Audio
"የአላህ መለኮታዊ መልካምና ውብ ስሞች" ክፍል1
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/TZRvZk
Join us➤ t.me/abuhyder
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/TZRvZk
Join us➤ t.me/abuhyder
"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" 6
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
2. ለነቢይነታቸው ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸው ማስረጃ
ሠ. የንፋስና የመላእክት ሰራዊት፡-
በአምስተኛው አመተ ሒጅራህ በኸንደቅ ዘመቻ (የአሕዛብ ዘመቻ) ላይ የተከሰተ ክስተት ነው፡፡ ሰበቡም፡- ከበኒ-ነዲር ጎሳ የሆኑ አይሁዶች ከመልክተኛው ጋር ገብተው የነበረውን ቃል-ኪዳን አፈረሱ፡፡ እሳቸውንም ለመግደል ሞከሩ፡፡ መልክተኛው ሰራዊታቸውን በመያዝ ሰዎቹ እጃቸውን እስኪሰጡ (እስኪማረኩ) ድረስ ከበቧቸው፡፡ ከዛም ከከተማው አባረሯቸው፡፡ በኒ-ነዲሮችም ቂምን በልባቸው በመያዝ፡ ዳግም ለመበቀል በማሰብ፡ የዐረብ ጎሳዎችን መዲናን በመውረር ላይ አነሳሷቸው፡፡ ከዐረቦቹም ቁረይሾች፣ ገጥፋን፣ በኑ-ሙርራህ፣ በኒ ሰሊም፣ በኒ አሰድ፣ የአይሁዶቹ በኒ ቁረይዟ ጎሳዎች ለወረራው ተስማሙ፡፡ የአላህ መልክተኛም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለአሕዛብ ዘመቻ ተዘጋጁ፡፡ በሰልማኑል ፋርሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ሃሳብ ሰጪነት፡ ሶሓባዎች ከነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ጋር በመሆን፡ በመዲና ዙሪያ፡ ሙሽሪኮች (አሕዛቦች) እንዳይገቡ ለመከላከል በሰሜን አቅጣጫ አንድ ምሽግን ቆፍረው መሽገው ነበር፡፡ አሕዛቦቹ መዲና ድንበር ሲደርሱ ለመግባት አቃታቸው፡፡ ግን ሶሐባዎቹ ተከበዋል፡፡ ረሀቡም ጠናባቸው፡፡ የአላህ መልክተኛም፡- "አላሁመ ኢነል-ዐይሸ ዐይሹል አኺራህ፣ ፈግፊር ሊል-አንሷሪ ወል-ሙሃጂራህ" ሲሉ፡ ሶሐባዎቹም ቀበል አደረጉና፡- "ነሕኑ-ለዚ ባየዕና ሙሐመዳ ዐለል-ጂሃዲ ማ-በቂና አበዳ" በማለት መለሱ፡፡ የመልክተኛው ንግግር ትርጉሙም፡- አላህ ሆይ! ኑሮ ማለት የአኼራ ነው፡፡ አንሷሮችንና ሙሃጂሮችን ይቅር በላቸው (ማራቸው) ሲሆን፡ የሶሐቦቹ ምላሽ ደግሞ፡- ከመልክተኛው ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋር በህይወት እስካለን ድረስ በጂሃድ ላይ ቃል የገባነው እኛው ነን! የሚል ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት በድንገት ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ብርቱ ንፋስ እና የመላእክት ሰራዊት፡ የከሀዲያንን ችቦ ማጥፋት ጀመረ፣ ሃይላቸውን መከተ፣ ግንባታዎቻቸውን አፈራረሰ፣ ሴራዎቻቸውን በጣጠሰ፣ ፈረሶቻቸውንና ግመሎቻቸውን ደንብረው እንዲጠፉ አደረገ፡፡ እነዛም ከሩቅ ስፍራ ተጉዘው የመጡና ሙስሊሞችን ለረጅም ቀናት ከብበው የነበሩ የአሕዛብ ሰራዊት፡ የተዋረዱና የከሰሩ ሆነው ተመለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛና ሶሐቦችም ይህን ቃል መደጋገም ጀመሩ፡- "አልሐምዱ ሊላሂ ወሕደህ፣ ሰደቀ ወዕደህ፣ ወነሰረ ዐብደህ፣ ወአዐዘ ጁንደህ፣ ወሀዘመል አሕዛበ ወሕደህ"፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ምስጋና ለአንዱ አላህ ብቻ የተገባ ይሁን፣ ያ ቃሉን የፈጸመ ጌታ ለሆነው፣ ባሪያውንም ለረዳ፣ ሰራዊቱንም ላጠናከረ፣ የአሕዛብ ሰራዊትንም ብቻውን ላዋረደው ጌታ ምስጋና ይገባው›› ማለት ነው፡፡ ይህን በማስመልከትም ቀጣዩ አንቀጽ ወረደ፡-
"يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَاءَتْكُمْ جُنُودٌ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ رِيحًا وَجُنُودًا لَمْ تَرَوْهَا وَكَانَ اللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرًا * إِذْ جَاءُوكُمْ مِنْ فَوْقِكُمْ وَمِنْ أَسْفَلَ مِنْكُمْ وَإِذْ زَاغَتِ الْأَبْصَارُ وَبَلَغَتِ الْقُلُوبُ الْحَنَاجِرَ وَتَظُنُّونَ بِاللَّهِ الظُّنُونَا " سورة الأحزاب 10-9
"እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ብዙ ሰራዊት በመጣችባችሁና በነሱ ላይ ነፋስንና ያላያችኋትን ሰራዊት በላክን ጊዜ፣ በናንተ ላይ (ያደረገላችሁን) የአላህ ጸጋ አስታውሱ፤ አላህም የምሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው። ከበላያችሁም፣ ከናንተ በታችም፣ በመጡባችሁ ጊዜ ፣ዓይኖችም በቃበዙ፣ ልቦችም እላንቃዎች በደረሱና በአላህም ጥርጣሬዎችን በጠረጠራችሁ ጊዜ፤ (ያረገላችሁን አስታውሱ)" (ሱረቱል አሕዛብ 9-10)፡፡

ረ. የበድር ዘመቻ ክስተት፡-
ሶሓባዎች ከሙሽሪኮች ጋር ለመፋለም በመዘጋጀት ሁሉም ቦታውን ይዟል፡፡ በቁጥራቸው አናሳ (የጠላትን 1/3)፣ በኃይልም ደካማ በመሆናቸው ግን ስጋት ገብቷቸዋል፡፡ ይባስ ብሎም አላህ እንቅልፍን ለቀቀባቸው፡፡ ከፊሎቻቸው ደግሞ ኢሕቲላም (ጀናባ) ሆኑ፡፡ ሸይጧንም አጋጣሚውን በመጠቀም፡ እነሱን ከትግል ሜዳ ለመመለስ ጉትጎታና ከሞት ማስፈራራት ጀመረ፡፡ አላህም እንዲታጠቡበት፣ እንዲጠጡና ወደ ትግሉ ሜዳ ሲጓዙም መንገዱ ምቹ ይሆን ዘንድ ከላይ ዝናብን አወረደላቸው፡፡ የሙስሊሙ ሰራዊትና የጠላት ሰራዊትም ገና ሲገናኙ ከላይ የመላእክት ሰራዊት ወረደ፡፡ ገና በመጀመሪያው የትግል ሰዓት ከሀዲያን አስቀያሚ የሆነ ውርደትን ተከናነቡ፡፡ ይህን በተመለከተም ቀጣዩ አንቀጽ ወረደ፡-
"إِذْ يُغَشِّيكُمُ النُّعَاسَ أَمَنَةً مِنْهُ وَيُنَزِّلُ عَلَيْكُمْ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً لِيُطَهِّرَكُمْ بِهِ وَيُذْهِبَ عَنْكُمْ رِجْزَ الشَّيْطَانِ وَلِيَرْبِطَ عَلَى قُلُوبِكُمْ وَيُثَبِّتَ بِهِ الْأَقْدَامَ * إِذْ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى الْمَلَائِكَةِ أَنِّي مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا الَّذِينَ آمَنُوا سَأُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ فَاضْرِبُوا فَوْقَ الْأَعْنَاقِ وَاضْرِبُوا مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍ " سورة الأنفال 12-11
"ከርሱ በሆነው ጸጥታ (በጦር ግንባር) በእንቅልፍ በሸፈናችሁና ውሃንም በርሱ ሊያጠራችሁ፣ የሰይጣንን ጉትጎታ ከናንተ ሊያስወግድላችሁ ልቦቻችሁንም (በት ዕግሥት) ሊያጠነክርላችሁ፣ በርሱም ጫሞችን "(በአሸዋው ላይ) ሊያደላድልላችሁ፣ በናንተ ላይ ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውሱ)።ጌታህ ወደ መላእክቱ፦ እኔ (በርዳታዬ) ከናንተ ጋር ነኝና፣ እነዚያን ያመኑትን አጥናኑ፤ በነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፤ ከአንገቶችም በላይ (ራሶችን) ምቱ፤ ከነሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ፤ ሲል ያወረደውን (አስታውስ)።" (ሱረቱል አንፋል 11-12)፡፡
ሰ. በሂጅራ መሀል የተከሰተ፡-
ቁረይሽ ነቢዩን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ለመግደል ወሰኑ፡፡ ወጣቱም ከተማይቱን ከብቦ ይጠባበቅ ጀመር፡፡ የአላህ መልክተኛ ግን በመሀከላቸው አልፈው ወጡ፡፡ አላህ አይናቸውን ሸፍኖት ነበርና፡፡ ከዛም በሒራእ ዋሻ ውስጥ ከባልደረባቸው አቡ-በከር ሲዲቅ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ጋር ተደበቁ፡፡ ጠላትም እሳቸውን ፍለጋ በዋሻው ጫፍ ላይ ቆሞ ይጠባበቅ ነበር፡፡ አይናቸውን ወደ ዋሻው ዝቅ ቢያረጉ እንኳ ማየት በሚችሉበት ቅርበት ያህል ተጠግተው ነበር፡፡ ግን አላህ አይናቸው ወደ ዋሻው ስር እንዳይመለከት አደረገ፡፡ ከዛም ኋላ ላይ ከዋሻው ወጥተው ሲጓዙ፡ ስልጡኑ የፋርስ ጦረኛ ሱራቀተ-ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተመለከታቸው፡፡ በፈረሱ ላይ ሆኖ እሳቸውንና አባ በክርን ማሳደድ ጀመረ፡፡ መጨረሻም ላይ ደረሰባቸውና ልክ መልክተኛው ጋር ሲጠጋ፡ አራቱም የፈረሱ እግሮች አሸዋው ስር ሰመጡ፡ እሱም ከፈረሱ ላይ ወደቀ፡፡ እሳቸውን ለመግደል ሲፈልግና ሲቋምጥ የነበረውም ሰውዬ አሁን በተቃራኒው መልክተኛውን እንዳይገሉት በመስጋት መማጸን ጀመረ፡፡ ይህን በተመለከተ ደግሞ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"إِلَّا تَنْصُرُوهُ فَقَدْ نَصَرَهُ اللَّهُ إِذْ أَخْرَجَهُ الَّذِينَ كَفَرُوا ثَانِيَ اثْنَيْنِ إِذْ هُمَا فِي الْغَارِ إِذْ يَقُولُ لِصَاحِبِهِ لَا تَحْزَنْ إِنَّ اللَّهَ مَعَنَا فَأَنْزَلَ اللَّهُ سَكِينَتَهُ عَلَيْهِ وَأَيَّدَهُ بِجُنُودٍ لَمْ تَرَوْهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ الَّذِينَ كَفَرُوا السُّفْلَى وَكَلِمَةُ اللَّهِ هِيَ الْعُلْيَا وَاللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ " سورة التوبة 40
"(ነቢዩን) ባትረዱት እነዚያ የካዱት ሕዝቦች የሁለት (ሰዎች) ሁለተኛ ሆኖ (ከመካ) ባወጡት ጊዜ አላህ በእርግጥ ረድቶታል ሁለቱም በዋሻዉ ሳሉ ለጓደኛዉ ነዉና ባለ ጊዜ አላህ እርካታዉን በርሱ ላይ አወረደ፤ ባላያችኋቸዉም ሰራዊት አበረታው፤ የነዚያንም የካዱትን ሰዎች ቃል ዝቅተኛ አደረገ፤ የአላህም ቃል እርሷ ከፍተኛ ናት፤ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።" (ሱረቱ-ተውባህ 40)፡፡
ሰ. የአቡ ጀህል መሐላና ውጤቱ፡- አቡ ጀህል ነቢዩን (ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) ሲሰግዱ ካያቸው፡ ከኋላ ጫንቃቸውን እረግጣለሁ ብሎ በላትና በዑዝዛ በመማል ለራሱ ቃል ገባ፡፡ አንድ ቀን ሲሰግዱ ያገኛቸውና፡ ለራሱ የገባውን ቃል ሊፈጽም ወደሳቸው ሄደ፡፡ አጠገባቸው እንደደረሰም በድንገት በእጁ እየተከላከለ ወደ ኋላው መመለስ ጀመረ፡፡ ምን ሆንክ? ሲሉት፡- በኔና በሱ መሀል የእሳት ጉድጓድ ይታየኛል፡ የሚያስፈራ ክንፍም አለ አላቸው፡፡ የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- ወደ እኔ ትንሽ ጠጋ ቢል ኖሮ፡ መላእክት ሰውነቱን በብልት በብልት በቆራረጡት ነበር (ሙስሊም)፡፡ እንዲህ የሚለው የቁርኣን አንቀጽም ወረደ፡-
"أَرَأَيْتَ الَّذِي يَنْهَى * عَبْدًا إِذَا صَلَّى * أَرَأَيْتَ إِنْ كَانَ عَلَى الْهُدَى * أَوْ أَمَرَ بِالتَّقْوَى * أَرَأَيْتَ إِنْ كَذَّبَ وَتَوَلَّى * أَلَمْ يَعْلَمْ بِأَنَّ اللَّهَ يَرَى * كَلَّا لَئِنْ لَمْ يَنْتَهِ لَنَسْفَعًا بِالنَّاصِيَةِ * نَاصِيَةٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَةٍ * فَلْيَدْعُ نَادِيَهُ * سَنَدْعُ الزَّبَانِيَةَ * كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِبْ " سورة العلق 19-9
"አየህን? ያንን የሚከለክለውን፣ ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ አየህን ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢሆን፣ ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን? ይተው ባከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን። ውሸታም ስሕተተኛ የሆነችውን አናቱን። ሸንጎውንም ይጥራ፤ (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን። ይከልከል፤ አትታዘዘው፤ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም።" (ሱረቱል ዐለቅ 9-19)፡
ታዲያ ይህ ሁሉ ነቢይ ለመሆናቸው በቂ ማስረጃ አይሆንምን?
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

👍1
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
"የአላህ መለኮታዊ መልካምና ውብ ስሞች" ክፍል1 ☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ ➤ https://goo.gl/TZRvZk Join us➤ t.me/abuhyder
Audio
"የአላህ መለኮታዊ መልካምና ውብ ስሞች" ክፍል2
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/7VA6Di
Join us➤ t.me/abuhyder
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/7VA6Di
Join us➤ t.me/abuhyder
የዚህ መጽሐፍ 2ኛ ዕትም ወጥቷል!!
በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
"አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው ...." (ሱረቱ አሊ–ዒምራን 3:19)።
የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያ ዕትም በ3,000 ኮፒ ታትሞ ከሁለት ሳምንታት በፊት ከአዲስ አበባ ውጭ (አርባ ምንጭ፣ ደሴ እና ሀላባ) ባሉ ከተሞች ተዳርሷል። አሁን ደግሞ ሁለተኛው ዕትሙ በ3000 ኮፒ ስለወጣ: ከነገ ጀምሮ (በመርካቶ ባዩሽ በቤቴል እና በበኒን) መስጂዶች ለፈላጊዎች ይከፋፈላል። እንዲሁም የፊታችን እሁድ በአወሊያ ኤግዚብሽን ለሚገኙ ሰዎች ይዳረሳል። አላህ በመጽሐፉ ተጠቃሚዎች ያድርገን።

Forwarded from የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
በኦሮሚያ አካባቢ ከፍተኛ የሚሽነሪ እንቅስቃሴ ለመፍጠር እንደታሰበ መረጃዎች እየደረሱኝ ነው። በተለይ ሙስሊም የሚበዛባቸው አካባቢዎች ላይ በቦታው ተገኝቶ ከማስተማር ጀምሮ እስከ ኦንላይን ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ሰዎችን ለማክፈርም መጠነሰፊ ስራ ተጀምሯል..!
ኦሮምኛ መናገር የምትችሉ ወንድምና እህቶች ሰብሰብ በማለትና በመደራጀት መወያየት ከናንተ ይጠበቃል። መረጃዎችን በመለዋወጥም አላማቸውን ማክሸፍ ቀጣይ ስራችሁ ነው። ተሰባስባችሁ ለምትመጡ ወንድምና እህቶች አጫጭር የኦንላይን ኮርስ ስልጠናዎችን በኔ በኩል ለመስጠት ፍቃደኛ ነኝ..!
____
t.me/yahya5
ኦሮምኛ መናገር የምትችሉ ወንድምና እህቶች ሰብሰብ በማለትና በመደራጀት መወያየት ከናንተ ይጠበቃል። መረጃዎችን በመለዋወጥም አላማቸውን ማክሸፍ ቀጣይ ስራችሁ ነው። ተሰባስባችሁ ለምትመጡ ወንድምና እህቶች አጫጭር የኦንላይን ኮርስ ስልጠናዎችን በኔ በኩል ለመስጠት ፍቃደኛ ነኝ..!
____
t.me/yahya5
Forwarded from የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
ሀይማኖታዊ ውይይቶችን አስመልክቶ ...
ብዙ ሰዎች ሀይማኖታዊ ውይይትን አስመልክቶ ያላቸው አመለካከት የተሳሳተ ነው። ማህበረሰባችን በሚያምንበት አጀንዳ ዙሪያ ፊትለፊት መወያየት ላይ የጠነከረ ባህል የለውም። ያልጣመንን ነገር ቀጥታ ማውገዝ እንጅ በሰለጠነ መልኩ የማናምንበትን ነገር እያስቀመጥን መሞገት አለመደብንም። በዚህ ምክንያት ውይይት ሲባል ጦርነት የተባለ እስኪመስለን እንጨነቃለን። ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው። ውይይት የሰለጠነ ማህበረሰብ መገለጫ እንጅ የሚያናጭ አውድማ አይደለም።
በታሪክ ከጥንት ፈላስፋዎች ጀምሮ የሚያምኑበትን ነገር ይዘው ህዝብ ፊት ተሟግተዋል። በጥንታዊ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አባቶች ከተለያዩ የእምነት አባቶች ጋር በነገስታት ፊት ሳይቀር እንደተሟገቱ እናነባለን። ከአይሁድ እምነት አባቶች ጀምሮ እስከ ካቶሊኮች ከጥንት የእርቶዶክስ አባቶች ጋር ተወያይተዋል፣ተከራክረዋል።
በእስልምናውም ያለው እሳቤ ተመሳሳይ ነው። ከነብዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ ሊቃውንት ማስረጃዎችን እየነቀሱ ተሟግተዋል። በነብዩ ጊዜ የነበሩ የነጅራን ክርስቲያኖች መስጅድ ድረስ በመምጣት ከነብዩ ጋር ተወያይተዋል። በወቅቱ የነበሩ አይሁዶችም መሠል አጀንዳዎችን እየያዙ ከነብዩ ጋር ይመጡና ይከራከሩ ነበር። ከቀደምት ሰለፎች መካከል እንደ ኢብን ሀዝም፣ ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ፣ ኢማም አል-ገዛሊ በዚህ ዘርፍ የተካኑ ነበሩ።
በቅርብ ጊዜያትም ይህ አካሄድ የተለመደ ነበር። የዘመናዊው አለም የንፅፅር አዋቂ የሚባሉት ከ200 አመት በፊት የነበሩት ራሀመቱላሂ አል ሂንዲ (የኢዝሀሩል ሀቅ ማራኪ ጥራዝ ደራሲ) ሌላው የቅርብ ጊዜ ፋና ወጊ ተሟጋች ናቸው። ባለንበት ዘመን አሻራቸውን ያሳረፉት ሸይኽ አህመድ ዲዳት፣ ዶ/ር ዛኪር ናይክ፣ ዶ/ር ሻቢር አሊ ወዘተ .. ሌላው የዘርፉ ተጠቃሽ ሰዎች ናቸው።
እናም ወገኖቼ ሀይማኖታዊ ውይይት የሚያስበረግግ ጉዳይ ሳይሆን የሚበረታታ የሰለጠነ ሰው መለያ ነውና ሊደገፍ የሚገባው ተግባር ነው። ከዚህ በዘለለ ምናልባት ውይይቱን ወደ ብሽሽቅ ሊያመሩ የሚችሉ ዘለፋና ስድቦችን አስመልክቶ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በሰለጠነ መንገድ ተነጋግሮ መግባባት ካልተቻለ በመልካም ቃላት መለያየት ተገቢና እስልምናው የሚያስተምረን ተግባር ነው።
© t.me/yahya5

"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" 6 በአቡ ሀይደር በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡ 2. ለነቢይነታቸው ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸው ማስረጃ…
"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" 7
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
2. ለነቢይነታቸው ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸው ማስረጃ
ቀ/ ትንሽ ውሃ እጅግ መብዛቱ
ሙስሊሞች (ሶሀባዎች) መዲና ውስጥ እያሉ ለውዱእ ውሃ እጅግ በጣም ይቸግራቸው ነበር፡፡ ታዲያ ምን ተከሰተ?፡-
عَنْ أَنَسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، قَالَ: أُتِيَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِإِنَاءٍ، وَهُوَ بِالزَّوْرَاءِ، فَوَضَعَ يَدَهُ فِي الإِنَاءِ، «فَجَعَلَ المَاءُ يَنْبُعُ مِنْ بَيْنِ أَصَابِعِهِ، فَتَوَضَّأَ القَوْمُ» قَالَ قَتَادَةُ: قُلْتُ لِأَنَسٍ: كَمْ كُنْتُمْ؟ قَالَ: ثَلاَثَ مِائَةٍ، أَوْ زُهَاءَ ثَلاَثِ مِائَةٍ.
አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡- “ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘውራዕ በተባለው ስፍራ ከባልደረቦቻቸው ጋር እያሉ ውሃ መያዣ እቃ መጣላቸው እጃቸውንም በእቃው ላይ አስቀመጡና አነሱት ከዚያም ከጣታቸው መካከል ውሃ መፍለቅ ጀመረ፡፡ ህዝቦቹም ውዱእ አደረጉ” ቀታደታ የተባለው ሰው (ረሒመሁላህ) አነስ ኢብኑ ማሊክን (ረዲየላሁ ዐንሁ) (በወቅቱ ከጣታቸው ይፈልቅ በነበረው ውሀ ለዉዱእ የተጠቀማችሁት) ስንት ነበራችሁ? ብሎ ጠየቀው፡፡ አነስም ‹‹ሶስት መቶ ነበርን›› አለ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት)፡፡
عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ: عَطِشَ النَّاسُ يَوْمَ الحُدَيْبِيَةِ وَالنَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بَيْنَ يَدَيْهِ رِكْوَةٌ فَتَوَضَّأَ، فَجَهِشَ النَّاسُ نَحْوَهُ، فَقَالَ: «مَا لَكُمْ؟» قَالُوا: لَيْسَ عِنْدَنَا مَاءٌ نَتَوَضَّأُ وَلاَ نَشْرَبُ إِلَّا مَا بَيْنَ يَدَيْكَ، فَوَضَعَ يَدَهُ فِي الرِّكْوَةِ، فَجَعَلَ المَاءُ يَثُورُ بَيْنَ أَصَابِعِهِ، كَأَمْثَالِ العُيُونِ، فَشَرِبْنَا وَتَوَضَّأْنَا قُلْتُ: كَمْ كُنْتُمْ؟ قَالَ: لَوْ كُنَّا مِائَةَ أَلْفٍ لَكَفَانَا، كُنَّا أَلْف وَأَرْبَع مِائَةٍ. رواه البخاري 3576
ጃቢር ኢብኒ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "ሰዎች (ሶሓባዎች) የሑደይቢያ ጊዜ ተጠሙ፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ ደግሞ ከቆዳ የተሰራ ትንሽዬ የውሀ መያዣ እቃ ነበር፡፡ እሳቸውም ዉዱእ አደረጉበት፡፡ ሰዎቹም ወደሳቸው ዘንድ መጡ፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹ምን ሆናችሁ?›› ሲሏቸው፡ እነሱም፡- እርሶ ዘንድ ካለው ውጪ ለዉዱእም ሆነ ለመጠጥ የምንገለገልበት የሆነ ውሀ እኛ ዘንድ የለንም አሉ፡፡ መልክተኛውም እጃቸውን በእቃው ላይ አደረጉና ሲያነሱት፡ ልክ እንደ ምንጭ ከጣታቸው መሀል ውሀ መፍለቅ ጀመረ፡፡ እኛም ጠጣን፡ ዉዱእም አደረግን፡፡ (ዒምራን ኢብኑ ሑሰይንም) ለጃቢር፡- በወቅቱ ስትን ነበራችሁ? አልኩት አለ፡፡ ጃቢርም፡- ‹‹አንድ መቶ ሺህ ብንሆንም ይበቃን ነበር!!፡፡ እኛ ግን አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበርን›› በማለት መለሰ" (ቡኻሪይ 3576፣ አሕመድ 14522፣ ሶሒሕ ኢብኑ-ሒባን 6542)፡፡
በ/ ትንሽ ምግብ እጅግ መብዛቱ
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እጅግ ተርበው ነበር፡- አቡ ጦልሐም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ጥቂት የገብስ ቁራሽ ይዞላቸው መጣ ነቢዩም እንዲፈተፈት አዘዙ ከዚያም ዱአ አደረጉበትና ሶሓባዎችም አስር አስር ሆነው በመቀመጥ እንዲበሉ አዘዙ ያቺን ጥቂት የገብስ ቁራሽ ሁሉ ጠግበው በሉ፡፡ ብዛታቸውም ሰማኒያ ነበሩ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
እንደዚሁ አንድ ጊዜ በነቢዩና (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሶሐቦቻቸው ላይ በዘመቻ ምሽግን እየቆፈሩ ሳለ ረሃብ ጠናባቸው፡፡ ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ፍየል ለነቢዩና ለሶሓቦቹ አረደ፡፡ ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በእርዱ ላይ ዱዓእ በማድረግ የዘመቻውን ሰዎች እንዳለ በመጣራት እንዲበሉ ተደረገ፡፡ ሁሉም ጠግበው በሉ ብዛታቸው ግን አንድ ሺህ ነበር፡፡ (ቡኻሪ የዘገበው)፡፡
ተ/ የቴምር ግንድ መንሰቅሰቅ
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የጁሙዓህ ኹጥባ የሚያደርጉት የቴምር ግንድን በመደገፍ ነበር፡፡ ሚንበር ከተሰራላቸው በኋላ ግን ያንን የቴምር ግንድ ትተው ወደተሰራላቸው ሚንበር ሲወጡ ያ የቴምር ግንድ እንደ ግመል መንሰቅሰቅ ተንሰቅስቆ አለቀሰ፡፡ የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደርሱ በመምጣት እጃቸውን ሲያሳርፉበት ወዲያው ፀጥ አለ፡፡ (ቡኻሪ ነሳኢይና ቲርሚዚይ የዘገቡት)፡፡
ቸ/ የምግብ ተስቢሕ ማድረግ
የነቢያችን ባልደረባዎች (ሶሓቦች) ነቢዩ ባሉበት ስፍራ ላይ አብረው ሲመገቡ፡ ምግቡ ራሱ ተስቢሕ ሲያደርግ በጆሮዋቸው ይሰሙ ነበር፡፡ (ቡኻሪና ቲርሚዚ የዘገቡት)፡፡ ሌሎችም ብዙ ብዙ…

Forwarded from ንፅፅር
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
በአሁኑ ሰአት እየተሰጡ ካሉ ኮርሶች መካከል አንዱ የሆነው "ቀደምት መለኮታዊ መፅሀፍትና ይዘታቸው" የተሰኘውና ተውራትና ዘቡርን በጥቅሉ ብሉይ ኪዳንን የሚያጠናው ኮርስ ሊገባደድ ጥቂት ይቀረዋል። ኮርሱ በወንድም የሕያ ኢብኑ ኑህ የሚሰጥ ሲሆን 100 ተማሪዎች አሉት። ኮርሱ ሲጠናቀቅ በቀጣይ "የቁርአን አሰባሰብና ጥበቃ" በሚል ማዕከሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር ይሆናል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሁሉም ክፍል የንፅፅር ተማሪዎች የሚሰጠው "መሠረታዊ የእስልምና አስተምህሮ" በወንድም ኢልያህ ማህመድ የሚቀጥል ይሆናል። አዲሱን ኮርስ አስመልክቶ ምዝገባ የሚጀመርበትን ቀን በዚሁ ፔጅ የምናሳውቅ ይሆናል።
© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
@Hidayaislam

በሃይማኖት ማስገደድ የለም!!
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
ዛሬ የምንመለከተው፡ ኢስላም፡- ሰዎች እስልምናን ካልተቀበሉ፡ ሸሀደተይንን (የአላህን አምላክነት እና የነቢዩ ሙሐመድን መልክተኝነት) ካልመሰከሩ ግደሏቸው ብሎ ያዛል የሚለውን ከንቱ የባዶ ሜዳ ጩኸት ነው፡፡
አምላካችን አላህ፡ ባሪያዎቹ ወደውና ፈልገው እንጂ፡ ጠልተውና ተገደው እንዲያመልኩት አይፈልግም፡፡ ለዚህም ትልቁ ማስረጃችን፡ በኢስላም ውስጥ እምነትም ሆነ ስራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው መሟላት ከሚገባቸው ሶስት መስፈርት ውስጥ አንዱ ‹‹ኢኽላስ›› የሚባለው መኖሩ ነው፡፡
‹‹ኢኽላስ›› ማለት፡- የሚሰራን ማንኛውንም አይነት መልካም ስራ ለአላህ ብቻ ብሎ ማድረግ፡ ከምድራዊ ጥቅም ፍለጋና ከሰዎች እዩልኝ ስሙልኝ እራስን ማራቅና ማግለል ማለት ነው፡፡ አላህን ማምለክ የሚፈልግ ሰው፡ አምልኮቱም ፍሬያማ እንዲሆን በ‹‹ኢኽላስ›› ብቻ የሚተገብር መሆን አለበት፡፡ ታዲያ ሰዎች ተገደው፡ መሳሪያ ተደቅኖባቸው፡ ህይወታቸውን ለማትረፍ ብለው እንጂ ለአላህ ብለው ባይሰልሙና ባያምኑ ምኑ ጋር ነው ትርፋቸው? ማስገደዱስ ለምን? ለፍቶ መና ከመሆን ውጪ የሚያተርፉት ነገር የለምና!!፡፡
ኢስላም የሌላ እምነት ተከታዮችን ሃይማኖታቸውን ትተው ወደ ኢስላም እንዲመጡ ያስገድዳል የሚለው ተረት ተረት፡ ኢስላምን በጦር መሳሪያ ማሸነፍ ሲያቅታቸው፡ በሀሰት ወሬ ለማዳከም የሚደረግ የከንቱዎች መፍጨርጨር ነው፡፡ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው አይደል የሚባለው፡፡ እኛ:– በኢስላም አስተምህሮ ሰው እምነቱን ለቆ ወደ ኢስላም እንዲቀላቀል የምርጫ ጉዳይ እንጂ፡ ግዳጅ እንዳልተጣለበት ለማወቅ ከፈለግን ቀጣዩን ማስረጃዎች እንመልከታቸው፡-

1. በቀጥታ ቋንቋ፡-
አላህ በሃይማኖት ማስገድ እንደሌለ፡ ሰው የሚከተለውን እምነት ትቶ ወደ ኢስላም መምጣት ወይም በዛው ክህደቱ ላይ መዘውተር የግለሰቡ የምርጫ ጉዳይ እንደሆነ በማብራራት ይነግረናል፡-
" لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ قَدْ تَبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ فَمَنْ يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِنْ بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَى لَا انْفِصَامَ لَهَا وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ " سورة البقرة 256
"በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 256)፡፡
- ‹‹በሃይማኖት ማስገደድ የለም›› የሚለው፡- ሙስሊም ያልሆነ ሰው በጠቅላላ (ካፊሩ ኅብረተሰብ) ኢስላምን ኢንዲቀበል ማስገደድ አይቻልም ይለናል፡፡ ለምን? ብለን ጥያቄ ስናነሳ፡ መልሱም፡-
- ‹‹ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ›› የሚለው ይሆናል፡፡ እውነት ከጸሀይ በላይ የበራና የደመቀ ነው፡፡ አላህ ነቢዩ ሙሐመድን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይ አድርጎ በመላክ፡ ቅዱስ ቁርኣንን ለሰዎች ሁሉ የህይወት መመሪያ ይሆን ዘንድ የመጨረሻ መለኮታዊ መጽሐፍ አድርጎ በማውረድ፡ እውነቱን ከሀሰት ለይቶ ገለጸው፡፡ ከዚህ በኋላ፡-
- ‹‹በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው›› በማለት፡- ፈቅዶና ፈልጎ በአላህ ብቸኛ አምላክነትና ተመላኪነት ያመነ፡ እንዲሁም በጣኦት (ከአላህ ውጭ የሚመለክ ማንኛውም አካል) አምልኮ የካደ ሰው፡ የዚህ ሰው ተስፋው፡-
- ‹‹ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ›› በማለት፡ ወደ ጀነት የሚያደርሰውን የህይወት ጎዳና (ኢስላም፣ ላኢላሀ ኢለሏህ) አስተማማኝ በሆነ መልኩ ያዘ ብሎ ይነግረናል፡፡ ከዛ ውጭ ለተረፈው ነገር ደግሞ፡-
- ‹‹አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው›› በማለት፡ የሰዎችን ንግግር ሰሚና አዳማጭ፡ የልባቸውንም ክፋትና ደግነት ዐዋቂ ጌታ እሱ ብቻ ስለሆነ፡ ተቆጣጣሪነቱ በኔ ይብቃ እያለ ነው ጌታችን፡፡
" وَقُلِ الْحَقُّ مِنْ رَبِّكُمْ فَمَنْ شَاءَ فَلْيُؤْمِنْ وَمَنْ شَاءَ فَلْيَكْفُرْ إِنَّا أَعْتَدْنَا لِلظَّالِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمْ سُرَادِقُهَا وَإِنْ يَسْتَغِيثُوا يُغَاثُوا بِمَاءٍ كَالْمُهْلِ يَشْوِي الْوُجُوهَ بِئْسَ الشَّرَابُ وَسَاءَتْ مُرْتَفَقًا " سورة الكهف 29
"እውነቱም፥ ከጌታችሁ ነው፤ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ፣ በላቸው፤ እኛ ለበደለኞች አጥርዋ በነሱ የከበበ የሆነችውን እሳት አዘጋጅተናል፤ (ከጥም) እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ፥ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ፥ ይረዳሉ፤ መጠጡ ከፋ! መደገፊያይቲም ምንኛ አስከፋች!" (ሱረቱል ከህፍ 29)፡፡
- ‹‹እውነቱም፥ ከጌታችሁ ነው በላቸው›› በዚህም አንቀጽ ላይ፡- የአማኞች ግዳጅ እውነቱ ያለው ከጌታ አላህ ዘንድ መሆኑን ማብራራትና መመስከር ብቻ እንደሆነ ይገልጽና፡ ከነሱ በኩል ደግሞ፡-
- ‹‹የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ፣›› በማለት፡ ከፈለጉ በዛው ክህደታቸው መዘውተር እንደሚችሉ፡ ያም ካልሆ ደግሞ የመጨረሻው ዓለም ጀነት ይሻለናል ካሉ ማመን እንደሚችሉ ገለጸላቸውና፡ ክህደቱን ለመረጡት ግን በመጨረሻው ዓለም፡-
- ‹‹እኛ ለበደለኞች አጥርዋ በነሱ የከበበ የሆነችውን እሳት አዘጋጅተናል›› በማለት፡ የሚጠብቃቸውን አስከፊ የጀሀነም ቅጣት ዘረዘር እንጂ፡ እስኪሰልሙ አስገድዷቸው፡ ወይንም ግደሏቸው አላለም፡፡
" قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ * لَا أَعْبُدُ مَا تَعْبُدُونَ * وَلَا أَنْتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ * وَلَا أَنَا عَابِدٌ مَا عَبَدْتُمْ * وَلَا أَنْتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ * لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ " سورة الكافرون 6-1
"በላቸው፦ እናንተ ከሐዲዎች ሆይ፣ ያንን የምትግገዙትን (ጣዖት አሁን) አልግገዛም። እናንተም አሁን የምግገዛውን (አምላክ አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም። እኔም ያንን የተገዛችሁትን (ወደፊት) ተገዢ አይደለሁም እናንተም እኔ የምግገዛውን (ወደፊት) ተገዢዎች አይደላችሁም። ለናንተ ሃይማኖታችሁ አላችሁ፤ ለኔም ሃይማኖቴ አለኝ።" (ሱረቱል ካፊሩን 1-6)፡፡
- ‹‹ያንን የምትግገዙትን አልግገዛም›› በዚህም አንቀጽ ላይ ለከሀዲያን በመላ፡ እነሱ የሚያመልኩትን የሀሰት አማልክት እኛ አሁንም ሆነ ወደፊት እንደማንገዛ፡ እንድንነግራቸው ጌታችን ያዘናል፡፡ እነሱም፡ በፈቃደኝነት እኛ የምንገዛውን እውነተኛ አምላክ አላህን ለመገዛት የማይፈልጉ መሆናቸውን (አላህ መልካም የሻለት ብቻ ሲቀር) ያስረዳንና መጨረሻም፡-
- ‹‹ለናንተ ሃይማኖታችሁ አላችሁ፤ ለኔም ሃይማኖቴ አለኝ በላቸው›› በማለት፡ እኛ የራሳችን የሆነ እውነተኛ ሃይማኖት (ኢስላም) አለን፡ እናንተ ደግሞ የራሳችሁ የሆነ የሀሰት ሃይማኖት (ከኢስላም ውጭ እውነት ስለሌለ) አላችሁ፡ ብለን መለያየታችንን እንድንነግራቸው እንጂ ወደኛ ሃይማኖት እንዲመጡ እንድናስገድዳቸው አላዘዘንም፡፡

2. በነቢዩ ተልእኮ፡-
ሌላው ኢስላም በሃይማኖት ማስገደድ አለመኖሩን ያወጀው፡ የነቢዩ ሙሐመድን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የተልእኮ ሚና በመግለጽ ነው፡፡ በብዙ የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾች ላይ የሳቸውን ተልእኮ የመጨረሻ ግብ የሚገልጸው፡- ‹‹ባንተ ላይ ያለብህ መልእክቱን በተብራራ መልኩ ማድረስ ብቻ ነው›› እንዲሁም፡- ‹‹አንተ በነሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም፣ አልተሾምክምም›› በማለት ነው፡፡ ታዲያ ምኑ ላይ ነው ኢስላም በሃይማኖት ያስገድዳል የሚባለው? እስኪ ቀጣዮቹን አንቀጾች እንመልከታቸው፡-
" فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ وَقُلْ لِلَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ وَالْأُمِّيِّينَ أَأَسْلَمْتُمْ فَإِنْ أَسْلَمُوا فَقَدِ اهْتَدَوْا وَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا عَلَيْكَ الْبَلَاغُ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ " سورة آل عمران 20
"ቢከራከሩህም :- ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች (እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ) በላቸዉ፤ ለእነዚያም መጽሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሀይሞቹ፦ሰለችማሁን? በላቸዉ፤ ቢሰልሙም በእርገጥ ተመሩ እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለበህ ማድረስ ብቻ ነዉ:: አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው::" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 20)፡፡
- ‹‹ቢከራከሩህም:- ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች (እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ) በላቸዉ››፡- በማለት ከላይ በቁጥር 19 ላይ አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢስላም ብቻ መሆኑን ከገለጸ በኋላ፡ በሃይማኖት ጉዳይ ቢከራከሩህ፡ ያንተ ምላሽ፡- እኔና የተከተሉኝ ሰዎች ለአላህ እጅ ሰጥተናል (ታዘናል) ነው መሆን ያለበት አላቸው፡፡ ከዛም፡-
- ‹‹ለእነዚያም መጽሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሀይሞቹ፦ሰለችማሁን? በላቸዉ›› በማለት፡ በወቅቱ የነበሩ ያልተማሩ ዐረብ ጣኦታውያንና የመጽሐፉን ሰዎች (አይሁድና ክርስቲያን) ሰልማችኋል ወይ? ለአላህ እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ናችሁ ወይ? ብለህ ጥርሪ አቅርብላቸው ብሎ አዘዛቸው፡፡ እነሱ ደግሞ፡-
- ‹‹ቢሰልሙም በእርገጥ ተመሩ እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለበህ ማድረስ ብቻ ነዉ›› በማለት፡ እሺ ብለው ኢስላምን ፈቅደውና ወደው ቢቀበሉ በእርግጥም ወደ እውነት ተመሩ፡ ካልፈቀዱና ካልፈለጉ ግን አንተ ግዳጅህ፡- መልእክቱን በተብራራ መልኩ ማድረስ እንጂ እነሱን እንዲሰልሙ ማስገደድ አይደለም ብሎ የሳቸውን ሚና ይገልጽና፡ ስለነሱ እንቢተኝነት ደግሞ፡-
- ‹‹አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው›› በማለት፡ የባሮቹን ሁኔታ የሚቆጣጠረውና የሚመለከተው፡ የልባቸውን ሀሳብ የሚያውቀው እሱ ብቻ መሆኑን ይገልጻል፡፡
" قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ فَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا عَلَيْهِ مَا حُمِّلَ وَعَلَيْكُمْ مَا حُمِّلْتُمْ وَإِنْ تُطِيعُوهُ تَهْتَدُوا وَمَا عَلَى الرَّسُولِ إِلَّا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ " سورة النور 54
"አላህን ተገዙ፤ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትሸሹም (አትጐዱትም)፤ በርሱ ላይ ያለበት የተገደደውን ማድረሰ ብቻ ነው፤ በናንተም ላይ ያለባችሁ፣ የተገደዳችሁት (መታዘዝ) ብቻ ነው፤ ብትታዘዙትም ትምመራላችሁ፤ በመልክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም፤ በላቸው" (ሱረቱ-ኑር 54)፡፡
- ‹‹አላህን ተገዙ፤ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትሸሹም (አትጐዱትም)›› በማለት፡ ለኛ የሚበጀን መንገድ፡- አላህን መገዛትና የላከውን መልክተኛ(ሙሐመድን) መታዘዝ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ከዚህ አምልኮና ታዛዥነት ብንሸሽ የምንጎዳው እራሳችንን እንጂ አላህንና መልክተኛውን እንዳልሆነ ያስረዳና፡ መልክተኛው እንደሆነ፡-
- ‹‹በርሱ ላይ ያለበት የተገደደውን ማድረሰ ብቻ ነው፤ በናንተም ላይ ያለባችሁ፣ የተገደዳችሁት (መታዘዝ) ብቻ ነው›› ብሎ የመልክተኛው ግዳጅ መልእክቱን ማድረስ እንደሆነና እሱም እንዳደረሰ ገልጾ፡፡ የናንተ ግዳጅ ደግሞ፡ መታዘዝ ነው በማለት እንዲታዘዙ ከነገራቸው በኋላ ውጤቱን ደግሞ፡-
- ‹‹ብትታዘዙትም ትምመራላችሁ፤ በመልክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም፤ በላቸው›› በማለት፡ መልክተኛውን የታዘዘ ሰው ቅኑን መንገድ እንደተመራ፡ እምቢ ላለ ሰው ደግሞ፡ የመልክተኛው ግዳጅ መልእክቱን ግልጽ በሆነ መልኩ ማድረስ እንጂ ማስገደድ እንዳልሆነ በመግለጽ ይቋጨዋል፡፡
" نَحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ وَمَا أَنْتَ عَلَيْهِمْ بِجَبَّارٍ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَنْ يَخَافُ وَعِيدِ " سورة ق 45
"እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነን፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም፡፡ ስለዚህ ዛቻየን የሚፈራን ሰው በቁርኣን አስታውስ፡፡" (ሱረቱ ቃፍ 45)፡፡
- ‹‹እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነን›› በማለት፡ ከሀዲያን የነቢያችንን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይነት እንደሚስተባብሉና፡ እሱም ይህንን ሁኔታቸውን እንደሚያውቅ ከገለጸ በኋላ፡ ለሳቸው ደግሞ፡-

‹‹አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም›› በማለት፡ መልእክቱን በግልጽ ከማድረስ ውጪ ያንተን ነቢይነት እንዲመሰክሩ ማስገደድ አትችልም በማለት ይነግራቸዋል፡፡ ከዛ ይልቅ፡-
- ‹‹ስለዚህ ዛቻየን የሚፈራን ሰው በቁርኣን አስታውስ›› በማለት፡ የሳቸው ሚና የጌታውን የቂያም ቀን ዛቻን የሚፈራን ሰው በቁርኣን ማስታወስና መገሰጽ እንደሆነ ይገልጻል፡፡
በዚህ ዙሪያ የተነገሩ በጣም ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ለናሙና ያህል ግን ሶስቱን እንደ ምሳሌ ካየናቸው፡ የተወሰኑትን ደግሞ በግል እንድትመለከቷቸው ምንጩን ልስጣችሁ፡-
(ሱረቱ-ኒሳእ 80፣ ሱረቱል ማኢዳህ 92.99፣ ሱረቱል አንዓም 104.107፣ ሱረቱ-ነሕል 82፣ ሱረቱል ዐንከቡት 18፣ ሱረቱ-ሹራ 48፣ ሱረቱ-ተጋቡን 12፣ ሱረቱል ጋሺየህ 22)፡፡
3. በአላህ ሁሉን ቻይነት፡-
ሌላው በሃይማኖት ማስገደድ እንደሌለ የሚያመላክተው ቅዱስ ቁርአናዊ ትምሕርት፡- የአላህን ያልተገደበ ፈቃድ በመግለጽ ነው፡፡ አላህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ልብ በኃይልና በግዳጅ እንዲያምኑ ለማድረግ ቢፈልግ ኖሮ፡ በምድር ያሉ ነቢያትንና ተከታዮቻቸውን፡- አስገድዱ ከማለት ይልቅ እራሱ የሰዎችን ልብ በአንዴ መቀየር አይችልም ነበር? ይህንንስ ለማድረግ የሚያግደው ምን ኃይል ይኖራል? የአደም ልጆች ልብ በጠቅላላ ያለው በሱ መለኮታዊ እጅ ስር ነው፡፡ የፈለገውን እንደፈለገው ማድረግ ይችላል፡፡ ታዲያ ይህን ማድረግ እየቻለ ያላደረገው ግን፡ ሰዎች በምርጫቸው የፈለጉትን የእምነትን ጎዳና እንዲከተሉ እንጂ፡ እሱ ማድረግ አቅቶት፡ እኛ እንድናግዘውና ፈቃዱን እንድንፈጽምለት አይደለም፡፡ ለዚህ ሀሳብ ደጋፊ የሆኑ አንቀጾችን ደግሞ ቀጥለን እንመልከታቸው፡-
" وَإِنْ كَانَ كَبُرَ عَلَيْكَ إِعْرَاضُهُمْ فَإِنِ اسْتَطَعْتَ أَنْ تَبْتَغِيَ نَفَقًا فِي الْأَرْضِ أَوْ سُلَّمًا فِي السَّمَاءِ فَتَأْتِيَهُمْ بِآيَةٍ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَجَمَعَهُمْ عَلَى الْهُدَى فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْجَاهِلِينَ " سورة الأنعام 35
"(ኢስላምን) መተዋቸውም ባንተ ላይ ከባድ ቢኾንብህ በምድር ውስጥ ቀዳዳን ወይም በሰማይ ውስጥ መሰላልን ልትፈልግና በተአምር ልትመጣቸው ብትችል (አድርግ)፡፡ አላህም በሻ ኖሮ በቅኑ መንገድ ላይ በሰበሳባቸው ነበር፡፡ ከተሳሳቱትም ሰዎች በፍጹም አትኹን፡፡" (ሱረቱል አንዓም 35)፡፡
- ‹‹(ኢስላምን) መተዋቸውም ባንተ ላይ ከባድ ቢኾንብህ›› በማለት፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ለሰዎች ካላቸው እዝነትና ርኅራሄ የተነሳ የኢስላምን መልእክት ባለመቀበላቸው፡ ለጥፋት መዳረጋቸው እጅጉኑ ይጨንቃቸውና ያሳስባቸው እንደነበር ይገልጽና፡-
- ‹‹በምድር ውስጥ ቀዳዳን ወይም በሰማይ ውስጥ መሰላልን ልትፈልግና በተአምር ልትመጣቸው ብትችል (አድርግ)›› በማለት፡ እነዚህ ሰዎች ለእምነት የተዘጋጁ እንዳልሆኑ ገለጸላቸው፡፡ ከፈለግክም ደግሞ፡ ምድርን ሰርጉደህም ሆነ ወደ ሰማይ አርገህ እነሱን ሊያሳምናቸው የሚችል ተአምር አምጣና ሞክራቸው፡፡ እነሱ ግኑ አያምኑም ብሎ ነገራቸው፡፡ በግድ እንዲያምኑ ለማድረግ ቢሆንማ፡-
- ‹‹አላህም በሻ ኖሮ በቅኑ መንገድ ላይ በሰበሳባቸው ነበር›› በማለት፡ እኔ በፈቃዴ የሁሉንም ልብ በኃይል በመቀየር በቅኑ ጎዳና (በኢስላም) ላይ በሰበሰብኳቸው ነበር፡ ብሎ የሱን ሁሉን ቻይነት ያስረዳናል፡፡ ግን ያላደረገው፡ እምነት በፈቃደኝነት እንጂ በግዳጅ የሚፈጸም ነገር ባለመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም አንተ፡-
- ‹‹ከተሳሳቱትም ሰዎች በፍጹም አትኹን›› በማለት፡ አላህ በክህደታቸውና በአመጻቸው ምክንያት ሂዳያ ያልሻላቸውን ሰዎች፡ አንተ በመጨነቅ ሂዳያ እንዲያገኙ እያልክ ስህተት ውስጥ አትግባ አላቸው፡፡
" وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ مَا أَشْرَكُوا وَمَا جَعَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا وَمَا أَنْتَ عَلَيْهِمْ بِوَكِيلٍ " سورة الأنعام 107
"አላህም በሻ ኖሮ ባላጋሩ ነበር፡፡ በእነሱም ላይ ጠባቂ አላደረግንህም፡፡ አንተም በእነሱ ላይ ኃላፊ አይደለህም፡፡" (ሱረቱል አንዓም 107)፡፡
- ‹‹አላህም በሻ ኖሮ ባላጋሩ ነበር›› በማለት፡ ከአላህ ውጪ ያለን አካል በማምለክ በአላህ ላይ ያጋሩ ሰዎች፡ አላህ ቢፈልግ ኖሮ በኃይል ማጋራታቸውን አስቁሞ ወደ እምነት መስመር መመለስ እንደሚችል ገለጸ፡፡ ነገር ግን ሰዎች በገዛ ምርጫቸው የፈለጉትን የእምነት መንገድ እንዲከተሉ ተዋቸው፡፡ ከዛም ለመልክተኛው፡-
- ‹‹በእነሱም ላይ ጠባቂ አላደረግንህም፡፡ አንተም በእነሱ ላይ ኃላፊ አይደለህም›› በማለት፡ እነሱን እንዲያምኑ በማድረግ ከኔ ቅጣት ልትጠብቃቸው አትችልም፡ ደግሞም ልትጠቅማቸውም አትችልም ብሎ ገለጸ፡፡
" وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ لَآمَنَ مَنْ فِي الْأَرْضِ كُلُّهُمْ جَمِيعًا أَفَأَنْتَ تُكْرِهُ النَّاسَ حَتَّى يَكُونُوا مُؤْمِنِينَ " سورة يونس 99
"ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን?" (ሱረቱ ዩኑስ 99)፡፡
- ‹‹ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር›› በማለት፡ አሁንም ጌታ አላህ ቢፈልግ ኖሮ፡ በምድር ላይ ያሉ ሰዎችን ሁሉ በመሰብሰብ እንዲያምኑ ማድረግ ይችል ነበር፡ ይህን ከማድረግ ሊከለክለው የሚችል ምንም ነገር የለም እያለ ነው፡፡ ያንን ከማድረግ የተወው ግን ሰዎች በምርጫቸው እንዲወስኑ ስለፈለገ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ቀጥሎም ለመልክተኛው፡-
- ‹‹ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን?›› በማለት፡ ያንተ ሚና መልእክቱን በተብራራ መልኩ ማድረስ እንጂ፡ መልእክትህን አምነው እንዲቀበሉ ማስገደድ አትችልም እያለ ነው፡፡
ስለዚህ በሃይማኖት ማስገደድ አለ የሚለው፡ የሀሰተኞች ከንቱ ልፈፋ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ጥቅሶችን ደግሞ በግል እንድትመለከቱት ላስቀምጥላችሁ፡-
(ሱረቱ ሁድ 118፣ ሱረቱ-ነሕል 9.93፣ ሱረቱ-ሰጅዳህ 13፣ ሱረቱ-ሹራ 8)፡፡

4. ከስራ ተቀባይነት አንጻር፡-
ሌላው በኢስላም በሃይማኖት ማስገደድ የለም የምንልበት ምክንያት ደግሞ ይህ ነው፡፡ አንድ ሰው ስራው አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ማመኑ ግድ ነው፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያላመነ ሆኖ መልካም ስራን ቢሰራ፡ በኢስላም ስራው ከንቱ ነው ይባላል፡፡ መናፍቃን (ሙናፊቆች) በምላሳቸው አምነናል እያሉ፡ በሰውነታቸውም የሙስሊሞችን የአምልኮ ተግባር (ሶላት፣ ሐጅ..) እየፈጸሙ፡ ግን በመጨረሻው ቀን ከከሳሪዎች የሚሆኑት ለምንድነው? ልባቸው አምኖ ስላልተቀበለው አይደል? ታዲያ ዛሬ አንድ ሙስሊም ያልሆነን ግለሰብ በመሳሪያና በኃይል በማስገደድ ውስጡ ያላመነበትን ኢስላምን በምላሱ እንዲመሰክር ብናደርገው፡ ለሱ ምን ይጠቅመዋል? እኛስ ምን ትርፍ እናገኛለን?
አላህ መናፍቃንን በምላሳቸው በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል እያሉ፡ የነቢዩ ሙሐመድን መልክተኝነት እንመሰክራለን እያሉ፡ ጌታችን ግን አላመኑም ውሸተኞች ናቸው፡ በመጨረሻው ዓለምም አሳማሚ ቅጣት አላቸው ይለናል፡፡ ቀጥሎ የሚቀርቡትን ጥቅሶች እንመልከታቸው፡-
" وَمِنَ النَّاسِ مَنْ يَقُولُ آمَنَّا بِاللَّهِ وَبِالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَا هُمْ بِمُؤْمِنِينَ * يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّا أَنْفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ * فِي قُلُوبِهِمْ مَرَضٌ فَزَادَهُمُ اللَّهُ مَرَضًا وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ بِمَا كَانُوا يَكْذِبُونَ " سورة البقرة 10-8
"ከሰዎችም «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ አልሉ፤ እነርሱም አማኞች አይደሉም፡፡ አላህንና እነዚያን ያመኑትን (ሰዎች) ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ ነፍሶቻቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሽታ አለባቸው፡፡ አላህም በሽታን ጨመረባቸው፡፡ ለነርሱም ይዋሹ በነበሩት ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 8-10)፡፡
" إِذَا جَاءَكَ الْمُنَافِقُونَ قَالُوا نَشْهَدُ إِنَّكَ لَرَسُولُ اللَّهِ وَاللَّهُ يَعْلَمُ إِنَّكَ لَرَسُولُهُ وَاللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَكَاذِبُونَ " سورة المنافقون 1
"መናፍቃን በመጡህ ጊዜ አንተ የአላህ መልክተኛው መሆንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን ይላሉ፤ አላህም አንተ በ እርግጥ መል ዕክተኛ መሆንህን ያውቃል፤ አላህም መናፍቃን (ከልብ እንመሰክራለን በማለታቸው) ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል።" (ሱረቱል ሙናፊቁን 1)፡፡
እንግዲያውስ ጉዳዩ እንደዛ ከሆነ፡ ሳይወዱ በግዳቸው ኢስላምን እንዲቀበሉ የሚደረጉ ሰዎች ካሉ፡ ምን ሊጠቅማቸው ይችላል? በመሆኑም ኢስላም በሃይማኖት ማስገደድን አያምንም፡፡
አምላካችን አላህ ሆይ! ከሞት በፊት ትክክለኛ ተውበትን፣ በሞት ጊዜ ሸሀዳን፣ በቀብር ውስጥ ጽናትን፣ በአኼራ ደግሞ ጀነትን በራሕመትህ ወፍቀን፡፡ ከገርገራ ጭንቀት፣ ከቀብር ፈተና እና ከጀሀነም እሳትም ቅጣት አርቀን፡፡
የአላህ ሰላምና መልካም ውዳሴ በነቢያችንና በቤተሰቦቻቸው፡ ፈለጋቸውንም በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን፡፡