በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር። የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር።" (ሱረቱ-ሷፍፋት 37፡50-57)፡፡
® የጥላቻ አለመኖር፡- "በደረቶቻቸው ውስጥ ያለውንም ጥላቻ እናስወግዳለን፤ ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ፤ ለዚያም ወደዚህ (ላደረሰን ሥራ) ለመራን አላህ ምስጋና ይገባው፤ አላህ ባልመራንም ኖሮ አንመራም ነበር፤ የጌታችን መልክተኞች በእውነት ላይ ሲኾኑ በእርግጥ መጥተውልናል ይላሉ ይህቻችሁም ገነት ትሰሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ።" (ሱረቱል አዕራፍ 7፡43)፡፡
"ባልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚቀጣጩ ወንድማማቾች ኾነው በደረቶቻቸው ውስጥ ከቂም ያለውን ሁሉ እናስወግዳለን፡፡ በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካቸውም፡፡ እነሱም ከእርሷ የሚወጡ አይደሉም፡፡" (ሱረቱል ሒጅር 15፡47-48)፡፡
® ሰላም እንጂ ረብሽ የለም፡- "ግን የተጸጸተና ያመነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰዉ እነዚህ ገነትን ይገባሉ፤ አንዳችንም አይበደሉም። የመኖሪያን ገነቶች፣ ያችን አልረሕማን ለባሮቹ በሩቅ ኾነዉ ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸዉን፣ (ይገባሉ) እርሱ ተስፋዉ ተፈጻሚ ነዉና፤ በርሷ ሰላምን እንጂ ዉድ ቅን ነገር አይሰሙም፤ ለነሱም በርሷ ዉስጥ፣ ጧትም ማታም ሲሳያቸዉ አላቸዉ።" (ሱረቱ መርየም 19፡60-62)፡፡
® ሕይወት ዘላለማዊ ነው፡- "እነዚያንም ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘለዓለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእርግጥ እናስገባቸዋለን…" (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡57)፡፡
አቢሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ አሉ፡- "አንድ ተጣሪ (መልአክ) እንዲህ በማለት ይጣራል፡- (የጀነት ሰዎች ሆይ!) ከአሁን በኋላ ሁሌም ጤነኛ ናችሁ፡ ለዘልዓለም አትታመሙም፣ ሁሌም ሕያው ናችሁ ፈጽሞ አትሞቱም፣ ሁሌም ወጣት ናችሁ ፈጽሞ አታረጁም፣ ሁሌም ተጠቃሚዎች ናችሁ ፈጽሞ አትቸገሩም" (ሙስሊም የዘገበው)፡፡
ከዛ ውጭ አንተ ከየትም ለቃቅመህ የሞነጫጨርካቸው ጥቅሶች: ስለ ዝሙት ሳይሆን ከትዳር አጋሮቻችን ጋር በጀነት ስለምናሳልፈው ስጋዊ ፀጋ ነው የሚስተምሩት። እነዚያም የትዳር አጋሮቻችን በምድር ላይ አብረውን የነበሩ: በእምነት እስከመጨረሻው ፀንተው የሞቱ ሚስቶቻችን እና: በጀነት ለአማኞች የተዘጋጁ እንስቶች (ሑረል ዒን) ናቸው። ከዛ ውጭ ዝሙት የአንተና የተከታዮችህ እምነት መገለጫ እንጂ የሙስሊሞች እምነት አይደለም።
ንሰሀ የምንገባው ወደ ፈጠረን አላህ እ ጂ ወደ ተፈጠረው ኢየሱስ አይደለም። ቅጣትም ምሕረትም የአላህ ስልጣን ብቻ ነው። ወገኔ በእሳት ላይ ቆመህ እየጨፈርክ ነው። ከነገው ፍርድ ለማምለጥ ወደ ተፈጠርክበት ኢስላም በቶሎ ተመለስ። አላህ ልብ ይስጥህ።
Join us➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

ትዳርን ከዝሙት መለየት ያልቻሉ አዕምሮዎች!!
በአቡ ሀይደር
በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው
1/ ዝሙት ህገ-ወጥነት ነው፡፡ ህገ-ወጥነት ደግሞ ከህጋዊነት የሚለየው በሕግ መነጽር ሲታይ ነው፡፡ ያ ህግ ደግሞ ፍጹም መለኮታዊ የኾነው የአላህ ህግና መመሪያ ነው፡፡ እኛ ሁላችንም የአላህ ፍጥረትና ባሪያ በመኾናችን፡ ሕይወታችንን እንዴት መምራት እንዳለብን፣ በምን አይነት ስርአት መመላለስ እንዳለብን ህግን የሚደነግገው ጌታ አላህ ነው፡፡ በመኾኑም ይህ ጌታ የፈቀደው ሁሉ፡ መልካምና ህጋዊ ሲኾን፡ እሱ ያወገዘው ነገር በጠቅላላ ደግሞ ህገ-ወጥ ይባላል፡፡
ከዚህ እውነት ተነስተን ነው የአንድን ነገር ህጋዊነትና ህገ-ወጥነትን መለየት የምንችለው፡፡ አለበዚያ ማንም ከመሬት ተነስቶ፡ ለራሱ ስሜት ስላልተመቸው፣ ወይም እሱ በሚከተለው እምነት ስለሌለ ብቻ፡ አንድን ነገር ማውገዝ አይችልም፡፡ ይህ ጭፍንነት ነው፡፡ ዝሙት የሚባለው፡- አላህ ያልፈቀደው፣ በወንድና ሴት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት ነው፡፡ ይህን ግኑኝነት ቁርኣን እንዲህ ብሎ ይገልጸዋል፡-
"ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!" (ሱረቱል ኢስራእ 32)፡፡
ኢስላም ዝሙትን ማውገዝና መከልከል ብቻም ሳይኾን፡ በዚህ ተግባሩ ላይ ኾኖ፡ ተውበት ከማድረጉ (ንሰሀ ከመግባቱ) በፊት፡ በአራት የአይን ምስክሮች እጅ ከፍንጅ የተያዘንም ሰው ቅጣትን ደንግጎበታል፡፡ ቅጣቱም ትዳር የሌለው ሰው ከኾነ መቶ ግርፋትን መገረፍ ሲኾን፣ በትዳር ዓለም ላይ ያለና ያገባ የነበረ ከኾነ ደግሞ ተወግሮ መሞትን ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን፤ (ያላገቡ እንደሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፋዋቸው በነርሱም በአላህ ፍርድ ርኅራኄ አትያዛችሁ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደ ሆናችሁ በምእምናን (አትራሩ)፤ ቅጣታቸውንም ከምእመናን ጭፍሮች ይገኙበት።" (ሱረቱ-ኑር 2)፡፡
ዝሙትን በዚህ መልኩ ያወገዘና ለዝሙተኞች ቅጣትን የደነገገ ሃይማኖት ተመልሶ በጀነት ውስጥ ለአማኞች ይፈቅዳል ብሎ ማሰብ ከጤነኞች አይጠበቅም፡፡
2/ ፈጣሪ አምላካችን አላህ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አማኝ ባሪያዎቹን ሲያወድሳቸው ከፊል ባሕሪያቸውን በማውሳት ነው፡፡ ከነዚህም ባሕሪያት መካከል አንዱ ‹‹ከዝሙት የራቁና ብልቶቻቸውን የጠበቁ›› መሆናቸውን በመግለጽ ነው፡፡ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
"ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)….እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡" (ሱረቱል ሙእሚኑን 1–5)፡፡
"የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ ሰላም የሚሉት ናቸው…እነዚያም፣ ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፤ #የማያመነዝሩትም ናቸው፤ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል።" (ሱረቱል ፉርቃን 63–68)፡፡
ኢስላም ዝሙትን የሚያወግዘው በዚህ መልኩ ነው፡፡
3/ በጀነት ውስጥ ለአማኞች ወንዶችና ሴቶች የተደገሱ ጸጋዎች በጥቅሉ በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም ጸጋዎች መንፈሳዊና ስጋዊ ጸጋ በመባል ለሁለት ይከፈላሉ፡፡ ከመንፈሳዊ ጸጋዎች መካከል፡- ፈጣሪ አምላካችንን ማየት፣ የሱን ውዴታ ማግኘትና መርካት፣ የሰላምታና የምስጋና ቃሉን መስማት፣ የነቢያትን ጉርብትና መጎናጸፍ፣ በእምነት ከተከተሉን ቤተሰቦችና ጓደኞች ጋር አንድ ላይ መኾን ወዘተ…፡፡ ከስጋዊ ጸጋዎቹ መካከል ደግሞ፡- የጀነት መብልና መጠጦች፣ የክብር መገለጫ የኾኑ ባለ አጎበር አልጋዎችና ጠረጴዛዎች፣ ለመጠጥነት የሚያገለግሉ የማር፣ የወተት፣የኸምርና የውሃ ወንዞች፣ የትዳር አጋሮች ወዘተ ….ናቸው፡፡ ስለ ዝርዝር መረጃው ይህን ሊንክ በመጫን ያንብቡ:–
ጀነት እና ጸጋዎቿ
ክፍል አንድhttp://on.fb.me/1p6bF0V
ክፍል ሁለትhttp://on.fb.me/1QBGPqe
ክፍል ሶስትhttp://on.fb.me/1R4JXYM
በወገኖቻችን ዘንድ አዋራ ያስነሳውና ለትችትና ለስድብ ይጠቅመናል ብለው የተንጠለጠሉትም የትዳር አጋሮች የሚለው ላይ ነው፡፡ ለዚህ ትችት መነሻቸው በሉቃስ ወንጌል ላይ የሰፈረው ‹‹ያንን ዓለም ለማየት የተገቡት ግን አያገቡም፣ አይጋቡም›› የሚለውና፡ ‹‹ስጋና ደም የእግዚአብሄርን መንግስት አይወርሱም›› ከሚለው የጳውሎስ ንግግር ተነስተው ነው፡፡
ችግሩም እሱ ነው፡፡ የሰዎችን ፊት በተሰነጠቀ መስታወት ለማየት የሚሞክር ሰው፡ በውጤቱ የሚያገኘው መጥፎ የፊት ገጽታን እንጂ፡ ጥሩ ምስልን አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ቁርኣንን ለመረዳትና ለማረቅ መሞከር፡ እጅግ ሲበዛ ስህተት ነው፡፡ ስለ ጀነት ጸጋዎች፡ በውስጥዋ ምን እንዳለ ምንም ያልተነፈሰና ዝርዝር ነገር የሌለው መጽሐፍ፡ ሌላውን ለማውገዝ ምን መነሻ ይኖረዋል?
እኛ ሙስሊሞች የሙታን ትንሳኤ በመንፈስ ብቻ ሳይኾን በአካልም ጭምር እንደኾነ ነው የምናምነው፡፡ በመቃብር ዓለም የበሰበሰውና አፈር የኾነው ገላችን፡ በዛው በስብሶ አይቀርም፡፡ ሩሐችን ወደ አካሉ በመመለስ ዳግም ነፍስን በመዝራት ከነ-ሙሉ ሰውነቱ ይቀሰቀሳል፡፡ በጌታው ዘንድም ለፍርድ ይቀርባል፡፡ አካል ከመቃብር መቀስቀሱን ካመን ደግሞ፡ የሚቀሰቀስበት ዓላማ በምድር ላይ ለፈጸመው ጥፋት ቅጣትን፣ ወይም ለሠራው መልካም ስራ ድነትን ይቀበል ዘንድ ነው፡፡ እንደዛ ከኾነ፡ የጀሀነም ቅጣትና የጀነት ጸጋ፡ በመንፈስ ብቻም ሳይኾን በስጋም ጭምር ይኾናል ማለት ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ነው፡ በጀነት ውስጥ ከመንፈሳዊ ጸጋዎች በተጨማሪም ስጋዊ ጸጋዎች የተዘጋጁት፡፡
4/ በጀነት ያሉ ከወንዶች ጋር ተጣማሪ የሚባሉ እንስቶች(የትዳር አጋሮች) ሁለት አይነት ናቸው፡፡ ከአደም ዘር የኾኑ የሰው ሴት ልጆች እና በጀነት የተፈጠሩ እንስቶች (ሑረል-ዒኖች) ይባላሉ፡፡ ወገኖቻችን የጠቃቀሷቸው የቁርኣን ክፍሎች በጠቅላላ የሚናገሩት ስለነዚህ ሑረል-ዒን ተብለው ስለተጠሩት የሚያወሩ ናቸው፡፡ ኾኖም በአንዱም ጥቅስ ላይ ዝሙትን የሚገልጽና የሚፈቅድ ነገር ሽታው እንኳ የለም፡፡ ይበልጥ ለመረዳት ጥቅሶቹን እናቅርባቸው፡-
ሀ/ "እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው፡፡ ከርሷ ከፍሬ (ዓይነት) ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር (ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ) «ይህ ያ ከአሁን በፊት የተመገብነው ነው» ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጡት፡፡ ለነሱም በውስጧ ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች አሏቸው፡፡ እነሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 25)፡፡
ይህ ጥቅስ በግልጽ የሚያስረዳው፡- በአላህ ያመኑና መልካምን የሰሩ ሙስሊሞች፡ በጀነት ዓለም ውስጥ፡- የተለያዩ ፈሳሽ ወንዞች፣ ለመብልነት የሚያገለግሉ፡ ጣእማቸው ጣፋጭ የተደረጉ ፍራፍሬዎች፣ ከእርኩሰትና ከቁሻሻ ነገር ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች መኖራቸውን ነው፡፡ ታዲያ በዚህ አንቀጽ ሥር ዝሙትን የሚወክለው የትኛው ገለጻ ነው? አንቀጹ የሚናገረው ‹‹ንጹህ ተደረጉ ሚስቶች›› በማለት ስለ ትዳር አጋር እንጂ፡ ‹‹ለዝሙት የተደገሱ እንስቶች›› በማለት ስለ ዝሙት አያወራም፡፡ ወይንስ ከትዳር አጋር ጋር ግብረ–ሥጋ ግኑኝነት ማድረግ ፍቁድ የሆነው: በዚህ ምድር ላይ ብቻ ነው ልትሉን አስባችሁ ነው? በዚህ ምድር ላይ ትዳርንና በመሀከላቸው የፍቅር ጨዋታን የፈቀደው አላህ: ይኸው ስርአት በጀነት መቀጠሉን መግለፁ እንዴት ዝሙት ሊያሰኘው ይችላል?
ለ/ "ጥንቁቆቹ

ለ/ " ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡ (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡" (ሱረቱ-ዱኻን 44፡51-53)፡፡
ሐ/ "በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ኾነው (በገነት ይኖራሉ)፡፡ ዓይናማዎች በኾኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡ እነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በእምነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን በእነርሱ እናስጠጋለን፡፡ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፡፡ ሰው ሁሉ በሠራው ሥራ ተያዢ ነው፡፡" (ሱረቱ-ጡር 52፡21-22)
መ/ "ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡ ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡" (ሱረቱል ዋቂዓህ 56፡21-22)፡፡
ሠ/ "ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡ አትክልቶችና ወይኖችም፡፡ እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡ የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡ በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡" (ሱረቱ ነበእ 78፡31-35)፡፡

ረ/ "በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡ " (ሱረቱ-ራሕማን 55፡70-73)፡፡
እነዚህ ጥቅሶች በጠቅላላ መልእክታቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ እሱም፡- በጀነት የሚኖሩ አማኝ የአላህ ባሪያዎች ፡ ከወንዞች፣ ከፍራፍሬዎች፣ ከውብ ማረፊያዎች በተጨማሪ የትዳር አጋር እንዳላቸው የሚገልጽ ነው፡፡ ስለነዚህ የትዳር አጋር የሚኾኑት (ሑረል-ዒን) ገጽታና መልክ ሲገልጽ፡- ልክ እንደ ተሸፈነ ሉል የሚመስሉ፡ ባለ ነጫጭ አይናማዎች፡ ጡተ ጉቻማዎች፣ ጠባየ መልካሞችና ማንም ያልነካቸው ደናግሎች መኾናቸውን ነው የዘረዘረው፡፡ በጥቅሱ ላይ ምንም አይነት ስህተትም ሆነ ለነቀፌታ የሚያገለግል ሀሳብ የለም፡፡ ዝሙት የሚለውም ሀሳቡም ሽታውም የለም፡፡ ምክንያቱም ቃሉ የሚናገረው ስለ ትዳር-አጋሮች (ሚስቶች) ነውና፡፡
5/ በተጨማሪም በጀነት ውስጥ ከትዳር አጋር ጋር ግብረ–ሥጋ ግኑኝነት መፈፀሙ: በምንም መልኩ ነውር እንዳልኾነ ለመረዳት: የአደምና የሐዋእን ታሪክ ማየቱ ጠቃሚ ነው። እነዚህ ሁለት ወላጆቻችን በጀነት ነበር የሚኖሩት። ጌታ አላህ ከአደም የጎን አጥንት ሐዋእን በመፍጠር: ለአባታችን አደም ሚስት ትሆነው ዘንድ ለግሶታል። ታዲያ አደም ሚስት ትኾነው ዘንድ ሐዋእን የተሰጠው: እንደ ፎቶ ቅርጽዋንና መልኳን እያየ ሊያደንቃት ነው? ወይስ እንደ አባት ሆኖ ሊያሳድጋት ነው? እውነታው ግን አደም አጋር ስለሚያስፈልገው: እራሱንም በማርካትና ትውልድንም በመተካት የሰው ዘር ቀጣይነት እንዲኖረው ነው። ታዲያ በአደምና ሐዋእ መካከል በጀነት ውስጥ የግብረ–ሥጋ ግኑኝነት መኖሩን ከተቀበልን: ለምን ተመልሰን በጀነት ውስጥ ስለ ትዳር አጋር የሚናገረውን የቁርኣን ክፍል እንቃወማለን??
6/ ጉዳዩ ከዝሙት ጋር ምንም ግኑኝነት እንደሌለው የምንረዳበት ሌላው መንገድ: ቅዱስ ቁርኣን ስለነዚህ ሴት ሑረል ዒኖች ባሕሪ ሲናገር "አይናቸውን አሳጣሪዎች) ብሎ መግለጹ ነው። ይህ ማለት:– እነዚህ ሴቶች ከባሎቻቸው ውጭ ከሌላ ጋር ሊወሰልቱ ይቅርና: አይናቸው እንኳ ከባሎቻቸው ውጭ ወደማንም ዘወር እንደማይል ነው። ጉዳዩ ዝሙት ቢሆን ኖሮ: አይናቸው በትዳር አጋራቸው ላይ ብቻ ባልታጠረና: የማንም መጫወቻ በኾኑ ነበር። የአላህ ቃል እንዲህ ይላል:–
"እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡" (ሱረቱ አልሷፍፋት 48)።
"እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች እኩያዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡" (ሱረቱ ሷድ 52)።
"በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡" (ሱረቱ አል ረሕማን - 56)
የወገኖቻችን ችግር፡ ኢስላምን መመልከትና መረዳት የሚፈልጉት፡ በነፃ አዕምሮ ሳይኾን: በጭፍን ጥላቻና በተቃኙበት ክርስቲያናዊ ምልክታ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሸውራራ ምልከታ ነው፡፡ በጀነት ጸጋዎች ዙሪያ እንኳን ሌላውን ልትተቹበት ይቅርና፡ እናንተን ማርካት በሚችል መልኩ በመጽሐፋችሁ የቀረበ ምንም ዝርዝር ነገር የለውም፡፡ እናንተም መጽሐፋችሁን ተከትላችሁ ዝም ማለት ነበር የሚገባችሁ፡፡ እኛ ግን ትንሳኤ በስጋም ጭምር ነው ብለን ስለምናምና መጽሐፉም ስለሚነግረን፡ በጀነት ውስጥ መንፈሳዊና ስጋዊ ጸጋ መኖሩን እናምናለን፡፡ በዛው መልኩም በጀሀነም እሳት ውስጥም ቅጣቱ፡ በመንፈስና በስጋም ጭምር ነው እንላለን፡፡ በጀነት ያለው ጸጋ በመንፈስ ብቻ፣ በጀሀነም ያለው ቅጣትም ደግሞ በመንፈስ ላይ ብቻ ቢሆን ኖሮ፡ የሙታን አካል ከመቃብር መነሳት አላስፈላጊ በኾነ ነበር፡፡ ምክንያቱም ሙታን ከመቃብር የሚቀሰቀሱት ለፍርድ ለመቅረብ ነውና፡፡ ፍርዱ ደግሞ መንፈስ ላይ ብቻ ቢኾን ኖሮ፡ አካልን መቀስቀሱ ትርጉም አልባ በኾነ ነበር፡፡ በስህተት ትምሕርት ላይ ሆናችሁ ሌላውን አታሳስቱ፡፡
ዝም ያልናችሁ ጥያቄያችሁ በአግባቡና በስርአቱ የማይቀርብ፣ በማሾፍና በስድብ የተሞላ፡ ለምሁራዊ ውይይት የማይጋብዝ በመኾኑ እንጂ፡ ለናንተ መልስ አጥተን ወይም የቀረቡት ጥቅሶች የሚያሳፍሩ ኾነው አይደለም፡፡ የምናፍረው እንዲህ አይነት ጥቅስ ቢኖረን ነበር፡-
መኃልየ. 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት።
² አንቺ የመኰንን ልጅ ሆይ፥ እግሮችሽ በጫማ ውስጥ እንዴት ውቦች ናቸው! ዳሌዎችሽስ በአንጥረኛ እጅ እንደ ተሠሩ እንደ ዕንቍዎች ይመስላሉ።
³ እንብርትሽ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት እንደ ተነጠጠ ጽዋ ነው፤ ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአበባም እንደ ታጠረ ነው።
⁴ ሁለቱ ጡቶችሽ እንደ ሁለቱ መንታ እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።
⁵ አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፤ ዓይኖችሽ በሐሴቦን ውስጥ በባትረቢ በር አጠገብ እንደ ውኃ ኵሬዎች ናቸው፤ አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አፋዛዥ እንደሚመለከት እንደ ሊባኖስ ግንብ ነው።
⁶ ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ በላይሽ ነው፤ የራስሽም ጠጕር እንደ ሐምራዊ ሐር ነው፤ ንጉሡ በሹርባው ታስሮአል።
⁷ ወዳጄ ሆይ፥ እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!
⁸ ይህ ቁመትሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም የወይን ዘለላ ይመስላሉ።
⁹ ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ ጫፎችዋንም እይዛለሁ አልሁ፤ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ የአፍንጫሽም ሽቱ እንደ እንኮይ ናቸው።
¹⁰ ጕሮሮሽ ለወዳጄ እየጣፈጠ እንደሚገባ፥ የተኙትን ከንፈሮች ይናገሩ ዘንድ እንደሚያደርግ፥ እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ነው።
¹¹ እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው።
¹² ውዴ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እንውጣ በመንደሮችም እንደር።
¹³ ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፤ ወይኑ አብቦ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያ ውዴን እሰጥሃለሁ።
¹⁴ ትርንጎዎች መዓዛን ሰጡ፤ መልካሞች ፍሬዎች ሁሉ፥ አሮጌው ከአዲሱ ጋር፥ በደጃችን አሉ፤ ውዴ ሆይ፥ ሁሉን ለአንተ ጠበቅሁልህ።
ይህ ነው የፈጣሪ ቃል? እነዚህን ጥቅሶችስ ያነበበ ሰው: ምን አይነት ስነ ምግባር ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል?
በሰለሞን ፍቅር እብድ ያለች ፀሐይ መልኳን ያከሰለው ጥቁር ናት፤ ንጉሡ ሰለሞንም የከንፈር ወዳጇ ነው፦
"እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች። ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አትዩኝ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ" መኃልየ 1፥5-6
"በአፉ መሳም ይሳመኝ፥ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና።" መኃልየ 1፥2
ንጉሥ ሰለሞን ይህቺን የሱናማይቱ ልጃገድ አካል ዐይንሽ፣ ከንፈርሽ፣ ጥርስሽ፣ አፍሽ፣ አንገትሽ፣ ጡትሽ፣ እምብርትሽ፣ ዳሌሽ እያለ ሲያብድ፤ እርሷም በተራዋ ቀሚሷን አውልቃ ንጉሡ እጁን በአፍረተ ስጋዋ ውስጥ ሲከተው አንጀቷ ተላወሰ፤ ለእርሱም የደጅዋን መወርወሪያ ማለት እግሯን ከፈተችለት፤ እርሷም ስሜቷን አፈሰሰች፤ ምን አለፋችሁ ይህንን ጥቅስ አንብቡት፦

"ቀሚሴን አወለቅሁ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ እንዴት አሳድፈዋለሁ? ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ። ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ እጆቼ በደጅ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ።" መኃልየ 5፥3-5
በመጨረሻም ለወገኖቻችን የምናስተላልፈው መልእክት፡- በእሳት ላይ ቆማችሁ አትጫወቱ፡፡ ካላችሁበት ጨለማ ወደ ኢስላም ብርሀን ኑ! አንድ አምላክ የኆነውን አላህን በማምለክ ብቻ ወደ ጀነት መግባት ይቻላል፡፡ ፍጡርን ማምለክ ፍጻሜው እሳት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
"የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡" (ሱረቱ አሊ–ዒምራን 3:64)።
Join us➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
እንኳን ለ1,441ኛው የዒዱል ፊጥር በዓል አላህ በሰላም አደረሳችሁ!
ተቀበለሏሁ ሚንና ወሚንኩም
ዒዱኩም ሙባረክ!
ተቀበለሏሁ ሚንና ወሚንኩም
ዒዱኩም ሙባረክ!
❤ሸዋል እና ስድስቱ የጾም ቀናት!
በአቡ ሀይደር
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
የረመዷን ወር ፆም መገባደድን ተከትሎ (አላህ ይቀበለን) የሚመጣው የሸዋል ወር ፆም ነው፡፡ እሱን በተመለከተ መጠነኛ ማስታወሻን እንካችሁ ለማለት ወደድኩ፡፡ ወማ ተውፊቂ ኢልላ ቢላህ፡፡
1/ ሸዋል የወር ስም እንጂ የፆም ስም አይደለም፡፡ ይህ ወር እንደ ረመዷን ወር 29/30 ቀናት አሉት፡፡ ከረመዷን በኋላ ተከትሎ የሚመጣ 10ኛ ወር ነው፡፡
2/ በዚህ ወር ውስጥ የሚፆም የስድስት ቀናት ፆም አልለ፡፡ ይህንን ስድስት ቀናት ከረመዷን ጋር አብሮ ለፆመ ሰው፡ የአንድ ዓመት ፆምን ያህል አጅር ያገኛል፡፡ መልካም ስራ መነሻ ብዜቱ በአስር ነውና (አል-አንዓም 6፡160) የአንድ ወር የረመዷን ፆም በአስር ወር ሲባዛ፣ የሸዋል ወር ስድስት ቀን ፆም ደግሞ በስልሳ ቀናት (ሁለት ወር) ይባዛና፡ በድምሩ አስራ ሁለት ወራት (ሙሉ አንድ ዓመት) ፆም ይሆናል ማለት ነው፡፡
3/ የሸዋል ወር ፆም የአባቶችና እናቶች፡ ወይንም የኢማሞችና የትልልቅ ሰዎች ፆም ብቻ አይደለም፡፡ የረመዷንን ፆም የተሳተፈ የአላህ ባሪያ ሁሉ፡ የሸዋልን ወር ፆምም መሳተፍ ይችላል፡፡ ዕድሉ ለሁሉም ክፍት ነውና፡፡
ወይንም፡- ባልፆመው የማስጠይቀኝ፡ ግዴታ ያልሆነ ተግባር ነው ብለን አንሳነፍ፡፡ በመፆማችን ደግሞ የምናገኘውንም አጅር እናስላ፡፡ አንድ ወር ሙሉ በተከታታይ በአላህ ተውፊቅና እገዛ መፆም ከቻልን፡ ስድስት ቀናትን መፆም ደግሞ እንደምን ይጠናብናል?
አንዳንዱ ደግሞ ፆሙ ይከብዳል እንደ ረመዷን አይቀልም ይላል፡፡ እውነት ነው የሸዋል ወር ፆም ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም፡-
አንድ፡- በረመዷን የታሰረው ቀንደኛው ጠላታችን ሸይጧን ከዒድ ሶላት መጠናቀቅ በኋላ ተፈትቷልና ወደ ስራው ይመለሳል፡፡ እኛንም ለማሳሳት ይጥራል፡፡
ደግሞም ይህንን የሸዋልን ፆም ልክ እንደ ረመዷኑ ቤተሰብ፣ ጓደኞችና የመስጂድ ጀመዓዎች ሁሉም በአንድ ስለማይፆሙት፡ በሚፆሙት ላይ (አላህ ያገራለት ሲቀር) ሊከብድ ይችላል፡፡ ቢሆንም አላህ ዘንድ የሚገኘውን ሽልማት ያሰበና ያመነ ባሪያ ሊከብደው አይገባም፡፡
4/ የሸዋል ወር ፆም እንደ ረመዷን ወር ዋጂብ (ግዳጅ) የሆነ ፆም ሳይሆን፡ ድርጊቱ ሙስተሐብ (የተወደደ) የሆነ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ፆሙን ያልተሳተፈ ሰው ኃጢአተኛ ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ ትልቅ አጅር አመለጠው እንጂ፡፡
5/ የሸዋልን ወር ፆም መሳተፍ የሚፈልግ የአላህ ባሪያ፡- ከፈለገ ከዒዱ ማግስት አንስቶ በተከታታይ ስድስት ቀናት፣ ወይንም አፈራርቆ በተመቸው ቀን ስድስት ቀናትን መርጦ፣ ወይንም ከሰኞና ሀሙስ ፆም ጋር በአንድ ኒያ ሁለቱንም በማገናኘት (የሰኞና የሀሙስን እንዲሁም የሸዋልን ስድስቱን)፣ ወይም ከአያመል-ቢድ (የወሩ 13.14.15ኛው ቀን) ጋር በማቆራኘት፣ ወይም እሱ በተመቸው መንገድ ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት መፆም ይችላል፡፡ (ፈታዋ ኢስላሚያህ፡ ኢብኑ ዑሠይሚን 2/154)፡፡
6/ መቼም ይሄ (shortcut) አቋራጭ መንገድ የሚባለው ነገር ተላምዶናል፡፡ በሰላምታ ወቅት (as wr wb) በሰላዋት ጊዜ (s.a.w) በምስጋና ተግባር ላይ (jzk)… ታዲያ አሁንም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ፡ የረመዷንን ቀዷእና የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም በአንድ በመነየት አጣምሮ መፆም ይቻላል ወይ? የሚል ጥያቄ ከተነሳ፡፡
ይህን ጥያቄ ፈዲለቱ-ሸይኽ ሙሐመድ ቢን-ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይመልሱታል፡-
‹‹የረመዷን ቀዷ እያለበት የዐረፋን ቀን ወይም የዐሹራእን (የሙሐረምን 10ኛ ቀን) የፆመ ሰው ፆሙ ትክክል ነው፡፡ ደግሞም እነዚህን ቀናት የረመዷንን ቀዷእ በመክፈል ኒያ በአንድ ላይ ቢፆማቸው ሁለት አጅርን ያገኛል፡፡ የዐረፋ ቀን ፆምና የዐሹራእ ፆምን አጅር ከረመዷን ቀዷእ አጅር ጋር ማለት ነው፡፡ እሱም እነዚህ የሱና ፆሞች ቀጥታ ከረመዷን ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌላቸው በመሆናቸው ነው፡፡ የሸዋል ወር ስድስት ቀናት ፆም ግን ከረመዷኑ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ምክንያት በአንድ ኒያ ሰብስቦ መፆሙ አይሆንም፡፡ ቅድሚያ ቀዷውን ከፍሎ ከዛም የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም ያስከትል›› (ፈታዋ-ሲያም 438)፡፡
በዚህም ሰበብ የረመዷን ቀዷ ያለበት ሰው፡ በሸዋል ወር ውስጥ ከሸዋል ስድስቱ የሱና ፆሞች ጋር በአንድ ኒያ ሰብስቦ መፆም እንደማይችል የኢስላም ሊቃውንት ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያብራሩ፡- የረመዷን ቀዷእ ሊከፈል የሚገባው ግዴት (ዕዳ) ሲሆን፡ የሸዋል ወር ስድስቱ ቀናት ፆም ግን በግለሰቡ ምርጫ ላይ የተወሰነ ነው፡፡ ከፈለገ ሊፆመው ካልፈለገ ሊተወው ይችላልና፡፡ ስለሆነም የግድ ኒያውን ከአላህ መብት በመጀመር ግዴታውን መክፈል ይጠበቅበታል፡፡
7/ የረመዷን ቀዷእ ያለበት ሰው፡ ቀዷውን ከመክፈሉ በፊት የሸዋልን ወር ስድስት ቀናት ፆም መፆምና ከዛ በኋላ በተመቸው ወቅት የረመዷንን ቀዷእ ማውጣት ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ፡ በዑለማዎች ዘንድ የሀሳብ ልዩነት የተንጸባረቀበት ነው፡፡ የሀሳብ ልዩነቱ መነሻ የሆነውም ቀጣዩ ሐዲሥ ነው፡-
عَنْ أَبِي أَيُّوبَ الْأَنْصَارِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: "مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كَانَ كَصِيَامِ الدَّهْرِ". أخرجه أحمد (5/417 رقم 23580) ، ومسلم (2/822 رقم 1164) ، وأبو داود (2/324 ، رقم 2433) ، والترمذى (3/132 ، رقم 759).
ከአቢ አዩብ አል-አንሷሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ረመዷንን የፆመና ከሸዋል ወርም ስድስት ቀናትን ያስከተለ፡ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ሆኗል" (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ 23580፣ ሙስሊም 1164፣ አቡ ዳዉድ 2433፣ ቲርሚዚይ 759)፡፡
በዚህ ሐዲሥ ላይ የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም ያስከተለ የተባለው ረመዷንን የፆመው ሰው ነው፡፡ በዑዝር ምክንያት የረመዷን ቀዷእ ያለበት ሰው ደግሞ ወሩን ባለማጠናቀቁ፡ ‹ረመዷንን የፆመ› የሚባለው ውስጥ የሚካተት አይደለምና፡ ቃል የተገባለትን ሙሉ የአመት ፆም አጅር ያገኝ ዘንድ ቅድሚያ ከቀዷእ መጀመር አለበት የሚለው የከፊል የኢስላም ሊቃውንት አቋም ነው፡፡
1. ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ ኑሩን ዐለ-ደርብ ካሴት ቁ 918
2. ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ አል-ሐረሙል መኪይ ካሴት ቁ 7
ነገር ግን የሸዋልን ወር ስድስት ቀናት አስቀድሞ ቢፆምና ከዛ በኋላ በተመቸው ወቅት የረመዷንን ቀዷእ ቢያስከትል፡ የረመዷኑ ፆም ምንም እንደማይሆንበትና ፆሙም ችግር እንደማይፈጥርበት አክለው ገልጸዋል፡፡ ችግሩ ያለው የሸዋል ወር ስድስቱ ቀናት ፆም ላይ ነው፡፡ የነዚህን ስድስት ቀናት ፆም አጅር ለመሸመት፡ በሐዲሡ በተነገረው መሰረት ቅድሚያ የረመዷን ወር ፆም (ከነ-ቀዷው) መጠናቀቅ አለበት የሚል ነው፡፡

👍1
ከኺላፍ መውጣት በራሱ ተወዳጅ ተግባር ነውና፡ ሁሉንም ሊያስማማና የኛንም ቀልብ ሊያረጋጋ በሚችል መልኩ
ከቀዷእ ጀምረን ከዛም በመቀጠል ወደ ስድስቱ የሸዋል ፆም መሸጋገር መልካም ነው፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ከቀዷእ ጀምረን ከዛም በመቀጠል ወደ ስድስቱ የሸዋል ፆም መሸጋገር መልካም ነው፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
የኡሱሉ ሰላሳ ኪታብ ትምሕርቱ ዛሬ ማታ 3:00 ይጀምራል።
ከቪዲዮውም በተጨማሪ በቴሌግራም ላይም በኦዲዮ ይቀርብላችኋል። ለዚህ የምተለፋውን እሕታችንን አላህ በጀነት ይካሳት።
https://tttttt.me/abuhyde

ኡሱሉ ሰላሳህ .pdf
1 MB
ሊንኩ ላይ ዳውንሎድ ካልሆነላችሁ እዚ ማውረድ ትችላላችሁ
https://waqfeya.com/book.php?bid=397
ኡሱሉ ሰላሳህ ኪታብ የሌላችሁ
التحميل مباشر የሚለውን በመጫን አውርዱት
https://waqfeya.com/book.php?bid=397
ኡሱሉ ሰላሳህ ኪታብ የሌላችሁ
التحميل مباشر የሚለውን በመጫን አውርዱት
የሸዋል ፆም ፍች (ትንሹ ዒድ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት የአላህ ባሮች ይሁን፡፡
በተወሰኑ (ሁለት ወይም ሶስት) ብሔሮች ዘንድ ከረመዷን ዒድ (ዒዱል-ፊጥር) ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም ይጾሙና ሰባተኛውን ቀን እንደ ዒድ ያከብሩታል፡፡ ምክንያቱን ጠይቄ ለማወቅ እንደሞከርኩት ይህን ይመስላል፡-
የዒዱል-ፊጥር ቀን ደብዘዝ ብሎ በደንብ ሳይሞቅ የምናሳልፈው ቀኑ አንድ ቀን ስለሆነና በነጋታው ተመልሰን ወደ ሸዋል ጾም ስለምንገባ ነው፡፡ ስለዚህ ባሉት ተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም በመጾም ሁለቱንም (ረመዷንንም ሸዋልንም) እንጨርስና ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ በደንብ ዒዱን እናከብራለን፡፡ እንበላለን እንጠጣለን፡፡ ጎረቤት፣ ጓደኛ፣ ዘመድ እንጠይቃለን፡፡ ብዙ ቀናቶች አሉንና፡፡
ከዚህ ምክንያት መረዳት እንደሚቻለው ሰዎቹ የዒዱል-ፊጥር ቀን አንድ ቀን ብቻ በመሆኑ በሰፊው ለመብላትና ለመጠጣት፣ ከዘመድ አዝማድ ጋር ለመዘያየር የማይበቃ መሆኑ ነው እንጂ የሸዋል ዒድ አለ ብለን አይደለም የሚል ነው፡፡
ማስተካከያ፡-
1ኛ/ የኢስላም ሃይማኖት እንዳስተማረን ከሁለቱ ዒዶች (ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ) ውጪ፡ ሙስሊሞች ሌላ ዒድ የላቸውም፡፡ የአላህ መልክተኛ ከደነገጉት ውጪ አዲስ ስርአትን መደንገግ በሃይማኖቱ ላይ መጨመር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቢድዐ ይባላል፡፡ የሸዋል ወር 8ኛው ቀን የሸዋል ፆም መፍቻ ዒድ ቢሆን ኖሮ፡ በዒድ ቀን መፆም ሐራም ነውና በዚህ ቀን አትፁሙ የሚል ትእዛዝ በሐዲሥ በሰፈረ ነበር፡፡ ግን የለም፡፡
2ኛ/ የሸዋል መጀመሪያ ቀን ዒዱል ፊጥር መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዒድ ደግሞ የመደሰቻ፣ የመብያና የማብያ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጫ ቀን ነው፡፡ ግን በመጀመሪያው ቀን ብቻ ነው መብላትና ማብላት፣ መዘየርና መደሰት የሚቻለው ያለው ማነው? የሸዋልን ሁለተኛና ሶስተኛ ቀናትስ መብላትና ማብላት፣ መዘያየር አይቻልም? ይቻላል፡፡ ስለዚህ ከላይ የቀረበው ምክንያት አጥጋቢ አይደለም፡፡
3ኛ/ የሸዋል ስድስት ቀናት ጾም በመጀመሪያዎቹ የሸዋል ቀናቶች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ሸዋል ሙሉ አንድ ወር 29/30 ነው፡፡ ስለዚህ ከወሩ ውስጥ የሚመቸውን ቀን መርጦ በማከታተልም ሆነ በማፈራረቅ ሸዋልን መጾም ይቻላል፡፡ እናም የደስታውን ቀን ማርዘም የሚፈልግ ከዒዱል-ፊጥር በኋላ ያለውንም ቀን መጠቀም ይቻላል፡፡ በቀሩት ቀናት ደግሞ ሸዋልን መጀመር ይቻላል፡፡
4ኛ/ ከዒዱል-ፊጥር ማግስት ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ስድስት ቀናት የጾመ ቤተሰብ በቀጣዩ ቀን በመብላትና ቀኑን እንደ ዒድ ቆጥሮ ሲያሳልፈው፡ ከመሐከላቸው አንድ ሰው ጾሙን ባለመጨረሱ (ቀዷእ ቢኖርበት ወይም ዘግይቶ ቢጀምር) እነሱ የሚበሉበትን ቀን ቢጾመው የቤተሰቡ አካላት ይቃወሙታልን? በዒድ ቀን እንዴት ትበላለህ ይሉታልን? አዎ! ከሆነ ምላሹ፡ ሰዎቹ ቀኑን ዒድ አድርገው ይዘውታል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በዲነል-ኢስላም ላይ የተጨመረ ፈጠራ ‹‹ቢድዓህ›› ይባላል፡፡ አላህና መልክተኛው ከዒዱል-ፊጥር እና ከዒዱል አድሓ ውጪ የበዓል ቀን አልደነገጉልንም፡፡ የሸዋል ዒድ የሚባለው መሰረት የለውም እና እንደ-ዒድ አድርገው የሚይዙ ሰዎችን ቢድዓ መሆኑን ማስተማርና ማስገንዘብ ይጠበቅብናል፡፡
4. ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር፡- ከዒዱል ፊጥር ማግስት ጀምሮ በተከታታይ የሸዋልን ስድስት ቀናት የጾመ ሰው በቀጣዩ ቀን መብላት መጠጣት አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ሰውየው ጾሙን እስካጠናቀቀ ድረስ መብላት መጠጣት ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቀኑ ላይ ሲበላም ሆነ ሲጠጣ ቀኑን ዒድ ነው ብሎ እንዳይመለከተውና እንደ-ዒድ አድርጎ እንዳይዘው ነው፡፡ የዒዱል-ፊጥር ቀንንም በአግባቡ ሊያከብረው ይገባል፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤http://tttttt.me/abuhyder

🔥1
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
ሒዳያ ቲዩብ – ኪታብ ኡሱሉ ሠላሠህ
ክፍል አንድ
ክፍል አንድ
Audio
ኪታብ ኡሱሉ ሠላሠህ
📖 ክፍል -2
🎙 ኡስታዝ አቡ ሐይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://bit.ly/3ceS8nm
Join us➤ t.me/abuhyder
Click and Like➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder