"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" 2
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
1. ስለ ነቢይነታቸው የተነገረ ትንቢት፡-
ከትላንት በፊት ስለ ረሱላችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይ ሆኖ መነሳት የተነገረ ትንቢት በሚለው ስር፡ የመጀመሪያውን ነጥብ፡ ቀደምት ነቢያት ስለ እሳቸው መናገራቸውን ተመልክተናል፡፡ ዛሬም የጌታችን አላህ ፈቃድ ከሆነ ሁለተኛውን ክፍል፡ ማለትም ቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍት የተናገሩትን እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-
ለ. በመጽሀፍት በኩል፡-
ነቢዩ ሙሐመድ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይ ሆነው እንደሚነሱ ቀደምት ነቢያት ብቻ ሳይሆኑ ትንቢትን የተናገሩት፡ ከቅዱስ ቁርኣን በፊት የነበሩ ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት በተለይም ተውራትና ኢንጂል ስለ ነቢይነታቸው ተናግረዋል፡፡ በውስጣቸውም የሳቸውን ወደፊት ነቢይ ሆኖ መነሳት በመተንበይ ላመነ ሰው ብስራትን አቅፈዋል፡፡ እነሆ ማስረጃውም ይኸው፡-
"وَاكْتُبْ لَنَا فِي هَذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ إِنَّا هُدْنَا إِلَيْكَ قَالَ عَذَابِي أُصِيبُ بِهِ مَنْ أَشَاءُ وَرَحْمَتِي وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ فَسَأَكْتُبُهَا لِلَّذِينَ يَتَّقُونَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَالَّذِينَ هُمْ بِآيَاتِنَا يُؤْمِنُونَ " سورة الأعراف 156
"ለኛም በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም (መልካሟን) ጻፍልን፤ እኛ ወደ አንተ ተመለስን፤ (ሲል ሙሳ ጸለየ፤ አላህም) አለ፦ ቅጣቴ በርሱ የምሻውን ሰው እቀጣበታለሁ፤ ችሮታየም ነገሩን ሁሉ ሰፋች፤ ለነዚያም ለሚጠነቀቁ ዘካንም ለሚሰጡ ለነዚያም እነሱ በአንቀጾቻችን ለሚያምኑ በእርግጥ እጽፋታለሁ።" (ሱረቱል አዕራፍ 156)፡፡
በዚህ አንቀጽ ውስጥ የምናገኘው፡- ሙሳና ተከታዮቹ ወደ ጌታ አላህ ዱዓእ ማድረጋቸውን ነው፡፡ ዱዓውም፡- እኛ ወደ አንተ መንገድ ተመልሰናልና፡ በምድራዊ ህይወታችንና በመጨረሻው ዓለም መልካምን ነገር እንድትወስንልን ነው የሚል ነበር፡፡ ጌታችንም፡- የኔ ራሕመት (ጀነት) ሁሉን ነገር የሰፋች በመሆኗ፡ ለነዚያ የትም ስፍራ ሆነው እኔን ብቻ ለሚፈሩኝ፣ ግዴታ የሆነውን ምጽዋት የሚሰጡ፣ በአንቀጾቼም ለሚያምኑት እጽፋታለሁ አለ፡፡ ነገሩ በዚህ አልቆመም፡፡ አንቀጹም ይቀጥልና አሁንም ይህቺ ጀነት ለነማን እንደምትጻፍ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፡-
"الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِنْدَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنْجِيلِ يَأْمُرُهُمْ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنْكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ وَالْأَغْلَالَ الَّتِي كَانَتْ عَلَيْهِمْ فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنْزِلَ مَعَهُ أُولَئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ " سورة الأعراف 157
"ለነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነብይ የሆነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለሆኑት (በእርግጥ እጽፋታለሁ)፤ በበጎ ስራ ያዛቸዋል፤ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፤ መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፤ መጥፎ ነገሮችም በርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል። ከነርሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በነሱ ላይ የነበርሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) በርሱ ያመኑ ያከበሩትም የረዱትም ያንንም ከርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚድኑ ናቸው።" (ሱረቱል አዕራፍ 157)፡፡
በዚህኛው አንቀጽ ላይ ደግሞ፡- አሁንም ጀነቴን ለነዚያ ማንበብና መጻፍ የማይችል የሆነውን ነቢይ ለሚከተሉት እጽፋታለሁ እያለ ነው ጌታችን፡፡ ደግሞም ይህ ማንበብና መጻፍ የማይችል የሆነው ነቢይ በነሱም ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ስሙና ባሕሪው ተጽፎ የሚገኝ ነው እያለን ነው፡፡ ታዲያ ተውራትና ኢንጂል እየተናገሩ ያለው ስለ ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) አይደለምን? ይህ ማንበብና መጻፍ የማይችለው ነቢይ! የተባለው ማነው? ከተባለም፡ ያለ ምንም ማመንታት መልሱ፡- ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ናቸዋ! የሚል ይሆናል፡፡ ለዚህም ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"وَمَا كُنْتَ تَتْلُو مِنْ قَبْلِهِ مِنْ كِتَابٍ وَلَا تَخُطُّهُ بِيَمِينِكَ إِذًا لَارْتَابَ الْمُبْطِلُونَ " سورة العنكبوت 48
"ከርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፤ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራሩ ነበር።" (ሱረቱል ዐንከቡት 48)፡፡
…"فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ النَّبِيِّ الْأُمِّيِّ الَّذِي يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَكَلِمَاتِهِ وَاتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ " سورة الأعراف 158
"…በአላህና በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነብይ በሆነው መልክተኛው እመኑ፤ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት።" (ሱረቱል አዕራፍ 158)፡፡
ተውራትና ኢንጂል ስለ እሳቸው ትንቢት መናገራቸውን ለማረጋገጥ፡ ዛሬ በክርስቲያኖችና አይሁዶች እጅ የሚገኘውን መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተን፡ ከውስጡ ጥቅስ መፈለግ ግድ አይደለም፡፡ ጌታ አላህ በቅዱስ ቁርኣኑ ከነገረን በቂ ነው፡፡ እሱ እኮ ነው ተውራትንና ኢንጂልንም ያወረደው፡፡ ታዲያ ባለቤቱ የነገረንን ትተን ሰዎች በእጃቸው የበረዙትን መጽሀፍ ለማረጋገጫነት እንጠቀማለን እንዴ? ከነሱ መጽሐፍ መጥቀስ ያስፈለገው እኮ፡ ቢያንስ በቁርኣን ካላመኑ በያዙት መጽሀፍ እንኳ እውነቱን እንዲያዩ ለመርዳት እንጂ፡ ለምስክርነትማ ‹‹ወከፋ ቢላሂ ሸሂዳ›› (መስካሪነትማ በአላህ በቃ!) ፡፡ ተውራት ስለ እሳቸው ነቢይነት እንደሚናገር ሌላ ማጠናከሪያ ከሐዲሥ እንመልከት፡-

عنْ عَطَاءِ بْنِ يَسَارٍ قَالَ : لَقِيتُ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قُلْتُ : أَخْبِرْنِي عَنْ صِفَةِ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي التَّوْرَاةِ. قَالَ أَجَلْ وَاللَّهِ إِنَّهُ لَمَوْصُوفٌ فِي التَّوْرَاةِ بِبَعْضِ صِفَتِهِ فِي الْقُرْآنِ {يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا} وَحِرْزًا لِلْأُمِّيِّينَ أَنْتَ عَبْدِي وَرَسُولِي سَمَّيْتُكَ المتَوَكِّلَ لَيْسَ بِفَظٍّ وَلَا غَلِيظٍ وَلَا سَخَّابٍ فِي الْأَسْوَاقِ وَلَا يَدْفَعُ بِالسَّيِّئَةِ السَّيِّئَةَ وَلَكِنْ يَعْفُو وَيَغْفِرُ وَلَنْ يَقْبِضَهُ اللَّهُ حَتَّى يُقِيمَ بِهِ الْمِلَّةَ الْعَوْجَاءَ بِأَنْ يَقُولُوا لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَيَفْتَحُ بِهَا أَعْيُنًا عُمْيًا وَآذَانًا صُمًّا وَقُلُوبًا غُلْفًا. رواه البخاري 2018
ዐጣእ ኢብኑ የሳር (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላል፡- "ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምሩ ኢብኑል-ዓስን (ረዲየላሁ ዐንሁማ) አገኘሁትና፡- ስለ አላህ መልክተኛ ባሕሪ በተውራት ውስጥ ያለውን ንገረኝ አልኩት፡፡እሱም፡- እሺ! ወላሂ እሳቸው በተውራት ውስጥ ከፊል ባሕሪያቸው በቁርኣን ውስጥ፡- "አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን ላክንህ።" ተብሎ እንደተገለጸው ተጠቅሶአል፡፡ (የተውራቱ ቃል ይቀጥልና እንዲህ ይላል) መሀይማኖችን ጠባቂ አድርጌ ልኬሀለሁ፡፡ መጥፎን ቃል ተናጋሪ ወይም ልበ ደረቅ አይደለህም፡፡ በገበያ ማእከሎችም ድምጽህን ከፍ በማድረግ የምትጮህ አይደለህም፡፡ መጥፎ ቢሰራብህ በመጥፎ የምትክስ ሳትሆን፡ ነገር ግን ይቅር ባይ እና መሐሪ ነህ፡፡ አላህ ባንተ ሰበብ የጠመሙ ጎዳናዎችን ቀጥ እስኪያደርጋቸውና ሰዎች ላ ኢላሀ ኢልለሏህ እስኪሉ ድረስ በፍጹም አይገድልህም፡፡ ባንተው ሰበብ የታወሩ አይኖች ሐቅን ለመመልከት፣ የደነቆሩ ጆሮዎች ሐቅን ለመስማት፣ የተዘጉ ልቦች ሐቅን ለመቀበል ይከፈታሉ" (ቡኻሪይ 2018)፡፡
ይህ ከላይ የተጠቀሰው በተውራት የተቀመጠው የነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ባሕሪ ነው፡፡ ተውራትና ኢንጂል አይደለም ስለሳቸው ስለ ተከታዮቻቸው (ሶሐቦች) እንኳ ባሕሪቸው ምን አይነት እንደሆነ ሲገልጹ እንዲህ ይናገራሉ፡-
"مُحَمَّدٌ رَسُولُ اللَّهِ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ تَرَاهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا سِيمَاهُمْ فِي وُجُوهِهِمْ مِنْ أَثَرِ السُّجُودِ ذَلِكَ مَثَلُهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَمَثَلُهُمْ فِي الْإِنْجِيلِ كَزَرْعٍ أَخْرَجَ شَطْأَهُ فَآزَرَهُ فَاسْتَغْلَظَ فَاسْتَوَى عَلَى سُوقِهِ يُعْجِبُ الزُّرَّاعَ لِيَغِيظَ بِهِمُ الْكُفَّارَ وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ مِنْهُمْ مَغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا " سورة الفتح 29
"የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሐዲዎች ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፤ አጎንባሾች ሰጋጆች ሆነው ታያቸዋለህ፤ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፤ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትሆን በፊቶቻቸው ላይ ናት፤ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው፤ በኢንጅልም ውስጥ ምሳሌአቸው ቀንዘሉን እንደአወጣ አዝመራና (ቀንዘሉ) እንዳበረታው እንደወፈረምና ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ሆኖ በአገዳዎች ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ፣ (አዝመራ) ነው፤ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሐዲዎችን በነሱ ሊያስቆጭ ነው፤ አላህም እነዚያን ያመኑትና ከነሱ በጎዎችን የሰሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል።" (ሱረቱል ፈትሕ 29)፡፡
ተውራትና ኢንጂልም ስለ እሳቸው መናገራቸውን በተወሰነ መልኩ እንዲህ ካየን፡ በቀጣዩ ደግሞ ወደ ሶስተኛው ነጥብ በአላህ ፈቃድ እንሸጋገራለን ኢንሻአላህ፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder

"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" 3
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
1. ስለ ነቢይነታቸው የተነገረ ትንቢት፡-
ከትላንት በስቲያ ስለ ረሱላችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይ ሆኖ መነሳት የተነገረ ትንቢት በሚለው ስር፡ ሁለተኛውን ነጥብ፡ ቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍት ስለ እሳቸው ነቢይነት መናገራቸውን ተመልክተናል፡፡ ዛሬም የጌታችን አላህ ፈቃድ ከሆነ ሶሥተኛውን ክፍል፡ ማለትም የመጽሀፉ ባለቤቶች የሆኑት (የአይሁድና የክርስቲያን) ሊቃውንት የሳቸውን ነቢይነት በሚገባ ያውቁ እንደነበር እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-
ሐ. በመጽሀፍቱ ሊቃውንት ዘንድ፡-
የነቢዩ ሙሐመድ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይነት፡ በቀደምት ነቢያት አንደበትና በመለኮታዊ መጽሐፍት ውስጥ ብቻም የሰፈረ አይደለም፡፡ በተጨማሪም በሃይማኖቱ ሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ጉዳይ ነው እንጂ፡፡ የአይሁድና የክርስቲያን ሊቃውንቶች የሳቸውን ነቢይነት በሚገባ ያውቁ ነበር፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَعْرِفُونَهُ كَمَا يَعْرِفُونَ أَبْنَاءَهُمْ... " سورة البقرة 146
"እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል…" (ሱረቱል በቀራህ 146)፡፡
"الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَعْرِفُونَهُ كَمَا يَعْرِفُونَ أَبْنَاءَهُمْ... " سورة الأنعام 20
"እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል…" (ሱረቱል አንዓም 20)፡፡
በነዚህ ሁለት ቅዱስ ቁርኣናዊ አንቀጾች መሰረት የመጽሀፉ ሊቃውንቶች የነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይነት፡ የገዛ ልጃቸውን የሚያውቁትን ያህል፡ እሳቸውንም እንደሚያውቁ መረዳት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም በመጽሀፉ ውስጥ ስለ እሳቸው የተነገረውን ያውቃሉና፡፡
በነቢያችን(ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የነቢይነት ዘመን ኢስላምን ከተቀበሉት ስመ ጥር የአይሁድ ሊቃውንቶች አንዱ የነበረው፡ ዐብዱላህ ኢብኑ ሰላም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ይህን አንቀጽ በተመለከተ በዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ጥያቄ ቀርቦለት ተከታዩን ምላሽ መስጠቱን ኢብኑ ከሢር በተፍሲር ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይገልጹታል፡-
قال القرطبي: ويروى أن عمر قال لعبد الله بن سلام: أتعرف محمدًا صلى الله عليه وسلم كما تعرف ولدك ابنك، قال: نعم وأكثر، نزل الأمين من السماء على الأمين، في الأرض بنعته فعرفته، وإني لا أدري ما كان من أمره. تفسير ابن كثير. سورة البقرة 146
ኢማሙል ቁርጡቢይ (የተፍሲር ሊቅ ናቸው) ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- ዑመር ለዐብደላህ ኢብኑ ሰላም፡- ወንድ ልጅህን የምታውቀውን ያህል መሐመድን ታውቀው ነበርን? ዐብዱላህ ኢብኑ ሰላምም፡- አዎን! እንደውም የበለጠ እንጂ! የሰማዩ ታማኝ (መልአኩ ጅብሪል) በምድር ያለው ታማኝ (ነቢዩ ሙሐመድ ዘንድ) ወሕይን ይዞ ወረደ፡ እኔም በምልክቱ አወቅሁት፡፡ (የልጄ ጉዳይ ግን) ከእኔ ቤት ለቆ መውጣት በኋላ (ሌላ ወንድ ወደ ሚስቴ በመግባት) ሊሆን የሚችለውን ነገር አላውቅም ብሎ መለሰ፡፡ (ተፍሲር ኢብኑ ከሢር፡ ሱረቱል በቀራህ 146)፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ ሰላም (ረዲየላሁ ዐንሁ) እኔ በሌለሁበት ሌላ ወንድ ቤቴ ገብቶ ልጁ የተወለደው ከሌላ ቢሆንስ? እያለ ነው፡፡ ይህ ልጅ ያንተ ነው፣ ካንተው ነው የወለድኩት ያለችኝ ሚስቴ ነች፡፡ የሳቸው ነቢይነት ግን በመጽሀፋችን ውስጥ ምልክቱ ተነግሮ ስለነበር ሳልጠራጠር አውቃቸዋለሁ አለ፡፡
እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ እሱም፡- ታዲያ የሳቸው ነቢይነት ሊቃውንቶቹ ዘንድ ይህን ያህል ግልጽ ከነበረ፡ ለምን ሌሎቹስ አልሰለሙም? የሚል፡፡
ምላሹንም፡- እዛው አንቀጽ ላይ እናገኘዋለን፡፡ አንቀጹ ሙሉው ሲነበብ ሚስጥሩ ይገለጻል፡፡ እንዲህ ይላል ቅዱስ ቁርኣን፡-
"الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَعْرِفُونَهُ كَمَا يَعْرِفُونَ أَبْنَاءَهُمْ وَإِنَّ فَرِيقًا مِنْهُمْ لَيَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَهُمْ يَعْلَمُونَ " سورة البقرة 146
"እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል፡፡ ከነሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያወቁ ሲኾኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 146)፡፡
"الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَعْرِفُونَهُ كَمَا يَعْرِفُونَ أَبْنَاءَهُمْ الَّذِينَ خَسِرُوا أَنْفُسَهُمْ فَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ " سورة الأنعام 20
"እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል፡፡ እነዚያ ከእነርሱ ውስጥ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት እነርሱ አያምኑም፡፡ " (ሱረቱል አንዓም 20)፡፡
በመጀመሪያው አንቀጽ ላይ ያለው የሚገልጸው፡- እውነታውን እያወቁ ለማመን ያልፈለጉ ቡድኖች ይህን እውነት ሰው ሰምቶ እንዳይቀበል የመደበቅ ስራ እንደሚሰሩ ነው፡፡ መደበቅ ሲባል፡- አንድም በመጽሀፉ ላይ እጃቸውን በመክተት የተነገረውን ቃል በማጥፋትና በመሰረዝ በምትኩ ሌላ መጨመር፡ ወይንም ያንን እውነት ለሰዎች ይፋ ሳያደርጉ የተጣመመ ትርጉም መስጠት ነው፡፡ ሁለቱንም መንገዶች በመጽሐፉ ላይ ተጠቅመውበታል፡፡
ሁለተኛው አንቀጽ ደግሞ፡- በነበረባቸው የዐረብ ጥላቻና ምቀኝነት ሳቢያ፡ ነቢይ ከነሱ መነሳቱን በመጥላት ላለማመን ወስነው፡ እራሳቸውን ለክስረት የዳረጉ መሆናቸውን ነው፡፡ በጣም የሚገርመው ደግሞ፡- ነቢዩ ሙሐመድ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይ ሆነው ከመነሳታቸው በፊት፡ የሳቸው የነቢይነት ዘመን ቶሎ ተቃርቦ አላህም በነቢይነት እንዲልካቸው ይማጸኑ የነበሩት እነሱው አይሁዶች መሆናቸው ነው፡፡
ከዐረቦች ጋር በሚገጥሙት ጦርነት እንዲህ ይሏቸው ነበር፡- በመጽሐፋችን ላይ በመጨረሻው ዘመን ይመጣል የተባለ ነቢይ አለና፡ እሱ ሲመጣ ከሱ ጋር በመሆን እናንተን ከምድር ገጽ እናጠፋችኋለን! ‹‹አምላካችን አላህ ሆይ! መጨረሻው ዘመን በሚመጣው መልክተኛ ተማጽነንሀልና፡ እባክህ የዚህን መልክተኛ መምጣት አቃርብልንና ከሱ ኋላ በመሆን እነዚህን ዐረብ ሙሽሪኮችን እናጥፋቸው›› ይሉ ነበር፡፡ ጊዜው ደረሰና የአላህ መልክተኛም ነቢይ ሆነው ሲላኩ፡ አይሁዶቹ ከንግግራቸው 180 ዲግሪ ዞሩና፡- እኛ እኮ የምንፈልገው ከራሳችን ዘር ከአይሁድ የሆነ ነቢይ ነው እንጂ፡ ከጠላታችን ከዐረብ እንዴት ይነሳል! በማለት በማመን ፈንታ ካዱ አስተባበሉ፡፡

ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
"وَلَمَّا جَاءَهُمْ كِتَابٌ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ مُصَدِّقٌ لِمَا مَعَهُمْ وَكَانُوا مِنْ قَبْلُ يَسْتَفْتِحُونَ عَلَى الَّذِينَ كَفَرُوا فَلَمَّا جَاءَهُمْ مَا عَرَفُوا كَفَرُوا بِهِ فَلَعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الْكَافِرِينَ "سورة البقرة 89
"ከነሱም ጋር ያለውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ የኾነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ (ከመምጣቱ) በፊት በነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲኾኑ ያወቁት ነገር በመጣላቸው ጊዜ በርሱ ካዱ፡፡ የአላህም ርግማን በከሓዲዎች ላይ ይኹን፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 89)፡፡
"ይረዱበት የነበሩ ሲኾኑ " የሚለው ትርጉም የሚያመላክተው፡- አይሁዶቹ አላህን እንደሚማጸኑ፡ የመጨረሻውን መልክተኛ ቶሎ እንዲያመጣላቸው የሚጠይቁ እንደነበሩ ነው፡፡
"وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَسْتَ مُرْسَلًا قُلْ كَفَى بِاللَّهِ شَهِيدًا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ وَمَنْ عِنْدَهُ عِلْمُ الْكِتَابِ " سورة الرعد 43
"እነዚያም የካዱት ሰዎች፥ መልክተኛ አይደለህም ይላሉ፤ በኔና በናንተ መካከል መስካሪ በአላህና እርሱ ዘንድ የመጽሐፉ ዕውቀት ባለው ሰው በቃ፥ በላቸው።" (ሱረቱ-ረዕድ 43)፡፡
በዚህም አንቀጽ በግልጽ የምናየው፡- ምንም ሰዎች የሳቸውን ነቢይነት ቢክዱም፡ በከሀዲዎችና በሳቸው ነቢይ መሆን ጉዳይ ላይ የአላህ ምስክርነት ብቻውን በቂ ነው ብሎ መመስከሩንና፡ እንዲሁም የመጽሀፉ ዕውቀት ያለው ሰው የሚሰጠው ምስክርነት በቃ! ማለቱን ነው፡፡ የመጽሀፉ ሊቃውንቶች የሳቸውን ነቢይነት በሚገባ ያውቁ እንደነበር ይህም ሌላ ማስረጃ ነው፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ነቢይነታቸውን በተመለከተ የተነገረ ትንቢት፡ በሚለው ስር፡- ከነቢያት፣ ከመጽሐፍቱና ከሊቃውንቱ አንደበት የተመለከትናቸው መረጃዎቻችንን በዚሁ እናበቃና በቀጣዩ ደግሞ ሌላ ነጥብ ላይ እናተኩራለን ኢንሻአላህ፡፡

Forwarded from የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
1. መጽሀፍ ቅዱስ ከቁርዓን ስለሚቀድም የተሻለ ተዓማኒ ነውን?
2. እንዴት በነብያት ያልተነገረ ነገር ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተምራሉ?
3. የፈጣሪ ቃል እንዴት ይበረዛል?
____
@Yahya5

የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
በፈጣሪ_ማመን_ክፍል_3_By_Dai_Sadiq_Moha.m4a
77።_በፈጣሪ_ማመን_ክፍል_4_By_Dai_Sadiq_.m4a
2.8 MB
በፈጣሪ ማመን
"የፈጣሪ ፅንስ ሀሳብ በቁርአን እና በቀመደምት መፅሐፍት" ክፍል 4
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/T8NJLU
Join us➤ t.me/abuhyder
"የፈጣሪ ፅንስ ሀሳብ በቁርአን እና በቀመደምት መፅሐፍት" ክፍል 4
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/T8NJLU
Join us➤ t.me/abuhyder
"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" 4
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
2. ለነቢይነታቸው ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸው ማስረጃ
በቁጥር አንድ ትምሕርታችን ስለ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይነት በቀደምት ነቢያት፣ መለኮታዊ መጽሐፍትና በመጽሐፍቱ ሊቃውንት አንደበት የተነገረ ትንቢት በሚለው ስር ለሶስት ተከታታይ ክፍሎች መረጃዎቹን ስንማር ቆይተናል አልሐምዱ ሊላህ፡፡
አሁን ደግሞ ጌታ አላህ ፈቃዱ ከሆነ በሁለተኛው ነጥብ ስር፡ ነቢይነታቸውን የሚጠቁሙ ማስረጃዎች ምን ምን እንደሆኑ በመጠኑ እንቃኛለን ኢንሻአላህ፡፡ መልካም ንባብ፡-
" لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنْزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ…" سورة الحديد 25
"መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደነርሱ አወረድን…" (ሱረቱል ሐዲድ 25)፡፡
በዚህ የአላህ ቃል መሰረት፡ ጌታ አላህ ወደ ህዝቦቻቸው የሚላኩ መልክተኞች በጠቅላላ፡ የአላህ መልክተኛና ነቢይ መሆናቸውን ሊያሳይ የሚችል ማስረጃ እንደሚሰጣቸው መረዳት ይቻላል፡፡
ምክንያቱም፡- ነቢይም ሆነ ረሱል የሚመረጠው ከሰዎች ውስጥ በመሆኑ፡ አንድ ሰው ከሰዎች መካከል ተነስቶ፡- እኔ ከናንተ ውስጥ በአላህ ተመርጬ ወደናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ! ብሎ ቢናገር፡ ማንም በቀላሉ አይቀበለውም፡፡ ሰዎች እሱን የሚያውቁት ከዚህ በፊት እንደነሱ የሚበላና የሚጠጣ፡ የእለት ጉሮሮውን ለመዝጋት በስራ ላይ ደፋ ቀና የሚል፡ ትዳርን መስርቶ ልጆችን የወለደ መሆኑን ነው፡፡
አሁን ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው እሱ ነቢይ ነኝ ሊል የቻለው? ከማኃበረሰቡስ በተለየ መንገድ እሱን ከአላህ ጋር ሊያገናኘው የሚችል የነቢይነት ማዕረግ እንደተሰጠው በምን ማወቅ ይቻላል? ለዚህ ሁሉ ግልጽ ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡ ያለ ማስረጃ ከሆነማ፡ በአቋራጭ በህዝቦቻቸው ላይ ለመክበር ሲሉ ሀሰተኞችም ነቢይ ነን ማለታቸው አይቀርምና፡፡ ታዲያ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይነትን የሚጠቁሙ ማስረጃዎች ምን ነበሩ? በመጠኑ እንዳስሰው፡-

ሀ. የአላህ ምስክርነት፡-
ከመረጃዎች ሁሉ በላጩና ዋነኛው ማስረጃችን ነው፡፡ እራሱ ነቢይና መልክተኛ አድርጎ ከላካቸው አላህ የበለጠ ምስክርነት የትም የለም፡፡ ጌታ አላህ አንተ መልክተኛዬ ነህ በማለት መስክሯል፡፡ ይህ ምስክርነትም በቂ እንደሆነ ገልጾአል፡-
" وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَسْتَ مُرْسَلًا قُلْ كَفَى بِاللَّهِ شَهِيدًا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ وَمَنْ عِنْدَهُ عِلْمُ الْكِتَابِ " سورة الرعد 43
"እነዚያም የካዱት ሰዎች፥ መልክተኛ አይደለህም ይላሉ፤ በኔና በናንተ መካከል መስካሪ በአላህና እርሱ ዘንድ የመጽሐፉ ዕውቀት ባለው ሰው በቃ በላቸው።" (ሱረቱ-ረዕድ 43)፡፡
በዚህ ቅዱስ ቃል ውስጥ አላህ ለመልክተኛው ትእዛዝን ያስተላልፋል፡፡ ትእዛዙም፡- በእኔ እውነተኛነትና በናንተ ማስተባበል መሀል የአላህ ምስክርነት እንዲሁም የመጽሐፉ ዕውቀት የነበራቸው (ኢስላምን የተቀበሉ የአይሁድና የክርስቲያን ሊቃውንት) ምስክርነት በቂ ነው፡፡ የናንተ ማስተባበል እኔን ነቢይነቴን ወይም የአላህ መልክተኛ መሆኔን አይቀይረውም በላቸው የሚል ነው፡፡ መስካሪነትም በአላህ በቃ!!!!
" إِذَا جَاءَكَ الْمُنَافِقُونَ قَالُوا نَشْهَدُ إِنَّكَ لَرَسُولُ اللَّهِ وَاللَّهُ يَعْلَمُ إِنَّكَ لَرَسُولُهُ وَاللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَكَاذِبُونَ " سورة المنافقون 1
"መናፍቃን በመጡህ ጊዜ አንተ የአላህ መልክተኛው መሆንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን ይላሉ፤ አላህም አንተ በእርግጥ መልዕክተኛ መሆንህን ያውቃል፤ አላህም መናፍቃን (ከልብ እንመሰክራለን በማለታቸው) ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል።" (ሱረቱል ሙናፊቁን 1)፡፡
በዚህ አንቀጽ ውስጥም፡- ሙናፊቆች በልባቸው ያላመኑበትን በአንደበታቸው እሳቸው የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ሲመሰክሩ፡ ጌታ አላህ ደግሞ፡- ሙናፊቆች ምስክርነታቸው በልባቸው የሌለና ያላመኑበት ነገር በመሆኑ ውሸታም ናቸው፡፡ አንተ መልክተኛዬ እንደሆንክ እኔ አውቃለሁ በማለት ለሳቸው የመልክተኛነት ምስክርን ሰጠ፡፡ መስካሪነትም በአላህ በቃ!!!
" تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ وَإِنَّكَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ " سورة البقرة 252
"እነዚህ (አንቀጾች) በውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ አንቀጾች ናቸው፤ አንተም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 252)፡፡
በዚህ አንቀጽ መሰረትም፡- ጌታ አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሙሳ በኃላ ስላሉት ህዝቦች፡ በተለይ ስለ ነቢዩ ሳሙዔል (ዐለይሂ-ሰላም)፣ ንጉሱ ጣሉት (ሳኦል) (ዐለይሂ-ሰላም)፣ ነቢዩ ዳዉድ (ዐለይሂ-ሰላም)፣ እና የካፊሩ ጃሉትን (ጎልያድ) ታሪክ ከነገራቸውና ከዘረዘረ በኋላ፡- ይህ ሁሉ በአንተ ላይ የምናነበው ከሩቅ (ገይብ ከሆኑ) ዜናዎች ነው፡፡ አንተ በወቅቱ ባትኖርም እኔ እተርክልሀለሁ፡ ምክንያቱም አንተ ከመልክተኞቼ አንዱ ነህና! ማለቱን እናገኛለን፡፡ መስካሪነትም በአላህ በቃ!!!
ለ. ቅዱስ ቁርኣን፡-
ቅዱስ ቁርኣን ለነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ከተሰጣቸው ተአምራት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ አላህ ቁርኣንን በሳቸው ላይ ማውረዱ ብቻ ለነቢይነታቸው በቂ ማስረጃ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ቃሉም እንዲህ ይላል፡-
" أَوَلَمْ يَكْفِهِمْ أَنَّا أَنْزَلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ يُتْلَى عَلَيْهِمْ إِنَّ فِي ذَلِكَ لَرَحْمَةً وَذِكْرَى لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ " سورة العنكبوت 51
"እኛ መጽሐፉን በነሱ ላይ የሚነበብ ሆኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታና ግሣጼ አለበት።" (ሱረቱል ዐንከቡት 51)፡፡
የቅዱስ ቁርኣን ተአምራዊነት፡ ከቀደምት ነቢያት ተአምራት በሁለት መልኩ ይለያል፡-
- ‹‹መዕነዊይ›› መሆኑ፡- የቀደምት ነቢያት ተአምራት ‹‹ሒስሲይ›› ይባላል፡፡
‹‹ሒስሲይ›› ማለት፡- በአይን የሚታይ፣ በእጅ የሚዳሰስ ማለት ነው፡፡ በሙሳ በኩል፡- በትር ወደ እባብ ሲቀየር፣ ባህሩ ደርቆ መሻገሪያ መንገድ ሲሆን፣ እጅ መልኩ ተቀይሮ የሚያበራ ነጭ ሲሆን የሚታይና የሚዳሰስ ይባላል፡፡ በዒሳ በኩል፡- የሞቱት ሲነሱ፣ የዕውሮች አይን ሲበራ፣ ለምጽ የነበረባቸው ሲሽሩ የሚታይና የሚዳሰስ ተአምር ይባላል፡፡ ለነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይነት እንደ ማስረጃ የተሰጣቸው ቁርኣን ግን ‹‹መዕነዊይ›› ነው፡፡
‹‹መዕነዊይ›› ማለት፡- ህሊናን የሚያናግር፡ አእምሮን የሚቆጣጠርና ልብን የሚገዛ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ቀርኣን ሲቀራ በመስማት ብቻ የሰውን ልብ ይገዛል፡፡ በሚያስተላልፋቸው መልእክቱ፡ ሰዎችን ለለውጥ ይዳርጋል፡፡
- ‹‹አበዲይ›› መሆኑ፡- የቀደምት ነቢያት ተአምር ከነቢይነት ዘመናቸው ጋር ብቻ የተቆራኘ ነው፡፡ ከነሱ ሞት በኋላ ያበቃል፡፡ ሙሳ ከሞተ በኋላ በትር ወደ እባብ አይቀየርም፡ ባህር ደርቆ መንገድ አይሆንም፡፡ ዒሳ አላህ ወደ ራሱ ከወሰደው በኋላ፡ የሞተ አልተነሳም፡ የእውር አይን አልበራም፡፡ ቅዱስ ቁርኣን ግን ከነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ሞት በኋላ እንኳ ተአምራዊነቱ አላከተመም፡፡ እስከ ቂያማ ድረስ ድሮ በነበረው ተአምራዊነቱ ይቀጥላል፡፡ ስለዚህም ‹‹አበዲይ›› (ዘውታሪ) ይሰኛል፡፡ ከቅዱስ ቁርኣን ተአምራቶች መካከል የተወሰኑትን እንመልከት፡-
1. አምሳያው ፈጽሞ አለመገኘቱ፡- በቅዱስ ቁርኣን አምላካዊ ቃልነት ላይ ጥርጣሬ ያደረባቸው ሰዎች ካሉ፡ ጌታ አላህ አንድ ማጣሪያ ሰጣቸው፡፡ እሱም፡- ይህ ቁርኣን የሰው ድርሰት ነው፡ ብላችሁ ከተጠራጠራችሁ፡ እናንተም ሰው ናችሁና ያ ሰው የተጠቀመውን መንገድ በመጠቀም ቁርኣንን የሚመስል ነገር ጽፋችሁ አምጡ!! አላቸው፡፡ ቅዱስ ቁርኣን በአነጋገሩ ጠቅላላነት፡ በአረፍተ ነገሮቹ አሰካክ፡ ስድም ቅኔም ሳይሆን ለየአንቀጾቹ ዜማዊ ማሳረፊያዎች ያሉት፡ ትርጉሙን የተረዳውንም ሆነ ያልተረዳውን ሰው ቀልብ የሚገዛ በመሆኑ፡ እርሱን የሚመስል አነጋገርና አጻጻፍ ማን ማምጣት ይችላል? እያለ ነው፡፡ ቅዱስ ቁርኣን አምሳያዬን አምጡ ብሎ ሰዎችን በቀጣዮቹ መንገድ ተፎካክሯል፡-

1. ሙሉውን ቁርኣን ማምጣት፡-
"أَمْ يَقُولُونَ تَقَوَّلَهُ بَلْ لَا يُؤْمِنُونَ * فَلْيَأْتُوا بِحَدِيثٍ مِثْلِهِ إِنْ كَانُوا صَادِقِينَ " سورة الطور 34-33
“ወይም ቀጠፈው ይላሉን? አይደለም በውነቱ አያምኑም፡፡ እውነተኞችም ቢሆኑ መሰሉ የሆነን ንግግር ያምጡ” (ሱረቱ-ጡር 33-34)፡፡
2. ሙሉውን ካልቻሉ 10 ሱራ ብቻ
"أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ قُلْ فَأْتُوا بِعَشْرِ سُوَرٍ مِثْلِهِ مُفْتَرَيَاتٍ وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ " سورة هود 13
“ይልቁንም (ቁርአንን) ቀጣጠፈው ይላሉን?፡- እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን አስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን (ረዳት) ጥሩ በላቸው፡፡” (ሱረቱ ሁድ 13)፡፡
3. 10ሩን ካልቻሉ ደግሞ አንዲትን ሱራ ብቻ
"أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ قُلْ فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِثْلِهِ وَادْعُوا مَنِ اسْتَطَعْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ " سورة يونس 38
“በውነትም (ሙሐመድ) ቀጣጠፈው ይላሉን? ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ እውነተኞች እንደሆናችሁም (ተጋግዛችሁ አምጡ) በላቸው፡፡” (ሱረቱ ዩኑስ 38)፡፡
"وَإِنْ كُنْتُمْ فِي رَيْبٍ مِمَّا نَزَّلْنَا عَلَى عَبْدِنَا فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِنْ مِثْلِهِ وَادْعُوا شُهَدَاءَكُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ * فَإِنْ لَمْ تَفْعَلُوا وَلَنْ تَفْعَلُوا فَاتَّقُوا النَّارَ الَّتِي وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ أُعِدَّتْ لِلْكَافِرِينَ " سورة البقرة 24-23
“በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ ከቢጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ እውነተኞችም እንደሆናችሁም ከአላህ ሌላ መስካሪዎቻችሁን ጥሩ፡፡ (ይህንን) ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጊያዎች የሆነችውን እሳት ተጠበቁ ለከሓዲዎች ተደግሳለችና፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 23-24)፡፡
በመጨረሻም ሰዎችም ጋኔኖችም በጋራ ቢሰባሰቡ፡ ቁርኣንን የሚመስል ለማምጣት ቢጥሩ፡ ፈጽሞ እንደማይሳካላቸው በመግለጽ ቁርጡን ነገራቸው፡-
"قُلْ لَئِنِ اجْتَمَعَتِ الْإِنْسُ وَالْجِنُّ عَلَى أَنْ يَأْتُوا بِمِثْلِ هَذَا الْقُرْآنِ لَا يَأْتُونَ بِمِثْلِهِ وَلَوْ كَانَ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ ظَهِيرًا " سورة الإسراء 88
“ሰዎችም ጋኔኖችም የዚህን ቁርአን ቢጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆንም እንኳ ብጤውን አያመጡም በላቸው፡፡” (ሱረቱል ኢስራዕ 88)፡፡
2. እርስ በርሱ ባለመጋጨቱ፡- ሌላው ቅዱስ ቁርኣን ከአላህ ዘንድ የመጣ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተአምር መሆኑን የሚያመላክተው፡ በውስጡ የሰፈሩ ሀሳቦችና ቃላቶች ምንም አይነት መፋለስ፡ እርስ በርስ መጋጨት የማይታይባቸው መሆኑ ነው፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِنْدِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا " سورة النساء 82
“ቁርአንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡” (ሱረቱ-ኒሳእ 82)፡፡
"الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَنْزَلَ عَلَى عَبْدِهِ الْكِتَابَ وَلَمْ يَجْعَلْ لَهُ عِوَجًا " سزرة الكهف 1
“ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ መጣመምን ያላደረገበት ሲሆን በባሪያው ላይ ላወረደው ይገባው፡፡” (ሱረቱል ከህፍ1)፡፡
3. አምላካዊ ጥበቃው፡- ይህ ደግሞ ሌላው ማስረጃ ነው፡፡ ከወረደበት ማግስት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በመጀመሪያው ቅርጽና ይዘቱ ተጠብቆ የቆየ ብቸኛው መለኮታዊ መጽሐፍ ቅዱስ ቁርኣን ነው፡፡ አንድም ፊደል ሳይጨመርበትና ሳይቀነስበት ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ቅዱስ ቁርኣን በመጽሐፍ መልክ ብቻ ሳይሆን ተጠብቆ የቆየው፡ በአማኞች ልቦና ውስጥም በቃል የተያዘ ሆኖም ጭምር ነው፡፡
"إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ " سورة الحجر 9
“እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡” (ሱረቱል ሒጅር 9)፡፡
"إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِالذِّكْرِ لَمَّا جَاءَهُمْ وَإِنَّهُ لَكِتَابٌ عَزِيزٌ * لَا يَأْتِيهِ الْبَاطِلُ مِنْ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِ تَنْزِيلٌ مِنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍ " سورة فصلت 42-41
“እነዚያ በቁርአን፣ እርሱ አሸናፊ መጽሐፍ ሲሆን፣ በመጣላቸው ጊዜ የካዱት (ጠፊዎች ናቸው)። ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነውጌታ የተወረደ ነው።“ (ሱረቱ ፉሲለት 41-42)፡፡
4. በንባብም ሆነ በመስማት ብዛት የማይሰለች መሆኑ፡- እጅግም የሚደንቅ ተአምር ነው፡፡ እኛ በጣም የምንወዳቸው ዳዒዎችና ዐሊሞች በአንድ ርእሰ-ጉዳይ ዳዕዋ ሲሰጡ፡ ምናልባትም ያንን ዳዕዋ እስከ ሶስት አራት ጊዜ ደጋግመን ልንሰማው እንችል ይሆናል፡፡ ከዛ በኋላ ግን ይሰለቻል፡፡ ሌላ አዲስ የዳዕዋ ስራ እንፈልጋለን፡፡ የማንም ሰው ንግግር ሲደጋገም ይሰለቻልና፡፡ ሙስሊሞች ሱረቱል ፋቲሓን በቀን ስንቴ ነው ሚደጋግሙት? አጫጭር ሱራዎችን ስንቴ ነው የሚቀሩት? የቁርኣን ሒፍዝ ማእከሎች ተማሪዎችን በመቀበል፡ ተማሪዎች ቁርኣንን በቃል ለመሐፈዝ ብቻ በየቀኑ አንዱን ሱራ ስንቴ ነው የሚቀሩት? እንደዛም ሆኖ ግን የመዳከም እንጂ የመሰላቸት ስሜት አይታይባቸውም፡፡ ይህ ብቻ የአላህ ቃል ለመሆኑ በቂ አይሆንምን?

በፈጣሪ_ማመን_ክፍል_5_By_Dai_Sadiq_Moha.m4a
11 MB
በፈጣሪ ማመን
"የፈጣሪ ፅንስ ሀሳብ በቁርአን እና በቀመደምት መፅሐፍት" ክፍል 5
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/HPNpN1
Join us➤ t.me/abuhyder
"የፈጣሪ ፅንስ ሀሳብ በቁርአን እና በቀመደምት መፅሐፍት" ክፍል 5
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/HPNpN1
Join us➤ t.me/abuhyder
አዲስ_ሙሀደራ_የዒሳ_ማንነትና_ደረጃው_በደሴ_አረብገንዳ_መስጂድ.mp3
60.9 MB
"የዒሳ ዕ.ሰ ማንነትና ደረጃ በኢስላም" በአረብ ገንዳ መስጅድ የቀረበ አዲስ ሙሀደራ☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/KQcLYz
Join us➤ t.me/abuhyder
Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
➤ https://goo.gl/KQcLYz
Join us➤ t.me/abuhyder
"ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" 5
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
2. ለነቢይነታቸው ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸው ማስረጃ
በክፍል አራት ላይ የነቢዩ ሙሐመድን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ነቢይነት ሊያረጋግጡ ከሚችሉ ማስረጃዎች ሁለቱን ተመልክተን ነበር፡፡ እነሱም፡- የጌታ አላህ ምስክርነት እና የቁርኣን ተአምርነት ማለት ነው፡፡ ከዛ የቀጠለውን ማስረጃችንን ዛሬ እንመለከታለን ኢንሻአላህ፡-
ሐ. "ኢስራእ" እና "ሚዕራጅ"
አላህ መልክተኛውን ሙሐመድን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ወደ "ሲድረቱል ሙንተሀ" (የነገሮች ሁሉ ማብቂያ ወደሆነችው ቁርቁራይቱ ዛፍ) ከሰባት ሰማይ በላይ ወዳለችው ሊወስዳቸው ፈለገ፡፡ ነገር ግን ካሉበት መካ በቀጥታ ወደ ሰማያት እንዲያርጉ አልፈለገም፡፡ ከዛ ይልቅ ከነበሩባት መካ ወደ "በይቱል መቅዲስ" (ፈልስጢን) በሌሊት እንዲጓዙ አደረገ፡፡
በዚያም ነቢያትን ሁሉ ተገናኝነተው፡ ኢማም ሁነው ካሰገዱ በኋላ፡ ከበይቱል መቅዲስ ደግሞ ወደ ሰማያት በዛው ሌሊት ውስጥ እንዲያርጉ ተደረገ፡፡ ወደ ሰማያትም ካረጉ በኋላ ከጌታችን ጋር በቀጥታ ተነጋግረው (ያለ መልአክ ጣልቃ ገብነት) የአምስት ወቅት ሶላት ግዳጅነትን ይዘው መጥተዋል፡፡ በአንድ ሌሊት ከ መካ ወደ በይቱል መቅዲድ ያደረጉት ጉዞ "ኢስራእ" ይባላል፡፡
ወራት የሚያስኬደውን ርቀት በአንድ ለሊት መጓዝ መቻላቸው፡ ለነቢይነታቸው በቂ ማስረጃ ነው፡፡ በወቅቱ የነበሩ ከሀዲያኖች የሳቸውን ነቢይነት አልተቀበሉም ነበርና፡ ይህን ወሬ ሲሰሙ ወደ አቡበከር-ሲዲቅ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ዘንድ በመምጣት፡- ወዳጅህ በአንድ ሌሊት በይቱል መቅዲስ ሄድኩ ይላል! ሲሉት፡ አቡበክርም፡- እሱ ካለ እውነቱን ነው፡ አይዋሽም በማለት የእምነት ምስክርነት ቃሉን ሰጣቸው፡፡
አይሁዶችም ለምን ስለ በይቱል መቅዲስ አንዳንድ ነገር በመጠየቅ መሄድ አለመሄዳቸውን አናጣራም? በማለት፡ ወደሳቸው በመምጣት ስለ ሀገሩ ሁኔታ ጠየቋቸው፡፡ እሳቸውም የበይቱል መቅዲስን አቀማመጥ፡ የነጋዴዎቹን ሁኔታ፡ ከየትኛው ጎሳ እንደሆኑ ሁሉ በመጨመር ዘርዝረው አስረዷቸው፡፡ እሳቸው ከዚህ በፊት ወደዚያ ሀገር እንዳልሄዱ ሁሉም ያውቃል፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ መናገራቸው በአላህ ፈቃድ በአንድ ሌሊት መጓዛቸውን አመላካች ነው ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ቁርኣንም እንዲህ ይላል፡-
"سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَى بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ " سورة الإسراء 1
"ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፤ ከታምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፤ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው።" (ሱረቱል ኢስራእ 1)፡፡
ከበይቱል መቅዲስ ደግሞ ወደ ሰማያት ማረጋቸው "ሚዕራጅ" ይባላል፡፡ ይህን ጉዳይ ደግሞ ቁርኣን በሌላ ክፍል ላይ እንዲህ ይገልጸዋል፡-
"مَا كَذَبَ الْفُؤَادُ مَا رَأَى * أَفَتُمَارُونَهُ عَلَى مَا يَرَى * وَلَقَدْ رَآهُ نَزْلَةً أُخْرَى * عِنْدَ سِدْرَةِ الْمُنْتَهَى * عِنْدَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَى * إِذْ يَغْشَى السِّدْرَةَ مَا يَغْشَى * مَا زَاغَ الْبَصَرُ وَمَا طَغَى * لَقَدْ رَأَى مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَى " سورة النجم 18-11
"(ነቢዩ በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም። ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል። በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትሆን። ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)።ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፤ ወሰንም አላለፈም። ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ።" (ሱረቱ-ነጅም 11-18)፡፡
የአላህ መልክተኛም በዚህ የሰማይ እርገታቸው ላይ ጌታችንን ባይመለከቱትም፡ መለኮታዊ ቃሉን ግን ያለ መልአክ አማካኝነት ሰምተዋል፡፡ ጀነትና ጀሀነምንም ተመልክተዋል፡፡
መ. የጨረቃ ለሁለት መከፈል፡-
የተፈጥሮ ስርኣት ሁሌም የጸና፡ ቋሚና የማይቀያየር ህግ ነው፡፡ አላህ ሲፈልግና ሲፈቅድ ግን ሁሉም ለርሱ ታዛዥ ነው፡፡ ጨረቃ አንድ አካል ነው፡፡ ማንም ሰው ለሁለት ሊከፍለው አይችልም፡፡ ታዲያ የመካ ሙሽሪኮች ወደ ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) በመምጣት፡- እርሶ እውነተኛ ነቢይ ከሆኑ፡ ለማስረጃነት ጨረቃ ለሁለት ተከፍላ ማየት እንፈልጋለን! አሉ፡፡ አላህ ለሳቸው ማስረጃ ይሆን ዘንድ ጨረቃን ለሁለት ከፈለላቸው፡፡ እሳቸውም፡- በሉ እንግዲህ አሁን በአይናችሁ አይታችኋልና መስክሩ አሏቸው፡፡ እነሱም፡- ሙሐመድ አይናችን ላይ ደግሞብን ነው አሉ፡፡ ያዩትን ነገር ማስተባበል አልቻሉም፡፡ ላለማመን ግን አይናችን ላይ ተደገመብን! አሉ፡፡ ከመሐከላቸው አንዱም፡- እውነት ይህ ነገር ተደግሞብን ከሆነ፡ ድግምቱ ሌላ ቦታ አይሰራምና፡ ነጋዴዎች ወደዚህ ሀገር ሲገቡ በዚህ ቀን ምን ተከስቶ እንደነበር እንጠይቃቸው የሚል ሀሳብ አቀረበ፡፡ እነሱም በሀሳቡ ተስማሙ፡፡ በሌላ ቀን ነጋዴዎች ወደ ሀገሩ ሲገቡ፡- በዚህ ቀን በሀገራችሁ ምን ተከስቶ ነበር? ብለው ቢጠይቋቸው፡ የእነሱም ምላሽ፡- ጨረቃ ለሁለት ተከፍላ ተመልክተን ነበር አሉ፡፡ አሁንም ሰዎቹ በነጋዴዎቹ ምስክርነት ከማመን ይልቅ፡- ድግምቱ ቀጣይና ሁሉን ያካበበ ነው! ብለው እርፍ!!፡፡ ጌታ አላህም እንዲህ አለ፡-
"اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانْشَقَّ الْقَمَرُ * وَإِنْ يَرَوْا آيَةً يُعْرِضُوا وَيَقُولُوا سِحْرٌ مُسْتَمِرٌّ * وَكَذَّبُوا وَاتَّبَعُوا أَهْوَاءَهُمْ وَكُلُّ أَمْرٍ مُسْتَقِرٌّ " سورة القمر 3-1
"ስዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፤ ታምርንም ቢያዩ (ከአምነት) ይዞራሉ (ይህ) ዘውታሪ ደግመት ነውም ይላሉ፡፡ አስተባበሉም፤ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፤ ነገርም ሁሉ ( ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው::" (ሱረቱል ቀመር 1-3)፡፡