፩ ሃይማኖት
8.93K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ከጋብቻ በኋላ ግንኙነት የሚከለከለው ለስንት ቀን ነው?

ቤተክርስቲያን አስተምሮ ተክሊል እና ሰርግ የተለያዩ ናቸው። ተክሊል ጋብቻው ሲሆን ስርጉ ደግሞ የተክሊሉ በዓል ነው። በቀደመው የቤተክርስቲያን ትውፊትም ተክሊል ሰርግ በአንድ ቀን አይፈጸሙም ነበር። ቤተክርስቲያን ተጋቢዎች ከጋብቻ /ተክሊል በኃላ ለ40 (አርባ) ቀናት በጾምና በሱባዔ ቆይተው ሰርግ ማድረግ አለባቸው የሚል ትውፊት አላቸው።

የፍትሐ ነገስት አንቀጽ 24 ትርጓሜም በጋብቻ ጊዜ የሚደረገው ሥርዓት ከዘረዘረ በኃላ እሱ ከአባቱ እሷም ከእናቷ ጋር ሲተኙ ይሰነብታሉ ፥ ቊርባኑን በሚሹበት ጊዜ እየሔዱ ይቆርባሉ አርባው ቀን ሲፈጸምም ሰርጉ ያደርጉላቸዋል ፤ ይላል ሙሹሮች ተክሊል ተፈጽሞላቸው ፤አሰቀድሞ ቆርበው ከወጡ በኋላ ወደየቤታቸው ይሔዳሉ ቢል እሱ ከአባቱ ጋር ሴቷም ከእናቷ ጋር የእየተኙ ለአርባ ቀናት ይቆያሉ።

ይህስ ከጋብቻ በኃላ ተለያይቶ መኖር አይገባም ወደ ወንዱ ቤት ይሔዳሉ ብሎ እሱ ከአባቱ ጋር ፤ ሴቷም ከእናቷ ጋር ( ከእናቷ ጋር የሚለውን የሙሸራውን እናት ለሙሽራይቱ አደርጎ መናገር ነው) እየተኙ ይሰናበታሉ ማለት ነው። በአርባ ቀን ውስጥ ሙሽራው ቤተስብ የማሰተዳደርን ሥራ ከአባቱ፣ ሙሽራይቱ ልጅ ወልዶ የማሳደግን ተግባር ከእናቷ (ከሙሽራው እናት ) እየማሩ ፣በመከከሉ እየቆረቡ ይቆያሉ።

በአርባኛው ቀን ሰርግ ይደረግላቸዋል። ይኽውም ጌታ ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ፣ ሕሙማን ነፍስን በትምህርቱ እየፈወስ ከቦታ ፣ ቦታ እየተዘዋወረ ከማሰተማሩ በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ 40 ቀንና ፣40 ለሊት እንደጶም፤ ሐዋርያትም ይህን ዓለም ዕጣ በዕጣ ብለው ተከፋፊለው ወንጌልን ለማሰተማር ከመውጣታቸው በፊት 40 ቀናት እንደጾሙ አብነት በማድረግ ነው።

ሙሸሮች 40 (አርባ) ቀናት የሚለያዬበት ምክኒያት ጾም ጸሎት አድርጎ፤ ሥጋ ወደሙን ደጋግሞ ተቀብሎ ትዳርንና የሚወለደውን ልጅ ለማስባረክ ነው።

እንዲሁ አድርገው ተጋብተው የተወለደው ልጅ መንፈሳዊ ቢሆን እንደ እንጦስ እንደ መቃርስ ፣ ሥጋዊ ቢሆን እንደ ቆስጠንጢኖስ እንደ አኖሬዎስ ይሆናል ፣ እንዲል ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ (24 ገጽ 323 ) ።

ሰርጉ ከተክሊሉ የመለየቱ አሰፈላጊነቱ ደግሞ ሥጋ ወደሙ ተቀብሎ ፎቶ ለመነሣት ከመንገላታት፣ በድካም ምክኒያት ከሙወጣው ላብ ለመጠበቅና ለቅዱስ ቊርባን ሊሰጠው የሚገባው ክብር ለመስጠት ነው። መለያየቱን ምክንያት በማድረግ ሰርጉን ፊጽሞ ዓለማዊ ማደረግ ፣ ከልብስ መራቆትና ዘፈን ግን ተገቢ አይዴልም ።

በስርጉ ዕለት ለክርስቲያን በተፈቀደው መጠን ማጌጥ ፤መደሰት ፤መብላትና መጠጣት አልተከለከለም። ለሌሎች ሕይውት ሓላፊነት ለመውሰድ የሚፈጽሙ ምሥጢራት በጾም በጸሎት ፈቃደ በእግዚአብሔር ሊጠየቅባቸው ይገባል።

ጋብቻ ደግሞ እንዲ የአንዱን ሸክም ለመሽከም፥ልጅ ወልዶ ለማሳደግ የሚገጥም ምሥጢር ሰለሆነ ተጋቢዎች ለአርባ ቀናት እግዚአብሔር ደጅ እየጠኑና እየተማጸኑ መቆየት ይገባቸዋል።

40 ቀን እስኪፈጸም በጾምና በሱባኤ የሚሰነብቱትም እንደ ፍትሐ ነገሥት ከወላጆቻቸው ጋር በመተኛት ነው ። በአሁኑ ነባራዊ ሁኔታ ከእናት አባት እየተኙ ማሳለፍ የሚቻልበት ዕድል ባይመቻች እንኳን ለፈተና በማያጋልጥ ሁኔታ ማሳለፍ ይገባል።

በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያን ትውፊት ጋብቻ ከተፈጸመበት ዕለት እስከ ስርጉ ዕለት (ለ40ቀናት) ግንኙነት ማድረግ አይቻልም። የቤተክርስቲያን ትውፊት ይህ ቢሆንም አሁን ያለው ሥርዓት ስሕተት ነው ማለትም አይደለም ።ይኽውም ተክሊልና ስርግ አንደ ቀን የሚፈጸም ቢሆንም ተዋህዶተ መርዓዊ ወመርዓት (በጥምቱ ትውፊት ጫጉላ) በዕለቱ ሰለሌለ ማለት ነው ትርጓሜ ወንጌል ስርግ ተዋህዶተ መርዓዊ ወመርዓይ የሚደረግበት ነው። ሰለሚል ስርግ ከትክሊል/ ጋብቻ ዕለት የተለየ መሆኑ ግልጽ ነው።ምክኒያቱም ሥጋ ወደሙ ተቀብሎ በዚይምኑ ዕለት ግንኙነት ሊደረግ አይቻልምና።

ጋብቻ በቅዱስ ቍርባን የሚገባው ጥንቃቄ ሊደረግለትም ይገባልና። ቅዱስ ቍርባን ከተቀበሉ በኃላ ለሁለት ቀናት ግኙነት ማድረግ የተከለከለ ነው።

ሁለት ቀን ማለት ለአርባ ስምንት ስዓት ማለት ነው። በምሳሌ ብናየው እሑድ ቅዱስ ቊርባን የተቀበሉ ባልና ሚስት መገናኘት የሚችሉት ዕለቱ ጾም ካለሆን ሐሙስ ነው ማለት ነው ።

ሦስተኛው ቀን ማክሰኞ ቢሆንም ማክስኞ ለረቡዕ አጥቢያ የሚቆጠረው ወድ ረቡዕ ሰለሆን ጾም ነው።

የሁለት ቀን ክልከላው መሠረቱ በሉቃስ ወንጌል ካህኑ ዘካርያስ ቤተ መቅደስ ሲያጥን ብሥራተ ቅዱስ ግብሬኤል ስምቶ አግልግሉቱን ጨርሶ ወደ ቤቱ ከሔደ ከሁለት ቀናት በኃላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ እንደጸነስች ሰለሚናገር በዚሁ መሠረት ነው።

አንድምታ ወንጌሉ ከሁለት ቀን ኖሮ ተገናኝቷታል። ዛሬም ሕጋውያን ሰለ ሥጋ ወደሙ ክብር ለሁለት ቀን ኑረው መገናኘት ይገባቸዋል፤በማለት በግልጽ አሰቀምጦታል።

ወስበአት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲተ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክብር ለዘለአለሙ አሜን
በ ዲ/ን ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
​​ሃያል ነህ አንተ

ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል /2/
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት /2/
በዱራ ሜዳ ላይ........ገብርኤል
ጣዎት ተዘጋጅቶ.......ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ.......ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ.......ገብርኤል
ሲድራቅና ሚሳቅ አብናጎም ፀኑ
ጣዎቱን እረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ተቆጣ ንጉሡ.......ገብርኤል
በሶስቱ ሕፃናት .......ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ.......ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት.......ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መልአኩ
ከሞት አዳናቸው እሳት ሳይነኩ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
እቶኑ ስር ሆነው........ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ........ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው.......ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ.......ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር
አዩ መኳንንቱ የእግዚአብሔር ክብር
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ናቡከደነጾር........ገብርኤል
እጁን በአፋ ጫነ.......ገብርኤል
ሠለስቱ ደቂቅን........ገብርኤል
ከእሳት ስላዳነ.......ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከው መልአኩን
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን.
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንኳን አደረሳችሁ
“ዝክረ ጴጥሮስ ጳጳስ ወሰማዕት ዘምስራቅ ኢትዮጵያ”
=====
(ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ከ1875-1928ዓ/ም) ሐምሌ 22 ቀን ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በአረመኔው ፋሺስት
ኢጣሊያ ሰማዕትነትን የተቀበሉበት ዕለት
@And_Haymanot
የአባታችን በረከት ይደርብን!!!
Forwarded from አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ሽሽታችሁ በክረምት .....እንዳይሆን ፅልዩ
ማቴ [ 24÷20 ]


እንደሚታወቀው በሀገራችን ክረምት ተብሎ የሚጠራው ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ያለውን ያጠቃልላል ፡፡ በዚህ ወራት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን መግቦቱን ቸርነቱን በዝናብ አብቅሎ ማብላቱን ትሰብካለች ፡፡ በተጨማሪም የዳግም ምፅአቱን ነገር አበክራ ትናገርበታለች ፡፡ ምክንያቱም ጌታ ዳግም የሚመጣው የት ነበራችሁ ምን ሰራችሁ ብሎ መዝኖ ዋጋ ሊሰጠን ነውና ፡፡
የፅድቅ ፋሬ አፋርተን ካልጠበቅን መጠጊያ መሸሻ አጥተን የምንጨነቅበት ቀን ነውና ተዘጋጁ ትለናለች፡፡
ታዲያ ወርሃ ክረምት ከዚህ ጋር ምን አገናኝው ስንል እንደሚታወቀዉ ገበሬው በቤት ውስጥ ያለውን እኽል አውጥቶ ዘርቶ በመጀመርያው ቡቃያውን ለማየት ይጓጓል ቀጥሎም ቡቃያውንና ቅጠሉን እያየ ወደፋት ደግሞ አበባና ፍሬን ለማየት ወርኃ ጽጌን በተስፋ ይጠብቃል ፡፡ በዚህ ግዜ ሽሽት ቢመጣ ለመንገድ የሚሆን ስንቅ የለውምና ከባድ ይሆንበታል ፡፡
@pope_shenouda
ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያነም ይህን መሠረት አድርገው ቡቃያና ቅጠል እንጂ ፍሬ በማይገኝበት ክረምት ስደት አስቸጋሪ እንደሆነ ሁሉ መንፈሳዊ ፍሬ ሳናፈራ የጽድቅ ሥራ ሳንሰራ ጌታ ለፍርድ መጥቶ የት ነበራችሁ ??? ምን ሰራችሁ ??? ባለን ጊዜ ምክንያትና ምላሽ እንዳናጣ በሃይማኖት ቁመን ትሩፋት እንድንሰራና መጨረሻየን አሳምርልኝ ፍሬ ሳላፈራ ቀኑ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ እያልን በጸሎት እንድንተጋም ያስተምረናል ።።

@pope_shenouda
@pope_shenouda

ምንጭ [ስምዐ ጽድቅ ]
ፈሪሳውያን ፣ሰዱቃውያን እና ጻፎች ምንድን ናቸው?

👉 ፈሪሳውያን
👉 ሰዱቃውያን
👉 ፃፎች
ሰላም ተወዳጆች ዛሬ በጥያቄያችሁ መሠረት ለተሃድሶ መናፍቃን እና ለሌሎች ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያገኙባቸውን ድህረ ገፆችን እነሆ ለማለት ወደናል፡፡
ኦርቶዶክስ መልስ አላት!!
ㅤዕቅበተ እምነት
👉 ✥ Youtube ✥
✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥
ቅድስት አርሴማ ደጓ እናቴ
👉 ✥ Facebook ✥
✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥
ሐራ ዘተዋሕዶ
👉 ✥ Blog ✥
✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥
፩ ኃይማኖት
👉 ✥ Telegram ✥
እግዚአብሔር አብ
እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ
.
.
.
ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕት ድንግል ማርያም እመ አምላክ
.
.
.
ቅዱሳን መላእክት
ቅዱሳን ሰማዕታት
ቅዱሳን ሐዋርያት
ቅዱሳን መነኮሳት
ቅዱሳን ደናግላን
ቅዱሳን መናንያን
ፓትርያርክ
ጳጳሳት
ኤጲስ ቆጶሳት
ቆሞሳት
ቀሳውስት
ዲያቆናት
ምዕመናን
.
.
.
ቅድሳት መጽሐፍት
ንዋያተ ቅድሳት
ታቦት(መሰዊያ)
ቅድሳት ስዕላት
.
.
.
ዶግማ
ቀኖና
.
.
.
ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን
አእማደ ምሥጢራት
.
.
.
አንዲት ቤተክርስቲያን! የማትታደስ!
@And_Haymanot
እግዚአብሔር ይመስገን ይኽን ቀን ላሳየን ።
@And_Haymanot
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ አባታችን በሰላም ገብተዋል
ደስም ብሎናል
@And_Haymanot
የአባታችን በረከታቸው ይደርብን
መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?
- - - - - - -
መጽሐፍ ቅዱስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ሲሆን ጸሐፊዎቹ ግን ከእርሱ የተላኩ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ ጸሐፊዎቹ ብዛታቸውም ከአርባ በላይ ሲሆን አንዳቸውም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ
አልጻፉም፡፡ “በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” 2ጴጥ 1፡20
- - - - - - -
-+- መጽሐፍ ቅዱስ አሁን በእጃችን ላይ እንዳለው በአንድ የተጠረዘ መጽሐፍ ነበር?
- መጽሀፍ ቅዱስ በአንድ ወቅት በአንድ ጊዜ ተጠርዞ የተሰጠ ወይም ከሰማይ የወረደ ሳይሆን የተለያዩ ክፍሎች በተለያዩ ጸሐፍት እና ዘመናት የተጻፉ ናቸው፡፡ በጥንት ዘመን መጸሀፍት
በጥቅል ተጠቅልልው ይቀመጡ እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች
አሉ፡- ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ ያነበበው የነቢዩ ኢሳያስን ጥቅልል መጽሐፍ ነበረ፡- “የነቢዩን የኢሳያስን መጽሀፍ ሰጡት መጽሐፉንም
በተረተረ ጊዜ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው …….. ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ፡፡ መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ
ሰጠውና ተቀመጠ፡፡” ሉቃ 4፡17-20 ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው ቅዱሳት መጻህፍት ለየብቻቸው በአንድነት
ሳይጠረዙ እንደነበሩ ነው፡፡
- - - - - - -
-+- ቅዱሳት መጻህፍት አሰባሰብ?
-ቅዱሳት ሐዋርያት ስለ ስርዓተ ቤተክርስትያን የተለያዩ ቀኖናትን
ደንግገዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ስለ ቅዱሳት መጻህፍት ነው፡፡ በ325 እ.ኤ.አ በኒቂያ በተካሄደው ጉባኤ ላይ እውነተኖቹን ቅዱሳት መጻህፍት ለመሰብሰብ በተወሰነው መሰረት ቅዱስ
አትናቲዎስ በ367 ዓ.ም በ39ኛው የትንሳኤ ምልዕክቱ ላይ የቅዱሳትን መጽሐፍትን እና አይነት በአብዛኛው አስታውቋል፡፡ ከዚያም በሎዶቅያ በተካሄደ ጉባኤ እና በ393፣399 እና 419
እ.ኤ.አ በሰሜን አፍሪካ ትገኝ በነበረችው ቅርጣግና /ካርቲጅ/ በተካሄዱት ጉባኤዎች ቅዱሳት መጽሐፍትን ለይቶ ለማወቅ ጥረት ተደርጓል፡፡ የካርቴጁ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአንድ ላይ መጠረዝ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል/ጥራዝ/ ተብሎ መጠራት ተጀመረ::
- - - - - - -
- - ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ብዛት ሰማንያ አንድ መሆኑን ትናገራለች፡፡ ዳሩ ግን በዓለም ላይ በብዛት ተሰራጭቶ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ስልሣ ስድስት ነው፡፡

- በስልሣ ስድስቱ ውስጥ የሌሉት መጻሕፍት:-
🔷 ሀ. ከ ብሉይ (2ኛ የቀኖና መጻሕፍት):-
1.መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል
2.መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ
3.መጽሐፈ ጦቢት
4.መጽሐፈ ዮዲት
5.መጽሐፈ አስቴር
6.መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ
7.መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ
8.መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ
9. መጽሐፈ ሲራክ
10.ጸሎተ ምናሴ
11. ተረፈ ኤርሚያስ
12. ሶስና.
13. መጽሐፈ ባሮክ
14. መጽሐፈ ጥበብ
15. መዝሙረ ሰልስቱ ደቂቅ
16. ተረፈ ዳንኤል
17. መጽሐፈ ኩፋሌ
18. መጽሐፈ ሄኖክ
- - - - - - -
🔷 ለ. ከሐዲስ ኪዳን:-
1. ትዕዛዘ ሲኖዶስ
2. ግስው ሲኖዶስ
3. አብጥሎ ሲኖዶስ
4. ሥርዓተ ጽዮን ሲኖዶስ
5. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ
6. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ
7. ቀለሚንጦስ
8. ዲዲስቅሊያ (እነዚህ የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት አሁን በእጃችን በሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም፡፡
ይህም የሆነው እያንዳንዳቸው በጣም ትልቅ መጻሕፍት በመሆናቸው ለማካተት አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ግን ከ81
መጻሀፍት መድበን ነው የምንቆጥራቸው፡፡ ሁሉም መጻህፍት
በቤተክርስትያኖች ቤተ-መጻሀፍት ውስጥ ይገኛሉ እንዲሁም
ገዝቶ ማንበብ ይቻላል፡፡
- - - - - - -
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሕፍት ሳታጓድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትቀበላለች፡፡ ዘመናዊ ነን የሚሉ እምነቶች ግን ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌላ የለም ሲሉ ይሰማሉ፣ ለዚህም የሚጠቀሱት ዩሐንስ ራዕይ መጨረሻው ላይ ያለውን ቃል ነው። ‹‹ማን በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ
መጽሐፍ የተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል››፡፡ ራእይ 22‹18
- ይህን አባባል በጥሞና ስናጤነው የዩሐንስ ራዕይን ብቻ የሚመለከት ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ “በዚህ በትንቢት መጽሐፍ” አለ እንጂ ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አላለም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “የትንቢት መጽሐፍ” ብቻ ሳይሆን የ”ወንጌል” ፣የመዝሙር፣ የመልዕክታት እና የመሳሰሉት መጽሐፍ ነው፡፡
- በተጨማሪ የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጠፍቶ ስለነበር እንደገና ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር ገልጾለት ስለጻፈው " በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር" ብሎ የጻፈው ወጌላዊው ዮሐንስ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው።
- ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው እንደዚሁ አንድ ላይ እንደተጠረዘ ሆኖ የተገኘ አይደለም፡፡ ጻሕፍቱ በተለያየ ዘመን የነበሩ እንደሆነ ሁሉ ፣መጻሕፍቱም በተለያዩ ዘመናት የተጻፉና በአንድ ወቅት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጸሐፍ ተጽፈው አልቀው በጥራዝ መልክ እንደወጡ አድርጎ በመውሰድ የዩሐንስ
ራዕይን ማጠቃለያ ለሁሉም መጻሕፍት አድርጎ መውሰድ አለማወቅ ወይንም ተንኮል ነው፡፡
- - - - - - -
- 👉 መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ፡-
-+- የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት:-
- የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁለት አይነት የቀኖና ክፍሎችን ያካትታል እነሱም ፕሮቶካኒካል እና ዲዩትሮካኖኒካል ይባላሉ፡፡
- (የመጀመሪያ)፡- እነዚህ መጻሕፍት የተሰበሰቡት በካህኑ እዝራ ሲሆን መጀመሪያ በቀኖና መጻሕፍትነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ 1ኛ. መቃብያን 2፡10 “ነህምያም የነገስትን መጻሕፍት
የያዘ ቤተ መጻሕፍት አቋቁሞ ነበር“ እነዚህም መጻሕፍት በ ሶስት ይከፈላሉ እነሱም ቶራህ (አምስቱ ብሔረ ኦሪት) ፣ ነበኢም (ቀደምት ነብያት እና ደኃርት ነብያት) እና ከተቢም (ታላላቅ የታሪክ መጽሐፍትና ታናናሽ የታሪክ መጽሐፍትን ያካትታል) ተብለው ይጠራሉ፡፡ እንዲሁም
- ዲዩትሮካኖኒካል የምንላቸው አይሁድ እንደ ቀኖና መጻሕፍት የማይቀበሉዋቸው ግን እንደ አዋልድ መጻህፍት የሚቀበሉዋቸው ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ
-> አይሁዶች 24 የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ብቻ ሲቀበሉ (የመጽሐፋቸው አቆጣጠር ከእኛ አቆጣጠር ይለያል)
-> ፕሮቴስታንቶች 39 የብሉይ ኪዳን እንዲሁም 27 የሐዲስ ኪዳን ይቀበላሉ፡፡
-> ካቶሊኮች 46 የብሉይ ኪዳን መጻህፍት እና 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ሲቀበሉ እኛ
-> ኦርቶዶክስ ተዋህዶዎች ግን 46 የብሉይ ኪዳን እና 35 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንቀበላለን፡፡ (ከካቶሊኮች ጋር በብሉይ ኪዳን የምንቀበላቸው መጻሕፍት ላይ የአቆጣጠር እና
የመጻሕፍት ልዩነት አለ፡፡)
- እዚህ ላይ ከላይ በግልጽ እንደምንረዳው 81 የነበረው
የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ብዛት ቀስ በቀስ በሰዎች እየተቀነሰ እንዲሁም በነበሩት ጦርነቶች መጻሐፍቱ እየጠፉ
በመምጣታቸው፣ መጀመሪያ 73 እንዲሆን በመቀጠልም ማርቲን
ሉተር ሲያምንበት ከነበረው የካቶሊክ እምነት ፣ከካቶሊክ መነኮሳት ጋር በነበረው የግል ጸብ እና የፖለቲካ ጸብ (የጀርመን ዜጋ ስለነበር የአይሁዶች ጥላቻ ስለነበረው) በነበረው ቅራኔ
ምክንያት 7 መጻህፍትን በገዛ ፈቃዱ ቀንሶ ዛሬ በምዕራብውያን ዘንድ በስፋት የተስፋፋውን እና የእኛን ሐገር ጨምሮ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ሀይል የሌላቸውን ሀገራት የተቆጣጠረውን የ66
መጻሐፍት ሊያስፋፋ ችሏል፡፡ ይቀጥላል ...
፩ ሃይማኖት
Photo
#ጅጅጋ
* በሶማሌ ክልል በደጋህቡር ከተማ ጀረር ዞን የሚገኝ ቤተክርስቲያን ተቃጥሏል
* በጅጅጋ ከተማ የሚገኘው የምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያንም ቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል
* የጅጅጋ ደብረመዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ዝርፊያ ተፈፅሞበታል።
* ክርስቲያኖች እና የሱማሌ ጎሳ ያልሆነ ግድያና ማዋከብ እየደረሰበት ነው
* ሌሎች በአደጋ ላይ ያሉትን ቤተክርስቲያኖች ከአደጋ ለመታደግ የአካባቢው ማኅበረሰብ ድጋፍ ወሳኝ ነው!
" በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:28)
አምላክ ለሀገራችን ለህዝባችን እና ለቤተክርስቲያን ሰላምን ያምጣልን።🙏🙏
@And_Haymanot
ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
( ከተቃጠለው ሕዝብ ይልቅ የአቃጣዩ አያያዝ በሚያስጨንቃቸው
ሰዎች ሥር መኖር ከባድ ነው )
" ዲ/ዳንኤል ክብረት "
በሶማሌ ክልል ሰሞኑን የተሠራው ዘግናኝና አረመኔያዊ ሥራ ነው፡፡ ሰውን በቁሙ ማቃጠል፡፡ ሴቶችን መድፈር፡፡ መኪና ይዞ በየቤቱ እየዞሩ የሰው ንብረት መዝረፍ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል፡፡ ለመሆኑ መንግሥት የለም? አንድ ክልልስ ሥልጣኑ የሰው ዘርን እስከማጥፋት ድረስ ነው? ይህን መሰሉ ግፍ ዚያድባሬ ኢትዮጵያን የወረረ ጊዜ ነበር በምሥራቁ ክፍል የተፈጸመው፡፡ ዚያድባሬ አለ ማለት ነው? የክልሉ ፕሬዚዳንት የልቡን ከሠራ በኀላ ትናንት ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መጥቶ
እንመካከር ሲል ነበር፡፡ ሰው ከተቃጠለ፡ ንብረት ከተዘረፈ፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠለ በኀላ የምን ምከከር ነው? አሁን በዚያ ክልል ስላለው ሕዝብ እንደ አዲስ ማሰብ አለብን፡፡ ሌላ መፍትሔም ማምጣት አለብን፡፡ ከተቃጠለው ሕዝብ ይልቅ የአቃጣዩ አያያዝ በሚያስጨንቃቸው ሰዎች ሥር መኖር ከባድ ነው፡፡

በሰሞኑ ግጭት የተጎዱ አብያተ ክርስቲያናትና ካህናት
1. የዋርዴር ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
ሲቃጠል ቄስ ያሬድ ኅቡዕ ተገደሉ፣
2. ቀብሪ ደኃር ደብረ መድኃኒት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ተቃጥላለች፡፡
3. ደጋሐቡር መካነ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
ሲቃጠል ቄስ ኪዳነ ማርያም ንብረቱ ተገድለዋል፡፡
4. በጅጅጋ የምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል
እና የደብረ ሰዋስው ገዳም የተቃጠሉ ሲሆን
አባ ገብረ ማርያም አስፋው፣ መ/ር አብርሃም ጽጋቡ እና ሌላ
አንድ ካህን ተገድለው አስከሬናቸው ተቃጥሏል፡፡
5. .ጅጅጋ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል
1 ካህን ተገድሏል
6. ጅጅጋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተቃጥሏል
7. ሽላቦ ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲን ተቃጥሏል
8. ጎዴ ቅዱስ ገብርኤል አጥሩ ተቃጥሏል @And_Haymanot
ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
Share
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
​​" አበው በተጋድሎ ያወረሱኝ ቅርሴ
የበረከቴ ምንጭ የስጋ የነፍሴ ፡
ከማንም ከምንም ሀምሳያ የሌለሽ
የዘላለም ቤቴ ጎጆዬ አንቺነሽ ፡
የማትታደሺ የምታድሽ ሁሉን
የምትታደጊው መላ አለሙን ፡
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!.............!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
@And_Haymnot
​​"ፍልሰታ መጣች"
"ሕጻኑም ወጣቱም ወንዱም ሴቱም ዕድሜው የገፋውም
ሁሉም በፍቅር የሚጾሟት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል
ማርያም ረድዔትና በረከት የሚታፈስባት፣ ፍቅረ እግዚአብሔር
በሰው ልቡና የሚሰለጥንባት ፈሪሃ እግዚአብሔር
የሚያይልባት፣ የንሰሐና የምህረት ጾም ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡
በዓለም ያሉ ወደ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ያሉ ወደ
ገዳማት የሚገሰግሱባት ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡"
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
@And_Haymanot
መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?
- - - - - - -
.....የቀጠለ።
> መናፍቃን 81 /ሰማንያ አሃዱ/ መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉባቸው ምክንያቶች እና እንዲቀበሉ የሚያስገድዳቸው ምክንያቶች እንዲሁም ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የሉም እንዳይሉ ማስረጃዎች ፡-
-> ተቃዋሚዎች ከ66 ውጭ መጽሐፍ የለም ቢሉም ሐዋርያት ሆኑ ጌታ ከ81 መጻሐፍት እየጠቀሱ አስተምረዋል፡፡ ይህን እስቲ በማስረጃ እንመልከተው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 1. - ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር ይለናል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (ሉቃ.3፡3) - እንግዲህ ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ30 ዓመቱ በፊት የት ነበረ? ምን እየሰራ ነበረ? ብልን ስንጠይቅ መልሱን በ66 መጻሕፍት ውስጥ ሳይሆን
በቤተክርስቲያናችን የትውፊት መጻህፍት ውስጥ እድገቱምን እንደሚመስል በዝርዝር ተጽፎ እናገኛለን፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 2. - በማቴዎስ ወንጌል 27፡3-10 (በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥
ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ። ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ
ሠላሳ ብር ያዙ፥ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ።) በዚያን ጊዜ የነቢዩ የኤርሚያስ ቃል ተፈጸመ ይለናል ይሁዳ… እንዲህ ያለው ‹‹የእስራኤል ልጆች የተስማሙበትን የክቡርን ዋጋ ሠላሳውን ብር ወሰዱ›› ይህን ቃል የምናገኘው በስድሳ ስድስቱ ውስጥ ሳይሆን በተረፈ ኤርሚስ 7፡ 2-4 ባለው ላይ ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ትንቢተ ኤርሚያስን ጠቅሶ ሲጽፍልን 'በነብዩ ኤርሚያስ የተባለው ብሎን ነው፡፡' ምን
ተባለ ስንል ማቴዎስ ''የተባለውን'' እና ''ተፈጸመ'' ያለንን የምናገኘው መናፍቃኑ አንቀበለውም በሚሉት በ81 መጽሐፍት
ውስጥ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 3. - ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፡፡ ‹‹እንፍጠር›› ሲል ከአንድ በላይ ብዛትን ሲያመለክት 2 ወይም 4 ወይም 10
ሳይሆኑ ስላሴን /ሶስትነት/ ስስት መሆናቸውን የሚነግረን በሲራክ 2፤22 ሄኖክ 5፤38 ሄኖክ 6፤24 ሄኖክ 13፤14 እዝራ ስቱኤል 4፤56 እዝራ ስቱኤል 12፤48 ሲራክ 44፤10 በግልጽ ሥላሴ እያለ በማሳየት ነው፡፡ ክብር ለቅድስት ሥላሴ ይሁን!
_ _ _ _ _ _ _
ማስረጃ 4. በሉቃስ 14:13-14 “ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ” የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት 4፡7፡10 የተገኘ ነው ‹‹ከገንዘብህም ምጽዋት ስጥ ምጽዋትም በመጸወትህ ጊዜ በገንዘብህ አትዘን፣ ከድሃም ፊትህን አትመልስ፤ እግዚአብሔርም ገጸ በረከቱን ካንተ
አይመልስም፡፡››
_ _ _ _ _ _
_ማስረጃ 5. 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡2 በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ የሚለውን ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ከጦቢት 4፡12 ጠቅሶ ነው ያስተማረው የተገኘ ነው፡፡
_ _ _ _ _ _ _ ይቀጥላል ...
መርከቧን የሚያውክ ንፋስ መቷል
አድኅነን ጌታ ሆይ ተጨንቀናል
አድኅነን ክርስቶስ ተማጽነናል

አንድ እግዚአብሔር ጥላ ተሰብስበው ሳሉ
በቀለም በጎሳ ይከፋፈላሉ
እጅግ ተናውጣለች ታንኳችን ተገፍታ
አውጅልን ደርሰህ ታላቁን ፀጥታ/2/
አዝ.....
የጥፋት እርኩሰት በመርከቧ ነግሶ
እረኛ ነኝ ይላል ተክሏው ለምድ ለብሶ
ቤተሰቤ ሁሉ ተጨንቋል በነፍሱ
ሞገዱን ገስጸው ፀጥ ይበል ንፋሱ/2/
አዝ...
እኔ በልጥ እኔ በልጥ መባባሉ በዝቷል
የትህትና መጉደል መርከቧን አውኳል
ስንጠፋ አይገድህም ብለን ስንጣራ
አንተ ግን አንተ ነህ ዛሬም ለኛ እራራ/2/
አዝ...
በቁጥር የበዙ ታንኳዎች እያሉ
አንተ ባለህበት አይሏል መዕበሉ
ዘንበል በልልን ጌታ ዝም አትበለን
በእምነት ከመዛል ከመስጠም አድህነን /2/
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
የክርስቶስ አምላካችን ሠላም ከሁላችን ጋር ይሁን ተወዳጆች በቤተክርስቲያናችን እና ሃገራችን እየደረሠ ያለውን ዘግናኝ ድርጊት እግዚአብሔር በቃ እንዲለን እና ለቤቱም እንዲነሳ በጸሎት ልንጠይቀው ይገባናል፡፡
እናት ተዋህዶ ሠውን ሠው በመሆኑ
👉 በዘር
👉 በጎሳ
👉 በቀለም
እንዲሁም ሌላውን የምትገፋ እናት አይደለችም፡፡ ለዚህም በቅርቡ በሃዋሳ ያሥጠለለቻቸው ህዝቦች ማሥረጃ ናቸው፡፡

ክርስቲያን ነህ(ሽ) ??? አዎ ከሆነ መልስህ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ልዩ ፍጥረት ነውና አክብረው መለያየት የዲያብሎስ ነውና በጭራሽ ቦታ አትስጠው፡፡

👉 ትግሬ፣ኦሮሞ፣አማራ፣ሲዳማ .... የትኛውን ነህ???? በዚህ የማንነት መሥፈርት የእግዚአብሔርን መንግስት ልትወርስ አትችልምና በዚህ አመለካከት ታጥረህ ከመንግስቱ እንዳትጎድል ፀልይ ደሞ አትርሳ ክርስቲያን ለሌላውም የሚያሥብ ነውና በጸሎትህ ለሌሎችም አንድነትን፣ፍቅርን፣ይቅርታን ለምን፡፡

🙏 አደራህን ክርስቲያን ባትሆን እንኳን ለህሊናህ ሥትል ጥሩ ሥራ፡፡

❤️ ተወዳጆች ስለ አንድነታችን እንጂ ስለ መለያየት እንድናስብ ቅድስት ርትዕት ንፅይት የሆነችው ተዋህዶ ሃይማኖታችን አታሥተምረንምና ከመለያየት እግዚአብሔር ይሰውረን
ዘረኝነት ይጥፋ ፍቅር ይንገስ
ሼር በማድረግ ዘረኝነትን አብረን እንዋጋ!
፩ ኃይማኖት
Join @And_Haymanot
@And_Haymanot
ሃሳባችሁን አድርሱን
👉 @AHati_Haymanot
Forwarded from Ethio🍀 ቢዝነስ ግሩፕ
_አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሄር!!! ቅኔ ማሕሌቱ በደም ረሰረሰ
መቅደስሕ ተቃጥሎ መሰዊያሕ ፈረሰ።
ጮሁ ምእመናን ደም እንባ አለቀሱ፤
በቅዱሱ ስፍራ ታርዷልና ቄሰ።

ሠላም መስሎን ነበር መውጣትመግባታችን፤
ለካስ በእሾሕ ታጥሯል ዙሪያው ጎዳናችን።
የጽዮን መንገዶች@haimanoteabew በእንባ ተሞልተዋል፤
የሚያምሩት ግንቦቿ በለሌት ፈርሰዋል፤

የቁጣሕን በትር ማን ይቋቋመዋል፤
የሀይልሕን ጽናት ማንስ ይችለዋል፤
የሽማግሌው ፊት አልታፈረምና፤
እንዴት ቀና እንበል እንዴት እንጽናና፤

እንደ ዘካርያስ እንደእግዚአብሄር ወዳጅ፤
ወደቁ ብዙዎች መጡና ካንተ ደጅ፤
ሕጻን አዛውንቱ ጎበዞቹ ሁሉ ተሰዉ
ለፍቅርሕ አንክድም እያሉ፤
አቤቱ የሆነብንን አስብ!!!!
@haimanoteabew
@haimanoteabew
በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም! ዮሃ 14

👉 ይህን በመያዝ ሌሎች አካላት አማላጅ ማለታቸው ትክክል ነውን?
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
ኦርቶዶክስ መልስ አላት!
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot