#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
....ወይዘሮ እንኰዬ የእናታቸውን ንግግር ሲሰሙ ከሐሳባቸው መለስ አሉና በኩራት የነጠላቸውን ባለ ደማቅ ጥልፍ ጥለት አስተካክለው፣ “ሰማህ?” በሚል ሁኔታ ኢሳያስን ተመለከቱት።
ኢሳያስ ግን እጥር ምጥን ያሉትን ዮልያናን እያየ፣ “ጃንሆይም እኮ
ያጤ ሚናስ ነገድ መሆናችሁን አውቀዋል። ልዣችሁን የመረጡበት ዋናው ምክኛት ግን እሱ ማዶል። ባይናማነቷ፣ በጠባይዋና በብሩህ አይምሮዋ ደስ ተሰኝተው ነው” አላቸውና በራፍ ላይ የቆመውን አገልጋይ፣ “ያነን ማሙየን ሴቶቹ ዕቃውን ይዘው እንዲመጡ ንገራቸው
በለው” አለው።
አሳላፊው ቀልጠፍ ብሎ ወጥቶ ሲመለስ አብረውት ሁለት ደንገጡሮች የቀርከሀ ሰንዱቆች ይዘው ገቡ። ኢሳያስ ሰንዱቆቹን እንዲከፍቱና ዕቃዎቹን እንዲያሳዩ በእጁ ምልክት ሰጣቸው። ለጥሎሽ የመጡትን
የሐር ቀሚሶች፣ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ካባ፣ ቆዳ ጫማ፣ ከወርቅ የተሰሩ ያንገትና የጆሮ ጌጦች፣ እንዲሁም አምባሮች በእቅፋቸው አድርገው
ለተሰበሰበው ሰው አሳዩ።
እነግራዝማች ትንፋሻቸውን ውጠው ተመለከቱ። ተነሥተውም
በአክብሮት እጅ ነሡ፤ የምርቃት መዓት አዥጎደጎዱ።
ወለተጊዮርጊስ ጥሎሹን ለማየት ዐይኗን ከወዲያ ወዲህ አዘዋወረች።እንደልብ ማየት አቃታት። ቤተሰቦቿ ፊት ላይ ከሚንፀባረቀው የኩራትና የደስታ ስሜትና ከአዘነቡት የምስጋና ቃላት ግን የመጣላት ጥሎሽ ቀላል እንዳልሆነ ተገነዘበች።
እንዳው ሰውየው... አረ ንጉሥ ነው ሚባሉ... ንጉሡ ኸኛ ጋር ምን
አገጣጠማቸው? ንዳድ እንዲህ ጉድ ታምጣብን እያለች ስትገረም
ቆየችና ንጉሠ ነገሥቱ እነሱጋ፣ በነበሩ ጊዜ እሷን ለማግባት ማሰባቸውን የሚጠቁም ነገር እንዳው ፍንጭ አኸገኝ እንደሆን ብላ፣ ሐሳቧ ወደ ኋላ ሽምጥ ጋለበ።
ጨታመው በመጡ ማግስት እናቷ አዘዋት ፊታቸውን በጨርቅ ስታብስ ንጉሠ ነገሥቱ ዐይናቸውን ገለጥ አደረጉ፤ እንደደነገጡ አስተዋለች። ለምን እንደሆነ አልገባትም። እሳቸው ዐይናቸውን ከድነው በስመአብ አሉ። ዐይናቸውን ድጋሚ ሲከፍቱ፣ እነዚያው ይዘዋቸው የመጡት
ሰዎችና እነግራዝማች ናቸው የከበቧቸው። ቅዠት ኑሯል? ትኩሳቱ ነው ሴት ልዥ ያየሁ ያስመሰለኝ ብለው ዐይናቸውን መልሰው ከደኑት።
ወለተጊዮርጊስ አጥሚት ይዛ ተመልሳ መጥታ፣ በለሰለሰ አንደበት፣ “እስቲ ትንሽ ይቅመሱ” ስትላቸው በድንገት ከእንቅልፋቸው እንደባነኑ
የደከመ ዐይናቸውን ከፈት ሲያደርጉ፣ የተኙበት መደብ አጠገብ ሴት ልጅ ሸብረክ ብላለች። ቀደም ብለው ያይዋት ወጣት እንደሆነች ሲገነዘቡ፣ ዐይኖቿ እንደ ኮከብ እሚያበሩ፣ ቆዳዋ የማር ወለላ የመሰለ፣ እንዴት ያለች ዐይናማ ናት በሩፋኤል? አሉ፣ አንድም ቀን
ስለታቸውንና ጥያቄያቸውን አስተጓጉሎባቸው የማያውቀውንና እሳቸው ጐንደር ውስጥ የተከሉትን ሩፋኤልን ጠርተው።
ወለተጊዮርጊስ ፈገግታ ለገሠቻቸው። ዐይኗ ላይ ያዩት ርህራሄ መጽናናትን ሰጣቸው። ልባቸው በደስታና በአድናቆት ከቦታው ተነቃነቀ። አጥሚት የያዘውን የሸክላ ጽዋ ወደ አፋቸው ስታቀርብላቸው፣ ወይዘሮ እንኰዬ፣ “እስቲ ይቅመሱ፣ እሷው ናት የሠራችልዎ” አሏቸው። የምግብ ፍላጎት ባይኖራቸውም፣ እንደ ኩበት የደረቀ አፋቸውን ታግለው ከፈቱላት። አንገታቸውን በአንድ እጇ አቅንታ ከአጥሚቱ
አስጎነጨቻቸው። ከበዋቸው የተቀመጡት፣ “ተመስገን፣ ለሱ ምን ይሳነዋል?” ብለው ወደ ላይ አንጋጠጡ።
በሚቀጥሉት ቀናት ከበሪሁን መድኃኒት በተጨማሪ ወለተጊዮርጊስ ከምትኖርበት ከአያቷ ቤት ማልዳ እየመጣች ምግብ እየሠራች፣ እያጎረሰች፣ አጥሚት እያጠጣችና እየተንከባከበቻቸው ራሳቸውን
ሲችሉም፣ እጅ እያስታጠበችና ምግብ እያቀረበች፣ ደከመኝ ሳትል
አስታመመቻቸው። እሳቸውም በሩፋኤል እንዴት ያለች ዐለላ...ሰንደቅ የመሰለች ናት ትትናዋስ? እያሉ ተስተናገዱ።
በተኙበትም ሰው ውልብ ባለ ቁጥር እሷ እየመሰለቻቸው ዐይናቸው ሲባክን፣ ሲያይዋት ልባቸው ከአፎቱ ተመንጥቆ የወጣ ሲመስላቸው፣ፊታቸውን በውሃ ስታብስ የእጇ ልስላሴ ሊያስተኛቸው ሲቃጣው፣
ትንፋሿ በሽታቸውን ከላያቸው ሲገፍላቸው፣ ሕዝኸ ወድያ ጥድቅ
ኸየት ይገኛል? አቤት አቤት እንዴት ያለች መልከ መልካም ናት?
ደም ግባቷ የተደራጀ፣ ጠጉሯ እንደ ሜላት የተፈተለ፣ ወገቧ እንደ ንብ
ንግሥት የቀጠነ፣ እንደ እርጎ የረጋች በምግባር የታነጠች እያሰኘ አከረማቸው።
እንኳንስ አይተዋት፣ ሳያይዋት ስለእሷ ማሰቡ ብቻ በወባ የዛለ
አካላቸውን ዘና ሲያደርግላቸው፣ ከዐይናቸው ስትርቅ ምግብ፣ ውሃ
ወይንም አጥሚት ይዛ የምትመጣበትን ሰዐት ሲናፍቁ፣ ጀንበር መጥለቂያዋ ላይ ወደ አያቷ ቤት ስትመለስ ሆድ ሲብሳቸው፣ ጠዋት ስትመጣ ከእናቷና ከአያቷ የወረሰችውን እንደ ውሃ የጠሩ ዐይኖቿን
ከብለል እያደረገች የወደዱትን እየመረጠች የሠራችውን፣ “እስቲ ትንሽ ይቅመሱ፣ እኼኛው ይሻልዎ ይሆን?” ስትላቸው፣ ጆሯቸው የተዋበ ዜማ የሰማ ያህል ወደ እሷ ዘመም ሲል፣ ልባቸው ለማራኪ ዐይኖቿ ሲገዛ ቀናት አለፉ።
ሌሎች ውበቷን አይተው እጇን ሲጠይቁ እሳቸው ከመልኳ ባሻገር
ለጋሥ መንፈሷን፣ አስተዋይነቷን፣ ሠናይ ምግባሯንና ትሕትናዋን
አስተውለው ወደዷት። በአኳኋኗና በልባዊ መስተንግዶዋ ልባቸው
ተነካ። ተወዳጅ ገፅታዋ፣ አነጋገሯ፣ ርጋታዋ፣ ወደ ሙሉ ሴትነት
በመሻገር ላይ ያለው ዳሌዋና ለግላጋነቷ በወባ የተንገላታችው ልባቸው ላይ ነፍስ ዘሩበት።
ድኘ እጐንደር ስገባ ይችን ልዥ አገባለሁ እያሉ ደጋግመው ዛቱ።
እሳቸው እንደዚህ እያሉ ይዛቱ እንጂ፣ ወለተጊዮርጊስ ወደዋት
እንደነበር የሚያሳይ አንዳችም ፍንጭ አላገኘችም። እሳቸውም በግልጽ ያሳይዋት ነገር አልነበረም።
የሚሄዱ ቀን፣ ግራዝማችንና ቤተሰባቸውን ከታላቅ ምስጋና ጋር
ተሰናብተው፣ ውድ ንብረት ወደ ኋላ የተዉ ያኸል እየተገላመጡ፣ ያችን “የአጥቢያ ኮከብ የመሰለች” ሲሏት የከረሙትን የአስራ ስድስት ዓመት ጉብል በዐይናቸው ፈልገው አመሰገኑ። ወለተጊዮርጊስ በተለይ ለእሷ ለቀረበው ምስጋና እጅ ነሥታ ቀና ስትል ዐይኖቿ ከሰውየው ዐይኖች ጋር ተጋጩ።
ከእሳቸው ዐይነ ብሌን ባሻገር ግን ከቋራ እስከ ጐንደር የሚወስደው
መንገድ እንደተቃና አላስተዋለችም።
ከሐሳቧ ስትመለስ ጨዋታው ቀዝቀዝ ብሏል። እንግዶቹም የተዳከሙ መስለዋል። ቤቱም ጨለምለም ብሏል። ሥራ ቤት በየበኩሉ ማሾ ሊያበራ ሽር ብትን ይላል።
ኢሳያስ፣ “እንግዲህ ልዥቱን ይዘን ነገ ጐንደር እንዝለቃ” አለ፣
ግራዝማችን፣ እንኰዬንና ዮልያናን በየተራ እየተመለከተ።
ነገ አለች፣ ወለተጊዮርጊስ። በረጅሙ ተነፈሰች፣ ወላጆቿና አያቷ የሚሉትን ለመስማት ጆሮዋን አቀናች።
“ባይኾን ኸነገ ወዲያ ይሁን፣ ጥቂትም ቢኾን ልዣችንን እንድናዘጋጅ” አሉ፣ አያቷ።
“እንዳላችሁ ይሁን” አለ፣ ኢሳያስ።
ጐንደር መሄዷ ነው! ተጨነቀች። ተርበተበተች። ኸጐንደር ልኸድ? አለች። ንጉሥ ላገባ ጥላዬስ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን”
ጥላዬ፣ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ስለራሱና ስለወለተጊዮርጊስ ዕጣ
ፈንታ ያስባል። እናቱ ወይዘሮ ጌጤነሽ የምሽቱን ግብር ውሃ ወጥተው ሲመለሱ አየት አደረጉት። “አምሽተህ ነው?” አሉትና ለራሳቸው ሰምቶ
ይሆን? አሉ። ዛሬ ከልባቸው አዝነውለታል። ወደ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት፣ “በምሽት እንኳ ዕረፍት አይኖርህ ልጄ?” አሉት፣ መሬት ላይ የሚጭረውን አይተው።

👍14
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
ሲልቪ
ላይ ላዩን
..ተመስገን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስሰራ አንዳንዴ ውቢቱ ሲልቪ ትመጣና «Salut Castro noire» ትለኛለች። («ሰላም፣ ጥቁር ካስትሮ») (ፂም ስላለኝ ነው፡፡)
«Que la paix soit avec toi Scheherazade Blanche» እላታለሁ
(«ሰላም ላንቺ ይሁን፣ ፃእዳይቱ ሻህራዝድ ሆይ»)
ትስቃለች። በምስራቃውያን አነጋገር እንቀጥላለን። ቀልድ
ነው። ከሲልቪ ጋር ሁልጊዜ ቀልድ ነው:: እውነተኛ ፈረንሳዊት ናት፣ ስለምንም ነገር ቢሆን «Moi je men fous!» ነው የምትለው
(«እኔ ስለዚህ ነገር ደንታ የለኝም»)
ታድያ ደስ ትላለች። ሰፊ አፏ
ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል፡፡ አብረሀት ስትሆን ሳቅ ቀልድ ታበዛለህ፣
«ዠማንፉቲዝሟ» ይጋባብሀል፤ ስለምንም ነገር ደንቴ አይኖርህም
አንድ ቀን ግን
«ምንድነው ሁልጊዜ ስትፅፍ የማገኝህ?» አለችና ደብተሬን
አየችው:: የምን ፅህፈት ነው ይሄ? ያገራችሁ ነው?» አለችኝ
«አዎን»
«ምኑም አይገባም»
«ቀላል ነው፡፡ ሁለት መቶ አርባ የሚሆኑ ፊደላት አሉት»
«Quel horreur! (ኧረ የጉድ ያለህ!) እንግዲያው አታስረዳኝ
ይቅርብኝ .. ምንድነው ምትፅፈው?»
«ምንም አይደለም»
«ልብወለድ ነው?»
«ብጤ ነው»
«እንዴት ማለት ብጤ?»
«እንዴት ልበልሽ? ልብወለድ ነው፣ ግን ፈጥሬው አይደለም፣
ያየሁትን የሰማሁትን ነገር ሰብስቤ ቅርጹን እለዋውጣለሁ እንጂ፣
ላንባቢ እንዲጥም»
«ቆይ ቆይ፡፡ አሁን መፃፍ አለብህ ወይስ ለጊዜው ልትተወው
ትችላለህ»
«ልተወው እችላለሁ»
«እንግዲያው ከዚህ እንሂድና ቡና ልጋብዝህ:: እና ስለድርሰት
እናውራ። ይስማማሀል?»
«በደምብ ነዋ! ቆንጆ ሴት ቡና ስትጋብዘኝ ሁልጊዜ
ይስማማኛል»
«Malin Castro noir va!» («ሂድ ወድያ! ፎሌ ጥቁር ካስትሮ!»)
Deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ ከገባን በኋላ
«ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም፡፡ ማርሰይ እንሂድ?»
አለችኝ
እየቀለድን እየሳቅን ደጋግማ «Moi, u sais je m en fous!»
እያለች፣ በሆዴ ውበቷን እያደነቅኩ፣ ማርሰይ ደረስን፡፡ የንግድ ሳይሆን የግል የመደሰቻ ልዩ ልዩ አይነት ጀልባዎች ከተደረደሩበት ወደብ አጠገብ አንድ ካፌ ገብተን ቢራ ካዘዝን በኋላ፣ ጉልህ ሰማያዊ
አይኖቿ በፈገግታ እያዩኝ
«ንገረኛ ስለምትፅፈው» አለችኝ
«ምን ልንገርሽ?»
«ስለሰዎቹ፣ ስለጊዜው፣ ስለግንኙነታቸው፣ ማን ማንን እንደ
ሚወድ፣ ማንስ ማንን እንደሚጠላ፣ መፅሀፍህ አንዴት እንደ ሚጀመር፣ አሁን የት እንደደረሰ፣ በኋላ እንዴት እንደሚያልቅ፣
ምን ምን ነገር እንደሚያስቸግርህ፣ መፅሀፍህ ምን እንዲል እንደ
ምትፈልገው፣ ሁሉን ንገረኝ
ቆንጆ ስለሆነች ይሁን፣ አጠያየቁን ስላወቀችበት ይሁን ወይ ሌላ ያልተገለፀልኝ ምክንያት ይኑር እንጃ፣ ስለመፅሀፌ ሁሉን
ነገርኳት። ለማንም ነግሬ የማላውቀውን ለሷ አጫወትኳት፡፡ ችግሩን ደስታውን፣ ብስጭቱን፣ የድል አድራጊነት ስሜቱን፣ ምንም
ሳልደብቅ አዋየኋት። ፈረንሳይኛው ሲያስቸግረኝ ልክ ልናገረው
የፈለግኩትን ቃላት ታቀብለኛለች፣ ምክንያቱም ሀሳቤ ቃላቱን
ቀድሞ ደርሷት ይቆያል። አንዳንድ ቦታ አንድ ሀሳብ ተናግሬ
ጨርሼ ሌላ ሀሳብ አልመጣልህ ሲለኝ አንድ ጥያቄ ትጠይቀኛለች
እሱን ጥያቄ ስመልስ፣ ሌላ ሀሳብ ይመጣልኝና እቀጥላለሁ፡፡ እንደዚህ ብዙ ካወራሁ በኋላ
«ይገርምሻል፣ ይህን ለማንም ነግሬ አላውቅም» አልኳት
«Jen suis lattee» አለችኝ (ክብር ይሰማኛል።)
«እኔ እውነቴን ነው»
«እኔም እውነቴን ነው»
«አሁን ተራሽን አውሪልኝ
«ቆይ» አለችና ከያዘችው የመፃህፍት ቦርሳ አንድ አስር የሚሆኑ ባንድ በኩል ብቻ በታይፕ የተፃፈባቸው ነጠላ ወረቀቶች ሰጠችኝ።
አንብበው አለችኝ፡፡ አነበብኩት፡፡ አጭር ልብ ወለድ ታሪክ ነው።
ስጨርስ ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«አንቺ ነሽ የፃፍሽው?» አልኳት
«አዎን» አለችኝ
«አዝናለሁ። ጥሩ ታሪክ አይደለም»
«ምንድነው የጎደለው?»
«እርግጠኛ አይደለሁም። አየሽ፣ አንድ ሰው የሚወዳትን ሴት
ሊገድል ይችል ይሆናል፡፡ ግን ባስር ገፅ ውስጥ ይህን መናገር
የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሁለት መቶ ገፅ
ያስፈልገዋል»
«ይህንንም አንብብ እስቲብላ ሌላ አስራ ሶስት ገፅ ሰጠችኝ።
አነበብኩት። ግሩም ታሪክ ነበር፡፡
«ይህንንም አንቺ ነሽ የፃፍሽው?»
«አዎን»
«ታሪክ ይሉሻል ይሄ ነው! ይህን ጊ ደ ሞፓሳን ራሱ ነው የፃፈው ቢሉኝ አምናለሁ» አልኳት
ጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ ልዩ አስተያየት ሰጡኝ፣ እንደማቀፍ ያለ
አስተያየት፣ ሙቀት ያለው አስተያየት
«Merci»አለችኝ
«Je ten prie (ኧረ ምንም አይደለም) ይህን የመሰለ ለመፃፍ
ስትችዪ፣ እንዴት አርገሽ የቅድሙን ፃፍሽው?» አልኳት
መሳቅ ጀመረች (ጥርሶቿ ትክክል ሆነው ነጫጭ ናቸው። ነጭ
የፈረንጅ ጥርስ ብዙ እይታይም) «እኔ እንጃ አለችኝ «በምፅፍበት
ሰአት ሁሉም እኩል ጥሩ ሆኖ ይሰማኛል። ካንድ ሁለት ወር በኋላ
ሳነበው ነው እውነተኛው ዋጋው የሚታየኝ»
«ይሄ መጥፎው መቼ ነው የተፃፈው?»
«ካንድ አመት ተኩል በፊት
«እንግዲያው መጥፎ መሆኑ
ድሮ ገብቶሻል። ለምን
እስነበብሽኝ?»
«ላውቅህ ስለፈለግኩ። ማንም ሰው ቢሆን፣ እንደምፅፍ ካወቀ
ወይም እንዲያውቅ ከፈለግኩ፣ መጀመሪያ መጥፎ ታሪኬን
አስነብሰዋለሁ። አንብቦት ጥሩ ነው ካለ በቃው። ሁለተኛ እኔ
የፃፍኩትን አያነብም። እስካሁን ለአንድ ስምንት ሰው አስነብቤያለሁ።
አንተና አንድ የፓሪስ ጓደኛዬ ብቻ ናችሁ መጥፎውን መጥፎ
ያላችሁት። ስለዚህ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ ጥሩውን ያነሰሳችሁ»
«ሌላ የፃፍሽው አለ?»
«ሃያ ሶስት አለኝ፡፡ አስራ አንዱ ጥሩ ይመስሉኛል። ሰባቱ
በጣም መጥፎ ነው:: አምስቱ ግን ጥሩም አይደል፣ መጥፎም
ኣይደል እንደኔ እስተያየት። ስለዚህ አንተ እነዚህን አምስት
አንብበህ ምን እንደሚመስልህ ብትነግረኝ፣ ተስፋ የሌለውን
እጥለውና ተስፋ ያለውን እየመከርከኝ አሻሽለዋለሁ»
«ክብር ይሰማኛል፣ ግን ልመክርሽ መቻሌን እንጂ
«ትችላለህ። ታግዘኛለህ? »
«ከቻልኩማ በደስታ! አሁን ስለራስሽ ንገሪኝ፡፡ ቅድም እኔ
እንደነገርኩሽ»
ነገረችኝ፡፡ የምንፅፍበት ቋንቋ ተለያየ 'ንጂ ሙከራችን፤
ችግራችን፣ አስተያየታችን በጣም ይመሳሰላል፡፡ ስንወያይ መሸ፡፡
«እማውቃት ጥሩ ርካሽ ምግብ ቤት አለች» ብላ ሳን ሻርል
ባቡር ጣቢያ አጠገብ ወስዳ እራት ጋበዘችኝ። በፈረንሳይ ደምብ ከምግቡ ጋር አንድ ጠርሙስ ወይን ጠጣን፡፡ ሲኒማ ላስገባሽ አልኳት፡፡ ሁለታችንም እንደዚህ ልንጨዋወት የምንችልበት ጊዜ
መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ አይታወቅም አለችኝ፡፡ እውነትሽን ነው አልኳት
ወደ ወደቡ ተመልሰን በእግር እየተዘዋወርን ወሬያችንን ቀጠልን። በተርታ የቆሙ ጀልባዎች የሚወዛወዙበት ውሀ ውስጥ የማርሰይ መብራት ይጫወታል። የባህር ሽታ ይዞ ከባህር በኩል የሚመጣው ነፋስ ቅዝቅዝ ያለ ሆኖ ይለሰልሳል። እንደኛው እያወሩ
የሚዘዋወሩ ሰዎች አሉ፤ አብዛኛዎቹ ተቃቅፈዋል፡፡ መንሽራሽር ሲበቃን አንድ ካፌ ገብተን ቁጭ ብለን ቢራ አዘዝን

👍27❤1👏1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት እስር ቤት ውስጥ ሲቀመጥ ኣንድ ቀን እንኳን እንባ አልወጣውም::
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከቤተክርስቲያን አናት ላይ የተሰቀለው ሰዓት ስምንት ሰዓት ሲደውል ዣን ቫልዣ ከእንቅልፉ እንደገና ነቃ፡፡ ከአራት ሰዓት በላይ ጥሩ እንቅልፍ ወስዶት ተኝቷል፡፡ ድካሙ ሁሉ ወጣለት:: ለዚህን ያህል ጊዜ የእረፍት ሰዓት ኣግኝቶ አያውቅም፡፡ ዓይኑን ገልጦ በአካባቢው በሰፈነው ጨለማ
ዘልቆ ለማየት ሞከረ፡፡ ለማየት ባለመቻሉ እንደገና እንቅልፍ እንዲወስደው ዓይኖቹን ጨፈነ፡፡
ቀኑን ሙሉ አእምሮ በብዙ ነገሮች ተበጥብጦ ከዋለና የተለያዩ ነገሮች ከተመላለሱበት አንድ ጊዜ እንጂ ሁለት ጊዜ እንቅልፍ ሊወስድ እንደማይችል
ሁሉ ዣን ቫልዣንም ሊወስደው አልቻለም:: እንቅልፍ መጀመሪያ ሲመጣ ያዳፋል፡፡ ሁለተኛ ግን ቢለማመጡትም በዓይን አይዞርም:: እንደገና እንቅልፍ
ሊወስደው ስላልቻላ ማሰብ ጀመረ::
ብዙ ዓይነት አሳብ ከኀሊናው ውስጥ ገባ፡፡ ግን ሌሎቹን ሁሉ እየዋጠ እርሱ ብቻ እየተመላለሰ ያስቸገረው አንድ አሳብ ነበር፡፡ እነዚያ መዳም ማግልዋር ከጠረጴዛው ላይ የደረደሩዋቸው የሚያማምሩ ስድስት ከብር
የተሠሩ ሣህኖችና ትልቅ የብር ጭልፋ በዓይኑ ዞሩ፡፡ በጣም ወዷቸዋል:: አጠገቡ ከጳጳሱ ትራስጌ በኩል ቡፌ ውስጥ ሴትዬዋ ሲያስቀምጧቸው
አይቶአል፡፡ ከብር የተሠሩ ጥንታዊ ቅርስ በመሆናቸው ከነጭልፋው እስካ 200 ፍራንክ እንደሚያወጡ ያውቃል፡፡
ኅሊናው ከወዲያ ወዲህ እየዋለለ አንድ ሰዓት አለፈ፡፡ በአሳብ እየዋተቱ አንድ ሰዓት ማሳለፍ፤ ያውም ሌሊት በጨለማ ምን ያህል ረጅም እንደሆነ
የደረሰበት ያውቀዋል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ሰዓት ደወል ዘጠኝ ሰዓት መሆኑን አበሰረ:: ዓይኑን በድንገት ገልጦ ከአልጋው ዘልሉ ወረደ:: ስልቻውን በእጁ
እየዳሰሰ ፈለገና እንደያዘው ከአልጋው ጠርዝ ቁጭ አለ፡፡ ሳያውቀው ብዙ ተቀመጠ፡፡ ሰዓቱ በየአሥራ አምስት ደቂቃና ግማሽ ሰዓት ደወል እየደወለ ባይቀሰቅሰውማ እስኪነጋ ድረስ በተቀመጠ፡፡ ደወሉ «አይዞህ፣ በርታ» የሚለው መሰለው::
ተነስቶ ቆመ፤ ለመራመድ ግን አመነታ:: አንድ እርምጃ ወደፊት
ተራምዶ አዳመጠ፡፡ ሁሉም ነገር ጸጥ ብሎአል:: ቀስ ብሎ በጥንቃቄ ወደ መስኮቱ ተጠጋ፡፡ ሌሊቱ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ የተዋጠ ኣልነበረም:: ጨረቃ
በሩቁ ትታያለች:: ሆኖም ደመና ዞሮባታል፡፡ ደመና ጨረቃዋን በጋረዳት ቁጥር ቤቱ ትንሽ ጨለም ይላል፡፡ ውጪው በደምብ ሲታይ እቤት ውስጥ ግን ያንገዳግዳል፡፡ መስኮቱ አጠገብ ደርሶ መስኮቱን ሲመለከት በቀላሉ
እንደሚከፈት ስለተገነዘበ ከፈተው:: ሆኖም ኃይለኛ ብርድ ስለገባ መልሶ ዘጋው:: መስኮቱ መስታወት ስለነበር እንደተዘጋ ግቢውን ቃኘ፡፡ ግቢው
በአነስተኛ ግምብ መከለሉን ተመለከተ:: ከግምቡ ውጭ ረጃጅም ዛፎች ነበሩ፡፡ በሁለት ዛፎች መካከል ያለውን ርቀት ሲያጤን ርቀታቸው ተመሳሳይ
ሆኖ ስላየው ምናልባት ማዘጋጃ ቤቱ የተከላቸው ዛፎች መሆናቸውን በመገመት ከአጥሩ ውጭ ያለው መንገድ አውራ ጎዳና መሆን አለበት ብሎ ደመደመ::
ወደ ውሳኔ አሳብ እንደደረሰ ሰው በቆራጥነት ወደ አልጋው ተመለሰ፡፡ አቆማዳውን አንስቶ ከፈተውና ከውስጠ ምናምን ፈለገ፡፡ ኣንድ ነገር አውጥቶ
አልጋው ላይ አስቀመጠ፡፡ ጫማውን ኪሱ ውስጥ ከተተ፡፡ ኣልጋው ላይ ካስቀመጠው እቃ ሌላ የተቀሩትን እሳስሮ ትከሻው ላይ አኖረ፡፡ ቆቡን አጠለቀና ዱላውን ፈልጎ ከያዘ በኋላ ያሰረውን እቃ ከመስኮቱ ሥር
አስቀመጠው:: ወደ ኣልጋው ተመልሶ ያስቀመጠውን እቃ አነሳ:: እቃው ከአንድ ጫፍ እንደ ጦር የሾለ፣ ከሌላው ጫፍ ቋር ያለው ወፍራም ብረት ነበር፡፡ በዚያ ጨለማ ብረቱ ለምን ሥራ እንደተዘጋጀ ለመለየት አስቸጋሪ
ነበር፡፡ ዱላ ነው ወይስ እቃ ማንሻ? አይታወቅም:: ቀን እንኳን ቢሆን
የማዕድን ሠራተኞች መቆፈሪያ ነው ለማለት ያስችላል፡፡ በዚያን ጊዜ ቱሉን ከተባለ ቦታ አካባቢ በሚገኙ ከፍተኛ ኮረብታዎች ላይ ድንጋይ እንዲፈልጡ
የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ይቀጠሩ ነበር፡፡ ወንጀለኞቹ ብዙውን ጊዜ የዚያን ዓይነት ብረት የመሰለ መፍለጫ ይይዛሉ፡፡
ዣን ቫልዣ ያን ብረት በቀኝ እጁ ያዘ፡፡ ትንፋሹን ውጦ በዝግታ
ተራመደ:: ወደ ጳጳሱ መኝታ ቤት አመራ:: ወደ በሩ ሲጠጋ አለመቀርቀሩን ተመለከተ፡፡ «አባታችን በራቸውን ሳይቆልፉ ነው የሚተኙት» አለ በልቡ፡፡
ዣን ቫልዣ ጆሮውን አቅንቶ አዳመጠ፡፡ ድምፅ የሚሉት ነገር
የለም:: በሩን ከፈት አድርጎ ሲፈራ ሲቸር በጣቶቹ ጫፍ ቀስ ብሎ ገፋው::ጥንቃቄው ከድመት ይበልጣል:: በሩ ምንም ድምፅ ሳያሰማና ለመንቀሳቀሱ
እንኳን በሚያጠራጥር ሁኔታ በዝግታ በመገፋቱ ከመጀመሪያው ይበልጥ ጥቂት ከፈት አለ፡
ለጥቂት ጊዜ ከበሩ አጠገብ ቆም አለ፡፡ አሁን ግን በይበልጥ ድፍረቱ
ስለተሰባሰበለት ከቀድሞ በበለጠ ጉልበት በሩን ገፋ አደረገው:: በዚህ ጊዜ የበሩ ማያያገዥ የዛገ ብረት ረዘም ያለ የሚሰቀጥጥ ድምፅ አሰማ፡፡
ልቡ የተሰነጠቀ መሰለው:: እንደ እንጨት ደርቆ ከቆመበት ሐውልት
ይመስል ሳይንቀሳቀስ ለጥቂት ጊዜ ተገተረ:: ለመነቃነቅ አቅም አነሰው ድፍረትም አልነበረውም:: ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ:: በሩ ወለል ብሎ ተከፍቷል:: ወደ ክፍሉ ተመለከተ:: የተንቀሳቀሰ ነገር የለም:: አዳመጠ፤ የሚንቀሳቀስ ወይም ድምፅ የሚሰጥ ነገር አሁንም ከጆሮው ኣልገባም::
የበሩ ድምፅ ማንንም አልቀሰቀሰም ማለት ነው::
የመጀመሪያው አደጋ አለፈ:: ልቡ ግን በጣም ፈርቷል ፤ ሆኖም
አላወላወለም:: የፈለገውን ቶሎ ለመጨረስ ቁርጥ አሳብ አደረገ፡፡ በአንድ እርምጃ ከክፍለ ውስጥ ገባ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ጸጥታ ሰፍኖበታል፡፡ ዣን ቫልገዣ ከወንበርና ጠረጴዛ ጋር እንዳይጋጭ እየተጠነቀቀ ወደፊት ተራመደ::ጳጳሱ ክፍለ ውስጥ ጥግ ይዘው ተኝተው በኃይል ሲተነፍሱ አዳመጠ፡፡በድንገት ቆም አለ:: ከጳጳሰ አልጋ አጠገብ ደርሷል፡፡
ቶሉ የደረሰ መሰለው::አንዳንድ ጊዜ ተፈጥሮ የምንሠራውን ሥራ ለማራገብ ከእኛ ጋር ታብራለች:: ለግማሽ ሰዓት ያህል ደመና ጨረቃን በመጋረድዋ አካባቢው
ጨልሞ ነበር፡፡ አሁን ግን ልክ እንደተማከረ ሰው ዣን ቫልዣ ከጳጳሱ አልጋ አጠገብ እንደቆመ ደመና ለጨረቃ ቦታዋን ለቀቀች:: የጨረቃ ብርሃን በመስኮት በኩል ዘልቆ በመግባት ከጳጳሱ የገረጣ ፊት ላይ አበራ:: ጭልጥ
አድርጎ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። የሌሊቱ ብርድ ከባድ ስለነበር ወፈር ያለ የሌሊት ልብስ ለብሰው በጀርባቸው ተዘርረው ነው የተኙት፡፡ ስንት ደግ ሥራ የሠራው ታማኙና ነዳያን የሳሙት እጃቸው ካልጋው ጠርዝ አልፎ ወደመሬት ተንጠልጥሎአል፡፡ ሌላው እጃቸው ከደረታቸው ላይ በማረፉ
የጵጵስና ቀለበታቸው ያበራል፡፡ እዚያ ተጋድመው ሲያይዋቸው መላ አካላቸው የተስፋ ፣ የደስታና የእርካታ ማኅደር እንደሆነ ይናገራል:: በቃላት ለመግለጽ የሚያዳግት የማይታይ ብርሃን ከግንባራቸው ላይ አርፎአል፡፡
የጨረቃው በሰማይ ላይ መንጣለል፤ የምድር በከፊል የተኛች መምሰል ፤ የግቢው አትክልት እርጭ ማለትና የቤቱና የዚያች ሰዓት ፀጥታ እኚህ መለኮት የቀረባቸውን ሰው «አክብሩ አትድፈሯቸው» የሚያሰኝ
ነበር፡፡ ዓይናቸውን ጨፍነው እንደተኙ የነበራቸው ግርማ ሞገስና ለተስፋ ምንጭ የሆነውና በጨርቅ ያልተሽፈነው ግንባራቸው ሲያዩት በፍርሃት የሚያርበደብድ ነበር፡፡

👍19❤1
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
“እንዴት ነህ ጃ?” አልሁት፣ ከተንጋለልሁበት መነሳት የእረጥብ አራስ ያህል እያቃተኝ፡፡ ያቆላመጥሁት ራሱ አልመሰለኝም ማን ብዬ ነዉ ግን የጠራሁት? እንደ እህት ጃ ነዉ ወይስ እንደ ቀበሌ ጃሪም ብዬ? እንጃልኝ
ብቻ።
“ጭራሽ አልጋዬ ላይ?”
"በይ አልጋዬን ልቀቂልኝ ያለ በሚመስል ዓይኑ ጠቅ አድርጎኝ ሲቆም፣ ብድግ ብዬ ከአልጋዉ ላይ ወርጄለት ወደ ራሴ ክፍል ሄድሁ። ምን እንዳለኝ እንኳን ልብ ያልሁት በኋላ ሻንጣዎቹን ወደ ዉጪ ማመላለስ ሲጀምር ነበር።
የእመዋ ቤት ጎስቆል ያለች ብትሆንም፣ አሠራሯ ሁልጊዜም
ያስገርመኛል። ክብ አይሏት፣ አራት ማዕዘን አይሏት፣ የግንብ አይሏት፣
የጭቃ አይሏት፣ ብቻ ግን ሁሉንም ትመስላለች። በዚያ ላይ የሞቀች
ናት፡፡ እኔም፣ ምንም እንኳን ከቤተሰባችን ጋር አባታችንን እየተከተልሁ በዞርሁበት ክፍለ ሀገር የኖርሁባቸዉ ቤቶች ሁሉ የነበረኝ ትዝታ ባይለቀኝም፣ በቅጡ ነፍስ ያወቅሁባት ቤት ናትና እንደዚችኛዋ የሚሆንልኝ ቤት ግን የለም፡፡ ጠባብ ብትመስልም ለእኛ ግን ጠብባን አታዉቅም። በዚች ቤት ሁላችንም የየራሳችን ክፍል አለን፡፡ በእርግጥ በዚች ቤት ያለንን ክፍል መጀመሪያ የያዝነዉ እንደ ዋዛ፣ በሽሚያ ነበር።
ትዝ ይለኛል፤ መጨረሻ ከነበርንበት ከተማ ቀይረን ወደ'ዚች ቤት ልንገባ ደጁን የረገጥነዉ ኅዳር 29፣ ሐሙስ ቀን ነበር።
“በሉ እንግዲህ” አለችን እመዋ፣ ልክ ወደ'ዚች ቤት በራፍ
ከመድረሳችን፣ ቤቷ ወዳሏት ክፍሎች እየለቀቀችን፡፡ “መቼም እንግዲህ አድገናል ብላችኋል። ለየብቻ ማደሩን ከሆነ የጓጓችሁለት ይኸዉ እንዳሻችሁ ሞክሩት ደግሞ። በሉ፤ ኮተቶቻችሁን በየክፍላችሁ አስገቡ”
“በየክፍላችሁ?” አልሁኝ እኔ፣ እንክት ብዬ፡ ያደግነዉ አንድ ሰፊ
ምንጣፍ መሀል ወለሉ ላይ አንጥፈን፣ ተቃቅፈን እየተኛን ነዉ። እየተኛን አልሁ እንጂ፣ የሌሊቱን እኩሌታ እንኳን የምናሳልፈዉ እንዲሁ እንዳዉካካን ነበር። ለወጉ መብራቱን እናጠፋፋና፣ ልብሳችንንም ለዋዉጠን በዚያ ሀገር በሚያህለዉ ምንጣፍ ላይ በጎን በጎናችን እንሆናለን። ከዚያ ተረቡ፣ አሽሙሩ፣ ቀልዱ፣ ተረቱ፣ እንቆቅልሹ፣ እንካ ስላንቲያዉ፣ መሳሳቁ፣ መላፋቱ ይመጣል። ያልሆነዉ ምን አለ? ዛሬ ተረኛ እኔ የሆንሁ እንደሆነ፤ አንዴ በቃል ተረብ፣ ቀጥለዉ በልፊያ፣
ቀጥለዉ ቁንጥጫ ሁሉም ይረባረቡብኛል። ታዲያ ያሉኝን ቢሉኝስ ወንድሞቼንና እህቶቼን ላኮርፋቸዉ? ኧረ በጭራሽ! እንዲያዉም አሁን አሁን ሳስበዉ፣ ተረባቸዉን እና ልፊያቸዉን ሁሉ ለመከላከል አደርገዉ
የነበረዉ መፍጨርጨር ሁሉ ሳይጠቅመኝ አልቀረም። ቢያንስ ቢያንስ ንግግሬ እና ጡንቻዬን አዳብሮልኛል። በዚያም ላይ እኮ እኔ በተራዬ የቀመስኋትን ሁሉ፣ እነሱም በየተራቸዉ ይቀምሷታል።
“በየክፍላችሁ? አረ ምን ዓይነት፣ የማን ሐሳብ ነዉ ግን ይኼ?” አልኋት እመዋን፣ ሆዴን ባር ባር እያለዉ።
“ቀርፋፎ! ይልቅ ተመርጦ ሳያልቅብሽ ክፍልሽን አትመርጪም?” አለችኝ
ኣንደኛዋ እህቴ፣ የራሷን ክፍል መርጣ ማንም እንዳይነካባት ቆልፋዉ ወደኔ እየተመለሰች።
ብቻዬን እንደ ቀረሁ አስተዋልሁ። ሁሉም ይሻለኛል የሚለዉን ክፍል
ተሻምቷል። እኔ እዚህ በትዝታ ወዲያ ወዲህ ስል፣ እንደ ዱሯችን
እንድንተኛ እንድመካከራቸዉ እንኳን የሚሆን አፍታ ሳይታገሱኝ መስኮት ያላቸዉን እና በመስኮት በኩል አሻግሮ ለማየት የሚያመቹትን ክፍሎች ሁሉ ተሽቀዳድመዉባቸዋል፡፡ በተለይ የጃሪም ደግሞ ልዩ ነዉ፡፡ ከመስኮት በተጨማሪ፣ በዚህ በኩል ወደ ዋናዉ ሳሎን የሚያስገባ እና በዚያ በኩል
ደግሞ ወደ ዉጪ የሚያስወጣ በር ያለዉን፣ ሰፊዉን ክፍል ነዉ ተሻምቶ የያዘዉ።
ምንም አማራጭ ስላጣሁ እነሱ ያያዟቸዉን ክፍሎች እየተዟዟርሁ
ስመለከት ቆይቼ፣ ያሉኝን ኮተቶች ሁሉ እየጎተትሁ ወደ ተተወችልኝ
ምራጫ ክፍል አስገባሁባት። ያም ሆኖ ግን እምብዛም አልከፋኝም ነበር። ምክንያቱም፣ ዞሮ ዞሮ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ናቸዉ። ለስሙ ክፍሉ የየራሳቸዉ ቢባልም፣ መቼም በፈለግሁት ክፍል እንዳላድር የሚከለክለኝ
አይኖርም፡፡ እነሱም ለጊዜዉ መስሏቸዉ ነዉ እንጂ፣ በዚህ ምርጫቸዉ እንደሚጸጸቱ ገምቻለሁ። ለአንድ ወይም ላኹለት አዳር ለየብቻ ከሞከሩት
በኋላ ወደ መሀል ወለል መጥተዉ እንደ ዱሯችን አብረን እንተኛ
ማለታቸዉ አይቀርም፡፡ ይኼን ይኼን ሳስብ ትንሽ ቀለል ብሎኝ የነበረ ቢሆንም፣ ዉሎ አድሮ የሆነዉ ግን እንደ ጠበቅሁት አይደለም።
ይኼዉ በእንደዚያ ያለ ሁኔታ የያዝነዉ ክፍል አሁንም ድረስ ድርሻችን እንደሆነ አለ። የኋላ በኋላም ቢሆን፣ ጨክነን የየራሳችንን ቤት ስላልሠራን፣ በዚሁ ቤት ያለዉ ክፍላችን እንደ ተጠበቀ አለ። በርግጥ ገሚሶቹ ወንድሞቼ ወጣ ገባ እያሉ የኪራይ ቤት ኑሮ የሞካከሩ አሉ።
የሆነዉ ሆኖ፣ አሁን የየራሳችንን ሥራ ከያዝን እና የየራሳችን ኃላፊዎች ሆነናል ካልን በኋላም የምንኖረዉ እዚሁ ግቢ ነዉ። ቀን የየራሳችንን ሥራ ስንከዉን ዉለን አዳራችንም በየራሳችን ክፍል፣ በየራሳችን አልጋ ሆኗል። በእርግጥ እኔ ከሌሎቹ በተለየ መልኩ፣ ክፍት ባገኘሁት አልጋ
ሁሉ ነዉ የምተኛዉ። እንዲያዉም ብዙ ጊዜ ክፍት ሳይሆንም ጭምር፣ ጠጋ በሉልኝ ብዬ አብሬ የምተኛበት ጊዜ አለኝ። እያየኋቸዉም እንኳን
ደርሰዉ ንፍቅ በሚሉኝ ሰዓት ስስቴን የማስታግሰዉ፣ እነሱን እቅፍ አድርጌ ትንፋሻቸዉን ስምግ ያደርሁ እንደሆነ ብቻ ነዉ። እንደ ነፍሴ በምሳሳላቸዉ እህቶቼ እና ወንድሞቼ አልጋ ላይ ብተኛ፣ ነዉሩ ምን ላይ እንደሆነ አሁንም አይገባኝም፡፡ በእርግጥ ማንም ከልክሎኝ አያዉቅም ነበር። እኔ እንዲያዉም ደስ የሚላቸዉ ነበር የሚመስለኝ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ማጉረምረም አመጡ፡፡ አንዳንዶች እንደ ጨዋታ እያስመስሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ የሆነች የጀመሯት ነገር አልሳካ ያለቻቸዉ
እንደሆነ፣ ቀድመዉ የሚያላክኩት ወደኔ ሆኗል። የእነሱ ማለት የእኔም ነዉ እያልሁ ባደረስኝ ክፍል ሁሉ ስንት እና ስንት ልብስ እና ጌጣጌጥ ያኖርሁ ቢሆንም፣ አሁን ግን እሱን ጭምር ብላሽ አስቀርተዉብኛል።
“ምነዉ ሻንጣህን ሸካከፍህ፣ ንብረት እያሸሽህ ነዉ'ንዴ ወንድሜ?” አልሁት፣ በእኔ ቤት ቀልጄ ሞቼ ልቤ ዉልቅ እያለ፡፡ ይኼም አልበቃ ብሎኝ እኮ ጥርሴን ለፈገግታ አግጥጨዋለሁ ሳላስበዉ ነፍሰ ጡር እንደሆንሁ፣ ሕይወቴ ምስቅልቅሉ እንደወጣ፣ የእሱ የወንድምነት ምክር
እንደሚያስፈልገኝ ልነግረዉ በልቤ ወስኛለሁ። በመሆኑም የመጨረሻ
ሻንጣዉን አንጠልጥሎ ወደ በሩ ሲጣደፍ ተከተልሁት። ለካንስ ሌላ
ደልዳላ ሰዉ ደግሞ ከበሩ በእዳሪ ሆኖ እየተቀበለ ወደ መኪናዉ
እያጓጓዘለት ኖሯል። ልብ ባልለዉ እንጂ፣ ከልብሶቹ ሌላም የእኔ ናቸዉ የሚላቸዉን እቃዎች ከሳሎን ሳይቀር ለቃቅሞ በመኪናዉ ቀርቅቦ አስጭኖ ጨርሷል። አልጋዉን ራሱ ከምን ጊዜዉ እንዳወጣዉ አላየሁትም።
“ምን እያደረግህ ነዉ አንተ?” አልሁት፣ ልሳቅ አልሳቅ በሚል ቃና።
“ቻዉ!” አለኝ፣ ጥያቄዬን እንዳልሰማ ሁሉ የመኪናዉን የጋቢና በር ከፍቶ እየገባ፡፡
“አንተ ጃሪም! ቆይ እንጂ ወዴት ... ምን እየሆንህ ነዉ?” አልሁት፣
ተንደርደሬ ከፊት ለፊቱ መንገዱን ዘግቼ እየቆምሁበት።
“አይበቃንም ብለሽ ነዉ?”
“ምኑ ነዉ የሚበቃን?”
“ዉሽቱ ሁላ! ለጥቅማችሁ ስትሉ ጠብ እርግፍ አላችሁ እንጂ፣ እኔ እኮ ከዚህ ቤተሰብ አይደለሁም። እናትሽም እናቴ፣ አንቺም እህቴ፣
ዘመዶችሽም ምኔም አይደላችሁም በቃ”
“ምንድነዉ የምታወራዉ?”

👍34❤2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
... ሚሲዝ ሔር እሳቷን አስነድዳ ወንበሯን አስጠጋችና አግሮቿን ከምድጃውጠርዝ ዘርግታ ስትሞቅ ባርባራ ግን አሁንም ሐሳቧ እንደ ተበተነ ልቧ እንደ ተሰቀለ ነበር " በመጨረሻ ከልብስ መስቀያው አንድ የሱፍ ያንገት ልብስ አውርዳ ከትከሻዋ ደረበችና ወጥታ ሔደች የግቢውን የአግር መንገድ ይዛ በቀጥታ ሔዳ ከብረቱ በር ስትደርስ ቆም ብላ ወደ ሕዝቡ ጐዳና ትመለከት ጀመር " ነገር ግን ያ ጐዳና በዚያ ሰዓትና ቦታ፡እንደ ሌላው ጊዜ ሕዝብ አልነበረበትም!ጸጥ ብሎ ነበር
የግንቦት መጀመሪያ ላይ ስለ ነበረ በጣም ቀዝቃዛ ይሁን እንጂ ጸጥ ያለ አስደሳች የጨረቃ ምሽት ነበር።
“ ከቶ መቸ....ይመለስ ይሆን ? አለች ባርባራ ከበሩ ተደግፋ ብቻዋን ስታወራ (እሱ የሌለበት ሕይወት ምን ሕይወት ነው ! አሁን በነዚህ ጥቂት ቀኖች ውስጥ ምን ያህል ተጨነቅሁ ? እንደ ኮርኒሊያ አባባል ከሆነ ለአንድ ቀን ብቻ ነበር የሔደው " ለመሆኑ ወደዚያ ምን ጉዳይ ቢኖረው ነው የሔደው ?
የእግር ዳና ከጆሮዋ ጥልቅ አለ በዚያ ሰዓትና ቦታ ማንም መንገደኛ እንዲያያት አልፈለገችም ስለዚህ ወደ ኋላዋ ምልስ ብላ ከዛፎቹ ጥላ ሥር ተከለለች "
የኮቴው ድምፅ እየቀረበ ሲመጣ ከዚያ በፊት የምታውቀው አረጋጥ መሆኑን ለየችው ስሜቷ ተለዋወጠ ዐይኖቿ በሩ ጉንጮቿ ፍም መሰሉየደም ሥሮቿ
ከደስታዋ ብዛት ነዘሩ እንዳትታይ ተጠንቅቃ በበሩ ቁልቁል ስትመለከት አንድ ረጅም ሰውዬ ከወደ ዌስት ሊን ሲመጣ አየች " የኋሊት ሽሽት አለች እውነተኛ
ፍቅር ድንጉጥ ነው " የባርባራ ሔር ሌሎች ተስጥዎች ያፈቀደውን ቢባሉም ፍቅሯ
ግን ልባዊና ጥልቅ ነበር ከበሩ ሲደርስ ይገባል ብላ ስትጠብቀው ዐልፎ የሚሔድ ይመስል ወደ በሩ እንኳን ዞር ብሎ አላየም " ባርባራ ሐሞቷ ፍስስ አለ እንደገና
ወደበሩ ተጠግታ ፍዝዝ ብላ በጕጒት መመልከት ጀመረች።
በርግጥም ስለሷ ምንም ሳያስብ ወደሷ ዘወር ሳይል ዐልፎ ወደፊቱ ሲገሠግሥ ስታይ በዚያች ቅጽበት በመጣበት የስሜት ግፊት «አርኪባልድ» ብላ ጠራችው።
« ባርባራ ... ሌቦችና ሕገ ወጥ አዳኞች እንዳይቡ እየጠበቅሽ ነው እንዴ ? እንደምነሽ ? » አለ
«እንደምነህ?» አለችው በአንድ በኩል በሩን ከፍታ ይዛ ስታስገባው በሌላ በኩል ደግሞ ከሱ ጋር እጅ ለእጅ ስትጨባበጥ እየገነፈለ ያስጨነቃትን ስሜት ለማመቅ ከራሷ ጋር እየተናነቀች » « መቸ መጣህ ? » አለችው " « አሁን በሁለት ሰዓቱ ባቡር መድረሴ ነው " ላንዳፍታ ከቢሮ ገባሁና አሁን ደግሞ ሚስተር ቦሻምን ለአንድ ጉዳይ ስለምፈልገው ወደሱ እየሔድኩ ነው " በይ ስመለስ እገባ ይሆናል " አሁን ግን ቸኩያለሁ አመሰግናለሁ " »
አዬ አባባና ሚስተር ስፒርነርም ከዚያ ስለአሉ ' ከነሱ ጋር ቆይተው ወደዚህ ለመምጣት በጣም ይመሽብሃል “ እነሱ እንዶሆኑ ከአምስትና ከስድስት ሰዓት በፊት
አይላቀቁም " »
« እነሱ እዚያ ካሉስ ከሚስተር ቦሻም ጋር ያለኝ ጉዳይ የግል ስለሆነ ለነገ ማስተላለፌ ነው » የያዘችውን በር ተቀብሎ ዘጋውና ክንዷን በክንዱ ይዞ ወደቤት
አመሩ እሱ ይህን ያህል የሚቀርባትና የሚይዛት በምንም ስሜታዊ ግፊት ሳይሆን
ከልማዳዊው ትሕትና በመነሣት ማክበሩ ነበር ባርባራ ሔር ግን ክንዷን ከክንዱ አቆላልፋ ጐን ለጐን ሆነው እያነጋገራት ሲሔዱ ኤደን ገነት ውስጥ እንደ ገባች ሆና ሀይሰማት ነበር "
«ታዲያስ ባርባራ ... ... ... በነዚህ ጥቂት ቀኖች ውስጥ እንዴት ሰነበታችሁ?
« መሔድህን ሳንሰማ ምን ነገር ነው ድንገት ብድግ አድርጎ የወሰደህ ? »
« ተናርሺው እኮ ባርባራ!...... ... አንድ ያልታሰበ የሥራ ጉዳይ ተፈጠረ ሔድኩ »
« ኮርኒሊያ ግን ለአንድ ቀን ብቻ መሔድን ነበር የነገረችኝ»
« አለችሽ እንዴ ? ለንደን ከደረስኰ በኋላ ብዙ የምፈጽማቸው ነገሮች
ገጠሙኝና ቆየሁ " ሚስዝ ሔር እንደምን ስነበቱ ? »
« እሷ ያው ናት እኔስ ግማሾቹ በሽታዎቿን በሐሳቧ የፈጠረቻቸው ይመስሉኛል " አሁን በግድ እየተነሣች ብትንቀሳቀስ ይሻላት ነበር " ምንድነው ከሱ ጠቅለህ የያዝከው ? »
« ሚሲዝ ሔርን እንጂ አንቺን ስለማይመለከት አትጠይቂኝ " »
« ለእማማ ያመጣህላት ነገር ነው ማለት ነው አርኪባልድ ? »
« አዎን ' አንድ ገጠሬ ለንደን ከደረሰ ለወዳጆቹ ምን ስጦታ ይዞላቸው እንደሚመለስ ነው የሚያስበው " የጥንት ወጉ ይኸ ነበር " »
« እና አሁን በርግጥ ለእማማ ያመጣህላት ነው? »
« ምነው እየነገርኩሽ …. ባርባራ ላንቺም እንድ ነገር አምጥቼልሻለሁ»
« ምን አመጣልኝ ? » አለችው ፊቷ እንዳመሉ እየቀላ ቀልዱን ይሁን እውነቱን እስክታውቅ ድረስ ሐሳቧ በጕጒት እየተንጓለለ "
« ቀስ በይ እኮ አትቸኩይ !ምን እንደሆነማ ልታይው አይደል » አላትና የያዘውን ጥቅል አጠገባቸው ከነበረ ከአንድ ያትክልት ቦታ ወንበር ላይ አስቀመጠና ኪሶቹን ሁሉ ቢዳብስ አጣ "
« ባርባራ ... ካንዱ ሳልጥለው ቀረሁ ብለሽ ? » አለና እንደገና
ኪሶቹን ሁሉ ፈለገ አራገፈ " በመጨረሻ አንድ ያልታሰበ ኪስ ውስጥ አንድ ነገር ጐረበጠው
«አይ እዚህ አለ መሰለኝ ። ግን እዚህ ምን አመጣው ? » አለና አንዲት ትንሽ ሣጥን አውጥቶ በመክፈት ከውስጧ አንድ ረጂም የወርቅ ሐብል አንሥቶ ባንገቷ አጠለቀላት ከሐብሉ ጋር ባንድ በኰል ጌጥ በሌላ በኩል የጥቃቅን መታስቢያዎች ለመያዣ የሚያገለግል ትንሽ የወርቅ ሙዳይ ተያይዞ ነበር ።
ልቧ በኃይል ሲመታ የፊቷ ቅላት እንደ ልቧ አመታት ቦግ እልም ይል ጀመር አንዲት የምስጋና ቃል እንኳን መተንፈስ አልቻለችም " ሚስተር ካርላይል ያኖረውን ጥቅል አንሥቶ ወደ ሚስዝ ሔር ዘንድ ገባ። ሻማ ባይያያዝም በክፍሉ ሲነድ የነበረው እሳት ቦግ ብሎ በርቶ ነበርዠ።
« መቸም እንዳይሥቁብኝ» አለ ያመጣውን ጥቅል እየፈታ እስከዚህም የረባ ስጦታ አይደለም ብቻ ብዙ ጊዜ ሲመኙት እሰማ ስለ ነበር ከአንድ ሱቅ መስኮት ላይ አይቼ በአየር የሚሞላ መከዳ ነው ያመጣሁለዎ » ብሎ ሰጣት » በመጋደምና በመቀመጥ ሰውነቷ ያለቀው ሚሲዝ ሔር እንደዚያ ያለ ዕቃ ለንደን እንደሚገኝ
ከመስማቷ በቀር ከነማየቷም አታስታውሰውም እንደ ጓጓች ተቀበለችውና በምስጋና ትክ ብላ ተመለከተችው "
« አንዴት ብዬ ነው የማመሰግንህ? » አለችው የደስታ ዕንባ እየተናነቃት
« አስበህ ስለ አመጣሀልኝ አመሰግንሃለሁ»
« አሁን ለባርባራ ስነግራት ነበር " ወደ ለንደን ከሔድን ለወዳጆቻችን ምን ይዘን መመለስ እንደሚገባን ማሰብ እንጀምራለን ባርባራንስ እንዴት እንዳሳመርኳት አዩዋት አይደል ? » አላት ሚስተር ካርላይል "
ባርባራ ሐብሉን ካንገቷ ቶሎ አወለቀችና ከናቷ ፊት አኖረችው "
«አቤት እንዴት ያምራል ልጄ!መቸም ለዚህ ያወጣኸው ገንዘብ ልክ አይኖረውም»
« ኧረ እሱስ ጥቂት ነው ፍሬም የለው» አለ ሚስተር ካርላይል እንደ መሳቅ ብሎ " « እንዴት እንደገዛሁት ላጫውታችሁ የጅ ስዓቴ ማሰሪያ እየተፊታ አስ
ቸገረኝና ወደ አንድ ወርቅ ሠሪ ዘንድ ጎራ ብዬ ነበር በዚያ ብዙ አይነት ሐብሎች ተሰቅለው ሳይ ኮርነሊያና ባርባራ አብረውኝወደ ሊንቦራ ሔደው በነበረ ጊዜ ባርባራ የጠፋባትን ሐብል አስታወሱኝ " ስለዚህ ለባርባራ አንገት የሚስማማውን መርጬ

👍23
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...ሳሎን ሶፋ ላይ እንድንቀመጥ አደረገች። እናቴ ወፍራሙን ፖስታ ሳትከፍተው ገና ማልቀስ ጀመረች ከዚያ በዝግታ የደብዳቤ መክፈቻ አመጣችና በሚንቀጠቀጡ እጆቿ ሦስት ወረቀቶችን ከፖስታ ውስጥ አውጥታ ደጋግማ አነበበቻቸው: እያነበበች እያለ እምባዋ የተቀባችውን ሜካፕ እያበለሻሸ ቀስ እያለ በጉንጮቿ ይወርድ ነበር።
እያየኋት ለስላሳና ማራኪ ገፅታዋ ወዲያው ወደሚያስፈራ ኮስታራነት
እየተቀየረ አፈጠጠችብን፡ ያኔም ቀዝቃዛ ብርድ ታች አከርካሪዬ ድረስ ደርሶ አንቀጠቀጠኝ ከዚያ ልክ ደብዳቤው ላይ ለተፃፈ የሆነ ጥያቄ መልስ የምትሰጥ ይመስል በሚንቀጠቀጡ እጆቿ ወደያዘቻቸው ወረቀቶች እንደገና
ደግሞ ወደ መስኮቱ ተመለከተች
እናታችን እንግዳ የሆነ ፀባይ እያሳየችን በመሆኑ ስለተደናገርን ባልተለመደ ሁኔታ ዝም አልን፡ የእናታችንን ምላስ የቆለፈና አይኖቿን ያደነደነው ባለሶስት ገፅ ደብዳቤ ሳይጨመር እንኳን አባት የሌለበት ቤታችን በበቂ ሁኔታ
አስፈራርቶን ነበር ለምን ይሆን እንደዚህ እንግዳ በሆነ አይን የምትመለከተን?
በመጨረሻ ጉሮሮዋን አፀዳችና በተለመደው ለስላሳና ሞቃት ድምፅ ሳይሆን የእሷ በማይመስል ቀዝቃዛ ድምፅ መናገር ጀመረች: “አያታችሁ በመጨረሻ
ለደብዳቤዬ መልስ ፅፋልኛለች: የፃፍኩላት እነዚያ ሁሉ ደብዳቤዎች ላይ...በቃ ተስማምታለች: ሄደን ከእሷ ጋር እንድንኖር ተስማምታለች” አለች።
መልካሙን ዜና ለመስማት ስንጠብቀው የነበረ በመሆኑ ልንደሰት ይገባን ነበር ግን አልተደሰትንም: እናታችን በድጋሚ ወደዚያ ዝምታዋ ተመለሰችና
እዚያው እንደተቀመጠች እኛ ላይ ማፍጠጥ ቀጠለች ምን ሆና ነው? የልብስ ማስጫ ገመድ ላይ የተቀመጡ ወፎች የምንመስል አራት እንግዳ ፍጥረታት
አይደለንም፧ የእሷ ልጆች እንደሆንን አታውቅም?
“ክሪስቶፈር፣ ካቲ፣ አስራ አራትና አስራ ሁለት ዓመት ዕድሜ ላይ ስለሆናችሁ የምለውን ለመረዳት፣ ለመተባበርና እናታችሁን ካለችበት ተስፋ መቁረጥ ለማውጣት በቂ እድሜ ላይ ናችሁ።” መናገሯን ቆም አድርጋ ጣቷን ጉሮሮዋ
ላይ አድረገችና በጭንቀት በከባዱ ተነፈሰች: ለማልቀስ የደረሰች ትመስላለች
ባል የሌላት ምስኪኗ እናቴ በጣም፣ እጅግ በጣም አሳዘነችኝ፡፡
“እማዬ ሁሉም መልካም ነው? አልኳት።
“አዎ ውዴ ሁሉ መልካም” ብላ ፈገግ ለማለት ሞከረች: “ነፍሱን ይማረውና አባትሽ ረጅም እድሜ እንደሚኖርና በቂ የሆነ ንብረት እንደሚያጠራቅም ያስብ ነበር፡ ገንዘብ እንዴት መስራት እንደሚቻል ከሚያውቁ ሰዎች መሀል ስለመጣ እድሜ ቢሰጠው ኖሮ ያቀደውን በትክክል እንደሚፈፅም ምንም
ጥርጣሬ አልነበረኝም ሰዎች ሁልጊዜ መጥፎ ነገሮች ሌሎች ሰዎች ላይ እንጂ እነርሱ ላይ እንደማይደርስ አድርገው የሚያምኑበት መንገድ አላቸው
አደጋዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አንገምትም። በወጣትነት መሞት እንዳለ አንጠብቅም አባታችሁና እኔ አብረን እንደምናረጅ እናስብ ነበር። በአንድ ቀን አብረን ከመሞታችን በፊትም የልጅ ልጆቻችንን እንደምናይ ተስፋ ነበረን::አንደኛችንም፣ ብቻችንን ቀርተን በሌላኛችን ሞት እናዝናለን ብለን አስበን አናውቅም ነበር።
እንደገና በጭንቀት ተነፈሰች “ከዛሬ ቀድመን እየኖርን እንደነበር መናገርh እፈልጋለሁ። ማለቴ ከወደፊታችን ላይ እንኳን ገንዘብ እንበደር ነበር፧ ከማግኘታችን በፊት እናጠፋ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ እሱን እንዳትወቅሱት: ስለ ድህነት በደንብ ያውቅ ነበር። እኔ ግን ስለ ድህነት ብዙም ስለማላውቅ
ጥፋቱ የኔ ነበር። እንዴት ያሞላቅቀኝ እንደነበር ታውቃላችሁ። ይህንን ቤት
ስንገዛ እንኳን የሚያስፈልጉን ሶስት መኝታ ክፍሎች ያሉት ቤት ነው ብሎኝ ነበር። እኔ ግን አራት ካልሆኑ አልኩት። አራትም በቂ አይመስለኝም ነበር።
“ተመልከቱ፣ ይህ ቤት የሰላሳ ዓመት የባንክ ዕዳ አለበት። ውስጡ ያሉት የትኞቹም ዕቃዎች የእኛ አይደሉም መኪኖቹም፣ ወጥቤት ያሉት ዕቃዎችም
ሆኑ የልብስ ማጠቢያው ክፍል ውስጥ ያሉት የትኞቹም ነገሮች ሙሉ ዋጋ የተከፈለባቸው አይደሉም”
ፈራን… ደነገጥን፡ ፊቷ ቀልቶ መናገሯን ቆም አደረገችና አይኖቿ የእሷ ውበት አምሳያ የሆነውን የሚያምረውን ክፍል መቃኘት ጀመሩ የሚያምሩት ቅንድቦቿ በመጓጓት አይነት ተኮሳተሩ። “አባታችሁ ተይ እንዳይለኝ ይወደኝ
ነበር ስለሚወደኝም ያሞላቅቀኝ ነበር። እኔም እንዴት ላሳምነው እንደምችል አውቅ ነበር። በመጨረሻ እነዚያ የቅንጦት ነገሮች አስፈላጊዎቻችን እየሆኑ
መጡና እጅ ሰጠ፡ ሁለታችንም ፍላጎቶቻችንን ለማሳካት መንገዶች ነበሩን።
እንግዳ በሆነ ድምጿ የምትናገረውን ከመቀጠሏ በፊት ፊቷ ከባዶ ትዝታዎቿ በአንዱ የተዋጠ መሰለ፡ “አሁን ሁሉም ውብ ነገሮቻችን ተወስደዋል። በህግ ቋንቋ ሁኔታው መውረስ ይባላል የገዛችሁትን ነገር ዋጋውን ከፍላችሁ ለመጨረስ በቂ ገንዘብ ከሌላችሁ እነሱ እንደዚያ ነው የሚደረጉት። ለምሳሌ ያንን ሶፋ ውሰዱ፤ ከሶስት ዓመት በፊት ዋጋው ስምንት መቶ ዶላር ነበር።
ሁሉንም ከፍለን የቀረን አንድ መቶ ዶላር ብቻ ነው: ግን በቃ ይወስዱታል።
ሁሉም ነገር ላይ የከፈልነውን ጭምር እናጣለን ይሄ ደግሞ ህጋዊ አሰራር ነው። የምናጣው እቃዎቹንና ቤቱን ብቻ አይደለም መኪናቹንም ጭምር ነው። ከልብሶቻችንና ከአሻንጉሊቶቻችሁ በስተቀር ሁሉንም እናጣለን ማለት
ነው። የጋብቻ ቀለበቴን እንድወሰደው ፈቅደውልኛል። እኔ ደግሞ ስንተጫጭ የሰጠኝን የአልማዝ ቀለበት ደብቄዋለሁ ስለዚህ እነሱ ለማረጋገጥ ሲመጡ
ለአንደኛቸውም እንኳን የቃልኪዳን ቀለበት እንዳለኝ እንዳትናገሩ፡"
“እነሱ” ማን እንደሆኑ ማናችንም አልጠየቅንም መጠየቅም አልመጣልኝም። ካለፈ በኋላ ደግሞ አስፈላጊ አልነበረም።
ከክሪስቶፈር ጋር ተያየን: ለመረዳት በመፈለግ ውስጥ እንዳልሰምጥ
እየታገልኩ ነበር። እውነታው ግን በትልልቅ ሰዎች የሞትና የዕዳ አለም ውስጥ እየሰመጥኩ መሆኑ ነው። ወንድሜ እጁን ዘርግቶ ያዘኝና ባልተለመደ ወንድማዊ የማረጋገጫ ምልክት ጣቶቼን ጨመቅ አደረጋቸው።
ለማንበብ ቀላል የሆንኩ የንፋስ መጥረጊያ ነኝ አንዴ ዋና አጥቂዬ የሆነው ወንድሜ እንኳን ሊያፅናናኝ የሚፈልገው? ምን ያህል ትልቅ ሰው እንደሆንኩ
ለማረጋገጥና እነሱ ሁሉንም ነገር በመውሰዳቸው ምክንያት የተሰማኝን ፍርሀትና ደካማነት ላለማሳየት ፈገግ ለማለት ሞከርኩ። የትኛዋም ትንሽ
ልጅ በእኔ ክፍል ውስጥ እንድትኖርም ሆነ እኔ አልጋ ላይ እንድትተኛና እኔ በምወዳቸው ነገሮች እንድትጫወት፣ አሻንጉሊቶቼን እንድትነካም ሆነ
በሙዚቃ ሳጥኔ እንድትጫወት አልፈልግም እነዚያንም ይወስዱብኝ ይሆን?
እናቴ የእኔንና የወንድሜን ሁኔታ በቅርበት እየተመለከተች ነበር። ከዚያ እንደገና በቀድሞው ጣፋጭ አነጋገሯ “ልባችሁ አይሰበር፤ እኔ ስነግራችሁ
እንደሚመስለው ያህል መጥፎ አይደለም: አሁንም ገና ትንንሽ ልጆች መሆናችሁን ረስቼ ሀሳብ የለሽ በመሆኔ ይቅር በሉኝ። መጥፎውን ዜና በመጀመሪያ የነገርኳችሁ ጥሩውን ወደ ኋላ አስቀርቼ ነው አሁን ትንፋሻችሁን
ያዙ! ወላጆቼ እጅግ ሀብታሞች እንደሆኑ ስነግራችሁ አታምኑኝም: መካከለኛ ኑሮ የሚኖሩ ሀብታሞች እንዳይመስሏችሁ፤ በማይታመን አይነት በጣም በጣም ሀብታሞች ናቸው! ቨርጂኒያ ውስጥ በሚገኝ ግዙፍ ቤት ውስጥ ነው የሚኖሩት። እንደዚያ አይነት ቤት ከዚህ በፊት አይታችሁ አታውቁም
የተወለድኩትና ያደግኩት እዚያ ነው ያንን ቤ ትዚህ ጋር ስታነፃፅሩት ይሄኛው እንደ ትንሽ ጎጆ ነው

👍39❤1🥰1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
...ይህንን ማሰቡ በራሱ አንቀጠቀጣት፡፡ ወደ ክፍሏ ተመለሰችና ራሷን አረጋግታ ለአባቷ የምትለውን ነገር አሰላሰለች፡፡ ረጋ ማለት አለባት፡፡ እምባ እንደማያሳዝናቸውና ቁጣ ለስድብ እንደሚጋብዛቸው ታውቃለች፡፡ ምራቁን እንደዋጠ ሰው ነው መናገር ያለባት፡፡ ተጨቃጫቂ ከሆነች ቁጣቸውን ይቀሰቅስባቸውና ፍርሃት ተሰምቷት ያሰበችውን ከመናገር ልትታቀብ ትችላለች፡.
እንዴት ብላ ትጀምር? ስለ ወደፊቱ አንድ ነገር ለመናገር መብት
አለኝ?.ትበል።
አይደለም ይሄ ጥሩ አይደለም፡፡ ለአንቺ ህይወት ሀላፊው እኔ ነኝ፧ እኔ ነኝ መወሰን ያለብኝ ይሏታል፡
ምናልባትም ስለአሜሪካ ጉዞ ላናግርህ› ብትል ይሻል ይሆን?
‹ምንም የምንነጋገረው የለም› ይሏት ይሆናል፡
አጀማመሯ ተቃውሞ የማይቀሰቅስ መሆን አለበት፡፡
‹አንድ ነገር ልጠይቅህ› ልትላቸው ወሰነች፡፡ ለዚህም እሺ› ይሏታል፡ ከዚያ በኋላስ? ቁጣቸውን ሳትቀሰቅስ እቅዷ ጋ እንዴት ትጠጋ፡፡ባለፈው ጦርነት የጦር ሰራዊቱ ውስጥ ነበርክ ትበላቸው ይሆን? ፈረንሳይ ውስጥ መዋጋታቸውን ታውቃለች፡፡ እናታችንስ ነበረችበት?› ትበል ይሆን?እናታቸው የቆሰሉ የአሜሪካ ወታደሮችን በፈቃደኝነት ለማከም ለንደን ውስጥ
አገራዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ሁለታችሁም ሀገራችሁን አገልግላችኋል፧ መቼም እኔም ይህን ለማድረግ እንደምፈልግ ልትረዱት ይገባል፣› ማለት ሊኖርባት ነው።
ይህን የአገር ማገልገልን መርህ የሚቀበሉ ቢሆን እንኳን ሌላ ተቃውሟቸውን ሊቀሰቅስ የሚችለውንም ነገር አሰበች፡፡ ጦር ሰራዊቱን እስክትቀላቀል ዘመድ ጋ መቆየት ትችላለች፡ ይህም ለተወሰኑ ቀናት ነው፡፡አሁን አስራ ዘጠኝ አመቷ ነው፡ በዚህ እድሜ ላይ ያሉ ሴት ወጣቶች በቀን
ስድስት ሰዓት ይሰራሉ፡፡ መኪና ለመንዳት፣ ለትዳርም ሆነ ወህኒ ለመውረድ
እድሜዋ ይፈቅድላታል፡ እንግሊዝ ውስጥ እንዳትቆይ የማይፈቅዱበት
ምንም ምክንያት የለም፡
አሁን ያሰበችው ነገር ትክክል እንደሆነ ገመተች። የሚያስፈልጋት ድፍረት ብቻ ነው፡
አባቷ ከንግድ ድርጅታቸው ኃላፊ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ ማርጋሬት ከክፍሏ ወጣች፡ ደረጃውን ስትወርድ በፍርሃት እግሮቿ ራዱ፡፡
አባቷ ለሚቃወማቸው ንዴታቸው የከረረ ሲሆን ቅጣታቸውም የከፋ
ነው፡፡ በሰባት አመቷ አልጋ ላይ በመሽናቷ አሻንጉሊቷን ተነጥቃለች፡፡የአስራ አንድ አመት ልጅ ሳለች አንድ እንግዳ አንጓጣ ቀኑን ሙሉ ፊቷን ወደ ግድግዳ አዙራ እንድትቆይ አድርገዋታል፡ አንድ ጊዜ ተናደው ድመቷን
ከፎቅ በመስኮት ወርውረውባታል፡
አሁን እንግሊዝ ውስጥ
እንደምትቀርና ናዚዎችን እንደምትዋጋ ለአባቷ ብትናገር ምን ያደርጋሉ?
ደረጃውን በፍጥነት ወረደች፤ ነገር ግን የንባብ ክፍላቸው ጋ ስትደርስ
ፍርሃት ዋጣት፡፡ ሲናደዱ፣ ፊታቸው ሲቀላና አይናቸው ሲጎለጎል ታያት፤ጉልበቶቿ ተብረከረኩ፡፡ ራሷን ለማረጋጋት ሞከረች፡፡
አባቷ ያሉበት ክፍል በር ላይ ስትደርስ ቤት ጠባቂዋ ሚስስ አለን አዳራሹን አቋርጣ መጣች፡ ሚስስ አለን የቤት ሰራተኞች አለቃ ስትሆ በስሯ ያሉትን ሰራተኞች አሽቆጥቁጣ ነው የምታስተዳድረው፡፡ ቤተሰቡን በሙሉ ስለምትወድ አገር ለቀው መሄዳቸው በጣም አሳዝኗታል“ የእንጀራ ገመድ ተበጠሰ ማለት ነው፡፡ ለማርጋሬት ያሳየችው ፈገግታ በእምባ የታጀበ ነበር፡፡
ማርጋሬትም ሚስስ አለንን ስታይ ልቧ ተነካ፡፡ ወዲያውኑም የመጥፋት
ዕቅዷ በአዕምሮዋ ውስጥ ቅርፅ እየያዘ መጣ፡፡ ከሚስስ አለን ገንዘብ ትበደርና ቤቱን አሁኑኑ ለቃ የአስር ሰዓት ከሃምሳ ደቂቃውን ባቡር ተሳፍራ ወደ ለንደን ትሄዳለች፧ በአክስቷ በካትሪን ቤት ሌሊቱን ታሳልፍና በጧት የምድር ጦር መምሪያን ትቀላቀላለች፡፡ አባቷ ሲደርሱ እሷ ሰራዊቱን ስለምትቀላቀል ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡
‹እቅዱ በጣም አደገኛና ድፍረት የሚጠይቅ በመሆኑ ሊሳካ አይችልም ብላ ሃሳቧን ከመለወጧ በፊት ‹‹ኦ ሚስስ አለን ትንሽ ገንዘብ ትስጪኛለሽ?
አንድ ነገር ገበያ ሄጄ ልገዛ አስቤ ነበር፤ አባባን ደግሞ መረበሽ አልፈለኩም በስራ ተጠምዷል፣›› አለቻት፡
ሚስስ አለን ሳታመነታ ‹‹እሺ እመቤቴ ምን ያህል ነው የሚፈልጉት? ማርጋሬት ወደ ለንደን ለመጓዝ የባቡሩን ዋጋ አታውቀውም፡፡ ትኬት
ገዝታ አታውቅም፡፡
እንዲያው በግምት ‹‹አንድ ፓውንድ ይበቃኛል›› አለቸ
ወዲያው በሃሳቧ ላደርገው ነው?› አለች፡፡
ሚስስ አለን ከቦርሳዋ ውስጥ ሁለት የአስር ሽልንግ ኖቶት አወጣች
ብትጠይቃት ዕድሜዋን ሙሉ ያጠራቀመችውን ገንዘብ ትሰጣት ነበር፡
ማርጋሬት ገንዘቡን እየተንቀጠቀጠች ተቀበለች፡፡ ይሄ የነፃነቴ ትኬት ይሆን ይሆናል› ስትል አሰበች፡፡ ፍርሃት ልቧን ቢያርደውም እንደ እሳ
የሚንቀለቀል ተስፋ ልቧ ውስጥ ተጫረ፡፡
ሚስስ አለን አገር ለቀው መሄዳቸው አሳዝኗት የማርጋሬትን እጅ
ጭምቅ አደረገች፡፡
‹‹ክፉ ቀን ነው የመጣብን እመቤት ማርጋሬት ለሁላችንም›› አለችና
ሽበት የወረረውን ጭንቅላቷን በሃዘን እየወዘወዘች ወደ ማድቤቷ ሮጠች።
ማርጋሬት በመረበሽ ዙሪያውን ቃኘች፤ አንድም ሰው አይታይም፡፡ ልቧ
ይደልቃል፧ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል፡፡ከተጠራጠረች እቅዷ አፈር ድሜ መብላቱ ነው፡፡ ኮቷን ለመልበስ ጊዜ ሳታጠፋ ገንዘቧን በእጇ ጨብጣ በፊት ለፊቱ በር ወጥታ ሄደች፡፡
የባቡር ጣቢያው ከቤታቸው ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ይርቃል፡፡በመንገድ ላይ የአባቷ ሮልስ ሮይስ መኪና ከኋላ የሚመጣ እየመሰላት
ትደነብራለች፡፡ ምን እንዳደረገች እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ? መጥፋቷ ቢያንስ ከራት ሰዓት በፊት ሊታወቅ አይችልም፡፡ ሚስስ አለን ገበያ መሄዷን ትነግራቸዋለች፡፡
ባቡር ጣቢያ ቶሎ ደረሰች ቲኬት ገዝታ ብዙ ገንዘብ ተርፏታል፡ የሴቶች መቆያ ክፍል ገብታ የግርግዳ ሰዓቱን አየች፡
ባቡሩ ዘግይቷል፡
አስር ሰዓት ከሃምሳ አምስት ሆነ ከዚያም አስራ አንድ እያለ አስራ አንድ ከአምስት ሆነ፡ በዚህ ጊዜ ማርጋሬት ከመፍራቷ የተነሳ እቅዷን ሰርዛ ወደ ቤቷ በመመለስ ጭንቀቷን ማስወገድ እንደሚሻል ተሰማት፡፡
ባቡሩ አስራ አንድ ሰዓት ከአስራ አራት ደቂቃ ላይ መጣ፡፡ አባቷ በአካባቢው አይታዩም፡፡
ማርጋሬት ልቧ በጉሮሮዋ ተወትፎ ባቡር ላይ ተሳፈረችና መስኮቱ ጋ
ቆማ ‹አባቴ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ መጥቶ ይወስደኛል› ስትል ተጨነቀች፡፡
በመጨረሻም ባቡሩ ተንቀሳቀሰ፡፡
ማምለጧን ማመን አቃታት፡፡
ባቡሩ ፍጥነቱን ሲጨምር የመጀመሪያው የደስታ ፍንጣቂ በልቧ ተጫረ፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባቡሩ ጣቢያውን ለቆ ተጓዘ፡፡ ማርጋሬት
መንደሩ ወደ ኋላ ሲጓዝ ስትመለከት ልቧ በድል አድራጊነት ሲግል
ተሰማት፤ አደረገችው፤ አመለጠች፡፡
ወዲያው ጉልበቷ በድካም ተብረከረከ፡፡ መቀመጫ
ዙሪያውን ሲማትር ባቡሩ ሙሉ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ተገነዘበች፡:ሁሉም ወንበሮች ተይዘዋል፤ አንደኛ ማዕረግም ቢሆን፡፡
ወለሉ ላይም የተቀመጡ ወታደሮች ነበሩ፡፡ እሷ ግን እንደቆመች ቀረች፡ ጉዞዋ ቅዠት ቢመስልም በልቧ የሚሰማት ደስታ አልቀነሰም፡፡
በየጣቢያው ባቡሩ ውስጥ ሰዎች ይጠቀጠቃሉ፡ ሪዲንግ ከተማ ላይ
ባቡሩ ሶስት ሰዓት ተገተረና አረፈው፡፡

👍21👎2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ከሎ ከተቀመጠበት ስፍራ ላይ ጕልበቱን ሰብሰብ አድርጎ በመታቀፍ ከንፈሩን እያኘከ የሚተነፍገውን የወይጦ በረሃ የእፅዋት
ሽታ ይምጋል ከየጉድባው ወጥተው ድብልቅልቅ በሚያደርግ ድምፅ የሚያገሱት አንበሶች፣ በቀጭንና ወፍራም ድምፅ ጨለማን ተገን አድርገው ድምፃቸውን በነፃነት የሚያስተጋቡትን የአራዊት
ትርምስ እያዳመጡ ሁለቱም በሐሳብ ተውጠው ቆዩ"
ከዋክብት ሰማዩ ላይ ሆጨጭ ብለው ብርሃናቸውን ብልጭ
ድርግም ሲያደርጉ፣ ገና የተወለደች ጨረቃ ካለአቅሟ ግዙፉን
ጨለማ ከዝሆን ጋር እንደሚታገል ዝንብ በብርሃን ድል ለማድረግ
ከተራራው አናት ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ፣ በበረት የታጎሩት ከብቶች እያመነዠኩ ሲያቃስቱ፣ ካርለትም ሆዷ እየተሸበረ፣
በምትፈጥረው ወኔ ግን እራሷን እየደለለች እንደ ከብቶች ላይ ላይ
እየተነፈሰች ታቃስታለች።
የወይጦ በርሃ በተለይም በቀትር ላይ ሙቀቱ እንደ ደመራ እሳት ይጋረፋል" የአራዊቱና የእፅዋቱ አካል ሳይቀር በሙቀቱ ስለሚቀረና አካባቢው ለየት ባለ ሽታ ይታፈናል" በዚህ ወቅት እንግዳ ሰው እንደ
ውሻ እያለከለከ የሚስበው አየር ፍለጋ አፍንጫውን እንደ አንቴና አቁሞ ያንጋጥጣል። ሆኖም ግን የፀሀይ ማኅበረሰብ፣ ሰጎን፣ አንበሳ፣ የሜዳ ፍየል፣ ጉርኑክና የመሳሰሉት እንስሳት በደስታ ተዝናንተው
ይኖሩበታል።
የወይጦ በረሃ ግለት እየቀነሰ ሲመጣ የፀማይ ማኅበረሰብ አባላት
ከማሳ፣ ከወንዝ፣ ከከብት ጥበቃ፣ ከአደን፣ ከማር ቆረጣ፣ከመንገድ...
ወደየመንደሩ ሲከት፣ ከተለመደው ውጭ ነጭ መኪና፣ ጸጕሯ ረዘም ያለ ነጭ ሴት፣ ልብስ የለበሰ ጠይም ከተሜ መንደራቸው
ውስጥ ድንኳን ከትመው አገኛቸው" በዚያን ወቅት፣ ድፍን የፀማይ ኗሪ ስልክና ሌላ መገናኛ ባይኖርም የሰማው ላልሰማው መልእክቱን በቃል እያስተላለፈ፣ ቤት ለቤት የሚውሉ ሽማግሌና ባልቴቶች ሳይቀሩ «ነጭ በቆሎ» የመሰለችውንና ብልጭልጭ ቅራቅንቦ
የተቀረቀበባትን መኪና፣ ለማየት ጎረፉ።
በካርለት ጸጕርና እጅ ላይ ብዙ የፀማይ «ተመራማሪ» እጆች አረፉበት እንደ አንበሳ ጐፈሬ የለሰለሰ ጸጕር፣ እንደ እብነ በረድ የነጣና የለሰለሰ ገላ፣ የትንባሆ አጢያሽ የመሰለ ጥርስ ሲመለከቱ፣
«ይህች ሰው ምንድ ናት?» ብለው ሲደነቁ ቆዩ። ከመካከል አንዱ፣
«ፈረንጅ ናት» አለ፣ ነቃ ያለው።
«ፈረንጅ...ኡ» አሉ፣ በአድናቆት አፋቸውን እየያዙ“
«አሃ ፈረንጅማ ከሆነች ያች በፍየልና ማር ከነጋዴ
የምንለውጣት የሽጉጥ ጥይት የመሰለችው የፈረንጅ መድኃኒት ትኖራለች» ተባባሉ እርስ በእርሳቸው ከሎ ሆራ ፀማይኛ አይችልም
አንዳንድ ፀማዮች ግን ሐመርኛ ስለሚችሉ መድኃኒቷን እንድትሰጠን
ጠይቅልን አሉት፥ ለምልክት አንድ የ«ቴትራሳይhሊን» እንክብል እያሳዩት" ፀማዮች ካርለትና ከሎ ቋንቋቸውን ባለመቻላቸው በተለይ
ሴቶችና ጎረምሶች ግራ ገብቷቸዋል፣ «ሆሆይ ለካ እናንተዬ ፀማይኛም የማይችል ሰው አለ!» ብለው ተሳልቀዋል።
በዚህ መልክ ራቁታቸውን የሆኑ ሕፃናት፣ ጎረምሳና አዋቂ ወንዶች ግልድም ያገለደሙ፣ ከወገባቸው በታች የለበሱት ቆዳ
መሬት ለመሬት የሚጎተት ትንሽ እንጨት ያለበት ሴቶች ካርለትን እንደ ጉድ ተመለከቷት እሷም እነሱን በተመስጦ እየተመለከተች
የሁለት ወገን ጉዶች ካለ ቋንቋ በጥቅሻ ሲነጋገሩ፣ አንዱ ሌላውን ለመግባባት ሲጣጣር ቆይተው የምሽቱ የአራዊት ትርምስና ጨለማ
ሳያሸብራቸው በየአቅጣጫው በመሄድ ቀስ በቀስ ተበታተኑባት"።
ካርለት፣ hአዲስ አበባው ሒልተን ሆቴል ወደ አርባ ምንጩ በቀለ ሞላ ሆቴል፣ ከአርባ ምንጩ ሆቴል ወደ ድንኳን አዳር እየወረደች
የምትበላውም መጠኑና ዓይነቱ በጣም እየቀነሰ
ቢመጣም፣ በጣም የተቸገረችበት ጉዳይ ሌላ ነበር። እስከ አሁን
እንዳስተዋለችው ፀማይ መንደር ውስጥም ሆነ መንገድ ላይ ሽንት ቤት አላየችም። ለመጸዳዳት ወደ ጫካ ሲገቡ ተመልhታለች" እሷ ደግሞ ጫካ ሄዳ መጸዳዳቱን ሕሊናዋ ሊቀበለው አልቻለም" በጕዞዋ ባሳለፈችው ቆይታ በሶፍት እየተጸዳዳች በማቃጠል፣ እየተጠቀመች
ነው። ሐመር ስትሄድ ግን በዚሁ መልክ መቀጠል የሚቻላት አይሆንም" ሽንት ቤት አስቆፍራ እንዳትጠቀም ለአካባቢው እንግዳ ሁኔታ በመፍጠሯ መልካም ግንኙነት ላይኖራት ነው“ ስለዚህ ሊታይ
በማይችልና መጠነኛ ጥልቀት ባለው ጉድጓድ መጠቀሙን እያሰበችበት ነው።
በእርግጥ እንኳን ካደጉበት ባህል ውጭ ላተወሰነ ጊዜ
ከተከታተሉት ባህልን ለየት ወዳለ ሲገባ የመጨነቅ ስሜት መፈጠሩ
የነበረ ነውና ካርለትም የኢንግላንድ ዘመናዊነት፣ የለንደን ከተማ፣
ማንችስተር የሚገኙት አያቶቿ፣ የወንድና ሴት ጓደኞቿ፣ መዝናኛዎች፣ የጭፈራ ቦታዎች ቀርተው ራቁታቸውን ከሚሄዱ ጥቋቁር ሰዎች፣ ከከብቶች በረት፣ ከፍየልና በጎች ጋጥ አካባቢ መሆንዋ
ሕልም እንጂ እውን ሊመስላት አልቻለም።
ካርለት ወደ ኢትዮጵያ ለጥናት ከመምጣቷ በፊት የአገር ቤቱን ሕይወት ለመለማመድ ወደ ስፓኝ በመሄድ «የስፓኝ በር» ተብላ በምትታወቀው የሁልቫ ከተማ የበጋ መዝናኛዋን በማድረግና ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በብርቱካንና የሱፍ ማሳ አቅራቢያ ተቀምጣ ፀሐይ ላይ ብዙ መቆየት፣ ብርድና፣ ብቸኝነትን ለመለማመድ ሞካክራ ነበር።ያን ጊዜ የወደፊት የጥናት ቦታዋ በአሥር እጅ ከዚያ ሊለይ
እንደሚችል ብትገምትም አሁን ግን ዘጠና ዘጠኝ እጅ ያላሰበችውና
ያልገመተችው ዓይነት ሆነባት"
ካርለት እንዲህ በሐሳብ ጉና ስትንጨዋለል፣ እያንቋረረ
የሚከፈተውን የከሎን ጕሮሮ ስትሰማ ከሰመመኗ ተመለሰች።ከዚያም ዓይኗንና ሕሊናዋን ወደ እሱ መለሰች።፣
እስከ አሁን ከከሎ ጋር ባደረገችው ቆይታ ካላናገሩት የማይናገረው ጥቁሩ ወጣት በራሱ ፍላጎትና አነሳሽነት፣ ሊያወጋት መዘጋጀቱ ሳያስደንቃት አልቀረም።
«ሚንጊ ነኝ» አለ ከሎ ድንገት።
«ምን?» አለች ካርለት፥ የጠቀሰው ቃል አልገባሽ ብሏት
«ሚንጊ ማለት በሐመር ቋንቋ ገፊ ማለት ነው» አሁንም የባሰ ተደነጋገረችI ስለዚህ፣ እንዲግባቡ ለማድረግ ገለጻውን ሰፋ አድርጎ ጀመረ።
«ሕፃን ልጅ በሽማግሌዎች ፈቃድ ይወለዳል።»
«ካለ ሽማግሌ ፈቃድ መውለድ አይቻልም? ለመውለድ የሽማግሌዎችን ፈቃድ እንዴት ይጠየቃል? ሽማግሌ የተባሉት ልዩ
ችሎታ ያላቸው ሰዎች ናቸው?» ካርለት ልጅ ለመውለድ ሲያስፈልግ የሐኪም፣ ካስፈለገም የሥነአእምሮ ጠቢብ ምክር
ሊጠየቅ እንደሚችል ታውቃለች" ይህም ቢሆን ችግር ያለባቸውና
በማኅበራዊ ጠንቅ ውስጥ እንዳይዘፈቁ የሰጉ ሰዎች የሚፈጽሙት እንጂ ለማንኛውም ዜጋ የተደነገገ ሕግ አይደለም" ሆኖም፣ ሽማግሌ የተባሉት ለየት ያለ ችሎታ ያላቸው ይሆናሉ ብላ ገመተች።
«አንችን ለማስረዳት ለኔ ከባድ ነው" በኋላ ቀስ በቀስ
ልታውቂው ትችያለሽ ሽማግሌ የተባሉት ግን በዕድሜና በልምድ
ተደማጭነት ያላቸው ሲሆኑ ማንም የሐመር ማኅበረሰብ ሴት ባሏ ጥሎሽ ጥሎ እሱ ዘንድ ካመጣት በኋላ አንድ ቅል አሸዋና አንድ ቅል
ወተት ይዛ ወደ ክልሉ ሽማግሎች ዘንድ ትሄድና ትመረቃለች"ከዚያም ወተቷን ትሰጥና አሸዋውን የያዘውን ቅል ቤቷ አምጥታ
ግርግም ላይ ታንጠለጥለዋለች" ከዚያ፣ ከባሏ ጋር የግብረሥጋ
ግንኙነት አድርጋ ፅንስ ከፀነሰች፣ ወደ ሽማግሎች ሄዳ መፀነሷን ታስታውቃለች። አንዴ መፀነሷን ሽማግሎች ከሰሙ፣ ባሏና እሷ
ፅንሱ አድጎ ከተወለደ በኋላ ጥርስ ማብቀል እስኪጀምር ድረስ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አይፈጽሙም።»

👍30
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ
እድላችን ነው: አሁን መነሳት ያለበት ጥያቂ አይደለም።
መልሉ የተሰጠ ጥያቄ ጥያቂ ሊሆን አይችልም
ይልቅስ ሁሉንም በፀጋ ተቀብሎ መኖር ነው" ለምን በምን. ላይ ያተኮረ
ሃሳብ ሃሳብ እንዳላት ሊገባው አልቻለም ስለዚህ ደስታው እየኮለመነ ግራ መጋባቱ እያየለ ሄደ።
“ልታነጋግሪኝ የፈለግሽው ምንድን ነው? ፈገግ ለማለት
እየሞከረ በጥሞና ጠየቃት:
“...እንደውሻ ቢያላዝኑ ሰሚ በሌለባት ምድር ለምን
ተወለድሁ! መወለዴን ሳስበው ይቆጨኛል! መሞቴም ያበሽቀኛል፤
ለምን ተወለድኩና ለምንስ ደግሞ እሞታለሁ። ስወለድም ለሞት
የምኖረውም ለሞት... አይኖችዋ ድንገት በእንባ ተጥለቀለቁና ቁልቁል ተደፋ: ያን ጊዜ ጨነቀው፡
የሚለበልበው እንባዋ
የማያውቃት ልጅ ድንገት እቤቱ መምጣቷ ብቻ አንሷት እንደበደላት ሁሉ ስታለቅስበት የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፋው።
“የኔ እህት የሶራ ገልቻ ቤት የብሶት መወጫ የበደል
ማራገፊያ ነው ያለሽ ማን ነው?... ደግሞስ እንዲህ ስታለቅሺ ሰው ቢመጣ ምን ይላል? ልቅሶ ካማረሽ ብሶትሽን ማካፈል ከፈለግሽ...”ብሎ በውስጡ የተፈጠረውን ሃሳብ በአእምሮ አዘጋጅቶ ከመቋጨቱ በፊት አናጠባቸው:
“ወኔ ቢስ! ይህን ስትል አታፍርም አይደል! እልህ
ውስጥህ አይንጠውም አይደል! እዚች ሃገር መወለዴ እድሌ መሆኑ ጠፍቶኝ የጠየቅህ ይመስልሃል? እንዴት ያስጨነቀኝ ጥያቂ መለስህልኝ ባክህ ጅል!" ብላ በእልክ እያለቀሰች በስርዓት የተጠቀለለ ፀጉሯን ነጨችው።
“ቆይ እስኪ እንዴ
እኔ አልበደልኩሽ የኔ እህት: አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዲሉ ካለበደሌ..."
ዝም በል! ደሞ አልበደልኩሽ ይላል” በለባጣ ሳቅ ተፍለቀለቀች። ጥርሶችዋ ያምራሉ! እያለቀሰች እንኳን አይኖችዋ
ያንፀባርቃሉ በጣቶችዋ
የምትበትነውኀፀጉሯም ውበቷን አላጎደለውም:
“ጤነኛ ነሽ? ለመሆኑ ከማን ጋር ለምን እንደምትነጋገሪ
ታውቂያለሽ?" አላት ትንሽ መረር ኮስተር ብሎ።
እሷ ግን “እብድ መሰልኩህ? እልኸኛ በመሆኔ በማስመሰያ ግብረገባዊነት በውስጤ የሚንተከተከውን ሃሳቤን ሳላፍን እንደ እሳተ ጎሞራ ፈንድቶ ሲወጣ እየለበለበኝ የሚፈሰው እንባዬን,
ስሜቴን በማካፈሌ እብድ በለኛ! ለነገሩ ማን መርምሮኝ ጤንነቴን
አውቀዋለሁ። አመመኝ ስል አውልቂ እባላለሁ... በሽታዬ ይገኛል እፈወሳለሁ ስል ጭኖቼ ተበርግደው ቆሻሻ ይደፉብኛል” ብላ
በትዝብትና ጥላቻ አየችው።
ከሴት ልጅ የምትፈልጉት ይህን ነው አይደል?!" ቀሚሷን ወደ ላይ ገለበችው:: ፈጣን አይኑ በለስላሳ ጭኖችዋ አልፎ
በለበሰችው ስስ ፓንት ያለውን ነገር ተመለከተ:
“...ይህን እንካ ብልህ እብድ ነሽ! አትለኝም ነበር። ከሃሣቤ ይልቅ ሳያስረዱህ የምታውቀው የስሜት ለሃጭህን የምታዝረከርከው
የሴት ልጅ ጭን ስታይ ነው አይደል!... ብሽቅ! አለችውና
ጭንቅላቷን ያዘች
“..እኔ ምንህም አይደለሁም. የአንተ እህት ግን ጓደኛዬ ናት። እንደ ሎሚ ተመጣ የምትጣል! ጭኖችዋን ለስሜት ሳይሆን ለገንዘብ የምትከፍት! የማታውቀውን ጠረን የምትታጠን... ለመሆኑ ስለእሷና ስለጓደኞችዋ አስበህ አዝነህ... ታውቃለህ? እህትህ ለተጠማው ወንድ ሁሉ በገንዘብ ተገዝታ የምትጠጣ መጠጥ
ተመልሳ ደግሞ እንደ ሽንት ቆሻሻ ላይ የምትሸና ጉድፍ መሆኗን ታውቃለህ?"
እህትህ' ስትል ነደደውና
ሶራ በጥሞና ሲያዳምጣት እንዳልቆዬ ሁሉ እህትህ
“የማን እህት?... የኔ... የኔ እህት?…" አፈጠጠባት: በንቀት እያየችው ቆየችና ረጋ ብላ፦
“ጠባብ በአብራh ክፋይ የምታምን ቂል. ሸርሙጣ እህት የለኝም እያልክ ያን የበከተ እምነትህን በመግለፅ ልትኮፈስ ይሆናል።''
“የኔ እህት ልትሰድቢኝ'ኮ…"
“ዝም በል አንተ?” ባረቀችበት።
“የተማርከው! እንደ ባንዲራ እየዘመራችሁ ወደላይ ስቀሉኝና አየሩ ላይ ልውለብለብ ንፁህ አየር ነፍሴን ያስደስታት የነዳያንን
ጩኸት ወደማልሰማበት ፉከታቸውን ወደማላይበት! ወደላይ ሽቅብ ልውጣ... ባይ ነህ አይደል! እንደ ብዙዎቹ ምስኪን ያገራችን
ምሁራን፡
“የኛ መማር ከድሃው Uዝብ በተለየ ደሴት ውስጥ ለመኖር ነው። የተማርነውን
ንድፈ ሃሳብ ኮሯጆችን ውስጥ ከተን አንጨምርበት አኝከን አንትፋው ስንውጠው አንታይ!... ብቻ
ተሸክመነው እላይ ወጥተን መውለብለብ ንግግሯን ገታ አድርጋ አየችው አያት፡ ተያዩ ምን እንደሚላት ጠፋው: ውጭልኝ ለማለትም ወኔ አጣ: እሷ ግን ቤቱን ደግማ አማተረች:: አይኗ
ከምኝታው ራስጌ ካለው ኮመዲኖ ባለው የሚማርh ፍሬም ላይ አረፈ።
“ምንድን ነው ይሄ?” ብላ ፈገግ እያለች በንቀት አየችው:
“የቱ?” አላት ወደራስጌው እየተመለከተ
"ዲግሪ ስትቀበል የተነሳኸው ፎቶ! አለችና ሳቀችበት።
“አያምርም! አየ አስተያየት አየ መልክ... አቤት ኩራት!
አሁንም የምፀት ሣቋን ለቀቀችው።
“...ምን ሰራሁበት ብለህ ነው ከራስጌህ ያስቀመጥከው?
መካኒክ የመካኒክነት ሙያ ንድፈ ሃሳብ በመማሩ መፍቻዎቹን ደረቱ
ላይ ደርድሮ ፎቶ ቢነሳ ምንድነው ትርጉሙ? ጉራ ብቻ! ሥራበት አዲስ ቅርፅ አዲስ ምርት አምርትበት ጠቅመህ ተጠቀምበት
የተባለውን መፍቻ እንደሰራው ሁሉ ደረቱ ላይ ደርድሮ ፎቶውን ገጭ አድርጎ ግድግዳው ላይ ቢሰቅለው ወይንም እንዳንተ ኮሚዲኖው ላይ ቢያስቀምጠው ፍችው ምንድነው?
ሶራ ተቁነጠነጠ ቀዝቃዛ ላብ በጆሮ ግንዱ ስር ተንቆረቆረ: “...ሌሎች የፈጠሩትን ለማወቅህ ሌሎች ያሉትን ለመስማትህ የተቀበልከውን መተማመኛ
የደረሰህን ለማዳረስ ቃለ መሃላ የፈፀምክበትን ጥቁር ጨርቅና ወረቀት ለሰራኸው ቁም ነገር ለፈፀምከው የስው ልጅ መልካም ተግባር እንደተሰጠህ ሁሉ ቀለሙ በሚጮህ ፍሬም ውስጥ ከተህ ለእይታ ዳረግኸው፡
“ማንነትህ እንዲታወቅ... ያልተማረ እንዳትባል... በሃሣብህ ጨቅላነት የናቀህ ፎቶህን አይቶ እንዲያከብርህ እንደ ፋሲካ ዶሮ አልጋህ ላይ ልታርዳት የምታመጣት ሴት ኧረ የተማረ ይግደለኝ
ብላ በንድፈ ሃሳብ ሞረድ በተሳለው ምላስህ ሳትፈራገጥ
እንድትታረድልህ... ነው አይደል! ዲግሪ የተቀበልክበትን ፎቶ ራስጌህ ያስቀመጥኸው:
“ስትሰራ ህዝቡን ስትረዳ.. የተነሳኸውማ ምን ማስታወሻ አለህ? ማረሻ የያዘና ባዶ እጁን የቆመ ሁለቱም አንዳች ሥራ
እስካልሰሩ ድረስ ምን ለውጥ አላቸው?
“ለመሆኑ ለምን እዚች አገር ተወለድሁ? ከኬንያ
ከታንዛንያ... ያነሰች ደሃ ተብላ በምትናቅ፤ እምትኮራበት ታሪክ
አንጂ ቤሳ ቤስቲኒ ስልጣኔ በሌለባት ሃገር ለምን ተፈጠርሁ ብለህ
ቀንተህ ታውቃለህ ከርሳም ጀብ ድሮ ጅብ ሆዱ ከሞላ በየት አገር ነው የሚቀናው: ሆዱ ከሞላ ባገኘው የቀበሮ ጉድጓድ ገብቶ መጋደም ነው: ክርፋቱ አይሸተው ጥንብ ነው ብሎ አይጠየፍ ስለ ማደሪያው አያስብ…
“በእንዳንተና እኔ አይነት ግዴለሾች ግን ችግር ችግር
እየተከመረ ዋጠን በህሊናና እጆቻችን ሰርተን ከመጠቀም ይልቅ
የህይወት ከርፋት ውስጥ ተጠቅልለን ማልቀስ መጮህ... እጣ ፈንታችን ሆነ" አላችና በሐዘን አንገቷን አቀረቀረች᎓ እንባዋ ዱብ
ዱብ ሲል ታየው: የመጣችበት ጉዳይና የምትናገርበት ምክንያት

👍37❤2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አራት
////
እንዳትሰማኝ ድምፄን ዝቅ አድርጌ‹‹የእውነት አድናቂሽ ነኝ"አልኩ ..እውነቴን ነው ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ብቻዋን ገልብጣ ገድገድ ሳትል ...እኔ ገና በግማሽ ብርጭቆ ጉልበቴ እየተብረከረከ ነው።
ተነሳሁና የተከፈቱ መስኮቶችን መዘጋጋት ጀመርኩ..ማብራቶችን አጠፍሁ፡፡ የሴትዬዎን ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ይዤ ወጣሁና የሆቴሉን በራፍ ቆልፌ ቁልፉን በጥንቃቄ ሚስጥር ኪሴ ውስጥ ሽጉጬ ወደ አልጋ ክፍል አመራሁ...አቀብያት በዛው ወደ ቤቴ ሄዳለሁ ሞባይሌን አውጥቼ ሰዓት ሳይ 7፡40 ይላል።
ደረስኩና አንኳኳሁ...
‹‹ግባ ክፍት ነው››
የሚል ድምፅ ስሰማ ቀስ ብዬ በራፍን ወደ ውስጥ ገፋ አደረኩትና ውስኪ ጠርሙስ የያዘ እጄን አስቀድሜ አንገቴን አሰገግኩ፡ መሀል ወለል ላይ ቆማ ተበትኖ ጀርባዋ ላይ የተኛውን ፀጉሯን አንድ ላይ ጠቅልላ እያሰረችው ነው..ቅድም ለብሳ የነበረውን ጅንስ ሱሪ አውልቃ ስስ የለሊት ቢጃማ ቀሚስ ለብሳለች...፡፡ ቢጃማው ሮዝ ቀለም ሲኖረው አጭር እና በቀላሉ አይን ውስጥ የሚመሰግ ነው...አስተውሎ ላየው ቀሚስ ሳይሆን ቁምጣ ነው የሚመስለው..እና ያ የሚንቀጠቀጥ እና ሊፈርጥ የደረሰ ዳሌዋ በከፊል እርቃን ነው...፡፡
"በራፍ ላይ ተገትረህ ታድራለህ ወይስ ትገባለህ ?"
"እ እሺ ገባለሁ ››አልኩና ወደውስጥ ገብቼ ጠርሙሱን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጬ ለመውጣት ዞር ስል እሷ ከቦታዋ ተንቀሳቅሳ ወደበራፍ እያመራች ነው፡፡
‹‹...ብርድ አስመታሀኝ ››"በሚል ሰበብ ክፍት ጥዬ የመጣሁትን በራፍ ዘጋችና ቆለፈችው፡፡
"ቆይ እኔ ሳልወጣ?"አልኩ ደንግጬ፡፡
"ትንሽ አጣጣኝ እና ትሄዳለህ.. ያውልህ ብርጭቆ…
"ቅዳልኝ" የንግግሯ ቃና ወደ ትዕዛዝ ያዘነበለ ነው.፡፡
ግራ በመጋባትና በመርበትበት እንዳለቺኝ አደረኩና እዛው ጠረጴዛ ጎን ያለ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ..፡፡እሷም ወደእኔ መጣችና ብርጭቆዋን አንስታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች ...፡፡አቀማመጧ በእኔ ትክክል ነው...፡፡አይኔ ወደታች ወደተጋለጠው ጭኗ እየተንሸራተተ አስቸገረኝ ፡፡...እሷ የእኔን ሁኔታ ከቁብም የቆጠረች አይመስልም፡፡ጭኗ እንደሴቶች ጭን ልል እና ለስላሳ አይደለም…፡፡እንደስፖርተኛ የዳበረ እና ፈርጣማ ነው፡፡ሲነኩት ትንቡክ የሚል አይነት ሳይሆን ሲነካ ጭፍልቅ የሚያደርግ አይነት፡፡
"አሁን ጋሼ እንዲህ ከእንግዳ ጋር በውድቅት ለሊት ቤርጎ ውስጥ ገብቼ ዘና ስል ቢያየኝ ምን ይለኛል? ጓደኞቼስ ቢያዩ ተረባቸውን እችለዋለሁ?››
በዝምታ ውስጥ ሆና የቀዳሁላትን ጠጥታ ጨረሰችና ከተቀመጠችበት ተነስታ እራሷ ለራሷ ቀዳች ፡፡..ልትቀዳ ስትል ታከከቺኝ..እናም ደግሞ የተቀባችው ሽቶ ያለፍላጎቴ በአፍንጫዬ ሰርጎ ገባ...እና እየጠጣሁ ካለሁት መጠጥ ጋር ተጋግዞ አነቃቃኝ...፡፡
ወደቦታዋ ተመልሳ ተቀመጠች ፡፡አቀማመጧ ግን እንደቅድሙ እግሮቿን አጣምራ ሳይሆን ፈርክክ አድርጋ ከፍታ ነው፡፡ ...እና በክፍተቱ አይንን ሚያጥበረብር ቀይ ፓንት አየሁ..፡፡ለምን አየህ ?ብላ ተነስታ የምታንቀኝ መስሎኝ ከመርበትበቴ የተነሳ ብርጭቆ ውስጥ ያለችውን መጠጥ በአንድ ትንፍሽ ገርገጭ አድርጌ አጋባኋት፡፡
"በቃ እግዜር ይስጥልኝ አሁን መሸብኝ ልሂድ..›› ለማለት አስቤ ገና አፌን ሳልከፋት ከተቀመጠችበት ተነስታ በድጋሚ ቀዳችልኝ፡፡ ..ለመናገር የተከፈተ አፌን ቀስ ብዬ ዘጋሁትና አንዴ መጠጡን አንዴ እሷን እያፈራረቅኩ ማየት ጀመርኩ።"አሁን ብዥ እያለብኝ ነው..፡፡ሞባይሌን አወጣሁና ሰዓት ተመለከትኩ...8:18 ይላል።
"ምነው መሸብህ እንዴ?"
"አይ አንቺን እንቅልፍ ነሳሁሽ ብዬ ነው"
"ጥሩ አስመሳይ ነህ"አለችኝ.፡፡
‹‹እስቲ በጌታ አሁን እንዲህ ይባላል?››አንገቴን በእፍረት ከማቀርቀር ውጭ ምንም መልስ አልሰጠኋትም፡፡ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደሻንጣዋ በመሄድ መጎርጎር ጀመረች‹‹...ምን ልትሰጠኝ ነው?"ብዬ ሳሰላስል ክሬም ቅባት አወጣችና አልጋ ላይ ወረወረች..መቀመጫዋን ወደ እኔ ፊቷን በተቃራኒው ወደግድግዳው አዞረችና በቆመችበት አጭሩን የለሊት ቀሚሷን ሞሽልቃ አወለቀች።አይኖቼን ጨፈንኩ..ገለጥኩ...መልሼ ጨፈንኩ...ቅድም በስሱ ካየሁት ቀይ ፓንት በስተቀር ምንም የጨርቅ ዘር በሰውነቷ አልቀረም....፡፡ጡቶቾ እንደሩሲያ አስፈሪ ሚሳዬሎች ጫፋቸውን ወደእኔ ቀስረው ልቤን አራዷት ብላችሁ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን እየታዩኝ አይደለም፡፡ፐ!! ከኃላዋ የሚታየው የሰውነቷ ቅርፅ ግን ከአንገቷ በላይ ያለውን መልኳን በሁለት ሶስት እጥፍ ይበልጣል።
ዘለህ ተጠምጠምባት የሚል ስሜት ከሁሉም የስሜት ህዎሳቶቼ ተሰባስቦ ጉሮሮዬ ላይ ተወተፈብኝ... እጇቼ ገላዋን ለመዳሰስ አይኖቼ ከግራ ወደቀኝ እያገላበጠ መላ ሰውነቷን በምስጠት ለመመልከት፤ አፍንጫዬ አንገቷ ስር ተደፍቶ ጠረኗን ወደውስጥ መማግ፤ጆሮዎቼ አፍ አካባቢ ተለጥፈው ከአንደበቷ የሚወጣውን ሹክሹክታ በፅሞና ለማዳመጥ እና እንትኔ ደግሞ ጭኖቾን ፈልቅቆ ወደ ውስጠቷ መስመጥ ፈለገ(ውይ እንትኔ ለካ የስሜት ህዋሳቴ አይደለም...ነው እንዴ?)
ዘፍ ብላ በሆዷ አልጋው ላይ ተኛች...አሁን በህይወቴ በአካልም በፊልምም ጭምር ካየኋቸው ባለ እርቃን ሴቶች ሁሉ ተወዳዳሪ የሌላት ፍፅም አማላይ ሆና ታየችኝ፡፡.. ፀጉሯ ብትን ብሎ ከፊል ጀርባዋን እና የተንተራሰችበትን ትራስ ሸፍኖታል..፡፡ከዛ ወረድ ስንል ልምጥ ብሎ የሚታየው ወገቧ የሩብ ጨረቃን ቅርፅ ይዞ አይንን ያፈዛል ፡፡..ከዛ ሽቅብ ወደላይ ስንወጣ መቀመጫዋ ቀይ ፅጌረዳ አበባ የሸፈናቸው ግዙፍ መንታ ተራሮች ይመስላሉ፡፡..ከዛ በመነሳት ለሁለት ተከፍለው የተዘረጉት እግሮቾ ለምለም መስክ ላይ የተዘረጋ የአክሱም ሀውልትን ይመስላሉ...እጣቶቾ ደግሞ....
"ትንሽ እሸኝና ትሄዳለህ.."የሚለው ንግግሯ ስለውበቷ ተቀኝቼ ሳልጨርስ ከሀሳቤ አናጠበኝ።
" ሎሺኑን ተጠቀምና እሸኝ.."ደገመችልኝ።
"እሸኝ ማለት ምን ማለት ነው..?እንዴት ነው የማሻት..?የሚታሽና የማይታሽ የሠውነት ክፍል ይኖራት ይሆን ?ካሸዋትስ በኃላ የሚከተል ነገር ይኖራል..?በሰከንድ ውስጥ በምናቤ ብልጭ ድርግም ያሉ ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው..፡፡እጆቼን ሰበሰብኩና ወደአልጋው ተራመድኩ፡፡ ጠርዝ ላይ ተመቻችቼ ተቀመጥኩ..፡፡ጃርባዋን ያለበሰውን ፀጉሯን ሰበሰብኩና ወደትራሱ አሻገርኩት...እና ሎሺኑን አነሳሁና ጨመቅ ጨመቅ አድርጌ እጄ ላይ አፈሰስኩና ከትከሻዋ ጀመርኩ...፡፡ይህ ሰውነት ከዚህ በፊት እንደማውቃቸው የሴት ገላዎች የሀር ጨርቅ አይነት ልስላሴ የለውም..፡፡በዳበሩ ጡንቻዎች የተገነባና በጠንካራ ቆዳ የተሸፈነ ልዩ አይነት ሰውነት ነው፡፡ቢሆንም ሲያሹት እጅን ሙልጭ ሙልጭ እያደረገ ቢፈታተንም ደስ ይላል፡፡ ‹‹ አዎ ትግስት ካለኝ ተገልብጣ በጀርባዋ ስትተኛና ከፊት ለፊቷ ያለውን የሰውነት ክፍሏን እንዳሻት ስትመቻችልኝ ቀስ ብዬ ልክ እንደዚህ ሎሺን ጡቶቾን አሸት አሸት እያደረኩ ከውስጣቸው ፍቅር እንዲያመነጩ አስገድዳቸዋለሁ፡፡›› ስል በአይነ ህሊናዬ በመሳል ጎመዣሁ..ምራቄን ገርገጭ እያደረግኩ ዋጥኩ ።

👍54❤1