✞ ✞ ✞ ታቦት ✞ ✞ ✞
ተወዳጆች በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ እያልን ዛሬ በታቦት ዙርያ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ይዘን ቀርበናል
☞ ታቦትን ሌሎች ሃገራት እንዴት ይጠቀሙታል?Read more
☞"ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ"
ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል?
አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ "የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ አይሹትም ፣ አይደረግምም" የሚለውን በመጥቀስ የሐዲስ ኪዳነ ታቦትን ይቃወማሉ።...
Read more
☞ ታቦት ተሽሯል? Read more
☞ ይህ ሁሉ ታቦት ከየት መጣ? Read more
☞ የሐዲስ ኪዳን ታቦታችን ክርስቶስ ነው ሌላውን ሽሮታል? Read more
ተጨማሪ ለማንበብ ☞ ይህን ይጫኑ

ትላንት ማታ ጨረቃ ላይ የጌታችንንና የመጥምቁን ሥዕል ያዩ ምእመናን (ለመዋሸት ምንም ምክንያት የሌላቸው ወንድሞች ሳይቀር) በደስታ ሲነግሩን ፎቶ ሲልኩልን አምሽተዋል። ነገሩን ለማጣራት መቼም "ጨረቃ ሆይ አንድ ጊዜ ድገሚው" ማለት አንችልም። ይህን አምኖ ፈጣሪን ማመስገን አያስነቅፍም። ያየውን የሚመሰክር ሰው ሲገጥመንም ዝም ብለን አንነቅፍም። ይሁንና "ላይሆን ይችላል ፣ በፎቶሾፕ የተሠራ ቢሆንስ" ወዘተ ብሎ መጠርጠርም (Sceptical መሆንም) በምልክት ማመን የእምነት መለኪያ ስላልሆነ አያስቀጣም። በሐሰት ምልክት ከመነዳትም ስለሚጠብቅ ጥሩ ነው። ደቀ መዛሙርቱም ክርስቶስን ተከትለውት ተአምር አዩ እንጂ ተአምር አይተው አልተከተሉትም።
ጨረቃን የፈጠረ ብለን የምናመልከው አምላክ በጨረቃ ላይ ምልክት ቢያሳየንም ባያሳየንም አምላክ ነው። እስከ ጨረቃ ድረስ የሚያይ ዓይናችንን እንደ ቴሌስኮፕ የገጠመው እርሱን በጨለማ የምታበራዋን ኳስ የፈጠራትን እርሱን ለማድነቅ በሚልየን የሚቆጠሩ ብዙ ምክንያቶች አሉን።
በጨረቃ ላይ በታየው ነገር ለየሰዉ የሚታየው ነገር እንደማንነቱ ነው። መንፈሳዊ ዓይን ያለው መንፈሳዊ ነገር ያያል። ሌላው ደግሞ ድራገን ፣ ጊንጥ ወዘተ አየሁ ሊል ይችላል። በሌላው ዓለም ዜና ማሠራጫዎችም የየራሱ ትንታኔ ተሠጥቶታል። ጥምቀትን ላከበረው ክርስቲያን ምእመን ግን መጥምቁ ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቅ ታይቶታል።
በአንድ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ተማሪዎች ማታ ወጥተው ሲዘምሩ አምሽተዋል። ወጣቶች በሌሊት ተነሥተው ወደ ጭፈራ ቤት ከመሔድ ይልቅ ፈጣሪን ሲያመሰግኑ ማደራቸው ራሱ ብቻውን ተአምር ነው። ጨረቃ ላይ ከታየው መሬት ላይ የታየው በለጠ ያሰኛል። ጨረቃ ላይ ፍጡር ካለ ወደ ምድር ቁልቁል እያየ ይኼን ዝማሬ ማድነቅ ይኖርበታል።
ከዚያ ውጪ እኛ ኦርቶዶክሳውያን መጥምቁ ዮሐንስን ግን ጨረቃ ላይ ካየነው ቆይተናል።
መጥምቁ ዮሐንስ ራሱ ጨረቃ ነው። ጨረቃ በጨለማ ያበራል ፣ ፀሐይ ሲወጣ ለፀሐይ ሥፍራውን ይለቅቃል። መጥምቁ በጨለማው የብሉይ ኪዳን ዘመን ካበሩ ነቢያት የመጨረሻውና ከሁሉ የሚበልጠው ነቢይ ነበር። "እርሱ የሚነድ መብራት ነበረ ፣ ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ" እንደተባለ መጥምቁ ዮሐንስ በሌሊት ያበራ ጨረቃ ነበረ። (ዮሐ 5:35)
ፀሐይ ከወጣች በኋላ ጨረቃ ብርሃንዋ እንደማያስፈልግና ለፀሐይ ቦታዋን እንደምትለቅ መጥምቁ ዮሐንስም እውነተኛው ፀሐይ ክርስቶስ ሲመጣ "እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባኛል" ብሎ ሥፍራውን ለቀቀ። (ዮሐ 3:30)
ዮሐንስ በራእዩ ያያት ፀሐይን ተጎናፅፋ ፣ ዐሥራ ሁለት ከዋክብት ዘውድ የሆኑላት ፣ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ሴትም በአንድ በኩል ሙሽራይቱ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን በሌላ በኩል "ወንድ ልጅ ወለደች" የሚለው ቃል እንደሚያስገድደን ድንግል ማርያም ናት። ፀሐይ ክርስቶስን የተጎናጸፈችውም በማኅፀንዋ ማደሩ ከእርስዋ በመወለዱ ሲሆን ከዋክብቱም የከበቧት ሐዋርያት ነበሩ። ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ጨረቃ ገና በእናቱ ማኅፀን እያለ የሰላምታዋን ድምፅ ሰምቶ የሰገደው መጥምቁ ዮሐንስ ነው።
ኦርቶዶክሳውያን መጥምቁ ዮሐንስን ጨረቃ ላይ ስናየው ቆይተናል። ጨረቃ ላይ ሥዕሉን ብናይም ባናይም ጨረቃን ባየን ቁጥር መጥምቁ ዮሐንስን ማሰባችን አይቀርም።
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 13 2011 ዓ ም
ስቶክሆልም ስዊድን
@And_Haymanot

💒 116ኛው የግብጽ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ በፓትርያርክነት ዘመናቸው ይቀመጡበት የነበረው በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል የሚገኝ አንድ ያረጀ ክፍል ነበረ። በዚህ ክፍል ሲኖሩ አንድ የካቶሊክ መነኩሴ ሊጎበኛቸው መጣ። የፓትርያርኩን ማረፊያ ቤት እና እቃዎቻቸውን ሲመለከት ለክብራቸው የሚመጥን ባለመሆኑ እጅግ ደነገጠ።
❖ መነኩሴው አቡነ ቄርሎስን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው "እባክዎን በእንዲህ ያለ ቤት መኖር ለእርሶ የሚመጥን አይደለም። ፍቃድዎ ከሆነ እኔ ቤትዎን ላሳድስሎት እና አዳዲስ ምርጥ ዕቃዎችን ላስገባሎት?" የፓትርያርኩ ይህን ሲሰሙ ፈገግ ብለው በፍቅር አይን ከተመለከቱት በኋላ"የእኔ ልጅ በጣም አመሰግናለሁ! እርግጥ ነው ይህ ቤት በጣም የተጎሳቆለ ነው። እንደዚያም ሆኖ ግን ጌታ ከተወለደበት በረት ይሻላል!!" አሉት።
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot

ድረስልን
በቃ ብሎን ጌታ ግፍ እና መከራ
ይላክልን አንተን እስቲ እኛን አብስራ ።
ዘመናችን ሆኗል እንደ ዓመተ ፍዳ
ድረስልን ማልደህ ገብርኤል ፈጣኑ ድሆቹን ተራዳ ።
[ዳንኤል ግርማ ]
@And_Haymanot
የመልአኩ ተራዳይነት አይለየን
መልካም ዕለተ ሰንበት
በቃ ብሎን ጌታ ግፍ እና መከራ
ይላክልን አንተን እስቲ እኛን አብስራ ።
ዘመናችን ሆኗል እንደ ዓመተ ፍዳ
ድረስልን ማልደህ ገብርኤል ፈጣኑ ድሆቹን ተራዳ ።
[ዳንኤል ግርማ ]
@And_Haymanot
የመልአኩ ተራዳይነት አይለየን
መልካም ዕለተ ሰንበት
አስተርእዮ ማርያም
፠★፠★፠★፠★፠★
:
ወር በገባ በ21ኛው ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን
የምናስብት ቀን ነው፡፡ ለመሆኑ ምክንያቱ ምንድር ነው?
:
ምክንያቱ የእመቤታችንን በዓለ እረፍት የምናስብት በመሆኑ ነው
፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ
በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር 21
እሑድ ነው ።
:
ጥር 21 አስተርእዮ ማርያም ይባላል፡፡ አስተርእዮ ማለት
መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፡ ተገለጠ
ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን
ኢየሱስክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ
የተገለጠበት(የታየበት) ፣አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት
በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ
አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት
በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ
ማርያም”ተብሏል።
፡
የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን)
ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት
በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን
አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ
ለምኝልን። አሜን።

ዘርፌ አዳራሹን ብትቀላቀልም ኦርቶዶክስ ናት ብላችሁ ዛሬም ጥብቅና የምትቆሙላት ንስሃ ግቡ ንቁ ንቁ ንቁ ሰውን ሳይሆን አማኑኤልን ተከተሉ። እግዚአብሔር ሰውን ከመከተል ይጠብቀን ፣
ሁሉን ማድረግ የሚቻለው ጌታ ልብ ይስጣት
👍አሜን👍
@And_Haymanot
ሁሉን ማድረግ የሚቻለው ጌታ ልብ ይስጣት
👍አሜን👍
@And_Haymanot
"ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡ ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ፡፡ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ
ክርስቶስን እየሰደብከው እንደኾነ አስተውል፡፡ #እንዴት? ያልከኝ እንደኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል፡፡ የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቅኸው ማለት
ክርስቶስን ናቅኸው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከኾነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ሐሞትን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም፡፡ ስለዚህ ወንድምህን እኅትህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥
ምንጭ፡- ሰማዕትነት አያምልጣችሁ

ተዋህዶ እና ቅብዐት
#ፍኖተ_ጽድቅ_ዘተዋሕዶ
በተዋሕዶ እና በቅብዐት መካከል ስላለው ሰፊ ልዩነት ሁሉም ያውቅ ይረዳ ዘንድ ሁሉም በየሞባይሉ ሊጭነው እና ሊያነበው የሚችለው መተግበሪያ በወንድማችን በዲ.ን ጌታሁን አማረ
ተዘጋጅቶ ቀረበልን፡፡ ይህን መተግበሪያ ለሠራልኝ ወንድሜ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው፡፡
ይህ መተግበሪያ ደብረ አሚንን የሚተካ አይደለም፡፡ መሠረታዊ የሆኑ ልዩነቶቻችንን ከሦስቱ የቅባት መጻሕፍት ሀሳብ በመነሣት የሚተነትን መተግበሪያ ነው፡፡ የትም ሆነው አውርደው ሊጭኑት
የሚችል ሲሆን መተግበሪያውን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ግን 20 ብር መክፈልና የመክፈቻ የምስጢር ኮድ መቀበል ይኖርብዎታል፡፡ በዚህ ዝቅተኛ ዋጋ መተግበሪያውን ያቀረብነው
ሁሉም ሰው እንዲያነበው በማሰብና ከዚሁ በሚገኘው ገቢም ወደፊት ለምሠራቸው ሥራዎች የማንንም እርዳታ ላለመጠየቅ በማሰብ ነውና እንደ ገንዘብ ሰብሳቢ እንደ ነጋዴ እንዳትቆጥሩኝ
አበክሬ እማጸናለሁ፡፡ ገንዘቡን ለመላክ ሞባይል ባንኪንግን መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዴት መላክ እና የምስጢር ኮድ መቀበል እንደሚቻል መተግበሪያውን አውርዳችሁ ስትጭኑት በዚያ ላይ
ያሳያችኋል፡፡
አፕሊኬሽኑን ለማየትና ለመጫን https://play.google.com/store/apps/details?id=org.goranda.finotetsidk
.....
ከመልካሙ በየነ የፌስቡክ ገፅ የተወሠደ፡፡
መተግበሪያውን(Application) እኛም በዚሁ ይዘንላችሁ ለመቅረብ ቃል እንገባለን፡፡ ፩ ኃይማኖት
Share share share

"የበለስ ቅጠል ሰፊና ደስ የምታሰኝ ናት፤ ወደ ጥፋት የምትወስደው የኃጢአት መንገድም ሰፊ በር ናት፡፡ የበለስ ፍሬ
ሲበሉአትና ሲያላምጡአት ጣፋጭ ናት፡፡ ኃጢአትም ሲሠሩአት ደስ ታሰኛለች፡፡ ከሠሩአት በኋላ ግን [እንደ በለሲቱ] መከራን ታመጣለች፡፡ በሚሠሩአት ጊዜ ጣፋጭ፥ ከሠሩአት በኋላ ግን መራራ ናትና እርስዋን ከመሥራት ሽሽ፡፡"
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

¶ በዩጋንዳ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች በሚገርም ፍጥነት
እየጨመረ ነው ። በ2019 ቁጥሩ 1 million ደርሷል ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
እየጨመረ ነው ። በ2019 ቁጥሩ 1 million ደርሷል ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
👍1
Forwarded from መሠረተ ያሬድ ሰ/ት/ቤት ዘአሣሣ
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን
✍ የተሃድሶ መናፍቃን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያን ብለን አንጠራም ይላሉ እነርሱ ቤተ ክርስቲያን የሚሉት ጉባኤውን ብቻ ነው እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ቅዱሳት መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያንን ቀደምት አበውን መሠረት አድርገን የተቀደሰውን ሥፍራ ቤተ ክርስቲያን እንለዋለን ነገር ግን የተሃድሶ መናፍቃኑ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት፦
@Meserete_Yared_Asasa
✞ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ትርጉም አለው እነርሱም፦
፩ኛ፦ የተወሰነ ቦታ (ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን)፦ ይህም በዘፀ 25፥8 ላይ "በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ" በሚለው በአምላካችን ቃል መሠረት በፈቃደ እግዚአብሔር የተገኘ በመሆኑ ነው ስለዚህ ለአምላካችን ማደሪያ የምንሰራው መቅደስ ቤተ ክርስቲያን ይባላል።
፪ኛ፦ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት፦ ቅዱስ ጴጥሮስ በ1ኛ ጴጥ 5፥13 ላይ "ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል" በማለት ባስተላለፈው መልእክቱ ላይ የገለፀው በባቢሎን ያለችውን የክርስቲያኖች ማሕበር ወይም ጉባዔን የሚያመለክት ነው ስለዚህ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት ቤተ ክርስቲያን ይባላል።
፫ኛ፦ እያንዳንዱ ክርስቲያን፦ ይህም ከያዕቆብ የተወለደ ሁሉ ቤተ እስራኤል እንደሚባል ሁሉ በመንፈሳዊና በምስጢራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ ምእመናን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ ቤተ ክርስቶስ እንደማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ቆሮ 3፥17 ላይ "ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" ብሏል ይህ ቃል እኛ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችንን ያመለክታል ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ይባላል።
☞ በእንግሊዝኛ #Church ፣ በጀርመንኛ #Kirche ፣ በደች #Kerke የሚሉትና ሌሎች ተመሳሳይ ስሞች ሁሉ #Kyriakon ከሚለው የግሪኩ ቃል የተገኙ ናቸው ትርጉሙም፦ "ማንኛውንም የክርስቶስ የሆነ ነገር" ማለት ነው ይህም ቃል ከመነሻው ለቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ስያሜ ይውል የነበረ ነው የላቲኑም ቃል "አቅሌስያ_Ecclesia" እና ከእርሱ ወጥተው በልዩ ልዩ የላቲን ቤተሰብ ቋንቋዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ተመሳሳይ ቃላት ሁሉ በመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋሉት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመጥራት ነበር የላቲኑ ቃል መነሻው የግሪኩ "አቅሌሲያ" ሲሆን የቃሉ ትርጉምም "የራስ ገዝ ከተማ የዜጎች መሪ ጉባኤ" ማለት ነው።
@Meserete_Yared_Asasa
❖ ሐዋርያት በተለያየ ቦታ በቤተ ክርስቲያን ይሰበሰቡ ነበረ ይህም፦
✅ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት በጽርሐ ጽዮን በኢየሩሳሌ ተሰብስበው ሳሉ ነበር/የሐዋ 2፥1/
✅ ሐዋ 11፥26 ላይም "በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ" ተብሎ ተጽፏል።
✞ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ቤተ ክርስቲያንን በቅዱሳን ስም ትሰይማለች ይህም አስቀድሞ በነብዩ ኢሳይያስ ትንቢት ተነግሮ ነበር "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ /ኢሳ 56፥4-5/ ብሎ በተናገረው መሠረት አብያተ ክርስቲያናት በቅዱሳን ስም ይጠራሉ የመጀመሪያዋም ቤተ ክርስቲያን የተሠራችው በፊልጵስዩስ ከተማ ሲሆን ይኼውም በ34 ዓ/ም ነው።
✞ ቤተ ክርስቲያን "የሰማይ ደጅ" ትባላለች አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራእይ መላእክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት፣ እግዚአብሔርም በላይዋ ተቀምጦባት ያያትን ቦታ "ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው" አለ /ዘፍ 28፥17/ ያዕቆብ ቦታውን ያከበረበት ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ተጠብቆ ዛሬም አዲስ ቤተ ክርስቲያን ይከብርበታል።
✍ የተሃድሶ መናፍቃኑ ከላይ ያየነውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታዎች ባለመረዳት ምንፍቅናቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስባል በሐዋ 17፥24 ላይ "ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም" የሚለውን ኃይለ ቃል በመጥቀስ ለማወናበድ ይጥራሉ።
@Meserete_Yared_Asasa
☞ ለመሆኑ "ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም" ማለት ምን ማለት ነው?
✞ የእግዚአብሔርን አነዋወር በተመለከት ቅዱሳት መጻሕፍት በልዩ ልዩ መንገድ ገልጠውታል ለምሳሌ፦
✅ በሰማይ የምትኖር /ማቴ 6፥9/፦ ይህም ክብሩን ለመናገር ነው
✅ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ /ዮሐ 6፥56/፦ ይህም ማለት በጸጋ አድሬበት እኖራለው ማለት ነው
✅ ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን /መዝ 131፥7/፦ ይህም በአንድ በኩል እግሮቹ የቆሙበትን መስቀል በሌላ በኩልም መቅደሱን ነው
❖ በመሆኑም እግዚአብሔር ሰው በሠራው ቤት አይኖርም ማለት አይወሰንም ማለት ነው የአሕዛብ ጣዖታት በቤተ ጣዖቱ ወይም መኖርያቸው ነው በሚባለው በኦሊምፐስ ተራራ የተወሰኑ ናቸው እግዚአብሔር ግን ለመገለጫው ቦታ ይመርጣል ማለት በዚያ ቦታ ይመሰናል ማለት አይደለም ክርስቲያኖች "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?" ተብለናል /1ኛ ቆሮ 3፥16/ ያ ማለት በጸጋ አድሮባችሁ ይኖራል ማለት ነው እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእናንተ ውጭ የለም ማለት አይደለም፣ ወይም ደግሞ በእንተ ተወስኖ ይኖራል ማለት አይደለም።
✍ ስለዚህ ተወዳጆች ይቺ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን የማትታደስ እንደመሆኗ መጠን የተሃድሶ መናፍቃን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አያስፈልግም ከሚሉት ሀሰተኛ ትምህርቶች እራሳችንን ጠብቀን በንጽህቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችን ጸንተን መኖር ነው የሚገባን የተሃድሶ መናፍቃኑም ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ተረድተው፣ ልብ ገዝተው በክርስቶስ ደም ወደ ተመሠረተችውና የገሃነም ደጆች ወደ ማይችሏት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ይመጡ ዘንድ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጸሎት ነው።
❖ በዓለት ላይ ነውና ያቆማት አጽንቶ
❖ በደሙ ነውና የቀደሳት ዋጅቶ
❖ ይጠብቃልና ጠባቂዋ ተግቶ
❖ የገሀነም ደጆች አይችሏትም ከቶ
✞ አምላከ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ከቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ጠላቶች ከተሃድሶ መናፍቃን ይጠብቅልን አሜን!!!✞

"በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡ ... እግዚአብሔር ፍጥረታትን የፈጠረበት መንገድ እንደ ምን እንደሚለይ፣ ከሰው አሠራር ይልቅ እንደ ምን ተቃራኒ እንደ ኾነ ተመልከቱ፡፡ ምክንያቱም አስቀድሞ ሰማይን ዘረጋ፤ ከዚያም የምድርን መሠረት አስቀመጠ፡፡ አስቀድሞ ጣሪያን ከዚያም መሠረቱን ሠራ፡፡ እንደዚህ ያለ አሠራርን ያየ ማን ነው? እንደዚህ ያለ ነገርን የሰማ ማን ነው? ሰዎች ምንም ይሥሩ ምን ከጣሪያ ጀምረው መሠረት ሊያኖሩ አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር ካዘዘ ግን ኹሉም ፈቃዱን ይፈጽማል፤ ለሰው የማይቻለውም ለእርሱ ይቻላል፡፡"
~ ኦሪት ዘፍጥረት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድር.፪፥፲-፲፩ ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
~ ኦሪት ዘፍጥረት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድር.፪፥፲-፲፩ ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
"እምነት ያለ ሥራ (ምግባር) የሞተ ነው፤ ሥራም ያለ እምነት እንደዚሁ የሞተ ነው፡፡ በእምነታችን ሕፀፅ የሌለብን ብንኾንም እንኳን ምግባር ግን ከሌለን እምነታችን ብቻውን ምንም አይጠቅመንም፡፡ ልክ እንደዚሁ በጎ ምግባራትን ለመሥራት ብዙ መከራዎችን ብንቀበልም እምነት ግን ከሌለን ምንም አይረባንም፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦሪት ዘፍጥረት፣ ድር.፪፥፲፬ ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦሪት ዘፍጥረት፣ ድር.፪፥፲፬ ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
@And_Haymanot @And_Haymanot
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
✍ "500 ምዕመናን በደቡብ ኦሞ ተጠመቁ!"
* **** * * ******
@Meserete_Yared_Asasa
መናፍቃን በወረሯት በደቡብ ክልል ባገባደድነው በጥር ወር ብዙ ነፍሳት ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተጠምቀው ተመልሰዋል። ወንጌል ያልደረሳቸው የደቡብ ኦሞ ህዝቦች በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት በሺዎች የሚቆጠሩት አምነው ተጠምቀዋል፡፡ በዚህም ወቅት በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት ከ500 በላይ ምዕመናን ሲጠመቁ ለመጠመቅ የተመዘገቡትም ከ500 በልጠዋል። በደቡብ ኦሞ በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት የተጠመቁ ኢ-አማንያን፦
+በ05/4/2011 ከ151 በላይ ኢ-አማኒያን ተጠምቀዋል፡፡
+በ16/5/2011 በሳላማጎ ወረዳ በዳኩባ ቀበሌ ከ161 በላይ ሰው ተጠምቋል፡፡
+በ27/5/2011 በሳላማጎ ወረዳ በወይዴ ቀበሌ ከ183 በላይ ሰዎች ተጠምቀዋል፡፡
በማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት በሙርሲ ሃና የተለያዩ አብያተክርስቲያናት እየታነጹ ይገኛሉ፡፡
(መረጃውን ያደረሰኝ መ/ር አማኑኤ ነው - ከደቡብ ኦሞ)
30/05/2011 ዓ.ም (ሐሙስ)