እስኪ… ምን አስቸኮለህ…መጀመሪያ ትምጣ››

‹‹ማን?››

‹‹ምን ….ማንን ልናገኝ ነው የመጣነው…?ፍቅረኛህ ነቻ…በል ደውልላት፡፡››

‹‹ስልክ የላትም››

‹‹ታዲያ እንዴት ነው የምታገኘን››
‹‹የልቤን ምት አዳምጣ ትመጣለች››

‹‹ጥሩ ትቀልዳለህ….ይሄ የተለመደ መገናኛ ቦታችሁ ነው ማለት ነው…ገባኝ›› አስተናጋጁ መጣችና‹‹ምን ልታዘዝ ?››ብላ ጠየቀች፡፡

በፀሎት ቀደም ብላ‹‹ሰው እየጠበቅን ነው….››ብላ ለአስተናጋጆ መለሰችላት

‹‹አይ አሷን አንጠብቅም..ቆንጆ ፒዛ አሰሪልን…ፒዛው እስኪደርስ እሷም ትደርሳለች››

አስተናጋጆ ትዕዛዙን ተቀብላ ሄደች፡፡

ፊራኦል ወደእሷ አትኩሮ እያያት…..‹‹እስኪ ሻርፑን አንሺው››በማለት ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት

‹‹እንዴ ለምን?››

‹‹ሙሉ ፊትሽን ለማየት ፈልጌ››

‹‹ኖ ዌይ…..›

‹‹ምን ችግር አለው?››

‹‹እኔ  እራሴ  ሙሉ  በሙሉ  ፊቴ  እንደዳነ  እና  እንደማያስጠላ  እርግጠኛ  ስሆን እገልጠዋለው፡፡››

‹አንቺ እንዴት ልታስጠይ ትችያለሽ…ውብ እኮ ነሽ››

‹‹ሙሉ ፊቴን ሳታይ ውብ መሆኔን በምን አወቅክ…?››ኮስተር ብላ በመገረም ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔ እንጃ ውብ እንደሆንሽ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡››

መልስ ልትሰጠው አፏን ስትከፍት አስተናጋጇ የታዘዘውን ፒዛ ይዛ ፊታቸው ስታስቀምጥ አፏን ያለምንም ንግግር ከደነች፡፡

‹‹‹ለእኔ እስፕራይት አምጪልኝ…..ላንቺስ ?›

‹‹እንዴ ልጅቷ ሳትመጣ….?››
‹‹ባክሽ የሆነ ነገር እዘዢ እሷ ስትመጣ የራሷን ነገር ታዛለች››

ግራ እየገባት አዘዘች …ፒዛውን ቆርሶ መብላት ሲጀምር ፣ በገረሜታ ተከተለችው… በልተው ጨርሰው እንኳን ልጅቷ አልመጣችም››

‹‹እንደዛ  ቅኔ  ምትቀኝላት  ልጅ  እስከአሁን  ካልመጣች  ከአሁን  ወዲያም  የምትመጣ አይመስለኝም፡፡››

‹‹መጣችእኮ››

‹‹የታለች?››

‹‹ይህቹት ፊት ለፊቴ ቁጭ ብላ እያወራቺኝ ነው፡፡››

‹‹እየቀለድክብኝ ነው እንዴ?››

‹‹እሺ አትበሳጪ..እኔ ምንም አይነት ፍቅረኛ የለኝም….አንቺን ወጣ አድርጌ ማዝናናት ስለፈለኩ ነው እንደዛ ያልኩሽ››

‹‹አንተ ውሸታም……..ቆይ ምንም ፍቅረኛ ሳይኖርህ ነው እንደዛ ፈዘህ በውድቅት ለሊት ቅኔ ስትዘርፍ የነበረው››

‹‹በተጨባጭ ፍቅረኛ የለኝም አልኩሽ እንጂ በምናቤ ስዬ የማስባት ሴት የለችም አላልኩሽም…..እንደዛ አወራ የነበረው በልቤ ውስጥ ተንሰራፍታ የተቀመጠችውን ልክ እንደአንቺ ውብ የሆነችውን ልጅ እያሰብኩ ነበር››

‹‹ምን አይነት አዝግ ልጅ ነህ….?እኔ ደግሞ እንዴት አይነት ቆንጆ ልጅ ትሆን እያልኩ ለሊቱን ሙሉ ሳስብና ስጓጓ ማደሬ››

‹‹ምን ያጓጓሻል…የፈለገ ውብ ብትሆን ካንቺ አትበልጥ…አንቺ እኮ ሁለመናሽ ውብ ነው…ማለት ስብዕናሽ ፖስቸርሽ..እርግጠኛ ነኝ መልክሽም ውብ ነው..ፍቅረኛዬ ልክ አንቺን ካልመሰለች ልቤን ማሸነፍ አትችልም››ፊራኦል ቀጥታ መንገር ፈርቶ ነው እንጂ ከበፀሎት ፍቅር ከያዘው ሰነባብቷል…ስሩ ሆና እራሱ ትናፍቀው ከጀመረች ቆይታለች..ለዛ ነው ሙሉ ፊቷን ማየት በጣም የናፈቀው…ቆንጆና ውብ ፊት ነው በምናቡ የሳለው…
‹‹ጥሩ ..ግን ስለውበትና ቁንጅና እኮ በእህትና በወንድም መካከል የሚወራ ኮንሰፕት አይደለም…..ባምርም ባስጠላም እንደእህትህ ነኝ…ለውጥ አያመጣም፡፡››

‹‹እንደእህት እና እህት ግን ይለያያል››

ለዚህ ንግግሩ ምን ብላ መልስ ልትሰጠው እንደምትችል ሊመጣላት አልቻለም…‹‹.እኔ የእህትህን ልብ በውስጤ የተሸከምኩ ሴት መሆኔን ብታውቅ ይሄን ሁሉ ርቀት ለመጓዝ አይዳዳህም ነበር››ስትል በውስጧ አብሰለሰለች

//////

በማግስቱ-----
እቤት ውስጥ ማንም የለም..ሌንሳ ብቻ ከበፀሎት ጎን ቁጭ ብላ እያወራቻት ነው፡፡
እህቴ ስራ በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ሆኜያለው….ይገርምሻል ፀሀፊ ሆናለው ብዬ አንድም ቀን ኣስቤ አላውቅም ነበር…››

‹‹ላንቺ እኔ በጣም ደስ ብሎኛል… ስራውን ግን እንዴት ነው..እየለመድሽው ነው? ››

‹‹አሪፍ ነው ..ተመችቶኛል፡፡››
‹‹የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ነው ያልሽው?››

‹‹አዎ እህቴ …ብታይ ሰውዬው ማለቴ አለቃዬ በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡››

‹‹ለምንድነው የሚያሰዝነው? እሱም ፍቅር ይዞታል እንዴ?፡፡››

‹‹አይ እሱን አላውቅም … ያሳዝናል ያልኩሽ…ምንም ደንበኛ የለውም….ዝም ብለን እኔና እሱ ቢሮ ውስጥ ተፋጠን ነው የምንውለው…››ለምን ያሳዝናል እንዳለች ታስረዳት ጀመር፡፡

‹‹ምነው በስራው ጎበዝ አይደለም እንዴ?››

‹‹አረ በቅርብ ነው ከውጭ የመጣው..በሞያው ኤክስፐርት ነው…እንደነገረኝ ከሆነ አሜሪካ እያለ በሞያው ከሶስት አመት በላይ ሰርቶ በጣም ብዙ ሰዎችን ረዳቷል …እዚህ መጥቶ የራሱን ድርጅት ቢከፍትም እንዳሰበው አልሆነለትም….እንደምታውቂው የእኛ ሰው ድብቅ ነው …ባለትዳሮችም ቢሆኑ እዛው ቤታቸው ውስጥ ሲቋሰሉ ይኖራታል እንጂ ገበናቸውን ወደአደባባይ ማውጣት አያስብትም ..ባስ ቢልባቸው እንኳን እዛው የሰፈር ሽማጊሌ ጠርተው በምስክር ፊት ይጨቃጨቃሉ እንጂ ወደባለሞያ አይሄዱም፡፡ለዚህ ጉዳይ ባለሞያም እንዳለው የሚያውቅ የማህበረሰብ ክፍል አንድ ፐርሰንት የሚሞላ አይመስለኝም፡
‹‹ታዲያ እኮ የሰፈር ሽምግልናው ቀላል ነገር አይምሰለሽ…ሁለቱም ለእኛ ጥሩ ያስባል እና ያስማማናል የሚሉትን ሰው በማሀከላቸው አስቀምጠው ችግራቸውን በግልፅ በመነጋገር
ለመፍታት መሞከር ትልቅ ዋጋ ያለው ማህበራዊ እሴታችን ነው፡፡በዚህም መንገድ በጣም በርካታ ሺ ትዳሮች በየአመቱ ስንጥቃቸው ይደፈናል ስብራታቸው ይጠገናል፡፡››
👍6713🥰8👏3😱1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰላሞን የሆነ ሰው እየተጫወተበት እንደሆነ ነው የተረዳው‹‹ግን ማን ነው እንዲህ ያለ ጫወታ ከእኔ ጋር ለመጫወት የሚደፍረው?››በዙሪያው ያሉ ሰዎችን እያሰበ እራሱን እስኪያመው ቢያስጨንቅ በዙሪያው ካሉ ሰዎች እንዲህ መላ ቅጡ የጠፋበት ቀልድ ከእሱ ጋር ለመቃለድ የሚሞከር ሰው ሊመጣለት አልቻለም፡፡

ነገሩ ቀልድ እንዳልሆነ የተረዳው ልክ በተነገረው መሰረት ከሶስት ቀን በኃላ ተመሳሳይ ስልክ ሲደወልለት ነው፡፡በጉጉት አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ..አወቅከኝ?››

‹‹መሰለኝ… አደናጋሪዋ ልጅ ነሽ አይደል?››

‹‹መሰለኝ….የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ?››

‹‹ምን ለማድረግ?››

‹‹በተነጋገርነው መሰረት ስራ ማስጀመሪያ መቶ ሺ ብሩን እንድልክልህ ነዋ››

‹‹እንዴ? ስራው ምን እንደሆነ ሳላውቅ…ልስራው አልስራው መወሰን የምችለው እኮ ስራውን ሳውቅ ነው…መጀመሪያ በአካል ተገናኝነተን ስለስራው ማውራት አለብን››

‹‹ለጊዜው በአካል ላገኝህ አልችልም…ስራው በአባትና እናቴ መካከል ያለውን ችግር መቅረፍ ነው…እናትና አባቴ ያለፉትን 28 አመታት በጋብቻ አሳልፈዋል….እኔ ሀያ አንድ አመቴን ጨርሼ 22 ዓመት ውስጥ ነኝ…በእድሜዬ አንድም ቀን ሰላም ሆነው አይቻቸው አላውቅም…መኝታ  ለይተው  በየራሳቸው  መኝታ  ቤት  ነው  የሚያድሩት….ሁል  ጊዜ
እንደተጣሉና እንደተጨቃጨቁ ነው.ከዛም አልፎ አንዱ ሌለኛውን ለማስወገድም እስከመፈለግ የሚያደርስ ጥላቻ በመካከላቸው አለ..ወይ አይፋቱ ወይ እንደሰው የእውነት አብረው አይኖሩ፣….እና የፈለኩህ ይሄንን የሻገተና የበሰበሰ ጋብቻ የበሰበሰውን ቅጠል ከላዩ አራግፈህ የደረቀውን የጋብቻ ግንድ ቆርጠህ ከስር አዲስ የፍቅር ቅርንጫፍ እንዲያቆጠቁጥ እንድታደርግ ነው…ቢያንስ እንደባለትዳር መልሰው መተቃቀፍ ባይችሉ እራሱ እንደጓደኛሞች እንዲጨባበጡ ማድረግ እንድትችል ነው፡፡ይሄ ጉዳይ የእኔ የህይወቴ ትልቁ አላማ ነው…እባክህ ይሄንን ጉዳይ እንደጉዳይህ ልትይዘው ትችላለህ….?›››

‹‹በእውነቱ ከጠበቅኩት በተቃራኒ የሆነ መሳጭ ነገር እየነገርሺን ስለሆነ ቀልቤን ገዝተሸዋል…የምትይውን በደንብ እየተከታተልኩሽ ነው፡፡፡ለመሆኑ እኔን የምታናግሪው አባትሽ ወክለሽ ነው ወይስ እናትሽን…..?ማለት እኔን ለስራው እንድታናግሪኝ የጠየቀሽ ማን ነው?፡፡››

‹‹በእውነቱ ሁለቱም ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር የለም….›

‹‹ይሄ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ ያደርገዋል..እሺ ቆይ ለመሆኑ እኔን ለምን…?እንዴት እኔን መረጥሽ?››

‹‹ለጊዜው ማንነቱን ልነግርህ የማልችለው አንድ አንተን የሚያውቅ ሰው ነው ሰለአንተ በሆነ ጉዳይ አንስተን ስንጨዋወት በጋብቻ ጉዳይ ላይ እንደምትሰራና በጉብዝናህም እንደሚተማመንብህ የነገረኝ..እንዳአጋጣ ሚ ሆኖ ደግሞ ያንን ሰው እኔ አምነዋለው…እሱ ጎበዝ ነህ ካለህ ጎበዝ ነህ ማለት ነው…

ተመለሰልህ?፡››

‹‹በከፊል አዎ…ግን እንደነገርሺኝ በወላጆችሽ መካከል ያለው ችግር ለረጅም አመት የተከማቸ የተወሳሰበና ዘርፈ ብዙም ነው፡፡››

‹‹በትክክል ገልፀኸዋል››

‹‹ችግሩ ምን መሰለሽ..በቀደም እንደነገርኩሽ አንድ የጋብቻ አማካሪ በጋብቻ መካከል የተፈጠረ ችግርን ለመፍታት የሚችለው ሁለቱም ተጋቢዎች በመሀከላቸው ችግር እንዳለ አምነው ያንን ለማስተካከል ከአማካሪው ጋር ለመተባበር ሙሉ ፍቃደኛ ሲሆኑ ብቻ ነው…አሁን ያንቺን ጉዳይ ስንመለከት ወላጆችሽ ጉዳዩን እንኳን አያውቁትም..ቢያውቁትም ፈፅሞ ከእኔ ጋር ለመስራት ላይቀበሉት ይችላሉ.››.

‹‹እሱን ለእኔ ተወውና አሁን የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ… ገንዘቡን ትራንስፈር ላድርግልህ››

‹‹ይሄውልሽ ፣እኔ በነገርሺን ታሪክ በጣም ተስቤያለሁ…አንድ ወጣት ሴት በወላጆቾ ግንኙነት ተረብሻ እንዲህ ነገሮችን ለማስተካከል ስትጥር እኔም የበኩሌን እገዛ ለማድረግ ፍጽም ፍቃደኛ ነኝ..እዚህ ላይ ዋናው ገንዘብ አይደለም.. እሱ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው…አሁን መጀመሪያ አንቺ ራስሽ ወላጆችሽን ከቻልሽ አንድ ላይ አስቀምጠሸ ካልሆነም ለየብቻ ያሰብሽውን ንገሪያቸውና ለማሳመን ሞክሪ..እነሱ ፍቃደኛ ከሆኑ በኃላ ደውይልኝ..ከዛ ፕሮግራም እናወጣና ያለውን ችግር እያየን ለማስተካከል እንሞክራለን፡፡››

‹‹እነሱን በቀጥታ ማናገር አልችልም››

‹‹ለምን?››

‹‹ስሜ በፀሎት ኃይለልኡል ይባላል››

‹‹እሺ በፀሎት…ለምንድነው ወላጆችሽን ማናገር የማትችይው..?እነሱን ማናገር የማትቺይ ከሆነ እንዴት አድርጌ ነው ወላጆችሽን መርዳት የምችለው?››

‹‹ማለት ስሜን የነገርኩህ ስለእኔ የተወሰነ መረጃ እንዲኖርህ ነው..በፀሎት ኃይለልኡል በልና ድህረገፆች ላይ ወይም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፈልግ ..ከ30 ደቂቃ በኃላ መልሼ ደውልልሀለው፡፡››አለችና ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋችበት፡፡

ስልኩ ቢዘጋም እሱ ግን ስልኩ ላይ እንዳፈጠጠ ነው…የገባው የመሰለው የልጅቷ ሁኔታ መልሶ እየተበታተነበት ነው‹‹…ድህረ-ገፅ ላይ ስለእሷ ምን…?ታዋቂ ሰው ነች ማለት ነው…?››

ጎግል ከፍቶ ››በፀሎት ኃይለመለኮት››ብሎ ሰርች መድረግ ጀመረ..በርካታ መረጃዎች ተዘረገፉ….እውነትም ይህቺ ልጅ ታዋቂ ነች መሰለኝ..ብሎ የመጀመሪያውን ሲያነብ

‹‹የታዋቂ ቢሊዬነሩ የኃይለመለኮት ብቸኛ ወራሽ በውድቅት ለሊት ከቤት ወጥታ ከጠፋች 14 ቀን አልፏታል፡፡››

‹‹ታዋቂው ቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ በፀሎት ለምን ከቤቷ ጠፋች?››
‹‹በጸሎት ኃይለመለኮትን ያለችበትን የጠቆመ የ5 ሚሊዬን ብር  ሽልማት እንደሚሸልሙ አባቷ ለፋና ቴልቨዥን በሰጡት መግለጫ አሳወቁ››

በሚያነበው ዜና ሁሉ ደነዘዘ…..ማንበቡን አቆመና..ደወለላት

‹‹ሄሎ ..››

‹‹አሁን በመጠኑ ገባህ?››

‹‹ማለት አሁንም እንደጠፋሽ አይደለሽም አይደል…..?ማለቴ ወደቤት ተመልሰሻል?››

‹‹አይ  አልተመለስኩም…ወደቤት  እንድመለስም  እንደወጣው  በዛው  እንድቀርም የምታደርገኝ አንተ ነህ፡፡››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ከእቤት የጠፋሁት የወላጆቼ ጭቅጭቅና የእርስ በርስ ጥላቻ ምርር ብሎኝ ነው….እኔ የእነሱን ሀብታቸውንም ሆነ ውርሳቸውን አልፈልግም፡፡ እኔ የምፈልገው ፍቅራቸውን ነው..ቢያንስ የሁለት ጓደኛሞችን አይነት እርስ በርስ የመግባባት እና የመረዳዳት ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ወደዛ ቤት አልመለስም…እና እቅዴ ምን መሰለህ..ለእነሱ ደብዳቤ ፅፌ ልክልሀለው….በዛ ደብዳቤ ላይ ግልፅ የሆነ ፍላጎቴን አሰፍራለሁ…ማለቴ በግልፅ ከአንተ ጋር ሰርተው በማሀከላቸው ያለውን ግንኙነት ካስተካከሉ…እናም ያንን አንተ ካረጋገጥክልኝ ወደቤት እመለሳለው..ካለበለዚያ በቃ እኔም እነሱን እረሳለው አነሱም እኔን ይረሱኛል ማለት ነው፡፡›

‹‹በተሰቀለው..ነገሩ ካሰብኩት በላይ የተወሳሰበና ..አደገኛም ጭምር ነው፡፡››

‹‹ለዚህ እኮ ነው አምስት ሚሊዬን ብር እንድታገኝ የማደርግህ..ገብቷሀል አይደል አባቴ እኔን ላገኘ ወይም ያለሁበትን ለጠቆመ ሰው የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል ..ያ ማለት ነገሮች እንደተሳኩ እርግጠኛ በሆንኩ ጊዜ አንተ እንድታገኘኝና ለቤተሰቦቼ እንድታስረክበኝ አደርጋለሁ…እናም ለሽልማት የተዘጋጀውን ብር ከአባቴ ተቀብዬ ለአንተ አስረክብሀለው፡፡››
👍62🥰123
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

‹‹ለማንኛውም ተመልሼ መጣለሁ..ና ወደቢሮ እንመለስ …››ብለው ሰለሞንን አስከትለው ወደቢሯቸው ተመለሱ፡፡
‹‹በል አሁን ንገረኝ ልጄ እንዴት ናት?››
‹‹እኔ እንጃ እንዴት እንደሆነች አለውቅም?››

‹‹ማለት ደብዳቤውን ስትሰጥህ አይተሀት የለ..?ከስታለች…እንዴት ነች ተጎሳቁላለች?ልቧስ እንዴት ነው…?ታውቃለህ አይደል የልብ በሽተኛ ነች››
‹‹ደብዳቤውን በአካል መጥታ አይደለም የሰጠችኝ..ማለቴ ቢሮዬ በሚገኝበት ህንፃ መታጠቢያ ቤት አስቀምጣ ስልክ ደወለችና እንድወስድ አዘዘችኝ..ስልኬን ከየት እንዳገኘች አላውቅም…ሁሉን ነገር የተነጋገርነው በስልክ ነው…በወላጆቼ ትዳር መካከል አለመግባባት አለና እርዳቸው ብላ መቶ ሺ ብር በደብተሬ አስገብታለች….መልሼ ስልኳን ብደውልላት አይሰራም…እራሴ ስፈልግህ መልሼ አገኝሀለው ነው ያለችኝ..እኔ የማውቀው ይሄኑን ነው፡፡››
ኪሱ ገባና ቢዝነስ ካርዱን አውጥቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠ‹‹ይሄው አድረሻዬ …ቢሮዬ ሜኪሲኮ ኬኬር ህንፃ ላይ ነው….ዝግጁ ስትሆኑ ደውሉልኝ….ካልሆነም ይንገሩኝ ገንዘቡን ተመላሽ አደርጋለው፡፡አሁን ልሂድ፡፡››
‹‹እሺ በቃ…አመሰግናለው..አሁን ተረጋግቼ ማሰብ አለብኝ..ደውልልሀለው፣ልጆቹ ይሸኙሀል››አሉት፡፡
እሱም ሌላ ምንም ተጨማሪ ቃላት ሳይናገር  ቦርሳውን ያዘና ሹልክ ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
በሁለተኛው ቀን የሚጠብቀው ቁጥር ተደወለ…የልብ ምቱ ፍጥነት እንደጨመረ እየታወቀው ነው…እንደምንም ለመረጋጋት ሞከረና አነሳው፡፡
‹‹አቤት …..››
‹‹ሃይለ ልኡል ነኝ….››
‹‹አወቅኮት፣ ሰላም ኖት ?››
‹‹ደህና ነኝ….እቤት ብቅ ብትል ይመችሀል?››ሰከን ባለና በተረጋጋ የድምፅ ቅላፄ ጠየቁት፡፡
‹‹መቼ…አሁን››
‹‹አዎ አሁን ብትመጣና ..በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ብናወራ ደስ ይለኛል››
‹‹እሺ….ከአንድ ሰዓት በኃላ እደርሳለሁ..››
‹‹አመሰግናለሁ….ከባለቤቴ  ጋ ሆነን እንጠብቅሀለን››

‹‹ጥሩ በቃ መጣሁ….››ስልኩን ዘጋና ቀጥታ ቦርሳውን ይዞ ከመቀመጫው ተነሳ….ወደፊት ለፊተኛው ክፍል ሲገባ ለሊሴ ፊትለፊቷ ያለውን ኮምፒተር ከፍታ አፍጥጣ ነበር….
‹‹ልወጣ ነው…ዘሬ ተመልሼ የምመጣ አይመስለኝም››
‹‹እሺ በቃ..ባለጉዳይ ከመጣ…ለነገ ቀጠሮ ይዤላቸዋለው››አለችው፡፡
‹‹ጥሩ እንደዛ አድርጊ….መልካም ውሎ››ብሏት ቢሮውን ሙሉ በሙሉ ለቆ ወጣ፡፡
መኪናውን እራሱ እያሽከረከረ….አእምሮውም በሀሳብ እየተሸከረከረ ቀጥታ ወደአቶ ኃይል ልኡል ቤት ነዳው…ምን እንደሚጠብቀው አያውቅም..እርግጥ ና ብለው ሲጠሩት በጣም በተረጋጋ እና በተለሳለሰ ድምፅ ነው…ግን ያንን ያደረጉት ሁሉ ነገር ሰላም ነው ብሎ በማመን በገዛ እጁ ሄዶ እጅ እንዲሰጣቸው አስበው ከሆነስ? ይሄ የእቅዳቸው አንዱ አካል ቢሆንስ?››እራሱን ደጋግሞ ጠየቀ…በሀሳብ ከመብሰልሰል ለደቂቃ እንኳን ሳያነጥብ ሰፈራቸው ደረሰ …መኪናውን ከሩቅ አቆመና ደወለ፣ስልኩ ተነሳ››
‹‹ኪያ እንዴት ነሽ?››
‹‹ሰልም ነኝ….አንተስ?››
‹‹አለው…እዛ የነገርኩሽ ቦታ ጠርተውኝ እየሄድኩ ነው››
‹‹የት?››
‹‹አንቺ ደግሞ …የጠፋችው ልጅ ወላጆች ጋር ነዋ››
‹‹ና ብለው ጠሩህ?››
‹‹አባትዬው አሁን ጠርተውኝ በራፋቸው ጋር ደርሼ ወደውስጥ ዘልቄ ከመግባቴ በፊት መኪናዬን አቁሜ ነው የምደውልልሽ››
‹‹ምነው ፈራህ እንዴ?››
‹‹አይ ለምን ፈራለሁ….ማለቴ ከገባሁ በኃላ በፀጥታ ከእነሱ ጋር ለመነጋገር ስልኬን ስለማጠፋ ድንገት ደውለሽ ስልኬ ካልሰራልሽ እንዳታስቢ ብዬ ነው››
‹‹አይ ጥሩ አደረክ…ለማንኛውም እንደወጣህ ደውልልኝ››

‹‹እሺ….ኪያ …ቸው››ስልኩን ዘጋ፡፡ቀለል አለው፡፡‹‹ቢያንስ አሁን እዛው በገባሁበት ከቀረሁ በቀላሉ አድርሻዬን ታገኘዋለች፡፡››ብሎ አሰበና መኪናውን አንቀሳቀሰ….የውጭ በራፍ ጋር ደረሰና ክላክሱን አንጣረረ….ወዲያው በራፉ ተከፈተና…ጠብደል ጥቁር ሱፍ የለበሰ ጠባቂ ወደእሱ መጣና …ማንነቱን ጠየቀው‹‹አዎ አንተን እየጠበቁሀ ነው››ብሎት መልሶ ሄደና በራሀፍን ከፈተለት ….ወደውስጥ ዘልቆ ገባና ከአራት መኪና በላይ ወደቆመበት ገራዥ በመሄድ ክፍት ቦታ ፈልጎ መኪናውን አቆመና ሞተሩን አጥፍቶ ወረደ…..ጠባቂው እየመራ ሳሎን በራፍ ድረስ ወሰደውና ወደኃላ ተመለሰ…
እራሳቸው አቶ ኃይለልኡል ነበሩ በራፍ ድረስ መጥተው በወዳጅነት አቀባበል አቅፈው የተቀበሉት….ወደሳሎን ይዘውት ዘለቁ…መጀመሪያ ምግብ እንብላ…‹‹እስከአሁን ቁርስ ሳንበላ እየጠበቅንህ ነው››አሉት፡፡
‹‹ዝም ብላችሁ ተቸገራችሁ….እኔ እኮ በልቼ ነበር የመጣሁት››
‹‹ቢሆንም…ና ቁጭ በል….››ቀድመው ተቀመጡና የሚቀመጥበትን ቦታ አሳዩት…ተቀመጠ
‹‹ልጇች..ስንዱን ጥሯት››
ሰራተኞቹ ግራ የገባቸው ይመስል ዝም ብለው ሰውዬው ላይ አፈጠጡ፡፡
‹‹ምን አፍጥጣችሁ ታዩኛላችሁ…ክፍሏ ነች…አንዳችሁ ሂዱና እንግዳው መጥቷል ነይ በሏት…የተቀራችሁ ቁርሱን አቅርቡ››
ሁሉም ትዛዙን ሰምተው ተበታተኑ
‹‹እንዴት ነው …ወ.ሮ ስንዱ ተሸላቸው?፡፡››ሰለሞን ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ…እድሜ ላንተ የልጃችንን ሰላም መሆን ዜና ካሰማሀን በኃላ ተሸሏታል…የተሳሰረ የነበረ እግሯቾም ታምራዊ በሆነ ፍጥነት ተላቀውላት አሁን በራሷ መራመድ ችላለች፡፡››
‹‹በእውነት በጣም እስደሳች ዜና ነው…ያልኳችሁን ስላመናችሁኝ ደስ ብሎኛል››
‹‹አይ እሱ እንኳን በቀላሉ አላመንህም…ስላአንተ ለሁለት ቀን ሳስጠና ነበር…በዛ ላይ ከእሷ ጋር የተደዋወላችሁትን የስልክ ልውውጥ አግኝቼ አዳምጬዋለው…የልጄን ድምፅ ሰምቼያለው…በሰላምና በጤና መኖሯን ያረጋገጥኩት ከዛ በኃላ ነው…በቀላሉ ላምንህ

ሳላልቻልኩ ይቅርታ….ደግነቱ እንዲህ በቀላሉ እንደማላምንህ ልጄ አስቀድማ ነግራሀለች…ይገርማል ይሄን ያህል ጠልቃ ምታውቀኝ አይመስለኝም ነበር››
‹‹ልጆት አይደለች…ልጆች እኮ ወላጆች የሚያደርጉትን እያንደንዱን ድርጊት በጥልቀት ያስተውላሉ ፣በአእምሮቸውም ይመዘግባሉ…ስለወላጆቻቸው በጥልቀት ነው የሚያውቁት››
‹‹ትክክል ነህ ..››ንግግራቸውን በወ.ሮ ስንዱ መምጣት ምክንያት አቆረጡ….ሰሎሞን ከመቀመጫው ተነስቶ በትህትና ሰላምታ ተቀበላቸው….ወንበር ስበው ተቀመጡ..ቁርስ ቀረበ….ጠረጴዛው ሙሉ ቢሆንም ያን ያህል አፒታይት የነበረው ሰው አልነበረም….ቁርሱ እንደተጠናቀቀ ከወንበራቸውን ተነስተው አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የአቶ ኃይለልኡል ቢሮ ተያይዘው ሄዱ.. ወደሶፋው ሄዱና ተቀመጡ..፡፡
‹‹እንግዲህ አሁን መነጋገር እንችላለን››አቶ ኃይለልኡል ጀመሩ
ወ.ሮ ስንዱ ተቀበሏቸው‹‹ልጄ እንደው አባክ እርዳን ..ልጃችን ወደቤቷ እንድትመለስ አሳምናት››ከመቀመጫቸው ተነስተው እግሩ ላይ ሊደፉ ሲሉ በአየር ላይ ትከሻቸውን ያዘና መልሶ አስቀመጣቸው፡፡
‹‹አይገባም..እኔ እዚህ ያለሁት እኮ ልረዳችሁ ነው..የእኔም ምኞትና ፍላጎት ያ ነው››
‹‹እኮ አድርገዋ….ያለችበትን እንድትነግርህ አሳምናት›››
‹‹አይ በእንደዛ አይነት ሁኔታ እንኳን ምትስማማ አይመስለኝም..እሷ ወደቤቷ ምትመለስበትን አንድና ብቸኛ መንገድ በግልጽ ተናግራለች…ምንም አይነት ችግር ሳይፈጠር ደስተኛ ሆና ወደቤቷ እንድትመለሰ ያለችውን አድርጎ ማሳየት ብቻ ነው ያለብን፡፡››
‹‹ይሄውልህ ልጄ…ልጃችን ያለችውን ለማድረግ እኔም ባለቤቴም ተስማምተናል…..ለዛ ቃል እንገባለን..አንተ ትረዳናለህ እኛም በመሀከላችን ያለውን ችግር እንፈታዋለን..››
👍7613