ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዶክተር ዋልተር ማርቲን ዘካሪያስ 12፥10 ላይ "እኔ" የሚለው አብን "እርሱ" የተባለው ወልድ እንደሆነ በመግለጽ ስለ ሁለት ማንነት ተናግረዋል።
አሏህን መርዳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

47፥7 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ብትረዱ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن تَنصُرُوا اللَّهَ يَنصُرْكُمْ وَيُثَبِّتْ أَقْدَامَكُمْ

በቁርኣን ከተገለጹ የአሏህ ስሞች አንዱ "አል-ገኒይ" الْغَنِيّ ሲሆን "ተብቃቂው" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ከፍጥረቱ ምንም የማይከጅል የተብቃቃ በተቃራኒው ፍጥረቱ ግን ከእርሱ ከጃዮች ናቸው፦
22፥64 በሰማያት ውስጥ ያለው እና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَإِنَّ اللَّهَ لَهُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ
35፥15 እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፥ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንዳ አሏህ ከፍጥረቱ እርዳታ ይፈልጋልን? እረ በፍጹም ምንም አይፈልግም። የማይፈልግ ከሆነ "አሏህ መርዳት" ምን ማለት ነው? "አሏህ መርዳት" ማለት በጥቅሉ የአሏህን ዲን መርዳት ማለት ነው፦
47፥7 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ብትረዱ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن تَنصُرُوا اللَّهَ يَنصُرْكُمْ وَيُثَبِّتْ أَقْدَامَكُمْ

ቢመዕና "አሏህን መርዳት"ማለት "የአሏህ ሃይማኖት መርዳት" ማለት ስለሆነ የዐማርኛ የቁርኣን ትርጉም ላይ በቅንፍ "ሃይማኖቱን ብትረዱ" ተብሎ ተቀምጧል። አሏህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፦
22፥40 አሏህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አሏህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

"አሏህን ብትረዱ ይረዳችኋል" ማለት የመስጠት እና የመቀበል አዙሪት ነው" ላላችሁት ያህዌህ፦ ያከበሩኝን አከብራለሁ" ማለቱ የመስጠት እና የመቀበል አዙሪት ነውን፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥30 ያከበሩኝን አከብራለሁና። מְכַבְּדַ֥י אֲכַבֵּ֖ד

"ያህዌህን ማክበር አምልኮ ከሆነ ያህዌህ የሚያከብሩት ማክበሩ አምልኮ ነው" ብሎ መፈሠር ይቻላልን? "ፈጣሪን ማክበር ፈጣሪ ተዋርዶ ወይም ጎድሎት ነው" እንደማትሉ ሁሉ "አሏህን መርዳት ማለት አቅም አንሶት ወይም ጎሎት ነው" ብላችሁ መረዳት የለባችሁም። በተጨማሪ የያህዌህ መልአክ፦ "ያህዌህን ለመርዳት አልመጡምና። የተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ" ማለቱ በራሱ ያህዌህ የሚረዳ መሆኑን ያሳያል፦
መሣፍንት 5፥23 የያህዌ መልአክ፦ ሜሮዝን እርገሙ! ያህዌህን በኃያላን መካከል "ለመርዳት"፥ ያህዌህን "ለመርዳት" አልመጡምና። የተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ" አለ። אֹ֣ורוּ מֵרֹ֗וז אָמַר֙ מַלְאַ֣ךְ יְהוָ֔ה אֹ֥רוּ אָרֹ֖ור יֹשְׁבֶ֑יהָ כִּ֤י לֹֽא־בָ֙אוּ֙ לְעֶזְרַ֣ת יְהוָ֔ה לְעֶזְרַ֥ת יְהוָ֖ה בַּגִּבֹּורִֽים׃

ቁርኣኑ ላይ "አሏህ ብትረዱ" ለሚለው የገባው ቃል "ተንሱሩ አሏህ" تَنصُرُوا اللَّهَ ሲሆን የዐረቢኛ ባይብሉ ላይ ደግሞ "ያህዌህን ለመርዳት" ለሚለው የገባው ቃል "ሊኑስረቲ አሏህ" لِنُصْرَةِ اللهِ ነው፥ የሁለቱም የግሥ መደቦች ሥርወ ቃሉ "ነሶረ" نَصَرَ መሆኑ በራሱ መፈናፈኛ የሚያሳጣ ጥቅስ ነው። ያህዌህ እንደሚረዳ ስትሰሙ ምን ይውጣችሁ ይሆን? "ያህዌህ መርዳት" ማለትስ ምን ማለት ነው? ፈሥሩልን! በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው። ቁምነገሩ ጭጎት"shelf" ላይ መጽሐፍ ደርድሮ ማሳየት ሳይሆን ተፍ ተፍ እና ጉድ ጉድ ብሎ ማንበብ ይጠይቃል። ለነገሩ እናንተ መንደር ልቅነት እና ሊቅነት ምን እንደሆነ በቅጡ ስላልተረዳችሁ አንፈርድባችሁም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አማኑኤል ማን ነው? በሚል ትምህርት ተለቋል። ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች "አምላክ ተወለደ" ለሚል ትምህርታቸው እንደ መመከቻ የሚጠቅሱአቸው ኢሳይያስ 7፥14 እና ኢሳይያስ 9፥6 ናቸው። እኛ ደግሞ "እነዚህ ጥቅሳት ለዚያ ትምህርት ድምዳሜ አያደርሱም" ብለን ሞግተናል። ነገረ ክርስቶስን"Christology" ያማከለ ሙግት ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/q6SrruB5yIA?si=l7tizTAqPRmuijzd

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
የኢየሱስ ጌታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ

"አዶን" אָדוֹן ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን "አዶኒም" אֲדֹנִ֣ים ማለት "ጌቶች" ማለት ነው፥ "አዶኒ" אדֹנִ֗י ማለት "ጌታዬ" ማለት ሲሆን "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ደግሞ በግነት ወይም በብዜት "ጌታዬ" ማለት ነው። ነቢያት አንዱን አምላክ "ጌታዬ" ለማለት ሲፈልጉ "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י በማለት ይጠቀማሉ፦
መዝሙር 16፥2 ያህዌህን አንተ "ጌታዬ" ነህ አልሁ። אָמַ֣רְתְּ לַֽ֭יהוָה אֲדֹנָ֣י אָ֑תָּה
መዝሙር 110፥5 "ጌታዬ" በቀኝህ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል። אֲדֹנָ֥י עַל־יְמִֽינְךָ֑ מָחַ֖ץ בְּיֹום־אַפֹּ֣ו מְלָכִֽים׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጌታዬ" ለሚለው የገባው ቃል "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ሲሆን ለአንድ ነጠላ ማንነት በግነት እንደገባ አስተውል! ዳዊት "በቀኝህ" እያለ በሁለተኛ መደብ የሚናገረው ስለ መሢሑ(ወልድ) ሲሆን "ጌታዬ" የሚለው ደግሞ አብን(ያህዌህን) ነው። በተመሳሳይ መሢሑ በትንቢት መነጽር ያህዌህን "ጌታዬ" ብሎታል፦
ኢሳይያስ 61፥1 "የ-"ጌታዬ" የያህዌህ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ያህዌህ ቀብቶኛልና። ר֛וּחַ אֲדֹנָ֥י יְהוִ֖ה עָלָ֑י יַ֡עַן מָשַׁח֩ יְהוָ֨ה אֹתִ֜י לְבַשֵּׂ֣ר עֲנָוִ֗ים

እዚህ አንቀጽ ላይ "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ማለት "ጌታዬ" ማለት ከሆነ ኢየሱስ ያህዌህን "ጌታዬ" ማለቱ በራሱ የሚገዛለት ጌታ እንዳለው አመላካች ነው። ያህዌህ መሢሑን "ባሪያዬ" ይለዋል፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል። הֵ֤ן עַבְדִּי֙ אֶתְמָךְ־בֹּ֔ו בְּחִירִ֖י רָצְתָ֣ה נַפְשִׁ֑י נָתַ֤תִּי רוּחִי֙ עָלָ֔יו מִשְׁפָּ֖ט לַגֹּויִ֥ם יֹוצִֽיא׃

ኢየሱስ ጌታውን "ጌታዬ" ካለው እንዲሁ ጌታው ኢየሱስን "ባሪያዬ" ካለው እንግዲያውስ የኢየሱስ ጌትነት በመደረግ ላይ የተመሠረተ መነሾ እና ጅማሮ ያለው ስለሆነ የባሕርይ ጌትነት በፍጹም አይደለም፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 ኢየሱስን አምላክ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። ἀσφαλῶς οὖν γινωσκέτω πᾶς οἶκος Ἰσραὴλ ὅτι καὶ Κύριον αὐτὸν καὶ Χριστὸν ἐποίησεν ὁ Θεός, τοῦτον τὸν Ἰησοῦν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ባለቤት ሲሆን "ኢየሱስ" ተሳቢ ነው፥ በባለቤት እና በተሳቢ መካከል "እንዳደረገው" የሚል ተሻጋሪ ግሥ አለ። ጌታ አድራጊው አንዱ አምላክ ሲሆን ጌታ ተደራጊው ኢየሱስ ነው፥ አምላክ ኢየሱስን ጌታ ካረደገው የኢየሱስ ጌትነት መነሾ እና ጅማሮ ያለው ስለሆነ እና ጌታ ከመደረጉ በፊት በባዶነት ስለሚቀደም ጌትነቱ ሥልጣን እና ሹመት ወይም እልቅና እና ማዕረግን ያሳያል። ምክንያቱም "እንዳደረገው" ለሚለው የገባው ቃል "ኤፓዬሴን" ἐποίησεν ሲሆን ከዚህ በፊት ያልሆነ ወደ መሆን በመደረግ ለመጣ ነገር በግሪክ ኮይኔ ይጠቀምበታል፦
ዘፍጥረት 45፥9 "አምላክ" በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ "ጌታ" አደረገኝ። ἐποίησέ με ὁ Θεὸς κύριον πάσης γῆς Αἰγύπτου·

የግሪክ ሰፕቱአጀንት ዮሴፍ "አደረገኝ" ላለበት የተጠቀመበት ቃል "ኤፓዬሴ" ἐποίησέ እንደሆነ ልብ አድርግ! አምላክ ዮሴፍን ጌታ ማድረጉ ሥልጣን እና ሹመት ወይም እልቅና እና ማዕረግን ያሳያል ከተባለ እንግዲያውስ አምላክ ኢየሱስን ጌታ ማድረጉ ሥልጣን እና ሹመት ወይም እልቅና እና ማዕረግን ያሳያል። ኢየሱስ ጌታ ካለው፣ ለጌታው ባሪያ ከሆነ፣ ጌትነቱ በመደረግ ላይ የተመሠረተ መነሻ እና ጅማሮ ካለው እንግዲያውስ በጌትነቱ ባርነት የሌለበትን የባሕርይ ጌታ አሏህን በብቸኝነት አምልኩ! "የባሕርይ ጌታ" ማለት ጌትነቱ በራሱ የተብቃቃ እና ጌትነቱ የራሱ ገንዘቡ የሆነ ማለት ነው። ኢየሱስ ከአሏህ የተሰጠው ተልእኮ "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" የሚል ነበር፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል "ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ" ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ

እንደ ኢየሱስ ለጌታችን ባሪያ መሆን ምንኛ መታደል ነው? ስለዚህ የኢየሱስን ጌታ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ጌታችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነቢዩ ኢብራሂም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

21፥69 «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡ قُلْنَا يَا نَارُ كُونِي بَرْدًا وَسَلَامًا عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ

ኩሽ የኖሕ ልጅ ሲሆን ናምሩድን ወለደ፥ ናምሩድ በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ። እንስሳት የሚያድን አዳኝ"hunter" ነበረ፦
ዘፍጥረት 10፥8 ኩሽም ናምሩድን ወለደ፥ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ። וְכ֖וּשׁ יָלַ֣ד אֶת־נִמְרֹ֑ד ה֣וּא הֵחֵ֔ל לִֽהְיֹ֥ות גִּבֹּ֖ר בָּאָֽרֶץ׃
ዘፍጥረት 10፥9 እርሱም በያህዌህ ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፥ ስለዚህም፦ “በአምላክ ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ" ተባለ። הֽוּא־הָיָ֥ה גִבֹּֽר־צַ֖יִד לִפְנֵ֣י יְהוָ֑ה עַל־כֵּן֙ יֵֽאָמַ֔ר כְּנִמְרֹ֛ד גִּבֹּ֥ור צַ֖יִד לִפְנֵ֥י יְהוָֽה׃

"ኒምሩድ" נִמְרוֹד ማለት "አመጸኛ" ማለት ሲሆን "ኒምሩድ" የሚለው ስም በኃላ ላይ ልክ እንደ አጼ፣ ሄሮድስ፣ ፈርዖን፣ ቄሳር የባቢሎን ነገሥታት ስም ሆነ፥ ይህ ስም በዋነኝነት የባቢሎን የመጀመሪያው ንጉሥ ስም ነበረ፦
ዘፍጥረት 10፥10 የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር "ባብኤል፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው። וַתְּהִ֨י רֵאשִׁ֤ית מַמְלַכְתֹּו֙ בָּבֶ֔ל וְאֶ֖רֶךְ וְאַכַּ֣ד וְכַלְנֵ֑ה בְּאֶ֖רֶץ שִׁנְעָֽר׃

"ባብ-ኤል" בָּבֶ֔ל ማለት "የአምላክ በር" ማለት ነው፥ ቦታውን ወደ አምላክ የሚያስገባ በር እንደሆነ አስበው ወደ ሰማይ ወደ አምላክ የሚደርስ ግንብ ለመሥራት ሲያስቡ ያኔ በቋንቋ ተበታተኑ። ሙሐመድ ኢብኑ ጀሪር አጥ ጦበሪይ "ታሪኹ አር ረሡል ወል ሙልክ" تاريخ الرسل والملوك በተባለ መጽሐፋቸው ላይ "ኑምሩድ" نُمْرُود የተባለው የመጀመሪያ የባቢል ንጉሥ ግንብ እንደገነባ እና አሏህ ያንን እንዳፈረሰ እንዲሁ ቀደም ሲል የሰዎች ቋንቋ ሲሪያኪኛ(ዐረማይስጥ) እንደነበር እና በኃላ በመዘበራረቅ ሰባ ሁለት ቋንቋዎች እንደሆኑ ዘግቧል።
ይህ ባብኤል የተባለው አገር የናምሩድ አገር ይባላል፦
ሚክያስ 6፥6 የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ "የናምሩድንም አገር" በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ። וְרָע֞וּ אֶת־אֶ֤רֶץ אַשּׁוּר֙ בַּחֶ֔רֶב וְאֶת־אֶ֥רֶץ נִמְרֹ֖ד בִּפְתָחֶ֑יהָ

ነቢዩ ኢብራሂም በተነሳበት ዘመን ደግሞ ሌላ የባቤል ንጉሥ የነበረው አሏህ ንግሥናን የሰጠው ሲሆን ኢብራሂም ለእርሱ፦ "ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግ እና የሚያሞት ነው" ሲል ንጉሡም "እኔ ሕያው አደርጋለሁ አሞታለሁም" አለው፦
2፥258 ወደዚያ አሏህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን? ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግ እና የሚያሞት ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ አሞታለሁም» አለ፡፡ أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ

ማሞት እና ሕያው ማድረግ ጋይብ ነውና በሚታይ ነገር ኢብራሂም፦ "አሏህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት" አለው፡፡ ያም የካደው ንጉሥ መልስ አጣ፦
2፥258 ኢብራሂም፡- «አሏህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው፡፡ ያም የካደው ሰው መልስ አጣ፥ አሏህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

ለእነዚህን ጣዖታውያን ኢብራሂም "ታዲያ ለእናንተ ምንም የማይጠቅማችሁን እና የማይጎዳችሁን ነገር ከአሏህ ሌላ ታመልካላችሁን? ሲላቸው እነርሱም ደግሞ ኢብራሂምን "አቃጥሉት" በማለት በእሳት ላይ ጣሉት፥ አሏህም፦ "እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አለ፦
21፥69 «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡ قُلْنَا يَا نَارُ كُونِي بَرْدًا وَسَلَامًا عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ
ሚሽነሪዎች፦"አብርሃም በእሳት እንደተጣለ ባይብል ላይ የለም፥ ስለዚህ ቁርኣኑ ከየት አመጣው" ብለው ይተቻሉ።
፨ሲጀመር አንድ ታሪክ ባይብል ላይ አልተዘገበም ማለት ታሪኩ ነባራዊ ሳይሆን ምናባዊ ነው አያሰኝም።
፨ሲቀጥል አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነው፥ ቁርኣን ላይ ታሪኩን የተረከልን እራሱ የዓለማቱ ጌታ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል።
፨ሢሰልስ በታልሙድ ውስጥ ኢብራሂም ጣዖት አላመልክም በማለቱ እሳት ውስጥ እንደተጣለ ይናገራል፦
ታልሙድ ፐሳቺም 118 A ቁጥር 20
ክፉው ናምሩድ አባታችን አብርሃምን ወደ እሳት እቶን ውስጥ በጣለ ጊዜ ገብርኤል በቅዱሱ እና በተባረከው ፊት እንዲህ አለ፡- የዓለማት ጌታ ሆይ! እኔ ወርጄ እቶን አቀዘቅዛለው፥ በዚህም ጻድቁን አብርሃምን ከእሳት እቶን አድናለሁ"። בְּשָׁעָה שֶׁהִפִּיל נִמְרוֹד הָרָשָׁע אֶת אַבְרָהָם אָבִינוּ לְתוֹךְ כִּבְשַׁן הָאֵשׁ אָמַר גַּבְרִיאֵל לִפְנֵי הַקָּדוֹשׁ בָּרוּךְ הוּא: רִבּוֹנוֹ שֶׁל עוֹלָם, אֵרֵד וַאֲצַנֵּן וְאַצִּיל אֶת הַצַּדִּיק מִכִּבְשַׁן הָאֵשׁ.

ይህንን ስታነቡ ምን ይውጣችሁ ይሆን? ወይስ እንደተለመደው "ተኮርጆ ነው" የሚል ዲስኩራችሁ ትደሰኩሩ ይሆን?
፨ሲያረብብ በዕብራይስጥ "ዑር" אוּר ማለት "የእሳት እቶን" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ "እሳት" እና "እቶን" ለሚል ቃል "ዑር" אוּר በሚል ይመጣል፦
ኢሳይያስ 31፥9 አምባው ከፍርሃት የተነሣ ያልፋል መሳፍንቱም ከዓላማው የተነሣ ይደነግጣሉ፥ ይላል እሳቱ በጽዮን እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነ ያህዌህ። וְסַלְעֹו֙ מִמָּגֹ֣ור יַֽעֲבֹ֔ור וְחַתּ֥וּ מִנֵּ֖ס שָׂרָ֑יו נְאֻם־יְהוָ֗ה אֲשֶׁר־א֥וּר לֹו֙ בְּצִיֹּ֔ון וְתַנּ֥וּר לֹ֖ו בִּירוּשָׁלִָֽם׃ ס

እዚህ አንቀጽ ላይ "እሳት" እና "እቶን" ለሚል የገባው ቃል "ዑር" אוּר እንደሆነ አስተውል! እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንዳ ፈጣሪ አብርሃምን ያወጣው ከከለዳውያን የእሳት እቶን ነው፦
ዘፍጥረት 15፥7 "ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን "ዑር" ያወጣሁህ ያህዌህ እኔ ነኝ" አለው። וַיֹּ֖אמֶר אֵלָ֑יו אֲנִ֣י יְהוָ֗ה אֲשֶׁ֤ר הֹוצֵאתִ֙יךָ֙ מֵא֣וּר כַּשְׂדִּ֔ים לָ֧תֶת לְךָ֛ אֶת־הָאָ֥רֶץ הַזֹּ֖את לְרִשְׁתָּֽהּ׃

"ዑር" אוּר ማለት "የእሳት እቶን" "የእሳት ነበልባል" ማለት ነው፥ "ዑር" אוּר በሚል ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው ቃል "ሜ" מֵ ደግሞ "ከ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው። ስለዚህ ኢብራሂም በእሳት ውስጥ ተጥሎ አሏህ ከእሳት እንዳዳነው መናገሩ በመለኮታዊ ቅሪት ውስጥ እንዲህ ይገኛል፥ በማታውቁት ነገር መዘላበድ እንዲህ ዋጋ ያስከፍላችኃል። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እውን ኢየሱስ የባሕርይ ጌታ ነውን? በሚል ትምህርት ተለቋል። ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች "ኢየሱስ ጌታ ነው" ብለው ሊሰብኩ ይሞክራሉ፥ በእርግጥ ኢየሱስ የባሕርይ ጌታ ሳይሆን የማዕረግ ጌታ ነው። ያ ምን ማለት ነው? ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/WJxh4gMa3BU?si=uM19JJaUzGYTSzsG

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፓስተር ፍሬው ቤዛ ይበል የሚያስብል ትልቅ ለውጥ ነው። አንድ አምላክ የኢየሱስ አምላክ መሆኑን፣ ኢየሱስ ሰው እንጂ የአምላክ እና የሰው ውሕደት አለመሆኑን፣ ሥላሴ ባይብላዊ አለመሆኑን፣ "አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው" የሚል ባይብል ላይ አለመኖሩን መገንዘብህ እና ኢየሱስ ጌታ ሲባል ማዕረግን እንጂ ባሕርይን እንደማያመለክትን መረዳትህ ድንቅ ጥናትህን ያሳያል። አሏህ ሂዳያህ እንዲሰጥህ ምኞቴ እና ዱዓዬ ነው።
የኢየሱስ አምላክ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥172 አል-መሢሕ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ

በዕብራይስጥ "ባሳር" בָּשָׂר ማለት እና በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ሳርኮስ" σαρκὸς ማለት "ሥጋ" ማለት ሲሆን በጥቅሉ እና በጅምላ "ሰው" ማለት ነው፦
ኢዮኤል 2፥28 ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፥ መንፈሴን በሥጋ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ። אֶשְׁפֹּ֤וךְ אֶת־רוּחִי֙ עַל־כָּל־בָּשָׂ֔ר
መዝሙር 65፥2 ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል። שֹׁמֵ֥עַ תְּפִלָּ֑ה עָ֝דֶ֗יךָ כָּל־בָּשָׂ֥ר יָבֹֽאוּ׃

መቼም እነዚህ አናቅጽ ላይ "ሥጋ" ሲል የቁርበቱ እና የቆዳው ክፍል ብቻ ሳይሆን "ሰው" ማለት እንደሆነ በቀላሉ እንረዳለን። ይህን ከተረዳን ዘንዳ "እኔ" የሚለው አንዱ አምላክ የሰው ሁሉ አምላክ ነው፦
ኤርምያስ 32፥27 እነሆ እኔ የሥጋ ሁሉ አምላክ ያህዌህ ነኝ። הִנֵּה֙ אֲנִ֣י יְהוָ֔ה אֱלֹהֵ֖י כָּל־בָּשָׂ֑ר

ይህ የባሕርይ አምላክ ከሰው በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ አምልኮን የሚቀበል ስለሆነ የሥጋ ሁሉ አምላክ ነው፥ ኢየሱስ ሰው ነውና አንዱን አምላክ በትንቢት መነጽር "አምላኬ" በማለት ያመልከዋል፦
መዝሙር 40፥7 በዚያን ጊዜ አልሁ፦ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፤ "አምላኬ" ሆይ! ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው"። אָ֣ז אָ֭מַרְתִּי הִנֵּה־בָ֑אתִי בִּמְגִלַּת־סֵ֝֗פֶר כָּת֥וּב עָלָֽי׃ לַֽעֲשֹֽׂות־רְצֹונְךָ֣ אֱלֹהַ֣י חָפָ֑צְתִּי וְ֝תֹ֥ורָתְךָ֗ בְּתֹ֣וךְ מֵעָֽי׃
ዕብራውያን 10፥7 በዚያን ጊዜ፦ ‘እነሆ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ "አምላኬ" ሆይ! ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ" አልሁ፥ ይላል"። τότε εἶπον Ἰδοὺ ἥκω, ἐν κεφαλίδι βιβλίου γέγραπται περὶ ἐμοῦ, τοῦ ποιῆσαι ὁ Θεός, τὸ θέλημά σου.

"አምላክ" በሚለው መድረሻ ቃል ላይ "ክ" የነበረውን ሳድስ ወደ "ኬ" ኃምስ ስናመጣው "ኬ" በሚለው ቃል ውስጥ "የእኔ" በግሪክ "ሞዩ" μου የሚል በውስጠ ታዋቂ አገናዛቢ ዘርፍ አለ፦
መዝሙር 22፥1 አምላኬ አምላኬ አንተ እኔን ስለ ምን ተውኸኝ? אֵלִ֣י אֵ֭לִי לָמָ֣ה עֲזַבְתָּ֑נִי
ማርቆስ 15፥34 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም፦ አምላኬ፥ አምላኬ አንተ እኔን ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው። καὶ τῇ ἐνάτῃ ὥρᾳ ἐβόησεν ὁ Ἰησοῦς φωνῇ μεγάλῃ Ἐλωῒ Ἐλωῒ λαμὰ σαβαχθανεί; ὅ ἐστιν μεθερμηνευόμενον Ὁ Θεός μου ὁ Θεός μου, εἰς τί ἐγκατέλιπές με;

ኢየሱስ በባለቤት ሁለተኛ መደብ "አንተ" የሚለው አንዱን አምላክ ሲሆን በተሳቢ መጀመርያ መደብ "እኔን" የሚለው ደግሞ እራሱን ነው፥ 'ተውኸኝ" የሚለው ተሻጋሪ ግሥ በባለቤት አምላክ እና በተሳቢ ሰው መካከል የገባ መሆኑ ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ በማንነት እና በምንነት እንደሚለያዩ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ኢየሱስ ሊያርግ ሲል አምላክ እንዳለው ለማመልከት "አምላኬ" በማለት ተናግሯል፦
ዮሐንስ 20፥17 "እኔ ወደ አባቴ እና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው" አላት። καὶ εἰπὲ αὐτοῖς Ἀναβαίνω πρὸς τὸν Πατέρα μου καὶ Πατέρα ὑμῶν καὶ Θεόν μου καὶ Θεὸν ὑμῶν.

"ወደ" የሚለው መስተዋድድ ኢየሱስን እና አምላኩን መነጠሉን በሰዋስው አወቃቀር ተመልከት! "ቴዎን ሞዩ" Θεόν μου ማለት "የ-"እኔ አምላክ" የሚል ትርጉም ይይዛል። ስለዚህ አንዱ አምላክ አምላክነቱ ለኢየሱስ ሙሉ "እኔነት" "ሁለንተናዊ ማንነት እና ምንነት" እንጂ ለሥጋው፣ ለሰውነቱ፣ ለቁርበቱ ብቻ ነው" የሚል ድራማና ቁማር ተውኔት እና ቲያትር አይሠራም። ኢየሱስ "አምላካችን" በማለት ፈንታ "አምላኬ" ማለቱ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ እና ለሐዋርያቱ አምላክነቱ ለየቅል አያረገውም፦
ዘፍጥረት 43፥23 እርሱም አላቸው፦ "ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁስ ደርሶኛል"። וַיֹּאמֶר֩ שָׁלֹ֨ום לָכֶ֜ם אַל־תִּירָ֗אוּ אֱלֹ֨הֵיכֶ֜ם וֵֽאלֹהֵ֤י אֲבִיכֶם֙ נָתַ֨ן לָכֶ֤ם מַטְמֹון֙ בְּאַמְתְּחֹ֣תֵיכֶ֔ם כַּסְפְּכֶ֖ם
ዮሴፍ ወንድሞቹን እና አባታቸውን አካቶ "አምላካችሁ" ከማለት ይልቅ አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ" ማለቱ አንዱ አምላክ ለወንድሞቹ እና ለአባታቸው አምላክነቱ ለየቅል ካልሆነ እንግዲያውስ ኢየሱስ "ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካችሁ" ማለቱ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ እና ለሐዋርያቱ አምላክነቱ ለየቅል አያረገውም። ኢየሱስ እኮ "አምላካችን" ብሏል፦
ኢሳይያስ 61፥1 "የ-"ጌታዬ" የያህዌህ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ያህዌህ ቀብቶኛልና። ר֛וּחַ אֲדֹנָ֥י יְהוִ֖ה עָלָ֑י יַ֡עַן מָשַׁח֩ יְהוָ֨ה אֹתִ֜י לְבַשֵּׂ֣ר עֲנָוִ֗ים
ኢሳይያስ 61፥2 የተወደደችውን የያህዌን ዓመት "አምላካችን" የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ እና የሚያለቅሱትን ሁሉ አጽናና ዘንድ ልኮኛል። לִקְרֹ֤א שְׁנַת־רָצֹון֙ לַֽיהוָ֔ה וְיֹ֥ום נָקָ֖ם לֵאלֹהֵ֑ינוּ לְנַחֵ֖ם כָּל־אֲבֵלִֽים׃

በትንቢት መነጽር "አምላካችን" የሚለው ኢየሱስ ስለመሆኑ ሉቃስ 4፥17-20 ተመልከት! ኢየሱስ ካረገ በኃላ ሰማይ ላይ አንዱን አምላክ "አምላኬ" ብቻ ሳይሆን "አምላካችን" ብሎ ይናገራል፦
ራእይ 3፥2 ሥራህን "በ-"አምላኬ" ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን። οὐ γὰρ εὕρηκά σου ἔργα πεπληρωμένα ἐνώπιον τοῦ Θεοῦ μου·
ራእይ 3፥12 ድል የነሣው በ-"አምላኬ" መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የ-"አምላኬን" ስም እና የአምላኬን ከተማ ስም ማለትም ከሰማይ ከ-"አምላኬ" ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ እንዲሁ አዲሱን ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ። Ὁ νικῶν, ποιήσω αὐτὸν στῦλον ἐν τῷ ναῷ τοῦ Θεοῦ μου, καὶ ἔξω οὐ μὴ ἐξέλθῃ ἔτι, καὶ γράψω ἐπ’ αὐτὸν τὸ ὄνομα τοῦ Θεοῦ μου καὶ τὸ ὄνομα τῆς πόλεως τοῦ Θεοῦ μου, τῆς καινῆς Ἱερουσαλὴμ ἡ καταβαίνουσα ἐκ τοῦ οὐρανοῦ ἀπὸ τοῦ Θεοῦ μου, καὶ τὸ ὄνομά μου τὸ καινόν.
ራእይ 19፥5 ድምፅም እንዲህ ሲል ከዙፋኑ ወጣ፦ “ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! "አምላካችንን" አመስግኑ”። καὶ φωνὴ ἀπὸ τοῦ θρόνου ἐξῆλθεν λέγουσα Αἰνεῖτε τῷ Θεῷ ἡμῶν, πάντες οἱ δοῦλοι αὐτοῦ, οἱ φοβούμενοι αὐτόν, οἱ μικροὶ καὶ οἱ μεγάλοι.

"አምላካችን" የሚለው ቃል ይሰመርበት! ከዙፋኑ የወጣው "አምላካችን" የሚል ድምፅ በዙፋኑ መካከል ካለው ከኢየሱስ የወጣ ድምፅ ነው፦
ራእይ 7፥17 "በዙፋኑ መካከል ያለው" በጉ እረኛቸው ይሆናልና። ὅτι τὸ Ἀρνίον τὸ ἀνὰ μέσον τοῦ θρόνου ποιμανεῖ αὐτούς

የሥነ መለኮት ምሁር እና ተንታኝ ዮሐንስ ጊል "አምላካችን" የሚለው ኢየሱስ ስለመሆኑ ባብራሩበት የትርጓሜ መጽሐፍ እንዲህ ብለዋል፦
"ድምፅም እንዲህ ሲል ከዙፋኑ ወጣ" የሚለው በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር አብ አይደለም፥ "አምላካችንን አመስግኑ" የሚለው ሐረግ በትክክለኛነት እና በአግባብነት በአብ ሊነገር አይችልም። ይልቁንም መካከለኛ ሆኖ ስለ አብ ለሕዝቡ፦ "አምላኬ እና አምላካችሁ፥ እና አባቴ እና አባታችሁ" ያለው በዙፋኑ መካከል ካለው በግ ከክርስቶስ ነው። Gill's Exposition of the Whole Bible Commentary, Revelation 19:5

"የባሕርይ አምላክ" ማለት "የሚመለክ አምላክ" ማለት ከሆነ እንግዲያውስ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ የባሕርይ አምላክ ስለሆነ ኢየሱስ አምላኪ ሰው ስለሆነ አምላኩን ያመልክ ነበረ፦
ዮሐንስ 4፥22 እናንተስ ማታውቁትን ታመልካላችሁ፥ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና የምናውቀውን "እናመልካለን"። ὑμεῖς προσκυνεῖτε ὃ οὐκ οἴδατε, ἡμεῖς προσκυνοῦμεν ὃ οἴδαμεν, ὅτι ἡ σωτηρία ἐκ τῶν Ἰουδαίων ἐστίν·
ዮሐንስ 4፥23 ነገር ግን በእውነት አምላኪዎች አብን በመንፈስ እና በእውነት "የሚያመልኩበት" ጊዜ ይመጣል፥ አሁንም ሆኖአል። "አብ ሊያመልኩት" እንደ እነዚህ ያሉትን ይፈልጋልና። ἀλλὰ ἔρχεται ὥρα καὶ νῦν ἐστιν, ὅτε οἱ ἀληθινοὶ προσκυνηταὶ προσκυνήσουσιν τῷ Πατρὶ ἐν πνεύματι καὶ ἀληθείᾳ· καὶ γὰρ ὁ Πατὴρ τοιούτους ζητεῖ τοὺς προσκυνοῦντας αὐτόν·

"እናመልካለን" የሚለው ይሰመርበት! የሚመለከውም ዐውዱ ላይ አብ ብቻ ነው። ኢንሻላህ ይቀጥላል......

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢየሱስ አምላክ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥172 አል-መሢሕ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ

"አምላክ" በሚለው መድረሻ ቃል ላይ "ህ" የነበረውን ሳድስ "የአንተ" የሚል በውስጠ ታዋቂ አገናዛቢ ዘርፍ ስላለ "የ-"አንተ አምላክ" የሚል ትርጉም ይይዛል፥ አንዱ አምላክ የኢየሱስ ሙሉ አንተነት አምላክ ስለሆነ ነቢዩ ዳዊት በሁለተኛ መደብ "አምላክህ" በማለት ይናገራል፦
መዝሙር 45፥7 ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ፡
አምላክ አምላክህ የደስታ ዘይትን ቀባህ። ׀ מְשָׁחֲךָ֡ אֱלֹהִ֣ים אֱ֭לֹהֶיךָ שֶׁ֥מֶן שָׂשֹׂ֗ון מֵֽחֲבֵרֶֽיךָ׃
ዕብራውያን 1፥9 አምላክ አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ። ἔχρισέν σε, ὁ Θεός, ὁ Θεός σου ἔλαιον ἀγαλλιάσεως παρὰ τοὺς μετόχους σου.

ነቢዩ ዳዊት በሁለተኛ መደብ "አምላክህ" እንዳለ ሁሉ ነቢዩ ሚልኪያስ ደግሞ በሦስተኛ መደብ "አምላኩ" በማለት ያህዌህ የኢየሱስ አምላክ መሆኑን ተናግሯል፦
ሚክያስ 5፥4 እርሱም ይቆማል፥ በያህዌህም ኃይል "በአምላኩ" በያህዌህ ስም" ግርማ መንጋውን ይጠብቃል። וְעָמַ֗ד וְרָעָה֙ בְּעֹ֣ז יְהוָ֔ה בִּגְאֹ֕ון שֵׁ֖ם יְהוָ֣ה אֱלֹהָ֑יו וְיָשָׁ֕בוּ
ዮሐንስ 17፥12 ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን "በስምህ" እኔ እጠብቃቸው ነበር። ὅτε ἤμην μετ’ αὐτῶν, ἐγὼ ἐτήρουν αὐτοὺς ἐν τῷ ὀνόματί σου ᾧ δέδωκάς μοι,

ነቢያት ኢየሱስ አምላክ እንዳለው እንደተናገሩት ሁሉ ሐዋርያት ኢየሱስ አምላክ እንዳለው በሦስተኛ መደብ "አምላኩ" እና "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ" በማለት ተናግረዋል፦
ራእይ 1፥6 መንግሥትም "ለ-አምላኩ" እና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን! አሜን። καὶ ἐποίησεν ἡμᾶς βασιλείαν, ἱερεῖς τῷ Θεῷ καὶ Πατρὶ αὐτοῦ, αὐτῷ ἡ δόξα καὶ τὸ κράτος εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.
1ኛ ጴጥሮስ 1፥3 የጌታችን "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ" እና አባት ይባረክ። Εὐλογητὸς ὁ Θεὸς καὶ Πατὴρ τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ,

"አባት" ማለት ለአንዱ አምላክ "አስገኚ" ማለት ከሆነ "አምላክ" ማለት ለአንዱ አምላክ "የሚመለክ" ማለት ከሆነ እንግዲያውስ ኢየሱስ ያስገኘው አስገኚ እና የሚያመልከው አምላክ አለው። ጳውሎስም "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ" በማለት ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ተናግሯል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 1፥3 የጌታችን "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ" እና አባት ይባረክ። Εὐλογητὸς ὁ Θεὸς καὶ Πατὴρ τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ,
2ኛ ቆሮንቶስ 11፥31 ለዘላለም የተባረከ የጌታችን "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ" እና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል። ὁ Θεὸς καὶ Πατὴρ τοῦ Κυρίου Ἰησοῦ οἶδεν, ὁ ὢν εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας, ὅτι οὐ ψεύδομαι.
ኤፌሶን 1፥3 የጌታችን "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ" እና አባት ይባረክ። Εὐλογητὸς ὁ Θεὸς καὶ Πατὴρ τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ,

"ሆ ቴዎስ ቱ ኩሪዩ ሄሞን" ὁ Θεὸς τοῦ Κυρίου ἡμῶν ማለት "የጌታችን አምላክ"the God of our Lord" ማለት ሲሆን ይህ ጌታ የተደገው ሰው ለጌትነቱ አምላክ አለ፦
ኤፌሶን 1፥17 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ..። ἵνα ὁ Θεὸς τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ,

ኢየሱስ "አምላኬ" የሚለው ነቢያት እና ሐዋርያት "አምላክህ" "አምላኩ" "የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ" የሚሉት አብን ብቻ እና ብቻ ነው፥ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አምላክ አለመሆናቸው በራሱ አንድ አምላክ አብ ብቻ እንደሆነ በቂ ማሳያ ነው። ኢየሱስ የራሱን አምላክነት የት አስቀምጦ ነው አብን ብቻ "አምላኬ" የሚለው? መንፈስ ቅዱስንስ እረስቶት ነው "አምላኬ" ያላለው? ማቴዎስ 26፥39 ላይ "በፊቱ ወደቀ" የሚለውን ግዕዙ "ሰገደ በገጹ" ይለዋል፦
ማቴዎስ 26፥39 ወተአተተ ሕቀ እምኔሆሙ ወ-"ሰገደ በገጹ" ወጸለየ ወይቤ፦ “አቡየ፡ እመሰ ይትከሀል ይኅልፍ እምኔየ ዝንቱ ጽዋዕ፡ ወባሕቱ ፈቃደ ዚኣከ ይኩን፡ ወአኮ ፈቃደ ዚኣየ።”

"ሰገደ" በግዕዝ አላልታችሁ "ገ" ፊደልን ስታነቡት በዐማርኛ "ሰገደ" አጥብቃችሁ "ገ" ፊደልን ስታነቡት ማለት ነው፥ አንድምታውም፦ "ግንባሩን ምድር አስነክቶ ሰገደ" ይለናል፦
የማቴዎስ ወንጌል 26፥39 አንድምታ
"ከዚያ ጥቂት እልፍ ብሎ ግንባሩን ምድር አስነክቶ ሰገደ"።

ግንባሩን ምድር አስነክቶ ከሰገደ አምላኪ እንጂ ተመላኪ መሆን የለበትም። በተመሳሳይ ማርቆስ 14፥35 ላይ "በምድርም ወድቆ" የሚለውን ግዕዙ "ሰገደ ውስተ ምድር" ይለዋል፦
ማርቆስ 14፥35 ወእምዝ ተአተተ ሕቀ ወ-"ሰገደ" ውስተ ምድር ወጸለየ፦ "ከመ ትኅልፍ እምኔሁ ይእቲ ሰዓት ለእመ ይትከሀል"።

አንድምታውም፦ "ግንባሩን ምድር አስነክቶ ሰገደ" ይለናል፦
የማርቆስ ወንጌል 14፥35 አንድምታ
"ከዚህም በኃላ ወደ ፊት እልፍ ብሎ ከምድር ሰገደና ጸለየ"።

ከምድር ከሰገደ ሰጋጅ እንጂ ተሰጋጅ መሆን የለበትም። በተመሳሳይ ሉቃል 22፥41 ላይ "በምድርም ወድቆ" የሚለውን ግዕዙ "ሰገደ ውስተ ምድር" ይለዋል፦
ሉቃል 22፥41"ወተአተተ እምኔሆሙ መጠነ ምውጋረ እብን ወሰገደ ወጸለየ"።

አንድምታውም፦ "ግንባሩን ምድር አስነክቶ ሰገደ" ይለናል፦
የሉቃስ ወንጌል 22፥41 አንድምታ
"የድንጋይ ውርወራ ያህል ማለት ድንጋይ ወርውሮ እስኪደርስበት ድረስ ከእርሳቸው እልፍ ብሎ ሰገደ ጸለየ"።

በዲኑል ኢሥላም "መዕቡድ" مَعْبُود‎ ማለት "ተመላኪ" ማለት ሲሆን "ዓቢድ" عَابِد‎ ማለት ደግሞ "አምላኪ" ማለት ነው፥ በተመላኪ እና በአምላኪ መካከል ያለው ሥርዓት "ዒባዳህ" عِبَادَة‎ ደግሞ "አምልኮ" ማለት ነው። ለአሏህ አምልኮን የሚያቀርብ "ባሪያ" በቁርኣን "ዐብድ" عَبْد ይባላል፥ ዒሣ አሏህን በብቸኝነት ስለሚያመልክ "ዐብዱሏህ" عَبْدُ اللَّه ማለትም "የአሏህ አምላኪ" "የአሏህ ባሪያ" ተብሏል፦
4፥172 አል-መሢሕ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ

አል-መሢሕ አሏህን ከማምለክ ፈጽሞ የማይጸየፍ ከሆነ እንግዲያውስ የኢየሱስን አምላክ አሏህ በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ኢየሱስ አብ ነውን? በሚል ትምህርት ተለቋል። አሐዳውያን(only Jesus) "ኢየሱስ አብ ነው" ለሚለው ትምህርታቸው እንዲሁ ሥላሴአውያን "ኢየሱስ አምላክ ነው" ለሚል ትምህርታቸው ዮሐንስ 10፥30 ዮሐንስ 14፥7-9 ዮሐንስ 8፥24-25 ይጠቅሳሉ፥ በእርግጥ ኢየሱስ አብ ወይም አምላክ ሳይሆን የአብ መልእክተኛ ነው። ያንን ስሙር ምንጨታዊ እና ርቱዕ በሆነ ሙግት ሞግተናል። ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/8NR7KHeUUKM?si=Oi83KilHzueKoX5n

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
ገና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

19፥25 «የዘምባባይቱንም ግንድ ወደ አንቺ ወዝውዣት በአንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና» አላት፡፡ وَهُزِّي إِلَيْكِ بِجِذْعِ النَّخْلَةِ تُسَاقِطْ عَلَيْكِ رُطَبًا جَنِيًّا

ጠበቅ አርገን "ገና" ብለን የምንጠቀመው ቃል "ጌና" γέννᾰ ከሚል የግሪክ ኮይኔ ቃል የተገኘ ሲሆን "ልደት" ማለት ነው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም "ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። Τοῦ δὲ Ἰησοῦ Χριστοῦ ἡ γένεσις οὕτως ἦν. μνηστευθείσης τῆς μητρὸς αὐτοῦ Μαρίας τῷ Ἰωσήφ, πρὶν ἢ συνελθεῖν αὐτοὺς εὑρέθη ἐν γαστρὶ ἔχουσα ἐκ πνεύματος ἁγίου.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልደት" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔሲስ" γένεσις ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "የሆነ" ማለት ነው፥ ኢየሱስ ያለ ወንድ ዘር ከማርያም የማኅፀን ፍሬ የሆነ ተአምር ነው። ማርያም የወለደችው ሆዷ ውስጥ የተፀነሰ ፅንስ ነው፥ "ፅንስ" ደግሞ ተፈጥሮ በተለያየ ሂደት የሚያድግ ውላጤ ነው፦
ሉቃስ 1፥31 እነሆም ትፀንሻለሽ፥ "ወንድ" ልጅም ትወልጃለሽ። ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። καὶ ἰδοὺ συλλήμψῃ ἐν γαστρὶ καὶ τέξῃ υἱόν, καὶ καλέσεις τὸ ὄνομα αὐτοῦ Ἰησοῦν.

"ወንድ" የሥጋ መደብ የሆነ ፆታ እንደሆነ ልብ አድርግ!
፨ከመነሻው ማርያም መለኮትን አልፀነሰችም አልወለደችና "አምላክ ተወለደ" ለሚሉት "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ሐራም ነው።
፨ሲቀጥል "የኢየሱስን ልደት አክብሩ" የሚል ሽታው ባይብል ላይም አንድም ጥቅስ የለም፥ ከሐዋርያት ጀምሮ እስከ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ልደቱን ያከበረ አንድም ሰው በታሪክ ላይ የለም፦
"ጥንታዊ ክርስትያኖች የኢየሱስን መወለጃ ቀን በዓል አርገው አያከብሩም፡፡ ይህም የሆነው የማንንም ሰው የልደትን ቀን ማክበር ጣዖታዊ ሥርዓት በመሆኑ ነው"።
World Book Encyclopedia, Volume 3. 1966, pp. 416

ስለዚህ "ሰው ተወለደ" ለሚሉት ደግሞ "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ቢድዓህ ነው።
፨ሢሰልስ ኢየሱስ የተወለደው በጥቅምት ወር እንጂ በታኅሣሥ ወር አይደለም። የዕብራውያን የመጀመሪያ ወር ኒሳን ሲሆን ይህም በጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር የሚያርፈው ሚያዢያ ላይ ነው፥ ይህን ከተረዳን ዘካርያስ ካህን ሲሆን የክህነት ምድቡ ከአብያ ክፍል እንደሆነ እና በተራው ሊያጥን እንደነበር እንረዳለን፦
ሉቃስ 1፣5 በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን "ከአብያ ክፍል" የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ።

ዘካርያስ እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ በአብያ ክፍል ዕጣ ለማጠን ሲገባ መልአኩ ገብርኤል አናገረው። በዕብራውያን በዓመት ሃያ አራት የክህነት ምድብ አለ፥ በአንድ ወር ውስጥ ሁለት ክፍል ሲኖር በአሥራ ሁለት ደግሞ ሃያ አራት ምድብ አለ። ይህን ከተረዳን አባያ ከሃያ አራቱ ምድብ ስምንተኛው ምድር አራተኛው ወር ነው፦
1ኛ ዜና መዋዕል 24፥10 ሰባተኛው ለአቆስ፥ ስምንተኛው "ለአብያ"፥።

የመጀመሪያው ወር ኒሳን ማለትም ሚያዥያ ከሆነ አራተኛው ወር ደግሞ ተሙዝ በጎርጎሮሳውያን ሃምሌ ይሆናል፥ መልአኩ ወደ ዘካሪያስ የመጣው በሃምሌ ወር ከሆነ ወደ ማርያም ደግሞ የመጣው ከዘካርያስ ጋር ከመጣበት በስድስተኛው ወር ነው። ይህም ስድስተኛ ወር ጥር ነው፦
ሉቃስ 1፥26 በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።

እንግዲህ ገብርኤል በጥር ከመጣ ኢየሱስ ፅንሱ የሚጀምረው በጥር ነው። ከጥር ወር የፅንሱ ጊዜ ዘጠኝ ወር ስንቆጥር ጥቅምት ይሆናል፥ ኢየሱስ የተወለደው በጥቅምት ይሆናል ማለት ነው። ከባይብል አንጻር "ኢየሱስ የተወለደው በታኅሣሥ ወር ነው" የሚለው ትርክት ምንጭ አልባ እና ሠነድ አልባ ነው፥ ታኅሣሥ እኮ ለዕብራውያን ብርድ ነው ከቤት አይወጡም። ኢየሱስ ሲወለድ ግን የበልግ ወራት ሆኖ እረኞች በሜዳ ያድሩ ነበር፦
ሉቃስ 2፥8 በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።

ስለዚህ ኢየሱስ የተወለደው ክረምት ላይ ሳይሆን የበልግ ወራት ላይ ነው፥ ይህንን አምላካችን አሏህ በተከበረ ንግግሩ እንዲህ ይተርክልናል፦
19፥23 ምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት፡፡ «ዋ ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ» አለች፡፡ فَأَجَاءَهَا الْمَخَاضُ إِلَىٰ جِذْعِ النَّخْلَةِ قَالَتْ يَا لَيْتَنِي مِتُّ قَبْلَ هَـٰذَا وَكُنتُ نَسْيًا مَّنسِيًّا
19፥25 «የዘምባባይቱንም ግንድ ወደ አንቺ ወዝውዣት በአንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና» አላት፡፡ وَهُزِّي إِلَيْكِ بِجِذْعِ النَّخْلَةِ تُسَاقِطْ عَلَيْكِ رُطَبًا جَنِيًّا

በእስራኤል የዘምባባ ተምር ፍሬ የሚያፈራው በበልግ ወራት መሆኑ ቁርኣኑ ሆነ የሉቃስ ትረካ የነገሩን እውነት "በዕብራውያን ከክረምት ታኅሣሥ 25 ወይም 29 ተወለደ" የሚለውን ተረት ድባቅ ያስገባዋል።
፨ሲያረብብ ታኅሣሥ 25 "ሚጥራስ"Mithras" እና "ተሙዝ"Tammuz" የተባሉ ጣዖታት የተወለዱበት ሲሆን የገና የበዓሉ አከባበር ደግሞ ሳተርን ለተባለው ጣዖት ከሚከበርበት "ሳቱርናሊያ"Saturnalia" ከሚባል የክረምት ክብረ በዓል የተቀዳ ነው።
ይህንን በዓል በቅጡ እና በአግባብ ሳታውቁ የምታከብሩ ክርስቲያኖች እና የምታከባብሩ ሙሥሊሞች ይህንን መልእክት ከሰማችሁ ጀምሮ ሑጃህ ቆሞባችኃልና በንስሓ ወደ አሏህ ተመለሱ! በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ብዙዎችን ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ፦
5፥77 እላንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የሆነን ማለፍ ወሰንን አትለፉ፥ በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ብዙዎችን ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ" በላቸው። قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ غَيْرَ ٱلْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوٓا۟ أَهْوَآءَ قَوْمٍۢ قَدْ ضَلُّوا۟ مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا۟ كَثِيرًۭا وَضَلُّوا۟ عَن سَوَآءِ ٱلسَّبِيلِ ።

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነገረ ክርስቶስ

በ 22 አርስት የተሰደረ እና የተሰነደ የነገረ ክርስቶስ ትምህርት በዩቱብ ቀርቦላችኃል።

1.ኢየሱስ
https://youtu.be/7oao4CB_JSk?si=xVJ0fBzyFaLxArPy

2. መሢሕ
https://youtu.be/spmyxipCR4Q?si=jZkwcwxgUVUt6O2T

3. ክርስቶስ በሥጋ መጣ
https://youtu.be/UPieN1R7068?si=vP6i4HbWctl-1kS0

4. ኢየሱስ ፍጡር ነው ክፍል አንድ
https://youtu.be/2mkPHlb65nA?si=49jhq03m9qTUhgxx

5. ኢየሱስ ፍጡር ነው ክፍል ሁለት
https://youtu.be/E2Ogz55Ac_w?si=t4Y07Tu_tUy_6TF7

6. ኢየሱስ ምንም አልፈጠረም
https://youtu.be/-9NqwdlObIQ?si=Ydxke7vjbklD2aXX

7. ኢየሱስ ሰው ነው
https://youtu.be/zTW15As7PF0?si=ZysuaNINs4cE4pba

8. ኢየሱስ የባሕርይ አምላክ አይደለም
https://youtu.be/Tw755dMvIcw?si=pYUZuy21592lyuhk

9. ኢየሱስ አምላኪ ነው
https://youtu.be/O1JmxxKVTCg?si=WTE9_je_u3b-IA8H

10. ኢየሱስ አይመለክም
https://youtu.be/Ra-k_2-cjQk?si=S6PRqNj5RCaLq8eB

11. ኢየሱስ ነቢይ ነው
https://youtu.be/2NYQEMTXpT8?si=n1LgN9jV0NKNJYfy

12. ኢየሱስ መለኮት አይደለም
https://youtu.be/RQr8ButaUJc?si=MUcjr_kdppMl3cc7

13. ኢየሱስ የተስፋ ቃል ነው
https://youtu.be/MNx0y7xV18Y?si=N7cV2VMqtuMVVke9

14. ኢየሱስ ቅድመ ህልውና የለውም ክፍል አንድ
https://youtu.be/UY98XH1DKP8?si=Cc1o1KJt8IzY1b84

15. ኢየሱስ ቅድመ ህልውና የለውም ክፍል ሁለት
https://youtu.be/ThIlPF3mQLY?si=6tzD1qoJSv4x2eZT

16. ኢየሱስ የባሕርይ ልጅ አይደለም ክፍል አንድ
https://youtu.be/ZPc7TFGPKmo?si=-sR1eqs7vphJT-do

17. ኢየሱስ የባሕርይ ልጅ አይደለም ክፍል ሁለት
https://youtu.be/ZPc7TFGPKmo?si=bhgj1G3o8HyS0kQn

18. እውነተኛ እና ታላቁ አምላክ ማን ነው?
https://youtu.be/Vt47C4OlcDg?si=9sTa_NdJWncm80Hr

19. ቶማስ ጌታዬ እና አምላክ ያለው ማንን ነው?
https://youtu.be/VGGpF97HKw4?si=pQ06jj1RU5L6Au-0

20. አማኑኤል ማን ነው?
https://youtu.be/q6SrruB5yIA?si=ES2faR_ZfcIz6yeM

21. ኢየሱስ የባሕርይ ጌታ ነውን?
https://youtu.be/WJxh4gMa3BU?si=M6LV0vx4bEMiFjr1

22. ኢየሱስ አብ ነውን?
https://youtu.be/8NR7KHeUUKM?si=4Ug06orXCx9uiZvr
ውላጤ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥6 አሏህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነውና፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ

"ውላጤ" ማለት "መለወጥ" "መለዋወጥ" ማለት ሲሆን አንድ ፅንስ በማኅፀን ውስጥ የተለያየ ዕድገት ለማምጣት መለዋወጥ ይኖርበታል፥ ኢየሱስ ፅንስ የነበረ ሲሆን ከፅንስ ወደ ውልደት ከውልደት ወደ እድገት ተለዋዋጭ ነበረ፦
ሉቃስ 2፥52 ኢየሱስም ደግሞ በጥበብ፣ በቁመት እና በሞገስ በአምላክ እና በሰዎች ፊት "ያድግ ነበር"። Καὶ Ἰησοῦς προέκοπτεν ἐν τῇ σοφίᾳ καὶ ἡλικίᾳ καὶ χάριτι παρὰ Θεῷ καὶ ἀνθρώποις.

"ያድግ ነበር" የሚለው ይሰመርበት! ኢየሱስ ተለዋዋጭ ስለነበር እእምሮው በጥበብ፣ አካሉ በቁመት፣ መንፈሱ በሞገስ ያድግ ነበረ፥ እድገት መለወጥ እና መለዋወጥ ነው። ኢየሱስ የሚለወጥ እና የሚለዋወጥ ከሆነ ከኢየሱስ በተቃራኒ አንዱ አምላክ የማይለወጥ እና የማይለዋወጥ ነው፦
ሚልክያስ 3፥6 እኔ ያህዌህ አልለወጥም። כִּ֛י אֲנִ֥י יְהוָ֖ה לֹ֣א שָׁנִ֑יתִי

ኢየሱስ የሚለዋወጥ ከሆነ አንዱ አምላክ የማይለዋወጥ ከሆነ የሚለወጠው ኢየሱስ የማይለወጠውን አንዱን አምላክ በምን ዓይነት መልኩ እንዴት አድርጎ ሊሆን ይችላል? አምላካችን አሏህ ስለ እርሱ ኑባሬ በሦስተኛ መደብ ሲናገር፦ "አሏህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነው" በማለት በእርሱ ባሕይር ላይ መለዋወጥ እንደሌለበት ይናገራል፦
29፥6 አሏህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነውና፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ

"አል-ገኒይ" الْغَنِيّ ማለት "የማይለዋወጥ"the Immutable" ማለት ነው፥ ፈጣሪን ፍጥረቱ በጊዜ በቦታ ሳይወስኑት ከፍጥረት የተብቃቃ ነው። አንዱ አምላክ አሏህ የሁሉ ነገር መንስኤ"cause" ስለሆነ በእርሱ ባሕርይ ያለው "ነው-ነት"Being" የሚባል ባሕርይ ብቻ ነው፥ ፍጡራን ግን የእርሱ ውጤት"effect" ስለሆኑ በእነርሱ ባሕርይ "ሆነ-ነት"Becoming" የሚባል ባሕርይ አላቸው።

በ 451 ድኅረ ልደት በንጉሥ መርቅያኖስ ሊቀ መንበርነት የኬልቄዶን ጉባኤ ላይ 130 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም ተሰብስበው የቆስጠንጢኒያ ኤጲስ ቆጶስ የነበረውን አውጣኬ ያነሳውን ሙግት ለመታደም መጡ፥ "አውጣኬ"Eutyches" ከ 380 እስከ 456 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ ሲሆን "አውጣኬ፦ "የትስብእት ባሕርይ በመለኮት ባሕርይ በመዋጥ ኢየሱስ አንድ ልሙጥ ባሕርይ ብቻ አለው፥ መለኮት ሥጋን በመዋጥ ሥጋን ለወጠው" በማለት ሙግቱን አቀረበ። "ፊሲስ" φύσις ማለት "ባሕርይ"nature" ማለት ሲሆን "ሞኖስ" μόνος ማለት ደግሞ "ብቻ" ማለት ነው፥ ይህ "ውላጤ" የሚባለው የአውጣኬ እሳቤ "ሞኖ ፊሲስ" μόνο φύσις ይባላል። የኬልቄዶን ጉባኤ የእርሱን ሙግት በማውገዝ፦ "ኢየሱስ ከሰው ጋር እና ከአብ ጋር "በባሕርይ የተስተካከለ"consubstantial" ሲሆን በአንድ አካል ሁለት ባሕርይ አለው" በማለት አጸደቀ፥ "ዲያ" δυο ማለት "ምንታዌ" ወይም "ሁለት" ማለት ሲሆን ይህ የጉባኤው ውሳኔ "ዲያ ፊሲስ" δυο φύσις ይባላል።

ሥጋ በመለኮት ተለወጠ ከሚለው ከአውጣኬ ትምህርት በተቃራኒው መለኮት በሥጋ ተለወጠ የሚል የውላጤ ትምህርት በዘመናችን ጥቂት ፕሮቴስታንት ውስጥ ተሰራፍቶ የሚገኝ የኬኖሲስ ትምህርት ነው፥ "ኬኖሲስ" κένωσις የሚለው የግሪክ ኮይኔ ቃል "ኬኖ" κενόω ማለትም "ባዶ አደረገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ከንቱነት" "ባዶነት"emptiness" ማለት ነው፦
ፊልጵስዩስ 2፥7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን "ባዶ አደረገ"። ἀλλὰ ἑαυτὸν ἐκένωσεν μορφὴν δούλου λαβών, ἐν ὁμοιώματι ἀνθρώπων γενόμενος· καὶ σχήματι εὑρεθεὶς ὡς ἄνθρωπος

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባዶ አደረገ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ኤኬኖሴን" ἐκένωσεν ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ኬኖ" κενόω ነው፥ "ባዶ አደረገ" የሚለውን አንዳንድ የፕሮቴስታንት አንጃ እና ጎጥ፦ "አምላክነቱን ትቶ መጣ" በሚል ይረዱታል። አምላክነት የሆነ ቦታ አስቀምጠህ የምትመጣበት ጃኬት አይደለም፥ መጨመር እና መጉደል የፍጡር እንጂ የመለኮት ባሕርይ አይደለም። "አምላክነቱን ዝግ"mute" አርጎ አልተጠቀመበትም" የሚል ኬኖሲስ የመጀመሪያው ኬኖሲስ ሲሆን ሁለተኛው ኬኖሲስ ደግሞ "አምላክነቱን ትቶ በመምጣት ሰው ብቻ ነው" የሚል ትምህርት ነው፦
ዮሐንስ 1፥14 ቃልም ሥጋ ሆነ። Καὶ ὁ Λόγος σὰρξ ἐγένετο
እዚህም አንቀጽ ላይ "ሆነ" ለሚለው የግስ መደብ የተጠቀመት ቃል "ኤጌኔቶ" ἐγένετο ሲሆን "ሆነ" ያልሆነበትን ወደ መሆን ስለሆነ "ተለወጠ" የሚል እምነት አላቸው፦
ዘጸአት 4፥2 ጌታም፦ “ይህች በእጅህ ያለችው ምንድር ናት?” አለው። እርሱም፦ “በትር ናት፡” አለ። εἶπε δὲ αὐτῷ Κύριος· τί τοῦτό ἐστι τὸ ἐν τῇ χειρί σου; ὁ δὲ εἶπε· ῥάβδος.
ዘጸአት 4፥3 “ወደ መሬት ጣላት፡” አለው፤ እርሱም በመሬት ጣላት፥ እባብም ሆነች፤ ሙሴም ከእርሷ ሸሸ። καὶ εἶπε· ρίψον αὐτὴν ἐπὶ τὴν γῆν. καὶ ἔρριψεν αὐτὴν ἐπὶ τὴν γῆν, καὶ ἐγένετο ὄφις· καὶ ἔφυγε Μωυσῆς ἀπ᾿ αὐτοῦ.

"ካይ ኤግኔቶ ኦፊስ" καὶ ἐγένετο ὄφις·ማለት "እባብም ሆነች" ማለት ሲሆን "ሆነ" ማለት "ተለወጠ" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል፦
ዘጸአት 7፥15 እባብም ሆና "የተለወጠችውን" በትር በእጅህ ትወስዳለህ። καὶ τὴν ράβδον τὴν στραφεῖσαν εἰς ὄφιν λήψῃ ἐν τῇ χειρί σου.

"የተለወጠችውን" የሚለው ቃል ይሰመርበት! "ይህ ወደ ሥጋ የተለወጠው ቃል ወደ አምላክነት ከትንሳኤ በኃላ ወይም ከዕርገት ተመልሷል" የሚል ትምህርታቸው "ሚጠት" ይባላል፥ "ሚጠት" ማለት "መመለስ" ማለት ነው። "ቃል ሥጋ ሆነ" ማለት "ቃል ሥጋ ለበሰ" ማለት ቢሆን ኖሮ "በትር እባብ ሆነ" ማለት "በትር እባብ ለበሰ" ማለት ይሆን ነበር፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን "ቃል ሥጋ ሆነ" ማለት "ከጥንት ሲነገር የነበረው ቃል ሰው በመሆን ተፈጸመ" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ ለኢዩ፦ "ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ" ተብሎ የተነገረው የአምላክ ቃል ጊዜው ሲደርስ ሆኗል፦
2ኛ ነገሥት 15፥12 ለኢዩ፦ "ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ" ተብሎ የተነገረው የጌታ ቃል ይህ ነበረ፥ እርሱም "ሆነ"። ὁ λόγος Κυρίου, ὃν ἐλάλησε πρὸς ᾿Ιοὺ λέγων· υἱοὶ τέταρτοι καθήσονταί σοι ἐπὶ θρόνου ᾿Ισραήλ· καὶ ἐγένετο οὕτως.

በግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ "ካይ ኤጌኔቶ አውቶስ" καὶ ἐγένετο οὕτως ማለትም "እርሱም ሆነ" ተብሎ ተቀምጧል፥ "እርሱ" ተብሎ የተቀመጠው ተውላጠ ስም "የጌታ ቃል" የሚለውን ባለቤት ተክቶ የመጣ ነው። "ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ" የሚለው የአምላክ ቃል ጊዜው ሲደርስ "ሆነ" እንደተባለው ሁሉ "የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ" ተብሎ የተነገረው ቃል ጊዜው ሲደርስ ሥጋ ማለትም ሰው "ሆነ" ማለት ነው፦
ሕዝቅኤል 12፥28 ስለዚህ በላቸው፦ አዶናይ ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ "የምናገረው ቃል ይፈጸማል" እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥ ይላል አዶናይ ያህዌህ። לָכֵ֞ן אֱמֹ֣ר אֲלֵיהֶ֗ם כֹּ֤ה אָמַר֙ אֲדֹנָ֣י יְהוִ֔ה לֹא־תִמָּשֵׁ֥ךְ עֹ֖וד כָּל־דְּבָרָ֑י אֲשֶׁ֨ר אֲדַבֵּ֤ר דָּבָר֙ וְיֵ֣עָשֶׂ֔ה נְאֻ֖ם אֲדֹנָ֥י יְהוִֽה׃ ס

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቃል" ለሚለው የገባው ቃል "ደበር" דָבָר ሲሆን ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ "ሎጎስ" λόγος ይለዋል። ይህም "የምናገረው ቃል" ስለሚል የሚናገረው ቃል ፍጻሜውን በማግኘት ሥጋ ሆነ፥ "ቃል ሥጋ ሆነ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ በዚህ መልክ እና ልክ ተረድተነዋል። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ምንታዌ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥17 እነዚያ አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሢሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

"ምንታዌ" ማለት "ሁለት" "ሁለትነት" ማለት ሲሆን በ451 ድኅረ ልደት በኬልቄዶን የጸደቀው "ዲያ ፊሲስ" δυο φύσις ትምህርት ነው፥ "ዲያ" δυο ማለት "ምንታዌ" "ሁለት" ማለት ሲሆን "ፊሲስ" φύσις ማለት ደግሞ "ባሕርይ"nature" ማለት ነው። በጥቅሉ "ዲያ ፊሲስ" δυο φύσις ማለት "ሁለት ባሕርይ" ማለት ሲሆን የኬልቄዶን ጉባኤ የአውጣኬን ትምህርት በማውገዝ፦ "ኢየሱስ ከሰው ጋር እና ከአብ ጋር "በባሕርይ የተስተካከለ"consubstantial" በአንድ አካል ያለ ውላጤ፣ ያለ ሚጠት፣ ያለ ትድምት፣ ያለ ቱሳሔ፣ ያለ ቡዓዴ ሁለት ባሕርይ አለው" የሚል እሳቤ ነበር።

፨ "ውላጤ" ማለት "መለወጥ" ማለት ሲሆን "ሥጋ ወደ መለኮት ተለወጠ" ወይም "መለኮት ወደ ሰውነት ተለወጠ" የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ሚጠት" ማለት "መመለስ" ሲሆን "ሥጋ ከትንሳኤ ወይም ወደ ከእርገት በኃላ ወደ መለኮት ተመለሰ" የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ቱሳሔ" ማለት "ቅልቅል" ማለት ሲሆን "ልክ እንደ ውኃ እና ማር ብርዝ አሊያም እንደ ወተት እና ቡና ማኪያቶ ጣዕም እና መልክ በመቀላቀል ተዋሐደ" የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ትድምት" ማለት "መደመር" ወይም "መደረብ" ማለት ሲሆን "ልክ ልብስ በአካል እንደሚደረብ እና እንደሚለበስ መለኮት መለኮትን ሳይለቅ ሥጋ ጨመረ፣ ደረበ፣ ለበሰ" "ደመረ" የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ኅድረድ" ማለት "ማደር" ማለት ማለት ሲሆን "ልክ ቤተመቅደስ አምላክ እንደሚያድር መለኮት ሥጋ ላይ አደረበት ወይም ልክ ውኃ በማድጋ፣ ሰይፍ በሰገባ፣ መጽሐፍ በተደጎሰ ማኅደር፣ ጽላት በታቦት እንደሚያድሩ መለኮት ሥጋ ላይ አደረበት የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ቡዓዴ" ማለት "መለየት" ማለት ሲሆን "ልክ ብረት ብረትትነቱን ሳይለቅ ከእንጨት ጋር በብሎን ተለያይቶ እንደሚተሳሰር መለኮት ከሥጋ ጋር ተለያይቶ በአንድ አካል ተሳሰረ" የሚል እሳቤ ነው።

ይህንን የሁለት ባሕርይ እሳቤ የሚያራምዱት ካቶሊክ፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክ እና ፕሮቴስንታንት ናቸው፥ ይህ ሁሉ ውዝግብ ግን በባይብል ላይ የለም። ከዚያ ይልቅ አምላክ እና ሰው ሁለት ለየቅል ባሕርዮት ሲሆኑ በአንድ ማንነት"person" አይኖሩም፥ ባሕርይ አንድ ሳይሆን አካል"person" አንድ አይሆንም፦
ኢሳይያስ 31፥3 ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም። וּמִצְרַ֤יִם אָדָם֙ וְֽלֹא־אֵ֔ל
ሕዝቅኤል 28፥2 ነገር ግን ልብህን እንደ አምላክ ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። וְאַתָּ֤ה אָדָם֙ וְֽלֹא־אֵ֔ל וַתִּתֵּ֥ן לִבְּךָ֖ כְּלֵ֥ב אֱלֹהִֽים׃

"አምላክ" መለኮታዊ ኑባሬ ከሆነ "ሰው" ሰዋዊ ኑባሬ ከሆነ ሰው እና አምላክ ሁለት ለየቅል ማንነት እና ምንነት ናቸው፦
ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና። כִּ֣י אֵ֤ל אָֽנֹכִי֙ וְלֹא־אִ֔ישׁ

"እኔ" እያለ የሚናገር አንድ ነጠላ ማንነት በምንነቱ ሰውነት ስለሌለበት "እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና" በማለት እንቅጩን ፍርጥ አርጎ ይናገራል። አምላክ በማንነት አንድ ስለሆነ አንድ አምላክ አለ፥ ሰው ግን በማንነት ብዙ ስለሆነ ብዙ ሰዎች አሉ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥4 ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን። καὶ ὅτι οὐδεὶς Θεὸς εἰ μὴ εἷς.
1 ጢሞቴዎስ 2፥5 አንድ አምላክ አለና፥ በአምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። εἷς γὰρ Θεός, εἷς καὶ μεσίτης Θεοῦ καὶ ἀνθρώπων, ἄνθρωπος Χριστὸς Ἰησοῦς,

በአንድ አምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው መካከለኛ ከአንዱ አምላክ እየሰማ የሚያስተላልፍ ሰው ነበር፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 ከአምላክ ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ። ἄνδρα ἀποδεδειγμένον ἀπὸ τοῦ Θεοῦ εἰς ὑμᾶς.
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። νῦν δὲ ζητεῖτέ με ἀποκτεῖναι, ἄνθρωπον ὃς τὴν ἀλήθειαν ὑμῖν λελάληκα, ἣν ἤκουσα παρὰ τοῦ Θεοῦ·

እዚህ አንቀጽ ላይ ላኪ "አምላክ" ባለቤት ተላኪ "ሰው" ተሳቢ መሆኑ እና በባለቤት እና በተሳቢ መካከል "የሰማሁት" የሚል ተሻጋሪ ግሥ መሆኑ በራሱ አምላክ እና ሰው ሁለት የተለያዩ ማንነቶች መሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ ከዚያም ባሻገር አምላክ በኑባሬ ከሰው በምንነት ስለሚለያይ አምላክ የተባለው ላኪ እና ሰው የተባለው ተላኪ ሁለት የተለያዩ ምንነቶች መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። ስለዚህ መሢሑ ሰው፣ ነቢይ፣ መልእክተኛ ሆኖ ሳለ አምላክ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥17 እነዚያ አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሢሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"የሥላሴ ትምህርት መግቢያ" በሚል ትምህርት ተለቋል። "ሥላሴ" የሚለው ቃል “ሠለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን "ሦስትነት"threeness" ማለት ነው፥ “ሥሉስ” ማለትም “ሥስት”three" ማለት ሲሆን ሥላሴ ደግሞ የሥሉስ ግሣዊ ስም ነው። "አምላክ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሥስት ነው"Triune God" የሚል ትምህርት "ነገረ ሥላሴ"triadology" ይባላል። ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/jTGV0vTyhhE?si=q67nge-dteIAAUcr

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!
ተዋሕዶ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነሆ በአሏህ የሚያጋራው ሰው አሏህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፥ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

አንድ እናት ልጅ ስትወልድ "ምን ወለደች" ብለን ስንጠይቅ "ወንድ" ወይም "ሴት" ስንል ወንድ እና ሴት ምንነት ነው፥ "ፊሲስ" φύσις ማለት "ባሕርይ"nature" ማለት ሲሆን ወንድ ወይም ሴት ምንነት ስለሆነ ባሕርይ ነው፦
ሮሜ 1፥26 ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ። αἵ τε γὰρ θήλειαι αὐτῶν μετήλλαξαν τὴν φυσικὴν χρῆσιν εἰς τὴν παρὰ φύσιν,
ሮሜ 1፥27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ። ὁμοίως τε καὶ οἱ ἄρσενες ἀφέντες τὴν φυσικὴν χρῆσιν τῆς θηλείας ἐξεκαύθησαν ἐν τῇ ὀρέξει αὐτῶν εἰς ἀλλήλους,

እዚህ ጥቅስ ላይ "ባሕርይ" ለሚለው የገባው ቃል "ፊሲከን" φυσικὴν ሲሆን "ፊሲስ" φύσις ለሚለው ገላጭ ቅጽል ነው፥ ወንድነት እና ሴትነት ሁለት የተለያዩ ባሕርዮት ሲሆኑ በመገናዘብ፣ በተዐቅቦ፣ በመጠባበቅ አንድ ይሆናሉ፦
ማቴዎስ 19፥5 አለም፦ "ስለዚህ ሰው አባቱን እና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል። ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ" የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? καὶ εἶπεν Ἕνεκα τούτου καταλείψει ἄνθρωπος τὸν πατέρα καὶ τὴν μητέρα καὶ κολληθήσεται τῇ γυναικὶ αὐτοῦ, καὶ ἔσονται οἱ δύο εἰς σάρκα μίαν;

እዚህ አንቀጽ ላይ "አንድ" ለሚለው የገባው ቃል "ሚያን" μίαν ሲሆን "ሚያ" μία ለሚለው ገላጭ ቅጽል ነው፥ ባል የወንድነት ባሕርይውን ሳይለቅ እንዲሁ ሚስት የሴትነት ባሕርይዋን ሳትለቅ ያለመቀላቀል እና ያለመደባለቅ አንድ ሥጋ በመሆን ይገናዘባሉ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 7፥4 ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ። እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ። ἡ γυνὴ τοῦ ἰδίου σώματος οὐκ ἐξουσιάζει ἀλλὰ ὁ ἀνήρ· ὁμοίως δὲ καὶ ὁ ἀνὴρ τοῦ ἰδίου σώματος οὐκ ἐξουσιάζει ἀλλὰ ἡ γυνή.

ግን ይህ ለአንድ ባሕርይ ትምህርት ምሳሌ መሆን አይችልም። ምክንያቱም ወንድ ሴት እንዲሁ ሴት ወንድ አይደለም፥ ሴት ወንድ አትሆንም እንዲሁ ወንድ ሴት አይሆንም። ሴት እና ወንድ አንድ ከሆኑ በኃላ ሁለት አካላት"person" እና ሁለት ባሕርያት እንጂ አንድ አካል አንድ ባሕርይ አይደሉም፥ ስለዚህ ባይብል ላይ ያለው "ሚያ ፊሲስ" μία φύσις ለተዋሕዶ እሳቤ ናሙና መሆን አይችልም። በ451 ድኅረ ልደት በኬልቄዶን የተወገዘው የእስክንድርያው ኤጲስ ቆጶስ የዲዮስቆርዮስ እሳቤ "ሚአ ፊሲስ" μία φύσις ሲባል ትርጉሙ "አንድ ባሕርይ" ማለት ነው፥ "ተዋሕዶ" የሚለው የግዕዝ ቃል "አንድ" ማለት እንጂ "ቱሳሔ" ማለትም "ቅልቅል" "ድብልቅ" "ውሕደት" ማለት አይደለም። ትስብእት እና መለኮት በመገናዘብ፣ በተዐቅቦ፣ በመጠባበቅ አንድ ባሕርይ የሚባለው ትምህርት "ተዋሕዶ" ይባላል።

፨ "ትስብእት" የሚለው የግዕዝ ቃል "ተሰብአ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሰውነት" ማለት ነው፥ የስም መደቡ ደግሞ "ሰብእ" ማለትም "ሰው" ነው።
፨ "መለኮት" የሚለው የግዕዝ ቃል "መለከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አምላክነት" ማለት ነው፥ የስም መደቡ ደግሞ "አምላክ" ነው።
ተዋሕዶ አሳቡ "መለኮት በትስብእት ፍጡር፣ ሰው፣ አምላኪ ሆነ፥ ትስብእት በመለኮት ፈጣሪ፣ አምላክ፣ ተመላኪ ሆነ" የሚል ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 78 ቁጥር 31
"ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ "ሥጋ አምላክ እንደሆነ" እንናገራለን"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 112 ቁጥር 31
"ፈጣሪ ከእኛ ባሕረይ ከተገኘች በእውነት ድንግል ከምትሆን ከማርያም ፍጡር ሆነ"
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 61 ቁጥር 23
"ሰው አምላክ ሆነ"
ዮሐንስ 2፥14 አንድምታ፦ "አምላክ ሰው ሆነ፥ ሰው አምላክ ሆነ" እያሉ ርደቱን እና ዕርገቱን ለመንገር።

"ሥጋ አምላክ እንደሆነ" "ፈጣሪ ፍጡር ሆነ" "አምላክ ሰው ሆነ" "ሰው አምላክ ሆነ" የተባሉት ቃላት ይሰመርበት! የመለኮት ገንዘብ ለትስብእት የትስብእት ገንዘብ ለመለኮት ስለሚነገር በሚል ፈሊጥ "መለኮት በትስብእት ፍጡር፣ ሰው፣ አምላኪ ነው፥ ትስብእት በመለኮት ፈጣሪ፣ አምላክ፣ ተመላኪ ነው" የሚል ይህን የዲዮስቆርዮስ ስብጥር ትምህርት የሚያራምዱ ጽብሓውያን ክርስቲያን"oriental Christian" የግብፅ፣ የአርመንያ፣ የሕንድ፣ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።

፨ ፈጣሪ ለፍጡር አምላክነቱን እና አምልኮቱን ካጋራ ትልቁ ሺርክ ነውና እራሱ አሻራኪ ይሆናል፣
፨"ፈጣሪ ከፍጡር ጋር አንድ ነው እና አንድ ሆነ፥ ፍጡር ከፈጣሪ ጋር አንድ ነው እና አንድ ሆነ" ማለት ትልቁ ሺርክ ነው፣
፨ "ፍጡር ከፈጣሪ ጋር ተስተካከ እና ተቆራኘ፥ ፈጣሪ ከፍጡር ጋር ጋር ተስተካከ እና ተቆራኘ" ማለት ትልቁ ሺርክ ነው።
እውነት ነው! "ፈጣሪን ፍጡር ነው፥ ፍጡር ፈጣሪ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፥ መሢሑ ኢየሱስ ያስተማረው፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ» የሚል ነው። እነሆ! በአሏህ የሚያጋራ ሰው አሏህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፦
5፥72 እነዚያ «አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አል መሢሕም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩ፡፡» እነሆ! በአሏህ የሚያጋራ ሰው አሏህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

ሙሽሪክ መኖሪያውም እሳት ናት፥ የአሏህን የአምልኮ ገንዘብ ለፍጡር ማጋራት በአሏህ ሐቅ ላይ የሚፈጸም ታላቅ በደል ነውና ለበዳዮችም ከእሳት ቅጣት የሚያስጥላቸው ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም