አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

“መንግሥታችሁን ታጥናላችሁ፤ አልጋችሁን ትጠብቅላችሁ” እያሉ
መረቋቸው።

ሕዝቡ ከሚፈልጋቸው ነገሮች አንዱ አብያተ ክርስቲያናት
እንዲሠሩለት በመሆኑ ምንትዋብ ስለጉዳዩ ከልጇ ከብርሃን ሰገድ
ኢያሱ ጋር መከረች። ኢያሱ አስራ አንድ ዓመት አልፎታል። ንጉሠ
ነገሥቱ እሱ በመሆኑ፣ሳታማክረው የምታደርገው ነገር የለም።

አንድ ከሰዐት በኋላ፣ ቤተመንግሥት እንግዳ መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል። ሁለቱም ያንን መጠነኛ ስፋት ያለውን ክፍል ይወዱታል።ቅልብጭ ያለ በመሆኑ፣ የልባቸውን ለመጫወትና ስለመንግሥት ሆነ
ስለራሳቸው ጉዳይ ለማውራት ይመቻቸዋል።

ቀይ ከፋይ ጨርቅ የለበሱ ወንበሮች ዙርያውን ተደርድረዋል።
ምንትዋብ ከመግቢያው በስተቀኝ በኩል ከቀንድ የተሠራው የካባና
የባርኔጣ ማሳረፊያ ላይ ጎን ለጎን የተሰቀሉትን የእሷንና የእሱን ካባዎች ትመለከታለች። የቀረበላትን ጠጅ ቀመሰችና ቀና ብላ አየችው።

ኢያሱ ደረስህልኝ። እንዲህ አድገህ በማየቴ ታላቅ ደስታ
ይሰማኛል። ደጅ ኻልወጣሁ እያልክ ምታስቸግርበት ግዝየ ስንኳ ሩቅ አልነበረም። ያነዜ ዛዲያ አንዱ ይገድልብኛል እያልሁ እጨነቅ ነበር።አሁን እያደግህ ስትመጣ ሁሉ ነገር እየገባህ መጣ። እዝጊሃር ይመስገን” አለችው።

“አንቺ እኮ ለኔ በጣም ስለምትጨነቂ ነው እንጂ ምወጣውና ምገባው ኸሰው ጋር ነው። ምኑ ነው ሲጨንቅሽ የነበረው?”

“አየ ኢያሱ የእናት ሆድ ምን ያለ እንደሆነ አለማወቅህ ነው
እንዲህ ሚያስብልህ። አሁን እንደምታየው አገራችን ሰላም ሁኗል እኔም እንግዲህ ፊት አንስቸልህ እንደነበረው ልቤ ያለው ቤተክሲያን ማሠራት ላይ ነው። ድኻው ቤተክሲያን እንድናሠራለት ይፈልጋል ። እኔም ብሆን ነፍስ ካወቅሁ ዠምሮ ክፍሌ ለሆነችው ለቁስቋም ማርያም ቤተክሲያን ማሳነጽ ፈልጋለሁ። ጃንሆይም እኮ በነገሡ ባመታቸው ነው
ኸዝኸ ኸጐንደር ቅዱስ ሩፋኤልን የተከሉት። ደፈጫ ኪዳነ ምረትንም
እሳቸው ናቸው የደበሩ። አያትህ ታላቁ ኢያሱም ቢሆኑ ደብረብርሃን
ሥላሴንና አደባባይ ተክለሃይማኖትን የመሳሰሉ ቤተክሲያኖች ተክለዋል። ታቦት ተሸክመው እደብረብርሃን ሥላሤ ከመንበሩ ሲያገቡ ማዶል እንዴ፡-

ወዴት ሂዶ ኑራል ሰሞነኛ ቄሱ፣
ታቦት ተሸከመ ዘውዱን ትቶ ኢያሱ።
የተሸሽገውን ያባቱን ቅስና፤
ገለጠው ኢያሱ ታቦት አነሳና።
አየነው ኢያሱ ደብረብርሃን ቁሞ፣
ሰውነቱን ትቶ መላክ ሆነ ደሞ።
ሥላሴን ቢሸከም ኢያሱ ገነነ፤
ላራቱ ኪሩቤል አምስተኛ ሆነ።
ተብሎ የተገጠመላቸው?” አለችው።

ፈገግ አለ።

ጐንደር የገባች ቀን ያየቻቸውን፣ ከዚያ በኋላ የተሳለመቻቸውን፣
የደጎመቻቸውንና ሳትሰስት ጉልት እና መሬት የሰጠቻቸውን አብያት
ክርስቲያናት ሁሉ ባየችና ባሰበች ቁጥር፣ ጐንደር የቤተክርስቲያን
ባለፀጋ እንደሆነች ብታውቅም፣ የኔ የምትላትን እንደምታሠራ ስትዝት ቆየታ ጊዜው አሁን ነው pብላለች። ከባሏ ሞት በኋላ፣ “ሁሉን በግዝየው ማረግ” የሚለው ሐሳብ አእምሮዋን በመግዛቱ ጊዜ ሳታባክን ማድረግ
ያለባትን ማድረግ እንዳለባት ራሷን ስታስታውስ ቆይታለች።

እናም እንዳልሁህ ለቁስቋም ቤተክሲያን ላቆምላት ተነስቻለሁ።"

“አንቺ እናቴ እንዳልሽው ይሁን” አላት።

“ያባቶችህ በረከት አይለይህ። እኔ መቸም አሳቤ ብዙ ነው።
ቤተክሲያን ብቻ ሳይሆን ለኔም ቤተመንግሥትና ሌላም ሌላም ማሠራት ፈልጋለሁ። አንተም የራስህ መኖሪያ ያስፈልግሀል። ይኸ ላንተ ሊሆንህ ይችላል” አለችው።

አሁን የሚኖሩበት አፄ ፋሲለደስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ስላሠራችው
ቤተመንግሥት እያወራች። ቀጥላም፣ “ሙያ ያላቸው ጠርአና ሶሪያዎቹ ኸኛ ሰዎች ጋር ሁነው ቢሠሩ ብዬ አስቤያለሁ። እንዳው እንደ ገብረሥላሤ ያለ ግንበኛ ባገኝማ! እንዳው እንዴት ያለ ግንበኛ ነበር ይላሉ። በአያትህ ግዝየ ዠምሮ ነበረ። ኸኛ ሰዎችም አላፊ ሁነው ሚሠሩም መድባለሁ።”
ባለችው ተስማማ።

ሳይውል ሳያድር ግንበኞችና ባለሙያዎች ተቀጥረው ከፋሲለደስ ቤተመንግሥት እምብዛም ሳይርቅ፣ ጉብታ ላይ የደብረ ፀሐይ ቁስቋም ግንባታ ተጀመረ። ባጭር ጊዜ መቃረቢያው ተሠርቶ አልቆ ቅዳሜ
ቀን ታቦተ ሕጉ ከአቡነ ክርስቶዶሉ ቤት ተነስቶ ወደ ቁስቋም ሲወሰድ፣የፊት ዐጀብ ከፊት እየመራ፣ የጎንና የኋላ ዐጀብ ተከትሎ፣ አስቴር ብላ የሰየመቻትን ሕፃን ከግራዝማች ኢያሱ በቅርቡ የወለደችው አራሷ ምንትዋብ በበቅሎ፣ ዳግማዊ ኢያሱ በፈረስ ሆነው፣ የወርቅ በትረ መንግሥታቸውን ጨብጠውና ግርማ ሞገስ ተጎናጽፈው፣ ለሽኝት
ወጡ።
ዐቃቤ ሰዐቱና ዕጨጌው እነሱን ሲከተሉ፣ ካህናቱ ቀይና አረንጓዴ
ለብሰው ሰንደቅ እያውለበለቡ፣ የወርቅና የብር መስቀልና የወርቅ
ፀናፅል ይዘው፣ እየዘመሩና እያሸበሸቡ፣ ነጋሪት እየተጎሰመ፣ መኳንንቱ፣ሊቃውንቱ፣ ወይዛዝርቱና ባለሟሉ ደግሞ እንደየደረጃቸው ተሰልፈው
ተከተሉ።

ሕዝቡ መንገድ ዳር ቆሞ መሬት እየሳመ በዕልልታና በሆታ
ተቀበላቸው። ታቦተ ሕጉ በአቡኑ ተባርኮ ቤተመቅደስ ገባ።

ምንትዋብም ዋናውን የቁስቋም ማርያም ሆነ የሌሎች ግንባታዎችን እንዲከታተሉ አዛዥ ተክለሃይማኖትን፣ አዛዥ ሕርያቆስን፣ አዛዥ ናቡቴን፣ አዛዥ ማሞንና በጅሮንድ ኢሳያስን የበላይ ተቆጣጣሪ አድርጋ
ሾመች። ግሪክና ሶርያውያን ሕንጻ ሥራ አዋቂዎችም ተፈልገው
መጥተው ከሃገሬው ሰው ጋር ሆነው እንዲሠሩ ተደረገ።

ምንትዋብና ኢያሱ ከሥራው አልተለዩም። ምንትዋብ ዘወትር
ጠዋት የቤተመንግሥት ጉዳይ ከፈጸመችና ካስፈጸመች በኋላ፣ እሷ በቅሎ ላይ፣ ኢያሱ ፈረስ ላይ ሆነው በባልደራስ በር ወጥተው ቁስቋም ግንባታ ስፍራ ይሄዳሉ።

ኢያሱ ከቀቢዎች ጎን ሆኖ እየቀባ፣ እሷ እየተቸች፣ ያልወደደችውን
እያስፈረሰች፣ ራሷ በምትፈልገው መሠረት እያሰራች፣ ዕንጨት
ከአርማጨሆና ከወልቃይት እያስመጣች፣ በድንጋይ ባለ ሰባት በሯ ቁስቋም ማርያም ተሠራች። ውስጥ መግቢያ ደረጃዎቿ ከሕንድ በመጣ ሸክላ ተሰሩላት። ግቢዋ ዝግባ፣ ጥድና ወይራ ተተከለበት፣ አፈር ደብረ
ቍስቋም ከምትገኝበት ሃገር ከግብፅ መጥቶ ተበተነበት። ቁስቋም ከውስጥና ከውጭ በወርቅ አሸበረቀች።

ምንትዋብ በሥዕል ልታስጌጣት ብላ ያንን የልጅነት ምስሏን የላከውን ሠዓሊ ማስመጣት ፈለገች። ትዝ ሲላት የሰውየውን ሆነ የመነኩሴውን ስም አታውቅም። መነኩሴውን ራሳቸውን ማን ብላ እንምታስፈልጋቸው ግራ ገባት፤ ተበሳጨች።
በመጨረሻም ቁስቋም ጐንደር ባሉ ሠዓሊዎች ሥራዎች አጌጠች።ምንትዋብ ከውስጥ የማርያምን ሥዕል አሥላ፣ ከፋይ ካባዋን በትንንሹ አስቀድዳ ዙርያውን አስለጠፈችበት::

ግንባታ መጠናቀቂያው ላይ ማስጌጫ ገንዘብ ሲያጥር፣ ሥራው እንዳይቋረጥ ምንትዋብ ከራሷ ወርቅ፣ ቀለበቷ ሳይቀር፣ ሰጠች።አንድ ሰሞን ጐንደር “ጉድ” አለ፤ “እቴጌ የጣታቸው ቀለበት ሳይቀር ለቤተክሲያን ማሠሪያ ሰጡ” እያለ አደነቀ።

የቁስቋም ማርያም ግንባታ በሦስት ዓመት ውስጥ ተጠናቀቀ።

ታቦቷ በታላቅ በዓል ቋሚ ማደሪያዋ ስትገባ ሕዝቡ፣ “እሰይ! እሰይ!” አለ፣ አመሰገነ። ካህናቱ ምንትዋብንና ኢያሱን፣ “
ለማርያም ቁስቋምን
እንዳቆማችሁላት፣ ቤተመቅደሷንም ዐይናችሁ እንቅልፍ ሳያይ ደፋ ቀና
ብላችሁ እንደሠራችሁላት፣ ለናንተም ትቁምላችሁ። መንግሥታችሁን ታጥናላችሁ፤ አልጋችሁን ትጠብቅላችሁ” እያሉ መረቋቸው።

ምንትዋብ ከልጇ ጋር ቁስቋም ማርያምን ማደራጀት ላይ አተኮረች። አንድ ቀን፣ የየደብሩን ካህናትና ሊቃውንት ወርቅ ሰቀላ ሰበሰበቻቸው።

“እቴጌ ምን ሊሉን ነው?” እያሉ እርስ በእርስ ተጠያየቁ።
👍10
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


....ምንትዋብ አልጣሽ የተባለችውን ሁለተኛ ልጇን ወልዳ ከአራስ ቤት እንደወጣች እንደገና በግዛት ዘመኗ ልትፈጽማቸው ያሰበቻቸው ነገሮች ላይ ትኩረት አደረገች።

ትምህርት ቁስቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማስጀመር ከብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጋር መከረች። ብዙ ጊዜ እንደሚያደርጉት አንድ ቀን እንግዳ መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል።

ትክ ብላ አየችው። ፈንጣጣ ፊቱ ላይ ምንም ምልክት ሳይተው
ማለፉ ገረማት። በቁስቋም ረድኤት መዳኒቱ ሠርቷል። ይኸን የመሰለ መልኩን ሊያበላሽብኝ እሷ የቁስቋሟ ማረችልኝ፡፡ አሁን ኢያሱን የመሰለ ልዥ አለ? የተባረኩ እያለች በሐሳብ ጭልጥ ብላ ሄደች።

ኢያሱ በሐሳብ እንደነጎደች ኣውቆ ከሄደችበት እስክትመለስ ዐይን
ዐይኗን እያየ ጠበቃት።

“አያትህ ታላቁ ኢያሱ ለትምርት ብዙ ዋጋ ሚሰጡ ሰው ነበሩ…
አለችው፣ ከሄደችበት ስትመለስ።

“አውቃለሁ። አንቺም ነገርሽ ሁላ እንደሳቸው ነው። ደሞስ የሳቸው
ስም መቸ ኻፍሽ ጠፍቶ ያውቃል?”

ከት ብላ ስትስቅ እሱም ሳቀ።

“ስለ ትምርት ላወራህ ፈልጌ ነው የሳቸውን ስም ያነሳሁ” አለችው፣
ፈገግ ብላ። “በሳቸው ዘመን የተማሮች ቁጥር ኸዝኸ ኸደብረሥላሤ ስንኳ ብዙ ነበር ይላሉ። ስንክሳርም በብዛት የተጣፈው በሳቸው ግዝየ
ነው። እንደ ክፍለ ዮሐንስ የመሰሉ ሊቃውንትም ኸጎዣም ያመጡ
እሳቸው ናቸው። ሊቁ አዛዥ ከናፍሮም ቢሆኑ በሳቸው ግዝየ ነው የነበሩ። ዛዲያ ልነግርህ የፈለግሁት ቁስቋም ውስጥ ትምርት ቤት ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ ለተማሮቹና ላስተማሮቹ ድጋፍ ማረግ አለብን
ሚለውን ነው።”
“እኔም ስለሱ ነግርሻለሁ እያልሁ ነበር። ሌላ ደሞ ባለፈው መጻሕፍት ኻረብኛና ኸዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ እንዲመለሱ ፈልጋለሁ ስትይ
ማልነበር?”

"ትርጉም.... አዎ ስል ነበር። ሁሉ ባግባቡ ነው። ባለፈው መላከ
ጠሐይ ሮብዓምን ትርጉም ላይ ቢበረታ ብያቸው ኻረብኛና ኸዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ሚመልሱ ሰዎች አምጥተው ሥራ እንዲዠምሩ ተደርጓል።
ለእነመላከ ጠሐይ ሃይማኖትን ሚያስተምረውንና ላገር ሚጠቅመውን ሁሉ እንዲያስተረጉሙ ነግሬያቸው እነሱ ተመካክረው ወስነዋል።”

"የትርጉም ሥራ ለገዳማቱ ቢሰጥ ጥሩ ነው ሲሉ ሰምቸ።”

“ዛዲያ ምን አለ... ይሰጣል ። በጎ አሳብ ነው። ትዛዝ ሰጣለሁ። እኔ
መቸም ቢሞላልኝ አገር ሁሉ መጻፍ በመጻፍ እንዲሆንና ትምርት
እንዲስፋፋ ነው ምፈልግ። እኔ ራሴም ብሆን አንድ ቀን ስለ እመቤታችን ማርያም ታምር አስጥፋለሁ ብየ አስባለሁ። ደሞ እሑድ እሑድ ለሊቃውንቱና ለካህናቱ ግብር እናግባላቸው። አንተም ለነሱ ትልቅ ክብር አለህ። ቅኔም ተምረሀል። ቅኔ እውቀቴ እንዳንተ ባይሆንም፣ሊቃውንቱ ቅኔ ሲቀኙ ስሰማ መንፈሴ ሁሉ ይታደሳል። በተለይማ
የአክስትህን ልዥ እመት ወለተብርሃንን ስሰማ እንዳው እንደሳቸው ቅኔ በቻልሁ እላለሁ፡፡ አንተማ ኸኔም የበለጠ ትወዳቸዋለህ።”

የአክስቱ ልጅ ነገር ሲነሳ ፈገግ አለ። “ውነትሽ ነው እመት ወለተብርሃን ታላቅ የቅኔ ሊቅ ናቸው። እሑድ እሑድ ግብር ለሊቃውንቱና ለካህናቱ ማግባት ያልሽው ተገቢ ነው። በተነጋገርነው መሠረትም በአካባቢው ወይን እንዲተከል ቦታ ብታስጠኚ። ቃሮዳ አየሩ ለወይን ተስማሚ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ። ቅርብም ነው።”

“ውነትህ ነው። ዛሬውኑ ሰው ይላካል።”

ሁለቱም ዝም አሉ።

“ግና ካህናቱና ሊቃውንቱ... ምናለ ልብሳቸውን ቢያጠዱ?” አላት።

ያልጠበቀችው በመሆኑ ከት ብላ ሳቀች። “ልብሳቸውን እንዲያጥቡ
ማረግ ይቻላል ። በጐንደር ዙርያና በየገዳማቱ እንዶድ ኣስተክለን
ልብሳቸውን እንዲያጥቡ እናረጋለና” አለችው፣ አሁንም እየሳቀች።

“ዋናዎቹ ካህናት ደሞ የወርቅ ጫማ እንዲያረጉ ፈልጋለሁ።”

“ወርቅ አሳብ ነው። ይታዘዝላቸዋል። የአክብሮትህ ምልክት ነው።

እንደገና ዝም ብለው ተቀመጡ። ኢያሱ ሐሳብ የገባው ይመስላል።
እሷም ዝም ብላ ታየዋለች።

ዐይን ዐይኗን እያየ፣ “አደን ብኸድ ትፈቅጅልኛለሽ?” እናቱን ፈሪና
አክባሪ ነው።

ዕጢዋ ዱብ አለ። አፏ ተያዘ። ሊመጣበት የሚችለው አደጋ
አሳሰባት። ጥያቄው ግን አንድ ቀን እንደሚመጣ ታውቃለች።

“ኣባትህ ስንኳ በኸዱ ቁጥር እጨነቅ ነበር። ኢያሱ እንድትኸድ
አልፈልግም፤ ጭንቀቱን አልችለውም።”

“ምን ችግር አለው?”

“ባትኸድ መርጣለሁ። ኢያሱ አልጋውን እኮ ባየነቁራኛ ሚጠባበቅአለ!”

“ሁሉስ እያደኑ ማዶል እንዴ የኖሩት?”

“ገና ልዥ እኮ ነህ ኢያሱ።”
ድምጽዋ ተርበተበተ።

“አትጨነቂ። ምንም ሚመጣ ነገር የለም። ሰዎች ይዠ ነው ምኸደው
በዝኸ ላይ ደሞ አልቆይም።”

“ኻንተ መለየት አልፈቅድም ኢያሱ ... መቸ ትነሳለህ?”
ነገ።”
“ነገ?”
“አዎ! ነገ።”
“ታሰብህበት ቆይተሀል ማለት ነዋ! መቸስ ምን ኣረጋለሁ። ቁስቋም
ደሕና ትመልስህ። በጠሎቴ አልለይህም።”

አይዞሽ አትጨነቂ። በጠዋት ስለምኸድ ካሁኑ ልሰናበትሽ” አላት፣ጠዋት መጥቶ ቢሰናበታት እንባዋን ማየት ስለማይችል። ተነስታ ወደ እልፍኟ ስትሄድ በጭንቀት ተመለከታት።

በማግስቱ ጠዋት ከእናቷ ጋር በመስኮት ቆመው የአደን ዕቃው
በቅሎ ላይ ሲጫን አይተው ሆዳቸው ባባ። ኢያሱ ፈረሱ ቀርቦለት፡ በሹሩባው ዙርያ ነጭ ሻሽ አስሮ፣ ካባውን ደርቦ ከዐጀቡ ጋር ብቅ ሲል፣ የቤተመንግሥት ባለሟሉ፣ ወታደሩ፣ ጋሻ ጃግሬውና ሌላው ሰገደ።ምንትዋብና እናቷ ግን ሲቃ ያዛቸው።
ከቤተመንግሥት ግቢ ሲወጣ፣
ምንትዋብ ጩሂ ጩሂ አላት። እንኰዬ ትከሻዋን መታ መታ አደረጓት።እሳቸውም እንባ እንባ ብሏቸዋል፤ ግን እሷን ማረጋጋት መረጡ።

ሁለቱም በየክፍላቸው ገብተው ወገባቸውን በገመድ አስረው ሱባዔ ገቡ። መሬት ላይ ተኙ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ጸሎታቸው ሠምሮ ኢያሱ በሰላም ተመለሰ። እናትና ልጅ ገመድ ትጥቃቸውን ፈቱ።የነበሩበትን ጭንቀት ሳይናገሩ በደስታ ተቀበሉት።

እያደር የአደን ፍቅር በረታበት፤ መዝናኛው አደረገው። በሄደ ቁጥር
እናቱና አያቱ ወገባቸውን በገመድ ጠፍረው መሬት መተኛትና ሱባዔ
መግባት፣ ሲመጣ ደግሞ ገመዳቸውን ፈትተው መጣል፣ ጸማቸውን መፍታት ልማድ አደረጉት። እንደዚህ እያለም ኢያሱ የከፋ ነገር ሳይገጥመው ቀለል ያለ አደን ማካሄዱን ቀጠለ።

ከእናቱ ጋር በተስማሙት መሠረት ከንባብ ቤት እስከ ትርጓሜ ቤት
ደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያምን በትምህርት ለማደራጀት ወጡ ወረዱ።ሁለት መቶ የሚጠጉ ምርጥ ሊቃውንት ከጐንደር ገዳማትና ከሌላ የሃገሪቱ ክፍሎች እየመጡ ወንበር ዘረጉ
የተማሪ ጎጆዎች ተቀለሱ። ትምህርት ከቁስቋም ሌላ በየገዳማቱና በየደብሮቹ ተስፋፋ። ወሬውን የሰማ ተማሪ ከየቦታው ፈልሶ ጐንደር ገባ፡፡ ጐንደር ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የሊቃውንት ማፍሪያና
መሰብሰቢያ ሆነች። ከጐንደር ውጭም ትምህርት ቤቶች ተስፋፉ።

የዜማ ሊቃውንት ድርጎ በማግኘታቸው ሙያቸውን አበለፀጉ ቤተክርስቲያንን አገለገሉ፤ ቤተመንግሥትንም አዝናኑ።

የሥዕል ሥራ በአያሌው አደገ። ቀለም አጠቃቀም ጥንት ከነበረው
ለውጥ አመጣ፣ የአቀራረብና የይዘት ለውጦች መጡ። ሠዓሊዎች ድጎማ እየተደረገላቸው አብያተ ክርስቲያናትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስጌጡ።
👍9
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


“አንተ የሥዕል ንጉሥ ነህ።”

ጥላዬ፣ የአለቃ ሔኖክን አርባ አውጥቶ፣ የምንትዋብን ንግሥ በዐይኑ በብረቱ አይቶ ደብረ ወርቅ ከተመለሰ በኋላ፣ ከዐዲሱ መምህሩ ከአለቃ ግዕዛን ጋር ትምህሩቱን ቀጠለ።

ብራና እያስጌጠ የሚያገኘውን እህል ወይም አሞሌ ጨው ምግብ ለምታቀርብለት ኮማሪት.. እንጎች.. እየሰጠ፣ የዓመት ልብሱን እየለበሰ ትምህርቱን ተያያዘው። ሥነ-ስቅለትን ከሠራ በኋላ በሙያው ትልቅ ዕመርታ አሳየ። ስሙ በደብረ ወርቅ ብቻ ሳይሆን ዲማና ሌሎችም ቦታዎች ድረስ ተዛመተ።

ለምንትዋብ የላከላት ሥዕል ምን ዓይነት ስሜት እንዳሳደረባት
ለማወቅ እየሞከረ መልስ ስለማያገኝለት ነገሩን ይተወዋል። እነማይ መነኩሴው ዘንድ ሄዶ ሊጠይቃቸው ያስብና ስሙ በአካባቢው እየታወቀ
በመምጣቱ ከመሄድ ይቆጠባል ።

በትምህርቱ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት ወስኖ ወደሚቀጥለውና
የመመረቂያ ሥራው ወደሆነው ትኩረቱን አደረገ።

“እንግዲህ እስታሁን የሣልኻቸው በሙሉ ፍጡራን ናቸው። አሁን
አንድ ቀን፣ አለቃ ግዕዛን ቤት ተቀምጠው ሲጫወቱ፣ አለቃ ግዕዛን፣የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ የሆነውን አምላካችንን... አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሤን - የኃያላኑ መቀመጫ የሆነውን - መንበረ ፀባኦትን መሣያ ግዝየህ ነው” አሉና፣ ባለቤታቸው ባፈና እንዲሰሙት ያልፈለጉትን ነገር
ለመናገር እጁን ይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

ወደ ጥላዬ ዞረው፣ “የሥላሤ ምሥጢር ሴትና ምሥጢሩን ማወቅ የሌለበት ሰው ፊት አይወራም። ሥላሤ ምሥጢራቸው ጥልቅ፣ ሐሳቡ
ረቂቅ ስለሆነ ነው። ይኸ አሁን ምትሥለውና የመጨረሻ የሆነው፣
ከሁሉም ሚከብደውና ለመሣልም ጥንቃቄ ሚጠይቀው ሥራ ነው.
ምሥጢሩም ጥልቅ፣ ሐሳቡም ረቂቅ ነውና” አሉት።

“ሦስት አካል በአንድ አምሳል፣ ያለ ምንም ልዩነት መሣሉ ነው?
ሲል ጠየቀ፣ ከተቀመጠበት ተነሥቶ።

“ኣየ... እሱማ ተስተውሎ ይሠራል።”

“ዛዲያ ምኑ ነው ሚከብድ?”

“የሥላሴን ሥዕል ኣይተኻል?”

“ኣብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሉ?”

“አድምጠኝና ልንገርህ። ሥላሤ ሚሣሉበት ሠሌዳ ዐራት ማዕዘን
ይሆንና በዐራቱም የማዕዘኖች መገናኛ ላይ ሌሎች ዐራት እኩል
ማዕዘኖች ይሠመራሉ። ስምንት አልሆኑም?”

ጥላዬ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ።

“የሥላሤ በስምንት ማዕዘን መሣል ሚያመለክትህ፣ አንደኛ የስምንቱ
የሰማይ መስኮቶች ምሳሌ መሆናቸው፣ ሁለተኛ የዓለም ቅርፅ ይዘው በክብ እኩል ማዕዘን ውስጥ መቀመጣቸው ሲሆን ሦስተኛ በተመሳሳይ መልክ መሣላቸው ነው። በስምንቱ መስመሮቹ ውስጥ፣ የሰው፣ የአንበሳ፡ የላምና የንስር ምስሎች ይሣላሉ። አየህ ያልተመራመረ ተመልካች እነዝኸን በየማዕዘኑ የተሣሉ ዐራት ፍጡራን ምንነት ብትጠይቀው ዐራቱ ወንጌላውያን ናቸው ብሎ ይመልስልህና ያልፋል።”

“ዛዲያ የምንድር ናቸው?”

“አትቸኩል ላስረዳህ ነው። አየህ የነሱን ምንነት ለመገንዘብ
በመዠመሪያ በእኩል ነጥብ መኻል ላይ ከሚይዙት ክብ ነገር መዠመር አለብህ። ከክቡ ተነስተህ ደሞ ወደ ስምንቱም አቅጣጫ ብታሰምር፣ ሚከተለውን ክብ ንድፍ ታገኛለህ” ኣሉት፣ መሬት ላይ በስንጥር ክብ
ቅርፅ ሰርተውና በክቡ ቅርፅ ውስጥ ስምንት መስመሮች አስምረው።

ጥላዬ፣ ራሱን እየነቀነቀ የሚሥሉትን ይመለከታል።

“እንግዲህ የክቡ ትርጓሜ ዓለም በመዳፋቸው ላይ መሆኗ ነው።
ክብ የዓለማችን ቅርጥ መሆኑንና የዓለማችን ፈጣሪም መዠመሪያውም ፍጻሜውም የማይታወቀው የኅያው እዝጊሃር ምሥጢር ነው። አሁን
ዐውደ ዓመት በዐራቱ ወንጌላውያን ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ እየተመሰለ በየዐራት ዓመቱ ይመላለሳል አዶለም? በነገራችን ላይ
ማቴዎስ በሰው፣ ማርቆስ በአንበሳ፣ ሉቃስ በላም ሲመሰሉ ዮሐንስ ደሞ በንስር ይመሰላል። ይኸም ምሳሌ በዘፈቀደ የተሰጠ እንዳይመስልኸ።
የየወንጌላቸው አካኼድ ተጠንቶ ነው ይኸ ምሳሌ መሰጠቱ። እንዲያው ለአብነት ብናይ ማቴዎስ በሰው መመሰሉ 'አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፣
ይስሐቅ ያዕቆብን እያለ የክርስቶስን ሰዋዊ የዘር ሐረግ በመዘርዘር ስለሚጀምር ነው። ዮሐንስም ንሥር መባሉ 'ዘልዑለ ይሠርር' ይለዋል ከፍ ብሎ የሚበር በመኾኑ።
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ በመጀመሪያ
ቃል ነበረ ብሎ የመጠቀ አሳብ በማምጣቱ ነው። ማርቆስና ሉቃስም የየራሳቸው ትርጓሜ አላቸው፤ መጣፉን ተመልከተው። እና ዐውድ ማለት ክብ ማለት ነው። የክቡ መኻል የብርሃን መገኛ ምንጭ ነው ጠሐይ ማለት ነው። ጠሐይ ሙቀት አላት ማዶል? ሙቀቱ እንግዲህ
አብ ነው። አካሉ ደሞ ወልድ ነው... ጠሐይ አካል ማዶለች? ብርሃኑ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ጠሐይ ብርሃን እንዳላት ሁሉ። እና እኼን ሁሉ አውቀህና ተረድተህ ነው ሥላሤን መሣል ምትችለው። ደሞም በሥላሤ ራስ ላይ እግረ ፀሐይ ትሥላለኸ፤ የብርሃን ክበብ ነው። ዛዲያ ሥላሤ ብቻ ሳይኾኑ ቅዱሳን ኹሉ እግረ ፀሐይ በአናታቸው ዙሪያ ሳይደረግ
አይሣሉም። ለምን ቢሉ የሥላሤ ብርሃን ያረፈባቸው፤ መንፈስ ቅዱስ የዋጃቸው መኾኑን ማሳያችን፣ ኸጥንት የነበረ ትውፊታችን ነው።”

“ይኸ ራሱ ነገሩን ያከብደዋል።”

“ሥላሤ አንድም ሦስትም ስለሆኑ በተመሳሳይ ምንገድ ይሣላሉ።
በተመሳሳይ ምንገድ መሣላቸው ደሞ ቅድም እንዳልሁህ የፍጹም
አንድነታቸው ማሳያ ነው። ስለዝኸ የተለያዩ ገጥታዎችን አንድ ገጥታ
ሰጥተህ ነው ምትሥላቸው።”

“ተረድቻለሁ።”

“መልካም... ሥላሤን ስትሥል ግራም ቀኝም፣ ኸላይም ኸታችም
እኩል ማረግ አለብህ። ምትሥልበትን ቦታ ጭምር አመጣጥነህ ነው ምትሥል። እነሱ ጉድለት የለባቸውምና ምንም ዓይነት እንከን ሳይኖርባቸው... ምንም ዓይነት ጉድለት ሳታሳይ... ሳታዛንፍ ነው መሣል ያለብህ። አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ ማረግ አይቻልም። ፊታቸው ላይ
ሚታየውንም ገጥታ አንድ ማረግ ያስፈልጋል። ይኸን ሁሉ ስታውቅ፡
ችሎታህ ሲዳብር ነው፣ ቤተክሲያን ውስጥ መሣል ሚፈቀድልህ።፥

“እህ...”

“አዎ እንደሱ ነው ደንቡ።"

ከዚያ በኋላ፣ ጥላዬ ንባብ ላይ ተጠመደ፡፡ አለቃ ግዕዛን በአስተማሩት ላይ ተጨማሪ ንባብ አደረገ፤ ብራናዎችን አገላበጠ፤ ከሊቃውንት ጋር ተቀምጦ ተወያየ።

አለቃ ግዕዛን ሥላሤን ለመሣል በቂ እውቀት አከማችቷል ብለው
ሲያስቡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ እንዲስል ፈቀዱለት።

የመጨሻዎቹ ቀናት ቤቱ ውስጥ በር ዘግቶ ጾምና ጸሎት ያዘ። ተንበርክኮ፣ “አምላኬ ሆይ፣ ማደርያህ የሆነችው ቤተክርስቲያንህ ውስጥ ገብቸ መዐዛቸው ዕጣን ሳይሆን ወንጌል የሆነውን ሥላሤን መሣያ ግዝዬ ስለደረሰ ጥበብን ስጠኝ። መልካቸውን ግለጥልኝ። አንተ አበርታኝ”ሲል አምላኩን ተማጸነ። በረከት ይሆነው ዘንድ የቅዱሳንን ገድል እንዲሁም ወንጌልን እየደጋገመ አነበበ።

ከሦስት ተከታታይ ሱባኤያት በኋላ፣ እሑድ ቀን ሥጋ ወደሙን
ተቀበለ። ሰኞ ጠዋት፣ ከእንቅልፉ ሲነቃ የፀሐይ ጨረር በበሩ ቀዳዳ
ገብታለች። የረፈደበት መስሎት ሥላሤ ፊት መቅረቢያ ሰዐቱ ስለደረሰ ተጣጠበ። የክት ልብሱን ለብሶ፣ ራሱ ላይ እንደወተት የነጣ ጥምጥም አድርጎ፣ በባዶ ሆዱ፣ ደጅ ሲወጣ ፀሐይቱ ሞቅ ብላለች። ብርሃኗ ዐይን
ያጥበረብራል። ሰማዩ ጥርት ብሏል።

ደስ ደስ አለው። የሰማዩ ጥራት ማረከው። ፀሐይቱና ሰማዩ የዛሬ
ውሎው የተቃና እንደሚሆንለት ቃል ኪዳን የገቡለት መሰለው።
መንፈሱን አበረቱት። በዚያች ቀን በሕይወት መኖሩም አስደሰተው።
አቤቱ አምላኬ! ይችን ቀን ስላሳየኸኝ ከልቤ አመሰግንሀለሁ። የዛሬ
ሥራየንም እንደዝች ጠሐይ የበራ እንደዝኸ ሰማይ የጠራ አድርግልኝ
ኣለ።
👍134
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ሰሞኑን ቀለሞቹ ከደረቁለት በኋላ፣ እየተመላለሰ ሲቀባ፣ ሲያስተካክል፣ ሲያበጃጅና ሲሞሽር ቆይቶ ከአምስት ቀናት ድካምና ጥንቃቄ የተሞላው
ሥራ በኋላ፣ ሦስቱን ሥላሤ ሥሎ ጨረሰ። የመጨረሻው ቀን ራቅ
ብሎ ሥዕሉን ሲመለከት ተደነቀ። ሦስቱም በሁሉም አቅጣጫ እኩልና የተመጣጠኑ ናቸው። አንድም የተዛነፈና ከቦታው ውጭ የሆነ ነገር የለም። የፊታቸው ገፅታ ፍፁም ተመሳሳይ ነው። ፊታቸው ሙሉ ለሙሉ ይታያል። በሰማያዊ፣ በቢጫ፣ በነጭና በቀይ ቀለማት አምረዋል።

ተንበርክኮ ምስጋና አቅርቦ ወጣ።

በማግስቱ፣ አለቃ ግዕዛን ከሊቀጠበብት አዳሙ፣ ከአለቃ ተክለየሱስና ከሊቀጠበብት ያሬድ ጋር መጥተው ሥዕሉን ተመለከቱ። ጥላዬ፣ከኋላቸው ቆሞ፣ በእነዚህ ታላላቅ ሠዓሊዎችና የሥዕል መምህራን ላይ ያሳደረውን ስሜት ለማወቅ ተጠባበቀ።

መምህራኑ ፈዘው ተመለከቱ፤ የሚያዩትን ማመን አቃታቸው።

አለቃ ግዕዛን፣ “ጥላዬ፣ ይኸ የፍቅር ውጤት ነው። ፍቅር ብቻ ነው ይኸን የመሰለ ሥራ ሊያሠራ ሚችለው። እስታሁን በሥራህ ደስተኛ ነበርሁ። ዛሬ ግን ይኸን የመሰለ የላቀ ሥራ ስላሳየኸኝ አከብርሃለሁ።

ይኸን የመሰለ የጥበብ ውጤት እንዳይ ዕድሜ ለሰጡኝ ሥላሤ ምስጋናዬን ሳቀርብ፣ ላንተ ደግሞ አድናቆቴን ገልጣለሁ። አንተም ሥላሤን ብቻ ሳይሆን እኔንም ነው ያከበርኸኝ። እኔን እንዳከበርኸኝ አንተን ደሞ ሥላሤ ያክብሩህ። አንተ የሥዕል ንጉሥ ነህ። ከይኸ ቀደም ማንም አልቀደመህም፣ አሁንም ሚደርስብህ የለም ወደፊትም ሚተካህ ዠግና
ሚመጣበት ግዝየ ሩቅ ነው” አሉት፣ ደብቀውና ተጠንቅቀው የያዙትን፣ለማንም ተማሪ አድረገውት የማያውቁትን ምስጋና እያዘነቡለት።

ጥላዬ እግዚሐር ይስጥልኝ ማለት ፈልጎ፣ ልሳኑ ተዘጋበት። በዝምታ
እግራቸው ሥር ተደፋ።

“ተነስ ልዥ ። ንጉሥ እሰው እግር ሥር ኣይወድቅም” አሉት።

ሊቀጠበብት አዳሙም፣ “ውነትም የሥዕል ንጉሥ ነህ። አንተ ዛሬ
ግዕዛንን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ነው ያከበርኸው፣ ያኮራኸው። ውበት ማለት ይኸ እንጂ ሌላ ምን አለ? አንተ ለብዙ ተማሮች አርአያ
ትሆናለህ። ሚያሳዝነው ሥዕል እንደዝኸ ድንቅ ነገር ሁኖ ሳለ እንደ ቅኔና ዜማ በርካታ ተማሮች የሉትም። ደብረ ወርቅ እንደመጣህና ትምርት እኔጋ እንደዠመርህ፣ ውነትም የሥዕል ንጉሥ እንደምትሆን አውቄ ነበር። የናትህ ማጠን ይለምልም። ዛሬ የአለቃ ሔኖክ ነፍስም በሰማይ ቤት ትዘምራለች። ሥላሤ እጅህን ያለምልሙት” ብለው
ሊስሙት ሲጠጉት፣ ፈጠን ብሎ እግራቸውን ሳመ።

አለቃ ተክለየሱስና ሊቀጠበብት ያሬድም አድናቆትና ምስጋና
አዥጎድጎዱለት፤ ባረኩት፤ እንኳን ደስ ያለህ ብለው ሳሙት። እሱም
እግራቸውን ሳመ።

በምስክር ፊት በሥዕል ትምህርት ተመረቀ።

የመመረቂያውን አነስተኛ ድግስ እንዲቀምሱለት ሁሉንም ወደቤቱ
ይዟቸው ሄደ። እንጎች ያዘጋጀችውን ምግብ በልተው፣ አረቄ ጠጥተው አመስግነውትና መርቀውት ሊሄዱ ሲሉ፣ ሊቀጠበብት ያሬድ በድንገት
ሲቆሙ፣ ሌሎቹም ቆሙ።
ሁሉንም በተራ እየተመለከቱ፣ “በሉ ወንድሞቼ ኸመኼዳችን
በፊት አንድ ቅር ያለኝን ጉዳይ ልናገር ነው” አሉ። “ተማሪ እናታባቱ ያወጡለትን ስም እየተወ ለራሱ ስም ያወጣል። ዜማ ሲማር 'ጥዑመ ልሳን ነኝ ይላል። ቅኔ ሲማር ባሕረ ጥበብ ነኝ... ማንቴስ ነኝ ይላል።አንዳንዴም እሰበሱ ስም ይሸላለማል። ይኸ ልዣችን ግን ትሑትና የሥራ ሰው በመኾኑ ይኸው የባላገር ስሙን እንደያዘ ጥላዬ እንደተባለ
አለ። ምሥጢሩ ደግ ነው፤ ጥላ ከለላ ትኾነኛለኽ ሲሉ ማዶል አባቱ
“ጥላዬ ማለታቸው? ድንቅ ስም ነው። ግና ለእንዳንተ ያለ ጠቢብ
ዛሬ እናንተ ወንድሞቼ ኸፈቀዳችኹልኝ 'ሥሙር' ብዬዋለኹ። ደሞም አይኾንም። ሠዓሊ ተኹኖ ጥላዬ መባል ምሥጢሩ አይገጥምም። ስለዚኸ
ፊቱኑ የነበረ ወግ ነው። መምህራን ለጥበብ ልዦቻቸው ይስማማል
ያሉትን ስም ይሽልማሉ። እና ምን ትላላችኹ? ሥሙር አይዶለም
ጥላዬ?”
ሁለቱም መምህራን በአንድ ድምጽ በደስታ አደነቁት፣ “ቃለ ሕይወት ያሰማዎ ጌታዬ፤ ድንቅ ነው፤ ሥሙር ነው፤ ስሙም አሰያየሙም የተገባ ነው” ብለው አጸኑለት።”

መምህሮቹ በደስታ እያውካኩ ሲሄዱ ሸኝቷቸው እንደተመለሰ መደብ ላይ ጋደም አለ። የተዋጣለት ሥራ እንደሠራ አረጋገጠ። ሕልሙ ሁሉ
እውን ሆነ። ቋራ እያለ ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን? ያለውን አስታወሰ።ምኞቱ ሠመረ።

ዝናው በደብረ ወርቅ ብቻ ሳይሆን፣ አድባራቱን አልፎ መርጡለማርያም ድረስ ዘለቀ። በየደብሩ ያሉት የሥዕል መምህራን እንዲያስተምር
ገፋፉት። ዝናውን የሰሙ የአካባቢው ባላባቶች ደብራቸውን እንዲያስጌጥ ተረባረቡበት።

እሱ ግን አንዴ ለአንዱ ባላባት አድሮ መሥራት ከጀመረ ወደሌላው መሄድ ስለማይችል ለማንም አልታዘዝ አለ። በተጨማሪ፣ ሥዕል ታሪክ
ተናጋሪ፣ አስተማሪ፣ አብራሪ፣ ስሜትንና አእምሮን ቀስቃሽ እንጂ ለስም መጠሪያ ቤተክርስቲያን ማስዋቢያ ብቻ ሆኖ መወሰድ እንደሌለበት ተናገረ። በባላባቱ ዘንድ ቅሬታን አተረፈ።

ጐንደር ተመልሶ መሄድ ፈልጎ ከሀያ ዓመት በላይ በመቆየቱ
ባይተዋር የሚሆን መሰለው። ጐንደርን እንደዛ ወዶ ይህን ያህል
ርቆ መቀመጡ አልገባ አለው። ደብረ ወርቅ ብዙ አስተምራዋለች።
በርግጥም የሥዕል ንጉሥ አድርጋዋለች። ሆኖም ደብረ ወርቅ
የሕዝብ ዓይነት አይታይባትም። ደብረ ወርቅ ነዋሪዎቿን
የጐንደርን ዓይነት ታላቅነትና ግርማ ሞገስ የላትም። እንደ ጐንደር አድርጋ የመቀመጥ ባህርይ ሲኖራት፣ ጐንደር አደባባይ አውጥታ ታሟግታቸዋለች፤ የቤተክርስቲያን ምርጫ ትሰጣቸዋለች፣ ለድሆቿ
የእንፋሎት መታጠቢያ እንኳን አዘጋጅታለች።
ታዲያ ይህችን ጐንደርን እንዴት አድርጎ ለዘላለም ይተዋት? እንደ
ወለቴ የልጅነት ፍቅሩ፣ የጎልማሳ ዘመኑ ትዝታው አይደለችምን?
ጐንደር ለመሄድ ባሰበ ቁጥር፣ “እቴጌ ኸባላቸው እት ልዥ ጋር
ወዳጅነት ያዙ” የሚለውን ወሬ መርሳት ስላልቻለ ልቡ ያመነታል።
ባሏ ከሞቱ ጊዜ የቀድሞው ስሜቱ አንሰራርቶ የነበረው ዜናውን
ሲሰማ ልቡ ተሰርጉዶ ምንትዋብ ላይ ቅሬታ አድሮበታል።

በምንትዋብ ቅር መሰኘቱ ቅር የሚያሰኘው አልፎ አልፎ ደግሞ
የሚያስቀው ነገር ሆኖ አግኝቶታል ቅሬታው የመነጨው እኔ ይህን
ያህል ስለእሷ ሳስብ እሷ እንዴት ሳታስፈልገኝ ቀረች በሚል ነው።
የሚያስበው ሁሉ ተገቢ እንዳልሆነ ቢያውቅም፣ “ውነት ትወደኝ ኸነበረ እንዴት አታስፈልገኝም?” ብሎ ደግሞ በስጨት ይላል። በሌላ በኩል አፄ በካፋ ሲሞቱ ልቡ ውስጥ የተስፋ ጭላንጭል የተቀረፀበትን ጊዜ ያስብና ከት ብሎ ይስቃል። ድጋሚ ሌላ ሥዕል ሊልክላት ወሰነ።ሆኖም እንደመነኩሴው ታማኝ ሰው እንዴትና የት እንደሚያገኝ ማሰብ
አቃተው።

ቀደም ብሎ ስለአብርሃ ወሬ ይሰማ የነበረውን ያህል ባለመስማቱም በሕይወት ይኖር ይሆን እያለ መጨነቁም አልቀረም። ካንድ ሁለት
ጊዜ መልዕክት ልኮበት ሳይደርሰው ቀርቶ ይሁን ወይንም ደርሶት ዝም ብሎት እንደሆነ ለማወቅ ተቸገረ።

አንድ ቀን፣ ደብረ ወርቅ ማርያም ውስጥ የቅኔ መምህር ከሆኑት
ከመጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ ጋር ቤተክርስቲያኗ ግቢ ውስጥ ያለ ጥድ ስር ተቀምጠው ሲጨዋወቱ በቅርቡ ጐንደር ሄደው እንደነበር ነገሩት።

“እደብረብርሃን ሥላሤ ደርሰው ነበር?” አላቸው።

“አዎን።”

“እንዲያው መጋቤ አብርሃ ሚባል ጓደኛ ነበረኝ። መልክትም
ብልክበት አልደረሰው ሁኖ ነው መሰለኝ መልስም አልሰጠኝ።”
“አሉ። መቸም ጐንደር ኻፈራቻቸው ሊቃውንት አንዱ ናቸው ነው ሚሉ።”

ጥላዬ ደስ አለው። ጐንደር የመሄድ ፍላጎቱ ተነሳሳ።

“እንዴት ያለ ጥሩ ነገር ነገሩኝ። እኔማ ተጨንቄ ቆይቻ።”
👍10
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

“ደብረ ወርቅ ማርያም የሥዕል ንጉሥ አለ።”

የአስራ ስምንት ዓመቱ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ በትምህርት የበሰለ፣
በአስተሳሰቡ የበለፀገ፣ በመልኩና በአቋሙ ያማረ ሆነላት ምንትዋብ።ፈረስ ላይ ተቀምጦ፣ ነጭ ሻሹን ሹሩባው ላይ አስሮ፣ በወርቅ ያጌጠ ካባውን ደርቦ፣ የወርቅ በትረ መንግሥቱን ጨብጦ፣ ቀይ ድባብ ተይዞለት፣ ባልደራስ አጅቦት ከግቢ ሲወጣ፣ ሕዝቡ፣ “አቤት አበቃቀሉ!
አቤት የፊቱ አወራረድ!” እያለ አደነቀው: ወደደው፤ አከበረው፤
ሰገደለት፤ “ቋረኛው ኢያሱ” የሚል ቅጽል ስምም አወጣለት።

አደን አፍቃሪው ኢያሱ እንደ በፊቱ ሰስና ድኩላን ሳይሆን፣ ዝሆን፣
አውራሪስና ጎሽ እየገደለ መምጣት ጀምረ። ምንትዋብና እናቷ ግን ለአደን በወጣ ቁጥር ወገባቸውን በገመድ እየታጠቁ፣ መሬት እየተኙ፣ እየጸሙና እንቅልፍ እያጡ ይሰነብታሉ።

ኢያሱ በድፍረቱና በጀግንነቱ ተወዳዳሪ አጣ። ስለሃገር ጉዳይም መከታተል፣ ውሳኔ መስጠትና እርምጃ መውሰድ ያዘ። ከእናቱ መዳፍ ሥር ወጥቶ የራሱ ሰው ሆነ። አክሱም ጽዮን ሄደ። የእናቱን የትውልድ
ቦታ ለማየትም ቋራ ደርሶ መጣ። አንድ ጊዜ የግዛት ማስፋፋት ፍላጎቱ አድጎ ሰቆጣ ሄዶ ተሸንፎ ቢመጣ፣ በቁጭት ወኔውን ሞልቶ ሱዳን ጠረፍ ሄደ፡፡

የገጠመውን ጦር አሸንፎ በሰላም ተመለሰ።
በሰላም ይመለስ እንጂ ከእናቱ ጋር አተካራና ቅያሜ ውስጥ ገባ።
በግራዝማች ኢያሱና በእናቱ መሃል ያለው የፍቅር ግንኙነት ይከነክነው
ገባ። ምንትዋብም ወለተእስራኤል ያለቻትን ሦስተኛ ልጇን ከወለደች
ቆይታለች።

ኢያሱ እናቱ ላይ ቅሬታና ምሬት አደረበት። ምንም እንኳ እናቱን
ቢያከብርና ቢፈራ፣ ከግራዝማች ኢያሱ ጋር ያላትን ግንኙነት ችላ
የማይለው ጉዳይ ሆነበት።

ፀሐይ መግቢያ ላይ ነው። እናትና ልጅ ቤተመንግሥት እንግዳ
መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል። ኢያሱ ነገር ሲገባው ታውቃለች
ምንትዋብ። ገና፣ “ኸያሱ ጋር..” ሲልና ሲጠጣበት የነበረውን የወርቅ ዋንጫ ሲያስቀምጥ፣ የንግግራቸው አቅጣጫ ወዴት እንደሆነ ገባት።

“ኸያሱ ጋር ባለሽ ግንኙነት ሰው ሁሉ ያማሻል። ቀደም ብየ ብሰማም ዕድሜየም ገና ስለነበር ፈርቸ እስተዛሬ በዝምታ ቆየሁ” አላት።

“ኢያሱ አባትህኮ ሲሞቱ ዕድሜዬ ገና ነበር። ብቸኛም ነበርሁ።
ልችም መውለድ ፈልግ ነበር። ደሞስ እንዲህ ያለው በኔ ተዠመረ?” አለችና፣ ለራሷ ዛዲያ እንዴት ልሁን ሰው መሆኔ ቀረ? እቴጌ ያሉኝ እንደሁ ሰው ማይደለሁ እንዴ? ሰው መሆን ዛዲያ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? ስትል መናገር ሲጀምር ቀና አለች።

“የመዠመርና ያለመዠመር ጉዳይ ማዶል” አለ፣ እናቱ ላይ አድርጎ
በማያውቀው መንገድ ፊቱን አኮማትሮ።

ከእሷ ስሜት በላይ ክብር የሚባል ነገር አለ።

መልስ አልሰጠችውም። ስሜቱ እንደተጎዳ አውቃለች። እባክህ
አምላኬ ኸልዤ ጋር እንዳልጣላ ትግስት ስጠኝ አለች።

“ኢያሱ አንደኛ ያክስቴ ልዥ ነው” ሲል ቀጠለ። “ያባቴ እት...
የወለተስራኤል ልዥ እኮ ነው። ያባቴ ክብርስ ቢሆን፣ ስለምን ይነካል? ላንቺም ቢሆን ነውር ነው። ስለምንስ ስማችን በዝኸ ይነሳል? መልካም ስምሽንስ ስለምን ታጎድፊያለሽ? ግራማች ብትይውም ሰዉ አሁንም
ምልምል ኢያሱ ነው ሚለው። ኸዝኸ ወዲያ ውርደት ምን አለ?”

ንግግሩ ጎመዘዛት። ከንፈሯን በጥርሷ ነከስ ኣድርጋ በግራ ሌባ ጣቷ መታ መታ አደረገችው። ቁጣ ሰውነቷ ውስጥ ሲቀሰቀስ ተሰማት።

“ተው እንጂ ኢያሱ! እኔን እናትህን እንዲህ አትናገር። ምወድህ
እናትህ እንጂ ሌላ ነኝ?”

“ሰዉ ያማሻል እኮ!” ግንባሩ ኩምትር ብሏል።

“አምተው በቅቷቸዋል። ኢያሱ ... ኸግራማች ጋር ተዋልደናል እኮ!
እህቶችህ የማን ይመስሉሃል? እኔ ያባትህን ስም ለማጉደፍ ሳይሆን፣
ብቸኝነት ስላጠቃኝ ነው። ተረዳኝ እንጂ!”

“ኸዝኽ ወዲያ ውርደት ምን አለ?” የሚሉት ቃላቶቹ ረበሿት። ትክ ብላ አየችው። ፊቱ ላይ ቅያሜ አየች። ዛዲያ ዕድሜዬን እንዲሁ
ላሳልፍ ኑሯል እንዴ? አለች።

ለእሱ የክብር ጉዳይ እንደሆነ አላጣችውም። እንኳንስ የባሏን
የእህት ልጅ ባሏ የሞተባት ንግሥት ጨርሶ ሌላ ማግባት እንደሌለባት ታውቃለች።

ግን ደግሞ ውጣ ውረድ ከበዛበት የቤተመንግሥት ሕይወት ዘወር ብላ የምትዝናናበትና ሐሳቧን የምትከፍልበት ነገር ባለመኖሩ፣
አንድ ቀን ከልጇ ጋር የሚያቃቅራትና አልፎም ሊያጣላት የሚችል ነገር እንደሆነ ብታውቅም አድርጋዋለች።

ከልጇ ጋር ይህን ያህል ጠንከር ያለ ንግግር ተለዋውጠው ስለማያውቁ ቅር ብትሰኝም፣ የምትወደውንና የምትሳሳለትን ገራሙን ልጇን መቀየም
አልሆነላትም። ቅሬታና ቅይሜ በሆዷ አምቃ መሄድ አልፈለገችም።

የአባቱ ብቻ ሳይሆን የእሱ፣ ብሎም የእሷ ክብር እንደተነካበት ስላወቀች ትችቱን ተቀብላ ዋጥ ማድረግን ፈለገች።

በራሷ አምሳል ቀርጻ ያወጣችው ቢመስላትም፣ እየተመካከረች፣
ሲሻትም እየተጫነችው ያሳደገችው ልጇ ብሩህ አእምሮ ያለውና በራሱ አስተሳሰብ የሚመራ መሆኑን በመገንዘብ ልቧ ላይ ሊሰርፅ የቃጣውን
ቅሬታ ለመግታት ታገለች።

ለብቻው ለመግዛት ዕድሜው ቢፈቅድለትም፣ ለእሷ ካለው ፍቅር፣አክብሮትና ፍራቻ ጭምር የእሷን የበላይነት ተቀብሎ መኖር እንደቻለ ተገነዘበች። እሱም ቢሆን ከሥልጣኗ ለማውረድ የሚያስችለው በቂ
ምክንያት የለውም።

እንዲያውም የእሱ መንግሥት በእሷ ብርታት፣ ጥበብና ዘዴ የተሞላው አመራር መደላደሉን፣ አንዳንድ መኳንንት ቋረኞች ላይ ያላቸውን ጥላቻ አርግባ ተስማምታና አስማምታ መቆየቷን፣ ከአንዴም ሁለት
ጊዜ የተቃጣባቸውን ዓመጽ ድል መቀዳጀታቸውን፣ ሌሎችን ደግሞ
በሰላማዊ ድርድር እየፈታች ሰላም እንዲሰፍን ማድረጓን ይገነዘብ
እንደሆነ ራሷን ጠየቀች። ይህን ልታስታውሰው ግን አልፈለገችም፤
ዝም ብላ ተቀመጠች። ተነስቶ ሲወጣ በተለመደው የእናትና የልጅ ፍቅር አልተሰነባበቱም።

ከሄደ በኋላ፣ የተነጋገሩትን ሁሉ በጭንቅላቷ ከለሰችው። መቸም
እኔስ ብሆን በነገሩ ሳልጨነቅ ቀርቸ ነው? አልሆንልኝ ብሎ ነው እንጂ።ብቸኝነት አጥቅቶኝ ነው ኸኢያሱ ጋር እዚህ ሁሉ ውስጥ የገባሁት።እሱም ቢሆን እነአስቴርን የመሳሰሉ ልዦች ሰጥቶኛል። ኸንግዲህ
ምን አረጋለሁ። የአብራኬ ክፋይ እንዲህ ሲለኝ መስማት ለእኔ ደግ
ማዶል። መቸስ የክብር ጉዳይ ሆኖበት ነው። በዝኸ አልቀየመውም። እነሱ እንዳይጣሉብኝ እንጂ። ለግራማች ኢያሱ ነግረዋለሁ እያለች አሰላሰለች።

ግራዝማች ኢያሱ፡ “ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ተለውጦብኛል” ማለት
ሲያዘወትር፣ እንዳይጣሉባት ሰጋች፤ በሐሳብ ባከነች። እየቆየም በሁለቱ መሃል ነገሮች እየከረሩ፣ ግንኙነታቸው ወደ ፀብ መቀየሩ እንቅልፍ አሳጣት። አስታራቂ ሽማግሌዎች ላከች።
ይህ ሳያንሳት በመጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ አማካኝነት ሁለተኛው የጥላዬ ሥዕል መጣላት። የሥዕሉ ውበትና የያዘው ጥልቅ ሐሳብ
ቢያስደስታትም፣ ሁለቱም ሥዕሎች ከአንድ ሥሙር ከሚባል ሰው መምጣታቸውን በሥራው አረጋገጠች፤ ለወራት ተረበሸች።
እነዚህን ሥዕሎች የሚልከው ሰው ምን አስቦ እንደሆነ ለማወቅ
ቸገራት። እኼ ሰው ስለምን ማንነታቸው ስንኳ በማይታወቅ ሰዎች ይልካል? ይኸ ከበጎ አሳብ የመጣ ነው ወይንስ እኔን ሰላም ለመንሳት ሚደረግ እኔ ለራሴ ኸልዤ ጋር ችግር ውስጥ በገባሁበት ግዝየ ስለምን
እንደዝኸ ያለ ነገር ይገጥመኛል? አንቺ ምወድሽ ቁስቋም የዝኸን ሰው ማንነት አንቺው ግለጭልኝ እያለች ማርያምን ተለማመነች። ለሌላ ሰው የማታዋየው ምሥጢር ሆኖባት ሥዕሉን በመጣበት ጨርቅ መልሳ ጠቅልላ ከበፊተኛው ሥዕል ጋር ደብቃ አስቀመጠችው።
👍14
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....የቁስቋም ግቢ ግብር አዳራሽም ሥራ በተቀላጠፈ መንገድ ተያያዘ።አዳራሹ ውስጡ ከላይም ከታችም ለምንትዋብና ለኢያሱ መቀመጫ የሚሆን ገባ ያለ ቦታ ተሠራለት። በስተቀኝ በኩል ስድስት፣ በስተግራ
ደግሞ አምስት ማሾ ማስቀመጪያ ሸክላዎች የሚይዙ ድፍን መስኮቶች ተደረጉለት።

ሠራተኛው ከፊሉ ድንጋይ ሲያግዝ፣ ሌላው ዕንጨት ሲያቀርብ፣የቀረው ሲለስን፣ ኖራ ሲቀባ፣ አነዋሪው ተቀምጦ ወይም ቆሞ እየተዟዟረ ሲያነውር፣ የተበላሸውን ሲጠቁም፣ በትክክል ያልተለሰነ ወይንም በትክክል ያልገባ ዕንጨት ወይንም ድንጋይ ሲያይ ሲጠቁም ኢያሱ
ከሠራተኛ ጋር ሲሠራ፣ እናትና ልጅ እርስ በእርስ፣ ከሙያተኞችና
ከሠራተኞች ጋር ሲወያዩ፣ ሐሳብ ሲሰሙና ሲሰጡ ይቆያሉ።

“እስቲ በሉ የተበላሸ ያያችሁትን ተናገሩ” ትላቸዋለች ምንትዋብ፣
ሠራተኞቹን።

“እቴጌ ኸግማርዳ ጥዱ አይሻልም ኑሯል?” ይላታል አንዱ ግንበኛ።

“ግማርዳ ነው እንጂ ለንድህ ያለው” ይላል ሌላው።

“ሁሉም ለመጡበት ጉዳይ ያገልግላሉ” ይላሉ እናትና ልጅ።

ሠራተኞቹ ነገሥታቱ ከእነሱ ጎን ሆነው መሥራታቸው፣ የእነሱን ሐሳብ መስማታቸው አስደነቃቸው። እንደ ሰማይ ከዋክብት ሩቅ የመሰሏቸው፣ ብሎም እንደነሱ ከስጋና ከደም የተሰሩ የማይመስሏቸው የነበሩት ነገሥታት ሰው ሆነው አገኟቸው። በተለይም ደግሞ ኢያሱ ራሱ ሥራው ላይ ተሰማርቶ ከእነሱ እኩል ሲቀባና ሲሠራ አይተው
ተደመሙ።

ወትሮውንም ማንም ፍርድ ፈላጊ ሰተት ብሎ ቤተመንግሥት ገብቶ
እንዲዳኝ ስላደረገ፣ ፍትሕ ለጎደለበት ፍትሕ ስለሰጠና ለድኃ ስለቸረ ይወዱትና ይሳሱለት ነበረና እንደዚህ በቅርብ ከነሱ ጋር ሲሠራ ሲያዩት ይበልጥ ወደዱት።

አንድ ጠዋት ሠራተኞቹ በግብር አዳራሹ አንድ ወገን ላይ እየተሠራ
ስላለው ረጅም የእንቁላል ቅርጽ ያለው ግንብ ድምጻቸውን ዝቅ
አድርገው ያወራሉ። ምንትዋብና ኢያሱ ጎን ለጎን ቆመው የተሠራውን ሥራ ይመለከታሉ።

“አላየህም እንዴ ኸዛ ላይ ሁነህ? ቀሀ እኮ ወለል ብሎ ይታያል” አለ፣
አንዱ ግንበኛ።

“ቀሀ ትላለህ? ጣና ይታይ የለ? ቀሀማ ኸዝሁ ነው።” ከት ብሎ ሳቀ ሌላው።

“ጣና ይታያል ነው ምትሉት?” አለች ምንትዋብ፣ በመገረም።

“አዎ እቴጌ ሲያልቅ ያዩታል። እንዲያው ጣና ወለል ብሎ ነው
ሚታይ” ኣላት፣ አንደኛው ግንበኛ።
“እስቲያልቅ ምን አቆየን፣ አሁን አናየውም?” አላት ኢያሱ።

እናትና ልጅ ፎቁ ላይ ወጡ።

“ውነት ነው ኢያሱ። ያውልህ ... ያ ሚታየው ጣና እኮ ነው። ይኸማ
ለጥበቃ አይሆንም። ለኔ ነው ሚሆን” አለችው።

“ውነትም ወለል ብሎ ይታያል። ቀሀም ይኸው። ውነትሽ ነው።
ላንቺ ይሆናል። ዐጥሩ ተሠርቶ ሲያልቅ ቁስቋም ፊት ለፊት እንደ
ተደረገው የጥበቃ ሰቀላዎቹ ዙርያውን ይሠራሉ።”
ምንትዋብ ደስ አላት። እንዴት እሰተ ዛሬ አላሰብሁትም ብላ
ተገረመች። የተመረጡ እንደ ግራዝማች ኢያሱ፣ ሮብዓምና ሌሎችም እንግዶች መቀበያና ለራሷም መዝናኛ እንደምታደርገው ወሰነች።

አንድ ቀን፣ ምንትዋብ አፄ ፋሲለደስ ቤተመንግሥት ልጇ ኢያሱጋ ለመሄድ፣ በልዩ ልዩ ጌጣ ጌጥ የተሸለመችው በቅሎዋ ላይ ተቀምጣ፣የእሷና የኢያሱ መግቢያና መውጫ ብቻ በሆነው በር ከዐጀቧ ጋር እንደ ሁልጊዜው ባለ ወርቀ ዘቦ ድባብ ተይዞላት ከግቢ ወጣች።

ቤተመንግሥት ስትገባ እንደወትሮው ሁሉም ሰገዱላት። ወደ ኢያሱ መኖሪያ አመራች። ኢያሱ ወጥቶ በደስታ ተቀበላትና ውስጥ ገብተው ጨዋታ ጀመሩ። ኢያሱ ልትነግረው የምትፈልገው ነገር ሲኖር ያውቃል። ምን ልትነግረው፣ ወይንም ምን ልትጠይቀው እንደፈለገች
በጉጉት መጠበቅ ለምዷል።

“ኢያሱ ዛሬ የመጣሁት” አለችው፣ በመጨረሻ። “አንድም አንተን
ለማየት ሌላም ቀደም ብሎ እንደተነጋገርነው ቃሮዳና ዙርያውን
የተተከለው ወይን እንዴት እንዳፈራ ልነግርህ ነው። ትናንት ይዘው
መጡ፤ መቸስ ጉድ ትላለህ። እንዳው ማማሩን ብታይ ጉድ ትላለህ።”

“እንዴት እንደዝኸ ተሎ ደረሰ?”

“ደረሰ። ይገርምሀል። እና አሁን የግብር ቤቱም ሥራ እያለቀ ነው።
ለሊቃውንቱና ለካህናቱ ግብሩን በሰፊው እናርግላቸው።የስተዛሬው እንዳው በቂ ከልነበረም።”

“እናርግላቸው እንጂ አሁንማ። ምን እንጠብቃለን?”

“ወይኑ መጠመቅ እንዲጀምር ትዛዝ ሰጥቻለሁ።”

“መልካም ነው።”

ጥቂት ስለቤተመንግሥት ጉዳይ ከተወያዩ በኋላ ተነስታ ወጣች።
ከወራት በኋላ፣ አንድ ቅዳሜ ዳግማዊ ኢያሱ ማለዳ ላይ ቁስቋም መጣ።ሰማዩ ጥርት ብሏል። ፀሐይዋ ደምቃለች። ምንትዋብ ከቤተመንግሥቷ
በደረጃ ወጥታ ተቀበለችው። እያወሩ ቁልቁል ሲወርዱ ተሰርቶ
ያለቀውን የግብር አዳራሽ አይታ ንግግሯን አቋርጣ፣ “ኢያሱ እይልኝ!ጉድ በልልኝ! እይልኝ እንዴት እንደሚያምር!” አለችው። በደስታ እንደ ልጅ በጨፈረች ደስ ባላት፣ የቤተመንግሥት ሥርዐትና ዕድሜ አልፈቅድ ብለዋት እንጂ።

“ውነትሽ ነው ያምራል! ሁለዜ ስለምናየው እስታሁን እንደዝኸ
እንደዛሬው ማማሩን አላወቅነም እኮ።”

ምንትዋብ ቀልቧ ግንቡ ላይ ነው። አልሰማችውም።

በተጠጋች ቁጥር የግንቡ ግርማ ሞገስ አስደነቃት። የአሠራሩ ጥራት፣የልስኑ ማማርና መርቀቅ፣ የቀለሙ ውበት ከገመተችው በላይ ሆነባት።

ኣጠገቡ ሲቆሙ ስሜቷ አሽነፋትና እንባዋ ዱብ ዱብ አለ።
ከኋላቸው የቆሙት የቤተመንግሥት ባለሟሎች፣ ሠዓሊዎች፣ሮብዓም፣ ካህናትና ሊቃውንት አዳራሹን በአድናቆት ተመለከቱ።

ሁሉም በአንድ ላይ ምንትዋብንና ኢያሱን፣ “እዝጊሃር ያክብራችሁ።
የናንተ ሥራ ነው” እያሉ አመሰገኗቸው።ምንትዋብ መናገር ተስኗት የለም የለም የሁሉም ነው። ሰው ተረባርቦ ነው ይኸን መሳይ ታላቅ ሥራ የሠራው። ሁሉም ይመሰገናል። የሠሩትን
ሁሉ ትናንትም አመስግኛቸዋለሁ። ያለኝን ሁሉ ሰጥቻለሁ። እዝጊሃር
ያክብራቸው አለች፣ ለራሷ። ራሴን ማመስገን አይሁንብኝና ልክ
እንዳልሁት፣ ልክ በሰጠሁት አሳብ መሠረት እኮ ነው የተሠራ አለች።
ባልስን፣ በቀለም ምርጫና በአጠቃላይ ላይ አሻራዋን የጣለችበትን ግንብ እያየች።

በስተቀኝ በኩል ወደ ላይ የወጣውን እንቁላል ግንብ አይታ፣ እሱስ ቢሆን እንዴት አምራል? ኸ'ያሱ ጋር እንደልብ ቁጭ ብሎ ለማውራት ይመቻል አለች፣ በአደባባይ እንደልብ መገናኘት ሰለማይችሉት ስለ
ግራዝማች ኢያሱ አስባ። ኸመላከ ጠሐይ ሮብዓምም ጋር ጥሩ ወግ
መያዝ እችላለሁ ኸዝያ አለች።
ፊቷን ወደ ልጇ መልሳ፣ “ኢያሱ ኸላይ እግንቡ ላይ በግራ በኩል
ያሉትን የመስቀል ቅርጦች አየኻቸው? ቀጥሎ ያለውንስ ዘውድ?”

“ሁሉም ቁልጭ ብለው ይታያሉ። አየሽው ከጎኑ ያለውን በጉን
ሲገድል ሚታየው አንበሳ? ኸጎኑ አንበሳ ላይ የተቀመጠውስ ንጉሥ ያገራችን ምልክት! እንዴት ጥሩ ወጥቷል። ቀጥሎ ያሉት ዝሆንና
አንበሳስ እንዴት እንዳማሩ አየሽ?”

“አዎ ልክ አንተ እንዳልኸው ነው የተሠሩት። የጣድቁ የአባ
ሳሙኤልና የአቡነ ዮሐንስ ምስሎችስ ቢሆኑ እንዴት እንዳማሩ” አለች፣
የዋልድባውን መነኩሴ የአባ ሳሙኤልንና የዐዲሱን አቡን የዮሐንስን ምስል እየተመለከተች።
ራሷን አረጋግታ ዙርያውን ቃኘች። አስቀድማ ያሰበችው ሐሳብ
ሥራ ላይ የሚውልበት ሰዐት

ተቃርቧል።ወደ ኢያሱ ዞረች።

“ኢያሱ ኸዝኸ ኻዳራሹ በስተግራ በኩል ኻሰብሁት በላይ በቂ መሬትአለ። የሴቶች ሙያ ተማሪ ቤት ማሳነጽ ፈልጋለሁ ብዬ ማልነበር? ያውልህ ኸጠሎት ቤቱ ዠርባ ዋርካው አጠገብ ደሞ ሌላ ሰፊ መሬት።እሱም ቢሆን እንዳሰብሁት...”

“ምን አስበሽለት ነበር ለቦታው?”
👍15
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....የሕዳር ቁስቋም ዕለት ነው። ምንትዋብ ትልቅ ግብር ጥላለች። ምግቡም፣ወይን ጠጁም፣ ጠጁም፣ አረቄውም በገፍ ተዘጋጅቷል። አስቀድማ፣
ዛሬ ሊቃውንቱና ካህናቱ ከገቡ ወዲያ ዋናውን ሆነ የስርቆሹን በር
እንድትዘጉ። የወይን ጠጅም እየደጋገማችሁ እንድትሰጧቸው” ብላ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።

“ይኸ ሁሉ ስለምንድርነው?” ሲል ጠየቃት፣ ኢያሱ።

“ዛሬ ካህናቱንና ሊቃውንቱን ጉድ ሠራለሁ።”

“እንዴት አርገሽ... ደሞስ ስለምን?”

“እነሱ ሁልግዝየ በቅኔው፣ በተረትና ምሳሌውና በመጠጥ ያቸንፉኛል።
ዛሬ ግን እኔ አቸንፋቸዋለሁ ብዬ ተነስቻለሁ።”

ሳቀ ኢያሱ ።
ከቅዳሴ በኋላ፣ ከየደብሩ የተጋበዙት ካህናትና ሊቃውንት ወደ ቤተመንግሥት ተመሙ። ሠዓሊዎችና ሙዚቀኞችም ጎረፉ። የግብር ሥርዐት ተጠብቆ ምግብ ተበላ። የወይን ጠጅ ተቀዳ ። የካህናቱና የሊቃውንቱ ዋንጫ ሲጎድል አጋፋሪዎች በታዘዙት መሠረት እየተመላለሱ ሞሉ።

እንግዶቹ ፊኛቸው አስቸገራቸው። ሊወጡ ፈልገው ቢነሱ ከፊት
ከኋላ በሩ ዝግ ነው። የሚከፍት የለም። ተጨነቁ፤ ተጠበቡ። እየተያዩ መቅበጥበጥ ብቻ ሆነ። በመጨረሻ መለኛው ሊቅ አለቃ ኢሳያስ ተነሥተው እናትና ልጁን እጅ ነሱና፣ “እቴጌ አንድ ነገር እንድጠይቅ ይፈቀድልኝ” አሏት።

“ይበሉ ይጠይቁ።”

“እቴጌ አምስት መቶና አምስት መቶ ስንት ነው?”

ያልጠርጠረችው ምንትዋብ፣ “ምን ያለ ጥያቄ ነው? ይኸ ሊያቅተኝ? ሽ ነዋ!” አለች።

አለቃ ኢሳያስ፣ “እቴጌ “ሽናዋ' ብለዋል” ሲሉ ያ ፊኛው አስጨንቆት የነበረ ሊቅና ካህን ሁሉ የተቀመጠበትን ከህንድ ሃገር የመጣ ስጋጃ አረሰረሰ።

ምንትዋብ በመሸነፏ ሳቀች፣ ተንኮሏ እንዳልሠራ ተገነዘበች።
በእርግጥም ሊቃውንቱን ማሸነፍ እንደማትችል ተገነዘበች። አለቃ
ኢሳያስን ለብልሐታቸው ሽለመቻችው። አዲሱ የግብር ኣዳራሽም በሕዝብ ዘንድ “ሽናዋ” የሚል ስያሜ አተረፈ።

ከሽናዋ በኋላ፣ የሴቶች ሙያ ትምህርት ቤቱ ግንባታ ተጀመረ።
ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ሴቶች ተመርጠው እንደ
ፈትል ያሉ ልዩ ልዩ የእጅ ጥበባትና ዶሮ መገነጣጠል እንዲማሩ ሆነ።
ተማሪዎቹ ዶሮ አስራ ሁለት ብልት እንዳላት አወቁ። ፊደልና የቁም
ጽሕፈት እንዲከታተሉ ተደረገ። ምንትዋብ ልትጎበኛቸው በሄደች
ቁጥር በሙያና በትምህርት በርትተው እንዲማሩ አስጠነቀቀች።ከዓመታት በፊት አያቷ የነገሥታት ዝርያዎች ወህኒ ይላካሉ እዛው አርጅተው ይሞታሉ፣ ብለው ሲነግሯት፣ “ክፉ ነገር። እኼማ መሆን የለበትም” እንዳለችው ከጸሎት ቤቷ በስተቀኝ በኩል የአፄ በካፋ ዘመዶች ሆኑ የሌላ ነገሥታት ዝርያዎች ወይንም የራሷ ዘመዶች መኖሪያና መማርያ የሚሆን ህንፃ አሠርታ፣ ልጆቹ ወህኒ አምባ በእግር
ብረት ታስረው ከመማቀቅ ይልቅ ፊደል፣ የቁም ጽሕፈትና ፍትሖ
ነገሥት እንዲማሩ ሆነ።

ምንትዋብና ኢያሱ ስማቸው ከአጥናፍ አጥናፍ ገነነ።

ምንትዋብና ዳግማዊ ኢያሱ ስማቸው ቢገንም፣ አልፎ ኣልፎም ቢሆን በመኳንንቱ ዘንድ “ቋረኞች” ላይ ጥርጣሬ ስላለ፣ ምንትዋብም ብትሆን ያለነሱ ድጋፍ ርቃ እንደማትሄድ ስለምታውቅ በጉዳዩ ከኢያሱ ጋር መምከር ፈለገች።

“ኢያሱ እንዳው አንድ ነገር ላጫውትህ ብየ” አለችው፣ አንድ ቀን እንቁላል ግንብ ውስጥ ተቀምጠው እየተጫወቱ ሳለ።

“ምን ነገር?”

“እንደምታውቀው “ቋረኞች” ሚሉ ዘይቤ እንደ ዱካ ይከተለናል።
ሥልጣኑን ሁሉ ቋረኞች ይዘውታል ይላሉ። ይሰንብት እንጂ ቀን
ጠብቀው በኛ ላይ መነሳታቸው አይቀርም። የጎዣም፣ የትግሬ፣
የቤገምድርና የስሜን መኳንንት ዋዛ ማዶሉ። ይመስገነው እስታሁን ሰላም ነን። ወደ ፊት ግን እንጃ ሰላማችን ሊደፈርስ ይችላል ብየ ሰጋለሁ።ሰላም ማጣት ብቻ ሳይሆን አልጋውን ሊፈታተኑ ይችላሉ። የወህኒዎቹ
እንደሆኑ ዐይናቸው መቸም ግዝየ ኻልጋው ላይ ተነስቶ አያውቅም።
ተዘጋጅቶ መቀመጡ አይከፋም። ሥልጣን አይበቃቸው፣ ጉልት፣
ርስትና ርስተ ጉልት ለስንቱ መኳንንት ሰጠን። አይጠቅማቸውም።ኢያሱ ጥቂቱ እኮ ነው ላገሬ ሚለው። ኻለነሱ ድጋፍ ደሞ አይሆን።እነሱን ለማስታገስ ስንቱን ድሬ ጨረስሁ። አሁንም ቢሆን አርቀን ማሰብ አለብን። ነገ አንዱ ቢነሳ አጋዥ ያስፈልገናል። እና አሳቤ ምን
መሰለህ ይኸ የስሜን፣ የጎዣም፣ የቤገምድርና የትግሬ ባላባት ሁሉ
ቀልቡን ሰብስብ እንዲያረግ ወሎዎች ጠንካራ ጦር አላቸውና ኸነሱ ጋር በጋብቻ ብንተሳሰር ምን ይመስልሀል?”

“ኣሳብሽ መልካም ነው። ማነን ልታጋቢ አሰብሽ?”

“አንተን።”

“እኔን?” ከት ብሎ ሳቀ።

“አዎ አንተን:: ብዙ አስቤበት ነው። አሁን ኸወሎች ጋር መጋባት
ያስፈልጋል። የልገሮችህ እናት...” ዕቁባት ሆና ትቀመጣለች ማለት
ፈልጋ ዝም አለች።?
“እና እኔን ኸማን ልታጋቢ ነው?” አላት፣ ዝም ስትል ።

“ውቢት ምትባል የወሎ ባላባት ልዥ አለች። አጠያይቄ አለላ ናት
አሉ። ብቻ የወሎ ልዥ ስለሆነች በድብቅ መሆን አለበት።”

ኢያሱ ስለመኳንንቱ ያለችው አሳስቦት ነበርና ዝም አለ። ምንትዋብ ዝምታውን እንደ እሺታ ቆጠረች።

ብዙም ሳይቆይ ምንትዋብ የወሎ ባላባት ልጅ የሆነችውን ውቢትን
ከኢያሱ ጋር አጋባች። ውቢትን ክርስትና አስነስተው ወለተቤርሳቤሕ አሰኝተው፣ የመኳንንቱን ጉምጉምታ ለማቀዝቀዝ በድብቅ ኣስቀመጡ።
ውቢት ኢዮአስ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደች።

ምንትዋብና ኢያሱ ምንም እንኳን ራስ ቢትወደድ ወልደልዑል
መንግሥታቸውን ከዘመዶቹ ጋር አስከብሮና አጠናክሮ ቢይዝላቸውም፣ባላባቶች ከወሎ በማምጣት ሥልጣን ላይ አስቀመጡ። ሲያንገራግር
የነበረውን የጎጃሙን ባላባት ዮሴድቅን ደግሞ፣ ደጃዝማች ብለው፣ይዞታውን ጨምረው፣ በኋላ ሞጣ ጊዮርጊስን የደበረችውን ወለተእስራኤልን ድረውለት አረጋጉት።

እናትና ልጅ ያሰቡትን ሥራ ላይ ከማዋል አልቆጠብ አሉ። በተለይም ኢያሱ ለአትክልት ቦታ ልዩ ፍቅር ስለነበረው፣ ጐንደርን አፀድ በአፀድ አደረጋት። ሎሚና ሌሎች ፍሬዎች ጐንደርን የመዓዛ ባለፀጋ አደረጓት።

አብያተ ክርስቲያናትን በጭልጋ፣ አለፋ ጣቁሳና ጐንደር በኖራ
አሠሩ። ሌሎችን አሳደሱ። ጣና ሐይቅ በታንኳ እየተመላለሱ ኢያሱ
ክብራን ገብርኤልን ሲያሳድስ፣ እሷ ደቅ ውስጥ “ስሞት እቀበርበታለሁ” ያለችውን ናርጋ የኛ - ሥላሤን በጡብና በጐንደርኛ ይዘት አሠራች። ናርጋ ሥላሤን ስታሠራ፣ ሥሙር የተባለውን የራሷን ምስል የላከላትን ሠዓሊ አስታወሰች። እንዴት ሊገኝ እንደሚችል አሰበች።ሌሎች ሠዓሊዎች በሥዕል ሥራው ተሳተፉ። ናርጋ ሥላሤ በሥዕል
አሸበረቀች። ምንትዋብ አክብሮቷን ለመግለፅ ከማርያምና ከክርስቶስ
እግር ሥር የራሷን ምስሎች አሠራች። አብያተ ክርስቲያናቱ የሥዕል ባለቤት ሆኑ።

ብርሃን ሰገድ ኢያሱ “ብዙው መጻሕፍት ወደ ክብራን ገብርኤል
እንዲሄዱ ፈቃዴ ነው” ባለው መሠረት ከተለያዩ የሃገሪቱ ከፍሎች የተሰበሰቡ በሺህ የሚቆጠሩ መጻሕፍት ክብራን ገብርኤል ገብተው
ተቀመጡ።

“አንተ ደሞ ሁሉ ነገር ወደዛ እንዲኸድ ትፈልጋለህ” ብላ ፈገግ
አለች፣ ምንትዋብ አንድ ቀን። ቀጠል አድርጋ፣ “ለየደብሩ እኩል
ማከፋፈል ነው እንጂ” አለችው።
👍11
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ከንስሐ ስትወጣ መቅሰፍት ተከተላት። እሷና ኢያሱ በነገሡ በአስራ ስድስተኛ ዓመታቸው ላይ አንድ ጠዋት ምንትዋብ ወደ ጸሎት ቤት ልትሄድ ስትዘጋጅ፣ አንደኛዋ ደንገጡሯ መጥታ፣ “ኧረ እቴጌ ሰማይ ምድሩ ዕርድ መስሏል” አለቻት፣ ቢጫ ስለለበሰው ሰማይና መሬት።

“እንዴት?”

“እንዲህ ዕርድ ሲመስል በነገታው አንበጣ ይወራል አሉ። ደሞም
ንፋስ እየነፈሰ ነው፣ ሰማዩም ደመና አዝሏል። ሁለቱም ነገሩን
ያባብሱታል።”

ፈጠን ብላ ወደ መስኮቱ ሄደች ምንትዋብ። እውነትም የጐንደር
ሰማይ ቢጫ ሆኗል። አፏን በእጇ ይዛ፣ “ምን ጉድ ነው? ምን ይሻላል?” አለች።

“እግዚኦ ማለት ነው እንጂ ሌላ ምን አለ?” አለች፣ ደንገጡሯ።

ኢያሱ መቸም ይሰማል... ይነግሩታል ኣለች ምንትዋብ፣ ለራሷ።

ካህናቱ በፍጥነት ጸሎት እንዲይዙ መልዕክት ላከችባቸው። ጸሎት
ቤቷ ለመሄድ ወጥታ ተመልሳ እልፍኟ ተቀመጠች። ሰማይና ምድሩ እንደዛ ሆኖ ስታየው አስፈራት።

በማግሥቱ የአንበጣ መንጋ ሰማዩን አለበሰው። የአንድ ቀን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ለቀናት በመቆየቱ ቤተመንግሥትም ጐንደርም ተጨነቁ፤ተጠበቡ። ሕዝቡ፣ “እግዚኦ” አለ። ታላቅ መቅሰፍት እንደመጣ አመነ።
ምሽት ላይ ሳይቀር አንበጦች ሰማዩን አንለቅ አሉ። ከባድ ዝናብና
ንፋስ ወረራውን አባባሱት።
ውሎ አድሮም ሰብል ተበላሽ። እየቆየ ሲሄድ ጐንደር ትልቅ ችግር
ላይ ስትወድቅ፣ ሕዝቧንና እንስሳዋን ረሐብ አጠወለገው፤ በሽታ አጣደፈው። ቀናትና ወራት እያለፉ ሲመጡ ቀባሪ እስኪጠፋ ሙታን በየወደቁበት ቀሩ። የተረፉት ከነገሥታቱ ጀምሮ በኃይለኛ ጉንፋን ተያዙ። እንዲህ እያለ ሁለት ዓመት አለፈ።
ሰዉ ካደረሰበት ጉዳት ገና ሳያገግም፣ ተምች በመመለሱ ችግር ብቻ ሳይሆን፣ ከቀድሞው የበለጠ ረሐብ ገባ።

ጌታችን ወርዶ ከባሕር፣
ኣዳምን ዋና ሊያስተምር፣
አፋፍ ላይ ሁነን ብናየው፣
እያጣ አለቀ ሰው።

ተብሎ እንደተገጠመው ሁሉ ጐንደርን ጨምሮ በደጋም በቆላም ሰው አለቀ። ከቤተመንግሥት የተቻለውን ያህል የእህል እርዳታ ቢደረግ እያደር ዐቅም አነሰ። የቻለ ጐንደርና አካባቢዋን ጥሎ ተሰደደ ::መሬቱን፣ ንብረቱንና ደብሩን ጥሎ መሄድ ያልሆነለት ለረሐብና ለበሽታ ተጋለጠ።

ጐንደሬዎች የሕይወት ምልክቱ ከፊታቸው ላይ ጠፍቶ ባዶው ላይ
አፈጠጡ። ከንፈራቸው ሐሩርና ውርጭ የመታው ይመስል ከስሞ፣
ቆዳቸው ተሰነጣጥቆ፣ የአንገታቸው ቆዳ ተንጠልጥሎ፣ የጉንጫቸው አጥንት አፈንግጦ፣ የሰለሉ እጆችና እግሮቻቸውን ማንሳት ተስኗቸው በረሐብ፣ በጥምና በበሽታ ተንጠራወዙ።

መከራ በሰዎች ገጽታ ላይ ግዘፍ ነሥቶ ታየ።

ለእናት፣ ለአባትና ለልጅ ቀባሪ የሚሆን ዐቅም ጠፍቶ ጐንደሬዎች
ዐይናቸው ቦዞ፣ እንባቸው ደርቆ፣ እጅና እግራቸው ዝሎ ተቀመጡ።
ትናንት ስቀው፣ ወደው፣ ጠልተው ከቶውንም በልተው የማያውቁ
መሰሉ። ዛሬ ተስፋቸውን ተነጥቀው ከሞት ጋር ተፋጠጡ። ነገ የእነሱ እንዳልሆነች አውቀው እጃቸውን ለሞት ሰጡ።

ሞት፣ ያ የሰው ልጅ የቁም ቅዠት አላስደነግጥ አለ። እንደተራ
ነገር ተቆጠረ። ጐንደሬዎች የሚዘክራቸው መላዕክትና ቅዱሳን ሁሉ ወዴት እንደሄዱ ጠየቁ። የእግዚአብሔርንም መኖሪያ አጠያየቁ። እንደ ዳዊት፣ “ጆሮን የፈጠረ አይሰማምን? ዐይንን የፈጠረ አያይምን?” ብለው
አቤቱታ አስገቡ። ሕጻናት ጡት አፋቸው እንደሸጎጡ እናቶቻቸው
እቅፍ ውስጥ ለዘላለም አሽለቡ።

ጐንደር ጉልበቷ ዛለ።

“ግዝየ ምንድነው?”

1748 ዓ.ም ለምንትዋብ ሆነ ለሃገሪቱ ጥሩ ዓመት አልሆን አለ።
ብርሃን ሰገድ ኢያሱ በጽኑ ታመመ። እናቴ ትጨነቃለች ብሎ
መታመሙን ደበቀ። ለሀያ አምስት ዓመታት ከእናቱ ጋር በስምምነት፣
በምክክርና በሰላም የገዛው ዳግማዊ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ሐሙስ ሰኔ 21 ቀን ዐረፈ። የሕመሙ መንስኤ ባይታወቅም፣ የግራዝማች ኢያሱ እኅት የወንድሟን ደም ለመበቀል መርዝ አብልታው ነው የሚል ወሬ
ጐንደር ውስጥ ተዛመተ፡፡

አሳዛኙ ዜና ለምንትዋብ ደረሳት። ስትበር ልጂጋ ሄደች።
የምትሳሳለት ልጇ በሞት ተለይቷታል። ጉልበቷ ከዳት፤ መቀነቷን ፈታች። ጮኸች። አበደች። “ወዮልኝ ልጄ! ወዮልኝ ውዱ ልቼ! የዐይኖቼ ብርሃን! የልቤ ደስታ! ወዮልኝ ልጄ” እያለች ደረቷን ደቃች፣እየወደቀች ተነሳች፣ ፀጉሯን ነጨች፤ ፊቷን ቧጠጠች።

“የላስታን ዓቀባት ያለፈረስ ያለበቅሎ የወጣህ፣ እንዴት ታሰረ
እግርህ። አገር አንድ ለማረግ እንዳልጣርኸው፣ ጫካ ገብተህ አድነህ እንዳልመጣህ፣ ኸነብር ኻንበሳ ጋር ተጋፍጠህ እንዳላሸነፍህ፣ አሁን ማን እግርህን በገመድ አሰረህ?” እያለች አነባች።

ራሷን እስከመሳት ደረሰች።

“ያ እንደ አንበሳ ሚያስገመግመው ድምፅህ የት ጠፋ? ምን ነበር
እመምህ? መታመመህን ያልነገርኸኝ ምን ሁነህ ነው? ያላንተ ማን አለኝ? የአባትህ ዐደራ ነህ። አንተ ለኔ አባቴ፣ እናቴ፣ እህቴ፣ ወንድሜ፣ ጋሻ መከታዬ፣ ክብሬ፣ ሁሉ ነገሬ ነህ። አሁን ምን ይበጀኛል ልዤ? ኸንግድህ እንዴት ልኖር ነው? እንድህ አልጋ ላይ ተኝተህ ኸማይህ ሞቶ መቀበር ይሻለኝ ነበረ” እያለች ጮኸች።

ወዳጅ፣ ዘመድ፣ መኳንንትና ሌሎችም ለመያዝ አቃታቸው።
“ጠንካራው ማንነትሽ የት ኸደ? እርጋታሽ... አስተዋይነትሽ የት ኸደ? አሁንም ይች አገር ባንቺ ዠርባ ላይ ናት። እንምከር... ሁሉንም ነገር በቅጡ እናርገው” ሲሉ ተማጸኗት።

እሷ ግን መጽናናት አልሆነላትም።

“ማነው እንዳንተ ኸንጉሥ የተገኘ ዠግና ወንድ ልዥ፣ ለጠላቶቹ
ማይመለስ፣ ክንዱ ማይዝል? እንዳንተ ይቅር ባይ፣ ማነው እንዳንተ በሃይማኖቱ ጽኑ? ለድኻ ሚራራ፣ ሚዘክር፣ ማነው? እንዳተ የድኻውን ሮሮ ሰሚ፣ ማነው እንዳንተ ፍርድ ጎደለ፣ ደኻ ተበደለ ብሎ ውነት ፈራጅ? ማነው እንዳንተ አገር ወዳጅ? እንዳተ የናቱን ምክር ሰሚ፣ ማነው? እንዳንተ ታላቆቹን ኣክባሪ፣ ማነው? እንዳንተ ሸጋ ማነው?
እንዳንተ ጥርሰ መልካም፣ እንዳንተ ዕንቁ፣ እንዳንተ ወርቅ ማነው?
አሁን ምን ላርግ? የት ልኸድ? የት ልግባ? ቀድሞ በሕይወትህ
አስደስትኸኝ፣ አሁን በሞትህ አነደድኸኝ” እያለች ዋይታዋ ማባሪያ ኣጣ።

በአጎቷ በደጅአዝማች እሸቴ ራስቢትወደድ ወልደልዑልን
አስጠራች። ወልደልዑል ሲሰማ ሲሮጥ መጣ፤ አበደ፤ ጨርቁን ጣለ።እንደ እሱ የኢያሱን መሞት ያልሰሙ መኳንንት መጉረፍ ሲጀምሩ፣ እንደገና ዋይታና ሰቆቃ ሆነ። ጩኸትና ዋይታ ከዳር እዳር አስተጋባ።

ጩኸቱና ዋይታው ወህኒ አምባ ከመድረሱ ቀደም ብሎ እልፍኝ
አስከልካዮች የብርሃን ሰገድ ኢያሱ አስከሬን ያለበትን ቤተመንግሥት ቆለፉ። ወልደልዑል በአስቸኳይ መደረግ ወዳለበት ነገር ትኩረቱን
አደረገ ምንትዋብን፣ “እቴ ብርሃን ሞገሳ ሆይ፣ ብርሃን ሰገድ
ልዥሽ በሕይወት ሳለ ምን ነግሮሽ ነበር? መንበረ መንግሥቱን ማን
እንደሚወርስ አልነገረሽም? ኸሦስቱ ልዦቹ ከአቤቶ አፅቁ፣ ከአቤቶ ኃይሉና ከአቤቶ ዋዩ መኻል የትኛው ይንገሥ አለ? የነገረሽ ኻለ እባክሽ ንገሪን” ሲል ወተወታት።

“ኸመቤት ውቢት የተወለደው አቤቶ ዋዩ በእኔ መንበረ መንግሥት ይቀመጥ። ዮዳኤ የሰባት ዓመቱን ኢዮአስን እንዳነገሠው እናንተም
ልጄን ኢዮአስን አንግሡት፤ እኔንም አባቴን በካፋንም ሊተካ ይችላል።
ምወደው እሱን ነው” ብሏል፣ አለቻቸው ሲቃ እየተናነቃት።

ወልደልዑል፣ የቅርብ ዘመዶችና የቅርብ መኳንንት በር ዘግተውና
በነፍጥ አስጠብቀው መከሩ። አቤቶ ዋዩ ወይንም ኢዮአስ ገና የሰባት ዓመት ልጅ ነበርና፣ “እቴጌ በነበረችበት ሥልጣን ትቀጥል” ብለው ወሰኑ።
👍14👏1
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....“ግዝየ እኛ ነን።”

ጥላዬ፣ በወርቅ ያሸበረቀችው ቁስቋም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ሲገባ በቤተክርስቲያኗ ውበት ተማረከ። በአጥሩ ግንብ ማማር ተደነቀ።ፀሐይዋ አለዚያን ቀን እንደዚያ አብርታ የማታውቅ መስላ ታየችው።ቆም ብሎ ሁሉን በዓይኑ ቃኘ።

ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ከሞተ በኋላ፣ ምንትዋብን የማግኘት ፍላጎቱ
ቢበረታም አስራ ዐራት ዓመት ሙሉ ቆርጦ አለመነሳቱ ኅሊናውን
ሲቆጠቁጠው ቆይቶ፣ የኢዮአስን ሞትና የመንግሥቱን ማብቃት ሲሰማ አላስችል ብሎት ወደ ጐንደር አቀና።

ከአብርሃም ቤት ወጥቶ ቁልቁል ሲወርድ፣ የተጫጫነው ትካዜ፣ ገና ከደብረ ወርቅ ሲነሳ ምንትዋብ ላይ የደረሰው ድርብ ሐዘን፣ የጐንደር መበጥበጥ፣ የሃገሩ መረበሽ የልብ ስብራት የፈጠረበት መሆኑ ቀርቶ ዛሬ ቁስቋም ግቢ ውስጥ ሲቆም፣ ድንገት ሰላምና መረጋጋት በማግኘቱ ያችን ሰዐት ለዘላለም ለማቆየት የፈለገ ይመስል እዚያው ያለበት ቦታ
ቆሞ ቀረ።

ውስጡ የተቀጣጠለው የተስፋ ስሜት ያቺ ደማቅ ፀሐይ ከረጨችው ብርሃን ጋር ተዋሕዶ ልቡን አሞቀው። ለጊዜው እዚያ ቦታ ላይ ለምን እንደተገኘ ረስቶ፣ ሄዶ መሳለም ብሎም ጸሎት ማድረስ እንዳለበት ዘንግቶ ከቆመበት አልንቀሳቀስ አለ። ቁስቋምን በምናቡ ብራና ላይ
ሣላት። ቀደም ብሎ ጐንደር እንዲመጣ በሮብዓም ግብዣ ሲቀርብለት አለመቀበሉ የሚያየው ውበትና ታሪክ ተካፋይ ሳያደርገው በመቅረቱ ተቆጨ። አንዲት መነኩሴ እጅ ሲነሱት ደንገጥ ብሎ ሰላምታ ሰጣቸው።
ምን ያህል ጊዜ እዚያ እንደቆመ ባያውቅም ወደ ቤተክርስቲያኗ በዝግታ አመራ። በወንዶቹ መግቢያ በኩል ሄዶ በሩን ተሳለመ። ቆም ብሎም
ዳዊቱን ከማኅደሩ አውጥቶ ደገመ።

ሲጨርስ፣ ዙርያውን ተመለከተ። ወደ ቤተመንግሥት የሚመራው
ሰው በዓይኑ ፈለግ ፈለግ አደረገ። ወደ መጣበት ሲመለስ፣ አንድ ቄስ
ከግቢ ሊወጡ ሲሉ አያቸውና “አባቴ!” ብሎ አስቆማቸው። እንዲባርኩት ከተጠጋቸው በኋላ፣ ወደ “እቴጌ ቤተመንግሥት በየት ነው ምሄድ?” ሲል ጠየቃቸው።

ቄሱም፣ “በዝያ በወንዶቹ መግቢያ በኩል ሲኸዱ ዘበኞቹን ያያሉ።
እነሱ ያሳይዎታል” ብለውት ተሰናበቱት።

ተመልሶ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ወንዶች መግቢያ አመራ። በስተጀርባ በኩል ቁልቁል ሲወርድ፣ ቄሱ እንዳሉት በግንብ የታጠረው በር ላይ ዘበኞች ቆመዋል። ትኩር ብለው ያዩታል። ራቅ ብሎ እጅ ነሳና፣ “እቴጌ
ዘንድ ጉዳይ ነበረኝ። ስሜ ሥሙር ነው። ኸነማይ ነው የመጣሁት።
የእቴጌ ዘመድ ነኝ።” ብሎ የያዘውን የተጠቀለለ ዕቃ አሳያቸው።

ዘበኞቹ፣ ጉዳዩ ምን እንደሆነ ደግመው ደጋግመው ከጠየቁት በኋላ፣እንዲጠብቅ ነግረውት አንደኛው ወደ ውስጥ ገባ። ጥቂት ቆይቶ አንድ ያደገደገ አስተናጋጅ መጥቶ ማን እንደሆነና ጉዳዩ ምን እንደሆነ አጥብቆ ከጠየቀው በኋላ ሄደ። ጥላዬ እንደገና ዘለግ ላለ ተጨማሪ ጊዜ ከጠበቀ በኋላ፣ አስተናጋጁ ተመልሶ መጥቶ እንዲከተለው በእጁ
ምልክት ሰጠው።

ግቢው ውስጥ ሲገባ፣ የምንትዋብ ቤተመንግሥት ከፊት ለፊቱ ገዝፎ ታየው። በስተቀኙ ያለው የጸሎት ቤቷን እያደነቀ ሲሄድ ግቢው ውስጥ ያለው የሰው ብዛትና ጫጫታ ገረመው። ሕፃናት ከወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ። “ኸነዝኸህ ውስጥ የልዥ ልዧቿ አሉበት መቸም”
ብሎ ወደፊት ሲመለከት ወይዛዝርትና ባለሟሎች ከወዲያ ወዲህ ይዘዋወራሉ። አስተናጋጁ በዝምታ ሲመራው ድንገት ግዙፍ የሆነ ግንብ ሲያይ ዝናውን የሰማው “ሽናዋ” የግብር አዳራሽ መሆኑ ገባው።የግንቡ ማማር ከፀሐይዋ ብርሃን ጋር ተደምሮ ዓይኑን አጭበረበረው።ምንትዋብን ራሷን እንደዛ ገዝፋ ያያት መሰለው።

ስለ ምንትዋብ ሲያስብ፣ ምን እንደሚጠብቅ ማወቅ አልቻለም።
ልጄ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ሞቶ፣ ቤተመንግሥት ሁለት ተከፍሎ ብሎም ፍርክስክሱ ወጥቶ፣ ወጣቱ ንጉሠ ነገሥት አድያም ሰገድ ኢዮአስ በሻሽ ታንቆ ተገድሎ፣ ሬሳው ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ፣ መሣፍንት በየበኩላቸው
ተቆራቁሰው፣ ሃገር ተተራምሶ፣ ወንድሟ ወልደልዑልና ዘመዶቿ አንድ በአንድ ሞተው፣ እሷ ቤተመንግሥቱን ጥላ ወጥታ ምን ልትመስል እንደምትችል መገመት ተሳነው። ቁስቋም ግቢ ውስጥ ሲገባ ተሰምቶት የነበረው የመንፈስ መነቃቃት ከውስጡ ሊተን ቃጣው።

አስተናጋጁ፣ በሽናዋ አዳራሽ በስተቀኝ በኩል ወዳለው እንቁላል
ግንብ ወደሚወስደው ደረጃ ሲወጣ ተከትሎት ወጣ። ቁና ቁና ተነፈሰ።ጉልበቱ ላለበት። ዕድሜው እንደገፋ ቢያውቅም አሁን በቅጽበት ጨምሮ የሸመገለ መሰለው። ደረጃውን ሲጨርሱ፣ ላብ አሰመጠው።በፍጥነት ግንባሩን ያራሰውን ላብ በኩታው ተም ተም አደረገው። እጁ
ውስጥ ሊንቆረቆር የሚታገለውን ላብ እጀ ጠባቡ ላይ ጠራረገው። በርላይ ሲደርሱ ቆም ብሎ ኩታውን አስተካከለ።
ግራና ቀኝ ያደገደጉ አስተናጋጆች ቆመዋል። አስተናጋጁ እርሱን
ለእነሱ አስረክቦ ወደኋላ ሲቀር፣ አንደኛው እልፍኝ አስከልካይ እጅ
ነስቶ “ይግቡ” አለና ቀደም ብሎ ገብቶ እጅ ነስቶ፣ “እቴጌ እንግዳው መጥተዋል” ብሎ አስቀደመው

ጥላዬ፣ ልቡ ከታች ምላሱ ካላይ ጉሮሮውን የዘጉበት መሰለው።

ምንትዋብ፣ ቀይ ከፋይ የለበሰ ሰፊ ወንበር ላይ ተቀምጣለች።
የለበሰችው ረጅምና ባለቀይ ጥበብ ቀሚስ ላይ የደረበችው በወርቅ ያጌጠው ሰማያዊ ካባ ልዩ ድምቀት ሰጥቷታል። ሹሩባዋ ላይ ሸብ ያደረገችው ነጭ ሐር ሻሽ ግርማ ሞገስ አክሎላቷል።

ጥላዬ፣ ልቡ ቷ አለበት፤ ሰውነቱ ራደ። ግርማ ሞገሷ አስፈራው።

ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። ያ በር ላይ ሲደርስ ሊያጥለቀልቀው የቃጣው
ላብ ፊቱ ላይ ክልብስ አለበት።

“ይቀመጡ” ብላ፣ ፊት ለፊቷ ያለ ወንበር በእጇ አሳየችው።

በእጁ ግንባሩን አሻሽና በጨርቅ የተጠቀለለውን ብራና ከብብቱ
ስር አውጥቶ፣ የተሸፈነበትን ጨርቅ ከላዩ ላይ አንስቶ እንደገና ለጥ ብሎ እጅ ነሥቶ፣ ሲሰጣት ምንትዋብ ተቀበለችው። ዕንጨት ላይ የተወጠረውን ብራና ስታየው ከዓመታት በፊት መነኩሴው ይዘውት መጥተው የነበረው ዓይነት የራሷ ምስል ነው።

“እርስዎን ደሞ ማን ላከዎት?” አለችው።

“ማነም አላከኝ። ዛሬስ ራሴ መጣሁ።”

“ሥሙር ማለት እርስዎ ነዎት?”

“እርስዎ አያስታውሱኝም። ግዝየውም ርቋል። የባላምባራስ ሁነኝ ልዥ ... ጥላዬ ነኝ።”

“ባላምባራስ ሁነኝ የቋራው ... የሳቸው ልዥ ... ጥላዬ?” ብላ የሷ
ያልመሰላት ድምፅ ከውስጧ ሲወጣ ተሰማት።

“አዎ... የቋራው ... ጥላዬ።”

ምንትዋብ ደነገጠች፤ ምላሷ ተቆለፈ። ከጥቂት ዝምታ በኋላ
እንደምንም ብላ፣ “ኧረ... በቁስቋሟ ተቀመጥ እንጂ!” አለችው፣ ወንበር እያመለከተችው።

ተቀመጠ።

ሁለቱም በዝምታ ተያዩ።

“ለካንስ አንተ ኑረኻል ካንዴም ሁለቴ ምስል ስትልክ የነበርኸው።
ለመሆኑ እስተዛሬ የት ነበርህ?”

ጥላዬ ፈገግ ብሎ ዝም አለ። ከመምጣቱ በፊት ሊላት በሐሳቡ
ያወጣው ያወረደው፣ ያለመውና የተመኘው ሁሉ ከጭንቅላቱ ብን
ብሎ ጠፍቷል። የቀረው ዝምታ ብቻ ብዙ ሐሳቦችን፣ በርካታ
ትዝታዎችንና ስሜቶችን የያዘ ከንግግር የላቀ ዝምታ። ለዚህ ቀን
ምን ዓይነት ቃላት ይበቁ ነበር? በዚያ ሁሉ የሐሳብ ውዥንብር ውስጥ አንድ ነገር ከአእምሮው አልወጣ አለ ንግሥታዊ ግርማ ሞገሷ።አፍዝ አደንግዝ የያዘው ይመስል አፉ ተሳሰረ። ስትናገር ደንገጥ ብሎ መስማት ጀመረ።

“ዛዲያ እስተዛሬ እንደዝኽ መምጣት እየቻልህ ስለምን ይኸን ያህል ግዝየ ቆየህ? እኔኮ ኸቋራ ኸወጣሁ ዠምሮ የት እንደደረስህም አላውቅም
ነበረ። ቤተመንግሥት እኮ እንዲህ ኸዘመድ እንደልብ ሚያገናኝ ቦታ
ማዶል ። እንደዝህ ስጎዳ ስለምን አልጠየቅኸኝም?”
👍8
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ለዓመታት በርካታ የመንፈስ ድል ስትቀዳጅ ቆይታ ልጇ ከሞተ በኋላ፣ ይኸው ድል ወደ ሽንፈት የተቀየረ በመሰላት ሰዐት እሱን በማግኘቷ ልቧ ተነሳስቶ ኸንግዲህ ሞት እንጂ ሌላ አይለየንም አለች።
አስተናጋጅ ወይን ጠጅ አምጥቶ ቀድቶላቸው ወጣ።

“ጠጣ እስቲ!” አለችው፣ ፈገግ ብላ።

የትካዜው ድባብ ተገፈፈ።

“ለመሆኑ ሥዕል እንዴት ዠመርህ?”

“ቋራ ሁኘ ነው የዠመርሁት” አለና ስለግድግዳው ታሪክ ነገራት።

ከት ብላ ሳቀች። “ሥዕል ትሥል እንደነበር ዛዲያ እንዴት
አላወቅሁም?”

“አባባ ለምሠራው ነገር ቁብ ሰጥተውት አያውቁም ነበር። ወዲያው ያጠፉት ነበረ። ቋራን ትቸ ጐንደር ዘልቄ እመኝ የነበረውን ሥዕል መማር ዠመርሁ። ኋላም ደብረ ወርቅ ማርያም ኸድሁ። መቸም በርስዎና በንጉሥ ኢያሱ ዘመን ሥዕል አደገ። ጐንደር ውስጥ የባሕር ማዶ ሰዎች ኸመጡ ወዲያ ሥዕል ለውጥ ኣምጥቶ ነበረ...” ብሎ ከጠጁ
ተጎነጨ።

“እንዴት?”

“የቀድሞዎቹን ሥዕሎች ያስተዋሉ እንደሆን መለኮታዊ ይዘት
ያላቸውና ታሪክ ተራኪ ነበሩ። ኋላ ግን መለኮታዊ ብቻ ሳይሆን ሥዕል ወደ ሰው ወረደ። ሥጋ ለባሾች... ነገሥታት ሚሣሉበት ዘመን ላይ መጣን። የቀለም አጠቃቀም ሁሉ ለውጥ አመጣ። መቸም የአጤ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመንም በትምርትም ሆነ በሥዕል ብዙ ለውጥ የመጣበት
ዘመን ነበር። ቁም ጸሐፊው፣ ደብተራው ቁጭ ማለት ያመጣበት ግዝየ ስለነበረ ቁጭ ሲባል ፉክክር፣ ክርክርና አሳብ ለአሳብ መለዋወጥ መጣ።እንዲያም ብሎ አንድምታ ትምርት ተዠመረ። ይኸ አሳብን መግለጽ ወደ ሥዕለም መጣ።”

“እንዴት ያለ ነገር ነገርኸኝ? ሁሉ ሚሆነው በግዝየው ነው መሰለኝ
ብላ ፈገግ አለች።
“አዎ ሁሉ ሚሆነው በግዝየና በቦታ ነው። አለግዝየውና አለቦታው ሚሆን ምን አለ?”

“ግዝየ ምንድነው?”

“ግዝየ እኛ ነን።”

“የግዝየ ነገር ይገርመኛል።”

“የሰው ነገር ይገርመኛል ማለትዎ ነው? ግዝየን ሆነ ቦታን ምንፈጥር
እኛ ሰዎች እኮ ነን። እዝጊሃር ምድርና ሰማይን ፈጠረ። እኛ ደሞ
ግዝየንና ቦታን ፈጠርን። ግዝየ ሆነ ቦታ አለኛ የሉም? ቦታም ግዝየም እኛ ነን። እኛ ጥሩ ስንሆን ግዝየም ጥሩ ይሆናል። እኛ ጥሩ ስንሆን የሰማዩም ደስ ይለዋል፣ ምድርም ለፍጥረታት ሁሉ ምቹ ቦታ
ትሆናለች።”

“አሳብህ ገባኝ። ግዝየ ሳይሆን እኛ ነን ምንገርመው ማለትህ ነው?
እንግዲያማ የሰው ነገር ይገርመኛል።”

“አየ እቴጌ ዝናዎን ሰምቻለሁ። ሊቃውንት ሆኑ ካህናት ያደንቅዎታል።እርስዎ የጠለቀ ዕውቀት... ትምርት ያለዎ... አንደበታምና ታሪክ
አስተካካይ... የሰው ባሕርይ ይግረምዎ?”

“አንተ የሥዕል ንጉሥ፣ የሰማዩንም የምድሩንም ብራና ላይ
ምታስቀምጥ እስቲ ንገረኝ። ሰው ማለት ምን ማለት ነው?”

“እቴጌ ሰው ማለት ምን ማለት እንደሆነ ኻወቅሁማ ፈጣሪን ሆንሁ።እኛ ሰዎች መሆን የነበረብን ሚዛኑ ከፍ አለና እኛ አነስን። መሆን ሚገባንን መሆን አልቻልንም። መቸም ጉድለት አለን ብንል ፈጣሪ ጉድለት ያለው ፈጠረ ማለት ይሆንብናል። ሙሉ ግን ማዶለን።”

“ዛዲያ የተሟላን መሆን ቢያቅተን፣ ኸሚዛኑ ብንጎድል፣ ለመሙላት
አንጥርምን?”

“ቢሆንልንማ እንዲያ ነበር።”

“እኔስ እንዲያው በተለየ አሁን ያለንበትን ሳስብ ክፋትና ደግነት
አብረውን የተወለዱ ናቸው ነው እምል።”

“ስለ ሰው ባሕርይ ተመራምረን ምንደርስበት አይመስለኝም::”
አለ ጥላዬ ከጠጁ አሁንም ጎንጨት ብሎ። እሷ የቀረበላትን ጠጅ አልነካችውም። “ይጠጡ እንጂ” እንዳይላት ድፍረት መሰለው።

“እኔ ለነገሩ ሰው ማለት ምን ማለት ነው ብየ የጠየቅሁት እንዳው
ያገራችን ነገር አሳስቦኝ ነው። ይረዳሉ ብለህ ያሰብኻቸው ሁሉ
አንተንም አገርንም ሲጎዱ ስታይ ይገርማል። ሰላም ጠፋ።”

“ርግጥ ነው ... ርግጥ ነው እቴጌ... ሁላችንን ሚያሳስበን ይኸው ነው” አለ፣ በሐሳብ ተውጦ ሳይመልስላት በመቅረቱ ደንገጥ ብሎ። “እቴጌ በእርስዎና በንጉሥ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ዘመን ደግ ግዝየ አለፈ።
እናንተ ደግ ጥሩ ነበራችሁና ግዝየውን ደግ... ጥሩ አረጋችሁ።
አዋቂው እንዳለው እኛ መልካም ስንሆን ግዝየውም መልካም ይሆናል። ከቶም ያገሩ ንጉሥ ወይም ገዥ ደግ ተኾነ ሕዝቡም ደግ ነው ሚኾን፤ገዥው ተከፋም ሕዝቡም አብሮ ይከፋል። “እስመ ከመ መኰንና ለአገር ከማሁ ይገብሩ እለ ውስቴታ ይላል፤ አገረ ገዥው የሚያደርገውን ነገር ሁሉ በአገሪቱ ያሉ ያደርጋሉ ሲል ነው። መቸም በሩቅም ቢሆን
ስለእርስዎ ደግነት ብዙ ሰምቻለሁ ሁሉ ያመሰግንዎታል። እርስዎ
ለምለም ልቡና ያለዎና ልበ ጽኑ በመሆንዎ አምላክ መንግሥትዎን
ሥሙር አርጎልዎ፣ አቅንቶልዎ ለዐርባ ዓመት ገደማ ሰላም የመላበት ዘመን ሰጡን። አጤ ኢያሱ ካደጉ በኋላ እርስዎም እሳቸውም ባሳያችሁት
ትጋት እፎይ ብለን ዐርፈን አለሥጋት ተማርን፤ ሠራን። አሁን ግን ይኸው ተኝተን ሳይሆን በቁማችን እንባንናለን።”

“የኛ ዘመን ... መቸም ዕድለኛ ሁነን...”

“ዕድለኛስ አይበሉ እቴጌ! ነገርዎን አቋረጥሁ እንጂ..”

“ኧረ ግዴለህም እህትህ ነኝ እንደ ሹመኛ አትሽቆጥቆጥብኝ
አለችው፣ በፈገግታና በሚያቀራርብ ቅላጼ።

“አይ ግዴለዎትም ቀስ እያልሁ እዘናለሁ፤ ክብረት ይስጥልኝ። ደሞስ መሽቆጥቆጥ ለካህናተ ደብተራ ወግ ማዶል” ብሎ ፈገግታውን እንደያዘ ነገሩን ቀጠለ። “ንጉሥ ኢያሱ ልዥ በነበሩ ግዝየ ያን ሁሉ ትጋትዎን አይተን... ሰምተን ማልነበር? እሳቸውም ካደጉ በኋላ ተባብራችሁ
አገራችንን ሰላም አረጋችሁ፤ ደከማችሁላት። የጥጋብ ዘመን ሰጣችሁን።ሰዉም ወደዳችሁ። የሰው መውደድ ብል አጤ በካፋስ እያሉ ቢሆን እርስዎ ተወዳጅ ነበሩ። ጠንካራም ይባሉ ነበር። ይኸ ዛዲያ እንደምን ስለ ዕድል ይቆጠራል? እኔማ ቢጠይቁኝ ዕድል ሚሄድበትን ያቃል እላለሁ። ያኔ በለጋነቴ እምብዛም አይገባኝም ነበር። አንዴ ዛዲያ
መምህሬ የነበሩት አለቃ ሔኖክ ዕድል ከሰማይ አይወድቅም' ዕድል እንደ ሥዕል ነው። የሚገባውጋ ነው ሚኸድ። ማይሆነው... ዝግጁ ሆኖ
ማይጠብቀውጋ ኣይኸድም' ብለውኝ ያውቃሉ።”

“እኔም እሚታ ዮልያና ዕድል ኸሰማይ ይወድቃል?' ስትል
ሰምቻለሁ። አሳቡ አንድ ነው። እኔ ግን ዕድል ሚሰጠን እዝጊሃር ነው
እላለሁ።”

“ግና ማንችለውን አይሰጠንም። ማንችለውን ሰጥቶን ብንወድቅ...
ሳንችል ብንቀር ማን ሊጠየቅ ነው?”

“አየ ጥላዬ... ሰውን ትፈታተናለህ መሰል” አለችና ከት ብላ ሳቀች።

“እቴጌ... በመንበርዎ ትንሽ በቆዩ ኑሮ አሁን ኸመጣብን መቅሰፍት
እንድን ነበር” አለ፣ ጨዋታውን ለውጦ። “ድኻውም እኮ ቢሆን እርስዎን ተገን አርጎ ነበር የኖረ። ዛሬ ለሱ ሚያስብለት ማን አለው? ጉያዎ ደብቀው ያቆይዋትም አገር ይኸው አሁን መፈንጫ ሆነች። አሳቢ ጠፋ። አዋቂ ጠፋ። የዕውቀት ውጤቱ ሰላምና ቅንነት ነው፤ የዕውቀት ደግነቱ ማስተዋል ነው ብሎም ማልነበር ፈላስፋው? አሁን ሰላምም፣ ቅንነትም፣ ማስተዋልም የለ።”

ምንትዋብ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች። “አእምሮ ለነፍስ መዳኒቷ ነው፤ የልብ ሽልማት አእምሮ ነው' ይል የለ ፈላስፋው?”
👍14