፩ ሃይማኖት
8.9K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዓይኔን ጨፍኜ ብጸልይስ????

@And_Haymanot

አይንን ጨፍኖ መፀለይ የጨለማ
ምልክት ነው፤ ጨለማ ደግሞ የሲዖል ምልክት ነው፡፡ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምእመናን የምንጸልየው ዓይኖቻችነንን ከፍተን ወደላይ ወደሰማይ አቅንተን ነው ምክንያቱም እንዲህ መጸለይ የቅዱሳን አበው ስርዓት ነውና ይህንን በተመለከተ ልብ አምላክ ዳዊት ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አንሳሁ ብሏል፡፡
(መዝ120፡1) በተጨማሪም በሰማይ የምትኖር ሆይ አይኖቼን ወደ ተራሮች አነሳሁ እነሆ የሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እንዲሆኑ የባሪያቱም ዓይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሆነ እንዲሁም
እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚያብሔር ነው ብሏል፡፡ (መዝ 123፡1-2) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ያስተማረው ዓይንን ከፍቶ ወደ ሰማይ አቅንቶ መፀለይ
ነው፡፡ (ዩሐ11፤41) ከዚህም የተነሳ የሐዲስ ኪዳን ምእመናን ሁሉ የሚከተሉት ይህንን የጸሎት ስርዓት ነው ለምሳሌ ቅ/ ስጢፋኖስ በአይሁድ እጅ በድንጋይ እየተወገረ እርሱ ግን አይኑን
ከፍቶ ወደ ሰማይ አቅንቶ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል እያለ ሲጸልይ እና ይህንን ሐጥያት አትቁጠርባቸው እያለ ያማልድ ነበር፡፡ (የሐዋ 7፤54) ከላይ በአጭሩ ለመግለጽ እንሞከርኩት
መሰረታዊው ነገር ይህ ሲሆን ዓይንን ጨፍኖ ግን ለመጸለይ የሚቀርበው ምክንያት ሀሳቤን ይሰበሰብልኛል፤ ልቦናዬን ያረጋጋልኛል የሚል ነው፡፡ ነገር ግን አይን ስለተጨፈነ አሳብ አይሰበሰብም ልቦናም አይረጋጋም ምክንያቱም #አይንን_በመጨፈን_አሳብ_የሚሰበስብ_ቢሆን_ኖሮ_ዓይኖቻቸው_የጠፋባቸው_ወገኖች_ሁሉ_ለጸሎት_በሚነሱበት_ጊዜ_ልቦናቸው_አይበትንባቸውም_ያስብል_ነበር፡፡ ምን አልባት ነገር በአይን ስለሚገባልንል እንችል ይሆናል፡፡ ዳሩ ግን #በጆር_የሚገባውንስ???? ስንጸልይ ጆሮኣችንን በጥጥ ልንወትፈው ነው? ነገር እኮ ከልቦና ይመነጫል ይህንንስ እንዴት ልናደርገው ነው የተወዳዳቹ አንባቢዎች እኛ በስሜታዊነት በአንድ ጊዜ ከመንፈሳዊነት ሕይወት ጫፍ ላይ
ለመውጣት በአንድ ጊዜ ከፍጹም ማዕረግ ለመድረስ ስለምንፈልግ እንጂ አሳብን ሰብስቦ በተረጋጋ መንፈስ መጸለይ በአንድ ጊዜ የሚደረስበት ጸጋ አይደለም፡፡ ምክንያቱም መንፈሳዊ
ህይወት ደረጃ አለው በመሆኑም በብዙ ገድል ከአንድ ደረጃ ወደሌላ ደረጃ በእግዚያብሔር ቸርነት እያደጉ ይደረስብታል እንጂ ቁጭ ተብሎ ስለፈለጉ ብቻ የሚገኝ አይደለም ስለዚህ
በምንጸልይበት ጊዜ የሚረብሹን ብዙ የሀሳብ ውጣ ውረዶች ቢኖሩ ከእነርሱ ጋር በእምነት እየተጋደልን እስከመጨረሻው መጽናት አለብን፡፡ ስለሆነም እንደ አሁኖቹ ፕሮቴስታንቶችም ሆነ ሌላ የእምነት ድርጅቶች ውስጥ አይንን ጨፍኖ መጸለይ ኢየሱስ ክርስቶስም መፅሐፍ ቅዱስም አይደግፈውም እና በምንጸልይበት ጊዜ አይናችንን ወደ ሰማይ አምላክ በመግለጥ መጸለይ
እንዳለብን መጽሀፍ ያስረዳል፡፡
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
እንቁጣጣሹ...የኦርቶዶክሶች
መስቀሉ....የኦርቶዶክሶች
የገና ፆም...የኦርቶዶክሶች
ጥምቀቱ....የኦርቶዶክሶች
ገዳማቱ.....የኦርቶዶክሶች
የፋሲካው ፆም...የኦርቶዶክሶች
ትንሳኤው....የኦርቶዶክሶች
ቡሄው....የኦርቶዶክሶች
ፃድቃንን ሚያከብሩ..ኦርቶዶክሶች
መላዕክትን ሚፈሩ...ኦርቶዶክሶች
ቅዱስ ያሬድ...የኦርቶዶክሶች
ፃድቁ ተክለሀይማኖት...የኦርቶዶክሶች
አበባይሆሽ...የኦርቶዶክሶች
አድዋ ላይ ታቦት ይዘው ያሸነፉት..ኦርቶዶክሶች
.
.
...የኦርቶዶክሶች...ጌታ ይመስገን እንዲ ሙሉ ስላደረገን...

አንድ ሃይማኖት

#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~JoIN~~~
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
ምንፍቅና በቅዱስ ቃሉ ሲፋቅ!
#ስግደት_ለመላእክት
👉ኢያሱ ለመልአኩ ሰገደ
👉ዮሀንስ ስለምን አትስገድልኝ ተባለ?

@And_Haymanot

መናፍቃን የሚያነሱትን ጥያቄ ቀለል ባለ
መንገድ ስንመልስ!!
👉1. የእስራኤል መስፍን የሆነው ኢያሱ “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን” ብሎ
እንዳላለ !!መጽ.ኢያሱ 5ቁ13“……እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኘ አሁን መጥቻለሁ አለ. ኢያሱም ‘ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና’ ጌታየ ለባሪያው
የሚነግረው ምንድር ነው አለው. የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን አውልቅ አለው” የምታመልኩትን ምረጡ ያለው ኢያሱ ለመልአኩ በስህተት ሰገደ ብለን አናምንም!!!ለመልአኩ በግንባሩ መደፋቱም መልአኩን ለማክበር እንጅ ለማምለክ እንዳልሆነ እናውቃለን!!!ዛሬም ኢያሱን ተከትለን እንዲሁ ስናደርግ አምላክን ከመልአክ ለይተን ነው!!!የአንዱን ላንዱ ሳንሰጥ፣ሳንቀላቅል!!

👉2. ወንጌላዊው ዮሐንስ፡በራእይ 19ቁ10 እና 22ቁ8 ….በመልአኩ እግር ፊት ሰገድኩለት እሱ ግን አትስገድልኝ፣ ሁለታችንም የእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን አለኝ….የሚለውን ጥሬ ንባብ ለመላእክት ስግደት እንደማይገባ ለማሳየት መናፍቃን ያቀርባሉ!!!ተሳስተዋል!!
✔️(ሀ)ወንጌሉን፣መልእክታቱን፣ራእዩን የጻፈው ዮሐንስ ለመልአኩ የሰገደው ባለማወቅ ነው ማለት ይሄን ሁሉ የጻፈውን ዮሐንስ ለማን መስገድ እንዳለበት እንኩዋ የማያውቅ አዲስ ምእመን ማስመሰል ነው!!!ዮሐንስ የሰገደው መስገድ ስለሚገባው ነው!!!
✔️(ለ)መልአኩ አትስገድልኝ ያለው ስግደት የበላይና የበታች መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ዮሐንስ በክብር እደተስተካከለው አውቆ ነው!!!ለትህትና!!!
✔️(ሐ)መልአኩ በምእራፍ 19 ቁ 10 እንደተገለጸው ዮሐንስን አትስገድልኝ ቢለውም ዮሐንስ ግን በምእራፍ 22 ቁ 8’ም ዳግመኛ ለመልአኩ ሲሰግድ እናገኘዋለን!!ዮሐንስን ያህል የጌታ
ወዳጅ(ፍቁረ-እግዚእ) ተብሎ የተነገረለትና በጰራቅሊጦስ
መንፈስቅዱስ የወረደበት አባት ለመልአክ መስገድ ስህተት
መሆኑ ጠፍቶ፣ እየተነገረው ጭምር ከአንዴም ሁለቴ ሰገደ ማለት ቅድስናውን መጠራጠር ይሆናል!!!ስለሆነም መልአኩ
አትስገድልኝ ያለው ለትህትና ነው ስንል እናምናለን!!!

👉3. የሞቱ ቅዱሳን ከእኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም የምትሉ ሰዎች አላችሁ!!!እሺ ቅዱሳኑስ ይሁኑ ታዲያ መላእክት እኮ አይሞቱም!!!ስለታናናሾች የአብን ፊት ያያሉ እንጅ-በማቴ 18ቁ 10 እንደተጻፈው!በዘካርያስ 1 ቁ 13 የመልአኩ ምልጃ እንዲህ
ተጽፉዋል “አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ እነዚህ 70 አመት የተቆጣሀቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተማዎች የማትምራቸው እስከመቼ ነው አለው እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው” ታዲያ ሳንለምነው እንዲህ የሚማልድልን መልአክ ብንለምነውማ ምን ያህል ይማልድልን?ሰአሉ ለነ ሚካኤል ወገብርኤል እንበላቸውማ!!!

👉4.የሞቱ ቅዱሳን በክርስቶስ ህያው ስለሆኑ ከእኛ ጋር በመንፈስ
እንደሚገናኙ ደግሞ ይሄው!!!የሞቱ ቅዱሳን “እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነሱ እንደማያፍር” በዕብ 11 ቁ 16 ተጽፉዋል!!!የሞቱ ቅዱሳን አላዋቂዎች ሳይሆኑ ወደፍጹምነት የተሸጋገሩ ‘ፍጹማን’ መሆናቸው በዕብ 12 ቁ 22 ሰፍሮልናል!!! ጌታም ከአመታት በፊት በሞት የተለዩትን አብርሃምን፣ይስሀቅንና
ያዕቆብን ጠቅሶ “የህያዋን አምላክ ነኝ” ሲል በማቴ 22 ቁ 32 ገልጹዋል!!!ጌታችን በስጋ ስለሞተው አብርሃም በዮሀንስ 8 ቁ56 ሲናገር፡ “አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴትን አደረገ፤አየም ደስ አለው” ይላል!!!በአጸደ ነፍስ ያለው አብርሃም የጌታን ቀን አይቶ የተደሰተው በሰማይ ያሉ ቅዱሳን በምድር ካለነው ጋር ህብረት ስላላቸው ነው!! ዮሐንስ በራዕዩ ምዕራፍ 8 ቁ 3 “የዕጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚብሔር ፊት ወጣ” ይለናል!!መላእክት ጸሎታችንን ያሳርጋሉ!!!አእርጉ ጸሎተነ የምንላቸውም ለዚሁ ነው-እንደ ቅ/ያሬድ-እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ!!ሙሴስ በዘጸአት 32 ቁ 13 “በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ይስሀቅንና እስራኤልን አስብ” ብሎ በአጸደነፍስ ነፍስ ባሉ ቅዱሳን ስም ጌታውን ሲማጸን ከሞቱ ቅዱሳን ህብረት ስላለን አይደለምን?ነው እንጅ!!!

👉5. ይሄን ሁሉ ስንል ባለቤቱን ረስተን አይደለም!!!በቀጥታም እሱን ማረን እንለዋለን-እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በምህላ- መሀረነ አብ በማስታኮት!!!ስማን፣ተማለደን፣ታረቀን እንለዋለን!!! ግን እንደሌሎቹ አማልደን አንለውም!!!ሌሎቹ የሚያማልደን ጌታ ነው እያሉ ቤዛነቱን እንደአማላጅነት ስለሚወስዱት ነው እኛ ቅዱሳንን አማልዱን ስንል አምላክ ያደረግናቸው የሚመስላቸው!!! አምላካችን አንድ ነው!!!የሃይማኖታችን መሰረትም እሱ-ለዚህም ነው ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን ስንል የሃይማኖት ጸሎታችንን የምንጀምረው!!!
ይቆየን
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
✞✞ልቦናዬ_በጎ_ነገርን_አወጣ እኔስ የማርያምን ክብር
እናገራለሁ ፡፡በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ፡፡
✞ እኔስ የድንግልን ውዳሴ እናገራለሁ መዘንጋት ባለበት
ቃል በማስረዘም አይደለም በማሳጠር ነው እንጂ .........
@Tsere_Tehadso
"ተሐድሶ ማለት ነፍሳትን ወደ ሲኦል(አዳራሽ) የሚገብር ገባር ወንዝ ነው"

#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
"ተአምሯን የሰማ ስጋውን ደሙን እንደ ተቀበለ ይሆንለታል"።

@And_Haymanot
ለተሃድሶ መናፍቃን የተሠጠ መልሥ

ይህን ፅንሰ ሀሳብ ለመረዳት በመጀመሪያ በመቅደሙ የተፃፈውን ቃል እንዳለ መመልከት ጠቀሜታ ይኖረዋል። አስቀድመን እንደተናገርን የታወቀ ምክንያት ኋጢአት ደዌ ካልከለከለው በዚች ቀን ተአምሯን ሰምቶ ስጋውን ደሙን ይቀበል። ስጋውን ደሙን መቀበል ካልተቻለው ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሒድ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል ይደረግልኛል በማለት ቢሰማ ይላል የዚህን አንቀጽ መልዕክት አንድ በአንድ በመተንተን ስንመለከት የሚከተሉትን ሶስት አበይት መልዕክቶች እናገኛለን።

👉ሀ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ፦
ይህ አንቀፅ በመጀመሪያ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚያስተላልፈው መልዕክት ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ የሚል ነው። ምክንያቱም በፍትሐ ነገስት ከቀዳም ሥዑር በቀር ቅዳሜ ቅዳሜ እና እሁድ እሁድ በቤተክርስቲያን ተሰብስባችሁ ስጋውን ደሙን ተቀብላችሁ ደስ ይበላችሁ ተብሎ ታዝዟል ይህም ብቻ ብቻ ሳይሆን በበረሃ ያሉ ባህታውያን ሳይቀሩ መልዐከ እግዚአብሔር ስጋወ ደሙን ሰንበት ነው። / በዓላት-ምን ?
ለምን ? እእንዴት ? ገፅ ፵፮ እና ፷፮ / ነገር ግን በስርዐተ ቤተክርስቲያን አንድ ሰው ስጋውን ደሙን እንዳይቀበል ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ይኖራሉ። እነዚህም በዚህ አንቀፅ የተገለፁት አንደኛ የታወቀ ምክንያት / እንደ ወሊድ ፤ ሀዘን ፤ ለቅሶ ፤ ...የመሳሰሉት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ኃጢዐት ነው። ይከለክሉታል ተብለው ከተጠቁሱት በመጨረሻ የተገለፀው ደግሞ ደዌ ነው። አንድ ሰው በደዌ ምክንያት ነገር ከሰውነቱ እየወጣ፤ ደም እየፈሰሰው ይህን የመሰሉ ነገሮች እያሉበት ስጋወ ደሙን ላይቀበል ይችላል እነዚህ ሁሉ ግን ሰውየውን በቤተክርስቲያን ቅፅር ተገኝቶ ከመፀለይ፤ ቅዱሳት መፀሀፍትን ምንባባት ከመስማት ግን ላይከለክሉት ይችላሉ። ስለዚህ አንድ ሰው እነዚህ ምክንያቶች ካልከለከሉት በቀር ስጋወን ደሙን ይቀበል በማለት ወንጌልን ይሰብካል እንጅ ከወንጌል የወጣ ቃል የለውም።

👉ለ ቤተክርስቲያን አትቅር ፦
ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልህ ግን ስጋውን ደሙን መቀበል አይቻለኝም ብለህ ወደ ቤተክርስቲያን ከመሄድ አትከልከል የሚለው። ተአምረ ማርያም ከቅዳሴ በፊት ያለው የቤተክርስቲያን የፀሎት
ክፍል አንድ አካል ነው።
መቅድሙም የሚለው ፦
።።።///።።።።///።።።
#ስጋወ_ደሙን_መቀበል_ካልተቻለው_ተአምሯን_ሰምቶ_ወደ_ቤቱ_ይሂድ_ነው
።።።///።።።።///።።።
ይህም ማለት ባትቆርብም ቤተክርስቲያን አትቅር ማለት ነው።በፀሎቱ ትምህርትና በመሳሰለው መርሀግብር ሁሉ ተሳተፍ። ዕለቱ ሰንበትና በዓላት ከሆነ አንድ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ካልሄደ በዚያም ተገኝቶ ካልተማረ ካላመሰገነ ክርስትናውን በምን ይገልፀዋል ?
በዚህ አገላለፅ ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሂድ የሚለውን በአስተውሎትና በቅንነት ከተመለከትነው የሚናገረው ስለተአምሯ ብቻ አይደለም። ታአምሯን አታስታጉሉ ሲል ወደ ቤተክርስቲያን ሂዳችሁ በዚያ ካለው ባለው አገልግሎት ተሳተፉ ማለት ነው። ምክንያቱም ተአምረ ማርያምን እንዴትና መቼ እንደሚነበብ እናውቃለን። ከተአምሩም በፊት፤ ከተአምሩም በኋላ ሌሎች ፀሎቶችና ምንባባት አሉ። ይህን አጠቃላይ አገልግሎት ለምዕመኑ በታወቀ በተረዳ ነገር በዚህ ስያሜ ማስታወቅ ክፋትም ኋጢአትም አይደለም። ሌላው አገልግሎት በዚህ አገላለፅ ለምን ጠሩት ቢባል በትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ላይ እንደተፃፈው ሌላውን አገልግሎት በመናቅ ማቅለል ሳይሆን ለእመቤታችን ባላቸው ፍቅር ነው።

👉ሐ አትጠራጠር፦
ሶስተኛውና የየመጨረሻው የዚህ አንቀፅ መልዕክት በታወቀ ምክንያት
+++ በዚች ዕለት +++ ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልክ ለሌሎች የተደረገው አይደረግልኝም የዕለቱ በረከት አይደርሰኝም ብለህ አትጠራጠር የሚል ነው። መፀሀፉ የተአምራት መፀሀፍ እንደመሆኑ መጠን ተአምራትም የሚደረገውና ተአምራትም የሚያሰኛቸው ከዘወትራዊ የህይወት ተግባራትና ድርጊቶች የተለየ ለሰው የማይቻል በእግዚአብሔር ብቻ የሚቻል ነገር መደረጉ በመሆኑ አንተም ይደረግልኛል በማለት በዕምነት ከፀሎቱ ተካፍለህ ከተአምሯም ሰምተህ ብትሄድ #በዕለቱ የቆረቡትን ሰወች በረከት ታገኛለክ ማለት ነው። ይህ ደግሞ በቅዱሳት መፀሀፍ የተፃፈ ነው። ራሱ ጌታችን በወንጌሉ የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ዕምነት ቢኖራችሁ ተራራ ማፍለስ፤ ባህር መክፈል..........
ሌላም ሌላም ትችላላችሁ ሲል አስተምሯል። ይህም በዕምነት ሀይል እግዚአብሔርን በረከተ እግዚአብሔርን ታገኛላችሁ ከእግዚአብሔር ትገናኛላችሁ ማለት ነው። ስጋወ ደሙ በየሳምንቱ ወይም ከዚህ ባነሰም ይሁን በበዛም የምንቀበለውም ለዚሁ ሀይለ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርገን ኋጢያታችን አስተስርየን በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስ አግኝተን ለመኖር ነው። በዚያች ዕለት አልቻልክ ብሎ ባትቀበል በዕምነትም ይህን ታገኛለክና አትጠራጠር ይሉናል ሊቃውንቱ። የየመቅደሙ መልዕክት ይኸ ሁኖ ሳለ "አውቆ የተኛን " ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደሚባለው ሰወችን ሆን ብሎ ለማጠራጠር ከቅዱሳን በረከት ለመለየት አጋንንት በሰወች አድረው ሊቃውንቱ ያላሉትንና ሊሉም ያላሰቡትን ያቀርባሉ። ቤተክርስትያኒቱ " ስጋውን ደሙን አትቀበሉ " ስጋወ ደሙን መቀበልና ስጋወደሙን ሳይቀበሉ ተአምረ ማርያምን መስማት እኩል ናቸው የሚል ትምህርት አስተምራ አታውቅም እእንዲህም አታምንም። ተአምሯን የሚሰሙትና የሚያሰሙትም ስጋውን ደሙን የተቀበሉ ወደፊትም የሚቀበሉ ናቸው እንጅ አረማውያን ወይም በስጋወ ደሙ የሚጠራጠሩ አይደሉም።
/// ይደረግልኛል በማለት ቢሰማ /// የሚለው ጊዜ የተገደበ
ነው፡፡ ታዲያ ይህ በዕውኑ ለምዕመኑ መንፈሳዊ ህይወት መጨነቅ ወይስ ለኑፋቄ ሽፋን መፈለግ ???
ምንጭ ትምህርተ ተዋህዶ አፕሊኬሽን። ልዑል እግዚአብሔር በተዋህዶ በረት እንድንፀና ያድርገን ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችንም ጋር
ይሁን አሜን::
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
ቅዱሳት ስዕላትና ጣዖት

@And_Haymanot

ጣዖት ማምለክ እጅግ ጸያፍ ኃጢያት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንደገለጸው ይህንንም የእግዚአብሔርን መንግስት
አይወርሱም፡፡ 1ቆሮ. 6:9,10 እጅግ የሚደንቀው ነገር ለሙሴ በቅዱሳን እጆቹ አዘጋጅቶ በሰጠው ጽላት ላይ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ያለው እግዚአብሔር፣ ሙሴን ከነሐስ እባብ እንዲያዘጋጅና በአላማ ላይ እንደሰቅለው ማዘዙ ነው፡፡ ዘኁ.21፡8፡፡ ያንን እባብ
የሚያዩና ድምጹን የሚሰሙ ከበሽታቸው እንደሚፈወሱም ነገረውም፡፡ ሙሴም በአላማ እድረጎ በሰቀለው በዚህ የነሐስ
እባብ ብዙ እስራኤላውያን ዳኑ፡፡ ይህም ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ለማዳኑ ምሳሌ ሆነ፡፡ ዮሐ.3፡14 ይህ ሙሴ አዘጃጅቶ በአላማ የሰቀለው እባብ፣ ምንም እንኳን በሙሴ እጅ የተቀረጸ
ቢሆንም ከእኔ በቀር ሌላ አታምልክ ያለውን የእግዚአብሔር ህግ ጥሷል፤ ጣዖት ነው አይባልም፡፡ እንዲያውም በጣዖት አምልኮ በበሽታ የተቀጡትን እስራኤልን ከመቅሰፍታቸው የፈወሰ ነበር፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሔር ሙሴን በታቦቱ ላይ ከወርቅ የኪሩቤል
ምስል እንዲያዘጋጅ ነገረው፡፡ ሙሴም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ዘጸ.25:18:: ማንም ሰው ይህንን ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ያለውን ህግ ሙሴ አፍርሷል፤ ጣዖት አዘጋጅቷል ሊል
አይችልም፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም ቤተመቅደሱን በኪሩቤል ስዕል አድርጎ እና የቤተመቅደሱን ዙሪያ በአበባና በእጽዋት አስጊጦ ነበር፡፡ ሁለቱም በሮች በወርቅም የተለበጡ ነበሩ፡፡ 1ኛ.ነገ.6፣29-31. ሌሎች በርካታ ተመሳሳይ ነገር መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በእግዚአብሔር ቤት ያሉና ለስርአተ
አምልኮ የምንገለገልባቸው መንፈሳዊ የእደ ጥበበው ውጤቶት
ኃጢያት አይደሉም፡፡
+ በጽሐፍ ቅዱስ ኢያሱ ልብሱን ቀደደ፣ እስከ ምሽትም በታቦቱ ፊት ሰገደ ይላል፡፡ ኢያ.7፣6 ማንም ኢያሱ ታቦቱን አመለከ ብሎ ሊደመድም አይችልም፡፡ በታቦት ፊት መስገድም ከኢያሱ ስግደት የተለየ ትርጉም አይሰጠውምም፡፡ ልክ እንደዚሁ የተከበረው የእስራኤል ንጉስ ዳዊት፣ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ልብሱ እስኪወልቅ ሲያመሰግን ሲዘምር፣ ሚስቱ ሜልኮል ትስቅበት ነበር፡፡ በዚህም ቅዱስ ዳዊት በረከትን ሲያገኝ የሳወቀችበት
ሚስቱም ከእግዚአብሔር ቅጣቷን ተቀብላለች፡፡ 2ኛ ሳሙ. 6:12-15 እና 23 እንደ ስዕል ያሉ ለስርዓተ አምልኮ የሚውሉ የቤተመቅደስ ንዋያት
የሰማይ ደጆች ናቸው፡፡ ሰው ሲያያቸው በምድር ሳለ ኅሊናው ወደሰማይ ይሻገራል፡፡ እግዚአብሔርን፣ ሰማያውያኑን ቅዱሳኑን በኅሊና መነጽር ያይባቸዋል፡፡ ወደ ቤተመቅስ ስንገባና
ስንጸልይም ከስላሴ ዙፋን ጀምሮ በኪሩቤልና በሱራፌል፣ በቅዱሳን የታጀመውን ስዕል፣ እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ የተሳለውን እያየን ስንጸልይ ኅሊናችን
ይመሰጣል፤ አካላችን በምድር ሳለ ልባችን ወደሰማይ ይሻገራል፡፡ ስለሆነም ስዕል በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የስዕሉን ባለቤት
በኅሊናችን የምናይበት መነጽር ነው፡፡ የስዕል ክብር ከስዕሉ ባለቤት ክብር የሚመነጭ ነው፡፡ በስዕል ፊት መስገድ ለስዕሉ ባለቤት መስገዳችን ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ማሰብ ፍጹም ስህተት ነው፡፡ ስዕልና ጣዖት አለመለየት አላዋቂነት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረትም የለውም፡፡ ስዕልን ጣዖት ማለት ይህን
ያዘዘንን እግዚአብሔርንና በእርሱ የታዘዙትን አገልጋቹንም በጅምላ መወንጀል ነው፡፡ በትውፊት እንደምንረዳውም ሐዋርያትን ተከታዮቻቸው በቤተመቅደስ በስዕል ጭምር እግዚአብሔርን ያገለግሉ ያመልኩም ነበር፡፡ የእመቤታችንን ምስለ ፍቁር ወልዳ ስዕል የሳለው ወንጌላዊው ሉቃስ ሲሆን፣ የጌታችንን የስቅለት
ስዕል የሳለው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው፡፡ ብዙ ፕሮቴስታንት እንዲህ ዓይነት ነገር ስንነግራቸው ጥቅሱን አሳዩን የሚል ጥያቄ እንደሚያስከትሉ ይገባናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ አልፎ የሚያስ እውነትንና አውቀትን ፍለጋ አሻግሮ የሚያይ ፕሮቴስታነትን ቢኖር እርሱን አደንቃለሁ፡፡ ይህንን እውነት ለማወቅ በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጻሕፍት ሳይወሰን ለተጨማሪ ማገናዘቢያ በእንግሊዝኛና ሌሎች ቋንቋዎች የተጻፉ እንደ ኢንሳክሎፒዲያና የቤተክርቲያን ታሪክ መጻህፍት ላይ ማናዘብ ይቻላል፡፡ እንደ ሐዋርያው ቶማስ በአይኔ ያላየሁትን ማመን አልፈልግም የሚል ቢኖር መብቱ ነው፡፡ እኛ ግን ኦርቶዶክሳውያን ነን፡፡ ማንም በግን ተኩላ ናት ቢለን እንቀበለውም፣ ይልቁንም አለማወቁን እናስረዳለን እንጂ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
የአዲስ ዓመት እንግዳ

መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም በአሌፍ የቴሌቭዥን ጣቢያ ከረፋዱ 4፡00 - ቀኑ 8፡00 በማኅበረ ቅዱሳን ከሚቀርቡ ዝግጅቶች አንዱ የአዲስ ዓመት እንግዳ ነው፡፡

የአዲስ ዓመት እንግዳችንም በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔ ዓለም ገዳም የአራቱ ጉባኤያት መምህር እና የገዳሙ አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ናቸው፡፡

ሊቁ በርካታ የቤተ ክርስቲያን መምህራንን አስተምረው ለመንፈሳዊ አገልግሎት ከማብቃታቻው ባሻገር ሃይማኖተ አበው፣ መጽሐፈ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ተረፈ ቄርሎስ ወጰላድዮስ እና ሌሎች መጻሕፍትን በጉባኤ ቤታቸው ስም አሳትመዋል፡፡

ድንልናን ከምንኵስና፤ ምንኵስናን፣ ከሊቅነት፤ ሊቅነትን ከቅንነት እና ከትሕትና ጋር አስተባብረው የያዙትን እኒህን አንጋፋ የቤተ ክርስቲያን አባት ማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ ዓመት እንግዳ አድርጎ አቅርቦላቸኋል፡፡

ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ከመለሱልን ጥያቄዎች መካከል፡-

• በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዘመን ቈጠራ የሚጀመረው ከፍጥረተ ዓለም ወይስ አዳም ከገነት ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ?

• በሀገራት መካከል ያለው የአቆጣጠርና የጊዜ ልዩነት (የዓመት፣ የቀንና የሌሊት፣ የሰዓት) ከምን የመጣ ነው?

• የዘመን መለወጫ በዓል ለምን በመስከረም ወር ተደረገ?

• የወራቱ (ከመስከረም - ጳጕሜን ያሉት) ስያሜ የተሰጠው ከምን አኳያ ነው?

• በአራቱ ወንጌላውያን (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሐንስ) እና በጸወርተ መንበር /አራቱ እንስሳ/ ማለትም ገጸ ሰብእ፣ ገጸ አንበሳ፣ ገጸ እንስሳ እና ገጸ ንስር መካከል ያለው የስም ትስስር ምሥጢሩ ምንድን ነው?

• ዳግም ምጽአት፣ ርኅወተ ሰማይ (የሰማይ መከፈት) እና የጸሎት ማረግ (ወደ እግዚአብሔር መድረስ) በጳጕሜን ወር የሚነገርበት ምክንያት ምንድን ነው?

• ‹‹በስምንተኛው ሺሕ ዓለም ያልፋል›› የሚለው አስተሳሰብ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንዴት ይታያል?

የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በተጨማሪም

• በወርኀ ጳጕሜን በቤተ ክርስቲያን ስለሚነገሩ ምሥጢራት፣

• ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ትምህርት እና ስለ ሄሮድያዳ ስሕተት፣

• ስለ ዕንቍ ጣጣሽ እና ‹‹አበባየሁሽ›› (‹‹አበባ አየሽ ወይ››) ስለሚለው የልጃገረዶች ጨዋታ፣

• አዲስ ዓመት ሲመጣ፣ በዓሉንም ሲያከብሩ ስለሚያስታዉሱት ቁም ነገር እና

• ስለ አዲስ ዓመት መንፈሳዊ አከባበር

መጽሐፋዊ ትዝታዎችን በማካተት ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ቃለ እግዚአብሔር ያስተምሩናል፡፡

ዝግጅቱ መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 - ቀኑ 8፡00 በአሌፍ ቴሌቭዥን ጣቢያ ይተላለፋል፡፡

መርሐ ግብሩን እንድትከታተሉ በአክብሮት ጋብዘናችኋል፡፡

ምስጋና

• ለጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔ ዓለም ገዳም ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤትና ማኅበረ ካህናት፤

• ጥያቄያችንን ተቀብለው፣ ፈቃደኛ ኾነው፣ ጊዜ ሰጥተው ላስተማሩን፣ ለመከሩን፣ ለገሠፁን ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ፤

• ለመንበረ መንግሥት መድኃኔ ዓለም የአራቱ ጉባኤያት ትምህርት ቤት ደቀ መዛሙርት፤

• ለጎንደር ማእከል ልዩ ልዩ ክፍል አስተባባሪዎች፤

• ለዐፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት ሠራተኞች፤

• የግል ሥራውን ትቶ ከምንፈልገው ቦታ ድረስ በግል መኪናው በማጓጓዝ ቀረፃውን በተቀላጠፈና በተሳካ መንገድ እንድናከናውን ላገዘን ለዲያቆን መልካሙ ጸጋዬ፤

በአጠቃላይ ይህን መርሐ ግብር ለመቅረፅ ወደ ጎንደር ከተማ በሔድንበት ወቅት በልዩ ልዩ መንገድ ለተባበሩን ወገኖች ዅሉ በመድኃኔ ዓለም ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡


አንድ ሃይማኖት

#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~JoIN~~~
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
" በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። "
(መዝሙረ ዳዊት 65:11)
🌹🌹🌹🌷🌷🎋🌼🍂🌼
እንኳ አደረሳችሁ አደረሠን አዲሱ🌼🌻🌿🌿 አመት
🌺🌺🌺🌻 @And_Haymanot የሠላም💝🌺🌸🌸🌸የፍቅር 🌺🌺🌺🌺🌺💐💐🌻🌼🌼የአንድነት🌺🌺🌺🌺­🌺🌼🌻🌺🌺🌺🌺🌺🌸
🌹🌺🌺የወንጌል 🌸🌸🍁🍓🌷🌿🌿💐🌻🌼የንነስሃ🍂🍂💕🌺­🌺🌹🌹የመከባበር🌹🌺🌺🌺🌻🍓💝 የጎደለው ሚሞላበት🌹🌺🌺🌹🌼🌸💝💝💝💝💝💝🌸🌸🌹­🌺🌺💐
🌺🌺🌺🌹መልካም 🌺🌺❤️🌼🌼🌼አዲስ 🌹🌹🌹🌹💐💐💝🌿🌿🌿አመት🌹🌹🌹🌺🌺🍀🌸­🌹🌺🌺 ይሁንልን 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌸አሜንን 🌺💕🌸
@And_Haymanot
🌺💕💕🌺💕🌺Happy 🌹🌺💕 🌹🌺💕🌸New 🌹🍁💝💝💕🌺💝🌸💕🌺🍀Year 💐🌻🌹🌺💕🌸🌸🌸💝💝💝💝🌸🌸😘😘😘😘😘😘
አንድ ሃይማኖት ተዋህዶ
እንኳን ለዘመነ ማርቆስ አደረሠን
ሃይማኖት የልብ ብቻ አይደለም!!

@And_Haymanot

አንዳንድ ሰዎች የማዕተብ ሥርዓትን ለመቃወምና ዘመናውያን መስለው ለመታየት ‹‹እምነት በልብ ነው›› ይላሉ፤ ተሳስተዋል! ሃይማኖት የልብ ብቻ አይደለም፤ የጠቅላላው ሕዋሳት ሁሉ ናት፡፡ እግዚአብሔርን ስንወደውና ስናመልከው በልባችን ብቻ ሳይሆን በአፋችንም በአንገታችንም በጠቅላላው ሰብአዊ ተፈጥሯችን ሁሉ መሆን ይገባዋል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር
የጠቅላላው ሰውነታችን አምላክና ፈጣሪ ስለሆነ ነው፡፡ ‹‹ስለዚህ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ፡፡›› (ማቴ.10÷32÷33)
በዚህ ቃለ ወንጌል መሠረት በኢ-አማንያን ዘንድ ክርስቲያን መሆናችንን የምንገልፀው በልባችን ብቻ ሳይሆን በቃላችንና በሥራችንም ጭምር ነው፡፡ በአንገታችንስ እንዳንመሰክርለት ማን ያግደናል? በአንገታችን ባለው ማዕተብም ለእግዚአብሔር
እንመሰክራለን፡፡ የስሙን ምልክት በአንገታችን እናኖራለን፤
አናፍርበትም!! የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በጥምቀታችን እንደምንመሰክር የጥምቀታችንንም ዓርማ በማተባችን እናረጋግጣለን፡፡ (ሮሜ16÷13፤ ኢዩኤ. 2÷32፤ ሮሜ 6÷1-5፤ ማቴ.5÷11-12፤
1ኛጴጥ.3÷21-22፤ 4÷12-16)

አንድ ሃይማኖት
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ተዋህዶ
ልጆቼ
አገልግለው ጠፉ
ተሰብስበው ተበተኑ
ከመባል ይሠውራችሁ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የማርያም ልጅ ከቤቱ አይለየን የተዋህዶ ልጆች
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጋሻው ተሃድሶ የሚባል ተቋም የለም ቢኖርና ብታሳዩኝ ያለው የሱን ቤት እንድናሳየው ነው እንዴ¿
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ተዋህዶ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአሰግድ ሳህሉን ውግዘት እነሆ...
እግዚአብሔር ቤቱን ያፅዳ ለጠፉትም ልቦና ይሥጥልን
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ተዋህዶ