Forwarded from ተዋህዶ ሃይማኖቴ
✞✞ #ልቦናዬ_በጎ_ነገርን_አወጣ_እኔስ_የማርያምን_ክብር_እናገራለሁ ፡፡በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ፡፡
.
✞ እኔስ የድንግልን ውዳሴ እናገራለሁ መዘንጋት ባለበት
ቃል በማስረዘም አይደለም በማሳጠር ነው እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ በኃጢያት ፍትወት የተፀነሽ አይደለሽም
በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ አንገታቸው እንደሚገዝፍ እንደ
ዕብራዊያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም
በንፅሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ
አይደለሽም ከሠማይ ሠማያት የበሠለ ሠማያዊ ኀብስትን
ነው እንጂ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ካንቺ አስቀድሞ ከአንቺ በኋላም እንዳሉ
ሴቶች እድፍ የምታውቂ አይደለሽም በንፅሕና በቅድስና
ያጌጥሽ ነሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጎልማሶች ያረጋጉሽ
አይደለሽም የሠማይ መላእክት ጎበኙሽ እንጂ፡፡ እንደተነገረ
ካሕናትና የካሕናት አለቆች አመሠገኑሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ለዮሴፍ የታጨሽ ለመገናኘት አይደለም
ንፁሕ ሆኖ ሊጠብቅሽ ነው እንጂ ::
.
✞ እንዲሁም ስለሆነ እርሱ ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር
አብ ንፅሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ
መልአኩን ወደ አንቺ ላከ መንፈስ ቅዱስም በላይሽ
ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል አለሽ እንጂ ፡፡
.
✞ እመቤቴ አንቺን የሚመስልሽ ማንም ምንም የለም
እኛም እንወድሻለን እናገንሻለን፡፡
@Tsere_Tehadso
@Tsere_Tehadso
.
✞ እኔስ የድንግልን ውዳሴ እናገራለሁ መዘንጋት ባለበት
ቃል በማስረዘም አይደለም በማሳጠር ነው እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ በኃጢያት ፍትወት የተፀነሽ አይደለሽም
በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ አንገታቸው እንደሚገዝፍ እንደ
ዕብራዊያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም
በንፅሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ
አይደለሽም ከሠማይ ሠማያት የበሠለ ሠማያዊ ኀብስትን
ነው እንጂ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ካንቺ አስቀድሞ ከአንቺ በኋላም እንዳሉ
ሴቶች እድፍ የምታውቂ አይደለሽም በንፅሕና በቅድስና
ያጌጥሽ ነሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጎልማሶች ያረጋጉሽ
አይደለሽም የሠማይ መላእክት ጎበኙሽ እንጂ፡፡ እንደተነገረ
ካሕናትና የካሕናት አለቆች አመሠገኑሽ እንጂ ፡፡
.
✞ ድንግል ሆይ ለዮሴፍ የታጨሽ ለመገናኘት አይደለም
ንፁሕ ሆኖ ሊጠብቅሽ ነው እንጂ ::
.
✞ እንዲሁም ስለሆነ እርሱ ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር
አብ ንፅሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ
መልአኩን ወደ አንቺ ላከ መንፈስ ቅዱስም በላይሽ
ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል አለሽ እንጂ ፡፡
.
✞ እመቤቴ አንቺን የሚመስልሽ ማንም ምንም የለም
እኛም እንወድሻለን እናገንሻለን፡፡
@Tsere_Tehadso
@Tsere_Tehadso