፩ ሃይማኖት
9.08K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ሉቃ.13፡24/፡፡ ስለዚኽ ከኃጢአት መራቅ የሚፈልግ ሰው የመተው ልምምድን አኹንኑ መዠመር አለበት፡፡ “ዛሬ ዘፈን አላዳምጥም፡፡ ዛሬን በዚኽ ምትክ መዝሙር አዳምጣለኁ” ብሎ መለማመድ አለበት፡፡ በዚኽ ውሳኔው ጸንቶም ዛሬን ይውላል፤ ያድራልም፡፡ ሌሎች ነገሮችም እንደዚኽ ናቸው፡፡ የመጠጥ ልምድ ያለው ሰው “ዛሬ አልጠጣም፤ ዛሬ በምጠጣበት ሰዓት እዚኽ ቦታ እሔዳለኁ፡፡ እዚያ ሒጄ እውላለኁ፡፡ በበጎ ነገር አሳልፈዋለኁ” ሲል ዛሬን ይውላል፡፡ ማታ ላይ ሲመሽ “ለካ ይቻላል፡፡ ለካስ እኔ ከበረታኁ እግዚአብሔር ያስችለኛል” የሚለውን በኅሊናው ያሳምናል፡፡ ነገሮችን የመተው ልምምድ በተግባር ማሳየት ማለት ይኸው ነው፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያ ያስቸግረን የነበረው ተደጋጋሚ ኃጢአት ታሪክ ይኾናል፤ ለሌላ ሰው መካሪ ኾነን ራሳችንን በለውጥ ቦታ ላይ እናገኟለን፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
በቀሲስ ፋሲል ታደሰ
ምንጭ፦ መቅረዝ ዘተዋሕዶ

@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሆሳዕና
.
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ.
12÷12-15
.
የዘንባባ ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን
የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ
ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና
በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡
የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ
ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።
.
በዓሉን በዓለ ክብር ፣ በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ አ ሜ ን !!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ይህ ማነው?
👆 👆

@And_Haymanot

=>ሁሉን ሳለው ከድሆች ቤት ያደረ
=>ክቡር ሲሆን የተናቁትን ያከበረ
=>ባለ ፀጋ እርሱ ከምስኪኖች ደጃፍ የቆመ
=>ንጉስ እርሱ ያገልጋዬቹ እግር የሳመ
👉ይህ ማነው?
=>እየጣሉት የሚያነሳ
=>እየቀሙት የሚለግስ
=>እያቆሰሉት የሚጠግን
=>እየራበው የሚያጎርስ
=>እየታረዘ የሚያለብስ
=>እየተጠማ የሚያጠጣ
👉ይህ ማነው?
=>ሙሽራ ሲሆን ያላዘዘ
=>ባለመድሀኒት ሲሆን የታመመ
=>ከሁሉ ከፍ ያለ ሲሆን ያነሰ
=>ኃያል ሲሆን የደከመ
👉ይህ ማነው?
=>ቀና ሲል ሰማይን ሞልቶ ያየሁት
=>ዝቅ ስልም ከድንግል ጎን ያየሁት
👉ይህ ማነው?
=>በሰማይ የማይወሰን ከድንግል ማህፀን ያረፈ
=>በእጁ አላማትን የጨበጠ
=>በፍጡር ጀርባ የታዘለ
=>በብላቴና ክንድ የታቀፈ
👉አረ ይህ ማነው?
=>ከዙፋኑ ሳይለቅ ከአገልጋዬች ጋር አብሮ ያለ
=>ከላይ ሙሉ የሆነው ከታችም ያልጎደለው
=>አይኔ ባቀና ከላይ የማየው
=>ባጎነብስም የማላጣው
👉ይህ ማነው?
=>ቀንድ ሳለው የማይዋጋ
=>ጥፍር ሳለው የማይቧጭር
=>ጉልበት ሳለው የማይጋፋ
=>ክንድ ሳለው የማይሰብር
👉ይህ ማነው?
=>የገፉትን የደገፈ በጨካኞች ፊት የራራው
=>የሰበሩትን የጠገነ የወጉትን ያበራ
👉ይህ ማነው?
=>ሞትን በሞቱ ያሸነፈው
= የጥላት ኃልን ድል የነሳው
=>የክፋትን ክንድ የሰበረው
=>የዕዳችን ደብዳቤ የሻረው
=>ጨለማውን የገፈፈው
=>የወደሙትን የበረበረ
=>ታላቁን ዜና ያበሰረ
=>ፍቅር የፍቅር መምህር
=>ትሁት የትሁታን ክብር
=>በሁሉ ዘንድ የተወደደው
=>ግና ከሁሉ የተለየው
👉ኧረ ይህ ማነው?
👉እርሱማ የፍቅር አባት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
@And_Haymanot
=>እወድሀለሁ ጌታየ ሆይ እስኪ ስማኝ
=>አንድ የማጫውትህ ጉዳይ አለኝ
=>በፊትሄ ቡዙ በደልኩ
=>ከክብሬ በፍቃድ አነስኩ
=>አትብላ ያልከኝን በላሁ
=>አታድርግ ያልከኝን አደረሁ
=>አትየው ያልከኝን አየሁ
=>አትቅረበው ያልከኝን ቀረብሁ
=>ከውቡ ቃልህ ሸሸሁ
=>ጥሩ ምክርህን አቃለልሁ
=>ጥልን በልቤ አፈራሁ
=>ትእዛዝህን አፈረስኩ
=>ቅዱሱ ባህሪን አሳደፍኩ
=>ጌታሆይ በምኔ ይሆን የወድድከኝ?
=>ሞቴን በሞትክ ሽረህ ከክፉ እሳት ማርከህ ያወጣኸኝ
=>ጌታየ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ እወድሀለሁና ልምበርከክልህ
=>እንግዲህ እንደምወድህ ታውቅ ዘንድ ዋስ ማንን ላቅርብልህ?
=>ዋስም ሌላ የለኝም ድንግል ማርያም ናት
=>ቅድስት ወላጅህ ከሁሉ ይልቅ የምትወዳት
=>እርሷም ከሁሉ ይልቅ የምትወድህ
@And_Haymanot
👉ስለዚህ እኔም እወድሀለሁ
👉ስለ እናትህ ድንግል ብለህ ይቅር በለኝ እልሀለሁ

👉ይህ ማነው?
{ምንጭ ከ ማርቆስ ወንጌል 4:40}


👉💒ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን
@And_Haymanot
ጉልባን

ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚባላ ንፍሮ ነው፡፡
የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር፤ አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ
እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበርና ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና
ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል፡፡

በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን
አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያም አብዛኛዎቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡
በዲ/ን ቤርዜሊ ተስፋዬ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
በተዋህዶ ቤት እንዲህ ክርስቶስ በተግባር ይሰበካል

የአባቶቻችን በረከት ይደርብን አምላካቸው አምላካችን ሁለንተናችንን ይባርከው
@And_Haymanot
የትሁታን አምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ
@And_Haymanot
"-----4፤ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤

5፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።

6፤ ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም። ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።

7፤ ኢየሱስም መልሶ። እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።

8፤ ጴጥሮስም። የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም። ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት።

9፤ ስምዖን ጴጥሮስም። ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።

10፤ ኢየሱስም። የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።

11፤ አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና፤ ስለዚህ። ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለው።

12፤ እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው። ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?

13፤ እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።

14፤ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።

15፤ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።

16፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።

17፤ ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።...."
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን
አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው።
በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው
እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና
በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤
@And_Haymanot
መድኃኔአለም አዳነን በማይሻር ቃሉ፡፡
እልልልልልልልልልልልል በሉ
እንኳን አደረሳችሁ
፩ኃይማኖት
@And_Haymanot
ትንሣኤከ ለእለ አመነ /2/ 
ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ /4 
ትንሳዔክን ለምናምን ለኛ /2
ብርሃንን ላክልን ወደኛ/4
@And_Haymanot
"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል" /1ቆሮ 15፡20/

"ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የታለ?" /1ቆሮ 15፡55/
@And_Haymanot
መልካም በዓል
ለምን አንጾምም?

ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች?

ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም?
በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/።

"የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ
15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት
ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው።
በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ
እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም
ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
የእግዚአብሔርን ቅጣት ፈርቶ ንስሓ መግባትና የእግዚአብሔርን ቅድስና ፈልጎ ንስሐ መግባት ይለያያል።

☞ እውነተኛ ክርስቲያንም ንስሐ የሚገባው ገሃነመ እሳትን ፈርቶ
ሳይኾን የመንግሥተ ሰማያትን ጣዕም ስለሚናፍቅ ነው።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ትዝብት

በትላንትናው ዕለት በተደረገው የቀብር ሥነሥርዓት ላይ የተላከልንን ትዝብት እነሆ ብለናል ተዋህዶን በመተቸት ለተጠመዱ ሁሉ ይድረስልን፡፡

* እኛ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የምናደርገውን ነገር ከተቃወማችሁ በኋላ ዞራችሁ ደግሞ እናንተ ስታደርጉት ይታያልና ይህ የአቋም መዋዠቃችሁ መቼ ነው የሚስተካከለው?
* ለምሳሌ፡-
* 1ኛ. ለሞተ ሰው የሚደረግ ጸሎት /ፍትሐት/
* ይህን ስርዓት እኛ ስንፈጽመው፣ …ለሞተ ሰው ለምን ጸሎት
ይደረግለታል? ምንስ ይጠቅመዋል?... በሚል ሀሳብ ስትቃወሙንና ስትከራከሩን ነበር፡፡ ነገር ግን እናንተም ስታደርጉት
አየን፡፡ ስለዚህ የምትቃወሙትንና የምታደርጉትን ለምን አትለዩም?

* 2ኛ. መስቀል መጠቀም
* እኛ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የጌታ መስቀል ስንይዝ እናንተ ግን ‹‹የተሰቀለውን እንጅ የተሰቀለበትን አንሰብክም›› በሚል ትክክለኛ ያልሆነ ሀሳብ መስቀል መጠቀምን ስትቃወሙን
ነበር፡፡ ነገር ግን እናንተም አማኝ ለመምሰል ይሁን ባለውቅም መስቀሉን ስትጠቀሙ ይታያልና ይህ ነገራችሁ መቼ ነው ወጥ የሚሆነው?
~~~~~~~~~~~~
ፀልዩ ፀልዩ!!!! ለጠፉት ልቦናን ይስጥልን እኛንም ከእቅፉ አይለየን፡፡
እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ።

"ድንግል ሆይ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ምልጃሽ አይለየን "
@And_Haymanot
@And_Haymanot
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን

@And_Haymanot

“ተወዳጅ ሆይ! እግዚአብሔር አይሰማኝም አትበል፡፡ አንተ ተናገር
እንጂ ርሱ ይሰማኻል፤ ባትናገርም ያደምጥኻል፡፡ ኾኖም ርሱ አንተን ሲሰማኅ ችግሮችኅ ይስተካከላሉ፤ ርሱን ስትሰማው ደግሞ አንተ ትስተካከላለኅ፡፡

ያልተስተካከለን ችግር የተስተካከለ
ሰው ይሻገሯል፤ ያልተስተካከለ ሰው ግን የተስተካከለን ችግርም አይሻገርም፡፡ “እንዴት?” ብለኽ ከጠየቅከኝ ግን መልሴ
“አካሔድ የማያውቀውን የተነጠፈም ጐዳና ጠልፎ ይጥለዋል” የሚል ነው፡፡ ከችግሮች ኹሉ እኛ ችግሮች ስንኾን ቀኖች ይከብዳሉ፡፡ መሣሪያው ሲበላሽ ሥራው ይበላሻል፡፡ ስለዚኽ መሣሪያው ተሠርቶ ሥራው ይሠራል፡፡ አንተ ከተበላሸኽ የሚስተካከል ነገር የለም፡፡ አንተ ከተስተካከልክ ግን ሌላው
ቢበላሽ ራስኽን ታድናለኽ፡፡ “ከምንም ነገር አንድ ነገር” ይባላልና ይሔ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወዳጄ! እውነት
እውነት እልኻለኁ እመነኝ፤ አንተ ስትስተካከል ብቻኽን አትስተካከልም፡፡ በተስተካከለ የሚስተካከሉ፣ በዳነ የሚድኑ ብዙዎች ናቸውና፡፡ የአየር ንብረቱን ዐይቶ ልብስን ማስተካከል
ካለ የዘመንን መልክ ዐይቶ ልብን ማስተካከል ተገቢ ነው እልኻለኁ፡፡ ፀጉርን ለማስተካከል ከአስተካካዩ ጋር፣ የከበረ ልብስን ለማስተካከል ከአልባሹ ጋር፣ ዕውቀትን ለማስተካከል ከመምህሩ
ጋር፣ … ትገናኛለኅ፡፡
@And_Haymanot
ሕይወትን ለማስተካከል ግን ማንን አግኝተኅ ይኾን? አንተን ለሕይወት የሠራኅ እንጂ ሌላ ማንም አያስተካክልኽም፡፡ ሰው ኹሉ ከራስኅ በላይ የሚነፍስ ነፋስ ኾኖብኅ “ለእኔ እኔ - ከእኔ ወደ እኔ” ብለኅ ከራስኅ ጋር ቃል ኪዳን ተጋብተኽ አዲስ ኑሮ ዠምረኽ ነበር፡፡ ነገር ግን ለመስተካከል ዓቅም አጥተኽ የመስተካከልን በጐ ፈቃድ ብቻ
ይዘኅ ቀረኽ፡፡ ስንት ዘመን የራስኽ ጥበብ ስንፍና፣ የራስኽ ብርታት ድካም፣ የራስኽ ሙከራ መከራ እንደኾነብኅ ዐውቂያለኹ፡፡ ስለዚኽ ለፈጠረኽ ጌታ ራስኽን አሳልፈኅ ለመስጠት ወስን፡፡ በራስኽ ላይ እንደዚኽ ዓይነቱን ውሳኔ
እንደማስተላለፍ አስቸጋሪና እጅግ ውብ የኾነ ነገር በዚኽ ዓለም ላይ አታገኝም፡፡ ወደ ፈጠረኽ መምጣትኅ ዥማሬኅ ነው፤ ከርሱ ጋር ያለው ቈይታኅ ዕድገትኅ ነው፤ ርሱን አምነኅ እንደኖርኅ አምነኅ ስትሞትም ሕይወትኅ ነው፡፡ እውነት አንተስ ዕድለኛ ነኽ!!! እናም ምክሬን ስጠቀልልኅ፡- የእውነት ልመና “ጌታ ሆይ!
አስተካክለኝና ትክክል ልኹን!” የሚል መኾኑን ደግሜ በማስታወስ ነው፡፡ “እንዳስተውል ርዳኝ፤ በሕይወትም አኑረኝ” / መዝ.118፡144/፡፡”
© ዲ/ን ቃለኣብ ካሣዬ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ዮም ፍስሐ ኮነ ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/2/
በባርነት ሳለን ~ፍስሐ ኮነ
ሀጢአት ባለም ነግሳ ~ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ ~ ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ ~ፍስሐ ኮነ
አዝ
እግዚአብሄር መረጠሽ ~ፍስሐ ኮነ
ልትሆኝ እናቱ ~ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ ~ፍስሐ ከነ
የዳዊት ትንቢቱ ~ ፍስሐ ኮነ
አዝ
የሄዋን ልጆች ተስፋ ~ ፍስሐ ኮነ
የአዳም ህይወት ~ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሀና ~ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት ~ ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድሂን ~ ፍስሐ ኮነ
ኪዳነ ምህረት ~ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች ~ ፍስሐ ኮነ
የጌታየ እናት ~ፍስሐ ኮነ
አዝ
በሄዋን ምክንያት ~ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም ~ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው ~ፍስሐ ከነ
በድንግል ማርያም ~ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል ~ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ ~ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለች እና ~ፍስሐ ኮነ
የዓለም ሁሉ ተስፋ ~ፍስሐ ኮነ
ዮም ፍስሐ ከነ ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም
እልልልልልልእልልልልልልእልልልልል
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ባትወለድ ኖሮ……


መለኮትን ያህል - በእጅ እንደ መጨበጥ - በሆድ እንደ መወሰን
ምን ክብር ይገኛል - ምን ምጡቅ ልዕልና? - ምንስ ገላጭ ልሳን?
ባትወለድ ኖሮ - ብላቴናዋ ባትኖር - ያች የምስጢር ማህደር
ተራ ተዓምር ሁሉ - እንደ አምልኮት - በሆነብን ነበር፡፡

ባትወለድ ኖሮ - እሷን ተመልክተን - መመኪያ ባላልናት
በሔዋን ተስፋ ውስጥ - ብርሃንን አዝላ - ደምቃ ባላየናት
የተዘጋች ገነት - ቀድሞ እንዳጣናት - ርስታችን ባላልናት፡፡

አዳም ባልተጽናና - ደሙም ባላቆመ - ሲፈስ በኖረ
“ህይወቴ ነሽ” ብሎ - ሔዋንን ባልጠራት - ተስፋው ባልነበረ
የማግሰኞም እርሻ - ዘርን ባላስገኘ - ባዶውን በቀረ
ሁሉም ይቀር ነበር - ሰውም በውድቀቱ - እንተቸገረ
ባትወለድ ኖሮ - አሁን አይኖርም ነበር - ጥንት እንደ ነበረ፡፡

ትንቢትን ባላየን - ይወለዳል ብለው - ተስፋ ባልሰነቁ
“ክንድህን ከአርያም ላክ” - ብለው ባልተጽናኑ - ፊቱ ባልወደቁ
ዘርም ባልቀረልን - እንደ ተበተንን - ከቤት እንደ ወጣን
ባላወቅን እረኛ - ጋጣ እንደሌለን - ማደሪያ እንዳጣን
እንደ ከንቱ ፍጥረት - በምድር እንደሚቀር - እንደ ዱር ቀበሮ
ሰው በሆነ ነበር - ያች እንቁ ፍሬ - ባትወለድ ኖሮ፡፡

ምስራቃዊት መቅደስ - የታተመችን በር - ህዝቅኤል ባላየ
የሙሴ ሐመልማል - በነበልባሉ ’ሳት - ተዋህዶ ባልቆየ
ረዥሙ ተራራ - ለዳንኤል ባልታየ - ተስፋ ባልሰነቀ
ባትወለድ ኖሮ - ሁሉም ጠፍቶ ነበር - ያኔ እንደ ወደቀ፡፡

ቴክታና ጴጥርቃ - (እ)ራዕይ ባላዩ - ህልም ባልታያቸው
ከጥጃ ጨረቃ - እንደምትወለድ - ባልተነገራቸው
ከጨረቃም ፀሃይ - ዓለምን ሲያበራ - ባልተመለከቱ
የጨለማ ዘመን - በዘለቀ ነበር - ልክ እንደበፊቱ፡፡

ሄርሜላና ማጣት - ሃናን ባልወለዷት - ተስፋም ባልቀረበ
ኢያቄም ባልመጣ - ከይሁዳ ነገድ - ድኅነት ባልታሰበ
ባልተነገራቸው - በስተ እርጅናቸው - ባላዩ' ደስታ
ባትወለድ ኖሮ - ሁሉም መራር ነበር - በመጣፈ ጥፈንታ፡፡

መልአኩም ባልመጣ - ብስራቱን ባልሰማን - ቃል ስጋ ባልሆነ
ልደቱን ስቅለቱን - ትንሳኤውን ባልሰበክን - ሁሉ በባከነ
ባትወለድ ኖሮ - እመአምላክን ባናይ - ያችን የድኅነት በር
ምክንያት ፈጥረን ሞተን - መልሰን ለመዳን - ምክንያት ባጣን ነበር፡፡

(አክሊሉ ደበላ ሚያዝያ 30/2006ዓ.ም)

@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa