እምነትህን በሥራ አሳይ
@And_Haymanot
ያዕ 2፥14-26
14 ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
15 ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥
16 ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
17 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
18 ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
20 አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?
21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
22 እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?
23 መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።
24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።
25 እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?
26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - እንደ አስተማሪ
@And_Haymanot
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከሌሎች ቅዱሳን አባቶች ልዩ የሚያደርገው አንዱ ነገር፥ ሃይማኖትን ከምግባር ጋራ አዋሕዶ ማስተማሩ ነው - ተዋሕዶ ! የተረጎማቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ስንመለከታቸው መጀመሪያ ኃይለ ቃሉን ይተረጉማል፤ ቀጥሎም ያ ኃይለ ቃል ወደ መሬት እንዴት ማውረድ (መተግበር) እንደሚገባ ያስተምራል፡፡ እንደ ምሳሌ ብንወስድ የዕብራውያን መልእክትን ሲተረጉም ወደ አማርኛ ሲመለስ ድርሳንና ተግሣፅ ተብሎ በኹለት መጽሐፍ የቀረበ ቢኾንም አንድ ወጥ መጽሐፍ ነው፡፡ ድርሳን አንድና ተግሣፅ አንድ ተብለው የተጠቀሱት አንድ ወጥ ድርሳን (ክፍለ ትምህርት) ነው፡፡ በማቴዎስ ወንጌል፣ በኦሪት ዘፍጥረት እንደ ተመለከታችሁት ማለት ነው፡፡
እንደዚህ ማስተማሩም ክርስቲያኖች በነገረ ሃይማኖቱ ትምህርት የተራቀቁ በምግባር ግን የጎደሉ እንዳይኾኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰምተው ብዙ የሚናገሩ እግዚአብሔርን ግን የማያውቁት እንዳይኾኑ ይጠብቃቸዋል፡፡
የኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ዋና ዓላማውም ይህ ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ብዙ መራቀቅ ሳይኾን እግዚአብሔርን በገቢር ማወቅ ! ስለ ጸሎት ብዙ ማወቅ ሳይኾን በተግባር መጸለይ ! ስለ ጾም እጅግ ብዙ ቅጾች ያሏቸውን መጻሕፍት መጻፍ ሳይኾን እንደ ዓቅም በአግባቡ መጾም !
ይህን ካለ መገንዘብ የተነሣ ብዙ ሰዎች ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን እንደ ምግባር ሰባኪ ብቻ አድረገው ይመለከቱታል፡፡ ነገር ግን ከላይ እንደ ጠቀስነው የቅዱስ ዮሐንስ ዋና አሳብ፥ አንድ ክርስቲያን በተግባር ክርስትናን የሚኖር ከኾነ በትምህርት ብዛት እግዚአብሔርን ከሚያውቀው በላይ በዚያ በኑሮው ውስጥ እግዚአብሔርን ወይም አጠቃላይ ነገረ ሃይማኖቱን እንዲያውቀው ማድረግ ነው፡፡ ስለ ፍቅር ብዙ ከማወቅ ይልቅ ፍቅርን በተግባር ኑሮ እንዲቀምሰው ማድረግ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን ይበልጥ ድኅነቱን እንዲፈጽም የሚያደርገውም ይህ ነውና፡፡
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ

“ሰው ሆይ ! በዚህ ዓለም መጻተኛ ኾነህ ትኖር ዘንድ እያዘዝሁህ ሳለ፥ አንተ ግን የትውልድ ሀገርህን ጠቅሰህ የምትታበየው ስለ ምንድን ነው?” ይላል እግዚአብሔር ! “ይህ ዓለም ለአንተ እንደማይገባ አስበህ እንድትንቀው ስነግርህ አንተ ግን ስለ ትውልድ ቀዬህ የምትመካው ስለ ምንድን ነው?” እነዚህ ነገሮች ፈጽመው የተናቁ ናቸውና፤ በክርስቲያኖች ዘንድስ ይቅርና በግሪክ ፈላስፎች ዘንድም ቢኾን የተናቁ የተጠቁ ናቸውና፥ “ውጹአን” ተብለውም ይጠራሉና፥ ዝቅ ያለ ግምትም ይሰጣቸዋልና፡፡
@ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ፱፥፯
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ፱፥፯
@And_Haymanot
@And_Haymanot
“ወዳጄ ሆይ! የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብኻልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርኻል፡፡ የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮኻልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለኽ፡፡ የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮኻልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምኅረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለኽ፡፡ ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞኻልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለኽ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትኽ ልል ዘሊል ብትኾን ይኽን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትኾናለኽ፡፡ ቆሽሸኻልን? እንኪያስ ወደዚኹ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርኻለኹ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለኽ፡፡”
ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✅ "ፀንሳ ተገኘች" ✅
@And_Haymanot
[ማቴዎስ ሆይ !] እባክህ ንገረኝ ልደቱ እንዴት ነበር? “እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ” (ማቴ.1፡18)፡፡ “ድንግል” አላለም፤ “እናቱ” እንጂ፡፡ ይኸውም ትምህርቱን በቀላሉ ይቀበሉት ዘንድ ነው፡፡ በመኾኑም ጥቂት ነገር ሰጥቶ ሰማዒውን እንዲህ ካሰናዳውና መሠረት ካስቀመጠ በኋላ፥ ቀጥሎ ያለውን ኃይለ ቃል በመናገር ደግሞ፡- “ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች” በማለት እንዲደነቅ ያደርገዋል፡፡ “ወደ ሙሽራው (ወደ ዮሴፍ) ቤት ከመምጣትዋ በፊት ፀንሳ ተገኘች” አላለም፤ አስቀድማ እዚያ ነበረችና፡፡ በጥንቱ የአይሁድ ባሕል ባሎች እጮኞቻቸውን አስቀድመው በቤታቸው ውስጥ የመጠበቅ ልማድ ነበራቸው፤ አሁንም ይህ ልማድ እንደ ተፈጸመ አንድ ሰው መገንዘብ ይችላል፡፡ [“ሎጥም ወንድን ያላወቁ ኹለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጉአቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና። … ሎጥም ወጣ፥ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም ነገራቸው፥ አላቸውም። ተነሡ፤ ከዚህ ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው” እንዲል] በዚሁ ልማድ መሠረት የሎጥ የወንድ ልጆቹ እጮኞችም በቤቱ ይኖሩ ነበር (ዘፍ.19፡8፣14)፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምም በዮሴፍ ቤት ትኖር የነበረችው በዚህ ባሕል ነው፡፡ [ምሥጢሩ ግን ያገለግላት ዘንድና ከላይ እንደ ተገለጠው ከአጋንንትና ከአይሁድ ፅንሱን ለመሰወር ነው፡፡]
ለዮሴፍ ከመታጨትዋ በፊት አለመፅነስዋስ ለምንድን ነው? ቀደም ብዬ እንደ ተናገርሁት፡-
☞ እስከ ጊዜው ጊዜ ሥራው [ከሰይጣን] ይሰወር ዘንድ ስላለው፣
☞ [ላቲ ስብሐትና] ቅድስት ድንግል ማርያም “ከዝሙት ፀንሳ ተገኘች” ተብሎ በድንጋይ እንዳትወገር [ከአይሁድ] ለመጠበቅ ነው፡፡
ከሌሎች ሕገ ኦሪትን እንጠብቃለን ከሚሉት ሰዎች ይልቅ [“ከሌላ ሰው ጋር ዝሙት ፈጽማ ተገኘች” ብሎ] እጅግ ሊቀና ይችል የነበረው ጻድቁ ዮሴፍ በፍጹም ለሌሎች ሳይገልጣት ወይም ሳያዋርዳት እንዲያውም ፀንሳ ከተገኘች በኋላ ከተቀበላትና ካገለገላት፥ ፀንሳ የተገኘችው በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደ ኾነ አስቀድሞ ተነግሮትና እርሱም አምኖ ተቀብሎት ባይኾን ኖሮ በቤቱ እንዲቀበላትና በሚያስፈልጋት ነገር ኹሉ ሊያገለግላት አይችል እንደ ነበረ በጣም ግልፅ ነው፡፡ በመኾኑም ወንጌላዊው፡- “ፀንሳ ‘ተገኘች’” ማለቱ ይህን ድንቅ፣ ከሕገ ተፈጥሮ [ከጋብቻ] አፍአ የኾነውን ሥራ፣ በልብ ከመታሰብና ከመመርመር ውጭ መኾኑን፣ ከዚህ በፊትም ከዚህ በኋላም መቼም ቢኾን መች ያልታየና የማይታይ መኾኑን በግልፅ የሚያስረዳ ነው፡፡
ስለዚህ [እመን ታመንም እንጂ] ከተጻፈልህ ነገር አልፈህ አትመርምር፡፡ ከተባለውና ከተነገረው ነገር አልፈህ ምንም አትሻ፡፡ “ድንግል በድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ፀንሳ የተገኘችው እንዴት ነው?” ብለህም አትጠይቅ፡፡ በዘር በሩካቤ የሚገኝ ፅንስ እንኳን እንዴት ፅንስ እንደሚፈጠር ማወቅ የማይቻለን ከኾነ መንፈስ ቅዱስ ተአምራትን ሲያደርግ’ማ እንደ ምን ማወቅ ይቻለናል? ወንጌላዊውም እንዳታስጨንቀውና እነዚህን ነገሮች አዘውትረህ በመጠየቅ እንዳታውከው ብሎ አስቦ የተከናወነው ነገር ተአምር እንደ ኾነ ነገረህ፤ እንዲህ አድርጎም ራሱን ነጻ አደረገ፡፡ “የተከናውነው ነገር በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከመኾኑ በቀር ከዚህ ውጭ ምንም ምን የማውቀው ነገር የለም” አለህ፡፡
@ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን 4፥5

በተመሳሳይ ኃጢአት እየወደቅኩ ተቸገርኩኝ፡፡ ምን ላድርግ?
@And_Haymanot
ጥያቄ፦ አንድ ኃጢአት በተደጋጋሚ እሠራለሁ፡፡ ንስሐ አባቴ ጋር በተደጋጋሚ ብሔድም ኃጢአቴን መተው አልቻልኩም፡፡ ምን ላድርግ? እባካችሁ ጉልበት የሚኾነኝ ምክር ስጡኝ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡”
አንድ ሰው “ምን ላድርግ?” ብሎ ሲጠይቅ መንፈሳዊ ሕይወትን መፈለጉ ማሳያ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን “ምን ማድረግ ይገባኛል?” የሚል ጥያቄ ካነሣ ለማደግ መፈለጉን፣ መንፈሳዊ መፍትሔ መሻቱን፣ እግዚአብሔር እንደሚረዳው በማያጠያይቅ መንገድ ማመኑን ያመለክታል፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ፣ ቀራጮች እንዲኹም ጭፍሮች እየመጡ፡ “ምን እናድርግ?” ይሉት ነበር ሉቃ.3፡10-14 ፡፡ ስለጠየቁም “ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ” ብሏቸዋል /ማቴ.3፡8/፡፡ ሐዋርያት ሲያስተምሩ፡- “ወንድሞች ሆይ! ምን እናድርግ?” ያሉት የገባቸው ናቸው /ሐዋ.2፡37/፡፡ ስለዚኽ ምንም ደካሞች ብንኾንም ድካማችንን ከእኛ የሚያርቀው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር “በርሱ ቃል እታነፃለኁ፤ እመከራለኁ” ብሎ “ምን ላድርግ?” ብሎ መጠየቅ ታላቅነት፣ አንድም ትሕትና፣ አንድም የመንፈሳዊ ሕይወት ፍላጎትን የሚያሳይ ነውና ኹል ጊዜ ጠያቂዎች ለካህናት፣ ለቤተ ክርስቲያን መምህራን “ምን ማድረግ ይገባኛል?” ብለው ሲጠይቁ ሊበረታቱ ይገባቸዋል፡፡ በመኾኑም ውድ ጠያቂያችን ምሥጢራቸውን በማካፈል የኃጢአት ልምምድ ድል መንሻ ጥበባትን እንድንማማር ምክንያት ስለኾኑን በልዑል እግዚአብሔር ስም ላመሰግናቸው እወዳለኁ፡፡ ጥያቄው የብዙ ሰዎች ጥያቄ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ፡- “ሰው ኾኖ የማይበድል እንጨት ኾኖ የማይጤስ” እንዲሉ እንደየኑሮአችን ደረጃ፣ እንደየሥራችን ዓይነት ይለያይ እንደኾነ እንጂ ክርስትና ሕይወታችን ስንመላለስ አንድ ከሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ ኃጢአት የሚስማማን መኾኑ ነው፡፡ ጥያቄአችንም ጠያቄአችን እንዳነሡት “ምን እናድርግ?” ነው፡፡ በርግጥም “ምን እናድርግ?”፦ የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ማወቅ፡- አንድ ሰው የሚወድቅበት ሌላኛው የማይወድቅበትና ትኩረት የማይሰጠው ሊኾን ይችላል፡፡ ከዚኽ አንጻር ጠያቂው “በተመሳሳይ ኃጢአት ደጋግሜ እወድቃለኁ” ያሉት ኃጢአት ምንድነው? እየተደጋገመ ያስቸገራቸው ምንድነው? ከምንም በፊት የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ያጢኑት፡፡ መፍትሔው የሚዠምረው ከዚኽ ነው፤ የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ከማወቅ፡፡ የኃጢአቱን ምንነትና መነሻውን ከለዩ በኋላ ለዚያ ከሚዳርጉን ቦታዎች፣ ወይም ጓደኞች፣ ወይም ኹኔታዎች መሸሽ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ወደምንወድቅበት ኃጢአት የሚገፋፉ ኹኔታዎችን፣ ቦታዎችን ወይም ጓደኛን በአጠቃላይ እንደየኃጢአቱ መነሻነት መራቅ ያስፈልጋል፡፡ “ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ኾነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ኾነህ ትገኛለህ” ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት /መዝ.18፡ 26/፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም፡- “አትሳቱ፤ ክፉ ባለንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል” ይላል /1ኛ ቆሮ.15፡33/፡፡ በዚኽ መሠረት ጠያቂያችን ብቻ ሳይኾኑ ኹላችንም ኃጢአትን ደጋግመን የምንሠራው በኹኔታዎች ተጽዕኖ ነው? ወይስ በጓደኞች ግፊት? ወይስ በምንሰማው፣ በምናየው፣ በምንዳስሰው ተጽዕኖ? ይኽን በአግባቡ ከለየን በኋላ ከምንጩ ለማድረቅ ለዚያ ከሚዳርጉ ኹኔታዎች መሸሽ ነው፡፡ ይኽን ስናደርግም ከምንም በፊት ኅሊናን ማሳመን ይጠይቃል፡፡ በመቀጠልም አካላዊ ውሳኔ መስጠትን ነው፡፡ ለኃጢአት በሚዳርግ ቦታ ተቀምጠን “በፍጹም አይነካኝም፤ አይደርስብኝም” ማለት መመጻደቅ ነው፡፡ ሰይጣንም እኛን ለመጣል አያርፍምና የምንወድቅበትንም መንገድ ያዘጋጃልና በኅሊናም በአካልም ከዚያ መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ የጴጢፋራ ሚስት ዮሴፍን ለክፉ ሥራ ስትከጅለው ቆሞ አልተሟገተም፤ ጥሏት ሸሸ እንጂ /ዘፍ.39/፡፡ ስለዚኽ ለተደጋጋሚ ኃጢአት ከሚዳርጉንና ከሚገፋፉን ነገሮች “እችለዋለኁ፤ እቋቋሟዋለኁ” ብሎ መመጻደቅ ሳይኾን መሸሽ ካለብን መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ እንደየኹኔታው በይበልጥም ከክፉ ቦታዎች፣ እንደየኃጢአቱ መነሻነት መሸሽ ያስፈልጋል፡፡ ኃጢአቱ በሥጋም በነፍስም ጎጂ እንደኾነ ማስተዋል፡፡ ይኽ በተመሳሳይ እየወደቅንበት ያለው ኃጢአት በሥጋም ጭምር የሚጎዳን ይኾናል፡፡ ከክርስትና ሕይወት ባሻገር ስብእናን የሚያጎድፍ፣ ጤናን የሚያውክ ሊኾን ይችላል፡፡ ከዚኽ አንጻር የዚኽ ጉዳት በጥልቀት ማስተዋል ያስፈልጋል፤ ጉዳት ማሰብ ለመጠንቀቅ ይረዳልና፡፡ ከመምህረ ንስሐ፣ ከመምህራን እንዲኹም ከመጻሕፍት ትምህርት ማግኘት፡፡ እድገት በደረጃ ነው፡፡ በአንድ ጀምበርም ለውጥ ላይመጣ ይችላል፡፡ በመኾኑም በሒደት ያንን የመተው መስመር ውስጥ እንድንጠነክር ከዚኽ ኹኔታም ፈጽመን ለመራቅ በራሳችን ጉልበት ብቻ አንችልም፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብሎናልና /ዮሐ.15፡5/፡፡ በዚኽም መሠረት ከመምህራን የምንሰማው የእግዚአብሔር ቃል፣ ከመጻሕፍት የምናገኘው፣ ከመምህረ ንስሐም በጸሎትና በምክር የምናገኘው ሐሳብ ያ እያጠቃንና እየጣለን ያለውን እንዲኹም የምንደጋግመውን ኃጢአት ለማስወገድ ኃይል ይኾነናል፡፡
@And_Haymanot
መንፈሳዊ ተግባራትን ማዘውተር፡፡ እንግዲኽ እንደየ ክስተቱ ለየትኛውም የኃጢአት ተግባር መንፈሳዊ ሕይወት፣ መንፈሳዊ ተግባር ድል መንሻው ነው፡፡ ይኽም “እንዲኽ ያለውን ክፉ መንፈስ ያለ ጾም ያለ ጸሎት ከእናንተ አይወጣም” እንዳለ /ማር.9፡29/ ጾምን፣ ጸሎትን፣ ንስሐን የሕይወታችን መሠረት ማድረግ ነው፡፡ መተውን መለማመድ፡፡ ይኽም ማለት ጠቢቡ “ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር” እንዳለ /ምሳ.23፡17/ “እስኪ ዛሬ ተቆጥቤ ልዋል” ብሎ መወሰን ማለት ነው፡፡ ከዚያ ከምንጠላው ግን ደግሞ እየወደቅንበት ካለው ስሕተት ተቆጥበን ከዋልን ማታ ላይ ተመስገን ብሎ ጸልዮ ማደር ነው፡፡ ነገም ሲነጋ “ዛሬም እንዲኹ እንደ ትናንትናው መንፈሳዊ መንገድና ሒደት ልዋል፡፡ ዛሬም እንዲኽ ካለው ተግባር ፍጹም ተቆጥቤ መዋል አለብኝ፡፡ ደግሞም እችላለኁ፡፡ እግዚአብሔር ያስችለኛል፡፡ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ኹሉን እችላለኁ፡፡ እግዚአብሔር ያበራታኛል” ስንልና ዕለት ዕለት ኹኔታውን እየኰነንነው፣ እያወገዝነው፣ “በዚያ መንፈስ ዛሬ አልውልም፡፡ ይልቁንም በመንፈሳዊ መንገድና በጥንካሬ እውላለኁ” ብለን ስንወስን ያን ውሳኔአችንን እያደነቅን ስለተደረገልን ጥንካሬም ተመስገን እያልን ልምምድ ማድረግ ይቻላል፡፡ ደጋግመን የምንሠራው ኃጢአት እጅግ ብዙ ዘመናት ከእኛ ጋር የቆየ ሊኾን ይችላል፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ኃይል በላይ የኾነ ኃጢአት የለም፡፡ ዋናው የእኛ ውሳኔ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የምንታለለው እዚኽ ጋር ነው፡፡ ለመተው እንፈልጋለን፤ ለመተው ግን በተግባር አንወስንም፡፡ ንስሐ መግባት የማይፈልግ ሰው የለም፤ በተግባር ወስኖ የሚገባ ግን ጥቂት ነው፡፡ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ መኖር የማይፈልግ ክርስቲያን አይኖርም፡፡ ብዙዎች መቁረብ ይፈልጋሉ፤ ወስነው የሚቆርቡት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙ ሰዎች ከዝሙት ኃጢአት መራቅ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ዝሙትን የሚያበረታቱ ማስታወቂያዎችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ምስሎችን እንዲኹም የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ዘፈኖችን እንዲኹም ጽሑፎችን፣ ዝሙትን የሚያበረታቱ ንግግሮችን ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ እነዚኽን ሰዎች ስናያቸው በውስጣቸው ከዚያ ኃጢአት የመራቅ ፍላጎት አለ፤ ተግባሩ ላይ ግን ከዚያ የሚያሸሻቸው አይደለም፡፡ ለዚኽም ነው ጌታ፡- “ብዙዎች ይፈልጋሉ፤ አይችሉምም” ያለው

ሉቃ.13፡24/፡፡ ስለዚኽ ከኃጢአት መራቅ የሚፈልግ ሰው የመተው ልምምድን አኹንኑ መዠመር አለበት፡፡ “ዛሬ ዘፈን አላዳምጥም፡፡ ዛሬን በዚኽ ምትክ መዝሙር አዳምጣለኁ” ብሎ መለማመድ አለበት፡፡ በዚኽ ውሳኔው ጸንቶም ዛሬን ይውላል፤ ያድራልም፡፡ ሌሎች ነገሮችም እንደዚኽ ናቸው፡፡ የመጠጥ ልምድ ያለው ሰው “ዛሬ አልጠጣም፤ ዛሬ በምጠጣበት ሰዓት እዚኽ ቦታ እሔዳለኁ፡፡ እዚያ ሒጄ እውላለኁ፡፡ በበጎ ነገር አሳልፈዋለኁ” ሲል ዛሬን ይውላል፡፡ ማታ ላይ ሲመሽ “ለካ ይቻላል፡፡ ለካስ እኔ ከበረታኁ እግዚአብሔር ያስችለኛል” የሚለውን በኅሊናው ያሳምናል፡፡ ነገሮችን የመተው ልምምድ በተግባር ማሳየት ማለት ይኸው ነው፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያ ያስቸግረን የነበረው ተደጋጋሚ ኃጢአት ታሪክ ይኾናል፤ ለሌላ ሰው መካሪ ኾነን ራሳችንን በለውጥ ቦታ ላይ እናገኟለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
በቀሲስ ፋሲል ታደሰ
ምንጭ፦ መቅረዝ ዘተዋሕዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
በቀሲስ ፋሲል ታደሰ
ምንጭ፦ መቅረዝ ዘተዋሕዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሆሳዕና
.
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ.
12÷12-15
.
የዘንባባ ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን
የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ
ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና
በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡
የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ
ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።
.
በዓሉን በዓለ ክብር ፣ በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ አ ሜ ን !!!

↗ይህ ማነው?↖❤
👆 👆
@And_Haymanot
=>ሁሉን ሳለው ከድሆች ቤት ያደረ
=>ክቡር ሲሆን የተናቁትን ያከበረ
=>ባለ ፀጋ እርሱ ከምስኪኖች ደጃፍ የቆመ
=>ንጉስ እርሱ ያገልጋዬቹ እግር የሳመ
↗👉ይህ ማነው?↖
=>እየጣሉት የሚያነሳ
=>እየቀሙት የሚለግስ
=>እያቆሰሉት የሚጠግን
=>እየራበው የሚያጎርስ
=>እየታረዘ የሚያለብስ
=>እየተጠማ የሚያጠጣ
↗👉ይህ ማነው?↖
=>ሙሽራ ሲሆን ያላዘዘ
=>ባለመድሀኒት ሲሆን የታመመ
=>ከሁሉ ከፍ ያለ ሲሆን ያነሰ
=>ኃያል ሲሆን የደከመ
↗👉ይህ ማነው?↖
=>ቀና ሲል ሰማይን ሞልቶ ያየሁት
=>ዝቅ ስልም ከድንግል ጎን ያየሁት
↗👉ይህ ማነው? ↖
=>በሰማይ የማይወሰን ከድንግል ማህፀን ያረፈ
=>በእጁ አላማትን የጨበጠ
=>በፍጡር ጀርባ የታዘለ
=>በብላቴና ክንድ የታቀፈ
↗👉አረ ይህ ማነው?↖
=>ከዙፋኑ ሳይለቅ ከአገልጋዬች ጋር አብሮ ያለ
=>ከላይ ሙሉ የሆነው ከታችም ያልጎደለው
=>አይኔ ባቀና ከላይ የማየው
=>ባጎነብስም የማላጣው
↗👉ይህ ማነው?↖
=>ቀንድ ሳለው የማይዋጋ
=>ጥፍር ሳለው የማይቧጭር
=>ጉልበት ሳለው የማይጋፋ
=>ክንድ ሳለው የማይሰብር
↗👉ይህ ማነው?↖
=>የገፉትን የደገፈ በጨካኞች ፊት የራራው
=>የሰበሩትን የጠገነ የወጉትን ያበራ
↗👉ይህ ማነው?↖
=>ሞትን በሞቱ ያሸነፈው
= የጥላት ኃልን ድል የነሳው
=>የክፋትን ክንድ የሰበረው
=>የዕዳችን ደብዳቤ የሻረው
=>ጨለማውን የገፈፈው
=>የወደሙትን የበረበረ
=>ታላቁን ዜና ያበሰረ
=>ፍቅር የፍቅር መምህር
=>ትሁት የትሁታን ክብር
=>በሁሉ ዘንድ የተወደደው
=>ግና ከሁሉ የተለየው
↗👉ኧረ ይህ ማነው?↖
👉እርሱማ የፍቅር አባት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
@And_Haymanot
=>እወድሀለሁ ጌታየ ሆይ እስኪ ስማኝ
=>አንድ የማጫውትህ ጉዳይ አለኝ
=>በፊትሄ ቡዙ በደልኩ
=>ከክብሬ በፍቃድ አነስኩ
=>አትብላ ያልከኝን በላሁ
=>አታድርግ ያልከኝን አደረሁ
=>አትየው ያልከኝን አየሁ
=>አትቅረበው ያልከኝን ቀረብሁ
=>ከውቡ ቃልህ ሸሸሁ
=>ጥሩ ምክርህን አቃለልሁ
=>ጥልን በልቤ አፈራሁ
=>ትእዛዝህን አፈረስኩ
=>ቅዱሱ ባህሪን አሳደፍኩ
=>ጌታሆይ በምኔ ይሆን የወድድከኝ?
=>ሞቴን በሞትክ ሽረህ ከክፉ እሳት ማርከህ ያወጣኸኝ
=>ጌታየ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ እወድሀለሁና ልምበርከክልህ
=>እንግዲህ እንደምወድህ ታውቅ ዘንድ ዋስ ማንን ላቅርብልህ?
=>ዋስም ሌላ የለኝም ድንግል ማርያም ናት
=>ቅድስት ወላጅህ ከሁሉ ይልቅ የምትወዳት
=>እርሷም ከሁሉ ይልቅ የምትወድህ
@And_Haymanot
👉ስለዚህ እኔም እወድሀለሁ
👉ስለ እናትህ ድንግል ብለህ ይቅር በለኝ እልሀለሁ
↗👉ይህ ማነው?
{ምንጭ ከ ማርቆስ ወንጌል 4:40}
👉💒ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
👆 👆
@And_Haymanot
=>ሁሉን ሳለው ከድሆች ቤት ያደረ
=>ክቡር ሲሆን የተናቁትን ያከበረ
=>ባለ ፀጋ እርሱ ከምስኪኖች ደጃፍ የቆመ
=>ንጉስ እርሱ ያገልጋዬቹ እግር የሳመ
↗👉ይህ ማነው?↖
=>እየጣሉት የሚያነሳ
=>እየቀሙት የሚለግስ
=>እያቆሰሉት የሚጠግን
=>እየራበው የሚያጎርስ
=>እየታረዘ የሚያለብስ
=>እየተጠማ የሚያጠጣ
↗👉ይህ ማነው?↖
=>ሙሽራ ሲሆን ያላዘዘ
=>ባለመድሀኒት ሲሆን የታመመ
=>ከሁሉ ከፍ ያለ ሲሆን ያነሰ
=>ኃያል ሲሆን የደከመ
↗👉ይህ ማነው?↖
=>ቀና ሲል ሰማይን ሞልቶ ያየሁት
=>ዝቅ ስልም ከድንግል ጎን ያየሁት
↗👉ይህ ማነው? ↖
=>በሰማይ የማይወሰን ከድንግል ማህፀን ያረፈ
=>በእጁ አላማትን የጨበጠ
=>በፍጡር ጀርባ የታዘለ
=>በብላቴና ክንድ የታቀፈ
↗👉አረ ይህ ማነው?↖
=>ከዙፋኑ ሳይለቅ ከአገልጋዬች ጋር አብሮ ያለ
=>ከላይ ሙሉ የሆነው ከታችም ያልጎደለው
=>አይኔ ባቀና ከላይ የማየው
=>ባጎነብስም የማላጣው
↗👉ይህ ማነው?↖
=>ቀንድ ሳለው የማይዋጋ
=>ጥፍር ሳለው የማይቧጭር
=>ጉልበት ሳለው የማይጋፋ
=>ክንድ ሳለው የማይሰብር
↗👉ይህ ማነው?↖
=>የገፉትን የደገፈ በጨካኞች ፊት የራራው
=>የሰበሩትን የጠገነ የወጉትን ያበራ
↗👉ይህ ማነው?↖
=>ሞትን በሞቱ ያሸነፈው
= የጥላት ኃልን ድል የነሳው
=>የክፋትን ክንድ የሰበረው
=>የዕዳችን ደብዳቤ የሻረው
=>ጨለማውን የገፈፈው
=>የወደሙትን የበረበረ
=>ታላቁን ዜና ያበሰረ
=>ፍቅር የፍቅር መምህር
=>ትሁት የትሁታን ክብር
=>በሁሉ ዘንድ የተወደደው
=>ግና ከሁሉ የተለየው
↗👉ኧረ ይህ ማነው?↖
👉እርሱማ የፍቅር አባት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
@And_Haymanot
=>እወድሀለሁ ጌታየ ሆይ እስኪ ስማኝ
=>አንድ የማጫውትህ ጉዳይ አለኝ
=>በፊትሄ ቡዙ በደልኩ
=>ከክብሬ በፍቃድ አነስኩ
=>አትብላ ያልከኝን በላሁ
=>አታድርግ ያልከኝን አደረሁ
=>አትየው ያልከኝን አየሁ
=>አትቅረበው ያልከኝን ቀረብሁ
=>ከውቡ ቃልህ ሸሸሁ
=>ጥሩ ምክርህን አቃለልሁ
=>ጥልን በልቤ አፈራሁ
=>ትእዛዝህን አፈረስኩ
=>ቅዱሱ ባህሪን አሳደፍኩ
=>ጌታሆይ በምኔ ይሆን የወድድከኝ?
=>ሞቴን በሞትክ ሽረህ ከክፉ እሳት ማርከህ ያወጣኸኝ
=>ጌታየ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ እወድሀለሁና ልምበርከክልህ
=>እንግዲህ እንደምወድህ ታውቅ ዘንድ ዋስ ማንን ላቅርብልህ?
=>ዋስም ሌላ የለኝም ድንግል ማርያም ናት
=>ቅድስት ወላጅህ ከሁሉ ይልቅ የምትወዳት
=>እርሷም ከሁሉ ይልቅ የምትወድህ
@And_Haymanot
👉ስለዚህ እኔም እወድሀለሁ
👉ስለ እናትህ ድንግል ብለህ ይቅር በለኝ እልሀለሁ
↗👉ይህ ማነው?
{ምንጭ ከ ማርቆስ ወንጌል 4:40}
👉💒ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን
@And_Haymanot
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን
@And_Haymanot
ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚባላ ንፍሮ ነው፡፡
የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር፤ አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ
እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበርና ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና
ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል፡፡
በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን
አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያም አብዛኛዎቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡
በዲ/ን ቤርዜሊ ተስፋዬ

የትሁታን አምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ
@And_Haymanot
"-----4፤ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤
5፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።
6፤ ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም። ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።
7፤ ኢየሱስም መልሶ። እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።
8፤ ጴጥሮስም። የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም። ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት።
9፤ ስምዖን ጴጥሮስም። ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።
10፤ ኢየሱስም። የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።
11፤ አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና፤ ስለዚህ። ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለው።
12፤ እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው። ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?
13፤ እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።
14፤ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።
15፤ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
16፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።
17፤ ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።...."
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13)