፩ ሃይማኖት
8.99K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ታቦት 1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር
#አንድ_አይደለም፡፡
📌📌📌📌📌 ይቀጥላል
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ታቦት 2
ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)
📌📌📌📌 ይቀጥላል
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ታቦት 3

በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡
📌📌📌📌 ይቀጥላል
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ተወዳጆች ስለታቦት በአጭር በአጭር ማቀረባችን ረጅም.... 'ጽሁፍ ታበዛላችሁ' ለሚሉን እንዲሁም መናፍቃን በብዛት በሚያነሱት ጉዳይ እና ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ጥሩ መረዳት እንዲኖረን በማሰብ ነውና ይህ አቀራረባችን የተመቻችሁ በቦቱ ( @And_Haymanot_bot ) አሳውቁን ሌሎች ርእሶችንም በዚሁ መልኩ አልፎ አልፎ እንቀጥላለን

___፩ ሃይማኖት ___
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
"ከሰማይ መስቀል፣ ጽዋ...መውረዱን በቅዱሳት ገድላት መገለጹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለምን???
@And_Haymanot
✞ ፩. የንዋያተ ቅድሳት መውረድ፤
እንደ ገድለ ቅዱስ ላሊበላና ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ባሉ ገድላት ላይ ከሰማይ መስቀል፣ ጽዋ...መውረዱ ተገልጧል።
አብርሃም በፍጹም ሃይማኖት መታዘዙን ይገልጥ ዘንድ አንድ ልጁን መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ እግዚአብሔር ሲፈትነው እርሱም "እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛሃለሁ።" ያለኝን ዘነጋውን? ወይንስ ተወው? ብሎ ሳይጠራጠር ልጁን ይዞ በቀረበ ጊዜ
እግዚአብሔር ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ የታሰረ ነጭ በግ እንደወረደለት ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል። ዘፍ.22፥3-19።
በሰማይ በግ የሚያረባ ኑሮ ነውን? በጭራሽ!! በአምላካዊ ተኣምር የተገኘ እንጂ። ለሙሴም እግዚአብሔር ሁለት ጽላቶችን የሰጠው ጸፍጸፍ(ሰሌዳ) ሰማዩን ከየት አምጥቶት ነው? ቢባል
በአምላካዊ ተኣምር መገኘቱን ከመግለጥ ያለፈ በምርምር
አይደረስበትም። ዘጸ.32፥1-16። ለእስራኤል ዘሥጋ የወረዳው መናም ይህንኑ አሳባችን ያስረግጣል። ዘጸ.16።
✞ አምላከ ቅዱሳን አምላካችን እግዚአብሔር እሱ ባወቀ ለእሥራኤል ዘሥጋ ከሰማይ ሥጋ ማውረዱን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል/ዘኁ.11፥1-34/። በሰማይ ቄራ ኖሮ ነው? በማኅበር የተደራጁ ሥጋ አራጅ ማኅበራት በሰማይ አሉ?
❖ ከሰማይ ሰው የሚበላውን ያውም ከአይሁድ ሰንበት/ ከቅዳሜ/ በቀር በየቀኑ ትኩስ፥ ትኩስ ሥጋ ከሰማይ እንደዝናብ ያዘነበ አምላካችንን ከየት አመጣኸው? ሳንል አምነን በፍጹም
ምስጋና ከተቀበልን ብርሃናዊ ቅዱስ መስቀል፥ ጽዋ...ከሰማይ ቢወርድ ከየት አመጣኸው? ልታደርገው አትችልም ሊለው የሚደፍር ማነው???
ከሰማይ ስለወረደው መስቀልና ጽዋ የሚጠይቁ ቢኖሩ ለነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ ከሰማይ እንጎቻና በማሰሮ ውኃ
ያወረደለትን እግዚአብሔር/1ኛነገ.12፥6/ በትክክለኛ እምነት ሆነው በጸሎት ቢጠይቁት ይገልጥላቸዋል።
እነዚህን ለመሰሉ ነገሮች ሁሉ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን "ከግብር አምላካዊ ተገኙ።" ትላለች። ይህም ስለ ጽላቶቹ "... ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም በጽላቶቹ ላይ የተቀረጸባቸው
የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።" ዘጸ.32፥16 የሚለውን መሠረት
ያደረገ ነው።

✞ ፪. የሰንበት መናገር፤
❖ በድርሳነ ሰንበትና በቅዳሴ አትናቴዎስ እንዲሁ በሰዓታቱ ላይ ሰንበተ ክርስቲያን እንደምትናገር መገለጹ አንዳንድ ሰዎችን
ያሳስባቸዋል ። ሰንበት አካል የላት/እጅ፣ እግር፣ አፍ፣ ...የላት/ እንዴት? የሚል ጥያቄ የሚፈጥርባቸውም አልጠፉም።
በመጀመሪያ እንደ ሰንበት ያሉ ረቂቃን አካላትን በሰውኛ ዘይቤ መግለጽ በጥንት መጻሕፍት ዘንድ የተለመደ ነው።
(Personification) ይሉታል። በአይሁድ ጥንታዊ መጽሐፍ በታልሙድ "ረቢ ሐኒና በሰንበት ዋዜማ ፀሐይ በምትገባበት ጊዜ እንዲህ አለ፤ ኑ ንግሥት ሰንበትን እንቀበላት ዘንድ እንሂድ፤ ሙሽራዬ ሆይ ነይ ሙሽራዬ ሆይ ነይ።" እንደሚል ተመዝግቧል
[The Babylonian Talmud, seder mooed sabath II,
London 1938, P.588]።
ከሥነ ፍጥረት ምሥጢር አንጻር ስንመለከተው ደግሞ ዕለታት የሁለት ፍጥረታት አንድነት ናቸው። የጨለማና የብርሃን። ጨለማና ብርሃን ሁለትነታቸው ሳይቀር በአንድነት ቀን ወይንም
ዕለት ይባላል። ስለዚህ ስለ ሰንበት መናገር ማለት የእነዚህን የሁለቱን አንድነት መናገር ማለት ነው። ይህም የነፍስን ነባቢነት ከሥጋዊ ብልት(ከሰውነት ክፍል) ከአፍ ከምላስ ጋር ተዋሕዶ እንደሚገለጠው ያለ ነው። ይህም ተዋሕዷቸውን ለመናገር
እንጂ ግዘፍ አካል አላቸው ለማለት አይደለም። ፍጥረት እስከ ሆኑ ድረስ ደግሞ ለፈጣሪያቸው ይናገራሉ መልስም ይሰጣሉ። እኛ ለምን አልሰማናቸውም ሌላ ጥያቄ ነው። ፍጡር ለፈጣሪው
የማይመልስ ከሆነ ችግሩ የፍጥረቱ ሳይሆን የፈጣሪ ነው ወደ ማለት ጥልቅ ክህደት ውስጥ ያስገባል። ሎቱ ስብሐት(ለእርሱ ክብር ይግባው)ና ፈጣሪያቸው እንዳያውቁት አድርጎ ፈጥሯቸዋል ያሰኛል።
ለእርሱ ክብር ምስጋና ይግባውና እርሱ የፈጠረው ሁሉ ምሉዕ ስለሆነ "መልካም እንደሆነ አየ፤" ተብሎ ተገልጿል።
ዘፍ.1፥1-22። ስለዚህ ሰንበት ልትመሰክር ትችላለች። ቋንቋው
ግን በልሳነ ሰብእ(በሰው ቋንቋ) ላይሆን ይችላል። ጌታችን በተሰቀለበት ዕለት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ መሬትና መቃብር የመሰከሩት በሰው ቋንቋ ሳይሆን ለሰው በታወቀ በተረዳ ተኣምር
እንደሆነው ሁሉ የሰንበትም እንደዚሁ ይሆናል። በቅዱስ መጽሐፍ መሬትና ውኃ ፍጥረታትን እንዲያወጡ ሲታዘዙ ሰምተው ፈጽመዋል። የሰውን ጆሮ የመሰለ ጆሮ ግን አልነበራቸውም።
ከእርሱ ለሚወጣው ቃል ስለ ፈቃዱም የሚታዘዙና የሚመልሱ ሆነው ለራሳቸው በሚስማማ ጸጋ ከብረው ተፈጥረዋልና። ቅዱስ ዳዊትም "አቤቱ ውኆች አይተውህ ፈሩ።" /መዝ.76፥6/ ያለው
አምላካቸውን ዐውቀው መታዘዛቸውን ለመናገር እንጂ የሰውን የመሰለ ዓይነ ሥጋ አላቸው ለማለት እንዳልሆነ የታወቀ ነው። ከዚህ አንጻር ሰንበት ትናገራለች።
"ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።" መዝ.113፥3 ሲል ባሕር የምታይበት እንደ ሰው ዓይን አላት? የዮርዳኖስ ወንዝስ ወደ ኋላው የተመለሰው እንደ እኛ እግር
ኖሮት ነው? "መልሶም። እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች
ይጮኻሉ አላቸው።" ሉቃ. 19፥40። መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የቢታንያ ድንጋዮች እንደሚጮኹ ሲናገር ድንጋዮች እንደ ሰው ልሳን፥ አፍ አላቸው ማለቱ ነውን? ለእኛ ለፍጡራን ድንጋይ
ግዑዝ በድን አካል ቢሆንም ለፈጣሬ ዓለማት ለቅድስት ሥላሴ ግን እሱ ባወቀ እንዲናገሩ ያረጋቸዋል፥ ሥራም ያሰራቸዋል።

✞ አካል ስለሌላት አትናገርም ማለት አካል ሳይኖራት እንዴት አከበራት ብሎ እግዚአብሔርን እንደ መተቸት ይሆናል።
"እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።" ተብሎ
ተጽፏልና። ዘፍ. 2፥3።
፠ በአጠቃላይ ገድላትን በሚገባ ለመረዳትና በገድልና በትሩፋት
የኖሩትን አበውና እማትን/እናቶችን/ ሃይማኖትና ምግባር መያዝ፤ በመንገዳቸውም መጓዝ ተገቢ ነው። ያለበለዚያ የይመስለኛል እምነት መድረሻው ክህደት፤ የክህደትም መደምደምያው ሞት ነው።
by ዘማርያም ዘለቀ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
"ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡
ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ፡፡ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደኾነ አስተውል፡፡ እንዴት? ያልከኝ እንደኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል፡፡ የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቅኸው ማለት
ክርስቶስን ናቅኸው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከኾነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ሐሞትን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም፡፡ ስለዚህ ወንድምህን እኅትህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
​​ገድሉ ተአምራቱ

@And_Haymanot

ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው 
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው 
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ 
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ 
አዝ ------------------ 
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ 
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ 
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ 
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ 
አዝ --------------------- 
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት 
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት 
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ 
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ 
አዝ ----------- 
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው አቡዬ 
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ 
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት 
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት 
አዝ ----------------- 
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት 
ጥላህ ያረፈበት ሆንዋል ጸበል እምነት 
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ 
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ 
አዝ ------------------
@And_Haymanot
@And_Haymanot
† በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል ላይ የሚነሱ
አንዳንድ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
--------------
በዲያቆን ቴዎድሮስ
👇👇👇
@And_Haymanot
ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፩

@And_Haymanot
ጥያቄ ፩
ገድለ ተክለ ሃይማኖትላይ ‘ሰይጣንን አጠመቁት’ ይላል እያሉ የተሐድሶ መናፍቃን ይተቻሉ፡፡ እውን ግን ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በቁሙ ሰይጣንን አጥምቀዋልን?

መልስ፡- በቀድሞ መጻሕፍት ሥጋ ለበስ የሆኑ አጋንንት ታሪክ የታወቀ ነው፡፡ እነዚህ ሥጋ ለበስ አጋንንት የአጋንንትን ሥራ የሚሠሩ ቢሆኑም
የሚዳሰስ ሥጋ ግን አላቸው፡፡ ለምሳሌ ድርሳነ ሚካኤል ዘጥር ላይ እንደ ተገለጠው እነዚህ በሽታዎችን ሁሉ የሚያመጡ ሥጋ ለበስ አጋንንት
እንደ ሰው ሁሉ ይታመማሉ፤ ይራባሉ፤ ይሞታሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በበረሐ ውስጥ አንዳንድ ጊዜም በውኃ ውስጥ ይኖራሉ፡፡

+ በገድለ ተክለ ሃይማኖትና በልደተ አበው ላይ እንዲህ ይላል “አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእነዚህ አውራጃዎች ሲመላለስ አንድ ቀን በውኃ ዳር ዐረፍ አለ፡፡ ጋኔንም ከውኃው ወጣና ደቀ መዛሙሩን ያዘው፡፡ አሳመመውም፡፡ እርሱም ጋኔን መሆኑን ዐወቀ፡፡ በረድኡ ላይም በመስቀል ምልክት አማተበበት፡፡ ጋኔኑም ፈጥኖ ወጣ ሸሸ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በእጁ ያዘው፡፡ ሥራዩንም አወጣበት፡፡ ያን ጊዜም ለሁሉ ታየ፡፡ እርሱም “ማነው ስምህ?” አለው፡፡ ጋኔኑም “ባሕር አልቀም” አለው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም “ከኔ ጋር ትኖራለህን?” አለው፡፡ እርሱም ገዘረውና ወደ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ጥምቀት አገባው፡፡ ስሙንም ክርስቶስ ኀረዮ(ክርስቶስ መረጠው ማለት ነው) አለው፡፡ ረድእም አደረገው፡፡ ወደ በኣቱም አስገባው፡፡ እርሷም አስቦ ናት፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚወድና ወንድሞቹንም ሁሉ የሚያስደስት ሆነ፡፡” (ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፩፤ ገጽ. 177-178፤ Getachew Haile, Geneaology, P.11&12)

+ በጥንታውያን ሰዎች ዘንድ በአጋንንት አሠራር ተጠምደው የሚኖሩ ጣዖት አምላኪ ሰዎችን ባደሩባቸው አጋንንት ስም መጥራት የተለመደ ነው፡፡ ሰው በውስጡ ባለው ነገር ይጠራልና፡፡ ልክ ጌታ ጴጥሮስን “አንተ ሰይጣን ከኋላየ ሒድ” (ማቴ.16፡23) እንዳለው ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ታሪኮች በብዙ ጥንታውያን መጻሕፍት አሉ፡፡ ሥጋ ለበስ አጋንንት የሚሏቸው እነርሱን ነው፡፡ የተለያዩ የምትሐት ነገሮችን ይሠራሉ፡፡ በባሕር ይኖራሉ፣ በእሳት ውስጥም ገብተው በደኅና ይወጣሉ፡፡ ዋሊስ ባጅ ባሰተመው የደብረ ሊባኖስ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ላይ ጸሐፊው ከሌሎቹ የአካባቢው ቅጅዎች ለየት ብሎ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያጠመቁት ክፉ መንፈስ ያለበትን ሰው እንጂ መንፈስ የሆነውን ሰይጣን አለመሆኑን በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች ያብራራል፡፡ (E.A.W. Budge, The Life and Miracles of Takla Hay-manot, (London,1906), P. 80).
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፪


-------ጥያቄ ፪-------
‘የተክለ ሃይማኖት ተቅማጥ ከክርስቶስ ደም ጋር እኩል ነው’ ይላል ይላሉ፡፡ በውኑ ይላልን?

መልስ፡- ሙሉ ገጸ ንባቡ “ክቡር አባታችንም ጌታዬ ወደ ሰማዕትነት ዐደባባይ ሄጄ በስምህ እንድሞት እዘዘኝ አለው፤ ጌታም መጋደልስ ፈጸምክ ከሞት በቀር ምንም አልቀረህም፡፡” አለው ነው የሚለው፡፡ [ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፯፤ ገጽ. 195] ከዚህም በኋላ፡- “ወናሁ ትመውት በሕማመ ብድብድ በእኩይ ሞት ወእሬሲ ለከ ኪያሃ ከመ ስቅለትየ በከመ ደመ ሰማዕት እለ እምቅድሜከ አኮ ለባሕቲትከ አላ ደቂቅከኒ እለ ይመውቱ በሕማመ ብድብድ በውስተ ዛቲ ገዳም እኌልቆሙ ምስለ ሰማዕታት ወአወፍዮሙ ለከ በመንግሥተ ሰማያት፡፡”[ዝኒ ከማሁ] ነው ያለው፡፡

+ የቃሉ የግእዝ ትርጒም ሕማመ ብድብድ ማለት ቸነፈር ማለት ነው፡፡ ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት የሞቱት በቸነፈር በሽታ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዕለተ ዐርብ እንደ ተቀበልኩት መከራ መስቀል አደርግልሃለሁ ያለው፤ ገድላቸውንና በደዌ የተቀበሉትን መከራ ነው፡፡ በመልክዐ ጊዮርጊስ ላይም እንዲህ የሚል አብነት ይገኛል፡፡ ሰላም ለሰኳንዊከ ምስለ ክልኤሆን መከየድ፡፡ ለአጻብዒከ ሰላም ወለአጽፋረ እግርከ አምሳለ መረግድ፡፡ ገባሬ መንክራት ጊዮርጊስ በአቊጽሎ ይቡስ ዐምድ፡፡ አድኅነኒ በጸሎትከ እምነ መከራ ክቡድ፡፡ እስመ እምኔሁ ይወጽእ ቀታሊ ብድብድ፡፡ (መልክዐ ጊዮርጊስ) ትርጓሜውም፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ በሁለቱ ተረከዞችህ ጋር ለጫሞችህ ሰላም እላለሁ፡፡ እንደ ከበረ ዕንቊ ለሚያበሩት ለእግር ጽፍሮችህና ጣቶችህም ሰላም እላለሁ፡፡ ተአምር አድራጊው ሰማዕት ሆይ! ደረቁን ምሰሶ ለምለም ተአምራትህን ገልጸሃልና፡፡ ከጽኑ መከራ በጸሎትህ አድነኝ፡፡ ሰውስ ለሥቃይ የሚዳርጉ ረኀብ ቸነፈር ከእሱ ይፈልቃሉና፡፡ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም "ብድብድ" የሚለው ረኀብ፤ ቸነፈር ተብሎ ይተረጎማል፡፡

+ የተሐድሶ መናፍቃኑ እንደ ሚሉት ‘ተቅማጥህ እንደ ስቅላቴ ደም ነው’ የሚል ሐረግም ከገድሉ ላይ አይገኝም፡፡ “… እሷንም እንደ ስቅላቴና ካንተ በፊት እንደ ነበሩ ሰማዕታት ደም እቆጥርልሃለሁ፤” [ዝኒ ከማሁ(Ibid)] ነው ያለው፡፡ ይህም ማለት የተክለ ሃይማኖት ሕማም ከሰማዕታት ደም ጋር እኩል እንደሆነ እንጂ ከክርስቶስ ደም ጋር እኩል እንደሆነ አያስረዳም፡፡
ይህም የሆነበት ምክንያት ከገድሉ ላይ እንደምንረዳው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባ ተክለ ሃይማኖት ብዙ ተጋድለሃል ከእንግዲህ ይበቃሃል ነፍስህ ከመከራ ተለይታ ወደ እረፍት መሄጃህ ጊዜ ደርሷል ባላቸው ጊዜ አባ ተክለ
ሃይማኖት በሰማዕትነት እንድሞት አድርገኝ ብለው ስለለመኑት ነው፡፡ + በሚሞቱበት ጊዜ የሚደርስባቸውን ሕማም እንደ ራሱ መከራና በጦር ተወግተው በስለት ተቆርጠው ደማቸው እንደ ፈሰሰው ሰማዕታት ደም ሲቆጠርላቸው ነው፡፡ ሰማዕታት ለክርስቶስ ሲሉ በጦር ተወግተው በስለት ተቆርጠው ደማቸው እንደሚፈስ አባ ተክለ ሃይማኖትም ለክርስቶስ ሲሉ ሃገር ለሃገር ጫካ ለጫካ ሲንከራተቱ ሕማመ ብድብድን (ቸነፈርን) በጦር ተወግተው ደማቸው እንደፈሰሰው ሰማዕታት ቆጠረላቸው፡፡ ስለዚህ የአባ ተክለ ሃይማኖት ሕማመ ብድብድ (ቸነፈር) እንደ ሰማዕታት ደም ሆኖ ቢቆጠር ሃይማኖት ላለውና ለሚያስተውል ሰው አያደንቅም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ገድለ ተክለሃይማኖት ፫


@And_Haymanot
ጥያቄ ፫
፫. “ከሩቅም ከቅርብም ቢመጣ ወደ መቃብርህ የሄደውን እኔ ወደ መቃብሬ ኢየሩሳሌም እንደ ሄደ አደርገዋለሁ፤ በመታሰቢያህ ቀን ሥጋውን ደሙን የተቀበለውንም ስማቸው ከተጠራው ገድላቸው ከተነገረው ልጆችህ ጋራ እኔ እቈጥረዋለሁ፡፡” [ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፯፤ ገጽ. 193] ማለት ምን ማለት ነው?

+ መልስ፡- ወደ መቃብርህ የመጣውን ወደ መቃብሬ እንደመጣ አደርገዋለሁ ማለት በአንተ አማላጅነት በእኔ በርነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ማለት ነው፡፡ ይህም እናንተን የተቀበለ
እኔን ተቀበለ ያለው የወንጌል ቃል በተግባር ሲተረጎም ነው፡፡ + በተክለ ሃይማኖት በመቃብር ላይ በተክለ ሃይማኖት ስም በተሠራው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደ ሚገኝበት በመምጣት በመጸለይ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ነው፡፡ የእግዚአብሔር በረከት ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ ዋጋ እንደሚገኝም መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ 2ኛ.ነገ.5፡1፤
ዕብ. 11፡23፤ ሩት. 1፡16-18፡፡

+ “በመታሰቢያህ ቀን ሥጋውን ደሙን
የተቀበለውንም ስማቸው ከተጠራው ገድላቸው ከተጻፈው ልጆችህ ጋር እኔ አኖራቸዋለሁ፡፡” የሚለውም ቃል የኢየሱስ ክርስቶስን መግቢያ
በርነት የበለጠ ያስተምራል እንጂ

አያስቀርም፡፡ በአንተ መታሰቢያ
ዕለት የእኔን ሥጋና ደም ተቀብሎ በአንተ አስተማሪነት በእኔ በርነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ማለት ነው፡፡

፬ የመናፍቃን ጥያቄ ከገድለ ተክለሐይማኖት ውስጥ: "እባብን የገደለ ይጽድቃል" ይላል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሁሉ እባብን እየፈለጉ ለመጽደቅ እባብን መግደል አለባቸው ወይ የሚል ነው። አይ ይህቺ የመናፍቃን ጭንቅላት ትንሽ ብትሰፋ! ወገኖቼ መጸሐፍ ቅዱስ እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል መግባት ነው ይላል:: አንዱ ብርሃን መሆን አለበት:: ዛሬ ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ታውረዋል፡፡ አባታችን ተክለ ሐይማኖት ይፈውሱዋቸው አሜን :: ወገኖቼ እባብን የገደለ ይጸድቃል ማለት እባብ የተባለ ዲያቢሎስ ነው:: ለምሳሌ ያህል በመዝሙር ምህራፍ 73 ቁጥር 14 እንዲህ ይላል “አንተም የዘንዶውን እራስ ቀጠቀጥክ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው፤” ይላል :: ታዲያ አንተ የዘንዶውን እራስ ቀጠቀጥክ
ሲል ታዲያ እግዚአብሔር ዘንዶ ያለበትን እየሔደ እራስ እራሱን ቀጠቀጠው ማለት ነውን? አይደለም :: ዘንዶ የተባለው ሰይጣን ነው:: ሰይጣንን ደግሞ እግዚአብሔር በመስቀሉ
ቀጥቅጦታል :: እንዲሁም ገድለ ተክለ ሐይማኖት ላይም እባብን የገደለ ይጽድቃል ሲል ሰይጣንን የገደለ ይጸድቃል ማለቱ ነው :: ሰይጣንን የምንገለው ደግሞ በጾም በጸሎት እና በስግደት ነው:: በነዚህ እባብ (ዲያቢሎስን ) መግደል እንችላለን:: በተጨማሪም ደግሞ ራእይ ዮሐንስ ምህራፍ 12 ቁጥር 7 እንዲህ ይላል፡- “በሰማይም ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና ሰራዊቱ ዘንዶውን ተዋጉት :: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙን ሁሉ የሚያስት ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፡፡ ወደ ምድርም ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ፤” ይላል:: ታዲያ ሚካኤልና ቅዱሳን መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ ሲል ከእንስሳ ጋር ተዋጉ ማለት ነውን? አይደለም፡፡ ዘንዶ የተባለው የቀደመው ሰይጣን እርሱ ዲያቢሎስ ነው ይለናል:፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
---------ልቦናን ያድልልን -----------
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Join
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ገድል_ያወጣል_ከገደል
የገድላት ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም በገድላት ዙርያ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን የምንዳስስበት ተከታታይ ትምህርት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ሼር በማድረግ ምዕመናንን የመዳን ሥራ አብረን እንስራ
ክፍል ፩
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
@Konobyos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ገድል_ያወጣል_ከገደል
ክፍል ፪
@And_Haymanot
ሼር በማድረግ ምዕመናንን የመዳን ሥራ አብረን እንስራ

በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
@Konobyos
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
#ገድል_ያወጣል_ከገደል ክፍል ፪ @And_Haymanot ሼር በማድረግ ምዕመናንን የመዳን ሥራ አብረን እንስራ በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ @Konobyos @And_Haymanot
ገድል ያወጣል ከገደል ፪

በገድላት መሰረታዊ መረዳት እንዲኖረን የሚረዳ ትምህርት ነውና እነሆ

መልካም ንባብ ተወዳጆች
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ነገረ ማርያም

ተወዳጆች እንደምን ቆያችሁን
እነሆ ነገረ ማርያምን በስፋት ልንዳስስ በዝግጅት ላይ ነን በውስጥ በተደጋጋሚ ነገረ ማርያም ላይ ጥያቄ እየደረሰን በመሆኑ ከዚህ በፊት ያነሳናቸውን እንዲሁም እንድናነሳላችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄ በ @And_Haymanot_bot በኩል አድርሱን
√ መልእክቶች በብዛት ስለሚላኩልን ሃሳባችሁን ብቻ አስቀምጡልን
የ እናታችን ምልጃ እና ጸሎት አይለየን
@And_Haymanot
✞✞ልቦናዬ_በጎ_ነገርን_አወጣ እኔስ የማርያምን ክብር እናገራለሁ ፡፡ በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ፡፡
✞ እኔስ የድንግልን ውዳሴ እናገራለሁ መዘንጋት ባለበት
ቃል በማስረዘም አይደለም በማሳጠር ነው እንጂ .........
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
በእንተ ቅድስት ድንግል ማርያም
@And_Haymanot

ከትውልድ ሊቆጠሩ ያልተገባቸው ሐሳውያን የክፋትና የክህደትን ቃል እንደ ጸሎት ደጋግመው ስለሚናገሩና ስለሚጽፉ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም ያሰፈረውን ማስረጃ በአጭሩ እንዘረዝራለን ። በእምነት ያለነውን በእምነታችን ያጽናን በጥፋት መንገድ ያሉትንም ልቦናቸውን ያቅናልን ። አሜን ።

🙏🙏🙏ድንግል ማርያም 🙏🙏🙏

👉 1. ስለ ቅድስናዋ - የቅዱስ አምላክ እናት በመሆኗ [ኢየሱስ የጸነሰችው የወለደች ያሳደገችው የማህጸኗ ፍሬ ስለሆነ (ሉቃ 1:31:42 ፥ 2:7)] ወላዲተ አምላክ እያልን እንጠራታለን ። የቅዱስ አምላክ እናት ድንግል ማርያም ክርስቶስን ያህል መለኮታዊ አካል በማህጸኗ ስለወሰነች ቅድስት ትባላለች ። እኛ ክርስቲያኖችም ቅዱስ የተባልነው ቅዱሱ አምላክ ከርሷ ከተወለደና በቅዱስ ደሙ ከዋጀን በኋላ ነው ። ቅድስት ማርያም በነፍሷም በሥጋዋም ቅድስት ናት ። ሰው የሆነ ሁሉ ኃጢአትን ከመሥራት እንጂ ከማየት ፥ ከማሰብ ፥ ከመናገር የሚነጻ የለም። ርሷ ግን ከማየትና ከመስማት ፥ ከማሰብና ከመናገር ሁሉ ንጽሕት ናት። ስለዚህም ድንግል በክልኤ (በሁለት ወገን ድንግል) ትባላለች። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከእግዚአብሔር ተልኮ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ ሲላት ፥ የተለየችና የተቀደሰች መሆኗን በምስጋና ቃል መግለጡ ነው ። ቅድስት ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተነድታ ፥ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ብላ በመጮኽ ዳግም አረጋግጣለች ። ስለዚህም የመንፈስ ቅዱስ ቃል ፥ ድንግል ማርያም ቅድስት መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን እያልን በነፍስ በሥጋ ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን ።

👉 2. ድንግልናዋ - ቅድስት ማርያም እመቤትነትን ከገረድነት ፥ እናትነትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የያዘች ስለሆነችም የክብር ስሟ ድንግል ወእም እም ወዓመት የሚል ነው ። ድንግልናዋም ዘለዓለማዊ ስለሆነ ድንግል ዘለዓለም እንላታለን ። በአይሁድ ዘንድ ንጽሕናና ድንግልና የተወደደ፥ የተለመደ ፥ የተቀደሰም ህግ ነበር ። ይህን ህግ አፍርሶ የሚገኝ ወደ እሳት
ይጣላል ፥ በድንጋይም ተወግሮ ይሞታል። ስለዚህም ወንድ ሚስት እስኪያገባ ፥ ሴቷም ባል እስክታገባ ድረስ በድንግልና መኖር ግዴታቸው ነው ። በመሆኑም እነዚህ ደናግሎች ከጋብቻ በመራቅ ማለት ከሥጋዊ ሥራ ድንግል ይሁኑ እንጂ ከሐሳብ ፥ ከማየት ፥ ከመስማትና ከመናገር ድንግሎች አልነበሩም ። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በዘመኗ ከነበሩት ደናግል ተለይታ ፥ ከሐሳብ ድንግል ናት ፥ ከማየትና ከመስማት ድንግል ናት ፤ ክፋት ከመሥራትም ድንግል ናት ። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ንጽሕናና ቅድስና በመረዳት "እሞሙ ለሰማዕታት ወእኅቶሙ ለመላእክት ትምክህቶሙ ለወራዙት ወለድንግል" ማለትም "ለሰማዕታት እናታቸው ለመላእክት እህታቸው ለደናግላን ትምክህታቸው"
እያለች ታመሰግናታለች ።

👉 3. ቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና እንዲገባት ፤ እመቤታችን ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ስለሆነች ፥ ዘወትር ምስጋና ይገባታል ። የመጽሐፍ ማስረጃዎቻችንም የሚከተሉት
ናቸው
🙏 ሀ/ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምስጋና (ሉቃ 1:28)
🙏 ለ/ የቅድስት ኤልሳቤጥ ምስጋና (ሉቃ 1:42-43)
🙏 ሐ/ ትውልድ ሁሉ እንዲያመሰግናት የእመቤታችን የምስክርነት ቃል (ሉቃ 1:48)
🙏 መ/ አንዲት ሴት የተሸከመችህ ማኅጸን ቡርክት ናት አጥብተው ያሳደጉህ ጡቶችም ብሩካን ናቸው በማለት ያቀረበችው ምስጋና (ሉቃ 11:27)
🙏 ሠ/ ቅዱስ ጳውሎስም እግዚአብሔር ያከበረውንና የመረጣቸውን የሚከራከርና የሚወቅስ ማነው? እግዚአብሔር ያጸደቀውንስ የሚኮንን ማነው? በማለቱ (ሮሜ 8:33)
🙏 ረ/ ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ብሎ መጽሐፍ ስለሚዘንያ (ሮሜ 13:7) እመቤታችን ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል አለች እንጅ የተወሰነ ቀንና የተለየ ህዝብ አልጠቀሰችም ፤ መልአኩም ቡርክት ነሽ አለ እንጂ ነበርሽ ብሎ ስለአለፈው ብቻ አልተናገረም ፤ ቅድስት ኤልሳቤጥም ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ አለች እንጅ ነበረሽ አላለችም ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይኸን ሁሉ አስረጅ ገንዘቧ ስላደረገች ፥ ከቀድሞ ጀምሮ ዛሬም ወደፊትም ንጹሕ ክብርና ምስጋናን ለእመቤታችን በሰፊው ሰጥታ ስታመሰግን ትኖራለች ።

👉 4. ክብር እንደሚገባት:- ቅድስት ድንግል ማርያም ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ እርሷ በማህጸኗ ወስናለችና ፥ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነ ክብር አላት ። እንዲህም ከሆነ ከሰማይ ከምድርም እርሷ
ትበልጣለች እርስዋም ትከብራለች ማለትም በሰማይና በምድር ካሉት ከግዙፋኑና ከረቂቃኑ ፍጥረታት ሁሉ እርስዋ ትበልጣለች እርስዋም ትከብራለች ። ልዑልና ኃያል እግዚአብሔር ማህጸኗን ዙፋኑ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን አድሯልና ። እግዚአብሔር በመንፈሱ በሰው ላይ ለማደር እንኳን ሰው አላገኘም ነበር ። ነገር ግን ቅድስት ማርያም በንጽሕና በድንግልና ብትገኝ የልዑል እግዚአብሔር ማኅደር ለመሆን
በቃች ። ስለዚህ ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች የሆነ ክብር ተገባት ። ጌታችን ራሱን ከዓለም ግሳንግስ አንጽቶና በድንግልና ጠብቆ ህዝብን ስለንስሐ ያስተምር የነበረውን ዮሐንስን እንኳን፥ ሴቶች ከወለዱት እንደ ዮሐንስ የለም ብሎ ሲመሰክርለት እመቤታችንንማ ከንጽሕናዋ ከድንግልናዋ ጋር የአምላክ እናት ስለሆነች ከሁሉ በላይ እንዴት በበለጠ አትከብር? አምላክ የርሷን ሥጋ ተዋሕዷል ሰውም በዚህ ሥጋና ደም
ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆ የእግዚአብሔር መንግሥትን የሚወርስ ሆኗልና በክርስቶስ ደም ድኛለሁ የሚል የሰው ልጅ ሁሉ ሊያከብራት ይገባል ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት????
@And_Haymanot
አንድ እህታችን በውሥጥ የላከችልን መልዕክት ነው፡፡
ስለ እመቤታችን ሲነሳ የተሃድሶ መናፍቃን ዛሬም ከእናታችን እቅፍ ሊለዩን ተነስተዋል ከጥፋት ትምህርታቸው አንዱ ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት። በዛ ዘመን ብንኖር ከእኛ መሃል ከአንዳችን ኢየሱስ ይወለድ ነበር ብለው ያስተምራሉ ያምናሉ።

-ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን ከመውለድዋ በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች ሴት ናት ።
እንኳን የአምላክ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለም ማንኛችንም እግዚአብሔር የፈጠረን ፍጡር ወደዚህ አለም ከመምጣታችን በፊት ለምን አላማ እንደምንወለድ እንኳን ገና ሳንፈጠር እግዚአብሔር ያውቃል:: ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ኤርምያስ 1:5 እንዲህ ይላል ።
የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ ለአህዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።

-ቅድስት ድንግል ማርያም ለአምላክ እናት እንድትሆን ገና ሳትፈጠር እግዚአብሔር የመረጣት ሴት ናት። ከእሷም ባይሆን ከሌላ ይወለድ ነበር ለሚሉ የጥፋት ልጆች ከእግዚአብሔር አላማና ሃሳብ ጋር የተጣሉ የእግዚአብሔርን ሃሳብ በራሳቸው አመለካከት እና ሃሳብ ለመቀየር የሚያስቡ ደፋሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም
እንዲወለድ ነበር የእግዚአብሔር አላማ::
ከእሷ ባይሆን ለሚሉት የእግዚአብሔር ሀሳብ ሳይሆን የቀረበት ግዜ የለምና ከእሷ ውጭ ከማንም ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ሃሳብ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲወለድ እንጂ ሌሎች እንደሚፈላሰፉት ከአዳራሽ ጨፋሪዎቻቸው ሴቶች መሃከል ኢየሱስ ሊወለድ አይችልም:: ከፍጥረት ሁሉ ፣የአምላክ እናት እንድትሆን የተመረጠች ቅድስት ማርያም ብቻ ናት። ለመዳናችን ምክንያት ለሆነች ከሴቶች ሁሉ ለተለየች የአምላክ እናት ክብር ይገባታል ።

በተጨማሪም ሊታወቅ የሚገባው ማንኛውም ሠው በነብያትና በሐዋርያት መንገድ መጓዝ ከቻለ ሐዋርያት የደረሱበትን የክብር ደረጃ መድረስ ይችላል፡፡ ነገር ግን በክብር ላይ ክብር ብናገኝ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኝ ስራ ብንሠራ እንኳ ድንግል ማርያም የደረሰችበት የክብር ደረጃ ላይ መድረስ የሚችል ሰው ማንም የለም፡፡ ወደፊትም እንደዚህ አይነት ክብር እና ጸጋ ለማንም አይሰጥም፡፡፡፡

.....ይቆየን፡፡
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው
ለእኛም ግለጽልን።
አሜን አሜን አሜን!!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
‹‹ቤዛ›› ማለት ምን ማለት ነው?

እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም የአለም ቤዛ ናትን ?

@And_Haymanot

ብዙ ጊዜ ድንግል ማርያም እንዴት የአለም ቤዛ ትሆናለች? ይላሉ፤ በእርግጥ ግን እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም የአለም ቤዛ ናት ።
‹‹ ቤዛ ›› በቁሙ ሲተረጐም ዋጋ አለው ወይም ጥቅም አለው ማለት ነው ። እንዲሁም ቤዛ የሚለው ቃል "ቤዘወ"፦ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ቤዛ በቁሙ ሲተነተን እንዲህ ማለት ነው ። ዋጋ ፣ ካሳ ፣ ለውጥ ፣ ምትክ፣ሀላፊ ፣ ዋቢ ፣ ዋሥ ፣ መድኅን ፣ ተያዥ ፣ ጥላ ፣ ጋሻ ... ማለትነው ። ቤዛ በደቂቅ አገባብ ሲፈታ ደግሞ ሥለ፣ ፋንታ፣ ምክንያት የሚሆንተብሎም
ይተረጐማል ። አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ መፅሐፍ ሠዋሠው ውግሥ በመዝገበ
ቃላት ሐዲሥ 1948 ዓ ም ገፅ 266፡፡ ወይምደግሞ በሌላ መንገድ ከሣቴ ብርሐን ተሠማ መፅሐፋቸው ቤዛ ሲተረጉሙ እንዲህ ብለው አሥቀምጠውልናል ለውጥ፣ካሣ፣ወይም ደግሞ በአንድ ሠው ላይ መከራና ሞት ተላልፎ መሞትማለት ነው ወይም ታደገኝ ወይም ምትክ ሆነኝ ማለት ነው ወይም ደግሞ ለመከራ ለሞት ለወጠኝ ማለት ነው ወይም ቤዛ ሆነኝ ማለትነው።

የበለጠ ለመረዳት አልያም ቤዛ ሥለሚለው ቃል በደንብ ለማወቅ እነዚህን መፅሐፍቶች መመልከት ይቻላል ። እንደዚሁምቤዛ የሚለው ቃል ፦ ካሣ ፣ የደም ቤዛ ፣ አንዱ ሠው የሠውንደም ሥለሚያፈሠው ለውጥ ወይም ዋጋን ፣ ገንዘብን ፣ ካሣን መሥጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው ። ከሣቴ ብርሐን 1951 ዓ.ምገፅ 532

ድንግል ማርያምን ስለምን የአለም ቤዛ እንላታለን? የእመቤታችን ቤዛነትም ከላይ በተረዳነው መሠረት ቤዛ ከሚሉት የትርጓሜ ቃላት መካከል ምትክ፣ ዋሥ፣ምክንያት ... ከሚሉት መካከል ምትክ የሚለውን ስንወስድ
ድንግል ማርያም የህይዋን(ሔዋን) ምትክ በመሆኗ ነው፤ ‹ምክንያት› የሚለውን ስንወስድ ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም ለኛ መዳን ምክንያት ስለሆነች ነው። እግዚአብሔር ለአለም መዳን በድንግል ማርያም ታላቅ ስራን አድርጉአልና ቤዛዊት ዓለም እንላታለን። የድንግል ማርያም በእምነት መታዘዝ ለዓለም መዳን
ምክንያት ሆናለች። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ስለተቤዤ ቤዛዊት ዓለም እንላታለን። ቤዛ የሚለው ቃል ለሙሴም ተሰጦት እናነባለን። ( የሐዋ ሥራ 7:35) በመልአክ እጅ
እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው። እንግዲህ ይህ የፍጡር ቤዛነት የእግዚአብሔርን ቤዛነት ይሽራልን? አይደለም፡፡ እንዲያውም ቸር እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የሚሰጠውን የባለሟልነት ስጦታ ብዛት ይገልፃል እንጂ፡፡ ሙሴ
ወገኖቹን ከመጥፋት እንደምን አዳናቸው(ተቤዣቸው)(ታደጋቸው)? እንደክርስቶስ ደሙን በማፍሰስ ነውን? አይደለም በእግዚአብሔር ዘንድ ‹ይህን ኀጢአታቸውን
ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍኽ እባክኽ ደምሰሰኝ›
በማለትየተወደደፀሎቱንበማቅረብእንጂ (ዘጸ.32፤32) ፡፡ ዳዊትም ‹ሙሴ
በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ›› ሲል የገለፀው ይሄንኑ ነው፡፡ስለዚህም
መጽሐፍ የፃድቅሰውፀሎት በስራዋ እጅግ ሃይልን ታደርጋለች ይላል፡፡

የእመቤታችንና የድንግል ማርያም ቤዛነት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርሥቶስ ቤዛነት ጋር ያለው ልዩነትእጅግ የሚራራቅ ነው። ጌታችን በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው ። እንዲሁም በደሙ ዋጅቶ በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው። ቤዛ ማለትእራሥን
ሥለሌሎች አሣልፎ መስጠት ማለት ሥለሆነ ጌታችንም ሥለበጐቹ እራሱን አሣልፎ ሠጥቷል ሆኖም የአለም ቤዛ ነው ። ታዲያ የአለምቤዛ ክርስቶስ ከሆነ ድንግል ማርያምስ ቤዛዊት አለም መባሏ ስለምን ነው ቢሉ፦ ክርስቶስ አለምን ሁሉ ከሞት ወደህይወት ያሻገረበት፣ ሃጢአታችንን ሁሉ የደመሰሰበት፣
የሚደመስስበትም ክቡር ደሙ፣ ቅዱስ ስጋው ከእመቤታችን ስለነሳው ነው፤ በዚህም ክርስቶስ ከመወለዱ አንስቶ በቤተልሄም የከብት ግርግም ተጀምሮ፡ በግብፅ ስደቱ በቀራኒዮ ስቃዩና ሞቱ ሁሉ አብራው አለችና በክርስቶስ የድህነት
ስራ ውስጥ የእመቤታችን ስራ ጉልህ ሆኖ ይታያልና ነው፡፡

ለማጠቃል ያክል፡-
ሙሴ ምክንያት ሆኖ ነጻ ያወጣቸው ለጥቂት ነገዶች ወይም ‹ለእስራኤላውያን› ብቻ በመሆኑ‹‹ቤዛ›› ብቻ ተብሏል፡፡ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ግን ምክንያተ ድኅነት ሆና ነጻ ያወጣችው ‹ዓለም ሙሉ› ስለሆነ (ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ተሰቅሏልና) ‹‹ቤዛዊተ ዓለም›› ትባላለች፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን ለቅዱሳንም በጸጋ ተሰጥቷል፤
በመጸሐፍየጸጋ አምላክነት ለቅዱሳን ተሰጥቶ እናያለን ‹እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦እይ፥እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌኻለኹ›፤ ክርስቶስየዓለም ብርሃን እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ቅዱሳንንም ‹እናንተየዓለም ብርሃን ናችኹ› በማለት በጸጋ የዓለም ብርሃን እንደሚባሉ መጽሐፍ ምስክርነው ( ዘጸ7፤1 ማቴ 5፤14)
የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲህ ነዉ፤ ክብርና ምሥጋና ለቤዛዊት አለም ለእመቤታችን ለቅድሥት ድንግልማርያም ይሁን
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
🙏1