ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ኢየሱስ ሰው ነውና መፀዳጃ ቤት ተቀምጦ ሲያንኳኩበት ምን ይላል?

ሀ. ሰው አለ!
ለ. አምላክ አለ!
ሐ. ዝም!

መልስ ከእናንተ!

የሰው ልጅ የሆነው ኢየሱስ እየበላና እየጠጣ መጥቷል፤ ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ በሌላ መልኩ ከሰውነት ይወገዳል፦
15:17 “ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን”?

ታዲያ በልቶና ጠጥቶ ወደ እዳሪ የሚጥለውና የሚበሰብሰው ሰው፣ የሚተላው ሰው እንዴት ተመልሶ ሙሉ አምላክ ነው እንላለን? እግዚአብሔር አምላክ እኔ ሰው አይደለሁም እያለ?
ኢዮብ 25:6 ይልቁንስ “ብስብስ የሆነ ሰው”፥ “ትልም የሆነ የሰው ልጅ” ምንኛ ያንስ!
ሆሴ.11:9፤ እኔ “አምላክ” ነኝ እንጂ “ሰው” አይደለሁምና፥

ኢየሱስ ሙሉ አምላክ ከሆነው ከእግዚአብሔር ሰምቶ የሚያስተላልፍ ሙሉ ሰው ነው፦
ዮሐ.8:40 ነገር ግን አሁን “ከእግዚእብሔር የሰማሁትን” እውነት “የነገርኋችሁን ሰው” ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።
ሐዋ 2:22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም “ከእግዚአብሔር” ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ “ሰው ነበረ”፤

ኢየሱስ
1. ይራብና ይጠማ ነበር፦
ማቴዎስ 21፥18 በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ #ተራበ
ዮሐንስ 19፥28 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፡— #ተጠማሁ፡ አለ።

2. ይበላና ይጠጣ ነበር፦
ማቴዎስ 11፥19፤ የሰው ልጅ #እየበላና #እየጠጣ መጣ፥

3. ያ ወደ አፍ ያስገባውን በሌላ መልኩ ከሰውነቱ ያስወጣ ነበር፦
ማቴዎስ 15፥17 ወደ አፍ #የሚገባ #ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?

"ወደ አፍ የሚገባ #ሁሉ ወደ እዳሪ ከተጣለ ኢየሱስ የሚበላውና የሚጠጣው ይወገድ ነው።

እነዚህ ሥድስት ሕጎች ማለትም መራብ፣ መጠማት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መሽናት እና መጸዳዳት ናቸው። እነዚህ የተፈጥሮ ሕጎች የሚገዙት አካል ማምለክ ሺርክ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom