አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
====================
ከአንድ አመት በኃላ በትዳር ውስጥ ወሲብ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም፡፡ግን ደግሞ ሊቀር የማይችል ከዋነኞቹ አስፈላጊ ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡በተጣማሪዎች መካከል የሚከሰትን ማንኛውንም የከረረ ነገር የሚያለዝበው፤ የተጣመመ ስሜታቸውን የሚያቃናው፤የጎበጠ ግንኙነታቸውን የሚያቃናው ወሲብ ነው፡፡
የኑሮ ችግር ቢኖር መፅናኛ..አለመመቸት ቢኖር ማስረሻ ነው..ወሲብ፡፡እናም ባለትዳሮች የኑሮቸውን ኢኮኖሚያው ቀዳዳ ለመድፋት በስራ ደፋ ቀና እንደሚሉት ሁሉ የስሜታቸውን ክፍተት ለመድፈን ስለወሲብ ብቃታቸውና ችሎታቸው እኩል ትኩረት መስጠት አለባቸው፡፡ለዛውም ያልተቆራረጠ ቀጣይነት ያለው ትኩረት ፡፡ምክንያቱም ወሲብ ለፍቅር ተጣማሪዎች ልክ እንደምግብ ነው፡፡ምግቡ ቁርስ ላይ  ያበሉት  ሆድ ምሳ ላይ አምጡ ብሎ እንደሚጠይቀው ሁሉ ወሲብም ሰኞ እስኪዝለፈለፉ አድርገው እሮብ ላይ ጭንቅላቶትን እስኪያዞሮት ሊያምሮት ይችላል፡፡ይሄ ለምን ሆነ ተብሎ መጠየቅ የለበትም..፡፡እንደውም የሰውነቶትንም ሆነ የአእምሮትን ሙሉ ጤናማነት የሚያሳይ አንድ ምልክት ተደርጎ መወሰድ ነው ያለበት፡፡
በአላዛርና በሰሎሜ ትዳር ውስጥ ዋነኛውና ብቸኛው ስብራት ይህ ነው፡፡ወሲብ፡፡ታዲያ ወሲብ ብቸኛው ችግራቸው ከሆነ እንዴት በመሀከላቸው ያለን አንድ ችግር መፍታት ያቅታቸዋል? በሌሎች ትዳሮች እኮ ከደርዘን በላይ የታጭቁ ችግሮች እያሉ እንኳን ትዳሩን በፀና መሰረት ላይ ማስኬድ ይቻላል፤ታዲያ የእነሱ እንዴት ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ግን ነገሩ ከላይ እንደሚታየው ቀላል አይደለም፡፡ወሲብ ማለት የፍቅር መግለጫ ማህተም ነው….ወሲብ ማለት የአብራክ ክፍይን መተኪያ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ልጆች ደግሞ ለአንድ ትዳር የተለየ ትርጉም የሚሰጡ ፍፅማዊ በረከቶች ናቸው፡፡
ሰሎሜና አላዛር እናትዬውን ለመጠየቅ ኮዬ ፈጬ ከንደሚኒዬም ይገኛሉ፡፡የተለየ ጉዳይ ካልተፈጠረ በስተቀር በ15 ቀን አንዴ እንዲህ እየመጡ እናትዬውን ይጎበኛሉ፡፡ይሄንን በየ15 ቀን የሚደረጉትን ጉብኝት ከእነሱ በላይ እናትዬው ነች የምትናፍቀው፡፡ምክንያቱም እነሱ እንድታገለግላት ከቀጠሩላት አጋዥ ልጅ እግር ሴት  በስተቀር ለብቻዋ ነው የምትኖረው፡፡አላዛርም ሆነ ሰሎሜ አብራቸው እንድትኖር ደጋግመው ለምነዋት ነበር፡፡እሷ ግን ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡
አላዛርን ሳሎን እንደተቀመጠ ከጎኑ የተቀመጠችው ሰሎሜ  ከተቀመጠችበት ተነሳችና .‹‹ማሬ እስኪ እማዬን ኪችን ሄጄ ላግዛት፡፡››አለችው፡፡
‹‹ምነው ልጅቷ የለችም እንዴ?››
‹‹ዛሬ  ቤተሰቦቼን ልጠይቅ ብላ ፍቃድ ተሰጥቶት ሄዳለች.. ››አለችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ እቴቴን ይዘናት ወጣ ብለን ውጭ መዝናናት እንችላለን..ኪችን ገብታ ለእኛ ምግብ ማዘጋጀት የለባትም ፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ እቴቴን የማታውቃት ይመስላል…ለማንኛውም መጣሁ…እንዳይደብርህ ሪሞቱ ያውልህ ቲቪውን ክፈተው፡፡››ብላው ወደኪችን ገባች፡፡እናትዬው በእስቶቭ ላይ ጎን ለጎን ሁለት ድስት ጥዳ አንዱን ስታማስል ነበር የደረሰችው፡፡
‹‹መጣሽ ልጄ?››
‹‹አዎ አማዬ…ምን ላግዝሽ?››
‹‹ምንም …በቃ እየበሰለ ነው፤ራባችሁ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም ..አርፍደን ከእንቅልፋችን ስለተነሳን  ቁርስ በቅርብ ነው የበላነው፡፡››
በሰጠቻቸው መልስ ባለመደሰት አፋቸውን ወደጎን በማሽሟጠጥ አጣመው‹‹ጥሩ ነው.. እስከአራት አምስት ሰዓት መተኛቱ ጥሩ ነው..ግን ዝም ብሎ መተኛት ምን ረብ አለው?››ሲሉ መለሱላት፡፡
የንግግራቸውን አቅጣጫ እያወቀች ‹‹እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?..››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹ካንቺ በኃላ ያገቡ ጓደኞችሽ ሁሉ እኮ  ወለዱ..ሌላው ይቅር ከአምስት ወር በፊት ያገበችው ቤተልሄም የዛሬ ሳምንት ወልደ ሄጄ ጠየቅኳት፡፡››
‹‹እንዴ እማ …ልጅ በዘጠኝ ወር አይደል እንዴ የሚወለደው?በአምስት ወር እንዴት ማድረስ ቻለች?››
‹‹ቀልጂብኝ…ደግሞ እኮ ስላረገዘች ነው ተካልባ ያገባችወ እያሉ ሲያሟት እኔም አብሬ ማማቴ..ምነው አንቺም ከማግባትሽ በፊት አርግዘሽ ቢሆን ኖሮ…፡፡››
‹‹እቴቴ…. እንተዋወቃለን እኮ..አሁን እደዛ አድርጌ ቢሆን አታዝኚብኝም ነበር..?››
‹‹ልዘና ..የተወሰነ ጊዜ ተነጫንጬ ተወዋለው…ምንም ባዝን አሁን እያዘንኩ እንዳለሁት አላዝንም…ደግሞም  እስካሁን በእግሩ ለመሄድ የሚታገል ወፌ ቆመች ወፌ ቆመች የምለው የልጅ ልጅ ይኖረኝ ነበር፡፡››
‹‹አይዞሽ እማዬ… በተከታይ ሶስት አራቱን አንጠባጥብልሻለሁ፡፡››
‹‹ልጄ እናት መሆን እንዲሁ ተራ ነገር አይምሰለሽ..ለህይወትሽ ጥልቅ ትርጉም የሚሰጥሽ እናትነት ነው፡፡እናት መሆን ማለት በህይወት ውስጥ ስርሽን የህይወት እንብርት ድረስ ዘረጋሽ ማለት ነው፡፡እናት ስትሆኚ ለህመም በቀላሉ እጅ አትሰጪም፤እናት ስትሆኚ ብትቸገሪ እራሱ በቀላሉ ተስፋ አትቆርጪም፤እናት ስትሆኚ ለቀናት እህል ባትቀምሺ ራሱ ተዝለፍልፈሽ ለመውደቅ  አትሞክሪም፤እናት ስትሆኚ  መሞት ብትፈልጊ እንኳን ለመሞት መብት የለሽም፤እኔ አንቺን አጎጉል በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ነው የወለድኩሽ..እንደእንቺ በወግ በማአረግ አግብቼ መሰረቱ የፀና ትዳር መመስረት አልቻልኩም፡፡እና ደግሞ አንቺን ስወልድ በደረሰብኝ የማህፀን ጉዳት ሌላ ልጅ ወልጄ ወንድም ወይም እህት እንዲኖርሽ ማድረግ አልቻልኩም…አሁን የምትወልጂያቸው ልጆች ልጆችሽ ብቻ አይደለም የሚሆኑት ወንድምና እህቶችሽም ጭምር ነው የምትወልጂው..ለዛ ነው ቀንና ሌት የምጨቀጭቅሽ፡፡››
‹‹ይገባኛል እቴቴ…አይዞሽ!! ››
ሁል ጊዜ ይሄንን ጥያቄ እናትዬው ባነሳችላት ቁጥር ‹‹አይዞሽ››ከማለት ውጭ ሌላ የምትመልስላት መልስ ኖሯት አያውቅም፡፡አሁን አሁን ግን መልሷ በጣም ከመደጋገሙ የተነሳ ለእናቷ ብቻ ሳይሆን ለእሷም በጣም እጅ እጁ እያላት ነው፡፡ግን ለጊዜው ሌላ ምርጫ የላትም፡፡
እናትዬው‹‹አይዞሽ ብቻ ምንም አይረባኝም…የምትጠቀሚውን መከላካያ መድሀኒት ዛሬውን አውጥተሸ  ሽንት ቤት እንድትጥይው ፈልጋለሁ፡፡፡››አሏት፡፡
‹‹እሺ እኮ አልኩሽ እማዬ..እሺ››
‹‹በይ ወጡ ደርሶል…ታጠቡና ተዘጋጁ፡፡ ››
‹‹እሺ›› ብላ በደፈረሰ ስሜትና በተከፋ ፊት ወደ ባሏ ተመለሰች፡፡ይሄ ጭቅጭቅ ምርር እያደረጋት ነው፡፡ደግሞ የእናቷ ብቻ ቢሆን ምን አለበት..ጠቅላላ የሚያውቋት ሰዎች በተለይ ትንሽ ጠና ያሉ ሴቶች በሙሉ በሆነ አጋጣሚ ፊት ለፊት ሲያገኞት‹‹..እሺ መቼ ነው ገንፎ የምንበላው…?ምነው ሰውነትሽ ጨመረ..?አረገዝሽ አይደል?››በቃ ቋቅ እስኪላት ድረስ ምርር ያደረጎት ጉዳዬች ናቸው፡፡
እናቷ ደጋግማ ስትጠይቃት…‹‹ትንሽ ልቆይ ብዬ ነው..መድሀኒት ስለምጠቀም እንጂ እስከአሁን አረግዝ ነበር ፡፡››የሚሉ መልሶችን ደጋግማ መልሳላቸዋለች፡፡ታዲያ ‹‹አይ እናቴ እስከአሁን ያላረገዝኩት ያገባሁት ባሌ ከእኔ ጋር ወሲብ መፈፀም እምቢ ስላለ ነው፡፡እስከአሁን ድንግል ስለሆንኩ ነው ፡፡››ትበላቸው እንዴት ? የዚህ ነገር መቋጫው የት እንደሆነ መገመት እራሱ እየከበዳት ነው፡፡
ምሳ ቀርቦ በልተው ካገባደዱ በኃላ ይዘው የመጡትን ወይን ለሶስቱም ተቀድቶ እሱን እየተጎነጩ በግማሽ ልብ የተከፈተውን ቴሌቭዥን እያዩ በግማሽ ልብ የባጥ የቆጡን ርእስ እያነሱ ሲጫወቱ ቆዩ ፡፡በድንገት ግን ቀልብ የሚስብ ፕሮግራም ወሬያቸውን እንዲያቆሙና ሙሉ በሙሉ ፀጥ ብለው እንዲያዳምጡ አስገደዳቸው፡፡ጣቢያው ኢቢኤስ ነበር፡፡
👍648😢2👏1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

በሰሎሜ ላይ እየሆነ ያለው ግን ተቃራኒው ነው፡፡ወሲብን ሊሰጣት ያልቻለው እሱ ነው፡፡ግን ደግሞ ቢያንስ እስከአሁን ጥላው አልሄደችም፤ቢሆንም በውስጧ የፈጠረባትን ስለልቦናዊ ቀውስ ልትቋቋመው ከምትችለው በላይ እየሆነባት ነው፡፡እንደማንኛውም ሴት በእሷ አረዳድ‹ ከእኔ ጋር ወሲብ የማይፈፅመው  ወሲብ የማድረግ ፍላጎት ሳይኖረው ቀርቶ ሳይሆን እኔን ስለማያፍቅረኝ ቢሆንስ?› የሚለው ሀሳብ ሁሌ ነው በአእምሮዋ እየተሰነቀረ የሚያስጨንቃት፡፡
ከወራት በፊት ግን ይሄንን ለማረጋገጥ አንድ ነገር አድርጋ ነበር፡፡‹‹እንዴት አድርጌ የእውነት እንደሚያፈቅረኝ አውቃለሁ?ከእኔ ጋር ወሲብ ማይፈጽመው ሌላ ቦታ በድብቅ የሚሄድባት ሴት ብትኖስ?››በወቅቱ ዋና አላማዋ እነዚህን በእምሮዋ ይጉላሉ የነበሩ ጥያቄዎችን በተግባር ማረጋገጥና ውጤቱን ተከትሎ የራሷን ውሳኔ ለመወሰን ነበር፡፡
ከብዙ መብሰልሰልና መብከንከን በኃላ ምርጥ ያለችውን እቅድ አወጣች፡፡ ለዚህ ተልዕኮ ልትረዳት የምትችል አንድ ጓደኛዋ ትዝ አለቻት፡፡ሀይስኩል አብራት የተማረቻና ስታገባም  ሚዜዋ የነበረችውን  ሂሩትን ደውላ ቀጠረቻት፡፡
ሂሩት ሰሎሜን ብቻ ሳይሆን አላዛርንም በደንብ ታውቃዋላቸው ….አብረው በመማራቸው የቀረቤታቸው መጠን ይለያይ እንጂ ለሁለቱም ጓደኛ ነች ማለት ይቻላል፡፡ እንደውም ሂሩት ዘጠነኛ ክፍል እያሉ በተወሰነ መልኩ ወደግሩፑ የተቀላቀለችው ለአላዛር ከነባራት የተለየ ፍቅር የተነሳ ነበር፡፡በወቅቱ አማልዬ የራሴ አደርገዋለው የሚል ፅኑ እምነት ነበራት፡፡ለዛም ይረዳት ዘንድ የግሩፑ ብቸኛ ሴት የነበረችውን ሰሎሜን በተለየ ሁኔታ ቀረበቻት፡፡ በኃላ ግን የአላዛር ጉዳይ እንዳሰበችው ባይሳካላትም ከሰሎሜ ጋር ያላትን ጓደኝነት እንደውም ካሰበችው በላይ በጠበቀ ሁኔታ ማስቀጠል ችላለች፡፡ሂሩት ከሰሎሜ ጋር  ስትነፃፀር በጣም ልቅም ያለች ቆንጆ ልጅ ነች፡፡በዛ ላይ በጣም ተጫዋችና ቀልጣፋ፡፡
የተቀጣጠሩበት ሆቴል እንደተገናኙ ለወሬ የቸኮለችው ሂሩት ገና በቅጡ ተቀምጠው ያዘዙት መጠጥ እንኳን ሳይቀርብላቸው ‹‹በፈጣሪ… እንዲህ አንገብግበሽ የጠራሺኝ ምን ልትነግሪኝ ነው?፡፡›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ቆይ ተረጋጊ …ነግርሻለው፡፡››
‹‹የጠረጠርኩት ብቻ እንዳይሆን?››
ሰሎሜ ደንግጣ ‹‹ምንድነው የጠረጠርሽው?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ክርስትና እናት ልትሆኚ ነው እንዳትይኝ?››
ሰሎሜ የሄሩትን ያልተጠበቀ ወሬ ስትሰማ ዘወትር ‹‹መቼ ነው አያት የምታደርጊኝ ?››የሚለው የእናቷ ንዝንዝ ትዝ አላት፡፡
‹‹እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?››
‹‹አንቺ ደግሞ መቼስ እኔ እያለሁ ልጅሽን ለሌላ ሰው ክርስትና አትሰጪያትም!!››
‹‹የምን ልጅ?››
‹‹ተይ ባክሽ…!!!ገና እንገናኝ ስትይኝ ነው የጠረጠርኩት ..አርግዣለሁ ልትይኝ ነው አይደል…?ስንት ወር ሆነሽ…?መቼስ እናትሽ በአንድ እግራቸው ቆመው ደንሰዋል?››
‹‹ፅድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ ››አለች እቴቴ፡፡
‹‹ያንቺ እናት ደግሞ ሁሌ የማይገባ ተረት ነው የሚተርቱት…ምን ማለት ነው?፡፡››
ሰሎሜ በማይረባ የጓደኛዋ ግምት ተበሳጨች‹‹አሁን በፅሞና አድምጪኝ …መጀመሪያ አሁን የምነግርሽን  ነገር ለማንም እንዳትናገሪ…እንደው ብንጣላ እንኳን ሚስጥር አድርገሽ እስከወዲያኛው በውስጥሽ እንድትቀብሪው እፈልጋለው፡፡››
ሂሩት  ፈራች‹‹አረ ችግር የለውም አታውቂኝም እንዴ…?.››
‹‹በእናትሽ ማይልኝ፡፡››
‹‹ይሄን ያህል ምን ቢሆን ነው..?ሰው ገድለሽ ቀብረሽ ነው እንዴ..?ነው ወይስ እንዳቃብርሽ ልትለምኚኝ ነው?በእማሚ ሞት እኔ እንዲህ አይነት ነገር ፈራለሁ፡፡››
‹‹አትቀልጂ!!!... ወይ ማይልኝ ካለበለዚያ  አልነግርሽም፡፡›› ኮስተርተር አለቻባት፡፡
‹‹እሺ እማዬ ትሙት…ለማንም አልናገርም፡፡››
‹‹የባልና ሚስቶች ጉዳይ ነው…››
‹‹ማለት..?››
‹‹የእኔ እና የአላዛር ጉዳይ..››
‹‹አንቺና አላዛር ምን ሆናችሁ?››
‹‹እንዴት ብዬ ልንገርሽ …አሳፋሪ ነው፡፡››
‹‹እንደፈለግሽ አድርገሽ ንገሪኝ፡፡ምንድነው እኔ ጓደኛሽ ነኝ እኮ ..በእኛ መካከል መተፋፈር አለ እንዴ..?ለዛውም ካስማልሺን በኃላ ትቅለሸለሻለሽ?ግፋ ቢል ሰረቅኩበት ልትይኝ ነው፡፡›› በማለት ቅድሚያ ወደአእምሮዋ የመጣላትን ሀሳብ ሰነዘረች፡፡
‹‹በስመአብ….አንቺ …አታውቂኝም ማለት ነው..?እንዴት በባሌ ላይ ሰርቃለሁ?››
‹‹ያልሆነ ነገር እንድገምት ካልፈለግሽ… ንገሪኛ፡፡››
‹‹ወሲብን በተመለከተ ነው፡፡››
ሂሩት ይበልጥ ተነቃቃች..‹‹ወሲብ ምን ?አደገኛ ሆኖ አሰቃየሽ….?ምን…. ኩላሊትሽን እያመመሽ ነው?››
ሰሎሜ ከት ብላ ሳቀች..የመገረም ሳቅ…የንዴትና የብስጭት ሳቅ፡፡
አምጣ..አምጣ ‹‹ወሲብ ማድረግ ካቆምን በጣም ቆየን …››ስትል ጉዳዩን አፈረጠችው፡፡
‹‹ቆየን ማለት…?አምስት ቀን….አንድ ሳምንት..ወይስ አንድ ወር?››
በተጎተተ ንግግር ‹‹ስድስት ሰባት ወር አለፈን…..››አለቻት…፡፡
‹ጭራሽ አድርገን አናውቅም እሰከዛሬ ድንግል ነኝ ›› ብላ ልትነግራት አቅም ማግኘት አልቻለችም….እንዴት ከገባሁ አንድ አመት ቢያልፈኝም ባሌ እስከዛሬ ነክቶኝ አያውቅም..  ብላ ከአንደበቷ  አውጥታ ትናገር.. ለዚህ ነው ከፊል እውነትና ከፊል ውሸት ደባልቃ ነግራት መፍትሄ ያለችውን ሀሳብ አቅርባላት እንድትተባበራት ለመጠየቅ የፈለገችው፡፡
‹‹ሰባት ወር…!!ምነው ?እናንተ ባለትዳሮች እኮ አንዴ በእጃችሁ አስገብታችሁ እና የራሳችሁ መሆኑኑ ካረጋገጣችሁ  በኃላ ችላ የምትሉት ነገር አለ፤እምቢ ብለሽው ነው አይደል?››
‹‹አይ …አኔ አይደለሁም፤እሱ ነው እምቢ ያለኝ፡፡››
‹‹እኔ አላምንም..እንዲሁ አይን አይንሽን አፍጥጦ እያየ ..አፍ አውጥቶ አምቢ እልፈልግም ጠግቤያለሁ..አለሽ?››
‹‹ያው አፍ አውጥቶ እምቢ ባይልም…እናድርግ ብሎኝ ግን ጠይቆኝ አያውቅም፡፡››
‹‹እንዴ ባልሽ አይደለ እንዴ…?እሱ ተዘናግቶ መጠየቅ ካቆመ አንቺ አትጠይቂውም?ብዙ ጊዜ እኮ ብር የሚያሳድዱ የቢዝነስ ሰዎች እንዲህ ናቸው….ሚስታቸውና እና ብራቸውን መለየት ይከብዳቸዋል ፡፡ስለዚህ እሱ ዝም ካለ አንቺ መጠየቅ ነበረብሽ››
‹‹እንዴት ብዬ? ምን ነካሽ ሴት እኮ ነኝ?››
‹‹እንዴ ባልሽን…?ወይኔ እኔ በሆንኩ… ከስር አስተኝቼ ነበር ….በግድ የምደፍረው››
‹‹ባክሽ አትቀልጂ…ወንድ ልጅን ደግሞ እንዴት አድርገሽ ነው የምትደፍሪው?፡፡››
‹‹ለምን አልደፍረውም ..ምነው ጉልበተኛ ስለሆኑ..?እነሱ ጉልበተኛ ቢሆኑም እኛ ደግሞ ከእነሱ የተሻልን ጥበበኞች ነን››
‹‹የጉልበቱ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ …እንዴት አድርገሽ ታቆሚዋለሽ››አላቻት እያፈረች፡፡
‹‹ባክሽ ዘዴ አይጠፋም…አሽቼም ሆነ አልቤ እንዲቆም ማድረግ አያቅተኝም፡፡››
‹‹ይሁንልሽ… አሁን  ይሄንን ጉዳይ እንድፈታ እንድታግዢኝ ነው  የምፈልገው፡፡››
‹‹እንዴት አድርጌ …?በማቆም ነው በመድፈር…?ምን? እጅና እግሩን እንድይዝልሽ ትፈልጊያለሽ?››
‹‹እኔ ተጨንቄ ምሆነው ጠፍቶኛል አንቺ ትቀልጂብኛለሽ አይደል…?በቃ ተይው ተነሽ እንሂድ››ሰሎሜ ተበሳጨች፡፡
‹‹በቃ እሺ ይቅርታ….ንገሪኝ እሺ ምን እንዳግዝሽ ነው የምትፈልጊው?፡፡››
‹‹ምን አልባት ከእኔ ጋር ወሲብ መፈፀም ያቆመው ጠልቶኝ ማለቴ ፍቅሩ አልቆ ይመስለኛል..ያንን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፡፡››
‹‹አረጋግጠሸስ?››
👍678
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
===================

አላዛር አልጋ ላይ ተጋድሞ በጥልቀት እያሰበ ነው፡፡ሰሎሜ ቀን ከሂሩት ጋር ያወራችውንና የዶለተችውን ነገር መልሳ በደንብ እያመዛዘነች ስለሆነ ፈጥና ወደመኝታ ቤት ለመግባት አልፈለገችም፡፡ሳሎን ሶፋ ላይ ተዘርግታ አይኖቾን የተከፈተው ቲቪ ላይ በመሰካት በሀሳብ ግን ነጉዳለች፡፡

በተመሳሳይ አላዛርም የባለቤቱን የከረረ የስሜት መለዋወጥ በእራት ሰዓት ስላስተዋለ ጥልቅ ትካዜ ውስጥ ገብቷል፡፡ ‹‹እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምቀጥለው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ሚስቱን ያፈቅራታል..፡፡በጣም ነው የሚያፈቅራት፡፡ለመጀመሪያ ቀን ካገባት ቀን ጀምሮ በሙሉ ልቡ እየተንከባከባት ነው፡፡ግን ምንም ያህል ቢጥር ደስተኛ ሊያደርጋት አልቻለም፡፡እስከአሁን እንደወንድሟ ነው አብሯት እየኖረ ያለው፡፡መሆን የሚገባው  የሚጠበቅበትም ግን እንደባሏ መሆን ነበር፡፡እንደዛ ቢሆን ልክ እንደተመኘው ሙሉ ደስተኛና ፍልቅልቅ ትሆንለት ነበር፡፡ ያንን ማድረግ ግን አልቻለም…፡፡በጣም እያስጨነቀው ያለው ደግሞ እስከአሁን አለመቻሉ አይደለም..፤ መቼ ሊችል እንደሚችል ፍፁም አለማወቁ ነው፡፡እጅን አንቀሳቀሰ እና ወደቢጃማ ኪሱ ሰደደ..ስልኩን አወጣና ጎግል ከፈተ፡፡ ስንፈተ ወሲብ ብሎ  ሰርች ሲያደርግ ብዙ ምርጫዎች መጡለት፡፡

ከመካከላቸው በደመነፍስ መረጠና አንዱን ከፈተው፡፡ትራሱን ቀና አድርጎ አስተካከለና  የሆነ የሚጠቅም ነገር ባገኝ በሚል ተስፋ ማንበብ ጀመረ፡፡

ርእሱ ‹‹የስንፈተ ወሲብ አይነቶች ፤ምክንያቶችና መፍትሄዎቹ›› ይላል፡፡

በወንዶች ላይ የሚታዩት የስንፈተ ወሲብ ችግሮችን በሶስት መልኩ ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው የብልት መነሳት ችግር ወይም በሌላ አገላለፅ ስንፈተ ወሲብ እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ ሁለተኛው እርካታ ደረጃ ሳይደርስ የዘር ፈሳሽ ማውጣት ወይም ገና አካባቢው ጋር እንደደረሱ  መርጨት   ሲሆን ሶስተኛው  ደግሞ የወሲብ ስሜት አልባነት ወይንም ጭሩሱኑ ወሲብ  ለማድረግ  ፍላጎት ማጣት ናቸው፡፡
አላዛር ንባቡን ገታ አደረገና ስላነበበው ነገር ማሰላሰል ጀመረ..‹‹ከእነዚህ ሶስት ምክንያቶች መካከል የእኔ ችግር የትኛው ላይ ነው የሚያርፈው?››ሲል እራሱን ጠየቀና

ማሰላሰል ጀመረ፡፡የእሱ ችግር ሙሉ በሙሉ የወሲብ ስሜት ማጣት እንደሆነ ተረዳ፡፡እና ንባቡን ካቆመበት ቀጠለ፡፡
የመጀመሪያውን ስንመለከት የብልት መነሳት ችግር ያለባቸው ሰዎችን በብዛት እናገኛለን፡፡ ይሄ አይነት የወሲብ ችግር በተለያየ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ላይ የሚከሰት ቢሆንም  በተደጋጋሚ ወደ ህክምና የሚመጡት ግን ዕድሜያቸው ከስልሳ ዓመት በላይ የሆኑት ሰዎች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ወጣቶችም አልፎ አልፎም ቢሆን የዚህ ጉዳይ ተጠቂዎች መሆናቸውን ሪፖርት ሲያደርጉ ይታያል፡፡

ችግሩ ከየት ይነሳል? ብለን ስንመለከት ሁለት አይነት ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ከስነ ልቦና  ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተለያዩ በሽታዎች  በሚፈጥሩ የጎንዬሽ ተፅዕኖ ምክንያት ይከሰታል፡፡ ዋነኛው የስንፈተ ወሲብ መንስኤ ተብሎ የሚጠቀሰው የስነ-ልቦና ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአዕምሮ ውጥረት ፤ ጭንቀት እና የተለያዩ ሀሳቦች ለስንፈተ ወሲብ ችግር ያጋልጡናል፡፡  የአካል ድካም እና መዛልም ሌለኛው ምክንያት ነው፡፡ ለምሳሌ አካሉ በብዙ ስራ ሲንገላታ የዋለ ሰው በግንኙነት ወቅት የብልት መነሳት፣ ስሜት ማጣት አሊያም ለወሲብ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሊገኝ ይችላል፡፡
አንድ ሰው የሀሳብ መደራረቦች በአእምሮው እንደታጨቀ ወሲብ ለማድረግ በሚሞክርበት ጊዜ  ብልት ትክክለኛው ጥልቀት ላይ ደርሶ ተገቢውን እንቅስቃሴ ከማድረጉ በፊት   አስቀድሞ ጥንካሬውን የሚያጣበት ሁኔታ ይከሰታል ፡፡ ይህን በምሳሌ ብንመለከት ከፍቅር ጓደኛው ጋር ወሲብ በሚፈፅምበት ወቅት ነጋዴ ከሆነ ስለተጋረጠበት የንግድ ችግር የመስሪያ ቤት ኃላፊ ከሆነ ስላልተሳኩ የድርጅቱ እቅዶች ካለው ኃላፊነት ጫና የተነሳ በአዕምሮው ሊመላለሱበት ይችላሉ፡፡ ይህም ጥሩ ያልሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳይከውን ምክንያት ይሆነዋል፡፡ግብረስጋ ግንኙነት ደግሞ በባህሪው ሙሉ ለሙሉ ትኩረት የሚሻ የስሜት ተራክቦ ነው፡፡ ሌላው በባልና በሚስት መካከል አለመግባባት እና ቅሬታ በሚኖርበት ጊዜ ተነሳሽነቱ በሁለቱም ወገን ይቀንሳል፡፡……..
እስከአሁን ያነበባቸው የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚያጋልጡ ምክንያቶች ለጠቅላላ እውቀት ጥሩ ግንዛቤ የሰጡት ቢሆንም ቀጥታ የእሱን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል መፍትሔ ሚጠቁሙ ሆነው አላገኛቸውም..ቢሆንም ግን ተስፋ ቆርጦ ንባቡን ማቋረጥ አልፈለገም…ትንፋሹን ሰበሰበና ማንበቡን ቀጠለ፡፡
የአንድሮጂን ሆርሞን መመረት ወንዶች ላይ ብዛት ያለው  የደም ፍሰት ወደ ብልት እንዲዘዋወር በማድረግ ብልት እንዲነሳ ያደርጋል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸው እንደ ጭንቀት፤በስራ መዛል ወዘተ አይነት  ምክንያቶች ይህን ሆርሞን በተገቢው መንገድ እንዳይመረት ያደርጋል፡፡በዛም ምክንያት ወደብልት የሚፈሰው የደም መጠን አናሳ ስለሚሆን የብልት በተገቢው ጥንካሬ የመቆም ችግር ያጋጥመዋል፡፡ይሄን ለማካካስ ሲባል በተለይ በወጣቶች የወሲብ  ፊልሞች ለማየት ወደመነሳሳት  ያዘነብላሉ፣ ይሄም  በጫና፣ በሃዘን እና በድካም ላይ ሆነንም የወሲብ ስሜታችን እንዲነሳሳ ያደርጋል፡፡ያ ደግሞ በተለይ ለብልት መነሳሳት አና ለፍላጎት መጨመር ጊዜያዊ መፍትሄ ሆኖ ቢያገለግልም በቆይታ ግን የራሱ የሆነ የጎንዬሽ ጉዳት ማስከተሉ አይቀርም፡፡የፊልም ኢንደስትሪው ሚያመነጫቸው የወሲብ ፊልሞች በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከዛም አልፎ በጎልማሶች ዘንድ በደንብ የሚታዩ ናቸው፡፡እንዚህ ወሲብ ፊልሞች ከላይ ሲታዩ እጅግ ማሪኪ ስሜት ቀስቃሽና መንፈስ አነቃቂ መስለው ቢታዩም በሚያየው ወጣት ላይ የሚያስከትሉት ስነልቦናው ቀውስ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡አንደኛ ወጣቱ የአካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ዝግጅት ሳያደርግ ወጣ ያሉ አፈንጋጭ ወሲባዊ ተራክቦ እንዲያደርግ ይወሰውስታል፡፡ያ ደግሞ ለቋሚ  የጤና ችግርና  ወሲባዊ ችግር ይዳርገዋል፡፡ሁለተኛ በፊልሞቹ የሚደረጉ ወሲባዊ ተራክቦዎች ከሰውኛ ይልቅ ሜካኒካል ገፅታ ያላቸው ከ30 ደቂቃ አስከአንድ ሰዓት የሚዘልቁ አይነቶች ናቸው፡፡

እርግጥ አንድ ሰው በውሲብ ግንኙነት ያንን ያህል ሊቆይ አይችልም ለማለት አይደለም….ግን ከሺ ጥንዶች በአንዶቹ የሚከሰት ነገርን  እንደኖርማልና የተለመደ አድርጎ ማቅረብ በአብዛኛው ላይ የሚፈጥረው ስነልቦናዊ ውዥንብር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ለምሳሌ በስንፈተወሲብ ችግር የሚመደበው ቀድሞ መርጨት ችግር የሚባለው አንድ ሰው ወሲብ ጀምሮ ከአንድ ደቂቃ በታች በሆነ የጊዜ ርዝመት ውስጥ የዘርፍሬውን ካፈሰሰ ነው፡፡እንግዲህ ሁለትም ሶስትም አምስትም ደቂቃ ኖርማልና በብዙ ውንዶች የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡ይሄንን ሀቅ ወንዱም ሆነ ሴቷ ማወቅ አለባቸው፡፡ሀያ ..ሰላሳ ደቂቃ መቆየት የቻለም እንደዛው ያንን እንደጀግንነት ማውራት ትርጉመ ቢስ ነው፡፡ዋናው ምን ያህል የጊዜ ርዝመት ቆየ ሳይሆን በቅፅበት ውስጥም ቢሆን ምን ያህል ፍፃማዊ ደስታ ተቀያይረናል…ምን ያህል በአየር ላይ ተንሳፈን ነበር…?ምን ያህልስ ሰዓት አንዳችን  በሌላችን ውስጥ ጠፍተን ነበር…?የሚለውን ነው መመዘኛ መሆን ያለበት… እና አንድ ሰው በተቻለው መጠን እነዚህን የምራባዊያን የወሲብ ፊልሞችን ከማየት እራሱን
👍5310
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
================

ሰሎሜና ሂሩት እንደተባባሉት ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል፡፡ .. ሂሩት በሰበቡ እነሱ ቤት እንደምታድር ለአላዛር ነግራው በሰዓቱ እንድትገኝ አደረገች፡፡እራት በልተው መጠጥ እየቀማመሱ ካመሹ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ ከእናትዬው እንደተደወለላትና እንዳመማቸው በመናገር ብቻቸውን ትታቸው ሄደች፡፡ አላዛር ልከተልሽ ቢላትም እምቢ አለችው፡፡ቀጥታ እናቷ ቤት ሳይሆን ቀን ወደዘጋጀችው ከሰፈራቸው ብዙም የማይርቅ ሆቴል ነበር የሄደችው፡፡ቀጥታ የተከራየችው ቤርጎ ገብታ  ምን ይፈጠር ይሆን እያለች ስትጨነቅና ስትገላበጥ አደረች፡፡እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር ነበር ንጊቱን የሚያበስሩ የወፎችን ዝማሬ የሰማችው…ሂሩትም   ገና ሰማይና ምድሩ በቅጡ ሳይላቀቅ ከለሊቱ 12 ሰዓት አካበቢ ነበር የደወለችላት፡፡ወዲያው ክፍሏን ለቃ ወጣችና የሆቴሉ ፓርኪንግ ጋር ያቆመቻትን መኪና ውስጥ ገብታ ወደነገረቻት ቦታ ተፈተለከች፡፡በወቅቱ የተከፈተ ካፍቴሪያ ወይም ሆቴል ማግኘት ስላልቻሉ ሰሎሜ መኪና ውስጥ ቁጭ ብለው ነበር ያወሩት፡፡

ሶሎሜ ስታገኛት ፈክታና ተፍለቅልቃ አገኛታለሁ ብላ ነበር ያሰበችው..ግን አኩርፋና ለምቦጯን ጥላ ነው ያገኘቻት፡፡ይሄ ደግሞ ይበልጥ አስደነገጣት፡፡‹‹የሆነ ነገር ባይፈጠርማ እንደዚህ አትነፋፋም ነበር፡፡በቃ ተሳክቶላት አሳስተዋለች..በቃ ችግሩ ከእኔ ነው››ብላ ደመደመች፡፡ድምጽ አውጥታ ብትጮህ ወይም እንባዋን ዘርግፋ ብታለቅስ ደስ ይላት ነበር፡፡ግን እንደዛ በማድረግ ሂሩት ፊት ደካማ ሆና መታየት አልፈለገችም፡፡

ከአሁን አሁን አንደበቷን አላቃ የሆነ ነገር ትለኛለች ብላ ብትጠብቅ ዝም ብላ እንዳቀረቀረች የቀኝና የግራ እጇን መዳፎች አንድ ላይ አቆላልፋ እያፍተለተለች ነው፡፡እሷን እንድትናገር መጠበቁ አሰልቺ ሆኖ ስለታያት‹‹እሺ እንዴት ሆነ?››በማለት ቃል አወጣችና ጠየቀቻት፡፡

‹‹በፊትም ተይ ይቅርብኝ ያልኩሽ ይሄን ፈርቼ ነበር…››እንባዋን ዘረገፈችው፡፡

‹‹አይዞሽ ..ምንም የሚያስለቅስ ነገር እኮ የለም..ምንም ነገር ሊፀፅትሽ አይገባም…እኔ እራሴ ፈቅጄና ገፋፍቼ እኮ ነው እንድታደርጊ ያደረኩሽ…አሁን ሁሉ ነገር ግልፅ ሆኖልኛል…… ስለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ›› አለቻት፡፡

ከአንደበቷ እየተወረወረ የሚወጣው ቃል ለራሷ እራሱ ሻካራነቱ እየተሰማት ነበር..እስከዛሬ ለሌላ ሰው ከተናገረቻቸው ንግግሮች እጅግ  መራሩ ንግግር ነው፡፡እንደውም ንግግር እንዲህ ሊመር እንደሚችል ሲሰማት የመጀመሪያ ቀን የህይወት ልምዷ ነበር፡፡

ሂሩት የሆነ ነገር ትላለች ብላ ስትጠብቅ እሷ ግን እጇን ወደኪሷ ከተተችና ሞባይሏን በማውጣት ከፈተችና  ሰጠቻት፡፡

‹‹ምንድነው?››

‹‹እይው በቃል ከምነግርሽ   በምስል ይሻላል ብዬ አንቺ ከወጣሽ በኃላ ያለውን ትእይንት ሁሉ እሱ ሳያውቅ ቀርጬዋለሁ››

‹‹ምን ሊያደርግልኝ ነው የማየው?‹‹ገና ስታስበው ዘገነናት…የገዛ ባሏ… ቀለበት እጣቷ ላይ አጥልቆ ያጫት፤ ቬሎ ሰውነቷ ላይ አልብሶ ያገባትና አንድ ቀን ጭኗን ፈልቅቆ ማያውቀው ሰው አሁን ፊት ለፊቷ የተቀመጠችውን የገዛ ጓደኛዋን እርቃን ሰውነቷን አቅፎ ፤ቅስር ጡቶቻን እየጠባ…መቀመጫዋን እየጨመቀ…ሲያስጮኸት…እላዮ ላይ ወጥቶ ..ሁለቱም በስሜት እሳት ግለው ነበልባሉ በዙሪያቸው ሲንበለበል በምናቧ ሳላችና ዝግንን አላት..እንደምንም የሰጠቻትን ሞባይል አስጠግታ የተቀረፀውን ማየት ጀመረች፡፡ከጠበቀችው ፈፅሞ ተቃራኒ የሆነ ነገር ነው እያየች ያለችው፡፡
ሂሩት እየደነሳች ተራ በታራ ልብሷን ስታወልቅ…አላዛር ፊቱን ስልኩ ላይ አቀርቅሮ እሷን ላለማየት ሲጠነቀቅና ሲሸማቀቅ…እርቃኗን ሔዳ ስልኩን ከእጁ ነጥቃ ወደሶፋው ወርውራ እላዩ ላይ ለመቀመጥ ስትሞክር፤ከላዩ ላይ ወርውሮ ወለል ላይ ጥሏት እየተንዘረዘረ ሲናገር‹‹አንቺ ምን አይነት ክፉ ሴት ነሽ..ጓደኛሽ አንቺን አምና እኮ ነው ባሏን ጥላልሽ የሄደችው…እኔ እንኳን ልሳሳት ፈቅጄ ባስቸግርሽ አንቺ ትሞክሪዋለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም..ደግሞ ከነዛ ሀሉ ጓደኞቾ አንቺን መርጣ ሚዜ ማድረጓ..?አዝናለሁ..እኔ ሰሎሜን በጣም ነው የማፈቅራት ስልሽ እንዲሁ ተራ ፍቅር መስሎ እንዳይሰማሽ….ነፍስ ካወቅኩበት ቀን ጀምሮ ከእናቴ ቀጥሎ ስወድና ሳፈቅራት.. በየሄደችበት እየሄድኩ ሳጅባት… ስታለቅስ አልቅሼ ስትስቅ ስስቅ እድሜዬን የፈጀሁባት ..የማንነቴ ክፋይ ነች፡፡እሷን ከዳሁ ማለት እራሴን ከዳሁ ማለት ነው፡ያ ከሚሆን ደግሞ ህይወቴን ዛሬውኑ ባጣ ይሻለኛል….በይ ልብስሽን ልበሺና እንግዳ ቤት ገብተሸ ተኚ….ይሄንን ቅሌትሽን እንዳልተፈጠረ እንርሳው…ምክንያቱም የማፈቅራት ሚስቴ በጓደኛዋ መከዳቷን አውቃ እንድታዝና አልፈልግም…››ብሎ ጥሏት አንደኛ ወለል ላይ ወደሚገኘው መኝታ ቤታቸው በመንደርደር ሲወጣ ያሳይና ቪዴዬ ይቋረጣል፡፡

‹‹ታድዬ.!!.ይወደኛል ማለት ነው..?አሁንም ከእኔ ፍቅር እደያዘው ነው››…ተንደርድራ ጉንጯ ላይ ተጣበቀችባትና፡፡ አገላብጣ ሳመቻት‹‹ሂሩትዬ አመሰግናለው….ጋንግሪን ሆኖ ሲበላኝ ከከረመ ጨለማ ጥርጣሬ ነው የገላገልሺኝ››

‹‹ችግር የለውም ..በቃ አሁን ልሂድ››

‹‹እንዴ የት ነው የምትሄጂው.?.የምትሄጂበት ላድርስሽ››

‹‹አይ የመጣሁበት ታክሲ እኮ እየጠበቀኝ ነው››መኪናውን በራፍ ከፍታ ወጣች….፡፡

‹‹ወይኔ በጌታ ቁርስ እንኳን አብረን ሳንበላ?››

‹‹አይ ቤት ሄጄ ልብስ ቀያይሬ ወደስራ መሄድ አለብኝ….ሌላ ጊዜ››
ሰሎሜ ከዚህ በላይ ልትጫናት አልፈለገችም‹‹በቃ ሰሞኑን ደውልልሽና እናወራለን አመሰግናለሁ፡››

ሄሩት ሄደችና ከኋላ ቆማ የነበረችው ታክሲ ውስጥ ገባች፡፡
///
የሰው ልጅ ለህይወት ሚያስፈልጉትን ነገሮች በራሱ ለማድረግ በተደጋጋሚ ልምምድ ይማራል…ለምሳሌ ምግብ እንዴት መመገብ እንዳለበት በወላጆቹ ሶስት አራት አመት እያጎረሱት ያለማመዱታል…ከዛ እንዴት ተጠቅልሎ እና ተዝቆ መብላት እንዳለበት መሞከርና ይጀምራል… ከዛ ይችላል…ግራ ቀኙን ለይቶ በትክክለኛው ጫማ ማድረግም እንደዛለው ሁለት ሶስት አመት ይወስድበታል….
የሰው ልጅ ምንም ሳይማር ቀጥታ ወደማድረግ እንዲሸጋገር የሚጠበቅበት ብቸኛው ለህይወት ወሳኝ የሆነው ነገር ወሲብ ነው፡፡ወሲብ ምን እንደሆነ…?እንዴት መነቃቃት..?እንዴትስ ማነቃቃት እንደሚቻል…?እንዴት መሳም እንዴት መዳበስ እንደሚገባው..?በየት በኩል እንዴት አድርጎ እንደሚያደርግ ማንም የሚያስተምረው የለም፡፡በትምህርት ቤት እንኳን ሚሰጡ ትምህርቶች ወሲብን እንደመራቢያ እና መባዣ መንገድ ብቻ በማየት እና እሱ ላይ ብቻ በማተኮር የሚሰጥ ነው፡፡ለመዋለድ ደግሞ ምንም አይነት የወሲብ ጥበብ አይጠይቅም.. ወጣ ገባ ብቻ በማድረግ ትንሽ ገባ ብሎ ዘር መድፋት ብቻ በቂ ነው፡፡ያ ግን የወሲብ አንዱ ግንጥል ጥቅም ነው፡፡ደግሞ ያ አይደለም የሚገርመው…ያለምንም ልምድ ባገኛቸው ቅንጭብጫቢ ሹክሹክታ መሰል መረጃዋች ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ሲፈፅም ‹‹አይ የመጀመሪያው ስለሆነ ነው  ብሎ ለብቃቱ ይቅርታ የሚያደርግለት የለም…በተለይ ወንዱ የዚህ ጉዳይ ተጠቂ ነው፡፡ከመጀመሪያዋ ቅፅበት ጀምሮ ፍፅምነት ይጠበቅበታል ካልተሳካለት እንዲሸማቀቅ ይደረጋል፤ከዛ ህመሙ እየባሰበት ይሄዳል፡፡
👍525👏3
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አላዛር እጅግ ሸበላ የሚባልና  እና የበዛ ውበት አላቸው ተብለው ከሚመደቡ ወንዶች መካከል አንዱ ነው፡፡አብዛኛውን ጊዜ አይደለም ሴቶች ወንዶችም እይታ ውስጥ ለመግባት ለእሱ ዠቀላል ነው፡፡በዚህም የተነሳ የቅርቧም ሆኑ ድንገት ያገኘቻቸው ሰዎች በተለይ ሴቶች እሱን ባሏ ማድረግ በመቻሏ በአለም ላይ ካሉ እድለኛ ሴቶች መካከል አንዷ እንደሆነች በእርግጠኝነት ደጋግመው ይነግሯታል፡፡እሷም በልብ ቁስለትና በፊት ፈገግታ ጥርሷን ብልጭ አድርጋ ምንም አስተያየት ሳትሰጥ ታልፈቸዋለች፡፡

ማታ ከአራት ሰዓት ጀምሮ ነበር ከባለቤቷ ከአላዛር ጋር ደስ ሚል ሙድ ውስጥ የገቡት፡፡ነጭ ወይናቸውን እየተጎነጩ…ጎን ለጎን ተጣብቀዋል፡፡..ጥልቅ የስሜት ትስስር ያለው መላ ሴልን የሚያነቃቃ አይነት ማራኪ የፍቅር ፊልም አብረው ሲያዩ  ነው ያመሹት፡፡ወደ መኝታ ቤታቸው ተከታትለው ሲገቡ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ሰውነቷ ሁሉ ግሏል …አረ ከዛም አልፎ እየተቃጠለች ነው ማለት ይቻላል፡፡‹‹ዛሬ የተለየ ነገር እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ››ስትል በልቧ እያብሰለሰለች ነበር ቧሏን በፈገግታ ተከትላ ወደመኝታ ቤቷ የገባችው፡፡እንደዛ ተስፋ እንድታደርግ ያበረታታት ደግሞ ባለቤቷ ላይ ያየችው ከወትሮ የተለየ መነቃቃትና በፈገግታ የተሞላ አስተያየት ነው፡፡
አልጋ ላይ ቀድሞ ወጣና ብርድልብሱን ገልጦ ከውስጥ ገባ ፡፡ሙሉ ቢጃማውን እንደለበሰ ነበር፡፡እሷም ተቃራኒው አወላለቀችና በፓንት ብቻ ተከተለችውና ከውስጥ ገብታ ተለጠፈችበት፡፡ በጀርባው ነበር የተኛው፡፡ ደረቱን ተንተራሰችና እጆቾን ወደ ሆዱ ላከች፡፡ በስሱ ማሻሸት ጀመረች፡፡ያለምንም እንቅስቃሴ በፀጥታ ላይ ነው፡፡ቀስ አለችና እጆቾን ወደታች አንሸራታ የለሊት ሱሪውን ሰቅስቃ ገባችና ወደታች ወደብልቱ ወረደች…ቀስ እያለች ጨብጣ ማሻሸት ጀመረች፡፡ያው እንደተለመደው ብልቱ ልፍስፍስ እንዳለ ነበር፡፡‹‹እንዴት ነው ግን ይሄንን የመሰለ ዝግባ መሰይ ጠንበለል ሰው እንዲህ አይነት ለንቆሳና ልፍስፍስ ብልት ባለቤት የሆነው?››ሁል ጊዜ ስለእሱ ስታስብ የምትደነቅበት ነገር ነው፡፡ግን አንድ ቀን እንደምንም  ጠንካራና የልብ አድርስ ይሆናል የሚል እምነት አላት ፡፡ለዛ ነው ሁል ጊዜ ዘዴዎቾን እየቀያየረች ከመሞከር የማትሰንፈው ..ቀጥላለች….ምንም የሚያበረታታ ነገር እያየች አልነበረም፡፡ይባስ ብሎ እጁን አንቀሳቀሰና የእሷን እጅ ይዞ ቀስ ብሎ በማስለቀቅ እጇን ወደቦታው መለሰ፡፡ከደረቱ ላይ ቀስ ብሎ አንሸራቶ ትራስ ላይ አስተኛትና ፊቱን አዙሮ እንደተለመደው ጀርባውን ሰጣትና ሽብልል ብሎ ተኛ፡፡በወቅቱ ውስጧ ኩምትርትር ብሎ ሲጨማደድ ይታወቃታል…ከውስጥ ከልቧ አካባቢ የሆነ ታፍኖ ሲብላላ የከረመ እሳት ጎመራ ፈንድቶ እቶን እሳት በመላ ሰውነቷ ሲተፋ እየታወቃት ነው፡፡ቃጠሎውን አልቻለችም ነበር፡፡ .ትግስቷ ተሞጠጠ፡፡ካለመቻሉ በላይ  ለመቻል የሚያደርገው ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ይበልጥ አበሳጫት፡፡
ከአልጋዋ ላይ ተፈናጥራ ተነሳች፡፡እጅግ ከፍተኛ የሚባል ንዴት ላይ ነበረች፡፡ተስፈንጥራ ከአልጋዋ ወረደችና እርቃኗን ሆና ቁልቁል አዘቅቃ ታየው ጀመረ፡፡በእውነት ከሆነ ልታንቧርቅበት…ኮመዲኖው ላይ ያለውን የራስጌ መብራት አንስታ ግንባሩን ልትፈረክሰው….ወይንም በጥፍሮቾ ሁለት አይኖቹን ፈጥርቃ ልታፈርጥለት…ብዙ ብዙ ነገር ማድረግ ፈልጋ ነበረ፡፡ግን ሁሉም የስሜት ህዋሳቶቾ ሊታዘዙላት አልቻሉም፡፡አንደበቷ ተላቆ እንኳን የሆኑ ሁለት ሶስት ቃላትን ለማውጣት አልቻለችም፡፡
ባለቤቷ አልአዛር   አልጋው ላይ እንደተዘረረ ወደላይ አንጋጦ እየተመለከታት ነበር፡፡አቅፎ ሊያባብላት፤ ስሞ ሊያረጋጋት ይፈልጋል፡፡ግን ደግሞ እንደዛ ማድረግ አይችልም፡፡አዎ ለዛ የሚሆን ወኔ የለውም፡፡ፊት ለፊት ካለ ጠረጴዛ ላይ ያለውን ቢጃማውን አነሳችና አጠለቀች…ከኮመዲኖ ላይ ያለውን የመኪና ቁልፍ አነሳችና መኝታ ቤቱን ለቃ ወጣች፡፡ተከትሏት ተነስቶ ነበር፡፡ መኝታ ቤቱን ሳይለቅ ወደመስኮት አመራና አንገቱን አስግጎ እስከመጨረሻው ያያት ጀመር፡፡የውጩን በር በርግዳ ስትከፍት፤ወደመኪናው ገብታ  ሞተሩን አስነስታ ጊቢውን ለቃ ስትወጣ ሁሉ በዝምታ እየተመለከታት ነበር፡፡
ሳሎሜ በውድቅት ለሊት መኪናዋን አስነስታ ቤቷን ለቃ ወጥታ ወደቄራ መስመር አምስት ኪሎ ሜትር በላይ ስለባሏ ክፉውንም ደጉንም እያሰላሰለ ከነዳች በኃላ ነው ሙሉ በሙሉ ወደቀልቧ መመለስ የቻለችው፡፡ምርር  ያለ ንዴት ነበር የተናደደችው፡፡እርግጥ እንዲህ አይነት ንዴት መናደድ የጀመረችው ዛሬ አይደለም፡፤ባለፉት ሁለት አመታት አላዛርን አግብታ እቤቱ ከገባች ጀምሮ  አብሯት ያለ ጨለማ ስሜት ነው፡፡የዛሬውን ልዩ የሚያደርገው ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ነው፡፡
‹‹አሁን ወዴት ልሂድ?››ብላ..አሰበችና ተበሳጨች፡፡ብስጭቷን እጥፍ የሚያደርግባት ደግሞ ይሄ ነው፡፡በባሎ ተበሳጭታ ከቤቷ ለቃ ብትወጣም የትም መሄድ አትችልም.፡፡እናቷ ጋር መሄድ አትችልም፡፡ጓደኞቾ ጋርም ፍፅም አይታሰብም….ምክንቱም በምን ተጣላችሁ ተብላ ብትጠየቅ ማስረዳት አትችልም፡፡እንዴት ብላ፡፡እንባዋ ይረግፍ ጀመር፡፡እያለቀሰች በመሆኗ ደስ አላት፡፡አዎ ሁሉ ጊዜ እንዲህ አይነት አስጠሊታ ስሜት ላይ ስትሆን በማልቀስ እና እንባዋን በማርገፍ ነው ቀዝቀዝ ማለት የምትችለው፡›ማልቀስ ባይኖር እንደውም በውስጥ ሀዘኗ ደርቃ የምትሰነጣጠቅና የምትበታተን ነው የሚመስላት፡፡
መኪናዋን አዙራ ወደቤቷ ለመመለስ ወሰነች…መሪዋን ስትጠመዘዝ  እየተክለፈለፈ ከሚመጣ ሴኖትራክ ጋር ፊት ለፊት ተጋጠመች፡፡ በ5 ሜትር ርቀት ላይ መሆኗን አየች፤በደመነፍስ ቅፅበታዊ ውሳኔ ወሰነችና መኪናዋን ወደግራ ጠመዘዘች በዚህን ጊዜ ከመንገድ ተፈናጥራ ወጣችና ፊት ለፊቷ ካለ የብሎኬት አጥር ጋር ተላተመች፡፡አጥሩ ተፈረካክሶ ሲረግፋ ና ፍርስራሹ የመኪናዋን አካል ሲያለብስ በሰመመን ታያት፡፡ ለደቂቃዎች እራሷን እንደመሳት አድርጎት ነበር፡፡ነቅታ አይኗቾን ስትገልጥ ግን ከግራና ከቀኝ ሶስት ፖሊሶች መሳሪያ ደቅነውባት በተጠንቀቅ ቆመው ነበር፡፡መጀመሪያ ህልም ውስጥ ያለች መሰሏት ነበር፡፡በጥንቃቄ ከፍተው ጎትተው ሲያወጧት ነው…ሁሉ ነገር ተጫባጭ እውነት እንደሆነ  የተረዳችው፡፡..ካልጠፋ የአዲስአበባ አጥር ለዛውም በውድቅት ለሊት የፖሊስ ጣቢያ አጥር ጥሳ መግባቷን ማመን አልቻለችም፡፡ድንዝዝ ነው ያላት፡፡ምን ማሰብ እንዳለባት እራሱ ግራ ተጋብታ ነበር…በመሳሪያ አጅበው ወስደው አንድ ክፍል በመክፈት ከሴት እስራኞች ጋር ቀላቀሏት፡፡
የተኙትን ሰባት የሚሆኑ እስረኞችን እንዳትቀሰቅስ እየተጠነቀቀች..አንድ ኮርነር ላይ ያለች ባዶ ባታ ሄደችና ኩርምት ብላ ቁጭ አለች፡፡በህይወቷ እንደዚህ አይነት ቦታ በስህተት እንኳን ተገኝታ አታውቅም፡፡ከአንድ ሰዓት በፊት ዘመናዊ ቤላ ቤቷ ውስጥ በሞቀ አልጋ ዋ ላይ የቀዘቀዘ ባሏን አካል አቅፋ ተኝታ ነበር ..አሁን ግን ወንጀል ሰርታ ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር ታስራ መገኘቷ ፊልም እንጂ እውነተኛ ታሪክ እየመሰላት አይደለም፡፡የሰው ልጅ ህይወት እንዲህ ቅፅበታዊ  በሆነ አጋጣም እንዳልሆነ ይሆናል የሚል ግምት ኖሯት አያውቅም ነበር፡፡
‹‹ሰሎሜ አብቅቶልሻል…››ስትል ለራሷ ተናገረች፡፡እንደዚህ ልትል የቻለችው የፖሊሶችን የእርስ በርስ ንግግር ስላዳመጠች ነው፡፡
👍6511
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

ማንኛውም የሰው ልጅ መላ አቆሙን እንቅስቃሴውንና ንግግሩን ትኩር ብለው ሲያዩት ከሆነ እንስሳት ጋር ይመሳሰላል፡፡ለምሳሌ አንዳንድ ሰው ከታች ከእግሮቹ ቀጭን ይሆንና ወደላይ ሲሄድ እየሰፋ እየሰፋ ይሄዳል..ትከሻው ከሰውነቱ ባልተመጣጠነ ሰፊ ሲሆን በመጠኑ ጎበጥ ያለ ይሆናል..አንገቱ ደልዳላና አጭር ሆኖ ወደታች ዘንበል ያለ ነገር ሲሆን ከጎሽ ጋር ይመሳሰላል..በቃ በአራት እግሩ ቆሞ የሚሄድ ጎሽ ነው የሚመስላችሁ፡፡ሌላው ደግሞ አላ ረጅም መለሎ ነው ግን ከስር እስከ ላይ ወጥ ነው..ሁሉ ጊዜ ለመጋለብ የተዘጋጀ ይመስላል…እናም ከፈረስ ጋር ይመሳሰላል፡፡ሌላው ደግሞ አለ ስልክክ ያለ ቆንጆ ነው..ፀጉሩ ከግራና ከቀኝ ገባ ብሎ ከፊት ለፊት ወደፊት የወጣ ነው..አይኖቹ ትንሽ የሆኑ ጥልቅ ጥርት ያሉና ተቁለጭላጭ ናቸው…ደረታቸውና ነፍተውና ቀና ብለው በመወጣጠር ነው የሚሄዱት፡፡አይን ያሰብራሉ እንጂ አይን አይሰብሩም..አነዚህ ልክ እንደ አንበሳ ነው የሚመስሉት ፡፡አሉ ደግሞ ሌሎች ሙልጭልችና ስብርብር ያሉ… ተንኮለኞችና ተናዳፊዎች..ልክ እባብን የሚመስሉ፡፡

ሰሎሜ ደግሞ ሲያዬት ሁሌ በራ አበባ ላይ ለማረፍ ክንፏን እያማታች ያለች ቢራቢሮ ነው የምትመስለው፡፡መላ ሰውነቷ ላይ አይነግቡ ደማቅ ቀለማት የተበተኑባት ነው ምትመስለው፡፡ለዛ ነው ጓደኖቾ አልፎ አልፎ ቢራቢሮ እያሉ የሚጠሯት  ፡፡
አላዛር ባለቤቱን በመስኮት ቁልቁል አዘቅዝቆ እያያት በጭንቀት‹‹በፈጣሪ በዚህ ውድቅት ለሊት ይህቺ ቢራቢሮ ወደየት ነው የምትበረው ?››ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹በቃ ወደ እናቷ ቤት ልትሄድ ነው፡፡››ሲል በመገመት ነበር እርግጠኛ የሆነው…ተከትሏት መሄድ እንደማይችል እርግጠኛ ነው፡፡ማድረግ የሚችለው ከአንድ ሰዓት በኃላ እናቷ ጋር ደውሎ በሰላም መድረሷን መጠየቅ ነው፡፡ቢጃማውን ደረበና ወደውጭ ወጣ፡፡የተበለቀጠውን የውጭ በራፍ መልሶ ዘጋና ወደሳሎን ተመልሶ ቁጭ አለ ፡፡ደግሞ ተነሳና ከመደርደሪያው ውስኪ ጠርሙስ ከብርጭቆ ጋር ይዞ ወደመቀመጫው ተመለሰ፡፡መጀመሪያ የቀዳውን በአንድ ትንፋሽ ነው የጨለጠው፡፡በዚህ ውድቅት ለሊት የልጅነት ጓደኛው የእድሜ ዘመን ፍቅሩና የቤቱ ዋልታ ሚስቱ ጥላው ስለሄደች በእሷ አልተበሳጨም፡፡ ፈፅሞ በእሷ ለመበሳጨት መብት እንደሌለው ያውቃል፡፡ .በራሱም አልተበሳጨም….ግን ደግሞ በእድለ ቢስነቱ በጣም አዝኗል፡፡

‹‹እንዲህ አይነት አፀያፊ ጉድለት በእኔ ላይ እንዴት?እግዚያብሄር በየትኛው ሀጥያቴ ነው የፈረደብኝ?››መልስ የሌለውን ጥያቄ እራሱን ጠየቀ፡፡እና አባቱን አስታወሰነ ምን አልባትም በህይወት ዘመኑ ለአንድ ሺኛ ጊዜ ከአንጀቱ ረገመው፡፡

አባት ልጅን ሲረግም የተለመደ ነው፡፡ወደኃላ ተመልሶ ልጅ አባትን ሲረግም ግን ነገሩ ውስብስብ ነው፡፡
ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡እናቷ ጋር ነው የደወለው፡፡ይጠራል..ግን ደግሞ አይነሳም፡፡‹‹ሳይለንት ላይ አድርገውት ይሆናል፡፡››አለና በቤት ስልክ ደግሞ ሞከረ፡፡፡አሁንም ይጠራል የሚያነሳ የለም..ይበልጥ ግራ ተጋባ፡፡ ….ደግሞ ደወለ…ይግረምህ ብሎ ተዘጋበት፡፡መልሶ ደወለ፡፡አይሰራም፡፡

‹‹በቃ ደርሳለች ማለት ነው፡፡.በዚህ ለሊት ልጄን እንዴት አባረራት ብለው ስለተበሳጩብኝ ነው ስልኬን የማያነሱት….››ሲል ደመደመ፡፡‹‹በቃ ጥዋት በማለዳ እቤታቸው ሄጄ አያታለው..ቢገላምጡኝም እችለዋለሁ››፡፡አለና ብርጭቆ ውስጥ የነበረውን መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠና አዛው የተቀመጠበት ሶፋ ላይ ኩርምትምት ብሎ  ተኛ፡፡እና ማሰብ ጀመረ ፡፡ይህቺን ፍቅሩን ነፍስ ካወቀበት ቀን አንስቶ በልቡ አለች፡፡እሷን ማግባት ይፈልግ የነበረው ገና ማግባት እራሱ ምን መሆኑን ሳያውቅ በፊት ነው፡፡በእሷም ምክንያት መስዋዕትነት መክፈል የጀመረው በጮርቃ እድሜው ጀመሮ ነው፡፡ትዝ ይለዋል…
ሰሎሜ  በ5 ወር ትበልጠዋለች፡፡ያደጉት  በአንድ  ሰፈር ውስጥ በሚገኝ ከመንገድ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ በትይዩ በሚገኙ ቤቶች ውስጥ ነው፡፡ጭቃ ተጋግዘው  አቡኩተዋል…አፈር በአንድ ላይ በትነው ተጫውተዋል፡፡በተቀዳደደ አሮጌ ካልሲ ውስጥ ላስቲክ ጠቅጥቀው  ኳስ በመስራት አብረው ጠልዘዋል፡፡ሌባና ፖሊስ…ለኪ ለኪቾ… መሀረቤን ያያችሁ ..ሁሉንም ሀገርኛ የጫወታ አይነቶችን  ተጫውተው  ተደስተዋል፡፡ከሁሉ በላይ ግን የማይሰለች ጫወታቸው ዕቃ ዕቃ ነበር፡፡የአባትነት ብቃት የእናትነት ኩራት.. የፖሊስነት ስልጣን ወዘተ የሚያጎናፅፋቸው፡፡ በህይወት ባህር ላይ በትንሹ አእምሯችው  የታዘቡትን እና  የኮረጅትን …ወደፊት የሚገጥማቸውን የህይወት ውጣ ውረድ ባዩትና እና በገባቸው  ልክ የሚለማመድበት ድራማ መሳይ የጫወታ አይነት ነው..ዕቃ ዕቃ፡፡
ያው እቃ እቃ ካለ ደግሞ ባልና ሚስት የግድ ይኖራል፡፡ ማንኛውም ህፃን በቅድሚያ ምኞቱ ወንዱ አባቱን መተካት ሴቷ ደግሞ እናቷን መተካት ነው፡፡ወጣት እየሆኑና ለአባትና እናትነት እየቀረብ  ሲሄድ  ግን  ሸክሙ ምን ያህል እንደሚያጎብጥ ስለሚረዱ  በተቃራኒው  ፈሪና ድንጉጥ በመሆን  ስለጋብቻ በተነሳ ቁጥር በርጋጋ ይሆናሉ)
ታዲያ ብዙውን ጊዜ በተለይ ብቻችውን ሲሆኑን ባልና ሚስት ሆነው መተወን የየእለት ድርጊታቸው ነበር፡፡
ትዝ ይለዋል አንድ ቀን አለማየሁና ሁሴን ተነጥለው በቦታው አልነበሩም፡፡እሱና ሰሎሜ ብቻ ነበሩ፡፡ በወቅቱ ሁለቱም የስድስት ወይም የሳባት አመት እንቡጦች ነበሩ፡፡በእለቱ ታዲያ ዘወትር እንደሚያደርጉት እቃ እቃ ለመጫወት ቅራቅንቦ ኮተታችውን  ሰብስበው  ከእነሶሎሜ ቤት ጀርባ   ወደሚገኝ ቦታ ተያይዘው  ሄድ ፣ስብርባሪና የተጣሉ እቃዎችን ደረደሩና ልክ እቤት እንደሆነ ካዘጋጁ በኋላ ያው አላዛር  እንደባልነቱ  ውጭ በመውጣትና ስራ በመስራት ብር ማምጠት ስላለበት ‹‹ ስራ መሄዴ ነው›› በማለት ተሰናብቷት  ይወጣና  ዞር ዞር ብሎ ይመለሳል፡፡

‹‹እባክሽ ደክሞኛል.. እራት አልደረሰም እንዴ?››ልክ እንደአባቱ ጅንን ብሎ ይጠይቃል፡፡

‹‹መጣሁ ደርሷል ቁጭ በል፡፡;››ንግግራቸው ሆነ ድርጊታቸው  ከሁለቱም ቤት   ከእየእለት ክንውን የተቀነጨበ እና የተቀዳ ነበር፡፡ሰሎሜ በቆርኪ ክዳን እጁን እንዲታጠብ አደረገችና በሰባራ ሸክላ ላይ  ቅጠል አንጥፋ በላዩ ላይ በውሀ የተለወሰ ጭቃ አድርጋበት(ወጥ መሆኑ ነው)አቀረበችለት፡

‹‹ብላ››

‹‹ነይ እንጂ እንብላ….ልጆቹንም ጥሪያቸው፡፡››

‹‹ልጆቹ በጊዜ በልተው ነው የተኙት….››

በወቅቱ ተደብቆ የሚሰማቸው  ሰው ቢኖር መቼም ሳይገረም አይቀርም ‹‹የመአድ ስርዓቱ ከተጠናቀቀ በኃላ አላዛር ‹‹ጥዋት ስራ ገቢ ነኝ ..ልተኛ›› አለ፡፡

ትንሿ ሰሎሜም ‹‹ቆይ አልጋውን ላንጥፍ ››ትላለች፡፡

አላዛርም ልክ የገዛ አባቱ እናቱን በሚያናግርበት የድምፅ ቃና  ጠንከር ብሎ‹‹እስከአሁን አልጋው አልተነጠፈም…?በየመንደሩ እየዞርሽ  ቡናሽን ስታንቃርሪ ምን ጊዜ አለሽ?በጅራፍ ጀርባሽን መለጥለጥ ነበር››

ሰሎሜ‹‹እንግዲህ ጭቅጭቅህን  ጀመርክ ››በማለት የለበሰችውን የእናቷን ፎጣ ከተከሻዋ ላይ ገፋ መሬት ላይ  አነጠፈችና ‹‹ያው ተኛ ››ብላው  ፊቱ  ስትገተር ቀድሟት  ተኛና እሷንም ጎትቶ አስተኛት፡፡ከዚያም ትንሹ አላዛር  ስለሚቀጥለው ትዕይነት አሰላሰለ፡፡ እናትና አባቱ ወደሚተኙበት እውነታኛ  አልጋ በምናብ ተጓዘ ..ትዝ አለው፡፡

‹‹እንትን እናድርግ፡፡››የሚል ሀሳብ አቀረበላት፡፡

‹‹ምን?››ግራ በመጋት ጠየቀችው፡፡

‹‹እናትና አባቴ ሲተኙ እንደሚያደርጉት››
👍5210😁6
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

ጥዋት ሶስት ሰዓት አካባቢ ነበር ከክፍሏ ወስደው ለምርመራ አንድ ክፍል ያስገቧት፡፡የሆነ አንድ መርማሪ ፖሊስ ፊት ለፊት ቁጭ ብላ ለመመርመር የምትሄድ ሳይሆን ወደሞት የምትሄድ አይነት መስሎ ነው የተሰማት፡፡ምን አሲረውና ነገሮችን እንዴት እንዴት አጣመው እንደሚጠብቋት ምንም ስላማታውቅ በጣም ነው የፈራችው፡፡በዚህ ሰዓት እንደዛ ያበሳጫት እና በውድቅት ለሊት እቤቷን ለቃ እንድትበር ያደረጋት አላዛር ከጎኗ ቢሆን ተመኘች፡፡እንደምንም ብሎ ከዚህ ነገር እንደሚያወጣትና እንደሚታደጋት እርግጠኛ ነች፡፡ምንም እንኳን የሀዘኗ እና  የብስጭቷ ምንጭ ቢሆንም ከመጠን በላይ እንደሚያፈቅራት እና እሷን ከክፉ ነገር ሁሉ ለመጠበቅ ህይወቱን ጭምር እንደሚሰጥ እርግጠኛ ነች፡፡ለዛም ነው…ጨክና ልትጎዳው የማትደፍረው፤ለዛ ነው ጥላው ለመሄድ አቅም ያጣችው፡፡ከፈለገች  ችግሯን ለህግ አቅርባ ግማሽ ንብረቱን ተካፍላ ልትፈታው እንደምትችል ታውቃለች፡፡ግን እንዴት ብላ…?ይዟት የሄደው ፖሊስ አንድ ክፍል አስገባትና እንድትቀመጥ አዟት ተመልሷ ወጣ፡፡ወዲያው ሽክ ያለ ወታደራዊ ዩኒፎርሙን የለበሰ…ባለማዕረግ መሆኑን ተከሻው ላይ   ባለው የኮከብ ምልክት ማወቅ የሚችል ፖሊስ ገባና   ወደተሸከርካሪ ወንበሩ ሄዷ ተቀመጠ….
ሰሎሜ አንገቷን እንዳቀረቀረች የሚለውን መጠበቅ ጀመረች፡፡

‹‹እሺ ስራችንን እንቀጥል፡፡››ሲል በሻካራ እና በሚያርድ ንግግር ተናገራት፡፡ድምፁ በብርሀን ፍጥነት ነው ተምዘግዝጎ ልቧ ላይ ያረፈው፡፡ፈራ ተባ እያለች ቀና ብላ አየችው፡፡

….አቀርቅሮ እየፃፈ ነው፡፡ድንዝዝ አላት፡፡.ይህ ተአምር ነው፡፡ሄን ሰው ታውቀዋለች፤.ለዛውም ስረ መሰረቱን፤መላ ማንነቱን፤.ውስጡንና ውጩን፤የሚወደውንና የሚጠላውን፤የሚያበሳጨውንና የሚያስቀውን ነገር በጠቅላላ….ሰውነቱ ላይ ያሉትን ጠባሳዎችና የማርያም ስሞሹን በጣቅላላ ቦታቸውን ከነቁጥራቸው ታውቅቸዋለች፡፡

‹‹አሌክሶ….!!››
የሚፅፈውን አቆመና ቀና አለ…በመደነቅ አፍጥጣ የምታየውን ሴት በተራው አፍጥጦ አያት

‹‹ሰሎሜ ነኝ እንዳትይ?››

‹‹አዎ አሌክሶ..ሰሎሜ ነኝ….ወንድሜ ከየት ተገኘህ?››

‹‹በፈጣሪ…ምን አይነት ጉድ ነው..?››መቀመጫውን ለቀቀና ዞሮ ወደእሷ ሄደ፡፡ ተጠመጠመባት…ደረቱ ላይ ለጥፎ ከሰውነቱ አጣብቆ ወዘወዛት፡፡የልቧ ድውድውታ ለልቡ ተሰማው፡፡ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ…ከንፈሯ ከመጠን በላይ ጉንጮቹን አጋሉት….ለአስር ደቂቃ መላቀቅ አልቻሉም፡፤የክብር ወንበሩን ሙሉ በሙሉ ዘንግቶ ከፊት ለፊቷ ቁጭ አለ፡፡
‹‹ወይኔ ሰሎሜ…አንቺ ትዳር እንዲህ ያሳምራል እንዴ?››ሲል እውነታኛ የመደነቅ ስሜቱን ሳይሸሽግ ጠየቃት›፡፡

ቅዝዝ ባለ ድምፅ‹‹እንደዛ ነው ብለህ ነው…?››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹ታዲያ ሌላ ሚስጥር አለው..?ከሆነ እኛም እንጠቀምበት ይነገረን››

‹‹አንተስ ብትሆን ከዚህ በላይ ምን ትሆን..? አምሮብሀል..ቆፍጣናና ወንዳወንድ ሆነሀል..በዛ ላይ ዩኒፎርሙ ያምርብሀል….ባለግርማ ሞገስ አድርጎሀል››አለቸው..

ንግግሯ ከዚህ በፊት ከማንም ሰምቶት ከሚያውቃቸው ሙገሳዎችና አድናቆቶች ሁሉ ወደር የሌላቸውና ልብን የሚያሞቁ ሆነው ነው ያገኘኛቸው፡፡

‹‹ባክሽ አታሳፍሪኝ፡፡››
‹‹ትገርማለህ ግን ..እዚህ ሆነህ ነው ዝም ያልከኝ?ምን አለበት ታዲያ አድራሻዬን ወስደህ ብትደውልልኝ?››

‹‹እኔ እንጃ….እቴቴ አግብታለች ብላ ስትነግረኝ  ደነገጥኩ መሰለኝ አድራሻሽን ሆነ ስልክሽን ልጠይቃት አልቻልኩም፡፡››

‹‹አልቻልኩም ነው ወይስ አልፈለኩም?››

በጀመሩበት ርዕስ እንዲገፋበት ስልፈለገም‹‹አሁንም ነገረኝነትሽ አልተውሽም ማለት ነው?››አላት ፡፡

‹‹አንተ ነገረኛ ነበርኩ እንዴ..?ከአብሮ አደግህ ጋር አትሰደድ የሚባለው እኮ ለዚህ ነው… ለመሆኑ ከተለያየን ስንት አመት ሆነን ማለት ነው?፡፡››

‹‹ስድስት አመት መሰለኝ፡፡››በግምት መለሰላት፡፡

‹‹ግን በዚህ ስድስት አመት ውስጥ አንዴም ልታገኘኝ ሞክረህ አታውቅም፡፡የሚገርመው ደግሞ በየጊዜው ለእናቴ ትደውልላታለህ ….ብር ትልክላታለህ….ብዙ ብዙ ነገር….›› ወደሚሸሸው ርዕስ መልሳ ከተተችው፡፡

‹‹ያው መቼስ እቴቴ ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ለእኔም እናቴ ነች፡፡ወላጆቼን ካጣሁ በኋላ እንደራሷ ልጅ ተቀብላ ትምህርቴን እስክጨርስ  ከአንቺ እኩል አሳድጋኛለች…እና እሷን ችላ ማለት አልችልም››

‹‹እኔንስ ..እሺ ከልጅነታችን ጀምሮ ጓደኛ እንደሆን እርሳው …ግን እህትህ አልሆንኩልህም ነበር?እናቴ ለእኔ ያላትን ፍቅር ቀንሳ ላንተ ስትሰጥ ከመደሰት ውጭ ለምን ብዬ ተቃውሞ አሰምቼ አውቃለሁ….?ለምን እኔን ነጥለህ እረሳኸኝ››

‹‹ባክሽ..ይቅር በይኝ….ጉዳዩ የተወሳሰበ ነው….ቀስ ብዬ አስረዳሻለሁ፡፡›

‹‹ምንም ብታስረዳኝ የሚገባኝ አይመስለኝም፡፡››

‹‹አይ እሱስ ትክክል ነሽ..ያው እንደምታውቂው ትምህርት እንደጨረስን  ወዲያው. ፖሊስነት ተቀጥሬ ማሰልጠኛ ገባሁ…ከዛ ከወጣሁ በኋላም  ለአለፉት ሶስት አመት ድሬ ደዋ ነበር የምሰራው..እዚህ ተቀይሬ ከመጣው ገና ሁለት ወሬ ነው፡፡››

‹‹የፖሊስነት ስልጠናውን ጨርሰህ ድሬ ደዋ እንደተመደብክማ አውቃለሁ….ብዙ ጊዜ እንደውም ድሬ ድረስ ሄጄ ምን እንዳስቀየምኩት ልጠይቀው ብዬ አስብና ደግሞ የማላውቀው ሀገር ሄጄ ባላገኘውስ?አግኝቼው የት አውቅሻለሁ ብሎ ፊት ቢነሳኝስ? ብዬ ብዙ ብዙ ነገር በማሰብ ፈርቼ ተወዋለው፡፡››

አዎ ሰሎሜ እንዳለችው ከቡዙ አመት መጠፋፋት በኃላ ነው  የተገናኙት፡፡ከሰፈር ከለቀቀ  በኃላ አግኝቷትም ሆነ አይቷት አያውቅም፡፡ከሰፈርም ከቤትም ርቆ  የጠፋበት ምክንያት ረጅም ነው፡፡ ግን ድንገት ፖሊስ ቤት ተቀጥሮ  ለስልጠና  ገባ….በምክትል ኢኒስፔክተርነት  ማዕረግ ተመርቆ  መርማሪ ፖሊስ ሆኖ  ከአዲስ አበባ ብዙ ኪሎ ሜትር ርቆ ድሬ ደዋ በመመደብ ስራ ጀመረ፡፡ስለእሱ ይሄንን ታሪክ ብቻ ነው የምታውቀው፡፡በዚህ  የጊዜ ክፍተት መሀከል  ምን እየሰራና በእንዴት አይነት የህይወት መስመር ሲኖር እንደነበረ አታውቅም፡፡
በእሱ በኩል ግን ስለእሷ ዘወትር ማሰቡንና መተከዙን አላቆመም ነበር፡፡የዛሬ አመት አካባቢ እንደምንም ጨከን ብሎ እናቷን ለመጠየቅ  እቤታቸው ሄዶ ነበር፡፡እናቷን ቢያገኝም እሷ ግን አልነበረችም፡፡ከእናቷ ከእቴቴ ጋር ብዙ ካወጋና ከተጫወተ በኃላ በወሬ በወሬ ስለእሷ ጠየቀ፡፡የገዛ ጓደኛውን   ካገባች አመት እንዳለፋት ተነገረው፡፡በፊትም የሚጠረጥረው እና የሚጠብቀው  ነገር ስለነበር ብዙም አላስገረመውም …የት ነው ያገባችው…?ስልኳን ስጡኝ ወይንም ጥሯትና ላግኛት አላለም…እናትዬውም እንደዛ አይነት ሀሳብ አላቀረቡለትም፡፡ በዛም ምክንያት….በቃ የልቡን በልቡ ይዞ ምንም የተለየ ዓላማ  እንደሌለው ሰው ሌላ ጊዜ በድጋሚ መጥቶ እንደሚጠይቃት ለእናቷ ቃል በመግባት  ሹልክ ብሎ ወጣና ወደ ምድብ ስራው ተመለሰ፡፡
እንግዲህ ከአመት ቆይታ በኃላ መሆኑ ነው በዝውውር ወደ አዲስ አበባ የተመደበው ፡፡አዲስአበባ ከገባ ከሁለት  ወር  በኋላ ድንገት ባልገመተው  ተአምራዊ መንገድ እስረኛው ሆና አገኛት፡፡

ከሀሳብ እንደመባነን አለና  ‹‹ ያገባሽው አላዛርን እንዳደሆነ ሰምቼለሁ፡፡.››አላት

‹‹አድራሻህን ባታጠፋ ኖሮ የመጀመሪያ ሚዜው አንተ ነበርክ…የሚገርመው ደግሞ  ከመጣህ በኋላ እንኳን ለምን ልታገኘን እንዳልፈለክ ነው..?እኔም ሆንኩ  እሱ ጓደኞችህ ነበርን….››ለአመታት ሲከነክናት እና አእምሮዋን ሲበላት የነበረውን ጉዳይ ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቀችው፡፡
👍5514
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
====================

ኩማንደር አለማየሁ የአላዛርን ስልክ ተቀብሎ እሷን ወደማረፊያ ክፍል ከላካት በኃላ ጥልቅ ትዝታ ውስጥ ነው የተዘፈቀው፡፡ከእሷ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ጋር የነበረው የልጅነት እና የወጣትነት ትዝታ በብዙ ውጣ ውረዶች የተሞላ፤ደስታንም ሀዘንንም በውስጡ ያጨቀ ነበር፡፡አዎ አለማየሁ እንደሚያስታውሰው ሰሎሜ ለሶስቱ ወንዶች ልክ እንደጨረቃቸው ነበረች፡፡እነሱ ደግሞ በዙሪያዋ እየተሸከረከሩ ውበቷን የሚያጎሉላት ፍንጥርጣሪ ከዋክብቶች፡፡እናም ሰሎሜ ሶስቱንም ጓደኞቾን የምትወድበት የራሷ የሆነ የተለየ ምክንያት እንደነበራት ይገምታል፡፡ለምሳሌ አላዛርን በውበቱና በልስልስ ባህሪው…እሱን በኮሚክነቱና በድፍረቱ ሁሴንን በጉብዝናው እና በብልሀቱ ፡፡

አሌክስ ፤አላዛር እና ሁሴን ከልጅነታቸው ጀምሮ በእሷ ምክንያት ችግር ውስጥ እንደገቡ ነበር፡፡አረ ከእነሱም አልፎ ወላጆቻቸውን ጨምሮ በተደጋጋሚ ጊዜ ችግር ውስጥ ገብተው እንደሚያውቀው ያስታውሳል፡፡አንድ ጊዜ የዘጠኝ አመት ገዳማ ልጆችና የሁለተኛ ክፍል ተማሪ እንደሉ ነበር፡፡ጊዜው የበልግ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ስለሆነ መስኩ ጠቅላላ ውሀ ባቆሩ መሬቶችና ጭቃ ባላቆጡ መንገዶች የተሞላ ነበር፡፡ታዲያ የትምህርት ቤት የእረፍት ጊዜ ደውል ከተደወለ በኋላ ሰሎሜ ከእነሱ ተነጥላ ሳያዮት ሾልካ ትሔዳች፡፡እደዛ ያደረገችው ሽንቷ ወጥሯት ስለነበረ ወደ ሽንት ቤት ነበር፡፡ስትመለስ ግን ጎረምሳ ጎረምሳ ከሚጫወቱ የስድስተኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች እጅ ትወድቃለች፡፡ሴቶቹ እድሜያቸው አስራዎቹ ቤት የገባና በቁጥርም ሶስት ነበሩ፡፡ዙሪያዋን ከበዋት ጆሮዋን እየቆነጠጡ ውሀ ያቆረ ሜዳ ውስጥ በባዶ እግሯቾ ገብታ እያንቦረጨቀች መዝሙር እንድትዘምርላቸው አስገደዷት፡፡
እንዳሏት እየዘለለች ስትዘምር በጭቃ የላቆጠው እና ውሀ ያቆረው መሬት እየተፈናጠረ የለበሰችውን ሙሉ ነጭ ቀሚስ እንዳልነበረ አበላሸባት…፡፡ከዛም አልፏ ፊቷና ጸጉሯ ላይ ሳይቀር ተፈነጣትጥሮባት.. በጭቃ የተሰራች አሻንጉሊት አስመሰሏት ነበር …በንዴትና በፍርሀት እንባዋ እየረገፈ ያሏትን ስታደርግ ቆየች..ልጆቹ የትምህርት ቤት የእርፍት ጊዜ ማለቁን የሚያበስር ደውል ሲደወል ነበር  ጥለዋት የሄዱት …ከዛ ምን ታድርግ ተማሪዎች ሁሉ ወደክፍል ከገቡ በኃላ እያለቀሰች ሄዳ ክፍላቸው ጀርባ  ባለ መቀመጫ ተቀመጠች፡፡እንደዛ ጨቅይታና ልብሷ ጠቅላላ ተበላሽቶ እንዴት ወደክፍል ትግባ..?አስተማሪውስ ምን ይላታል?፡፡ ወደቤት እንዳትሄድ ደግሞ ቦርሳዋ ክፍል ውስጥ ነበር፡፡
በዚያን ቀን እሱን ጨምሮ  ሁለቱ  ጓደኞቾ እረፍትን ጨምሮ  ክፍል ውስጥ ባለመኖሯ እንዴት ተደናግጠው እንደነበረ ትዝ ይለዋል፡፡‹‹የት ሄደች?››የሶስቱም ጥያቄ ነበር፡፡የሚቀርቧትን ሴቶች ሁሉ ቢጠይቁ አይተናታል የሚል ሰው አላገኙም፡፡…አስተማሪ መጥቶ ክፍለጊዜው ከመጀመሩ በፊት እሷን ፍለጋ ክፍሉን ለቀው በመውጣት የትምህርት ቤቱን አጥር ጊቢ በሳምሶማ ሩጫ ማሳስ ጀመሩ፡፡በስተመጨረሻ ከክፍላቸው ጀርባ   እንዳልሆነች  ሆና አገኞት፡፡….ሶስቱም ነበር አብረዋት ያለቀሱት፡፡በዛን ወቅት ሲያያት የተሰማውን ድንጋጤና ንዴት ትዝ አለውና ፈገግ አለ ና ወደ ትዝታው ተመለሰ፡፡
በወቅቱ ወደ ቧንቧ ወሰዷት ..ፊቷንና፤ ፀጉሯን እና እግሮቾንም  በማጣብ  የአንዳቸውን ጃኬት አለበሷት…ሶስቱም ወደክፍላቸው ገብተው የእሷን እና የራሳቸውን ቦርሳ ጭምር በመያዝ ወጡና እሷን መሀከል አድርገው በማፅናናት  ወደቤት ነበር ይዘዋት የሄድት፡፡
ከዛ ምሽቱን ሙሉ በወላጆቻቸው ተገደው ወደቤት  እስኪገቡ ድረስ ‹‹እንዴት አድርገን ነው የእኛን ንግስት ያስለቀሷትን ሴቶች በእጥፍ የምናስለቅሳቸው?›› ብለው ሲማከሩና እቅዶች ሲነድፉ አመሹ ፡፡

የእነሱን ሰሎሜን ያቆሸሾትና  ያስለቀሷት ልጆቹ ሰሚራ፤ ሳራና፤ ሰላም ይባለሉ እንደነበር አሁን ድረስ ስማቸውን ከነመልካቸው ያስታውሰዋል፡፡

‹‹እኛ ሶስት ነን አይደል?››ሲል ነበር አለማየሁ ጓደኞቹን የጠየቀው፡፡

‹‹አዎ››መለሱለት፡፡

‹‹እሺ ሰሎሜን ያስለቀሷትም  ሴቶች ሶስት ናቸው››

‹‹አዎ ትክክል ሶስት ትላልቅ ሴቶች ናቸው››መለሱለት፡፡

‹‹ጥሩ..አንዳ እንድ እንከፋፈላቸዋለን››አለ አለማየሁ፡፡
አላዛር ተቃወመ‹‹አይሆንም እኔ አልስማማም››

‹‹ለምንድነው ማትስማማው?››

‹‹እኔ ከሰሎሜ ውጭ ሌላ ሴት አልፈልግም…..የእኔን ድርሻም ከፈለጋችሁ ተካፈሉና ውሰዷት››ሲል ነበር አቋሙን ያሳወቀው፡፡

‹‹አንተ ጀዝባ የሆንክ ልጅ …የምንካፈላቸው እኮ የእኛ  ልናደርጋቸው አይደለም.. ልናሰቃያቸውና ልናስለቅሳቸው ነው…ለሰሎሜ  ልንበቀልላት ነው፡፡››

ሁሴን ‹‹ገባኝ..ለመበቀል ግን ለምን መከፋፈል አስፈለገ?››ሲል ጠየቀ

‹‹‹ለእያንዳንዳችን የደረሰችንን ሴት የሆነ ዘዴ ፈልገን በተማሪ ፊት እንድታፍር ፤ እንድታለቅስና እንድትፀፀት እናደርጋታላን፡፡ታዲያ ከሶስታችን በጣም በአስቂኝና አስደናቂ መንገድ ተጠቅሞ ማስለቀስ የቻላ የበለጠ ሰሎሜን ያፈቅራታል ማለት ነው፡፡››እንደዚህ አይነት ሀሳብና እቅድ በዛ እድሜ እንዴት ማመንጨት እንደቻለ ዛሬም ሲያስበው በራሱ ይገረማል፡፡

ሁሴን‹‹ተስማምቼለው…እኔ ከሁለታችሁም በላይ ጂኒዬስ ስለሆኑክ ካሁኑ መሸነፋችሁን እመኑ››ሲል ጎረረ፡፡

‹‹ሞኞ በትምህርት ጎበዝ ሆንክ ማለት በእንደዚህ አይነት ነገርም ጎበዝ ነህ ማለት አይደለም?››ሲል ነበር  የመለሰለት፡፡
በክርክራቸው የተሰላቸው አላዘር‹‹እባካችሁ አትጨቃጨቁብኝ. .አሁን እንዴት አድርገን ነው ሴቶቹን ምንካፈላቸው››ሲል ግራ የገባውን ነገር ጠየቀ፡፡

‹‹እጣ እንጥላለን›› ብለው ተስማሙና በዛው መሰረት ተከፋፈሉ…ለሁሉም የአንድ ሰምንት ጊዜ ተሰጣቸው፡፡

ይሄ ውይይት በተደረገ በአራተኛው ቀን ሰላም በምትባለው ልጅ ላይ የመጀመሪያው ጥቃት ደረሰባት፡፡ሁሴን ለመጀመሪያ ሁለት ቀናት ልጆቹን ስር ስራቸው እየሄደ የሆነ ቦታ ተቀምጠው ሲያወሩ በሆነ ከለላ እየተደበቀ የሚያወሩትን በመስማት መረጃ ሰበሰበ፡፡በሶስተኛው ቀን እንደምንም ወደስድስተኛ ክፍል ሾልኮ ገባና ከሰላም ቦርሳ ውስጥ አንድ ደብተር በመስረቅ ወደቤቱ ይዞ ሄዳ፡፡ከዛ ለሁለት ሰዓት ያህል  ፊደል   አጣጣሏንና የእጅ ፅሁፏን ሲለማመድ ቆየ..ከዛ እርግጠኛ ሲሆን ያሰበውን ወደማድረግ ተሸጋገረ፡፡

በእሷ ስም ለአንዱ የክፍሏ ልጅ ደብዳቤ ፃፈ፡፡

ውድ ወንድይራድ…..እንዴት ነህ..?እኔ የአንተ ፅጌረዳ ከአንተ ሀሳብና ናፍቆት በስተቀር ሰላም ነኝ፡፡ይሄንን ደብዳቤ የፃፍኩልህ ምን ያህል እንደማፈቅርህ ፊት ለፊትህ ቆሜ  ልነግርህ መድፈር ስላቃተኝ ነው፡፡ታውቃለህ ደግሞ እነዛ አስጠሊታ ሁለት ጓደኞቼ ሁል ግዜ እንደተጣበቁብኝ ነው…ሲያስጠሉ፡፡ውዴ ከአሁን በኋላ አንተን ካገኘሁ እነሱ አያስፈልጉኝም…ድሮውም እንደመደበሪያ ነበር የምጠቀምባቸው፡፡ውዴ በእርግጠኝነት አንተም እንደምታፈቅረኝ አውቃለሁ…እንደእኔ አይነት ቆንጆ እንዴት ላታፈቅር ትችላለህ?፡፡ለማንኛውም መልስህን በጉጉት እጠብቃለው፡፡ደግሞ የመልሱን ደብዳቤ ስትሰጠኝ አነዛ ቅናታም  ጓደኞቼ እንዳያዩህ ተጠንቀቅ፡፡
👍656😁4👏1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አላዛር ቀኑን ሙሉ ሚስቱን ፍለጋ ሲባዝን ውሎ ሰባት ሰዓት አካባቢ ስልክ ተደወለለት..ቁጥሩን አያውቀውም…ግን ደግሞ ሰሎሜን ካገኛችሁ ደውሉልኝ ብሎ አደራ በማለት ስልኩን ለብዙ ሰው ስለሰጠ  በትልቅ ተስፋና ጉጉት ነበር በፍጥነት ያነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አላዛር ነህ?››ጎርናና ሻካራ የወንድ ድምፅ፡፡

‹‹አዎ ነኝ ፡፡ማን ልበል?››

‹‹ይሄንን ድምፅ አታውቀም?››

ተበሳጨ…ዛሬ የማንንም ሰው ድምፅ ለማወቅ ለአእምሮው የቤት ስራ የሚሰጥበት ሁኔታ ላይ አይደለም፡፡አንኳን የማያውቀውን ሰው ድምፅ የራሱንም ማንነት ለመርሳት ትንሽ ነው የቀረው‹‹ይቅርታ ማን ልበል..?እየነዳሁ ነው››አለ ኮስተር ብሎ፡፡

‹‹አሌክስ  ነኝ››

በታላቅ ድንጋጤ መኪናውን ወደ ዳር አወጣና አቆማት…..

‹‹አሌክስ አልኬስ…አሌክሶ የእኛ  እንዳትሆን?››

‹‹አዎ አሌክስ ነኝ…አሌክስ የእናንተው…የልጅነት እናም የጉርምስና ጊዜ ጓደኛችሁ››

‹‹ይገርማል…ፈፅሞ ያልጠበቅኩት ጉዳይ ነው…ለመሆኑ አለህ…?

ድሬደዋ እንዳለህ ሰምቼ ነበር..ግን ስልክህን ማግኘት ስላልቻልኩ ልደውልልህ አልቻልኩም፡፡››

‹‹አዎ አሁን ግን አዲስ አበባ ገብቼለሁ››

‹‹በጣም ይገርማል…አሌክሶ አሁን የሆነች ችግር ገጥሞኝ እሷን ለመፍታት እየተሯሯጥኩ ነው…..ይህ ያንተ ቁጥር ከሆነ ቆይቼ ልደውልልህ?››

‹‹ቆይ..እኔም ስለችግርህ ለማውራት ነው የደወልኩልህ››

አላዛር ድንግርግር አለው‹‹አልገባኝም?››

‹‹ችግርህ ስለሰሎሜ አይደለች..ማለቴ እሷን እየፈለክ አይደለህ?›››

የሚስቱን ስም ሲጠራ ይበልጥ ደነገጠ‹‹አዎ ግን እንዴት አወቅክ..ነው ወይስ እቴቴ ደውላልህ ነው?››

‹‹አይ…ከቴቴ ጋር አልተደዋወልንም.ሰሎሜ እኔ ጋር ነች››

አላዛር ይሄንን አረፍተ ነገር ሲሰማ ጭንቅላቱ ላይ ስል ሰይፍ አርፎ ለሁለት የሰነጠቀው ነው የመሰለው..በሰከንዶች ሽርፍራፊ ብዙ ብዙ ነገር ነው ያሰበው፡፡‹‹እንዴት እንዴት ብለው ተገናኙ?ከዚህ በፊትም በድብቅ ይገናኙ ነበር ማለት ነው…?እሱ እጅ ከገባች እንዴት ነው መልሼ የራሴ ላደርጋት የምችለው..?ነው ወይስ እስከወዲያኛው እያጣኋት ይሆን?፡፡››ሲል የስጋት ሀሳብ አሰበ፡፡
አለማየሁ ለረጅም ደቂቃዎች መልስ ሳይሰጠው ዝም ስላለበት ግራ ተጋብቶ ‹‹አላዛር…ምነው ዝም አልክ ..?ሰምተኸኛል?››

‹‹አዎ ሰምቼሀለው…ግን ምንም አልገባኝም…እንዴት ልታገኛት ቻልክ?››

‹‹እሱ ታሪኩ  ረጅም ነው ..ናና እንነጋገራለን››

‹‹የት ነው የምመጣው?››
‹‹ፓሊስ ጣቢያ..ማለቴ…›› ብሎ ትክክለኛ አድራሻውን ነገረው፡፡

‹‹ፖሊስ ጣቢያ ምን ትሰራለች?››

‹‹አንተን ልትከስ መጥታ ልበልህ..?ለማንኛውም  እየጠበቅኩህ ነው.. ፈጠን ብለህ ና››ብሎት ስልኩን ዘጋበት፡፡

አላዛር ድንዝዝ ነው ያለው…መኪናውና አንቀሳቅሶ በፍጥነት መሄድ እንዳለበት እንኳን ማስታወስ አላቻለም….‹‹የምን ክስ …?መቼስ ምንም አይን አውጣ ብትሆን ባሌ ከእኔ ጋር ግንኙነት አላደርግም አለኝ ›ብላ አትከሰኝም…..እንደዛማ አታደርግም…ደግሞ ካልጠፋ ቦታ ስንት ክፍለከተማ አቋርጣ እንዴት እዛ ድረስ …?እስከዛሬ እያወቀች እንዴት መቀየሩን ሳትነግረኝ ..?እንዲሁ እንደተብከነከነ እና የተንዛዙ ጥያቄዎች አእምሮውን አንዳጨናነቀ የተባለው ፓሊስ ጣቢያ ደረሰና መኪናውን  ፓርክ  አድርጎ ወደፖሊስ ጣቢያው ተጠጋ ፡፡በየት እንደሚገባ ግራ ተጋባ በራፍ እንዳለ ሆኖ በሆነ ሜትር ጠጋ ብሎ ደግሞ 5 ሜትር የሚሆን የተደርመሰ አጥር  በግማሽ ቀልቡ እያየ ወደውስጥ ዘለቀና ለአለማየሁ ደወለለት፡፡

የቢሮውን ቁጥር ሲነግረው  ፈራ ተባ እያለ አንኳኳና ወደውስጥ ገባ…ከስድስት አመት በፊት የተለየው የልጅነት ጓደኛውና አብሮ አደጉ ፊቱ በፂም ተሸፍኗ ትልቅ ሰው መስሎ እና የደንብ ልብሱን ለብሶ ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ከእሱ ውጭ ክፉሉ ውስጥ ማንም የለም.ሰሎሜንም አገኛታለሁ ብሎ ጠብቆ ነበር…ግን እየታየችው አይደለም፡፡‹‹የት ወስዶ አስቀምጧት ነው?››በውስጡ አጉረመረመ፡፡

እንዴት ብሎ ሰላም እንደሚለው ግራ ገባው…‹‹ጓደኛዬን ለማግኘት ነው የመጣሁት  ወይስ ተከስሼ ቃል ልሰጥ….?››ሲል እራሱን ጠየቀና ተደነጋሮት በራፍ ላይ ፈዞ ቆመ፡፡ አለማየሁ መቀመጫውን ለቆ መጣና ተጠመጠመበት…ከፍራቻው ጋር ሳይፋታ እሱም አቀፈውና የሞቀ ሳላምታ ተለዋወጡ ፡፡ይዞት ወደ ውስጥ ዘለቀና የሚቀመጥበት መቀመጫ ሰጠው..እሱም ከፊቱ ተቀመጠ….፡፡
አለማየሁ ደቂቃዎችን  ወሰደና አላዛርን በትኩረት አየው፡፡አለባበሱ  እንዳአንባሳደሮች ሽክ ያለ ነው..ደግሞ ልክ እንደድሮው …እንደውም ከዛም በላቀ ደረጃ ልቅም ያለቆንጆ ሆኗል፡፡ወንድን ልጅ  ቆንጆ ነው ብሎ  አያውቅም ፡፡ጓደኛውን የአላዛርን ቁንጅና ግን ፍጥጥ ያለ ስለሆነ ችላ ተብሎ የሚታለፍ አይነት አይደለም፡፡፡

ለንግግሩ አላዛር ቅድሚያውን ወሰደ‹‹በቅርብ ነው እዚህ የገባሀኸው?››
‹‹አዎ ገና ሁለት  ወሬ ነው››

‹‹ሁለት  ወር ሙሉ ስትቀመጥ እንዴት አስቻለህ? ነው ወይስ እኔ ብቻ ነኝ ያላገኘሁህ›?›

‹‹አይ ..እዚህ የተመደብኩት በሀላፊነት ቦታ ስለሆነ ነገሮችን እስክለማመዳቸውና እስኪዋሀዱኝ ወዲህ ወዲያ ማለት አልቻልኩም ነበር…መቼ እና እንዴት ላግኛቸው እያልኩ እያሰብኩ ሳለ ነው ድንገት ዛሬ ጥዋት ሰሎሜን ያገኘኋት፡፡››

‹‹ጥዋት?››

‹‹አዎ ጥዋት››

አላዛር ረጅም ትንፋሽ ወደ ውስጡ ሳበና እፎይ አለ…‹‹ለሊት ቀጥታ ከቤት እንደወጣች ወደእሱ ቤት ሄዳ ቢሆንስ ?››የሚል ጥርጣሬ ነበረው…እንደዛ ከሆነ ደግሞ ብዙ የሚፈጠሩና ወደኃላ ሊመለሱ የማይችሉ ችግሮች ይኖሩ እንደነበር ሲያሰላስል ስለቆየ  ከአለማየሁ የሰማው መልስ በጣም ነው ያስደሰተው፡፡

‹‹ታዲያ አሁን የታለች?››

‹‹እስር ላይ ነች››

‹‹ምን?››የሚሰማውን አምኖ ለመቀበል ተቸገረ፡፡

የተሳሳተ ቃል የሰማ ነው የመሰለው….‹‹እሷ እስር ላይ !!እንዴት ተብሎ?››

‹‹ስትገባ ያየሀው መሰለኝ..አጥራችንን ለሊት የናደችው እሷ ነች››

‹‹ተረፈች ታዲያ ..?ተጎድታለች..?ሀኪም ቤት ወሰዳችሃት?››

‹‹አታስብ ..ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባትም….››መኪናዋ ብቻ ትንሽ ተጫራለች…መንገድ ስለዘጋብን አንስተን ወደጎሮ አቁመናታል፡፡››

ከድንጋጤው ትንሽ ተንፈስ ብሎ‹‹መኪናዋ የራሷ ጉዳይ .እሷ ብቻ  እንኳን ተረፈች››አለ ፡፡

‹‹አዎ..ተርፋለች››
ልመና ሳይሆን ትዕዛዝ በመሰለ ቃላት‹‹ላያት እፈልጋለሁ..››ሲል ተናገረ፡፡

‹‹ደህና ነች አልኩህ እኮ››
‹‹በፈጣሪ ካላየኋት አልረጋጋም…..በጓደኝነታችን..እባክህ?››

አለማየሁ ከዚህ በላይ ሊጨክንበት አልፈለገም፡፡‹‹አረ ችግር የለውም… እዚሁ አስመጣታለሁ…››አለና ከመቀመጫው ሳይነሳ  ጠረጴዛው ላይ መጥሪያውን ተጫነው… ወዲያው አንድ ፖሊስ መጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጥቶት የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ሆኖ ይጠብቅ ጀመረ
ኩማደር አለማሁም‹‹እስረኛ ሰሎሜ ግርማን ይዘህልኝ ና››ብሎ ትዕዛዙን አስተላለፈ፡፡

ፓሊሱ ወጥቶ ሄደ‹‹እስረኛ ሰሎሜ ግርማ  ››ብሎ ሲናገር አላዛር ስቅጥጥ አለው፡፡

‹‹ኩማንደር  ቆይ ግን አጥሩን እኔ በሁለት ቀን ውስጥ ሙሉውን ከበፊቱ በበለጠ አሳምሬ እስገናባዋለሁ….አስፈላጊም ከሆነም  አሁኑኑ ደስ ያላችሁን ብር አስይዛለው..እሷ ማሰር እኮ አስፈላጊ አይደለም….››
👍5914👏1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

‹‹እናንተ ደግሞ ጅል አትሁኑ…ሰሎሜ ሰው ነች…ሰው ስለሆነች ታማለች…የተመመ ሰው ደግሞ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ህክምና ካላገኘ ይሞታል….ይሄ ሀቅ ለሌላ ሰው ከሰራ  ለሰሎሜም ይሰራል፡፡››ሁሴን ነበር የተናገረው፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ሁሉን ነገር አውቃለሁ የምትለው ነገር አለ››አለማየሁ በብስጭት መለሰለት፡፡

‹‹ትክክል ነኛ..ከእናንተ በተሻለ ብዙ ነገር አውቃለሁ…ይልቅስ ሰሎሜ ቀዶ-ጥገናዋን እንድታደርግ እኛ ምን ማድረግ አለብን ?የሚለውን መነጋገር ነው የሚጠቅመን፡፡››

‹‹ትክክል ነህ..የመጣልህ ሀሳብ አለ?››አለማየሁ ነው በጉጉት የጠየቀው፡፡

የቀዶ ጥገና እንዲደረግላት የተወሰነበትንና  እና የገንዘቡን መጠን የሚገልፅ ደብዳቤ ማግኘት አለብን›› ሁሴን ሀሳብ አቀረበ፡፡

‹‹አግኝተንስ ምን እናደርገዋለን?››አላዛር ጠየቀ፡፡

‹‹በሰፈር ጠቅላላ ዞረን እንለምናለን…በትምህርት ቤታችንም እንለምናለን፡፡››

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን ያንን ሁሉ ብር የምናገኝ ይመስልሀል?››በጥርጣሬ ጠየቁት፡፡

‹‹እስከቻልነው እንሞክራለን…ካልሞላልን ደግሞ ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን..አሁን ደብዳቤውን እንዴት እንደምናገኝ ማሰብ አለብን››

‹‹ለምን ሀኪም ቤት ሄደን ሰሎሜን የሚያክማትን ሀኪም አንጠይቀውም…››አላዛር ነው ሀሳቡን ያቀረበው፡፡

‹‹አይ አንተ ጅል የሆንክ ልጅ..አሁን ሄደን ብንጠይቀው ለ13 አመት ልጇች እንዲህ አይነት መረጃ ሚሰጠን ይመስልሀል?››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ስለገባኝ እኮ ነው፡፡››

‹‹ለምን እቴቴን አንጠይቃትም..እሷ ደብዳቤውን ልታስወጣልን ትችላለች››

‹‹አሌክስ ትክክል ነው..ጊዜ ሳናባክን አቴቴን እናናግራት››ሁሴን በአለማየሁ ሀሳብ ወዲያው ተስማማ፡፡

‹‹ግን እኮ እሷ ሆስፒታል ነው ያለችው››

‹‹እኮ እንሂዳ››
ተስማሙና ቀጥታ ሰሎሜ ወደተኛችበት ሆስፒታል ነበር የሄዱት፡፡ሰሎሜ የተኛችበት ክፍል ገብተው ያለችበትን ሁኔታ ካዩ በኃላ‹‹እቴቴ አንዴ ውጭ ልናናግርሽ ፈልገን ነበር፡፡››ሲሉ ጠየቋት፡፡

‹‹ምነው በሰላም?››

‹‹በሰላም ነው..ሰሎሜ ስለተኛች እዚህ ስናወራ እንዳንቀሰቅሳት ነው››አለ ሁሴን፡፡

‹‹እሺ እንዳላችሁ ››በማለት ተስማምታ  ተከትላቸው ወጣች፡፡እዛው ሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ካለ አግዳሚ ወንበር ላይ በመደዳ ተቀመጡ፡፡

ለነገሩ ብዙም ትኩረት ባለመስጠት‹‹እሺ ልጆች ..ለምንድነበር የፈለጋችሁኝ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡

‹‹ሰሎሜ እንዴት ነች?››

ቀዝቀዝ ባለ ስሜት ‹‹ደህና ነች..ምንም አትል››ስትል መለሰችላቸው፡፡

‹‹ማለት ስለቀዶ ጥገናው ነው የምናወራሽ…?እንዴት ነው የሚሆነው…?ያን ያህል ብር ከየት ታመጪያለሽ?››

‹‹ልጇች አትጨነቁ..ከየትም ብዬ ከየትም ይሄንን ብር አግኝቼ ብቸኛ ልጄን ማሳከም አለብኝ….አታስቡ ጓደኛችሁን እንድትድን የተቻለኝን አደርጋለሁ፡፡››ስትል እንባ እየተናነቃት መለሰችላቸው፡፡በእውነት ብሩን ከየት እንደምታመጣው…የትኞቹን ዘመዶቾን እንደምታስቸግር…የትኛውን ንብረቷን ብትሸጥ የተጠየቀችውን ብር ማግኘት እንደምትችል  ምንም አይነት ሀሳብም ሆነ ተስፋ  አልነበራት፡፡ግን ለልጆቹ ይሄንን ምን ብላ በምን አይነት ቋንቋ ልታስረዳቸው ትችላለች፡፡ለዛ ነው በደፈናው ልታፅናናቸው የወሰነችው፡፡

‹‹እቴቴ…ሰሎሜን ለማዳን የተቻለንን ብቻ ሳይሆን ከምንችለው በላይ ነው ማድረግ ያለብን…ሶስታችንም ልክ እንደአንቺ እሷን ለማጣት ዝግጁ አይደለንም…እና የሆነ ነገር ለማድረግ አስበናል፡››ሁሴን ነበር ተናጋሪው፡፡

አቴቴ ግራ በመጋባት‹‹ምን ማለት ነው …?እናንተ ደግሞ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?››

‹‹ከሀኪም ቤቱ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት መወሰኑን እና  ለዛም የሚያስፈልገውን ብር የሚገልጽ ደብዳቤ እንዲሰጡሽ ጠይቂያቸው››

‹‹ማለት ..ደብዳቤው ምን ያደርግልኛል?››

‹‹አይ ላንቺ አይደለም..ለእኛ ያስፈልገናል››

‹‹ለምን .?.ምን ልታደርጉበት?››
ትምህርት ቤታቸውን ሆነ በሰፈራችን እርዳታ እየዞርን እንጠይቃለን..ከየአንዳንዱ ሰው አንድ  ብርም ሆነ አስር ብር እየዞርን እንሰበስባለን…ለዛ ግን ሰው እንዲያምነን እና ስራችን ቀላል እንዲሆንልን መረጃው ያስፈልገናል፡፡››

በወቅቱ የሰሎሜ እናት ስሜቷን መቆጣጠር አልቻለችም ነበር…ሁሉንም አንድ ላይ አቅፋ ጉያዋ ውስጥ በመወሸቅ ስቅስቅ ብላ ነበር ማልቀስ የጀመረች፡፡

አለማየሁ ጉንጮ ላይ ያለውን እንባ በመዳፎቹ እየጠረገላት ‹‹እቴቴ አይዞሽ.. አታልቅሺ …ሰሎሜን እናድናታለን…እሷ የእኛ ንግስት ነች..ንግስታችንን ማጣት አንፈልግም፡፡››ሲል አፅናናት ፡፡

‹‹ያስለቀሰኝ  ሀዘን አይደለም ደስታ ነው፡፡ልጄን ወንድም ወይም እህት ሳልወልድላት ብቸኛ አደረኳት ብዬ ብዙ ጊዜ አዝኜና አልቅሼ ነበር፡፡አሁን ግን እንደተሳሳትኩ በደንብ ነው የገባኝ፡፡ወንድሞች ቢኖሯትም እናንተ ከምትወዷትና ከምትንከባከቧት በላይ ሊንከባከቧት አይችሉም ነበር፡፡
በጣም ነው የማመሰግናችሁ፡፡ እናንተ ስላላችኋት ልጄ በጣም እድለኛ ነች››

‹‹አይ እቴቴ….እሷ ስላለችን እኛ ነን እድለኞች…አሁን መላቀሱ አይጠቅመንም…ሂጂና ዶክተሮቹን ጠይቀሽ ደብዳቤውን አግኚልን፡፡››

‹‹እሺ በቃ ውስጥ ገብታችሁ ጠብቁኝ …መጣሁ››ብላ በነጠላዋ ጫፍ በጉንጮቾ የረገፈ እንባዋን እየጠረገች ወደአስተዳደር ቢሮ ሄደች፡፡

ደብዳቤውን በእጃቸው ካስገቡ በኋላ ሰፈራቸው ወደሚገኝ ባነር መታሚያ ቤት ነበር  የሄድት፡፡ ደብዳቤውን አሳይተውና ሁኔታውን አስረድተው…የሰሎሜ አሳዛኝ ፎቶ የሚታይበትንና ያለችበትን ሁኔታ እጥር ምጥን ባለ ግልፅ ዓረፍተ ነገር አፅፈው ሁለት ሜትር በአንድ ሜትር በሆነ ባነር አሳተሙ፡፡ ..በማግስቱ ወደትምህርት ቤት ይዘው ሄዱ፡፡ቀጥታ ወደ ዳሪክተሩ ቢሮ ሄዱና ሁኔታውን አስረዱት….፡፡.ተማሪዎች በተሰለፉበት ባነሩ ለሁሉም እንዲታይ ተዘርግቶ ሰሎሜ ያለችበትን ሁኔታና የሚያስፈልጋትን ነገር ለሁለቱም ፈረቃ ተማሪዎች ተነገረ…፡፡በእለቱ በኪሳቸው ያላቸው ተማሪዎች ወዲያውኑ ማዋጣት ጀመሩ…ሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር አካባቢ ተሰበሰበ፡፡በማግስቱ ሁሉም ተማሪ ለወላጆቹ በማስረዳት የቻለውን ይዞ እንዲመጣና በስም ጠሪዎች አማካይነት በየክፍሉ እንዲሰበስብ ተደረገ፡፡
በአጠቃላይ በሶስት ቀን ውስጥ ከመላው ተማሪና አስተማሪዎች 23 ሺ ብር ተሰበሰበ፡፡ትምህርት ቤቱ የሰሎሜን እናት ጠርቶ ቀጥታ ብሩን አስረከባት፡፡  የትምህርት ቤቱን ቅፅር ግቢ በእልልታ አናጋችው….ሶስቱን የልጇን ጓደኞች እያገላላበጠች ሳመቻቸው፡፡ከልቧ መረቀቻቸው፡፡ከነፍሷ ወደደቻቸው፡፡
እነአለማየሁ ግን እንደእሷ ባገኙት ነገር ፍፅም ደስታ አልተሰማቸውም ነበር፡፡የእነሱ ግምት ቢያንስ 40 እና 50 ሺ ብር እናገኛለን የሚል ነበር፡፡ወዲያው ጊዜ ሳያባክኑ ባነሩን ለሁለት ጉን ለጉን ይዘው አንደኛው በአጀንዳ ላይ እያንዳዱ ሰው የሚሰጠውን ስምና ብር  እየመዘገበ  በሰፈር ውስጥ እያንዳንዱን ቤት እያንኳኩ እና የድርጅቶችንም ቢሮ ዘልቀው እየገቡ  ጭምር መጠየቅ ጀመሩ፡፡
በአራት ቀን ውስጥ ሌላ 20 ሺ ብር አገኙና ለእናትዬው አስረከቧት..፡፡እሷ በፊት ደብተሯ ላይ የነበራትናን ከቢሮዋ ሰራተኞች ተዋጥቶ የተሰጣት አንድ ላይ ሆኖ እነሱ ከሰበሰቡት ጋር  50 ሺ ብር አካባቢ በእጇ ያዘች፡፡
ሶስቱም በአንድ ላይ ተሰብስበው ሄደው ‹‹እቴቴ..አሁን ስንት ብር ሆነልሽ?››ብለው ጠየቋት፡፡
👍599👏1