#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አራት
////
እንዳትሰማኝ ድምፄን ዝቅ አድርጌ‹‹የእውነት አድናቂሽ ነኝ"አልኩ ..እውነቴን ነው ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ብቻዋን ገልብጣ ገድገድ ሳትል ...እኔ ገና በግማሽ ብርጭቆ ጉልበቴ እየተብረከረከ ነው።
ተነሳሁና የተከፈቱ መስኮቶችን መዘጋጋት ጀመርኩ..ማብራቶችን አጠፍሁ፡፡ የሴትዬዎን ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ይዤ ወጣሁና የሆቴሉን በራፍ ቆልፌ ቁልፉን በጥንቃቄ ሚስጥር ኪሴ ውስጥ ሽጉጬ ወደ አልጋ ክፍል አመራሁ...አቀብያት በዛው ወደ ቤቴ ሄዳለሁ ሞባይሌን አውጥቼ ሰዓት ሳይ 7፡40 ይላል።
ደረስኩና አንኳኳሁ...
‹‹ግባ ክፍት ነው››
የሚል ድምፅ ስሰማ ቀስ ብዬ በራፍን ወደ ውስጥ ገፋ አደረኩትና ውስኪ ጠርሙስ የያዘ እጄን አስቀድሜ አንገቴን አሰገግኩ፡ መሀል ወለል ላይ ቆማ ተበትኖ ጀርባዋ ላይ የተኛውን ፀጉሯን አንድ ላይ ጠቅልላ እያሰረችው ነው..ቅድም ለብሳ የነበረውን ጅንስ ሱሪ አውልቃ ስስ የለሊት ቢጃማ ቀሚስ ለብሳለች...፡፡ ቢጃማው ሮዝ ቀለም ሲኖረው አጭር እና በቀላሉ አይን ውስጥ የሚመሰግ ነው...አስተውሎ ላየው ቀሚስ ሳይሆን ቁምጣ ነው የሚመስለው..እና ያ የሚንቀጠቀጥ እና ሊፈርጥ የደረሰ ዳሌዋ በከፊል እርቃን ነው...፡፡
"በራፍ ላይ ተገትረህ ታድራለህ ወይስ ትገባለህ ?"
"እ እሺ ገባለሁ ››አልኩና ወደውስጥ ገብቼ ጠርሙሱን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጬ ለመውጣት ዞር ስል እሷ ከቦታዋ ተንቀሳቅሳ ወደበራፍ እያመራች ነው፡፡
‹‹...ብርድ አስመታሀኝ ››"በሚል ሰበብ ክፍት ጥዬ የመጣሁትን በራፍ ዘጋችና ቆለፈችው፡፡
"ቆይ እኔ ሳልወጣ?"አልኩ ደንግጬ፡፡
"ትንሽ አጣጣኝ እና ትሄዳለህ.. ያውልህ ብርጭቆ…
"ቅዳልኝ" የንግግሯ ቃና ወደ ትዕዛዝ ያዘነበለ ነው.፡፡
ግራ በመጋባትና በመርበትበት እንዳለቺኝ አደረኩና እዛው ጠረጴዛ ጎን ያለ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ..፡፡እሷም ወደእኔ መጣችና ብርጭቆዋን አንስታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች ...፡፡አቀማመጧ በእኔ ትክክል ነው...፡፡አይኔ ወደታች ወደተጋለጠው ጭኗ እየተንሸራተተ አስቸገረኝ ፡፡...እሷ የእኔን ሁኔታ ከቁብም የቆጠረች አይመስልም፡፡ጭኗ እንደሴቶች ጭን ልል እና ለስላሳ አይደለም…፡፡እንደስፖርተኛ የዳበረ እና ፈርጣማ ነው፡፡ሲነኩት ትንቡክ የሚል አይነት ሳይሆን ሲነካ ጭፍልቅ የሚያደርግ አይነት፡፡
"አሁን ጋሼ እንዲህ ከእንግዳ ጋር በውድቅት ለሊት ቤርጎ ውስጥ ገብቼ ዘና ስል ቢያየኝ ምን ይለኛል? ጓደኞቼስ ቢያዩ ተረባቸውን እችለዋለሁ?››
በዝምታ ውስጥ ሆና የቀዳሁላትን ጠጥታ ጨረሰችና ከተቀመጠችበት ተነስታ እራሷ ለራሷ ቀዳች ፡፡..ልትቀዳ ስትል ታከከቺኝ..እናም ደግሞ የተቀባችው ሽቶ ያለፍላጎቴ በአፍንጫዬ ሰርጎ ገባ...እና እየጠጣሁ ካለሁት መጠጥ ጋር ተጋግዞ አነቃቃኝ...፡፡
ወደቦታዋ ተመልሳ ተቀመጠች ፡፡አቀማመጧ ግን እንደቅድሙ እግሮቿን አጣምራ ሳይሆን ፈርክክ አድርጋ ከፍታ ነው፡፡ ...እና በክፍተቱ አይንን ሚያጥበረብር ቀይ ፓንት አየሁ..፡፡ለምን አየህ ?ብላ ተነስታ የምታንቀኝ መስሎኝ ከመርበትበቴ የተነሳ ብርጭቆ ውስጥ ያለችውን መጠጥ በአንድ ትንፍሽ ገርገጭ አድርጌ አጋባኋት፡፡
"በቃ እግዜር ይስጥልኝ አሁን መሸብኝ ልሂድ..›› ለማለት አስቤ ገና አፌን ሳልከፋት ከተቀመጠችበት ተነስታ በድጋሚ ቀዳችልኝ፡፡ ..ለመናገር የተከፈተ አፌን ቀስ ብዬ ዘጋሁትና አንዴ መጠጡን አንዴ እሷን እያፈራረቅኩ ማየት ጀመርኩ።"አሁን ብዥ እያለብኝ ነው..፡፡ሞባይሌን አወጣሁና ሰዓት ተመለከትኩ...8:18 ይላል።
"ምነው መሸብህ እንዴ?"
"አይ አንቺን እንቅልፍ ነሳሁሽ ብዬ ነው"
"ጥሩ አስመሳይ ነህ"አለችኝ.፡፡
‹‹እስቲ በጌታ አሁን እንዲህ ይባላል?››አንገቴን በእፍረት ከማቀርቀር ውጭ ምንም መልስ አልሰጠኋትም፡፡ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደሻንጣዋ በመሄድ መጎርጎር ጀመረች‹‹...ምን ልትሰጠኝ ነው?"ብዬ ሳሰላስል ክሬም ቅባት አወጣችና አልጋ ላይ ወረወረች..መቀመጫዋን ወደ እኔ ፊቷን በተቃራኒው ወደግድግዳው አዞረችና በቆመችበት አጭሩን የለሊት ቀሚሷን ሞሽልቃ አወለቀች።አይኖቼን ጨፈንኩ..ገለጥኩ...መልሼ ጨፈንኩ...ቅድም በስሱ ካየሁት ቀይ ፓንት በስተቀር ምንም የጨርቅ ዘር በሰውነቷ አልቀረም....፡፡ጡቶቾ እንደሩሲያ አስፈሪ ሚሳዬሎች ጫፋቸውን ወደእኔ ቀስረው ልቤን አራዷት ብላችሁ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን እየታዩኝ አይደለም፡፡ፐ!! ከኃላዋ የሚታየው የሰውነቷ ቅርፅ ግን ከአንገቷ በላይ ያለውን መልኳን በሁለት ሶስት እጥፍ ይበልጣል።
ዘለህ ተጠምጠምባት የሚል ስሜት ከሁሉም የስሜት ህዎሳቶቼ ተሰባስቦ ጉሮሮዬ ላይ ተወተፈብኝ... እጇቼ ገላዋን ለመዳሰስ አይኖቼ ከግራ ወደቀኝ እያገላበጠ መላ ሰውነቷን በምስጠት ለመመልከት፤ አፍንጫዬ አንገቷ ስር ተደፍቶ ጠረኗን ወደውስጥ መማግ፤ጆሮዎቼ አፍ አካባቢ ተለጥፈው ከአንደበቷ የሚወጣውን ሹክሹክታ በፅሞና ለማዳመጥ እና እንትኔ ደግሞ ጭኖቾን ፈልቅቆ ወደ ውስጠቷ መስመጥ ፈለገ(ውይ እንትኔ ለካ የስሜት ህዋሳቴ አይደለም...ነው እንዴ?)
ዘፍ ብላ በሆዷ አልጋው ላይ ተኛች...አሁን በህይወቴ በአካልም በፊልምም ጭምር ካየኋቸው ባለ እርቃን ሴቶች ሁሉ ተወዳዳሪ የሌላት ፍፅም አማላይ ሆና ታየችኝ፡፡.. ፀጉሯ ብትን ብሎ ከፊል ጀርባዋን እና የተንተራሰችበትን ትራስ ሸፍኖታል..፡፡ከዛ ወረድ ስንል ልምጥ ብሎ የሚታየው ወገቧ የሩብ ጨረቃን ቅርፅ ይዞ አይንን ያፈዛል ፡፡..ከዛ ሽቅብ ወደላይ ስንወጣ መቀመጫዋ ቀይ ፅጌረዳ አበባ የሸፈናቸው ግዙፍ መንታ ተራሮች ይመስላሉ፡፡..ከዛ በመነሳት ለሁለት ተከፍለው የተዘረጉት እግሮቾ ለምለም መስክ ላይ የተዘረጋ የአክሱም ሀውልትን ይመስላሉ...እጣቶቾ ደግሞ....
"ትንሽ እሸኝና ትሄዳለህ.."የሚለው ንግግሯ ስለውበቷ ተቀኝቼ ሳልጨርስ ከሀሳቤ አናጠበኝ።
" ሎሺኑን ተጠቀምና እሸኝ.."ደገመችልኝ።
"እሸኝ ማለት ምን ማለት ነው..?እንዴት ነው የማሻት..?የሚታሽና የማይታሽ የሠውነት ክፍል ይኖራት ይሆን ?ካሸዋትስ በኃላ የሚከተል ነገር ይኖራል..?በሰከንድ ውስጥ በምናቤ ብልጭ ድርግም ያሉ ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው..፡፡እጆቼን ሰበሰብኩና ወደአልጋው ተራመድኩ፡፡ ጠርዝ ላይ ተመቻችቼ ተቀመጥኩ..፡፡ጃርባዋን ያለበሰውን ፀጉሯን ሰበሰብኩና ወደትራሱ አሻገርኩት...እና ሎሺኑን አነሳሁና ጨመቅ ጨመቅ አድርጌ እጄ ላይ አፈሰስኩና ከትከሻዋ ጀመርኩ...፡፡ይህ ሰውነት ከዚህ በፊት እንደማውቃቸው የሴት ገላዎች የሀር ጨርቅ አይነት ልስላሴ የለውም..፡፡በዳበሩ ጡንቻዎች የተገነባና በጠንካራ ቆዳ የተሸፈነ ልዩ አይነት ሰውነት ነው፡፡ቢሆንም ሲያሹት እጅን ሙልጭ ሙልጭ እያደረገ ቢፈታተንም ደስ ይላል፡፡ ‹‹ አዎ ትግስት ካለኝ ተገልብጣ በጀርባዋ ስትተኛና ከፊት ለፊቷ ያለውን የሰውነት ክፍሏን እንዳሻት ስትመቻችልኝ ቀስ ብዬ ልክ እንደዚህ ሎሺን ጡቶቾን አሸት አሸት እያደረኩ ከውስጣቸው ፍቅር እንዲያመነጩ አስገድዳቸዋለሁ፡፡›› ስል በአይነ ህሊናዬ በመሳል ጎመዣሁ..ምራቄን ገርገጭ እያደረግኩ ዋጥኩ ።

👍54❤1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
////
አሁን ወደ ቤቴ ልሄድ ወሰንኩና ወደ እሷ ዞርኩ ...እና አሁንም በድጋሜ ከፊል እርቃኗን ስመለከት እርብድብድ አልኩና"አይ በዚህ ሰአት ዘበኞቹ ሰለሚተኙ ግቢውን አይከፍቱልኝ ይሆን እያልኩ እያሰብኩ ነው።››
"ነውእንዴ? ታዲያ እዚህ እደራ!!"ብላ ዘጭ ያለው ሞራሌን መልሳ ሰማይ ሰቀለችው..፡፡እያንቀጠቀጠኝ የነበረው የውስጥ ቅዝቃዜ ከውስጤ እየተወገደ በምትኩ ሙቀት ሲራወጥ ታወቀኝ፡፡
"ይሻላል?"
"አዎ ..ችግር የለውም...፡፡አለችና አንሶላውን እና ብርድ ልብሱን ገልጣ ከውስጥ ገባች...፡፡እኔም በአፌ ምራቅ እየሞላ ጫማዬን ማውለቅ ጀመርኩ፤ ሸሚዜን አወለቅኩ፤ፓክ አውቴንም አልተውኩ አወለቅኩ፤ በመጨረሻ ሱሪዬን አወለቅኩና ልክ እንደእሷ በፓንት ብቻ ወደ አልጋ ላይ እየተስገበገብኩ ወጣሁ።..እያየኋት ብርድልብሱን ወደእኔ ገፋችና በአንሶላና አልጋልብሱ ተጠቅልላ አንደኛውን ጠርዝ ይዛ ተኛች ..
"ብርድልብሱን ልበስ..ደህና እደር"ብላኝ መብራቱን አጠፋችና ለሽ...፡፡
"እንደተባልኩት በብርድ ልብሱ እርቃኔን ጠቅልዬ ለመተኛት ሞከርኩ...፡፡ምን አይነቱ እንከፍ ነኝ እስኪ ደህና እደር እንዳለችኝ ያልሆነ ነገር ከምቀባጥር በክብር ፈጠን ብዬ ይሄን ክፍል ለቅቄ ብወጣስ?...እሷ እያንኮራፍች ነው፤እኔ ግን ..?እኔማ በሁለት እጇቼ እንትኔን አፍኜ ይዤ እየተገለባጥኩ ነው።በግድ ጉብ ልበልባት ይሆን ?አይ ይሄ አይሆንም ጓደኞቼ በፓለቲካ ምክንያት ታስረው ጀግና ሲባሉ እኔ በአስገድዶ ደፈራ ሀያ አመት ....አይ መታገስ መልካም ነው፡፡እኔ ደግሞ በትግስት አልታማም ..በእፅዋት ሳይንስ ከሀረማያ በዲግሪ ተመርቄ አዲስአበባ ላይ በአስተናጋጅነት ተቀጥሬ በመስራት ኑሮዬን እየገፋሁ ያለው ትሁት ትዕግስተኛ። ከዚህ በላይ ትግስት ምን አለ...?በተወለድኩባት አዲስአበባ ከተማ በተማርኩበት ሞያ ስራ ለማግኘት ከአመት በላይ በየመስሪያ ቤቱ ተንከራተትኩ ..ምንም ጠብ ያለልኝ ነገር የለም...አንድ መስሪያ ቤት ጋምቤላ ልላክህ ይላል...ሌላው ጋ ስሄድ የበጋ ስንዴ ፕሮጀክት አርሲ ላይ አለን እዛ እንላክህ ይለኛል።"ምነው ውትድርና የሰለጠንኩ መሠላቸሁ እንዴ? "ብዬ በእነሱ ይሁን በራሴ እያላገጥኩ አላውቅም ሁሉንም እርግፍ አድርጌ ያለሞያዬ ስባክን ይሄው ይሄን የመሠለ ፈተና…..
የባጥ የቆጡን ሳስብ ምንጊዜ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም፡፡ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስደኝ፡፡ ….....የበር መንኳኳት ነበር ከእንቅልፍ አለም መዞ ያወጣኝ
‹‹...ማነው? ምንድነው ?››በርግጌ ተነሳው፡፡
"ፅዳት ነው ሰዓት ደርሷል"
"ፅዳት "ዙሪያ ገባውን ቀኘሁ፡፡ነግቷል፡፡ክፍሉ ባዶ ነው.፡፡.ልጅቷ የለችም...፡፡ልብሷቾም ሆነ ዕቃዋቾ የሉም...፡፡ጠረኗ ብቻ ነው ያለው...፡፡ሄዳለች ማለት ነው..፡፡.ምኑ እንክርፍፍ ነገር ነኝ በፈጣሪ...?ምን አለ በጥዋት ተነስቼ ቢያንስ ለመጨረሻ ጊዜ እነዛን አይኗቾን ማለቴ መቀመጫዋን አይቼ በተሰናበትኳት...፡፡በንዴት ከላዬ ላይ ብርድ ልብሱን አሽቀንጥሬ ከላዬ ላይ ወረወርኩ፡፡ ...ከአልጋው ወረድኩ… ጠረጴዛ ላይ ያለውን ልብሴን ሳነሳ የሆኑ ባለመቶ ብር ድፍን ብሮች እና ብጣሽ ወረቀት ድብ ብሎ ወለል ላይ ወደቀ...ብሩን ተውኩና ወረቀቱን አነሳሁት አነበብኩት።
‹‹ደህና ሁን ቆንጇ...ቁርስ በእኔ ነው"ይላል ...
ብሩን አነሳሁና ቆጠርኩት 500 ብር ነው፡፡
‹‹እኔን ብሎ ቆንጆ›› አልኩና በቅጡ እንኳን ልብሴን አስተካክዬ ሳለብስ በንዴት ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ፡፡
ከውስጤ እየተንቀለቀለ ያለው ንዴት በቀላሉ ሊበርድልኝ ስላልቻለ እቤቴ ስደርስ እንኳን የበራፍ አከፋፈቴና አዘጋጌ ኃይል የተቀላቀለበት ነበር ፡፡
‹‹አንተ ቀልማዳ….››
‹‹አቤት አያቴ››
‹‹የትአባህ ነው ያደርከው…?ሰው ያስባል አትልም እንዴ…?ከአሁን አሁን መጣ እያልኩ ቁጭ ብዬ እኮ ነው ያደርኩት››
‹‹ውይ በጣም ይቅርታ ..ጋሼ ስራ አዞኝ እስከ 9 ሰዓት ስሰራ ስለነበር ደከመኝና እዛው ተኛሁ፡፡››
‹‹እና ሮጥ ብለህ አንድ አፍታ መጥተህ ላድር ነው ብትል የትኛውን ድንበር ስታቆርጥ ነው››ጠንከር ባለ የንዴት ቃና ሲቆጡኝ እንባዬ በአይኔ ሞላ ..ተበሳጫቼ አይደለም..፡፡ይሄን ያህል የሚያስብልኝ ሰው ይኖረል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበረ…፡፡
‹ሁለተኛ አይለመደኝም››ቃል ገባሁ፡፡
‹ፍፅምዐእንዳይለመድህ .
ትደግመውናትጣላኛለህ
.በል አሁን እንደደካከመህ ድምፅህ ያስታውቃል ትንሽ ተኛ፡፡››
‹‹እሺ አያቴ›አልኩና አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ፡፡
‹‹ዜና ወርቅ… ›
›.‹‹የዜናወርቅ አዎ እንደዛ ብላ ነበር ስሟን የነገረችኝ…ለዛም ይመስለኛል የዜናወርቅ የሚለው ስም ከእምሮዬ ሞልቶ እየፈሰሰ ያለው….
‹‹ወይ ጉድ ፍቅር ስለሚለው ቃል እራሱ ያሰብኩት ከስንት ጊዜ በኃላ መሆኑ ነው…?አዎ ከስድስት ረጂም አመት በኃላ …፡፡ ፍቅርን እርም ብዬ ነበር…፡፡ልክ እየደጋገሙ እየተንበገበገ ባለ እሳት እጣቱን ከተው እስኪቆስልና ቆዳወ እስኪገሸለጥ ድረስ እያቃጠሉ እንዳስፈራሩት ልጅ አይነት ነበርኩ፡፡.አዎ ፍቅርን የምፈራው ልክ ያ ህፃን ልጅ እድሜ ልኩን እሳትን በሚፈራበት መጠን ነው፡፡እና ጊዜያዊ ስሜቴን ማስወገድ አለብኝ.››.አስቤ አስቤ ሲደክመኝ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
‹‹ወይ ዝም ብዬህ ቻው እንኳን ሳልልህ ሄድኩ አይደል?››
‹‹አዎ…ግራ አጋባሺኝ እኮ››
‹‹አይ አስቸኮይ ነገር ስላጋጠመኝ ነው .ይቅርታ››
‹‹አይ ምንም አይደል…ግን እቤቴን ማን አሳየሽ? ››
‹‹አለቃህ…ማለቴ የሆቴሉ ባለቤት ለመነኩትና ከአንድ ጩጬ ጋ ላከኝ፡፡››
‹‹እሺ የቤቱን በራፍስ ማን ከፈተልሽ...?እኔ ተኝቼ ነበር››
‹እሱን ተወው .በመምጣቴ አልተደሰትክም እንዴ?››
‹‹አረ በጣም ተደስቼያለሁ…ነገሮች ድንገተኛ ስለሆኑብኝ ግራ ተጋብቼ ነው››
‹እንደዛ ከሆነ እቀፈኝ››
‹‹እሺ…ይሄው….ወደራሴ ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት…››
‹‹እዬብዬ.›በተሰባበረ እና በሚያቃትት ድምፅ ጠራችኝ፡፡
‹‹ወዬ ዜናዬ.››
‹በጣም ሞቀኝ…ልብሴን ላውልቅ››
‹አዎ አውልቂ…. እንደውም እኔም ላውልቅ.››አልኩና እኩል እየተረዳዳን ልብሳችንን አወለቅንና እርቃናችንን ተመልሰን እቅፍቅፍ ብለን ተጋደምን….፡፡እርቃናችን ሲፋተግ እሳት ፈጠረ..ነደድኩ… ከንፈሯ ላይ ተጣበቅኩባት…ጭኗን ፈለቀቅኩና ሰርስሬ ከመሀል ገባሁ….ቃተተች…‹‹ወይ የእኔ ጀግና ጎዳኸኝ….ቀስ በል..አመመኝ›››
በእጆቼ አፏን አፈንኳት..እንደዛ ያደረኩት የዜናወርቅን የመቃተት ጩኸት አያቴ እንዳይሰሙንና እንዳይረበሹ ስለፈራሁ ነው፡፡እንኳን እንዲህ የምትቃትት ሴት ይቅርና ጮክ ብሎ የሚያወራ ወንድ ጓደኛ እዚህ ቤት ይዤ መጥቼ አላውቅም፡ተጨነቅኩ፡፡ ስላፈንኳት እሷ ተንፈራገጠች…፡፡ግራ ገባኝ፤ ልልቀቃትና መጮኸን ትቀጥል ወይስ እንዳፈንኳት ልቀጥል …?ብትሞትብኝስ..?፡፡ከመጨነቄ የተነሳ ላቤ መንጠባጠብ ጀመረ …ተስፈንጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁ፤መኝታዬ ባዶ ክፍሉም ኦና ነበር…ዜናወርቅ ሀሳብ ብቻ ነበረች.፡፡ምኞት የፈጠራት ህልም››
‹‹ተመስገን›አልኩ፡፡
‹‹ተመስገን ያልኩት ዜናወርቅ ቤቴ ስላልመጣችና ስላልተዋሰብን ተደስቼ አይደለም..ይልቁንስ የእውነት ሆኖ ጋሽ ሙሉአለም ስላረበሽኳቸውና ስላላስቀየምኳቸው ተደስቼ ነው ተመስጌን ማለቴ..አንዳንዴ ግን ህልም ባይኖር በምኞታችን እና በምናገኘው ነገር መካከል ያለውን ክፍተት በምን እንሞላው ነበር?››
✨ይቀጥላል✨

👍72❤2👏2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
///
ከሀያ ቀን በኃላ ፤ስለእሷ ማሰብ ካቆምኩ በኃላ ...ኦልሞስት ከረሳኋት በኃላ ድንገት ተከሰተች። እለቱ ቅዳሜ ነው ፤ቅዳሜ ለአብዛኛው ሰራተኛ የደመቀች ቀን ነች። ፈገግታ የሚፈስባት ..ሙዚቃ የሚንቆረቆርባት..የዳንስ ጥበብ የሚጠበብባት ወሲብ የሚወሰብባት በስራ ሳይሆን በመዝናናት ብዛት የሚደከምባት...በወጪ ብዛት ኪስ የሚታጠብባት አዲስ ፍቅረኛ የሚጠባበስባት ክንድ ላይ ያለ ፍቅረኛ ድንገት ሾልኮ የሚሰወርበት… የታሪክ መፃፊያ ቀን ነች።
ከቅዳሜው የተትረፈረፈው ወደ እሁድ ይዘዋወራል።
ያው ከላይ በገለፅኩላችሁ ምክንያት ለእኛ ለአስተናጋጆች ዋና የስራ ቀናችን ነው።እና በዛው ልክ ወከባ አለ፡፡ ከአንዱ ወደሌላው ጠረጴዛ መስፈንጠር ..ከአንዱ ተስተናጋጅ ትዕዛዝ ወደሌላው...ብቻ ከባድ ግን ደግሞ ወሳኝ ቀን ነች።ከባድ ያልኩት የስራውን ጫና ፤ የተስተናጋጆቹ ወከባ፤ የትዕዛዝ መደበላለቅ፤ የሰከራሙ ትንኮሳ፤የሂሳብ መጉደል የመሳሰሉትን ጫና አስቤ ነው። ወሳኝ ያልኩት ሳምንቱን ሙሉ የማናገኘውን ቲፕ እና መሠል ተጨማሪ ገቢ የምናገኝበት ቀን ስለሆነ ነው።ዛሬም እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት እንደወትሮ የተለመደ ስራዬን እየሠራሁ ሳለ ጋሼ አስጠረኝ።
‹‹አቤት ጋሼ፡፡››
‹‹ወንበርህን ለሌሎቹ አስረክብና ቪ.አይ.ፒ ቁጥር 4 ያሉትን እንግዶች አስተናግድ"
ፈጠን ብዬ ‹‹እሺ ጋሼ "አልኩና በደቂቃ ውስጥ ወንበሬን ለጓደኞቼ አስረክቤ ወደታዘዝኩት ቦታ ሄድኩ ፡፡ በእኛ ሆቴል ስድስት የቪ.አይ.ፒ ቦታዎች አሉ።ልክ እንደትያትር ቤት በሆቴሉ ሰፊ አዳራሽ አራቱ ኮርነሮች ላይ ከፍ ብሎ የተገነብ ሲሆን ወደ እዛ የሚወጣው ከሆቴሉ ሳይገባ በውጭ በኩል ባለ እስቴር ነው።የሁሉም መግቢያ ለየብቻ ሲሆን ቀጥታ በጓሮ በር ገብቶ መልሶ በጎሮ መውጣት ያስችላል..የቤቱ ዙሪያ በጠንካራ ኮንክሪት ግድግዳ የተገነባ ሲሆን አንድ ጎን ማለት ወደሆቴሉ ያለው ጥይት በማይበሳው መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ነው ..፡፡መስታወቱ እታች ሆቴል ያለውን እንቅስቃሴ ጭፈራውንና እያንዳንድን እድምተኛ ቁልጭ አድርጎ ሲያሳይ ከሆቴል ወደላይ ግን ድፍን ጥቁር መስታወት ግድግዳ ብቻ ነው የሚታየው።ክፍሉ በጣም ዘመናዊ፤ ምቹ ሶፋዋች እና እንደ አማራጭ የባለጌ ወንበሮች ከምቹ ባልኮኒ ጋር ተገጥሞላቸዋል
መብራቶቹም በምርጫ የሚቀያየሩ ተደርገው የተሠሩ ሲሆን ሙዚቃን በተመለከተ ቀጥታ እታች የሚለቀቀው በጥራት የሚመጣበት ወይም ያንን ዘግቶ እዛው የራሳቸውን የተመረጠ ሙዚቃ የሚጠቀሙበት አማራጭ አለው። እዛ ክፍል …ተጠቃሚዎች ወይ በራፍ ላይ ቆሞ ወይ ውስጥ ተቀምጧ የሚያስተናግዳቸው የብቻቸው አስተናጋጅ ይመደብላቸዋል። የተለየ ፕራይቬሲ ከፈለጉ ደግሞ አስተናጋጅ ከክፍሉ ውጭ ይሆንና ልክ መጥሪያውን ተጭነው ከመድገማቸው በፊት ተስፈንጥሮ በመግባት ትዛዛቸውን ተቀብሎ የሚፈልጉትን ያመጣላቸዋል።
ይህን ክፍል የሚጠቀሙት ለደህንነታቸው ወይም ለስማቸው አብዝተው የሚጨነቁ ትላልቅ የቢዝነስ ሰዎች፤ዝነኞችና እና ባለስልጣኖች ናቸው። ቢሆንም ለሁሉም አገልግሎቶች ከመደበኛው ከአራት እጥፍ በላይ ያስከፋላል ።አስተናጋጅም ብዙን ጊዜ ጠቀም ያለ ጉርሻ ያገኛል።እናም ሁሉም እዚህ ቦታ ሲመደብ በደስታና በፈንጠዝያ ነው የሚቀበለው።
ደረስኩ ..በራፋን እንደመቆርቆር አደረኩና ገፋ አድርጌ ስከፍት ደነገጥኩ...፡፡እንደጠበቅኩት ቀለል ያሉ ሰዎች አይደሉም የገጠሙኝ። እርግጥ ሴቲቷ ጀርባዎን ሰጥታኝ የተቀመጠች በመሆኑ ፊቷ አይታየኝም፡፡ግን ዝንጥ ብላለች።ደማቅ ሰማያዊ ረጅም ቀሚስ፤ መካከለኛ ታኮ ካለው ሰማያዊ ጫማ ጋር አስማምታ ለብሳለች። ፀጉሯ የእውነት የእሷ ከሆነ ውብ መሆኑን በቀላሉ መናገር ይቻላል ፤ወገቧ ላይ ተበትኖ ይታያል .፡፡
.ሰውዬው ከእኔ ፊት ለፊት ናቸው ያሉት ፤ትልቅ ሰው ናቸው።ቆፍጣና ፤ኮስታራና አስፈሪ ..ፀጉራቸው ገብስማ ነው..፡፡ሙሉ ዠንጉርጉር የመከላከያ ልብስ ለብሰዋል።ትከሻቸው ላይ አራት ኮከብ ወደጎን ተደርድሯል።መቼስ በዚህ አለባበስ የሆነ ስብሰባ ላይ ወይም ወሳኝ ሀገራዊ ተልዕኮ ላይ አምሽተው ከጊዜ መጣበብ የተነሳ ወደቤታቸው ጎራ ብለው ለመቀየር ሳይችሉ ቀጥታ መተው ነው እንጂ ይሄ የክብር ልብስ ቦታው አይመስለኝም"በውስጤ አጉረመረምኩ ...
እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ወደፊት የተወሰነ እርምጃ ጠጋ አልኩና ‹‹ጌታዬ የጎደለ ነገር አለ?››ብዬ ጠየቅኳቸው፡
"ሚበላ ምን አላችሁ?"ጎርናና እና ሻካራ ድምፅ...እኚ ጄኔራልማ እቤታቸው ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸውን አስቀምጠው ነው ከዚህች ኮረዳ ጋር የሚማግጡት› በሆዴ አማኋቸው፡፡እስቲ አሁን ምን አውቄ ነው ለሰከንድ ያየኋቸውን ሰዎዬ ወደማማትና መፈረጅ የገባሁት ብዬ እራሴን ወቀስኩ።
"ጌታዬ ሜኑ ላምጣ"
"አይ አንድ ክትፎ አምጣልን...ክትፎቸው አሪፍ ነው" አለች ሴቲቱ...አሁንም በደበዘዘው ብርሀን ከእኔ በተቃራኒ የዞረ ፊቷ እየታየኝ አይደለም ።ድምፆ ግን የሚነዝር ኃይል ነበረው። የሚያደነዝዝ...በምን ምክንያት ነዘረኝ...?ስለምንስ ውስጤ ተናጠ... ?
"በቃ ጎረምሳው እንዳለችህ አድርግ"አሉኝ ጄኔራሉ ..ንግግራቸው ብቻውን ምሽግ የሚንድ አይነት ነው፤ተስፈንጥሬ ወጣሁ።በተቻለ ፍጥነት በልዩ ሁኔታ ክትፎውን አሰርቼ ይዤ ተመለስኩ።
"የእጅ ውሀ እዚሁ ልታመጣልን ትችላለህ?"ሴቲቱ ነች ጠያቂዋ፡
"ይቻላል እመቤቴ.. አሁን አመጣለሁ"አልኩና በደቂቃ ውስጥ የእጅ ውሀ ይዤ መጣሁ። ተንደርድሬ ሄጄ በክብር ጎንበስ ብዬ ልክ እማማ ኢትዬጰያን እያስታጠብኩ እንደሆነ ኩራት እየተሠማኝ ጄኔራሉን አስታጠብኩና ወደ ሴቲቱ ዞር ስል ፊት ለፊት አይን ለአይን ግጥም ...ምን ተአምር ነው?...ልደሰት ወይስ ልዘን? ላልቅስ ወይስ ልሳቅ ?
ጎንበስ ብዬ እያስታጠብኳት ቢሆንም ግን በደመነፍስ ነው። ድምፅ አውጥቼ ላወራት አልቻልኩም ? አውቅሻለሁ... ጋብዘሺኛል.. እርቃን ገላሽን በዓይኖቼ አይቻለሁ...በጣቶቼ ዳብሼሻለሁ ልላት ፈፅሞ አልቻልኩም።
‹‹አይ የጎረምሳ ነገር....ውሀውን ደፍተህ ጨረስከው እኮ"አሉኝ ጀኔራሉ እንደመሳቅ ብለው። ለካ እሷ መታጠብን ጨርሳ እጇን ብትሰበስብም እኔ ግን አይኔን አይኖቾ ላይ እንደተከልኩ ፈዝዤ ውሀውን ማንጮርጮሬን ቀጥያለሁ...በጄኔራሉ ንግግር ባነንኩና ተስፈንጥሬ ከስራቸው ወደበሩ መራመድ ጀመርኩ።
"በራፋ አካባቢ ነኝ፤ ስትፈልጉኝ መጥሪያውን ተጫኑ ››አልኩና ክፍሉን ዘግቼላቸው ወጣሁ።የእጅ ማስታጠቢያውን አስቀምጬ በረንዳው ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተሸከረከርኩ መብሰልሰል ጀመርኩ፡፡
"ፍፅም እንደማታውቀኝ እኮ ነው የሆነችው...ምን አይነቷ ባለጌ ነች?" ከንፈሬን በብስጭት ነከስኩ ..‹‹አንድ ለሊትም ቢሆን እኮ እንዲህ በቀላሉ የሚረሳ ነገር አልነበረንም ያሳለፍነው..? ነው ወይስ ውሽማዋን ፈርታ ነው?››
"ብትፈራ ይፈረድባታል .. ጄኔራሉ እኮ እንኳን በጎናቸው የሸጎጡት ሽጉጥ ተጨምሮበት ይቅርና እንዲሁ ያን ግንባራቸውን ቋጠር ፈታ ሲያደርጉት ያርበደብዳሉ...እኔስ ሀይ ሰላም ነሽ የሚል አጭር ሰላምታ እንኳን ለመስጠት ድፍረት ያጣሁት እሳቸውን ከመፍራት አይደል?።ግን ውሽማዎ ናቸው ነው ያልኳችሁ ..?ያንን በምን አወቅኩ ?አልነገሩኝ...ሲሳሳሙ እንኳን አላየሁም"
የመጥሪያው መንጣረር ከሀሳቤ አናጠበኝ። ፈጥኜ ወደውስጥ ገባሁና መሽቆጥቆጤን ሳልቀንስ "አቤት ጌታዬ"አልኩኝ፡፡

👍56❤2👎2👏1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
...በሙዚቃው ደነስኩ.. ውልቅልቅ እስክል ውስኪውን አንጠፍጥፌ ጠጣሁ"..አዎ አውቃኛለች... ፈፅሞ አልረሳችኝም...ከሁሉም ያስደሰተኝ ደግሞ ‹‹ቀናህ!!!›› የምትለዋ ቃል ነች...ምክንያቱም ቅናት እነጠቃለሁ ብሎ ከመፍራት ጋር ወይም ከመሠሠት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስሜት ነው።ፍርሀትም ስስትም ምንጫቸው ፍቅር ነው...እርግጠኝነት ከጎደለው ፍቅር።እና ታፈቅረኛለህ እያለችኝ ነው?ግን እንዳዛ ስላሰበች ለምንድነው እንደዚህ የፈነጠዝኩት? የእውነት እያፈቀርኳት ይሆን እንዴ ? እንዴ ከነጠላ ስሞ ሌላ ስለእሷ ምንም የማላውቃትን ሴት እንዴት ላፈቅራት እችላለሁ? ግን እኮ ፍቅር የኋላ ታሪክን አጥንቶ የወደፊት መድረሻን ገምቶ አሁን የቋሙበትን ድልዳል በሚዛን መዝኖ የሚገባበት የምክንያትና ውጤት ቁርኝት ማሳያ አይደለም..?ፍቅር ጨርቁን እንደጣለ ዕብድ ነገረ ስራው ቅፅበታዊና ተአምራዊ ነው።ስለዚህ ሳላቃትም በፍቅሯ ብወድቅ የሚደንቅ አይደለም!ግን ዕድሜዋ ጉዳይስ? ቢያንስ 10 አመት ትበልጠኛለች? እርግጥ በዕድሜ ሰላሳም ሀምሳም የምትበልጠውን እንስት ማፍቀር የተለመደ ነው?ቢሆንም ግን ቢገለበጥ ነበር የሚያምረው ..እኔ 10 አመት ብበልጣት።
ወየጉድ አሁንኮ ነገረ ስራዬን ላየ የመጀመሪያ የፍቅር አይነጥላዬን ገና እየገለጥኩ ያለው ጀማሪ አፍቃሪ ነው የምመስለው ፤ግን እኔ ቢያንስ አምስት አጫጭር ጣፍጭ ለወግ የሚበቁ እና አንድ ረጅም የተወሳሰበ ልቤንም ቅስሜንም አብሮ እንቅሽቅሽ አድርጎ የሠበረ.. በአለንጋ ተደጋግሞ በመገረፍ የተነሳ ትላልቅ ተጠላላፊ ሰንበር እንደተጋደመበት ጀርባ የእኔም ልብ በዛ ፍቅር ምክንያት ዙሪያ ጥምጥም የዞረበት ጠባሳ የተጋደመበት ሆኗል...
"ያ ፍቅር ህይወትን አስተምሮኛል ?ያ ፍቅር ደስታን አሳይቶኛል...?ያ ፍቅር ዘመዶቼን አሳጥቶ የከተማ ስደተኛና ምፅተኛ አድርጎኛል...ያ ፍቅር በራስ መታመኔን እንቅሽቅሽ አድርጎ የህይወት መስመሬን ከላይ ወደታች ገለባብጦታል…ያ ፍቅር ዛሬ ቢቋረጥም ግን ትዝታ ብቻ ሆኖ የቀረ እንደይመስላችሁ፡፡ ዛሬም ጣጣው እያደነኝ ነው...፡፡
እስከህይወቴ ፍፃሜ እንደተጣባኝ የሚዘልቅ ይመስለኛል። ...ይሄው ስድስት አመት ሞላኝ ባዶ ሆኜ መኖር ከጀመርኩ ...እና አሁን የማፍቀር ስሜት ሲሰማኝ የተገረምኩት ለዛ ነው።እውነት እርቃን ገላዋን ስላሳየችኝ ...ተዳፍኖ የኖረው የወሲብ ስሜቴ ስለተወጣጠረ ነው የተምታታብኝ። ግን አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከለል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል፤ ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ...የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር እስከ እርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች ስለሆን ይሆናል።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል..ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር ከቃላት ልውውጥ እና ከአይን መሠራረቅ ላያልፍ ይችላል፤ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቋረጥ ይችላል..እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ አለ?።
ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ ስላለቀ ነው ብለን መደምደም አንችልም... አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው ጉዞቸውን በተለያየ ጎዳና ሊቀጥሉ የሚገደዱባቸው አያሌ አጋጣሚዎች አሉ። ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።
ወይ ጉድ ..በዚህች እንግዳ ሴት የተነሳ የፍቅር ኤክሰፐርት መሆን ዳዳኝ እኮ….ጠርሙሶ ውስጥ ያለችውን መጠጥ እያወዛወዝኩ ከሆቴል ወጣሁና በእኩለ ለሊት ወደቤቴ ገባሁ፡፡በፀጥታ አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ….፡፡ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰደኝ፡፡
ጥዋት
..ከእንቅልፌ ባንኜ አይኖቼን ብገልጥም ቀልጠፍ ብዬ ከአልጋዬ መውረድ አልቻልኩም። ብነሳም ምን አልባት ምሳዬን ሰርቼ ከመብላት ውጭ ሌላ የምሄድበት ቦታ የለም ።ምሳ ደግሞ አላሰኘኝም፡፡ ምን አልባት ቁርሴን ከጋሽ ሙሉአለም የተሠጠኝን ቋንጣ ፈርፍር በደንብ ስለበላሁ ይሆናል። ተንጠራራሁና ከኮመዲኖዬ ላይ rich Dad poor Dad የሚለውን መፅሀፍ አነሳሁና ማንበብ ጀመርኩ .. አንድንም አባት የሌለው ሰው ሁለት አባቶች ያሉት ሰው የፃፈውን መፅሀፍ ለማንበብ መቋመጡ የሚገርም ነው። ብቻ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሁለት ገፅ ሳላነብ ስልኬ ጠራ አነሳሁና አየሁት..፡፡
የማላውቀው ቁጥር ነው ፡፡ላንሳው ልተወው ተወዛገብኩ።በስተመጨረሻ አነሳሁት
‹‹ሄሎ»
"ሄ...ሎ"ጥፍጥ ያለ የህፃን ድምፅ...ደነገጥኩ፡፡
‹‹ሄሎ..ሄሎ ..ማን ልበል?"
«ተአምል...ነኝ»
"ተአምር"የተኛሁበት የእንጨት አልጋ ከስር እርብራብ ተቀንጥሶ ይዞኝ ወደታች እየሰመጠ መሠለኝ...፡፡ስልክ ባልያዘው ቀኝ እጄ ፍራሹን ጨምድጄ ያዝኩ....፡፡እለተ መፅአት የፊታችን እሁድ መሆኑን ተረጋገጠ የሚል አዎጅን አስከትሎ የነጋሪት ጉሰማ ብሰማ ራሱ እንዲህ ሰማይ ምድሩ አይዞርብኝ፡፡
ልጅቷ ኩልትፍትፍ ባለ ድምፅ ንግግሯን ቀጠለች
"አዎ ተአምል...ል..ጅህ"
ይሄ መቼስ ተአምር ነው....፡፡ ተአምር አሁን ስምንት አመቷ ነው።በአካል ከተያየን 6 አመት አልፎናል።ማለቴ ቀጥታ በአካል ያየዋት አቅፌ የሳምኮት :ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ስታለቅስ ያባበልኮት የዛሬ ስድስት አመት ገና ክፉና ደጉን በቅጡ መለየት ባልቻለችበት ጊዜ ነው። ለዛውም እንደአባትና እንደልጅ እኮ አይደለም እንደ እህቴ ልጅ...እንደአጎቷ ሆኜ..፡፡ለምን እንደዛ ሆነ የእውነትም አጎቷ ስለሆንኩ፤ እንደዛም ስለመሰለኝ...፡፡ከዛ ወላጆቾ የውጭ ፕሮሰስ ጀምረው ስለነበር ተአምር ዲ.ኤን. ኤ ምርመራ ማድረግ ግዴታ ሆነ …ተመረመረች...ውጤቱ ለቤተሠብ በሀይለኛ መብረቅ የመመታት ያህል ድብ እዳና አስደንጋጭ ነበር... ልጅቱ የእህቴ ባል አይደለችም?
‹‹እንዴት ሆኗ...?"የህግ ሚስቱ እኮ ነች…፡፡››
"በተክሊል ነው እኮ የተጋብት"ብዙ ብዙ ተባለ... እኔ የምገባበት ጠፋኝ..ጠጋ አልኩና
በወቅቱ"ምስር ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ?››ብዬ ጠየቅኳት።
"አንተም እንደሌላው እንዴት ሆነ ብለህ ትጠይቀኛለህ?"
‹‹ምን ማለት ነው ?እንዴት አልጠይቅሽም?"
‹‹ያደረከውን ታውቃለህ ብዬ ነዋ ?››

👍56😁2😱1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
#ክፍል_ስምንት
////
"ሠላም ነሽ ታአምር?"
"ሠላም ነኝ"
" አባዬ...ድምፅህን ስለሠማው ደስ ብሎኛል"
"እኔም ደስ ብሎኛል የእኔ ጣፋጭ...ግን ስልኬን እንዴት አገኘሽ?"
"የጓደኛዬ የቢጡ አባት ነው አባቴን ባገኝ ደስ ይለኛል እያልኩ ሳለቅስ አሳዘንኩትና ..ከፌስብክ ላይ ፈልጎ ባንተ ስም የሚመሳሰል ሶስት ቁጥር ሰጠኝና …ሞክሬ …ሞክሬ.. ከዛ አገኘውህ...እናም ደስ አለኝ"
"ውዴ..እስከዛሬ ፈልጌ ስላላገኘውሽ በጣም ይቅርታ...እቴቴን ስላስቀየምኳት ፈርቼ እኮ ነው"
ዕድሜ ልኬን ከብዙ ሰዎች ጋር በክፉም በደጉም ብዙ ንግግር ተነጋግሬያለሁ... እንደዛሬው ግን የምይዘው የምጨብጠው ጠፍቶኝ አያውቅም...ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፊት ብቀርብ እራሱ እንዲህ አልርበተበትም።
"አባዬ"
አልተቀየምኩህም..እቴቴም ደግሞ ሰው ሳያያት ክፍሏ ውስጥ ትደበቅና ያንተን ፎቶ እና የእናትህን ፎቶ እያየች "የእህቴን አደራ በላሁ›› እያለች ታለቅሳለች ..፡፡
"እውነትሽን ነው..?"
"አዎ አባዬ እውነቴን ነው"
""ታአምሬ"
"ወዬ አባዬ"
"ስልኩ..ማለት የደወልሽልኝ በማን ስልክ ነው?"
"ስልኩ የራሴ ነው...እማዬ ከአሜሪካ ስትደውል በራሴ ስልክ እንዳናግራት ልካልኝ ነው"
"እና በዚህ ብደውል አገኝሻለሁ?"
"አዎ ግን..ማለቴ አንተን እንዳገኘሁህ እቴቴ ስለማታውቅ ፈርቼ ነው"
"ችግር የለም"
ሲመችሽ..እንዳወራሽ ስትፈልጊ ሚስኮል አድርጊልኝ"
"እሺ አባዬ"
"ቻው...እወድሀለሁ"
"እኔም በጣም ወድሻለሁ..ቻው"ስልኩ ተዘጋ፡፡
ስልኩን ከዘጋሁ በኃላ እንኳን እንባዬንም ስሜቴንም መቆጣጠር አልቻልኩም.፡፡ አልጋውን ለቅቄ በመውረድ ቤት ውስጥ ከላይ ወደ ታች እየተመላለስኩ ወለሉ ላይ የተዝረከረከኩትን ዕቃዎች እየረገጥኩ ዘለልኩ ..፡፡በቃ እብድ ነው የሆንኩት ። የማልረባ ነኝ...፡፡እኔ ሰው አይደለሁም፡፡መኖር ፈፅሞ አይገባኝም…
ከብዙ ቆይታና መታገስ በኋላ ጋሽ ሙሉአለም ድምፅ አውጥተው ተናገሩ ...፡፡ ውስጤ መተራመሱ ብሶ ቤቱን በማተራመሴ እሳቸውንም እየረበሸኩ መሆኑን እስከአሁን ልብ አላልኩም ነበር።
"ልጄ ምን ገጠመህ?"
‹‹አያቴ ጉድ ሆኜሎታለሁ? ..እኔ እኮ ሰው አይደለሁም?
‹‹ሠው አይደለሁም ስትል?
"በስህተት እና ሀጥያት የተጨማለቅኩ እርኩስ ነኝ።
"እንደዛማ ከሆነማ እንደውም ኦርጅናሌ ሰው ነህ...››
‹‹አያቴ ትክክል ኖት ..ግን ይሄን ታሪክ ብነግሮት ቀጥታ ይጠሉኛል...ዛሬውኑ ነው ቤቱን ለቀህ ውጣልኝ የሚሉኝ "
"ይበልጥ አጓጓኸኝ..‹.ምን ሰራው ቢለኝ ነው ይሄንን ልጅ የምጠላው?›እያልኩ ውስጤን እየጠየቅኩ ነው?...እስቲ ንገረኝና የትዕግስቴንና ይቅር የማለት ችሎታዬን ልክ ልፈትሽበት።››
"ልጄ ደወለችልኝ"
"ልጄ ..?.›
‹‹አዩ አያቴ ገና ከመጀመሪያው ደነገጡ አይደል?"
"ሂድ ከዚህ…. ቀላማጅ፡፡ እኔ አልደነገጥኩም...ይልቅ ቅድምአያት ስላደረከኝ ተደስቼ ነው"
‹‹ይሁን እሺ….ልጅቷን የወለድኩት ካሳደገችኝ ከአክስቴ ልጅ መሆኑን ስነግሮትስ ምን ይሰማዎታል....? 40 ለሚሆን ደቂቃ ከመጀመሪያው አንስቼ አወራሁላቸው...በፅሞና አዳመጡኝ።
"የማልረባ ሰው ነኝ አይደል?"እንዲጮሁብኝ …እንዲረግሙኝ ፈልጌለሁ፡፡
.እሳቸው ግን ለስለስ ብለው ሀዘኔታ ባጠቃው አነጋገር"የማትረባም ብትሆንም ልጄ ያው ሰው ነህ… ዋናው እሱ ነው።ሰው ደግሞ በማንኛውም ጊዜና አጋጣሚ አውቆም ሆነ ሳያውቅ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ስህተት ይሰራል!ምክንያቱም ሰው እንደዛ ስለሆነ?ልዩነቱ አንዳንድ የሰራውን ስህተት ለመሸፈን ሌላ ስህተት ሲጨምር አጠቃላይ ሁኔታውን ጭምልቅልቅ አድርጎ እስከወዲያኛው ያበላሸዋል..፡፡ሌላው ደግሞ ስህተቱን በማረምና ያስከፋቸውን ሰዎች በመካስ ቀሪ ህይወቱን ያስተካክላል..፡፡.ደግሞ ያንተ የሚገርም ነው..፡፡ልጅ አለችህ..ልጅቷ ደግሞ ስህተት ልትሆን አትችልም..፡፡.እሷ ንፁህ እውነት ነች...፡፡ስህተቱ እሷ የተገኘችበት መንገድ ነው...፡፡እሱም ቢሆን አንዴ የተዘረጋ መንገድ ነው... በመንገድ ዙሪያ ያለውን ገደል ማስተካከል ነው የምትችለው፡፡ መንገድን ለሁለት በመክፈል የለያዩት ገደሎች ድልድይ መስራት ነው የምትችለው፤ድልድዩ ደግሞ በይቅርታ ብረትና በፍቅር አርማታ ነው የሚገነባው... ፡፡
‹‹እንደሚሉት ቀላል አይደለም››
‹‹አትሞኝ ልጄ ፤የሰው ልጅ ከባባድ ነገሮችን ለመስራት ብዙም አይቸግረውም …ብዙ ጊዜ እንዝላል የሚሆነው ጥቃቅን ነገሮችን ለመስራት ነው፡፡ያው ዞሮ ዞሮ ጥቃቅን ነገሮች ተደምረው ነው ከባድ ችግሮችን የሚፈጥሩት ፡፡አሁን የነገርከኝን ታሪክ ስትሰራ በአንድ ቅፅበትና በአንድ ቀን አይደለም..ቀስ በቀስ፣አንድን በአንዱ ላይ እየደረብክ….በአመታት ውስጥ ነው የሆነው፡፡ለማጥፋት እንደዛ ከሆነ ያንን የጠፋውንም ለማደስ እንደዛው ቀስ በቀስ ምን አልባት የአራት እና በአምስት አመታት ጥረትና ልፋት ይጠይቅ ይሆናል..ግን በየእለቱ የምትችለውን ስራ.››
‹‹እንዴት አድርጌ አያቴ?››
‹‹ይው እኮ አስበህበትም ባይሆን ዛሬ ጀመርክ፡፡››
‹‹አልገባኝም፡፡››
‹‹ያው ከልጅህ ጋር አወራህ፣ድምፆን ሰማህ፤ምን ያህል አንተን እየናፈቀች እንደሆነ እና በአንተም ምንም ቅሬታ እንደሌላት ከአንደበቷ አረጋገጥክ፡፡››
‹‹አዎ አያቴ እሱን እንኳን እውነቶትን ነው፡፡››
‹‹አዎ እውነቴን ነው፤ አሁን ማድረግ ያለብህ ከጭንቀትና ትካዜ እራስህን ሙሉ በሙሉ አላቅና ከልጅህ ጋር ያለህን ግንኙነት በጥበብ በጣም ሳታግለበልበው ፤በጣም ሳታደፋነው በሚገባው ልክ ይዘህ አስቀጥለው››
‹‹ማግለብለብ ማለት?››
‹‹ለምሳሌ የሚቀጥለው እሁድ ብር ብለህ ደብረብርሀን ሄደህ ላግኝሽ ብትላት ቤተሰቦቾ ሳይዛጁበት ይሰሙና ልጃችንን ይዞብን ሊጠፋ ነው ብለው ፈፅሞ እንዳታያትና እንዳታናግራት በሊያደርጉ ይችላሉ.. ወይም እናቷ ጋ አሜሪክ ሊልኳት ይችላሉ….ስለዚህ መጀመሪያ በስልክ ግንኙነትህን በደንብ አጠንክር..ስለቤተሰቦችህ አሁናዊ ሁኔታ ቀስ በቀስ ከልጅህ እየጠየቅክ ተረዳ..፡፡ታዲያ ስትጠይቃት በጥበብ ማለቴ ድንገት በወሬ በወሬ ትዝ ብሎህ እንዳነሳህ እያስመሰልክ መሆን አለበት..፡፡የዛሬ ልጆች ቀላሎች አይደሉም…..እሷን ስለዘመዶችህ መረጃ ለማግኘት እየተጠቀምክባት እንደሆነ ከተሰማት ልትቀየምህ ትችላለች፡፡ከዛ አጠቃላይ ሁኔታውን ከተረዳ በኃላ ምን አይነት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብህ ትወስናለህ…፡፡ችግሮችሀን በደረጃ ከፋፍላቸው…ከዛ እያንዳንዱን በተናጠል ስታየው መፍትሄ ለማበጀት ያን ያህል ከባድ አይደለም…..፡፡
ለምሳሌ የልጅህን በአካል ማግኘት፤ከልጅህ እናት መታረቅ፤የአክስትህን ልጆች ይቅርታ መጠየቅ፤ የአክስትህን ባል ይቅር እንዲልህ መማፀን፤ የእራስህን ህይወት ለልጅህ በሚመጥን መልኩ ማስተካከል፡ እነዚህን ሁሉ ኮተት ችግሮች በአንድ ኩንታል ውስጥ ጠቅጥቀህ ካየሀቸው ዘላለም በጫንቃህ ተሸክመህ ስታላዝን ትኖራለህ እንጂ መቼም አትፈታቸውም፤ግን እያንዳንዱን በፔስታል ለየብቻ አድርገህ ያዛቸው ቅደም ተከተል ስትሰጣቸው በአንድ ጊዜ አንዱ ፔስታል ብቻ ተሸክመህ መዞር ቀላል ስለሆነ ሳትጨናነቅ በተወሰነ ጥረትና መስዋዕትነት ትፈታዋለህ፡፡ እሱን መፍታትህ ለሁለተኛው ፔስታል ውስጥ ላለው ችግርህ መፍቻ መንደርደሪያ ይሆናል.እንደዛ ነው ልጄ››

👍71❤2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው፡፡የምሰራበት ሆቴል ቤርጎ ይዛለች፡፡ስራ እንደጨረስክ ና ብላኝ ስለነበረ ስራዬን ጨርሼ ወደእሷ ለመሄድ እየተዘጋጀው ነው፡፡ስደርስ በረንዳ ላይ ባለ ወንበር ላይ ኩርምት ብላ ቁጭ ብላለች አይኖቾን ሰማይ ላይ ሰክታ ፈዛለች፡፡ከጎኗ ቁጭ አልኩና‹‹ጨረቃን እያየኋት ነው እንዳትይኝ?››አልኳት፡፡
‹‹አልኩህ››
‹‹እራስሽን ምን አሳየሽ?››
‹‹ማለት? ››
‹‹ያው እንቺም ጨረቃ ነሽ ብዬ ነዋ...››
‹‹ጨረቃ ነሽ ስትል በቀጥታ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››
"ከዚህ ንግግሬ ምን የማይገባ ነገር አገኘሽበት... ጨረቃ ነሽ ስል አደንዛዥ የሆነ ውበት ባለቤት ነሽ ማለቴ ነዋ።"
‹‹ጨረቃ እውነትም እንደምትለው አደንዛዥ ውበት አላት ?››
" የላትም እንዴ?"
‹‹እኔ ምን አውቄ እንደዛ ስላልከኝ ነው..ይህቺን አባባል ሁሉም ሰው ይጠቀማታል …ግን በትክክል በምሽት ስራዬ ብሎ የቤቱን በራፍ ከፍቶ በረንዳ ላይ ወጥቶ አንገቱን ወደ ሰማይ አንጋጦ፤ አይኖቹን ጨረቃ ላይ ተክሎ፤ ውበቷን ያስተዋለ ድምቀቷን ያጣጣመ.. ከመቶ ሺ አንድ ሠው ይገኝ ይመስልኸል...ግን ዝም ብሎ ስለሚባል ብቻ ትክክል ይሁን አይሁን ሳያውቅ ሁሉም ይደሰኩራል....
"እና ማጠቃለያሽ ጨረቃ ቆንጆ አይደለችም ነው?›
"አይ ነችምም አይደለችምም..ለምሳሌ እኔ ቆንጆ ነኝ?"
"ግጥም አድርጎ ...በጣም ውብ ነሽ"
"ከዚህ በፊት ሁለት ሰዎች ቀጥታ አሁን አንተ እንደቆምከው ፊቴ ቆመው ምንሽም የማያምር አስቀያሚ ሴት ነሽ ብለውኝ ያውቃሉ።እንደውም እንደዛ አይደለም.አስቀያሚ ወንዳወንድ ነገር ነሽ ነው ያሉኝ፡፡››
"እና ማንኛችንን አመንሽ?"
"ሁለታችሁኑም"
"ሁለታችንንማ ልታምኚ አትችይም ..አንቺ ወይ ቆንጆ ወይ አስቀያማሚ ነሽ.."
"አይ እንደየሁኔታው ቆንጆም አስቀያሚም ልሆን እችላለሁ...ውበት እንደየተመልካቹ ነው በሚለው ንግግር አምናለሁ...ለዚህ ነው ቆንጇ ነሽ ሲሉኝ ብዙ የማልፈነጥዘው አሰቀያሚም ሲሉኝ አንገቴን የማልደፋው።"
‹‹እና ማየቴን ላቁም?››
‹‹እንዳሰኘህ…ግን ጨረቃ በትከክልም ምን ግዜ ውብ እንደምትሆን ታውቃለህ?››
‹‹አላውቅም ንገሪኝ ››
ጦር ሜዳ ፊት ለፊት ግምባር ላይ እያለህ የሆነ ግዳጅ ተሰጥቶህ ከጓደኞችህ ጋር ድቅድቅ ባለ ጨለማ እየተጓዝክ መንገድ ጠፍቶህ ከጠላት ምሽግ ሰተት ብዬ ገባሁ ወይስ የጠላት ደጋፊ ከሆኑ ህብረተሰብ እጅ ወደቅኩ እያልክ አቅጣጫህን እንዴት እደምታስተካክል ግራ ገብቶህ እያለ ድንገት ብልጭ ብላ ስትወጣ…ከዛ እየደመቀች ስትሄድ….በቃ ውብ መሆኗ የሚገባህ የዛን ጊዜ ነው፡፡ምክንያም ህይወትህ የምታድንበት ጭላንጭል እድል ሰጥታሀለችና፡፡
‹‹ወይም ደግሞ›› ብዬ እኔ ቀጠልኩላት
‹‹ወይ ደግሞ.. በጣም የምትወጃትን ማለቴ የምታፈቅሪያት ልጅ አባትዬው ከእቅፍሽ ነጥቀው ለሌላ ሊድሩብሽ መሆኑን ስትሰሚ እሷን በጠፍ ጨረቃ ከቤት አስኮብልለሻት በየጫካው ይዘሻት ስትጠፊ በዛን አስደሳችና ጭንቀት በተቀላቀለበት ወሳኝ ሰዓት ለመንገድሽ ብርሀን ሆና ከፊት ለፊትሽ ቦግ ስትል .. በዛን በክፉና በደስታ ቀን የመንገድሽ አጃቢና መሪ ብሎም ለፍቅርሽም ድምቀት ስትሆን…አዎ የዛን ቀን ነው ጨረቃ ከውብም ውብ መሆኗን በደንብ የሚገባሽ››
‹‹አየህ ጨረቃን እንደየልምዳችን ነው ለውበቷ ትርጉም የሰጠነው..››
‹‹እንደልምዳችን ማለት?አንቺ ወታደር ነሽ እንዴ?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኳት፡፡
‹‹አይ ማለቴ ጓደኛዬ ወታደር ነው….ታውቃለህ አይደል?››
‹‹አዎ የበቀደምለታው ጄኔራል አይደል?››
‹‹አዎ ..እሱ ነው››
‹‹ግን…እንዲህ ከሌላ ሰው ጋር በምትሆኚበት ጊዜ ችግር አይፈጥርብሽም?››
አይኖቾ በንዴት ግልብጥብጥ አሉ….‹‹እንደዚህ ከማን ጋር ስሆን አይተኸኛል?›አፋጠጠችኝ፡፡
‹‹አረ አረጋጊው…ከእኔ ጋ ለማለት ፈልጌ ነው›
‹‹ካንተ ጋርስ ምን አድረግናል?››
‹የባሰ አለ ሀገርህን አትልቀቅ› ይላል የሀገሬ ሰው..ድንብርብሬ ወጣ…ምን ብዬ በንዴት ወደላይ የተመነጠቀ ስሜቷን ልመልሰው?‹‹ምንም አለማድረጋችንን እኮ የምናውቀው እኔና አንቺ ብቻ ነን…ቢያንስ ሁለት ቀን አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ አድረናል…››
‹እ..እሱስ እውነትን ነው….ግን ያ ምንም ችግር የለውም..እሱም አመቱን ሙሉ ከሚስቱ ጋ ሲተኛ እኔ ምንም ብዬው አላውቅም፡፡››
‹‹ሚስቱ?›
‹‹አዎ ሚስቱ….ሚስትና ሶስት ልጆች አሉት››
‹‹ከባድ ነው››
‹‹አዎ ፍቅር ምን ጊዜም ቀላል ሆኖ አያውቅም››
‹‹ግን ምንድነው ስራሽ..?››
‹‹እሱን ማፍቀር?››
‹‹አይ ስራ መትተዳደሪበትን ነው የጠየቅኩሽ..?››
‹‹ነገርኩህ ስራዬ እሱን ማፍቀር ነው….ገንዘብ ማገኝበትን ከሆነ የጠየቅከኝ ሌላ ጊዜ ነግሀለሁ…ግን ለራሴ የሚበቃ በቂ ገቢ አለኝ፡፡››
‹‹አይ ጥሩ ነው‹‹
‹‹ጥሩ ባይሆንስ ምን ምርጫ አለኝ....በል አሁን ይብቃን ገብተን እንተኛ››
‹‹አዎ ተነሽ.. ግን እኔ ወደቤቴ ልሂድ››
ፈገግ አለች‹‹ምነው ምን አሳቀሽ?››
‹‹አይ ወደቤት ልሂድ አባባልህ እራሱ ያስቃል..ምነው የጄኔራሉ ሽጉጥ ፊትህ ላይ ሲደቀንብህ በምናብህ አየህ እንዴ ››
‹‹ቀላል…ትቀልጂያለሽ እንዴ…?ገና በቅጡ እንኳን ያላየኋት እና ያላሰደኳት ልጅ አለችኝ..ድፍት ቢያደርገኝ ምን እላለሁ፡?፡››
ከተቀመጠችበት ተነስታ እጄን ይዛ ወደክፍሏ እያመረን ነው.. በራፍ አካባቢ ስንደርስ ነው ስለልጄ የነገርኳትን …ስትሰማ በድንጋጤ እጄን ለቀቀችና ባለችበት በመቆም አፍጥጣ አየችኝ፡፡
‹‹አንተ የእውነትን እንዳይሆን?››
‹‹ግራ ገባኝ ..ስለፍቅረኛዬ እያወራኋት ቢሆን ልሸመጥጣት እችል ነበር ..የልጅ ነገር ግን እንዴት አድርጌ…?መጀመሪያ አዳልጦኝ የተናገርኩ ቢሆን ወደኃላ ልመልሰው ግን እልፈለኩም …ቀጠልኩበት፡፡
‹‹አዎ ልጅ..አለቺኝ..የ7 አመት ልጅ..ተአምር ትባላለች››
‹‹ከዚህ በፊት ግን ፍቅረኛም ሚስትም እንደሌለህ የነገርከኝ መሰለኝ››
ይሄን ደግሞ መች ይሆን የቀባጠርኩላት…ማስታወስ አልቻልኩም፡፡አሁን ወደፊት ተንቀሳቅሰን በራፍ ጋር ደርሰናል….በእጇ ያንጠለጠለችውን ቁልፍ በማስተካከል በራፉን እየከፈተች ነው‹‹አዎ አሁንም ሚስትም ፍቅረኛም የለኝም ….እውነቴን ነው››
ወደውስጥ ገባች…ሄዳለሁ ያልኩት ሰውዬ ተከትያት ወደውስጥ ገባሁ ..መልሳ በራፉን ከውስጥ ቆለፈችው፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡ከጎኗ ተቀመጥኩና ወሬዬን ቀጠልኩ፡፡
‹‹ነገሩ ውስብስብ እና የድሮ ታሪክ ነው… ሀይስኩል ተማሪ እያለው ነው የልጅ አባት የሆንኩት››
‹‹ታድለህ….ምን አለ እኔም ከእናቴ ቤት ሳልወጣ አንድ ዲቃላም ቢሆን ወልጄ በሆነ››
‹‹እውነትሽን ነው?፡፡››
‹አዎ..እውነቴን ነው…..የህይወቴ አንዱ ህመም የልጅ እናት ካለመሆኔ ጋ የተያያዘ ነው…››አይኖቾ በእንባ ተሞሉ…አረ ዘረገፈችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ አሁንም ይቻላል.. ገናነው አልረፈደም…ሶስትም አራትም ልጅ መውለድ ትችያለሽ››
ኩስትርትር ብላ‹‹መቻሌን በምን አወቅክ?››በሚል ጥያቄ አስበረገገችኝ፡፡

👍53❤2😢2🤔1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
እራሴን አመም ስላደረገኝ አስፈቅጄ ወደቤት ስገባ ሶስት ሰዓትም አልሆነም።..ሹክክ ብዬ ገብቼ አልጋዬ ላይ "በመውጣት አረፍ እንዳልኩ ስልኬ ጠራ...አሁን ማንንም ቢሆን አንስቶ የማናገር ፍላጎት የለኝም የዜና ወርቅም ብትሆን እንኳን፡፡ስልኩ መጥራቱን ቀጥሏል ማንም ቢሆን ላለማንሳት ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ ማንነቱንም ማየት አስፈላጊ አልነበረም ..እኔ ግን እጄን ሰድጄ ስልኬን አነሳሁ፡፡ እስክሪኑን ወደአይኔ አስጠጋሁ..ተፈናጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁና ቁጭ አልኩ..እንዳይዘጋብኝ እየተስገበገብኩ አነሳሁት..
‹‹ሄሎ የእኔ ውድ..?
"ሄሎ አባዬ እንዴት ነህ?
"አለሁልሽ ..በጣም ሰላም ነኝ..አልተኛሽም እንዴ?"
"አይ ገና ልተኛ እየተዘጋጀሁ ነው...አባዬ የእኔ ክላስ የትኛው እንደሆነ ታውቃለህ አይደል?"
በምናብ ወደ አደኩበት ቤት ፈረጠጥኩ..ሁሉንም ክፍሎች በሀሳቤ ቃኘሁ ከእነቴቴ መኝታ ቤት ቀጥሎ ያለችው ክፍል ነች አይደል?"ግምቴ መቼስ የቤቱ ትንሽዬ ህፃን ስለሆነች ለቁጥጥርም ለሊት ተነስቶ ደህንነቷን ለማየትም ቅርብ ያለው ክፍል ነው የሚመረጠው ብዬ ነው...፡፡
"አይደለም..እዛ ህፃን ሆኜ ነበር አሁን ትልቅ ስሆን የአንተና የእማዬ የነበረውን ክፍል ወሰድኩት
ደነገጥኩ"በእውነት እሱ ክፍል መኖሩ ትዝ አላለኝም ነበር፡፡ እንደዛ ያልኩት ከዛ ሁሉ ዝብርቅርቅ ክስተት በኃላ እቴቴ ክፍሉን ምንቅርቅር አድርጋ የአንድን ሳይድ ግድግዳ በመደርመስ ከሌላው ጋር በመቀላቀል ክፍሉ ለታሪክነትም እንዳይታወስ የምታደርገው ነበር የሚመስለኝ ..ለዛ ነው ያንን አይነት ጥያቄ የጠየቅኳት"
"ልጄ ሳይገኝ ያ ክፍል አይከፈትም ብላ ከእነዕቃው አሽጋበት ነበር...ከዛ እኔ አክስቴ ትልቋን ለመንኩና እሷ በሌለችበት አስከፈቼ ገባሁበት፡፡"
"ታዲያ አልተቆጣችሽም?"
"አይ ምንም አላለቺኝም ግን አለቀሰች፡፡"
እኔም አሁን አለቀስኩ የሚቆጠቁጥ እምባ በቀኝ ጉንጬ ረገፈ"የእኔ ማር እናትሽ ለእቴቴ ትደውልላታለች አይደል?"ድንገት በእምሮዬ ብልጭ ያልኝን ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡
"ትደውልላታለች...እቴቴ ግን ትሰማታለች እንጂ አታናግራትም፡፡"
"ለምን?"
‹‹"እኔ እንጃ አባዬ...የሙት እህቴን ቃል እንድበላ አደረጋኛለች..ልጄን ወይ በህይወት አልያም ሞቶ ከሆነ ሬሳውን አግኝቼ እርሜን ሳላወጣ ከእሷ ጋር ባወራ እግዜር ይቀየመኛል ትላለች...ግን አባዬ እርም ማውጣት ማለት ምን ማለት ነው?።››
"ቁርጥ ማወቅ ማለት ነው የእኔ ልጅ"ቀላል ነው ብዬ ባልኩት ቃል ገለፅኩላት።
"አባዬ"
"ወዬ የእኔ ልጅ"
"እቃችሁን ስጎለጉል የእማዬ ማስታወሻ ደብተር አገኘሁት..ሁል ጊዜ አነበዋለሁ.. ደስ ይላል..።"
"እናትሽ ማስታወሻ ደብተር ነበራት እንዴ? እኔ አላውቅም..."
"አዎ አላት ..ትልቅ ሰማያዊ ደብተር....እና ደግሞ ስላንተ ብቻ ነው የፃፈችው...ትንሽ ትንሽ አንብቤው ስላልገባኝ ተውኩት.. ››
የእውነትም በጣም ተገርሜ "በእውነት ይገርማል .!"አልኩ ፡፡
በድንገት ማስታወሻው ላይ ያለውን ሀሳብ ለማወቅ የሚቀስፍ አይነት የጉጉት ስሜት ተሰማኝ..ልጄ የውስጤን እንዴት ማንበብ እንደቻለች አላውቅም"አባዬ ከፈለክ ትንሽ ትንሽ ፎቶ እያነሳው ልልክልህ እችላለሁ"ደ
ተነቃቃሁ"እንዴት አድርገሽ?"
"ቴሌግላም መጠቀም እኮ በጣም እችላለሁ...ለእማዬ ፎቶዬንና የፈተና ውጤቴን እያነሳሁ ሁሌ ነው የምልክላት"
"በጣም ደስ ይለኛል የእኔ ማር...በይ አሁን ተኚ"
"እሺ አባቢ ..ደህና እደር...እወድሀለሁ"
"እኔም እወድሻለሁ"
ስልኩ ተዘጋ...እራስ ምታት የሚባል ነገር ከጭንቅላቴ ተጠራርጎ ወዴት ጥርግ እንዳለ እኔ እንጃ።ልጅ መድሀኒት ነው የሚባለው ለካ ዝም ብሎ አባባል አይደለም፡፡
ስልኬ ተንጣጣ...ሚሴጅ ነው..ከልጄ ነው ከፈትኩት
‹‹ልኬያለሁ›› ይላል ወዲያው ዳታ አበራሁና ቴሌግራም ከፈትኩ .ተአምር እዬብ ሁለት ፋይል ልካልኛለች...የእኔ ቅመም ልጅ...፡፡ዳውን ሎድ አደረኩትና ከፈትኩት ፡፡ እውነትም ልምድ አላት ፡፡ፍይሉ በጥራት የሚነበብ በጥንቃቄ ተነስቶ የተላከ ነው።የእናቷን የእጅ ፅሁፍ ሳየው ሰውነቴን ነዘረኝ ፅሁፍና ምስሏ በአእምሮዬ እየተፈራረቀ ትዝታ ውስጥ ጨመረኝ...ምን አለ እህቴ ባትሆኚ።ትራሴን አስተካክዬ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩና ማንበብ ጀመርኩ።
ግንቦት 5/2008 ከምሽቱ 5 ሰዓት
እቤታችን ሲመጣ 9 አመቱ ነበር ።የመጣበትን ቀን በደንብ ነው የማስታውሰው እማዬና አባዬ ለቅሷ ብለው ወደ አዲስአባ ከሄዱ ከሳምንት በሀላ ነው ጥቁር በጥቁር ለብሰው ፊታቸው ጨልሞና ከፍቶቸው ሌላ የከፋው ፤ለንቦጩን የጣለና ግራ የገባው ልጅ ይዘው የመጡት፡፡ልጁን ቀድሞውንም አውቀዋለሁ፤ ያውቀኛል፡፡ አዲስአባ ያለችው የአክስቴ ልጅ ነው።የአሁኑ አመጣጡ ግን እንደከዚህ ቀደሙ ቦርቆና ፈንድቆ ከእኔና ከእህቶቼ ጋር ለአራት ለአምስት ቀን እቃ እቃ ተጫውቶ ለመመለስ እንዳልሆነ ገብቶኛል።
ትላልቅ ሰዎች አክስቴም ባሏም በድንገተኛ አደጋ ዘእንደሞቱ ሲያወሩ ሰምቼያለሁ ..ግን ይሄ ድንገተኛ አደጋ የተባለው ሰውን የሚገድል አውሬ ምን አይነት ነው?ስል በወቅቱ በነበረኝ የልጅነት አዕምሮዬ አሰብኩና በጣም ተበሳጨሁ። አክስቴን በተመለከተ ጣፋጭና የማይሳሳ አይነት ትዝታ ነው ያለኝ።በሶስት ወር ሆነ በስድስት ወር ልትጠይቀን ስትመጣ ..ኬክ፤ቸኮሌት፤ እና ልብስ ቀሚስ፤ ቲሸርት ጫማ ብቻ አንድ ነገር ይዛልን ትመጣ ነበር።
ትምህርት ቤት ሲዘጋ ደግሞ አዲስአባ እንሄዳለን...ያንን ቢሄድ ማለቂያ የሌለውን ከተማ በፈንጠዝያ ስንዝናናበት ቆይተን ሽክ ብለን በአዳዲስ ልብስ አሸብርቀን እንመለሳለን..አመቱን ሙሉ ከደብረብርሀን ወጥተው ለማያውቁ ጓደኞቻችን ስለአዲስአባ ተረት መሰል ታሪኮችን እየተረክን ስንጎርርባቸው እንከርማለን ለእኔ የአክስቴ ሞት ትርጉም በዛ የጨቅላነት ዕድሜዬ እንኳን በደንብ ነበር የገባኝ...ከአሁን በሀላ ከአዲስ አበባ የሚመጣልኝ ምንም ኬክ ሆነ ቸኮሌት እንደማይኖር ገባኝ..ዘናጭና ፍሽን ቀሚሶችም ከአክስቴ እንደማይበረከቱልኝ ከሁሉም በላይ ግን ክረምት መጥቶ ት/ቤት በተዘጋ ቁጥር አዲስአበባ ሄዶ መዝናናት የማይቻል መሆኑን ምን አልባትም ትልቅ ሰው እስክሆን አዲስአበባን እንደማላያት ተረዳሁ..
እና እዬቤን እማዬ ከሌሎች ሀዘንተኞች ጋር ይዛው ስትመጣ እላዩ ላይ ተጠምጥሜ አንገቱን አቅፌ አለቀስኩ..ቢያባብሉኝ እራሱ ላቆም አልቻልኩም... በወቅቱ እንደዛ ማለቀሴ አክስቴን አስታውሼ ነበር. የምታመጣልኝ ኬክና ቸኮሌትም ስላማራኝ ነበር...እናም አዲስአባም መሄድ ስለፈለኩ ግን ደግሞ እንደማልችል ስለገባኝ ነበር.፡
.ታላላቆቼ በድርጊቴ ግራ ቢጋቡም እኔ ግን በጣም አዝኜ ነበር..እና ለእዬቤ የራሱ አልጋ ከአዲስአባ እስኪመጣለት አልጋዬን አጋራሁት..እርግጥ አብዛኛውን ጊዜ እማዬ እያለ ሲቃዠና ሲንፈራገጥ እማዬ እየመጣች ወደራሷ መኝታ ቤት ትወስደውና ከማዬና አባዬ መሀል ይተኛ ነበር...እንደዛ ሲያደርግ እኔም ምን አለ አብሬው ሄጄ መሀከላቸው በተኛሁ እላለሁ፡፡እኛ ልጆቻቸው እንደው ፍርጥ እንላታለን እንጂ ከእነሱ ጋር የመተኛት እድል አናገኝም።እና በዚህ አይነት ሁኔታ እዬቤ ወንድማችን ሆነ፡፡ እቃቸው ከአዲስአባ መጣና ከእኛ ቤት እቃ ጋር ተቀላቀለ..ቤታቸውም እንደተከራየ እማዬ ስታወራ ሰምቼያለሁ። አልጋውም መጣለትና ከእኔ አልጋ ጎን ቦታ ተመቻቸለት።ግን ስንላፋና ስንጫወት ቆይተን ሳናስበው ወይ እሱ አልጋ ላይ ጥቅልል ብለን ተቃቅፈን

👍67❤3👎1🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ቀኑ ጭፍግግ ያለው ነው።እቤት ተቀምጬ ከግድግዳዬ ባሻገር ካሉት ጋሽ ሙሉአለም ጋር የተለመደውን የአያትና የልጅ ወሬ ማውራት በጣም ፈልጌ ነበር ...ግን ዛሬ ዝም እንዳሉ ነው...አንዳንዴ እንዲህ ያደርጋቸዋል፡፡
ዝምታቸው ሶስት አራት ቀን ባስ ሲልም እስከ ሳምንት ይዘልቃል።እናም በዚህ ሁለት ቀን እየሆነ ያለው እንደዛ ነው።ያ ደግሞ ለእኔ ድብርት ይለቅብኛል። እና አሁን ለዚህ ነው እቤቴን ለቅቄ የወጣሁት። የስራ ሰዓት እስኪደርስ ሁለት ትርፍ ሰዓት አለኝ፡፡
.አይገርምም በዚህ ድህነቴ ይሄ ሁሉ ትርፍ ሰዓት ..
ኑሮዬ የሚያሻሽል መአት ነገር ልሰራበት እችል ነበር...ለምሳሌ ጀብሎ ሆኜ ሲጋራና መስቲካ ባዞር የተወሰኑ ብሮች በእርግጠኝነት አገኝ ነበር....ሊስትሮም ሆኜ ጫማ ብጠርግም እንደዛው...ግን ሰነፍ ነኝ ወይም ግብዝ ነኝ ..ዲግሪ ተመርቄ እንዴት ሊስትሮ? እንዴት ጀብሎ ?ግን ባለዲግሪ ሆኜ አስተናጋጅ መሆን ከቻልኩ ጀብሎስ መሆን ምኑ ይከብዳል? ዛሬ ደገሞ ምን አይነት ሀሳቦች ናቸው በአዕምሮዬ የሚራወጡት ?
ምንአልባት እንዲህ ምነጫነጨው ልጄ ናፍቃኝ ይሆናል..ድምፆን ከሰማው ሶስት ቀን አለፈኝ..ወይ ጉድ ለአመታት ረስቼት እንዳልነበር አሁን እንዲህ ታሪክ ይቀየር..?.በሀሳብ ስናውዝ አንድን መኪና እንዳልገጨው ስለፈራሁ ፊት ለፊቴ ካገኘሁት ካፌ ዘው ብዬ ገባሁ እና በቅርብ ያገኘውት ጠረጰዛ ላይ ወንበር ስቤ ተቀመጥኩ።
ማኪያቶ አዝዤ ለመጠጣት እያማሰልኩ ፊት ለፊቴ ያለው ቴሌቪዥን የሚያሰራጨውን ፕሮግራም እያየሁ ነው.፡፡:ፕሮግራሙ የተደገመ ይላል፡፡ምንአልባት ከሶስት ወይም ከአራት ቀን በፊት የተከናወነ ክንውን መሰለኝ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ለመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጡ .››ይላል፡ከዚህ በፊት በቴሌቭዝን የማውቃቸውም ፤በጦርነቱ ምክንያት በየፌስቡኩ ምስላቸውና የጀግንነት ስራቸው ያነበብኩላቸው ጉምቱ የሀገሪቱ የጦር ጄኔራሎች አሉበት.፡፡እኔም እንደወትሮው የቴሌቭዝን ፕሮግረሞች በተሰላቸ መንፈስ ሳይሆን በተነቃቃ ስሜት ነበር ስከታተል የነበረው..
የማዕረግ እድገቱ ኮረኔሮችን እና ጀኔራሎችን ያከተተ ነው..የፈረጠሙና የገዘፍ የጦር ሹሞቹን ብርጋዴር ጄኔራል፤ሜጄር ጀኔራል.፤ሌፍተራን ጄኔራል እያሉ ትከሻቸወ ላይ ማዕረጉን የሚያሳይ ኮኮብ ሲያስሩላቸው ደስ ይላል፤ይነሽጣልም፡፡፡ምን አለበት እኔም ባለፈው ምልመላ ብመዘገብና ወታደር ብሆን በዚህ ህይወት ከመርመጥመጥ አይሻልም ነበር? ብዬ እራሴን ጠየቅኩ ፡፡ጥያቄዬ አግባብ ነው ወይስ አልፎ ሂያጅ ግልብ ስሜት የፈጠረው..?መልስ ከማግኘቴ በፊት በመሀከል ነጎድጎድ ተንጓጓ፤ ፍንጥቅጣቂና ዝብርቅርቅ ቀለማት በአካባቢዬ ተረጩ፤ መብረቅ በድንገት ወደቀ…ከመቀመጫዬ ተነሳሁ ወደእስክሪኑ አፈጠጥኩ አዎ እራሷ ነች..፡፡
ኮረኔል ዜናወርቅ ይግዛው ወደ ብርጋድር ጀኔራልነት ተሸጋግረዋል፡፡በዛ በእውቅ ቀራፂ በአመታት ጥረትና ልፋት የተቀረፀ የሚመስለው የታነፀና የተገናባ ሰውነቷ ላይ ያንን ባለግርማ ሞገሱ የመከላከያ ልብስ ስትለብስበት ዋው…ጠቅላይ ሚስቴሩ ፊት ቆማ ቆፍጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠች…ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደጆሮዋ ጠጋ ብለው የሆነ ነገር እያንሾካሾኩላት ማዕረጉን በትከሻዋ አጠለቁላት.
እንደ አጀማማሯ ሰላምታ ሰጥታ ከመድረኩ ስትወርድ ጋዜጠኛ ተቀበላት፡
‹‹ብርጋዴር ጀኔራል እንኳን ደስ ያሎት››
‹‹እንኳን አብሮ ደስ ያለን?››
‹‹ሴት ሆኖ እዚህ ትልቅ ክብር ያለው ወታደራዊ ማዕረግ ላይ በመድረሶት ምን ተሰማዎት?››
‹‹ያው ይሄ ማዕረግ በደም እና በላብ ነው የሚገኘው…ደምና ላብ ደግሞ የወንድም ሆነ የሴት ጠረኑም ቀለሙም አንድ ነው…በአጠቃላይ ሴት ስለሆንኩ ሳይሆን ስለሚገባኝ ያገኘሁት ማዕረግ ስለሆነ ደስ ብሎኛል፡፡››
ጋዜጠኛው ያልጠበቀውን መልስ ማግኘቱ በሁኔታው ያስታውቃል፡፡
‹‹ምስጋና የሚያቀርብለት ሰው ወይም አካል ካለ እድሉን ልስጦት›የሚል የተለመደ የመዝጊያ ሀሳብ አቀረበ
‹‹የእውነት ወታደር እንድሆን እና ህልሜን እንድኖር የረዳኝን ተቋሜን አመሰግናለሁ….ሀገሬንም እንደዛው…በደሜ ቁስሏን አጥባለሁ.. በአጥንቴ በጀርባዋ የተሸከመችውን ችግሯን አክላታለሁ የሚል አላማ ነበረኝ ያንንም ያደረኩ ይመስለኛል….ወደፊትም በተለየ መልኩ ተመሳሳዩን ማድረጌን ኦቀጥላለሁ…አመሰግናለሁ፡፡›› ብላ ከእስክሪኑ ወጣች…እኔም ኪሴ ገብቼ የጣጣሁበትን የማኪያቶ ሂሳብ ጠረጳዛ ላይ አስቀመጥኩና ለብቻዬን እየለፈለፍኩ ወደቤት ተመለስኩ ተንቆራጠጥኩ ..ጨጓራዬን ለበለበኝ..ምን አስዋሻት?.የጄኔራሉ ውሽማ እንደሆነች ነበር የነገረቸኝ…?ታዲያ አሁንስ ስለአለመሆኗ ምን መረጃ አለኝ ?ብዬ እራሴን ጠየቅኩ.፡፡ውሸቷን ነዋ ውሸቷን…..ቅምጡ እንደሆነች እኮ ነበር የነገረችኝ….ስራ እንደሌላትም ነግራኝ ነበር…፡፡እንደእብድ በግትልትል ሀሳቦች ሰክሬ ቀባጠርኩ፡፡
ዘንድሮ ምን ውስጥ ነው የገባሁት…?የጄኔራል ቅመጥ አፈቀርኩ ብዬ ስሰጋና ስሸማቅ ጭራሽ እራሷ ጀኔራል…ለመሆኑ ስንት አመቷ ነው…?ስትታይ እኮ ሰላሳም የሞላት አትመስልም..መቼስ በሰላሳ አመት እዚህ ደረጃ ደርሳ እኔን አታሳቅቀኝም..እኔም እኮ ሰላሳ ሊሟለኝ ሁሉት አመት ያልሞላ ጊዜ ነው የቀረኝ…ይሄው ታዲያ እኔ ያለሁበትን እና እሷ ያለችበትን እዩት..
ግን ግላዊ ህይወቷ እንዴት ነው….?ለምን እንደዛ ታደርጋለች..?እንዴት እኔን መረጠችኝ…?ንቃኝ ነው አምናኝ…?
ግን እኮ እስከዛሬ ሶስት ለሚሆኑ ቀናቶች አብረን ተጫወትን አብረን አንድ አልጋ ላይ ተኛን እንጄ ምንም በመሀላችን የተፈጠረ አካላዊ ንክኪ ሆነ ፍቅራዊ ድርድር የለም፡፡..ዝም ብዬ ነወ የምቀባጥረው...እሷ እኔን የምትፈልገኝ ለመደበሪያ ነው..ካላባት ትልቅ ሀላፊነት እና የስራ ጫና ዘና ለማለት እና የህወትን ሌለኛውን ጀርባ ለማየት ስትፈልግ ይሆናል እንደዛ የምታደርገው….ኡኡ ላብደ ነው..፡፡ልብሴን ቀየርኩና ከቤት ወጣሁ ፡፡ሰዓቱ ስለደረሰ ወደስራ ነው የገባሁት..ከአንገት በላይ የግድ ስለሆነብኝ ብቻ ስራዬን መሰራት ጀመርኩ፡፡
ማታ አራት ሰዓት አካበቢ የደንበኞችን ትዕዛዝ ለመተግበር ከአንዱ ጠረጴዛ ወደሌላው ጠረጴዛ ስመላለስ አይኔ አንድ ነገር አየ..ጄኔራሏ እንደተራ ሰው ጅንስ ሱሪ ለብሳ ኮፍያ ያለው ቢጃማ ጃኬት አድርጋ ኮፊያውን ጭነቅላቷ ላይ ደፍታ በአይኖቿ ጥቁር መነፅሯን ሰክታ ልክ የሰፈር ማጅረት መቺ መስላ ሚሪንዳ ቶኒኳን ትጠጣለች፡ ፡ተንደርድሬ ስሯ ደረስኩና ጠረጴዛውን ተደገፍኩ…. አይኖቾ ላይ አፈጠጥኩባት ….ተረጋግታ ቀስ ብላ መነፅሯን አወለቀችና በፈግታ አየችኝ...ምለው ነገር ስለጠፋኝ ካጎነበስኩበት ቀና አልኩና ፊቴን ዞሬ ከመቀመጫዋ ራቅኩ…ተመልሼ ወደእዛ አልሄድኩም… .በጣም ተበሳጭቼባተለሁ፡፡
እንዲያ በተወጠረ ስሜት ላይ ሆኜ ሰዓቱ እንደምንም ገፋ፡፡ ተስተናጋጆችም አንደ በአንድ እያሉ ወጥተው አለቁ… ፡፡እሷም ምን ጊዜ እንደወጣች፤ወደየት እንደወጣች ባላያሁበት የጊዜ ቀፅበት ከእይታዬ ተሰወረች …ሂሳብ አሰረክቤና አንገቴን አቀርቅሬ በተከፋ ስሜት ወደቤት ሄድኩ..በራፍን ከፍቼ ገባሁ፡፡
‹‹አንተ ቀልማዳ መጣህ?››አያቴ ናቸው፡፡
ውይ ተመስጌን አያቴ መናገር ጀመሩ…
‹‹አዎ አያቴ..ግን ቢያዩ ድክም ብሎኛል››መናገር በመጀመራቸው በጣም ደስ ቢለኝም እኔ ደግሞ በተቃራኒዊ በዚህ ወቅት ምንም አይነት የመናገር አፒታይት የለኝም.፡፡ጥልቅ ምስጠት ውስጥ ገብቼ በሀሳብ መንቦራጨቅ ነው ያማረኝ፡፡

👍52❤7🔥1🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹እኔ እዬብ እኮ ነኝ.›› ብዬ ቃላት ከአንደበቴ ለማውጣት አፌን ስከፍት ከንፈሯ ከንፈሬን ጎረሰው…ተአምር ነው በዚህ ሀገር ስንት ሴት ጄኔራሎች አሉ…?ከእነዚህ ውስጥ ከ ጄኔራሎች ጋር ፍቅር ለመጋራት ስንት የአዳም ልጅ እድል አግኝቷል.?.ልቤ በትዕቢት ስታብጥ ታወቀኝ…፡፡እጄን በወገቧ ዙረያ ጠምጥሜ ይበልጥ ወደሰውነቴ አጣበቅኳት..ብስጭቴ ሁሉ ከጭንቅላቴ እየተነነ አየሩን ሲሞላ ታየኝ…ውስጤ ተንፈቅፍቆ መሳቅ ጀምሯል…
ከከንፈሯን አላቃ በአንድ እጇ ብቻ ወገቤን ይዛ ወደላይ አንጠለጠለችኝና አልጋው ላይ ወረወረችኝ…፡፡ወይኔ ዛሬ በቃ እስከመጨረሻው ነው…ቆይ ልብሴን ላውልቅ ብዬ ልነሳ ቀና ስል ግንባሬ ላይ ሽጉጥ ደቅናለች..መልሼ በድንጋጤ በመደንዝ አልጋው ላይ ተዘረርኩ፡
‹‹ሽጉጥ እንኳን ሊደቀንብኝ በህይወቴ በፊት ለፊቴ አይቼው አላውቅም በፊልም እና በፎቶ ብቻ ነው የማውቀው..እና የጋለው ሰውነቴ ቀዘቀዘ…››
‹‹እንዴ ምን አጠፋሁ..?››
‹‹ሌባ ነህ..››
‹‹እኔ እዬብ እኮ
ነኝ››ለስንተኛ ጊዜ ይሆን ስሜን የነገርኳት?፡፡
‹‹አዎ ልቤንም የሰረቅከው እዬብ የተባልከው አስተናጋጅ አንተ አይደለህ?››
‹‹ይቅርታ የእኔም ልብ እኮ የለም ›አልኳት በአሳዛኝ ድምፅ ሽጉጡን ከግንባሬ አንስታ ትራሷ ስር ሸጎጠችና ከጎኔ ተኛች
‹‹በፈጣሪ ምነው ምን አድርጌሽ ነው እንዲህ ምታስደነግጪኝ.?››
‹‹ይቅርታ››
‹‹እስከአሁን እንዴት ሳትተኚ››
‹‹አየጠበቅኩህ ነበር››
‹‹እንዴት …ወደቤት ሁሉ ሄጄ ተኝቼ ነበር.
‹‹እናስ?››
.እናማ እንቅልፍ አልወስድም ሲለኝ ተመልሼ መጣዋ››
‹‹መጀመሪያ ለምን ሄድክ? አኩርፈሀኝ ነበር አይደል?››
‹‹አዎ በጣም ነበር የተበሳጨሁብሽ ..ደግሞ ዛሬ ነው ያየሁት..ወታደር መሆንሽን ብትነግሪኝ ምን አለበት ?ለዘውም ጄኔራል.››
‹‹ምን ይጠቅምሀል… እኔ ከአንተ ጋ እየተገናኘሁ ያለሁት ጄኔራል ሆኜ ሳይሆን ዜና-ወርቅን ብቻ ሆኜ ነው..››
‹‹ኸረ ተይ በናትሽ..ከቀድሞ አውቄ ቢሆን ልቤን መች እንዲህ አዝረከርካት ነበር…››
‹‹ምን ወታደር አይመችህም እንዴ?.››
‹‹አረ እንደዛ ማለቴ
አይደለም ግን ይከብዳል…በተለይ ለአንቺ የሚከብድ ይመስለኛል..አለ አይደለ እኔ እንጃ ብቻ.››
‹‹ለማለት የፈለከው ገብቶኛል.ግን አታስብ በቅረብ ጡረታ ልወጣ ነው..››
‹ጡረታ ምነው በዚህ ዕድሜሽ.?ለዛውም የማአረግ እድገት ባገኘሽበት ማግስት ››
‹ ምክንቱን ሌላ ጊዜ እንግርሀለሁ …ግን ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ከሰራዊቱ እሰናበትና ሌላ የሲብል ስራ ላይ የምመደብ ይመስለኛል…››
‹‹አሁን ትንሽ ቀለል አለኝ…መቼስ ጡረታ ከወጣሽ በኃላ ችላ አትይኚም አይደል?››
‹‹አይ አልልህም….ግን አንድ ልደብቅህ ማልፈልገው ነገር አለ››
ስለጄኔራሉ ፍቅረኛዋ የሆነ ነገር ልትለኝ ነው ብዬ በታፈነ ስሜት‹‹ ምን?›› ስል ጠየቅኳት
‹‹አንተን በተመለከተ በጣም የተወዛገበ ስሜት ነው የሚሰማኝ…የሆነ ድሮ የማውቀው የጠፋ ዘመዴ ወይም ወንድሜ ነው ምትመስለኝ››ብላኝ እርፍ፡፡
‹‹ባክሽ አትቀልጂ …ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?፡፡››
‹‹እኔ እንጃ …ሁል ጊዜ ላገኝህና ላቅፍህ እፈልጋለው..አግኝቼ ሳቅፍህ ደግሞ ታናሽ ወንድምሽ እኮ ነው የሚል ስሜት ይተናነቀኛል፡፡››
‹‹ምነው የጠፋ ወንድም ነበረሽ እንዴ?››
‹‹ኸረ ፍፅም.. እኔ ምንም የጠፋም ያልጠፋም ወንድም ኖሮኝ አያውቅም››
ኮስተር ብዬ‹‹ተይው በቃ ይህ የእህት ነገር እጣ-
ክፍሌ አይደለም..ለጊዜው ጓደኞች ከሆን ይበቃል›› አልኳት …ውስጤ ግን ምንም አይነት ከእሷ ጋር ጓደኛ የመሆን ጉጉት የለውም…
በተረጋጋ አንደበት‹‹እንደዛ ከሆነ እንተኛ››አለችኝ፡፡
‹‹ደስ ይለኛል›አልኳት፡፡
እሺ ብላ አልጋው ላይ ቆመች…የለበሰችውን ቢጃማ አወላለቀችና በሰማያዊ ፓንት ቆመች.እኔ በተኛሁበት ከስር ወደላይ እያየኋት ነው..ይገርማል በቴቪ በዛ ግርማ ሞገስ ያያት ሰው አሁን እንዲህ እርቃኗን ቆማ ከነሙሉ ውበቷና ደምግባቷ ቢያያት ደግሞ ምን ይል ይሆን?፡እኔም በተኛሁበት ልብሴን አወላልቄ ወደጠረጳዛው ወረወርኩና ከውስጥ ገባሁ ..ቀድማኝ ገብታ ነበር፡፡ መብራቱን አጠፈሁና ከሰውነቷ ተጣበቅኩ፡፡እና ከየት እየተንቀዠቀዠች እንደመጣች ሳላውቅ የተአምር እናት በምናቤ ተሰነቀረች…የሴት ልጅን ገላ ሳቅፍ እንዲህ አይነት የሚነዝርና የሚያሾር አይንት ስሜት ሚሰማኝ ከእሷ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ዳሩ ነገሮች ባለምኳቸው መጠን እድገት አላሳዩም.. ሊቱን በሙሉ በመተቃቀፍ ገደብ ባይኖረውም ከዛ እልፎ ወደ ጭን መፈላለቅ ሊያድግ አልቻለም፡፡ ‹‹በፈጣሪ አሁን እኔ ምኔነው የእሷ ወንድም የሚመስለው?››ይሁን እስቲ ….ማምሻም ዕድሜ ነው ይባል የለ፡፡
…በማግስቱ ማታ
//
ከምሽቱም አምስት ሰዓት ከስራ መልስ ነው፡፡አልጋዬ ላይ ወጥቼ ከብርድልብሴ ስር ገብቼ ስለነበር ስልኬን ካስቀመጥኩበት አነሳሁና ተነጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁ፡፡ብርድልብሱን ተከናነብኩና ሞባይሌን ከፈትኩ ፡፡ቅድም ልጄ ተአምር ልካልኝ የነበረው ቴሌግራም ከፈትኩ….እናቷ ስለእኔ የፃፈችው ቀጣይ ፀሁፍ ነው….የእሷን ፅሁፍ ማንበብ የቡና ሱስ ነው የሆነብኝ፡፡ ተመቻችቼ ማንበብ ቀጠልኩ፡፡
ግንቦታ 16/2008 ዓ.ም
እዬቤ ከእህቶቼ በላይ ነው ማቀርበው…ከእህቶቼም በላይ ነው የምወደው..እሱ ለእኔ የሚስጥር ተጋሪዬ ነው..እሱ ለእኔ የትምህርት ቤትም ጓደኛዬ ነው።እርቃኔን እህቶቼ ፊት ስቆም ሰውነቴን ይበላኛል...እዬቤ ፊት ሲሆን ግን የራሴን ሰውነት በራሴ አይን እያየሁ ነው የሚመስለኝ።ለምን እንደዛ ሆነ ?ለእኔም ለራሴ ግራ ይገባኛል። ለምሳሌ ልብስ ለእህቶቼ ተገዝቶ ለእኔ ባይገዛ ችግር የለውም..ለእኔ ተገዝቶ ለእሱ ላይገዛ ግን አይችልም።በቃ ያንን ልብስ በምንም አይነት አለብሰውም።እሱም እንደዛው ነው።አንዳንዴ ያው የሙት ልጅ ነው በሚል ስሌትም ከቤተሠቦቹ ቤት ኪራይ የሚገኝ ገንዘብ ስላለ በሚል ስሌትም ብቻ ምክንያን አላውቅም ለእሱ ለብቻው ልብስ ይገዛለታል..እሺ ብሎ ይቀበልና አጣጥፎ ያስቀምጣታል"ለእኔ እስኪገዛልኝ ስድስት ወርም ቢፈጅ አይለብሳትም ።ከዛ በቤተሠብ ሁሉ ተለመደና ለሁለታችንም መግዛት እስኪችሉ ነጥለው መግዛት አቆሙ..
ከእዬቤ ጋር እድሜያችንም ተቀራራቢ በመሆኑ ክፍላችንም አንድ ነው። የምንቀመጠውም አንድ መቀመጫ ላይ ነው።ያው ግን ለትምህርት የምንሰጠው ትኩረት በጣም የተለያየ ነው።እዬቤ ከአንደኛ ክፍል አንስቶ እስከመጨረሻው አንደኛ ወይም ሁለተኛ ነው የሚወጣው..ተሳስቶ እንኳን 3 ተኛ መውጣቱን አላስታውስም ።ብዙ አያጠናም ..ክፍል ውስጥ አስተማሪ የሚያስተምረውን በፅሞና ያዳምጣል..የቤት ስራ ሳይረሳ ይሰራል፤ ፈተና ሲቃረበ ያጠናል በቃ...እኔ ግን ተውኝ "አንድ ቤት እየኖራችሁ አንድ ክፍል እየተማራችሁ አንድ አስተማሪ እያስተማራችሁ ይሄ ሁሉ ልዩነት ምንድነው?"የአባቴ የዘወትር ጥያቄ ነበር
"ቆይ አንድ ክፍል አይደል እንዴ የምትኖሩት? ለምን አብራችሁ አታጠኑም?" አባቴ ይጠይቀዋል
‹‹ጋሼ አብረን ነው የምናጠናው..ግን እሺ አትለኝም..እያጠናን ትተኛለች..ወይም ትረብሻለች"

👍60👏1🤔1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
///
እንደተለመደው ከሳምንት በኃላ ወደሆቴል መጥታ እኔም ስራዬን ስሰራ አሷም ስትዝናን አምሽተን እኩለ ለሊት ላይ ተያይዘን ወደተከራየችው ሆቴል በመግባት ተቃቅፈን ተኝተን እያወራን ነው፡፡እንዴት እንደሆነ አለወቅም ወሬው ደግሞ እንደወትሮው ፍቅር ፍቅር ሚሸት ሳይሆን ኮምጠጥ ያለ ሀገራዊ ጉዳይ ነው..፡፡ዛሬ እንኳን እሷን የሚመጥናትን ጫወታ ልጫወት ብዬ መሰለኝ በገዛ ጥያቄዬ ውስብስብ ወሬ ውስጥ እነንድንገባ መንገዱን የከፈትኩት
‹‹መቼስ ወታደር ነሽ…ለዛውም ባለትልቅ ማአረግ….የሀገሪቱን ችግር ለማከምና ከመከራዋ እንድትወጣ ለማገዝ በደምና በላብ ዋጋ ከፍለሻል…ግን አሁን ስታስቢው መስዋዕትነቴ ባክኗል….ደሜም ያለውጤት ፈሷል ብለሽ ታስቢያለሽ፡፡?››ስል ጠየቅኳት፡፡
እስኪ ምን ሚሉት ጥያቄ ነወ….ይሄንን ጥያቄ አንድን የተከበረች ጄኔራል ስጠይቅ የሀገሪቱ ደህንንት ቢሮ ጆሮ ቢገባ የትኛው ተቃዋሚ አካል ነው አስርጎ ያስገባህ ብሎ ቢያፍነኝ ይፈረድበታል?
እሷ ግን ተረጋግታ መመለስ ጀመረች‹‹ፈፅሞ አላስብም…አርግጥ እኔ እንዲሆን እያሰብኩና እያለምኩ እንደነበረው የተከወነ ነገር ላይኖር ይችላል፡፡ውጤቱ ከግምቴ በጣም ዝቅ ያለ ወይንም ሙሉ በሙሉ ተቃራኒ ሊሆን ይችላል…እንደዛም ነው የሆነው፡፡ግን እኔ ነገሮችን ለማስተካከል በተሰጠኝ ኃላፊነትና ሪሶርስ በአግባቡ በመጠቀም በቀናነት እናም በሙሉ ችሎታዬ ተንቀሳቅሼለሁ ወይ ?ብዬ ነው የምጠይቀው…መልሱ አዎ ከሆነ በቂ ነው፡
ነገሮችን ሁሉ በውጤታቸው ብቻ ከለካህ መጨረሻው ጥሩ አይሆንም… ወደፊትም አያስኬድህም፡፡
‹‹እስቲ አብራሪልኝ››
‹‹ስራዎችን ከመከወንህ በፊት ስለስራው ሞያዊ ጥናት ታርጋለህ፡ ውጤታማ የሚደርግህን እቅድ ትነድፋለህ ፡ከዛ ወደተግባር ትገባለህ…. .በእኔ አረዳድ እቅድ በወረቀት በሰፈረው መሰረት ተግባራዊ የሚሆነው ከ50 ፐርሰንት በታች ነው..ማንኛውም እቅድ ማለቴ ነው..የጦርነት እቅድ ሲሆን ደግሞ የተለየ ይሆናል….ግን ደግሞ እቅድ አስፈላጊና በጥንቃቄ መሰራት የሚገባው ጉዳይ ነው..ቢያንስ ነገሮችን ለመጀመር መነሻ ይሆንሀል፡: በሂደት ለሚያጋጥሙህ እዲስ ክስተቶች የሚሆን የሚሳራ ቅፅበታዊ እቅደም ለማቀድ መነሻ ፍንጭ ይሰጥሀል…በአጠቃላይ ለማለት የፈለኩት እንኳን እንደኛ የተወሳሰበና የተጨመላለቀ የችግር ትብታብ ያለባት ሀገር ይቅርና ባደጉት ሀገሮች የማስፈፀም ብቃት እንኳን ነገሮች እንደሀሳብ አይሄዱም..ምሳሌ አሜሪካ ኢራቅን ሰትወር የስንት ቀን ኦፕሬሽን ብላ ገባች? ስንት አመትስ ፈጀባት…?ራሺያ ዩክሬንን ላይ ለሳምንት ብላ የጀመረችው ጦርነት ምን ያህል ጊዜ ፈጀባት ?
ይሄ የወታደራዊ ፤ አመራሩ ችግር፤የፖለቲካኛው ችግር ፤የቦታው ነባራዊ ሁኔታ..የተፋላሚህ አቅድህን ለማበላሸት የሚነድፈው ሌላ እቅድ…የተፋላሚህ ወዳጆች ተፅዕኖ፤የአንተ ጠላቶች በሁኔታው ለመጠቀም የሚያደርጉት ጥረት፤ ጠላትም ወዳጅም ሳይሉ ከነገሩ ገቢያቸውን ለማደለብ የሚዳክሩ ሚዲያዎች፤ነጋዴዎች፤ ደላላዎች….ምኑ ቅጡ…የአንተ ዕቅድ በእግዚያሄር ካልተዘጋጀ በስተቀር የእንዚህን ሁሉ ተዋናይ ትርምስ ከግምት አስገብቶና በትክክል ተንብዮ የሚሰራ እቅድ ሊያዘጋጅልህ አይችልም…..እና መጀመሪያ ይሆናል ተብሎ ተነገሮህ አንተም ያንን አምነህ ወደጦርነት ትገባለህ..እንዳልከው ላብህም ይንጠባጠባል ፤ ደምህም ይረጫል …አካልህም እየተቦደደሰ ይበራል…..ነፍስህም ልትሰናበት ችላለች…. ውጤቱ ደግሞ ከታሰበው ተቃራኒ ወይንም በጎን የልታሰበ ሽንቁር ከፍተት እየተስገመገመ ወዳልታወቀ መዳረሻ የሚያደርስ ሊሆን ይችላል፡፡
፤የዛን ጊዜ ልትደነግጥ ትችላለህ…ሊከፋህ ይችላል…ግን በምንም አይነት ተስፋ አትቆርጥም…ተስፋ መቆረጥ ከሁሉም ጠባሳዎችህ እንዳታገግም እና ሁለተኛ እድል እንዳሞክር እስከወዲያኛው ነው የሚያደቅህ….ሀገር ደግሞ ቢያንስ ህልውናዋ ማስጠበቅ የምትችለው ሁል ጊዜ ተስፋ በማድረግና ከነመዝረክረኩም ቢሆን ወደፊት በመጎዝ ነው፡፡በምንም አይነት ሁኔታ በሀገርህ ላይ ያለህ ተስፋ በውስጥህ እንዲፈርስ ልትፈቅድ አይገባም፡፡በተለይ በዚህ የኢንፎርሜሽን ዘመን ጦርነት በጣም የማይተነበይ እና የሸረሪት ድር አይነት የተወሳሰበ ሆኗል፡፡
ከሌላ አካል ተልኮ ተሰጥቶት እንደሚጠይቅ እንደ ችኮ ጋዜጠኛ ሙግቴን ቀጠልኩ‹‹ግን የእኛ ሀገር ዋና ችግር ምን ይመስልሻል…?ድህነታችን መሆኑን አውቃለሁ…. ቢሆንም እንደወታደር በሀገሪቱ ፍፅም ሰለም እንዳትሆን ዋናው እንቅፋት ምንድነው?፡፡
‹‹ትክክል ነህ እኮ.. በግራም ዞርክ በቀኝ ለእኛ ሀገር ዋነው ችግራችን ድህነታችን ነው፡፡፡ሚያናጥቀንም ሚያላትመንም እሱ ነው፡፡ግን ከድህታችን በመለስ ዋናው ችግር ምንድነው ካልከኝ ፅንፈኝነት ነው…ፅንፈኝነት ማለት አይነ ልቦናል ጨፍኖ በደመነፍስ ማሰብ ነው፡፡ያ ማለት በውድቅት ለሊት የቤቱን መብራት ሁሉ አጥፍቶ የጠፋብንን መርፌ ለማግኘት የመዳከር ያህል ነው፡፡ቀንቶህ መርፌውን በዳበሳ መጨበጥ ብትችል እንኳን መወጋትህና መድማትህ አይቀርም፡፡
ፅንፈኝነት የራስን ፍላጎት ጥቅምና ስሜት ብቻ መሰረት አድርጎ ብይን መስጠት ለዛም ብይን ደምሳሽና ጨፍላቂ ውሳኔን መውሰድ ማለት ነው፡፡
አክራሪነት በብዙ ዘርፍ አለ....የብሄር አክራሪነት፤ የሀይማኖት አክራሪነት ፤የፆታ አክራሪነት ፤የፖለቲካ አክራሪነት…የሀገር አክራሪነት ወዘተ፡፡ፅንፈኝነት ነገሮችን ከአንድ የተቸነከረ ፖይንት ኦፍ ቪው ብቻ መመልከትና ፍርድ መስጠት ማለት ነው፡፡ወደአንዱ ፅንፍ በጣም ተለጥፈን ስንቆም ከሌላኛው ፅንፍ ያለን ርቀት በጣም ሰፊ ይሆናል…ከእይታችንም ይጠፋል፡፡
ፅንፈኞች መቼም የእኛ ነገር የመጀመሪያው ይሁን…የእኛ ነገር ይሰማ …የእኛ ነገር ይቀመስ ፤ የእኛ ነገር ይበላ….ባይ ናቸው፡፡ማመቻመች የሚባል ነገር ፈፅሞ አልፈጠረባቸውም…. የጋራ በሆነ ነገር ላይ ደግሞ የእኔ ብቻ አይሰራም…፡፡
እና እንደአንድ ወታደር የትኛውንም ሀይማኖት ተከታይ ብትሆን ችግር የለብኝም.፤የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ብትሆን እኔን አይመለከተኝም…አህዳዊ ብትሆንም ፌዴራሊስት ብትሆንም ግድ አይሰጠኝም….ግን ሁሉም ውስጥ ሆነህ ፅንፈኛ ከሆንክ የዛን ጊዜ ችግር አለ..አንዳንድ ሰው አክራሪነት ላይ የተሳሳተ የትርጉም ስህተት ሲፈፅም አያለሁ….አንድ ሰው የራሱን ሀይማኖት ይዞ የሀይማቱን ዶግማዊና ቅኖናዊ ህግጋን ሳያፋለስ በፍፅም መሰጠትና ትኩረት ተግባራዊ በማድረጉ አክራሪ ሀይማተኛ ነው ልንለው እንችላለን…አክራሪነቱ ግን የሌላው ሀይማኖት አማኝ ላይ ድንጋይ እስካልወረወረ እና የሌላውን አማኝ ማምለኪ ቦታ ላጥቃና ላውድም እስካላለ ድረሰ በክፍትም በስህተትም ሊወሰድ አይገባም….፡፡በብሄርም ስትመጣ እንደዛው…አንድ የኦሮሞ ብሄር ተከታይ በኦሮሚኛ ቋንቋ ማውራቱ..በእየእለቱ የኦሮሞ ባላዊ ልብስ መልበሱና ገንፎና፤አንጮቴ እና ወተት የእየለት ምግቡ ማድረጉ በፍፅም ችግር የለውም…..ችግሩ በአካባቢዬ ያለው ስው ሁሉ ከአንጮቴ ውጭ ሌላ ምግብ እንዳይቀምስ ካለና በጆሮዬ ከኦሮምኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ አንዳይሰማ በማለት ከሌላው ብሄር ጋር ባለው መስተጋብር ችግር መፍጠር ከጀመረ ነው፡፡

👍33❤7🔥2🥰2👏2😁1