ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን
አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው።
በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው
እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና
በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤
@And_Haymanot
አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው።
በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው
እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና
በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤
@And_Haymanot
"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል" /1ቆሮ 15፡20/
"ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የታለ?" /1ቆሮ 15፡55/
@And_Haymanot
መልካም በዓል
"ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የታለ?" /1ቆሮ 15፡55/
@And_Haymanot
መልካም በዓል
ለምን አንጾምም?
ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች?
ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም?
በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/።
"የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ
15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት
ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው።
በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ
እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም
ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም።

የእግዚአብሔርን ቅጣት ፈርቶ ንስሓ መግባትና የእግዚአብሔርን ቅድስና ፈልጎ ንስሐ መግባት ይለያያል።
☞ እውነተኛ ክርስቲያንም ንስሐ የሚገባው ገሃነመ እሳትን ፈርቶ
ሳይኾን የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም ስለሚናፍቅ ነው።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
☞ እውነተኛ ክርስቲያንም ንስሐ የሚገባው ገሃነመ እሳትን ፈርቶ
ሳይኾን የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም ስለሚናፍቅ ነው።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ትዝብት
በትላንትናው ዕለት በተደረገው የቀብር ሥነሥርዓት ላይ የተላከልንን ትዝብት እነሆ ብለናል ተዋህዶን በመተቸት ለተጠመዱ ሁሉ ይድረስልን፡፡
* እኛ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የምናደርገውን ነገር ከተቃወማችሁ በኋላ ዞራችሁ ደግሞ እናንተ ስታደርጉት ይታያልና ይህ የአቋም መዋዠቃችሁ መቼ ነው የሚስተካከለው?
* ለምሳሌ፡-
* 1ኛ. ለሞተ ሰው የሚደረግ ጸሎት /ፍትሐት/
* ይህን ስርዓት እኛ ስንፈጽመው፣ …ለሞተ ሰው ለምን ጸሎት
ይደረግለታል? ምንስ ይጠቅመዋል?... በሚል ሀሳብ ስትቃወሙንና ስትከራከሩን ነበር፡፡ ነገር ግን እናንተም ስታደርጉት
አየን፡፡ ስለዚህ የምትቃወሙትንና የምታደርጉትን ለምን አትለዩም?
* 2ኛ. መስቀል መጠቀም
* እኛ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የጌታ መስቀል ስንይዝ እናንተ ግን ‹‹የተሰቀለውን እንጅ የተሰቀለበትን አንሰብክም›› በሚል ትክክለኛ ያልሆነ ሀሳብ መስቀል መጠቀምን ስትቃወሙን
ነበር፡፡ ነገር ግን እናንተም አማኝ ለመምሰል ይሁን ባለውቅም መስቀሉን ስትጠቀሙ ይታያልና ይህ ነገራችሁ መቼ ነው ወጥ የሚሆነው?
~~~~~~~~~~~~
ፀልዩ ፀልዩ!!!! ለጠፉት ልቦናን ይስጥልን እኛንም ከእቅፉ አይለየን፡፡
እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ።
"ድንግል ሆይ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ምልጃሽ አይለየን "

አስተካክለኝና ትክክል ልኹን
@And_Haymanot
“ተወዳጅ ሆይ! እግዚአብሔር አይሰማኝም አትበል፡፡ አንተ ተናገር
እንጂ ርሱ ይሰማኻል፤ ባትናገርም ያደምጥኻል፡፡ ኾኖም ርሱ አንተን ሲሰማኅ ችግሮችኅ ይስተካከላሉ፤ ርሱን ስትሰማው ደግሞ አንተ ትስተካከላለኅ፡፡
ያልተስተካከለን ችግር የተስተካከለ
ሰው ይሻገሯል፤ ያልተስተካከለ ሰው ግን የተስተካከለን ችግርም አይሻገርም፡፡ “እንዴት?” ብለኽ ከጠየቅከኝ ግን መልሴ
“አካሔድ የማያውቀውን የተነጠፈም ጐዳና ጠልፎ ይጥለዋል” የሚል ነው፡፡ ከችግሮች ኹሉ እኛ ችግሮች ስንኾን ቀኖች ይከብዳሉ፡፡ መሣሪያው ሲበላሽ ሥራው ይበላሻል፡፡ ስለዚኽ መሣሪያው ተሠርቶ ሥራው ይሠራል፡፡ አንተ ከተበላሸኽ የሚስተካከል ነገር የለም፡፡ አንተ ከተስተካከልክ ግን ሌላው
ቢበላሽ ራስኽን ታድናለኽ፡፡ “ከምንም ነገር አንድ ነገር” ይባላልና ይሔ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወዳጄ! እውነት
እውነት እልኻለኁ እመነኝ፤ አንተ ስትስተካከል ብቻኽን አትስተካከልም፡፡ በተስተካከለ የሚስተካከሉ፣ በዳነ የሚድኑ ብዙዎች ናቸውና፡፡ የአየር ንብረቱን ዐይቶ ልብስን ማስተካከል
ካለ የዘመንን መልክ ዐይቶ ልብን ማስተካከል ተገቢ ነው እልኻለኁ፡፡ ፀጉርን ለማስተካከል ከአስተካካዩ ጋር፣ የከበረ ልብስን ለማስተካከል ከአልባሹ ጋር፣ ዕውቀትን ለማስተካከል ከመምህሩ
ጋር፣ … ትገናኛለኅ፡፡
@And_Haymanot
ሕይወትን ለማስተካከል ግን ማንን አግኝተኅ ይኾን? አንተን ለሕይወት የሠራኅ እንጂ ሌላ ማንም አያስተካክልኽም፡፡ ሰው ኹሉ ከራስኅ በላይ የሚነፍስ ነፋስ ኾኖብኅ “ለእኔ እኔ - ከእኔ ወደ እኔ” ብለኅ ከራስኅ ጋር ቃል ኪዳን ተጋብተኽ አዲስ ኑሮ ዠምረኽ ነበር፡፡ ነገር ግን ለመስተካከል ዓቅም አጥተኽ የመስተካከልን በጐ ፈቃድ ብቻ
ይዘኅ ቀረኽ፡፡ ስንት ዘመን የራስኽ ጥበብ ስንፍና፣ የራስኽ ብርታት ድካም፣ የራስኽ ሙከራ መከራ እንደኾነብኅ ዐውቂያለኹ፡፡ ስለዚኽ ለፈጠረኽ ጌታ ራስኽን አሳልፈኅ ለመስጠት ወስን፡፡ በራስኽ ላይ እንደዚኽ ዓይነቱን ውሳኔ
እንደማስተላለፍ አስቸጋሪና እጅግ ውብ የኾነ ነገር በዚኽ ዓለም ላይ አታገኝም፡፡ ወደ ፈጠረኽ መምጣትኅ ዥማሬኅ ነው፤ ከርሱ ጋር ያለው ቈይታኅ ዕድገትኅ ነው፤ ርሱን አምነኅ እንደኖርኅ አምነኅ ስትሞትም ሕይወትኅ ነው፡፡ እውነት አንተስ ዕድለኛ ነኽ!!! እናም ምክሬን ስጠቀልልኅ፡- የእውነት ልመና “ጌታ ሆይ!
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን!” የሚል መኾኑን ደግሜ በማስታወስ ነው፡፡ “እንዳስተውል ርዳኝ፤ በሕይወትም አኑረኝ” / መዝ.118፡144/፡፡”
© ዲ/ን ቃለኣብ ካሣዬ

ዮም ፍስሐ ኮነ ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/2/
በባርነት ሳለን ~ፍስሐ ኮነ
ሀጢአት ባለም ነግሳ ~ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ ~ ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ ~ፍስሐ ኮነ
አዝ
እግዚአብሄር መረጠሽ ~ፍስሐ ኮነ
ልትሆኝ እናቱ ~ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ ~ፍስሐ ከነ
የዳዊት ትንቢቱ ~ ፍስሐ ኮነ
አዝ
የሄዋን ልጆች ተስፋ ~ ፍስሐ ኮነ
የአዳም ህይወት ~ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሀና ~ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት ~ ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድሂን ~ ፍስሐ ኮነ
ኪዳነ ምህረት ~ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች ~ ፍስሐ ኮነ
የጌታየ እናት ~ፍስሐ ኮነ
አዝ
በሄዋን ምክንያት ~ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም ~ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው ~ፍስሐ ከነ
በድንግል ማርያም ~ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል ~ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ ~ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለች እና ~ፍስሐ ኮነ
የዓለም ሁሉ ተስፋ ~ፍስሐ ኮነ
ዮም ፍስሐ ከነ ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም
እልልልልልልእልልልልልልእልልልልል
@And_Haymanot
@And_Haymanot
በባርነት ሳለን ~ፍስሐ ኮነ
ሀጢአት ባለም ነግሳ ~ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ ~ ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ ~ፍስሐ ኮነ
አዝ
እግዚአብሄር መረጠሽ ~ፍስሐ ኮነ
ልትሆኝ እናቱ ~ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ ~ፍስሐ ከነ
የዳዊት ትንቢቱ ~ ፍስሐ ኮነ
አዝ
የሄዋን ልጆች ተስፋ ~ ፍስሐ ኮነ
የአዳም ህይወት ~ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሀና ~ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት ~ ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድሂን ~ ፍስሐ ኮነ
ኪዳነ ምህረት ~ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች ~ ፍስሐ ኮነ
የጌታየ እናት ~ፍስሐ ኮነ
አዝ
በሄዋን ምክንያት ~ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም ~ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው ~ፍስሐ ከነ
በድንግል ማርያም ~ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል ~ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ ~ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለች እና ~ፍስሐ ኮነ
የዓለም ሁሉ ተስፋ ~ፍስሐ ኮነ
ዮም ፍስሐ ከነ ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም
እልልልልልልእልልልልልልእልልልልል
@And_Haymanot
@And_Haymanot
Forwarded from መሠረተ ያሬድ ሰ/ት/ቤት ዘአሣሣ
ባትወለድ ኖሮ……
መለኮትን ያህል - በእጅ እንደ መጨበጥ - በሆድ እንደ መወሰን
ምን ክብር ይገኛል - ምን ምጡቅ ልዕልና? - ምንስ ገላጭ ልሳን?
ባትወለድ ኖሮ - ብላቴናዋ ባትኖር - ያች የምስጢር ማህደር
ተራ ተዓምር ሁሉ - እንደ አምልኮት - በሆነብን ነበር፡፡
ባትወለድ ኖሮ - እሷን ተመልክተን - መመኪያ ባላልናት
በሔዋን ተስፋ ውስጥ - ብርሃንን አዝላ - ደምቃ ባላየናት
የተዘጋች ገነት - ቀድሞ እንዳጣናት - ርስታችን ባላልናት፡፡
አዳም ባልተጽናና - ደሙም ባላቆመ - ሲፈስ በኖረ
“ህይወቴ ነሽ” ብሎ - ሔዋንን ባልጠራት - ተስፋው ባልነበረ
የማግሰኞም እርሻ - ዘርን ባላስገኘ - ባዶውን በቀረ
ሁሉም ይቀር ነበር - ሰውም በውድቀቱ - እንተቸገረ
ባትወለድ ኖሮ - አሁን አይኖርም ነበር - ጥንት እንደ ነበረ፡፡
ትንቢትን ባላየን - ይወለዳል ብለው - ተስፋ ባልሰነቁ
“ክንድህን ከአርያም ላክ” - ብለው ባልተጽናኑ - ፊቱ ባልወደቁ
ዘርም ባልቀረልን - እንደ ተበተንን - ከቤት እንደ ወጣን
ባላወቅን እረኛ - ጋጣ እንደሌለን - ማደሪያ እንዳጣን
እንደ ከንቱ ፍጥረት - በምድር እንደሚቀር - እንደ ዱር ቀበሮ
ሰው በሆነ ነበር - ያች እንቁ ፍሬ - ባትወለድ ኖሮ፡፡
ምስራቃዊት መቅደስ - የታተመችን በር - ህዝቅኤል ባላየ
የሙሴ ሐመልማል - በነበልባሉ ’ሳት - ተዋህዶ ባልቆየ
ረዥሙ ተራራ - ለዳንኤል ባልታየ - ተስፋ ባልሰነቀ
ባትወለድ ኖሮ - ሁሉም ጠፍቶ ነበር - ያኔ እንደ ወደቀ፡፡
ቴክታና ጴጥርቃ - (እ)ራዕይ ባላዩ - ህልም ባልታያቸው
ከጥጃ ጨረቃ - እንደምትወለድ - ባልተነገራቸው
ከጨረቃም ፀሃይ - ዓለምን ሲያበራ - ባልተመለከቱ
የጨለማ ዘመን - በዘለቀ ነበር - ልክ እንደበፊቱ፡፡
ሄርሜላና ማጣት - ሃናን ባልወለዷት - ተስፋም ባልቀረበ
ኢያቄም ባልመጣ - ከይሁዳ ነገድ - ድኅነት ባልታሰበ
ባልተነገራቸው - በስተ እርጅናቸው - ባላዩ' ደስታ
ባትወለድ ኖሮ - ሁሉም መራር ነበር - በመጣፈ ጥፈንታ፡፡
መልአኩም ባልመጣ - ብስራቱን ባልሰማን - ቃል ስጋ ባልሆነ
ልደቱን ስቅለቱን - ትንሳኤውን ባልሰበክን - ሁሉ በባከነ
ባትወለድ ኖሮ - እመአምላክን ባናይ - ያችን የድኅነት በር
ምክንያት ፈጥረን ሞተን - መልሰን ለመዳን - ምክንያት ባጣን ነበር፡፡
(አክሊሉ ደበላ ሚያዝያ 30/2006ዓ.ም)
@Meserete_Yared_Asasa

ዘማሪ ዳግማዊ!
«ኣድሳለሁ ያለው ኣዳሹም ፈረሰ
በልብ ተሐድሶ #ዳግም ተመለሰ»
... እንኳን በሰላም ተመለስክ ዘማሪ ዳግማዊ! የተሐድሶን ኑፋቄ በዝማሬዎችን ትበቀል ዘንድ ያብቃህ። በአንዱ መመለስ ምክንያት ብዙዎች ደስ አለን። በቅርቡ የቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ፣ የዳግማዊ ይፋዊ ይቅርታና የተሐድሶ ሴራ ማጋለጥን እንጠብቃለን። በውስጥ ለጠየቃችሁን ሁሉ ከላይ ድብዳቤውንም እነሆ ብለናል፡ የበለጠውን እውነታ እንዲሁም ስለ አገልግሎቱ ነገር ዝርዝርሩን እንመለስበታለን።

"ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም።"
ሉቃ 15፥24
@And_Haymanot
«ኣድሳለሁ ያለው ኣዳሹም ፈረሰ
በልብ ተሐድሶ #ዳግም ተመለሰ»
"ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም።"
ሉቃ 15፥24
@And_Haymanot
ያከብርዋ
ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት
በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት/2
ወኩሉ ፍጥረት ዓሳት ወአናብርት/2/
እለውስተ ደይን ያእረፉ ባቲ
እስመ ባቲ አእረፈ እምኩሉ ግብሩ /2/
ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት /2/
ጻድቃን በገነት
ፍጥረታት በሙሉ አሳዎችና አንበሬዎች
በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ /2/
በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት
በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት/2
ወኩሉ ፍጥረት ዓሳት ወአናብርት/2/
እለውስተ ደይን ያእረፉ ባቲ
እስመ ባቲ አእረፈ እምኩሉ ግብሩ /2/
ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት /2/
ጻድቃን በገነት
ፍጥረታት በሙሉ አሳዎችና አንበሬዎች
በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ /2/
በእርሷ እንዳረፈ ከሥራው ሁሉ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
❤ አቤት ፍቅር! ❤
🙏 አቤት መውደድ! 🙏
@And_Haymanot
ዓለምን ከነግሳግንሱ ቢፈጥረው ☞ ለእኛ፤
ነቢያትን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
ሐዋርያትን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
መላእክትን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
አንድያ ልጁን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
መንፈሱን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
መጻሕፍትን በእግዚአብሔርኛ ሳይኾን በሰውኛ ቋንቋ ቢያስጽፍ
☞ለእኛ፤
መጻሕፍትን የሚተረጕሙ ሊቃውንትን ቢልክ ☞ ለእኛ፤
ቤተ ክርስቲያን ቢታነጽ ☞ ለእኛ፤
ሰባክያንን ቢልክ ☞ ለእኛ ነው፡፡
@And_Haymanot
🔴 ወንድሞቼ! እኅቶቼ! ታድያ የዚኽን ድንቅ አባት ፍቅር መግለጽ ይቻላል?
ታድያ የዚኽን ወዳጅ መውደድ እንዴት መግለጽ ይቻላል?
🙏 እባካችኁ ይኽን ከመሰለ ጌታ አንራቅ፡፡
🙏 እባካችኁ ይኽን ከመሰለ አፍቃሪ አንሽሽ፡፡
🌍 ዓለም ብትወደን ውሸቷን ነው፡፡
ዓለም ዛሬ ብትወደን ነገ ልታስለቅሰን ነው፡፡
🌍 ዓለም ዛሬ ብታከብረን ነገ ልታዋርደን ነው፡፡
🌍 ዓለም ዛሬ ብታለብሰን ነገ ልታራቁተን ነው፡፡
🌍 ዓለም ዛሬ ተኙ የምትለን ነገ እንቅልፍ ልታሳጣን ነው፡፡
@And_Haymanot
🔴 ወንድሞቼ! እኅቶቼ! የአባታችንን ጥሪማ ተመልከቱልኝ “ኑና እንዋቀስ” /ኢሳ.1፡18/፡፡ “እኔው ሳልኾን እናንተው ራሳችኁ ራሳችኁን ወቅሳችኁ ኑና እንታረቅ” እኮ ነው እያለን ያለው፡፡
እኛ ተጣልተነው ርሱ እንታረቅ ይላል፡፡
እርሱ ተበድሎ እርሱ ይክሳል፡፡
🙏 እባካችኁ ፍቅሩን እንረዳለት፡፡ ፍቅሩን እንድንረዳ እንኳን የሚፈልገው እኛ እንድንጠቀም ነው፡፡ ለሕይወት እንጂ ለሞት አልፈጠረንማ!!!
✞ አቤቱ! አንተን የሚያዩ ዓይኖች እንዴት ንዑዳን ክቡራን ናቸው?
🙏 እባካችኁ ንስሐ እንግባና ከወዳጃችን ጋር እንታረቅ!!!
🙏 እባካችኁ ወደ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እንቅረብና በሕይወት
እንኑር!!! እስኪ ፍቅሩን እንቅመሰው፡፡
Share

ደጅ ጠናሁ
@And_Haymanot
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተጽናናሁኝ እረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሆኝኝ ቀሪው ዘመኔን
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የዓለምዋን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት
ባርያሽን ሰውረኝ ከአስጨናቂ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ልቤ በአንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላንን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ደጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክአቸው ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብላ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተጽናናሁኝ እረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሆኝኝ ቀሪው ዘመኔን
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የዓለምዋን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺም ደግነት
ባርያሽን ሰውረኝ ከአስጨናቂ ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ልቤ በአንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼም ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባርያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላንን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
ደጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹ
በመርገም ምክአቸው ሊለያዩኝ ሲሹ
እሱ የሰጠኝን እርሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብላ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ስጠራ
አለፈ ያሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዮ በአንቺ ነው የታበሰ
ሰላም ለኪ
@And_Haymanot
@And_Haymanot