አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ አምስት (25)


ቀኑ ጭጋጋማና እጅግ ቀዝቃዛ ነው ። ሚሪ ማለትም ናንሲ ማክአሊስተር ወደ ፌ አሊሰን ቢሮ ስትቃረብ የባርኔጣዋን ክፈፍ ቁልቁል ሳበች ። የደማቅ ቀይ ሱፍ ካፖርቷን ኮሌታም ሽቅብ ዘረጋች፤ ፊቷንና አንገቷን እንዲሸፍንላት ። ፍሬድ ውሻዋ እንደ ሁልጊዜው ተከትላታል ። ለፍሬድ የተጠለቀለት የአንገት ዘለበትና መሳቢያውም ልክ ሜሪ (ናንሲ) አንደለበሰችው ካፖርት ደማቅ ቀይ ናቸው ። አንገቷን ሰበር አድርጋ ውሻውን ቁልቁል እየተመለከተች ፈገግ አለች ። መንፈሷ በፌሽታ ሰፍፏል ። ደስተኛ መንፈሷ ጭጋጉና ብርዱም ሊሸፍኑትና ሊያቀዘቅዙት አልቻሉም። ወደ ፌ ቢሮ የሚወስደውን ደረጃ በሩጫ ከወጣችው በኋላ በሩን ከፍታ ገባች ። እና «ቤቶች ! የላችሁም እንዴ ? መጥተናል» አለች ። ከላላ ድምጺ በሞቃቱና ምቹው ቤት ውስጥ እስተጋባ ። ወዲያው ከሌላ ክፍል መልስ መጣ ። ሜሪ ካፖርቷን አወለቀች ። ከስር የለበሰችው ቀለል ያለ ወርቅማ ጌጥ ያለው ነጭ የሱፍ ቀሚስ ነበር። ይህን የገዛላት ፒተር ነው ። ከዚያም በከፊል ልብ ራስዋን በመስታወት ውስጥ ተመለከተች ባርኔጣዋን ወደ ጐን ዘንበል አደረገችና እንደገና አየችው ራስዋን። ምስሏን ተመልክታ ፈገግ አለች ። ደስ አላት ። መነፅር ማድረግ አቁማለች ። ምክንያቱም አይኖችዋ ላይ የነበረው ፋሻ ተነስቷል ። ፊቷ በጠቅላላ ፋሻ አይታይበትም ። ጥቂት ፋሻዎች ብቻ እግንባርዋ ላይ ይታያሉ ። እሱም ካሁን በኋላ ብዙ ጊዜ አይቆይም ። አለቀ ። እድሜ ለዘመናዊ የሕክምና ጥበብ ሜሪ (ናንሲ) ጠባሳ አይታይባትም ። አዲስ ፊት ፤ አዲስ ሰው ፤ አዲስ ስም ፤ አዲስ ሕይወት ።

«እመስተዋቱ ውስጥ ባየሽው ነው እንዲህ የተደስትሽው ናንሲ?» ይህን ድምፅ ስትሰማ ደንገጥ ብላ ዞር አለች ። ፌ አሊሰን ነበረች የተናገረችው፡፡ ፌ በፍቅር በተሞላ ፈገግታዋ ጥያቄውን ደገመችላት ። ራሷን በአወንታ ነቀነቀች ሜሪ ። በቃልም «አዎ። በሱ ነው የተደሰትኩት ብዬ አስባለሁ ። የሚገርምሽ በጠቅላላ የሆንኩትን እኔነቴን ሁሉ ለምጀዋለሁ። አንች ግን አለመድሽልኝም » አለች ። ፊቷ ላይ መቀየምና ቁጣ መሰል ነገር ይታይባት ነበር ። «ምን ማለትሽ ነው ፣ እንዲያ ስትይ ?» አለች ፌ አሊሰን ። «አለስሜ ትጠሪኛለሽ ሁሌ ። ሁሌ ናንሲ ነው እኮ እምትይኝ። ናንሲ አይደለሁም። ነበርኩ ቀረ። አሁን ሜሪ ነኝ ። በፍርድ ቤት ፀድቆ በሕግ ሊታወቅ ምንም ያልቀረው ስሜ ሜሪ አዳምሰን ነው»
«ገባኝ። ይቅርታ » ፌ ይህን ብላ ሁልጊዜም ሁለቱ ሲገናኙ አረፍ ብለው ወደሚጨዋወቱበት ምቹ ወደሆነውና ቅልል ወደሚለው ክፍል አመራች። «ይቅርታ ፤ ሁልጊዜም ናንሲ የሚለው ስም አፌ ላይ ደርሶ ጥልቅ ይላል » አለች ፌ አሊሰን ደግማ ። «ሁልጊዜ» አለች ሜሪ እምትወደው ወንበር ላይ እየተቀመጠች። ግን የተበሳጨች አትመስልም። ትንሽ ካሰበች በኋላ «አንዴ የለመደን ነገር ማስወገድ በጣም ክባድ ነገር ሳይሆን አይቀርም ። ይመስለኛል» አለች ሜሪ። ይህን የተናገረችው ፊቷን ቅጭም አድርጋ ነበረና ፌ አሊሰን ዝም አለች ። ከዚህ ጋር አያይዛ የምታመጣውን ነገር ለመስማት ።

«ይህን ነገር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው የተረዳሁት ። ሳስብ ሳስብ ገባኝ ። ብዙ ጊዜ ላስወግደው ስሞክር አሻፈረኝ ብሎ እቦታው ላይ ሲገኝ ግን አሁን ሳላራግፈው የቀረሁ አይምስለኝም » አለች ሜሪ ።
«ማይክልን ማለትሽ ነው?» ሜሪ አንገቷን በአወንታ ነቀነቀች እንጂ ምንም አልተና
ገረችም ። «እንዳራገፍሽው እንዴት ልትገምቼ ቻልሽ ?» አለች ፌ። «ወሰንኩ ። ምርጫ ጠፋ። ወሰንኩ ። ለምን ? በይኝ ። ምክንያቱም ያ አደጋ ከደረሰብኝ ይኽው ሁለት ዓመት መሙላቱ ነው፡፡ ዓመት ከዘጠኝን ወር… ሁለት ዓመት በይው ። ይህን ያህል ጊዜ ስቀመጥ ሊፈልገኝ አልሞከረም ። እንዳሰብኩት እናቱን ብትፈልጊ እንጦረጦስ ግቢ ብሏት ወደኔ አልመጣም። ተወኝ ። ረሳኝ ። ስለዚሀ እኔም ልተወው ፤ ልረሳው ይገባኛል ።››

«መርሳት ! መርሳት ቀላል አይደለማ ! በልብሽ ውስጥ ለብዙ ጊዜ ያገነንሽው ሰው እንዲህ በቀላሉ ይረሳል ብለሽ ነው? በልብሽ ያስቀመጥሽው ጊዜ ረጂም ነው እኮ »
«እጅግ በጣም ረጂም ። ያን ያህል ጠብቄውም እንዲህ አድርጐኝ ቀረ ። ጣለኝ… ረሳኝ »
‹‹ጣለኝ… ረሳኝ ስትይ ስለራስሽ ምንነት ምን ይሰማሻል ?»
«ስለኔ ምንም ዓይነት መጥፎ ስሜት የለኝም ። ያጠፋ እሱ ። ያናደደኝ እሱ ። እኔ ምን አጠፋሁ? »
«ማለቴ ባለፈው ትንሽ ራስሽን ጠልተሽ ነበር ። ለምን ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር ያን ስምምነት አደረግኩ ? ስትይ ነበር። ያ ስሜት አሁን ፈጽሞ አይሰማሽም? » ፌ አጉል ቁስል እየዘነቆረች እንደሆነ ገብቷታል ። ቢሆንም አለባብሶ ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ነውና መሸፋፈኑን አልወደደችውም ።

«ምርጫ… ምንም ምርጫ አልነበረኝም» አለች ሜሪ። «ኖረም አልኖረም ለምን እንዲህ አደረግኩ ብለሽ ራስሽን ወቅሰሽ አታውቂም ?»
«ለማን ብዬ? ለምን ብዬ? ማይክል ለምን አልጠየቅኳትም ብሎ በራሱ የሚናደድ ይመስልሻል ? ሳያስብልኝ በመቅረቱ የህሊና ወቀሳ እንቅልፍ ይነሳዋል ብለሽ ታስቢያለሽ ?»
«ማይክልን እንተወው የሚያሳስበን ያንቺ ነገር ነው አሁንም እሱን በማሰብ ዕንቅልፍ ታጪያለሽ ፤ናንሲ ? »
« ናንሲ አይደለም ሜሪ » አለች ሜሪ እያረመቻት ። «በፍጹም ። አልፏል ያ ቀረ ፤ ይህን የቁም ሕልም ለማስወገድ ወስኜ ተነሳሁ ። ብዙ ስለተሰቃየሁ ዛሬ ቆረጥኩ ። በቃ » አለች ። ድምጺም ቃላቱም ሆዷ የቆረጠ መሆኑን ይናገሩ ነበር ። « በምትኩ ? » አለች ፌ አሊሰን « በማይክል ቦታ ማንን ልትተኪ?» ፒተርን ብላ አሰበች። « በቃ እሠራለሁ ። ሥራ ! በመጀመሪያ ግን ወደ ደቡባዊ ምሥራቅ ግዛቶች ሄጄ ትንሽ መንፈሴን አዝናናለሁ… የገናን በዓል አስመርኩዤ ። እዚያም እየተዝናናሁ አላርፍም ። እሠራለሁ ። ዕቅዴን ነድፌ ጨርሻለሁ ። አሪዞናን ፤፣ ኒው ሜክሲኮን ካየሁ በኋላ ከመሰለኝ ወደ ሜክሲኮም መሻገር አስቤአለሁ ። ሦስት ሳምንት ቆይቼ ስመጣ ፤ ዕረፍት ! በቃ ! »
« ከዚያ በኋላስ ? »
« ከዚያማ መሥራት ፤ ሌት ተቀን መሥራት ። በቃ ! የኔ አእምሮ ካሁን በኋላ እስራ ላይ ብቻ ነው። ልቤ ሥራን ብቻ ነው እሚያስበው ። በነገራችን ላይ የፎቶ ግራፍ ትርኢት እንደማቀርብ ሰምተሻል ። ፒተር ሁሉን ነገር ጨርሶልኛል ። ጥር ወር ላይ ነው የሚሆነው ። እንዳያመልጥሽ ብታስቢበት መልካም ነው።»
« ያመልጣታል ብለሽ ታስቢያለሽ ? »
« እንዳያመልጥሽ እመኝልሻለሁ ። እንዲህ ቀላል አይምሰልሽ። ፎቶ ግራፍ በጣም አድርጐ ፍቅር ያስያዘኝ ሥራ ሆኗል ከምር የማፈቅረው ነው ስልሽ ። እና ደግሞ የሠራኋቸውን ነገሮች አብዛኞቹን አላየሻቸውም ። አንቺ ቀርቶ ፒተር እንኳ ያየው ጥቂት ነው። ኤግዚቢሽኑን ሲመለከት ደስ ቢሰኝልኝ እኔም ደስ ይለኛል ።»
« አትጠራጠሪ ደስ ይለዋል ። አንቺ ከሠራሽው ምንም ይሁን ለሱ ድንቅ ነገር ነው » አለች ፌ ። እና ቀና ብላ አየቻት ሜሪን። ከዚያ ‹‹ነገርን ነገር ያነሳዋል ናንሲ. . . ማነው? ሜሪ.. . ስለ ፒተር አልተነጋገርንም ? ስለ ፒተር የሚሰማሽን እስኪ ንገሪኝ »
👍17
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ስድስት (26)

ሜሪ አዳምስን ከፌ አሊሰን ተሰናብታ እንደወጣች በቀጥጥታ ወደ ዩኒየን ስኩዌር እመራች ፤ በታክሲ ። እዚያም የሄደችበት ምክንያት ቲኬት ለማስቆረጥ ነበር ። በጉዞው አስቀድማ ስላሰበችበት ከሁለት ሳምንት በፊች ቲኬት ለመቁረጥ ተመዝግባ ነበር ስለዚህም ችግር የለባትም ። ገንዘቡን ሰጥታ ቲኬት መቀበል ብቻ ነው ። ሜሪ ስለጉዞው ስታስብ እጅግ ደስ አላት ። ለመዝናናት ካሰበችበት ቆይታለች ። ይህ ጉዞ የመጀመሪያዋ ባይሆንም ብዙ ጊዜ ያደረገችው አይደለም ። አንዴት ነው ይህን ዓይነት ጉዞ ያደረገችው ። ከሜሪ ጋር ። በበዓለ ፋሲካ ።. . . ይህ ሐሳብ ረሰሻት። ማይክልን ማሰብ የለባትም ። ሐሳቡን እንደምንም ታግላ መለሰችው ።

ዩኒየን ስኩዌር እንደደረሰች ወደ ቲኬት መሸጫው ቢሮ ገባች፤ «አስቀድመሽ እንዲያዝልሽ አድርገሽ ነበር?» አለቻት የክፍሉ ሠራተትኛ ።
«አዎ ። ከአሥራ አምስት ቀን በፊት»
«ስምሽን ማን ልበል ?።»
«ሜሪ አዳምስ... ኖ ናንሲ ማክአሊስተር» አለች ሜሪ ። ናንሲ ማክአሊስተር የሚለውን ስም ስትሰማው እንግዳ ነገር ሆነባት። ስሟን ወደ ሜሪ አዳምሰን ቀይራ በዚሁ ስትጠራ ከሁለት ወር አለፍ ይላል ። እዲሱን ስሟን ለመልመድ ስትጣጣር የወትሮውን እየረሳችው እንደሆነ ተገነዘበች፡፡ ቲኬት ለመቁረጥ በናንሲ ማክአሊስተር የተጠቀመችው በከንቱ አልነበረም ። ምንም እንኳን ናንሲ ማክእሊአስተር መባሏ ቆርቶ ሜሪ አዳምሰን እንድትባል በሕግ የተፈቀደላት ቢሆን በወጣላት አዲስ ስም መጠራት የምትጀምረው ከአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ማለትም ከጀንዋሪ ( ጥር) ጀምሮ እንደሆነም ውሳኔ ተሰጥቶ ነበር ። ለዚሀም ነው ከገና በፊት ሜሪ አዳምሰን ተብላ ልትመዘገብ ያልቻለችው ።

ናንሲ ስለስሟና ስለጉዞው ስታስብ ገረማት ። ዛሬ ናንሲ ናት ። የዕረፍትና የመዝናናት ጉዞዋን ጨርሳ ስትመለስ ግን በሕግ ፊት ሳይቀር ሜሪ አዳምሰን ትሆናለች ። አገባሁ ማለትኮ ነው ! አለች በሐሳቧ ። አሁን የምሄደው የጋብቻ እረፍት ለማድረግና ለመዝናናት መሆኑ ነው ማለት ነው አለች ።

ከዚያ ስትመለስ አዳምሰን እንጂ ማክአሊስተር ተብላ እትጠራም። (የፈረንጅ ሴቶች ሲያገቡ የባላቸውን የቤተሰብ ስም ይወርሳሉና የስሟን መቆየር ነው እንደማግባት የቆጠረችው) ሜሪ አዳምሰን ናንሲ ማክአሊስትር አይደለችም ። ነበረች ። ግን አይደለችም ። ሜሪ አዳምሰን በስም ብቻ ሳይሆን በመልክም።
በሰውነት ቅርጽም ፤ በአነጋገርም፤ በድምጽም፤ በአካሄድም፤ ናንሲን አትመስልም ። መልኳን ዶክተር ፒቶሮ ግሬግሰን ቀይሮታል ። ከዚህ በፊት ናንሲን የሚያውቃትን ማንም ሰው የዛሬዋን ሜሪ አሳይቶ ናንሲ ናት ቢሉት አያምንም ። የዛሬዋ ሜሪ ውበቷ የሚያፈዝ ማንም ሴት የሷን መልክ በሰጠኝ ብላ የሚቀናባት ቆንጆ ነች ። ለራሷ ከሆነ ይች ቆንጆ እንግዳ አይደለችም ። ለምዳታለች ። ግን አብራት የኖረችው ናንሲ ማክአሊስተርም አይደለችም ። የምትናገረው ነገር ያው ይሁን እንጂ የእነጋገር ስልቷና ድምጽ አወጣጧ ስለተቀየረ ይህችኛዋ ስትናገር አድማጭን ታፈዛለች ። አፍ ታስከፍታለች ። ሰውነቷ ጠንከር ሲልና የሕክምናው ተግባር ሲገባደድ ፣ ዶክተር ፒተር ግሬግሰን የባሌ ዳንስ እንድትማር ፈቅዶላታል ። ትማራለች ። ይህ ደግሞ በእካሏ ላይ ምን ያሀል ለውጥ እንደሚያመጣ የታወቀ ነው ። የዮጋ ልምምድም ታደርጋለች ። ይህች ናት የዛሬዋ ሜሪ አዳምሰን ፤ የወትሮዋ ናንሲ ማክአሊስትር ። ተለወጥኩ ፡አዲስ ሰው ሆንኩ አለች በሐሳቧ ። ገረማት ። ደርሶ ንዴት ተሰማት ። እንጦሮጦስ ! አለች በልቧ ። ማይክል ረሳኝ ። እኔም ራሴ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እረሳዋለሁ አለች አሁንም በሐሳቧ ።

«እንድ መቶ ዘጠና ስድስት ዶላር ይሆናል ክፍያው»አለች የቲኬት ቢሮ ሠራትኛዋ ፣፤ ሜሪን ከሐሳቧ እየመለሰችና ኮምፒውተሩን እየተመለከተች ። ሜሪ ቼክ ጽፋ ስትሰጣት ልጅቷ አንዴ ኮምፒውተሩን አንዴ ሜሪን ትመለከት ጀመር ። ከዚያም ሜሪን ትኩር፤ ፈገግ ብላ ተመለከተቻች ። ሜሪ እንድ ነገር አላት ። አንዴ ካየሃት ዓይንህን ከሷ ላይ መንቀል ያስቸግርሃል ። ማናት ? ትላለህ ፤ ይህን የሚሉ ደግሞ ወንዶች ብቻ አልነበሩም ። ሴቶችም ቢሆኑ ያው ነው ።

ፍሬድን አቅፋ (መኪና እንዳይገጨው በመፍራት) ከቲኬት መሸጫው ቢሮ ወጥታ ጉዞዋን ቆጠለች ። አንድ በጣም ትልቅ ሱፐር ማርኬት ስታይ ወደዚያው ገባች ። ምን ለመግዛት እንደምትፈልግ ግን አታውቀውም ነበር ። ለራሴ አንድ ስጦታ እገዛለሁ ። ወይም ለጉዞዬ የሚያስፈልገኝ ነገር ሊያጋጥመኝ ይችላል አለች ። በዚያ ግዙፍ ሱፐር ማርኬት ውስጥ ካንደኛው ፎቅ ወደ ሌላው ከልብስ ክፍል ወደ ጫማ ፤ ክዚያም ወደ ጌጣጌጥ ፤ ከዚያም ወደ ሌላው እየተዘዋወረች አንዱን ዕቃ አንስታ እየጣለች ሌላውን አንስታ እየመረመረች ወይም እየሞከረች ብዙ ጊዜ አሳለፈች ። በመጨረሻ አንድ ነጭ የሱፍ ሹራብ ላይ ዓይኗ አረፈ ። ሹራቡን ለብሳ ሞከረችው። ከውብ ገፅታዋና ከጥቁር ሐር መሳይ ጸጉሯ ጋር ሹራቡ የውበት ዳርቻ የሆነችውን ልዕልት አስመሰላት ።ራሷም ይህን አሰበች ። ሃሳቧ አስደመማት ፤ አስደሰታትም፡፡ ሹራቡን አስጠቅልላ ወደ ዋናው አዳራሽ ተመለሰች ያሉትን ዕቃዎች በመደዳ ተመለከተች ። ከዚያም አንድ ታኒካ ቸኮላት ገዛች ። ይህን ቸኮላት ለፌ አሊሰን ነበር የገዛችው ፤የገና ስጦታ ። በታኒካው ላይ በተንጠለጠለው ካርድ ላይ « አመሰግናለሁ፤ ፌ። ከፍቅር ጋር ። ሜሪ» ብላ ጸፈችበት ። ሌላ ምን ብላ ልትጽፍ ፤ ምንስ ልትጨምር ትችላለች ? « ማይክልን እንድረሳው ስለረዳሽኝ ፤ ሁሉን ትቼና ረስቼ መኖር እንድችል ስለመከርሽኝ አመሰግናለሁ » ብላ ትጻፍበት ?

ይህን ሀሳብ እያውጠነጠነችና ከራሷ ጋር እየተጨዋወተች ሳለች ድንገት የሚያስደነግጥ ትዕይንት አጋጠማት ። ዛር ወይም ሰይጣን ያየች ይመስል ባለችበት ክው ብላ ቀረች ። ገንዘብ ተቀባይዋ ደረሰኝ ቆርጣ እጅዋን ሰንዝራ ነበር ። ይህን ስትቀበል እንኳ ዓይኗ ካየችው ነገር ላይ አልተነቀለም። ያየችው ዛር ቤን አቭሪ ነበር ። ቤን አቭሪ እሷ ካለችበት አለፍ ብሎ በጣም ውድ የሆነ የሴቶች የዕቃ ሻንጣ ይመለከት ነበር ። ሜሪ ካለችበት ንቅንቅ ሳትል ለረጂም ጊዜ ቆየች ። ከዚያም ቀስ ብላ ቤን ወዳለበት አካባቢ ጠጋ አለች ። ቀረብ ብላ ልታየው ፤ ቀረብ ብላ ልትነካው ፤ቀረብ ብላ ድምጹን ልትሰማው ፈለገች ። ላንዲት ቅፅበት የሆነውን ሁሉ በመርሳት አፍታ ያስታውሰኝ ይሆን የሚል ስሜት ተቀረጸባት። ያች አፍታ እስክታልፍም ባወቀኝ ፤ ባስታወሰኝ ስትል ተማፀነች ። ሆኖም ያቺ ቅፅበት አለፈች ። ያኔ በምንም ዓይነት መንገድ ሊያስታውሳት እንደማይችል ተገነዘበች ። ይህን ማሰቧ ቢያስከፋትም ፤ እረ እንኳን ያላወቀኝ ስትል ራሷን ወደ ደስታ ገፋፋችው ። እንዲህም ስትል ተፅናናች ። እንኳን ያላወቀኝ ቢያውቀኝ ኖሮ ያናግረኝ ነበር፡፡ ክፉ ሳይናገረኝ እንዲህ ተጠግቼ ልመለከተው እችል ነበር? እንኳን የቀረብኝ አለች ።

እንዲያ አጠገቡ ቆማ እያጤነችው ከማይክል ጋር አሁንም ይገናኙ ይሆን ? ከማይክል ጋር ይሆን የሚሰሩት ? ወይስ ቤን ሌላ መሥሪያ ቤት ገባ ? የሚሉ ጥያቄዎች ይጎርፉ ጅመር በአእምሮዋ ውስጥ ። ሹልክ ብላ አጠገቡ ደርሳ ከሚያገላብጣቸው ዕቃዎች ጎን ያሉትን ከፈይ የመዛግብት ቦርሳዎች ትመለከት ጀመር ። ቦርሳዎቹን የተመለከተች ትምሰል እንጂ ዓይኗስ ከቶም ከፊቱ ላይ አልተነቀለም ። ይህ ሲሆን ሳለ ድንገት ቤን ዞር ብሎ እያትና ያንን የምታወቀውን ገር ፈገግታውን አሳያት ግን . . .
👍22
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ሰባት (27)


« ግን ሻንጣ ፤ ቅራቅንቦ የሚያስፈልጋት መሆኑን ርግጠኛ ነህ » አለች። « ይመስለኛል ። ወደ አንድ ቦታ እንድንሄድ አስቤአለሁ። ሳታስበው እንዲሆን ስለምፈልግ ፤ ቲኬቱን እሻንጣ ውስጥ ከትቼ ላስገርማት ብዬ ነው» አለ ። አንድ ትኬት ደብቆ ለመስጠት አምስት መቶ ዶላር መክፈል ይገባል ቤን ? ቤን አቭሪ እንዲህ ገንዘብ በታኝ ሆነ ? አልፎለታል ማለት ነው ። « ዕድለኛ እመቤት ናት በለኛ»
« ዕድለኛውንኳ እኔ ሳልሆን አልቀርም››
«እንዴት ? ለመጋባት አስባችኋል ማለት ነው ?»
«የለም ነገሩስ ለሥራ ነው ። የሥራ ጉብኝት አለብን»
‹‹ ያኛው ቀይ ጥብጣብ ያለው ቡናማ ከፋይ ሻንጣ ቆንጆ መሰለኝ»
«እኔም እሱ ላይ ነው ዓይኔ ያረፈው» የሜሪን ምርጫ ተቀብሎ የሱቁን ረዳት ጠራት ። ‹‹አመሰግናለሁ ሚስ…..›› አለ፡፡ ለልጅቷ ሚገዛዉን እቃ ካሳያትና እንዲጠቀለልለት ከነገራት በኋላ ሜሪን እያየ ። «አዳምሰን» ስትል ስሟን ነገረችው «ምንም ምስጋና አያስፈልግም ። ምክንያቱም እኔም ደስ ብሎኛል ። ይልቅ ትንሽ ጥያቄ ሳላበዛብህ አልቀረሁምና ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ እኔ ነኝ መሰል ። ዓመትባል ሲቃረብ ይኸው ነኝ ። የማይሆን የማይሆን ነገር አደርጋለሁ»
«እኔም ያው ነኝ ። ብቻ የዘንድሮው ዓመት ሲያልፍ ቢከፋኝም አይፈረድብኝም ። ደስ የሚል ዓመት ነበር ። ኒው ዮርክ እንኳ ሳይቀር»
«ኒው ዮርክ ነው እምትኖረው ? »
«ከመሄድ ስገላገል ፣ አዎ ። ግን ሥራዬ ቁጭ እሚያደርግ አይደለም ። ካንዱ ወዳንዱ መዞር ነው» ይህም ቢሆን ከማይክል ጋር አብረው እንደሚሠሩ ርግጡን የሚናገር ነገር አይደለም ። ብትጠይቀው ደስ ባላት ግን አትችልም ። ይህን ስታስብ በጣም ከፋት ። ኦመማት። ስለሌላ የሷ ስላልሆነ ሰው መጠየቅ ስላሰኛት አመማት ። መጠየቅና ማወቅ ስትችል ባለመቻሏም አመማት ።

«ነገሩ እንኳ የጅል ነገር እንደሆነ ይገባኛል ። ግን ከዚህ ወጣ ብለን አንዳንድ ነገር ይዘን መጠጥ ቢጤ ይዘን ብንጨዋወት ? ለነገሩ እቸኩላለሁ ። አውሮፕላን መያዝ አለብኝ ። ግን ቅዱስ ፍራንሲስ ሆቴል ጐራ ብለን »
«እኔም ቢሆን በራሪ ነኝ ። ያም ሆኖ ሐሳቡ የድርጊቱን ያህል ነው ። አመሰግናለሁ ሚስተር አቭሪ. . .» አለች ። ፊቱ ድንገት ቅጭም አለና ፤ «ስሜን እንዴት ልታውቂ ቻልሽ ?» ሲል ጠየቃት ። «ደረሰኝ ሲቆርጡልህ ስምህን ሲጠሩ ሰማሁ» አለች አመላለሷ ፈጣን ነበረና በጥርጣሬው ሊገፋ አልቻለም ይልቁንም እንዲህ ቶሎ ተገናኝተው ቶሎ በመለያየታቸው አዘነ ። በጣም ቆንጅዬ ልጅ ናት ፤ አለ በሐሳቡ ። ዌንዲን እወዳታለሁ ። ቢሆንም ከአንዲት ቆንጅዬ ልጅ ጋር አንድ ነገር መጠጣት ኃጢአት አልነበረም ። ድንገት አንድ ሀሳብ ብልጭ አለበት «ወዴት ነው የምትሔጂው ፤ ሚስ አዳምሰን?»
«ወደሳንታፌ ፤ ኒው ሜክሲኮ » ተስፋ ቆረጠ ።
«ምን ዓይነት ርጉም እጣ ነው ። እኔ ደሞ ወደ ኒውዮርክ የምትሔጂ ቢሆን ስል »
‹‹ሻንጣ የተገዛላት እመቤት አንድ ላይ ብታዬን እጅግ ደስ እንደምትሰኝ አይጠረጠርም ነበር ። »
«እጅ ሰጠሁ ። ደግ እንግዲህ አምሳክ ካለ ሌላ ጊዜ...»
«ሳንፍራንሲስኮ ትመጣለህ እንዴ ፣ ብዙ ጊዜ?»
«ከዚህ በፊትንኳ አልነበረም ። ወደፊት ግን እይቀርም እመጣለሁ ። ማለት እንመጣለን ። የምሠራበት ድርጅት አንድ ትልቅ ፕሮጀክት አለው» አለ ። « እዚሁ ሳንፍራንሲስኮ ማለቴ ነው ። ስለዚህ ወደፊት ከኒውዮርክ ይልቅ ይኸ ሳይሆን አይቀርም መኖሪያዬ »
«እንዲያ ከሆነ ምናልባት እንገናኝ ይሆናል » ይህን ያለችበት ድምፅ በመጠኑ መከፋትን የሚገልዕ ነበር ምንም አይደለም ። ከማይክል እንጂ ከቤን ጋር ቂም የለኝም ። ስለዚህ አዘውትረን ብንገናኝም ክፋት የለበትም። የሱቅ ረዳቷ እቃው መሰናዳቱን ገለጸችላቸው ። ቤን ጨበጣት ። ጠበቅ አድርጋ ጨበጠችው።
በመገረም ቀና ብሎ አያት በለሆሳስ ። « መልካም የገና በዓል » አለችና በፍጥነት ካጠገቡ ተሰወረች « ወዲያ ወዲህ ተገላምጦ ቢያይም ሊያገኛት እይችልም ።

ከቤን እንደተለያዩ ሰውነቷ ድክምክም አለ ።
ከሱቅ እንደ ወጣች ታክሲ ተሳፍራ ወደ ቤቷ ጉዞ ቀጠለች ከዚያ በፊት ግን ፍሬድን ለእንስሳት ህክምናና ጥበቃ ድርጅት በአደራ መልክ ሰጠችው። ምክንያቱም አያስፈልጋትም። ጉዞዋ አለና በዚያም ላይ በርከት ያለ ቦታ ማየትና ማዳረስ አለበባትና የፍሬድ መኖር አመቺ አልነበረም። ብቻዋን መሔድ አለባት ። ናንሲ ማክአሊስተር በሚል ስም የዱሮ ሰብእናዋ የምትኖርባቸውን የመጨረሻ ሳምንታት ከማንም ጋር መካፈል የለባትም። ምስክር መኖር የለበትም። የአንድ ሕይወት መደምደሚያ ፤የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ነውና ብቸኝነት ያስፈልጋታል። እቤቷ እንደደረሰች ተዘዋውራ ተመለከተችው በሩን ስትዘጋ አንድ ሀረግ ተናገረች ። ለቤን አቭሪ፣ ለማይክል ፤ ያውቋት ለነበሩ ፤ ይወዷት ለነበሩ ፤ ታውቃቸው ትወዳቸው ለነበሩ ሁሉ « ደህና ሁኑ » የሚል ሀረግ ተናገረች ። ደረጃውን ስትወርድ እንባ ተናነቃት ። ካሜራዋንና የዕቃ ሻንጣዋን ይዛ ነበር ።

•••••••••••••••

እረፍቷን ጨርሳ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመለስ ፒተር እየር ማረፊያ ድረስ መጥቶ እንዳይቀበላት ቃል አስገካችው ። ምክንያቱም ያለሸኚ እንደወጣች ያለተቀባይ ልትገባ ስለፈለገች ነበር ። ጉዞውን ስትጅምር ልቧን ከብዷት መንፈሷም ተሸብሮ ነበር። ያንለት ቤን አቭሪን ማግኘቷ ወዳለፈው ሕይወቷ እየተመዘዘ በመመለስ ብዙ ነገሮችን እንድታስታውስ አስገደዳት ። በዚህም የተነሳ በመጀመሪያዎቹ እለታት ከማንም ጋር ለመነጋገር ማንንም ለማዳመጥ አልተቻላትም ። ከሀሳቧ ጋር ተፋጣ ነበር ። ያ ጉዞ ግን አብነት ስለነበረው ከጭንቀቷ ፈወሳት ። የሰላም ጊዜ አሳለፈች ። እጅግ ብዙ ነገርም ሠራች ። ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመለስ ፤ ከሳንፍራንሲስኮ ስትነሳ የነበረው ጭንቀት አልነበረም ። አሁን ስለቤን አቭሪ ማሰብ አያስፈራትም ። ያለፈውን ሕይወቷን መለስ ብላ ለመቃኘት አትፈራም ። ይህን ያህል በመለወጥ አዲስ ሰው ሆነች ። ለመጨረሻ ጊዜ ያለፈው ሕይወቷ የሌላ የምታውቃት ሴት ሆና ታያት ።

ናንሲ ማክአሊስተር ባዕድ ሆና እሷ ሜሪ አዳምሰንን ሆነች። ሜሪ የገናንም በአል ሆነ የዘመን መለወጫን በማታውቃቸው ሰዎች መካከል ሆና አሳለፈችው ። ሰዎች በአላትን ሲያክብሩ ናንሲ እነሱን ፎቶ ግራፎች አነሳቻቸው ። በተለይ የገናን በዓል በታአሰ አካባቢ ስታከብር የበረዶ ሸርተቴ የሚጫወቱት ብዙ ነበሩና ይህን ጨዋታ ለመሞከር ልቧ እጅግ ገፋፍቷት ነበር፡፡ እንዲህ ያለውን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ጨዋታ ላለመሞከር ለፒተር ቃል ገብታለት ነበርና ለራሷም በመፍራት ፍላጎቷን መግታት ግድ ሆነባት ። ፒተር የገባውን ቃል አክብሮ ሊቀበላት እንዳልመጣ! ስትገነዘብ ደስ አላት ። እንዲሀ በማያውቅህ ሠራዊት ውስጥ ስትገባ ማንም ነህ ። ማንም ማንንም አያይም ተሰውሮ መኖርን ደግሞ ብዙ ተላምዳዋለች ። ባለፉት ሁለት ዓመታት ፊቷ በፋሻ ተደግልሎ ሥጋ ሳይሆን መልኳ ሻሽ በነበረበት ጊዜ ላለመታየት ከማድረግ ፣ ከመደበቅ በስተቀር ሌላ አማራጭ አልነበራትም ። ይምሰላት እንጂ የትም ብትሔድ ፤ የትም ብትገባ ያለመታየት ዕድል አልነበራትም ። የተዋበው መልኳ ፣ አረማመዷና አጠቃላይ እንቅስቃሴዋ አለባበስዋ ይህ ሁሉ ዓይንን በግድ ይስባሉ ። የግንባሯን ላይ ፋሻ ለመከለል ያደረገችው ኮፍያ ሳይቀር ለሷ ውበት ሆኗታል ። ይሁን እንጂ ይህን አልተገነዘበችውም ። ስለዚሀም ማንም አያውቀኝም
👍23
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ስምንት (28)

እንደሚያፈቅራት ብትፈቅድለትና ፍቅራቸውን ለመካፈል ቢችሉ ደስ እንደሚለው ደጋግሞ ገልጾላታል ። ግን እሷ ልቧን ትጠራጠረዋለች ። በይመስለኛል ስሜት ተገፋፍታ ሳይሆንላት ቢቀር ፒተርን ማስቀየም
ይሆናል ። ይህንን ደግሞ ፈፅሞ አትፈልገውም ። ስለዚህ የፒተር ጥያቄ የኣሺታም የእምቢታም መልስ ሳያገኝ በውዝፍ ዶሴ ተይዞ ቀርቷል ። መዋደዳቸው ፤ መተሳሰባቸው ፤ ጓደኝነታቸው ግን አሌ የሚባል ነገር አይደለም ። «በጣም ናፍቀኸኝ ኖሯል ፒተር» አለች ሜሪ ። ይህን ብላ ህክምና በሚደረግላት ጊዜ እምትቀመጥበት ወንበር ላይ ተቀምጣ ሥራውን እንዲቀጥል ዝግጁ ሆነች ። ዓይኗን ገርበብ አደረገች ። ከወንበሩ ላይ ተነስቶ ትንሽ ከተመለከታት በኋላ « ዛሬ ደግሞ ለመታከም ጥድፊያ በጥድፈያ ሆነሻል » አላት በተለመደው ብርጩማው ላይ ፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡ « ሁለት ዓመት ሙሉ በፋሻ ስትሸፈን ፤ ፋሻ ሲላጥልክ ብታሳልፍና የመጨረሻው ቀን ቢመጣ አንተ ራስህስ ብትሆን ያንለት ለመገላገል መቻኮልህ ይቀር ነበር ? »

«አይቀርም ፤ እንዲሁ ለማለት ያህል አልኩ እንጂ ነገሩስ ይገባኛል ። ... በደንብ ይገባኛል የኔ መቤት» እግንባሯ ላይ ያለውን ፋሻ ካነሳላት በኋላ ፤ «አሁን አይንሽን መግለጥና ፊትሽን በመስታወት ማየት ትችያለሽ ፣ ሜሪ» አለ ። ሜሪ ግን ካለችበት ላይ ንቅንቅ አላለችም ። ብዙ ዓለም አይታ መጥታለች ። ሆኖም የአዲስ እሷን ፊት ሙሉውን አታውቀውም ። አንደኛው ጐን ቢገለጥ ሌላኛው ወይ በፋሻ ተሸፍኖ ወይ ፕላስተር ተለጥፎበት ወይም ተደርቶ ነበር የምታየው። «በያ ብድግ በይና ወደ መስታወቱ ቅረቢ» አለ ፒተር ያን አዲስ ፊት ፤ ያን ናንሲ ማክአሊስተር የነበረችውን የቀድሞ እሷን ሳይሆን ሜሪ አዳምሰን የተባለችውን አዲስ እሷን ለማየት ፍርሃት ተጫናት ። ምን ያለ የማይረባ ፍርሃት ነው አለች በሐሳቧ። ፍርሃቷን እሸንፋ ተነሳች ። ፊቷን በመስታወቱ ውስጥ ስታይ ፊቷ በሳቅ ቧ ብሎ ተከፈተ ። በጉንጯ ላይ ግን እንባዋ ይጐርፍ ነበር ። ይህ የስሜት ግንፈላ ተግ እስኪልላት ድረስ አልተጠጋትም ። አላነገራትም ። ያ ጊዜ የግሏ የሆነ ማንም ሊጋራት የማይገባ ጊዜ እንደሆነ በመገንዘብ ። «ፒተር ፤ እረ የፈጣሪ ያለህ ! እንዴት ቆንጆ ነው አለች ። «አይ አንቺ ቂል ፍጡር» አለ ፒተር በለሆሳስ እየሳቀ «እንዴት ቆንጆ ነው ሳይሆን እንዴት ቆንጆ ነኝ በይ… ያቺ የምታያት ሌላ ሰው ወይ ሌላ ነገር አይደለችም ። አንቺ ነሽ ራስሽ ነሽ›› ዞራ አየችው ። የተናገረው ትክክል እንደሆነ በቃላት መግለጽ አቃታት ። ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች ። ልክ ነው ። ሙሉ በሙሉ ተቀይራለች ። ከምታውቀው መልኳ የቀረ ቅንጣት ምልክት የለም ። አሁን ያላንዳች ማወላወል ሜሪ አዳምሰን ነኝ ስትል አመነች

«ፒተር !...» አለች ውለታ በበዛበት ድምጽ ። ሄዳ ተጠመጠመችበት ። ተቃቅፈው ብዙ ጊዜ ቆዩ ። በመጨረሻ ፊቷን ለማየት እስኪችል ድረስ በክንዶቿ ይዞ ራቅ አደረጋት ። ፈቷ በእንባ ርሷል ። በጣቶቹ ጠረገላት ። «ፒተር. . . አየህ እንባየ እንኳ ፊቱን አላሟሟውም ! » አለች ። «ያ ብቻ ሳይሆን በትንሽ በትንሹ ይሁን እንጂ ፀሐይም መሞቅ ትችያለሽ» አላት ። ከዚያ በኋላ ግን ዕድሜሽን በሙሉ የፈለግሽውን ነገር ማድረግ ትችያለሽ ። ደስ ያለሽን ብትሆኝ ምንም አደጋ አይኖርም ። በነገራችን ላይ ምን ለማድረግ ነው እቅድሽ ? »

ይህን ብላ እተሽከርካሪው ወንበር ላይ ተቀምጣ ፤ እግሯ ጉንጯን ነክቶ ከራሷ በላይ እስኪሆን ሽቅብ አንስታ ከወንበሩ ጋር መሽከርከር ጀመፎች ። «አምላኬ እስቲ ይኸን ምን ትለዋለህ ? ሴትዮዋ እቢሮዬ ውስጥ ገብታ አንድ አካሏ ቢጐድል ሰው ምን ይለኛል ። አበጀህ እንኳን ይለኝ ይሆን ?»
«አትፍራ እኔ እንደሆነ ዛሬ የመጣው ቢመጣ ጥርሴ እረገፈ ፤ እግሬ ተሰበረ ... ካሣ ምናምን እንደማልል ይግባህ ።የማከብረው እንጂ የምጨቃጨቅበት ቀን አይደለም»
«እንዲያም ከሆነ መልካም ። ይህ ቀን ዓመት ባልሽ መሆኑን መስማቴ ደሞ በጣም ደስ አስኝቶኛል » ፒተር ብቻ ሳይሆን ፍሬድም (ውሻው) በሆነው ነገር ደስ ያለው ይመስላል ። ይዘላል ፤ ይቧርቃል ፤ ጭራውን ይቆላል። የተናገርኩት ስለገባው ነው አለች ውሻውን እያሰበች ። ከዚያም ጨብጠኝ እንደማለት እጅዋን እየዘረጋችለት ፣ «አላወክም ነበር ማለት ነው ጅሎ !. ይህን ዕለት ለማክበር ለራሳችን ጢን ያለ የምሳ ግብዣ እናደርጋለን ፒተር›› አለች ። ስሙን ከጠራችው በኋላ ሙሉ በሙሉ እያየችው «ፒተር ውለታህን ልከፍልህ የምችል አይመስለኝም ። ግን ደግሞ እስከመቃብር ከልቤ አትጠፋም ። መቼም ቢሆን የትም ቢሆን አስታውስሃለሁ ። በበድን አካሌ ነፍስ የዘራህባት አንተ ነህ» አለች ።

«አ…እ… እኔ ሳልሆን ሌላ ሰው ነው» አለ ፒተር ። አዎ ማሪዮን ሂልያርድ ፤ የማይክል እናት ናት ፤ ይህ ሁሉ እንዲሆን ያደረገችው። ግን ደግሞ ሜሪ ማሪዮንን ምን ያህል እንደምትጠላት ስለሚያውቅ ስሟን ሊጠራ አልፈላገም ። ሌላ ሰው ብሎ ጠራት ።
ቀጥሎም...
«እኔ. .. እኔ በበኩሌ ግን ሜሪ… ያደረግኩልሽን ሁሉ ስላደረኩልሽ ደስ ይለኛል ። ለወደፊቱም ላደርግልሽ የምትፈልጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ» አለ ። «ነው?... ቀልድ መስሎሃል ፤ አደል ? እንዲያውም ከዛሬ እንጀምራለን ፤ ዛሬ በስድስት ሰዓት ተኩል ተገናኝተን ምሳዬን እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ ። እሺ?»
«ደስ ይለኛል»
«የት እንገናኝ ? » አንድ በቅርብ የተከፈተ ምግብ ቤት ጠቀሰላትና ታውቀው እንደሆነ ጠየቃት ።
«በሚገባ !» አለች ።
«ይስማማሻል ?››
«አሳምሮ ። እንዲያውም ካሁን ጀምሬ ወደዚያው አካባቢ ሄጂ ሰዓቱ እስኪደርስ ፎቶግራፍ ሳነሳ እቆያለሁ፡፡ አይን የሚገባ ነገር ከተገኘ»
«አሁን የልቤን ምኞት ነገርሺኝ ። ገበያ ሄጄ አዲስ ልብስ ስመርጥ ወይም ሌላ ብትይኝ ኖር ይከፋኝ ነበር» ተሰነባብተው ተለያዩ ፤ እስከምሳ ሰዓት ።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በምሳ ሰዓት ሲገናኙ ልብሷን ቀይራ ሽክ ብላ አገኛት ። «በእውነት ይቺ ሴት አንቺው ራስሽ ነሽ ?»
«ባለወርቅ ጫማዋ ልዕልት እነሆኝ ፡። እንዴት ነው ፤ አምሮብኛል ?»
«አምሮብኛል !? እንደ ቅዱሳን አንፀባርቀሻል እንጂ ፤ ምንማማር ብቻ! ... እንደፈራሁት ፎቶ ግራፍ ማነሳሳቱን ትተሽ ቀሚስ መረጣ ላይ ዋልሽ ልበል?»
«ምን ይደረግ ትላለህ ። ሳስበው ለካ ይህ ቀን የሚከበር ፌስታ የሚደረግበት እንጂ የሚሠራበት አይደለም» ድንገት አቅፈህ ሳማት የሚል ሐሳብ መጣበት ፤ እምግብ ቤቱ ውስጥ ያ ሁሉ ሰው እያዬ ። ሐሳቡን ገታና እጅዋን ጥብቅ አድርጐ ያዛት ። «ውዴ ይህን ያህል ደስ ብሎሽ ስላየሁ እኔንም እጅግ ደስ አለኝ» ኣለ ። «ፒተር በጣም ደስ ብሎኛል ። የዛሬዋ ቀን ለኔ ልዩ ናት። ስለገጽታዬ ብቻ አይምሰልህ ። የዛሬ ቀን. . . ነገ የፎቶግራፍ ተርኢት የማቀርብበት ፤ ኤግዚቢሽኔ የሚከፈትበት ቀንም ስለሆነ... አዲስ ሕይወት መጀመሬም ነው።... አንተም አጠገቤ እንዳለህና ድንቅ እንደሆንክ ስለማውቅ»
👍141
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ዘጠኝ (29)

«ውዴ . . . እስኪ ዚፔን ዝጋልኝ » ብላ ውብ ጀርባዋን አዞረችለት « እኔ እንኳ ደስ የሚለኝ… ብከፍተው ነበር››
«ፒተር ! . . . እንዲህ ያለ ወሬ… » አለች በማስጠንቀቅ መልክ ተገላምጣ እያያችው ። ሁለቱም ሳቁ ። አለባበሷን ሲመለከት ፣ ውበቷን ሲያይ በአድናቆት ተዋጠ ። «በኋላ ምን ብሎ ነበር ብለሽ ናቂኝ አንድ ሰው ፎቶግራፍሽን ቢያይ ከምላሴ ጠጉር »
« ለምን?»
«የተመልካች ዓይን አንቺው ላይ ያርፋል ። እዚያ ተተክሎ ይቀራል። በቃ !»
« ያን ያህል ?» ይህን ስትል ያለውን ነገር ፈጽሞ እንዳላመነች ገባው ። ጥርጣሬዋ የመገረም ሳቅ አሳቀው ። እሱም በኤግዚብሽን መክፈቻ ላይ ሽክ ብሎ ለብሷል ። ቢጋቡ የሚያስቀኑ ባልና ሚስት ይሆናሉ። «እንዴት ነው ? ፎቶ ግራፎቹን እንደምትፈልጊው አድርገው ሰቀሉልሽ ? ጊዜው ጠፋና ይህን እንኳ ልጠይቅሽ አልቻልኩም»
«ምንም ችግር የለም ። ያዘዝኩት ሁሉ እንዳዘዝኩት ሆኖ ተፈጽሟል ። እድሜ ላንተ ፤ ፒተር ። ይኸኔ ቅር ይላትና ዋ! ብለሀቸዋል ። ወይ አንተ ወይ ጃክ ይህን ያላችሁ ይመስለኛል » ጃክ የኤግዚብሽኑ አዳራሽ ባለቤት ሲሆን የፒተር ግሬሰ? የረጂም ጊዜ ጓደኛ ነው ። « ሁሉን ነገር ሰው ይሰራዋል ። እኔ በቃ አርቲስት ብቻ ነኝ የሚል ስሜት ይሰማኝ ጀመር››
«ሊሰማሽ የሚገባ ነው። ይሀ ትርኢት ሲያልቅ የኪነጥበብ ስራሽ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ያኔ ታያለሽ ።»

እንዳለውም ሆነ ። ኤግዚብሽኑ በተከፈት ማግስት በጋዜጦች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች በአድናቆት የተሞሉ ነበሩ። ፒተርና ሜሪ ጧት ቁርሳቸውን በልተው ቡና እየጠጡ ጋዜጦችን ሲያነቡ በጣም ደስ አላቸው ። «አላልኩሽም ?» አላት ፒተር ፤ ገና የመጀመሪያውን በአድናቆት የተሞላ አስተያየት ሲያነብ « አየሽ ? ኮከብ ነሽኮ »
«አንተ ደሞ ጅል ነህ ! » አለችና ጋዜጣውን አስደገፈበት ጭኑ ላይ ዘጭ ብላ ተቀመጠችበት ። ጋዜጣው ተጨማደደ። «እስከሚቀጥሊው ሳምንት ቆይና ደሞ ሌላ ተአምር ታያለሽ ። እያንዳንዱ ፎቶግራፍ እያራባ የሚሸጥ ድርጅትና ፎቶግራፍ አሻሻጭ ከመላ ሀገሪቱ ዳር እስከዳር ስልክ እየደወለ ባያስቸግርሽ ቱ! ከምላሴ ፀጉር ! »
«በቃ አዕምሮሀን እንደመንሳት እያደረገህ ነውኮ ውዴ!» ሆኖም የፒተር ግምት ሜሪ የገመተችውን ያህል ከእውነት የራቀ አልነበረም ። በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ከተለያዩ ሰዎች የስልክ ጥሪዎች ይመጡ ጀመር። ሰኞ ዕለት ከሎስ አንጀለስ እና ከችካጐ የተለያዩ ጥሪዎች ደረሷት ። እያንዳንዱ ሰው ስልክ ደውሎ የሚያቀርብላት ጥያቄና አድናቆት አስደነቃትም ። አስደሰታትም ። ስለዚህም ስልክ በተደወለ ቁጥር አሁን ደግሞ ምን ይሉ ይሆን ? በሚል ጉጉት ስልኩን ታነሣለች ። ይህ ቀጠለ ፤ ቤን አቭሪ እስኪደውልላት ድረስ ።

ቤን አቭሪ የደወለው አንድ ማክሰኞ ቀን ወደ ማታ አካባቢ ነበር ። በዚያም ሰዓት ሜሪ ፊልሞችን ለማሳደግና ለማጣብ በማሰናዳት ላይ ነበረች ። ከተለያዩ ቦታዎች ፎቶግራፎቿን ለመግዛት የትእዛዝ ጐርፍ መጉረፍ ጀምሮ ስለነበር ከፎቶግራፍ ማጠቢያው ክፍል (ዳርክ ሩም) ለመውጣት እንኳ ጊዜ አነበራትም ። በሥራዋ ተመስጣ እያለች ስልኩ ተንጫረረ። ሥራዋን አቋርጣ እየተጣደፈች ወጣች ። ምክንያቱም ፒተር «በዚያ ሰዓት ስብሰባ ስላለብኝ ደውዬ የት እንደምንገናኝ እነግርሻለሁ » ብሏት ነበር ። ስልኩን አንሥታ «ሃሎ » አለች ። «ሚስ አዳምሰን» አለ አንድ የማታውቀው ድምጽ፡፡ «ነኝ» አለች ፒተር ስለመሰላት በገጽታዋ ላይ ፈክቶ የነበረው ፈገግታዋ እየጨለመ ። «አኦ.. ከዚህ በፊት ለገና በዓል የስጦታ ዕቃዎችን ስገዛ ሚስ አዳምሰን ከምትባል ሰው ጋር ተዋውቀን ነበር ። ከሞክሼሽ ጋር ይሁን ካንቺ ጋር እርግጠኛ አይደለሁም ። የጉዞ ሻንጣዎች ስገዛ ተገናኝተን... » ቤን ነው ማለት ነው ። አይደለሁም ልበለው? ለምን?
« ከኔ ጋር ሳይሆን አልቀረም » አለች…. መዋሸት የሚያስፈልግ አልመሰላትም ። «ማለቴ ...እኔ.. ነው ? ማለት የማውቃት ሚስ አዳምሰን ነሻ ? »
«ነኝ»
« ይህንን ማረጋገጡም አንድ ነገር ነው ። ማለት ተቀራርበን ለመነጋገር ባንችልም እንተዋወቃለን ። ብቻ አሁን የደወልኩልሽ እንኳ የያኔ ትውውቃችንን በሚመለከት አይደለም ። የፎቶግራፍሽን ኤግዚብሽን ስላየሁ አንዳንድ ነገር እንድንነጋገር ስለፈለኩ ነው ።. ...ግሩም የሆነ ሥራ ነው ሚስ አዳምሰን ። እኔም ጓደኛዬ ሚስ ታውንሴንድም ኤግዚብሽኑን ዓይተን የተሰማን ስሜት ከፍተኛ ነው » የጠራት ሴት ዕቃው የተገዛላት ሴት ትሆን ? የማወቅ ፍላጐት አደረባት ። ሆኖም መጠየቅና ማወቁ አስፈላጊ መስሎ አልተሰማትም ። ስለዚህም በረጂሙ ተንፍሳ…. «ደስ ስለተሰኛችሁ እኔም ደስ ብሎኛል ፤ ሚስተር አቭሪ›› አለች ።
« ስሜንም አልረሳሽም?»
«ስሞችና የመሳሰሉ ነገሮችን አልረሳም ። አንድ ዓይነት እነዚህን ነገሮች የማያስረሳ ተፈጥሮ አለኝ »
«መታደል ነው ። እኔ ደሞ የስም ነገር አይሳካልኝም ። ይኽ ደሞ ለሥራዬ ጥሩ ነገር አይደለም። አንጐሌ ወንፊት ቢጤ ሆኖ ሲፈጠር ጊዜ ምን ማድረግ ይቻለኛል ! ወደ ፍሬ ነገሩ ልመለስና ተገናኝተን ስለሥራዎችሽ ብንነጋገር በጣም ደስ ይለኝ ነበር ።»
« በምን መንገድ ? » አለች ። ምን የሚያነጋግረን ነገር ተፈጠረ ደግሞ ! አለች በሐሳቧ ። «እንዲህ ነው ሚስ አዳምሰን ። እዚህ ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ አንድ የሕክምና ማዕከል ሕንፃ በመሥራት ላይ እንገኛለን ። በጣም ግዙፍ የሆነ ፕሮጄክት ነው ። ፕሮጀክቱን ስንቀበል ከገባናቸው ውሎች አንዱ ሕንፃውን እስከማስዋብ ያለውን ሥራ ፈጽመን ማስረከብ እንዳለብን ይገልጸል ። ያንችን ፎቶግራፎች ስመለከት ለዚህ ተግባር በጣም ሊያገለግሉን እንደሚችሉ ተረድቻለሁ ። እንዴት አድርገን በምን ሁኔታ እንደምንጠቀምባቸው ግልጽ የሆነልን ነገር የለም ። ስለዚህም ተገናኝተን ይህንን ጭምር ብንወያይበት ደህና ገቢም ይኖረዋል ። ላንቺም ቢሆን ሥራሽን ያስተዋውቅልሻል» አለ ቤን ። ይህን ሲናገር በሙሉ ልቡ እንደነበረ ድምጹ ይናገራል፡፡ «ገባኝ።. . . ግን የትኛውን ድርጅት ወክለህ እንዳነጋገርከኝ ልትነግረኝ ትፈቅዳለህ ? » አለች ። ድርጅቱ ማን ሊሆን እንዶሚችል ስለጠረጠረች ፤ ከላይ ከላይ ሊላት ያሰበውን ትንፋሷን ቁጥር አድርጋ መጠባበቅ ጀመረች ።
«ድርጅቱ» አለ ቤን ኮራ ብሎ «የኒውዮርኩ ኮተር ሂልያርድ ነው»
«ነው... ስላሰብክልኝ አመሰግናለሁ።፤ ሚስተር አቭሪ ግን አይሆነኝም »
«አይሆነኝም ? ለምን ?» አለ የመደመም በሆነ ድምጽ
👍14
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ (30)

የጨለማውን ክፍል በር ከፍታ ገብታ መልሳ ልትዘጋው ስትል ስልኩ የጥሪ ድምጽ አሰማ። ቤን አቭሪ መሆን አለበት እንደገና የደወለው። ተናደደችና በሩን በርግዳ ወጥታ ወደ ስልኩ ሄደች። መነጋገሪያውን መንጭቃ ካነሳች በኋላ «አይሆንም ማለት አይሆንም ነው ! መልሴ አንድ ነው። ይኸን ደግሞ ቁርጥ ባለ ቃል ነግሬሃለሁ» ስትል ጮኸች፡፡ ‹‹የፈጣሪ ያለህ ምነው ምን አጠፋሁ?» አለ ለስላሳውና ልቧን የሚያበራው የፒተር ድምጽ። የፒተርን ከፊል ሳቅ ያፈነው ከፊል ድንጋጤ የበረዘው ድምጽ ስትሰማ ንዴቷ ባንዴ ቀዘቀዘ። አዕምሮዋም ርጋታን ተላበሰ። «ፒተር! አስደነገጥኩህ አደል ? ይቅርታ ። አንድ ሰው ስልክ ደውሎ የማይሆን የማይሆን ነገር ነግሮኝ አይሆንም ብዬው ነበር። እሱ መልሶ የደወለ መስሎኝኮ ነው»
«የፎቶ ግራፍ ትርኢቱን በሚመለከት ነው?»
‹‹አዎ ወደዚያው ነው»
«የአዳራሹ አስተዳደር የስልክ ቁጥርሽን ለማንም መስጠት አልነበረበትም። መልዕክት ተቀብለው ላንቺ መንገር ነበረባቸው። ያለዚያ የማንም ቦዘኔ እየተነሳ ያልሆነ ነገር ሊያደርግ ይችላል» ። የተበሳጨ መስሎ ተሰማት ። ‹‹ግን ደህና ነሽ አደለም ? »
«ደህና ነኝ» ይሀን ስትል መረሽዋን በድምጺ ስለተረዳ ደህና ነኝ ያለችውን አላመነም ። «ደግ መጣሁ ከአንድ ሰዓት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ እደርሳለሁ ። እስከዚያ ድረስ ማንም ቢደውል ስልክ ማንሳት የለም ከዚያ በኋላ የሚደውለውን ሰው እኔ እንደሚሆን አደርገዋለሁ»

ሌሎች የንግግር ልውውጦች ካደረጉ በኋላ ስልኩን ዘጋች ። ግን እንደደወለና ምን እንዳበሳጫት ለፒተር አለመንገሯን ስታስበው ጥፋት እንደሠራች ተሰማት ። ፒተር ያሰበው ቦዘኔ ቀውስ እንዳስቸገራት ነው። ቤን አቭሪ ግን ሁለቱንም አይደለም ። የሱ ጥፋት ፤ የወረወራትና የናቃት የማይክል ሂልያርድ ሰራተኛ መሆኑ ብቻ ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ ይሀን ጉዳይ ለፒተር መንገርም ጥሩ እንዳልሆነ ገመተች ። የለም ጥሩ አይደለም አለች በሐሳቧ ። ይህን ጉዳይ ብትነግረው ፒተር ይበልጥ ይጨነቃል ።

የማይክል ነገር እስካሁን ከልቡናዋ አልወጣም ። በጣም ጠልቆ በመግባቱም እስከመቼም ላይወጣላት ይችላል ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል ። ጥቅም የለውም ብላ ተወችው ። ያን ዕለት ቤን አቭሬ ደግሞ አልደወለም ። ይህም ተመስገን የሚያሰኝ ነበር ። ፒተር መጥቶ ከሱ ጋር ስትጨዋወት ችግሩም መሸበሩም ቀስ በቀስ ከሜሪ አዕምሮ እየደበዘዘና እየጠፋ ሄደ። ግን አልቀጠለም… በማግስቱ ጠዋት ቤን አቭሪ ደግሞ ደወለ «ሃይ ሚስ አዳምሰን ። ቤን አቭሪ ነኝ»
«ስማ ፤ ትናንት ማታ ሁሉን ነገር ተነጋግረን የጨረስን መሰለኝ ። ይሆንሻል ያልከው ሥራ አይሆነኝም፣አይስማማኝም አልኩህ በቃ፡፡»
«ግራ የገባኝኮ አልፈልግም አልሽ እንጄ ምን እንደማትፈልጊ እንኳ ያወቅሽ አይመስለኝም ። ከእኔና ከጓደኛዬ ጋር ምሳ እየበላን ለምን አንነጋገርም አይተሽኛል ሰው ነኝ ።አልበላሽ ! መነጋገር ደግሞ ምንም ጉዳት የለውም ። ወይስ መነጋገሩም ሊጐዳ ይችል ይሆን ?» ይችላል ቤን በጣም ሊጐዳ ይችላል ! አንተ አጠገብ መሆን ብዙ የተደበቀ ትዝታ ጐትቶ ያመጣል… በሐሳቧ ። «አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ። ግን አይመቸኝም ። ሥራ ይበዛብኛል» አለች ። ሌላ መንገድ ቢሞክር ፍንክች ሳትል ቀረች ተስፋ የሌለው ነገር ነው በሚል መንገድ ዓይኑን አፍጦ እያንከባለለ ዌንዲ ታውንሴንድን ተመለከታት ። ኮተር ሂልያርድ ትልቅ ድርጅት ነው ። እንደ ሜሪ ያለች ሰውን ለማስቀየም አይችልም፡፡ ይኸ ግን በቀጥታ ከድርጅቱ ጋር ጠብ ያላት ይመስላል። ምን በደል ደረሰባት ኮተር ሂልያርድን ለምን ጠላችው ?
«ነገስ አይመችሽም ?»
«ስማ... ቤን... ሚስተር አቭሪ መቼም አይመቸኝም። ፍላጐቱም የለኝም ። ፍላጐቱ ከሌለኝ ምንም የምንነጋገርበት ነገር የለም። አሁን ነገሬ ግልጽ ነው ?»
«የምሥራች የሚባልለት አይደለም እንጂ ግልጽስ ነው» አለ።
ጸጥታ…
«ግን» አለ ቤን «ግን ትልቅ የሙያ ስህተት የሠራሽ ይመስለኛል። ጉዳይ አስፈጻሚ ወይም ወኪል ካለሽ ብታማክሪው ይህን እኔ የነገርኩሽን ነገር ደግሞ ይነግርሻል»
«ነበር ግን ወኪል ወይም ነገረ ፈጅ የለኝም ። ስለዚህም አይለኝም ። ወኪል የማያስፈልገኝ ደግሞ ከራሴ ሌላ ማንንም መስማት ስለሌለብኝ ነው»
«ከስህተቶችሽ አንዱ ይህ አስተሳሰብ መሆን አለበት በነገር ባንራራቅ ደግ ነው»
«ስላሰብክልኝ አመሰግናለሁ ። ምክንያቱም ለሌላ ሰው ማሰብ ቅንነት ነው ። ግን እንድትቸገር አያሻም ። እና እንደገና ባንደዋወል ይመረጣል»

••••••

ቤን አቭሪ ከምድር ውስጥ ባቡር ጣቢያ ወጥቶ በፓርክ አቬንዩ ወደሚገኘው ቢሮው የሚወስደውን መንገድ በእግሩ ሲፈጭ የፌብሩዋሪን (የካቲት) ቅዝቃዜ በመፍራት ኤሊ እድንጋዩዋ ውስጥ ተሰብስባ እንደምትገባ እሱ ደግሞ እካፖርቱ ውስጥ ለመደበቅ አንገቱ ትከሻውን እስኪነካ በመሰብሰብ ነበር ። ዝናብ ሊጥል አጓግቶ እንደመጣ ከአየሩ ሁኔታ ተረዳ ። ገና ለሁለት ሰዓት ጥቂት ደቂቃ ጉዳይ ቢሆንም ቸኩሏል ። የሥራ መግቢያ ሰዓት ማለትም ሦስት እስኪሞላ ሊጠብቅ አይችልም ። ብዙ ሥራ ይጠብቀዋል ። ከሳንፍራንሲስኮ የተመለሰው ትናንት ሲሆን ከኮተር ሂልያርድ ሥራ አስኪያጅ ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር አራት ሰዓት ላይ ስብሰባ እንደሚኖረው ተነግሮታል ። መልካም ነገር ይዞላት እንደሚቀርብም ይተማመናል ።

በመሥሪያ ቤቱ ማረፊያ ክፍል ውስጥ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል ። አሳንሰሮችም ጥቅጥቅ እያሉ በመሙላት ሰዎችን ወደየቢሮአቸው ማጓጓዝ ቀጥለዋል ። ገና ጥዋት ቢሆንም የንግድ ሥራው ዓለም መተራመሱን ጀምሯል ። ሕይወት ረጋ ብላ በምትፈስበት ሳንፍራንሲስኮ ቆይቶ የንግድ ዓቢይ ፈለግ ወደሆነችው ኒው ዮርክ ሲመለስ የዚችን ከተማ ትርምስ ለሚያውቃት ቤን አቭሪ እንኳ አስደንጋጭ ሆነበት ። የሱ ቢሮ ከሚገኝበት ፎቅ ደርሶ ሲመለከት ቀድሞት የገባና ሥራ የጀመረ ሰው አልነበረም ። ቢሮው ምንም እንኳ የማይክል ሂልያርድን ቢሮ ያህል የሰፋና እንደ ማይክል ቢሮም በልዩ ምርጫ የተሰናዳ ዕቃ ባይኖረውም ምቹና ያሸበረቀም ነው፡፡ ማርዮን ሂልያርድ ለኮተር ሂልያርድ ቢሮዎች ምቾትን ለመስጠት በወጭው ላይ ወደኋላ የማትል ሥራ አስኪያጅ ናት ። ካፖርቱን ካወለቀና ሰውነቱን ለማሟሟቅ ከመዳፍ ለመዳፍ ማፋጨት እስከወገብ እንቅስቃሴ ያለውን ከፈጸመ በኋላ ስለሥራው ማሰብ ጀመረ ። ሆኖም የኒውዮርክ የዝናብ ወቅት ብርድ ከሰውነቱ ሙልጭ ብሎ አልወጣም ። ቢሮው ራሱ በረዶ የተጋገረበት ያህል ቀዝቃዛ ነበር፣ መጋረጃውም ወፍራም ሕንፃውም ሙቀትን አፍኖ ለማቆየት የሚችል ሆኖ ቢሠራም እንኳ ግን ብርድ አለ ብሎ አርፎ መቀመጥ አይችልም ። የተለያዩ ጉዳዮችን የያዙ ወረቀቶችን ከቦርሳው እያወጣ እጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ተመሳሳይ ጉዳይ ያላቸውን አንድ ላይ ማድረግ ጀመረ ።

ስለተልዕኮው አሰበ ። ሁሉም ነገር ቀና መንገድ ይዟል ። ከአንድ አነስተኛ ነገር በስተቀር ። ያ ደግሞ የሚስተካከልበት መንገድ ይገኝለት ይሆናል ። ሰዓቱን ተመለከተ ። ይሁን አይሁን የሚል ጥያቄ መጣበት ። ቢሳካም ባይሳካም አንዴ መሞከር እንዳለበት ወሰነ ። ያን ያስቸገረውን ጉዳይ አንድ መልካም እልባት ላይ አድርሶ ስብሰባውን ቢካፈል ደስ ይለው ነበር ። ቤን አቭሪ ከሜሪ አዳምሰን የፎቶግራፍ ሥራዎች ጥቂቱን ይዞ መጥቷል ። ሜሪ እነዚያን ፎቶግራፎች እንዳልሰጠችው ግልጽ ነው ። በቀጥታ ከሷ ሳይሆን ከኤግዚቢሽኑ ቦታ ነበር የገዛው ። የፎቶግራፎቹ ዋጋ ደግሞ የሆነውን ቢሆን የባከነ ገንዘብ እንደማይሆን
👍25
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አንድ (31)

ያን ድምጽ ከዚህ በፊት ሰምቶታል ? የት? ሊያስታውሰው አልቻለም ። ግን ደግሞ ያ ድምጽ አዲስ አይደለም ። እንዲያውም የአንዲት በቅርብ የሚያውቃት ሴት ድምጽ እንደሆነ ይሰማዋል። የማንን ድምጽ ነው የሚመስለው ? አሰበ ። አሰበ… ሊያስታውስ አልቻለም « ልልሀ የፈለኩትን ነገር ገና ልትረዳልኝ አልቻልክም ይሆን በሥላሴ ? › እኒህ በቁጣ የጠነከሩ ቃላት ከፍለጋው መለሱት። ወደ አሁን አመጡት ። ከሜሪ አዳምሰን ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው ። እውነቱን እንዲያይ ፤ ይህቺ ሜሪ እንጂ ማንም እንዳይደለች እንዲረዳ አደረጉት ። ባኛል ሆኖም ተስፋ ያደረግኩት »
«ተስፋ ዝባዝንኬ!... ነገርኩህ'ኮ አልፈልግም አልኩህ ፤ በዚሀ ነገር ላይ ለመነጋገር ይህን ነገር አውጥቶ አውርዶ ለማሰብ ወይም ለኔ ምኔም ስላልሆነው የሳንፍራንሲስኮ የሕክምና ማዕከል አንዲት ቃል ለመነጋገር አልፈልግም ። በሥላሴ ይዤሃለሁ ፤ ተወኝ » ይህን ተናግራ እጆሮው ላይ ደረገመችበት ። የተዘጋውን ስልክ ማነጋገሪያ በእጁ ይዞ የጅል ፈገግታ ፈገገ ። ከዚያም «ይኸው አፈነዳሁትና አረፍኩ ወንድሞቼ» አለ ።

ቤን ይህን የተናገረው ለራሱ ነበር ። በሐሳብ ስለተዋጠ የቢሮውን በር ከፍቶ መቃኑን በመዝናናት ደገፍ ብሎ የቆመው ማይክልን አላየውም ። «እንኳን ደህና መጣህ ። ለመሆኑ ምንድነው ያፈነዳኸው ?» ማይክ ይህን ጥያቄ የጠየቀው ይህን ያህል ለማወቅ በመጓጓት አልነበረም ። የጓደኛው መመለስ እንዳስደሰተው ብቻ ነበር ገጽታው የሚገልጸው ። በፊቱ ላይ ደስታው እንደጐላ ወደ ቤን ቢሮ ገብቶ በምቹው የእንግዳ መቀበያ ሶፋ ላይ ቁጭ አለ። «ከጉዞሀ ተመልሰህ ሳይህ ደስ አለኝ»
«መመለሱስ አይከፋም ነበር ። ግን ምን ዋጋ አለው ? የሳንራንሲስኮን አየር ተለማምደህ መጥተህ የኒውዮርክን ብርድ ፍጹም ሰውነትህ አይቀበለውም»
«ለስላሳው ፍጡር ሆይ ካሁን ጀምሮ ከሞቃታማዎቹ የደቡባዊ ክፍሎች እንዳትወጣ የተቻለንን ያህል እንሞክራለን» አለ በጸሎት ድምጽ ።። ከዚያ ቀጠል አድርጐ «የስልኩ ጭቅጭቅ ስለምን ነበር ?» ሲል ጠየቀው ። «እሱን አታንሳው ። በዚህ የሥራ ጉብኝት ውስጥ እሾርባዬ ውስጥ ያጋጠመኝ አንድና አስቸጋሪ የሆነ ፀጉር ! » አለ።«ማለት ሁሉ ነገር እንደከረከሙት ሁሉ እየተስተካከለ ሲመጣ… እንዳሰብነው ፣ እንደፈለግነው ሲሆን . . . ርግጠኛ ነኝ ሪፖርቱ ሲቀርብ እናትህ ተፍነክንካም አታበቃ… አንድ ነገር ግን አሻፈረኝ አለ። ርግጥ ነው ፤ አልሳካ ያለው ነገር ይህን ያህል ትልቅ ችግር የሚባል አይደለም ። የኔ ሃሳብ ግን ሙሉ ስኬትን ለመፍጠር ነበር ።»
«እንዴት ነው ፤ ነገሩ ምን ይሆን እያልኩ መጨነቅ ልጀምር ወይስ?»
«አያስፈልግም ። ተሸወድኩ ልበልህ…. እንዴት መሰለህ አንዲት አርቲስት አጋጠመችኝ። ፎቶ ግራፍ አንሺ ናት ። ማለቴ ግዙፍ ችሎታ ያላት ፍጡር…. ማይክ እንዲህ ተራ ነገር እንዳትመስልህ ። ኤግዚቢሽን ታሳይ ነበር ። ኤግዚቢሽኑን ተመለከትኩት። ባለፈው ጊዜ በሕንፃ ማስጌጡ ሥራ ላይ ፎቶግራፎችን መጠቀም እንደሚቻል ሰብሰባ ላይ የተስማማንበትን አስታወስኩ። ልቀጥራት ፈለግኩ »
« እሺ?»
« ነገርኳት ››
«‹ መልሷ!? »
«አንገቴ ይቆረጣልንጂ ያንተን ስራ አልነካውም አለችኝ ። እንነጋገርበት አልኳት ። አይሞከርም አለች »
«ምን ምክንያት ሰጠችህ?... የኪነጥበብ ስራዬን ለገንዘብና ለንግድ አላውልም ነው ወይስ ሌላ ?»
«ምኑም ምኑ ሊገባኝ አልቻለም። ገና ነገሩን ሀ ብዬ ሳነሳ ጅራቷን ሸጉጣ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ጀመረች። ልታስጠጋኝ አልቻለችም» ማይክ ጅሎ በሚል አስተያየት እየተመለከተው ፣

«ነገሩ አይገባም አልክ? ግን ግልጽ ነው።» እምቢ ያለችህ በከንቱ አይምሰልህ ። ኮተር ሂልያርድ ምን ያህል ግዙፍ ድርጅት እንደሆነ ታውቃታለች ማለት ነው ። እምቢታዋ የሚታየው በርካታ ገንዘብ ይሰጥሻል እስክትባል ነው ። ለመሆኑ ይህን ያህል አሪፍ ናት?»
‹‹ተወዳዳሪ የላትም ስልህ ። ምን አለፋኝ እኔን ፤ ከፎቶግራፎችዋ ጥቂቶቹን ለናሙና ያህል ይዤ መጥቻለሁ አደል እንዴ ታያቸውና ራስህ ትፈርዳለህ »
«እንዲያ ከሆነ የፈለገችውን ማግኘት ትችላለች። የለም ፎቶግራፎቹን በኋላ እናያቸዋለን ። አሁን ለአንድ ጉዳይ ላነጋግርህ ፈልጌ ነው የመጣሁት » ማይክል ይህን ሲል በቁም ነገር ነበር። ነገሩን ለቤን ለመንገር ብዙ ጊዜ አስቦበታል ። «የሆነ ጥፋት ኣለ?»
«የለም… ምንም ጥፋት የለም ። እንዲያውም ይህን ጥያቄ ሳነሳብህ ምን ያህል አካባቢየን ማየት የማልችል አጋሰስ ነኝ የሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው። ሆኖም ደህና ማለት ከዌንዲ ጋር የሆነ ግንኙነት ፈጥራችኋል?»

ለዚህ ጥያቄ መልስ ከመስጠቱ በፊት ቤን አቭሪ የማይክልን ፊት በደንብ አድርጎ መመልክት ጀመረ ። ማይክል የማወቅ ፍላጐት ያደረበት እንጂ ፈጽሞም የተቀየመ አይመስልም። ርግጥ ነው ቤን ስለማይክልና ስለዊንዲ ግንኙነት በሚገባ ያውቃል ። ግን ደግሞ ማይክል ለዌንዲ ደንታ እንዳልነበረውም ያደባባይ ምስጢር ነው። ቢሆንም አሁን ሲያስበው ፤ በተለይም ከማይክል ጋር ከዚህ በፊት በዚህ ዓይነት ተገጣጥመው ስለማያውቁ እና ማይክ ይህ መሆኑን ሲገነዘብ የሚሰማውን ስሜት መረዳት ስላዳገተው ቤን አቭሪ ተጨነቀ ። ጓደኛው የቀመሳትን ፤ ቢተዋትም የሱ የነበረችን ሴት መውሰድ መልካም እንዳይደለ ገባው። ያም ሆነ ይህ እውነቱ እውነት ነው። ዌንዲና ቤን ይፋቀራሉ። ስራቸው አንድ ላይ በመሆኑም አንድ ላይ ይጓዛሉ ። ባለፉት ወራት በሳንፍራንሲስኮና በሎስ አንጀለስ ሲሰሩ ባልና ሚስት ሆነው ነው ያሳለፉት ። እንዲያውም ቤን የጫጉላ ቤታችንን ጊዜ በማሳለፍ ላይ እንገኛለን እያለ ሲቀልድባት ነበር ። « አልመለስክልኝምኮ » አለ ማይክል ። ቤን አቭሪ ከሃሳቡ ብትት ብሎ ነቃ ። «አስቀድሜ ባለመንገሬ ጅልነቴ ተሰማኝ ። መልሱ ግን ፤ እዎ ነው ። ቅር ይልሃል ማይክ !?»
👍13
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ሁለት (32)


ለሷ ማይክል ሂልያርድ የሚባል ሰው የለም፤ ስትፈልገው ሲሸሻት በስጋ አብሯት ተቀምጦ እንኳ በመንፈሱ ሲርቃት ምን ያህል እንዳቆሰላት የታወቀ ነው ። የለም አብርው ሆነው የሚያውቁም አይመስላትም ።
«እንሂዳ ። ያላዘጋጀኸው ነገር አለ ንዴ?»
« በቂ ያህል የተዘጋጀሁ ይመስለኛል »
« ደህና »
«በነገራችን ላይ ለሜሪ አዳምሰን ፎቶግራፍ አንሺዋ ደውየላት ነበር »
« ምን አለች ? »
« ሰውዬ ባትጨቀጭቀኝ ምናለ ! አለችኝ »
« የሚገርም ነገር ነው»


በስብሰባዋ ላይ ማሪዮን ሂልያርድ ከየክፍሉና ከየፕሮጀክቶቹ የመጡትን ሠራተኞች ተራ በተራ እንዲናገሩ የክፍሉን ወይም የፕሮጀክቱን ስም እየጠራች ትጠይቅ ጀመር ። የተከናወኑ ስራዎች ባለፈው ስብሰባ ላይ የቀረቡ ችግሮችና የተሰጣቸው መፍትሔ ባሁኑ የሥራ ክንዋኔ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ሁሉም ለስብሰባው ይልቁንም ለማሪዮ ከቀረቡ በኋላ በቂ መመሪያዎችና መፍትሔዎች ተሰጡ ። የሳንፍራንሲስኮ የህክምና ማዕከል ፕሮጀክትን በሚመለከት ቤን አቭሪና ዌንዲ እየተቀባበሉና እየተረዳዱ ራፖራቸውን አቀረቡ። ራፖሩን አቅርበው እንደጨረሱ የማሪዮን ፊት በደስታ ፈካ። በተለይም የዚህ የሳንፍራንሲስኮ ፕሮጀክት ዋና ኃላፊ ልጅዋ ማይክል ሂልያርድ በመሆኑ በዚያ ስብሰባ ላይ ከቀረቡትመ የሥራ አፈፃጸም ሪፖርቶች ሁሉ ይህ የሳንፍራንሲስኮው ፕሮጀክት ከፍተኛ ክንዋኔ እንዳደረገ ስለተረዳችና ይህም ማይክል ሂልያርድ ጠንካራ ሠራተኛና የሥራ መሪ መሆኑን ስላስገነዘባት የማርዮን ደስታ እጥፍ ድርብ ነበር። ምክንያቱም ይህ ኮተር ሂሊያርድ የተባለ ድርጅት ዞሮ ዞሮ በማይክል እጅ መግባቱ አይቀርም ። የኮተር ሂልያርድን ዋና ሥራ አስኪያጅነት ዙፋን ከመውረስ የሚተናነስ አይደለም ። የኮተር ሂልያርድ ግዝፈት ደግሞ በእድል የተገነባ ወይም ድንገት የሆነ ሳይሆን በጠንካራ ሰዎች የሌት ተቀን ጥረት ፤ ግረትና ብርታት የተገኘ ነው ። ማሪዮን ኮተር ሂልያርድን ለማስተዳደር ምን ያህል ኃይልና ፈቃደኛነት መስዋእትነትች እንደሚያስፈልግ ታውቃለች ። ማይክል ስራውን በሚገባ ሲያከናውን የተደሰተችውም ያን ጠንካራ ሰው ወልዳ ኮትኩታ አሳድጋ ስታየው ያሰበችው ሁሉ እንደሚሳካላት ስላወቀች ነው ።

«ሁሉ በወግ በወጉ ሲከናወን አንድ ትንሽ ነገር ብቻ ረበሸኝ» አሊ ቤን አቭሪ ። በማሪዮን የገረጣ ፊት ክንብል ብሎ የነበረው ቅላት ቀነሰ። ደም የመሰለው ጉንጯ ወደ ቀድሞ መልኩ ተመለሰ ። ይህን ሲያዩ በዚያ ክፍል ውስጥ የተሰበሰቡ ሁሉ ትንፋሻቸው መለስ አለ። በተለይም የቤን አቭሪ ። ስለሰአሊዋ ነገራት ።
«ይኸን ያህል ታስፈልገናለች? »
«በኔ ግምት በጣም ታስፈልገናለች ለናሙና ካነሳቻቸው ጥቂት ፎቶግራፎች ይዤ መጥቻለሁ ።»
«አላነጋግርህም አለችኝ እያልክ አልነበረም ? ታዲያ ፎቶግራፎቹን እንዴት ልትሰጥህ ቻለች?»
«እሷ ሰጥታኝ ሳይሆን ከትርኢት አዳራሽ ገዝቼ ነው ። የወጣው ገንዘብ በትክክል የወጣ ይመስለኛል ። ሆኖም ድርጅቱ ገንዘቡ የወጣበት ምክንያት በቂ አይደለም የሚል ከሆነ ገንዘቡን ከፍየ ፎቶግራፎቹን የግል ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ »
«እስኪ እንያቸው » ዌንዲ ፎቶግራፎቹዋን አመጣች ፤ ፎቶግራፎቹ ታዩ ። በጭብጥም በጊዜና በቦታ አመራረጥም የተዋጡ ነበሩ ። በፎቶግራፎቹ ላይ ዝብርቅርቅ ነገር አልነበረም ። ሌላ ሰው ቢያነሳቸው ወይ ጊዜውን ስላልጠበቀ ወይ በቦታው ላይ የሰፈሩ ነገሮች ተስማሚ ባለመሆናቸው የተነሳ ሊበላሽ ይችል ነበር ይሆን ? የሚያሰኙ ፎቶግራፎች ነበሩ ።

ማሪዮን ፎቶ ግራፎቹን በጥሞና ከተመለከተች በኋላ ቀና ብላ ቤንን ተመለከተችው ። ቤን ዝም አለ ። ቆይታ ፤ «እንዳልከው እንደምንም ልናግባባትና ልናስራት ይገባል›› አለች ። «ስለተስማማን ደስ አለኝ » አለ ቤን፡፡ «ማይክ ? » አለች ማሪዮን ሂልያርድ «ምን ይመስልሃል ?›› ማይክል ፎቶግራፎቹን ሲመለከት አንድ ዓይነት ስሜት ተሰማው ። የሚያስደነግጥ ። ወደ ኋላ የሚመልስ ስሜት ። የት እንዳየሁት እንጃ ግን አውቀዋለሁ የሚያሰኝ ስሜት በውስጡ ይመላለስ ጀምር ። ልቡን ቁልቁል ሳበው ። ጭብጣቸው ነው? ወይስ የሚነሳውን ነገር አመራረጥ ? ምኑን ነው የሚያውቀው ? ይህን ጥያቄ ሊመልስ ፈለገ ። ግን አልቻለም ። ፎቶግራፎቹን አትኩሮ በተመለከተ ቁጥር አእምሮው ላይ ጫና እየወደቀበት ሄደ። ፎቶ ግራፎቹ ጥበባዊ ኃይል እንዳላቸውም ተገነዘበ ። ስለዚህም ፤ «በጣም ድንቅ የጥበብ ሥራዎች ናቸው» አለ ። «እኔ ግሩም የጥበብ ሥራዎች ናቸው ብያለሁ ። ያን ያሀል ትልቅ ናቸው ነው እምትለኝ?» አለች ማሪዮን ፍርጥ አድርጐ እንዲነግራት እየገፋፋችው ። በቃላት ሳይሆን አንገቱን በአዎንታ ፅሙና በመነቅነቅ መለሰላት ። «ታዲያ ይችን ሴት በምን ሁኔታ ነው የኛ ልናደርጋት የምንችለው?» አለች ማሪዮን ፤«ቤን ምን ይመስልሃል?»
«የዚህን ጥያቄ መልስ ባውቀው እንዴት ደስ ባለኝ ነበር» አለ ቤን ። «ገንዘብ ነው መንገዱ ። ይህ ግልፅ የሆነ ነገር ነው» አለች ማሪዮን ። ለመሆኑ ሁኔታዋ እንደምንድነው ? ተገናኝታችሁ አይተሃታል?።»
«አይቻታለሁ። ማለት ይኸ ሁሉ ነገር ሳይሆን የገና በአል ከመዋሉ በፊት አንዳንድ የስጦታ እቃዎችን ስገዛ ድንገት ተገናኝተን ተነጋግረናል ። በጣም ቆንጆ ናት ። ማለት ቁንጅና እንዲህ እንደማንም ቁንጅና አይደለም ። እንከን አይወጣላትም ።ሙሉ በሙሉ ቆንጆ ። ደስ ባላት ቀን ከሆነ ማንንም ሰው ይሁን ልታናግረው፤ ልታጫውተው ፈቃደኛ ናት ። መልካም ሙያም አድሏታል፡፡ ቀደም ሲል ሰአሊ ነበረች የሚል ወሬ ሰምቻለሁ። የምትለብሳቸው ልብሶች በጥራትም በዋጋም በቀላል የሚገመቱ አይደሉም ። ችግር ያለበት አይመስለኝም ።

«የኤግዚቢሽን አዳራሹ ባለቤት እንደነገረኝ ከሆነ ወኪል ነገር አለት መሰለኝ ። አንድ በእድሜ ጠና ያለ ሀኪም ፤የታወቀ የቆዳ ቀዶ ጥገና (ፕላስቲክ ሰርጄሪ) ሀኪም ነው አሉ ። ብቻ በዚያም ተባለ በዚህ ያቀረብንላትን ጥያቄ ያልተቀበለችው ገንዘብ ለማስጨመር ብላ አይመስለኝም ። . . . የማውቀው ይህን ያህል ነው» አለ ቤን ። «ገንዘብ ካልሆነ ምን ?» አለች ማሪዮን ። ወዲያው አንድ ቀዥቃዣ ሃሳብ አእምሮዋ ውስጥ ተወራጨባት ። ደነገጠች ። የለም የለም ጭራሽ የማይሆን ቅዥት ነው አለች በሃሳቧ ። ግን ምኑ ይታወቃል ? እድሜዋ ምን ያህል ይሆናል ?» አለች ቤንን እየተመለከተች። «እንጃ ። ያኔ ከገና በፊት የተገናኘን እለት ዘርፈፍ ያለ ባርኔጣ ነበር ያደረገችው ። ፊቷን ክልሏት ስለነበር በደንብ አላየኋትም መሰለኝ ። ብቻ ከሃያ አራት ከሃያ አምስት ግፋ ቢል ከሃያ ስድስት ዓመት የሚበልጣት አይመስለኝም። ግን እድሜዋ ምን ያደርግልናል ?››

«እንዲሁ ነው ፤ ለማወቅ ያህል ። ይልቅ ስማኝ ቤን ። አንተና ዌንዲ የሚቻላችሁን ያህል ጥረት አድርጋችኋል። ድርጅቱ የሚፈልገውን ያህል ሰርታችኋል ። ልትመሰገኑ ይገባል ። ስለልጅቷም ቢሆን በናንተ በኩል ያለው አልቋል ። በሚቀጥለው ሣምንት ወደ ሳንፍራንሲስኮ መሄዴ ስለማይቀር እግረ መንገዴን ላነጋግራት እሞክራለሁ ። ምናልባት ከወጣቶች ይልቅ የአንዲት ባልቴት ነገር ሊከብዳት ይችላል››
👍21
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ሶስት (33)

‹‹እንግዲያውስ…. አንቺና ጆርጅ ተጋብታችሁ… ሥራውን ለቀሽ ማለት ነው፡፡ ለምን እየተደጋገፋችሁ ፤ ደስ እየተሰኛችሁ አትኖሩም ?! እግረ መንገዱን አዲስ አይነት ኑሮም ይሆንላችኋል » አለ ማይክ ። ማይክል ስለጆርጅ እና ስለ ማሪዮን ሂልያርድ ግንኙነት በግልፅ ሲናገር ይህ የመጀመሪያው ነበር ። ስለዚህ ጆርጅ ይህን ሲሰማ አፈረ ። ፊቱ ቀላ ። ሆኖም የመከፋት ስሜት አልታየበትም።
«ማይክል!» አለች ማሪዮን ። ያ ይህን አድርግ ፤ ይህን አታድርግ የሚለው ድምጽዋ እየተመለሰ «ማይክል እስበህ ተናገር። ሌላው ቢቀር ጆርጅን እስበው ። እንዴት እንዳስደነገጥከው ይታይሀል ? ያም ተባለ ይህ ሥራ ለመተው አልደረስኩም ። አመመኝም ቀረም ለመሥራት ጉልበት አላነሰኝም»
«እሱ እንዳልሽው ይሁን ፤እሺ ልበል። ምንም ማድረግ ልችልም። ግን ሥራ ቀንሺ። ማለት ለምሳሌ በሚቀጥለው ሳምንት ሳንፍራንሲስኮ መሄድሽ አስፈላጊ አይደለም ። እኔ ልሄድና ጉዳዩን ልፈፅም እችላለሁ ። እዚህ እዋናው መሥሪያ ቤት ቁጭ ብለሽ ይህን ያን አድርጉ ብትይን ልንረዳሽ እንችላለን ። በቃ፣ይህን ያህል እሺ በይኝ» ሳቀች እንጂ ሌላ መልስ አልሰጠችውም ። ከዚያም ብድግ ብላ ወደ መደበኛ የቢሮ መቀመጫዋ ሄደችና ተቀመጠች ። ስጋዋ እንደደከመ ይታያል ። መንፈሷ ግን ወደ ዱሮ ቦታው ተመልሷል ። ሁሉንም ካየች በኋላ ፡፡ «አሁን በከንፈር መጠጣና በአዘንልሽ አትጫኑኝ ። ሁላችሁም ማለቴ ነው ። ሂዱልኝ ። እናንተ ሥራ ከሌላችሁ… እንዲያ ይመስለኛል ሳያችሁ… እኔ ሥራ አለብኝ ፤ ልሥራበት»
«እማዬ ፤ ቤት አድርሼሽ ልምጣ።እስኪ አንዳንድ ቀን ሰው የሚልሽን እሺ በይ !» አለ ማይክል ቆጣና ኮረፍ ብሎ። «ማይክል የማይቻል ነገር አታውራ ። አሁን ቀጥ ብለህ ወደ ሥራህ ሂድ። ያለዚያ ጆርጅን እየገፈተርክ አስወጣልኝ እንዳልለው» ጆርጅ ፈገግ አለ… የነገሩ መታሰብ አስገርሞት ። «ባይሆን ሰዓት ደረሰ አልደረሰ ሳልል ለመሄድ እሞክራለሁ እንጄ አሁን አይሆንም ። በተረፈ ስለመልካም አስተሳሰብህና ስለሌላው እመሰግናለሁ ። በቃ ። ሩት ያን በር ክፈች» ጸሐፊዋ በሩን ከፍታ እንዲወጡ መጠባበቅ ጀመረች ። ማይክልና ቤን ወጡ ። ጆርጅ እደረጃው ላይ ቆሞ ፤
«ማሪዮን» አለ።
«እሀ»
«ወደ ቤት መሄድ አለብሽኮ »
«ትንሽ ቆየት ብዬ»
«ደግ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ እመለሳለሁ» ወጣ። ፈገግ አለች ። ሆኖም ወደራሷ ሀሳብ ስትመለስ ገና በሩ አልተዘጋም ።

የዛሬው ህመሟ የተነሳበት ምክንያት በሚገባ ታውቋታል ። ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ አለባት ። በሌላው ሌላ ምክንያት እየተነሳ እረፍት አሳጥቷታል ህመሙ። ሌላ መነሻ ሲጨመር ዝም ብላ ማየት አትችልም ። ለምን እንደሆነ አይግባት እንጂ ቤን አቭሪ ስለሜሪ አዳምሰን ሲናገር ሜሪ ማን እንደሆነች አውቃለች ። በርግጥ ናንሲ ማክአሊስተር ናት ብላለች ። ቅድም እስብሰባው ላይ በግልጥ እንደተናገረችው ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትሄድ ሜሪን ለማየትም ፤ ለማነጋገርም ወስናለች ። ግን ታውቃት ይሆን? ምናልባት የተደረገላት የቀዶ ጥገና ህክምና (ፕላስቲክ ሰርጀሪ) ፈጽሞ ለውጧት ሊሆን ይችላል ። ያስ ባይሆን ናንሲን በሚገባ ታስታውሳታለች እንዴ ? አይታወቅም ። ቤን አቭሪ የሰጣትን የሜሪ አዳምሰን አድራሻ አውጥታ ስልክ ደወለች። ስልኩ ሶስቴ ይሁን አራቴ ሲጮህ ተሰማት ። ተነሳ። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አቅሏን ስታ ወድቃ የነበረችው ማሪዮን ሂልያርድ መሆኗን ማንም ሊያምን በማይችልበት ደረጃ ረጋ ባለና ስልጣን በተሞላበት ድምጽ፤ «ሚስ አዳምሰን ። ማሪዮን ሂልያርድ ነኝ ፤ ከኒወዮርክ » ስትል ተናገረች ።

ንግግራቸው በጣም አጭር ፤ ተዝቃዛና በመደነጋገር የተሞላ ነበር። ማሪዮን ሂልያርድ ስለሜሪ አዳምሰን በተጨማሪ ያገኘችው እውቀትም አልነበረም ። ይሁን ። ልክ የዛሬ ሶስት ሳምንት ማወቅ የሚገባትን ሁሉ ታውታለች ። ሊገናኙ ተቀጣጥረዋል ። ማሪዮን ቀጠሮውን አጀንዳዋ ላይ ካሰፈረች በኋላ የወንበሯን መከዳ ደገፍ ብላ ወደ ኋላዋ ተለጠጠች ። አይኖቿን ዘጋች ።

ከሜሪ አዳምሰን ጋር ከተገናኙም በኋላ ምንም ጠቃሚ ነገር ላታገኝ ትችላለች ። ሁሉም እንዳሰበችው ላይሆን ይችላል ። ወይም ሜሪ ምንም ነገር ላለመናገር ትወስን ይሆናል... ሆናም ያን ቀን ትፈልገዋለች ። ልትናገራቸው ያውጠነጠነቻቸው ጥቂት ነገሮች አሉ ። ብቻ. . . ብቻ ከዚያ ወዲህ ክፉ ነገር እንዳያጋጥማት። ትልቁ ምኞቷ ይህ ብቻ ነው።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ሶስት ሣምንት ሲደርስ አጭር ጊዜ ነው፡፡ ሲያስቡት ይርዘም እንጂ፤ የማሪዮን ሂልያርድና የሜሪ አዳምሰን ቀጠሮ ደረሰ ከሶስት ሣምንት በኋላ እለተ ሰሉስ ።

ማሪዮን ሂልያርድ ፌይርሞንት በተባለው ሆቴል በተከራየችው የልዩ ማዕረግ ማረፊያዋ ሳሎን ውስጥ ተቀምጣለች ። እዚያ ክፍል ውስጥ አረፍ ብሎ ወደ ውጭ ለተመለከተ ሰው ደንቅ የሆነው ወደብና ከዚያ አልፎ የሚገኘው የማሪን ካውንቲ ውበት በእጅጉ ያስደምመዋል ። ከሌላ ሀሳብም ያወጣዋል ። ማሪዮን ሂልያርድ ግን ይህን ትእይንት ለማየት ፍላጐት አልነበራትም ። ስለዚያች ልጅ በማሰብ ላይ ነበረች ። ምን ሆና ይሆን? ምን ትመስል ይሆን? ግሬግሰን (ፒተር) ከሁለት ዓመት በፊት ታምር አሳይሻለሁ ብሎ አንደፎከረ ተሳክቶለት ታምር በርቶ ይሆን? ቤን አቭሪ ሜሪ አዳምሰንን ሲያያት የሚያውቃት ሴት እንዳልሆነችበት ግልፅ ነው… ማይክልም ቢያያት አያስታውሳትም ይሆን? እሷስ እንዴት ነው ይሆን የምትኖረው ? ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅር ይዞአት ይሆን ወይስ እንደማይክል ሁሉን ነገር ትታ አንገቷን ደፍታ ውስጧ እየበገነ መኖር ቀጥላ ይሆን ? ማሪዮን ሂልያርድ የቀጠሮው ሰዓት እስኪደርስ ስለ ናንሲ ማክአሊስተር ስታስብ ልጅዋ በመሀል ገባ። እሱም ፍቅር ያውቅ ነበር ። አፍቅሮ ነበር ። እንዲያውም አሁን እምትጠብቀው ማይክል ሂልያርድ በጣም ይወዳት የነበረችዋን ልጅ ነው። ግን…. እሷ ባትሆንስ ? ካልሆነች . . . ካልሆነች ምንም ለውጥ አያመጣም። እሷ ካልሆነች አንዲት የዚሁ አካባቢ ተወላጅ የሆነች ፎቶ አንሺ ናት ማለት ነው ቤን አቭሪ አይኑን የጣለባት ፎቶግራፍ አንሺ። በቃ። ሊሆን ይችላል ። ያወጣሁት ያወረድኩት ፤ አስቤ የቀመርኩት ፤እውነት ብዬ ያሰብኩት ነገር ሁሉ መሰረተ ቢስ ፤ አጉል ሀሳብ ሊሆን ይችላል አለች በሀሳቧ።

ምናልባት. . . ምናልባት
👍17
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አራት (34)

«ምን… ከኔ ጋር ? አዎ» አለች ማሪዮን ። ሁለቱም ፀጥ አሉ፣ ረጂም ለመሰለ ጊዜ ። በመጨረሻ «እንተዋወቃለን ናንሲ ። ፒተርን አውቀዋለሁ ። ላንች ያደረገልሽ ህክምናም እጅግ የሚደነቅ ነው» አለች ማሪዮን ።
«ትንሽ ስህተት ሳይፈጠር አልቀረም መሰለኝ ። እኔ ናንሲ ሳልሆን ሜሪ…» ንግግሯን አልጨረሰችም ። ጉልበቷ ተሟጦ ሲወጣ ተሰማት፡፡ ባዶ ሆነች። አጥንት አልባ የሆነች ይመስል ተልፈሰፈሰች ። እንባ አነቃት ። እንደምንም ብላ ተነሳች ። ወደ መስኮቱ ሄዳ ጀርባዋን ለማሪዮን ሰጥታ ቆመች ። እና «ማን . . . እንዴት ልታውቂኝ ቻልሽ ?» አለች ። የተሰበረ ድምፅ ነበር ። ማሪዮን ርግጠኛ ሆነች ። የዛሬ ሁለት አመት የሰማችው የናንሲ ማክአሊስተር ድምፅ ብቅ አለ። «ማን ነገረሽ ? » አለች ሜሪ ደግማ በሚያስገድድ ድምፅ ። «ማንም አልነገረኝም ። ገመትኩ ። ግምቱ ለምን እንደመጣብኝም አላውቅም ። ሆኖም ገመትኩ ። ገና ቤን ስለሁኔታሽ መግለፅ ሲጀምር እሷ ናት? የሚል ጥያቄ መጣብኝ ። የነገረን ነገር ሁሉ ስለአንቺ ከማውቀው ጋር ሙሉ በሙሉ ሲመሳሰል ጊዜ ነው መሰል »
«እንዲያ ከሆነ ... » አለችና ዝም አለች፡፡ ማይክልም ያውቃል ማለት ነዋ! ልትል ነበር ። የተረገመ ልብ መቼ ነው ተስፋ እሚቆርጠው! መቼ ነው መጥላት የሚገባውን የሚጠላው ? «አሁንስ ለምን እዚህ ድረስ መጣሽ ? መኖሬን ስታውቂ ጊዜ ፈራሽ? ውል እማፈርስ መሰለሽ ? እና ውሉ ያልፈረሰ መሆኑን ልታስታውሺኝ ፈለግሽ ? »
«አይደለም ። በዚያ በኩል አልጠረጥርሽም ። ቃልሽን ማክበር እንደምትችይ አረጋግጫለሁ» አለች ማሪዮን ፤ እጅግ ያረጀሰው በመሰለ ድክም ባለና ደግነት በተሞላ ድምፅ «ላይሽ ነው የመጣሁ ። ላነጋግርሽ ምን እንደመሰልሽ ፤ ይመችሽ ፤ይክፋሽ ... ላይሽ ነው የመጣሁ። ላያት የመጣኋት ልጅ አንች ነሽ ማለት ከደፈርኩ ። ሌላውን ምክንያት እኔም በቅጡ አላውቀው»
«ለምን ? ይህን ያህል አመት ትዝ ሳልልሽ ቆይቼ ድንገት ምን አዲስ ስሜት ተፈጠረ ?» የሜሪ ድምፅ የሚናደፍ መርዛም ነበር ። ማሪዮን ምንም አልመለሰችም ።

«ድንገት ምን ነገር ተፈጠረ ሚስ ሂልያርድ? ወይስ የግሬግሰንን ሥራ ተመልክቶ ማድነቅ ስላማረሽ ይሆን ? እንዲያ ከሆነ ... እንዴት ነው በአራት መቶ ሺ ዶላር ክፍያ ያሰራሻት አሻንጉሊት እምታምር አትመስልሽም? አራት መቶ ሺ ዶላር ቢወጣም አይቆጭ! የሚያሰኝ ነው?. . . የሚያሰኝ ነው ወይ ? ምነው ጭጭ አልሽ ? ጥያቄየን መልሺልኝ እንጂ… ደስ አለሽ ወይስ ከፋሽ?» ደስ ቢለኝ ኖሮ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር ! አለች ማሪዮን በሀሳቧ ። ድንገት ደስ ቢለኝ የሚል ምኞት አደረባት ። ግን የሰራችው ነገር ውጤት መጥፎ ፤ ያደረገችው ነገር አስቀያሚ እንደሆነ ወለል ብሎ ታያት። ለዚህ ገጽታ ሁሉም ብዙ እንደከፈሉ ግን ያ ሁሉ ከንቱ እንደነበረ ተገነዘበች ። ይህ ፀፀት ነው። ፀፀት ግን ዋጋ የለውም ። ሁሉም ነገር ካለፈ ፤ ምንጩ ከነጠፈ በኋላ ቢፀፀቱት ምን ፋይዳ አለው? ማይክልን አሰበች ። ናንሲን ተመለከተች ። እሷን ራሷንም ። አንዳቸውም እንደነበሩ አይደሉም። ሁሉም ሌላ ሆነዋል ። ማይክልና ናንሲ። ሁሉም ነገር ሩቅ ከሩቅ ፤ የራቀ ሩቅ ሆኗል ። ለነሱም ። አንዳቸው ላንዳቸው ይሆኑ ዘንድ የማይቻል ነው ። ህልማቸውን በግል ሲያባርሩ ፤ ሊያገኙት ከቻሉ ሌላ ቦታ ቢፈልጉት ይሻላል ። «ናንሲ በጣም ቆንጆ ልጅ ሆነሻል ኮ» አለች ማሪዮን ፤ ወንድ አይጠፋም ለማለት ያህል ። «ቆንጆ ስላልሺኝ አመሰግናለሁ ይገባኛል ። ፒተር ውብ የእጅ ሥራ ቀርጾአል ። ግን ይህን ለማድረግ የገባሁበት ውል…. ከሰይጣን ጋር እንደመዋዋል የሚቆጠር ነው ። ቆንጆ ፊት ለማግኘት ሕይወትን መሰዋእት ማቅረብ ። ሌላ ትርጉም የለውም»

«ሰይጣኒቷም እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ» አለች ማሪዮን በሀዘን በተሰበረ ድምፅ «ምንም እንኳ ዛሬ ይህን ላንች መንገር ርኩስ ተግባር እንደሆነ ቢገባኝም ፡ ያኔ ናንሲ ፣ያኔ ቃል እንድ ትገቢልኝ ሳግባባሽ ፤ ሊሆን የሚገባውን ነገር ያደረግኩ መስሎኝ ነበር»
«አሁንስ ? አሁንስ ምን ይመስልሻል ? » አለች ፊት ለፊት በድፍረት እየተፋጠጠቻት «አሁንስ ምን ይሰማሻል ፤ሚስ ሂልያርድ ? ለመሆኑ ማይክል ደስተኛ ነው? እኔን እንደ አሮጌ ዕቃ ወርውረሸ ከጣልሽለት በኋላ ደስ ብሎት መኖር ጀመረ? ተልእኮሽ ሰመረልሽ ? » ስሜት ተናነቃት ። በጥፊ ልታልሳት ፈለገች ። ይህን የወይዛዝርት ልብሷን እንደተጎናፀፈች ገፍትሬ ጥዬ መሬት ለመሬች ብጎትታት ! ስትል ተመኘች ። «የለም የለም አንዱም ነገር አልተሳካልኝም ። ማይክል ደስተኛ አይደለም ። ከጊዜ ጊዜ ሁሉን ነገር ይረሳል ፤ ሀዘኑ ይሽራል በሚል ተስፋ ስጽናና ቆየሁ ። ግን አልሆነም ። አንችም እንዲያ እንደምትሆኝ ተስፋ ነበረኝ ።ግን ሳይሽ ነሽ ሀዘንሽ አልሻረም ምንም ነገር አልተረሳሽም ። ወይስ የተሻለ መንገድ መርጠሻል? ብዬ እጠይቅሽ ነበር ። ሆኖም መብት ያለኝ አይመስለኝም »
«ልክ ነሽ። ያን ጥያቄ ለማቅረብ ምንም መብት የለሽም ማይክል ሚስት አገባ ወይስ ?»
«አግብቷል» አለች ማሪዮን ። ሜሪ ክው ብላ ደነገጠች ። ኡኡ ! ብላ ለመጮህ ፈለገች ። ድምጹን አፍና አስቀረችው ። ያ ድምፅ ከጉሮሮዋ ሳይወጣ ሟሟ። «አዎን ፤ ሜሪ ። አግብቷል ። ሥራውን አግብቶ ትዳር መስርቷል ። የሚበላው የሚጠጣው የሚተኛው እሥራው ላይ ሆኗል። ትንፋሹ ሳይቀር ሥራው ሆኗል ።» ሜሪ ትንፋሽዋ መለስ አለ። «ከሥራው ላይ ንቅንቅ አይልም ። በሥራው ውስጥ ሰምጦ ዘለአለም አለሙን ሊያሳልፍ የፈለገ እስኪመስል ። አብረን እንኖራለን ይባላል እንጂ መልኩን የማየው ከዝንተ አለም አንድ ጊዜ ነው»

የት አባሽ አንች ውሻ !እንኳን ! አለች ሜሪ በሀሳቧ «እንዲያ ካልሽ ፤ ስህተት መስራትሽን ተገንዝበሻል ማለት ነው። ማለት በአለም ላይ ካለው ሀብትና ማንኛውም ድንቅ ነገር አብልጨ እወደው እንደነበር ታውቂያለሽ ? » ይህን ብላ ስታበቃ በኃሳቧ ከዚህ ፊቴ በስተቀር…. ከፊቴ በስተቀር ! አምላኬ ምናልኩህ «በስተቀር» እንድል አደረግከኝ! «አውቃለሁ ። አውቅ ነበር ። ግን ፍቅር ነውና ያልፋል ብዬ ገመትኩ»
«ሆነ ? ግምቱ ትክክል ነበር ? ረሳኝ ? »
«እንጃ ። ምናልባት አልፎለት ይሆናል ። ስምሽን አንስቶ አያውቅም መቼም»
«በመጀመሪያ ወይም መቼም ቢሆን የት እንዳለሁ ለማወቅ ሙከራ አድርጎ ነበር ?» ማሪዮን በአሉታ ራሷን እየነቀነቀች «እልሞከረም» አለች ። ይህን ትበላት እንጂ ለማይክል ናንሲ ሞታለች እንዳለችው አልነገረቻትም ። «ያ ከሆነ ታዲያ ለምን ጠራሽኝ? እኔን የማየት ጉጉትሽ እንዲረካ ? ….. ፎቶግራፎች እንዳሳይሽ?. . . ለምን ?»
«እኔም ለምን እንደፈለግኩሽ አላውቅም ፤ ናንሲ ። ይቅርታ... ሜሪ ። ቅድም እንደነገርኩሽ ነው ። አላውቀውም።... በግድ እዘኑልኝ ማለት ፤ ወይም ሆደባሻነት ይመስላል እንጂ ደኅና አይደለሁም ። መሞቻዬ ሩቅ አይደለም ። እመቃብሬ አፋፍ ላይ የቆምኩ ይመስለኛል»
👍15