ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፪
-------ጥያቄ ፪-------
‘የተክለ ሃይማኖት ተቅማጥ ከክርስቶስ ደም ጋር እኩል ነው’ ይላል ይላሉ፡፡ በውኑ ይላልን?
መልስ፡- ሙሉ ገጸ ንባቡ “ክቡር አባታችንም ጌታዬ ወደ ሰማዕትነት ዐደባባይ ሄጄ በስምህ እንድሞት እዘዘኝ አለው፤ ጌታም መጋደልስ ፈጸምክ ከሞት በቀር ምንም አልቀረህም፡፡” አለው ነው የሚለው፡፡ [ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፯፤ ገጽ. 195] ከዚህም በኋላ፡- “ወናሁ ትመውት በሕማመ ብድብድ በእኩይ ሞት ወእሬሲ ለከ ኪያሃ ከመ ስቅለትየ በከመ ደመ ሰማዕት እለ እምቅድሜከ አኮ ለባሕቲትከ አላ ደቂቅከኒ እለ ይመውቱ በሕማመ ብድብድ በውስተ ዛቲ ገዳም እኌልቆሙ ምስለ ሰማዕታት ወአወፍዮሙ ለከ በመንግሥተ ሰማያት፡፡”[ዝኒ ከማሁ] ነው ያለው፡፡
+ የቃሉ የግእዝ ትርጒም ሕማመ ብድብድ ማለት ቸነፈር ማለት ነው፡፡ ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት የሞቱት በቸነፈር በሽታ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዕለተ ዐርብ እንደ ተቀበልኩት መከራ መስቀል አደርግልሃለሁ ያለው፤ ገድላቸውንና በደዌ የተቀበሉትን መከራ ነው፡፡ በመልክዐ ጊዮርጊስ ላይም እንዲህ የሚል አብነት ይገኛል፡፡ ሰላም ለሰኳንዊከ ምስለ ክልኤሆን መከየድ፡፡ ለአጻብዒከ ሰላም ወለአጽፋረ እግርከ አምሳለ መረግድ፡፡ ገባሬ መንክራት ጊዮርጊስ በአቊጽሎ ይቡስ ዐምድ፡፡ አድኅነኒ በጸሎትከ እምነ መከራ ክቡድ፡፡ እስመ እምኔሁ ይወጽእ ቀታሊ ብድብድ፡፡ (መልክዐ ጊዮርጊስ) ትርጓሜውም፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ በሁለቱ ተረከዞችህ ጋር ለጫሞችህ ሰላም እላለሁ፡፡ እንደ ከበረ ዕንቊ ለሚያበሩት ለእግር ጽፍሮችህና ጣቶችህም ሰላም እላለሁ፡፡ ተአምር አድራጊው ሰማዕት ሆይ! ደረቁን ምሰሶ ለምለም ተአምራትህን ገልጸሃልና፡፡ ከጽኑ መከራ በጸሎትህ አድነኝ፡፡ ሰውስ ለሥቃይ የሚዳርጉ ረኀብ ቸነፈር ከእሱ ይፈልቃሉና፡፡ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም "ብድብድ" የሚለው ረኀብ፤ ቸነፈር ተብሎ ይተረጎማል፡፡
+ የተሐድሶ መናፍቃኑ እንደ ሚሉት ‘ተቅማጥህ እንደ ስቅላቴ ደም ነው’ የሚል ሐረግም ከገድሉ ላይ አይገኝም፡፡ “… እሷንም እንደ ስቅላቴና ካንተ በፊት እንደ ነበሩ ሰማዕታት ደም እቆጥርልሃለሁ፤” [ዝኒ ከማሁ(Ibid)] ነው ያለው፡፡ ይህም ማለት የተክለ ሃይማኖት ሕማም ከሰማዕታት ደም ጋር እኩል እንደሆነ እንጂ ከክርስቶስ ደም ጋር እኩል እንደሆነ አያስረዳም፡፡
ይህም የሆነበት ምክንያት ከገድሉ ላይ እንደምንረዳው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባ ተክለ ሃይማኖት ብዙ ተጋድለሃል ከእንግዲህ ይበቃሃል ነፍስህ ከመከራ ተለይታ ወደ እረፍት መሄጃህ ጊዜ ደርሷል ባላቸው ጊዜ አባ ተክለ
ሃይማኖት በሰማዕትነት እንድሞት አድርገኝ ብለው ስለለመኑት ነው፡፡ + በሚሞቱበት ጊዜ የሚደርስባቸውን ሕማም እንደ ራሱ መከራና በጦር ተወግተው በስለት ተቆርጠው ደማቸው እንደ ፈሰሰው ሰማዕታት ደም ሲቆጠርላቸው ነው፡፡ ሰማዕታት ለክርስቶስ ሲሉ በጦር ተወግተው በስለት ተቆርጠው ደማቸው እንደሚፈስ አባ ተክለ ሃይማኖትም ለክርስቶስ ሲሉ ሃገር ለሃገር ጫካ ለጫካ ሲንከራተቱ ሕማመ ብድብድን (ቸነፈርን) በጦር ተወግተው ደማቸው እንደፈሰሰው ሰማዕታት ቆጠረላቸው፡፡ ስለዚህ የአባ ተክለ ሃይማኖት ሕማመ ብድብድ (ቸነፈር) እንደ ሰማዕታት ደም ሆኖ ቢቆጠር ሃይማኖት ላለውና ለሚያስተውል ሰው አያደንቅም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot

👍2
ገድሉ ተአምራቱ
@And_Haymanot
ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
አዝ ------------------
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
አዝ ---------------------
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
አዝ -----------
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው አቡዬ
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት
አዝ -----------------
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ
አዝ ------------------
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
አዝ ------------------
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
አዝ ---------------------
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
አዝ -----------
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው አቡዬ
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት
አዝ -----------------
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ
አዝ ------------------
@And_Haymanot
@And_Haymanot
👍5🕊1
ገድለ ተክለሃይማኖት ፫
@And_Haymanot
ጥያቄ ፫
፫. “ከሩቅም ከቅርብም ቢመጣ ወደ መቃብርህ የሄደውን እኔ ወደ መቃብሬ ኢየሩሳሌም እንደ ሄደ አደርገዋለሁ፤ በመታሰቢያህ ቀን ሥጋውን ደሙን የተቀበለውንም ስማቸው ከተጠራው ገድላቸው ከተነገረው ልጆችህ ጋራ እኔ እቈጥረዋለሁ፡፡” [ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፯፤ ገጽ. 193] ማለት ምን ማለት ነው?
+ መልስ፡- ወደ መቃብርህ የመጣውን ወደ መቃብሬ እንደመጣ አደርገዋለሁ ማለት በአንተ አማላጅነት በእኔ በርነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ማለት ነው፡፡ ይህም እናንተን የተቀበለ
እኔን ተቀበለ ያለው የወንጌል ቃል በተግባር ሲተረጎም ነው፡፡ + በተክለ ሃይማኖት በመቃብር ላይ በተክለ ሃይማኖት ስም በተሠራው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደ ሚገኝበት በመምጣት በመጸለይ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ነው፡፡ የእግዚአብሔር በረከት ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ ዋጋ እንደሚገኝም መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ 2ኛ.ነገ.5፡1፤
ዕብ. 11፡23፤ ሩት. 1፡16-18፡፡
+ “በመታሰቢያህ ቀን ሥጋውን ደሙን
የተቀበለውንም ስማቸው ከተጠራው ገድላቸው ከተጻፈው ልጆችህ ጋር እኔ አኖራቸዋለሁ፡፡” የሚለውም ቃል የኢየሱስ ክርስቶስን መግቢያ
በርነት የበለጠ ያስተምራል እንጂ
አያስቀርም፡፡ በአንተ መታሰቢያ
ዕለት የእኔን ሥጋና ደም ተቀብሎ በአንተ አስተማሪነት በእኔ በርነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ማለት ነው፡፡
፬ የመናፍቃን ጥያቄ ከገድለ ተክለሐይማኖት ውስጥ: "እባብን የገደለ ይጽድቃል" ይላል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሁሉ እባብን እየፈለጉ ለመጽደቅ እባብን መግደል አለባቸው ወይ የሚል ነው። አይ ይህቺ የመናፍቃን ጭንቅላት ትንሽ ብትሰፋ! ወገኖቼ መጸሐፍ ቅዱስ እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል መግባት ነው ይላል:: አንዱ ብርሃን መሆን አለበት:: ዛሬ ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ታውረዋል፡፡ አባታችን ተክለ ሐይማኖት ይፈውሱዋቸው አሜን :: ወገኖቼ እባብን የገደለ ይጸድቃል ማለት እባብ የተባለ ዲያቢሎስ ነው:: ለምሳሌ ያህል በመዝሙር ምህራፍ 73 ቁጥር 14 እንዲህ ይላል “አንተም የዘንዶውን እራስ ቀጠቀጥክ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው፤” ይላል :: ታዲያ አንተ የዘንዶውን እራስ ቀጠቀጥክ
ሲል ታዲያ እግዚአብሔር ዘንዶ ያለበትን እየሔደ እራስ እራሱን ቀጠቀጠው ማለት ነውን? አይደለም :: ዘንዶ የተባለው ሰይጣን ነው:: ሰይጣንን ደግሞ እግዚአብሔር በመስቀሉ
ቀጥቅጦታል :: እንዲሁም ገድለ ተክለ ሐይማኖት ላይም እባብን የገደለ ይጽድቃል ሲል ሰይጣንን የገደለ ይጸድቃል ማለቱ ነው :: ሰይጣንን የምንገለው ደግሞ በጾም በጸሎት እና በስግደት ነው:: በነዚህ እባብ (ዲያቢሎስን ) መግደል እንችላለን:: በተጨማሪም ደግሞ ራእይ ዮሐንስ ምህራፍ 12 ቁጥር 7 እንዲህ ይላል፡- “በሰማይም ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና ሰራዊቱ ዘንዶውን ተዋጉት :: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙን ሁሉ የሚያስት ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፡፡ ወደ ምድርም ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ፤” ይላል:: ታዲያ ሚካኤልና ቅዱሳን መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ ሲል ከእንስሳ ጋር ተዋጉ ማለት ነውን? አይደለም፡፡ ዘንዶ የተባለው የቀደመው ሰይጣን እርሱ ዲያቢሎስ ነው ይለናል:፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
---------ልቦናን ያድልልን -----------
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡

❤1👍1
➕➕➕እንኳን ለ ለብርሃነ ልደቱ ፤ በሰላም አደረሳችሁ።➕➕➕
"በጎል ሰከበ አፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ"
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቅለለ፡
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ
🕯🕯📖📖🕯🕯
📖📖📖
" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
(ኢሳ 7: 14)
📖📖📖
" እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።"
(ማቴ 1: 23)
📖📖📖
" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር" ኃያል "አምላክ" የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ኢሳ 9: 6)
መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ:)

👍1
✝ኃጢአትን ለንስሓ አባት/ለካህን መናዘዝ/
@And_Haymanot
ተወዳጆች የተሀድሶ መናፍቃን ምዕመናንን ከንስሃ ህይወት ለማራቅ ሃጢአትን ለንስሃ አባት መናዘዝ አያሥፈልግም በማለት ሀጢአትን ለካህን መናዘዝን ይቃወማሉ፡፡ እናት ቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታሥተምራለች
@And_Haymanot
ካህን የእግዚአብሔር ምሥጢራት አስፈፃሚ ስለሆነ ኃጢአትህን ንገረው ። ይህን ቅዱስ ጳውሎስም አስረግጦ ጽፎልሃል ። " እንዲሁ ሰው እኛን እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቁጠር ።" 1ቆሮ 4*1
አስቀድሞም በነቢዩ ሚኪያስ ያደረው እግዚአብሔር ሲናገር "ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነው "ይላል ።
ኃጢአትህን ለካህን በምትነግርበት ጊዜ የሚሰማህን ኃፍረት መሸማቀቅ ሁሉ ችለህ የመመለስን ምሥጢር እንዲያስፈጽምልህ ስትጥር እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ድርጊትህን እንደ ታላቅ መሥዋእትነት ቆጥሮልህ ኃጢአትህን ሁሉ ይደመስስልሃል ።/ ዩሐ 20*21*23/ ማቴ 18*18
ካህኑ ክርስቶስ በሰጠው በዚህ ሥልጣን መሠረት ከኃጢአት እሥራት መፈታትህን ያረጋግጥልሀል ። ሕይወት ለሚሆነው ሥጋና ደሙ እንድትበቃም ያደርግሃል ።/1ቆሮ 11*27/
በሕይወትህ ውስጥ የሚታዩትን ጉድለቶች (መንፈሳዊ ድክመቶች )እየተመለከተም እንዴት አሸናፊ መሆን እንደምትችል የሚመክርህ መንፈሳዊ መሪህ ካህን የንስሓ አባት መሆኑንም አትዘንጋ ።
ለካህን ኃጢአትን መናዘዝህ በራሱ የሚያተርፍልህ ነገር አለው ። ኃጢአትን መልሰህ ስትናገረው ለአንተ ለራስህ ምን ያህል አሳፋሪ እንደሆነ ይሰማሃል ። ይህም ዳግም እንዳትመለስበት ታላቅ ትምህርት ይሰጥሀል ። መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው ይህንኑ ነው ። " እርስ በእርሳችሁ ኃጢአታችሁን ተናዘዙ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ሰው ስለሌለው ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ።" /ያዕ 5*16 /
ምንጭ @pope_shenouda
@pope_shenouda
___፩ ሃይማኖት_______
ላልደረሳቸው እናዳርስ
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን
@And_Haymanot
#______አትታደስም______!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
============================
፩ ጌታ
፩ ሃይማኖት
፩ ጥምቀት ኤፌ4:5

👍6
ሰበር ዜና
ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ መላው ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት በደሉን ለዓለምዓቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚገልጽ አስታወቀ።

❤4👍1
#እናስተውል‼
በሆነው እና በሚሆነው በጎ ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ከማመስገን በቀር "እኛ እኮ እንዲህ ነን!" የሚል ግብዝነት ክርስቲያናዊ አይደለምና 'ራሳችንን እናርቅ!!
#እግዚአብሔር_ይመስገን!!
©Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

❤1
ከእንግዲህ ቤተ ክርስቲያን ችግር ሲገጥማት ጠብቀን የምንሰበሰብባት ስፍራ አትሆንም !!! በጊዜውም ያለ ጊዜውም በደጇ እንፅና !!!ሊያጠፏት የሚፈልጉ ጠላቶች እንዳሏት ካወቅን የኛ ድርሻ ከደጇ ባለመጥፋትም ፣ በፀሎትም ፣ በአንድነትም ፣ በመናበብም ፣ ባለመዘናጋትም ፥ ተጠናክከረን ከአጥፊዎቿ ተሽሎ መገኘት ነው።
©Belay
@And_Haymanot
©Belay
@And_Haymanot
❤1
"ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡
ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ፡፡ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደኾነ አስተውል፡፡ እንዴት? ያልከኝ እንደኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል፡፡ የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቅኸው ማለት
ክርስቶስን ናቅኸው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከኾነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ሐሞትን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም፡፡ ስለዚህ ወንድምህን እኅትህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ

Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ሃያል ነህ አንተ
ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል /2/
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት /2/
በዱራ ሜዳ ላይ........ገብርኤል
ጣዎት ተዘጋጅቶ.......ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ.......ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ.......ገብርኤል
ሲድራቅና ሚሳቅ አብናጎም ፀኑ
ጣዎቱን እረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ተቆጣ ንጉሡ.......ገብርኤል
በሶስቱ ሕፃናት .......ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ.......ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት.......ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መልአኩ
ከሞት አዳናቸው እሳት ሳይነኩ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
እቶኑ ስር ሆነው........ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ........ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው.......ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ.......ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር
አዩ መኳንንቱ የእግዚአብሔር ክብር
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ናቡከደነጾር........ገብርኤል
እጁን በአፋ ጫነ.......ገብርኤል
ሠለስቱ ደቂቅን........ገብርኤል
ከእሳት ስላዳነ.......ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከው መልአኩን
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን.
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንኳን አደረሳችሁ
ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል /2/
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት /2/
በዱራ ሜዳ ላይ........ገብርኤል
ጣዎት ተዘጋጅቶ.......ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ.......ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ.......ገብርኤል
ሲድራቅና ሚሳቅ አብናጎም ፀኑ
ጣዎቱን እረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ተቆጣ ንጉሡ.......ገብርኤል
በሶስቱ ሕፃናት .......ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ.......ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት.......ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መልአኩ
ከሞት አዳናቸው እሳት ሳይነኩ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
እቶኑ ስር ሆነው........ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ........ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው.......ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ.......ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር
አዩ መኳንንቱ የእግዚአብሔር ክብር
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ናቡከደነጾር........ገብርኤል
እጁን በአፋ ጫነ.......ገብርኤል
ሠለስቱ ደቂቅን........ገብርኤል
ከእሳት ስላዳነ.......ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከው መልአኩን
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን.
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንኳን አደረሳችሁ
👍35❤27
"የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል" ሐዋ 2፡21
@And_Haymanot
ይህ ቃል አስቀድሞ በትንቢተ ኢዩኤል ም 2 ላይ "የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል " ተብሎ የተገለጠው ነው፡፡ ቃሉን ዝም ብለን ስናየው በቃ በመጥራቱ
ብቻ ሰው ይድናል የሚል ይመስላል፡፡/በመጥራት ብቻ ይዳናል ከተባለ አህዛቡም የማያምነውም የሚያምነውም በክፋም በደጉም ይጠራዋል ስለዚህ ሁሉም ይድናል ያስብልብናል / የመጽሐፍቃ ል እንደ ሰንሰለት የተያያዘ ስለሆነ እስቲ ምን ማለቱ እንደሆነ እንይ፡፡ ከቃሉ ጋር ተያይዞ የሚነሣ ትልቁ ጥያቄ ስሙን እንዴት ብንጠራ ነው የምንድነው? የሚለው ነው፡፡ በማወቅ ነው ባለማወቅ?
በትህትና ነው በትዕቢት? በማመን ነው ባለማመን? መልሱን ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ መልሶታል ሮሜ ም10 ቀ1-4 እና ሮሜ. ም 10 ቁ 13-16 ሙሉውን ምዕራፍ 10
እናንተ አንብቡት 1-4 " ወንድሞች ሆይ፥ የልቤ በጎ ፈቃድና ስለ እስራኤል ወደ
እግዚአብሔር ልመናዬ እንዲድኑ ነው። በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና። የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥
ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ
ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። --------------"
13-16 "የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና። እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ? መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ
ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ? ነገር ግን ሁሉ ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ ጌታ ሆይ፥ ምስክርነታችንን ማን አመነ? ብሎአልና። እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም
በእግዚአብሔር ቃል ነው። " ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እስራኤል ዘሥጋ የጻፈው ነው፡፡ ቁጥር 13 ላይ የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል ካለ በኋላ እንዴት የሚጠራ የሚለውን አብራርቶታል እርሱን እንይ፡፡ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? የሚለው ጥያቄ በእምነት የሚጠሩት የሚድኑ መሆኑን ይገልጥል፡፡ ለማመን ደግሞ ምን ያስፈልጋል?
የሚለውን ሲመልስ እንዲህ ብሏል መስማት ይላል፤ ይህም ማለት ሁሉን አዋቂ ነኝ ብሎ በራስ ፍልስፍና መጻሕፍትን ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ ከእግዚአብሔር ከተላከ ሰባኪ
መስማት ይጠይቃል ብሎ አስቀምጦታል (ምሳሌ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የሐዋ. 8፡34 እንዲሁም 2ኛ ጴጥ. 1፡21)፡፡ ሲጠቀለል ሰው ሲማር ያውቃል ሲያውቅ ያምናል ያመነውን አምላኩን በእምነት ሲጠራው ይድናል የሚል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ማመን ብቻ አያድንም እንዲህ ተብሎ ተጽፎልና "አጋንንት ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል" ያዕ 2፤19 እንግዲህ ሰዎች በማመን ብቻ እንድናለን ስለምን ይላሉ? እምነታቸውን ከአጋንንት የሚለየው በእምነት ውስጥ ያለውን ህግ
መፈጸማቻው አይደለምን? ሰለዚህ ያዕቆብ እነዲህ ይላል ም2 ቁ20 "እምነት ያለሥራ የሞተች ናት" ይላል ከላይ ያየነውን የሚያጠነክሩ ጥቅሶች አንይ በዮሐ. 17፡3 “እውነተኛ አምላክ የሆንኽውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘላለም ሕይወት ናት፡፡" በዚህ
አምላከዊ ቃል መሰረት እግዚአብሔርን ማወቅ በራሱ የዘላለም ሕይወትን ያሰጣል፡፡
ግን ሰው እግዚአብሔርን ማወቁ በምን ይታወቃል? ቅዱስ ዮሐንስም በመልእክቱ 1ኛ ዮሐ. 2፡3 "ትእዛዛቱን ብንፈጽም እርሱን ማወቃችንን በዚህ እርግጠኞች እንሆናለን፡፡ እርሱን አውቃለሁ እያለ ትእዛዛቱን የማይፈጽም ግን ሐሰተኛ ነው
እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም፡፡ ነገር ግን ማንም ቃሉን ቢጠብቅ በእውነት የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ ፍጹም ሆኗል፡፡" ትእዛዛቱን የማይፈጽም እግዚአብሔርን አያውቅም ይላልና ከላይ
እንዳልንው ሰው ለመዳን አውቆ አማኖ ነው መጥራት ያለበት ብለናል፤ ስለዚህ ትእዛዛቱን ሳይጠብቅ አውቀዋለሁ ቢል ሀሰተኛ ከሆነ፤ ትእዛዛቱን ሳይጠብቅ ስሙን ጠርቼ እድናለሁ ቢል ……….
ከላይ ባየነው በሮሜ መልእክትም ስለ እስራኤል ቁ 2-4 "በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ
እመሰክርላቸዋለሁና። የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።" ይላል ይህም እስራኤል ለእግዚአብሔር ጽድቅ ባለመገዛታቸው እውቀታቸው የጎደለ መሆኑንና ክርስቶስ
ካለማወቃቸውም የተነሳ የእግዚአብሔር ፈቀድ ሳይሆን የራሳቸውን ጽድቅ ሊያቆሙ ይወዳሉ፡፡ ነገር ግን የሚያምን ሁሉ የጸድቅ ዘንድ የክርስቶስን የባህሪ አምላክነት መረዳትና ማወቅና
ማመን እና ፈቃዱን መፈጸም ይጠይቃል፡፡ አንድ ሌላ ከላይ ያየንውን ማጠንከሪያ እንጨምር ማቴ. 7፡21
"በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥
ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።" ይላል፡፡ ከላይ ያየነውን ሁሉ የሚያስርልን ኃይለ ቃል ነው፡፡ ስሙን የሚጠራሁሉ አይድንም፡፡ የሚድነው ትእዛዛቱን እየጠበቀ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እነደሆነ ተረድቶ እያደረገ ቅዱስ ሕያው ዘላለማዊ ስሙን በትዕቢት ያይደለ በትህትና፤ በጥርጣሬ ያይደል በእምነት፤ በክፋት ያይደለ በበጎነት፤ በድፍረት ያይደለ በፍርሀት፤ የሚጠራ ሁሉ ይድናል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔርን አወቅን የሚባለው ፈቃዱንም
ስናውቅና ስንፈፅም ነው፡፡ ፈቃዱ ምንድነው? ሁሉ ይድኑ ዘንድ ነው፤ ሰይጣን የሰው ልጆችን ለመጣል በብዙ ጎዳና ያጠምዳል እግዚአብሔር ደግሞ የሰው ልጆች ይድኑ ዘንድ ብዙ የመዳን
መንገዶችን ከፍቷል ኃጢአቱን አምኖ ንስሐ የሚገባ ልብ ላለው በቅዱሳን ቃልኪዳን በቅዱሳን ምልጃ በመላእክት ተራዳኢነት በጾም በጸሎት በምጽዋት ሊያድን የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው፡፡
ለማየምኑት ለሁሉም ጥቅስ መስጠትና ማብራራት እንደሚጠይቅ አምናለሁ ግን አሁን ከተነሣንበት ጭብጥ አንጻር ለማስረዳት የተፈለገው ግልጽ ስለሆነ የዚህ ማብራሪያ ካስፈለገ
በሚቀጥለው እጽፋለሁ፡፡
ከላይ ያየንው ባጭሩ የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል፡፡ ሮሜ10፤13-16 መጽሐፍን ከሚያውቁ መምህራን ተምሮ አውቆ አምኖ በመጥራት
ጌታን ማወቅ ራሱ የዘላለም ሕይወት ነው ዮሐ17፤5 ግን አውቀዋለሁ እያለ ትዕዛዘቱን የማይጠብቅ ደግሞ ሀሰተኛ ነው፡፡ 1ዮሐ2፤3 ማመንስ አጋንንት ያምናሉ ስሙንም እንደጠሩ በመጽሐፍ
ተጽፏል፡፡ ስለዚህ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል አጠራሩ ግን ከአጋንንት አጠራር የሚለየው እምነቱን ሙሉ የሚያደርግለት ሥራ ስላለው ነው፡፡ ያዕ2፤19-20 (እምነት ያለ ሥራ የሞተች ከሆነች፤ ሥራ ያለባት እምነት ሕያው ናት ነፍስ እነዳለው ስጋ)፡፡ ስለዚህ አንዲህ ብሎ መናገር ይቻላል ሕያው እምነት ይዞ
የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፡፡
ይቆየን
ኦሮቶዶክስ መልስ አላት፡፡

🙏5❤2👍2
👉ሃይማኖት ምንድነው?
👉ሃይማኖት ያድናል ወይስ አያድንም????
👉 ሃይማኖት ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም ???
👉ሃይማኖት ይወረሳል ወይስ አይወረስም???
✏️@And_Haymanot
ሃይማኖት፦ የሚለው ቃል ሃይመነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ነው።ትርጉሙም ማመን፣መታመን፣አማኝነት፣አመኔታ
ማለት ሲሆን መቀበል ተስፋ ማድረግ ፣አለመጠራጠር፣ያዩትን እና የሰሙትን እንዲሁም ያመኑትን እውነት በማያምኑት ፊት መመስከር ማለት ነው። ሮሜ 10÷9 ቆላ2÷6-7 የሐ 14÷1
* ሃይማኖት ምንጩና ባለቤቱ ኃያሉ አምላካችን እግዚአብሔር ነው።
👉 ሃይማኖት የሰው ልጆች ከእውቀት ማነስ ወይም ከፍርሃትና ከድንጋጤ ያመጡት አይደለም።ከፍልስፍና እን
ከመራቀቅም የተገኘ ሳይሆን እግዚአብሔር ለቅዱሳን የሰጣቸው
ውድ ስጦታ ነው። ይሁዳ 1÷3
👉 ሃይማኖት አንዲት ናት። ሁለተኛና ሦስተኛ የላትም።ፈጣሪና ፍጡራን የሚገናኙባት ረቂቅ መንገድ ናት። ኤፌ፡ 4÷5 ; ት.ኤር 6÷16; ማቴ. 7÷13-14
ሃይማኖት ሲባል ሰዎች የፈጠሩት ሳይሆን እግዚአብሔር በራሱ ፍቃድ እናውቀው ዘንድ ስለ ራሱ የገለጠው መገለጥ ነው።ስለሆነም ሃይማኖት እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ያሳየበት
መንገድ እና የሰው ልጅ ሊቀበለው በሚችለው መጠን ስለ ራሱ ማንነት ለእኛ የገለጠው እውነታ ነው።ስለዚህ ከዚህ እውነታ በመነሳት
👉(1ኛ) ሃይማኖት ያድናል ወይስ አያድንም????
👉(2ኛ) ሃይማኖት ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም ???
👉(3ኛ) ሃይማኖት ይወረሳል ወይስ አይወረስም ለሚሉ ጥያቄዎች የማያዳግም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መልስ እንሰጥበታለን።
✍ (1ኛ) በአንዲት እውነተኛ ሃይማኖት ውስጥ ያለ አንድ ሰው እና ምንም ሃይማኖት የሌለውን ሌላ ሰው ብናነፃፅር የመዳን ወይም እግዚአብሔርን የማወቅ ሰፊ እድል ያለው የትኛው ሰው ነው????? ስለዚህ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዲት ተብላ የተጠቀሰችው ሃይማኖት ሰዎች ከተጠቀሙባት መዳን በውስጧ አለ ታድናለች።ምክንያቱም የእግዚአብሔር አንድነትና ልዩ የሦስትነት ሚስጥር፤ጌታችን አምላካችን አባታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ፤የመስቀሉ ድንቅ ሥራው እንዲሁም እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ የገለጠበት ዋና መንገድ
ሃይማኖት በመሆኑ ሰው ለመዳን የግድ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ በተሰጠች ሃይማኖት ውስጥ ገብቶ ትምህርት ሃይማኖትን
መማርና ማወቅ አለበት።ካልተማረ የእግዚአብሔርን መኖርና የእግዚአብሔርን ፍቃድና አላማ እንዴት ያውቃል ??? ካላወቀ እንዴት ያምናል ???? ካላመነ እንዴት ሊድን ይችላል ???
ለዚያ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደተቀበላችሁ በእርሱ ተመላለሱ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነፁ እንደተማራችሁም በሃይማኖት ፅኑ ምስጋና ይብዛላችሁ።ቆላ፡ 2÷6-7
ስለዚህ ሰው በሃይማኖት መኖር አለበት።በሃይማኖ መኖር ብቻም አይደለም።ሃይማኖት የሚያዘውን ትዕዛዝ እየፈፀመ መኖር አለበት።ለዚያ ነው በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ
በብርቱ ውቀሳቸው ተብሎ የተፃፈው።ቲቶ 1÷13
* ሃይማኖትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።ተብሎ የተፃፈውም ሰው ሃይማኖቱን የሚከዳ ወይም በሃይማኖት የማይኖር ከሆነ ሊድን እንደማይችል የሚያስረዳ ቃል
ነው። 1ኛ ጢሞ 5÷8 ምክንያቱም ሃይማኖትን መካድ ወይም ከሃይማኖት መውጣት ከማያምን ሰው ይልቅ የሚከፋ ከሆነ በሌላ አነጋገር ሃይማኖትን የሚከዳ ሰው አይድንም ወይም ከማያምን ሰው ይልቅ ተጠያቂ ይሆናል ማለቱ እንደሆነ ማወቅ አለብን።
**** የፅድቅ አክሊል ከሚያጎናፅፈን አንዱ እና ዋናው ሃይማኖትን መጠበቅ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ
ተናግሯል፦ መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፣ሩጫውን ጨርሻለው፣ሃይማኖትን ጠብቄያለሁ።ስለዚህ የፅድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ይላል። 2ኛ ጢሞ 4÷8
✍(2ኛ) ሃይማኖት ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም????? መናፍቃን እና ተሐድሶዎች ፓስተሮቻቸውም ጭምር ሃይማኖት አያስፈልግም ሲሉ እንሰማቸዋለን።ለመሆኑ ሃይማኖት
የማያስፈልግ ከሆነ ለምን የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይሆኑ ??????
ለምንስ ከአንዱ ሃይማኖት ወደ ሌላው ሃይማኖት ይዟዟራሉ ???????
ሃይማኖት የማያስፈልግ ከሆነ ለምን የማንም ሃይማኖት ተከታይ
ሳይሆኑ አይኖሩም ነበር ??????
* ሲጀመር በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማያስፈልግ ነገር አይፃፍም።ቅዱስ ጳውሎስም ሃይማኖት በጣም አስፈላጊ መሆኑን ስለሚያውቅ ብዙ ቦታ ላይ ስለ ሃይማኖት ሰብኳል።ለምሳሌ በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ።2ኛ ቆሮ፡ 13÷5
* ንቁ በሃይማኖት ቁሙ።1ኛ ቆሮ 16÷13
* አንዲት ሃይማኖት ኤፌ 4÷5
*** ሃይማኖትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው። 1ኛቲሞ 5÷8 እያለ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሃይማኖት አስፈላጊነት የሰበከውን ስብከት መናፍቃን ደግሞ ሃይማኖት አያስፈልግም እያሉ የሚዘባርቁት የትኛው መፅሐፍ ቅዱስ ላይ አንብበው
ይሆን ???
✍(3ኛ) ሃይማኖት ይወረሳል ወይስ አይወረስም ???የእውነት የሆነ ሃይማኖት ይወረሳል።ትውልድ አልፎ ትውልድ በመጣ ቁጥር ሃይማኖት ይወረሳል እንጂ እየታደሰ እየተፈጠረ አይሄድም።ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጣቸው ሃይማኖት
በትውልድ ቅብብሎሽ እኛ ዘመን ላይ ደርሳለች። አባቶቻችን ከሐዋርያት የተቀበሏት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ
ሃይማኖትን ለእኛ አውርሰውናል እኛ ደግሞ ለልጆቻችን እናወርሳቸዋለን፡፡
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
✍ ፩ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~Share~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~Share~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
Share~
የአበው ሃይማኖት
አትታደስም፡፡

👍7🙏4
እምነትህን በሥራ አሳይ
@And_Haymanot
ያዕ 2፥14-26
14 ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
15 ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥
16 ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
17 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
18 ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
20 አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?
21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
22 እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?
23 መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።
24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።
25 እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?
26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@And_Haymanot @And_Haymanot

🙏4❤3👍2