፩ ሃይማኖት
#ኢየሱስ_ክርስቶስ_ማን_ነው ? ክፍል ሁለት +++ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ስለመባሉ ከሌሎች ሐዲሳት እነዚህ ክፍሎች ይጠቁሙናል። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። የሐዋ.፪፥፴፮ ወዲያውም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በምኩራቦቹ ሰበከ። የሰሙትም ሁሉ ተገረሙና።…
ነገረ ክርስቶስ(ካለፈው የቀጠለ)
#ክርስቶስን_እንደግል_አዳኝ_አድርገህ_ተቀበለው?
@And_Haymanot
1 «ጌታ ኢየሱስ እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበለው» የሚለው ትምህርት የሰዋሰው የነገረ ሀይማኖትም ስህተት አለበት። «እንደ» የሚለው ቃል በአማርኛ ማነፃፀሪያ ዘይቤ ነው።
«አበበ እንደ ከበደ ወፍራም ነው።» ማለት የአበበ ውፍረት የከበደ ይመስላል ማለት ነው። ይህንን ንፅፅር ለማድረግ ግን አበበና ከበደ የሚባሉ ሁለት ነገሮች ያስፈልጋሉ።
👉«ጌታ ኢየሱስ እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበለው» የሚለው ትምህርት ውስጥ ጌታ ኢየሱስ እና የግል አዳኝህ የተሰኙ ሁለት ተነፃፃሪዎች አሉ ማለት ነው። ስለዚህ ጌታ ኢየሱስን አንድ ከዚህ በፊት ህልው ሆኖ እንዲኖር የግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበለው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ሳይሆን እንደ አዳኝ አድርገህ የምንቀበለው ነገር ነው ማለት ነው።
👉2፣#በመጽሐፍ_ቅዱስም_ሆነ_በአበው_ትምህርት_ውስጥ_የግል_አዳኝ_የሚባል_ትምህርት_የለም። ቅዱስ መጽሐፍ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት በመሰከሩ ቁጥር መድኃኒአለም መሆኑን ነው የሚነግሩን።
•ኢሳ 53፥12 እርሱ የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ ።
•ማቴ 1፥21 እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ ።
•ሉቃ 2፥10 እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኃለሁ ።
•ዮሐ 3÷17 አለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በአለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ አለም አላከውም ።
•ዮሐ 4÷42 እነርሱም በእውነት በእውነት ክርስቶስ የአለም መድኃኒት እንዲሆን እናውቃለን ይሉአት ነበር
•1ኛ ዮሐ 4÷14 አባትም ልጁን የአለም መድኃኒት ሊሆን እንደላከው እንመሰክራለን።
•2ኛ ዮሐ 5፥19 እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ አለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር ።
👉3፣ እያንዳንዱ ሰው ድህነት የተገኘው እግዚአብሔር ለአለም ከሰጠው ድህነት እንጂ ከየአንዳንዱ ሰው የግል ድህነት የአለም ድህነት አልተገኘም። የሰው ልጅ የተፈተነው ይህንን ለአለም የተሰጠ የድህነት ፀጋ ተጠቅሞበታል ወይስ አልተጠቀመበትም በሚል ነው።
👉4፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋውን ቆርሶ ደሙን ቀድሶ በሰጠባት በምሴተ ሐሙስ ለሀዋርያት ማቴ 26÷29 "ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ; ለብዚዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው። "በማለት ደሙ የፈሰሰው ለብዙዎች ኃጢአት መሆኑ ገልጧል።
👉5፣ አዲሶቹ "የግል አዳኝ" የሚለውን አስተምሮ ያገኙት ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ሳይሆን የግለሰብን ነፃነትና መብት መሰረት ካደረገው #ከሊበራል አስተምሮ ነው። በዚህ አስተምሮ መሰረት የነፃነትም የመብትም መሰረቱ ግለሰብ ነው። ይህ አስተምሮ በፖለቲካው መስክ ሊሰራም ላይሰራም ይችላል በነገረ ድህነት ትምህርት ግን አለም በሙሉ ከተሰጠው የመዳን ፀጋ እያንዳዳችን ተካፋዮች እንሆናለን እንጂ ለእያንዳዳችን በየግል ከተሰጠው የመዳን ፀጋ አለም ተካፋይ አትሆንም።
👉6፣ ከሀዋርያትም ከሀዋርያውያን በአበው ከሊቃውትም ይህንን መሰሉን ትምህርት ያስተማረ የለም።
•ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በእየሩሳሌም ለበዓለ ሃምሳ የተሰበሰቡ አይሁድ ለመዳን ምን ማድረግ እደሰለባቸው ሲጠይቁት. ሐዋ 2÷36 "ንስሀ ግቡ"ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ።"አላቸው እንጂ"ጌታን እንደ ግል አዳኝ ተቀበሉ አላላቸውም።
•ሐዋርያው ፊሊጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ሲያጠምቀው"በፍፁም ልብህ ብታምን ተፈቅዶልሀል"አለው እንጂ"ጌታን እንደ ግል አዳን አድርገህ ብትቀበለው ተፈቅዶልሀል አላለውም። ጃንደረባውም የመጀመሪያው የሃይማኖት ምስክርነት/ creed/ የተባለውን "ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ "የሚል ምስክርነት ሰጠ እንጂ ጌታን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ተቀብዬዋለሁ አላለም።
•ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እና ሲላሳ ከእስር ቤት ያወጣቸው ጠባቂ "ጌታ ሆይ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ "በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመን: አንተና ቤተሰቦችህ ትድናላችሁ"አሉት/የሐዋ. 16÷27/ እንጂ ጌታን እንደ ግል አዳኝ አድርገህ ተቀበል አላሉትም።
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
✞ @And_Haymanot ✞
✞ @And_Haymanot ✞
✞ @And_Haymanot ✞
✞ @And_Haymanot ✞
✞ @And_Haymanot ✞
✞ @And_Haymanot ✞
❤ ✞_✞_✞ ❤