አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የድንቄ_ኑዛዜ

አባ ምንተስኖት እና የሰፈር አዛውንቶች ለምን የጎረቤታችንን የድንቄን ኑዛዜ እንድንሰማ እንደፈለጉ ለጊዜው አልገባንም፡፡ ድንቄ አለኝ የምትለው ልጅ እስከ አሁን ብቅ አላለም፡፡ በሰፈሩ ውስጥም እሱን ያየ ወይም ስለሱ የሰማ የለም፡፡ የንስሐ አባቷ የሆኑት አባ
ምንተስኖት ድንቄ ለልጇ የሰጠችውን ኑዛዜ ሊያሳውቁን በቦታው እንድንገኝ ባደራ ጭምር አስጠንቅቀውናል።

አባ ምንተስኖትንና የማናውቀውን የድንቄን ብቸኛ ወራሽ ልጅ በጉጉት መጠበቅ ጀመርን፡፡ ሁሉም የራስ የራሱን ወሬ ይዟል፡፡እኔም አልፎ አልፎ እነሱ የሚያወሩትን እያዳመጥኩ በራሴው
ትዝታ እቆዝማለሁ፡፡

ድንቄ እንደ ጎረቤቷ ሳይሆን እንደ ልጇ ትወደኝና ትንከባከበኝ ነበር፡፡ እናቴም ድንቄ ለኔ ያላትን ታላቅ ፍቅር ስለምታውቅ ሁልጊዜም ብሄድ አትከለክለኝም፡ስትሞት
ልቆጣጠረው የማልችለው ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል፡፡ ድንቄ በዐይነ ህሊናዬ አዘውትራ ትመጣለች።

የሚያብረቀርቀው ወዟ በጥቁር መልኳ ላይ ሲታይ ፈጣሪ በጥሩ ቅባት ሲወለውላት አድሮ የዋለ ይመስላል፡፡ ዐይኗ የጥንታዊ ስዕሎችን ዐይን አይነት የነጻና ቦግ ያለ ነው። ከንፈሮቿ ሁሌም
ያስደንቁኛል፡፡ በላይኛው ከንፈሯ ብቻ መኸል ለመሀል አግዳ መስመር ቢሳልበት ራሱን የቻለ የአንድ ሰው ከንፈር ይወጣዋል ረጅምና ወፍራም ናት።

“አመድዬ አመዶ መርሻ! መርሻዬ የኔ መርሻ” የኔን ስም እያቆላመጠ ጮክ ብሎ በጎረነነ ድምጽ የሚጣራ ሰው ከድንብ
በስተቀር ማንም እንዳይደለ የታወቀ ነው፡፡

አቀበቱን ጨርሳ ዘቅዘቅ ያለውን የቡሐ መንገድ ስትጀምር እጇን እያጋጨችና ያለርህራሄ በኃይለኛ እርምጃ ቡሐ ድንጋዩን እየደቀደቀች ከመንደር ስትደርስ፣
“መርሻ! መርሻዬ የኔ መርሻ...” እያለች የኔን ድምጽ በጎረነነ ድምጿ ትጣራለች፡፡

ከሰፈር ውስጥ ካሉ ልጆች ሁሉ መርጣ እኔን እንዴት እንደ ወደደችኝ ከድንቄ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም። ምናልባት የራሴ የሆኑ ግምቶች አሉኝ፡፡ ድንቄ የሚያዳምጣትን የሚያጫውታትን
ትወዳለች፡፡ በተጨማሪም ደግሞ፣
“ሌሉቹ ልጆች በልተው ስለሚሄዱ አልፈልጋቸውም።
ለሆዱ ብቻ የማይቀርበኝ አመዶ ብቻ ነው::” ስትል ሰምቻታለሁ።እኔም ደግሞ የአቅሜን ለሷ ከማድረግ ቦዝኜ አላውቅም። ሳላያት ከዋልኩኝ ትናፍቀኛለች። ብርጉድ ብርጉድ የሚሸት ልብሷንና ገላዋን እወድላታለሁ፡፡

ሁልጊዜም እቤታችን ስትመጣ የምትለብሳትን ነጠላ ሳብ አድርጌ አሽትና፣ አንዳንዴም በነጭ ጨርቆች መጣፉ ስለሚገርመኝ፣
“በነጠላ ላይ ነጠላ ይጣጣፋል?” ስላት ወደኔ መቀመጫ በእጇ እያመለከተች "ያንተ ቂጥ ብቻ ነው የሚጣፍ አሐዶ ትለኛለች።"

ደግሞ ሌላ ስራ እሰራለሁ። ከፊቷ ላይ ያለውን ወዝ ጥርግ አደርግና አመድ የመሰለውን እግሬን እባብሰዋለሁ

“አመዶ ተቀባ የኔ ወዝ እንኳን ላንተ ላስር አመዳም ይበቃል፡፡ እ...” ትለኝና ትስቃለች፡፡ ስትስቅ ደስ ትላለች። ጠቅላላ
ፊቷ ላይ ያለው ስጋ ተሰብስቦ ጉንጫ ላይ ይመጣና ይከመራል፡፡ ሳቋ ሳያልቅ የተጠራቀሙ ጉንጮቿን እይዛቸዋለሁ። እሷም ይህንን ስለምታውቅ እንደፈገገች ትቆያለች።

እሷን ከማጫወት ውጭ ሲደክማት የስሙኒ ቫዝሊን እገዛላትና እግሯን ከታጠበች በኃላ በትናንሽ እጆቼ እያሻሽሁ እሷን ማስደሰቴ አይቀርም፡፡

የድንቄ መሳቅና መጫወት ብቻ ለኔ በቂ ደስታ ነው፡፡ሁልጊዜ ድንቄ ስትጣራ ያለአንዳች ከልካይ እወጣለሁ። እሷም ያንን ለምዳዋለች፡ ሮጬ ካልወጣሁ ገስግሳ መጥታ፣ “አመድየ ምን ሆኖ
ነው?” ትላለች።

“እትዬ ድንቄ ምናለ አመዶ ባትይኝ?” እያልኩ ስወተውታት “ምን አይነት ስም ላውጣልህ አመድዬ?” ትልና እንደተለመደው ራሴን ታባብሳለች፡፡

አባ ምንተስኖትና በጉጉት የሚጠበቀው ልጅ አልመጡም፡፡
እናቴና ጎረቤቶቿ የማያቁትን የድንቄን ልጅ እያሽሟጠጡ ያወራሉ፡፡
“አበስኩ ገበርኩ እቴ! እስከዛሬ አይዞሽ ያላላት ልጅ ምን አይነት ይሆን?” አለች እናቴ፣ ሌላኛዋ ጎረቤታችን ቀጠሉ፡፡
“እኔ ብሆን ለማላውቀው ደሃ አወርሳለሁ እንጂ አንድም ቀን መጥቶ አይዞሽ ላላለኝ ልጅ...አላደርገውም።”

“እኛ የምናውቀው እሷንና ይሄን ቤት ያወረሷትን አክስቷን ብቻ ነው። እሷም እኮ የመጣችው እሳቸው ታመው ነው፡፡ እኔና
አክስቷ ይህን መሬት ከመመራታችን በፊት ሌላ አካባቢ አብረን ነበርን፤ ያኔም ቢሆን እሳቸውን ብቻ እንጂ ድንቄን አላውቅም፡፡
ድህነት ያዛትና ቤቱንም አስፋፍታ ሳትሰራ እሳቸው ያወረሷትን አንድ ክፍል ቤት ይዛ ኖረች፡፡ ግቢውን ከፍላ ሸጣ እንኳን ጥሩ ኑሮ ብትኖር ጥሩ ነበር።” አለችና እናቴ የጎረቤቶቿን ወሬ በተራዋ ማዳመጥ ጀመረች፡፡

ድንቄ የምትቀመጥበትን ሶስት እግር በርጩማ እናቴ ተቀምጣበታለች። ድንቄ ስትቀመጥበት መቀመጫዋ በሁለቱም ጎን ይተርፍና ሊወድቅ የተንጠለጠለ ይመስላል። ይህን ትርፍ መቀመጫዋን አልፎ አልፎ መዳበስ ትወዳለች።

አይኔን ሳዟዙር የድንቄን ምግብ ማቅረቢያ፣ በአለላ የተሰራ ስፌት አየሁና ምራቄን ዋጥኩኝ፡፡ ለምን የጨጓራ መረቅ
እንደማያንጠባጥብ ይገርመኝ ነበር፡፡ በልቼ እስከምጨርስ መረቁን ይዞ ይቆያል። ከዚያም ማወራረጃ ውሃ አያሥፈልገኝም።

ድንቄ ጠዋት ተነስታ መተዳደሪያዋ ወደ ሆነው ወደ ልብስ አጠባ ከመሄዷ በፊት የምታደርገው ነገር ቢኖር ገብሩ ስጋ ቤት
መሄድ ነው። ድንቄ የምትፈልገውን መናገር አያሥፈልጋትም፡፡ እንደደረሰች ገብሩ የምታወራውን በፈገግታ እያዳመጠ ጨጓራ በወረቀት መጠቅለል ይጀምራል ። ድንቄ ተቀብላ በእጇ እንደ መመዘን ታደርገዋለች።

“እኔኮ የራሴ ሚዛን እያለ የእጅሽ ሚዛንነት አይገባኝም?”ይላታል፤ አታዳምጠውም፡፡

ነገ ያልቃል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3
#የድንቄ_ኑዛዜ (መጨረሻው)


“እኔኮ የራሴ ሚዛን እያለ የእጅሽ ሚዛንነት አይገባኝም?”ይላታል፤ አታዳምጠውም፡፡

ቤቷ ገብታ እንደፊቷ ወዝ የጠገበች ማሰሮዋ ውስጥ ትጨምርና በላዩ ላይ ጨው በተን አድርጋ እሳት ትማግድበታለች።

ጠዋት ስራ ስትሄድ የጣደችው ጨጓራ በኩበትና በእንጨት ስትመጣ ገራም ሆኖ ይጠብቃታል፡፡ አሁን ጨጓራ የምትጥደው ለኔ ብቻ እስከሚመስለኝ ድረስ የምመገበው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ቁራጭ ጨጓራ ከበላች በአብዛኛው ለኔ
ትሰጠኛለች። በማሰሮ ውስጥ የሚቀራት ትንሽ ነው።

አናቴና ጎረቤቶቿ ከወሬ ወሬ እያፈራረቁ ስለድንቄ ንጽህና ማውራት ጀምረዋል። ንጽህናዋ ሰፈሩን ሁሉ ያስደነቀ ነው። ድንቄ እቤቷ ከሆነች የማታጥበው የማትጠርገው ነገር የለም፡፡ ብቻ ይህን
ለማድረግ በስካር ምክንያት አቅም አይነሳት እንጂ ስትጠርግ ውላ
ስትጠርግ ብታድር ደስተኛ ናት።

አዘውትራ “አምላክ ለደኸ ውሃ ባይሰጠው ጭቅቅቱም ይገለው ነበር!” ትላለች።

የእጇ አስተጣጠብ ስነ ስርአት ግዜውን ስለሚገድለው ያበሳጨኛል፡፡ መጀመሪያ በውሃ ትታጠባለች፡፡ ከዚያ ደግሞ ከቤቷ
ፊት ለፊት ወደ በቀለው ግራዋ ትሄድና ትል ያልበላውን ለምለም ቅጠል ስትበጥስ ትቆያለች። እየቀነጣጠበችና መሬት ላይ ከእጇ አምልጠው የወዳደቁ ቅጠሎች እየለቃቀመች አረፋ እስኪወጣ እጇ ላይ ትደፍቀዋለች፡፡ ውሃውን እጇ ላይ የማንቆርቆሩ ስራ ግን ለኔ ይተዋል። በሆዴ እረግማታለሁ፡፡ ምናለ ቶሎ ብላ ብትሰጠኝ እያልኩ መከረኛ ምራቄን ደጋግሜ እውጣለሁ።ጨጓራውን
ስትሰጠኝ እየተስገበገብኩ ስበላ አልፎ አልፎ፣ “አበስኩ ገበርኩ። ከነጋም ቁርስ አልሰጠችህም እናትህም ትላለች።

የአባ ምንተስኖት ድምጽ ከውጭ ሲሰማ ሁሉም ጨዋታውን አቆመ። እንደተባለው ወራሹን ልጅ ይዘው አልገቡም። ብቻቸውን
ነበሩ። ቁጭ እንዳሉ ወደዋናው ቁምነገር በቀጥታ አልገቡም፡፡ ትንሽ ሲያወሩ ከቆዩ በኋላ ከካፖርታቸው ውስጥ ወረቀት አውጥተው ጉሮሯቸውን ሲጠራርጉ አንድ ነገር ሊያነቡ እንደሆነ የገባት እናቴ፣

“ልጁ ሳይመጣ?” አለች።

አባ ምንተስኖት ሁላችንንም በፍቅር ዐይኖቻቸው ከተመለከቱ በኋላ ንግግራቸውን ጀመሩ።
“ልጆቼ! ድንቄ ይህን ኑዛዜ እናንተ ፊት እንዳነበው አስጠንቅቃ አዛኛለች። በእርግጥም ድንቄ ልጅ አላት። ልጇ ግን
እዚሁ ቅርባችን ነው ፤ እኛ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡

ሁላችንም በድንጋጤና በጉጉት ስናያቸው ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡

“ከመሞቷ በፊት አንድ ሳምንት ሲቀራት እኔና ሌሎች ሁለት ጓደኞቼን ጠራች። እኛም ያለችውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ
አሰፈርነው። ድንቄ ከዛሬ አስራ አምስት ዓመት በፊት ተቀጥራ ትሰራበት ከነበረበት ቤት ባለቤት አንድ ልጅ ወለደች፡፡”
አባ ምንተስኖት አልፎ አልፎ የሚያስላቸው ሳል የኑዛዜውን መጨረሻ በፍጥነት እንዳንሰማ ቢያደርገንም ሳላቸው አስኪያቆም ሁላችንም በያለንበት በጉጉት ጠበቅን፡፡

በመውለዷ የሚያስጠጋትና የሚረዳት ሰው ብታጣ ካለችበት ፍቼ ከተማ አክስቷ ወደ ሚኖሩበት መጣች። መውለዷ ሲነገራቸው ክፉኛ እንደተቆጡ ስትሰማ እንደማይቀበሏት ተረድታ ለረጅም ሰዓት
በለችበት ቆማ አለቀሰች፡፡ ከዚያም አክስቷ ቤት ልትደርስ ጥቂት ሲቀራት የቆመችበትን ቦታ አስተዋለች፡፡ ከአጠገቧ በግንብ የታጠረ ቤት አለ፡፡
ገርበብ ባለው አሮጌ የብረት በር ወደ ውስጥ ተመለከተች፡፡ በአካባቢውም ሆነ በግቢው አንድም ሰው አልነበረም፡፡
እንቅልፍ የወሰደውን የአንድ ወር ህጻን ከበሩ ላይ ቁጭ አድርጋው በፍጥነት ተሰወረች፡፡”

አባ ምንተስኖት ይህን እንደ ተናገሩ እናቴ እራሷን ይዛና ወደ መሬት አቀርቅራ እየየዋን አስነካችው። አባ ምንተስኖት እናቴ ለቅሶዋን እስክትጨርስ ይሁን አላውቅም ዝም ብለው አይዋት፡፡
ከእናቴ በቀር እንደዚያ ሆኖ ያለቀሰ አልነበረም፡፡

“ከዚያም...” ብለው ቀጠሉ አባ ምተስኖት... ከዚያም ያቺ ሴት መሐን ስለነበረችና ብቻዋን ስለምትኖር እግዜር ከሰማይ የላከላትን ልጅ በደስታ ተቀበለች፡፡ ይሄ የሆነው በፊት የድንቄ
አክስት ከሚኖሩበት ቦታ ነበር፡፡ ሰፈራቸው ፈርሶ ወደዚህ መጥተው ሲሰሩ ...”

እናቴ ለቅሶዋ እየጨመረ መጣ፡፡ አባ ምንተስኖት እናቴን በርህራሄ አይተው ጥቂት ዝም ካሉ በኋላ ። የዛሬው ሀብት ወራሽና

የድንቄ ልጅ፣ ተጥሎ የተገኘውና አሳዳጊዋ እናት ሆና ያሳደገችው
ልጅ መርሻ ነበር አሉ።”

ሁላችንም አለቀስን እኔም ሳትወልደኝ፣ እንደ እናት አድርጋ አንድም ሰው ልጂ አይደለም ብሎ ሳይጠረጥር ያሳደገችኝን እናቴን አቅፌ አለቀስኩ። እሷም እሩቅ ሀገር እንደሚሸኙት ሰው ጥብቅ
አድርጋ ይዛኝ ነበር፡፡

💫አልቋል💫
👍2