#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሁለቴ
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
...የጠዋት ፀሐይ የማንንም ፈቃድ ሳትጠይቅ ፈገግ ብላ በዝግታ ወደ ጥናት ክፍሉ ገባች ። ፈገግታዋ ሙቀት እንጂ
ድምፅ ስለ ሌለው ፥ አቤል ቶሎ አላያትም እያዘገመች የተቀመጠበት ወንበር ላይ ደርሳ ግራ ጐኑን ስትሞቀው ነቃ ከእንቅልፉ ሳይሆን በተመስጦ ይሠራው ከነበረው ጽሑፍ ላይ እና ብዕሩን ወረቀቱ ላይ ወርውሮ በተቀመጠበት ተንጠራራ ። ሰውነቱን አፍታታ ።
እጁ ላይ ሰዓት የለም ። ነገር ግን፥ከንጋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ መሆኑን ለመገመት አልተቸገረም” ። ከተቀመጠበት
ሳይነቃነቅ ሦስት ሰዓት ያህል መቆየቱ አላስገረመውም ። ከሌሊቱ ዐሥር ሰዓት ከእንቅልፉ እየነቃ እስከ ንጋት ድረስ
መሥራት፡ሰሞኑን ልማድ እያደረገው መጥቷል ። በንጹሕ አእምሮ ስለሚሠራ፥ ፍሬያማ ውጤትም አግኝቶበታል ።
ዮናታን ይህንኑ በመመልከት ለማንቃት እንዲረዳው የሳሎ ኑን ባለደወል የጠረጴዛ ሰዓት መኝታ ክፍሉ ውስጥ አድርገውለታል ። ቀን ቀን ለጥናት ጽሑፉ የሚረዱትን መጽሐፎች ሲያገላብጥ ውሎ በዚች በለሊቷ ሰአት መጻፉ ጥሩ መንገድ
ሆኖለታል።
ተንጠራርቶ ሲያበቃ ከተቀመጠበት ተነሣ ወደ በረንዳ መናፈሻ ብቅ ብሎ ፀሐይዋን ሙሉ በሙሉ ሊሞቃት ፈለግ ። የሰንበት ፀሐይ ! ጭለማው ገልጦ የእሑድ ፀሐይ ብቅ ካለች ከውጭ የሚመጣ ሰው አለ ስለዚህ የእሑድ እንግዳውን ለመቀበል ጸጉሩን ማበጣጠር ልብሱን መቀየር ነበረበት።
ጸጉሩን ሲያበጥር ልቡ ድቤ መምታት ጀመረ ። ዕረፍ ብለው አያሳርፉት ነገር ! የልብን ከበሮ አይቆጠሩት ነገር !
የገዛ ልቡ አናደደው ። ድንገት የበሩን ደወል የሰማ መሰለው ተሳስቷል ። ናፍቆት የፈጠረ ደውል ካልሆነ በስተቀር ፡ በክፍሉ ውስጥ የተሰማ ድምፅ የለም ። የሹካ ማንከያና የስሐን ድምፅ ግን በርግጥ ከሌላኛዉ ክፍል ይሰማል ።
ያቺ ሞኒካ ስትንደፋደፍ ነው ። መቼም እሷ ጠዋት መተኛት አትወድ።
ወደ በረንዳው መናፈሻ ወጥቶ ከፎቁ ቁልቁል ተመለከተ ። የዮናታን መኪና እቦታዋ የለችም ። ጠዋት ሲነሡ
ስለሰማ፡የት እንደሔዱ አላጣውም። በአስፋልቱ ሳይ ከሚሠሩ መኪናዎች መሐል ነጥሎ የሚለያት ይመስል ዐይኑን ወደ ሩቅ ወረወረ ። የቤት መኪናዎች እምብዛም የሉም ። ታክሲዎች ናቸው ሽቅብ ቁልቁል ውር ውር የሚሉት ።
ቆሞ መጠበቁ ሰለቸው ። የቆመበት ጊዜ ከዐሥራ አምስት ደቂቃ ባይበልጥም ለእሱ የዓመት ያህል ረዘመበት
“ምን ሆነው እንዲህ ቆዩ ? ” አለ በሐሳቡ፡ አልሔድም ብላቸው ይሆን ? ወይስ የሙሽራ ልብስ አልብሰው ሊያመጧት
ይሆን ? ?
ትዕግሥቱ አልቆ ወደ ውስጥ ተመለሰና ሞኒካ ጋ ሔደ።ወጥ ቤት ውስጥ ምግብ እያበሰለች ነበር ። የቡታ ጋዙን ሦስቱም ምድጃ ድስት ተጥዶበታል ። ሰርግ ሰርግ ሸተተው ፤ የወጡ ሽታ ራብ ለቀቀበት ። ቁሌቱ ገና ይንተሸተሻል ። የበሰለው ደግሞ ክዳኑን ሽቅብ እየገፈተረ ይንተከ
ተካል ። ሞኒካ ፊት ላይ ክፉኛ መቻኮል አነበበ ።
“ ምን ልርዳሽ ? ” አላት ። እሷም ፈገግ ብላ " ከምድጃው ላይ አንዱን ድስት አውርዳ ፥ ቡና በማንቆርቆሪያ
እንዲጥድላት ነገረችው ፡ሁለቱም የሥራ ድርሻቸው ላይ አትኩረው እግረ መንግዳቸውን ስለ ጽሑፍ ሥራው ሁኔታ መጨዋወት ላይ እንዳሉ ድንገት ደወሉ ተንቃጨለ።
አቤል ሲሰማው በላብ ተጠምቀ ፣ጭንቅ አለው ፤የልቡ ትርታ ፍጥነቱን ጨመረ ። ምን ሰው ያስደነግጣሉ ! ቀስ ብለው አይደውሉም እንዴ ? ” የቡና ማንቆርቆሪያ ክዳን እንደ ወደቀበት ያስተዋለው ቆየት ብሎ ትንሽ ከተረጋጋ በኋላ ነው።
ሞነካ ዋናውን በር ከፍታ እንግዶቿን ስትቀበል አቤል ወጥ ቤት ውስጥ እንደ ቆመ ጆሮውን ላከ። የተነባበረ የጫማ ድምፅ ። የማን የማን ይሆን ? የዮናታን ፡ የእስክንድር ፡ የሚሰማው የወንዶች ድምፅ ብቻ ሆነበት ። የልቡ ምት ስላስፈራው ደረቱን በእጁ ደገፈ ። ወዲያው ግን ሞኒካ ራሷን በእንግሊዝኛ ስታስተዋውቅ ስለ ሰማ አዲስ ሰው
መምጣቱን ገመት ።
ያላበውን እጁን አጠገቡ ያገኘው ነገር ላይ ጠራረገ ።ግንባሩን ፡ ጉንጩን ዐይኑን በእጁ አሻሸ እንደ ቆመ ጸጉሩን አበጣጠረ ። የሸሚዝ ኮሌታውን እያስተካከለ በረዥሙ ተነፈሰ ጭንቀት የሚያባርር፥ ፍርሐት የሚያስወግድ አተነፋፈስ : እና ርምጃውን በልቡ እየቆጠረ ወደ ሳሎን ገባ ።
ከአጭር ጠይም ሴት ልጅ ጋር ዐይን ለዐይን ተገጣጠሙ ። የሁሉም ፊት በፈገግታ ደምቆአል " ፈገግታው ሁሉ ለአቤል ጐልቶ የታየው የትዕግሥት ነው " በጉንጭ መሰርጐድ የታጀበ ፈገግታ ! ይህን ፈገግታዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየው አንሥቶ ከአምስት ወር ራብ በኋላ ማየቱ ነው ። የሚወደውን የጉንጯን ስርጉድ ቀርቦ ሲያይ የመጀመሪያው ጊዜው መሆኑ ነው ። ማንን ቀድሞ መጨበጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲርበተበት አብራው የቆየችውን
ሞኒካንም እንደ አዲስ ጨበጣት ።
ለእስክንድር ያለዉን ስሜት ቆንጥጦ መያዝ አልቻለም ። ስሜቱ ፈንቅሎት ጉንጩን ጥብቅ አድርጐ ሳመውና
ይህ ሁሉ የአንተ ጥረት ያስገኘው ፍሬ ነው አስው ። ፊቱን በቅጽበት ወዶ ዮናታን መል። እና ደግሞ የርስዎ ? ” አላቸው ። ፍቅሩን በዓይኑ ከመግለጽ ቀቀር ተንጠራርቶ ሊስማቸው አልደፈረም ። ሦስተኛ ባለውለታውን ሲያመሰግን ዘወር ሲል ከአጠገቡ አጣት ። ሞኒካ ድስት ሲገነፍል ሰምታ እየሮጠች ወደ ወጥ ቤቱ ተመልሳ ነበር ።
ትዕግሥት በነጭ የሀገር ልብስ ነው የመጣችው።አቤል ይህንኑ ለብሳ የተመለከተቀትን እሑድ ወዲያው አላስታወሰም " ቆይቶ ቆይቶ ነው ከእነ ማርታ ጋር ሰርግ ቤት ስትሄድ ልብሳው እንደ ነበር ያስታወሰው። ሰላምታውንና ምስጋናውን ጨርሶ ሲቀመጥም ልቡ እልተረጋጋም ነበር ።ይበልጥ የትርታውን ፍጥነትና አስጭናቂነት ጨመረ
ዘሎ ዘሎ አንዴ ቀጥ እንዳይል ፈራ።
ትዕግሥት ማለት እሷ ነች ። ታዲያ የተመኙትን ሲያገኙ መንቀጥቀጥ ነው ? ደብዳቤዉ ያሳደረበት ስሜትና ሲገናኙ የደረሰው ሁኔታ ባለመገጣጠሙ በልቡ በሸቀ። ያ ሁሉ የፍቅር ቃላት ጋጋታ ምን ዋጠው ? ይኖራል ! ጸጥታውን የሚሰብርለት ድምፅ አጥቶ ነው እንጄ በሁለቱም ውስጥ አለ ።
አቤል ኤቼዳች ቃል መተንፈስ ፈልጎ ምላሱን ተጠራጠረው " ምናልባት የተሳሰረበት እንደሆንስ ? ከፍቅር
እመቤቱ ፊት የተቀመጠው ገላው የሚንቀጠቀጥ ጀርክ የሚመታ መሠለው።
በድንገት ዐይኑ የእጁ ጠባሳ ላይ ዐረፈ ምግብ አዳራሹ ውስጥ የወደቀ ጊዜ የወጡ ፍንጣቂ ያተረፈለት ጠባሳ ።
መጥፎ ስሜት አልተናነቀውም መጥፎ የልብ ጠባሳ ነበር እንጂ የእጅ ጠባሰ ምንም አይደለም ። የልቡን ቁስል ደብዳቤዋ ባመነጨበት እንባ ካጠበው ሰንብቷል ።
ተጫወቺ የሚል ቃል እንደ ምንም ከአፉ
ገፍትሮ አወጣ ።
ትዕግት በእሺታ ፈገግ አለች ፈገግታዋ ጠዋት ከሥራው ላይ ካባነነችው ፀሐይ ይበልጥ ደምቆ ታየው።
ሳያስቡት የዝምታው ባሕር ዮናታን እስክንድርም ውጧቸው ነበር ። ከተቀመጡ ጀምሮ ቃል አልተነፈሱም
ታዛቢ ባይሆኑም ታዛቢ መሰለዋል ። ወጥ ቤት ውስጥ የሚንተሽተሽው ምግብ ሽታ የእስክንድርን አንጀት እያላወሰው ነበር። በአፉ ምራቅ ሲሞላ ተሰማው።
"በመጀመሪያ የመኝታና የጥናት ክፍሎችህን ለትእግስት አሰጎብኛት ! አሉ ዮናታን በቤቱ ውስጥ እንቅስቃሴና ድምፅ ለመፍጠር በማሰብ።
አቤል ከትዕግሥት ጋር ተነሣ" ዮናታንና እስክንድርን በዝግታ ከኋላቸው ተከተሏቸው ።
“ ፍቅራቸው በጥሩ መልክ ይቀጥል ይሆን ? ” አለ እስክንድር በሹክሹክታ ድምፅ ፥ ወደ ዮናታን ጆሮ ጠጋ ብሎ ።
ቢቀጥል መልካም ነው ። ባይቀጥልም አቤልን እንዳለፈው አይጐዳውም ። ተቀራርበው ቃላት ከተለዋወጡ
ዐይኑን መግለጥ ይችላል አሉ ዮናታንም በሹክሹክታ በአቤልና

👍2🥰2
ትእግስት መሐከል የጫማቸው ድምፅ ካልሆነ በስተቀር የቃላት ልውውጥ አልተሰማም ። የመኝታ
ክፍሉን ጎብኝታ ወደ ጥናት ክፍሉ ስትገባ ግን ትዕግሥት ተነፈሰች ።
“ በጣም ትልቅ ይቅርታ ! ” አለችው ፡ ዐይኗ ዕንባ እቅርሮ ።
“ ምነው ለምን ? ” አላት ፥ ዕንባዋ የቀሰቀሰበትን ስሜት ከጉሮሮው ወደ ውስጥ ለመዋጥ እየታገለ ።
"ትምህርትህ በእኔ ምክንያት በመቋረጡ ይቅርታ አድርግልኝ !! »
“ ታዲያ አንቺ ምን አጠፋሽ ? ” አለና አቤል አሁንም ጉሮሮው ላይ የሚተናነቀውን ነገር በምራቁ አወራርዶ
“ ይልቅ እዚሁ ቤት የጥናት ጽሑፍ ማዘጋጀት ጀምሬአለሁ ። ለሥራው የሚረዱኝ መጽሐፎችና ሐሳቦች በማፈላለግ ትረ ጂኛለሽ ? ” አላት ።
ፈቃደኝነቷን ለመግለጽ ራሷን መነቅነቅ ወይም ቃላት መናገር አላስፈለገም ።
“ እና ትምህርቴንም በአዲስ ዓመት ፥ በአዲስ ልቦና ፥ በአዲስ ተስፋ እቀጥላለሁ ።
ቃላት አንሰዋቸው ዐይን ለዐይን ሲተያይ አልተፋፈሩም ። ዐይኗ ብሌን ውስጥ ምስሉን ሲመለከት እሷም ዐይኑ ብሌን ወስጥ ምስሏን እየተመለከተች ነበር ።
ትዕግሥት ከአቤል ዐይን ዳርቻ ላይ ዐይን አር አየች ልትጠርግለት ብትሞክርም እጅዋ ይንቀጠቀጥ ይሆን? እንደ
ምንም ደፍራ እጅዋን ዘርግታ በጣቷ አነሣችለት ።
ምንድን ነው ? ” አላት ከንፈሩ እየተንቀጠቀጠ
“ ጉድፍ” አለችው የእሷም ከንፈር እየተንቀጠቀጠ ።
ዐይኑን የነካው እጅዋን ጥብቅ አድርጎ ሳመው ።
ዮናታንና እስክንድር በደስታ ፈዘው ቀሩ። እውን ሳይሆን የፊልም ትርኢት የሚያዩ ነበር የመሰላቸው ። በተለይ
እስክንድር ራሱን መቆጣጠር አቅቶት እንደ ሕፃን ፈንደቅ ፈንደቅ የሚል ስሜት ታገለው። ደስታ በሣቅ ሣቅም በጥርስ
የሚገለጽ ነገር ባይሆን ኖሮ መላ ሰውነቱ እየሣቅ ነበር ።
ለአፍታ ያህል ጓደኞቻቸው ፊቱ ላይ ድቅን አሉበት ። ማርታ የነገር ቅንድቧን እያርገበገበች ፡ ድብርት በጋቢው
ተጀቡኖ እየተልጐመጐመ ፥ ሚስተር ሆርስ ቼሱን ታቅፎ ቅልጥሙን እንደ ዘረጋ ቤተልሔም በፈተና ሰዓት ወደ
ሽንት ቤት እየሮጠች ፡ ሳምሶን ጉልቤው ጡንቻውን ወጣጥሮ ለአቤል ሊማታለት እየተጋበዝ - ሁሉም በእስክንድር
ሐሳብ ውስጥ ተሰለፈ ። “ ምነው አንዳፍታ መጥተው ይህን ትርኢት ለማየት በታደሉ ! ” አለ በልቡ ።
አቤል የትዕግሥትን እጅ ስሞ አልለቀቀውም እንደገና ወደ ደረቱ እስጠግቶ ጥብቅ አርጐ ያዘው ። እጇ
እንደ ኤሌትሪክ ሽቦ የአቤልን ልብ ትርታ እየተቀበለ ወደ እሷ ያስታሳልፍ ጀመር ። ትርታው ነዝሯት አላፈገፈገችም ። ይልቁንም መላ ሰውነቷን በዝግታ ወደ አቤል አካል አስጠጋችው ። ትንፋሻቸው ተገጣጠመ ። ሁልቱ እንደ አንድ ሰው !
“ እ --- እ --- እፀድሻለሁ ። ”
አስቸግራው የኖረቺውን አንዲት ቃል ተነፈሳት ።
💥ተፈፀመ 💥
ሰመመን ይሄን ይመስላል ብዙዎቻችሁ ድሮ አንብባችሁት አልፋችሁ ይሆናል አሁን በዚህ ቻናል ሲለቀቅም ገና ያነበበው ሊኖርም ይችላል የሁላችሁንም አስተያየት እፈልጋለው በ @atronosebot አድርሱኝ

🥰4👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
#ከሁለት_ወራት_በኋላ
እንደሻው በቀለንና ራሷን በጥይት አቁስላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ስትከታተል ከቆየች በኋላ በሁለተኛው ወሯ ሙሉ ለሙሉ ዳነች፡፡
በዚያ ጥይት ምክንያት ከላይኛው መንጋጋ ጥርሶቿ ላይ ሁለቱን አጥታለች፡፡ የግራ ጆሮዋ በመስማት በኩል ትንሽ ቅር ቢለውም ሙሉ ለሙሉ አልደነቆረም፡፡
ጥይቶቹ በተከታታይ ሾልከው የወጡበት ቀዳዳ መጠነኛ ጠባሳን ጥሉባት አለፈ እንጂ፤ ውበቷን እምብዛም የሚፈታተነው አልነበረም፡፡
ከዚህ ሁሉ ሥቃይ በኋላ ግን እቤቷ ገብታ አላረፈችም፡፡ ወንጀለኛ ናትና በቀጥታ በማረፊያ ቤት እንድትቆይ ተደረገ፡፡
የወንጀል ክሱ በዐቃቤ ህግ ከሳሽነት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡
ከሳሽ ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ ወይዘሪት ትህትና ድንበሩ የክሱ ምክንያት ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል ዐቃቤ ህጉ ተከሳሽ ሆን ብላ ተዘጋጅታ ወጣት እንደሻው በቀለ ከሚሰራበት የንግድ ሱቅ ድረስ በመሄድ በአራት ጥይቶች ያቆሰለችው መሆኑንና እራሷንም ለመግደል ሙከራ ማድረጓን ከገለፀ በኋላ፤ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና አንቀጽ ጠቅሶ አስፈላጊው ቅጣት እንዲወሰንባት
የተመሰረተ ክስ መሆኑን በማተት አቀረበ፡፡
ትህትና ድንበሩ ተከሳሽ ሆና ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበችበት ዕለት፤ ታናሽ ወንድሟ በችሎቱ ላይ በመገኘት ክሱን
አብሯት አዳመጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላት፡፡
ስምሽ?”
“ትህትና ድንበሩ”
“ዕድሜሽ?”
"አሥራ ሰባት ዓመት”
“አድራሻ?”
“አዲስ አበባ
“ሥራሽ?”
“ሥራ ፈላጊ”
“ወላጆችሽ በህይወት አሉ?”
“አባቴ ሞቷል እናቴም የአልጋ ቁራኛ ነች”
ይህንንና መሰል ጥያቄዎችን ከተጠየቀች በኋላ “የክሱ ቻርጅ ደርሶሻል?” የሚል ጥያቄ ቀረበላት፡፡
“አዎን ደርሶኛል”
ከዚያም የመሐል ዳኛው መነጽራቸውን ዝቅ አድርገው በግንባራቸው ዐይዋትና........
“ወይዘሪት ትህትና ለተመስረተብሽ ክስ እራስሽ ትከራከሪያለሽ ወይስ?
ጠበቃ ታቆሚያለሽ?” የሚል ጥያቄ አቀረቡላት፡፡
ቀስ ብላ ሻምበል ብሩክን አየችው፡፡ የመከራትን አስታወሰች፡፡
“ድሃ ስለሆንኩ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ?” የሚል መልስ ሰጠች፡፡
ይህንን መልስ ስትሰጥ በተቻላት መጠን ድምጿ እንዲሰማ ጮክ ብላ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱ በጥብቅና ሙያው የታወቀው አቶ ምንውዬለት ተዘራ ለተከሳሽ ጠበቃ እንዲሆንላት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ አቶ ምንውዬለትም ትእዛዙን በደስታ ተቀበለ፡፡
ይህ ከሆነ በኋላ ተከሳሽ የተከሰሰችበት ወንጀል በንባብ እንዲሰማ ተደረገ፡፡
“በተመሰረተብሽ ወንጀል ጥፋተኛ ነሽ አይደለሽም?” ተብላ ተጠየቀች፡፡
በዚህ ጊዜ ጠበቃው አቶ ምንውዬለት ጥቁር ካባውን እንደለበሰ
ብድግ ብሎ ቆመ፡፡
“ጥፋተኛ አይደለችም ክቡር ፍርድ ቤቱ” ሲል መልስ ሰጠ፡፡ ዳኛው መልሱን ከመዘገቡ በኋላ፤ ጠበቃው “ክቡር ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የዋስ መብቷ ተጠብቆ እንድትከራከር ይፍቀድልኝ” ሲል ጥያቄ አቀረበ፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ፤ ተከሳሽ በማረፊያ
ቤት ቆይታ እንድትከራከር በመወሰንና፤ ዐቃቤ ህጉ አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች እንዲያቀርብ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ አበቃ፡፡
ትህትና እዚያ የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ
ቆማ ስትቁለጨለጭ፣እንዳንድ ጊዜ በፍርሃት ተውጣ ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥ፣
ድምጿ ሲርገበገብ፣ ሲያልባት፡ እያየች አዜብ እንባ እየተናነቃት ነበር፡፡ ሆኖም አልቅሳ ልትረብሻት አልፈለገችም፡፡ ይልቁንም ሳቅ ፈገግ እያለች ሞራል ልትሰጣት ሞከረች፡፡
እውነትም እንደዚያ ሰውነቷ በፍርሃት ሲሸበርባት፣ ልቧ ድው ድው ሲል፣ ሻምበል ብሩክን፣ ወንድሟንና አዜብን ቀስ ብላ ታያቸዋለች፡፡ እነሱ ፈገግ ይሉና በ“አይዞሽ” ምልክት ሲያበረታቷት “አይዞኝ” በሚል ስሜት እራሷን ስታጠናክር ከቆየች በኋላ ችሎቱ ሲያበቃ በአጃቢ ፓላስ ታጅባ ወጣች፡፡
ከዚያም በአንዱአለም ጠያቂነት አብረው ምሣ ይበሉ ዘንድ ሻምበል ብሩክ አጃቢ ፓሊሱን አነጋገረውና አብረው ምሣ ለመብላት ፈቃድ ስለ አገኙ ፤ እዚያው አካባቢ በሚገኝ ወደ አንድ ሆቴል ገቡ፡፡
አንዱአለም የዛሬውን ምሣ ለመጋበዝ የፈለገበት ምክንያት ነበረው፡፡ የሚፈለገው ምግብና መጠጥ ታዘዘ፡፡
ከባህር ኃይሉ የተሰጠው የኪስ ገንዘብ ስለነበረው ምሣ የጋበዘው እሱ ነበር፡፡ አንዱአለምን ብሎ ጋባዥ በመገኘቱ እየተሳሳቁ፣እየተጨዋወቱ፣ ግብዣውን በደስታ ተቀበሉት፡፡ አጃቢ ፓሊሱ በሻምበል ብሩክ ላይ እምነት ስለጣላ እስረኛዋ ታመልጣላች የሚል ሥጋት አላደረበትም፡፡ እንደዚሁ እየተጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ.......
“አንድ ጊዜ” አለና አንዱአለም ትንፋሹን ሰብሰብ፣ ምራቁን ዋጥ አደረገ፡፡
አራቱም በፀጥታ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ከወትሮው ለየት ያለ ስሜት ይታይበታል፡፡ እነሱ ከተቀመጡበት አካባቢ ትንሽ ራቅ ብለው በርከት ያሉ እየተጨዋወቱ የሚሳሳቁ ሰዎች ድምጽ ብቻ ይሰማል፡፡
“ይህቺ የምሣ ግብዣ በአንድ በኩል እታለም ለመጀመሪያ ጊዜ
ፍርድ ቤት በቀረበችበት ቀን ተገኝቼ እውነተኛ ፍትህን አግኝታ በነፃ
እንድትለቀቅ መልካም ምኞቴን የምገልጽበት ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ
ለራሴ መሸኛ በማድረግ በግል ውሣኔዬ መሠረት ለነገው ጉዞዬ መቃናት
እንድትመርቁኝና፤ የወጪ እንድላችሁ በማሰብ የተደረገች ግብዣ ነች”
አለ፡፡ ስለምን እንደሚያወራ ቶሎ ማወቅ አልቻሉም :: “የምን ጉዞ? የምን መሸኛ?. “ምንድነው የምትለው አንዱዬ?” በድንጋጤና በጥርጣሬ ተውጣ አዜብ ጠየቀችው፡፡ “ ሁሉንም ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቄአለሁ፡፡
ከአንድ ሣምንት በፊት በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ውስጥ ተቀጥሬ ለስልጠና
መሄዱ ነው” ሲል ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በዚያ ጨዋታ መካከል ይህንን መርዶ አምጥቶ ሲጥልባቸው ልባቸው ክፉኛ አዘነ፡፡ በተለይ ትህትና የተሰማትን ስሜት መግለጽ ያስቸግራል፡፡ ጭውው አለባት፡፡ ግማሽ አካሏ፣ የምትወደው ታናሽ ወንድሟ ምንም እንኳን እስረኛ ብትሆንም በየጊዜው እየመጣላት ዐይኖቹን ስታየው
የምትጽናናበት አለኝታዋ ነበር፤ በሁኔታው መሪር ሀዘን ተሰምቷት አለቀሰች፡፡
አዜብም እንደዚያው፡ ሻምበል ብሩክም ክፉኛ ነበር የደነገጠው፡፡
ይህ ትንሽ ልጅ የዚህ ዐይነት ከባድ ውሣኔ ላይ ይደርሳል ብሎ ጭራሽ አልገመተም ነበር፡፡ የሱ ፍላጐት አንዱአለም በትምህርቱ ጠንክሮ ዩኒቨርስቲ
እንዲገባ እንጂ እንደዚህ በመሀሉ አቋርጦ ወደ ጦር ሜዳ እንዲሄድ አልነበረም፡፡ ከረጅም ፀጥታ በኋላ......
“እንደሱ ይሻላል አልክ አንዱአለም?” አለው ሻምበል በትካዜ አንደበት።
ትህትና እና አዜብ በእንባ ይንፈቀፈቃሉ፡፡ አጃቢ ፓሊሱ ግራ ተጋብቶ ሁሉንም በዐይኑ ይቃኛል፡፡
“በቃ ብንሄድስ” የሚል ፍላጉት አድሮበታል፡፡ ሞትም ቢሆን በተሰማበት ቅጽበት በድንጋጤ ያደርቃል እንጂ፤ ቀስ በቀስ መለመዱ አይቀርምና፤
ውስጥ ውስጡን እየተቃጠሉ፤ እንባቸውን እየጠራረጉ፤ዐይን፤ ዐይኑን፧ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ውሣኔው የፀና፣ ጉዳዩ ያበቃለት መሆኑን ቁርጥ አድርጉ ነገራቸው፡፡
እስከዛሬ ድረስ የቆየው እህቱ ፍርድ ቤት ስትቆምና የተከሰሰችበት ወንጀል ሲሰማ አብሯት ለመገኘት ፍቃድ በመውሰድ መሆኑን፣ ነገ በጠዋት በዋናው መሥሪያ ቤት ተገኝቶ ወደ ማሰልጠኛው ጉዞ የሚጀምርከ መሆኑን፣ለሻምበል ሲያስረዳው ለትህትና እና ለአዜብ ደግሞ የመርዶ ያህል ካረዳቸው በኋላ በአጃቢ ፓሊሱ አሳሳቢነት ተነስተው ወጡ፡፡
“እሺ አሥር አለቃ ስለተባበርከኝ በጣም ነው የማመሰግንህ አለው ሻምበል የአጃቢ ፓሊሱን ትከሻ ቸብ ቸብ እያደረገ፡፡
“እሺ ጌታዬ አኔም የርስዎ ነገር ሆኖብኝ እንጂ፤ ህግ መጋፋቴን አልዘነጋሁትም” አሥር አለቃ ጥላዬ እግረ መንገዱን ውለታውን

👍1
እያዘስመዘገበ....አንዱአለም ከእህቱ ጋር ተቃቅፈው፤ ተሳስመው ፤ ሲሰነባበቱ ግን አልቻልም፡፡ ሆዱ ባባና አቅፏት አለቀሰ፡፡
በመጨረሻም ትህትና ወደ እሥር ቤት ጉዞዋን ስትቀጥል፤ እሱ ደግሞ ዝግጅቱን ሊያጠናቅቅ ወደ ባህር ኃይል መሥሪያ ቤት ለመሄድ ሻምበል ብሩክን ተሰናበተና ከአዜብ ጋር ሆነው ታክሲ ውስጥ ገቡ......
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

#ላንቺው_ነው
💚 💛 ❤️
የጎደለው አንዳች የለም
የሚያሳንሰው . . . ከሰው ግብር፣
ለራሱ መኖርን አስንቆ
በቀን ሃሩር የሚያንገላታ
በሌ'ቱ ቁር የሚያሳድር፡፡
ቀና ሲል የሰማይ አድማስ
ደረቅ ቁጥቋጦ ሲያዘቀዝቅ፣
ቆምኩ ሲል የጋለ መሬት
ቢራመድ ከቆንጥር መናጠቅ
ምን ቢፈተን በተፈጥሮ
ጥርሱን ነክሶ ያሸነፈ ፣
በብርሃንሽ ላይ ያጠላውን
ጨለማሽን የገፈፈ፡፡
ሰላም ውለሽ እንድታድሪ
ከእንቅልፉ ጋር የተፋታ፣
ስለ ክብርሽ የመነነ
ስለ እረፍትሽ ያጣ ፋታ፡፡
ድንበርሽን ባጥንቱ አጥሮ፣
ሰንደቅሽን በደሙ ያቆመ
ከምትክ የለሽ ህይወቱ እንኳ፣
ህልውናሽን ያስቀደመ
ላንቺው ነው እምዬ እናቴ፣
ላንቺው ነው አንቺ እናት ሃገር
ለሰንደቅሽ ከፍታ ሲል፣
የወደቀልሽ ወታደር፡፡
ላንቺው ነው........!
በእረፍት የለሽ ኑሮ መሃል፣
ያንቺን ነገ እየሳለ
በረሃውን አለሙ አድርጎ፣
ከተፈጥሮ ጋር የታገለ
በተጋፈጣት ተራራ፣
በወረደባት ቁልቁለት
በተሻገራት ወንዝ ይሁን፣
በፈተነችው ተዳፋት፣
በተጓዘባት ሸለቆ
ባቆራረጣት ተረተር፣
በእያንዳንዷ ስንዝር መሬት
በረገጣት ቅንጣት አፈር፣
ያንቺን ክብር የሚመጥን
ላብ ከፍሎበታል ወታደር፡፡
ምንም ገፁ ቢጎሰቁል
ቢሻክር ደድሮ መዳፉ፣
ምንም አንጀቱ ቢታጠፍ
በውሃ ጥም----- ቢደርቅ አፉ፣
በጉዞ ብዛት ቢዝሉ
እረፍት አያውቄ እግሮቹ፣
በእንቅልፍ እጦት ቢዳከሙ
ቢደበዝዙ አይኖቹ
በማይታየው ውስጡ ግን
ባላየነው ልቡ ላይ፣
ሃገሬ አንቺ ነግሰሻል
ደምቀሻል ከፀሃይ በላይ፡፡
ላንቺው ነው........!
ላንቺው እንጂ መኖር የሚሻ
በበረሃው ሃሩር ነድዶ፣
ስለ ክብርሽ እንጂ የሚሞት
ስጋ አጥንቱን በእሳት ማግዶ
ወታደርኮ ሃቅ ነው ለገባው ቃል የታመነ፣
ቤት ንብረቴን - ልጄን ሳይል
ሃገር አፍቅሮ የመነነ፡፡
በጀግንነት ጠላት ጥሎ
ሲሰዋ እንኳን በጦር ስፍራ፣
በስስት እያያት ያሸልባል
የሃገሩን ውብ ባንዲራ፡፡
የጀግናችን የፍቅር ጥግ
ታውቂያለሽ እናት ሃገሬ፣
በአንቺ ነው አፉን የፈታ
ዜማው ነሽ ህብረ ዝማሬ፡፡
ማንም ሊደፍረው ባልተቻለው
ፀንቶ ባቆመው ድንበርሽ ላይ፣
የወታደር አፅም አለበት
በሃቅ ሚዛን ብቻ የሚታይ፡፡
ከአፈርሽ ጋር ተቀላቅሎ
ሉአላዊ ክብርሽ የፀናበት፣
በነፃነት ዱካሽ መሃል
የወታደር ደም አለበት፡፡
ላንቺው ነው!
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
💚 💛 ❤️
የጎደለው አንዳች የለም
የሚያሳንሰው . . . ከሰው ግብር፣
ለራሱ መኖርን አስንቆ
በቀን ሃሩር የሚያንገላታ
በሌ'ቱ ቁር የሚያሳድር፡፡
ቀና ሲል የሰማይ አድማስ
ደረቅ ቁጥቋጦ ሲያዘቀዝቅ፣
ቆምኩ ሲል የጋለ መሬት
ቢራመድ ከቆንጥር መናጠቅ
ምን ቢፈተን በተፈጥሮ
ጥርሱን ነክሶ ያሸነፈ ፣
በብርሃንሽ ላይ ያጠላውን
ጨለማሽን የገፈፈ፡፡
ሰላም ውለሽ እንድታድሪ
ከእንቅልፉ ጋር የተፋታ፣
ስለ ክብርሽ የመነነ
ስለ እረፍትሽ ያጣ ፋታ፡፡
ድንበርሽን ባጥንቱ አጥሮ፣
ሰንደቅሽን በደሙ ያቆመ
ከምትክ የለሽ ህይወቱ እንኳ፣
ህልውናሽን ያስቀደመ
ላንቺው ነው እምዬ እናቴ፣
ላንቺው ነው አንቺ እናት ሃገር
ለሰንደቅሽ ከፍታ ሲል፣
የወደቀልሽ ወታደር፡፡
ላንቺው ነው........!
በእረፍት የለሽ ኑሮ መሃል፣
ያንቺን ነገ እየሳለ
በረሃውን አለሙ አድርጎ፣
ከተፈጥሮ ጋር የታገለ
በተጋፈጣት ተራራ፣
በወረደባት ቁልቁለት
በተሻገራት ወንዝ ይሁን፣
በፈተነችው ተዳፋት፣
በተጓዘባት ሸለቆ
ባቆራረጣት ተረተር፣
በእያንዳንዷ ስንዝር መሬት
በረገጣት ቅንጣት አፈር፣
ያንቺን ክብር የሚመጥን
ላብ ከፍሎበታል ወታደር፡፡
ምንም ገፁ ቢጎሰቁል
ቢሻክር ደድሮ መዳፉ፣
ምንም አንጀቱ ቢታጠፍ
በውሃ ጥም----- ቢደርቅ አፉ፣
በጉዞ ብዛት ቢዝሉ
እረፍት አያውቄ እግሮቹ፣
በእንቅልፍ እጦት ቢዳከሙ
ቢደበዝዙ አይኖቹ
በማይታየው ውስጡ ግን
ባላየነው ልቡ ላይ፣
ሃገሬ አንቺ ነግሰሻል
ደምቀሻል ከፀሃይ በላይ፡፡
ላንቺው ነው........!
ላንቺው እንጂ መኖር የሚሻ
በበረሃው ሃሩር ነድዶ፣
ስለ ክብርሽ እንጂ የሚሞት
ስጋ አጥንቱን በእሳት ማግዶ
ወታደርኮ ሃቅ ነው ለገባው ቃል የታመነ፣
ቤት ንብረቴን - ልጄን ሳይል
ሃገር አፍቅሮ የመነነ፡፡
በጀግንነት ጠላት ጥሎ
ሲሰዋ እንኳን በጦር ስፍራ፣
በስስት እያያት ያሸልባል
የሃገሩን ውብ ባንዲራ፡፡
የጀግናችን የፍቅር ጥግ
ታውቂያለሽ እናት ሃገሬ፣
በአንቺ ነው አፉን የፈታ
ዜማው ነሽ ህብረ ዝማሬ፡፡
ማንም ሊደፍረው ባልተቻለው
ፀንቶ ባቆመው ድንበርሽ ላይ፣
የወታደር አፅም አለበት
በሃቅ ሚዛን ብቻ የሚታይ፡፡
ከአፈርሽ ጋር ተቀላቅሎ
ሉአላዊ ክብርሽ የፀናበት፣
በነፃነት ዱካሽ መሃል
የወታደር ደም አለበት፡፡
ላንቺው ነው!
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....ቀጠሮው ደረሰ፡፡ ትህትና ድንበሩ ለተመሠረተባት ክስ መልስ የምትሰጥበት ቀን... ጠበቃዋ አቶ ምንውየለት ተዘራ በመልሱ ላይ ተከሳሽ ሆን ብላ ተሰናድታ ሳይሆንእንደሻው በቀለ በእሷና በወንድሟ
ላይ በፈጸመውና ባስፈጸመው ተደጋጋሚ ወንጀል ምክንያት ህሊናዋ ስለቆሰለ፤ ንብረትነቱ የወላጅ አባቷ የነበረውን ከቤት የተቀመጠ መሣሪያ በድንገት ይዛ በመውጣት፤ በደም ፍላት ተነሳስታ፤ ድርጊቱን መፈጸሟን፣ ወጣት እንደሻው በቀለ በፈጸመባት አስገዳጅ የግብረ ሥጋ
ግንኙነት ምክንያት፤ ክብረ ንጽህናዋ በመደፈሩ፤ ለትዳር ከወጠነችው እጮኛዋ ጋር ከመጣላቷም በላይ፤ ታናሽ ወንድሟ አንዱዓለም ድንበሩ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ምክንያት፤ በእንደሻው በቀለ አማካይነት በገንዘብ በተገዛ ወሮበላ ተደብድቦ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን፤ እነዚህ
ተደራራቢ ጥቃቶች፤ ወንጀሉን እንድትፈጽም ያነሳሷት ድርጊቶች
ከመሆናቸው በተጨማሪ፤ ወጣቷ በዕለቱ ወጣት እንደሻውን ለማጥቃት ብቻ ሳይሆን በራሷ ህይወት ላይ የወሰደችው ቅጽበታዊ ሙከራ ሁሉ፤ የነበረባትን የአእምሮ ጭንቀት ደረጃ በግልጽ የሚያሳይ በመሆኑ፧ ክቡር ፍርድ ቤቱ የዕድሜዋን ሁኔታ፤ የደረሰባትን የሞራል መገደድ፣ የቤተሰብ ኃላፊነት ደረጃዋንና ከዚህ በፊት የነበራትን መልካም ስነ ምግባር፧ ከግምት ውስጥ በማስገባት በነፃ እንዲያሰናብታት ሲል በመጠየቅ መልስ ሰጠ፡፡
ለዚህም መልስ የመልስ መልስ እሰጣለሁ በማለት ዐቃቤ ህጉ ስለጠየቀ፤
የመልስ መልሱን እንዲሰጥ ተደረገ፡፡
ከዚህ በኋላ በፓሊስ የቀረበው የምርመራ መዝገብ፣ የሀኪም ማስረጃና፤ በእግዚቢትነት የተያዘው ኮልት ሽጉጥ ለፍርድ ቤቱ ቀረቡ፡፡ ዐቃቤ ህጉ በሰጠው የመልስ መልስ ላይ ተከሳሽም ሆነች
ወንድሟ ተፈጽሞብናል የሚሉት ወንጀል ቢኖር፤ በወቅቱ ጉዳዩን ለህግ አቅርበው ፍትህን መጠየቅ ሲችሉ፤ ይህንን ሳያደርጉ ቀርተው፤ ተከሳሽ ከተመሰረተባት የክስ ጭብጥ፤ ምክንያትና ውጤት ጋር፤ግንኙነት የሌለውን ሀተታ በመልስ ውስጥ በመዘርዘር፤ በነፃ እንድትለቀቅ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤ ወንጀልን ማካካስ የማይቻል
በመሆኑም በመልሱ ላይ የቀረበው የወንጀል ማካካሻ ጥያቄ ውድቅ
እንዲደረግ ጥያቄ በማቅረብና ፤ ተከሳሽ እራሷን ለማጥፋት ያደረገችው ሙከራም ህጋዊ ድጋፍ የሌለው ህገውጥ ድርጊት ከመሆን አልፎ ከጥፋትዋ ነፃ እንድትወጣ በቂና አሳማኝ ምክንያት ሊሆን የማይችል
ስለሆነ፤ ክቡር ፍርድ ቤቱ በተከሳሽዋ ላይ የጥፋተኛነት ውሳኔ
በዚህም መሰረት
ቃለ መሀላ
እንዲሰጥልኝ በማለት ስለተከራከረ ፤ ለተፈጸመው ወንጀል ያውቁልኛል
የሚላቸውን ምስክሮች እንዲያቀርብ ተደረገ በምስክርነት ያቀረባቸው ሶስት ምስክሮች ፍ/ቤት ቀርበው እንዲፈጽሙ ከተደረገ በኋላ ፤ ወንጀሉ የተፈጸመበትን ቦታ፣ ቀንና ሰዓት ጠቅሰው ተከሳሽ እንደሻው በቀለን በአራት ጥይቶች ደጋግማ ማቁሰሏን በማረጋገጥ፤ ተመሳሳይነት ባለው ቃል መሰከሩ፡፡
የዐቃቤ ህጉ ምስክሮች ተሰምተው እንዳበቁ በተከሳሽ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ከበድ ያሉ ሆነው በመገኘታቸው፤ ፍ/ቤቱ ተከሳሽን
እንድትከላከል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡በዚህ ጊዜ የተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮች ሆነው የቀረቡት
1ኛ ወ/ት አዜብ ተሾመ
2ኛ ወ/ት ወርቅ ያንጥፉ አደራ
3ኛ. አቶ አበራ ፈይሳ
አስፈላጊውን ቃለ መሀላ ከፈጸሙ በኋላ፤ ተከሳሽ በአስተዳደግ፤ በተማረችበት ትምህርት ቤት፤ በሥራ ቦታዋ ላይም ሆነ በመኖሪያዋ አካባቢ የነበራትን ሥነ ምግባር፣ ከዚህ በፊት ተከሳ ያልተቀጣች ጨዋ ወጣት መሆኗንና፤ ወጣት እንደሻው በቀለ ድምጽ በሌለው መሣሪያ አስገድዶ ክብረ ንጽህናዋን ለመድፈሩ፤ እያንዳንዳቸው የሚያውቁትንና
ያዩትን ዘርዝረው መሰከሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እራሱ ሻምበል ብሩክ ፍርድ ቤት ቀርቦ ከእጮኛው ከትህትና ድንበሩ ጋር ወጥነውት የነበረው የትዳር ዕቅድ፤
ከተፈጸመባት አስገዳጅ የክብረ ንጽህና መደፈር ጋር ተያይዞ በተፈጠረ
ያለመግባባት ምክንያት መበላሸቱን አስረዳ፡፡
ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረቡትን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ
“ተከሳሽ በማያጠራጥር ሁኔታ ድርጊቱን የፈጸመች ሆና ስለአገኘናት በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 27/524.ለ/ መሠረት ጥፋተኛ ነች ብለናል”
ሲል የጥፋተኛነት ውሣኔውን ሰጠ፡፡
ጥፋተኛነትዋ ተረጋግጦ ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ፤ ቀሪው በቅጣት ውሣኔው ላይ የሚካሄድ ክርክር ነው፡፡በዚህ መሠረት ተከሳሽዋ ለፈፀመችው ወንጀል የቅጣት ውሣኔውን ለመስጠት እንዲያስችል ዐቃቤ ህጉ የቅጣት ማቅለያ ወይንም የማክበጃ ሃሣብ ካለው እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ስለጠየቀ፤ ተከሳሽ ትህትና ድንበሩ በቀልን በልቧ በማሳደር፤ በቂ ዝግጅት በማድረግና፤ የጦር መሣሪያ በመያዝ፤ ከሥራ ቦታው ድረስ ሄዳ ወጣት እንደሻው በቀለን በአራት ጥይቶች ደጋግማ ህይወቱን ለማጥፋት ሙከራ ማድረጓ በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠባት በመሆኑ፡ ለዚህ ለፈጸመችው ወንጀል ተመጣጣኝ ቅጣት እንድታገኝ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና አንቀጽ ጠቅሶ ጠየቀ፡፡
የተከሳሽ ጠበቃም እንደዚሁ ስለህጉና፤ ስለጉዳዩ፤ በማብራራት ቅጣቱ እንዲቀልላት አስተያየቱን አቀረበ፡፡
በዚህ የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ላይ በወጣት እንደሻው በቀላ ወላጆች ቤት ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉት በተለይ የወጣት እንደሻው የሥጋ ዘመድ የሆነው አቶ አበራ ፈይሣ የዝምድና ደረጃው ሳያግደው በሃቅ እንደመሰከረውና፤ በቤት ሠራተኛነት ተቀጥራ የምታገለግለው ወይዘሪት ወርቅ ያንጥፉ አደራ በዐይኗ ባየችው ድርጊት ላይ በሰጠችው የምስክርነት ቃል በተረጋገጠው መሠረት፤ እንደሻው በቀለ ሃይል ተጠቅሞ፤ በተከሳሿ ላይ የሞራል ተቃራኒ የሆነ፤ የወደፊት የትዳር ህይወቷን ያበላሸና፤ ከምትኖርበት ማህበረሰብ ባህልና እምነት አንፃር ዝቅተኛ ግምት የሚያሰጣትን ወንጀል የፈጸመባት በመሆኑ፤ ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘም ጋርጠው መራን በገንዘብ በመግዛት በወንድሟ ላይ የድብደባ ወንጀል በማስፈጸም ያደረሰባት ድርብ፤ ድርብርብ ጥቃት ለጋ አእምሮዋን የነካና፤ ለወንጀል ያነሳሳት ድርጊት መሆኑን :: ወጣቷ
በምትኖርበትም ሆነ በተማረችበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፍጹም ጨዋና
ዕላማዊ ዜጋ መሆኗ የተመሰከረላት ከመሆኑ በተጨማሪ፧ ወላጅ አባቷ
ለግዳጅ ተጠርቶ በጦር ሜዳ ላይ በመሞቱ ምክንያት፧ በለጋ እድሜዋ
ከራሷ ጭምር ሶስት ቤተሰብ የማስተዳደር ሃላፊነት የተሸከመች ወጣት
በመሆንዋ ክቡር ፍርድ ቤቱ.....
ሀ. ተከሳሽ ወንጀሉን ለመፈጸም የተነሳሳችበትን ሁኔታ
ለ. የተከሳሽን የዕድሜ ሁኔታ
ሐ. ተከሳሽ ወንጀሉን ስትፈጽም የነበረችበትን ሁኔታ
መ. የተከሳሽን የቤተሰብ ኃላፊነት ደረጃ
ሠ. ተከሳሽ ከዚህ በፊት በማናቸውም ወንጀል ተከሳ ቅጣት ያልተፈፀመባትና፤ ለወደፊቱ ያላትን የሥነ ምግባር ታራሚነት ከግምት ውስጥ በማስገባት እስከዛሬ ድረስ በማረሚያ ቤት የቆየችበት ጊዜ በቂ
ሆኖ ቅጣቱ እንዲቀልላት በማለት አስተያየቱን ሰጠ፡፡
ከዚህ በኋላ የሚቀረው ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ የቅጣት ውሣኔ የሚሰጥበትን ዕለት በጉጉትና በናፍቆት መጠባበቅ ብቻ ሆነ
አንዱአለም በአሁኑ ሰዓት ምጽዋ በባህር ኃይል ውስጥ በስልጠና ላይ ይገኛል፡፡ ለኪስ የሚሰጠውን አነስተኛ ገንዘብ የሚልከው ለእህቱ ነው፡፡ እህቱ በማንኛውም ረገድ እንድትበረታ፣ መታሰር ማለት በህይወት ውስጥ ከሚገጥሙ የኑሮ ውጣ ውረዶች አንዱ እንጂ ከህብረተሰቡ መገለል ማለት ያለመሆኑን እየገለጸ “አይዞሽ” እያለ በማጽናናትና፤ ስለሱ እንዳታስብ በቀይ ባህር ዳርቻ፣ በመርከብ ላይ፣ ብቻውንና ከጓደኞቹ ጋር
ሆኖ የተነሣቸውን ፎቶ ግራፎች ለሷና

👍4
ለእናቱ በመላክ፡ ናፍቆታቸውን
እንዲወጡ እያደረገ ነው፡፡
“አይዞሽ እማምዬ ልጦርሽ ደርሻለሁ፡፡ አሁን ትልቅ ሰው ሆኜልሻለሁ፡፡ እንደድሮው ትንሽ ልጅ አይደለሁም፡፡ በቅርቡ ድነሽ መጥተሽ እንደምትጠይቂኝ ተስፋ አደርጋለሁ” ከሚል የማበረታቻና
የናፍቆት ደብዳቤ ጋር...
ለእናትና ለእህቱ የዚህ ዓይነት ደብዳቤ ሲያዘጋጅ ለአዜብ ተሾመ የሚልክላት ደብዳቤ ደግሞ ለየት ይላል፡፡ በጦር የተወጋ ልብ ያለበት ስዕል
በአበባ የተጌጠ ስዕል..... የቀለበት ስዕል የሚሳሳሙ ፍቅረኛሞች ያሉበት ፓስት ካርድ..... ስለ ፍቅር የተጠቃቀሱ ጥቅሶች.. ስለወደፊት የትዳር ህይወታቸው መልካም ምኞት ..... የማይፃፃፉት ነገር የለም፡፡
አዜብም በፍቅርና፤ በናፍቆት፤ ሙትት ብላለች፡፡ ትንሽ ገጽ ፍቅሯን የሚገልጽላት ስለማይመስላት፤ አምስት ስድስት ገጽ አይበቃትም፡፡ሁለቱ ፍቅረኛሞች በየልባቸው ውስጥ የተተከለው የፍቅር ችግኝ እያደገና እያበበ በመሄዱ ትዳርን እንዲጠነስሱት መሠረት እየጣለ
በመሄድ ላይ ነው፡፡ እሱ ከእሷ፤ እሷም ከእሱ ሌላ ለፍቅር የተፈጠረ የለም እስከሚያስኛቸው ድረስ ተዋደዱ፡፡ በፍቅር ድር ተተብትበው..በፍቅር ሰንሰለት ተቆራኝተው... ርቀት ሳያግዳቸው፤
በመንፈስ ሳይለያዩ፧ አንድ አምሳል፤ አንድ አካል፤ ሆነው፤ በትዳር ለመኖር ምኞታቸው ገደብ አልነበረውም፡፡
ፍርድ ቤቱ ለረጅም ጊዜ ሲያከራክር ከቆየ በኋላ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ፡፡ በዚሁ መሰረት የቀጠሮው ቀን ተገልጾ ለአንዱአለም ደብዳቤ ተጻፈለት፡፡ እህቱ የተከሰሰችበት አንድ ዓመት ሙሉ
ያከራከረው ክስ የሚቋጭበት ዕለት መወሰኑን የሚገልፀው ዳብዳቤ
እንደደረሰው ልቡ ተንጠለጠለች፡፡ ምንም እንኳን በአካል ርቋት ቢገኝም፤ በሃሣብ ከሷ ሳይለያት በመንፈስ ሲጨነቅና ሲጠበብ ቆይቷልና፤ አዲስ አበባ ሄዶ ከአጠገቧ ተገኝቶ የክሱ ምዕራፍ የሚዘጋበትን የፍርድ ውሣኔ ሊሰማ ከፍተኛ ጉጉት ስለአደረሰት ጉዳዩን ለጓደኞቹ አሳወቃቸው፡፡
ምን ያክል ይጨነቅና ይጠበብ እንደነበረ የሚያውቁት ጓደኞቹም ምኞቱ እንዲሳካለት ተረባረቡ፡፡ የጠየቀው ፍቃድ እንዲሰጠው በማስተባበርና ለመጓጓዣ የሚሆን ገንዘብ በማዋጣት፤ ከጐኑ ቆሙ፡፡ ከዚያም የአውሮፕላን ቲኬት ቆርጠው......
“አድባር ትከተልህ መልካም ዜና ለመስማት ያብቃህ” ብለው
መርቀው ሸኙት፡፡አንዱአለም በዚህ አጋጣሚ የእናቱን፣ የሻምበል ብሩክ እና
የአዲስ አበባን ናፍቆት ሊወጣ፤ ከፍቅረኛው ከአዜብ ተሾመ ጋር በአካል
ተገናኝተው ፤ አድማስ የጋረደው የፍቅራቸውን ግርዶሽ ወዲያ ገላልጠው ፤
የናፍቆታቸውን ጥም ሊቆርጡ፤ በመታደሉ ጭምር ጉዞው በአንድ ድንጋይ ሶስት ወፍ ሆኖለት በደስታ ተውጦ አውሮፕላን ላይ ወጣ፡፡.....

#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳንኤል
#ቅድመ_ታሪክ
እሪ! እሪ! ይላል አምቡላንሱ። ከፊቱ ያለውን እያተራመሰ፤እየደረማመሰ በጭለማው ውስጥ እንደ ቀስት ወደፊት
ይወነጨፋል፡፡ ቦግ..እልም ቦግ...እልም የሚሉትና የሚንቀለቀሉት ቀያይ የአደጋ መብራቶቹ የሚተፉት ቀይ ብርሃን በጨረቃ የለሹ ምሽት እየተወራጨ በዝናቡ ጎርፍ በተዘፈቀው አስፋልት ላይ ሲያርፍ ዙሪያው የደም ኩሬ ይመስላል። እሪ! እሪ! እሪ! ይላል አምቡላንሱ፤ በደሙ ኩሬ ውስጥ እየተንቦራጨቀ እሪ! እንደ መብረቅ ሲወረወር በሩቅ ያዳመጡት
አሽከርካሪዎች ጥግ ጥግ ይይዛሉ፡፡ እግረኞች ከመኪናው መንገድ ይሸሻሉ
በሩቅ ቆመው በምሽት ከር ሰበርግጎ እንደወጣ ጎሽ አፍጥጠው ይመለከቱታል። ከእራት ኪሎ አቅጣጫ የመጣው አምቡላንስ መሃል ለመሃል
ተርትሯት ሲገባ ካዛንቺስ ተሸበረች።
መንገድ ዳር የቆመችው የዲፕሎማቲክ መለያ ታርጋ የለጠፈችው መኪና ፈንጂ እንደተጠመደባት ሁሉ በቅ በሕዝብ ተከባለች፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በየመኪናዎቻቸው አናት ላይ የተገጠመላቸውን ሰማያዊ መብራት "ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም እያደረጉ የደረሱት ፖሊሶች ሕዝቡን ለመብተን ይጥራሉ፡፡ ከዚህ ሲበትኑት ከወዲያ ይጠራቀማል፡፡የደንብ ልብስ የለበሱ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች ከመኪናዋ ጎን እንደቆሙ የአምቡላንሱን ድምዕ ሲሰሙ ተቁነጠነጡ፡፡ ጠና ያለው ወደ መኪናዋ ተጠጋ፡፡ በመሪው በኩል ያለው በር ተከፍቷል፤ መስታወቱ ኣስፋልቱ ላይ ረግፏል፡፡ በሹፌሩ መቀመጫ ላይ የተቀመጠው የሞሮኮው ወታደራዊ አታሼ
ወደኋላ ተንጋሎ ዐይኖቹን ገርበብ አድርጓቸዋል፡፡ በስተግራ ከማጅራቱ ስር
ጥይቱ ከገባበት ጠባብ ቀዳዳ በቀጭኑ የሚንቆረቆረው ደም ግራ ትከሻውን
አበስብሶታል፡፡ ፖሊሱ ጠጋ ብሎ አጠናው፤ ግራ እጁን አንስቶ የልቡን ምት
አዳመጠ፡፡ አለ፡፡ አልሞተም፡፡ ደም የምትረጭ ልቡ የቀራትን እንጥፍጣፊ
እየጨመቀች ትር ትር ትላለች፡፡
የአምቡላንስ አዩዬ እያቀረበ መጣ፡፡ ፖሊሱ ትከሻው ሲነካ ተሰማው፡፡ ቀና ብሎ ተመለከተ፡፡ ከጀርባው ከቆመው ጓደኛው ጋር ተያዩ፡፡በመላ ተነጋገሩ፡፡ የአምቡላንሱ ድምዕ ቀረበ፡፡ ትርትር ትላለች ልቡ፡፡ ዋይ!
ዋይ! ይላል ኣምቡላንሱ። ፖሊሶቹ ተያዩ፡፡ የተሰጣቸው ትዕዛን ቁርጥ ያለ ነው:: ጠና ያለው ፖሊስ እጁን ሰደደና ከመሪው ጀርባ ጋላል ያለውን ቁስለኛ አፍና አፍንጫ ጥርቅም አድርጎ አፈነው፡፡ ትርትር አለች ልቡ:: ትንሽ ተፈራገጠ። ትር ትር ወዲያው ዝም አለ፡፡ ቀና አዕ ፖለሱ፦ ለመጀመሪያ
ጊዜ እርጋታ እየታየበት፡፡
#ቆንጆዎቹ_ገና_አልተወለዱም።
ኤኬ አርማህ
..አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና… እሁድ ሐምሌ 21.99… ማለዳ ያነባል. በርኖሱን ደርቦ፤ አንገቱን ቀልሶ እንባውን ያወርዳል ሰማዩ፡፡ ምድርን ከምድር ሲያይ፤ሲያዝን ሲተክዝ ሲባባ፤ ሲመረው... ሰማዩ ከሰማይ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል። እረፍ አልኩ ስል በርኖሱ ይተክዛል፡፡ ዳግም ሆዱ ሲርድ... አንጀቱ ሲላወስ ሆድ ዕቃው
ሲታሰስ መንፈሱ ሲታመስ አሄሄ!… እህህ! ነፍሱ ስታቃስት ዳግም ይጀምራል ሊያለቅሰው፣ ሊያነባ…. ሰማዩ ማለዲ
ክረምቱ ጨክኗል ዓለም ምድር… ማማ..ከል ለብሳለች...ትንፋሿ ዳምኗል.. ጥላሸት? ….. እንፋሎት? ጭጋግ ነው! ባዘቶ!...
በአፓርትመንቱ ሶስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በጉም በተሸፈነው የመኝታ ቤት መስኮት ቁልቁል የሚታየው ድብዝዝ ያለ ትርኢት አላጠግብህ ቢለው እጁቹን በመጋረጃ ውስጥ አሾልኮ ቀዝቃዛውን መስታወት በመዳፉ ወለወለው፡፡ ጨካኙ ቅዝቃዜ እንደመርፌ ጠቅ አደረገው እጁን ግን አልሰበሰበም፡፡
ከመንገዱ ባሻገር ያለው መናፈሻ ጭር እንዳለ ነው... ቢሆንም.…እየነጋ ነው. ሌላ ቀን አዲስ ቀን
ባዶ እግሩን ምንጣፉ ላይ እንደቆመ ራቁት ደረቱን አከክ አከክ አደረገና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡
እንድ ሊሆን ነው አንድ አንድ ቀን፡፡
ፊቱን ወደ አልጋው መልሶ ቆመ ፡፡ እንደ ሁሌው እግሮቿን ዘና አድርጋ እጆቿን እዚያና እዚያ አመናቅራ በጀርባዋ ተንጋላ ተኝታለች፡፡ከላይዋ ላይ ተንሸራቶ አንድ ጠርዙ ከመሬት ሌላው ጠርዝ ከአልጋው መሃል የደረሰው የብርድ ልብስ ክፉኛ አጋልጧታል፡፡ የተመነቃቀረውንና የተበታተነውን አልጋ ሲመለከት ሰውነቱ ተፍታታበት፡፡
ቶሎ ብሎ ዓይኖቹን ክተጋለጠው ሰውነቷ ላይ ነቀላና ወደ መታጠቢያ ቤት አመራ፡፡
ሰውነቱን በሙቅ ውሃ ተጣጥቦ በሰፊ ፎጣ ኣካላቱን እያደራረቀ ወደ መኝታ ቤቱ ተመለሰ። ፈገግ አለ ሲመለከታት። ከእንቅልፏ ተነስታ ሰፊው አልጋ መሃል ተቀምጣለች፤ እንቅልፍ ያሳበጠው ትኩስ ፊቷ ወደ ቀድሞ ቅርጹ አልተመለሰም። ቦዛዝ ያሉ ጥቋቁር ዓይኖቿ ገና ማየት የጀመሩ አይመስሉም፡፡ ብትንትን ብሎ ትከሻና ደረቷ ላይ የተዘራው ፀጉሯ የደነበሩ መንታ ሚዳቆዎች የሚመሳስሉ ራቁት ጡቶቿን መሸፈን መሸሸግ አቅቶት
ግራ ተጋብቷል፡፡
“እንዴት አደርሽ እንዳትለኝ፡፡” አለች እንቅልፍ ባጎረነነው ድምጿ ተሽቀዳድማ፡፡
ለምን?” ፈገግ አለ፡፡
“ደህና አልልህማ! እብደት ነበር'ኮ… ናቲ ሙት እብደት ነው፡፡አንዳንደሰ ሰው መሆንህን ያጠራጥረኛል። አውሬ! " አለች ድንገት በሁለት እጆቿ ጭንቅላቷን ያዝ አድርጋ።
“አዳም ካደረገው የተለየ ምን ሳደርግ ተገኘሁ?” አለ ናትናኤል እየሳቀ፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጦ ጎተት አደረጋት። ተጎተተችለት፡፡እጆቹን በብብቶቿ አሳልፎ አቅፎ ያዛት:: ሳመችው።
“አዳም እንዳንተ ከቀበጠ ሄዋን ብትጮህም የሚደርስላት የለም ብሎ
ነው፡፡ አንተ ግን ድገመኝና አስይዝሃለው…ጎረቤቶችህን ነው የምቀሰቅስልህ፡፡”
“ሀ! ሀ ! ሀ! ጎረቤቶቼ ከእኔ ተሽለው? ርብቃ፤ ሁሉም በየጓዳው አውሬ ነው፡፡ ፊት ከሰጡት ሁሉም አንድ ነው። ፊጥ ካለበት አይወርድም፡፡”እጆቹ በአንሶላው መሀል ዋኝተው አልፈው ጭኖቿ መሃል ገቡ፡፡
“እረፍ! እየው ደሞ ጀመረህ.. ቆይ! ናቲ!”
ሳይታወቀው ተመልሶ ገባበት፡፡ ስህተት:: ዛሬ ኣልጋ ላይ መዋል የለበትም፡፡በፍጹም! ምን ማድረጉ ነው ታዲያ? ድንገት ከአልጋው ላይ ተፈናጥሮ ተነሳ፡፡ ሳይታወቀው ፕሮግራሙን አበላሽቶ ነበር። ከርብቃ ጋር አንዴ ጨዋታ ከጀመረ! ልፊያ ከቀመሰ ቀኑ እንደማይበቃው ያቀዋል።አሽትቶ፣ ልሶ፧ ገምጦ፣ አኝኮ፤ ውጦ አያጠግባትም፡፡ ድጋሚ እንደ አዲስ
ሊያሸታት ይጀምራል፡፡ ሳይወድ በግድ ራሱን ተቆጣጥሮ ፊቱን መለስና ማበጠሪያውን አንስቶ , ፀጉሩን ያበጥር - ጀመር፡፡ : እናቷን! ይቺ ልጅ ሳይታወቀኝ መዳፏ ውስጥ ልትከተኝ ነው. አሰበ።
“ለምን ተነሳህ ግን በጠዋት?" በጀርባዋ “ክተንጋለለችበት ሳትነሳ ሽቅብ እያየች ጠየቀችው::
“ቀጠሮ” በመስታወቱ ውስጥ እየተመለከታት::
“በእሁድ!”
“አዎን ርብቃ፡፡” አለ በለሆሳስ፡፡
“ምንድንነበር ያልከኝ?…አበዛኸው! ናትናኤል ሙት አበዛኸው አሁንስ የቤትህ ቁሳቁስ መሰልኩህ መሰለኝ…” አለች እንደተከፋ ሕፃን እግሮቿን አመናጭራ ከአልጋ እየወረደች፡፡ “…በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ መገናኘታችን በዛና በእሁድም ቀጠሮ ተይዝ ጀመር…አልታወቀህም እንጂ በጣም ነው የተዘባነንከው፡፡” ከእልጋው ግርጌ የተቀመጠውን ነጭ የጠዋት ልብስ ኣንስታ ሳትደርበው መሬት ለመሬት እየጎተተችው እራቁቷን የመታጠቢያ ቤቱን በር በርግዳ ገባችና ከውስጥ ጠረቀመችው፡፡ደቂቃም ሳትቆይ ጮሃ ስትሳደብ ተስማው-“አንተ ብሽቅ!... እርኩስ!…”፡፡ ብቻዋን ትጮሀለች፡፡ ፈገግ አለ የጥርስ ሳሙና የተቀባውን የሽንት ቤት መቀመጫ አስታውሶ ስትናደድ!
ስትቆጣ፤ ግስላ ስትሆን ይበልጥ ታምረዋለች፡፡ተራ ህይወታቸው ብቻ
አይደለም፥ ፍቅራቸውም ትግል ነው! ንክሻ ፤ ቡጭሪያ እሷም ብትሆን ጠዋት ጠዋት ትነጫነጭ

👍3
እንጂ ያአፈቃቀር ዘዬውን ተላምዳዋለች፡፡ጠዋት 'አውሬ ብትለውም ማታ አትፈራው ሲነጋ 'ጭራቅ ብትለውም ሲመሽ አትሸሸውም ..እላይዋ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ አልነቀል ሲላት፤እንደ ቅንቅን ፡ በሰራ አካሏ ሲፍለከለላ እንደ አልቅት
ደሟን ሲመገምግ እንደምያሌ አካሏን ሲሰረስር ! እንደምስጥ በአጥንቷ
ሲያስኬዳት ያላንተ…ትለዋለች… ሌላ ፀሐይ ስትወጣ ደግሞ ሌላ ነገ ሲተካ... አውሬ 'ሰው በላ፡፡
ቅርፅ ባለው መስታወት ፊት ቆሞ ክራባቱን ያስር ጀመር፡፡ከፊቱ፡ የተቆለለውን ቀን እንዴት እንደሚንደው እርግጠኛ አይደለም::በትክክል የት መሔድ እንዳለበት ለራሱም ግልፅ አልሆነለትም፡፡ እውነቱን ለመናገር እርሱ ሱም ቢሆን ምን ለመስማት እንደጠበቀ አያውቅም፡፡ጥያቄውን ማቅረቡ ራሱ እስቸጋሪ ነው፡፡ ቢሆንም ለጥርጣሬው አንድ መልስ እስካላገኘ ድረስ ለጥያቄው የሚያቀርበው ያልተሟላ ብቻ ሳይሆን ባዶ ቀፎ እንደሚሆን ተሰምቶታል ፡፡ የትም ይሂድ የት ብቻ ለጥርጣሬው በቂ መልስ
ማግኘት አለበት::ለዚህ ነው እሁድን
ሲሰዋ ደሟን ሊያፈስ የቆረጠው::
ጥርጣሬውን ያገነነበት የላይቤርያው ወታደራዊ አታሼ የገባበት መጥፋት
ነወ፡ በአንድ ሳምንት ሶስተኛ ጥያቄ፡፡ ሊሆን የማይችል ተራ አጋጣሚ፡፡
ስውየው ቀደም ሲልም በዚህ የስራ መደብ ላይ ለስድስት ዓመታት ሲሰራ
እንደቆየና ለኣዲስ ኣበባም እንግዳ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ ድንገት
መስርን ምን አመጣው? የላያብኤርያ ኤምባሲ ባለሥልጣኖችስ ያሳዩት
ለዘብተኝነት እንዴት ጤነኛ ሊሆን ይችላል?የወታደራዊ አታሺውን መጥፋት
ችላ ማለቱ ለነገሮች ተገቢ አትኩሮት አለመስጠት መስሎ ታየው::
በመጀመሪያ ደረጃ በሳምንቱ መጀመሪያ በአዲስ አበባ የተከሰተው የጊኒና የሞሮኮ ወታደራዊ አታሼዎች ግድያ የምን ውጤት ነበረ? የወታደራዊ አታሼዎቹ ሬሳ በተለያዩ ቦታዎች የተጣለበትን ቢሆንም በተመሳሳይ ሁኔታ በየመኪናዎቻቸው ውስጥ ነበር የተገኘው፡፡ ለሁለቱም ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑት ጥይቶች ከአንድ ሽጉጥ ለመተኮሳቸው የቀረበው ሪፖርት በዝርዝር ያስቀመጠው ጉዳይ ነው፡፡ በሬሳዎቹም ላይ የተገኙት ቁስሎችና ሌሎችም የአካባቢና የቴክኒክ, ማስረጃዎች የሚያመለክቱት በሁለቱ ሰዎች ላይ የተፈፀሙት ግድያዎች በተመሳሳይ መሳሪያ፧ በተመሳሳይ ርቀት፤ በተመሳሳይ ማዕዘን ምናልባትም በአንድ ሰው መሆኑን ነው፡፡ ያ ሰው ማነው? መልስ ሊያገኝ የቻለ ጥያቄ አይደለም:: ሳምንቱ ከመገባደዱ በፊት ደግሞ ሌላ ሁኔታ ተፈጠረ የላይቤርያው ወታደራዊ አታሼ ድንገት የገባበት ጠፋ፡፡
ታዲያ ይህን እንዴት 'ተራ አጋጣሚ ብሎ ማለፍ ይቻላል?የእርግጥ የሰዎቹ አሟሟት በየተራ ነው፡፡ ነገር ግን የናትናኤልን ጭንቅላት እረፍት የነሳው የወታደራዊ አታሼዎቹ ሞትና መሰወር ምናልባት ባለፉት ጥቂት ወራት አዲስ አበባ ከሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ኤምባሲዎች ያልተለመደ እንቅስቃሴ ጋር
ዝምድና አለው ብሎ መጠርጠሩ ብቻ አልነበረም:: ባለፉት ወራት በተለያዩ የአፍሪካ አገሮችና በአውሮፓም ያጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች ያለወትሮ በርካታ ብቻ ሳይሆኑ ምክንያተ ቢስም ነበሩ፡፡
ቢሮው ውስጥ ቁጭ ብሎ ደጋግሞ ካነበባቸው የውጭ ዘገባዎች ጥቂቶቹ
ታወሱት::
ጅብራልተር:- መጋቢት ሃይታንጂየር ከምትባል የሞሮኮ የወደብ ከተማ
ተነስታ ካዲስክ ወደምትባል
የስፔይን የወደብ ከተማ በመጓዝ
ላይ የነበረች አንድ የሞተር ጀልባ የገባበት ጠፋ፡፡ የታመነ የወሬ ምንጮች በጀልባዋ ላይ ሞሮኮው የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር በምስጢር ተሳፍረው ነበር ይላሉ፡የሞሮኮ መንግሥት ጉዳዩን በተመለከተ ያለው የለም… (ዘ ኤዲፕንደንት)
ካሜሩን:- ሚያዝያ ሁለት የአገሪቱን ኤታማዦር ሹምና የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩን አሳፍራ ከያውንዴ ወደ ዱዋላ ትበር የነበረች የካሜሩን የጦር ሄሊኮፕተር በአየር ላይ እንዳለች ስትቃጠል በውስጧ በካሜሩን የእሥራኤል አምሳደርን ጨምሮ ስድስት ባለሥልጣኖች አለቁ… (ካሜሩን ትሪቡን)
ያውንዴ:- ሚያዝያ ስምንት የካሜሩን የአየር ሃይል አዛዥ ከዋና ከተማዋ , ወጣ ብሎ በሚገኝ የገጠር ቤታቸው ውስጥ ራሳቸውን ገደሉ ተባለ፡፡ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት የጄነራሉ ቤት ለአራት ቀናት በልዩ ኮማንዶ ሃይል ተከቦ የቆየ ሲሆን የባለሥልጣኑ ስልክም ተቆርጦ ነበር… (ዴይሊ ቴሌግራፍ)
ኔፕልስ:- ግንቦት አስር-ከአልጀርስ ተነስተው ወደ ጣሊያን ያልተጠበቀ .
በረራ ያደረጉት የአልጄሪያ · መከላከያ ሚኒስትር ኔፕልስ አውሮፕላን ማረፊያ ባረፉ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ህይወታ
ቸው ባልታወቀ አሸባሪ ጥይት አለፈች…(እልሞጃሂድ)
አጋጣሚ? ይህ ሁሉ ተራ አጋጣሚ?አዲስ አበባ ውስጥ የሚፈፀመው ግድያና መሰወርስ? ይህም አጋጣሚ? ከአራት ወር በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ይህ ሁሉ አጋጣሚ?…
በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ነበር ኣለቃው ወደ ቢሮአቸው ያስጠሩት፡፡
“ደውለው ፈልገውህ ነበር።” ብላው ነበር ፀሃፊው ያን ዕለት ጠዋት አርፍዶ ቢሮው ሲገባ፡፡ ማን? አላላትም፡፡ እሱ በሚሰራበት ሁለተኛ ፎቅ ላይ
'አንቱ' ፤ እርስዎ ! 'እርሳቸው እየተባለ የሚነገርላቸው የሱ ኣለቃ ብቻ ናቸው፡፡የተረፈው በዕድሜም በሥልጣንም ተቀራራቢ ነው 'አንተ አንዳንዴም 'አንቺ ነው የሚባባለው፡
“ይሄ ጭን ይገጠም ሳምሪ።” አላት ናትናኤል ወደ ቢሮው በር ሲያመራ ፈርከክ ያደረገቻቸውን ጭኖቿን እየተመሰከተ፥
• “ተወው ባክህ እሱ የከፈተውን ሳይዘጋው አያድርም ተብሏል።” አለች ሳምራዊት ፈረግ ብላ፡፡
“አዲስ የመጣ ሪፖርት አለ?” አላት እየሳቀ የቢሮውን በር ከፍቶ
ከመግባ ፣በፊት፡፡ሁለት፡” አለችው የታች ከንፈሯን በምላሷ አርጥባ፡፡ ልማዷ ነው።
ሳምራዊት ቆንጅዬ ልጅ ነች፡፡ የምትፈልገውንና የምትመኘውን
ትዳር እንዴት ሳታገኝ እንደዘገየች ሁሌ ይገርመዋል፡፡ ምናልባት በጣም ስለምትጓጓና ስሜቷንም ስለማትደብቅ ይሆናል፡፡ ናትናኤል ገና ከጠዋቱ ነው
የሸሻት፡፡ ሌላ ወሬ የላትማ! ባል ጋብቻ ትዳር፡፡ሸሽት። ጎመን በጤና።
ቢሮው ገብቶ ከወንበሩ ላይ ከመቀመጡ በፊት ጠረጴዛው ላይ የተቀመጡትን ሁለት ; ወረቀቶች አንስቶ ዋጣቸው፡፡ የጠበቀው ነበር አንደኛው ወረቀት ስለ ልጄርያ ወታደራዊ አታሼ፤ሁለተኛው ደግሞ ስለሞዛቢክ ወታደራዊ አታሼ የቀረበ ሪፖርት፡፡ ሁሉቱም ሰዎች ወደ
አገራቸው ሄደዋል - የሰሞኑ ተደጋጋሚ ዜና፡፡
ወረቀቶቹን በነበሩቀት አስቀምጦ ለአፍታ ዓይኖቹን ቡዝዝ አድርጎ ቆመ። 'ምን ማለት ነው? ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከሰላሳ የሚበልጡ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ኤምባሲዎች የሚሰሩ ወታደራዊ እታሼዎች እየተጠሩ ወደየ አገሮቻቸው ሄደዋል፡፡ ጥቂቶቹ ሲመለሱ የተቀሩት ሌሎች ተተክተዋል። ይሁን እንጂ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ለነዚህ ሁሉ ወታደራዊ አታሼዎች መጠራት ከሚወክሏቸው መንግሥታትም ሆነ ከሌላ አካል የተሰጠ ምክንያታዊ ፍንጭ የለም፡፡
💫ይቀጥላል💫

👍2❤1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_አርባ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
በዚያን ታሪካዊ ቀን አንዱአለም ብቻ ሳይሆን ያንን የመሰለ ክፉ ንግግር ተናግሮ አእምሮዋን ያቆሰለው ዶክተር ባይከዳኝም የፍርድ ውሳኔው በሚሰጥበት ዕለት እንዲገኝ ስለፈለገች ... አዜብ ልትጠይቃት
ወህኒ ቤት ሄዳ በተገናኙበት እለት.....
“አዜቢና እግዚአብሔር ከሞት ካተረፈኝና፤
ለዚህ ካበቃኝ፤ ዶክተር ባይከዳኝም በዚያን እለት ፍ/ቤት ተገኝቶ ሸርሙጣ ያለመሆኔን ቢያውቀው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አለቻት፡፡ ይህንን ስትናገር አዜብ ትኩር
ብላ ስታያት ቆየችና ፈገግ አለች :: የአዜብ የፈገግታ ምንጭ ለጊዜው ባይታወቃትም እሷን ተከትላ እሷም ፈገግ አለች፡፡
እንዲገኝ አደርገዋለሁ” አለቻት፡፡ በእርግጠኛነት፡፡ አዜብ እንደዚያ ፈገግ ያለችውና እንደሚገኝም እርግጠኛ የሆነችው ልትሰራው ያሰበችው ተንኮል ፍጻሜው መድረሱን በማወቋ ነበር፡፡ ሁል ጊዜም የሚከነክናት ነገር በዶክተርና በሻምበል መካከል የነበረው ልዩነት ነበር።
ትህትና ልጃገረድ ያለመሆንዋን ሲያውቅ ፤ ሻምበል ፍቅሩን ያቋረጠበት ሁኔታና፤ የዶክተር ሁኔታ፤ ፍጹም የተለያየ ነበር፡፡ሻምበል አባብሎና አጽናንቶ፤ነው የሸኛት፡፡ ዶክተር ግን አዋርዶ፡ ሞራሏን ነክቶና፡ የጭካኔ ንግግር ተናግሮ ነው ያባረራት፡፡ ለዚህ ድርጊቱ ደግሞ መቀጣት አለበት
ብላ ታስብ ስለነበረ ፤ በዚያን እሷና ብሩክ ብቻ በሚያውቁት እለት ተገኝቶ እንዲቀጣ ፈለገች፡፡
በማግስቱ የካቲት አሥራ ሁለት ሆስፒታል የደረሰችው ከቀኑ አምስት ሰዓት ሲሆን ነበር፡፡ ምሽቱን ስትቀምም ያደረችውን መልእክት ይዛ፡፡ እዚያ እንደደረሰች፤ የዶክተር ባይከዳኝን የምርመራ ክፍል ጠይቃ የሚያሳያት ሰው አገኘችና ወደዚያው አመራች፡፡
ዶክተር የመጨረሻውን በሽተኛ እየመረመረ ነበር፡፡ ቀስ ብላ በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ ተመለከተች፡፡ አጠገቡ የነበረችው ነርስ ፈጠን ብላ መጣችና.....
“ምን ፈለግሽ?” አለቻት አንገቷን ወጣ አድርጋ፡፡
“ለግል ጉዳይ ዶክተር ባይከዳኝ ዘንድ ነው የመጣሁት፡፡” ስትላት ሲስተሯ ከላይ እስከታች ተመለከተቻትና “በሽተኛ እየመረመረ ስለሆነ ጠብቂ” ብላ በሩን መልሳ ዘጋችውና ሰው የሚፈልገው መሆኑን ነገረችው ::
ዶክተር ምርመራውን ከጨረሰ በኋላ፤ እንድታስገባት ለሲስተሯ ነገራትና፤ በሩን ከፍታ እንድትገባ በምልክት ጠራቻት ከዚያም አዜብ በሳቅ እየተፍለቀለቀች ፤ እራሷን አስተዋወቀችው፡፡ ዶክተርም
እንድትቀመጥ ጋበዛት፡፡ ሁኔታዋ ግር አሰኝቶታል።
“ለትንሽ ደቂቃ ብቻህን ላነጋግርህ ፈልጌ ነበር ዶክተር” አለችው፡፡
በዚህ ጊዜ ሲስተሯ የዶክተርን የስንብት ቃል ሳትጠብቅ ሹልክ ብላ ወጣች፡፡
“የትህትና ጓደኛ ነኝ” አለችው፡፡ ለምን እንደሆነ ባያውቀውም የትህትናን ስም ሲሰማ ልቡ ዘለለች፡፡ ከዚያም አንዲት የተጣጠፈችና የተቀደደች ፖስታ ከኪሷ አውጥታ፤ አቀበለችው፡፡ በፖስታው ላይ
ያለውን አድራሻ ተመለከተ፡፡ ለዶክተር ባይከዳኝ ሙሉሰው የካቲት አስራ
ሁለት ሆስፒታል ይላል ፡፡ዶክተር ነገሩ ግራ አጋብቶት፤ አይን አይኗን እያየ፤ ደብዳቤውን ተቀበላትና በልቡ የምን መልእክት ይሆን የይቅርታ ወይንስ የስድብ? ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡ ከወዲሁ መገመት አልቻለም፡፡
መልሱን የሚያገኘው ከደብዳቤው ብቻ ነው፡፡ በጉጉት ተውጦ ደብዳቤውን
ገልጦ ማንበቡን ቀጠለ፡፡ እያንዳንዷ ቃላት ተመርጣ የተጻፈች ስለነበረ፡፡ ወደ ውስጥ በዘለቀ ቁጥር የልብ ምቱ እየጨመረ ሄደ፡፡ አዜብ ራሷ ያዘጋጀችው ቀኑ ያልተጻፈበት ደብዳቤ ነው፡፡ ደብዳቤው ልክ ትህትና ለሻምበል ብሩክ የጻፈችለትን አይነት ይዘት ነበረው፡፡ እጅግ የምታፈቅረው የምትወደውና፤ የምታከብረው፤ ባለውለታዋ መሆኑን ይገልጻል ፡፡በፍቅር ስላሳለፉት ጊዜያት ጣፋጭነትም ያወራል፡፡ የመለያየታቸው ምክንያት በመቃቃር ወይንም ደግሞ በመጠላላት ሳይሆን፤ በድንገት በተፈጠረ
ችግር ምክንያት መሆኑን ያስረዳል፡፡ የጸባቸው መንሰኤ በሆነውና የምትወደውን ሰው እንድታጣ ክብረ ንጽህናዋን በደፈረው ወንጀለኛ ላይ
እርምጃ ወስዳ ለመሞት መወሰኗን ካወራ በኋላ፤ እስከ ወዲያኛው አፍቃሪ እህትህ ትህትና ድንበሩ በሚል ይደመድማል፡፡ ምንድነው
ተአምሩ? ዶክተር ግራ ተጋብቶና፤ ፊቱ ላይ ቸፍ ያለውን ላቡን እየጠራረገ፤ በአዜብ ላይ አይኖቹን አፈጠጠ...
“አይዞህ ህይወቷ ተርፏል” ስትል አረጋጋችው፡፡ ዶክተር ከድንጋጤ ሳይመለስ ቡዝዝ ባሉት አይኖቹ ሲመለከታት ከቆየ በኋላ ስለሆነው ነገር እንደ አዲስ ጠየቃት፡፡ ከደብዳቤው የተረፈውን በቃሏ ተረከችለት፡፡ ትህትና ደብዳቤውን አሽጋ በጐረቤት በኩል የላከችላት መሆኑን፡ ደብዳቤው ተቀዶ ከተነበበና፧ እጅግ ከዘገየ በኋላ፤ እንደቀላል ነገር እንዲደርሳት መደረጉን፡አሁን ትህትና ለፍርድ ቀርባ ፍርዷን
እየተጠባበቀች መሆኑንና፤ ድርጊቱ የተፈጸመበትንም ጊዜ በግማሽ
አሳጥራ በቁጭት ስትነግረው ፤ አመናት፡፡አሁን ለዶክተር ቁም ነገሩ የጊዜው ጉዳይ አይደለም፡፡ ለሱ ዋናው ቁም ነገር እውነቱን ማወቁ ብቻ ነው፡፡
ዶክተር ለመጨረሻ ጊዜ ከትህትና ጋር የተለዋወጡት መራራ ቃላት ታወሱት፡፡
ካንተ በኋላ የተዋወቅሁት ፍቅረኛዬ በክብር የወሰደው ነው” የሚለው አጥንት የሚሰብረው ንግግሯ ታሰበው፡፡አሁን ደግሞ አዜብ የምትነግረውና የላከችለት ደብዳቤ የሚያወራው ታሪክ ከዚህ የተለየ
ነው፡፡ የትኛው ይሆን እውነቱ? በእርግጥም ትህትና በግድ የተፈጸመባት
ወንጀል ነበር ወይንስ የታሰረችበት ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን?
በአጠቃላይ እውነቱን ለማወቅ፣ የክሱን መንስኤ፣ የወንጀሉን አፈጻጸምና ድርጊት ለማረጋገጥና፤ ትህትና ለፍርድ ቀርባ ውሣኔ በሚሰጥበት እለት እዚያ አጠገቧ ተገኝቶ እውነታውን ለማየት፤ ልቡ ተንጠለጠለች፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ምንም እንኳን ከተለያዩ አንድ አመት ቢሞላቸውም ሙሉ ለሙሉ ከልቡ አልጠፋችም ነበረና፤ ሄዶ ዐይኖቿን በማየት፤ የአንድ ዓመት ናፍቆቱን ለመወጣት ቸኮለ፡፡
“አልቀርም እመጣለሁ” በማለት ፍርዱ የሚሰጥበትን ቀን በማስታወሻ ደብተሩ ላይ መዝግቦ ከያዘው በኋላ ስለእናቷ ጤንነት ጠየቃት። በዘውዲቱ ሆስፒታል በተመላላሽነት በመታከምና በተሻለ
የጤንነት ደረጃ ላይ የምትገኘ መሆኗን ነገረችው፡፡አዜብ ተሰናብታው
ከወጣች በሁዋላ፤ ዶክተር በሃሰብ ፈረሱ ላይ ተጭኖ ሽምጥ ይጋልብ ጀመር፡፡ ምንድነው ይሄ ተአምር? እውነት ትህትና ድንግልናዋን ያጣችው ተደፍራ ነበር ማለት ነው? አላታለለችኝም ነበር ማለት ነው? ይሄ ሆኖ ከተገኘ በቀላሉ ሊወጣው ከማይችለው የህሊና ጸጸት ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ሲያስበው፤ ዘገነነው፡፡ ነገሩ እውነት እንዳይሆን ተመኘ፡፡ ያሳለፉት ጊዜ ትዝታው እንደ አዲስ ተቀሰቀሰበት፡፡ የዚያ
የደብረዘይቱ የማይረሳ ትዝታ መጣበት፡፡ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ እየተላፉ
እሱ በፈለገው መንገድ አንድም ቀን ተቃውሞ ሳታሰማ፤ እሱን ደስ እንዲለው ታደርግ የነበረው ጥረት፤ ጠጥታ የማታውቀውን መጠጥ እንኳ ለሱ ስትል ታደርገው እንደነበረ፡ ድንግልናዋንም በፍቅር አሳልፋ ስትሰጠው የነበረው ሁኔታዋ : ድቅን አለበት፡፡ ከራሱ ደካማነት እንጂ ከእሷ ምንም የጐደለበት ነገር አልነበረም፡፡ ያቺ ለስላሳ :ያቺ ቅልስልስ፡
ያች ስትስቅ ስትናገር፤ አፍ የምታስከፍት ትንሽ ልጅ፡ ለሱ ሁሉንም ነገር ሆናለት ነበር፡፡ እሱ ግን እንደዚያ አልሆነላትም፡፡ ቅስሟን ሰብሮ፤ ሞራሏን ነክቶ ነበር፤ እንደውሻ ከቤቱ ያባረራት፡፡ ያውም እንደዚያ የምትንሰፈሰፍላት እናቷን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትሞት የቁም መርዶ አርድቶ ነው ያባረራት፡፡ እሷ ግን ይሄውና ለሱ ስትል ህይወቷን
እስከማጥፋት የሚደርስ እርምጃ ወስዳ፤ ፍቅሯን እየገለጸችለት ነው ነገሩ እውነት

ሆኖ ከተገኘ፤ እጅግ ከባድ ፀፀት ብቻም ሳይሆን ለደረሰባት አሰቃቂ አደጋ ጭምር ተጠያቂው እሱ መሆኑንን ጭምር አእምሮው ሹክ አለው....
በዚያን የፍርድ ውሳኔው በሚሰማበት ዕለት ሻምበል ብሩክ አዜብና አንዱአለም ፀአዳ ለብሰው አምረውና ደምቀው ውሣኔውን ሊሰሙ ወደ ፍርድ ቤት ሄዱ፡፡ እናቷ ወይዘሮ አመልማል በአካል አብራቸው መሄዱ ቢያቅታትም ልቧ ተከትሏቸዋል፡፡ በተለይ ሻምበል ብሩክ ሙሉ ጥቁር ሱፍ፣ ነጭ ሸሚዝና ፍንጥቅጥቅ ውሃ ሰማያዊ ክራቫት አስሮ
ሙሽራ መስሏል፡፡ ምን አስቦ ይሆን?.....
የወንጀል ችሎት... የፍትሐብሔር ችሎት... የሥራ ክርክር ልዩ ልዩ ችሎቶች በሚመረመሩበት በህግ የሚፈተሽበት
በአንቀጽ በሚተነተንበት ጠበቆች ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው በሚሟገቱበት፡ ዳኞች በጥቁር ካባቸውን
ተጐናጽፈው፤ በግርማ ሞገስ ተሰይመው ፍርድ ወደ ሚሰጡበት አምባ.....ግማሹ ሲስቅ፣ ግማሹ ወደሚያለቅስበት፡
የፍትህ አደባባይ፤የተፈረደለት ሲፈነድቅ፤ የተፈረደበት አንገቱን ወደሚያቀረቅርበት፤ ወደ ፍርድ ቤት ሄዱ፡፡
ሶስቱ ዳኞች ካባቸውን ደርበው ከፍ ብሎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ በግርማ ሞገስ ተሰይመዋል፡፡
በችሎቱ ውስጥ ታዳሚው ግጥም ብሎ ሞልቷል፡፡ ሞልቶ ተርፎም ከደጅ ድረስ ቆሟል። አንዳንዱ ልማድ ያለው እንጂ ጉዳይ ያለው ሆኖ አይደለም፡፡ እዚያ ፍርድ ቤት ሆነው የፍርድ ቤቱን ስርዓትና ደንብ
መመልከት፣ የህግ አንቀጾችን ማጥናት፣ የጠበቆችን የክርክር ስልት መከታተል፡ አንደሱስ የሆነባቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከእነዚህ መካከል አንድ ታዳሚ ግን የፍርድ ቤቱን ደጃፍ የረገጠው ገና ዛሬ ነው፡፡
ሁለመናው አቆብቁቦ፤ በሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ተከሳ የታሰረች ወጣት
ወደ ፍርድ ቤቱ አዳራሽ የምትገባበትን ጊዜ በናፍቆት እየተጠበባበቀ ይገኛል፡፡ ደጅ ደጁን አስር ጊዜ ያያል ።ከዚያም ያ
በናፍቆት ሲጠባበቀው የቆየው ስም ተጠራ :፡ልቡ ድው፧ ድው፤ አለችበት፡፡ አይኖቹ ወደ በሩ ተወረወሩ፡፡ ከዚያም ያቺ ወጣት በአጃቢ ፖሊስ አማካኝነት ታጅባ ወደ ፍርድ ቤቱ አዳራሽ ስትዘልቅ ተመለከተ ::
አይኖቹን ማመን አቃተው፡፡ ልክ ነው፡፡ ራሷ ናት፡፡ በግራ ጆሮዋ ላይ ጠባሳ
ተጋድሞባታል፡፡ መልኳም ትንሽ ተጐሳቁሏል፡፡ አንጀቱ ተርገፈገፈ፡፡
እንባው አመለጠው፡፡ እሱ እንደዚያ
በጉጉት ተውጦ ሁኔታዎችን ሲከታተል፤ አዜብ ደግሞ ተደብቃ የሱን ሁኔታ ትከታተል ነበር :: ተንኮሏ ስለሰራላት በጣም ተደስታ ነበር፡፡ የት አባቱ! ለሰራው
ግፍ አያንሰውም እያለች ነበር፡፡ በልቧ፡፡ በኋላ ላይ ግን ይህንን ሃሳቧን የሚፈታተን ድርጊት ስትመለከት ልቧ አዘነ፡፡ እንባ ከፊቱ ኮለል እያለ ሲወርድ ተመልክታ፤ የሆነ ስሜት፤ የመጸጸት ስሜት፤ ተሰማት :: ከዚያም ተከሳሿ በተከሳሽ መቆሚያ ሳጥን ውስጥ ሆና የፍርድ
ውሳኔው መሰማት ጀመረ፡፡
ረዘም ቀላ ያሉትና ፀጉራቸውን ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት የመሐል ዳኛ የዳጎሰ አረንጓዴ ፋይል አወጡ፡፡ በዛሬው ችሎት ላይ እንደሻው በቀለ ተገኝቷል በወላጆቹ ታጅቦ ከወዲያ ማዶ ሆኖ ከወዲህ ማዶ
የተቀመጡት እነ ሻምበል ብሩክን በቀሉት ዐይኖቹ ይገረምማቸዋል።
ከዚያም ዳኛው መነጽራቸውን አውልቀው ወለወሉና ፋይሉን ገለጡ፡፡
ከሳሽ፣ ዐቃቤ ህግ
ተከሳሽ፣ ወይዘሪት ትህትና ድንበሩ
የክሱ ምክንያት ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል
ተከሳሽ ትህትና ድንበሩ፤ የጦር መሣሪያ በመያዝ፤ ወጣት እንደሻው በቀለ ከሚሰራበት የግል የንግድ ሱቅ ድረስ በመሄድ፤ በአራት ጥይቶች ተኩሳ በማቁሰል፤ የመግደል ሙከራ በማድረጓ የተመሰረተ ክስ ሲሆን፤ ለክሱ መልስና የመልስ መልስ ተሰጥቶበታል፡፡ ከሳሽ የሆስፒታል ማስረጃ፣ የፓሊስ ሪፓርትና፤ ወንጀሉ የተፈጸመበትን የጦር መሣሪያ፧
በኤግዚቢትነት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡ ምስክሮች ቀርበው ተሰምተዋል።
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ፤ ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆና በማግኘቷ
የጥፋተኛነት ውሣኔ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሽ በተመሰረተባት ክስ መሠረት የቅጣት ውሣኔ ለመስጠት እንዲያስችል፤ ዐቃቤ ህግና የተከሳሽ ጠበቃ፤ የቅጣት ማቅለያ፤ ወይንም የቅጣት ማክበጃ፤ ሃሣባቸውን እንዲያቀርቡ ተደርጐ፤ በሁሉቱም ወገን የቀረበው የመፋረጃ ሃሣብ በፍርድ ቤቱ ተመዝግቧል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ የቀረበውን የግራ ቀኙን የመፋረጃ ሃሣብ በመመርመርና፤ የወንጀለኛ መቅጫ ህጐችን መሠረት በማድረግ፤ ከዚህ የሚከተለውን የፍርድ ውሣኔ ሰጥቷል፡፡
#ፍርድ
ተከሳሽ በፈጸመችው ወንጀል ጥፋተኛ ሆና ብትገኝም፤ ወንጀሉን ለመፈጸም የተነሳሳችበትን የሞራል ተቃራኒ ድርጊት፤ የተከሳሽን የቀድሞ ስነምግባር ሁኔታ፤ የቤተሰብ ሃላፊነት ደረጃን፤ የተከሳሿን የዕድሜ ሁኔታ፤ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ እንደዚሁም፧ ተከሳሽ ከዚህ በፊት በማንኛውም የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፋ ያልተቀጣችና፤ ለወደፊቱ
ከዚህ ጥፋት ተምራ መልካም ዜጋ ልትሆን የምትችል ታዳጊ ወጣት መሆኗን በማገናዘብ፤ እጇ ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ ለሶስት ዓመት በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ቆይታ እንድትታረም ወስነን፤ ፋይሉን ዘግተን፤ ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል፡፡
ፊርማ
የመሀል ዳኛ
ጸጥ አርጋቸው ተፈራ
በውሣኔው ቅር የተሰኘ ወገን ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ውሣኔውን ለመስማት ሁሉም ፀጥ ብሏል፡፡ እያንዳንዷ እንቅስቃሴና
ኮሽታዋ ሁሉ፤ ጎልታ ትሰማ ነበር፡፡ ልብ ድው፤ ድው! ሲል ይደመጣል፡፡ ትንፋሽ በአጭር በአጭሩ....ይሮጣል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝም የፍርዱ ውሳኔ እስከሚነበብ ድረስ የልቡ ምት ፍጥነቱን ጨምሮ ነበር፡፡
በዚያች ሰዓት ለትህትና እና ከጉኗ ለተሰለፉት ወገኖቿ የዓለም እንቅስቃሴ የቆመ መስሏቸው ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ ውሣኔው ከገመቱት በጣም ያነሰ ነበር የፍርድ ውሳኔዋን ሰምታ ከተከሳሽ
መቆሚያ ሣጥን እንደወረደች፣ ፓሊሱ ከፊት አስቀድሟት ወጣ፡፡ አዜብ
ሻምበል ብሩክና ወንድሟ ፓሊሱን ተከትለው አጀቧት፡፡ ከዚያም ሄደው
አቀፏትና......
“አይዞሽ አንዱን ጨርስሻል፡፡ የቀረችሽ ሁለት ዓመት ብቻ ናት፡፡
ሁለት ዓመት ማለት ሁለት ቀን ነች” በማለት ሞራል ሰጧት፡፡
እዚያ የተሰበሰበው ህዝብ የእነሱን ሁኔታ እያየ... አይዞሽ? አይዞሽ! አይዞሽ!” በማለት የማያቋርጥ የማበረታቻ ድጋፍ እየሰጣት ነበር፡፡ ተደጋጋሚ በደል የተፈጸመባት ወጣት በመሆኗ፤ አብዛኞቹ እንደ ወንጀለኛ በክፉ አይናቸው ሊያይዋት አልፈለጉም፡፡ዶክተር ባይከዳኝም
ከፍርድ ውሳኔው ዝርዝር በተጨማሪ አጠገቡ ተቀምጦ ከነበረው ታዳሚ
አንደበት፧ ልክ አዜብ በነገረችው መሰረት፤ የወንጀሉን ታሪክ ሰምቷል፡፡ በጉልበቱ ድንግልናዋን በወሰደው ሰው ላይ አደጋ አድርሳ በራሷም ላይ ጉዳት ማድረሷን፤ እንደሻውን ጠቁሞ በማሳየት ጭምር
አረጋግጦለታል፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ ይህንን ሁሉ ካረጋገጠ በኋላ፤ እንደፈራው አልቀረም፡፡ ከባድ ጸጸት አደረበት፡፡ በዚያን ዕለት መጥፎ ስድብ በሰደባት ዕለት የነበረችው ትህትና ታወሰችውና ራሱን ወቀሰ፡፡ ትህትና በአጃቢ ፖሊሱ ታጅባ ከችሎቱ እንደወጣች፤ ፖሊሱ ከፊትዋ ቀደመና፤ ፈጠን ፈጠን፤ እያለ አስከተላት፡፡ ከሁዋላ፤ ከሁዋላው፤ ተከተለችው :: ከዚያም
እዚያ በጣም ትልቅና በጥላው ምክንያት ቀዝቃዛ አየር ከሚነፍስበት የግራር ዛፍ አጠገብ ሲደርስ ቆም አለ ፡፡ ሻምበልም ወደ አጃቢ ፖሊሱ ጠጋ አለና ጀርባውን ቸብ፤ ቸብ፤ በማድረግ ፈገግ አለ፡፡ ፖሊሱም ሰፊ ፈገግታውን ለገሰው፡፡ መልካም... ይሁንልህ ማለቱ ይሆን? :: ከዚያም ሻምበል ብሩክ ለዚህች ለዛሬዋ አስገራሚ እለት የተዘጋጀበትን፡ አስቀድሞ
ፍቃድ ያገኘበትን፡ እቅዱን ሊያጠናቅቅ፤ ወደ ትህትና ተጠጋ፡፡ ፖሊሱም በአክብሮት ፈንጠር ብሎ ቆመና ቦታውን ለሻምበል

ለቀቀ :: ፖሊሱ የሕግ ነገር ሆኖበት ነው እንጂ፤ የዛሬን እንኳን ሊለቅለት በወደደ ነበር፡፡ ትህትና የተሰበሰበውን ታማትራለች፡፡ምንም የመደናገጥና የመረበሽ ስሜት አይታይባትም፡፡ ይልቁንም በፈገግታ ተሞልታ፤ የሻምበል ብሩክን ሁኔታ እየተከታተለች ፤ ነበር፡፡ ምን ሊያደርግ ነው? በሚል ስሜት ሰው ሁሉ ሻምበል ብሩክን ያስተውለዋል፡፡ ምን ለማድረግ
እንደፈለገ እሷም ማወቅ አልቻለችም ነበር፡፡.....
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
እንደፈለገ እሷም ማወቅ አልቻለችም ነበር፡፡.....
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ከከዳኸኝ_ክህደት_ይልቅ
እሳት ረግጠን ለብሰን እሳት፣
ከላይ ሃሩር ከፊት ጥይት፣
ከውስጥ ረሃብ የአካል ዝለት፣
ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብ
ከጠላት ጋር መተናነቅ፣
ለአንድ ኢትዮጵያችን ክብር
በጥቁር አፈሯ ላይ አብረን መውደቅ፡፡
ወዲህ ደግሞ ሲኖር ፋታ፣
ከዛፍ ጥላ ስር ተቀምጠን፣
ክላሻችንን ተመርኩዘን፣
የልብ ምስጢር የምንጋራ
አላማ ያስተሳሰረን፡፡
አደዬ ወላጅ እናትህ
የእናቴን ናፍቆት የሚያስረሱኝ፣
‹ ‹ ወደይ› › እያሉ ፍቅር የሰጡኝ፣
‹ ‹ አጁሃ›› ብለው ያበረቱኝ፣
ቋንቋህን መልመድ ተስኖኝ
እያበሸቅክ ያግባባኸኝ፣
አንተ ማለት የልቤ ሰው
የመወለድን ቋንቋነት
ወንድም ሆነህ የነገርከኝ፡፡
‹ ‹ ምድራዊ ፈተና በዝቶ
ዙሪያው ቢነድ በገሞራ፣
ጥሰነው እናልፈዋለን
የማይሞት ታሪክ ልንሰራ› ›
እያልን የዘመርን በጋራ፣
‹ ‹ የማንጨበጥ ነበልባል
እሳት ነን ለጠላታችን፣
ፍሙ ከርቀት ይፋጃል
ብረት ያቀልጣል ክንዳችን )
ብለን በወኔ ያዜምን፣
እኔና አንተ አንድ ነበርን፡፡
ጓዴ.......!
ካንተ ቀድሜ ፈንጂ ልረግጥ
ነብሴን ልሰጥህ የማልኩብህ፣
ምን ያህል አምኜህ ነበር
ጭምብልህን ገልጩ ያላየሁህ?
የቀበሮው ጉድጓድ ወንድሜ
አንተ የክፉ ቀን ጓዴ፣
ሃገሬን በጎጥ ሸጠሃት
ቃታ መሳብክን ልመን እንዴ?
በግፍ ጥለኸኝ እያየሁ
ለአሞራ ሲሳይ ስትሰጠኝ፣
በሬሳዬ ላይ ስትጨፍር
እፍኝ አፈር እንኳ ነፍገኸኝ
ቀርጥፈህ ከበላኸው ቃል በላይ
ከከዳኸኝ ክህደት ይልቅ፣
እመነኝ እጅግ ያመኛል
አንድ ጥያቂ ባልጠይቅ፡፡
ጥያቄዬ...!
ይሄ ሁሉ የግፍ መዓት
ባኖርኳችሁ ላብ ገብሬ፣
ምን አጎደልኩኝ ንገረኝ
ምን በደለችህ ሃገሬ?
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
//መታሰቢያነቱ በጁንታው በግፍ ለተገደሉት የሰሜን እዝ አባላት//

#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....አዜብና አንዱአለም አጠገቡ ናቸው፡፡ ከኪሱ ውስጥ የሆነ ነገር አወጣ፡፡ በትንሽ የፕላስቲክ ሳጥን ውስጥ የተቀመጠች..ውድ ነገር:: በመጠን በጣም ትንሽ፤ በቁም ነገር ግን እዚያ እላይ!! ቀለበት. የቃል ኪዳን ቀለበት ... ስለ እውነተኛ ፍቅር የተዘጋጀች ፤ የትዳር መጠንሰሻ:
የቃል መተሳሰሪያ፤ ቀለበት... በምህጻረ ቃል የሱና የሷ ስም የተጻፈበትን
ቀለበት አወጣና......
“በመንፈሰ ጠንካራነትሽ ለሰጠሽኝ ትልቅ ትምህርት፡ ለእውነተኛ ፍቅር ስትይ ለከፈልሽው መስዋዕትነት፣ በታማኝነት ፀንተሽ ኣብረን ለቆየንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ማስታወሻ እንድትሆን፡ ይህቺ ሁለት ዓመት ለቀሪ ህይወትሽ ትምህርት የምታገኝበት፣ እኔ ደግሞ ለሠርጋችንም ሆነ ከሠርጋችን በኋላ የትዳር ህይወታችንን በሰላም ለመምራት እንዲያስችለን የምዘጋጅበት እንዲሆንና፤ የማረፊያ ቤት ቆይታሽ፤ መጪውን ብሩህ
ተስፋ አሻግረሽ የምትመለከችበት የዕረፍት ጊዜ እንዲሆንልሽ በመመኘት፤
ያዘጋጀኋትን ገፀ በረከት፤ ይህችን የቃል ኪዳን ቀለበት፣ እንድትቀበይኝ” አለና ከጉልበቱ በርከክ ብሎ ሽቅብ ተመለከታት፡፡ ከዚያም ፍዝዝ ባለችበት
እንባዋ ጉንጮቿን እያቋረጠ፤ ቁልቁል መውረድ ሲጀምር፤ ቀልጠፍ ብሎ
የግራ እጇንና ቀለበቷን ወደ ላይ ከፍ አደረጋቸው፡፡
ከዚያ የከበበው ሰው በሙሉ በደስታና በሆታ አጨበጨበላቸው፡፡ ዕልልታውን አቀለጠላቸው፡፡ አንዱዓለምና አዜብ ተቃቀፉ፡ ሚስጥሩን የምታውቀው አዜብ ብቻ ነበረች፡፡ ቀለበቱንም የመረጠችለት እሷ ናት።
ለአንዱአለም ግን ሁኔታው ድንገተኛ ነበር፡፡ በፍርድ ቤቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ ሌላ ተዓምር፡፡ ቃል ኪዳን ......ከዚያም
ቀለበቷን በጣቷ ውስጥ ሲያጠልቅ፤ አዜብና አንዱአለም በደስታ ሲቃ ተውጠው፤ እልልታቸውን፤ አቀለጡት፡፡
ያቺን ቀለበት በዚህ በዛሬው ዕለት ሊያደርግላት የወሰነበት ምክንያት ነበረው፡፡ ይህቺ የውሣኔ ዕለት፣ ይህቺ የፍርድ ቀን፡ በነፃ የምትለቀቅበት ሳይሆን፡ የህግ እስረኛ ሆና በማረፊያ ቤት እንድትቆይ የሚወሰንበት ዕለት መሆኗን አስቀድሞ ስለሚያውቅ፣ በዚህች ቀን የህግ እስረኛ በመሆንዋ፤ የመገለል ስሜት እንዳይሰማትና፤ የሞራል ውድቀት
እንዳይደርስባት፣ መታሰር ማለት፤ ከዚህ ዓለም መገለል ማለት ያለመሆኑን ተረድታ፤ በጥንካሬና በጽናት የእስር ዘመኗን እንድትጨርስ ለማድረግ፣ በዚያች የውሣኔ ዕለት፤ እስረኛ ብቻ ሳትሆን፤ የታጨች ሙሽራ መሆኗን ጭምር እንድታውቅ፣ የህይወት አጋር ፤የትዳር
ጓደኛው ! ከሷ ሌላ ማንም እንደሌለው ሊያረጋግጥላት፡፡ ሊያበረታታት፡፡
ስለወሰነ፤ የቀለበት ስነ ሥርዓቱን ባልጠበቀችው በዚያ ሁኔታ ሲፈጽምና
ቀለበቷን በጣቷ ላይ ሲያኖርላት፣ በደስታ ሲቃ ተውጣ፣ እስረኛ መሆኗን ፍጹም ረስታ፤ በሳቅ እየተፍለቀለቀች፣ ሻምበልን አንገቱ ላይ ተጠመጠመችበት፡፡ ሻምበል አደራውን ተወጣ! የፈራረሰ በድን አካሏ በወደቀበት ስፍራ በመቃብሯ ላይ ሳይሆን፤ ያቺን ውብ የፍቅር ጽጌረዳ
አበባ፤ አለንጋ በሚመስለው የቀለበት ጣቷ ላይ እና፤ በፍቅሩ ምክንያት ታላቅ ጉዳትና ስብራት በደረሰበት ልቧ ውስጥ በክብር አስቀመጠላት ::
ዶክተር ባይከዳኝ በዚያ በሚያየው ነገር ተደናግጦ እና ተገርሞ አፉን በሰፊው ከፍቶ በመቅረቱ ምክንያት፤ እጆቹን ማራገብ እንኳ ተስኖት!በተከፈተው አፉ
ውስጥ ይመላለሱ የነበሩ ዝንቦች ፤ ያለከልካይ ተዝናኑበት፡፡ ከዚያም እንደምንም ብሎ ከሰመመኑ ሲመለስ፤ የሆነ የቅናት መንፈስ ሰውነቱን ውርር አደረገው :: ያንን ያልጠበቀውን
ትእንግርት እያየ፤ አፉን ከፍቶ በቀረበት ቅጽበት ሌላ ነገር ተደገመ
“እኛ ደግሞ ለዛሬ የወርቅ ቀለበት ያላዘጋጀን ቢሆንም፧ ልክ አንቺ ከማረፊያ ቤት ወጥተሽ፤ የጋብቻ ስነ ስርዓታችሁን ስትፈጽሙ ፤
እኔና አዜቢና ደግሞ፧ የቃል ኪዳን ቀለበታችንን የምናስርበት ዕለት
ለመሆኑ ማረጋገጫው፤ የቃል ኪዳን ማህተሙ፤ ይኸው!” አለና ወንድሟ
አዜብን፡ የምታፈቅራት ጓደኛዋን፡ ወደ ደረቱ ሳብ፤ እቅፍ፤ አድርጉ አንገቷን ቀና በማድረግ፤ ከንፈሯን ግጥም አድርጎ ሲስማት፡ ይህ ሁሉ ተአምር በፍጹም ያልጠበቀችው ነበርና፤ ትህትና ከደስታዋ ብዛት የምትሆነውን አጣች፡፡ ያቺ ከልጅነት እስከ እውቀት፤ በሀዘንና፤ በችግሯ
አንድም ጊዜ ተለይታት የማታውቅ፤ እንደነፍሷ የምትወዳት ጓደኛዋ፤
ይሄውና የወንድሟ ሚስት ልትሆን፡ የሚወልዱዋቸው ልጆች የአክስቴ ፡
የአጎቴ፡ ልጅ ሊባባሉ ነው፡፡ የጓደኝነት ፍቅራቸው ወደ ስጋ ዝምድና ሊሸጋገር ነውና፤ አልቻለችም፡፡እንባዋ በድጋሜ ኮለል ብሎ ሲወርድ አሁንም ህዝቡ
ጭብጨባውን አቀለጠላቸው......
በሚያየው ተደጋጋሚ ትርኢት ተደንቆ፤ በሳቅ እያውካካ ዶክተር ባይከዳኝ ከህዝቡ ፈንጠር ብሎ ቆሞ ነበር፡፡ ያንን ሁሉ ትርኢት ተመልክቶ ካበቃ በኋላ ግን፤ የቅናት ስሜቱ እየተገፈፈ ሄዶ፤በምትኩ የደስታ ስሜት ይሰማው ጀመር፡፡ ምንም እንኳ የዛሬው የሻምበል እድል የሱ እንደነበረ ቢሰማውም፤ በራሱ ጥፋት እድሉን አበላሽቷልና፤ ይህቺ ለሱ ፍቅር ስትል ትልቅ ዋጋ የከፈለች ቆንጆ ልጅ
ከዚያ ሁሉ ችግር በኋላ ከጐኗ ቆሞ አይዞሽ የሚላት አጋር በማግኘቷ
ተደሰተ :: ትህትና ምንም በደል ያላደረሰችበት ልጅ መሆኗን ህሊናው
ደጋግሞ ስለጨቀጨቀው ይቅርታ ሊጠይቃትና እንኳን ደስ አለሽ ሊላት
ፈለገ፡፡ ከዚያም ጠጋ አለና.....
“ለተፈጸመው ስህተት ሁሉ አዝናለሁ፡፡ ላደረስኩብሽ በደልም ከልብሽ ይቅርታ እንድታደርጊልኝ እለምናለሁ :: በሰላም የእስር ዘመንሽን እንድትጨርሺና! መልካም የቀለበት ስነ ስርአት እንዲሆንልሽም ከልብ እመኝልሻለሁ
አላት፡፡
አንተም ፈቃደኛ ሆነህ እዚህ በመገኘትህና እውነቱን በማወቅህ
እኔም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ አመሰግንሃለሁ፡፡ ያለፈውን ሁሉ
እረስቼዋለሁ፡፡ላንተም መልካሙ
ሁለ እንዲገጥምህ እመኝልሃለሁ፡፡ አዲስ ቀን ይመጣል : አዲስ ህይወት ይቀጥላል.በማለት አጸፋውን መለሰችለትና፣ ሻምበልን አየችው፡፡ ሻምበልም አያት::ከዚያም ሶስቱም እርስ በርሳቸው ተያይተው ፈገግ ሲሉ፤ አዜብም
ዶክተር ባይከዳኝን እያየች ፈገግ አለች፡፡ ሰራሁልህ ማለቷ ይሆን?
ለጊዜው ቢደብቋትም፤ ውሎ እያደር ለቅሶዋ ቢበዛና ውትወታዋ ቢያስጨንቃቸው፤ እውነቱን ነገሯት፡፡ እንደፈራችውም ልጇ በጤናዋ
እንዳልጠፋች ካወቀች ዕለት ጀምሮ፤ በበሽታዋ ላይ ሌላ በሽታ ተጨመረባት፡፡ ትህትና ከሆስፒታል ድና ብትወጣም እስር ቤት መግባቷን ሰማች፡፡ መርዶ... ትንሹ ልጇ አንዱአለም ደግሞ በእንጭጭነቱ ተለይቷት ለመሄድ መዘጋጀቱን ሰማች፡፡ ሌላ የልብ ስብራት... ያንን የምትወደው ባለቤቷን የነጠቀባት ጦርነት፤ አሁን ደግሞ ሮጦ ያልጠገበ አንድ ፍሬ ልጇን እንዳይነጥቅባት በሥጋት ተውጣ፤
ጠዋትና ማታ እዬዬ ብቻ ሆነ፡፡ሁለቱንም አለኝታዎቿን ከጐኗ ስታጣቸው፤ የወላድ መካን የሆነች መሰላት፡፡ ትህትና ከሆስፒታል ከወጣች በኋላም እቤቷ እንድትገባ ሳይሆን፤ ፍርድ ቤቱ በማረሚያ ቤት እንድትቆይ መወሰኑን ስትሰማ
ከዛሬ ነገ በነፃ ትለቀቅልኛለች ብላ በጉጉት እየተጠባበቀች ጭል፤ ጭል፤ትል የነበረች ተስፋዋ ድርግም ብላ ጠፋች፡፡
ይህ የጨለማ ህይወት ፍጹም ልትወጣው የማትችለው ሆነባት።የቤት ሰራተኛዋ እታፈራሁ የልጅ ያክል ብትንከባከባትና፤ ሻምበል ብሩክና አዜብም ልጆቿን ሊተኩላት ከጐኗ ሳይለዩ
ደፋ ቀና ቢሉም፤ሳይሆንላቸው ቀረ፡፡
ከዚህ በኋላ በሽታው በአንድ ወገን፤ የልጆቿ ናፍቆት በሌላው ወገን ሆነው፤ እየተጋገዙ፤ ስጋዋን እኝከው በመጨረስ፤ የሞት ድግሷን ያፋጥኑት ጀመር..
ትህትና ማረሚያ ቤት በቆየችበት ጊዜ ብቸኝነት፣ መታከት ተስፋ መቁረጥና

ናፍቆት፤ እነኝህ ሁሉ እያሰቃዩዋት፤ ልጆቼን፡ ልጆቼን እንዳለች፣ እንዳለቀሰች፣ ያቺ የቆንጆዎች እናት ቆንጆዋ አመልማል
ለመሆኗ ምልክቱ እንኳ ጠፍቶ፣ ገላዋ መንምኖና አልቆ ፤ በአጥንትና ቆዳ
ብቻ ከቀረች በኋላ፤ ልጂ ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት በእስር ቤት
እንደምትቆይ የመወሰኑን አሳዛኝ ዜና ሰምታ፤ ፍርዱ በተሰጠ በአራተኛው ወር ላይ፤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስትንፋሷ ቆመ፡፡
ዳግም በዐይኗ አይታቸው ናፍቆቷን ሳትወጣና ሳትሰናበታቸው፤ ከዚህ ዓለም በሞት ተሰናበተች......
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
ለመሆኗ ምልክቱ እንኳ ጠፍቶ፣ ገላዋ መንምኖና አልቆ ፤ በአጥንትና ቆዳ
ብቻ ከቀረች በኋላ፤ ልጂ ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት በእስር ቤት
እንደምትቆይ የመወሰኑን አሳዛኝ ዜና ሰምታ፤ ፍርዱ በተሰጠ በአራተኛው ወር ላይ፤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስትንፋሷ ቆመ፡፡
ዳግም በዐይኗ አይታቸው ናፍቆቷን ሳትወጣና ሳትሰናበታቸው፤ ከዚህ ዓለም በሞት ተሰናበተች......
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
😁1
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
ናትናኤል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተመድቦ ሲሰራ ስምንት ዓመት ሆኖታል። በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን እንደያዘ የተመደበው
አሁን በሚገኝበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ ጉዳይ በተለይ በምዕራብ አፍሪካ ክፍል ነበር። ለአራት ዓመታት ካገለገለ በኋላ ወደሰሜን አፍሪካ
እንዲዛወር ተደረገ፡፡ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ የአእምሮውን ፈጣንነት
የተገነዘቡ አለቆቹ የአፍሪካ ጉዳይ ምክትል ኃላፊ አድርገው ባይሾሙትም
ቢሮውንና ጠረጴዛውን ጭነው እየጋለቡት ነው፡፡
አእምሮው እውነትም ፈጣን ነው፡፡ አዳዲስ ሁኔታዎች ቶሎ ይገቡታል፡፡ አንዳንዴም የመቸኮል ባህሪው እልህ ውስጥ የሚያስገባውም ቢሆን
የነገሮችን ሂደት የመከታተል ትዕግሥቱ ያመዝናል፡፡አስተሳሰቡ ቀናና ቀጥተኛ ነው። ጠማማ መስመሮች ካጋጠሙት
በጠማማ መስመር መሄድም አያቅተውም ልብ ብሎ የተከታተለውን ጉዳይ እዳር ሳያደርስ ሰላማዊ እንቅልፍ የማያገኝ መሆኑ ደግሞ ዋናው ባህሪው ነው፡፡ናትናኤል ፍቅር አዋቂ : የመሆኑን ያህሎ ቶሎ የሚወድቁለትን አፍቃሪዎቹን ሰብዓዊ አመለካከት : የሚነፍግ አይደለም፡፡ እርግጥ አንዳንዴ ዓላማውን
ሲያዘናጉት ፀፀት ላይ ይወድቃል፡፡ ሆኖም ሰብዓዊነቱም ቆራጥነቱም አይከዱትም:: መልኩ መልካም ነዉ የቀይ ዳማ-ረዘም ያለ፡፡
ባለፋት ስምንት ዓመታት ውስጥ ይህን ያህል የተቸገረበት ጥያቄ! ሊዘለው ያልቻለው ዲብ አላጋጠመውም። የሰሞኑን ሁኔታ ግን ትርጉም ሊስጠው ተቸግሯል፡፡ በየአቅጣጫው ከተሰማሩ ቢሮዎች የሚመጡ ሪፖርቶች የሚሉት ነገር ቢኖር የዚህ - አገር ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ወደ አገሩ ተጠርቶ ሄዷል' የዚያኛው አገር ወታራዊ አታሼ ወደ አግሩ ተጠርቶ ከሄደ በኋላ በምትኩ እገሌ የሚባል ሰው ተተክቷል አለቀ።
በጠፈጴዛው.ላይ የተቀመጠው ቀይ የውስጥ ስልክ ሲጮህ ከሄደበት የሃሳብ ጉዞ ተመለሰ፡፡
“ይፈልጉሃል፡፡” ኣለችው ፀሃፊው፡፡
“ይፈልጉሃል” እሳቸው አለቃው ቦርጫሙ አለቃው:: ከጠረጴዛው ላይ ማስታወሻ ደብተሩንና ብዕሩን ይዞ ከቢሮው ወጣ፡፡
“ኖር! ኖር!” ከተቀመጡበት ለመነሳት ሳይሞክሩ በትትና ተቀበሉት::
“እንደምን አደሩ፡፡” አለ በአክብሮት፡፡
ከአፋቸው: ላይ የማይለየው የፒፖቸው :: ጠረን ክፍሉን አጨናንቆታል፡፡ ለምን እንደሆነ ባይገባውም ናትናኤል ቆዳ ቆዳ የሚለውን ትንባሆ ጠረን ይወደዋል፡፡ ቢሮአቸው አለቅጥ ሰፊ ነው:: ከጀርባ በስተቀኝ በኩል ያሉት ሰፋፊ መስኮቶች የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንን ውብ ህንፃ በሩቅ ያሳያሉ፡፡ በስተግራ ከግርግዳው ጋር ሊስተካከል ጥቂት የቀረው ሰፊ የአፍሪካ ፖለቲካዊ ካርታ ተዘርግቷል፡፡ በስተቀኝ የቢሮ ውስጥ ስብሰባ ማካሄጃ ጥቁር ጠረጴዛና በዙሪያውም አስራ ሁለት ወንበርች አሉ፡፡ በሰፊው ክፍል ከጥግ
እስከ ጥግ የተንጣለለው ቀይ ወፍራም ምንጣፍ የአለቅየውን ቢሮ ቁጡ
አስመስሎታል፡፡
ቁጭ በል! ቁጭ በል!” አሉ ወፋፍራም ጣቶቻቸውን ጠረጴዛቸው ፊት ለፊት ወደ አንደኛው ጥቁር የቆዳ ፎቴ ዘርግተው፡፡
ተቀመጠ፡፡
“ትናንት የሞሪቴንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የመካከኛውን ምሥራቅ በተለይ የአረቦችን እንቅስቃሴ በተመለከተ የተሰጠውን የሬድዮ ቃለ ምልልስ ሪፖርት አየኸው?” አለቃው በቀጥታ ወደ ቁም ካገሩ ገቡ፡፡
ሰውየው ሃይለኛ አንባቢ ናቸው፡፡ ያነባሉ ሳይሆን ያጋብሳሉ ማለት ይቀላል፡፡ በአፍሪካ ጉራንጉር የተፈጸመው ሁሉ እሳቸው ትላንት ማታ ያነበቡት
“እ… እ… አላየሁትም፡፡” አለ ናትናኤል እንደማፈር ብሉ፡፡
አንብበው! አንብሰው! እጅግ እስራሚ ነው... ሰሜን አፍሪካ አረባዊት ወይስ አፍሪካዊት? በሚለው ሃሳብ ላይ በሳል አስተያየት ሰንዝሯል ሰውየው፡፡ ትዝ ይልሃል..ከጥቂት ዓመታት በፊት በሞሪቴንያና በሴንጋል መሃል ተፈፅሞ በነበረው መቃቃር የአረቦችና የአፍሪካውያን ቅራኔ ናሙና ነበር ወይ?' በሚለው ጥያቄ ላይ አስገራሚ ሃሳብ አለው አንብበው...” እሱ ከጠረጴዛቸው የተለያዩ ወረቀቶች እያነሱ እየጣሉ፡፡ “... በአፍሪካ ጓዳ እያንዛረጡ የአፍሪካን ቀዝቃዛ ውሃ እየተጐነጩ ባዳ ነን ለሚሉ እስስቶች ጥሩ መልዕክት ይዟል አሁን እንኳን የፈለግሁህ ለዚህ ሳይሆን ሰሞኑን
በተደጋጋሚ ስለሚመጡ ሪፖርቶች ጉዳይ ነበር፡፡” አለቃው የፈለጉትን ወረቀት ያጡ ይመስል ጠረጴዛቸው ላይ የተከመረውን ሰነድ ያምሱት ጀመር።
ናትናኤል ለምን ወደ ቢሮአቸው እንዳስጠሩት ገባው፡፡ ስለወታደራዊ
አታሼዎቹ ጉዳይ መሆን ኣለበት።ሰሞኑን በተደጋጋሚ የሚመጡ ሪፖርቶች
የሚፅፉት” ያንን ብቻ ነው። ቢሆንም እርሳቸው ራሳቸው እስኪነግሩት
በትዕግሥት ተጠባበቃቸው፡፡
“አዎ” አሉ ፈልገው ያገኙትን ወረቀት ከፊታቸው ራቅ ኣድርገው ይዘው የማንበቢያ መነጽራቸውን በወፍራም አፍንጫቸው ላይ እያስተካከሉ፡፡
“…ነገሩን እንኳን አንተም ሳትታዘበው እንዳልቀረህ እርግጠኛ ነኝ ኣሉ ቀና
ብለው እየተመለከቱት፡፡ “ባለፋት ሶስት ወራት ብቻ በአፍሪካ ኤምባሲዎች
የሚሰሩ ሰላሳ ስድስት ወታደራዊ አታሼዎች ወደ አገራቸው ተጠርተው
ሄደዋል፡፡”
“ሰላሳ ስምንት“ አለ ናትናኤል ከተቀመጠበት ወንበር ላይ እየተመቻቸ፡፡ “ከቀድሞዎቹ በተጨማሪ ትናንት የአልጀሪያና - የሞዛምቢክ ወታደራዊ አታሼዎች ተጠርተው ወደ የአገሮቻቸው ሄደዋል፡፡” .
በጣም ግሩም” ኣለቃው ፈገግ አሉ፡፡ ይህ ነው የሚያረካቸው፡፡ ፈጣንነቱ ፤ ቀልጣፋነቱ፣ የሚያስበትን ቀድሞ አስቦ መገኘቱ፡፡ “ጉዳዩን ተከታትለኸዋል ማለት ነው፡፡'እሉ የያዙትን ወረቀት ወደ ጎን እያስቀመጡ፡፡
“ኣዎ” አለ ናትናኤል እያመነታ እርግጥ ሪፖርቶቹን በመሉ በጥንቃቄ ተመልክቻቸዋለው፡ ፡ ሆኖም
በሁኔታው ትርጉም ሊያገኝበት
አልቻለም፡፡
“እንግዳ `አልሆነብህም? ፒፓቸውን አንስተው ከውስጥ ያለውን አመድ በነሃሱ የሲጋራ መተርኮሻ ውስጥ እያራገፉ ጠየቁት፡፡
“እርግጥ…" ናትናኤል ግራ ተጋባ፡ ሁኔታው ለማንም ቢሆን እንግዳ ነው:: ማን…”
“
አዎ እንግዳ ነው” አሉ አለቅየው ሃሳቡን የተረዱ ይመስል ሽበት የተንጠባጠበበትን ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ፡፡ “ከአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ
ጋር የተገናኘ ምክንያት ይኖረዋል ትላለህ?” ፒፓቸውን እየጠቀጠቁ ጠየቁት::
“እ" ጭንቅላቱን በፍጥነት ለማስራት ሞክረ፡፡
“አዎ አስቸጋሪ ነው ለመናገር ፒፓቸውን አፋቸው ውስጥ ሻጥ አደረጉና የጫሩትን :: ክብሪት አስጠግተው ማግ... ቡልቅ ማግ. ቡልቅ እያደረጉ አያይዘው ሲያበቁ ያያዛትን እሳት ሳያጠፉ ክብሪቱን በጥንቃቄ በመተርኮሻው ውስጥ አስቀመጡና “ናትናኤል እስቲ አንድ መላምት ላይ ለመድረስ ሞክር፡፡” . ነበር ያሉት የአለቃ ሳይሆን የባልደረባነት ቃና ባለው ድምፅ፡፡
።።።።።።።።።።።።
“አንተ ብሽቅ! እንትኔን በኮልጌት አጨማለቅኸው አይደል.… እናቴ
ትሙት ብድሬን ባልመልስ! ለመሆኑ ከማን ጋር ነው ቀጠሮህ?” እለች ርብቃ!
እየሳቀች ከመታጠቢያ ቤት ወደ መኝታ ክፍሉ እየገባች፡፡
“እኔም ራሴ እርግጠኛ አይደለሁም ርብቃ” አለ ናትናኤል፡፡ “እውነቱን ለመናገር ቀጠሮ ማለቴ እዚያው በየቢርአቸው እየሄድኩ የማነጋግራቸው ሰዎች ናቸው፡፡” አላት፡፡
“ይሻላል ማን በእሁድ ቢሮው ይገባልሃል? የማይመስል ነገር ለእንትንህ አትንገር፡፡” አለች ሌሊቱን በርቶ ያደረውን የራስጌ መብራት እያጠፋች::
“ሙች እውነቴን ነው፡፡”
“ተው እንጂ ናቲ እንደምትታመን ሁን፡፡”
“ይልቅ አሁን ተይውና...” አለ ናትናኤል ክርክሩ እንደማያዋጣው ሲረዳ ቁጢጥ ብሎ የጫማውን ክር ከሚያስርበት ተነስቶ
ጉንጭና ጉንጯን በሁለት እጆቹ ይዞ እያባበላት። “ማታ እንገናኝና…”
“እ! ኣ! ኣ!” -

👍5
አቋረጠችው፡፡ "ስንት ጊዜ ልንገርህ እሁድ ሌሊትን ማሳለፍ ምፈልገው ተኝቼ ነው፡፡ ሰኞ ጠዋት ስራ ገቢ ነኝ፡፡ ገባህ? ካንተ ጋር ማደር አልችልም::”
እራት እጋብዝሽና ቤት አደርስሻለሁ፡፡”
ተንጠራርታ ቅንድቡን ሳመችው፡፡
ወደ ማዘጋጃው ክፍል ገባ ብሎ ከማቀዝቀዣው ውስጥ የጠርሙስ ቢራ አወጣና በቁሙ ወደ ሆዱ ደፋው...ቁርስ፡፡
የአፖርትመንቱን ጠመዝማዛ ደረጃዎች በሩጫ ወረዳቸው። ወደ ውጭ የሚያስወጣውን መስታወት በር ገፋ አድርጎ ሲወጣ ቁና ቁና እየተነፈሰ ነበር፡፡ የውጭው ብርድ ሰውነቱን አቆራመደው:: የመኪናውን በር ከፍቶ ከመግባቱ በፊት ቀና ብሎ ተመለከተ። የመኝታ ቤቱን መጋረጃ ወደጎን ሰብሰብ አድርጋ ቁል ቁል ትመለከተዋለች፡፡
እጁን አውለበለበላት፡፡ ጠጋ ብላ ከንፈሮቿን ቀዝቃዛው መስታወት ላይ አሳረፈቻቸው! ሳመቻቸው በስሜት ከራሱ ጋር እየተከራከረ የመኪይ በር ከፍቶ ገባ፡፡
''ግን ለምን?”
መኪናውን አስነስቶ ከአፖርትመንቱ ግቢ ወጣ፡፡ ከጎኑ ተሰባጥረው ከተደረደሩት የሙዚቃ ክሮች እንዱን አነሳና ማዘፈኞው ውስጥ ከተተው፡፡ለስላሳ ሙዚቃ፡፡ ወደ ቀኝ ታጥፎ ወደላይኛው ቤተመንግሥት አቀና።
ግን ለምንድነው ስሜቱን የሚደብቃት? መውደድን አምኖ መቀበል ደካማነት ነው እንዴ? ከአንቺ ስለይ አእምሮዬ ይረበሽ ጀምራል፤ ካንቺ ተለይቼ ሳድር ብስጭትጭት ያደርገኝ ጀምሯል ብሎ ተሸናፊነትን መግለጽ ደካማነት ነው እንዴ? ለምንድነው ዛሬም እንደ ድሮው ቀዝቃዛና ግድ የለሽ መስሎ ለመቅረብ የሚጥረው? ወደደም ጠላ የድሮው አይደለም:: ርብቃን ካገኘ ወዲህ ከቀን ወደ ቀን የገዛ ራሱን ለውጥ ተገንዝቦታል:: ታዲያ ተሸነፍኩልሽ ወደድኩሽ ብሎ ማለቱ ምኑ ላይ ነው ስህተቱ? የመኪናውን ቤንዚን መስጫ አጎነው።
በመናፈሻው ውስጥ ተሰባጥረው በተተክሉት ዛፎች መሃል ገባ፡፡ ሽሽግ ብላ ቆማ የነበረች ጥቁሩ 504 ፔጆ በእርጋታ ተነስታ - በርቀት ከጀርባው ስትከተለው አላስተዋለም፡፡
ለምን እንደምትወደው ፍጹም አያገባትም፡፡እርግጥ መውደድ
ያውቃል፥ ከዛ ውጪ ግን በሰዎች ልብ ጓዳ ውስጥ የሚፈላና የሚገነፍል የሚንተከተክ : ትኩስ : ስሜት እንደሌለው ከተረዳች ቆይታለች፡፡ ግን ትወደዋለች፡፡
“ብሽቅ!”
ወደጎን ሰብስባ የያዘችውን የመኝታ ቤቱን መጋረጃ ለቅቃ ወደ ምግብ ማዘጋጃው . ክፍል ገባች። በአራት ማዕዘን ቆርቆሮ ውስጥ ከተቀመጠው የቡና ዱቄት ሁለት ማንኪያ ቀንሳ ጀበና ውስጥ ከጨመረች
በኋላ በላዩ ላይ አንድ ብርጭቆ ውሃ ከለሰችበትና ምደጃ ላይ ጣደችው::
ውሃው እስኪፈላ ማን ይጠብቃል… አብረው ይንተክተክ ዳቦ በስሱ መቁረጥ
ጀመረች፡፡
ቁርስ ትወዳለች:: በተለይ ክዚያ አወሬ ያደረች ሌሊት ደንደን ያለ ቁርስ ከጥቁር ቡና ጋር አለበለዝያ ከሁለት አስፕሮ እንክብል ጋር እጅግ አስፈላጊ ነው
አለበለዝያ ራስ ምታቱ አይቻል ሲወድቅ ሲነሳ ያደረ ገላም ያጎሳቆላል፡፡ የገበታ ቅቤ የያዘውን ማቅረቢያ ማቀዝቀዣው
ውስጥ አውጥታ ትሪ ላይ አስቀመጠችውና ቡናው ደጋግሞ ቡፍ፡ እስኪል ታግሳ፥ ከምድጃው ላይ አውጥታ ወደ መኝታ ቤት ተመለሰች፡፡ አልጋው
ውስጥ ገብታ ትራሱን ከጀርባዋ አደላድላ ትሪውን በጭንና በጭኗ መሃል
አስቀመጠችና የቆረጠችውን ዳቦ ቅቤ ትቀባ ጀመር፡፡
ቁርስ ሳይበላ አንድ ብርጭቆ ወተት ብቻ ጠጥቶ እስከ ምሳ ሰዓት ሲቆይ ድንቅ ይላታል፧ ናቲ፡፡ እሷ ብትሆን ፍርክስክስ ብላ ከመሬት በተቆለለች:: ነገረ ስራውና መላ ኣፈጣጠሩ ሁሉ ግራ ግብት ነው የሚሳት፡፡ ይሄን ያህል ጊዜ አብራው ስትቆይ አሁንም ቢሆን ናትናኤልን አውቀዋለሁ ብላ ለመናር ትፈራለች። ግን ትወደዋለች፡፡ ለምን እንደሆነ ባይገባትም ሳታስበው! ሳትጠብቀው ከልቧ ወዳዋለች፣ ጭራው የማይያዝ፤ የማይጠመድ፧ ከእጅ የማይገባ ጋማውን እያመስ የሚፈነጭ የዱር ፈረስ ነው የሆነባት።....

Forwarded from ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘 (Tsi የማርያም 1⃣2⃣)
😂ተጠርጣሪው አስክሬን😂
✍አሌክስ አብረሃም
መምሬ አፈወርቅ ቀሚሳቸውን ሰብሰብ አድርገው በቤተ-መቅደሱ ኋላ እግሬ አውጭኝ ሲሉ ላያቸዉ ይሄን ሁሉ ዘመን ጧት እየተነሱ ሲቀድሱ የኖሩ ሳይሆን ጧት እየተነሱ ሩጫ ሲለማመዱ የሰነበቱ ነበር የሚመስሉት .....
መቶ አለቃ ታደሰ እየፎከሩ ለቤተክርስቲያኑ አጥር ጥገና ተብሎ በተከማቸው አሸዋ ላይ ዘለው ወደሴቶች በር በረሩ… ሴቶቹ ግማሾቹ ጫማቸውን ሌሎቹም የራሳቸውን ሻሽ እየጣሉ በጫጫታና በጩኸት በየቦታው ተበታተኑ፡፡ የሰፈራችን ታዋቂ ስፖርተኛ ጉግሳ እንኳን ፈሪ እንዳይባል ግራና ቀኝ እየተመለከተ ወደኋላውም ገልመጥ እያለ ሩጫ ቀመስ በሆነ እርምጃ አምልጧል፡፡ በአጠቃላይ ከሊቅ እስከ ከደቂቅ ሁሉም እግሩ እስከቻለለት ፍርሃቱ እስከፈቀደለት ሸሽቷል፡፡
አቶ ተሾመ የሚባሉ የመንደራችን ሰው ሙተው አስከሬናቸውን አጅበን ሃዘንተኛውና ቀባሪው ተከትሎ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ደረስን ፡፡ ፍትሃት ተደርጎ ግባተ መሬት ሊፈፀም ሲል ዝናብ በማካፋቱ አንድ የቆርቆሮ አዳራሽ ውስጥ አስከሬኑም ቀባሪውም ታጭቆ የሟቹ የሂወት ታሪክ መነበብ ጀመረ፡፡
"አቶ ተሾመ በ1957 ዓም ከእናታቸው ወ/ሮ ጥጊቱና ከአባታቸው አቶ ብሩ ተወለዱ ፡፡ እድሚያቸው ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት ስላልነበረ ሳይማሩ ቀሩ ፡፡ አቶ ተሸመ ለተራቡ እና ለታረዙ አባት ለተቸገሩ አበዳሪ ለተጣሉ አስታራቂ ነበሩ " አለ አንባቢው ፡፡ በእርግጥ የሞተ ሰው አይወቀስም እንጅ የሌላ ሰው የሂወት ታሪክ የሚነበብ ነበር የመሰለን፡፡
"እች መንደር እች ወረዳ እች ክፍለ ከተማ እች ከተማ ቀኝ እጇን አጥታለች " እያሉ አንባቢው ሊቀጥሉ ሲሉ ድንገት በፀጥታው ውስጥ "....ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ…" የሚል ሳቅ ተሰማ ፡ ሁሉም ሰው በድንጋጤ በድንጋጤ የጨው አምድ ሆነ ፡፡ ሳቁ ተደገመ ኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪ ሂሂሂሂሂሂሂሀሂሀሂሀሂሂሂሂሂ ይህን ጊዜ ነበር ሳቁ ከአስከሬኑ እንደወጣ ሁሉም ሰው ያረጋገጠው ፡፡ ከዛማ ሰው በሰው ላይ እየተደራረበ አንዱ አንዱን እየገፋና እየረገጠ በያቅጣጫው መፈትለክ ሆነ ፡፡ ሂሂሂሂሂሂሂሂሂ.......ኪኪኪኪኪ ኪ ኪ
ውጭ የቆመና ትርምሱን የተመለከተ ሁሉ
"ምንድን ነው " ብሎ ይጠይቃል
"አስከሬኑ ታሪኩ ሲነበብ ሳቀ"
"ትቀልዳለህ "
"ባክህ ቀልድ አይደለም እግሩን አንስቶ በሳቅ እየፈረሰልህ ነው " ይላል ሯጩ
ወዲያው ጉዳዩን የሰማው የወረዳው ፖሊስ የአስከሬን ምርመራ ባለሙያ የተካተተበት ቡድን በመያዝ በቦታው ደረሰ ፡፡ ሃላፊው ጉዳዩን ለማጣራት ያህል ለአንዳንድ ሰዎች ጥያቄ አቀረበ፡፡
"እ እንደተባለው አስከሬኑ ስቋል?" አለና የሟችን ባለቤት ጠየቀ
"አዎ ጌታየ "
:ባለቤተዎ በሂወት እንደነበረ ሳቅ ያበዛ ነበር?" ሲል ጠየቀ ኮስታራው ፖሊስ
"ኧረ በሂወት እያለስ ፊቱ ተፈቶም አያውቅ " አለች ባለቤቱ
"ለመሆኑ አስከሬኑን የገነዘው ማነው ? "
"እኔ ነኝ ጌታየ" አሉ ጋሽ መኮነን በፍርሃት
"ሟችን ...ይቅርታ 'ተጠርጣሪ ሟችን' ሲገንዙት መሞቱን በደንብ አረጋግጠዋል?"
"ተጠርጣሪ ሟች ምን ማለት ነው ጌታየ ? " አሉ ጋሽ መኮንን ግራ ተጋብተዉ
: ሰውየው በትክክል መሞቱ እስኪረጋገጥ ተጠርጣሪ ሟች ነው የሚባለው "
"አሃ እንደሱ ነው .......ጌታየ እኔ እንግዲህ ስገንዘው ሙቶ ነበር" ፖሊሱ መዘገበ
"ተጠርጣሪ ሟች ከሞተ በኋላ ልቡ ይመታ ነበር ?"
"ኧረ እሱ ልቡ ስራ ካቆመ ስንት አመቱ የቅርብ ወዳጆቹን እንኳን አያስታውስም ነበር ጌታየ " አሉ ገናዡ
"ተጠርጣሪ ሟች ሰውነቱ ቀዝቅዞ ነበር ?"
"መቀዝቀዝስ ካስር አመት በፊት ነው የቀዘቀዘው" አለች ባለቤቱ ድንገት ሳትጠየቅ ጥልቅ ብላ ፡፡ ከሟች ጋር አልጋ ከለዩ አስር አመት አልፏቸዋል እየተባለ ይወራ ነበር፡፡
የፖሊስ አዛዡ ድንገት አይኑ እኔ ላይ አረፈ "ና ስቲ አንተኛው አስከሬኑ ሲስቅ ሰምተሃል ?" አለኝ
"አዎ ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ ......... እያለ ቆየና ....ከዛ ኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪኪ......"
"በቃህ ! " ብሎ ጮኸብኝ በቁጣ ፡፡
የፖሊሱ አዛዥ ቆፍጣና ትዛዝ ሰጠ
"ሳጥኑን ክፈቱት " ፖሊሶቹ አብረቅራቂውን የእሬሳ ሳጥን ቀስ ብለው (ትንሽ ፍርሃትም ነበረበት እንጀራ ሁኖባቸው እንጅ ) ከፈቱት አቶ ተሸመ እንኳን ሊስቁ ድርቅ ብለው በስርአቱ ተኝተዋል ፡፡ ከነተቋጠረ ፊታቸው ፡፡ መርማሪው ጠጋ ብሎ ማዳመጫውን አስከሬኑ ደረት ላይ እያስጠጋ አዳመጠና ወደፖሊሱ አዛዥ ጠጋ ብሎ " ጌታየ ተጠርጣሪው ሙተዋል ፡፡ በዚህ አሟሟታቸው ለምፅአትም አይስቁ" በማለት ተናገረ ፡፡
አዛዡ አስከሬን መርማሪውን " እንደው የዚህ አይነት ገጠመኝ ሊያጋጥም የሚቸልበት ሳይንሳዊ ምክንያት ይኖርይሆን ? " ሲል ጠየቀው
"አይ ጌታየ አፍሪካ ውስጥ እንኳን የሞተ ሰው በሂወት ያለነውም የመሳቅ እድላችን ከመቶ አንድ ወይም ሁለት ፐርሰንት ቢሆን ነው" አለና መለሰ
"ይሄን አሁን የጠቀስከውን ቁጥር ኒዮ ሊበራሊስቶች ናቸው ያወጡት ወይስ የእኛው አገር ጥናት ነው ?"
"ሁለቱም አይደሉ ጌታየ..... እጣፋንታችን ነው!!"
አዛዡ ቀባሪውን ኮስተር ብሎ ተመለከተና "ይሄ በሰላም የሚኖረው ህዝብ ላይ ሽብር መንዛት ነው ፡፡ ከቀብሩ በኋላ በዚህ የፈጠራ ወሬ የህብረተሰቡን ሰላም ያደፈረሰውን ግለሰብም ይሁን ቡድን በቁጥጥር ስር እናውለዋለን ፡፡" አለና ወደእኔ ተመለከተ ፡፡ አስተያየቱ ዛቻ የተቀላቀለበት ነበር ፡፡ እንዴ እኒህ ሰዎች ምስክርና ወንጀለኛ አይለዩም እንዴ… ሆሆ
"ልክ ነው ጌታየ በወረዳችን አንዳንድ ሽብር የሚነዙ በሬ ወለደ ወሬ የሚያወሩ ግለሰቦችና ቡድኖች አሉ ፡፡ አሁንም የዚህ ሳቅ ጉዳይ የእነዚህ ፀረ ሰላም ሃይሎች ሴራና ደባ መሆኑ አያጠራጥርም" በማለት የቀበሊያችን ሊቀመንበር በለጠ የአዛዡን አባባል አሳምሮ ደገመው ፡፡
"እንዴ አንተ ራስህ ሳቁን ሰምተህ እንደፈረስ ስትጋልብ አልነበረም እንዴ አቶ በለጠ ? ለምን ውሸታም ታደርገናለህ ?" አሉት ጋሽ መኮንን ብስጭት ብለው ፡፡
"እኔ የሮጥኩት ህዝቡን ለማረጋጋት ነው " አለ በለጠ ፡፡ ግን በለጠ ህዝቡን ቀድሞ ሲፈተለክ ሁላችንም አይተነዋል፡፡
የፖሊስ አዛዡ ለሟች ባለቤትና ቤተሰቦች ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠና፡፡ "በአንዳንድ ፀረ ሰላም እና እና በጥባጭ ሃይሎች ድረጊት ሳትደናገጡ ህገመንግስቱ ባረጋገጠላች ሙታንን የመቅበር መብት በመጠቀም የቀብር ስነስርአታችሁን መፈፀም ትችላላችሁ፡፡ መልካም ቀብር" ብሎ ፊቱን ወደመውጫው በር አዞረና ቡድኑን እስከትሎ ገና ሁለት እርምጃ እንደተራመደ "ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ ....... ኪኪኪኪኪ ኪ ኪ ኪ ኪኪኪኪኪ" አለ አስከሬኑ ፡፡ አሁን ጉድ ፈላ !! የፖሊስ አዛዡ ሳይቀር ሊሮጥ ከጀመረ በኋላ እንደምንም እራሱን አረጋግቶ ወደአስከሬኑ ተጠጋ ፡፡
"ክፈቱት በፍጥነት"
ሳጥኑ እንደገና ተከፈተ ፡፡ አስከሬኑን ከነሳጥኑ በማውጣት ፖሊሶቹ ይዘውት የመጡት ታጣፊ ቃሬዛ ላይ አሳረፉት ፡፡
መርማሪው ግራ በመጋባት ምርመራውን እንደጀመረ
"ሂሂሂሂሂሂሂ .....ኪኪኪኪ" ሳቁ ተደገመ መርማሪው ደንግጦ ወደኋላው ቢስፈነጠርም ድምፁ ግን የመጣው ከባዶው የአስክሬን ሳጥን ውስጥ ነበር ፡፡ አንዱ ፖሊስ ወደሳጥኑ ተራምዶ አንድ ነገር አነሳ ሳምሰንግ ጋላክሲ 'ሞባይል' ስልክ !!
ጉዳዩ በኋላ እንደተጣራው ከሆነ ከውጭ አገር የመጣው የሟች ልጅ

👍2
የአባቱን አስከሬን ለማየት ሳጥኑን አስከፍቶ ነበር፡፡ አስከሬኑን አቅፎ እዬዬ ሲል የሸሚዙ ደረት ኪስ ያስቀመጠው ስልክ ሾልኮ የአስከሬን ሳጥኑ ውስጥ ገብቶ ኑሯል፡፡
ሂሂሂሂሂ ኪኪኪኪኪ አለ ቀባሪው ጉዳዩን ሲሰማ !!
✍✍✍✍✍
For any comment
@itsmetsita
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
Join and share
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
✨✨✨✨✨✨✨
ሂሂሂሂሂ ኪኪኪኪኪ አለ ቀባሪው ጉዳዩን ሲሰማ !!
✍✍✍✍✍
For any comment
@itsmetsita
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
Join and share
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
✨✨✨✨✨✨✨
😁1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
#ክፍል_ሶስት
#ትንሣኤ
በሁለቱ መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት የምርኮኞች ልውውጥ የሚጀመርበት የመጀመሪያው ምዕራፍ......
የድሬዳዋ ከተማ አሸብርቃለች፡፡ ገንደቆሬ፣ ገንደገራዳ፣ መጋላ፣ ከዚራ፣ ለገሀሬ፣ ..... መንደሮች በሙሉ በደስታ ስቀዋል፡፡
በየመንገዱ ግራና ቀኝ ተተክለው ቀዝቃዛና፤ ነፋሻማ አየርን የሚረጩት ዛፎች በደስታ ተውጠው የሚደንሱ ይመስላሉ፡፡ በዚያች ምድር ላይ የተካሄደው ቀውጢ ጦርነት አልፎ፤ ያንን የመሰለ የሰላም አየር መተንፈስ መቻል ዳግማዊ ልደት ነው፡፡
በሐረርጌ ምድር፡፡ በደገሀቡር፣ ቀብሪደሀር፣ መራራሌ፣ በሺላቦ፣
ደቦይን፣ በቆራሄ አሸዋማ ሜዳ፣ በኦጋዴን በረሃ፣ በካራማራ ተራሮችና በሌሎችም ሺህ ሌሊት ሺህ መአልት የፈሰሰው ደም፣ የተከሰከሰው አጥንት፣ያስገኘው ውጤት፡፡
በዚያን ቀውጢ ሰዓት ላይ ለዳር ድንበር ሲሉ ከጠላት ጋር እየተናነቁ አኩሪ ገድል የፈጸሙት፤ በደማቸው ማህተም፤ በአጥንታቸው ክስካሽ፤ ምድሪቱን ያቀሉት...የመስዋዕትነት ፈርጦች! የሚጠበቁበት ዕለት......
ሰማዩ በዚያን ቀውጢ የጦርነት ወቅት በኢትዮጵያ አየር ሃይል የተሠራውን አስደናቂ ትርኢትና ተአምር አፍ አውጥቶ ሊናገር፣ የታሪክ ምስክርነቱን ሊሰጥ፣ የተዘጋጀ ይመስል አጉረመረመ፡፡ ለሚወዷት እናት አገራቸው ዳር ድንበር ሲሉ የተፋለሙና ልዩ ልዩ ጀብድ ከፈጸሙ በኋላ በጠላት እጅ ወድቀው በባእድ ሀገር በምርኮኝነትና፤ በእስረኝነት ለበርካታ
አመታት ከቆዩ በኋላ በሁለቱ መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ዛሬ ወደሚያፈቅሯትና፤ ወደሚወዷት፤ እናት አገራቸው የሚመለሱበት እለት ስለሆነ፤ እነዚህን ውድ የሀገር አለኝታዎችና፤ ጀግኖች፤በልዩና፤ በደማቅ አቀባበል ፤ ሊቀበል ህዝቡ የአውሮፕላን
ማረፊያውን አካባቢ አጥለቅልቆታል....
ማርሽ የሚያሰማው ሠራዊት በተጠንቀቅ ቆሞ ይጠባበቃል።ባንዲራዎች ይውለበለባሉ፡፡ ህዝቡ ይሯሯጣል፡፡ ይራወጣል። ሰማይ ሰማዩን እያንጋጠጠ ይመለከታል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ትላልቅ አሞራዎች ያሳስታሉ፡፡ የሁሉም ልብ ተንጠልጥሏል፡፡ እነማን ይሆኑ?! ሞቱ ተብለው ደረት
የተመታላቸው፣ ተዝካር የተበላላቸው፣ ማን ያውቃል? በህይወት ሊገኙ
ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህ ጦርነት በተካሄደባቸው ብዙ አገሮች በተደጋጋሚ
የታየ ክስተት ነው፡፡
ሰዓቱ ደረሰ፡፡ ሰማዩ እንደገና በከፍተኛ ድምፅ አጉረመረመ፡፡አውሮፕላኗ በርቀት ታየች፡፡ ከዚያም እየጐላች ፤እየጐላች፤ መጣችና፤በማረፊያው ላይ እየዞረች፤ ማንዣባብ ጀመረች።
የሰው ጩኸት ሁካታ... ግርግር... ትርምሱ...ሌላ ሆኗል፡፡ማርሽ በረጅሙ ይሰማል፡፡ አውሮፕላኗ አዘቀዘቀች..... ከዚያም አኮበኮበችና አረፈች፡፡
ጀግኖች የታደሙባት አውሮፕላን! ለዳር ድንበሯ ሱሉ ደማቸውን ያፈሰሱላትን፣ በእስር የማቀቁላትን፣ ጥለው የወደቁላትን፣ ታስረው የተገረፉላትን፣ የጦር ምርኮኞችን ይዛ ይሄውና አውሮፕላኗ መሬት ላይ አረፈች....
የአውሮፕላኗ በር ተከፍቶ አንድ ረጅም፧ ቀጭን፤ መነጽር ያደረገና በአየር ኃይሉ ውስጥ በጦር ጄት የጠላትን ሃይል ድባቅ
በመምታት በደማቅ ቀለም ታሪክ ያስመዘገበ ምርኮኛ ብቅ አለ፡፡ማርሹ ይሰማል፡፡ እልልታው ቀለጠ!! ግማሹ በሲቃ ያለቅሳል፣ይፈነድቃል፡፡ ምርኮኞቹን ለማየት ሰው በሰው ላይ ይንጠላጠላል፣
ትዕይንቱ ብዙ ነው፡፡ ከዚያም የተዘጋጀውን እቅፍ አበባ ምርኮኛው ተቀበለ፡፡
ምርኮኞቹ ከአውሮፕላኗ እንደወረዱ መሬቷን ይስማሉ። አፈሯን ይልሳሉ፡፡ ያለቅሳሉ፣ ይንከባለላሉ፡፡ የደስታ እንባ... የናፍቆት እንባ... የትዝታ እንባ...
ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ከአገር፤ ከወገን፣ ከቤተሰብ ጋር ተለያይተው ፤ የብቸኝነትንና የመከራ ኑሮን ሲገፉ ከቆዩ በኋላ፤የሚወዱትንና፤ የሚያፈቅሩትን፤ ህዝብና አገር መቀላቀል ዳግም መወለድ
ነውና፤ ምርኮኞች ዳግም የተወለዱ ያህል በደስታ ሰከሩ። እንደዚያ ዳር ድንበርዋን ሊያስከብሩላት፤ ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው፡ ሳንጃ ለሳንጃ ተሞዣልቀው፡ ጥለው የወደቁላት፡ የውድ ሀገራቸውን ለም አፈር ለማሽተት በመቻላቸው በደስታ የሚሆኑትን አጡ ...ህዝቡም በእልልታና በሆታ የጀግና አቀባበል አደረገላቸው፡፡ ደስ የሚል ከህሊና የማይጠፋ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት......
ለተወሰኑ ቀናቶች በድሬዳዋ ከተማ እረፍት አድርገው ከቆዩና መንፈሳቸው ከተረጋጋ በኋላ፣ በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ሊቀላቀሉ የቸኮሉት ቀድመው ተንቀሳቀሱ፡፡
እለተ ቅዳሜ! አዲስ አበባ!! የኢትዮጵያ ዋና ከተማ! ቀዝቃዛ ንፋስ ይነፍስባታል ። በተለይ የባህር ማዶው ዛፍ ለቅዝቃዜው የራሱን ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል፡፡
ባቡሩ መንገደኞቹን ጣቢያው አራገፈ፡፡ ግፊያው ለጉድ ነው፡፡ግማሹ ሲመጣ ግማሹ ሲሄድ... የገቢና ወጪ መንገደኞች ምልልስ የማያቋርጥበት አምባ......
ጊዜው ለዐይን ያዝ ማድረግ የጀመረበት ሰዓት ነው፡፡
አንድ ቁመቱ ረዘም ያለ፣ ሰውነቱ በበረሃ ግርፋትና በእስር ስቃይ ምክንያት የተለበለበ ግንድ ቢመስልም፤ በሰላሙ ጊዜ ማራኪ መልክና ቁመና እንደነበረው አሁንም በግልጽ የሚታየው ትክለ ሰውነቱ
ዐቢይ ምስክርነቱን የሚሰጥለት፤ ከሲታ ሰው ከባቡሩ ወረደ፡፡
ደረቱ ሰፋ ያለ፣ ፀጉረ ዞማና ዐይኖቹ ጐላ ጐላ ብለው የሚታዩ ረጅም ሰው ነው፡፡ ሻንጣ አንጠልጥሏል፡፡ ከተሰጠው የኪስ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛውን ያዋለው ለሁለት ሴቶችና፤ ለአንድ ወንድ የሚሆኑ ልብሶችን በመግዛት ነው፡፡ ከባቡሩ ወርዶ፤ በአምባሳደር ቲያትር በኩል መጥቶ ፤ ወደ ኦርማ ጋራዥ አቀና፡፡ የሚራመደው በደመነፍስ ዐይነት ነው፡፡
በህልም ዓለም የሚራመድ ይመስላል፡፡
እሱ እራሱ የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን ተጠራጥሯል።ግራና ቀኙን በዓይኑ ያማትራል፡፡ ሰዎችን ይቃኛል፡፡ ምናልባት የማውቀው ሰው ካገኘሁ በሚል ግምት ነው፡፡ ግን ማንም የሚያውቀው ሰው አላገኘም፡፡ ድሮ የሚያውቁት ሲያዩት እንኳን፤ በቀላሉ ሊለዩት አይችሉም፡፡ ተለውጧል፡፡ ተጉሳቁሏል፡፡
መንገዶቹ የጠበቡ፣ ቤቶቹም ከምዕተ ዓመት በፊት የነበሩ መስለው ታዩት፡፡ በየመንገዱ ላይ ከሚያያቸው ሰዎች ውስጥ ሶስት ሰዎችን ለማግኘት በናፍቆትና በጉጉት ደጋግሞ ይቃኛል፡፡
የሱ ብርቅዬ፤ ድንቅዬዎች፡፡ ልዩ የህይወቱ ቅመሞች፡፡ የተዳፈነ የናፍቆቱ እምቅ ሊፈነዳ ተቃረበ፡፡ ልቡ ተሸበረ... እየተቃረበ ሲመጣ ልቡ ድው ድው የሚል ድምጽ ሰጠ፡፡ ትንፋሽ አጠረው፡፡
እጅግ አስገራሚ ነው! አስደናቂ
የማይጠበቀው ሰው ፤ እንደዚህ ባልተጠበቀ ሰዓት ከች! ሲል፤ እነሱ
ከአንጀቱ የሚያፈቅራቸው፣ የሚወዳቸው፣ የሚሞትላቸው ቤተሰቦቹ እንዴት ሆነው ይሆን? የሚወዳት ሚስቱ፣ የሚወዳቸው ልጆቹ እንዴት ሆነው ይሆን? ሲለያቸው በነበራቸው ዕድሜ ላይ አስራ አንድ ዓመት ሲጨመርበት የትየለሌ ነው፡፡ ምን መስለው ይሆን?
አቤቱ ፈጣሪ ያንተ ተአምር እንዴት ተወርቶ ያልቅ ይሆን? አደራህን ሁሉንም ለአንድ ቀን እንኳን ቢሆን ዐይናቸውን አይቼው
እንድሞት እርዳኝ፡፡ አንተ ታውቃለህ፡፡
ወባ እንደያዘው ሰው እየተቃረበ መጣ፡፡ ቤቱ ጋ ሲደርስ ሰውነቱ ተንዘፈዘፈበት :: ልቡ በፍጥነት ይመታ ጀመር፡፡
ግቢው ...ያ ...ግቢ የሚወደው ግቢ...እዚያ ውስጥ ያሉት እነ.. መራመድ አልቻለም፡፡ ቆመ፡፡ እንደሀውልት ተገትሮ ቀረ፡፡ ከዚያም ለዘመናት በወስጡ ሲንተከተክ የነበረው እንባ በድንገት ገንፍሉ ወጣ፡፡
ከደስታ ብዛት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ ቤቱን አየው፡፡ ልጆቹን አቅፎ የሳመበትን፣ ከሚያፈቅራት ባለቤቱ ጋር ደስታን ያሳለፈበትን፣ በመጨረሻም ወደ ጦርነት ሲሄድ ከቤተሰቦቹ ጋር ተላቅሶ

👍2🔥1
የተለያየበትን ቤት ከዚያም ቆሞ እንባውን በደንብ ጠራረገ፡፡ ትንፋሹን አስተካከለና
የአጥሩን በር እንኳኳ...
ጐረምሣው ልጁ፣ ወይንም ሴት ልጁ፤ ወይንም ሚስቱ፤ ብቅ ብለው በሩን ሲከፍቱለት ጉድ ሊመለከት፣ እሱ መሆኑን ሲያውቁ ምን እንደሚሉ ተአምር ሊመለከት፣ ሁለመናው አሰፍስፎ፣ በጉጉት ተውጦ ሲጠባበቅ፤ አንዲት አጠር ፈርጠም ያለች ምራቋን ዋጥ ያደረገች ሴት የአጥሩን በር ከፈተችና አንገቷን ብቅ አደረገችው፡፡
“አንተ ማንነህ?” በሚል አስተያየት ከላይ እስከታች አየችው፡፡
አቤት በዚያን ጊዜ የተሰማው ስሜት? አቤት የልብ ስብራት! አቤት አደነጋገጥ? አፉ ተከፍቶ፣ ስሜቱ ሁሉ ኩምሽሽ ብሎ ቀረ። ከዚያም ነፍሱን ሲገዛ፡፡
የሉም እንዴ የቤቱ ባለቤቶች?” ትንፋሹን እያስተካከለ ጠየቃት፡፡
“አሉ” አለችው፡፡
“ማን ይባላሉ?” በጥርጣሬ ተውጦ ዐይን ዐይኖቿን እያየ በድጋሚ ጠየቃት፡፡
“ማን ብለው መጡ ጌታዬ?” እሷም ሳቅ ብላ መልሳ ጠየቀችው፡፡
“የመቶ አለቃ ድንበሩ ቤት አይደለም እንዴ?” አሁንም ተሳስቶ እንዳይሆን በመጠራጠር፡፡
“የማናቸው መቶ አለቃ ድንበሩ?” የሰውዬው ሁኔታ ገርሟት ጥያቄውን በጥያቄ መለሰችለት፡፡
“ያንተ ያለህ!” እንደምንም ብሎ ትንፋሹን ተቆጣጠረና......
እ.ይቅርታ የኔ እመቤት፡፡ እኔ ይሄንን ቤት የማውቀው ከአሥራ አንድ ዓመታት በፊት ነበር፡፡ አሁን ማን ነው የሚኖርበት
ፈራ ተባ እያለ፡፡
“የቤቱ ባለቤት አቶ አሸብር ባንጃው ይባላሉ፡፡ ቤቱን የተከራዩት ከአንዲት ትህትና ከምትባል ሴት ላይ ነው፡፡ አባቷ በሶማሌ ጦርነት ጊዜ የሞቱ መሆናቸውን ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡” ሰውዬው በብርክ ተውጦ...
“የት ነው ያለችው እሷ?” ሲል ጠየቃት እየተርበተበተ፡፡
“ረጋ ይበሉ እንጂ ምን ነካዎት? እሷማ ባል አግብታ እዚሁ አዲስ አበባ ነው ያለችው”
“እናቷስ? ወ/ሮ አመልማልስ? ትንሹ ልጇ አንዱ አለምስ?”
“እናቷ?..!” በመገረምና በመጠራጠር ሽቅብ ተመለከተችው ::
“አዎን እናቷ ወ/ሮ አመልማልስ?”
እውነትም እርስዎ ለሁሉም ነገር እንግዳ ነዎት መሰለኝ፡፡
የመቼዎትን” ከንፈሯን ወደ ጉን አጣማ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ነው ተብሎ ሊገለጽ በማይችል ሁኔታ መንፈሱ ተተረማምሶ ፍዝዝ ብሎ ቀረ፡፡
መሬቷ የከዳችው መሰለው፡፡ እንደ ባሉን የሚንሳፈፍ መሰለው፡፡ በፍርሃት ተውጦ የመጨረሻውን ሊሰማ፣ ልቡ የጠረጠረውን ጉድ ከሴትዮዋ አፍ ሲሰማ፣ ዐይን ዐይኖቿን ትኩር ብሎ አያት፡፡
“እናቷ እንኳን ከሞቱ......” ንግግሯን ሳትጨርስ ሰውዬው ጅው ብሎ ወደ ኋላው ወደቀ፡፡
ከዚያም ሴትዮዋ ኡኡታዋን አቀለጠችው፡፡ ወዲያውም ጎረቤት
ከያለበት ወጣ፡፡
መንገደኛው እንግዳ ነፍሱን የዘራው ከረጅም ሰዓት በኋላ ነበር፡፡ዓይኖቹን ገለጥ አድርጐ ጣራ ጣራውን ተመለከተ፡፡ ከዚያም ግራና ቀኙን አማተረ፡፡ የተኛው መሬት በተነጠፈ ፍራሽ ላይ ነው፡፡
“የት ነው ያለሁት?፡፡” ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ቶሎ ማስታወስ አልቻለም፡፡
ቀስ በቀስ ህሊናውን እየገዛ ሲሄድ ሁኔታዎች ትዝ እያሉት መጡ፡፡ ድሬዳዋ በደማቅ ሁኔታ አቀባበል ሲደረግላቸው፣ ወርደው መሬቱን ሲስሙ፣ መስተንግዶው፣ የህዝቡ ዕልልታ፣ ወታደራዊው ማርሽ... ከዚያም ከድሬዳዋ በባቡር ወደ አዲስ አበባ ያደረገው ጉዞ፣
መንገድ ላይ ያጋጠሙት አዳዲስ ሁኔታዎች፣ ልክ ነው በናፍቆት ተቃጥሎ፤ በጉጉት ተውጦ፤ ቤተሰቦቹን ለማየት... በሩን እንኳኩቶ ከሆነች ሴት ጋር ማውራቱ፡ በኋላም ባለቤቱ፤ የሚወዳት ሚስቱ፤ የልጆቹ እናት የአመልማልን ሞት ሲስማ......በቃ ከዚህ በኋላ የሚያስታውሰው ነገር እዚያ ላይ አበቃ፡፡
እሱ ሞቷል ተብሎ ደረት የተመታለት፡ ዳግም ላይመለስ ሄዷል ተብሎ እርም የተወጣለት፤ የሃመልማ ባል የመቶ አለቃ ድንበሩ መሆኑ ሲታወቅ፤ በነዋሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ትርምስና፤ ግርግር አስከትሎ ነበር። ከዚያም ነፍሱን እስከሚገዛ በአንድ ክፍል ውስጥ እረፍት እንዲያገኝ
ተደርጐ፤ ህዝቡ ከደጅ ሆኖ እየተጠባበቀ ነበር፡፡ ከዚያም እንግዳው ከምሽቱ ሶስት ሰአት አካባቢ ከሰመመኑ ነቅቶ አካባቢውን ቃኘ፡፡ የት እንዳለ አወቀ፡፡ በድሮው ቤቱ ውስጥ፤ እሱና ባለቤቱ ይተኙበት በነበረው ጓዳ ውስጥ፤ ፍራሽ ላይ መተኛቱን እንዳወቀ፤ ከአንገቱ ቀና በማለት፤ ጣሪያና ግድግዳውን በአይኖቹ ፈተሸ፡፡ የድሮ አልጋቸውን ፈለገ፡፡ የለም፡፡
ከዚያም ትንፋሹን ውጦ ማልቀስ ጀመረ፡፡ ከተኛበት ብድግ ብሎ በእጆቹ
እንደ ብቅል አስጪ መሬቱን እያሰረ ፤ ግድግዳውን በእጆቹ በስስት
እየደባበሰ፤ .አመልማልዬ... ሙሽራዬ... እናቴ እመቤቴ.. ወይ በይኝ እንጂ.. ተይ እናቴ.. እንደ ዱሮአችን ይሻለናል፡፡ ልቤ ሲናፍቅሽ እኮ ነው የኖረው የኔ ፍቅር :: ኑሮው ከብዶሽ ድፍት አልሽ የኔ ከርታታ? እኔ ድፍት ልበል፡፡ ልጆቻችንን የት ጥለሽ አመልማሌ? ሲጮህ ድምጹ ይረብሻት ይመስል፤ በጆሮዋ የሚያንሾካሹክላት ይመስል፤ በሹክሹክታ ስሟን እየጠራ፤ ሙት መንፈስዋን እያነጋገረ ቆየና፤ ውስጥ ለውስጥ ሲንተከተክ የቆየው፤ የብሶት ቋያ የቀቀለው ፤ትኩስ እንባና እልህ እንደ እሳተ ገሞራ ገነፈለ፡፡ ከዚያም ኡኡ!! ብሎ እየጮኽ ዋይታውን ማስማት ሲጀምር፤ ከደጅ ተኮልኩሎ ሲጠባበቀው የነበረው ዘመድ አዝማድ በሙሉ ተከታትሎ ወደቤት መግባት ጀመረ፡፡ ስዎች እየተንጋጉ ገቡ፡፡ እሱም ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር መቀላቀሉን ሲያውቅ፤ እጅግ ሆድ ብሶት ማንባቱን
ቀጠለ...