የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.2K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኮረና ለምን በጣም ተጋነነ ለምንስ ነው ያስፈራን?
ኮረና የአላህ ቁጣ ነው
እንዴት ወደ አላህ እታረቅ

በኡስታዝ አቡ ሐይደር
መደመጥ ያለበት ወሳኝ ትምህርት
በዩቱብ ለመከታተል 👇👇
https://youtu.be/YcXvqviyquY
https://youtu.be/YcXvqviyquY
ኢብራሂም ኢብኑ ኢስሐቅ (ረሒመሁላህ) በበስራ (የዒራቅ ሁለተኛ ከተማ) የገበያ ማእከል ሲያልፍ: ሰዎች ወደሱ ተሰበሰቡና:– ያ አባ ኢስሐቅ ዱዓእ እያደረግን ለምንድነው ምላሽ ያጣነው? በማለት ጠየቁት።
እሱም:– ልባችሁ በአስር ነገራት በመሞቱ ምክንያት ነው። እነሱም:–
1 አላህን አውቃችሁት ስታበቁ ሐቁን ግን አልተወጣችሁም።
2 መልክተኛውን እንወዳለን ብላችሁ ትሞግታላችሁ: ግን ሱናውን ከመከተል ትታችኋል።
3 ቁርኣን ቀርታችኋል: ግን አትሰሩበትም።
4 ከአላህ ፀጋዎች ትመገባላችሁ: ግን አታመሰግኑም።
5 ሸይጧን ጠላታችን ነው ትላላችሁ: ግን ፈቃዱን ትፈፅማላችሁ።
6 ጀነት አውነት ነው ትላላችሁ: ግን አትሰሩላትም።
7 እሳት እውነት ነው ትላላችሁ: ግን አትሸሿትም።
8 ሞት እውነት ነው ትላላችሁ: ግን አትዘጋጁለትም።
9 ከእንቅልፋችሁ ስትባንኑ: የሰዎችን ነውር በመፈለግ ቢዚ ሆናችሁ የራሳችሁን ነውር ትረሳላችሁ።
10 ሙታኖቻችሁን ትቀብራላችሁ: ግን አትማሩባቸውም።
ወንድምና እህቶቼ ይህ ነገር ስለኛ ይሆን የተነገረው?

مر إبراهيم بن إسحاق بسوق البصرة فاجتمع إليه الناس
فقالوا له: يا أبا إسحاق مالنا ندعوا فلا يستجاب لنا ..!!؟؟
قال: لأن قلـوبـكم ماتت بعشـرة أشيـاء
.
الأول: عرفتم الله تعالى.. فلم تؤدوا حقه
الثاني:زعمتم أنكم تحبون رسوله صلى الله عليه وسلم وتركتم سنته
الثالث: قرأتم القرآن.. ولم تعملوا به
الرابع: أكلتم نعمة الله تعالى.. ولم تؤدوا شكرها
الخامس: قلتــم أن الشيطان عدوكم.. ووافقتمـــوه
السادس: قلتــم أن الجنـة حـق.. ولم تعملـوا لها
السابع: قلتـم أن النـار حـق.. ولم تهربوا منهــا
الثامن: قلتــم أن المـوت حـق.. ولم تستعــدوا له
التاسع: إذا انتبهتم من النوم.. اشتغلتم بعيوب الناس ونسيتم عيوبكم
العاشر: دفنتــم موتاكم.. ولم تعتبـروا بهم
Join us➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላህ
የኮሮና ቫይረስ በርካቶችን እያስጨነቀ ነው። ብዘዎቻችንም ስጋት ውስጥ ነን። ዛሬ በፈርንጆች
#April 1 ነው። ይህንንም ተከትሎ #አፕሪል_ዘ_ፉል በነጮቹ ዘንድ ይከበራል።

በእለቱ የሀሰት ዜናዎች በስፋት እየተሰራጩ በርካቶችን ያስደነግጣሉ። አንድ አንድ ጨዋታ መስሉዋቸው ወይም ሆን ብለው በማህበራዊ ሚድያ ሰዎችን የሚያስደነግጡ ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ እንዳትታለሉ። እባካችሁ ሀላፊነት የጎደላቸው ሰዎች በሚያደርጉት ነገር እንዳትረበሹ!
ቪድዩውን ይመልከቱ 👇👇👇

https://youtu.be/ROczwStP4mg
https://youtu.be/ROczwStP4mg
Audio
ለኮረና ይህን ያክል መጨነቅ አይገባም
ክፍል 3
➤ በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/2vbVJmz

Join us➤ t.me/abuhyder
በዩቱብ ለመከታተል➤
https://youtu.be/Z6DCDW1TSXo
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ለኮረና ይህን ያክል መጨነቅ አይገባም ሁሉም ነገር ለኸይሩ ነው" ክፍል 3 በኡስታዝ አቡ ሐይደር
Click and Like ➤➤
https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

https://www.youtube.com/channel/UCa97V2wLhSCREjwCkiTid-Q
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሶስቱ ጓደኛሞች (ዕውር፣ ለምጣም፣ ራሰ በራ) ፈተናና ውጤቱ
በኡስታዝ አቡ ሐይደር


Click and Like ➤➤
https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

Sub➤
https://www.youtube.com/channel/UCa97V2wLhSCREjwCkiTid-Q
Audio

ሸህሩ ረመዷን🌙
የረመዳን ክብርና ደረጃው ክፍል
➤ በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://goo.gl/QKxVtn

Join us➤ t.me/abuhyder
https://youtu.be/cgoEODXxat4
የመልካም ስራ ጥሪ

ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶችን በሚሰጠው በዚህ የመስጅድና የመርከዝ ግንባታ ላይ የአቅምዎን አሻራ ያሳርፉ። በመስጅዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ መርከዝን ጨምሮ የተለያዩ የወጣቶች መዝናኛ ስፍራን ያቀፈ ሰፊ ፕሮጀክት ሲሆን ሸሪዓውን በጠበቀ መልኩ ለሁለቱም ፆታዎች ግልጋሎት እንዲሰጥ ታስቦ እየተሰራ ይገኛል። በዚህ መልካም ስራ ላይ የአቅምዎን ድጋፍ ማድረግ ከፈለጉ በሚከተለው አካውንት ኒያዎትን ሊያደርሱ ይችላሉ፦

COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000281947878
SADIK MOHAMMED AHMED
00251911103231
WHATSAPP 00971566331753

"ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ ሰው፣ አላህ ለሱ በጀነት ቤትን ይገነባለታል" ረሱል ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
1/ የረመዷን ወር ክብር

1000298991245
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
ሳዲቅ መሐመድ አሕመድ
0911103231
ምሥኪኖችን ለማስፈጠሪያ ብቻ
00971566331753 whatsapp
አንዱ ሀሰተኛ ነቢይ ነኝ ብሎ ሲሞግት: ኸሊፋው ዘንድ አመጡት። ንጉሱም ሹማምንቶቹ በተሰበሰቡበት: ነቢይ ነኝ ባዩን:–

እውን አንተ ነቢይ ነህን?
እሱም:– አዎን!

ንጉሱም:– ማስረጃህ ምንድነው?
አሱም:– እናንተ ሁላችሁም በአሁን ሰአት በልባችሁ የምታስቡትን እነግራችኋለሁ! አለው።

ንጉሱም:– እሺ ንገረን ምን እያሰብን ነው?
እሱም:– አሁን የምታስቡት ይህ ሰው ሀሰተኛ ነቢይ ነው! እያላችሁ ነው አለ 😄

© ኡስታዝ አቡ ሀይደር

@Yahya5
Audio
ሸህሩ ረመዷን🌙
የፆም አስፈላጊነቱና ጠቀሜታው!ክፍል➋

🎙 አዘጋጅ⇊
➤ በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://goo.gl/ymmyu2

Join us➤ t.me/abuhyder
https://youtu.be/e_tlHgjJkac
ረመዷን ምንድነው?

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

ታላቁና ተወዳጁ ነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሶሐቦቻቸውን የረመዷንን መቃረብ አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ ብስራትን ሲገልጹ እንዲህ ይሏቸው ነበር፡- "የተባረከ ወር የሆነው ረመዷን መጣላችሁ!፡፡ አላህ ጾሙን በናንተ ላይ ግዳጅ አድርጓል፡፡ በዚህ ወር የሰማይ ደጃፎች ይከፈታሉ፡፡ የጀሀነም ደጃፎች ይዘጋሉ፡፡ አመጠኛ ሸይጣናት ይታሰራሉ፡፡ አላህ ከአንድ ሺህ ወር (ስራ) የምትበልጥ የሆነች አንድ ለሊት አለችው፡፡ የዚህን ወር መልካም ነገር የተነፈገ ሰው በርግጥም ከብዙ መልካም ነገራት የተነፈገ ነው፡፡" (አሕመድ 7148፣ ነሳኢይ 2106)፡፡

ይህ የነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ብስራት ዋና አላማው ሶሐባዎች (ረዲየላሁ ዐንሁም) ከወዲሁ ይህንን የተከበረ ወር ለመቀበል መንፈሳዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማነሳሳት ነው፡፡ እኛስ ምን ያህል ተዘጋጅተናል? ለዛሬ መግቢያ እንዲሆነን ስለ ረመዷን ፈዷኢል (በረከቶች) የተወሰነ ነገር እንነጋገር፡፡

1. የረመዷን ወር ክብር፡-

የረመዷን ወር በኢስላማዊው የወር አቆጣጠር መሰረት፡ ዘጠነኛ ወር ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ ወር ከተቀሩት 11ዱ ወራቶች ለየት የሚያደርገው የራሱ የሆኑ መለያዎች አሉት፡፡ ከነዚህም መለያዎቹ መካከል፡-

ሀ. የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ወር መሆኑ፡- የመልካም ስራ መንገዶችና የጥመት ጎዳናዎች በአስራ ሁለቱም ወራት (ሙሉ ዓመት) ለፈላጊዎችና ለሰሪዎች ክፍት ነው፡፡ የአላህ ባሮች ከረመዷን በፊት፣ በረመዷን ውስጥና ከረመዷን በኋላ ባሉት ወራቶች ላይ ወደ ጌታቸው አላህ የሚያቃርባቸውን መልካም ሥራ ከመሥራት አይቦዝኑም፡፡ የሸይጧን ሠራዊቶች ደግሞ (ተውፊቁን ካላገኙ) ከአላህ የሚያርቃቸውን የጥፋት መስመሮች ከመከተልና ክፋትን ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ የረመዷን ወር የሚለየው ግን ጀነት ለፈላጊዎቿ ተሸሞንሙና ደጃፎቿ ወለል ብለው ተከፍተው ሲታዩ፡ የጀሀነም በሮች ደግሞ የሚከረቸሙ መሆናቸው ነው፡፡

አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የረመዷን የመጀመሪው ለሊት ላይ አመጸኛ ሰይጣናት ይታሰራሉ፣ የእሳት በሮች አንድም ሳይቀር ይከረቸማሉ፣ የጀነት በሮች አንድም ሳይቀር ይከፈታሉ፣ በያንዳንዱ ለሊትም አንድ ተጣሪ እንዲህ በማለት ይጣራል፡- ‹‹መልካም ፈላጊ የሆንክ ሆይ! ፊትህን (ወደ መልካም ተግባር) አዙር፡፡ መጥፎን ፈላጊ የሆንከው ሆይ! (የምትሰራውን ክፋት) ቀንስ(አቁም)፡፡ በያንዳንዱ ለሊትም አላህ ከእሳት ነጻ የሚያደርጋቸው ባሮች አሉት" (አሕመድ 18438)፡፡

ለ. የኃጢአት ማስተሰረያ (ማጥፊያ) መሆኑ፡- በማንኛውም ወቅት የሚሰራ መልካም ስራና ወደ አላህ የሚደረግ የንሰሀ ተውበት ኃጢአትን ያጠፋል (ሁድ 114፣ አዝ-ዙመር 53)፡፡ የረመዷን ወር ደግሞ በአግባቡ ከተጾመ፡ ቀጣዩ አመት ረመዷን እስኪመጣ ድረስ በመሀከሉ የተፈጸሙ ጥቃቅን ኃጢአቶችን በመላ ያጠፋል፡፡ ትላልቅ ኃጢአቶች (ከባኢረ-ዙኑብ) የግድ ባለቤቱ ከነሱ ተውበት ሊያደርግ ያስፈልጋቸዋልና፡፡

አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አምስት ወቅት ሶላቶችን መስገድ፣ ጁሙዓ ተሰግዶ ቀጣዩ ሳምንት ጁሙዓህ እስኪመጣ፣ ረመዷን ተጹሞ ቀጣዩ ረመዷን እስኪመጣ ድረስ ሰውየው ትላልቅ ኃጢአትን እስከተጠነቀቀ ድረስ በመሀከላቸው ያለውን ትናንሽ ኃጢአት ያስሰርዛሉ" (ሙስሊም)፡፡

ሐ. የዑምራህ ደረጃህ ከፍ ማለቱ፡- ከሐጅ ስርዓት ውጪ ዑምራን ብቻ መፈጸም አጅር የሚያስገኝ የሱና (ሙስተሐብ) ተግባር ነው፡፡ በረመዷን የሚፈጸም ከሆነ ግን አጅሩ ከፍ ብሎ በማደግ የሐጅን ምንዳ ያህል ይደርሳል፡፡

ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "በረመዷን የሚደረግ ዑምራ (ምንዳው) ከሐጅ ጋር ይስተካከላል" (ሙስሊም)፡፡

መ. ቁርኣን የወረደበት ወር መሆኑ፡- የህይወታችን መመሪያ በመሆን፣ ማን እንደፈጠረን፡ ለምንስ እንደተፈጠርን፣ እንዴት መኖር እንዳለብንና ወደየትስ እንደምንጓዝ በቂ ምላሽን በመስጠት ማንነታችንን፡ የጠራ መስታወት በመሆን የሚነግረን አምላካዊ ቃል የሆነው ቅዱስ ቁርኣን የወረደው በዚሁ የተከበረ ወር፡ በተከበረች ለሊት፡ በውሳኔዋ ምሽት (ለይለቱል ቀድር) ውስጥ ነው፡፡

"(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው…" (ሱረቱል በቀራህ 2፡185)፡፡
"እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፤ እኛ አስፈሪዎች ነበርንና።" (ሱረቱ-ዱኻን 44፡3)፡፡

"እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛዪቱ ሌሊት አወረድነው።" (ሱረቱል ቀድር 97፡1)፡፡

ቁርኣን በረመዷን ወር ‹‹ወረደ›› የሚለው ሁለት መልእክትን ያቀፈ ነው፡-

1ኛ፡- ከለውሐል መሕፉዝ (ጥብቅ ሰሌዳ) ወደ ምድራዊ ሰማይ የተከበረው ቤት (በይቱል-ዒዝዛህ) ሲወርድ በጠቅላላ አንድ ጊዜ በዚህ ወር ውስጥ ወርዷል ሲሆን፡-

2ኛ. ከምድራዊው ሰማይ (በይቱል-ዒዝዛህ) ወደ ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ልብ በመልአኩ ጂብሪል (ዐለይሂ-ሰላም) አማካኝነት ሲወርድ በዚሁ ወር ነው መውረድ የጀመረው ማለት ነው፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

ሠ. ለይለቱል-ቀድር (የውሳኔው ለሊት) የምትገኝበት ወር መሆኑ፡- በዚህች አንድ ለሊት የሚሠራ መልካም ሥራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ካገኘ፡ የሥራው ደረጃ ሰውየው አንድ ሺህ ወራት (83 ዓመት ከ4 ወር) ተቀምጦ ከሚሠራቸው መልካም ሥራዎች የበለጠ ይሆናል፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡

"መወሰኛይቱ ሌሊት ምን እንደ ሆነች ምን አሳወቅህ? መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት።" (ሱረቱል ቀደር 97፡2-3)፡፡

ረ. ቂያሙ ረመዷን (ሶላቱ-ተራዊሕ) የሚገኝበት መሆኑ፡- በረመዷን ወር ሙስሊሞች ተሰባስበው ከዒሻእ ሶላት በኋላ በጀመዓ የሚሰግዱት ሶላት ቂያሙ ረመዷን (ሶላቱ-ተራዊሕ) ይባላል፡፡

አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የረመዷንን ወር አምኖና (ምንዳውንም) ለማግኘት ነይቶ (በዒባዳ) የቆመ ሰው፡ ከዚህ በፊት የፈጸማቸው ኃጢአቶቹ በመላ ይማራሉ" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡

ሰ. ኢዕቲካፍ የሚገኝበት ወር መሆኑ፡- በማንኛውም ቀንና ሰዓት አንድ ሙስሊም የተወሰነ ሰዓታትን በዒባዳ ለማሳለፍ ወስኖ በመስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ መቀመጥ ይችላል (አል በቀራህ 2፡187)፡፡ በረመዷን ግን ለየት ባለ መልኩ የመጨረሻዎቹን ሙሉ አስር ቀናት በመስጂድ ውስጥ በዒባዳ ለማሳለፍ ራሱን በማገድ (ኢዕቲካፍ) ማድረግ ይቻላል፡፡

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የረመዷንን የመጨረሻ አስርት ቀናት እስኪሞቱ ድረስ ሁሌም ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር፡፡ ከሳቸውም ሞት በኋላ ሚስቶቻቸው ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር" (ቡኻሪይ)፡፡

ሸ. የቸርነትና የለጋስነት ወር መሆኑ፡- ቸር መሆን በማንኛውም ቀንና በማንኛው
👍1
ም ሰዓት የተወደደ መልካም ተግባር ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በረመዷን!

ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሰዎች ሁሉ በላይ ቸርና ለጋስ ነበሩ፡፡ በተለይም እጅግ ቸርና ለጋስ ይሆኑ የነበረው በረመዷን ጅብሪል በሚገናኛቸው ወቅት ነበር፡፡ ጅብሪል (ዐለይሂ-ሰላም) በየለሊቱ እየመጣ ቁርኣንን ይጠናኑ ነበር፡፡ የሳቸው መልካም ነገር ላይ የነበራቸው ቸርነትም ከተላከ ነፋስ የፈጠነ ነበር" (ቡኻሪይ)፡፡

ቀ. አመጠኛ ሰይጣናት የሚታሰሩበት መሆኑ፡- ሸይጧን በረመዷን ወር የሚታሰር መሆኑን ለማመን ከሐዲሡም ውጪ በተግባር የሚታይ እውነታ ነው፡፡ ቢያንስ ሁለት ምክንያቶችን ማቅረብ ይቻላል፡-

1ኛ. የአላህ ቤቶች ሁሉ በሰጋጅ ይጨናነቃሉ፡፡ መስጂዶች ይሞላሉ፡፡ ሁሉም ሙስሊም፡- ይህ ሁሉ ሰው ከየት መጣ! በማለት ይገረማል፡፡ ኢስላምን የሚቀበሉ አዲስ ገቢዎች ጥቂት ቢሆኑም፡ አብዝኃኛው ግን በቤቱና በስራ ቦታው ይሰግድ የነበረ፡ እንዲሁም ከሶላት ጋር ትውውቅ ያልነበረው ሰው ነው፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ሕዝብ ከረመዷን በፊት በአላህ ቤት ለመታየት ያልገራለት፡ አሁን በረመዷን ግን መምጣቱ፡ ይፈታተነው የነበረው ሸይጧን መታሰሩን አያመላክትምን?

2ኛ. ዒባዳን ለመተግበር ይቀላል፡፡ ከረመዷን ውጪ ተዘግቶ በክብር ስፍራ የተቀመጠው ቁርኣን በረመዷን አንባቢው ይበዛል፡፡ በፊት 1ብር ለመለገስ የሰሰቱ ልቦች፡ በረመዷን ለማስፈጠርና ለሶደቃ ግን ይቻኮላሉ፡፡ ይህን ኸይር ስራ አሁን ለመስራት ከገራልዎት፡ ከአላህ ተውፊቅ በኋላ የሸይጧን መታሰርን አይጠቁምምን?

"የተባረከ ወር የሆነው ረመዷን መጣላችሁ
!፡፡ አላህ ጾሙን በናንተ ላይ ግዳጅ አድርጓል፡፡ በዚህ ወር የሰማይ ደጃፎች ይከፈታሉ፡፡ የጀሀነም ደጃፎች ይዘጋሉ፡፡ አመጠኛ ሸይጣናት ይታሰራሉ…" (አሕመድ 7148፣ ነሳኢይ 2106)፡፡

Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ t.me/abuhyder
ኡስታዝ ሳዲቅ መሃመድ *(አቡ ሃይደር)* 500 ለሚሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረጉ፡፡

በሃላባ ዞን በኮሮና ቫይረ ምክኒያት የገቢ አቅማቸው ለተዳከመ እንዲሁም የተለያዩ አቅመ ደካማ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ታላቁ የረመዳን ወር ፆምን በደስታ እንዲያሳልፉ ለማስቻል በሃላባ ቁሊቶ ከተማ ብላቴ ወንዝ አከባቢ በሚገኘው ዋዳ መስጂድ ለ400 የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ለአንድ አባወራ 50 ኪሎ ግራም በቆሎ ፥ 20 ኪሎ ግራም ቅንጬ እና 3 ሊትር ዘይት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተመሳሳይ ዜና ኡስታዝ አቡሃይደር በቄረንሶ ቀበሌ ከሃዲያና እና ከምባታ ዞኖች ለተውጣጡ 100 አቅመ ደካማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለእያንዳንዳቸው 50 ኪሎ ግራም በቆሎ ፥ 20 ኪሎ ግራም ቅንጬ እና 3 ሊትር ዘይት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉ የተሰበሰበው በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ከሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሆኑን የተናገሩት ኡስታዝ አቡ ሃይደር ድጋፉ በቅርብ ቀናትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አብራርተዋል፡፡

ምንጭ - የሀላባ ዞን ህዝብ ግንኙነት ቢሮ