አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እንዲህ_አይነት_ሰው_አይታችኋል?

ጥርስ እያለው - የማይስቅ
ሐሳብ እያለው
የማይጠይቅ፤
አፍ እያለው - ማያወራ
እጅ እያለው - የማይሰራ::

ዝም ብሎ
አይኑ ብቻ ሚንቀዋለል
በአውራ ጎዳና ሚንገዋለል፧
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?

ጤነኛ መሳይ - ግን ያበደ
ብቸኛ ፍጡር - የተካደ፤
መንገደኛን በአይኑ ሲከተል
ህዝብ ቆጣሪ የሚመስል፤
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?

ስሜት ያለው የማይመስል
በሰው አሽሙር ልቡ ማይቆስል፤
እሾህና አስፓልት የማይመርጥ
እግሩ የትም የሚረግጥ፤
ማዶ ማዶውን እያየ
ከገሃዱ ዓለም የተለየ፤
እንዲህ አይነት ሰው አይታችኋል?