"ተአምሯን የሰማ ስጋውን ደሙን እንደ ተቀበለ ይሆንለታል"።
✍ @And_Haymanot
ለተሃድሶ መናፍቃን የተሠጠ መልሥ
ይህን ፅንሰ ሀሳብ ለመረዳት በመጀመሪያ በመቅደሙ የተፃፈውን ቃል እንዳለ መመልከት ጠቀሜታ ይኖረዋል። አስቀድመን እንደተናገርን የታወቀ ምክንያት ኋጢአት ደዌ ካልከለከለው በዚች ቀን ተአምሯን ሰምቶ ስጋውን ደሙን ይቀበል። ስጋውን ደሙን መቀበል ካልተቻለው ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሒድ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል ይደረግልኛል በማለት ቢሰማ ይላል የዚህን አንቀጽ መልዕክት አንድ በአንድ በመተንተን ስንመለከት የሚከተሉትን ሶስት አበይት መልዕክቶች እናገኛለን።
👉ሀ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ፦
ይህ አንቀፅ በመጀመሪያ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚያስተላልፈው መልዕክት ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ የሚል ነው። ምክንያቱም በፍትሐ ነገስት ከቀዳም ሥዑር በቀር ቅዳሜ ቅዳሜ እና እሁድ እሁድ በቤተክርስቲያን ተሰብስባችሁ ስጋውን ደሙን ተቀብላችሁ ደስ ይበላችሁ ተብሎ ታዝዟል ይህም ብቻ ብቻ ሳይሆን በበረሃ ያሉ ባህታውያን ሳይቀሩ መልዐከ እግዚአብሔር ስጋወ ደሙን ሰንበት ነው። / በዓላት-ምን ?
ለምን ? እእንዴት ? ገፅ ፵፮ እና ፷፮ / ነገር ግን በስርዐተ ቤተክርስቲያን አንድ ሰው ስጋውን ደሙን እንዳይቀበል ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ይኖራሉ። እነዚህም በዚህ አንቀፅ የተገለፁት አንደኛ የታወቀ ምክንያት / እንደ ወሊድ ፤ ሀዘን ፤ ለቅሶ ፤ ...የመሳሰሉት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ኃጢዐት ነው። ይከለክሉታል ተብለው ከተጠቁሱት በመጨረሻ የተገለፀው ደግሞ ደዌ ነው። አንድ ሰው በደዌ ምክንያት ነገር ከሰውነቱ እየወጣ፤ ደም እየፈሰሰው ይህን የመሰሉ ነገሮች እያሉበት ስጋወ ደሙን ላይቀበል ይችላል እነዚህ ሁሉ ግን ሰውየውን በቤተክርስቲያን ቅፅር ተገኝቶ ከመፀለይ፤ ቅዱሳት መፀሀፍትን ምንባባት ከመስማት ግን ላይከለክሉት ይችላሉ። ስለዚህ አንድ ሰው እነዚህ ምክንያቶች ካልከለከሉት በቀር ስጋወን ደሙን ይቀበል በማለት ወንጌልን ይሰብካል እንጅ ከወንጌል የወጣ ቃል የለውም።
👉ለ ቤተክርስቲያን አትቅር ፦
ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልህ ግን ስጋውን ደሙን መቀበል አይቻለኝም ብለህ ወደ ቤተክርስቲያን ከመሄድ አትከልከል የሚለው። ተአምረ ማርያም ከቅዳሴ በፊት ያለው የቤተክርስቲያን የፀሎት
ክፍል አንድ አካል ነው።
መቅድሙም የሚለው ፦
።።።///።።።።///።።።
#ስጋወ_ደሙን_መቀበል_ካልተቻለው_ተአምሯን_ሰምቶ_ወደ_ቤቱ_ይሂድ_ነው።
።።።///።።።።///።።።
ይህም ማለት ባትቆርብም ቤተክርስቲያን አትቅር ማለት ነው።በፀሎቱ ትምህርትና በመሳሰለው መርሀግብር ሁሉ ተሳተፍ። ዕለቱ ሰንበትና በዓላት ከሆነ አንድ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ካልሄደ በዚያም ተገኝቶ ካልተማረ ካላመሰገነ ክርስትናውን በምን ይገልፀዋል ?
በዚህ አገላለፅ ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሂድ የሚለውን በአስተውሎትና በቅንነት ከተመለከትነው የሚናገረው ስለተአምሯ ብቻ አይደለም። ታአምሯን አታስታጉሉ ሲል ወደ ቤተክርስቲያን ሂዳችሁ በዚያ ካለው ባለው አገልግሎት ተሳተፉ ማለት ነው። ምክንያቱም ተአምረ ማርያምን እንዴትና መቼ እንደሚነበብ እናውቃለን። ከተአምሩም በፊት፤ ከተአምሩም በኋላ ሌሎች ፀሎቶችና ምንባባት አሉ። ይህን አጠቃላይ አገልግሎት ለምዕመኑ በታወቀ በተረዳ ነገር በዚህ ስያሜ ማስታወቅ ክፋትም ኋጢአትም አይደለም። ሌላው አገልግሎት በዚህ አገላለፅ ለምን ጠሩት ቢባል በትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ላይ እንደተፃፈው ሌላውን አገልግሎት በመናቅ ማቅለል ሳይሆን ለእመቤታችን ባላቸው ፍቅር ነው።
👉ሐ አትጠራጠር፦
ሶስተኛውና የየመጨረሻው የዚህ አንቀፅ መልዕክት በታወቀ ምክንያት
+++ በዚች ዕለት +++ ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልክ ለሌሎች የተደረገው አይደረግልኝም የዕለቱ በረከት አይደርሰኝም ብለህ አትጠራጠር የሚል ነው። መፀሀፉ የተአምራት መፀሀፍ እንደመሆኑ መጠን ተአምራትም የሚደረገውና ተአምራትም የሚያሰኛቸው ከዘወትራዊ የህይወት ተግባራትና ድርጊቶች የተለየ ለሰው የማይቻል በእግዚአብሔር ብቻ የሚቻል ነገር መደረጉ በመሆኑ አንተም ይደረግልኛል በማለት በዕምነት ከፀሎቱ ተካፍለህ ከተአምሯም ሰምተህ ብትሄድ #በዕለቱ የቆረቡትን ሰወች በረከት ታገኛለክ ማለት ነው። ይህ ደግሞ በቅዱሳት መፀሀፍ የተፃፈ ነው። ራሱ ጌታችን በወንጌሉ የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ዕምነት ቢኖራችሁ ተራራ ማፍለስ፤ ባህር መክፈል..........
ሌላም ሌላም ትችላላችሁ ሲል አስተምሯል። ይህም በዕምነት ሀይል እግዚአብሔርን በረከተ እግዚአብሔርን ታገኛላችሁ ከእግዚአብሔር ትገናኛላችሁ ማለት ነው። ስጋወ ደሙ በየሳምንቱ ወይም ከዚህ ባነሰም ይሁን በበዛም የምንቀበለውም ለዚሁ ሀይለ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርገን ኋጢያታችን አስተስርየን በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስ አግኝተን ለመኖር ነው። በዚያች ዕለት አልቻልክ ብሎ ባትቀበል በዕምነትም ይህን ታገኛለክና አትጠራጠር ይሉናል ሊቃውንቱ። የየመቅደሙ መልዕክት ይኸ ሁኖ ሳለ "አውቆ የተኛን " ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደሚባለው ሰወችን ሆን ብሎ ለማጠራጠር ከቅዱሳን በረከት ለመለየት አጋንንት በሰወች አድረው ሊቃውንቱ ያላሉትንና ሊሉም ያላሰቡትን ያቀርባሉ። ቤተክርስትያኒቱ " ስጋውን ደሙን አትቀበሉ " ስጋወ ደሙን መቀበልና ስጋወደሙን ሳይቀበሉ ተአምረ ማርያምን መስማት እኩል ናቸው የሚል ትምህርት አስተምራ አታውቅም እእንዲህም አታምንም። ተአምሯን የሚሰሙትና የሚያሰሙትም ስጋውን ደሙን የተቀበሉ ወደፊትም የሚቀበሉ ናቸው እንጅ አረማውያን ወይም በስጋወ ደሙ የሚጠራጠሩ አይደሉም።
/// ይደረግልኛል በማለት ቢሰማ /// የሚለው ጊዜ የተገደበ
ነው፡፡ ታዲያ ይህ በዕውኑ ለምዕመኑ መንፈሳዊ ህይወት መጨነቅ ወይስ ለኑፋቄ ሽፋን መፈለግ ???
ምንጭ ትምህርተ ተዋህዶ አፕሊኬሽን። ልዑል እግዚአብሔር በተዋህዶ በረት እንድንፀና ያድርገን ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችንም ጋር
ይሁን አሜን::
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
✍ አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡

ቅዱሳት ስዕላትና ጣዖት
@And_Haymanot
ጣዖት ማምለክ እጅግ ጸያፍ ኃጢያት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንደገለጸው ይህንንም የእግዚአብሔርን መንግስት
አይወርሱም፡፡ 1ቆሮ. 6:9,10 እጅግ የሚደንቀው ነገር ለሙሴ በቅዱሳን እጆቹ አዘጋጅቶ በሰጠው ጽላት ላይ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ያለው እግዚአብሔር፣ ሙሴን ከነሐስ እባብ እንዲያዘጋጅና በአላማ ላይ እንደሰቅለው ማዘዙ ነው፡፡ ዘኁ.21፡8፡፡ ያንን እባብ
የሚያዩና ድምጹን የሚሰሙ ከበሽታቸው እንደሚፈወሱም ነገረውም፡፡ ሙሴም በአላማ እድረጎ በሰቀለው በዚህ የነሐስ
እባብ ብዙ እስራኤላውያን ዳኑ፡፡ ይህም ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ለማዳኑ ምሳሌ ሆነ፡፡ ዮሐ.3፡14 ይህ ሙሴ አዘጃጅቶ በአላማ የሰቀለው እባብ፣ ምንም እንኳን በሙሴ እጅ የተቀረጸ
ቢሆንም ከእኔ በቀር ሌላ አታምልክ ያለውን የእግዚአብሔር ህግ ጥሷል፤ ጣዖት ነው አይባልም፡፡ እንዲያውም በጣዖት አምልኮ በበሽታ የተቀጡትን እስራኤልን ከመቅሰፍታቸው የፈወሰ ነበር፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሔር ሙሴን በታቦቱ ላይ ከወርቅ የኪሩቤል
ምስል እንዲያዘጋጅ ነገረው፡፡ ሙሴም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ዘጸ.25:18:: ማንም ሰው ይህንን ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ያለውን ህግ ሙሴ አፍርሷል፤ ጣዖት አዘጋጅቷል ሊል
አይችልም፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም ቤተመቅደሱን በኪሩቤል ስዕል አድርጎ እና የቤተመቅደሱን ዙሪያ በአበባና በእጽዋት አስጊጦ ነበር፡፡ ሁለቱም በሮች በወርቅም የተለበጡ ነበሩ፡፡ 1ኛ.ነገ.6፣29-31. ሌሎች በርካታ ተመሳሳይ ነገር መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በእግዚአብሔር ቤት ያሉና ለስርአተ
አምልኮ የምንገለገልባቸው መንፈሳዊ የእደ ጥበበው ውጤቶት
ኃጢያት አይደሉም፡፡
+ በጽሐፍ ቅዱስ ኢያሱ ልብሱን ቀደደ፣ እስከ ምሽትም በታቦቱ ፊት ሰገደ ይላል፡፡ ኢያ.7፣6 ማንም ኢያሱ ታቦቱን አመለከ ብሎ ሊደመድም አይችልም፡፡ በታቦት ፊት መስገድም ከኢያሱ ስግደት የተለየ ትርጉም አይሰጠውምም፡፡ ልክ እንደዚሁ የተከበረው የእስራኤል ንጉስ ዳዊት፣ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ልብሱ እስኪወልቅ ሲያመሰግን ሲዘምር፣ ሚስቱ ሜልኮል ትስቅበት ነበር፡፡ በዚህም ቅዱስ ዳዊት በረከትን ሲያገኝ የሳወቀችበት
ሚስቱም ከእግዚአብሔር ቅጣቷን ተቀብላለች፡፡ 2ኛ ሳሙ. 6:12-15 እና 23 እንደ ስዕል ያሉ ለስርዓተ አምልኮ የሚውሉ የቤተመቅደስ ንዋያት
የሰማይ ደጆች ናቸው፡፡ ሰው ሲያያቸው በምድር ሳለ ኅሊናው ወደሰማይ ይሻገራል፡፡ እግዚአብሔርን፣ ሰማያውያኑን ቅዱሳኑን በኅሊና መነጽር ያይባቸዋል፡፡ ወደ ቤተመቅስ ስንገባና
ስንጸልይም ከስላሴ ዙፋን ጀምሮ በኪሩቤልና በሱራፌል፣ በቅዱሳን የታጀመውን ስዕል፣ እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ የተሳለውን እያየን ስንጸልይ ኅሊናችን
ይመሰጣል፤ አካላችን በምድር ሳለ ልባችን ወደሰማይ ይሻገራል፡፡ ስለሆነም ስዕል በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የስዕሉን ባለቤት
በኅሊናችን የምናይበት መነጽር ነው፡፡ የስዕል ክብር ከስዕሉ ባለቤት ክብር የሚመነጭ ነው፡፡ በስዕል ፊት መስገድ ለስዕሉ ባለቤት መስገዳችን ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ማሰብ ፍጹም ስህተት ነው፡፡ ስዕልና ጣዖት አለመለየት አላዋቂነት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረትም የለውም፡፡ ስዕልን ጣዖት ማለት ይህን
ያዘዘንን እግዚአብሔርንና በእርሱ የታዘዙትን አገልጋቹንም በጅምላ መወንጀል ነው፡፡ በትውፊት እንደምንረዳውም ሐዋርያትን ተከታዮቻቸው በቤተመቅደስ በስዕል ጭምር እግዚአብሔርን ያገለግሉ ያመልኩም ነበር፡፡ የእመቤታችንን ምስለ ፍቁር ወልዳ ስዕል የሳለው ወንጌላዊው ሉቃስ ሲሆን፣ የጌታችንን የስቅለት
ስዕል የሳለው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው፡፡ ብዙ ፕሮቴስታንት እንዲህ ዓይነት ነገር ስንነግራቸው ጥቅሱን አሳዩን የሚል ጥያቄ እንደሚያስከትሉ ይገባናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ አልፎ የሚያስ እውነትንና አውቀትን ፍለጋ አሻግሮ የሚያይ ፕሮቴስታነትን ቢኖር እርሱን አደንቃለሁ፡፡ ይህንን እውነት ለማወቅ በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጻሕፍት ሳይወሰን ለተጨማሪ ማገናዘቢያ በእንግሊዝኛና ሌሎች ቋንቋዎች የተጻፉ እንደ ኢንሳክሎፒዲያና የቤተክርቲያን ታሪክ መጻህፍት ላይ ማናዘብ ይቻላል፡፡ እንደ ሐዋርያው ቶማስ በአይኔ ያላየሁትን ማመን አልፈልግም የሚል ቢኖር መብቱ ነው፡፡ እኛ ግን ኦርቶዶክሳውያን ነን፡፡ ማንም በግን ተኩላ ናት ቢለን እንቀበለውም፣ ይልቁንም አለማወቁን እናስረዳለን እንጂ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!