አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹ቆይ ግን እስከአሁን ስልኳንም እንኳን ማግኘት አልቻልክም?››

‹‹ምን አገኛለሁ፤አንድ ቀን ሳሪስ አካባቢ ካለ የህዝብ ስልክ ትደውልልኛለች፣ በሌላ ቀን ደግሞ ከካሳንቺስ ይሆናል፣ ሲያሰኛት ደግሞ ከቦሌ ትደውልልኛለች፡፡››

‹‹ግን ለእሷ ያለህ ስሜት ከአድናቆት አልፎ ወደ ፍቅር እንደተመነደገ ነግረሀታል?››

‹‹መቶ ጊዜ ነዋ፡፡››

‹‹እና ምን አለችህ?››

‹‹ብታየኝ ልትጠላኝ ለማፍቀሩ ምን አቅነዘነዘህ ?›› ::

‹አይ ሁሴን! እውነቷን እኮ ነው፡፡ መቼስ አንድ ችግር ሳይኖርባት እራሷን ይሄን ያህል አትደብቅም፤ለዛውም እንዲህ በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያላት ተስፈኛ ደራሲ ሆና...፡፡ እኔም እንደ እሷ የምመክርህ አንድ ነገር ቢኖር እርሳትና የቤት ልጅ ሲያምርህ ኤደንን ፣የቡና ቤት ሲያምርህ ደግሞ ትንግርትህን እየላስክ እንደቀድሞህ ኑሮህን በደስታ ዘና ብለህ ኑር ብዬ ነው፡፡ ሁለቱም ካስጠሉህ ደግሞ መቼም አንተን የማትመኝ የአዲስ አበባ ወጣት የለችም፤ እንኳን ዝና ታክሎበት ቀርቶ እንዲሁም ቁመናና መልክህ የሆሊውድ አክተር አይነት ነው፡፡››

‹‹ኡፍ! ለምን አይገባችሁም፤ እሷን እኮ ነፍሴ ነው ያፈቀራት፡፡በቃ ህልሜ ሆናለች፣ሀይማኖቴ አርጌያታለሁ፣ፈፅሞ ተስፋ አልቆርጥም፣ልረሳትም አልችልም፡፡››

‹‹ቆይ በየጋዜጣው የታተሙላትን ልብወለዶች ሠብስቤ እንድታሳትም አግባባታለሁ ያልከውስ?››

‹‹እባክህ እምቢ አለች፡፡››

‹‹እንዴት .. ? ተው ይህቺ ልጅ መንፈስ ሳትሆን አትቀርም!››

‹‹ይሆናል .. !ማሳተም ከፈለግኩ ግን ሙሉ ውክልና እንደምትልክልኝ ነግራኛለች፡፡››

‹‹ያንተ ያለህ!›› የሠሎሞን መገረም ጨመረ፡፡

‹‹እሺ መፅሐፍ ታተመ እንበል፤የሚገኘው ገቢስ?

‹‹በእኔ ስም ባንክ ቤት እንዳስቀምጠው አሳስባኛለች፡፡››

‹‹በል በል ይሄንን የእብደት ወሬህን አቁምልኝ... ልዝናናበት፤ለራሴ በየውብዳር ጭቅጭቅ አዕምሮዬ ተወጥሮ ነው የመጣሁት፤ሌላ አዕምሮ የሚወጥር ነገር አትጨምርብኝ፤ይልቅ ትንግርትህን ጥራትና ዘና ታርገን፡፡››

ይቀጥላል

ቤተሰቦች #የዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ  ለማድረግ የሚጠይቀው ውስጣዊ ቅንነትን፣ለሰዎች መልካም ማሰብን፣ደግነትን ብቻ ነው።
አሁን #ዩቲዩቡ 128 subscribers አሉት ይሄ ቻናል ከ100,000 በላይ አባላት አሉት ከነዚህ ውስጥ 10 ሰው subscribe ያደርጋል ብዬ እጠብቃለው በጣም ትንሽ ነው ማድረግ ትችላላችሁ በቅድምያ
ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12316😁8
የመጣችለት ሲጠብቃት የነበረችው ትንግርት አልነበረችም.... ኤደን እንጂ፡፡ ወደ ውስጥ ተመልሶ ሶፋው ላይ ተዘረፈጠ፡፡ኤደን ተሽቀርቅራለች፡፡ ከታች ሠማያዊ ጅንስ ሱሪ፣ከላይ በቀይና በጥቁር ቀለም የተዥጎረጎረ ሹራብ ለብሳለች፡፡ ወርቃማ ሉጫ ፀጉሯን ትከሻዋ ላይ ነስንሳዋለች፡፡ በንዴት የመነጨው ላቧ ጠይም ፊቷ ላይ ወዝ ረጭቶ
ተጨማሪ ውበት ለግሷታል፡፡ የለበሰችው ሹራብ ሰውነቷ ላይ ጥብቅ ስላለ ጡቶቿ ወደ ፊት ቀድመው አይን ውስጥ ይመሠጋሉ፡፡ የቁመቷን ማጠር ባደረገችው ባለ ተረከዝ ጫማ አካክሰዋለች፡፡

‹‹ቴሌቪዥን ላይ ለማፍጠጥ ነው አትምጪ ያልከኝ?›› በመውረግረግ ወደ ምትቀመጥበት ቦታ እያመራች የመጀመሪያ ጥያቄዋን ሠነዘረች፡፡

‹‹አይደለም፡፡›› አላት ሪሞቱን ተጠቅሞ ቴሌቪዥኑን እያጠፋ፡፡ አበሳጭታዋለች፡፡ካለ ባህሪዋ እንደ ችኮነቷ የሚያማርረው የለም፡፡ ‹‹ነገሮችን ከራሷ ፍላጎት አንፃር እንጂ ከሌሳ ሠው ፍላጎት አንፃር መዝኖ ማገናዘብ ፍፁም አልፈጠረባትም›› ሲል ሁሌ ይወቅሳታል፡፡››

<<እና?>>>

‹‹ቀጠሮ ስላለብኝ ነው፡፡››

‹‹ቀጠሮ? .... የምን ቀጠሮ? ... ከማን ጋር ?››

‹‹ከትንግርት ጋር፡፡››

‹‹ኧረ! .. ከሸርሙጣዋ ጋር ቀጠሮ!››

‹‹ሁላችንስ ሸርሙጦች አይደለን? እሷ ሸርሙጣ መሆኗን በአዋጅ ያስነገረች የአደባባይ ሸርሙጣ ስትሆን እኔ እና አንቺ ደግሞ ጓሮ ለጓሮ ከሠው ተሸሽገን በሚሥጥ የምንወሰብ ሸርሙጦች ነን፡፡ አሁንም እኮ የመጣሽው እንድንሸረሙጥ ፈልገሽ መሠለኝ >>

ሠውነቷ ተንቀጠቀጠባት፣የጨጓራዋ ቁስለት ሲለበልባት ይሰማታል፡፡ በትንግርት ጉዳይ ብዙ ጊዜ ተጨቃጭቀዋል፡፡ ለቀናቶች በተደጋጋሚ ተኮራርፈውም ያውቃሉ እስከአሁ የተለወጠ ነገር ባይኖርም፡፡ ብዙ ጊዜ እርግፍ አድርጋ ልትተወው ታስብና መሸነፍ ደግሞ ያስጠላታል.... እልህ ትገባለች፡፡‹‹እና ተመልስ እንድሄድልህ ትፈልጋለህ?››

‹‹እንደፈለግሽ፡፡››...

ይቀጥላል


ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ   አደለም ከ 100,000 በላይ አባላት ውስጥ ቢያንስ ይሄን የምታነቡ እንኳን subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅድምያ
ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1128🥰7🤔1
ኤደን በንዴት ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ወደ ክፍሏ በረረች፡፡‹‹እውነቴን ነው... ሁለታችንም ከምናጣው ብንካፈለው ጥሩ ይመስለኛል... ለእኔ ይመቸኛል፡፡ አንቺ ግን ምን አልባት የቤት ልጅ ስለሆንሽ ...›› ንግግሯን ሳትጨርስ ፊትዋን መልሳ ወደ ክፍሏ ዘልቃ አልጋው ላይ ከነልብሷ ተዘረረች፡፡

ሁሴንም ዝግ ባለ እርምጃ ወደ መኝታ ክፍሉ ለብቻው አዘገመ፡፡ መጨረሻ የተዝረከረከውን ክፍል ወግ አስይዞ ማስተካከል እና በራፎቹን መዘጋጋት የፎዚያ ስራ ነበር፡፡...

ይቀጥላል


ድርሰቱ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ  ዩቲዩብ ቻናል እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ አበረታቱን 5 10 ሰው እንኳን ቀለላል አደለም አስቡት ከ 100,000 ሰው ነው 10 5 ሰው Subscribe እንዲያደርግ የምንጠይቀው
አሁንም በቅድምያ
ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1017👏3😱1
‹‹እነዛ እርግብ የመሠሉ ልጆቼ ክንፋቸው ሲሰበር ይታይህ፡፡ እሷ ጋር ቢሆኑ እኔ አጣቸዋለሁ... እነሱም ያጡኛል፡፡እኔ ብወስዳቸው ደግሞ እሷን ያጧታል፡፡ መቼስ ጥሩ ሚስት ባትሆንም ጥሩ እናት መሆኗን መካድ አልችልም፡፡››

‹‹እሺ አብረሃት የምትኖረው ለልጆችህ ሞግዚት እንድትሆንላቸው ብቻ ነው ወይስ ሌላም ምክንያት አለህ?››

‹‹አንድ ተጨማሪ ምክንያት አለኝ፡፡ አሁን ብፈታት ስንት ብር ይዛ እንደምትሄድ ታውቃለህ? ቢያንስ አስራ አምስት ሚሊዮን ብር ይደርሳታል፡፡ ይታይህ አስራአምስት ሚሊዮን ብር ሙሉ ታቅፋ ሄዳ ለማን እንደምታስረክበው ታውቃለህ? ለእንዳንተ አይነቱ አማላይ አለሌ ወንድ! እኔ በየበረሃው ተንከራትቼ ስንት ጉድጓድ ቧጥጬና ድንጋይ ፈንቅዬ ያከማቸሁትን ብር እሷ እዚህ መሀል አዲስ አበባ በአሜሪካ ኮስሞቲክስ እያብረቀረቀች ፤በፈረንሳይ ሽቶ እየታጠበች ስታውደለድል ከርማ እንደቀልድ አስራ አምስት ሚሊዮን ብር!››

ሁሴን ደነቀው ‹‹በእውነት ስግብግብ ነህ፡፡››

‹‹ለምን አልስገበገብ፤ትርኪ ምሪኪ ወሬና አሉባልታ ለቃቅሜ በወረቀት አስፍሬ በመበተን አይደለም እኮ ንብረት ያፈራሁት፡፡››

‹‹አውቃለሁ አውቃለሁ .. ጥቂቱን ሰርተህ አብዛኛውን ደግሞ ከሙሰኞች ጋር በመተባበር ዘርፈህ መሆኑን በሚገባ አውቃለሁ፡፡›› ተረቡን በተረብ መለሠለትና ሌላ ጥያቄ አስከተለ፡፡ ‹‹ትቀናባታለህ አይደል? ለነገሩ የውብዳር ማንም ሊገምጣት የሚጓጓባት ኬክ ነች።

‹‹ኡፍ… ስንት ሸንቃጣዎች በሞሉበት ከተማ እሷ አገር ስታሳስትና ስታስጎመዥ ታየኝ!!!›› የውስጥ ስሜቱንና የዘወትር ድርጊቱን ለመደበቅ የሠነዘረው ቃል ነው እንጂ ሠሎሞን በየውብዳር መቅናቱን ከወዳጅ እስከ ጠላት የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ አለባበሷ ያበሳጨዋል፣ የሚደወልላት የስልክ ብዛት ያበግነዋል፣የምታርከፈክፈው ሽቶ መዓዛ ያጥወለውለዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በነገር ይጎነትላታል፤ እሷም በእጥፍ ትመልስለታለች፡፡ እንዲህ እንዲህ እያሉ ነገሮች ይባባሳሉ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የደባል በሚመስሉ ኑሮ ውስጥ ነው የከረሙት፡፡ ሁለቱም በየፊናቸው ያቅዳሉ፣ያሻቸውን ይከውናሉ፡፡ሁለቱም የየራሳቸው የገቢ ምንጭ ስላላቸው ማንም ማንንም ገንዘብ አይጠይቅም፡፡ መሳሳም አቁመዋል፤ አልጋም ለይተዋል፡፡ ዘመድ አዝማድ በእንግድነት እቤታቸው ሲመጣ ወይም እነሱ ተጋብዘው ሠርግና ግብዣ ቦታ ሲሄዱ ግን ለይምሰል ጎን ለጎን ተጣብቀው በሞተ ፈገግታ እየተያዩ፡፡

‹‹ምትገርም ነህ፡፡››አለው ሁሴን የእውነትም ገርሞት፡፡

‹‹ ካንተ አልብስም..ይልቅ አሁን ተነስ ወደ ቤት እንሂድ፡፡››

<<ለምን>>

‹‹እየነገርኩህ እንድታማልደኝ ነዋ…መቼስ እሷም እንዳንተ ንክ ስለሆነች ትግባባላችሁ ብዬ ነው፡፡››ብሎ ከመቀመጫው ተነስቶ ቢሮውን ለቆ ወጣ..ሁሴንም ተከተለው፡፡ ሁለቱም በየራሳቸው መኪና ውስጥ ገብተው ተከታትለው 22 አካባቢ ወደሚገኘው የሰሎሞን ቤት ጉዞ ጀመሩ …እስጢፋኖስ ጋር እንደደረሱ ግን ሰሎሞን መሪውን ጠመዘዘና የፒያሳን አቅጣጫ ያዘ…ሁሴን መኪናውን ሳያቆም ስልኩን አነሳና ደወለለት ‹‹ምነው.. ሀሳብህን ቀየርክ እንዴ?››

‹‹አይ ድንገተኛ ጉዳይ አጋጥሞኝ ነው፤ መዘጋጃ አንድ ፕሮጀክት ክፍያ ነበረኝ... አሁን ደርሶል ብለው ደውለውልኝ ነው፡፡››

‹‹ታዲያ ሌላ ጊዜ አይደርስም እንዴ?››

‹‹አይ አይደርስም ..ገንዘቤ መንግስት ጋር ብዙ ሲቆይ ይጨንቀኛል.. አንተ ወደ ቤት ሂድና ጨርስልኝ .. ባይሆን ማታ የተለመደው ቦታ እንገናኝ….፡፡››

‹‹እሺ..ግን ከክፍያው ላይ በደንብ ዘገን አድርገህ ይዘህ ና፡፡››

‹‹እንዳልክ አደርጋለሁ፡፡ ››ሁለቱም ጉዞቸውን በየፊናቸው ቀጠሉ፡፡

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰብ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍79🥰114🔥1👏1
#ትንግርት


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በዓይናችን ዓይተን ከወደድነው ነገር ይልቅ በምናባችን ቀርፀን ደጋግመን የተመኘነው ነገር ወደ ጣኦትንት የመቀየር ዕድሉ ሰፊ ነው፡

የውብዳር ለብ ባለ ውሃ ሠውነቷን ተለቃልቃና ፎጣ አገልድማ ፓንቷን በእጇ ይዛ ከባኞ ቤት በመውጣት ወደ መኝታ ቤቷ ልትገባ በእርምጃ ላይ ሳለች ሁሴን የሳሎኑን በር ከፍቶ ገባ፡፡

‹‹እኔ አላምንም፡፡ ቤቱን ማን አሳየህ?›› ወደ እሱ እየተራመደች ነበር የምትናገረው፡፡

ጉንጭ ለጉንጭ ከተሳሳሙ በኋላ ግማሽ እርምጃ ራቅ በማለት አስተዋላት፡፡ ድንቡሽቡሽ ያለች የምትበላ ብስል ቀይ ወይዘሮ ነች፡፡ ያገለደመችው ሮዝ ቀለም ያለው ፎጣ ከወገቧ እስከ ጉልበቷ ሸፍኗታል፡፡ ሌላው አካሏ እንደተጋለጠ ነው፡፡ ጡቶቿ አሁንም እንደልጃገረድነቷ እንዳጎጠጎጡ ናቸው፡፡ የቆዳዋ ጥራትም አስደምሟታል፡፡

‹‹ምን ያፈዝሀል? ቁጭ በል እንጂ›› አለችው፡፡ በእሷ ውበት መደመሙን ስታስብ ውስጧን የንዝረት ስሜት ተሰማት፡፡

‹‹ለምን አልፈዝ፡፡ ጓደኛዬ ለካ ይሄንን ሠውነት እንደ አሞሌ ጨው ሲልስ እያደረ ነው እንዲህ

‹‹ኡ . ኡ . ቴ <ቅጡም የምንኩስና ነው› አለች አክስቴ.... ለማንኛውም ልብሴን ለብሼ ልምጣ.... የሚጠጣ ከፈለክ ፍሪጁን ከፈት አድርግ፡፡›› በማለት እየተውረገረገች ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡

ሁሴን ፍሪጁን ከፍቶ ቢራ አወጣና እየተጎነጨ ማሠብ ጀመረ፡፡ ስለ ሰሎሞን ነበር የሚያስበው፡፡ በመጀመሪያ የውብዳርን ያፈቀራት ጊዜ ጨርቁን መጣል ነበር የቀረው፡፡ እሷን ማግባት ካልቻለ በህይወት መኖር
እንደማይችል ደጋግሞ ሲምል ነበር፡፡ በወቅቱ ደግሞ የእሷ ቤተሠቦች ፍቃደኞች አልነበሩም፡፡ ይሁን እንጂ የእሱ ፍቅር ብርታትና መስዋዕትነት የመክፈል ፅናቱ እሷንም ሙሉ በሙሉ በፍቅሩ እንድትጠመድና ከቤተሠቦቿ ፍቃድ ውጭ አሻፈረኝ ብላ እቤቱ እንድትገባ አስገደዳት፡፡ እናም ትዳራቸው በእንደዛ አይነት ሁኔታ በጽኑ ቁርጠኝነትና በከፍተኛ ደስታ ተጀመረ፡፡ ንብረት መጣ፣ልጆች ተወለዱ፣ሁሉ ነገር የሰመረ መሰለ፡፡ዳሩ ግን ውሎ አድሮ አካል ሲቀራረብ ፍቅር ቀስ በቀስ ከመሀከል ሾልካ ተነነች፤አንዳቸው ለአንዳቸው የወዳጅ ጠላት ሆኑ፡፡

‹‹እሺ አቶ ሁሴን... ደህና ነህ?›› እስከተረከዟ የሚደርስ ረጅም አብረቅራቂ ጥቁር ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ዊግ የተቀላቀለበት ሹሩባዋ ያምራል፡፡ የሁለት ጡቶቿ አካፋይ የስምጥ ሸለቆ ስንጥቅ መስሎ በከፊል ይታያል፡፡ የተቀባችው ሽቶ የሳሎኑን አየር በሠከንድ ነበር የቀየረው፡፡

‹‹አለሁልሽ... ከውዱ ባለቤትሽ ጋር ነበር የመጣነው ግን ከበራፍ ተመለሰ፡፡››

‹‹ምነው ውሽማው ጠራችው እንዴ?›. ግዴለሽ በሆነ አሽሞጣጭ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ! ውሽማው ጋር ነው የሄደው፤ወይዘሪት ገንዘብ ጋር ።

‹‹እነ ዕፀ-ህይወት ትምህርት ቤት ናቸው እንዴ? ... የጫወታውን አቅጣጫ ወደ መጣበት ጉዳይ እንዲያመራላት ነበር ጥያቄውን የሠነዘረው፡፡››

<<አዋ>>

‹‹ልደታቸው ደረሠ አሉ፡፡ ለምን ዝግጅቱ በእናንተ ወጪ እኔ ቤት አይሆንም? በዛውም እኔ አገባበታለሁ፡፡ ‹ብልጥ ዝንጀሮ በሞኝ ክምር ያገባል› አይደል የሚባለው፡፡›› ፈገግ አለች... ስለመጨቃጨቃቸው እንደሰማ እርግጠኛ ሆነች‹‹ሀሳብህ ጥሩ ነው፤ ቢያንስ ከጓደኛህ ይሻላል፡፡››

‹‹የእሱ ሀሳብ እንዴት ነው?››

‹‹እንደነገረህ ነዋ ..! ሆቴል ይዘጋጅ ነው የሚለው፡፡ አሁን አሁን ምን እያሠብኩ እንደመጣሁ ታውቃለህ፤ ለእሱ ስል ይሄንን ሳሎን ወደ ሆቴልነት በመቀየር በመጠጥ ሞልቼ ለእሱ እንዲመች ማድረግ… ፡፡››

‹‹እንግዲያው ከጓሮ ያሉትን ሰርቪስ ክፍሎችም ወደቤርጎ ቀይሪልን፤ እኔም አንዳንዴ ሴቶችን ሸጎጥ አድርጌ መጣና አረፍ እልበታለሁ።

‹‹ምን አንተስ የእሱ ጓደኛ አይደለህ፡፡››

‹‹ከእሱ በፊት እኮ የአንቺ ጓደኛ ነበርኩ…ኧረ እንደውም የዕቃ ዕቃ ባልሽ አልነበርኩ እንዴ?››

ፊቷ ቀላ፡፡ የውብዳር ሁል ጊዜ ስለ እሷ እና ስለ ሁሴን የልጅነት ታሪክ ስታስብ የሠውነቷ ሙቀት ይጨምራል፡፡ በተቀራራቢ ጊዜ አንድ ሠፈር ውስጥ ከማደጋቸው አንፃር ጣፋጭ የሆነ የልጅነት፤ ከዛም ዘሎ እስከ አሁን የዘለቀ የጓደኝነት ቁርኝት በመሀከላቸው አለ፡፡ ከሠሎሞን ጋር እንዲገናኙ መሠላል የሆናቸውም እሱ ነበር፡፡

ካለፈ ትውስታቸው እንደመባነን አለችና ‹‹አዋ እሱማ ለእኔም ጓደኛዬ ነህ፡፡ካንተ ጓደኝነት ያተረፍኳቸው ሦስት ትላልቅ ነገሮች ምን እንደሆኑ ታውቃለህ? ምርጥ ተወዳጅ ልጆች፣ብዙ ብር እና የምሁር ደደብ የሆነ ባል ናቸው፡፡ እና ላማርርህም ሆነ ላመሠግንህ ግራ ይገባኛል፡፡ ባይገርምህ ወደ ኃላ ተመልሼ ሳስብ የዛን ጊዜ ከእሱ ይልቅ አንተን ለምን እንዳልጠበስኩህ ድንቅ ይለኛል፡፡ እንደ ቤተሰብ ሆነን አብረን ማደጋችን እንደወንድምና እህት እንድንተያይ ተፅዕኖ ያሳደረብኝ ይመስለኛል፡፡ ግን እንደ አሁኑ በሳል
ሆኜ ቢሆን ኖሮ መቶ ጊዜ ደጋግሜ አንተን ነበር የምጠብሰው

‹‹ድሮም ሆነ አሁን ዱርዬ እንደሆንኩ እኮ ደጋግመሽ ነገርሽኝ ነበር››፡›› ሁሴን የድንጋጤ ንግግር ነበር የተናገረው፡፡ የውብዳር ስለ እሱ እንደዚህ አይነት ስሜት እንደሚሰማት ገምቶ አያውቅም፡፡

‹‹ዱርዬማ ዱርዬ ነህ፡፡ ግን ንፁህ ዱርዬ ነህ፡፡ አፍቃሪም ነህ፡፡ ከተረጋጋ ማህበራዊ ሕይወት ይልቅ በማዕበል የሚናወጽ ግን በደስታ የተጥለቀለቀ ሕይወት ይበልጥ ዋጋ አለው፡፡ ደስታ በሕይወት ለመኖር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው የምትረዳው ባጣኸው ጊዜ ነው፡፡ ፍቅር አልባ ሕይወት እኮ በቃ..… ንብ አልባ ባዶ ቀፎ ማለት ነው፤ንብ የሌለበት ባዶ ቀፎ ደግሞ ማር ሊመረትበት አይችልም፡፡ ብር ምን እንደሚያደርግልህ ታውቃለህ፡፡ ቁሳዊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያስገኝልሀል፡፡ ውጫዊ ችግሮችህን ሁሉ በቀላሉ ታስወግዳለህ፡፡ ሀብታም ሆነህ ሳለ የፍቅር ካዝናህ ባዶ ከሆነ ግን ..በቃ ቀንና ሌት ስለ እሱ ብቻ ታስባለህ፡፡ ሌሎች ፍላጎቶችህ ሁሉ ስለተሟሉ ሌላ የምትጨነቅበት ጉዳይ አይኖርማ፡፡ ስለዚህ ይበልጥ በፍቅር እጦትህ እንድትሠቃይ ትሆናለህ፡፡››

‹‹ቆይ ይሄንን ያህል እስክትማረሩ ድረስ ምን
ትሠራላችሁ፡፡ ለምን አትነጋገሩም?፡፡ የተከሰቱ
ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት ጥረት ለምን
አታደርጉም ? ፍቅር እኮ ዘላለማዊ ነገር አይደለም፡፡ ይወለዳል .. ያድጋል .. ይሞታል፡፡በልጅነቱ .. በወጣትነቱ አልያም አርጅቶ ሊሞት ይችላል፡፡ የዕድሜውን ርዝመት የሚወስነው ግን ሁለቱ ፍቅረኛሞች ስለፍቅር ባላቸው ግንዛቤና ለፍቅራቸው በሚያደርጉለት
እንክብካቤ መጠን ነው፡፡ እናንተም አያያዙን
ያወቃችሁበት አይመስለኝም፡፡ ሲጋቡ
አይታችሁ ተጣድፋችሁ ተጋባችሁ፤ ይሄው
ጀርባ ለመሠጣጣትም ብዙ አልዘገያችሁም፡፡ለማንኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ ሌላ ጊዜ በእርጋታ ቁጭ ብለን በሠፊው እንነጋገርበታን፡፡

አሁን ወደ መጣሁበት ጉዳይ እንመለስ
መግባባት ስላቃታችሁ የልጆቹ የልደት ዝግጅት ጉዳይ….፡፡››

‹‹እንዳልክ እሺ፡፡መቼስ አንተ ጠይቀኸኝ ምንም ነገር እምቢ ማለት እንደማልችል ስለሚያውቅ ነው የላከህ፡፡ ከዛ በፊት ግን ስለራበኝ የሚበላ ነገር እንድታመጣ ሠራተኛዋን ልዘዛት›› በማለት ወደ ማብሠያ ክፍል አመራች፡፡

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍13114👏5🔥3🎉2🤔1😢1
ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ ሱስ አስያዥ የተባሉትን ነገሮችን ሁሉ በየተራ ሞክሬያቸዋለሁ፡፡
ጫት፣ሲጋራ፣ሺሻ፣ሐሺሽ፣ መጠጥ በየዓይነቱ
ወዘተ…እየደጋገምኩ ወስጄያቸዋለሁ ፤ ጣዕማቸውንም እስኪበቃኝ
አጣጥሜያቸዋለሁ፡፡
ተፈቅሬያለሁ፣ተጠልቼያለሁ፣የተደበደብኩባቸው ቀናቶችም አሉ፣ታስሬም አውቃለሁ፣አንድ ሁለቴም በቡድን የመደፈር ሙከራ ተደርጎብኛል፡፡

በቃ በአጠቃላይ አንድ የቡና ቤት ሴት የሚያጋጥማት ችግርና ደስታ አጋጥሞኛል፡፡

የእኔን ለየት የሚያደርገው ግን እንደሌላው ተቸግሬ፣ ምርጫ አጥቼ ወይንም ስለ ሕይወቱ ያለኝ ግንዛቤ አናሳ ሆኖ አልነበረም ፡፡በሙሉ ፍላጎቴ አውቄ.. ሕይወቱ ምን እንደሚመስል ለመፈተሸ፣ስሜቱ እንዲሰማኝ፣ህመሙ እንዲያመኝ፣ቁስሉም እንዲቆጠቁጠኝ፣በአጠቃላይ ህይወቴን ለማጨማለቅ ስለፈለኩ የገባሁበት ኑሮ ነው፡፡

እናም በሦስት ዓመታት ሂደት ውስጥ ከጠበቅኩት በላይ ሸርሙጪያለሁ፡፡ ከጠቅበኩት በላይ እያንዳንዱን የቡና ቤት የሕይወት ፈርጅ ፈትሼ ቀምሼ አጣጥሜ ስለጠገብኩ.. እነሆ በዛሬዋ ቀን ይህንን ምዕራፍ ዘግቼ ወደ ሌላ የህይወት ገፅ ለመሸጋገር ወስኜ የመዝጊያውን ክብረ በዓል በማክበር ላይ እገኛለሁ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ከቃረምኳቸውና ካካበትኳቸው ታላላቅ የሕይወት ልምዶች በተጨማሪ እናንተን የመሠሉ በህይወቴ ትልቅ ቦታ የምሠጣቸው ወዳጆች ያገኘሁበት ቦታ ስለሆነ በገጠሙኝ ነገሮች ሁሉ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በነገራችን ላይ ከሽርሙጥና ስራዬ በሚተርፈኝ ጥቂት ጊዜ በመጠቀም ጫር ጫር ያደረኳቸው የተወሰኑ ስዕሎች አሉኝ፡፡ እና እናንተ የተከበራችሁ እንግዶቼ እግረመንገዳችሁን ብትጎበኙልኝ ደስተኛ እሆናለሁ፡፡›› ከእነሱ አስተያየት ሳትቀበል አፋቸውን በአድናቆት ከፍተው እያዳመጧት ሳለ ከተቀመጠችበት ተነስታ እንዲከተሏት ከጠየቀች በኋላ ከተዘጉት ሁለት ክፍሎች አንዱን ከፍታ ወደ ውስጥ ዘለቀች፡፡ ሌሎችም በየተራ ተከተሏት፡፡

ማንም ከአንደበቱ ድምጽ ማውጣት የቻለ የለም፡፡ መጠነኛ ስፋት ያለው ክፍል ግድግዳው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በተለያዩ የሸራና የቆዳ ላይ ስዕሎች ተሞልቷል፡፡

ከሁሉም በተለየ ሁኔታ... ሁሴን ጋዜጠኛ እንደመሆኑ መጠን በሕይወቱ ብዙ አስገራሚና አስደማሚ ክስተቶች አጋጥሞት ያውቃል፡፡ የዛሬው ግን የተለየ ነው የሆነበት፡፡ እንዴት ብሎ ስጋዋን ስትቸረችር የሚያውቃት አንዲት ሴት እንዲህ ድንቅ ሠዓሊ ትሆናለች ብሎ ሊገምት ይችላል?በፍፅም እንግዳ ነገር ነው የሆነበት፡፡ሁሉም በተመስጦ ድባብ ውስጥ ሠምጠው እያንዳንዱን ስዕል እየተዟዟሩ የሚገባቸውንም የማይገባቸውንም እየተመለከቱ ነው፡፡ትንግርትም የእያንዳንዱን የስሜት ለውጥ... የእጅ እንቅስቃሴያቸውን፤ የፊታቸውን መቋጠርና መፍታታት በፀጥታ እያስተዋለች ምን እየተሰማቸው እንደሆነ የራሷን ግምት ትገምታለች፡

ሁሴን ካስደመሙት ስዕሎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ‹‹ማነው ሸርሙጣ?›› የሚል ርዕስ የሰጠችው ነው፡፡ስዕሉ እንዲህ ይነበባል አንዲት እራፊ ጨርቅ በሠውነቷ አጋማሽ አካባቢ ጣል ያደረገች ለግላጋ ወጣት ሽበት የወረረው ሽማግሌ ጭን ላይ ተቀምጣለች፡፡ የቀኝ እጇን በትከሻው አዙራ ሽማግሌው ደረት ኪስ ውስጥ በመግባት ብር ስትመዝ በግራ እጇ ደግሞ በረሀብ የተጣበቀ የሚመስለው ሆዷን ጨምድዳ ጨብጣለች፡፡ ሽማግሌው ደግሞ በአንድ እጁ ቢራ ጨብጦ በሌላው
እጁ የጉብሊቷን ጭን ያሻሻል፡፡ ከሽማግሌው ፊት ያደፈ ልብስ ለብሳ እራፊ ነጠላ እላይዋ ላይ የጣለች ሴት በንዴት ፀጉሯን አንጨፍርራ ወደ ሰውዬው እየተንደረደረች ስትመጣበት ይታያል.... ከሴትዬዋ ኋላ አራት የደረሱ ሴቶችና ሦስት ወንድ ልጆች አጅበዋታል፡፡ ከሴቶቹ መሀከል ሁለቱ ህፃን ልጆች ታቅፈዋል፡፡ በአትኩሮትና በፅሞና ተመለከተው፡፡ ትርጉሙ ከአንድ ሙሉ መፅሐፍ በላይ ገዘፈበት፡፡ ሌሎች ስዕሎቿንም በየተራ ቃኛቸው፡፡ ‹አፍቃሪዋ ሸርሙጣ› ‹የፈረሰው መንደር› ‹መብረቅ› ‹ትኩሳት› ከስዕሎቹ መሀል የተወሰኑ ናቸው፡፡

ሁለቱ ሴቶች ለስዕል ያላቸው ግንዛቤ የተወሰነ ቢሆንም መደመማቸው ግን አልቀረም ነበር፡፡ በውስጣቸውም የተወሰነ መረበሽ ተፈጥሮባቸዋል፡፡የገዛ ሕይወታቸውን መለስ ብለው እንዲገመግሙ ተገደዋል፡፡‹‹እኛስ የተለየ ምን ነገር አለን…? ተናገሩ ቢሉን የምንናገረው .. አሳዩን ብንባል የምናስጎበኘው፡፡›› ብለው እንዲጠይቁ የትንግርት ስራ አስገድዷቸዋል፡፡

ከሠዓታት ተመስጦ በኋላ ሠሎሞን መናገር ጀመረ፡፡ ‹‹በፊትም ተዓምረኛ መሆንሽን ቀልቤ ይነግረኝ ነበር፡፡አሁን አረጋገጥኩ..በይ አሁን አስተያየቴን ልስጥሽ ተቀበይ….፡፡››

‹‹አይቻልም...በቃል መስማት አልፈልግም፡፡ ማስታወሻ ደብተሬ ላይ የተሰማችሁን በየተራ በፅሁፍ ታሰፍሩልኛላችሁ... ብቻዬን ሆኜ በተመስጦ ደጋግሜ እያነበብኩ ማጣጣም ፈልጋለሁ፡፡››
እንግዶቿን ከሸኘች በኋላ የተዝረከረከ ሳሎኗን አስተካክላ ማስታወሻ ደብተሯን ይዛ ተዘግቶ ወደዋለው መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡ ባለ ሜትር ከሃያ ሞዝቦልድ አልጋ ከወደ አንዱ ጥግ መስኮቱን ታኮ ተዘርግቷል፡፡ ሌላውን ግድግዳ ተደግፎ ትልቅ የመፅሀፍ መደርደሪያ ይታያል፡፡ መደርደሪያው አምስት ዘርፎች አሉት፡፡

የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ረድፍ አናት ላይ
ልብ-ወለድ የሚል ሀመግለጫ ተለጥፎበታል፡፡ ሦስተኛው ረድፍ ላይ ሥነ ግጥም ይላል፡፡ አራተኛው ረድፍ ሳይኮሎጂ እና ፍልስፍና ሲሆን የመጨረሻው ረድፍ ደግሞ ልዩ ልዩ የሚል ፅሁፍ ተለጥፎበታል፡፡ ከአልጋው ፊት ለፊት ባለ ባዶ ቦታ ላይ በሚገኝ አንድ ጠረጴዛ ላይ ላፕቶፕ ይታያል፡፡ የመኝታ ቤቷን በራፍ ዘግታ ተንደርድራ አልጋዋ ላይ ተፈናጠጠች፡፡ ድክምክም ቢላትም ውስጧ በልዩ ደስታ ተጥለቅልቋል፡፡ የተሰጧትን አስተያየቶች ለማንበብ ያላት ጉጉት ትንፋሽ ሊያሳጣት ትንሽ ነው የቀራት፡፡ ለማንበብ ተዘጋጀች.. ለመጀመር የፈለገችው ከሴቶቹ ነው፡፡

አንደኛዋ ሴት ...

‹‹እምትገርሚ ነሽ፡፡ እንደምታውቂው አንድ ዓመት ሙሉ አንድ ቤት አብረን ሠርተናል፡፡ ምርጥ ጓደኛሞችም የነበርን ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን ምን ያህል ደደብ ኖሬያለሁ፡፡ በእውነት በራሴ አፍሬያለሁ፡፡ እኔ እኮ ስለራሴ አንድም ሚስጥር ሳልሸሽግ ነበር ዘርግፌ የምነግርሽ፡፡.....

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች 200 አስገቡት

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8917👏6
#ከእዳ_ወደ_የምን_እዳ?

#በእውቀቱ_ስዩም

ጋሻው አዳል የተባለ የምወደው የቆየ ዘፋኝ እንዲህ የምትል ዝነኛ ዘፈን አለችው፥

“ማለዳ ማለዳ
ማለዳ መጥተሽ
አይ ! እህህ
ማለዳ መጥተሽ
እኔን ሳታገኝ ትመለሻለሽ"

ዘፈኑን በሰማሁ ቁጥር ጋሻውን እንዲህ እለዋለሁ”  አባ!  በማለዳ የት ሄደህ ነው የማታገኝህ? ውስጥህ የበቀለውን  ችግኝ ስታጠጣ አምሽተህ በዛው መንገድ ላይ የመሰረት ድንጋይ ተንተርሰህ አድረህ ነው?”

   ሳስበው፥ ጋሻው ይህንን ዘፈን የዘፈነው  ለፍቅረኛው ሳይሆን  ለአበዳሪው ይመስለኛል፤ ብድር ስር ምን ትዝ አለኝ !ኢትዮጵያ ብድር መመለስ ከተሳናቸው አገሮች አንዷ ሆና እንደተመደበች  ሰማችሁ አይደል? እምደንቅ እኮ ነው!

ባለፈው ያሜሪካው ያውሮፓ አበዳሪዎች ከኢትዮጵያ ግምጃ ቤት ሀላፊ ጋር ተገናኝተው በጠረጴዛ ዙርያ እና በጠረጴዛ ስር ተወያይተው ነበር;

በቦታው ተገኝቼ እንደታዘብኩት ውይይቱ ይህንን ይመስላል፥

ያሜሪካው - እዳችንን መች ነው ምትከፍሉን?

የኢትዮጵያው- የምን እዳ?🤔

ያውሮፓው- በቢሊዮን  ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንዳበደርናችሁ ረሳችሁት እንዴ?

የኢትዮጵያው - ስራ ስለሚበዛ እንረሳለን!

የአሜሪካው - እስቲ መፎጋገሩን ትተን በግልጽ እናውራ፤  በኢኮኖሚ ደረጃ  የት ላይ ነው የምትገኙት?

የኢትዮጵያው፤- ማለት?

የአውሮፓው ፤-  እርሙን የበላ ድሀ ናችሁ ? ወይስ ቀን የሚወጣለት ድሀ ናችሁ?

የኢትዮጵያው - የሰው ሀብት አለን ! መቶ አምሳ ሚሊዮን ደርሰናል ! ጠባይ ካላችሁ  አምሳ ሚሊዮኑን  ህዝብ ልንለግሳችሁ እንችላለን !

የአሜሪካው - እያወራን ያለነው ስለገንዘብ ነው !

የኢትዮጵያው - እንዳታባክኑት እኛው ጋ ይቀመጥላችሁ ብለን ነው እንጂ ገንዘቡም ቢሆን አለ!

የአውሮፓው- ሌላው ቢቀር ወለዱን  ክፈሉን

የኢትዮጵያው-   ለጊዜው አይርወለድ እንጂ ወለድ አላዘጋጅንም!
 
የአሜሪካው-- ሌላ ምን መፍትሄ ይኖራል?

የኢትዮጵያው-- ጥቂት የእፎይታ ጊዜ ስጡን!

ያውሮፓው --ምን ያህል ጊዜ?

የኢትዮጵያው- ትንሽ አምሳ አመት ብትታገሱን

ያውሮፓው- በአምሳ አመት ጊዜ ውስጥ ብድሩን የምትከፍሉበት የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ትደርሳላችሁ?

የኢትዮጵያው--አይ እናንተ ብድሩን የማትፈልጉበት ደረጃ ትደርሳላችሁ’

የአሜሪካው -- ከዛሬ ጀምሮ ከዛምቢያ እና ከጋና ቀጥሎ መበደር ከማይችሉ አገሮች ጎን ተመድባችሁዋል!

የኢትዮጵያው-  ይህንን ጨካኝ  ርምጃ ዝም ብለን አናየውም 🙁🙁

የአውሮፓው- ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ?

የኢትዮጵያው---ብድር የተነፈጉ አገሮች ማህበር መስርተን እንታገላለን  !

የአሜሪካው- እናያለን !

እዚህ ላይ፥ የኢትዮጵያው በንዴት ተሰናብቶ ከሄደ በሁዋላ እንደገና ተመልሶ መጣና ፥
“አንድ የመጨረሻ  ጥያቄ ነበረኝ ! “ አለ፤

ሁለቱ ሀያላን - ምንድነው?

የኢትዮጵያው፤-

“ዛምቢያን አስይዘን መበደር አንችልም?”



ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍44😁3311👎2🥰1👏1
ከዚህ በላይ ሊያናግረኝ
አልፈቀደም፡፡ ለሻዩ ወደ ኩሽና መንገድ ጀመርኩና መለስ ብዬ ዐየሁት

“ኤሊ...”

“እ...?” (ከልቡ ሳይሆን)

“ልቤን ለሴት ከምሰጥ፤ ለድመት ብሰጥ ይሻለኛል ነው ያልከኝ አይደል..?”

“እ...አዎ...”

የኩሽና መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ ሻይ ጀበናውን በውሃ ሞልቼ ምድጃው
ላይ ጣድኩ፡፡ ጦስኙን አዘጋጀሁ፡፡

ኤልዬ... የምወደው ልጅ እንዲወደኝ....

የእሱን ልብ እንዳገኝ ሰውነቱ ቀርቶብኝ፤ ምነው ለአንዲት ቀን ድመት ቢያደርገኝ?
የማፈቅረው ልጅ መልሶ እንዲያፈቅረኝ፤ ምነው ለአንድ ሌት

ሚያው ባስባለኝ?

ሚያው....

ሚያው....

            💫አለቀ💫

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍4712👎8😢5😁3
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍17👏21
እንደተገተረች አፍጥጣ አየችው፡፡ ምን መወሠን እንዳለባትም ግራ ገብቷታል፡፡ የማታውቀውን ሠው ተከትላ መሄድ ጨነቃት፡፡ እምቢ ብላም ከጨለማው ጋር መፋጠጥም ይበልጥ አስጨናቂ ሆነባት፡፡

ሁሴን ፍራቻዋ ስለገባው ስለ ራሱ ያብራራላት ጀመር፡፡ ‹‹እኔ ሁሴን ሙሀመድ እባላለሁ፡፡ የፍኖተ ጥበብ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነኝ፡፡

ጋዜጣውን ታውቂዋለሽ ብዬ እገምታለሁ፡፡››በማለት መታወቂያውን አውጥቶ ዘረጋላት፡፡ አልተቀበለችውም.. አላየችውምም፡፡

‹‹አውቅኩህ፤ማለት በአጋጣሚ ጋዜጣው እጄ ሲገባ አንዳንዴም ከጓደኞቼ በመዋስ የማንበብ ዕድል ገጥሞኛል፡፡ በጣም የምወደው ጋዜጣ ነው፡፡ አሁን ጋዜጣው ላይ ያየሁት ፎቶም ትዝ አለኝ›› በማለት ጎንበስ ብላ ደብተሯንና መፅሀፍቿን አስተካክላ በቀኝ እጇ ይዛ በግራ እጇ ሻንጣዋን ልታነሳ ስትሞክር እሱ ቀደሟት አነሳውና ወደ መኪናው ጉዞ ጀመረ... ከኋላው ተከተለችው፡፡

ቀጥታ ወደ ቤት ከመሄዳቸው በፊት ወደ ሬስቶራንት ጎራ ብለው እራት በሉ፡፡ ስለተለያዩ ነገሮች እያወራት ትንሽ ዘና እንድትል ካደረጋት በኋላ ወደ ቤት ይዟት ገባ፡፡

ሳሎን አረፍ ብለው ትንሽ ካወሩ በኋላ …‹‹ለመሆኑ ስምሽ ማን ይባላል?›› ሲል ጠየቃት፡፡

ፎዚያ

‹‹እሺ ፎዝያ..ደክሞሻል መሠለኝ፤ እዛ ጥግ የሚታይሽ ክፍል ገብተሸ ተኚ፡፡ ምንም ነገር አትፍሪ፡፡ እንደቤትሽ ቁጠሪው፡፡ ዘና በይ፡፡ የእኔ ክፍል ይሄኛው ነው፡፡ የምትፈልጊው ነገር ካለ አንኳክተሸ ልትጠይቂኝ ትችያለሽ፡፡ ሽንት ቤት ወይም ሻወር ከፈለግሽ ከክፍልሽ ፊት ለፊት ያለው ክፍል ነው፡፡ ምን እንዳጋጠመሽ ጥዋት በዝርዝር ትነግሪኛለሽ›› አላት፡፡እሷ ግን ይሄንን የታመቀ ብሦቷን ለሊቱን ሙሉ አፍና መቆየት አልፈለገችም፡፡ መተንፈስ፤ማውራት ፈልጋለች፡፡ እንኳን እንዲህ ችግሯን ሊረዳላት የሚችል ሠው አግኝታ ይቅርና እንሠማሻለን ካሏት ለግኡዞቹ ለጨረቃና ለከዋክብቶችም ብታወራላቸው ደስታዋ ነው፡፡

‹‹እኔ እንኳን አልደከመኝም፡፡ ከፈለክ አሁን ልነግርህ እችላለሁ፡፡ >> አለችው፡፡

‹‹እንደዛ ከሆነ ቀጥይ እኔም እንዳላጨናንቅሽ ብዬ ነው እንጂ ችግርሽን አሁኑኑ ብሠማ ደስ ይለኛል፡፡››

ማውራት ጀመረች ‹‹እናትና አባቴ ከአምስት አመት በፊት ነው በሚጓዙበት መኪና ላይ
በደረሠ የመገልበጥ አደጋ በአንድ ላይ የሞቱት፡፡ በወቅቱ የእናቴ ታናሽ እህት
የሆነችው ይህቺ አክስቴ እኛ ጋር ነበር የምትኖረው፡፡ ከእሷ በስተቀር ሌላ የሥጋ
ዘመድ አላውቅም፡፡ ስለዚህ ከእሷው ጋር አብሬ መኖር ቀጠልኩ፡፡ ወላጆቼ ከተወሠነ ቁሳቁስ እና ጥቂት ብሮች በስተቀር የረባ ነገር ጥለውልኝ አላለፉም፡፡ የምንኖርበትም ቤት እንኳን ሳይቀር የኪራይ ነበር፡፡ያው ያለንበትን ችግር ለመቋቋም ይመስለኛል ብዙም ሳይቆይ አክስቴ በዕድሜ በጣም የሚበልጣትን አንድ
አስተማሪ አገባች፡፡ይሄ አስተማሪ ይጠጣል፣ ያጨሳል፣ይረብሻል፣ ይደባደባል፡፡በቃ ፀባዩ መላ ቅጥ የሌለው ነው፡፡

ከቆይታ በኋላ ግን የእሱ ብቻ ሳይሆን የእሷም ፀባይ እየተበላሸ መጣ፡፡ በተለይ ልጆች ከተወለዱ በኋላ በጣም ትጨክንብኝ ጀመር...


ስቃዬ በዛ፡፡ ትምህርት ቤት ከምሄድበት ቀን ይልቅ የማልሄድበት ይበልጥ ጀመር፡፡ የልጆቹን ልብስ አጥባለሁ፣ለቤተሰብ ምግብ አበስላለሁ፣ቤት አፀዳለሁ፤ የማልሠራው ስራ የለም፡፡ እንዲያም ሆኖ ሠላም የለኝም፡፡
ከስድስት ወር ወዲህ ደግሞ ነገሮች በጣም እየከፉብኝ መጡ፡፡ የአክስቴ ባል አዲስ ፀባይ አመጣ፤ የአክስቴን ወጣ ማለት እየጠበቀ መቀመጫዬን ይመታኛል፣ጡቴን ሳላስበው ጨምቆ ያስለቅሰኛል ፤ ፀያፍ ቃላቶች ይናገረኝ ጀመር፣በቃ ጣሬን አበዛው፡፡ ምን ልሁን ለአክስቴ እንዳልነግራት ምን ብዬ፡፡
በኋላ እያደፈጠ ሊደፍረኝ መሞከር ጀመረ፡፡ ሁለት ሦስት ቀን በመከራ አመለጥኩት፡፡ የዛሬውም ችግር መነሻው ይሄው ነበር፡፡ አስራ አንድ ሠዓት ከትምህርት ቤት ሲመጣ ቤት ያለሁት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ አክስቴ ትንሿን ልጅ አዝላ ጎረቤት ለቅሶ ሄዳለች፡፡ ትልቁ ልጅ ደግሞ ጎረቤት ለመጫወት ሄዶ ነበር፡፡ እንደመጣ አለመኖሯን ጠይቆ ካረጋገጠ በኋላ ‹ውሃ
ጠምቶኛል ስጪኝ› አለኝና ወደ መኝታ ቤት ገባ፡፡ ውሀውን በብርጭቆ ቀድቼ በራፍ ላይ ቆሜ ሳንገራግር ... <ጠምቶኛል እኮ ነው የምልሽ አምጪ እንጂ›በማለት ሲጮህብኝ በድንጋጤ ተርበትብቼ ወደ ውስጥ ዘለኩና ስሰጠው ብርጭቆውን ትቶ እጄን ለቀም አደረገው፡፡ ሳላስበው ብርጭቆ ከእጄ ሾለከና ወለሉ ላይ ተከሠከሠ፡፡ ባለችኝ ጉልበት እጄን አስለቅቄ ለማምለጥ መታገል ጀመርኩ፡፡ እሱ ግን ባለ በሌለ ኃይሉ ተሸክሞኝ አልጋ ላይ ወረወረኝና ተከመረብኝ፡ታገልኩት፤ ታገልኩት፤እስኪደክመኝ ታገልኩት፤ በጥፊ መታኝና በቦክስ ደገመኝ፡፡ እኔን ለማድከም የቻለውን ሁሉ አደረገ፤በመጨረሻ ኃይሌ ተሟጠጠ፤ተስፋ ቆረጥኩ፤ እያለከለከ ሱሪውን አውልቆ ቀሚሴን በመግለብ ጭኔን ሲፈለቅቅ አክስቴ ልጇን እንደታቀፈች ዘው ብላ መኝታ ቤቱ መሀል አይኗን አጉረጥርጣ ታየን ጀመር፡፡እሱ ሲያያት አልደነገጠም፡፡ ተበሳጨ እንጂ፡፡ ‹ምን አይነት ምቀኛ ነሽ› በማለት ያወለቀውን ሱሪ በእጁ እንደያዘ ገፍትሯት መኝታ ክፍሉን ለቆ ወጣ፡፡ እሷም እንደመደንዘዝ ካለችበት ነቃችና መጮኽ ማልቀስና መራገም ጀመረች፡፡እንደምንም እየተጎተትኩ ከአልጋው ላይ ተነሳሁና በተዳከሙ ቀጫጫ አግሮቼ ወለሉ ላይ ቆምኩ፡፡

‹‹አንቺ ሸርሙጣ የልጆቼን አባት...› ብላ ጮኸችብኝ፡፡ ግራ ገባኝ፤ የተበደልኩት እኔ፣የተደበደብኩት እኔ፣ልደፈር የነበረው እኔ፣ጥቃት የደረሰው እኔው ላይ፣እርግማኗንም የምታወርደው በእኔ ላይ፡፡

‹‹ስሚ አሁኑኑ ጨርቅሽን ይዘሽ ከቤቴ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼን ላሳድግበት፡፡ ከፈለግሽ ሽርሙጥና ቤት ግቢና እንደፈለግሽ ሁኚ፤አልፈልግሽም፡፡ >> በማለት ጨርቄንና ደብተሮቼን ሠብስባ አስታቅፋኝ እየገፈተረችኝ ከቤቷ አውጥታ አባረረችኝ፡፡

በእንደዚህ ሁኔታ ነበርሰ ታሪኳን ያስረዳችው፡፡ ከዛም እንደ እህቱ አድርጎ ተቀበላት፡፡.....

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች በአንድ ፖስት 10 ሰው #Subscribe ካደረገ በየቀኑ #ትንግርት ይለቀቃል 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12421🥰3