#እድገትየሰው ልጅ፦
ዳዴ ሲል
ሁሉንም ነገር ወደ አፉ ያስገባል አይጥ ይመስል፤
#በወጣትነትትዕግስት የፈሪዎች ነው ቁጡ ነው የሱ ጀግንነት፤
#በጉልምስናሚናገረውን ሚሰማውን ያመዛዝናል በፅሞና፤
#በእርጅናዳዴ ማለት ይጀምራል ህፃን ይሆናል እንደገና፤
#በሞቱወደ ተሰራበት አፈር ይገባል አፈር ሊሆን እንደ ጥንቱ።
ህይወት ሽክርክሪት ናት ፀንታ የማትኖር አንዱ ጋ
መመለስ ይኖራልና መነሻችንን አንዘንጋ።