#እህቴ_በባትሆኚ_አገባ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል። ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ... የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር እስከእርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች እንሆናለን ።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል.. ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር በቃላት ልውውጥ እና በአይን መሠራረቅ ላያልፍ ይችላል።ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቆረጥ ይችላል ወይም እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ "የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ የለንም?።ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ አልቆ ብቻ አይደለም...አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው ጉዞቸውን በተለያየ ጎዳና ይቀጥላሉ።ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።
እንዲህ ስለፍቅር የምፈላሰፈው ከጄኔራሏ ጋር ወደ ቤቷ እየሄድኩ ባለሁበት ጊዜ ነው፡፡በራሷ መኪና ሰፈር ድረስ መጥታ ነው የወሰደችኝ፡፡ …ከ20 ደቂቃ በኃላ ፍፀም ያልጠበቅኩት ሰፈር ይዛኝ ገባች…፡፡አደነጋገጤን አትጠይቁኝ፡፡ይሄነው ቤቴ ብላ የመኪናውን አፍንጫ ወደአንድ ቢላ ቤት በራፍ አዙራ በማስጠጋት የመኪናዋን ጡሩንባ አስጮኸች፡፡
እኔ በራፉ ከመከፈቱ በፊት የመኪናውን በራፍ ከፍቼ ወረድኩና ፊቴና ወደማዶ አዙሬ ፈዝዤ ቆምኩ፡፡.ይሄ እንዴት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል..?ከጄኔራሏ ቤት ፊት ለፊት የሚታየው የድሮ ስሪት ቢላ ቤት እትብቴ የተቀበረበት ቤት ነው.. የወላጆቼ ላብ ጉልበት የፈሰበት ጥሪት ሀብታቸው ነው፡፡እዚህ ቤት ውስጥ ነው ደግሰው የተጋቡት፤እዚህ ቤት ውስጥ ነው ተፋቅረው ኖረው ልጅ የወለዱት፤ ከእዚህ ግቢ ውስጥ ነው እሬሳቸው ወጥቶ የተቀበረው….፡፡የዚህ ቤት ወራሽ አሁን እኔ ነኝ፡፡ግን በሞግዚትነት ስታስተዳድረው የነበረችው እቴቴ ማለት አክስቴ ስለነበረች አሁንም በእሷ እጅ እንዳለ ነው፡፡የእሷን አይን ለማየት ድፍረት በማጣቴ ምክንያት ይሄንን ንብረቴን መረከብ አልቻልኩም፡፡በአሁኑ የአዲስአባ ገበያ ባዶ መሬቱ ብቻ ቢያንስ 10 ሚሊዬን ብር ያወጣል.፤አቤቱ ሲጨመርበት ገምቱት..አዎ አሁን እኔ ባልጠቀምበትም ወደፊት ለልጄ ይሆናል ስል ተፅናናሁ፡፡
‹ኸረ ግባ በራፉ ተከፍቷል…ምንድነው እንዲህ ያፈዘዘህ..?››
‹‹እ እሺ ›ብዬ ከደነዘዝኩበት እንደመባነን አልኩና ወደውስጥ ገባሁ፡፡
እሷም መኪናዋን ወደግቢው ውስጥ አስገብታ አቆመችና ወረደች፡፡ለዘበኛው ሰላምታ ሰጠችውና ወደ ውስጥ ገባን ፡፡ግቢው ማህል ላይ እድሜ ጠገብ ትልቅ ቢላ ቤት ያለ ሲሆን ወደ አንድ ጥግ ደግሞ በግምት ሶስት ወይም አራት ክፍል ያለው አዲስ ህንፃ ይታያል…ወደ አዲሱ ህንፃ በረንዳ ላይ ሁለት ህፃናት ይጫወታሉ…
.‹‹ያንን አከራይቼው ነው››፡፡ብላ ወደ አሮጌው ቤት ይዛኝ ገባች፡፡
የድሮ መኳንንት መኖሪያ የመሰለ ባለብዙ ክፍል ቤት ነው፡፡ሙሉ ቤቱ የባለሞያ ጥበብ ያረፈበት ባለግርማ ሞገስ ሲሆን በጥንታዊና ዘመናዊ እቃዎች ስብጥር ተሞልቷል፡፡ለምሳሌ ከወደቀኝ ኮርነር አካባቢ ዘመናዊ የሆነ ባለነጭ ልባስ ሶፋ ሲታይ፤ ከእሱ ፊት ለፊት ፍፅም ባህላዊና ከጠፍርና ከእንጨት የተሰራ ልዩ መቀመጫዎች ይታያሉ፡፡ብቻ ቤቱ መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚዬም ነው የሚመስለው፡፡
‹‹ደህና አደራችሁ?››ብዬ ገባሁ
‹‹ቁልፍ ከፍቼ እየገባሁ እያየህ ደህና አደራችሁ ትላለህ እንዴ?፡፡››
‹‹ምን ላድርግ ይሄንን የሚያህል ግዙፍ ቤት ሰው አልባ አይሆንም ብዬ ነዋ››
‹‹በጊዜውማ ልጇች ትላለህ የልጅ ልጆች ሲተረማመሱበት ነበር.. ቁጭ በል
ቁጭ አልኩ‹አሁንስ?››
‹አሁን ግማሹ የራሱን ቤት እየመሰረተ ወጣ…ሌላው አውሮፓ..የተቀረው አሜሪካ ገብቷል…እኔና ቤቴ ግን ይሄው አለን››
‹‹ወላጆችሽስ?.››
‹›አባቴ ሞቷል ፤ እናቴ ትንሽ የጤና እክል ስላለባት አሜሪካ እህቶቼ ጋር ነው የምትኖረው….መጣሁ ዘና በል…››ብላኝ ወደኪችን መሰለኝ ገባች፡፡
‹‹ለዚህ ቤት አዲስነት አልተሰማኝም..ምንድነው ፊልም ተሰርቶበት እዛ ላይ አይቼው ይሆን እንዴ…?.››ሪሞት አነሳሁና ፊት ለፊት ያለውን ቴሊቭዝን ከፈትኩ..ጄኔራሏ ከነማዕረጎ የተነሳችው ፎቶ በትልቁ ፊተ ለፊት ግድግዳ ላይ ገጭ ብሏል፡፡ በሙሉ አይን ማየት ፈራሁና አንገቴን አቀረቀርኩ…፡፡የሙሉ ቤተሰቡ ፎቶ እዚህና እዛ በተናጠልና በጋራ የተነሱት ቤቱን ሞልቶታል፡፡ሲታዩ የደላቸው ቤተሰብ መሆናቸው ያስታውቃል፡፡ድንገት የተቀመጥኩበት ጠረጴዛ ስር የፎቶ አልበም አየሁ፡፡ መቼስ አልበም ፊት ለፊት እንግዳ ሲመጣ የሚቀመጥበት ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጠው…የመጣው ሁሉ እንዲያየው ነው ብዬ አወጣሁና ማየት ጀመርኩ…፡፡አብዛኛውን ስለማላውቃቸው ብዙም ስሜት አይሰጠኝም፡፡ ቤዛወርቅ ያለችበትን የህፃንነቷን ቲኔጀር ሆና የተነሳችው ….የሚገርመው ከልጅነቷም ስፖርተኛና ተቦቃሽ ነገር ነች..እንዴ ምንድነው..?ይሄ ፎቶ እዚህ ምን ይሰራል…..?ፎቶውን እንደያዝኩ ከመቀመጫዬ ተነሳውና ወደኪችን ተንደረደርኩ፡፡
‹‹…ቤዝ.ቤ..ዝ….››እያለከለኩ ቅድም ስትገባ ወደያኋት ክፍል ገባሁ
‹‹ምነው ምን ተፈጠረ ..?ቢላዋ በእጇ እንደያዘች ጥሪዬን ሰምታ ስትወጣ በራፍ ላይ ተገጣጠምን …..አልበሙን ወደ እሷ ዘርግቼ‹‹ይህቺ ማነች…?ይህቺኛዋስ?›
‹‹ጤና ትባላለች…በሚያሳዝን ሁኔታ አሁን በህይወት የለችም…..?ምነው ከሰው ጋር ተመሳሰለችብህ እንዴ?››
‹ጤናዬ ማለት? ጤናዬ አስረስ…የበሪሶ አያና ሚስት፡፡››
‹‹አዎ ጋሼ በሪሶ..የት ነው የምታውቃቸው….?››በገረሜታ ጠየቀችኝ፡፡
ፊቴን አዞርኩና ወደሳሎን ተመለስኩ…ሶፋው ላይ ዝርፍጥ አልኩና ጭንቅላቴን ያዝኩ፡፡
ቤዛ ሁሉ ነገር ግራ ገባትና ከኃላዬ ተከትላኝ መጣች ‹‹ቆይ ቆይ እነሱ እኮ ከሞቱ ቢያንስ 20 አመታት አልፏቸዋል….ቅድም ስንመጣ ከመኪና ወርደህ እቤታቸው ላይ ስታፈጥ ነገሩ ምድነው ብዬ ግራ ተጋበቼ ነበር››
‹‹ለመሆኑ አንቺ ታስታውሺያቸዋለሽ…?››
‹‹አዎ ሲሞቱ የደረስኩ ወጣትና 12ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ ሁሉን ነገር ነበር የማስታውሰው…ቤተሰብ ነበርን…አንድ ልጅ ነበራቸው..የሚያምር ወንድ ልጅ… ክርስትና ያነሳው አባቴ ነበር.አበልጆች ነበርን..?አይ እዬብ ይሄኔ አድጎ ትልቅ ሰው ሆኗል….ስሙ እዬብ ነበር…፡፡››
‹አዎ ስሜ እዬብ ነው፡፡››
‹‹ምን ?አንተ…!!!እኔ አላምንም..፡፡እዬቤ ነህ…፡፡ቆይ ቆይ…. ››አልበሙን ነጠቀችና ገለጥ ገለጥ አድርጋ እኔ ያለሁበትን ፎቶዎች አወጠች…፡፡ እሷ አቅፋኝ የተነሳሁት..አባቷ ታቅፈውኝ የተነሳሁት..አራት የሚሆኑ ፎቶዎችን አሳየችኝ….ከዛ በኃላ ቁርሱም ተረሳ.፡፡
✨ይቀጥላል ✨

👍70😱9❤7😁5