፩ ሃይማኖት
8.98K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
.+"የመስቀል ወፍ"+.

@And_Haymanot

ይህች ወፍ በአገራችን በኢትዮጵያ "የመስቀል ወፍ" በመባል
ትታወቃለች፡፡ ምክንያቱም ለተወሰኑ ወራት ያህል በሌላ ሥፍራ ተሰውራ ቆይታ የመስቀል በዓል (መሥከረም 17) ሲያቃርብ ብቅ ብላ ስለ ምትታይ ነው፡፡
.
እንግዲህ ከዚች ወፍ የዘንድሮ 2012 ዓ.ም የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ትልቅ ትምህርትን እንማራለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
መችም እግዚአብሔር በአንድም በሌላም መንገድ ሕዝቡን ያስተምራል፡፡ ኢዮ.33፡14
.
ዛሬስ ልዑል እግዚአብሔር ይህችን ወፍ ምክንያት አድርጎ ቢያስተምረን ማን ይከለክለዋል? ይህች ወፍ የመስቀሉ ፍቅር ከገባቸው ከኢትዮጵያውያን
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ጋር የመስቀሉን በዓል
በዝማሬና በምሥጋና ለማሳለፍ ለበዓሉ አከባበር የሚያስፈልገውን
ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቃ ከበዓሉ ቀደም ብላ በየ አከባቢያችን
መገለጧ የሚገርም ትርዒት ነው፡፡
ደግሞም ይህች ወፍ ለመስቀሉ ትልቅ ፍቅር ያላት ነው የምትመስለው፡፡
መናፍቃን ግን የዚህችን ወፍ ያህል እንኳ ዕውቀት አጥተው ከዕውቀት ነፃ በሆነ አመለካከት መስቀሉን እየተቃወሙ
ሆዳቸውን አምላካቸው አድርገው ክብራቸውን በነውራቸው ሽጠው
የመስቀሉ ጠላቶች ሆነው መመላለሳቸው የሚያሳዝን ነው፡፡ ፊል.3፡18
.
በእርግጥም የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት መናፍቃን ሞኝነት፥ አላዋቂነት፥ መሀይምነት፥ ድንቁርና... ቢሆንም ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው። 1ቆሮ.1:18
.
ምናልባት የመስቀሉ ፍቅር ያልገባችሁ ሰዎች! እስኪ ወፊቱን ጠይቋት!
ለምን ይሆን በመስቀል በመስቀል በዓል ላይ የምትመላለሰው? ለምንስ ይሆን ትኩረቷን በመስቀሉ ላይ ያደረገችው?
ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?
1ቆሮ.11:14
.
ይህች ወፍ የሙጥኝ ብላ ትኩረቷን በመስቀሉ በዓል ላይ በማድረጓ ትምክህቷም ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስን ትምክህት ነው የሚመስለው፡፡ ገላ.6፡14
.
እንግዲህ ይህች ወፍ የመስቀሉን ነገር የዘነጉ ሰዎች እንዲያስቡበት ቀደም ብላ መጥታ ከእግዚአብሔር በተሰጣት
ልዩ ዜማ የበዓሉን መድረስ ታበሥራለች፡፡
.
በቃ ምን አለፋችሁ! ወፊቷ አስተውሎ ለተመለከታት ሰው ሁሉ ስለ መስቀሉ ፍቅር በጥበብ የምትሰብክ ልዩ ሰባኪት ናት፡፡ ስለዚህ ልብ ብላችሁ ተመልከቷት ግብዣዬ ነው፡፡
.
አድራሻችሁ ከመስቀሉ ሥር የሆናችሁ ሁሉ መልካም የመስቀል በዓል የሠላምና የፍቅር በዓል ይሁንላችሁ!
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አስታርቂኝ


አስታርቂኝ ድንግል ማርያም /2/ 
ከልጅሽ /3/ ከመድኃኔዓለም 

አስታርቂኝ ኃጢአትን ሰርቼ 
አስታርቂኝ ጫካ ውስጥ ቆሜአለው 
አስታርቂኝ ሥራዬ አሳፍሮኝ 
አስታርቂኝ ዘወትር አነባለው 
አስታርቂኝ ልጄ አዳም ብሎ 
አስታርቂኝ አምላኬ ሲጠራ 
አስታርቂኝ እነሆኝ ለማለት 
አስታርቂኝ አንደበቴ ፈራ 
አዝ ------------ 
አስታርቂኝ ሀብትን ተካፍዬ 
አስታርቂኝ ከገዛ አባቴ 
አስታርቂኝ ከቤቴ ኮበለልኩ 
አስታርቂኝ ይሻለኛል ብዬ 
አስታርቂኝ ገፍቼ ወጥቼ 
አስታርቂኝ የቤቴን ገበታ 
አስታርቂኝ ልበላ ተመኘሁ 
አስታርቂኝ የእንስሳት ገፈራ 
አዝ--------- 
አስታርቂኝ ወደ አባቴ ልሂድ 
አስታርቂኝ አሁን ተነሥቼ 
አስታርቂኝ ይቅርታ ልጠይቅ 
አስታርቂኝ እግሩ ስር ወድቄ 
አስታርቂኝ ልጅነቴ ቀርቶ 
አስታርቂኝ አድርገኝ ባርያህ 
አስታርቂኝ ከሞያተኞችህ 
አስታርቂኝ እንደ አንዱ ቆጥረህ 
አዝ ------ 
አስታርቂኝ ገና ሩቅ ሳለው 
አስታርቂኝ አባቴ አይቶኝ 
አስታርቂኝ ወደእኔ ሮጦ 
አስታርቂኝ አቅፎ ነው የሳመኝ 
አስታርቂኝ ጠፍቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ተገኘልኝ አለ 
አስታርቂኝ ሞቶ የነበረው 
አስታርቂኝ ደግሞ ሕያው ሆነ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot
                    
+ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማን(The Martyrdom of St. Arbsima (Repsima) the Virgin) በተመለከተ ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ይሉናል?


በዘማርያም ዘለቀ

የሻሸመኔ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች 'አሁን በቅርብ የመጣች....' በሚል ጸያፍ አነጋገር ሲዘልፉ ይደመጣሉ፡፡ በውኑ ስለ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በትርጓሜ መጻሕፍት አልተነገረምን?!

👉 የመጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ይናገራ!! መጽሐፈ ቅዳሴ ከቀድሞ አባቶቾ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባቡና ትርጓሜው አዳኝተን(ዳኛ አድርገን) እንዲህ እንላቸዋለን፡፡

❖ ጸሎት ዘጎርጎርዮስ ቅድመ ግብዓተ መንጦላዕት(ወደ መቅደስ ከመግባት አስቀድሞ ጎርጎርዮስ የጸለየው ጸሎትን) ሲተረጉም:- ዲዮቅልጥያኖስ(Emperor Diocletian) መልከ መልካም ብላቴና ፈልጋችሁ ሥዕሏን ሥላችሁ አምጡልኝ ከዚያ በኋላ እሷን ታመጡልኝአላችሁ ብሎ ሠራዊቱን በያገሩ ሰደደ፤ ይህች አርሴማ ፸፪ (72) ያህል ደናግል ይዛ ከተራራ ላይ ወጥታ ተቀምጣለች፤ ኸያ ዓራቱ ደናግል፤ የቀሩት መዓስባን(ያገቡ) ናቸው፡፡ እመ ምኔቲቱ አጋታ(Agatha(Ghana)) ትባላለች። እየፈለጉ ካለችበት ደረሱ፡፡ ሥዕሏን ሥለው ወስደው ሰጡት፡፡ መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል፤ እስዋን አምጡልኝ አላቸው፡፡ እስዋም እንዳስፈለጋት አውቃ አርማንያ ወረደች፡፡ እሱም ከዚያ እንደ ወረደች አውቆ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ ይባላል፤ እንዲህ ያለች ብላቴና ወዳገርህ መጥታለችና አስፈልገህ ስደድልኝ ብሎ ላከበት፡፡ ቢያስፈልግ አገኛት፤ ቢያያት እንደ ፀሐይ ስታበራ አያት፤ ይህችንማ ለራሴ ምን ይዤ ለሱ እሰድለታለሁ ብሎ እመ ምኔቲቱን ይህችን ብላቴና ለምኝልኝ አላት፡፡ አይሆንም ያልሁ እንደሆነ ነገር አጸናለሁ ብላ ይሁን አለችው፡፡ ኋላ ግን ለሰማያዊ መርዓዊ ለክርስቶስ አጭቸሻለሁና ይህ ርኩስ እዳያረክስሽ እወቂ አለቻት(told her that she must not forsake her true Bridegroom, the Lord Jesus Christ)፡፡ ብላቴኖች ሰዶ አስወስዶ መልኳን አይቶ ብታምረው ተራምዶ ያዛት፤ ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ወቃችው፡፡ ንጉሥ ነውና ቢያፍር በሰይፍ አስመታት፡፡ ከዚያ አያይዞ መላውን አስፈጅቷቸዋል፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ያልሆነ ስራ ማሰራት ኋላ ማጸጸት ልማዱ ነውና መልኳ ትዝ እያለው እህል ውሃ የማይቀምስ ሆነ፡፡ ብላቴኖቹ ሲሞት እናያለን? አደን እንጂ ኃዘን ያስረሳል፤ አደን ይዘነው እንሂድ ብለው ይዘውት ሄዱ፡፡ በዚያ ባለበት ዕሪያ ሁኖ ቀርቷል፡፡ ማን ባዳነልን እያሉ ሲጨነቁ መልአክ ለእኅቱ ከጎርጎርዮስ (Saint Gregory, Bishop of Armenia) በቀር የሚያድንላችሁ የለም አላት። በሃይማኖት ምክንያት ተጻልቶት ከአዘቅተ ኲስሕ አስጥሎት ነበርና የሞተ መስሏቸው ደነገጡ፡፡ መልአክ ላንዲት መበለት ነግሮለት አንድ ፥ አንድ እንኩርኩሪት እየጣለችለት ፲፭ (15) ዓመት ያህል ኑሯል፡፡ የኒህ ክርስቲያን አምላክ ጽኑ እንጂ ነው እንዳለ ብለው ገመድ ቢጥሉ መኖሩን ለማስታወቅ ገመዱን ወዘወዘው ሐብሉን ቢስቡት ከሰል መስሎ ወጥቷል፡፡ ወንድሜን አድንልኝ አለችው፡፡ ያለበትን ታውቂውአለሽን አላት፡፡ አዎን አለችው፡፡ አስቀድሞ አጽመ ሰማዕታት ያለበትን አሳይኝ ብሏት አሳየችው፡፡ ዓፅመ ሰማዕታትን አስቀብሮ በዪ ውሰጂኝ አላት፡፡ ይዛው ሄደች፡፡ አንተ ባድንህ በፈጣሪዬ ታምናለህን አለው፡፡ ወአድነነ ርእሶ ወአንገሥገሠ ርእሶ ከመ ኦሆ ዘይብል ይላል፡፡ ግዕዛኑን (አዕምሮውን) አልነሣውም ነበርና ይሁን አለው። እንዳይታበይ ከእጁ ከእግሩ የእርያ ምልክት ትቶለት ጸልዮ አድኖታል፡፡ አስተማረው አሳመነው አጥምቀኝ አለው፡፡ ማጥመቅስ ሥልጣን ካላቸው ሂደህ ተጠመቅ፤ ለኔ ስልጣን የለኝም አለው፡፡ የአንጾኪያውን ሊቀ ጳጳስ አስመጥቶ ተጠምቋል፡፡ {መጽሐፈ ቅዳሴ ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባብና ትርጓሜው፤ ሥርዓተ ቅዳሴ፤ ምዕራፍ ፪፤ ገጽ. 20 -21}


✞ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አማላጅነት፤ ቃል ኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ Their intercession be for us, and Glory be to Our God, forever, Amen.✞✞✞

@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
ለአዲስ ዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ ገቢ ተማሪዎች

እንኳን ለከፍተኛ ትምህርት አበቃችሁ እያልን በምትሔዱበት ቦታ ሁሉ መልካም የትምህርት ዘመንን እየተመኘን ክርስቲያን በሁለት በኩል እንደተሳለ ሠይፍ ሊተጋ ይገባዋልና በምትሄዱበትና በሄዳችሁበት ከአለማዊ ትምህርት በተጨማሪ በመንፈሳዊ ትምህርታችሁ ጠንክራችሁ በተለይም ሊያስቷችሁ ተዘጋጅተው ከሚጠብቋችሁ ከሃድያን ራሳችሁን ጠብቃችሁ በግቢ ጉባኤ በሚዘጋጁ መርሃ ግብሮች እንድታሰተፉና በሃይማኖታችሁ እንድትፀኑ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ለአዲስ ገቢዎች በማዳረስ ተባበሩ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሰበር ዜና
ቤተ ክርስቲያን የጥቃት መከላከል ግብረ ኃይል ታቋቁም ዘንድ ፓትርያርኩ ጥሪ አቀረቡ

@And_Haymanot

ለቤተ ክርስቲያን መብት መከበር እስከሞት መሥዋዕት ለመኾን መሥራት አለብን ሲሉም አክለዋል፡፡ ዛሬ ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. በተጀመረው የጥቅምቱ ሲኖዶስ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግራቸው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
ምልዐተ ጉባኤው ሊመለከታቸው ከሚገባቸው ወሣኝ የተባሉ ነጥቦች መካከል ትኩረት እንዲደረግባቸው አመላክተዋል፡፡

• ፩. በሀገራችን በተፈጠረው ያለመረጋጋት ክስተት አብያተ
ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ካህናትና ምእመናን ተገድለዋል፤አሁንም ስጋቱ እንዳለ፣ ከቀረበልን የአህጉረ ስብከት ዘገባ ሰምተናል፤ በዐይናችንም ዐይተናል፤ ነባር የቤተ ክርስቲያናችን
ይዞታዎች ሥልጣንን መከታ ባደረጉ ወገኖች እየተነጠቁ ነው፤ምእመናን በሚደርስባቸው የማያባራ ተጽእኖና አድሎ ከቀያቸው እየተፈናቀሉና እየተሰደዱ ነው፡፡ ይህ ድርጊት እንዲቆም እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕት መኾን ከዚህ ጉባኤ አባላት ይጠበቃል፡፡

• ፪. መንግሥትም በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠውን የሃይማኖት ክብር ነፃነትና እኩልነትን በሚሸረሽሩ የታችኛው መዋቅር ባለ ሥልጣናት ላይ የማያዳግም የእርምጃ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጥብቅ ክትትል ማድረግ አለብን፡፡

• ፫. በውስጣችን ያለው ያልዘመነ አሠራርም የምእመናንን ልቡና እያቆሰለ የሚገኝ ሌላው መንጋውን ለመጠበቅ የተሰጠንን አደራ እንዳንወጣ እንቅፋት የኾነብን ጉዳይ ነው፤ ይህንን ችግር
ከሥር መሠረቱ ነቅለን በማጽዳት ማስተካከል አለብን፡፡

• ፬. ቀደም ሲል የተጠኑትን የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ችግር መፍትሔና የመሪ ዕቅድ ጥናቶች ይህ ዐቢይ ጉባኤ በወሠነው መሠረት በአስቸኳይ ይተገበር ዘንድ ጠበቅ ያለ መመሪያ ሊያስተላልፍ ይገባል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ በብልሹ አሠራር አዙሪት የሚታመስ የቤተ ክርስቲያን አሠራር ሊኖር አይገባም፤
በዚህ ዓመት አሠራራችንን ሁሉ አስተካክለን ወደ መንጋ ጥበቃና ወደ ልማት ሥራችን በፍጥነት መሸጋገር አለብን፡፡

• ፭. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን ዙሪያ መለስ ጥቃት ለመመከትና ለመከላከል ብሎም ለማስቆም አንድ የጥቃት መከላከል ግብረ ኃይል እንዲሁም በየአካባቢው የሚሰነዘሩት ጥቃቶች፣ወከባዎች፣ ተጽእኖዎችና አድሎአዊ አሠራሮችን እየተከታተልን ትክክለኛ መረጃ የሚያቀርብ የተዋስኦ (ኮሙኒኬሽን) ግብረ ኃይል በአሁኑ ጉባኤያችን አቋቁመን ቤተ ክርስቲያናችንንና
መንጋችንን ከመከራ እንድንታደግ የሀገራችን ሰላምና የሕዝባችንን አንድነትን በጽኑ እንድናስጠብቅ አባታዊ
መልእክታችንን እናስተላልፋለን ብለዋል፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሰበር ዜና

ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባውን ሊያቋርጥ ነው፤
“እየተቃጠለንና እየተገደልን አንሰበሰብም፤ ልጆቻችን ያሉበት
ሔደን እዚያው አብረን እንቃጠላለን፤ እንሞታለን”/ብፁዓን አባቶች/
• በኦሮሚያ ልዩ ልዩ ከተሞች በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን
ላይ እየተፈጸመ በሚገኘው አስከፊ ጥቃት እና ግድያ ሳቢያ ቅዱስ ሲኖዶስ የምልአተ ጉባኤውን ስብሰባውን ሊያቋርጥ ነው፤
• የተመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለብዙኀን መገናኛዎች እና ለዓለም ኅብረተሰብ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚያሰማውን መግለጫ እያረቀቁ ነው፤
• ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለመከላከያ ሚኒስትሩ እና ለሰላም ሚኒስትሯ ለመጨረሻ ጊዜ የሚደርስ ደብዳቤም እያዘጋጁ ነው፤
• በባሌ፣ በአርሲ፣ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በድሬዳዋ እና በአዳማ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን፣ የአክራሪዎች እና ነውጠኞች ሰለባ እየኾኑ ነው፤ ቤታቸው እና ንብረታቸው እየተጠቃ ነው፤ አስከፊ
እልቂት ማንዣበቡ ተገልጿል፡፡
•በትላንትናው እለትም ቅዱስ ሲኖዶሱ ፀሎተ ምህላ ማወጁ ይታወቃል።
ምንጭ: ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ የመንግሥት ልኡክ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋራ ይነጋገራል፤

ምልአተ ጉባኤው በሚቀርቡ
ማስረጃዎች ላይ መምከሩን ቀጥሏል
በተወሰኑ የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት ከተሞች፣በኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየደረሰ ያለውን የብሔር እና የሃይማኖት አክራሪዎች ጥቃት እና ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም በማድረግ ጉዳይ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ የፌዴራል መንግሥት ልኡክ፣
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን እንደሚያነጋግር ተጠቆመ፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ለማ መገርሳንና የሰላም ሚኒስትሯን ወ/ሮ ሙፈሪአት ካሚልን ያካተተው ይኸው ልኡክ፣ ምልአተ ጉባኤውን፣ ዛሬ ዓርብ፣ ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ላይ ያነጋግራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምልአተ ጉባኤው ትላንት ጠዋት የሦስት ቀናት የጸሎት እና የምሕላ ዐዋጅ ካወጣና የሰላም ጥሪውን ካስተላለፈ በኋላ የቀጠለውን መደበኛውን የስብሰባ ሒደት በድንገት በማቋረጥ፣ ከየአህጉረ ስብከቱ የደረሱ የጉዳት እና የስጋት መረጃዎችንና
ሪፖርቶችን እያሰባሰበ መወሰድ ባለበት አቋም ላይ መወያየት ጀምሯል፤ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ደብዳቤ ለመጻፍና መግለጫም ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደኾነ
መገለጹ ይታወሳል፡፡ “በአሁኑ ሰዓት መሥመር እየለቀቀ የመጣውን፣ በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን እየደረሰ ያለው ማቆሚያ የሌለው ጥፋት በጥብቅ ማቆምን ይመለከታል፤” በሚል ርእስ የተዘጋጀው ጽሑፍ በዋናነት፣ የክልል የጸጥታ ኀይሎች በአካባቢው እያሉ ቢጠየቁም ሊታደጉን አልቻሉም፤ ስለዚህ በአስቸኳይ አፋጣኝ ርምጃ በመውሰድ ጥቃቱን እንድታስቆሙልን የሚል እና
የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የቅዱስ ሲኖዶስ የምልአተ ጉባኤን በአስቸኳይ እንድታነጋግሩን በማለት የሚጠይቅ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ አጽንዖት ተሰጥቶት ተገቢ እና አፋጣኝ ምላሽ
የማይሰጠው ከኾነ ግን፤ ለሚደርሰው የሕይወት እና የንብረት ጉዳት መንግሥት ሓላፊነቱን እንደሚወስድ፤ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናንን በማስተባበር እና ችግሮች ወደተፈጠሩባቸው ቦታዎች በመሔድ ከአማኞች ጋራ አብረው ሰማዕትነት ለመቀበል እንደሚገደድ
የሚያስጠነቅቅ ነው፡፡
ምንጭ : ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ከመንግሥት ጋራ የሚደረገው ውይይት ለቤተ ክርስቲያን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና የሚያረጋግጥ ሊኾን ይገባል፤ “ለቋሚ
ስጋታችን ቋሚ የደኅንነት ዋስትና ውል ላይ መደረስ አለበት”

• መግለጫውን ከውይይቱ በኋላ ለመስጠት ታስቦአል፤ወደተመረጡ የችግሩ አካባቢዎች የሚሰማሩ ብፁዓን አባቶች ይመደባሉ፤
***
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ከሚመራው
የመንግሥት ልኡክ ጋራ የሚያደርገው ውይይት፣ የብሔር እና የሃይማኖት አክራሪዎች ቋሚ የጥቃት እና የተጽዕኖ ዒላማ እየኾነች ለምትገኘው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ቋሚ
የደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት የሚደረስበት ሊኾን እንደሚገባው ተጠቆመ፡፡
ብሔርንና ቋንቋን ዐቢይ እና ቀዳሚ የማንነት መገለጫ ከማድረግ አልፎ በአመዛኙ የጠርዘኝነት ዝንባሌ የሚታይበት ያለፉት 27 ዓመታት የአገራችን የፖሊቲካ አስተሳሰብና ሥርዐት፣ የኢትዮጵያውያን የአንድነት ምልክትና ተቋም ኾና የኖረችውን
ጥንታዊትና ታሪካዊት እናት ቤተ ክርስቲያን፣ የጥቃትና የተጽዕኖ ዒላማ ማድረጉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚገታ ባለመኾኑ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ መንግሥት ቋሚ የደኅንነት ዋስትና በሚሰጥበት ኹኔታ ላይ በግልጽ ሊነጋገር እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ ባለፉት ኹለት ቀናት ብቻ ለግለሰብ ድጋፍ በሚል በተለያዩ
የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተካሔዱ ሰልፎች፣ በቅጽበት የብሔርና የሃይማኖት መልክ ይዘው፣ ወገን ለይተው ምእመናንና ቤተ ክርስቲያንን የጥቃት ዒላማ ያደረጉበት ኹኔታ እየተለመደ
መምጣቱ የደኅንነት ዋስትና ውሉ የግድ አስፈላጊ መኾኑን ያሳያል፤ ተብሏል፡፡
ካህናትንና ምእመናን በአሠቃቂ ኹኔታ በመግደል እና አብያተ ክርስቲያናትን በማቃጠል፣ ንብረታቸውን አውድሞና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን አሽመድምዶ ከቀዬአቸው በማፈናቀል እየተገለጸ
ያለው ጥቃትና ተጽዕኖ በመሠረቱ፣ ርእዮተ ዓለማዊ እና መዋቅራዊ መነሻ እንዳለው አፈጻጸሙ በግልጽ የሚያሳይ
በመኾኑ፣ ከመንግሥት የሚጠበቀው የደኅንነት ዋስትናም በዚያው ትይዩ፣ መዋቅራዊና ሥርዐታዊ እንጂ በቃላት ሽንገላና ባዶ ተስፋ ሊታለፍ እንደማይገባው ተገልጿል፡፡

መዋቅራዊ እና ሥርዓታዊ የደኅንነት ዋስትናው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የብሔርና የሃይማኖት አክራሪዎች ተከታታይና ቋሚ የጥቃት ዒላማ እየኾነች ያለችበትን
ሐቅ በነባራዊነት አምኖና ተቀብሎ ጥቃቱን ከማስቆም እንደሚነሣ አስተያየት ሰጪዎቹ ያስረዳሉ፡፡ ይኸውም፣ ቅምጥ/ ግልጽ የደኅንነት ስጋት ያለባቸውን አካባቢዎች በጋራ ለይቶና የጸጥታ ዕቅድ አውጥቶ የታሰበውን ጥቃት አስቀድሞ ያመክናል፤
ይከላከላል፤ አደጋ ሲደርስም በፍጥነት ደርሶ ጉዳትን ይቀንሳል፡፡

በዚህ ረገድ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን የሀገራዊ ሰላምና ደኅንነት ዋነኛ አጋር ለማድረግና በዘላቂነት አብሮ ለመሥራት
ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋራ ግልጽ ስምምነት ላይ መድረስ ይኖርበታል፤
ብለዋል፡፡

እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ሌላው መዋቅራዊ እና ሥርዐታዊ የደኅንነት ዋስትና ማረጋገጫ፣ የሰሞኑን ጨምሮ በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ሲፈጸም ሓላፊነታቸውን ያልተወጡ፣በቀጥታ ይኹን በተዘዋዋሪ ተባባሪ የኾኑ ባለሥልጣናትን በሕግ ተጠያቂ በማድረግ፣ ተጎጂዎችንም በተገቢው በመካስ ፍትሕን ማረጋገጥ ነው፡፡
ሦስተኛው እና መሠረታዊው ደግሞ፣ በኢሕአዴጋዊ ርእዮተ ዓለም እና ፕሮግራም መነሻነት፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ማንነቷና አገራዊ ውለታዋ ተዘንግቶ፣ የአንድ ወገንና የጨቋኞች
አጋር ተደርጋ በትውልዱ ዘንድ የተሣለችበትን ያለፉት 27 ዓመታት ስሑት ፖሊቲካዊ ትርክቶች፣ ከመንግሥት የሥልጠና እና የትምህርት ሰነዶች እንዲታረሙ ማድረግ እንደኾነ
አብራርተዋል፡፡

ምልአተ ጉባኤው፣ ዛሬ ቀን 10፡00 ላይ ከባለሥልጣናቱ ጋራ ከሚያደርገው ውይይት ቀደም ብሎ፣ ከ17ቱ አጀንዳዎቹ መካከል በአስቸኳይነት የለያቸውን፣ የ2012 የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በጀት መርምሮ ያጸድቃል፤ በግንቦቱ የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤው የሠየመውን የሀገራዊ ሰላም እና አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ
ጥናት እና ሪፖርት ላይም ይነጋገራል፡፡
ከዚኹ ጋራ በተያያዘ፣ የጥቃት መከላከል እና የኮሚዩኒኬሽን ኀይለ ግብሮችን(በአጀንዳው ውስጥ በተቀመጠበት አገላለጽ፥ “የሕዝብ ግንኙነት እና የወቅታዊ ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ”) የማቋቋም ጉዳይንም እንደሚያነሣ ይጠበቃል፡፡
ከግንቦቱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ማግሥት ተቋቁሞ ሲንቀሳቀስ የቆየው የመንፈሳውያን ማኅበራት ኅብረት አስተባባሪ ኮሚቴም፣ የፈጸማቸው ተግባራት በዐቢይ
ኮሚቴው ሪፖርት የተካካተ ሲኾን፣ የሀገራዊ ሰላም እና አንድነት ዐቢይ ኮሚቴው አካል ኾኖ የሚቀጥልበት ይኹንታ ከምልአተ ጉባኤው እንደሚሰጠው ተጠቁሟል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ከባለሥልጣናቱ ጋራ ከተወያየና
ወደተመረጡ የችግሩ አካባቢዎች የሚሰማሩ ብፁዓን አባቶችን
ከመደበ በኋላ፣ ቀሪ አጀንዳዎችን በሌላ ጊዜ ተረጋግቶ ለማየት በመቅጠር መደበኛ ስብሰባውን በአጭሩ እንደሚያጠናቅቅ
ተነግሯል፡፡
ሐራ ዘተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ
ተጠለይ በእግዚአብሔር ታዛ


ከሚራራልን ፍቅር ከሆነው
ዘላቂ ሰላም ከእግዚአብሔር ነው
ይህን እወቂ ይህን ተረጂ
በልብሽ ጉልበት ለርሱ ስገጂ

አዝ ❖ ❖ ❖
በሠይፍ ያልቃሉ ሠይፍ የሚያነሱ
የሚራራልን ሲፈርድ ንጉሱ
በቀል የርሡ ነው አይደለም ያንቺ
በጸጋው ታጥረሽ በጸሎት በርቺ

አዝ ❖ ❖ ❖
ይህ ውጣ ውረድ ይህጉስቁልናው
በእግዚአብሔር ነው መከራ ማብቂያው
ሰላም ይሁን ሲል ይሆናል ሰላም
ያሳየሽውን ፍቅር አይረሳም

አዝ ❖ ❖ ❖
ማራት ኢትዮጵያን ማራት ሀገሬን
በየሔድኩበት መጠሪያ ስሜን
ይብቃት ሌሊቱ ይውጣላት ፀሃይ
አሁን ይዘርጋ እጅህ ከሰማይ

አዝ ❖ ❖ ❖
እንድትፈራርስ ጠላት ሸምቋል
ብርቱዉን ጉልበት ከአፈር ደባልቋል
ይህን ግፍ አስብ ዘንበል በልላት
ካንተ በስተቀር መሔጃ የላት
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
@And_Haymanot
ሰበር ዜና
Share
@And_Haymanot

የመንግሥት ልዑካን ቤተ ክርስቲያን ትራዳቸው ዘንድ ተማጸኑ

ዛሬ ዐርብ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት ለማነጋገር ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት
የመጡት የመንግሥት ባለሥልጣናት ቤተ ክርስቲያን ትራዳቸው ዘንድ ተማጽኖ አቅርበዋል፡፡ ወደ ጉባኤው የመጡት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ
መኮንን፣ የመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳ፣ የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል እና የፌድራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ናቸው፡፡
ለእነዚህ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አባቶች ኹለት
መሠረታዊ ጥያቄዎችን አቅርበውላቸዋል፡፡
*አንደኛ ቤተ ክርስቲያን ከዛሬ ነገ ይሻላል በማይባል ጥቃት ውስጥ ገብታለች፡፡ ይህ ያላባራ ጥቃት ይቆም ዘንድ መንግሥት የሚሰጠው ዋስትና አለን?
*ኹለተኛ፡- ጥቃት አድራሾችን ለይቶ ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ ያለው ቁርጠኝነት እስከምን ድረስ ነው? የሚሉ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች በተጨማሪ ብፁዓን አበው “አንዳንድ ወገኖች ቤተ ክርስቲያንን ሲላቸው በፊውዳል ስም፣ ሲላቸው በነፍጠኛ ስም፣ ሲላቸው በአንድ ጎሳ ስም እየፈረጁ ስሟን ሲያጠለሹ ታግሰናል፡፡ ግን ይህ አልበቃቸውም፡፡ ወደ አካላዊ ጥቃት ዘምተዋል፡፡ አሁን የምንጠይቃችሁ አንድ ጥያቄ ነው፡፡
እርሱም ችግሩን ለመቆጣጠር አቅም አላችሁን? የሚል ነው፡፡ አቅም ከሌላችሁ አሁኑኑ ንገሩን፤ እየሞተ የሚቀጥል
አይኖርም፡፡” በማለት ፍርጥም ያለ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በአንጻሩ ከፍተኛ የምንግሥት ባለ ሥልጣናት አበውን በማመስገን ለጥያቄው መልስ ሰጥተዋል፡፡ በጥቅሉ አቅም አለን፣ እየተነሣ ያለውን አቧራ በአንድ ጀምበር ጸጥ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህ ግን
መግደልን ይጨምራል፡፡ የመግደልን መንገድ ደግሞ የመጣንበት ስለኾነ አልፈለግነውም ነበር፡፡ ከእንግዲህ ግን
ትዕግስታችን ተሟጥጧል፡፡ የጎሰኝነት እና የሃይማኖት ጽንፈኝነት ከፍተኛ ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡ ነገራችን ሁሉ ሳቅ እና ሐዘን ኾኗል፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ብዙ
ሥራ አጥ ወጣት አለን፡፡ ይህንን ወጣት ጽንፈኞቹ በቀላሉ እየዘወሩት ይገኛል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ተረዱን እርዱንም፡፡
እናንተ ወደ ተቃውሞ ከሔዳችሁ ማን ነው ከጎናችን የሚቆመው? እርዱን እርዱን ነው የምንለው፡፡ ለልጅ ኹለትም
ሦስትም ዕድል ይሰጣል፤ አሁንም ዕድል ስጡን፡፡ የተጠየቁትን ጥያቄዎች መሠረት አድርገን ርምጃ መውሰድ
እንጀምራለን፡፡ ለጠቅላይ ሚንስትሩም ነገሩን እናደርሳለን በማለት ተሰናብተዋል፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
#ከማኅበረ_ሥላሴ_አንድነት_ገዳም_የተላከ_መልዕክት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ ለ 15 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።


#በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ለምትገኙ_ኦርቶዶክስ_ክርስቲያኖች_በሙሉ_ከጥቅምት_24_እስከ_30_ከህፃናት_እስከ_ሽማግሌ_ማንም_ሳይቀር_በማህበረ_መነኮሳቱ_አማካኝነት_ፆም_ታውጇል::
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱአምላክ አሜን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኛችሁና በደሙ የዋጃችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቤታችሁም ያላችሁ በህመም ምክንያት በሆስፒታል ያላችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ በጦር ሜዳም ያለችሁ እንዲሁም በተለያየ ስፍራ የምትገኙ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታችንን በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡
እኛ ማኅበረ ስላሴ እንድነት ገዳም የምንገኝ ማኅበረ መነኩሳት በሀገራችን ሰላም መታጣት ምክንያት ከሀዘናችን ጋር አምላክ አበው ክብር ምስጋና ይግባዉ ደኅና ነን፡፡
እግዚአብሔር ገና ሃያ ሁለቱን ስነ-ፍጥረት ፈጥሮ ሳያበቃ ሳጥናኤል በዓለተ ረቡዕ በሶስተኛዉ ሰማይ በጌታ ላይ በማመጽ በጀመረዉ ጸብ ምክንያት ከመላዕክቱ ጋር ተዋግቶ ተሸንፎ ወደ
ምድር ተጥሎ እነሆ ያለ እረፍት ለሰባ ሺ አምስት መቶ አመታት በመላዉ ዓለም ደም ሲያፈስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ፡፡ ጌታ የተሰጠዉ የቀጠሮ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ታግሶታል፡፡ አሁን ግን ከወትሮዉ ለየት ያለዉ ነገር የእግዚአብሔር ቤተ -
መቅደስ በሆነችዉና የቅዱሳን የአስራት ሀገር በተሰኘችው በኢትዮጵያ ሀገራችን የሳጥናኤል ጭፍሮች ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ብለዉ ዘምተዉ በታሪክም ያልሰማነዉ በዘመናችንማ አይተን የማናቀዉ የአርስ በአርስ እልቂት እንኳን ከክርስቲያን ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ድርጊት ተፈጽሟል እየተፈጸመም ነዉ፡፡
ሰይጣን ብቻዉን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ከሰዉ ጋር ሆኖ
በሰዉ ልብ አድሮ ግን ምንም የሚቀረዉ የሀጢያት ሥራ የለም፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፡፲፭ ላይ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ ያለዉ የጌታ ቃል ተጥሷል፡፡
ቀድሞ አንድ ሰዉ ለሥራም ሆነ ለንግድ ወይም ለተለያየ ጉዳይ ወደ ማያዉቀዉ ወደ ሚያዉቀዉም በኢትዮጵያ ክፍላተ
ሀገር ወይም ክልል ሲዘዋወር ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ነኝ ብሎ አይጨነቅም፡፡ የእግዚአብሔር እንግዳ ተብሎ ከመሸበት ገብቶ እግሩን ታጥቦ ቤት ያፈራውን በልቶ ጠጥቶ ከመልካም
ምንጣፍ ተኝቶ አድሮ ሲነጋ ተነስቶ መርቆ ቀሪዉን ምንገድ ይጓዛል፡፡
ዛሬ ግን ያ ቀረና የእግዚአብሔር እንግዳ እራቱ ጥይትና ገጀራ መጠጡ ደም ሆኗል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ ፳፭፥፵፪ ላይ የተጠቀሰዉ እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበላችሁኝም ብራብ አላበላችሁኝም የሚለዉ የጌታ ቃል ትዉልዱን እየተዋቀሰዉ ነዉ፡፡
በእርግጥም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ ብሎ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንደተናገረዉ እንግዶች የሰላም ተጓዦች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ነገር ግን የሰላም ሰዎችም አብረዉ ተጨፍልቀዉ የጥፋት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነ
እግዚአብሔር አሁንም ታግሶናል፡፡እኛ አሁን ከሞት የተረፍነዉ ከጥላ ያረፍነዉ በጽድቃችን አይደለም በቸርነቱ ለንስሐ ጊዜ ተሰጥቶን ነዉ እንጅ፡፡
ነቢያት ስለ ጥፋት ሲተነብዩ በሰዉ ልጅ ሐጥያት ከእግዚአብሔር የሚታዘዘዉን መቅሰፍት ማስገንዘባቸዉን እንጅ ጥፋት ዝም ብሎ ደርሶ የሚታዘዝ አይደለም፡፡
አሁን በኃጢያታችን ምክንያት እየተጎነጨነዉ ያለዉ መከራ ከዚህ
በፊት ብዙ የተነገረ ቢሆንም በትንቢተ ዮናስ ታሪካቸዉ እንደተጠቀሰዉ እንደ ሰብዓዊ ነነዌ ወደ እግዚአብሔር በጾም
በጸሎት ሆኖ በመለመን በማልቀስ መከራዉን ማስቀረት እንዲቻል ቅዱሳን በመጽሐፍት አስተምረዉናል፡፡
በኖህ ዘመን ምድር በዉሃ ሙላት የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት
ነዉ፡፡ በሎጥ ዘመን በሰዶም ሀገር የተቃጠለችዉና ከምድረ ገጽ
የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት ነዉ፡፡
ዛሬስ እየተሰራ ያለዉ ኃጢያት በዚያ ዘመን ከነበረዉ ያንሳልን ? ያን ጊዜስ በንስሀ ላልተመለሱ ሰዎች ፈርዶ ያጠፋቸዉ አምላክ ዛሬስ ፈርዶ ማጥፋቱ ይሳነዋል ወይ ? አይሳነዉም እንዲያዉም እንደ ዘመናችን ኃጢያት ብዛትና ክብደት
ላልፈረደብን እግዚብሔር እያመሰገንን ይህን መልዕክት በያላችሁበት ሲነበብላችሁ ከሰማችሁት በኋላ ወደ ልባችሁ ተመለሱ ከእንግዲህ ወዲህ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በቋንቋ ፣ በሀገር ፣
በብሔር መለያየት ይብቃ ፣ መገዳደል ይብቃ ፣ መዘራረፍ ይብቃ፣መሰደድም ይብቃ አጠቃላይ የጥፋት ዘመቻ ይብቃ፡፡ ወደ ቀድሞ ኢትዮጵያዊ አንድነታቸን እንመለስ በኅብረት ተቻችለን እንኑር፡፡
የኃጢያታችንን ካባ አዉልቀን በነብስም በሥጋም የሚያድነንን የንስሐ ካባ እንልበስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፥፲፪ ላይ እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ብሎ ጌታችን ባዘዘብ መሰረት ጥላቻን አስወግደን የዘር ፣የጎሳ፣ የቋንቋ ፣ የክልል ልዩነት ሳይኖረን እርረ በእርሳችን እንዋደድ፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፬፥፳፯ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ያለዉ ጌታ ቃሉ አይለወጥም እና ይህ ከሆነ ብቻ እዉነተኛዉን ሰላም ማግኘት ይቻላል፡፡
የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ነብዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ምዕ ፩፥፲፱ ላይ ‹‹ እሺ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት
ትበላላችሁ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኃለች የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና›› የሚለዉን የትንቢት ቃል ዛሬም በእኛ ኢትዮጵዊያን ላይ እንዳይደርስብን ለእግዚአብሔር
ቃል እንታዘዝ እና ክፋትን ሁሉ ትተን ንስሀ ገብተን የምድርና በረከት እንብላ፡፡ አለበዚያ ግን ምሕረት በእጁ የሆነ አምላክ መዓተም በእጁ ነዉና ምርጫዉ ግን የእናንተ ነዉ፡፡ በሀገራችን
ሰላም ይሰፍን ዘንድ ማንኛዉም ክርስቲያን የተጣላ ታርቆ ፣ የበደለ ክሶ ፣ ይቅር ተባብሎ ፤ ከጥቅምት ፳፬ እስከ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም ድረስ ልጅ አዋቂ ሳይለይ እስከ ዘጠኝ ሰዓት
እየጾማችሁ በሀዘን በለቅሶ ምህላ በመያዝ ከእግዚአብሔር ምህረትና ይቅርታ በጋራ እንድንለምን እኛ የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ማኅበረ መነኮሳት ሁሉን በፈጠሩ በቅድስት ሥላሴ ስም አምላክን በወለደች በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በታላቅ አክብሮት መልዕክታችንን ለመላዉ ሕዝበ
ክርስቲያን አስተላልፈናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም ይስጥልኝ
የሞቱትን ሁሉ ነብስ ይማርልን
የጠፋዉን የተቃጠለዉን የወደመዉን ንብረት ሆሉ ይተካላችሁ አሜን ይሁን ይደረግልን
መምህር አባ ወልደ ሰንበት ነጋሽ
የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም አበመኔት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Share share share share share share
1 ሰው ለ 15 ምዕመን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
👍1
አንድ ለዐሥር አደረጃጀት ለኦርቶዶክሳውያን ሁሉ

@And_Haymanot

አሁን በኦሮሚያ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በደቡብ ሲዳማ እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ጦማረ ሞቱን በእጁ ይዞ የሚንቀሳቀስ ኾኖ ተፈርዶበታል፡፡ በማንኛውም ሠዓት ምንም ዓይነት አደጋ ሊደርስ ይችላል፡፡ ምንም ዓይነት መዘናጋት አይኑር፡፡ የክርስቲያኖች በየቦታው መታረድ ላለፉት ኹለት ዓመታት እየባሰ እንጅ እየቀዘቀዘ አልመጣም፡፡
መንግሥት በተደጋጋሚ መረጃዎች ቢደርሱትም አንዲት ጠጠር እንኳ የማንሣት ያኽል ሊራዳ አልቻለም፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት መፍትሔ ያመጣሉ ሲባል እባካችሁ ዕድል ስጡን
ወደማለት ዝቅ ያለ ደረጃ ላይ መኾናቸውን ከፈረሱ አፍ በቀጥታ
ሰምተናል፡፡ ከሰማይ በታች የሚታደገን ማንም እንደሌለ ቢያንስ አሁን ሊገባን
ይገባል፡፡ የመስቀል በዓልን ለማክበር ተቸግረናል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን በእሳት መማገድ የምድጃ እሳትን የማቀጣጠል ያኽል ቀሏል፡፡ ሥጋችን ሞት አልበቃውም፡፡ እየተቆራረጠ
ለአውሬ እየተጣለ ነው፡፡ አሁንም ግን ጥቅሳቸውን ያልለወጡ ሰዎች ከመካከላችን አሉ፡፡ ራስን መከላከል ይፈቀዳል ወይ? ሲባሉ የለም ቀኝህን
ለሚመታህ ኹለተኛውን ደግሞ አዙርለት ነው የሚለው ይላሉ፡፡ እስቲ እነዚህን ሰዎች ጥቂት እንጠይቃቸው፡፡
 በጦር ሜዳ ስለ ሃይማኖታቸው ሲጋደሉ የወደቁት ግብጻዊው
አቡነ ስምዖን ይህን አያውቁም ነበርን?
 ለጣልያን ጦር አይደለም ሕዝቧ የኢትዮጵያ ምድር እንዳትገዛ
የገዘቱት ኢትዮጵያዊው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ ተሳስተው
ነበርን? ወንድማቸው አቡነ ሚካኤልስ?
 ንጉሠ ቁዝን በኃይለ እግዚአብሔር ያስወገደው ቅዱስ
ቴዎድሮስ ሰማዕት ሕግ አፍርሶ ነበርን?
 ንጉሥ ሕርቃል ዘምቶ አጽራረ ክርስቲያንን ያስወገደው በማን
ፈቃድ ነበር?
 ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ካሌብ የመን ድረስ ተሻግረው፣ በሀገረ
ናግራን የነበሩ ክርስቲያኖችን ነጻ ያወጡት ተሳስተው ነበርን?
 ለቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ አረአያ መስቀል ሰጥቶ ሒድ
ዝመት ብሎ የላከው እግዚአብሔር የገዛ ሕጉን ሽሮ ነውን?
 በነጠላው ቃሉን እንፈጽም የሚሉት ቀኛቸውን ሲመቱ
ኹለተኛውን ሊያዞሩ ይችላሉ፡፡ ከኹለተኛው በኋላስ ምን
ያደርጋሉ?
ወዳጄ መተርጉማኑ የቃሉን ፍች አስቀምጠውልናል፡፡ በነጠላ
ትርጉም እየነጎድን ሕዝባችንን አናስበላ፡፡ ሊቃውንተ ቤተ
ክርስቲያን ቀኝህን ለሚመታህ ኹለተኛውን ደግሞ አዙርለት
ያለውን ቃል ሲተረጉሙት እንዲህ ብለውታል፡፡ ፈቃደ ሥጋህን
ተው ቢልህ ፈቃደ ነፍስህን ተውለት፡፡ ልብ በሉ ቃሉ የጉንጭ
ወይም የአካለ ሥጋ ጥቃትን ሳይኾን የሚያመለክተው ከዚያ
የላቀ ምስጢራዊ ፍች እንዳለው ነው፡፡
ለምሳሌ በመጽሐፍ “እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ
መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት” ተብሏል፡፡ በነጠላው ትርጉም
እንረዳው ከተባለ ተጠያቂው ያለውን ሁሉ ሲሰጥ ሲሰጥ ራቁቱን
እንዲቀር ነውን? ይህማ አይኾንም አባታችን አዳም ራቁቴን
ስለኾንሁ ፈራሁ ቢለው የቆዳ ልብስ አልብሶታልና፡፡ ነገር ግን
ደግ ሥራን አብዝቶ ለመሥራት አትታክት በሕገ ወንጌል ላይ ሕገ
ትሩፋትን ጨምርበት፣ በሕግ ጾም ላይ የፈቃድ ጾም አክልበት
ማለት ነው፡፡ ባልተስተካከለ ትርጉም መምታታቱን ትተን ራሳችንን ለመከላከል
ቆርጠን እና ጠንክረን እንሥራ፡፡ አሁን ክርስቲያኖች በየሚኖሩበት አካባቢ (ሩቅ ለሩቅ ካሉት ጋር አይደለም) ዐሥር ዐሥር እየኾኑ ሊሰባሰቡ ይገባል፡፡ በተለያየ ምክንያት የተኳረፈ ካለ ሽማግሌ
ሳይጠብቅ ይታረቅ፡፡ አብሮ ለመሥራት ሁሉም ልቡን ይስጥ፡፡ እየተገናኙ መምከር አለባቸው፡፡ መረጃ መለዋወጥ ይገባቸዋል፡፡ ራሳቸውን የሚያድኑበትን መንገድ ለማሰብ ከዛሬ የተሻለ ቀን
የላቸውም፡፡ አንዱ ለሌላው የሚደርስበትን መንገድ የማመቻቸት
ተግባራዊ እንቅስቃሴ ይጀምሩ፡፡ እያንዳንዳቸው በዐሥር በዐሥር
የተደራጁ ክርስቲያኖች በተወካዮቻቸው በኩል ከሌሎች በዐሥር በዐሥር ከተደራጁት ጋር የሚገናኙበት ሠንሰለት ይፈጥራሉ፡፡ የዐሥሩ መሪዎች በአምስት በአምስት ይደራጃሉ፡፡ ማለትም
ከታች ዐሥር ክርስቲያኖች ይኖራሉ፤ ከእነርሱ በላይ የዐሥሩ ተወካዮች የሚገናኙበት አንድ ዕዝ ይኖራል፤ በአጠቃላይ ከሥሩ አንድ መቶ ይኖራሉ፡፡ እነዚህ አንድ አንድ መሪዎች ይመርጣሉ፡፡ ከሌሎች አምስት ተጓዳኞች ጋር ጥምረት ይፈጥራሉ፡፡ በእነዚህ
በአምስቱ ሥር አምስት መቶ ክርስቲያኖች ይኖራሉ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ከፍ ይላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዴት የራ መከላከሉን ስልት ምስጢር በአደባባይ ይነገራል የሚል ይኖራል፡፡ ይህ አደረጃጀት እንጅ ስልት አይደለም፡፡ ስልቱ ከአደረጃጀቱ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡
ፀሐይ ሳይጨልምብን እንሰባሰብ!
ለማተቤ ያለ ሼር ያድርግ!
በመምህር አባይነህ ካሴ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
በጣም አስቸኳይ!!! እባካችሁ መልእክቱን አድርሱ!!!! #አሰቦት ከሴቶች ገዳም አደጋ አንዣብቧል፤
* አቤቱታቸው ለመንግሥት አካላት ይድረስ
------
ለአሰቦት ገዳም ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደገለፁልን ከሆነ በአሰቦት ገዳም በተለይም ሴት መነኮሳይያት በሚኖሩበት
ከተራራው ግርጌ አካባቢ አደጋ እንዳንዣበበ፣ ገዳማውያኑም
መኖሪያቸውን ትተው ወደ ተራራው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መሰባሰባቸው
ተነግሯል። በተለያዩ ጊዜአት የአክራሪዎች የጥቃትት ዒላማ መሆኑ
የሚታወቀም የአሰቦት አባ ሳሙኤል ገዳም ከአሰቦት ከተማ 12 ኪሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን እናቶች መነኮሳይያት የሚኖሩበት የሴቶች ገዳም ከእግረ ደብር ይገኛል። ድንጋይ በመወርወር እና
ግቢው ውስጥ በመግባት ችግር እየተፈጠረበት ያለው ይኸው የሴቶች ገዳም መሆኑ ታውቋል። በአካባቢው ያለው መንግሥታዊ አስተዳደርም ሆነ የመከላከያ ኃይል በዚህ ታሪካዊ ገዳም ላይ ያንዣበበውን ከፍተኛ አደጋ
ተገንዝበው አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን። ምእመናንም ጉዳዩን ተረድተው የሚችሉትን ሁሉ ያድርጉ።
Cc. Ethiopian Federal Police Commission
ዝርዝሩን እየተከታተልን እንገልጻለን።
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ሰላም ተወዳጆች እንደምን ቆያችሁልን በውስጥ በጠየቃችሁን መሠረት በቻናሉ ያለውን አገልግሎት ትምህርቶችን(ስብከቶችን) በድምፅ ልናቀርብላችሁ ወደናል በመጀመርያ እንድንዳስሰው የታሰቡት 👉 ነገረ ክርስቶስ እና 👉 ነገረ ድህነት ናቸው እንድናስቀድምላችሁ የምትፈልጉትን ምረጡ እያልን በሚለቀቁት ክፍላት ላይ ያላችሁን ጥያቄ ትምህርቱን ሥንጨርስ ጠቅለል አድርገን የምናቀርብላችሁ ይሆናል።
public poll

ነገረ ክርስቶስ – 288
👍👍👍👍👍👍👍 64%

ነገረ ድህነት – 161
👍👍👍👍 36%

👥 449 people voted so far.
👍1
ዕለቱ አርብ ነው!


ኢየሱስ ይሰቀል!
ይሰቀል ኢየሱስ!
በርባን ግን ይፈታ!
2 ሺህ ዘመን
ይኸው ትጮሃለች
ዓለም አፍ አውጥታ።
በቀያፋ ምክር
በካህናት አድማ
በጲላጦስ ስልጣን
በግፈኞች ጡጫ
ዛሬም ይወገራል
ጌታ ይሰቀላል።
እውነት ነው!
በድምጽ ብልጫና
በቲፎዞ መድረክ
ለምትመራ ዓለም
ሌባውን አንግሶ
ንፁሁን ከመሸጥ
.
.
.
ሌላ አይጠበቅም።


ምንጭ፦ ፍሬ ተዋሕዶ

@And_Haymanot
@And_Haymanot
Audio
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፩
መምህራን
መምህር ብርሃኑ አድማሥ
መምህር ገብረ መድህን እንየው
አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ኢየሱስ ክርሥቶስ ማን ነው?
ተዋህዶ ምንድነው?

አዘጋጅ ማህበረ ቅዱሳን

size 23mb