#ነገረ_ክርስቶስ ፦
[[[[ሰላም የ፩ ሃይማኖት ተከታታዮች በነገረ ክርስቶስ ላይ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች በተከታታይ ክፍል ትምህርት ያዘጋጀን በመሆኑ እንዲማሩበትና ሼር በማድረግ የቤተክርስቲያንን ምላሽ እንድታደርሱ እንጠይቃለን]]]] #የማርያም_ልጅ_ይርዳን
👉@And_Haymanot
👉@And_Haymanot
ክፍል አንድ
#ኢየሱስ_ክርስቶስ_ማን_ነው ?
@And_Haymanot
ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ የባህሪ ልጅ ነው። በኋለኛው ዘመን ንጽህት ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ተወለደ።
አምላካችን ጌታችን መድኀኒታችን ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ከሆነ በኋላ የተጠራበት ስም " ኢየሱስ " የተባለው ነው።
" ኢየሱስ " የሚለው አጠራር የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙ " አዳኝ " ማለት ነው።
እርሱም ሕዝቡን ከኃጥአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። ማቴ.፩፥፳፩
ከዚህ ስም ጋር እየተቆራኙ የኢየሱስን ማንንነት የሚገልጡ ብዙ ክፍሎች አሉ።
ከብዙዎቹ መካከል ዋና ዋናዎቹን ከአራቱ ወንጌላትና ከሌሎቹ የሐዲስ ኪዳን ክፍሎች ማስረጃዎችን በመጥቀስ እንደሚከተለው እንመለከታለን።
[[[ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው። ]]]
👉 +++ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ስለመሆኑ #ከማቴዎስ_ወንጌል እነዚህ ክፍሎች ይጠቁሙናል።
የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው። እነርሱም አንቺ ቤተልሄም የይሁዳ ምድር ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ካንቺ ይወጣልና ተብሎ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተልሄም ነው አሉት። ት/ሚክ.፭፥፪ ማቴ.፪፥፬-፮
እርሱም(ጌታ)እናንተስ እኔን ማን እንደሆንኩ ትላላችሁ? አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልኽምና ብፁህ ነህ አለው። እኔ እልሃለው አንተ ጴጥሮስ ነህ። በዚህች ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለው። የገሃነም ደጆች አይችሏትም። የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለው። በምድር የምታስረው በሰማይም የታሰረ ይሆናል። በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀመዛሙርቱን አዘዛቸው። ማቴ.፲፭፥፲፮-፳
ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል ? የማንስ ልጅ ነው ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት። እርሱም እንኪያስ ዳዊት ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታዬ ብሎ ይጠራዋል ? ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል ? አላቸው። አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም። ከዚያ ቀንም ጀምሮ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም። ማቴ.፳፪፥፵፩-፵፮
ሕዝቡም ሁሉ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላቹ ትወዳላቹ ? አላቸው። በቅንዓት አሳልፈው እንደሰጡት ያውቅ ነበርና። እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ ስለ እርሱ ዛሬ በሕልሜ መከራ ተቀብያለውና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት። የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ። ገዢውም መልሶ ከሁለቱ ማንኛውን ልፍታላቹ ትወዳላቹ ? አላቸው እነርሱም በርባንን አሉ። ጲላጦስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው ? አላቸው ሁሉም ይሰቀል አሉ። ማቴ፥፳፯፥፲፯-፳፪
👉+++ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ስለ መባሉ #ከማርቆስ_ወንጌል እነዚህ ጥቅሶች ይጠቁሙናል።
ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱም በፊልጶስ ቂሳርያ ወዳሉ መንደሮች ወጡ በመንገድም ሰዎች እኔን ማን እንደሆንኩ ይላሉ ? ብሎ ደቀመዛሙርቱን ጠየቃቸው። እነርሱም መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎቹም ኤልያስ ሌሎቹም ከነብያት አንዱ ብለው ነገሩት። እናንተስ እኔን ማን እንደሆንሁ ትላላቹ ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰለት። ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው። ማር.፰፥፳፯-፴
የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኃ የሚያጠጣቹ ሁሉ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ። ማር.፱፥፵፩
ሊቀ ካህናቱም በመካከላቸው ተነስቶ አንዳች አትመልስምን ? እነዚህስ በአንተ ላይ የሚመሰክሩብህ ምንድን ነው ? ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው። እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰለትም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና። የብሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው። ኢየሱስም እኔ ነኝ የሰው ልጅም በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላቹ አለ ።
ማር.፲፬፥፷-፷፬
👉+++ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ስለ መባሉ #ከሉቃስ_ወንጌል እነዚህ ክፍሎች ይጠቁሙልና።
በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱ ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል። ሉቃ.፪፥፲፩
አጋንንትም ደግሞ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እልሉ እየጮኹም ከብዙዎች ይወጡ ነበር ገሠጻቸውም ክርስቶስም እንደ ሆነ አውቀውት ነበርና እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም። ሉቃ.፬.፵፩
በነጋም ጊዜ የሕዝቡ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቆች ጻፎችም ተሰብስበው ወደ ሸንጓቸው ወሰዱትና ክርስቶስ አንተ ነህን ? ንገረን አሉት። እርሱ ግን እንዲህ አላቸው ብነግራቹ አታምኑም።
ሉቃ.፳፪፥፷፮-፷፯
ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሳርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም። እኔ ክርስቶስ ንጉስ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው ይክሱት ጀመር።
ሉቃ.፳፫፥፪
እርሱም(ጌታ) ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነብያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው። በዚያም ጊዜ መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አዕምሮአቸውን ከፈተላቸው እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙንታ ይነሳል በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲህ ተጽፎአል። እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ
ሉቃ.፳፮፥፵፬-፵፮
👉+++ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ስለ መባሉ #ከዮሐንስ_ወንጌል እነዚህ ክፍሎች ይጠቁሙናል።
ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።ዮሐ.፩፥፲፯
የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩና። እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነብዩ ካይደለህ....እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና። መሢሕን አገኝተናል አለው። ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው። ዮሐ.፩፥፳፬-፵፪
ሴቲቱም ክርስቶስ የሚልባ መሢሕ እንዲመጣ አውቃለሁ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው። ኢየሱስም የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።...የሰማርያ ሰዎችም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ይኖር ዘንድ ለመኑት በዚያም ሁለት ቀን ያህል ኖረ። ስለ ቃሉ ከፍተኞች ይልቅ ብዙ ሰዎች አመኑ ሴቲቱንም አሁን የምናምን ስለ ቃልሽ አይደለም እኛ ራሳችን ሰምተነልዋና እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኀኒት እንደሆነ እናውልለን ይሏት ነበር። ዮሐ.፬፥፳፭-፵፪
ስምዖን ጴጥሮስ ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን ? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።
ዮሐ.፮፥፷፰-፷፱
እንግዲህ ከኢየሩሳሌም ሰዎች አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ። ሊገድሉት የሚፈልጉት ይህ አይደለምን