#እናትድህነቱ ይዞኝ
ችግሩ በዝቶብኝ
የማስበው ሳጣ ርሃብ ጠንቶብኝ
ዘመድ ጓደኞቼ ሁሉም ርቀውኝ
ሞትን ስሻት ላልኖር ካልጋዬ ተኝቼ
አለው ከማልለው የቁም ሞቴን ሞቼ
ድንገት ከሞት ነቃሁ የእናት ድምጽ ሰምቼ
በችግር ሃዘኔ ሁለተኛ ሟቼ
ስትለኝ ተሰማኝ “የነገ ተስፋዬ
ሀገር ተረካቢ የደስታ ጓዳዬ
የመኖሬ ትርጉም ብቸኛ አላማዬ”
እኔም ተፈወስኩ አስተዋሽ በማግኘቴ
የሞቴ ተጋሪ የኔ ማንነቴ
ሆና ያሳደገችኝ
እናትና አባቴ
የኔ አባባዋ
የኔዋ እናቴ።
🔘ፋሲል ሃይሉ
🔘