አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


‹‹እና ምን እያልከኝ ነው››

‹‹አንቺም የተሰጠሸን ህይወት ሙሉ በሙሉ ተቀበይው፤ገዳይ ሆንሽ አስገዳይ….ፃድቅ ሆንሽ ሀጥያተኛ….መጀመሪያ ባለሽበት ሁኔታ እራስሽን ተቀበይ፡እናም ደግሞ ሁሉም ሰው ከውጭ እንደምትመለከቺው እንዳልሆነም እወቂ..ስለዚህ አንቺም እራስሽን እንደምታይው ብቻ አይደለሽም፡፡ ልዩ ማለት ከሺ በላይ በጣም ድንቅ የሆኑ መልካም ምግባሮችና ፀባዬች ያሏት እንዲሁም በመቶ የሚቆጠሩ ትንሽ ሚጎረብጡና መስተካከል ያለባቸው እንቅፋቶች የተጋረጡባት ወኔ ሙሉ እና በኃይል የተሞላች ወጣት ነች፡፡ይሄንን ካወቅሽ ከነዛ መቶ እንቅፋቶች ላይ በየጊዜው የተወሰኑትን እየቀረፍሺ ሺዎች ላይ እየጨመርሽ መሄድ ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ፡፡

እወቂ መቼም መቶውንም እንቅፋት በአንዴ ማስወገድ አትችይም፡፡ በአመት 10ሩን እንኳን ካስወገድሽ በቂና ድንቅ ነዋ.. ዋናው ከአምናው በሆነ ነገር የተሻልሽ ሰው መሆንሽ ነው፡፡ ..እወቂ ሰው እስከሆንሽና በዚህ ምድር ላይ መኖር እስከቀጠልሽ ድረስ ፍፅም ሰው መሆን አትቺይም …ማንም ደግሞ እንደዛ እንድትሆኚ አንቺን የመጠየቅ ሞራል የለውም፡፡እሱም እንደዛው በመቶዎች የሚቆጠሩ የህይወት እንቅፋቶች በውስጡ ተሸክሞ ስለሚዞር ማለቴ ነው፡፡እና እራስሽን የተለየ ችግር እንዳለብሽ አድርገሽ በማሰብ ነፍስሽን ማሰቃየት አቁሚ…..››

በተመስጦ ቀል በባል ካዳመጠችው በኃላ‹‹አመሰግናለሁ..አንተ በጣም ጥሩ ሰው ነህ፡፡››አለችው

"እኔ ደጓች ስላሰደጉኝ ደግ ከመሆን ውጭ ምርጫ የለኝም። ››
"ልክ ለእኔ ደግ እንደሆንከው ማለትነው"
"ማለት?"

‹‹እንዴት ማለት አለ ስሰርቅህ ያዝከኝ ግን አብረኸኝ ተደበደብክ"
"አዎ ጥሩ ምሳሌ አመጣሽ ..ለአንቺ መስረቅ እኔም ከጥፋተኝነት እራሴን ንፁህ ማድረግ አልችልም፡፡ስልክ አያያዜ በጣም እንዝላልና ግዴለሽነቴን የሚያሳብቅ ነበር..አንቺ ለመስረቅ ስትመጪ እኔም ለመሠረቅ ዝግጅ ሆኜ ነበር እየጠበቅኩሽ ያለሁት፡፡ስለዚህ ከደሙ ንፁህ ነኝ ማለት አልችልም...ብደበደብም በገዛ ጥፉቴ ነው።››
‹‹አንተ መንፈሳዊና መልካም ሰው ከሆንክ ክፍትንና ክፉዎችን፤ ሀጥያትንና ሀጥያተኞችን አጥብቀህ ማውገዝና መኮነን አለብህ..አሁን ግን እንደማየው እየተከላከልክላቸው ነው"
"አደበላለቅሽው….እንዳልሽው ክፍትንና ፤ሀጥያትን አጥብቄ አወግዛለሁ። ክፍዎችንና ሀጥያተኞችን ላልሽው ግን አላደርገውም።እነዚህ ክፉና ሀጥያተኛ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው መወገዝና መወቀስ አይደለም፡፡ መፈቀርና መደመጥ ነው የሚፈልጉት። ከልክፍታቸው ለመፈወስ ህክምናው ፍቅር ነው። ውግዘትና ስድብማ እሳት የሆነ ተግባራቸው ላይ ቤንዚል ጨምሮ ማቀጣጠል ማለት ነው።ደግሞ ማንም ከመሬት ተነስቶ በፍቃድ ገዳይም ዘራፊም አይሆንም...ትናንትናውን ያበላሸበት አንድ ሰው ወይም አንድ አጋጣሚ ይኖራል። እያንዳንድ ወንጀለኛ ሰው በግለሠብ ደረጃ ኃላፊነት ቢኖርበትም በየደረጃው ያሳደጉት ወላጆች፤ ያስተማሩት መምህራን ፤አብረውት ያደጉት ጓደኞቹ ፤በውስጡ አቅፎ ያሳደገው ማህበረሰብ..እየተመላለሰ ሲያመልክበት የነበረው የሀይማኖት ተቋም፤ሲያስተዳድረው የነበረ መንግስት እነዚ ሁሉ የየድርሻቸውን ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው።ለአንድ ገዳይ ተገዳዩን ጨምሮ ከላይ የዘረዘርኳቸው በሙሉ ንፁህ አይሉም።›
‹‹እንዴ ተገዳዩ ደግሞ በመገደሉ የተሠራበት ግፍ ሳያንስ የምን ተጠያቂነት መሆን ነው?።
"ታሪኩን ስትመረምሪ በግልፅ ታገኚዎለሽ...የሆነ ነገር አድርጎ ገዳዩን አነሳስቶታል..ወይ ከሚስቱ ጋር ያልሆነ ቀረቤታ ፈጥሯል..ወይ በእምነት ያበደረውን ገንዘብ ክዶታል..ወይ እሱ ቸግሮት ባለበት ወቅት የበሬ ማሰሪያ የሚያህል ሀብል አድርጎ ተፈታትኖታል፡፡
"እንደዚህ እኮ ምታስበው አንተ ብቻ ነህ...››
"አይ ጥቂትም ቢሆኑ ሌሎቹም አሉ...ደግሞም አንቺም ብትሆኚ ከአሁን በኃላ እንደዚህ ከሚያስብት መካከል አንዷ የምትሆኚ ይመስለኛል፡፡"
"አይ አንተ ..እስኪ መጀመሪያ ከተፀናወተኝ ከዚህ ሌብነት ልፈወስ"
"ትፈወሻለሽ አይዞኝ"
"አይ አንተ እንዲህ ቀልድ መሠለህ ..እናቴ ከየአድባራቱ አስመጥታ ያረጨችኝ ፀበል የለም..ህክምናም በጣም ብዙ ሳይካታሪስቶች ሊያክሙኝ ሞክረዋል ..የመስረቅ ረሀቤ ትንሽ ጋብ እንዲልና ፋታ እየወሰድኩ እንዳደርገው ማድረግ ቻሉ እንጂ ከስሩ መንግለው ሊገላግሉኝ አልተቻላቸውም"
"ስለዚህ እራስሽን በራስሽ አክሚያ"
‹‹እሺ እንግዲህ እንዳልክ››
ልዩ ለጊፍቲ ቃል ቤት ከተገናኙ ከሳምንት በኃላ ደወለችላት
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ ማን ልበል?››አለቻት ግራ በተጋባ ድምፅ
‹‹አዲሷ ጓደኛሽ ነኝ፡፡ ››
‹‹ይቅርታ አላወቅኩሽም፡፡››
‹‹በቀደም ቃል ቤት እራሱ ቃል አስተዋውቆን ነበር፡፡››
‹እእእእእ…››የጊፍቲ የንግግር ቃና ደቂቃዎች ውስጥ ተቀየረ
‹‹አወቅሺኝ?››
‹‹አዎ…እሺ ምን ልታዘዝ?››
‹‹አረ አይባልም.. መጀመሪያ ሰላም ነሽ ወይ አይቀድምም?›
‹‹ይቅርታ ሰላም ነሽ?››
‹አለሁልሽ..እንደው ጊዜ ካለሽ ላስቸግርሽ ነበር፡፡››
‹ምንድነው .?ግን አሁን ስራ ቦታ ነኝ፡፡››
‹‹እኮ አውቀያለሁ መስሪያ ቤትሽ አካባቢ ነው ያለሁት.. ከ30 ደቂቃ በኃላ ስትወጪ እንድንገናኝ ፈልጌ ነው፡፡›
ልታገኛት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት በሚያሳብቅ ንግግር‹‹እሺ..ግን ለምን ጉዳይ ነው…?ከስራ በኃላም ሚመቸኝ አይመስለኝም…ሌላ ቀጠሮ ነበረኝ›› አለቻት…፡፡
ይህቺ ሴት እራሷን እያዋደደች ስለሆነ ቀልቧን ልግፈፈው ብላ ስሌት ሰራች‹‹የቃልዬን ምርጫ እኮ ከእኔ በተሻለ አንቺ ስለምታውቂው ብዬ ነው››አለቻት፡፡
‹‹የምን ምርጫ….ምን ማለት ነው››እንደገመተችው ጊፍቲ በደንብ ተነቃቃች….
ልዩም ሙሉ ትኩረቷን እንዳገኘች እርግጠኛ ስትሆን ንግግሯን አራዘመች‹‹አስራ ሁለት ሰዓት ላይ እራት ልጋብዘው ቀጥሬዋለሁ..እና ዝም ብሎ እራት ብቻ ከሚሆን የሆነ ስጦታ ልገዛለት ፈልጌ ነበር…ግራ ስለተጋባሁ በምርጫው ብታግዢኝ ብዬ ነው፡፡››
‹‹አሁን መጣሁ. 5 ደቂቃ ጠብቂኝ››ብላ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ጠረቀመችው፡
እንዳለችውም 5 ደቂቃ እንኳን ሳይሞላ መጠች…ልዩ የመኪናዋን መስታወት ወደታች በማውረድ እጇን ወደላይ በመቀሰር እንድታየት ምልክት ሰጠቻት ..የጨለመ ፊት ይዛ እየተውረገረገች ወደእሷ መጣች..ፈጠን ብላ የገቢናውን በራፍ ከፈተችላት… ገባቸ ና ዘጋችው፡፡
ለሆኑ ደቂቃዎች ዝም እንደተባባልን ተጓዙ.. በመሀል ጊፍቲ እንዳኮረፈች መናገር ጀመረች‹‹ ምን አይነት ዕቃ መግዛት ነው ምትፈልጊው?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ውይ ሳልነግርሽ ተውኩት እኮ››
‹‹ምኑን?›
‹‹ስጦታ ልገዛ ነው ያልኩሽን ነዋ›
‹እየቀለድሺብኝ ነው እንዴ?›


ይቀጥላል
👍10416🥰6😁2🔥1🤔1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
‹‹እና ምን እያልከኝ ነው››
‹‹እንዴ!! እንዴት እንዲህ ትያለሽ.?መጀመሪያ ከቃል ጋር እራት ቀጠሮ ነበረን..አሁን ለአንቺ ከደወልኩልሽ በኃላ ደውሎ ድንገተኛ ጉዳይ ስላጋጠመው ዛሬ እንደማይችል ነግሮኝ ይቅርታ ጠየቀኝ...የእራት ግብዣው አሌለ ደግሞ ስጦታው አያስፈልግም ››የመዋሸት ብቃቷ  ለእሷው ለራሷ አስደነቃት፡፡

‹‹እና መኪናሽ ወስጥ ሳልገባ ለምን እዛው አልነገርሺኝም፡፡››

‹‹ውዴ አረ ዘና በይ..መምጣትሽ ካልቀረ ሻይ ቡና እንባባል ብዬ እኮ ነው ..ያው የቃል ጓደኛ ነሽ ማለት የእኔም ጓደኛ ነሽ፡፡››

ጊፍቲ በጣም ከመናደዶ የተነሳ መከራከሩንም ስላልቻለች ዝም አለች፡፡ቦሌ ካልዲስ ገቡና የሚፈልጉትን አዘው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጡ፡፡

‹‹ከቃል ጋር የረጂም ጊዜ ጓደኛሞች ናችሁ?››ልዩ ነች የጠየቀችው፡፡
‹‹ከልጅነት ጀምሮ አብረን ነበርን…አንድ ጊቢ ውስጥ ነው ያደግነው፡፡››

ልክ ምንም እንደማያውቅ ሰው ‹‹እና ያው ጓደኛ ብቻ ናችሁ አይደል?.››ብላ የሚያበሰጭ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

.ለተወሰኑ ደቂቃዎች ፀጥ አለች‹‹እንዴት እንደህ ልትይ ቻልሽ? ቃል ነው እንዲህ ብሎ የነገረሽ?››
‹‹አረ በፍፅም›አለቻት ደንግጣ…የደነገጠችው ሄዳ ቃልን ብትጠይቀውስ.?ብላ በመስጋት ነው…በዚህ ጉዳይ ከቃል ጋር ብትጣላ  ለእሷ ትልቅ ኪሳራና እፍረት ነው፡፡
‹‹ቃል ጓደኛዬም፤ወንደሜም፤ፍቅረኛዬም ሁለነገሬ ነው››በማለት አንጀቷን ለመበጠስ ሞከረች፡፡

‹‹ምን ያህል ነው የምትፈልጊው?››የሚል ፍጥጥ ያለ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

ጊፍቲ መመለስ ጀመረች‹ቃልን የምፈልገው …እራሴን ከምፈልገው በላይ ነው…ቃል ህልሜ ነው፡፡የልጅነት ህልሜ…ሁለታችንም አንዳችን ከአንዳችን ለረጅም አመት ማለት ከልጅነታችን ጀምሮ ስንደጋገፍና የህይወትን ጨለማ ጎኗንም በመረዳዳት በብርሀኗም አንድ ላይ በመድመቅ ነው እዚህ የደረስነው….፡፡››

ይህቺ ልጅ የዋዛ አይደለችም ››አለች ልዩ..ጥያቄዋን አራዘመች‹‹እና ታገቢዋለሽ ማለት ነዋ?››

‹‹ይሄ ምን ጥርጥር አለው?››

‹‹እሱስ?››

‹‹ነገርኩሽ እኮ…እኛ እስከአሁን የመጣንበትን የሕይወት መንገድ  አብረን ነው የተጓዝነው...ከአሁን በኃላ ያለውን ህይወታችንንም አብረን ከመዝለቅ ውጭ ምንም ምርጫ የለንም፡፡››

‹‹ቃልና አንቺ ግን መች ነው የምትጋቡት?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ እንጃ ማለት.አልተነጋገረችሁበትም..?›
‹‹አይ ተነጋረንበታል…እናማ ሁኔታዎች ሲስተካከሉ እንጋባለን..ደግሞ ምን የሚያጣድፍ ነገር አለ?››

‹‹ቃልን ትወደጂዋለሽ አይደል?.›በሁኔተዋ ተጠራጥራ ጠየቀቻት..

‹‹በጣም እወዳዋለሁ…ባለወደው ከእሱ ጋር ምን አንዘለዘለኝ…. አፈቅረዋለሁ ማለት ታዲያ በኪራይ ቤት እሱን ለማግባት ፍቃደኛ ነኝ እያልኩሽ አይደለም.. በፍፅም እንደዛ አላደርግም….ግን ደግሞ ሌላ ወንድም ማግባት አልፈልግም እስከ ስልሳ አመትም ቢሆን እጠብቀዋለሁ…ምክንያቱም  ቃልን የመሰለ ባል የትም አይገኝም…..አምስት ወንድ እንድ ላይ ተደርበው ቢታሰሩ እሱን አይደርሱበትም፡፡››ብላ አንጀት ሚበጥስ ከረር ያለ መልስ ሰጠቻት፡
‹‹እኮ እኔም  እሱ ነው የገረመኝ….በጎዳና ላይ በተጣለ ዱንኳን ቤትም ቢያገቡት ያዋጣል ብዬ እኮ ነው››ሳታስበው የውስጧን ቀባጠረች፡፡
‹‹ተይ ተይ ህይወት እቃቃ ጫወታ  አይደለችም…ፍቅር እንጀራና ዳቦ መሆን አይችልም…እናንተ የሀብታም ልጆች ፊልምና ህይወት ይምታታባችኋል፡፡አንቺ አሁን ፍቅረኛ አለሽ አይደል?ሰትል እራሷን ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዎ›› አለቻት፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹እሺ አለኝ››
‹‹መች ታገቢዋለሽ..››
‹‹በቅርብ…ከሶስት ወር በኃላ፡፡;;
‹‹ቤት አለው…?››
‹‹አዎ አዲስአባባ እና ሰንዳፋ ላይ መኖሪያ ቤት አለው›
‹‹ሁለት ቤት ማለት ነው?››
‹‹አዎ….››
‹‹እሺ መኪናስ?››
‹‹ምን የቤት ነው የንግድ ?ማለት የካማፓኒያችን ከሆነ ቁጥራቸውን አላውቅም››
‹እሺ የቤትስ?››
‹‹ሶስት መኪኖች አሉት››
‹‹አየሽ ለምን እንደምታገቢው?››
ልዩ ተበሳጨች‹‹እና ለብር ብዬ የማገባው ነው ሚመስልሽ..?››
‹‹እና በጣም ስለምታፈቅሪው ነው…አይመስለኝም? ስለእሱ ስታወሪ አይኖችሽ ላይ የሚነድ የፍቅር እሳት አይታየኝም፡››
‹‹እርግጥ ምን ያህል እንደማፈቅረው አላውቅም….ግን ያ ማለት የማገባው ለገንዘብ ነው ማለት አይደለም…እኔ ከቤተሰቤ በውርስ ማገኘው ሀብት ምን አልባት ከእሱ ይበልጥ እንደሆነ እንጂ አያንስም፡፡››
‹‹አይ ይህቺ አለም…አየሽ ዲታውን ከዲታ ከምታጣብቅ ምን አለበት .ያለውን ከሌለው ብታፋቅር….ለፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልም አሪፍ ነበር.››ስትል ቁምነገሩን ከቀልድ ጋር ደባልቃ ተናገረች፡
‹‹ታዲያ ምን ችግር አለው? ባል አንቀያየራ››አለቻት ልዩ
‹‹አይ አንቺ ምን አለብሽ ?ቀልጂ….››
ልዩ ለመቀለድ ብላ አልነበረም የተናገረችው…ሰው አስቦ ይናገራል ፣እሷ ግን ተናግራ ማሰብ ጀመረች..‹ባል እንቀያየር››ደጋግማ ደጋግማ በእምሮዋ አሰላሰለች… ድንቅ ሀሳብ ነው፡፡
በንግግሯ ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ አልፈለገችም..አዎ ስልሳ አመትም ቢሆን ጠብቃው እንድታገባው ፈፅሞ ልትፈቅድላት አልፈለገችም ፡፡ እልክ ውስጥ ገባች፡፡ጊዜ አንፃራዊ ነው..‹‹እሷ ዕድሜ ልክ አብራው ቆይታለች ማለት ከእኔ በላይ ታፈቅረዋለች ወይም ከእኔ በተሻለ እሱ ላይ መብት አላት ማለት አይደለም …ፍፁም፡፡››ስትል የራሷን ድምዳሜ ሰጠች፡፡
ልክ ጊፍቲ  የህይወት ታሪኳን ለሌላ ሰው ስታወራ በጉልህ የምትጠቅሰውና አይኗ እየበራ ምታወራው ስለቃል እንደሆነ ሁሉ የልዩም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው…
‹‹.ምን አልባት በጣም ወደአካላቱ ለጥፎ አቅፎ ከንፈሮቾን ለሺ ምናምን ጊዜ ስሟቸው ሊሆን ይችላል…ጭኖቾንም ፈልቅቆ ለበርካታ ቀናትና አመታት የሚያቃትት አይነት ወሲብ ፈፅመውና እረክተው ሊሆን ይችላል…ይሄም ቢሆን ግን ከእኔ በላይ ቀርባዋለች ብዬ እንዳስብና እንዳምን አያደርገኝም…፡፡አዎ ..እሱን ማግባት ያለብኝ እኔ ነኝ ፡፡ይሄ የህይወቴ ዋናው ግብ ነው፡፡እኔ እሱን ነጥቃታለሁ፡፡ከዚህች  ልጅ ጋ በዘዴና በጥበብ መደራደር አለብኝ›› ስትል  ወሰነች፡፡
‹‹አዎ ባሌን ወስዳ ባሏን ብትሰጠኝ ሁለታችንም በጣም ደስተኞች እንሆናለን፡፡ አዎ ወንዶቹም የሚከፋቸው አይመስለኝም..አዎ ከዛሬ ጀምሮ ይሄንን ትልቅ አላማ አንግቤያለሁ ማለት ነው.ይሄን ሳላሳካ እንቅልፍ በአይኔ አይዞርም››ብላ በውስጧ ፎከረች፡፡
አዎ ቃልን ለማግኘት ስትል መድህኔን ልትሰጣት ወስናለች… ቃል የጊፍቲ ልጅነት ጓደኛዋና ወደፊት ልታገባው ያሰበችው ቃል ኪዳን የገባላት ፍቅረኛዋ እንደሆነ ሁሉ መድህኔም ለእሷ የልጅነት ጓደኛዋ እና እጮኛዋ ነው…..ነገር ግን አሁን እሷም በማታውቀው ምክንያት ቃልን አምርራ ትፈልገዋለች.... ጊፍቲ ደግሞ  መድሀኔን ባትፈልግም ተዋውቀው ሲለማመዱ ግን ልትፈልገው ትችላለች ብላ አሰበች …በእዛ ላይ ጭማሪ ሀብት ትፈልጋለች ብላ አሰበች…ያንን ደግሞ  ቃል ሊሰጣት አይችልም ..ቢያንስ በቅርብ አመት እንደዛ ማድረግ እንደማይችል በማያሻማ ቃል በራሱ አንደበት ነግሯታል.‹‹.ብንቀያየርስ..?ሁሉ ነገር ፐርፌክት ይሆናል፡፡›› ደመደመች፡፡
👍7210🎉4😁3👏2
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ሰዓቱ 11.10 ነው።22 አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላለች።ብቻዋን ነው ያለችው...ስልኳን አወጣችና ደወለች።
‹‹ሀይ ቃልዬ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁ ልዩ ደህና ነሽ?››
‹‹አለሁ ...ከስራ አልወጣህም እንዴ?››
‹‹ወጥቼያለሁ ..መገናኛ ነኝ።››
"ለምን መክሰስ አልጋብዝህም 22 ነው ያለሁት"
"ደስ ይለኝ ነበር.. ግን አሁን ጊፍቲ ደውላ  ሰፈር እየጠበቅኩህ ነው ስላለቺኝ ወደእዛው ልሄድ ነው"እንደዛ ያላት አውቆ ነው…ልዩ እንገናኝ ካለችው ጊፍቲንም ይዟት ሊሄድ ስለፈለገ ነው…
"ሰፈር ማለት አንተ ቤት ?"
‹‹አዎ"
‹‹ለምን ይዘሀት አትመጣም..እንደውም አሪፍ ነው?"
አንዳሰበው ስለሆነለት ፈገግ አለ"ልጠይቃትና መልሼ ልደውልልሽ"

"እሺ ቃልዬ...እዛው ቁጭ ብዬ ጠብቃለሁ"አለችውና ስልኩ ተዘጋ። ከጨጓራዋ አካባቢ የተነሳ ቃጠሎ  ጉሮሮዋ ድረስ ሲሰማት ታወቀት፡፡

ቃል የልዩን ስልክ እንደዘጋ ወደ ጊፍቲ ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ ቃለዬ..፡፡››
‹‹አለሁልሽ ጊፍቲ.ላግኝሽ?››
‹‹ደስ ይለኛል..መክሰስ ልትጋብዘኝ ነው ወይስ እራት?››
‹‹አይ መክስ ነው.. ግን ጋባዡ እኔ አይደለሁም.›
‹‹ችግር የለውም እኔ ጋብዝሀለው››
‹‹አይ ጋባዥ አለን›
‹‹ማን?››
ልዩ ደውላልኝ ነበረ ..ልጋብዛችሁ ስላልች ነው የደወልኩልሽ››
ቅሬታዋን መደበቅ አልቻለችም‹‹ቃል ግን እሷ ልጅ…››አንጠልጥላ ተወችው፡፡
‹‹እሷ ልጅ ምን…?››
‹‹እኔ እንጃ ነገረ ስራዋ አያምረኝም…ሌላ አላማ ያላት ይመስለኛል››
እንዳልገባው ሆነ‹ሌላ አላማ ስትይ..?››
‹‹ያው ማለቴ ምትወድህ ይመስለኛል..››
ደስ አለው…..አዎ ቅናት እየጀመራት ነው ሲል አሰበ..‹‹ብትወደኝ ምን ችግር አለው? ጓደኛዬ አይደለች..››
‹‹ቃል ደግሞ… እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም.ምታፈቅርህ ይመስለኛል.ደግሞ ይመስለኛል አይደለም እርግጠኛ ነኝ…››

‹‹አረ ተይ .እኔ ምንም እንደዛ አይነት ስሜት አላየሁባትም.ደግሞ ፍቅረኛዬ እንደሆንሽ ነግሬታለሁ እኮ››
ቢሆንም ተጠንቀቃት.ለማንኛውም የት ነህ ልምጣ.››ያለበትን ቦታ ነገራትና በፈግታ ስልኩን ዘግቶ ለልዩ እንደሚመጡ ለመናገር ደወለላት፡፡

"ይህቺ ጊፋቲ የምትባል ሴት እንዴት ላስወግዳት?"ልዩ እራሷን ጠየቀች... ...ስልኳ ተንጫረረ ..ቃል ነው.. ቀና መልስ እንዲመልስላት በውስጧ እየፀለየች አነሳችው፡፡
"እሺ ቃል?"
"15 20 ደቂቃ እናስጠብቅሻለን።
"ችግር የለውም አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቃችኋለው"አለችና በደስታ ያለችበትን ካፌ ስም ነግራቸው ስልኳን ዘጋችው፡፡

በራሷ ሁኔታ  መገረም ጀመረች"ወይ ጉዴ.. አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቃችኃለው"ስል አሁን መድህኔ ቢሰማ ጭንቅላቱን ይዞ ነው የሚጮኸው...›አለች እንዲህ ልትል የቻለችበት ምክንያት  5 ደቂቃ አረፈድክ ብላ ብዙ ቀን ጮኸበታለች...አስር ደቂቃ አርፍዶ ቀጠሮውን ሰርዛ ጥላው የሄደችበትም ቀናቶች ጥቂት አይደሉም።  

እንዳሉትም ከ20 ደቂቃ በኃላ እጅ ለእጅ ተያይዘው ፊቷ ተከሰቱ፡..መጀመሪያ ልክ እንደረጅም ጊዜ የልብ ጓደኛዋ እሷ ላይ ተጠመጠመችባት ..አገላብጣ ጉንጮቾን ሳመቻት...ጊፍቲ ያልጠበቀችው አይነት አቀባበል ስለሆነ  ግር እንዳላት    ከሁኔታዎ ያስታውቃል...እሷ እራሷ ለምን እንደዛ ኦቨር አክት እንዳደረገች አልገባትም ‹‹...ምን አልባት የይሁዳን መሳም ይሆናል የሳምኳት..››ስትል እራሷን ታዘበች፡፡.ቃልን ከእሷ መለስ ባለ  ሰላምታ  ሰላም አለችውና ሁለቱም ከፊት ለፊቷ ወንበር ስበው ሊቀመጡ ሲሉ‹‹..አይ ቆይ እንውጣ"አለቻቸው፡፡

"ምነው ታሳፍሪኛለሽ ..መክሰስ ትጋብዘናለች ብዬ እኮ ነው ይዤት የመጣሁት..መክሰሱ ቢቀር ቢያንስ ሻይ ጋብዢን እንጂ"ሲል ቀለደ

"አይ የመክሰሱን ሰዓትማ አሳለፍችሁት  አሁን የእራት ሰዓት ነው...እራት የሚገኝበት ቤት እንሂድ.."

‹‹እሱ የተሻለና የተቀደሰ ሀሳብ ነው"አለች ጊፍቲ ...

ተያይዘው ወጡና  መኪናዋ ውስጥ ገቡ… ወደ ዪሆሚያ ክትፎ ቤት ይዛቸው ሄደች ...እዛ ገብተው እስፔሻል ክትፎቸውን አዘው ቀላል ጫወታዎችን እየተጫወቱ ..በልተው ሲያጠናቅቁ አንድ ሰዓት ከሩብ  ሆኖ ነበር። ሂሳብ ልትከፍል ስትጠይቅ ተከፍሏል አሏት...ልቆጣጠረው የማትችለው ንዴት ተናነቃት፡፡..

‹‹ማን ነው የከፈለው ...?››ፊት ለፊቷ ያሉት ቃልና ጊፍቲ ላይ አፈጠጠችባቸው።ሁለቱም ደንግጠው እርስ በርስ ተያዩ   ..."አረ ተረጋጊ እኛ አልከፈልንም"አለት ቃል።
"ማን ነው የከፈለው?"አስተናጋጅን ጠርታ  ጠየቀችው፡፡

"ጋሽ መድህኔ ነው"

ተረጋጋች"እሱ ደግሞ ከእዚህ ቤት አይጠፍም" ስትል በውስጧ አልጎመጎመች፡

"መድህኔ ማን ነው?"ብላ ጠየቀቻት

‹‹ እስቲ አሁን ሆነ ብላ እኔን ለማሳቀቅ ካልሆነ የመድህኔ ማንነት ምን ይረባታል..? በውስጧ ነው ምታወራው…ቀና ብላ ቃልን ስታየው እሱም የመድህኔን ማንነት ለማወቅ የጓጓ መሆኑን በሚያሳብቅ  አስተያየት ነው እያየት ያለው..ለተጠየቀችው ጥያቄ መልስ ከመመለስ ውጭ ሌላ ምርጫ እንደሌላት ግልፅ ሆነላት፡፡ምን ብላ ትመልስ…ግራ ገባት" መድህኔ ጓደኛዬ...ማለቴ ፍቅረኛዬ ነው"አለች፡፡

‹‹የት አለ አስተዋውቂና አረ ጥሪው"ጊፍቲ አሽቃበጠች….፡፡

ልዩ አሁንም የሆነ ነገር ለማድረግ ከአባቱ ፍቃድ እንደሚፈልግ ህፃን በቆረጣ ቃልን አየችው፡፡

ቃልም ልክ ከዚህ በፊት መድሀኒ የተባለወን ስም እንዳልሰማ በማስመሰል "አዎ ጥሪውና እናመስግነው...በዛውም እንተዋወቀዋለን"አላት

"ደወለችለት"

"አንተ የት ነህ?"

"ውስጥ ነኝ ..እጄን እየታጠብኩ"

‹‹ታዲያ ሰላም አትለንም እንዴ?"

‹‹መጣሁ"ከ3 ደቂቃ በኃላ መድህኔ እንደወትሮ ዝንጥ ብሎ በሱፍ እንደታነቀ ፊት ለፊታችን ገጭ አለ...

‹‹ተዋወቁት መድህኔ ማለት እሱ ነው"በየተራ እየጨበጠ ተዋወቃቸው..

"ስለተዋወቅኩህ ደስ ብሎኛል...ልዩ ግን ይሄን የመሰለ ሸበላ ባል እንዳለሽ ለምን እስከዛሬ ደበቅሽኝ?"አለቻት ልዩ ተሸማቀች፡፡ የጊፍቲን ንግግር ለሚሰማ ሰው የሁለቱ ትውውቅና የጓደኝነት ታሪክ አመታትን ያስቆጠረ  ነው ሚመስለው? ልዩ ከውስጧ እየታገለች ዝም አለች

..ቃል ‹‹ቁጭ በላ›› አለው ቦታ እያመቻቸለት

"ቆይ ጓደኞቼን ተሠናብቼ ልምጣ ››አለ

ልዩ ግን መድሀኔ ተመልሶ እንዲመጣና እንዲቀላቀላቸው  ስላልፈለገች..."አይ ለምን እኛም እኮ ልንወጣ ነው"አለችው፡

"እኮ 2 ደቂቃ ብቻ ጠብቁኝና አብረን እንወጣለን ..እንዴ ክትፎ በልቶ ደግሞ አንድ ሁለት ሳይባል ቢገባ ጥሩ አይደለም...እራት እኔ አይደል የጋበዝኮችሁ አንቺና ጓደኞችሽ ደግሞ መጠጥ ትጋብዙኛላችሁ ...››ብሎ መልስ ሳይጠብቅ  ዞሮ ሄደ...ሳታስበው እንደውም ጥሩ ሀሳብ ነው..

ወደእነ ቃል ዞራ "ሰዎች እንግዲህ ቻሉት.. መድህኔ ካለ አለ ነው "አለች

ጊፍቲ"እንዲህ አይነት ድንገተኛ ግብዣ ተገኝቶ ነው...ጭፈራ ቤት ብንሄድ ደግሞ እንዴት ደስ ይለኛል መሰለሽ" ስትል ተቅለብልባ መለሰችላት..ቃል ዞር ብሎ አያትና"በቃ አንቺና ጭፈራ መች ነው የምትለያዩት"አለ፡፡

"ጭፈራ ትወጂያለሽ እንዴ?"ልዩ ነች ጠያቂዋ፡

"አትጠይቂኝ… ጭፈራ ከመውደዴ የተነሳ አንድ አመት ዲጄ ሆኜ ሰርቼያለሁ... "

‹‹አንግዲያው ከመድህኔ ጋር በጠም ትጣጣማለችሁ ማለት ነው›ሥትል ከኃላዋ መድህኔ መጣና በምንድነው የምንጣጣመው? ››ሲል ያልተዘጋጀችበትን ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡…

‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና  ተያይዘን ወጡ ...

ይቀጥላል
👍142🥰145🤔3😱2👏1😁1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና ተያይዘን ወጡ ...

‹‹እሺ ቦታ ትመርጣላችሁ ወይስ እኔ ልምረጥ?››መድህኔ ነው ወደ መኪና ከመግባታቸው በፊት የጠየቀው፡፡

"ቦታውን አንተ ምረጥ ..ግን ጭፈራ ቤት መሆን አለበት"አለችው ልዩ፡

"አሪፍ ነዋ"አለ ፊቱ በርቶ..ከዛ ወደ መኪናው መራመድ ጀመረ...ተከተሉኝ፡፡

እስከ ለሊቱ ሰባት ሰዓት ቀወጡት ..በዋነኝነት ተዋናዬቹ ሶስቱ ነበሩ፡፡ ከመሀከላቸው ቃል መጠጥ አይጠጣም .... ውሀ ይዞ እነሱን መከታተል ነበር ዋና ስራው፡፡ሲጨፍሩ ያየቸዋል... ሲንገዳገዱ ይደግፋቸዋል... ፡፡ እነሱም በእሱ ተማምነን ዘና ብለን እየቀወጡ ነው ምሽቱን በፈንጠዝያ ያሳለፉት።ለነገሩ ልዩም በአብዛኛው ከእሱ ተለጥፋ ነው ያመሸችው፡፡

‹‹ሚስትህ ባሌን እኳ አንሳፋፈችው››አለችው፡፡

‹‹ምነው ቀናሽ እንዴ?››

‹‹ለምን አልቀና እኔ እንደአንተ ደመበራድ አይደለሁም››

እና ምን ይሻላል

‹‹ያው ምን ይሻላል .መጨረሻቸውን ማለት ነው››

እስከወዲያኛው ብትቀማሽስ››

ትሞክረዋ›

<<ምን ታደርጊያለሽ››
እሾክን በሾክ ነዋ…እሷ እኮ ባል አላት›› አለችው…ፉከራዋ አሳቀው፡፡

መድህኔና ጊፍቲ ስለእነሱ ሹክሹክታ ደንታም ሳይሰጣቸው በጭፈራቸው ተመስጠዋል፡፡ ሁለቱም አደገኛ ጨፋሪዎች ናቸው ...ደግሞ በሚገርም ጥምረት ተግባብተው በአየር ላይ የመብረር ያህል አቅላቸውን ስተው ተጣብቀው ሲደንሱ ላያቸወ ከአየን ያውጣችው ያስብላሉ ፡፡ አሁን እዚህ ጭፈራ ቤት ያሉ ሁሉ ልዩና ቃልን ቀዝቃዛ ፍቅረኞች ….ጊፍቲና መድህኔ ደግሞ የበለጡ የሚያምሩና የሚግባብ የጋለ ፍቅር ላይ ያሉ ጥንዶች እንደሆኑ ምሎ ሊናገር ይችላል። ‹‹ግን በትክክልም መሆን ያለበት እንደዚህ ነው።አዎ መድህኔ እኮ በጣም ቆንጆ ፤ዘናጭ፤ ሀብታምና ጥሩ ስነምግባር ያለው ሰው ነው...እና ጊፍቲ መድህኔ ፍቅረኛዋ ቢሆን በጣም ጥሩና የተመቸ ኑሮ ትኖራለች...አዎ እሱን ብታገኝ በጣም እድለኛ ነች።›ስትል አብሰለሰልች፡፡

ግን መድህኔ እንደምትይው ሁሉን የሚያሟላ ተመራጭ ወንድ ከሆነ አንቺስ ለምን እሱን ለቀሽ ቃልን ተመኘሽ?ብሎ የሚጠይቃት ሰው ካለ ምን አይነት መልስ ልትመልስ እንደምትችል አታውቅም..

.ስለቃል የሚሰማት ስሜት ጥልቅና መንፈሳዊ ነው"..ልክ የመድህኔን ኳሊቲ በቀላሉ ዘርዝራ እንደተናገረችው የቃልን እንደዛ ማድረግ አትችልም...እና ደግሞ የቃልን ጉዳይ ባይሆንባት በማንም ሌላ ወንድ መድህኔን መቀየር አትፈልግም ነበር...እና ደግሞ ማንም ሌላ ሴት መድህኔን ልትቀማት ሞክራ ቢሆን ኖሮ አንገቷን ቀንጥሳ ነበር የምትጥላት።ስለ ቃል ሚሰማት ስሜት ይሄን ያህል ውስብስብ ነው

ሰባት ሰዓት ስላለፈ እዛው ሲጨፍሩበት ካመሹበት ሆቴል አንድ ባለ ሁለት አላጋ ክፍል ተያዘና እየተጓተቱ ሄድን ፡፡እውነት ለመናገር ብክት እስኪሉ ሰክረዋል.... መኝታ ቤት እንደገቡ ብርድ ልብስ ገልጦ ከውስጥ የገባ የለም...ልዩና መድህኔ አንድ አልጋ ላይ ቃልና ጊፍቲ አንድ ላይ ተመሳቅለው ተኙ። ልዩ ከጎኖ እጮኛዋን መድህኔ ሰውነቷ ላይ ተለጠፋ የተኛች ቢሆንም ነፍሷ ግን ቃል እቅፍ ውስጥ ነበር ተሸጉጣ ያደረችው።
///
ጥዋት አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ከአንቅልፋቸው ተነስተው ሁሉም ለብሰው ያደሩትን የተጨማዳደ ልበሳቸውን በተቻለ መጠን አስተካከሉና ወደሬስቶራንት ጎራ ብለው ፤አፒታይታቸው በፈቀደላቸው መጠን ቁርስ በልተው በማጠናቅ ሆቴሉን ለቀው ለመውጣት ዝግጁ ሆኑ ከዛ ልዩ ጊፍቲን ቢሮዋ ድረሰ ሸኝታት ወደትምህርት ቤት እንድትሄድ በተመሳሳይ ደግሞ መድህኔ ቃልን መስሪያ ቤቱ ድረስ አድርሶት ወደስራው ሊሄድ ድልድል አወጡ፡፡ልዩ እንዲሆን የፈለገችው ተቃራኒውን ነበር...እሷ ቃልን እንድትሸኘው መድህኔ ደግሞ ይህቺን መዥገር ነገር እንዲያደርሳት… በዛውም ሁለቱ ስለማታው የሰመረ የዳንስ ጥምረታቸው እያወሩና ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ እንዲሄዱ ፈልጋ ነበር ….ግን እንዴት ብላ ተቃውሞ ታቅርብ …?ሳትወድ በግድ በድልድሉ ተስማማችና ደስተኛ እንደሆነች ለማስመሰል እየጣረች ጊፍቲን አሳፍራ ወደቢሮዋ ጉዞ ጀመረች…ለረጂም ደቂቃ ምንም አልተነጋገሩም…..ጊፍቲ ነበረች ከዝምታዋ ያነቃቻኝ፡፡
‹‹ምነው እኔን ጥለሽ ጭልጥ አልሽ .?››
ድንገት አፏ ላይ የመጣላትን መልስ መለሰችላት‹‹ስለማታው አስደሳች ምሽት እያሰብኩ ነበር› …እንደዛ ያለችው. እውነት ስላለችው ነገር እያሰበችበት ስለነበር ሳይሆን ሰለማታው ቆይታቸው ምን እንደተሰማት ለመገምገም እንዲረዳት ነው፡፡
‹‹ውይ ብታይ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል...እንዲህ አይነት ፍንጥዝጥዝ ያለ ምሽት ካሳልፍኩ ረጂም ጊዜ ሆኖኝ ነበር.በጣም አመሰግናለሁ›› አለች ጊፍቲ…
ልዩም‹‹አሀ አንዳሰብኩት በጣም ደስተኛ ነበረች ማለት ነው?››ስትል በውስጧ አሰበቸና ይበልጥ ዝርዝሩን ለመረዳት ንግግሯን ቀጠለች ‹‹ደግሞ በጣም ደናሽ ነሽ›ስትል የአድናቆት ቃል ሰነዘረች፡፡
‹‹አዎ ዳንስና ጭፈራ በጣም ወዳለሁ..ግን ባልሽን ጫፍ ላይ አልደርስም…በስመአብ አጥንት ያለው እኮ አይመስልም››
ጊፍቲ በአንድ ቀን ቆይታ ለመድሀኔ ያደረባት አድናቆቶ ካሰበችው በላይ የተጋነነ ሆኖ ነው ያገኘችው…እርግጥ መድሀኔ ሁሉም የሚያወራለት ጨፋሪ እንደሆነ እራሷም ልዩ ታውቃለች…ጊፍቲ በምታወራለት ልክ ግን ሌላ ሰው ሲያደንቀው ሰምታ አታውቅም..እሷ ያው እንደቃል የቀዘቀዘች ባትሆንም ለጭፈራ ያን ያህል ስለሆነች በእሷ ልክ የመድሀኔን ችሎታ ባይታያት አይፈረድባትም፡ስለዚህ ይሄ መደነቋ ሳይበርድ ልትጠቀምበት ይገባል ብላ አሰበች…በጣም ፈጣን የሆነ እቅድ በእምሮዋ ተሰነቀረ፡፡
‹‹ውይ ይቅርታ…አንድ ነገር እያሰብኩ ነበር…ከመድህኔ ጋር ሳምንት ኩሪፍቱ ለመሄድ ቀጠሮ ነበረን፤ በእኛ እስፖንሰርነት ለምን አንቺና ቃል አትቀላቀሉንም››
ከተማ ወጥቶ የመዝናናት ምንም አይነት ዕቅድ የላቸውም ….ግን እሷ ከተስማማች መድህኔን ከከተማ ወጥቶ መዝናናት እንደምትፈልግ መናገር ብቻ ነው የሚጠበቅባት….ምንም አይነት ወሳኝ የስራ ቃጠሮ ይኑረው ወይም ሌላ ፕሮግራም ሁሉንም ጣጥሎ ፍላጎቷን እንደሚያሞላላት እርግጠኛ ነች…ለዛ ነው በልቧ ሙሉነት የግብዣውን ሀሳብ ያቀረበችላት፡፡
‹‹ወይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…?ግን ቃል የሚመቸው አይመስለኝም….መስሪያ ቤቱ ለአምስት ቀን ፊልድ ክፍለሀገር ሊለከው ነው…ነገ ክፍለሀገር ይሄዳል..››አለቻት፡፡
ልዩ በጊፍቲ መልስ ደስ አለት ፡፡ደስ ያለት ለአምስት ቀን ሙሉ ቃልን ላታየው ባለመቻሏ አይደለም…ግን በጉዞችን የቃል አለመኖር ጥሩ ሆኖ ነው ያገኘችሁት… ጊፍቲን ከመድህኔ ጋር ይበልጥ እንዲቀራረብ ለማድረግ አሪፍ እድል ይሆናል ብላ ስላሰበች ነው፡፡
‹‹ታዲያ ለምን አንቺ አትቀላቀይንም ?..በሌላ ዙር ደግሞ ቃልን ጨምረን ተሟልተን እንሄዳለን››
‹‹ተይ ባክሽ..ብቻችሁን ብታሳልፉ ይሻላል?፡፡››መግደርደር መሆኑን በደንብ በሚያሳብቅ ፈራ ተባ ባለ ንግግር መለሰችላት፡
👍845🔥2😱2
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

በእቅዷ መሰረት ኩሪፍቱ ይገኛሉ….ትናንትና ከመሸ ነው የገቡት፡፡ከጥዋቱ ሁለተ ሰዓት አካባቢ ሆኗል..መኝታውን ለቆ ተነስቶ ክፍል ውስጥ ሲንጎራደድ ከጀመረ 30 ደቂቃ ያህል አልፎታል አንዴ መታጠቢያ ቤት ይገባል…አንዴ ወደበረንዳ ይወጣል…እኔ እየሰማው ቢሆንም አንቅልፍ ውስጥ እንዳለ ሰው አድፍጣ ዝም….መታጠቢያ ቤት ሲገባ ፈጠን ብላ ተነሳችና ከቦርሳዋ ውስጥ መከታተያ ካሜራዋን በማውጣት ወንበር ላይ የተንጠለጠለው ጃኬቱ ላይ አንዳይታይ አድርጋ ኮሌታው አካባቢ አጣበቀችውና ቶሎ ብላ ወደመኝታዋ ተመለሰች …በስተመጨረሻ ትግስት አጥቶ ,..ፈራ ተባ እያለው ወደአልጋው ቀረበና ትከሻዋን ይዞ እየነቀቃት…..

‹‹ፍቅር ተኝተሸ ቀረሸ እኮ …በጣም እርቦኛል..ተነሽ ቁርስ እንብላ››አላት
‹‹ተወኝ በናትህ እንቅልፌን አልጠገብኩም…ጊፍቲን ቀስቅሳትና አብራችሁ ብሉ››
‹‹ተይ እንጂ ፍቅር..››
‹‹እየረበሽከኝ አኮ ነው..በፈጣሪ ተወኝ››ተነጫነጨችበት፡፡
‹‹እሺ.ስትነሺ  ተቀላቀይን›› ብሎ ዘረጥ ዘረጥ እያለ ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበሩ መራመድ ጀመረ…ፍፁም ንቁ ሁና ከአንገቷ ቀና አለችና..

‹‹እንዴ?››አለችው፡፡

በሁኔታዋ ግራ በመጋባት‹‹ምነው ልጠብቅሽ ?ትመጪያለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አይ አልመጣም ግን የውጩን ቅዝቃዜ አታየውም እንዴ…?››

‹‹እና ምን ?

ተኝተን እንዋል?››

ምን ለማለት እንደፈለገች አልተገለፀለትም፡፡

‹‹አላልኩም..በኃላ ኩሪፍቱ ወስደሽ ብርድ አስመታሺኝ እያልክ ስትወቅሰኝ እንዳትከርም….ጃኬትህን ለብሰህ ውጣ››

‹‹አረ ተይ… እንዲህ ተመችቶኛል››

‹‹አይሆን …ነገርኩህ እኮ….››

‹‹አንቺ ደግሞ በሚሆነውማ በማይሆነውም  መጨነቅ ታበዢዋለሽ…እኔ እኮ እስፖርተኛ ነኝ የምን በርድ ነው››እያለ በማጉረምረም ወደኃላ ተመልሶ ጃኬቱን ከተንጠለጠለበት ወንበር በማንሳት እየለበሰ ወጥቶ ሄደ…ፈገግ አለች…‹‹አይ ወንዶች ነገረ ሰራቸው  እኮ የህፃን ነው..በቀላሉ የሚታለሉ ገራገር ፍጥሮች… ሲመጣባቸውም እንደዛው ደንባራ አውሬዎች ናቸው…›አለችና …ከተኛችበት ተስፈንጥራ በመነሳት ክፍሉን ከውስጥ ቆለፈችው…ከዛ ላፕቶፖን አወጣችና ከፈተችው.. በገዛ እጮኛዋ  ደረት ላይ የሰካችውን ካሜራ ጋር የሚየገናኝውን አፕ ቁልፍ አበራችው…በዛን ሰከንድ አዲስአባ ቤቱ አልጋ ላይ ተኝቶ የሚገኘው  የቃል ስልክ ድምፅ አሰማ …ፈጥኖ ተነሳና ልክ ልዩ እንዳደረገችው ላፕቶፑን አነሳና አበራ…ከፈተውና ልዩ የምታየውን ማየት ጀመረ….
አዎ መድህኒ እየሄደ ነው..ጊፍቲ የተኛችበት መኝታ ክፍል በረንዳ ላይ እየወጣ ነው..አንኳኳ፡፡በራፍ ተከፈተና ጊፍቲ ከውስጥ ወጣች…ለባብሳና ሜካፖን ተቀባብታ ዝንጥ ብላለች…
‹‹እንዲህ ነው ንቁ ሴት..››አለ መድህኔ
እንደመሽኮርም አለችና‹ያው ለስራ ለሊት አይደለ ተነስቼ ምዘጋጀው ልምድ ሆኖብኝ ነው››

‹‹አይ በጣም ጥሩ ነው…በይ ወደ ቁርስ እንሂድ››

‹‹ልዩስ?››

‹‹እሷ እንቅልፍ ይበልጥብኛል ብላ እምቢ አለች›

በራፉን እየቆለፈች‹‹ምነው ማታ አምሽታችሁ ነበር እንዴ?››አለችው

‹‹ማለት? ጎድተሀታል ወይ እያልሺኝ ነው?›ሲል ጥያቄዋን በሌላ ጥያቄ መለሰላት፡፡

ፊቷ ቀላ..‹እረ እኔ…ማለቴ..›ተንተባተበች፡፡

‹‹ግድ የለም ስቀልድ ነው ..እውነታው ግን ልዩ እንዲህ ነች…አንዳንዴ ቅምጥል የሀብታም ልጅ  መሆን አጎጉል ያደርግሻል…›ወደቁርስ እየሄዱ ነው ልዩን የሚያሟት፡፡

ጥያቄ አስመስላ በውስጡ ግን አድናቆት እና ልብ ሚያሞቅ ቃል ጨምራበት፡፡‹‹አንተም እኮ የሀብታም ልጅ መሰልከኝ…ግን ይሄው   በጥዋት ንቁ ሆነህ ተነስተሀል›› አለችው….

‹‹አይ…የእኔ ስሙ ብቻ ነው…አባቴ እንዲህ የዋዛ ሰው መስሎሻል…እቤት ውስጥ ከ12 ሰዓት በኃላ የአንድ አመት ህፃን እራሱ አይተኛም…እያንዳንዱ የቤቱ ልጅ የየራሱ የስራ ድርሻ አለው….አልጋችንን እናነጥፋለን….አትክልት ዉሀ እናጠጣለን…ግቢ እንጠርጋለን…ከዛ በኃላ ነው ልብሳችንን ቀይረን ቁርሳችንን በልተን ወደ ትምህርት ቤት የምንሄደው….ከዛም ስንመለሰ ተመሳሳይ የተግተለተለ ስራ ይጠብቀናል…. የሚገርመው ደግሞ ይሄን ሁሉ ስራ የምንሰራው እኮ መአት ሰራተኞችና የደረሱ የዘመድ ልጆች ጭምር እቤት ውስጥ እያሉ ነው››

‹‹እና አሁን አንደዛ በመሆኑ እያማረርክ እንዳይሆን?››

‹‹አይ ሙሉ በሙሉ እያማራርኩ አይደለም...የእሱ አስተዳደግ አሁን ስራ ወዳድና ውጤታማ እንድሆነ አደርጎኛል….ግን ደግሞ ልጅነቴን ልክ እንደልጅ ሆኜ አጣጥሜ ተጫውቼ ስላላደኩ አሁንም የሆነ ከፍት ይሰማኛል…መኪና እየነዳሁ በሆነ መንደር ውስጥ በማልፍበት ወቅት  ልጆች መንገድ ዳር ተሰብስበው ብይ ሲጫወቱ ካየሁ ወርደህ አብርህችው ተጫወት የሚል ስሜት ይቀስፈኛል..ሌላው ይቀር ጭቃ እያቦኩ ግድብ የሚገድቡ ህፃናት ሳይ ውሰጤ ይቀናል እና አሁንም ያላደገ ህፃን በውስጤ ያለ ይመስለኛል፡፡››

‹‹እና አንተ ከልዩ ምትወልዳቸውን ልጆች እንዴት ለማሳደግ አሰብክ?››ብላ ጠየቀችው፡
በዚህ ጥያቄ ልዩን በጣም ነው ያስገረማት‹‹እኔ እንኳን አስቤ የማላውቀውን  ገራሚ ጥያቄ ነው›በማት መልሱን ልትሰማ ቋመጠች…ይህ መገረም አዲስአባ ያለው ቃልም ተጋብቶበታል፡፡
ጊፍቲና መድሀኔ ይሄን በሚያወሩበት ጊዜ ፊት ለፊት ተቀምጠው የሚፈለጉትን ቁርስ ከተደረደረው ቢፌ ላይ ወስደው ቁርስ እየተመገብ ነው፡፡

‹‹ልጅቷ ግን ፀሀፊ ሳትሆን ጋዤጠኛ ነው የምትመስለው፡፡ምን ብሎ ይመስልስላት ይሆን›አለች ልዩ…መድህኔ  የጎረሰውን አላምጦ ማውራት እስኪጀምር በጉጉት ትጠብቅ ነበር..
‹‹እንደእኔም ወግ አጥባቂ አስተዳደግ ሳይሆን እንደልዩም መረን የለቀቀ ስንፍና የተጫጫነው ሳይሆን በመካከል ባላ ዘመናዊ አስተዳደግ  እንዲያድጉልኝ ነው ምፈልገው››ሲል መለሰላት፡፡
ከትከት ብላ ሳቀች‹‹መረን የለቀቀ›› ስላለኝ የተደሰተች ይመስላል፡፡

‹‹ግን ስንት ልጅ ምትውልደ ይምስልሀል?›

‹‹እኔማ ስድስት ልጆች ብንወልድ ደስ ይለኛል…ግን ከማን?››
በዚህ መልሱ ፊት ለፊት ተቀምጣ ምታዳምጠው ጊፍቲ ብቻም ሳትሆን ከጀርባ ሆነው በሚስጠጥር የሚከታተሎቸው ልዩና ቃልም ጭምር ናቸው የደነገጡት

‹‹እንዴት ከማ…?ከሚስትህ ነዋ..›ጊፍቲ በገረሜታ ተሞልታ ጠየቀችው፡

‹‹ከሚስትህ ማለት ከልዩ?››
‹‹እንዴ ግራ አጋባሀኝ እኮ…ሌላ ሚስት አለህ እንዴ?››
እሱማ የለኝም...ልዩን ሳስባት ግን አንድ ልጅ እንኳን በስርአቱ አምጣ መውለድ የምትችል አይመስለኝም…ምግቧን እንኳን በእጆቾ ጠቅልላ መብላት የሚከብዳት እና በአጉራሽ የምትመገብ ቅንጡ .ልጅ ነች፡፡ታዲያ ልጅን  የሚያህል ነገር አርግዛ…. ለዛውም ዘጠኝ ወር….ለዛውም  ደጋግማ… ምን አልባት የመጀመሪያውን እንደወረት ልታደርገው ትችላለች.. ከዛ በኋላ ላሉት ግን እርግጠኛ ነኝ መሀፀን ተከራይልኝ ነው የምትለው››
ጊፍቲ ከት ብላ ሳቀች…‹‹ጓደኛዬንማ እንዲህ አትላትም…ይሄን ያህል ምነው?››መቆርቆሮ ሳይሆን የሆነ የሽሙጥና እሷ የተሻለች እንደሆነች በሚያረጋግጥ ስሜት ነው፡፡
እሱ ግን ቀጠለበት‹ባክሽ በጥልቀት ስለማታውቂያት ነው….የእሷ ጉዳይ ከምልሽም በላይ ነው….እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ያማውቃት….ቤተሰብ ነን….አሁንም የማስተዳድረው ካማፓኒ የሁለታችን ቤተሰቦች በጋራ የመሰረቱት ነው››
👍7012😁4👏3
#ባል_አስይዞ_ቁማር
:
:
#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

በማግስቱ ነው…እሷ ገንዳ ውስጥ ገብታ ትዋኛለች እሱ እየሠረቀ ይመለከታታል..
‹‹ለምን ገብተህ አብረሀት አትዋኝም?"
"አብረሀት ማለት?"ስኳር ሲሰርቅ እንደተያዘ ህፃን በርግጎ ጠየቃት፡፡

"እንዴ በአይንህ እኮ ዋጥካት"

"ስርዓት ያዢ እንጂ… የራስሽው ጓደኛ መስላኝ?"

"እሱማ እዚህ ከመምጣታችን በፊት ነዋ ..አሁንማ ቀማሀኝ..ለማንኛውም ይመቻችሁ"አለችውና ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡ጉንጩን ሳመችውና መራመድ ጀመረች፡፡
ደንግጦ"እንዴ! ወዴት ነው?"

"እግሬን ላፍታታ"
‹‹ልከተልሻ"አለ ከመቀመጫው እንኳን ለመንቀሳቀስ ሳይሞክር

"አይ ብቻዬን ይሻለኛል ››

‹‹ እሺ እዚሁ እንጠብቅሻለን›› ብሎ ሸኛት...ደስ አለት።ደስ ያለት ተንኮል ስላሠበች ነው።

ትንሽ እራቅ እንዳለች እንዳያዮት ተጠንቅቃ በዛፍ ተከልላ ተጠማዘዘችና ወደመኝታ ክፍል አመራች፡፡ ...እንደደረሰች  ልብሷን ቀያየረች ።ሻንጣዋን አዘጋጅታ ።ከቦርሳዋ  ዘወትር እንደምታደርገው እነዛን የድመት አይን የመሰሉ ካሜራዎችን ድብቅ ቦታ አስተካክላ አስቀመጠች..ወደጊፊቲ ክፍል ስትሄድ ፅዳቷ እያጸዳች ነበር፡፡

‹‹…ይሄንን ቻርጅ ከጎደኛዬ ተውሼ ልመልስላት ነበር..››አለችና ዝም ብላ ገብታ ኮመዲኖ ላይ ቻርጁን አስቀመጠች… የእሷን እይታ በሰውነቷን ጋርዳ እዛው ኮመዲኖ አጠገብ ካለ የቴሌቪዥን ጠርዝ ላይ የካሜራውን አይን ለጠፈችው….መልሳ ቻርጀሩን አነሳችና‹‹እንደውም ሀሳቤን ቀየርኩ እስክትመጣ ብጠቀምበት ይሻላል›› ብላ ወጥታ ሄደች….ቀጥታ የመኪናውን ቁልፍ እያወዛወዘች ወደ መድሀኔ መኪና ነው ያመራችው..ከፈተችና ገባች… መኪናውን አስነስታ ኩሪፍቱን ለቃ ወጣች ።30 ደቂቃ ከነዳች በኃላ ስልኳን አወጣችና…፡፡
‹‹መኪናህን ይዤ ከጊቢ ወጥቼያለሁ ከሁለት ሰዓት በኃላ እመለሳለሁ ››ብላ መልዕክት ላከችለትና ስልኳን አጠፍችው።
////
አዲስአበባ ገብታ እቤቷ ከደረስች በኃላ ነበር. ስልኳን ስትከፍት ሰዓቱ አንድ ሰዓት አልፎ ነበር ..ከከፈተች ከአስር ደቂቃ በኃላ ተደወለላት።

‹‹አንቺ የት ነሽ?››

"እቤቴ›››

‹‹ ማለት?"

"እቤቴ ነዋ.. አዲስአበባ..."
" ግን ጤነኛ ነሽ...?ምን ሆንኩኝ ብለሽ ነው?"ከንዴቱ ብዛት ድምፁ እየተቆራረጠ እና እየተርገበገበ ነበር..፡፡
"ምንም ..አሰኘኝ አደረኩት ..ለማንኛውም ለሹፌርህ ነግሬልሀለው...አሁን እቤት መጥቶ መኪናህን ወስዷል …ጥዋት እስከሁለት ሰዓት ይደርስልሀል፡፡"

"በጣም ታበሳጪያለሽ…  እኔስ ይሁን አንዴ ፈርዶብኛል.. የሠው ሠው ከቤቷ አክለፍልፈሽ አምጥተሽ  ባዶ ሜዳ ላይ ጥለሻት ትሄጂያለሽ?››

"ባዶ ሜዳ ላይ አይደለም  አንተ ላይ ነው ጥያት የመጣሁት...አንተ ማለት ደግሞ እኔ ነህ...ምነው ተሳሳትኩ እንዴ?››
"አሽሟጠጥሽ ማለት ነው...በይ ቻው"ብሎ ጠረቀመባት ።

እሷ ግን ሁሉም ነገር በእቅዷ መሠረት እየሄደ ስለሆነ  ደስ አላት።
///
"ሶስት ሰዓት የጀመረች ይሄው እስከአራት ሰዓት ተኩል ላፓቶፖን  አስተካክላ ወደክፍላቸው እስኪገብ እየጠበቀች ነው። ‹‹ውይ ተመስገን››አለች…
የጊፍቲ ክፍል ተከፈተና ገባች ...የእሱም ተከፈተ ገባና ዘጋው።ልዩ መልሳ ተበሳጨች…፡፡እቅዴ አልሰራም ወይም ግምቶ ትክክል አልነበረም፡፡ በተለይ እስከእዚህን ሰዓት ድረስ ወደ ክፍላቸው ሳይመለሱ መቆየታቸው ተስፍ ሰጥቷት ነበር ፡፡እነሱ ግን ይሄው ጨዋነታቸውን እንደጠበቁ በየክፍላቸው ገቡ..፡፡ይሄ ጉዳይ ደግሞ ልዩን ተስፋ ሲያስቆርጣት …የእሷን ላፕቶፕ ሀክ በምድረግ እሷንም ሰደሬ ያሉትን እነጊፍቲንም እየተመለከተ ያለው ቃል ደግሞ ፈገግ አለ፡፡
ልዩ‹‹ቆይ ቆይ እስኪ… ››ብላ ትኩረቷን መድሀኔ ክፍል ውስጥ ትኩረት ደረገች፡፡ እሱ ላይ ምንም የመረጋጋት መንፈስ አይታይበትም፡፡ ዝም ብሎ ወለሉ ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተመላለሠ ደቂቃዎችን አሳለፈ... ጊፍቲ ምንም የሚነበብባት የተለየ ስሜት የለም፡፡ ልብሷን አወለቀችና በፓንት ብቻ እርቃኗን ቆመች‹‹...ዋው ሰውነቷ ለእኔ ለሴቷም ያጓጓል..፡፡እርግጥ ከመጠን ትንሽ ተረፍረፍ ያለ ውፍረት ይታይባታል ቢሆንም ታምራለች፡፡››በማለት አድናቆቶን ተናገረች …ቃል ደግሞ በግማሽ ትኩረት የሚያውቀውን ገላ እየተመለከተ በገማሽ ቀልቡ ደግሞ የልዩን ጉሩምሩምታና መቁነጥነጥ እየታዘበ ቀጣዩን ትዕይንት ለማየት በጉጉት መከታተሉን ቀጠለ...
ጊፍቲ ከሻንጣዋ ውስጥ ሙሉ ቢጃማ ቀሚስ አወጣችና ለበሰች..ከዛ ሎሺን አወጣችና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ ከባቷ ጀምሮ ወደታች እግሮቾን መቀበባት ጀመረች...
መድህኔ  አሁንም ክፍሉ ውስጥ ሆኖ መንጎራደድን አላቆመም ..በውስጡ ከፍተኛ የሀሳብ ፍጭት እየተደረገ ይመስላል.. ድንገት እንደመባነን አለና ወደ ጠረጰዛው ሄደ ..ብዙም ያልተጠጣለት ብላክ ሌብል ውስኪ ነበር ..አንስቶ ያዘው..ትናንት ማታ ልዩ ይሄን መጠጥ ስለምትወድ  ለእሷ ብሎ ነበር  የገዛላት። ሊያንደቀድቀው ነው ብላ ስትጠብቅ ሁለት ብርጭቆ ይዞ ከክፍሉ ወጣ...የቃልም ሆነ የልዩ ልብ በየአሉበት ተንጠለጠለ… ሁለቱም የሚቀጥለውን ትዕይንት ለማየት ተነቃቁ ..የጊፍቲ ክፍል ተንኳኳ

"ማነው?"

"ጊፍቲ መድህኔ ነኝ"
ያለምንም ማቅማማት ቀልጠፍ ብላ ሄዳ ከፈተችለትና በራፍን ይዛ ቆመች..ከካሜራው ስለራቁ የሚያወሩት እየተሠማቸው አይደለም .ከደቂቃዎች ብኃላ ከበራፉ ገለል አለችና እሱን አስገባችው፡፡ በራፍን ዘግታ ወደነበረችበት የአልጋ ጠርዝ ተመልሳ ተቀመጠች...እሱ ውስኪውን ከነጠርሙሶቹ እንደያዘ ቆሟል።

‹‹እንዴ ቁጭ በል እንጂ?››

"እሺ"አለና በሁለቱም ብርጭቆ ቀዳና አንዱን አቀብሏት አንዱን ይዞ ከፊት ለፊቷ ያለ ደረቀ ወንበር ላይ ተቀመጠ...፡፡

"የጠጣሁት ወይን እራሱ አድክሞኛል..."

"አይዞሽ ምንም አይልሽ...ደግሞ አልጋሽ ላይ ነው ያለሽው ከደከመሽ ወደኃላ ክንብል ብሎ መተኛት ነው፡፡"

"እኔስ ክፍሌ ነኝ ክንብል ብዬ ተኛው...አንተስ በሰለም ወደቤትህ መግባትህን ቅድሚያ ማረጋገጥ የለብኝም?።››አለችው፡፡
"ለዛ አታስቢ  ..ከእዚህ ክፍሌ እስከሚደርስ ምን ያጋጥመዋል ብለሽ የምትሰጊ ከሆነ እዚሁ ከእግርሽ ስር እጥፍጥፍጥፍ ብዬ እተኛለሁ›› አላት፡፡
ጊፍቲ ከት ብላ የመገረም ሳቅ ሳቀች ."ይህቺ ጠጋ ጠጋ እቃ ለማንሳት ነው ...ሰውዬ በል ጠጣ ጠጣ አድርግና ወደ ክላስህ" አለችው ….
መልስ ሊመልስላት አፉን ሲከፍት የእሷ ስልክ ጠራ…እርብትብት አለች….መድህኔ  እየተከታተላት ነው…ስልኩን አላነሳችውም፡፡ ስልኩም እስከመጨረሻው ድረስ አልጠራም…በመሀከል ተቋራጠ፡፡ስልኩን የደወለው ቃል ነው..ይሄንን ያደረገው ሆነብሎ ስሜቱ እንደዛ እንዲያረግ ስለገፋፋው ነው፡፡
‹‹ወይ….በፈጣሪ!!›አለች፡፡
‹‹ምነው ?ማነው የደወለልሽ?››
ልዩም በላችበት ሆነ የዚህን ጥያቄ መልስ ለማወቅ ፈልጋ ነበር
‹‹ጓደኛዬ ነው፡፡››መለሰች ጊፍቲ፡፡
‹‹ጓደኛሽ ማለት ፍቅረኛሽ?››
‹‹በለው.. አዎ ፍቅረኛዬ››
‹‹ይሄን ያህል አደገኛ ነው እንዴ;?››
‹‹አዎ….ማለቴ ምንም ብታደርግ ምንም አይናገርህም…አያኮርፍህም ..አይቆጣህም..በቃ ዝም ብሎ ነው የሚያልፍህ››
👍6311👏1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ከምሽቱ 5 ሰዓት እቤት ክፍሌ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ስለቃል እያሰብኩ ነው….መቼስ ቃል ቃል ብዬ እናንተንም አሰለቸዋችሁ አይደል  ምን ላድርግ..ተለክፌ እኮ ነው….እንቅልፌ መጥቷል ግን ከመተኛቴ በፊት አሱን ማየት ፈለኩ…ማለቴ በተለያየ ቀን ከመተኛቱ በፊት የፀለያቸውን ያልተለመዱ አይነት ፀሎቶችን እሱ ቤት በቀበርኩት ስውር ካሜራ አማካይነት ቀድቼ ላፕቶፔ ውስጥ አሉ..ከእነሱ መካከል አንድ ሁለቱ ማድመጥ ፈለኩ በዛውም ለእኔም እንደፀሎት ሀኖ ይቆጠልርልኝ ይሆናል…
ይሄ ከዛሬ አስር ቀን በፊት የፀለየው ነው፡፡
///

የዛሬ ሳምንት የፀለየው ደግሞ በእኔ ላይ እየሆነ  ያለው ሁሉ ትክክል ነው…በዙሪዬ ምንም  ገደል የለም…የመታኝ እንቅፋት በንቃት እየተራመድኩ እንዳልሆነ ሊያስታውሰኝ እንጂ ሊያደማኝ ፈልጎ አይደለም፡፡ እየበሰበሰ ያለው ነገር ከመበስበስ ቡኃላ ህይወት መስጠት ስላለ ነው…እየረገፈ ያለው የጠወለገና ደረቅ ቅጠል ለአዲሱና እንቡጠቹ ቅጠሎች ይበልጥ እንዲያቡብና እንዲያፈሩ ነው፡፡በዚህ አለም ላይ  ምንም አይነት የተዘበራረቀ ነገር የለም..እሆነ ያለውነገር ሁሉ አንተ ስለፈቀድክና መሆን ስለሚገባው የሆነ  ነው…ለምለሰሙ ዝናብ ከሰመይ በመርገፍ ምድርን ከጥሞና እንዴያረካት ቀድሞ ሰማዩ በጥቁር ደመና መሸፈንና መዝጎርጎር አለበት…ጨለማው ከሌለ ብሩሆ ጨረቃ የምትተፋውን ብርሀን ፈፅሞ ማየትም ማድነቅም አንችልም….ሁሉ ነገር ድንቅ ነው..ሁሉ ነገር ብሩህ ነው፡፡
አሜን.ብዬ ላፕቶፔን ዘጋሁና መብራቱን አጥፍቼ ተኛሁ፡

///
ከሶደሬ ከተመለሱ ሀያ  ቀን አልፏቸዋል፡፡ዛሬ ለሳምንታት ያቀደችውን ነገር የምትፈፅምበት ቀን ነው፡፡አዎ የምትፈፅመው  ነገር የጽድቅ ስራ አይደለም…አእምሮ የሚጨመድድ ከሳጥናኤል አእምሮ ካልተቀዳ በሰው ሀሳብ የማይታሰብ ነገር እንደሆነ ታውቃለች….ግን ደግሞ በነፃ ሚገኝ  ነገር የለም በሚል እራሷን ለማፅናናት ገፍታበታለች….፡፡‹‹አዎ    ቃልን የራሷ ለማድረግ እሷም መክፈል የሚገባትን መስዋዕትነት በፍቃደኝነት ለመክፈል ቆርጣለች….የልጅነት ጓዳኛዋን፤ የረጅም ጊዜ እጮኛዋ የሆነውን መድህኔን በፍቃደኝነት አሳልፋ ልትሰጥ ነው….አዎ ያንን ለማድረግ ደግሞ የመጨረሻውን ማስፈንጠሪያ የምትጫንበት ቀን ነው…ብቻ እንዲቀናትና ነገሮች በእቅዷ መሰረት እዲከወኑ ለማን መፀለይ እንዳለባት አታውቅም ‹‹እግዚያብሄርን እርዳኝ ብዬ እንዴት ጠይቀዋለሁ….?አረ ያሳፍራል፡፡››አለች ..ብቻ እንዲሁ እንዲቀናት ለራሷ ስኬትን ተመኘች…..በዛው ቅፅበት መኝታ ቤቴ ተንኳኳ፡፡

‹‹ማን ነው?››

‹‹እኔ ነኝ ልዩ..››አለች ከሰራተኛቸው አንዷ፡፡

‹‹እ ..ምን ፈለግሽ?›››

‹‹መድህኔ መጥቷል››

‹‹መጣው ጨርሼያለሁ በይው››

‹‹እሺ….››ብላ ተመልሳ ሄደች፡፡በጣም ተጨንቃ ዝንጥ ብላ ነው የጠበቀችውኩ፤የሚያስፈልጋትን ነገር ሁሉ በቦርሳዋ መጨማመሯን አረጋግጣ ክፍሏን ለቃ ወደታች ወደሳሎን ስትወርድ መድህኔና እናቷ ልክ እንደወትሮቸው አፍ ለአፍ ገጥመው ሲያወሩ ደረሰች፡፡….
እናትዬው ገና እንዳዮት‹‹ወይ ልጄ መልአክ መስለሻል …››አለቻት … መድህኔም ዞር ብሎ ከስር እስከላይ በገምጋሚ አይኖቹ ቃኛትና ፈገግ አለ…..

ከተቀመጠበት ተነሳና‹‹…በቃ ማሚ ሰሞኑን እመጣና በዝርዝር እናወራበታለን›› አላቸው፡፡

‹‹እሺ የእኔ ልጅ..ነገ ተነገ ወዲያ ቢሆን ደስ ይለኛል…ጊዜ የለንም፡፡››አሉት፡፡
..ምንም እንዳልገባው ሆና‹‹ለምኑ ነው ጊዜ የሌላችሁ?›› ብላ ጠየቀች ..ስለሰራጋቸው እንደሚያወሩ ግልፅ ሆኖላታል፡፡..በዚህ ወቅት በእሷም ሆነ በእሱ ቤተሰቦች ቤት ከእነሱ ሰርግ ውጭ ሌላ አንገብጋቢ አጀንዳ እንደሌለ ታውቃለች፡፡

‹‹አይ የአዋቂ ወሬ ነው….››አላትና አቅፏት ይዟት ወጣ…
ሲሸኞቸው ከኃላ የተከተሏቸው እናቷ‹‹ካደራችሁ ደውሉ››አሏቸው…
‹‹አንደውልም  …ከአሁኑ እወቂው እድራናል›››መለሰችላቸው፡፡
በእሱ መኪና ውስጥ ገብተው ገና ከጊቢ እንደወጡ‹‹በል ጊፍቲ እስቴዲዬም እየጠበቀችን ነው››አለችው..
‹‹እነሱም አብረውን ያመሻሉ እንዴ ..?እኔና አንቺ ብቻ ምንሆን መስሎኝ ?››አላት..ቅር ባለው ፊት፡፡
‹‹አዎ እኔም እንደዛ ነበር እቅዴ ..አሁን ከሀያ ደቂቃ በፊት ደውላ ደብሯት እስቴዲዬም ብቻዋን እዳለች ነገረችኝ ››
‹‹እንዴ  ፍሬንዷ ጋር አትደውልም…?››ሙግቱን ቀጠለ
‹‹ፍሬንዷ ማን ?››
‹‹እያሾፍሽ ነው..?ቃል ነዋ››
‹‹ፍሬንዷ ስትል እኮ ዝም ብሎ ጓደኛዋ የምትል መስሎኝ ነው..ቃልማ ለስራ ክፍለሀገር ወጥቷል….ለዛ እኮ ነው እምቢ ማለት የከበደኝ …አንተ በስራ ቢዚ ሆነህ ችላ በምትለኝ ጊዜ የምታዳብረኝ እሷ አይደለች..አሁን ውለታዬን ልመልስ ነዋ…››አለችው፡፡
‹‹አቤት አቤት..አሁን እኔ መቼ  ነው አንቺ ልታገኚኝ ፈልገሽ ቢዚ የሆንኩት…..ደግሞ የድሮ ጓደኞችሽን እርግፍ አድርሽ  ግንኙነትሽን ጠቅላላ ከእነዚህ ባልና ሚስት ጋር እድርገሻል ምንድነው ?አልገባኝም?…››አላት

በመርማሪ አይኖቹ ፡፡
‹‹ምነው አልተመቹህም እንዴ..?እንደዛ ከሆነ ….››
‹‹እንደዛ ከሆነ ምን…?››
‹‹ካልተመቹህ ቀስ በቀስ አቆማለኋ…››
‹‹አዎ አልተመቹኝም›› ቢል እንደማታቆም በውስጧ ታውቃለች..ግን ደግሞ ማስመሰል አለባት፡፡  አቁሚ ቢላት እንደውም እልክ ይዞት ጨርቋን ጠቅልላ እነሱ ጋር የምትገባ ሁሉ ይመስላታል፡፡እሱም አመሏን በጥልቀት ስለሚያውቅ እንደእዛ አይነት ቅብጠት አይቃብጥም፡፡
‹‹ኸረ..እንደውም ከእነሱ ገር መዋል ከጀመርሽ በኃላ  አሪፍ ሆነሻል፡፡››
‹‹አሪፍ ስትል?››ተበሳጭች
‹‹በቃ ደስተኛ ሆነሻል..በረባ ባረባው መነጫነጭ ትተሻል ባልልም በጣም ቀንሰሻል .ለምትጠየቂው ጥያቄ ቀና መልሶች  መመለስ እየተማርሽ ነው..አረ ከሁሉም በፊት እንድንጋባ ፍቃደኛ የሆንሽው ከእነሱ ጋር ጓደኛ ከሆንሽ በኃላ እኮ ነው፡፡››ብሏት የቅርብ ጊዜ ለውጧቾን ዘረዘረላት….ምንም የተሳሳተው ነገር የለም…ሁሉንም በአስተውሎት ታዝቦል….ችግሩ ከለውጦቹ ጀርባ የሸሸገችውን ድብቅ ሚስጥራዊ ተልዕኮ አለማወቁ ነው፡፡

‹‹ምን አልባት በእነሱ ፍቅር ቀንቼ ይሆናል…››

‹‹አረ እንኳን  ቀናሽ..እኔ ተጠቃሚ ሆኜያለሁ፡፡››
‹‹ዛሬ እንደውም እንዲህ ተቆነጃጅቼ የወጣሁት የሆነ ነገር ሰጥቼ ሰርፕራይዝ ላደርግህ ነበር..ግን አሁን ፀባይህን ሳየው አይገባህም››

‹‹አይኖቹ በሩ…ምንደነበር ልትሰጪኝ ያሰብሽው…?››
‹‹እስከዛሬ ሰጥቼህ የማላውቀውን››
በደስታ ተፍነከነከ …‹‹በአንድ አፍ….አንዴ አስበሽ ወስነሻል……. ትሰጪኛለሽ፡፡››
‹‹እስኪ እስከምሽቱ ያለህ ፀባይ ታይቶ …ምን አልባት?››አንጠልጥላ ተወችው፡፡
…በዚህ ጊዜ ስቴዲዬም ደርሰው ነበር ..ጊዬን ሆቴል በራፍ አካባቢ መኪናቸውን አቆሙና ደወሉላት..ቅርብ ስለነበረች መጥታ ተቀለቀለቻቸ….  ወደፒያሳ ነበር የነዳው፡፡


ይቀጥላል
👍11313😁3🤔3🔥1🤩1
#ባል_አስይዞ_ቁማር››


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹ምነው…ፒያሳ ይሻላል እንዴ?››ልዩ ነች የጠየቀችው፡፡

‹‹አይ የሆነች ጉዳይ ሳላለችብኝ ነው… ደረስ እንልና እንደውም እዛው ኢሊሊ ራት በልተን ከዛ ወደምትፈልጉበት ጭፈራ ቤት እንሄዳለን..››

ጊፍቲ ፈገግ አለች….ቀጥታ ፒያሳ ወደሚገኙ መደዳ ወርቅ ቤቶች ነበር ይዟቸው የሄደው..ልዩ እራሱ ያልጠበቀችው ነገር ስለሆነ ግራ ተጋባች…እሱ ራሱ ቀድሞ ያሰበበት ጉዳይ አልነበረም..ሰጥሀለው የምትለዋ ቃል ከአንደበቷ ተስፈንጥራ ስትወጣ በውስጡ በተፈጠረ ፍንጠዛና በምርቃና ድንገት ብልጭ ያለለት ሀሳብ ነው፡፡

‹‹ምነው ምን መጣ..?››ጠየቀችው፡፡

‹‹ቀለበታችን ሳንመርጥ የቀለበቱ ቀን ደረሰ እኮ?››

‹‹እንዴ ገና ሁለት ወር ይቀረናል እኮ››

‹‹ሁለት ወር ምን አላት….አይደል ጊፍቲ፡፡›› አለ ወደ እሷ ዞሮ ድጋፍ እድትሰጠው በሚፈልግ ንግግር…

እሷ የሰማችው አይመስልም ቅዝዝ ብላ ጭልጥ ያለ ሀሳብ ውስጥ ገብታለች

‹‹ጊፍቲ፡፡››

‹‹እ..ታድላችሁ…አዎ ትክክል ነው..ሁለት ወር በጣም አጭር ጊዜ ነው…››አለችና ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡ…ተገቢውን ቀለበት አማርጦ ለመግዛት ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ነው የፈጀባቸው….በመጨረሻ እንደውም ጊፍቲ አሪፍ ነው ብላ ያሳየቻቸውን የዳይመንድ ፈርጥ ያለበት ቀለበትን ነው ሁለቱም በአንድ ድምፅ ተስማምተው የተገዛው..የሁለቱንም ቀለበት ሰጣትና ቦርሳዋ ውስጥ በመክተት እየተሳሳቁ ተያይዘው ወጡ…

እንዳአለውም ኢልሌ ሆቴል ጎራ አሉና እራታቸውን በልተው ሲወጡ ሶስት ሰዐት አልፎል…

‹‹አሁን ጭፈራ ቤት ለመሄደ ትክክለኛው ሰዓት ነው››አለ መድሀኔ…ፍንድቅድቅ ባለ ድምፅ፡፡
‹‹አዎ ግን እናንተ ብትሄዱ ይሻላል ..ከዚህ በላይ ካመሸው አከራዬቼ የውጭ በራፍ አይከፍቱልኝም…››አለች ጊፍቲ
‹‹እኛም አይከፍቱልንም››ሲል መለሰላት መድህኔ

‹‹አይ ቢሆንም እናንተ የራሳችሁ ማለቴ የወላጆቻችሁ ቤት ነው..ጨክነው አይጨክኑባችሁም እኔ ግን ኪራይ ቤት..››
ክንዷን ያዘችና ‹‹ነይ ባክሽ እስከአራት እስከ ከአምስት ሰዓት ዘና እንልና አዲሱ ቤታችን ሄደን ነው የምናድረው…አይደል መድህኔ?››

‹‹እ አዎ..ጥሩ ሀሳብ ነው….››አለ…..እሱም ያላሰበው አዲስ ሀሳብ ነው ያመጣችው፡፡
መኪና ውስጥ ገብተው መድሀኒ መንዳት ከጀመረ በኃላ…‹‹እንዴ አዲስ ቤት ተከራያችሁ እንዴ ?›› ስትል ጠየቀች

‹‹ አይ የእኔ ፍቅር አሪፍ ቤት ገዝቶ ሰርፕራይዝ አደረገኝ፣››አለችና መልስ ሰጠቻት፡፡ ለቤት ያላትን ፍቅር እሷም ሆነች ቃል ደጋግመው ነግረዋታል፡፡ለዛም ነው አይን አይኗን እያየች አድምቃ እያወራች ያለችው፡፡

‹‹ለእናንተ እኔ ደስ ብሎኛል አለች››የንግግሯ መዝረክረክ ግን ደስ እንዳላላት ያስታውቅባታል፡፡
‹‹ሰዎች የተለየ ሀሳብ አለኝ››ልዩ ነች ተናጋሪዋ፡፡

‹‹ምንድነው?››

‹‹ለምን የሚስፈልገውን መጠጥ ገዝተን ቀጥታ ወደቤታችን አንሄድም…..ግርግሩ ብቻ ነው የሚቀርብን …ሙዚቃው እንደሆነ እቤት አለ …እንቀውጠዋለን…››
መድህኔ ሁለቱንም እያፈራረቀ አያቸው…

‹‹ወይ በቃ ለካ ጊፍትዬ ጭፈራ ቤት ትወዳለች…››አለች ልዩ..አውቃነው እሷን ይሉኝታ ውስጥ ለመጨመር አስባ ይህቺን አረፍተ ነገር የሰነዘረችው፡፡

‹‹አረ በፍፅም.. አሪፍ እና የተለየ ሀሳብ ነው ያመጣሽው..እንደውም ጭፈራ ቤት አድሬ ነገ ጥዋት ተነስቼ ቢሮ መግባት ይከብደኛል.. እያልኩ እያሰብኩ ነው…››

መድህኔ ‹‹እንግዲያው ወደቤት ነዳሁት…››አለና አቅጣጫውን አስተካከለ…

ከሀያት ሪል እስቴት ወደተገዛው ግዙፍ ቪላ ነው የነዳው..መንገድ ላይ ቆሞ ሴቶቹን መኪና ውስጥ አስቀምጦ መአት አይነት መጠጦችንና የተወሰኑ የሚበሉ ነሮችን ገዝቶ ተመለሰ….እቤት ሲደርሱ አራት ሰዓት ተቃርቦ ነበር..የመኪናውን ጡሩንባ ቢያንጣጣም በቀላሉ ሊከፈት አልቻለም..ወርዶ በእጁ ጭምር መቀጥቀጥ የግድ ሆኖበት ነበር..ከዛ ዘበኛው በድንጋጤና በማለክለክ መጥቶ ከፈተና በተደናገጠ ደምፅ..‹‹ጋሺዬ ይመጣሉ ብዬ ስላላሰብኩ እንቅልፊቱ ጣለችኝ፣እንደው ይቅርታ››ተሽቆጠቆጠ፡፡

‹‹…ችግር የለውም…››ብሎ አረጋጋው…ኮፈኑን ከፈተና
‹‹ይህቺን እቃ ወደሳሎን ውሰድልኝ›› አለው…ዘበኛው በታዛዥነት አንከብክቦ ወደሳሎኑ ከነፈ…ጊፍቲ በግቢው ውበት ፈዛ ከግራ ወደቀኝ አይኗን እያስወነጨፈች ታያለች…የምታደርገውን እየተካታተለ እንዳልሆነ ሰው ችላ ብላ ክንዷን ያዘችና ወደቤት ይዛት ገባች…ከሳሎኑ ጀምራ እያንዳንዱን መኝታ ቤት…መታጠቢያ ቤቶችን… ኪችኑን አስጎበኘቻት….

‹‹እንግዲህ ልጅ እስኪመጣ ድረስ ለእኛ ይበቃናል?››አለቻት
‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››
‹‹ምን እቀልዳለው..እኔና እናቴ ከሰራተኞቻችን ጋር የምንኖርበት ቤት እኮ የዚህን ሶስት እጥፍ ይሆናል…ከዛ ወጥቶ እዚህ መኖር..ብቻ ይሁን አሪፍ ነው››
‹‹እና ከሁለት ወር በኃላ ልትጋቡ ነዋ››ጠየቀቻት፡፡

‹‹አይ ከሁለት ወር በኃላ ምርቃቴ ስለሆነ ቀለበቴ ነው በደባልነት የሚደረገው ሰርጋችን ከሶስት ወር ነው….ምን ይታወቃል… አብረን አንሞሸር ይሆናል?››

‹‹አይ!! ብለሽ ነው?››አለቻት… ትክዝና ቅዝዝ ብላ….፡፡አዎ የፈለገችውም እንዲህ ውስጧን መበጣጠስና ተስፋ ማስቆረጥ ….ወይንም ማስጎምዠት ነበረ…‹.እርግጠኛ ነኝ ይሄኔ ስንቴ ምን አለ ይሄ ቤት የግሌ በሆነ ብላ ተመኝታለች..እንግዲህ ይሄን ቤት ከፈለገች..የቃልዬን እጅ ለቃ የመድህኔን እጅ መያዝ አለባት ማለት ነው…ያንን እንደምታደርግ ደግሞ ከዛሬ ጀምሮ ምልክት ልትሰጠኝ ይገባል….ጊዜ የለንም፡፡››ስትል እሷን ከጎኗ አቁማ በውስጧ አብሰለሰለች፡፡

ጉብኝታቸውን ጨርሰው ወደሳሎን ሲመለስ መድህኔ ጠረጳዛውን በመጠጥና በሚበሉ ቀለል ባሉ ምግቦች ሞልቶት ግዙፍ እስፒከር ያለውን ቴፕ አዘጋጅቶ ጠበቃቸው…
‹‹የእኔ ፍቅር ምርጥ እኮ ነህ›› ብላ ተንጠልጥላበት ጉንጩን ሳመችው፡፡ ‹‹መቼስ ዛሬ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ቁልትልት ብዬበታለሁ……››ስትል እራሷን ታዘበች
ጊፍቲ ሶፋ ላይ ቁጭ አለች……

‹‹ምን ልቅዳለችሁ?›› መድሀኔ ጠየቀ፡፡

‹‹ወይን ቢሆን ደስ ይለኛል…››መረጠች ጊፍቲ፡፡…
‹‹አዎ ከቀላል እንጀምር ለእኔም ወይን››ልዩም ከጊፍቲ ምርጫ ጋር ምርጫዋን አስማማች፡፡
እንግዲያው ቆንጆ የፈረንሳይ ወይን አለኝ….አለና ከተኮለኮሉት ጠርሙሶች መካከል አንዱን መዞ በእያንዳንዳቸው ብርጭቆ ቀዳላቸው …እና የራሱንም ይዞ ከፊት ለፊታቸው ቁጭ አለ፡፡
መጠጡ በወይን ቢጀመርም..ወደውስኪ ሲሸጋገር አንድ ሰዓት አልፈጀበትም። ስድስት ሰዓት ላይ ተኪላ ነበር ሻት እየተደረገ የነበረው ...ዳንስ ..ጭፈራው ቅውጥ ያለ ነበር፡፡ ልዩም ዛሬ እንደው የእነሱን ያህል ችሎታው እንደሌላት ብታወቅም ቁብ ሳይሰጠት ከእነሱ እኩል ስትቀውጠው አመሸች...ልዪነቱ መጠጡ ላይ እየጠጣች በማስመሰል ስትደፍው ..አንዳንዴ ወደእነሱ ስትገለብጥ በተቻለኝ መጠን የሰከረች በመምሰል ግን ሳትሰክር እራሷን ለማቆየት የተቻላትን ጣረች..እናም ተሳክቶላት ሰባት ሰዓት ሲሆን ሁለቱም በዳንስ ብዛት ውልቅልቅ ብለው በላብ ወርዝተው ከላይ የለበሱትን እያወለቁ ጥለው እሱ በነጭ ፓክ አውት እሷ ደግሞ በጥቁር ጡት ማስያዣ ነበሩ...ልዩም ያው እነሱን ለማበረታት በጡት መያዠ ብቻ ቀርታለች...በዳንሱ ሞቅታ መካከል ሁለቱንም አቅፍቸውና አንድላይ አጣብቃ ወዳራሷ ትጨምቃቸዋለች…እንደዛ ሲሆን እርስ በርስ አንዲፍተጉ እያደረገች ቅርበታቸውን እያጠናከረች ነው፡፡..አንዳንዴ ሞቅ ብሏቸው የጋለ የእርስ በርስ
👍847😁5🥰3👎1🔥1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

"ሰጥሀለው መጀመሪያ ልብስህን አውልቅ ..፡፡››አለችና ጎንበስ ብላ ጫማዋን አወለቀችለት ..ከዛ የሱሪውን ቀበቶ ፈታችና ቁልፍን ከፍተች… ዚፑን ወደታች በማንሸራተት ሁለቱን እግሮቹን ከታች በመያዝ እንደምንም እየጎተተች ከላይ እየሳበች ሱሪውን ከፓንቱ ጋር አንድ ላይ ሞሽልቃ አወለቀች…..እንዲህ ጨርቅ ሆኖ እንትኑ አደባባይ መሀል የቆመ የነፃነት ሀውልት ይመስላል....‹‹ልዩ ይሄን የመሰለ ዕቃ ለሌላ አሳልፈሽ ከመስጠትሽ በፊት አንዴ ብትጠቀሚው?››የሚል ሴጣናዊ ምክር የሆነ መንፈስ በጆሮዬ ሹክ አለባት። ጆሮዋን ደፈነችና ተልዕኮዋን ላይ አተኮረች...አሁን የቀረው ፓካውቱን ማውለቅ ነው ሙሉ በሙሉ አልጋው ላይ ወጣችና እንደምንም ታግላ አወለቅችለት.. አሁን ሙሉ እርቃኑን ቀርቷል..አልጋ ላይ ቆማ ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ በትኩረት አይኖቾን እያመላለስች አየችው፡፡ ወንድ ልጅን እንዲህ መለመላውን በአካል ስታይ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው። ጥሩ የተባለ የእስፓርተኛ ሰውነት ከተመጠነ ውፍረትና ቁመት ጋር ነው ያለው ..እንዲያም ሆኖ ግን የወንድ አካላዊ ቁመና እንደሴት ማራኪ አይደለም ስትል አብሰለሰለች። ‹‹አሁን ይሄን ማሰቢ ጊዜ ነው ?››እራሷን ገሰፅችና ወደሳሎን ተመለሰች...ጊፍቲ አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እጅ አልሰጠችም" አሁንም የመጠጥ ብርጮቆዋን በእጇ እንደያዘች... እያላዘነች ነው፡፡

"ቃልዬ አሁን ናልኝ...ናና ሰውነቴን ዳብሰው...ናና ከንፈሬን ምጠጠው...ናና ጡቶቼን ጭመቃቸው...ናና ጭኖቼን ገነጣጥላቸው...ናና ..››

‹‹..ቃልዬን ፈልገሽው ነው?"

"አዎ ...ቃልዬን አምጪልኝ "

"ቃልዬን እንዳመጣልሽ...መጀመሪያ የያዝሽውን መጠጥ ጠጪ"

"መጠጥ ይሄው"

በአንድ ትንፋሽ ግልብጥ አደረገችው" ይሄው ጨረስኩ በያ አምጪልኝ"

"አመጣዋለሁ ..ግን ከአመጣሁት ትሰጪዎለሽ"

"ለቃልዬ..በደንብ ነዋ ...ለዛውም እንደፈለገው፡፡"

"እንቢ አልፈልግም ካለስ?"

"አንቺ ብቻ አምጪልኝ እንጂ በግድ ነው የምሰጠው..?"

‹‹እንግዲህ ተነሽ...ቃልዬ ልብሱን አወላልቆ ዝግጅ ሆኖ እየጠበቀሽ ነው...››

የእውነት ፈጥና መቀመጫዋን ለቃ ለመነሳት ብትሞክርም መቀመጫዋን ከሶፍው መላቀቅ አልቻለችም...ክንዷን ይዛ በመጎተት አስነሳቻትና እየጎተተች ማለት ይቻላል..ወደራሳቸው መኝታ ቤት ይዛት ገባች... መድህኔን ጠቅልላ እንዳስተኛችው ተኝቷል።

"የተኛ ሰው በማየቷ "ቃልዬ ነው እንዴ?"ስትል በተኮለታተፈ እና በተሰባበረ አረፍተ ነገር ጠየቀች፡፡

‹‹አዎ ግን በመስከርሽ እንዳይበሳጭ ድምፅሽን ቀንሺ አለቻት...በሁለት እጇ አፏን ፡አፈነች...አልጋው ጫፍ አስቀመጥኳት ‹‹...አሁን ልብስሽን ላውልቅልሽ..ተስማማሽ?›› ልክ እንደ መድህኔ እንዳደረገችው እያንዳንድን በሰውነቷ ላይ ያለውን ልብስ አወለቀችላትና መለመላዋን አስቀረቻት‹‹...ፐ ቅርፅ...›› በሚል አድናቆት እየጎተተች ከውስጥ አስገባቻት …እና ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብላ ‹‹እንግዲህ እኔ ሄድኩልሽ ..ያው ቃልዬ በደንብ ስጪው" አለቻት፡፡፡

መዲህኔ ላይ እየተጣበቀችበት‹‹ እ…ሺ ››.አለችን

መብራቱን አጠፍችና ከአልጋው ወረደች ..ተራመደችና ከክፍሉ አልወጣችም፤ እዛው መግቢያ ላይ ወዳለ ሶፍ ሄደችና ጋደም አለች...ከዛ የሚፈጠረውን ነገር መከታተል ጀመረች...

"ቃል አንተ ተኛህ እንዴ...?››ጊፍቲ ነች መድሀኔን እየወዘወዘች ያለችው፡፡

"አለው ....ልዪዬ"በሰመመን ውስጥ ሆኗ መለሰላት፡፡

"ከዛ የመተሻሸት ድምፅ ተሰማ ..ልዩ የሞባይሏን መብራት አበራችና ወደእነሱ አተኮረች ..ጊፍቲ እላዪ ላይ ወጥታበት ጎንበስ ብላ ከንፈሩን እየላሰችው ነው...ወገቧን ጨምቆ ይዞታል‹‹...ከደቂቃዎች በፊት ሁለቱም ተዝለፍልፈው እሬሳ መስለው አልነበረ እንዴ?›› ስትል በመገረም በውስጧ ጠየቀች፡፡ እንዲህ ልትል የቻለችው አንደኛው አንደኛውን ሲጨምቅና አንደኛው አንደኛውን በጥንካሬ ሲያንከባልል በማየቷ ነው....ከላይ አልብሳቸው የነበረ አልጋ ልብስም ሆነ ብርድ ልብስ ከላያቸው ተንሸራቶ ወደመሬት ወደቀ...አሁን ሁሉ ነገር በግልፅ ይታያት ጀመር...ሲተሻሹ..ሲሳሳሙ እና ሲዋሰብ በቂ የሆነ ፎቶም ቪዲዬም ቀረፀቻቸው፡፡.

ከዛ እነሱ እስኪረኩ መታገስ ከብዷት መሬት ካዝረከረኩት ልብስ ብድርብሱን ትታላቸው አልጋልብሱን ወሰደችና እሱን ተከናንባ እዛው ሶፋ ላይ ተኝች‹‹..እስቲ ሌሎች ሶስት መኝታ ክፍሎች ነበሩ ለምን እዛ ሄጄ አልተኛሁም..?››ስትል ጠየቀች…ምክንያቱን ግን አታውቀውም ነበር፡፡ወዲያው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት… ከእንቅልፏ ባና ሰዓቷን ሳታይ 12.10 ሆኖ ነበር..አይኗን አሻሽታ አልጋውን ስትመለከት ማመን አልቻለችም… ጊፍቲ መድሀኔ ክንድ ላይ ተንተርሳ አንደኛውን እግሩን ጭኖቾ መካከል ሰንቅሮ አንደኛውን ደግሞ ከላዬ ጭኖባት ጭልጥ ያለ እንቀለፍ ውስጥ ገብተው ያንኮራፋሉ… ማንኮራፋታቸው እራሱ ተራ በተራ ስለሆነ የራሱ የሆነ ስልተ ምት አለው….ከሶፋዋ ተነሳችና ቆመች.. .መኝታው ሰላልተመቻት ሰውነቷ ድቅቅ ብሏል…ተራመደች…ወደአልጋው ተጠጋችና እሪ ብላ ጩኸቷን ለቀቀችው……በመበርግ ሁለቱም ከእንቅልፋቸው ባነኑና ከተጣበቁበት ተላቀቁ፤ አንዴ እሷን አንዴ እርስ በረስ መተያየት ጀመሩ…፡፡

እሷ እንደድንቅ ብሄራዊ ተያትር ቤት ተዋናዬች ባጠናችውና በተዘጋጀችው መሰረት መድረኩን ተቆጠጣጠረችው፡

‹‹እንዴት እንዲህ ታደርጉኛላችሁ…ሰክራለች ብላችሁ እኔን ሶፋላ ላይ አስተኝታችሁ…?መድሀኒ ይሄ ለእኔ ይገባል.?››እራሷን ነጨች..ኸረ እንባዋ ሁሉ እየረገፈ ነው..መድሀኔ ተነስቶ ከአልጋው ወረደ… መለመላውን ሁለት ሴቶች ፊት ተገተረ….ጊፍቲ አንሶላውን ሰበሰበችና እርቃኖን ሸፈነች…ፊቷ በእፍረትና ግራ በመጋባት በአንዴ ሲገረጣ እየታየ ነው..
‹‹ልዩ ተረጋጊ …ምን እንደተፈጠረ በእውነት አላውቅም..››ወላል ላይ የተበታተነውን ልብሱን መሰብሰብ ጀመረ…ከመሀከል ፓንቱን እነሳና ለበሰ..፡፡
‹‹ሁለታችሁንም ከዛሬ ጀምሮ በአይኔ ማየት አልፈልግም….ያው ከመሀከላችሁ ወጥቼለሁ....እቤቱንም ተጋብታችሁ ልትኖሩበት ትችላላችሁ፡፡››
‹‹አረ ልዩ እንደዛ አይደለም…ይሄ ስህተት ነው››ጊፍቲ ነች እራሷን እንደምንም አበረታታ መናገር የጀመረችው፡፡

‹‹ምንም ስህተት አይደለም...እንደውም አሁን ሳስበው ይሄ ጉዳይ ከእኔም ሆነ ከቃል ጀርባ ሆናችሁ ስትፈፅሙት ዛሬ የመጀመሪያችሁ አይመስለኝም.››ነገሩን አንቦረቀቀችው፡፡
እንደ እብድ እየተወራጨችና እየተራገመች መኝታ ቤቱን ለቃ ወጣች፡፡ ሊለብስ ያዘጋጀውን ሱሪ በእጁ እንዳንከረፈፈ ሊከተላት ሞከረ….አልሰማችውም፡፡ ተንደርድራ ግቢውን ለቃ ወጣችና .ወዲያው ታክሲ ውስጥ ገባችና ከአካባቢው ተሰወረች…ስልኳን አጠፋችው፡፡

ቀጥታ ወደቤቷ ነው የሄደችው…..እናቷን እንኳን በቅጡ ሰላም ሳትል ወደ ክፍሏ ገባችና ከውስጥ ቀርቅሬ አልጋዋ ላይ ወጣች፡፡ድንግርግር ያለ ስሜት ነው እየተሰማት ያለው፡፡ ያሰበችውን ያህል ደስታ አልተሰማትም…ግን ቢሆንም ያሰበችውን በእቅዷ መሰረት ፈፅማዋለች....አሁን የሚቀራት ስህተቱን ተከትሎ መድህኔና ጊፊቲ ግንኙነታቸውን በዛው እንዲቀጥሉ ማድረግ ሲሆን በቀጣይነት ደግሞ ብቻውን የሚቀረውን ቃልን ብቻዋን ወደአለችው ወደራሷ ማምጣት…አዎ የመጨረሻ ግቧ ያ ነው፡፡አሁን መተኛት ስለፈለገች በአልጋ ልብሱ ሙሉ አካሏን ሸፈነች፡፡

ይቀጥላል
👍13323🤔14👏9😱5👎3🔥3😁1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ጊፍቲ ሕይወት ቀፏታል.. ሁሉ ነገር ጭልምልም ካለባትና ክፉ በሆነ በሀይለኛ እራስ ምታት በታጀበ ድባቴ ውስጥ ከገባች ሳምንት ሞላት

…..በዚህ ሀዘን ላይ በጣላት ክስተት ማንን ተወቃሽ እንደምታደርግ አለማወቋ ነው ይበልጥ ህመሟን ያጠነከረባት…ሰው ሰውን ሲቀየምና ሲጠላ ምንም አይደል…ሰው አምላኩን ቢቀየምም ምንም አይደል(ምክንያቱም አምላክ ለምን ተቀየማችሁኝ ብሎ እልክ በመጋባት ጥበቃውን አያቋርጥም)…. ሰው ራሱን ከተቀየመና ከጠላ ግን አደገኛ ነው…እራሱን የጠላ ሰው ለምንም ነገር ደንታ አይኖረውም.. እራሱን የጠላ ሰው ነገሮችን በቀና ሁኔታ  የማስተካከል ተነሳሽነቱ ዜሮ ነው…. እራሱን የጠላና የተጠየፈ ሰው አለምን እንዳለ ለማጥፋት እና ለማውደም ዝግጁ ነው፡፡ ጊፍቲም  በአሁኑ ጊዜ እንደዛ ነው የሆነችው..እራሷን ነው የጠላችው..እራሷን ነው የተጠየፈችው፡፡

ጊፍቲ ከደነዘዘችበት መቀመጫ ላይ ተስፈንጥራ ተነሳችና  ወደ መኝታ ክፍሏ አመራች፡፡ አልጋው ላይ በጀርባው ተዘርራ አይኗን ጣሪያዋ ላይ ተክላ ምስቅልቅል ሀሳቧቾን ታስብ ጀመር ..ደግሞም ተነሳችና  ኮሞዲኖ ላይ የተቀመጠውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳችና ከእነ ጠርሙሱ አፏ ላይ ደቅና አንደቀደቀችው………. የንዴት እና ሽንፈት አጠጣጥ ነበር፡፡እሩብ ያህሉን አጋምሳና ቀሪውን ይዛ ወደ መስኮቱ ተጠጋችና በጨለማው እየተሸነፈ ያለውን ውጭ እየቃኘች ምን ማድረግ እንዳለባት ማሰብ ቀጠለች‹‹ህይወቷን እንዴት ማስተካከል ትችላለች…?ከቃልስ ጋር እስከወዲያኛው ተለያይታ እንዴት ትችለዋለች? …. ሰውነቷ በላብ ወረዛ‹‹መሆን የለበትም በፍጹም አይደረግም ቃልዬን አጥቼ መኖር የለብኝም አዎ እራሴን ማጥፋት አለብኝ.. እናቴ ወደላችበት መቃብር እራሴን እልካለሁ ››በውሳኔዋ ረካች…. እና ከት ብላ ሳቀች..የንዴት ሳቅ…..የመበለጥ ሳቅ….የተሸናፊነት ሳቅ…ተስፋ የመቁረጥ ሳቅ..የእብደት ሳቅ ››
በዚህ ወቅት እቤቷ ተንኳኳ…ዝም ባለች ቁጠር የማንኳኳቱ ኃይል እየጨመረ ሲመጣ እንደምንም እግሯን እየገተች ሄዳ ከፈተችው…ስትከፍት ያገኘችው ሰው ግን ፍፅም ያልጠበቀችውና ስትሸሸወ የነበረ ሰው ነው፡፡

‹‹ውይ ምነው? ምን አደረኩህ?››

‹‹እኔስ ምን አደረኩሽ…?››
‹‹በራፉን ትታ ፊቷን ወደውስጥ መለሰችና እንዳመጣጧ እግሯን በመጎተት  ተራምዳ መቀመጫ ይዛ ተቀመጠች.እሱም ወደውስጥ በመግባት በራፉን ዘጋና ተከትሏት ከፊት ለፊቷ ተቀመጠና ማውራት ጀመረ…
‹‹ስልክ አይሰራም…ስትረጋጊ ትደውያለሽ ወይም ወደቤት ትመጪያለሽ ብዬ ጠበቀኩ ጠበቅኩ..ሲያቅተኝ መጣሁ .
‹‹ስልኬን የዘጋሁት እኮ ሰው ማግኘት ስለማልችል ነው…በተለይ አንተን››አይኖቹን ማየት አቅቷት አንገቷን ደፍታ የቤቱን ወለል እያየች መለሰችለት፡፡

‹‹ተይ እንጂ ጊፍቲ…እራስሽን መቅጣትስ ሳያንስሽ እኔንም ለምን ትቀጪኛለሽ..በጣም እኮ ነው የናፈቅሺኝ››

‹‹ቃል አይገባህም እንዴ ?እንዴት ብዬ ነው አንተን ለማግኘት ድፍረቱ ሚኖረኝ…?በጣም እኮ ነው የቆሸሽኩት …›
‹‹ሰው ሊሰራ የማይችለውን ምን የተለየ ተአምር ስራሸ …በዛ ላይ እንደሰማሁት በወቅቱ ሁላችሁም በጣም ጠጥታችሁና እስከመጨረሻው ሰክራችሁ ነበር….ለወደፊቱ ተመሳሳይ ስህተት ላለመስራት ከክስተቱ ትምህርት መውሰድ እንጂ እንዲህ እቤት ውስጥ እራስን እስረኛ በማድረግና አምርሮ በመቆዘም የሚቀየር ነገር የለም፡፡››
‹‹አሁን ጥፋቴን ቀለል አድርጎ በማቅረብ የምትደልለኝ ይመስልሀል?››

‹‹አይ እየደልኩሽ  አይደለም..የሚሰማኝን እውነት እየነገርኩሽ ነው…በውስጥሽ ያለውን ጨላማ ሀሳብ አስወግጂ
….በመሀከላችሁ ስር የሰደደ ጥላቻ መቼም ሊኖር አይችልም..እስኪ ነገሩን በራስሽ ገልብጠሸ አስቢው …አሁን አንቺ የሰራሁት የምትይውን ስህተት እኔ ሰርቼው ቢሆን ኖሮ አይንህ ላፈረ ብለሽ እስከወዲያኛው ፊትሽን ታዞሪብኝ ነበር፡፡ ምንስ ነገር ብበድልሽ አምርረሽ ልትጠይኝ ትችያለሽ.?ለዛ አቅሙ አለሽ?››

‹‹ቃል እንዲሁ አትድከም….ምንም ብትል መፅናናት አልችልም….በሰራሁት ቀሺም ስህተት ምክንያት በውስጤ የሚሰማኝ  ህመምና .ህሙም ያሳደረብኝን  ቁስለት ሊረዳልኝ የሚችል  አንድ ሰው በዚህ አለም ላይ አይኖርም…?ከአሁን በኃላ ህመሜን ብቻዬን ስታመም እኖራለሁ..ምን አልባት የመከራዬ መግል ሽታ የእኔ የሆኑትን ሰዎች እየከረፋቸው ስለሚቸገሩ ቀስ በቀስ ከጎኔ ሊጠፉ ይችላሉ….››ንግግሯን አቋረጠችና  እየተንሰቀሰቀች መነፍረቅ ጀመረች……ቃል መቀመጫውን ለቆ ተነሳና ከጎኗ ተቀመጠ...ቃላት ሳይጠቀም ወደደረቱ ጐተታትና አቀፎ ግንባሯን በመሳምና   ፀጉሯን በማሻሸት  ያጽናናት ጀመረ፡፡
‹‹ቃልዬ›› ለስለስ ባለ ድምጽ ጠራችው

‹‹ወዬ ጊፍቲ››

‹‹በፈጠረህ አንድ ነገር ላስቸግርህ፡፡››

‹‹ምንደነው  የፈለግሺውን››አላት

በውስጡ ግን አሁን ይቅር በለኝና ዛሬውኑ እንጋባ ብትለኝ ምን መልስ እሰጣታለሁ? እያለ መሳቀቅ ጀምሮ ነበር፡

‹‹እስቲ ስደበኝ…ሸርሙጣ ነሽ፤ከዳተኛና አዋራጅ ሴት ነሽ… ብለህ ስደበኝ ..ከተቻለህም በጥፊ አጠናግረኝ…ምራቅህንም ሀክ እንትፍ ብለህ ግንባሬ ላይ በመትፋት ጥለኸኝ ሂድ..ያዛን ጊዜ ትንሽ ቀለል ይለኝ ይሆናል፡፡››በማለት ያልጠበቀውን ንግግር ተናገረች፡፡አሳዘነችው፡በውስጡም የጥፋተኝነት ስሜት ያሰቃየው ጀመር፡፡
‹‹እንደዛ መቼም እንደማላደርግ ታውቂያለሽ…አንቺ ለእኔ እኮ ፍቅረኛዬ ብቻ አይደለሽም እህቴም ጭምር ነሽ…››
‹‹ይሄው እንደገመትኩት ክፉ እኮ ነህ..ሰውን የምትቀጣበት መንገድ መራር ነው…ያንተ ቅጣት ነፍስ ላይ ነው ጠባሳ ሚጥለው፡፡››
‹‹ስለተበሳጨሽ ነው እንዲህ የምትይው…ጊዜ የውስጥን ቁስል ይፈውሳል…ለራስሽ ጊዜ ስጪና ለመረጋጋት ሞክሪ…ሰው ስለሆንሽ ሰው ሚሰራውን ነገር ነው የሰራሽው ስህተት ቢሆን እንኳን ይቅር የማይባልና የማይስተካከል ስህተት የለም፡፡››
‹‹እንዴት ..?እስኪ ንገረኝ ብልቴ ውስጥ ሲዋኝ ያደረውን ብልቱን እንዴት አድርጌ እንዳልተፈጠረ ማድረግ እችላለሁ…?ዕድሜ ልኬን ላንተ እንኳን ከመስጠት ሰስቼ ሳሽሞነሙነው የነበረውን ድንግልናዬንስ እንዴት አድርጌ ወደቦታው ልመልሰው እችላለሁ..?ነው ወይስ ሰርጀሪ ላሰራው?፡፡››
‹‹ጊፍቲ ኮ… ተይ እንጂ.. አንቺ እኮ በጣም ጠንካራ ልጅ ነሽ ፡፡ በህይወትሽ ብዙ ከዚህ በጣም የከፉ አስቸጋሪ  መከራዎች አጋጠጥመውሽ በትግስትና በብልሀት አልፈሻቸዋል…አሁንም ንም ትወጪዋለሽ…ታውቂያለሽ እኔም ከጎንሽ ነኝ፡፡››

‹‹ተው ቃል ….በዚህ ልክ የህይወቴን መስመር ድብልቅልቁን የሚያወጣ መከራ ገጥሞኝ አያውቅም ወደፊትም አይገጥመኝም…ልፋ ሲልህ የማይሰራ ምክር ነው እየመከርከኝ ያለኸው...ተመልከተኝ እስኪ ክስተቱ ልቤን አድቅቆታል፤ ውስጤን  በታትኖታል…፡፡አዎ ሞራሌን ተሰባብሯል …ሰባአዊነቴንም አክስሞብኛል…  የሚቧጥጥ ጥፍርና..ያገጠጡ ስል ጥርሶች ያሉት   የሚዘነጣጥልና የሚሸረካክት አውሬ በውስጤ እየተፈጠረ ይመስለኛል….እኔ በጣም መጥፎ ሰው ነኝ  …? መጥፎነት ፈፅሞ አይግልጻውም..ፈፅሞ…››መለፍለፎን ማቆረጥ አልቻለችም፡፡
👍86😢128🔥2👏1