የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.2K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
በቀዷ ወል-ቀደር ማመን ማለት፡- በዚህ ዓለም ላይ የሚከሰት ማንኛውም ክስተት ጥሩም ሆነ መጥፎ፡ ከሰውም ይገኝ ከእንሰሳት፣ ከመላእክትም ይገኝ ከጂንኒዎች (አጋንንት)፣ ከበራሪዎችም ይሁን ከነፍሳት፣ በፈቃድና በምርጫም የተገኘ ይሁን በግዳጅ፡ አጠቃላይ ጉዳዩ አስቀድሞ አላህ ዘንድ የታወቀ፡ መጀመሪያውኑም በለውሐል መሕፉዝ (ጥብቅ ሰሌዳ) ላይ ተወስኖ የተጻፈ፡ የተጻፈለት ጊዜ በደረሰ ሰአት በአላህ ፈቃድና ይሁንታ የሚከናወን ነው ብሎ ማመን ማለት ነው፡፡

ከመፅሀፉ የተወሰደ

ከነገ ጀምሮ መፅሀፉ ገበያ ላይ ይውላል።
👍1
ዐረፋ ደረሰ

በአቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

የዐረፋ ቀን የሚባለው የዙል-ሒጃ 9ኛ ቀን ነው፡፡ ሓጅ አድራጊዎች ያለ ፆም በዐረፋ ተራራ ላይ ከእኩለ-ቀን (ዙህር) አንስቶ መግሪብ እስኪደርስ ይቆያሉ: በዱዓም ጌታቸውን ይማጸናሉ፡፡ ዙህርንና ዐሱርንም በአንድ ላይ ወደ ዙህር በማምጣት አሳጥረው ይሰግዳሉ፡፡ ጌታቸውም ወደነሱ ይቀርባል፡፡ በዚያም ቀን ብዙዎች በክፉ ተግባራቸው እሳት የተገባቸው: በአላህ ቸርነት ከእሳት ነጻ ይባላሉ፡፡ ሓጅ ያላደረጉት ደግሞ ቀኑን በፆምና በተለያየ ዒዳባህ ያሳልፉታል፡፡
ይህ ቀን ከሌሎች ቀናት ከሚለይባቸው ውስጥ፡-

1. ዲኑ የተሟላበት ቀን መሆኑ፡-

"...الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا..." سورة المائدة 3
"…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ…" (ሱረቱል ማኢዳህ 5:3)፡፡

ይህ ቅዱስ አንቀጽ የወረደው በዙል ሒጃ ወር፡ ሐጀተል ወዳዕ(የመሰናበቻው ሐጅ) በ 9ኛው ቀን: በዕለተ ጁምዓ በዐረፋ ተራራ ላይ ነበር፡፡

2. የሙስሊሞች ዒድ መሆኑ:–

ዑቅበተ ኢብኑ ዐሚር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን፣ የእርዱ ቀን፣ ቀጣዮቹም 3ቱ ቀናት የኛ ዒዳችን ነው" (ሶሒሑል ጃሚዕ 8192)።

3. ፆሙ የሁለት አመት ኃጢአት ያስምራል:–

አቢ ቀታዳህ እንዳሉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም የሁለት ዐመት (ያለፈውንና የሚመጣውን) ኃጢአት ያስምራል" (ከቡኻሪ በስተቀር ሁሉም የዘገበው)፡፡

4. ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን መሆኑ:–

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከዐረፋ ቀን ተሸሎ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን የለም" (ሙስሊም)፡፡

5/ ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ በዚህ ቀን መሆኑ:–

በማንኛውም ቀንና ለሊት፣ በማንኛውም ስፍራና ሁኔታ ወደ አላህ የሚደረገው ዱዓ በሩ ክፍት ነው። ተመላሽነት የለውም። ሆኖም በዐረፋ ቀን የሚደረገው ዱዓእ ግን ከየትኛውም ቀን የተሻለ ነው። ከዐብዱላህ ኢብኑ አምሩ ኢብኑል–ዓስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:– "ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓእ ነው፡፡ እኔና ከበፊቴ የነበሩት ነቢያት ከተናገርነው ቃላት ሁሉ በላጩ፡- ‹‹ላ ኢላሀ ኢልለሏሁ፡ ወሕደሁ፡ ላ-ሸሪከ ለህ፣ ለሁል-ሙልኩ፡ ወለሁል-ሐምድ፣ ወሁወ ዐላ-ኩሊ ሸይኢን ቀዲር›› የሚለው ነው" (ቲርሚዚይ 3585፣ ሶሒሑል-ጃሚዕ 3274)፡፡

6/ ለአምስት ቀናት የሚቆየው ተክቢራም የሚጀምረው በዚሁ በዐረፋ በዘጠነኛው ቀን ፈጅር ሶላት ጀምሮ ስለሆነ: በዚሁ ቀን ከፈርድ ሶላት በኋላ ሶስት ጊዜ አስተግፊሩላህ እንበልና ከዛም አላሁመ አንተ–ሰላም ...... ካልን በኋላ በቀጥታ ወደ ተክቢሩ በመግባት:– "አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር። ላ ኢላሀ ኢልለሏህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ" እንበል።

ዑዝር ላይ ላሉ ወንድም/እሕቶች:–

የዐረፋን ቀን ፆም ከልቡ ለመፆም የወሰነ ወንድም/እሕት፣ ነገር ግን በዑዝር ሰበብ (በሽታ፣ ሰፈር፣ ሐይድ፣ የወሊድ ደም፣ ወዘተ) ቀኑን መፆም ባይችልስ? ለሚለው ሸይኽ ስዑድ ከረመዷን ዐሽሩል አዋኺር ጋር ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው መልስ ስለሰጡበት: መልሱን እንዲህ አቅርበነዋል:–

ተጠያቂው ሸይኽ ኻሊድ ቢን ሱዑድ

ጥያቄ፡- አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ሸይኽ! በሐይድ ላይ ያለች ሴት ወይም የወለደች እንዴት አድርጋ የረመዷንን የመጨረሻ አስር ቀናት መጠቀም ትችላለች? ያ ሸይኽ! እኔ በጣም በመጨናነቄ ሰበብ እርሶ እንዲረዱኝና እንዲሁም ሀሳቡና ጭንቀቱ እንዲቀልልኝ እፈልጋለሁ፡፡ አላህም የለይለቱል-ቀድርን ምንዳ እንዳይከለክለኝ ዱዓእ እንዲያረጉልኝ እማጸንዎታለሁ፡፡

ምላሽ፡- ወዐለይኩሙ-ሰላሙ ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ የተከበርሽ እህቴ! ከሁሉ በፊት ቀድመሽ ልታውቂው የሚገባ ነገር፡- የወር አበባና የወሊድ ደም አላህ እሱ ብቻ ለሚያውቀውና ለፈለገው ጥበብም በአንቺ ላይ የወሰነው የተፈጥሮ ህግ መሆኑን ነው፡፡ መልካም ነገር ደግሞ አላህ ላንቺ የመረጠልሽ ነገር እንጂ አንቺ ለራስሽ የመረጥሽው አይደለም፡፡ አላህ ለወሰነው (ቀዷ ወል-ቀደር) እጅ ስጪ፡፡ ደግሞም አንቺ ለነፍሲያሽ ከጓጓሽው በላይ አላህ ላንቺ አዛኝ ጌታ መሆኑን እርግጠኛ ሁኚ፡፡

በተጨማሪም ልታውቂው የሚገባ ነገር፡- አንድ ሰው በዑዝር ወቅት በሰላም ጊዜ ይፈጽመው የነበረውን ነገር መቀጠል ቢያቅተው እንኳ አጅሩ ግን እንደማይቋረጥበት ነው፡፡ ተወዳጁ የአላህ ነቢይም (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡- "አንድ የአላህ ባሪያ ከታመመ ወይም ከመኖሪያ ክልል ርቆ (ሙሳፊር የሚሰኝበትን ያህል) ከተጓዘ: ጤነኛና የአካባቢው ነዋሪ ሆኖ ይፈጽመው የነበረው (መልካም ስራ) ሳይቋረጥ ይጻፍለታል" (ቡኻሪይ 2996)፡፡

አንቺ ደግሞ በሐይድ ወቅት ያለ ጥርጥር ዑዝር ያለሽ ነሽ፡፡ ምክንያቱም፡- ያለ ምርጫሽና ፍላጎትሽ የመጣ በመሆኑ፡፡ እንዲሁም ልትከላከዪውና ልታስቀሪው የማትችዪው ነገር ስለሆነ፡፡ በድጋሚም ማወቅ ያለብሽ ነገር፡- አንድ የአላህ ባሪያ አንድን ነገር ለመስራት ከልብ የቆረጠ ኒያ ካለው ከዛም ያንን የነየተውን ነገር ለመስራት ድንገተኛ ሁኔታና ክስተት ቢከለክለውና ቢያግደው፤ አላህ ግን እንደሰራው በመቁጠር ሙሉ አጅሩን የሚጽፍለት መሆኑን ነው፡፡ ይህንን አስመልክቶ የአላህ ነቢይም (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡-

"በመዲና ውስጥ ሰዎች አሉ፡፡ እናንተ አንድንም ሸለቆ አታቋርጡም መንገድንም አትዘልቁም እነሱ በአጅር ቢጋሯችሁ እንጂ፡፡ ከናንተው ጋር አብረው እንዳይጓዙ ዑዝር ከለከላቸው" (ቡኻሪይ)፡፡

በሌላ ቅዱስ ትምህርታቸው ላይ ደግሞ እንዲህ አሉ፡- "አላህን በፍጹም ልቡ ሸሂድነትን (ለዲን ሰማእት ሆኖ መሞትን) እንዲወፍቀው የለመነ ሰው ቀኑ ደርሶ በፍራሹ ላይ እንኳ ቢሞት(በኒያው ሰበብ) የሸሂዶችን (ሰማእታት) ደረጃ ያጎናጽፈዋል" (ሙስሊም)፡፡

ታዲያ አንቺም እንደ ሌሎቹ ሙስሊም እህቶችሽና ወንድሞችሽ እነዚህን አስር ቀናት በዒባዳ ለማሳለፍ ገና ከመጀመሪያው የነየትሽና የጓጓሽለት ከነበር ጌታሽ ኒያሽን ከንቱ እንደማያረግብሽ ባለሙሉ ተስፋ ሁኚ አብሽሪ፡፡

ሌላው ደግሞ ይህ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ሶላት ከመስገድ፣ ጾም ከመጾምና መስጂድ ከመግባት ቢያግድሽም ሌሎች ያልተከለከልሻቸው ዒባዳዎች መኖራቸውንም አትዘንጊ፡፡ ከነዚም መካከል፡- (ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር…) አዝካሮችን ማለት፣ ዱዓእ ማድረግ፣ በነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ላይ ሶላዋት ማውረድ፣ ሶደቃ ማውጣት፣ ኢስቲግፋር ማብዛት፣ በአላህ ስሞችና በሱ ስራዎች ማስተንተንን የመሳሰሉት፡፡
👍2👎1
በመጨረሻም ማወቅ ያለብሽ ነገር፡- እነዚህ አስር ቀናት በዑዝር ሰበብ ሊያመልጠኝ ነው ብለሽ ማሰብና መጨነቅሽ በራሱ የሚያመላክተው የኢማንሽን ታላቅነት፣ ወደ አላህ ለመቃረብ ያለሽን ጉጉት ነው ኢንሻአላህ፡፡ ስለዚህም የቻልሽውን ያህል ኸይር ስራ ለመስራት ታገዪ፣ ተረጋጊ አትጨናነቂ፣ አይዞሽ፣ አላህ ላይ ያለሽን ተስፋ ከፍ አድርጊ እሱ ኒያሽንም ሆነ መልካም ስራሽን አያባክነውም ምንዳውንም አይከለክልሽም፡፡ የሱ እዝነት አንቺን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን ሁሉ የሰፋና ያካለለ ነውና፡፡ ወሰሊላሁመ ወሰለም ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ ወዓላ ኣሊሂ ወሰሕቢሂ ወሰለም፡፡

ስለዚህ መጪው ሰኞ የዐረፋ ቀን ነውና ይህን ቀን እንጹመው እንዳያመልጠን፡፡ በእስር ያሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንንም እንዲሁም ዓለም ላይ ያሉ የሚሰቃዩትን ሙስሊሞችን በዱዓ እንዳንረሳቸው፡፡ አላህ ይወፍቀን አሚን፡፡

Click and Like ➤➤ http://fb.com/Ustaz.Abuhyder
1
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

እንኳን ለ1442ኛው የተከበረው ዒዱል አድሓ በዓል አላህ በሰላም አደረሳችሁ!

ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም ዒዱኩም ሙባረክ
ዐሹራእ ደረሰ

አቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

#ዐሹራእ ምንድነው?

ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አሥረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡

#ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው፡-

አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን (ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አሥረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡

#ለምን ይጾማል?

ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡
ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡

#ጥቅሙስ ምንድነው?

አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡ ሐዲሡ ዶዒፍ ነው የሚሉም አሉ ወላሁ አዕለም፡፡
ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡

#መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና?

የዐሹራእን ቀን መጾም ሑክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡

#መቼ እንጀምር?

የሙሐረም አስረኛው ቀን (ዐሹራእ) የፊታችን ረቡእ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ረቡእን ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡
ለ. ማቅሰኞና ረቡእን፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭና ሱንና ነው፡፡
ሐ. ከ ማቅሰኞ-ሀሙስ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህም በላጩ ነው፡፡
መ. ረቡእና ሀሙስን፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ 9ኛውን ቀን ጁምዓህ ለመፆም ያልተመቸው 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል፡፡
አላህ ይወፍቀን፡፡
Click and Like ➤➤
https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
👍3
📢የዘንድሮ -1443ዓ.ሂ
ዓሹራ መች ነው?
ሙሐረም አንድ ያለው ማክሰኞ ሲሆን ዓሹራ ሐሙስ ቀን እንደሚሆን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት የዘንድሮ ዓሹራ (10ኛው ቀን) የፊታችን ሐሙስ ማለትም ነሐሴ 13/2013 ይሆናል።
👍31
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የማርያም ልጅ (እየሱስ) ማንነት
በኡስታዝ አቡ ሐይደር
https://youtu.be/iYByEhlpbBQ
https://youtu.be/iYByEhlpbBQ
👍61
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከጦርነት መሸሽ በኢስላም ያለው ቦታ በኡስታዝ አቡ ሐይደር
https://youtu.be/ZmKueur2KMU 21:46
👍4
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ውድና የተከበራችሁ ተናፋቂ ሙስሊም ወንድሞቼና እሕቶቼ! እንደምን ከረማችሁ?

ለረጅም ጊዜ ያህል ከሚዲያ የቀጥታ ትምሕርት ጠፍቼ ነበር። በአላህ ፈቃድ ከፊታችን ማቅሰኞ ጀምሮ በሳምንት ለሶስት ተከታታይ ቀናት በተለመደው ፔጃችን እንጀምራለን ኢንሻአላህ።

ትምሕርቱም በሙሐደራ መልክ ሳይሆን በረመዷን ምንነት ዙሪያ የተዘጋጀ ባለ 64 ገፅ አነስተኛ ኪታብን በመቅራት ይሆናል። ኪታቡንም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማውረድ ወይንም በቴሌግራም ግሩፕ ውስጥ የሚለቀቀውን በማውረድ መከታተል ትችላላችሁ!

የትምሕርት ቀንና ሰአቱ ከማቅሰኞ–ሐሙስ በኢትዮጲያ አቆጣጠር ከምሽቱ 3:30 የሚጀምር ይሆናል።

https://www.noor-book.com/en/ebook-%D8%A7%D8%AD%D9%83%D8%A7%D9%85-%D8%A7%D9%84%D8%B5%D9%8A%D8%A7%D9%85-%D9%88%D8%A7%D9%84%D9%82%D9%8A%D8%A7%D9%85-%D9%88%D8%B2%D9%83%D8%A7%D9%87-%D8%A7%D9%84%D9%81%D8%B7%D8%B1--pdf

Click and Like ➤➤
https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
👍2
Audio
አዲስ ተከታታይ ደርስ ስለ ረመዷን ምንነት

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join ➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
2👍2