#ፉግር (እድለ-ቢስ)
ጅብ አያ ልክስክስ ፤
ካሰበው እስኪደርስ
የልቡን እስኪያደርስ፣
አንከስ
አንከስ
አንከስ....
አንክሶም አልቀረ፣
መጣ ተመልሶ
የልቡን አድርሶ፡፡
ማሙሽ እንኳ መጥቆ
በማልቀስ ፍላጎት - እንደሚሟላ አውቆ ፤
ልቡ የሻታትን - እስኪያገኛት ድረስ
ማልቀስ
ማልቀስ
ማልቀስ....
አልቅሶም አልቀረ፣
ተሳካ ምኞቱ
በየዋህ እናቱ፡፡
ልቤ ግን ፋግሩ፣
ወይ ላይዝ አንክሶ
ላያገኝ አልቅሶ
ከሄደበት ቦታ-
እያጨበጨበ መጣ ተመልሶ፡