፡፡
5ኛ. አሁንም ጉዳዩ በምንም መልኩ ከዝሙት ጋር እንደማይገናኝ ለመረዳት በቀጣዩ አንቀጽ ላይ የሰፈረውን ማየት ጠቃሚ ነው፡፡ አንቀጹም እንዲህ ይላል፡-
"ከናንተም ውስጥ ጥብቆች ምእምናት የሆኑትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው፣ እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምእመናት፣ ወጣቶቻችሁ (ባሪያን ያግባ)፤ አላህም እምነታችሁን ዐዋቂ ነው፤ ከፊላችሁ ከከፊሉ (የተራባ) ነው። (ባሮችን) በጌቶቻቸውም ፈቃድ አግቡዋቸው። መህሮቻቸውንም በመልካም መንገድ ስጧቸው፤ ጥብቆች ሆነው ዝሙተኞች ያልሆኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲሆኑ፣ (አግቧቸው)…" (ሱረቱ-ኒሳእ25)፡፡
በዚህ አንቀጽ ውስጥም እነዚን ጥብቆቹን (ነጻዎቹን) ለማግባት አቅሙ የሌለው ሰው በባርነት ቀንበር ውስጥ ውስጥ ካሉት አንዷን ጌታዋን (አሳዳሪዋን) በማስፈቀድ ያግባ አለ እንጂ በገንዘቡ ዝሙት ይፈጽም አላለም፡፡ ዝሙት በገንዘብ ክፍያ የተፈቀደ ከሆነ ለምን በጌቶቻቸው (አሳዳሪዋ) ፈቃድ እነሱን ያግባ! ማለት አስፈለገ? ደግሞስ መህሮቻቸውን በመልካም መንገድ ስጧቸው ብሎ ለምን አዘዘ?
6ኛ. እነዚህኑ የምታገቧቸው ሴቶች ‹‹ጥብቆች ሆነው ዝሙተኞች ያልሆኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲሆኑ›› ማለቱ ደግሞ የጠላትን ክስ የበለጠ ከንቱ ያደርገዋል፡፡ አንቀጹ ሴቶቹ፡- ከዝሙት የራቁ፣ ድብቅ ወዳጅ የሌላቸውና እራሳቸውን የጠበቁ መሆን እንዳለባቸው ካስተማረ፡ ታዲያ በገንዘባችሁ ፈልጉ ያለው ይህንኑ ህጋዊ ትዳርን እንጂ እንዴት ዝሙትን ነው ብሎ ማሰብ ይቻላል?
7ኛ. ቅዱስ ቁርኣን ዝሙትን አጥብቆ ያወግዛል፡፡ መንገድነቱም የከፋ መሆኑን ያስተምራል፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን ዝሙትን ሲፈጽም በአራት የአይን እማኞች የተገኘ፡ ወይም ከንሰሀ (ከተውበት) በፊት እራሱን ለሸሪዓው ዳኛ (ቃዲ) አሳልፎ በሰጠ ሰው ላይ ወንድም ይሁን ሴት ሃይማኖታዊ ቅጣትን ደንግጓል-
"ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!" (ሱረቱል ኢስራእ 32)፡፡
"ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን፤ (ያላገቡ እንደሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፋዋቸው በነርሱም በአላህ ፍርድ ርኅራኄ አትያዛችሁ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደ ሆናችሁ በምእምናን (አትራሩ)፤ ቅጣታቸውንም ከምእመናን ጭፍሮች ይገኙበት።" (ሱረቱ-ኑር 2)፡፡
ዝሙትን በዚህ መልኩ ያወገዘና ለዝሙተኞች ቅጣትን የደነገገ ሃይማኖት ተመልሶ በገንዘብ ክፍያ ከሆነ ግን ይቻላል እያለ ይደነግጋል ብሎ ማሰብ ከጤነኞች አይጠበቅም፡፡
8ኛ. ፈጣሪ አምላካችን አላህ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አማኝ ባሪዎቹን ሲያወድሳቸው ከፊል ባሕሪያቸውን እየዘረዘረ ነው፡፡ ከነዚህም ባሕሪያት መካከል አንዱ ‹‹ከዝሙት የራቁና ብልቶቻቸውን የጠበቁ›› መሆናቸውን በመግለጽ ነው፡-
"ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)….እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡" (ሱረቱል ሙእሚኑን 1.5)፡፡
"የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ ሰላም የሚሉት ናቸው…እነዚያም፣ ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፤ #የማያመነዝሩትም ናቸው፤ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል።" (ሱረቱል ፉርቃን 63.68)፡፡
ይህ የሚያሳየው ‹‹ዝሙት›› አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላ ተግባር መሆኑን እንጂ በገንዘብ መፈቀዱን አይደለም፡፡
በመጨረሻም ለነዚህ ወገኖቻችንም ሆነ ለሌሎች የምናስተላልፈው መልክት፡- እባካችሁ ከጭፍን ጥላቻና ከመሃይምነት ውጡና በልበ-ሰፊነት የኢስላምን መልክት ለመረዳት ሞክሩ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ‹‹የመሃይም መድኃኒቱ መጠየቅ ነው›› ባሉት መሰረት ለመጠየቅ እንጂ ለመፍረድ አትቸኩሉ እንላለን፡፡
ጥሪያችንም፡- አንድ አምላክና አንድ አምልኮ ብቻ የሚከናወንበት፡ አላህ እንጂ ፍጡር ወደማይመለክበት፣ ሁሌም አምላካዊ ባሕሪው እንጂ ሌላ የማይወሳበት ወደሆነው አላህ መንገድ (ዲነል-ኢስላም) በመምጣት ነፍሳችሁን ከዘላለም እሳት እንድታድኑ ነው፡፡
አላህ ቅኑን ጎዳና ይምራችሁ፡፡ ለኛም በእምነታችን ጽናቱን ይስጠን፡፡ ወቢላሂ ተውፊቅ!
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

ትዳርን ከዝሙት መለየት ያልቻሉ አዕምሮዎች!!
በአቡ ሀይደር
በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው
1/ ዝሙት ህገ-ወጥነት ነው፡፡ ህገ-ወጥነት ደግሞ ከህጋዊነት የሚለየው በሕግ መነጽር ሲታይ ነው፡፡ ያ ህግ ደግሞ ፍጹም መለኮታዊ የኾነው የአላህ ህግና መመሪያ ነው፡፡ እኛ ሁላችንም የአላህ ፍጥረትና ባሪያ በመኾናችን፡ ሕይወታችንን እንዴት መምራት እንዳለብን፣ በምን አይነት ስርአት መመላለስ እንዳለብን ህግን የሚደነግገው ጌታ አላህ ነው፡፡ በመኾኑም ይህ ጌታ የፈቀደው ሁሉ፡ መልካምና ህጋዊ ሲኾን፡ እሱ ያወገዘው ነገር በጠቅላላ ደግሞ ህገ-ወጥ ይባላል፡፡
ከዚህ እውነት ተነስተን ነው የአንድን ነገር ህጋዊነትና ህገ-ወጥነትን መለየት የምንችለው፡፡ አለበዚያ ማንም ከመሬት ተነስቶ፡ ለራሱ ስሜት ስላልተመቸው፣ ወይም እሱ በሚከተለው እምነት ስለሌለ ብቻ፡ አንድን ነገር ማውገዝ አይችልም፡፡ ይህ ጭፍንነት ነው፡፡ ዝሙት የሚባለው፡- አላህ ያልፈቀደው፣ በወንድና ሴት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት ነው፡፡ ይህን ግኑኝነት ቁርኣን እንዲህ ብሎ ይገልጸዋል፡-
"ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!" (ሱረቱል ኢስራእ 32)፡፡
ኢስላም ዝሙትን ማውገዝና መከልከል ብቻም ሳይኾን፡ በዚህ ተግባሩ ላይ ኾኖ፡ ተውበት ከማድረጉ (ንሰሀ ከመግባቱ) በፊት፡ በአራት የአይን ምስክሮች እጅ ከፍንጅ የተያዘንም ሰው ቅጣትን ደንግጎበታል፡፡ ቅጣቱም ትዳር የሌለው ሰው ከኾነ መቶ ግርፋትን መገረፍ ሲኾን፣ በትዳር ዓለም ላይ ያለና ያገባ የነበረ ከኾነ ደግሞ ተወግሮ መሞትን ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን፤ (ያላገቡ እንደሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፋዋቸው በነርሱም በአላህ ፍርድ ርኅራኄ አትያዛችሁ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደ ሆናችሁ በምእምናን (አትራሩ)፤ ቅጣታቸውንም ከምእመናን ጭፍሮች ይገኙበት።" (ሱረቱ-ኑር 2)፡፡
ዝሙትን በዚህ መልኩ ያወገዘና ለዝሙተኞች ቅጣትን የደነገገ ሃይማኖት ተመልሶ በጀነት ውስጥ ለአማኞች ይፈቅዳል ብሎ ማሰብ ከጤነኞች አይጠበቅም፡፡
2/ ፈጣሪ አምላካችን አላህ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አማኝ ባሪያዎቹን ሲያወድሳቸው ከፊል ባሕሪያቸውን በማውሳት ነው፡፡ ከነዚህም ባሕሪያት መካከል አንዱ ‹‹ከዝሙት የራቁና ብልቶቻቸውን የጠበቁ›› መሆናቸውን በመግለጽ ነው፡፡ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
"ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)….እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡" (ሱረቱል ሙእሚኑን 1–5)፡፡
"የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ ሰላም የሚሉት ናቸው…እነዚያም፣ ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፤ #የማያመነዝሩትም ናቸው፤ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል።" (ሱረቱል ፉርቃን 63–68)፡፡
ኢስላም ዝሙትን የሚያወግዘው በዚህ መልኩ ነው፡፡
3/ በጀነት ውስጥ ለአማኞች ወንዶችና ሴቶች የተደገሱ ጸጋዎች በጥቅሉ በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም ጸጋዎች መንፈሳዊና ስጋዊ ጸጋ በመባል ለሁለት ይከፈላሉ፡፡ ከመንፈሳዊ ጸጋዎች መካከል፡- ፈጣሪ አምላካችንን ማየት፣ የሱን ውዴታ ማግኘትና መርካት፣ የሰላምታና የምስጋና ቃሉን መስማት፣ የነቢያትን ጉርብትና መጎናጸፍ፣ በእምነት ከተከተሉን ቤተሰቦችና ጓደኞች ጋር አንድ ላይ መኾን ወዘተ…፡፡ ከስጋዊ ጸጋዎቹ መካከል ደግሞ፡- የጀነት መብልና መጠጦች፣ የክብር መገለጫ የኾኑ ባለ አጎበር አልጋዎችና ጠረጴዛዎች፣ ለመጠጥነት የሚያገለግሉ የማር፣ የወተት፣የኸምርና የውሃ ወንዞች፣ የትዳር አጋሮች ወዘተ ….ናቸው፡፡ ስለ ዝርዝር መረጃው ይህን ሊንክ በመጫን ያንብቡ:–
ጀነት እና ጸጋዎቿ
ክፍል አንድhttp://on.fb.me/1p6bF0V
ክፍል ሁለትhttp://on.fb.me/1QBGPqe
ክፍል ሶስትhttp://on.fb.me/1R4JXYM
በወገኖቻችን ዘንድ አዋራ ያስነሳውና ለትችትና ለስድብ ይጠቅመናል ብለው የተንጠለጠሉትም የትዳር አጋሮች የሚለው ላይ ነው፡፡ ለዚህ ትችት መነሻቸው በሉቃስ ወንጌል ላይ የሰፈረው ‹‹ያንን ዓለም ለማየት የተገቡት ግን አያገቡም፣ አይጋቡም›› የሚለውና፡ ‹‹ስጋና ደም የእግዚአብሄርን መንግስት አይወርሱም›› ከሚለው የጳውሎስ ንግግር ተነስተው ነው፡፡
ችግሩም እሱ ነው፡፡ የሰዎችን ፊት በተሰነጠቀ መስታወት ለማየት የሚሞክር ሰው፡ በውጤቱ የሚያገኘው መጥፎ የፊት ገጽታን እንጂ፡ ጥሩ ምስልን አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ቁርኣንን ለመረዳትና ለማረቅ መሞከር፡ እጅግ ሲበዛ ስህተት ነው፡፡ ስለ ጀነት ጸጋዎች፡ በውስጥዋ ምን እንዳለ ምንም ያልተነፈሰና ዝርዝር ነገር የሌለው መጽሐፍ፡ ሌላውን ለማውገዝ ምን መነሻ ይኖረዋል?
እኛ ሙስሊሞች የሙታን ትንሳኤ በመንፈስ ብቻ ሳይኾን በአካልም ጭምር እንደኾነ ነው የምናምነው፡፡ በመቃብር ዓለም የበሰበሰውና አፈር የኾነው ገላችን፡ በዛው በስብሶ አይቀርም፡፡ ሩሐችን ወደ አካሉ በመመለስ ዳግም ነፍስን በመዝራት ከነ-ሙሉ ሰውነቱ ይቀሰቀሳል፡፡ በጌታው ዘንድም ለፍርድ ይቀርባል፡፡ አካል ከመቃብር መቀስቀሱን ካመን ደግሞ፡ የሚቀሰቀስበት ዓላማ በምድር ላይ ለፈጸመው ጥፋት ቅጣትን፣ ወይም ለሠራው መልካም ስራ ድነትን ይቀበል ዘንድ ነው፡፡ እንደዛ ከኾነ፡ የጀሀነም ቅጣትና የጀነት ጸጋ፡ በመንፈስ ብቻም ሳይኾን በስጋም ጭምር ይኾናል ማለት ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ነው፡ በጀነት ውስጥ ከመንፈሳዊ ጸጋዎች በተጨማሪም ስጋዊ ጸጋዎች የተዘጋጁት፡፡
4/ በጀነት ያሉ ከወንዶች ጋር ተጣማሪ የሚባሉ እንስቶች(የትዳር አጋሮች) ሁለት አይነት ናቸው፡፡ ከአደም ዘር የኾኑ የሰው ሴት ልጆች እና በጀነት የተፈጠሩ እንስቶች (ሑረል-ዒኖች) ይባላሉ፡፡ ወገኖቻችን የጠቃቀሷቸው የቁርኣን ክፍሎች በጠቅላላ የሚናገሩት ስለነዚህ ሑረል-ዒን ተብለው ስለተጠሩት የሚያወሩ ናቸው፡፡ ኾኖም በአንዱም ጥቅስ ላይ ዝሙትን የሚገልጽና የሚፈቅድ ነገር ሽታው እንኳ የለም፡፡ ይበልጥ ለመረዳት ጥቅሶቹን እናቅርባቸው፡-
ሀ/ "እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው፡፡ ከርሷ ከፍሬ (ዓይነት) ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር (ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ) «ይህ ያ ከአሁን በፊት የተመገብነው ነው» ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጡት፡፡ ለነሱም በውስጧ ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች አሏቸው፡፡ እነሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 25)፡፡
ይህ ጥቅስ በግልጽ የሚያስረዳው፡- በአላህ ያመኑና መልካምን የሰሩ ሙስሊሞች፡ በጀነት ዓለም ውስጥ፡- የተለያዩ ፈሳሽ ወንዞች፣ ለመብልነት የሚያገለግሉ፡ ጣእማቸው ጣፋጭ የተደረጉ ፍራፍሬዎች፣ ከእርኩሰትና ከቁሻሻ ነገር ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች መኖራቸውን ነው፡፡ ታዲያ በዚህ አንቀጽ ሥር ዝሙትን የሚወክለው የትኛው ገለጻ ነው? አንቀጹ የሚናገረው ‹‹ንጹህ ተደረጉ ሚስቶች›› በማለት ስለ ትዳር አጋር እንጂ፡ ‹‹ለዝሙት የተደገሱ እንስቶች›› በማለት ስለ ዝሙት አያወራም፡፡ ወይንስ ከትዳር አጋር ጋር ግብረ–ሥጋ ግኑኝነት ማድረግ ፍቁድ የሆነው: በዚህ ምድር ላይ ብቻ ነው ልትሉን አስባችሁ ነው? በዚህ ምድር ላይ ትዳርንና በመሀከላቸው የፍቅር ጨዋታን የፈቀደው አላህ: ይኸው ስርአት በጀነት መቀጠሉን መግለፁ እንዴት ዝሙት ሊያሰኘው ይችላል?
ለ/ "ጥንቁቆቹ