ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የካፊር ፍቅር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥165 *”ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን በትንሣኤ ቀን ባዩ ጊዜ ኀይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መኾኑን እና አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን በዚህ ዓለም ቢያውቁ ኖሮ ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ ۗ وَلَوْ يَرَى الَّذِينَ ظَلَمُوا إِذْ يَرَوْنَ الْعَذَابَ أَنَّ الْقُوَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا وَأَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعَذَابِ

አንዲት እንቁራሪት በውኃ ውስጥ ትኖር ነበር፥ ከእለታት አንድ ቀን ከውኃ ስትወጣ ውኃ ውስጥ ያላየችውን ሕይወት ማየት ጀመረች። ፀሐይን፣ አቧራውን፣ ድንጋዩን ስታገኝ ከውኃው የተሻለ ሕይወት መሰላት፥ ወደ መንገድ ስትወጣ እላይዋ ላይ የነበረው ውኃ ቀስ በቀስ ሲደርቅ እያቃጠላት መጣ። ያንን የቀድሞ ሕይወቷን አስታወሳት፥ አይ ልመለስ ስትል የተጓዘችበት መንገድ እሩቅ ስለሆነ መንገድ ላይ እያለች ሞተች። ይህ ሕይወት ከኢሥላም ሕይወት ወጥተው በካፊር ፍቅር ለተነደፉ እና ለሚነደፉ ሁሉ ይመለከታል። አንዳንዶች ከኢሥላም እንደወጡ አካባቢ የዱንያው ነገር ይጥማቸው እና ወደ ዲኑል ኢሥላም ለመመስ መንገዱ እሩቅ ይሆንና ተውበት ሳያረጉ ሞት ይቀድማቸው። ይህ ዲንያን መምረጥ እና አኺራን መተው ነው፥ “ዱንያ” دُّنْيَا ማለት “ቅርቢቱ” ማለት ሲሆን የምንኖርበት ይህንን ዓለም ያመለክታል፥ “አኺራህ” آخِرة ማለት “መጨረሻይቱ” ማለት ሲሆን የሚቀጥለውን ዓለም ያመለክታል፦
2፥86 *”እነዚህ እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት በመጨረሻይቱ አገር የገዙ ናቸው፡፡ ከእነሱም ቅጣቱ አይቀልላቸውም፤ እነርሱም አይረዱም*፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ اشْتَرَوُا الْحَيَاةَ الدُّنْيَا بِالْآخِرَةِ ۖ فَلَا يُخَفَّفُ عَنْهُمُ الْعَذَابُ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቅርቢቱ” ለሚለው ቃል የገባው “ዱንያ” دُّنْيَا ሲሆን “መጨረሻይቱ” ለሚለው ቃል ደግሞ የገባው “አኺራህ” آخِرة ነው። እነማን ናቸው እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት በመጨረሻይቱ አገር የገዙ? ስንል ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን አላህን እንደሚወዱ ባላንጣዎችን የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ ናቸው፦
2፥165 *”ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን በትንሣኤ ቀን ባዩ ጊዜ ኀይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መኾኑን እና አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን በዚህ ዓለም ቢያውቁ ኖሮ ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ ۗ وَلَوْ يَرَى الَّذِينَ ظَلَمُوا إِذْ يَرَوْنَ الْعَذَابَ أَنَّ الْقُوَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا وَأَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعَذَابِ

እንግዲህ ከአላህ አስበልጦ ለዲንያ ተብሎ ካፊርን አፍቅሮ ከአላህ ፍቅር የካፊር ፍቅር በልጦበት አኺራውን የሚያጣ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን በዚህ ዓለም ቢያውቁ ኖሮ ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር። እነዚያ የቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ ሕይወት ይበልጥ የሚወዱ ከአላህም መንገድ የሚያግዱ መጥመሟንም የሚፈልጉዋት ናቸው፥ እነዚያ በሩቅ ስሕተት ውስጥ ናቸው፦
14፥3 *እነዚያ የቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ ሕይወት ይበልጥ የሚወዱ ከአላህም መንገድ የሚያግዱ መጥመሟንም የሚፈልጉዋት ናቸው፡፡ እነዚያ በሩቅ ስሕተት ውስጥ ናቸው*፡፡ الَّذِينَ يَسْتَحِبُّونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا عَلَى الْآخِرَةِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا ۚ أُولَـٰئِكَ فِي ضَلَالٍ بَعِيدٍ

እህቴ ሆይ! ዱንያ ላይ የምትኖሪው ሕይወት አጭር ነው፥ ምናልባት ደስታ አግኝቼበታለው ካልሽ ጊዚያዊ ደስታ ነው። ወደ አላህ በተውበት ተመለሺ፥ ከመነሻው ካፊር ወንድ ጋር ምን ታረጊያለሽ? ዱንያ እኮ ጨዋታ፣ ዛዛታ፣ ማጌጫም እና በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቂ፦
57፥20 *ቅርቢቱ ሕይወት ጨዋታ፣ ዛዛታ፣ ማጌጫም እና በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቁ፡፡ እርሷ በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ብጤ ናት፣ በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አለ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም*፡፡ اعْلَمُوا أَنَّمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِي الْأَمْوَالِ وَالْأَوْلَادِ ۖ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ الْكُفَّارَ نَبَاتُهُ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَاهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَامًا ۖ وَفِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانٌ ۚ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ

ዲንያ ልክ በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ብጤ ናት፣ በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት አለ። ካፊሮች የሚወዱሽ አይምሰልሽ፥ ሃይማኖታቸውን እስከምትከተይ ድረስ ከአንቺ ፈጽሞ አይወዱም፦
2፥120 *አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም*፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ

አላህ ሁላችንንም ሂዳያ ይስጠን፥ በዲኑል ኢሥላም ያጽናን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ንግሥና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

76፥20 *"እዚያም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋን እና ታላቅ ንግሥናን ታያለህ"*፡፡ وَإِذَا رَأَيْتَ ثَمَّ رَأَيْتَ نَعِيمًا وَمُلْكًا كَبِيرًا

"መሊክ" مَلِك የሚለው ቃል "መለከ" مَلَكَ ማለትም "ነገሠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጉሥ" ማለት ነው፥ የንጉሥ ንግሥና ደግሞ "ሙልክ" مُلْك ይባላል። አምላካችን አሏህ የፍጥረት ሁሉ ንጉሥ ነው፥ የሰማያትና የምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፦
114፥2 *"የሰዎች ሁሉ ንጉሥ በኾነው"*፡፡ مَلِكِ النَّاسِ
5፥120 *"የሰማያትና የምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው"*፡፡ لِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا فِيهِنَّ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

የእርሱ ንግሥና በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆን ስለሆነ በሰማያትና በምድር በውስጣቸውም ባሉት ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው፥ ይህንን ንግሥና የሚጋራው ማንም ምንም የለም። ይህንን እውነተኛ ንግሥና በውድም ሆነ በግድ የትንሳኤ ቀን ለእርሱ ብቻ ነው፦
25፥2 *"እርሱ ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ የኾነ፣ ልጅንም ያልያዘ፣ በንግሥናውም ተጋሪ የሌለው፣ ነገሩንም ሁሉ የፈጠረ እና በትክክልም ያዘጋጀው ነው*፡፡ الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُن لَّهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ فَقَدَّرَهُ تَقْدِيرًا
25፥26 *"እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልራሕማን ብቻ ነው"*፡፡ በከሓዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡ الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ لِلرَّحْمَـٰنِ ۚ وَكَانَ يَوْمًا عَلَى الْكَافِرِينَ عَسِيرًا

የአሏህ ንግሥና እና የፍጡራን ንግሥና ይለያያል፥ የአሏህ ንግሥና መነሻ የሌለው ቀዳማይ መጨረሻ የሌለው ደኃራይ ነው። የሰው ንግሥና ግን ተቀዳሚና ተከታይ ያለው ጊዚያዊ ጠፊ ነው፥ አምላካችን አሏህ ሰው በእንስሳ ላይ ንጉሥ እንዲሆን ፈጥሮታል፦
36፥71 *"እኛ እጆቻችን ከሠሩት ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው"*፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَا أَنْعَامًا فَهُمْ لَهَا مَالِكُونَ

"ባለ መብቶች" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ማሊኩን" مَالِكُون ሲሆን "ማሊክ" مَالِك ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ "ሚም" م በመድ ባለ ሁለት ሐረካት ሚም ፈትሓህ አሊፍ ስኩን “ማ” مَا ተብሎ የሚነበበው "ማሊክ" مَالِك እራሱ "ሚም" م ባለ አንድ ሐረካህ ሚም ፈትሓህ “መ” مَ ሲሆን "መሊክ" مَلِك ይሆናል። "መሊክ" مَلِك ማለት "ንጉሥ" ማለት ሲሆን ሰው የእንስሳ ንጉሥ ነው። ይህ ንግሥና ጊዜአዊ እና ሰው ሲሞት አብሮ የሚጠፋ ነው፥ ነገር ግን ሸይጧን አደምን፦ "በማይጠፋ ንግሥናም ላይ ላመላክትህን" አለው፦
20፥120 ሰይጣንም ወደ እርሱ ጎተጎተ «አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ እና *"በማይጠፋ ንግሥናም ላይ ላመላክትህን አለው"*፡፡ فَوَسْوَسَ إِلَيْهِ الشَّيْطَانُ قَالَ يَا آدَمُ هَلْ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ الْخُلْدِ وَمُلْكٍ لَّا يَبْلَىٰ

የማይጠፋ ንግሥና የአሏህ ንግሥና ወይም በትንሳኤ ቀን በጀነት ውስጥ ያለው ታላቅ ንግሥና ነው፦
76፥20 *"እዚያም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋን እና ታላቅ ንግሥናን ታያለህ"*፡፡ وَإِذَا رَأَيْتَ ثَمَّ رَأَيْتَ نَعِيمًا وَمُلْكًا كَبِيرًا

አደም በእንስሳት ላይ ያለውን ንግሥና ጊዜአዊ እና የሚጠፋ ስለሆነ ሸይጧን ግን "ይህንን ዛፍ ብትበሉ የማይጠፋ ንግሥና ታገኛላችሁ" ብሎ አታለላቸው።
አምላካችን አሏህ ከነቢያት መካከል ለዩሱፍ፣ ለዳውድ እና ለሱለይማን ንግሥና ሰጥቷል፦
12፥101 *«ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ»* አለ፡፡ رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ
2፥251 በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ፡፡ *"ንግሥናን እና ጥበብንም (ነቢይነትን) አላህ ሰጠው"*፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ وَآتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ وَالْحِكْمَةَ
38፥35 «ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ማር፡፡ ከእኔ በኋላ *ለአንድም የማይገባንም ንግሥና ስጠኝ*፡፡ አንተ ለጋሱ አንተ ብቻ ነህና» አለ፡፡ قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَهَبْ لِي مُلْكًا لَّا يَنبَغِي لِأَحَدٍ مِّن بَعْدِي ۖ إِنَّكَ أَنتَ الْوَهَّابُ

ለኢብራሂምም ቤተሰቦች ታላቅንም ንግሥና ሰጥቷል፦
4፥54 *"ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍን፣ ጥበብን እና በእርግጥ ሰጠን ታላቅንም ንግሥና ሰጠናቸው"*፡፡ فَقَدْ آتَيْنَا آلَ إِبْرَاهِيمَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَآتَيْنَاهُم مُّلْكًا عَظِيمًا
5፥20 *"ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ እና ነገሥታትንም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»*። وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

“ኢዝ” إِذْ በሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ ውስጥ “ኡዝኩሩ” اذْكُرُوا ማለትም "አስታውሱ" የሚለው ትእዛዛዊ ግን ሙስተቲር ሆኖ ይመጣል። “ኢዝ” إِذْ በሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ መጪውን ጊዜ ካመለከተ ወደፊት ነገሥታት ባደረገ ጊዜ አስታውሱ! ማለት ሲሆን ትንቢት ነው፥ ከሙሳ በኃላ ነገሥታት እንደሚመጡ አመላካች ነው። ለእነዚህ ነገሥታት ሆነ ለምድር ነገሥታት ንግሥና የሚሰጥ እና ሲሞቱ የሚነሳ የነገሥታት ንጉሥ አሏህ ነው፦
3፤26 በል፡- *«የንግሥና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና»* قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَاءُ ۖ بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

አምላካችን አሏህ በጀናህ ታላቅ ንግሥናን ከሚያዩ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ደርሱ በድምፅ ቀጥሏል። ላይክ፣ ሼር እና ሰብስክራይብ በማድረግ የደርሱን ተደራሽነት ያስፉ! ይህንን በማስፈንጠር ያዳምጡ፦ https://youtu.be/vWeA9z3Fz00
ለዲያብሎስ እርድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ አዘዝናቸው፡፡ አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۗ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

“መንሠክ” مَنسَك ማለት “መስዋዕት” ወይም “ሥርዓተ ሃይማኖት” ማለት ሲሆን “ሀድይ” هَدْي ማለት “የእርድ እንስሳ” ማለት ነው፤ ይህም እርድ ጊደር፣ በግ፣ ፍየል፣ ጥጃ፣ ግመል ነው፤ ይህ ለአላህ የሚቀርበው መስዋዕት “ቁርባን” ይባላል፤ “ቁርባን” قُرْبَان የሚለው ቃል “ቀርረበ” قَرَّبَ ማለትም “አቀረበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መቃረቢያ” “አምሃ” “እጅ መንሻ” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ለሕዝብም ሁሉ ወደ እርሱ መስዋዕት ማቅረብን አዟል፦
22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ አዘዝናቸው፡፡ አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۗ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

ይህ ሆኖ ሳለ ግን በባይብል ላይ መስዋዕት ለሁለት ምንነቶች እንዲቀርብ ታዟል፤ አንዱ ለፈጣሪ ሲሆን ሁለተኛው ለዲያብሎስ ነው፦
ዘሌዋውያን 16፥8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ *አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ ለዐዛዝኤል*።

ዕብራይስጡ፦
וְנָתַן אַהֲרֹן עַל-שְׁנֵי הַשְּׂעִירִם, גֹּרָלוֹת–גּוֹרָל אֶחָד לַיהוָה, וְגוֹרָל אֶחָד לַעֲזָאזֵל.
ዐረቢኛው፦
وَيُلْقِي هَارُونُ عَلَى التَّيْسَيْنِ قُرْعَتَيْنِ: قُرْعَةً لِلرَّبِّ وَقُرْعَةً لِعَزَازِيل
ኢንግሊሹ፦
“There he shall draw lots, using two stones, one marked *”for the LORD”* and the other *”for Azazel*.”(Good News Translation)

ሁለት ፍየል እጣ ይጣልበታል፤ አንዱ ለያህዌህ ሁለተኛ ለዐዛዝኤል ነው፤ ተርጓሚዎች “ዐዛዝኤል” የሚለው ቃል “መለቀቅ” “የምድረ-በዳ ፍየል” እያሉ ትርጉሙን ሊያዛቡ ቢፈልጉም የዕብራይስጡ “ዐዛዝኤል” עֲזָאזֵל የዐረቢኛው “ዐዛዚል” عَزَازِيل ብሎ በግልጽ አስቀምጦታል፤ “ዐዛዝኤል” ታዲያ ማን ነው? የጥንት ሆነ የአሁን የባይብል ማብራሪያዎች ጋኔን ነው ብለው አስቀምጠውታል፤ ይህ ጋኔን ስሙ በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ከሃያ አንዱ አጋንንት አስረኛው ጋኔን ዐዛዝኤል ነው፦
ሄኖክ 19፥10-12 *የእነዚያ የአጋንንት ስማቸው እንደዚህ ነው*፦
አለቃቸው ስማዝያ፣ ሁለተኛውም አርስጢኪፋ ነው፣ ሥስተኛውም አርሚን ነው፣ አራተኛውም ኮክብኤል ነው። አምስተኛውም ጡርኤል ነው፣ ስድስተኛውም ሩምያል ነው፣ ሰባተኛውም ዳንኤል ነው፣ ስምንተኛውም ምቃኤል ነው፣ ዘጠነኛውም በራቃኤል ነው፣ *አስረኛውም “አዛዝኤል” ነው*፣ አስራ አንደኛውም አርማሮስ ነው፣ አስራ ሁለተኛውም በጠርያል ነው*።
ሄኖክ 3፥10 *በዐዛዝኤል ሥራና ትምህርት ምድር ሁሉ ጠፋች፤ የሰውን ሁሉ ኃጢአት በእርሱ ጻፍበት አለው*።
ሄኖክ 15፥7 *በአዛዝኤል ይፈረድበታል፤ በወገኖችሁ ሁሉ፤ በመላእክት ጌታ ስም ባላመኑ በሰራዊቱም ሁሉ ይፈረድባቸዋል*።

ዐዛዝኤል በግዕዝ ትውፊታዊ አጠራሩ “ሳጥናኤል” ይባላል፤ ይህም ሳጥናኤል ዲያብሎስ ነው። ከሥነ-አምክኖ አንጻር እስቲ እዩት አንዱ ለፈጣሪ ሁለተኛው ለመለቀቅ ወይም ለምድረ-በዳ ፍየል ይገበርለት እንበልና፤ ለምንስ ለመለቀቅ ወይም ለምድረ-በዳ ፍየል ይገበራል? ከያህዌህ በስቀር ለሌላ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ ተብሏል እኮ፦
ዘጸአት 22፥20 *ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ*።

ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትና ምንነት መስዋዕት መሰዋት ይህንን ያክል ከባድ ወንጀል ከሆነ እንግዲያውስ ለሳጥናኤል የፍየል መስዋዕት አቅርብ የሚለውን የብርዘት ውጤት ትታችሁ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ብቻ እንድትሰዉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፤ ሙስሊም መስዋዕቱ ለፈጠረው ብቻ ነው፦
6፥162 *«ሶላቴ፣ “መስዋዕቴም”፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው»* በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዐዛቡል ቀብር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

35፥38 *"አላህ የሰማያትንና የምድርን የሩቅ ነገር ምስጢር በእርግጥ ዐዋቂ ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ عَالِمُ غَيْبِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ

"ዐዛብ" عَذَاب የሚለው ቃል "ዐዘበ" عَذَّبَ ማለትም "ቀጣ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቅጣት" ማለት ነው። "ቀብር" قَبْر የሚለው ቃል "ቀበረ" قَبَرَ ማለትም "ሸፈነ" "ደበቀ" "ሸሸገ" "ቀበረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቀብር" ማለት ነው፥ የቀብሩ ሥፍራ ደግሞ በነጠላ "መቅበራህ" مَقْبَرَة በብዜት "መቃቢር" مَقَابِر ሲሆን "መቃብር" ማለት ነው። በጥቅሉ "ዐዛቡል ቀብር" قَبْر العَذَاب ማለት "የቀብር ቅጣት" ማለት ነው።
"ቀብር" አጠቃላይ ከሞት በኃላ ከአምስቱ የስሜት ህዋሳት ባሻገር ተሸፍኖ፣ ተደብቆ፣ ተሸሽጎ ያለ ሁኔታ ሲሆን፥ እዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለው ቅጣት ለእኛ "አል-ገይብ" ነው። “አል-ገይብ” ٱلْغَيْب ማለት “የሩቅ ነገር ምሥጢር” ማለት ነው። የቀብር ቅጣት በምድር ያለ የሩቅ ነገር ምሥጢር ነው፥ ይህንን የምድር የሩቅ ነገር ምሥጢር አሏህ ብቻ ሁሉን ዐዋቂ ነው፦
35፥38 *"አላህ የሰማያትንና የምድርን የሩቅ ነገር ምስጢር በእርግጥ ዐዋቂ ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ عَالِمُ غَيْبِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ
11፥123 በሰማያትና በምድርም ያለው የሩቅ ነገር ምስጢር ሁሉ የአላህ ነው፡፡ وَلِلَّهِ غَيْبُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ
49፥18 *"አላህ የሰማያትንና የምድርን የሩቅ ነገር ምሥጢር ያውቃል"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ

“ኢሥቲዓዛህ” إِسْتِعَاذَة የሚለው ቃል “ኢሥተዓዘ” اِسْتَعَاذَ ማለትም “ተጠበቀ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መጠበቅ” ማለት ነው። ይህም መጠበቅ “አዑዙ ቢሏህ" أَعُوذُ بِاللَّه ማለትም "በአሏህ እጠበቃለው" ነው፥ የቀብር ቅጣት ባይኖር ኖሮ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ከቀብር ቅጣት ኢሥቲዓዛህ አያረጉም ነበር፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 5, ሐዲስ 169
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" ከቀብር ቅጣት፣ ከጀሀነም ቅጣት እና ከደጃል ፈተና በአሏህ ይጠበቁ ነበር"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ كَانَ يَتَعَوَّذُ مِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ وَعَذَابِ جَهَنَّمَ وَفِتْنَةِ الدَّجَّالِ ‏.‏

ሚሽነሪዎች፦ "ሰው ከሞተ እና ከፈረሰ በኃላ እራሱ በመዶሻ ሲመታ የሩሕ ቅጣት እንዴት ይባላል? ምክንያቱም መዶሻ፣ እሳት፣ ለቅሶ፣ ህመም ወዘተ ያለው በሕይወት ላለ ነው" ብለው ይጠይቃል። አንደኛ ይህ ገይብ ነው፣ ሁለተኛ ሩሕ ምን አይነት ባሕርይ እንዳለው የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ነው፣ ሦስተኛ በባይብልም እኮ የቀብር ቅጣት አለ። ሰው ከሞተ በኃላ ልጆቹ ቢከብሩ ዐያውቅም፤ ቢዋረዱም ዓያይም፥ ነገር ግን የገዛ ሥጋው ሕመም ብቻ ይሰማዋል። ለራሱም ብቻ ያለቅሳል፦
ኢዮብ 14፥21 *ልጆቹ ቢከብሩ ዐያውቅም፤ ቢዋረዱም ዓያይም። ነገር ግን የገዛ ሥጋው ሕመም ብቻ ይሰማዋል፥ ለራሱም ብቻ ያለቅሳል"*።
ሉቃስ 16፥23-24 *"በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ። እርሱም እየጮኸ፦ አብርሃም አባት ሆይ፥ ማረኝ፥ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ" አለ"*።

ልብ አድርግ! ሰው አካሉ ከፈረሰ በኃላ ጣት፣ ምላስ፣ ውኃ፣ የእሳት ነበልባል ተጠቅሰዋል። ጣት፣ ምላስ፣ ውኃ፣ የእሳት ነበልባል እማራዊ ሳይሆኑ ፍካሬአዊ ከሆኑ መዶሻ፣ እሳት፣ ለቅሶ፣ ህመም ወዘተ እማራዊ ሳይሆኑ ፍካሬአዊ ናቸው። "ሲኦል" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሼኦል" שְׁאוֹל‎ ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን "መቃብር" ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 44፥29 *"ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱት ክፋም ቢያገኘው፥ ሽበቴን በኅዘን ወደ "መቃብር" ታወርዱታላችሁ"*። וּלְקַחְתֶּ֧ם גַּם־אֶת־זֶ֛ה מֵעִ֥ם פָּנַ֖י וְקָרָ֣הוּ אָסֹ֑ון וְהֹֽורַדְתֶּ֧ם אֶת־שֵׂיבָתִ֛י בְּרָעָ֖ה שְׁאֹֽלָה

እዚህ አንቀጽ ላይ "መቃብር" ለሚለው የገባው ቃል "ሼኦላህ" שְׁאֹֽלָה መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "መቃብር" ለሚለው በ 280 ቅድመ-ልደት"BC" ግሪክ ሰፕቱአጀንት"LXX" ከዕብራይስጡ ወደ ግሪክ ኮይኔ ሲተረጉሙ "ሐዴስ" ᾅδης ብለው ተርጉመውታል፦
ዘፍጥረት 44፥29 *"ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱት ክፋም ቢያገኘው፥ ሽበቴን በኅዘን ወደ "መቃብር" ታወርዱታላችሁ"*። ἐὰν οὖν λάβητε καὶ τοῦτον ἐκ τοῦ προσώπου μου καὶ συμβῇ αὐτῷ μαλακία ἐν τῇ ὁδῷ, καὶ κατάξετέ μου τὸ γῆρας μετὰ λύπης εἰς ᾅδου.

የሉቃስ 16፥23 ጸሐፊም "ሲኦል" ለሚለው ቃል በግሪክ ኮይኔ "ሐዴስ" ᾅδης ብሎታል፦
ሉቃስ 16፥23 *"በሲኦልም" በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ"*። καὶ ἐν τῷ ᾅδῃ ἐπάρας τοὺς ὀφθαλμοὺς αὐτοῦ, ὑπάρχων ἐν βασάνοις, ὁρᾷ Ἀβραὰμ ἀπὸ μακρόθεν καὶ Λάζαρον ἐν τοῖς κόλποις αὐτοῦ.

በነገራችን "ሐዴስ" ᾅδης በግሪክ ሥነ-ተረት"mythology" ውስጥ "የታችኛው ዓለም አምላክ" ነው፥ ይህ ቃል በኃላ ላይ "መቃብር" ለሚለው አገልግሎት ላይ ዋለ። ሆነም ቀረ መቃብር የተባለው "ሲኦል" እና "ገሃነም" ሁለት የተለያየ ነገር ናቸው፥ በፍርድ ቀን ሲኦል እራሱ ወደ ገሃነም ይጣላል፦
ራእይ 20፥14 *"ሞት እና "ሲኦልም" በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው"*።

"ሲኦል" መቃብር ከሆነ መቃብር ውስጥ በሥቃይ እየጮኸ፦ "በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ" ካለ በእርግጥም የቀብር ቅጣት አለ። የራሳችሁን ባይብል ሳታዩ በኢሥላም ያለውን የቀብር ቅጣት እሳቤ መንቀፍ ማለት ማርን አምርሮና ወተትን አጥቁሮ ማሩ ይመራል፥ ወተቱ ጥቁር ነው እንደ ማለት ነው፥ ይህ ደግሞ ዐቅል አልባ ዘንባጣነት ነው። አሏህ ከቀብር ቅጣት ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መጅኑን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

89፥22 *"ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም"*፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ

"ጁኑን" جُنُون የሚለው ቃል "ጁነ" جُنَّ‎ ማለትም "ዐበደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዕብደት" ማለት ነው፥ ዕብደት ያለበት ዕብድ ደግሞ "መጅኑን" مَجْنُون‎ ይባላል። "መጅኑን" مَجْنُون‎ በቋንቋ ደረጃ "ጀነ" جَنَّ‎ ማለትም "ሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ዐቅሉ "የተሰወረ" "የተደበቀ" ማለት ነው፥ እሩቅ ሳንሄድ ማኅፀን ውስጥ ያለውን “ሽል” ለዓይናችን የተደበቀ ስለሆነ “አጂናህ” أَجِنَّة ማለትም “ስውር” ወይም “ድብቅ” ተብሏል፦
53፥32 *ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ማኅፀኖች ውስጥ “ሽሎች” በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በእናንተ ሁኔታ ዐዋቂ ነው*፡፡ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَإِذْ أَنتُمْ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ ۖ فَلَا تُزَكُّوا أَنفُسَكُمْ

እዚህ ድረስ ከተግባባን አንድ የአሏህ መልእክተኛ ሲመጣ የመጣበት ማኅበረሰብ፦ "መጅኑን" ነው" ይሉታል፦
51፥52 ነገሩ እንደዚሁ ነው፡፡ *እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልክተኛ ማንም አልመጣቸውም፥ እርሱን «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» ያሉ ቢኾኑ እንጂ*፡፡ كَذَٰلِكَ مَا أَتَى الَّذِينَ مِن قَبْلِهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا قَالُوا سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ

አምላካችን አላህ ከተረከን የሩቅ ነገር ወሬ አንዱ ኑሕ፣ ሙሣ ወዘተ በማኅበረሰቡ "ዕብድ" መባላቸውን ነው፦
54፥9 *ከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፥ ባሪያችን ኑሕንም አስተባበሉ፡፡ «ዕብድ ነውም» አሉ*፡፡ ተገላመጠም፡፡ كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ فَكَذَّبُوا عَبْدَنَا وَقَالُوا مَجْنُونٌ وَازْدُجِرَ
26፥27 *ፈርዖንም፦ «ያ ወደ እናንተ የተላከው መልክተኛችሁ በእርግጥ ዕብድ ነው» አለ*፡፡ قَالَ إِنَّ رَسُولَكُمُ الَّذِي أُرْسِلَ إِلَيْكُمْ لَمَجْنُونٌ

ነቢያችን”ﷺ” ሲመጡ በዛ ጊዜ የነበሩት ሕዝቦች፦ "ዕብድ" ብሏቸዋል፥ አምላካችን አላህም፦ "ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም" በማለት እና ለራቸውም በሁለተኛ መደብ፦ "አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም" ብሎ መልሶ ሰጥቷል፦
15፥6 «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ» አሉም፡፡ وَقَالُوا يَا أَيُّهَا الَّذِي نُزِّلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ
89፥22 *"ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም"*፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ
68፥2 *"አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም"*፡፡ مَا أَنتَ بِنِعْمَةِ رَبِّكَ بِمَجْنُونٍ

አንድ ሕዝብ አንድን ነቢይ "መጅኑን" ነው" ስላለ ያ ነቢይ መጅኑን የሚሆን ከሆነ እንግዲያውስ መጅኑን መሆን የነበረበት ኢየሱስ ነበር፥ ምክንያቱም ዘመዶቹም ሰምተው፦ "አበደ" ብለዋልና ሊይዙት ወደነበረበት ተራራ ወጡ፦
ማርቆስ 3፥21 *"ዘመዶቹም ሰምተው፦ "አበደ" ብለዋልና ሊይዙት ወጡ"*። وَلَمّا سَمِعَتْ عائِلَةُ يَسُوعَ عَنْ مَجيئِهِ، جاءُوا لِيَأخُذُوهُ مَعَهُمْ، لِأنَّ النّاسَ كانُوا يَقُولُونَ إنَّهُ مَجنُونٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አበደ" ለሚለው የገባው ቃል "መጅኑን" مَجنُون መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ዘመዶቹ "አበደ" ብለው ሊይዙት ስለ ወጡ ኢየሱስ አብዶ ነበር እንዴ? አይ "አንድ ሕዝብ አንድን ነቢይ "መጅኑን" ነው" ስላለ ያ ነቢይ መጅኑን ነው ማለት አይደለም" ካላችሁን እንግዲያውስ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርምና ነቢያችን”ﷺ” ሲመጡ በዛ ጊዜ የነበሩት ሕዝቦች፦ "ዕብድ" ስላላቸው እርሳቸው ዕብድ ነበሩ አይሰኝም ማለት ነው። የነቢያችንን”ﷺ” ነቢይነት ለማስተባበል ያመጣችሁት መስፈርት ስሑት ሙግት ስለሆነ ፉርሽ ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥራ ሁለቱ ነገዶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

“ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “አውሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ይህንን እስቲ ከቁርአን እንመልከት፦
66፡3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ *ይህን ማን “ነገረህ”? አለች፤ ዐዋቂው ውስጠ አዋቂው “ነገረኝ” አላት*። وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِ وَأَظْهَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُ وَأَعْرَضَ عَنْ بَعْضٍ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِ قَالَتْ مَنْ أَنْبَأَكَ هَذَا قَالَ نَبَّأَنِيَ الْعَلِيمُ الْخَبِيرُ ፤

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን “ነገረኝ” ለሚለው ደግሞ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ነው፤ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነበአ” نَبَّأَ የሚለው ቃል ነው፤ ስለዚህ ነቢይ ማለት ሁሉን ዐዋቂውና ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው፤ በዚህ ስሌት አሥራ ሁለቱ ነገዶች በሙሳ ዘመን በኢስራኢል ልጆች የተነሱ ነቢያት ናቸው፦
5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

“በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ ጊዜ” የሚለው ይሰመርበት፤ እነዚህ ነብያት ነገዶቹ ናቸው፤ አላህ ወደ ነገዶቹ ወሕይ አውርዷል፦
4፥163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ *ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
3፥84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ *በነገዶችም ላይ በተወረደው*፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው አመንን፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «በአላህና ወደኛ በተወረደው፣ ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብ እና *ወደ ነገዶቹም በተወረደው* በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
አላህ ወሕይ የሚወርድላቸውን እነዚህን ነገዶች አሥራ ሁለት አለቆች አድርጎ አስነሳቸው፤ ለአሥራ ሁለትም ሕዝቦች ከፋፈላቸው፦
5፥12 *አላህም የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው፡፡ ከእነርሱም አሥራ ሁለትን አለቆች አስነሳን*፡፡ وَلَقَدْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَبَعَثْنَا مِنْهُمُ اثْنَيْ عَشَرَ نَقِيبًا
7፥160 *አሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው*፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ መታውም *ከእርሱ አሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ*፡፡ وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ إِذِ اسْتَسْقَاهُ قَوْمُهُ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَرَ ۖ فَانبَجَسَتْ مِنْهُ اثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا

ጥንት የአሥራ ሁለቱ አበው የቃልኪዳን መጽሐፍ የነበረ ሲሆን አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ ውሳኔ የአፓክራፋ መጽሐፍ ብለው ቀንሰውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ብዙውን የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛውን በእርግጥ ልኳል፦
5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

“አፓክራፋ” የሚለው ቃል “አፓክራፈስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት አስፈላጊውን አላህ የገለጸ ሲሆን ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት ብዙውን ትቶታል፤ ወደ ነብያት ምን ተወርዶ እንደነበረ መልእክተኛው እንዲገልጹ ቁርኣንን አውርዷል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ *ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን*፡፡ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

ይህ ቁርኣን ከበፊቱ ከአላህ የተወረዱትን የአላህ ንግግሮች የሚያረጋግጥ እና በእነዚያ ንግግሮች ውስጥ ያለውን ጭብጥ የሚዘረዝር ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፤ *ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَمَا كَانَ هَـٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእግዚአብሔር ባሕርያት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

እግዚአብሔር ክፉን መንፈስን፣ የስሕተትን አሠራር፣ ጨለማን እና ክሳትን እንደሚልክ ባይብል ይናገራል፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
መዝሙር 105፥28 *ጨለማን ላከ* ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።
መዝሙር 106፥15 የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን *ክሳትን ላከ*።

ይሄ ክፉም መንፈስ እንደ ኡቃቤ ከእግዚአብሔር ዘንድ እየተላከ ሳኦልን አሠቃየው፦
1ኛ ሳሙኤል 16፥14 የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ *ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው*።
1ኛ ሳሙኤል 18፥10 በነጋውም ሳኦልን *ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው*፥

ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር ሹራ እያደረገ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል፦
1ኛ ነገሥት 22 20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል*፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።

እግዚአብሔር ሰዎች የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ይሰጣል፦
የሐዋርያት ሥራ 7፥42 እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ *የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው*፥

እግዚአብሔር ሰዎች በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ *እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥26 ስለዚህ *እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን *እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፦
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፦
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።ባይብል ላይ ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ኃይሉ ይገልጥበት ዘንድ እና ስሙ በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ነው፦
ዘጸአት 9፥16 ነገር ግን *ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ*።
ሮሜ 9፥17 መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና።

“ቃሻህ” קָשָׁה ማለት “ማደንደን” ማለት ሲሆን እግዚአብሔር ፈርዖን የእስራኤል ልጆችን እንዳይለቅ እና ሙሴን እንዳይሰማ የፈርዖንን ልብ አደንድኖታል፦
ዘጸአት 7፥3 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ אַקְשֶׁ֖ה * ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።
ዘጸአት 14፥4 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ וְחִזַּקְתִּ֣י * ፥ እርሱም ያባርራቸዋል፤
ዘጸአት 9፥12 እግዚአብሔርም *የፈርዖንን ልብ አደነደነ וַיְחַזֵּ֤ק *፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም።
ዘጸአት 14፥8 እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ *የፈርዖንን ልብ አደነደነ* וַיְחַזֵּ֣ק ፥

እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ልብን ስላደነደነው የፈርዖን ልብ ደነደነ፦
ዘጸአት 7፥13 *እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ የፈርዖን ልብ ደነደነ וַיֶּחֱזַק֙:*፥ አልሰማቸውምም።
ዘጸአት 7፥14 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ *የፈርዖን ልብ ደነደነ*፥ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ።
ዘጸአት 9፥7 ፈርዖንም ላከ፥ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። *የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ*፥ ሕዝቡንም አልለቀቀም።
እውን ፈርዖን ተጠያቂ ነውን? ልቡንስ ካደነደነው ህዝቤን ልቀቅ ብሎ ሙሴና አሮንን መላክ ለምን አስፈለገ? ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ ብሎ ፈርዖንን መውቀስ ለምንችአስፈለገ? በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን መንፈሱን አደንድኖታል፦
ዘዳግም 2፥30 የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ *እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና*፥ ልቡንም አጽንቶታልና።

ለነገሩ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፦
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፦
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።

ነቢዩም ቢታለል ያንን ነቢይ ያታለለው እግዚአብሔር ነው ይላል፤ ሕዝቅኤልን፣ ኤርሚያስን እና ኢሳይያስን ያታለለው እርሱ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፦
ሕዝቅኤል 14:9፤ ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ *ያታለልሁ* እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥
ኤርሚያስ 20:7 አቤቱ፥ *አታለልኸኝ* እኔም ተታለልሁ፥
ኤርሚያስ 4:10 እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ። ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ *አታለልህ* አልሁ።
ኢሳይያስ 63:17 አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን “አሳትኸን”? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የኢየሱስ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአዕምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው፡፡ هَذَا بَلَاغٌ لِلنَّاسِ وَلِيُنْذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ ” سورة إبراهيم

ቁርኣን ከወረደበት ምክንያት አንዱ የአዕምሮ ባለቤቶችም አላህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት ነው፦
14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአዕምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው፡፡ هَذَا بَلَاغٌ لِلنَّاسِ وَلِيُنْذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ ” سورة إبراهيم

ነገር ግን ይህንን አንድ አምላክ አንዴ በማንነት ሶስት ነው፣ አንዴ ሰው ሆነ፣ አንዴ ለሰው ኀጢአት ሞተ እያሉ በነውርና በጎዶሎ ባህርይ ያሻርኩታል፤ ይህ አንድ አምላክ በመለኮታዊ ቅሪት ሲናገር እንዲህ ይላል፦
ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥
ኢሳይያስ 44:6 ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።

አንዱ አምላክ እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም እያለን ተመልሰው “ሰውም አምላክ ነህ” ማለት እኛ ፍጡራን፦ ፈጣሪን “ስለ አንተ ከአንተ ይልቅ እኛ እናውቅልሃለን” እያልነው ነው፤ ነገር ግን ኢየሱስ በአንዱ አምላክ እና በሰዎች መካከል መካከለኛ ሆኖ ከአምላክ ሰምቶ የሚናገር ሰው ነው፤ በድንቆች በምልክቶችም ከአንዱ አምላክ ዘንድ ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው ነበረ፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 አንድ አምላክ Θεοῦ አለና፥ በአምላክ Θεοῦ እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም *ሰው* የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ Θεοῦ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤
የሐዋርያት ሥራ 2:22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላክ Θεοῦ በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከአምላክ Θεοῦ ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤

እንግዲህ ኢየሱስ ሰው ከሆነ እና አንዱ አምላክ የላከው ከሆነ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት የተለያዩ ማንነት እና ምንነት ናቸው ማለት ነው፤ ኢየሱስ የሚያመልከው የራሱ አምላክ አለው፦

ነጥብ አንድ
“አምላኬ”
“አምላኬ” ማለት “የእኔ” አምላክ ማለት ነው፤ “አምላኬ” በሚል የመጀመሪያ መደብ “እኔ” የሚል አገናዛቢ ተውላጠ ስም አለ፤ “የእኔ አምላክ”my God” የሚለው የኢየሱስ ሙሉ እኔነት አምላክ አለው፦
ማቴዎስ 27:46 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፡- ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፡- የእኔ አምላክ የእኔ አምላክ ፥ አንተ እኔን ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። “”My God, my God, why have you forsaken me””.
ዮሐንስ 20:17 ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ “አምላኬ” እና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።

በተለይ ኢየሱስ አንዱን አምላክ “አንተ” እራሱን ደግሞ “እኔ” በማለት “አምላኬ” ማለቱ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት ህልውናዎች መሆናቸው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ “ተውከኝ” ስላለም በተወው ባለቤት እና በተተው ተሳቢ መካከል “ተውከኝ” የሚል ተሻጋሪ ግስ”transitive verb” መኖሩ ኢየሱስን ከአምላኩ ይለየዋል፤ በተጨማሪም “ወደ” የሚለው መስተዋድድ*preposition* መጠቀሙ በሁለት ማንነት መካከል ለመለየት የሚመጣ ነው፣ ኢየሱስ ማርያምን *ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ* ማለቱ ወንድሞቹና ማርያም የተለያየ ማንነት እንዳላቸው እንደሚያሳይ ሁሉ “ወደ አምላኬ አርጋለው” ማለቱ አምላኩና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ህላዌዎች መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ኢየሱስ ካረገም በኃላ አብን አምላኬ ይላል፦
ራእይ 3፥2፤ ሥራህን #በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።
ራእይ 3፥12 ድል የነሣው #በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ #የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ #ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።
ነጥብ ሁለት
“አምላካችን”
ኢየሱስ “ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካችሁ” አለ እንጂ “ወደ አምላካችን” ስላላለ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ አምላክ የሆነበትና ለሃዋርያት አምላክ የሆነበት መደብ ይለያያል ይላሉ፤ ይህ ውሃ የማያነሳ ሙግት ነው፤ አንደኛ ይህ አነጋገር የተለመደ ነው፦
ዘፍጥረት 43፥23 እርሱም አላቸው፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ *አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ* በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁስ ደርሶኛል።

“አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ” ስለተባለ አንዱ አምላክ ለአባታቸው ለያእቆብ እና ለልጆቹ አምላክነቱ ይለያያልን? ሁለተኛ ኢየሱስ “አምላካችን” በሚል አንደኛ መደብ ብዜት ተናግሯል፦
ኢሳይያስ61:1-2 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት “”አምላካችንም”” የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ ልኮኛል፤
ማርቆስ 12:29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ “”አምላካችን”” አንድ ጌታ ነው፥

ነጥብ ሶስት
“አምላክህ”
መዝሙረኛ እግዚአብሔር ለኢየሱስ አምላክ መሆኑን ለማሳየት ” አምላክህ” በማለት በሁለተኛ መደብ ተናግሯል፦
መዝሙር 45:7 ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር “አምላክህ” የደስታ ዘይትን ቀባህ።
ዕብራውያን 1:9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር “አምላክህ” ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ።

ለኢየሱስ ባለንጀሮቹ ሲቀቡ የነበሩት ነብያት ናቸው፤ ክርስቶስ ማለት “የተቀባ” ማለት ሲሆን አምላኩ እግዚአብሔር ኢየሱስን የደስታ ዘይት በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ቀብቶታል፤ ቀቢው አንዱ አምላክ ከሆነ ተቀቢው ሰው ብቻ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 10:38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤

ነጥብ አራት
“አምላኩ”
ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ለማሳየት “አምላኩ” በማለት በሶስተኛ መደብ ተናግረዋል፦
ራእይ 1:6 መንግሥትም “”ለአምላኩ”” እና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥
ሚክያስ 5:4፤ እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል “”በአምላኩ”” በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፤ እነርሱም ይኖራሉ፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።

በተጨማሪም “የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ” በማለት ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ተናግረዋል፦
ኤፌሶን 1:17 የክብር አባት የጌታችን “”የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ”” እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።
2ኛ ቆሮንጦስ1:3 የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
2ኛ ቆሮንጦስ 11:31 ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል።

መደምደሚያ
ኢየሱስ በንግግሩ እራሱን ሁለተኛው የአንዱ አምላክ አባል አድርጎ አስተምሮ አያውቅም። ከዚያ ይልቅ እራሱ ከአንዱ አምላክ ውጪ ያደርግ ነበር፦
ማርቆስ 10:18 ኢየሱስም። ስለ ምን ቸር እኔን ትለኛለህ? ከአንዱ አምላክ በቀር ቸር ማንም የለም።Why callest you me good? there is none good but one, that is , God.
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘላለም ህይወት ናት። (1980 አዲስ ትርጉም)
ዮሐንስ 14:1 ልባችሁ አይታወክ፤ በአምላክ Θεοῦ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
ዮሐ7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ*myself አይደለም፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከአምላክ Θεοῦ ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ*myself የምናገር ብሆን ያውቃል።

አንዳንድ ቂሎች “ኢየሱስ አምላክ አለው ግን ለስጋው ነው” ይሉናል፤ ስጋው ፍጡር እና የራሱ ማንነት ከሆነ በስጋው የሚያመልከው አምላክ ካለው ኢየሱስ አምላኪም ተመላኪም ከሆነ ሁለት አይሆንም ወይ? ሲቀጥል “ስጋ” ብቻውን “እኔ” ይላል ወይ? የሰው ሁለተንተና መንፈሱ፣ ነፍሱ እና ስጋው ናቸው፦
1ኛ ተሰሎንቄ 5:23 የሰላምም አምላክ ራሱ “”ሁለንተናችሁን”” ይቀድስ፤ “መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም፣ ፣ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።”

ኢየሱስ የራሱ መንፈስ ካለው፣ የራሱን መንፈስ ለአንዱ አምላክ ከሰጠ የራሱ መንፈስ ከአንዱ አምላክ ይለያል፦
ዮሐንስ13:21 ኢየሱስ ይህን ብሎ “በመንፈሱ” ታወከ መስክሮም።
ሉቃስ 23:46 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ “መንፈሴን” በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ “መንፈሱን” ሰጠ። NIV

አንዱ አምላክ ደግሞ የመንፈስ ሁሉ አምላክ ከሆነ አንዱ አምላክ የኢየሱስ ሁለንተና አምላክ ነው፦
ዘኊልቅ 16:22 እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው። አምላክ ሆይ፥ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ አምላክ(the God of the spirits of all flesh,)፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን? አሉ።
ዘኊልቅ 27:16፤17፤ የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በፊታቸው የሚወጣውን በፊታቸውም የሚገባውን የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ (the God of the spirits of all flesh) እግዚአብሔር በማኅበሩ ላይ ይሹመው።

ስለዚህ አንዱ ኣምላክ አምላክነቱ ለመንፈሱም ጭምር ከሆነ እና ባይብል ላይ 17 ቦታ ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ከተገለፀ እውነትም ኢየሱስ አምላኪ ፍጡር ነው፤ በእውነት ሊመለክ የሚገባው የኢየሱስ አምላክ ብቻ ነው። አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አላህ መለኮት ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

43፥84 *”እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባ፥ በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው”*፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ዐዋቂው ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي فِي السَّمَاءِ إِلَـٰهٌ وَفِي الْأَرْضِ إِلَـٰهٌ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ

“ሥነ መለኮት”theology” በግሪክ “ቴዎ ሎጊያ” θεολογία ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ “ቴዎስ” Θεός ማለትም “አምላክ” እና “ሎጊያ” λογία ማለትም “ጥናት” ነው። “ቴኢዎስ” θεῖος የሚለው ቃል “ቴዎስ” θεός ማለትም “አምላክ”God” ለሚለው ቃል ገላጭ ቅጽል”adjective” ሲሆን “አምላክነት”God-head” ወይም “መለኮት”Divine” ማለት ነው፥ ይህም ቃል በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ 5 ጊዜ ተጠቅሷል።
ስለዚህ “መለኮት” ማለት በቋንቋ ደረጃ በቀላሉ “አምላክ” ማለት ነው። አምላካችን አላህ”ﷻ” “መለኮት” ነው፦
43፥84 *”እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባ፥ በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው”*፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ዐዋቂው ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي فِي السَّمَاءِ إِلَـٰهٌ وَفِي الْأَرْضِ إِلَـٰهٌ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ
6፥3 *”እርሱም ያ በሰማያትና በምድር ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው”*፡፡ ምስጢራችሁን ግልጻችሁንም ያውቃል፡፡ የምትሠሩትንም ሁሉ ያውቃል፡፡ وَهُوَ اللَّهُ فِي السَّمَاوَاتِ وَفِي الْأَرْضِ ۖ يَعْلَمُ سِرَّكُمْ وَجَهْرَكُمْ وَيَعْلَمُ مَا تَكْسِبُونَ

“ኢላህ” إِلَـٰه የሚለው ቃል “መለኮት” ወይም “አምላክ” ማለት ነው። “ኢላሂይ” إِلٰهِيّ‎ ማለት “መለኮታዊ” ወይም “አምላካዊ” ማለት ሲሆን “ኡሉሂያህ” أُلُوهِيَّة‎ ማለት ደግሞ “አምላክነት” ማለት ነው። “ኢላሂያት” إِلٰهِيَّات‎ ማለት በራሱ “ሥነ-መለኮት” ማለት ነው። አላህ ብቻውን አንድ መለኮት ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ መለኮት የለም፦
4፥171 *አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ سُبْحَانَهُ أَن يَكُونَ لَهُ وَلَدٌ ۘ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا
6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው*፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَإِنَّنِي بَرِيءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ
2፥163 *”አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም”*፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ

“መለኮት” ማለት “ሁሉን ነገር ማድረግ የሚችል” “ሁሉን ነገር የሚያውቅ” “ሁሉን ነገር የሚያይ” “ሁሉን ነገር የሚሰማ” “በባዶነት መነሻ በሞት መዳረሻ የሌለው ሕያው” ማለት ነው። አንተ ምንድን ነህ? ብባል “ሰው ነኝ” ብዬ የሰው ባሕርያት ተራቢ ነኝ፣ ተጠሚ ነኝ፣ በዪ ነኝ፣ ጠጪ ነኝ ወዘተ እያልኩኝ እናገራለን፥ አላህ ምንድን ነው? ብንባል “አምላክ ነው” ወይም “መለኮት” ነው ብለን የመለኮት ባሕርያትን በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፣ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፣ ሁሉን ሰሚ ነው፣ ሁሉን ተመልካች ነው፥ በባዶነት መነሻ በሞት መዳረሻ የሌለው ሕያው ነው እያልን ታላቁ ባሕርይውን እንናገራለን፦
29፥20 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው”*። إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
65፥11 *”አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው”*፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
58፥1 *”አላህ ሰሚ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِير
2፥110 *”አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
25፥58 *”በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ”*፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا

አላህ በሰማያትና በምድር ሊገዙት የሚገባ መለኮት ነው፥ ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ታላቅ ባሕርይ አለው፦
16፥60 *”ለአላህም ታላቅ ባሕርይ አለው”*፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ وَلِلَّهِ الْمَثَلُ الْأَعْلَىٰ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
30፥27 *”ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ታላቅ ባሕርይ አለው”*፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ وَلَهُ الْمَثَلُ الْأَعْلَىٰ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

“ባሕርይ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “አል-መሰል”الْمَثَل ሲሆን የአል-መሰል ብዙ ቁጥር ደግሞ “አል-አምሳል” الْأَمْثَال ነው። አላህ የእኔ ባሕርይ ይህ ነው ብሎ በቁርኣን የተናገረውን እንጂ እኛ ለእርሱ ምንም አይነት ባሕርይ ማድረግ ተከልክለናል፦
16፥74 *”ለአላህም ባሕርዮችን አታድርጉ፡፡ አላህ መሳይ እንደሌለው ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም*፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُون
42፥11 *”የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው”*፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
በሰማያትም በምድርም የእርሱን ታላቅ ባሕርይ የሚመስል ምንም ነገር የለም። “ነገር” ማለት “አጠቃላይ ፍጥረት” ነው። እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው፥ የእርሱ መስማት እና ማየት ጊዜና ቦታ አያካብበውም።
የሥነ-ኑባሬ ጥናት”ontology” ምሁራን እንደሚያትቱት “ዛት” ذَات ማለት “ህላዌ”essence” ማለት ሲሆን “ምንድን” ተብሎ የሚጠየቅ “ምንነት” ነው፥ ምንነት የማንነት መሠረት ነው። “ሸኽስ” شَخْص ማለት “እኔነት”person” ማለት ሲሆን “ማን” ተብሎ የሚጠየቅ “ማንነት” ነው፥ ማንነት የምንነት መገለጫ ነው። አላህ የራሱ አንድ ማንነት አለው፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

“አና” أَنَا ማለት “እኔ” ማለት ሲሆን አንድ ነጠላ ማንነትን የሚያሳይ ነጠላ ተውላጠ-ስም ነው፥ ይህም አንድ ማንነት ምንነቱ አምላክ ስለሆነ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” በማለት ይናገራል። አላህ የራሱ ማንነት ስላለው “ነፍሲ” نَفْسِي ማለትም “እራሴ” ይላል፦
20፥41 *ለነፍሴም መረጥኩህ*፡፡ وَاصْطَنَعْتُكَ لِنَفْسِي

በዚህ አንቀጽ ላይ “ለነፍሴ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሊነፍሢ” لِنَفْسِي ሲሆን “ለራሴ” ማለት ነው፤ የአላህ እራስነት”own self-hood” እንዳለው ያመለክታል።
አላህ ምንነቱን የሚያሳውቀን በሲፋው ነው። “ሲፋህ” صِفَة ማለትም “ባሕርይ”attribute” ማለት ነው፥ የእርሱ ባሕርያት የተሰየሙበት ስም አለው። “ኢሥም” اِسْم ማለት “ስም” ማለት ሲሆን አላህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል “አሥማኡል ሑሥና” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም “መልካም ስሞች” አሉት፦
20፥8 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ *”ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አሉት”*፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ

አላህ ምንድን ነው? ሲባል የምንነት ጥያቄ ስለሆነ የምንነቱ መታወቂያ የሆኑትን ባሕርያት የተሰየሙበትን ስም በመጥቀስ፦
1. “አል-ኻሊቅ” الْخَالِق ማለትም “ፈጣሪ” ነው፦
29፥24 *እርሱ አላህ “ፈጣሪው”፥ ከኢምንት አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ

2. “አስ-ሰመድ” الصَّمَد ማለትም “የሁሉ መጠጊያ” ነው፦
112፥2 *አላህ “የሁሉ መጠጊያ” ነው*፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ

3. “አል-ገኒይ” الْغَنِيّ ማለትም “ተብቃቂ” ነው፦
35፥15 እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ *አላህም እርሱ “ተብቃቂው” ምስጉኑ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

4. “አል-ለጢፍ” اللَّطِيف ማለትም “ረቂቅ” ነው፦
6፥103 ዓይኖች አያገኙትም፥ እርሱም ዓይኖችን ያያል፡፡ *እርሱም “ረቂቁ”፥ ውስጠ ዐዋቂው ነው*፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ

እያልን እንዘረዝራለን። እርሱ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያስገኘ ፈጣሪ፣ ፍጥረታት በእርሱ ላይ ጥገኛ የሆኑ የሁሉ መጠጊያ፣ ከፍጥረቱ ምንም የማይከጅል ተብቃቂ፣ የፍጡራም አእምሮ መርምሮ የማይደርስበት ረቂቅ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አንድያ ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"አንድያ ልጅ" የሚለው የግሪኩ ቃል "ሞኖ-ጌነስ" μονογενὴς ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቸኛ" ማለት ሲሆን "ጌኑስ" γένος ማለት ደግሞ "የተወለደ" ማለት ነው፤ በጥቅሉ "ብቸኛ የተወለደ"the only begotten" ማለት ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥9 እግዚአብሔር *"አንድ ልጁን"* μονογενῆ ወደ ዓለም ልኮታልና።

በግዕዝ "ወልድ ዋሕድ" ይሉታል። ይህንን ውልደት እግዚአብሔር በመዝሙር ኢየሱስን እኔ ዛሬ ወለድሁህ ብሎታል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ *"ዛሬ "ወለድሁህ"* γεγέννηκά ።

"ዛሬ" የሚለው የጊዜ ተውሳከ-ሥስ ጊዜን የሚያሳይ ነው፣ ኢየሱስ መወለዱ ጅማሬ ያለው መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣ ይህ ጊዜ ከሞት ሲነሳ እንደሆነ ጳውሎስ ይናገራል፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ *"እኔ ዛሬ ወለድሁህ"* γεγέννηκά ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ *ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና*።

"እኔ ዛሬ ወለድሁህ" ተብሎ በሁለተኛው መዝሙር የተጻፈው ቃል ኢየሱስ ሲነሳ ተፈጽሞአል እያለን ነው፤ ስለዚህ "ዛሬ ወለድሁህ" የተባለን ቅድመ-ዓለም ከአብ ያለ እናት የሚለው ዶግማ ውኃ የሚያስበላና ድባቅ የሚያስገባ ነው። ኢየሱስ ከሙታን በኵር ተብሏል፤ "በኵር” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፕሮቶ-ቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን የሁለት ቃላት ጥምረት ነው፤ አንዱ “ፕሮቶስ” πρῶτος ማለት “ፊተኛ” ሲሆን ሁለተኛው “ቶኮስ” τοκος ማለትም “መወለድ” ነው፤ በጥቅሉ "መጀመሪያ የተወለደ" ማለት ነው። ኢየሱስ በብዙ ወንድሞች መካከል ፊተኛ በመሆን ከሙታን በአብ እንደተወለደ ይናገራል፦
ሮሜ 8፥29 *“ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል “በኵር” πρωτότοκον ይሆን ዘንድ*፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤

"የበኵር ልጅ" ሁለተኛ ልጅ እስኪመጣ ድረስ ለወላጅ "አንድያ ልጅ" ነው፦
ዘካርያስ 12፥10 ሰውም *ለአንድያ ልጁ* እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም *ለበኵር ልጁ* እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።

"አንድያ ልጁ" እና "የበኵር ልጁ" ተለዋዋጭ ሆነው እንደገቡ ልብ በል፤ ታዲያ ቀጣይ ልክ እንደ ኢየሱስ ከአብ የሚወለዱ እነማን ናቸው? ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፦
1ኛ ዮሐንስ 5:1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር *ተወልዶአል* γεγέννηται ፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ *የተወለደውን* γεγεννημένον ደግሞ ይወዳል። የሐዋርያት ሥራ 17:28-29 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ። እኛ ደግሞ *ውልደቶቹ* γένος ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንቀሳቀሳለን እንኖርማለን። እንግዲህ የእግዚአብሔር *ውልደቶች* γένος ከሆንን፥
ዮሐንስ 1፥13 እነርሱም ከእግዚአብሔር *"ተወለዱ"* ἐγεννήθησαν እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ *"አልተወለዱም"*።

"ጌኑስ" γένος የሚለው ቃል ልክ ለኢየሱስ እንደተጠቀመበት እዚህ ላይም ተጠቅሟል፤ እንደ ጳውሎስ ትምህርት ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ እንደተወለደ ሁሉ አማኞች በትንሳኤ ቀን ሲነሱ ሲጠባበቁት የነበረውን ልጅነት ዳግም ያገኛሉ፦
ሮሜ 8፥23 *"የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን"* ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
ማቴዎስ 19፥28 *"በዳግመኛ ልደት"* የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥

ዳግም ልደት ማለት አዲስ ልደት ማለት ነው፤ ኢየሱስ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጅ የሚለው እሳቤ ፉርሽ ሆነ ማለት ነው፤ ምክንያቱም ከኢየሱስ በኃላ አማኞች ከእግዚአብሔር እንደሚወለዱ ሁሉ ከኢየሱስ ትንሳኤ በፊት መላእክእት፣ አዳም እና እስራኤል የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል፦
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *"እስራኤል የበኵር ልጄ ነው"*፤

እስራኤል የመጀመሪያ ልጄ ከሆነ ከእስኤል በፊት አዳም እና መላእክት እንዴት ልጆች ተባሉ? "በኵር” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፕሮቶ-ቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን ከላይ ለእስራኤል ከዚያ ለኤፍሬም፣ ቀጥሎ ለዳዊት፣ ለጥቆ ለኢየሱስ አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ኤርምያስ 31፥9 እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ *"ኤፍሬምም በኵሬ ነውና"*።
መዝሙር 89፥27 *እኔም ደግሞ በኵሬ አደርሀዋለው* ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል።
ዕብራውያን 1፥6 *"እግዚአብሔር የበኵር ልጁን ልኮ ወደ ዓለም"* ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት፥ ይላል። (1980 አዲስ ትርጉም)

"መውለድ" በእማሬአዊ የአብራክ ክፋይ ማለት ሲሆን ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በፍካሬአዊ ግን "መፍጠርን" ያመለክታል። “ልደት” ማለት “ፍጥረት” ማለት ስለሆነ “አዲስ ፍጥረት” የሚለውን ተክቶ “አዲስ ልደት” ተብሏል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት”* ነው።
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን *”ለአዲስ ልደት”* γένεσις በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥
መወለድ መፈጠር ባይሆን ኖሮ ሰማይንና ምድር ፍጥረት ሆኖ ሳለ “ልደት” ባልተባለ ነበር፤ ስለ ሰማይንና ምድር አፈጣጠር የሚናገረው መጽሐፍ “ዘፍጥረት” ይባላል፤ “ፍጥረት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ’ አያያዥ መስተዋድድ “የ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት” ማለት ነው፤ በግዕዙ አርስት ላይ “ዘልደት” ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ *”የሰማይና የምድር ልደት”* ይህ ነው።
ግዕዙ፦
ዝንቱ *”ፍጥረተ ሰማይ ወምድር”* ዘምአመ ኮነት ዕለት አንተ ባቲ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ።
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς, ὅτε ἐγένετο· ᾗ ἡμέρᾳ ἐποίησε Κύριος ὁ Θεὸς τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν

“ጀነሲዋስ” γενέσεως ማለት “ልደት” ማለት ነው፤ “Genesis” የሚለው የኢንግሊዝኛው ስያሜ “ጀነሲስ” γένεσις ከሚለው ከግሪኩ ቃል የመጣ ነው፤ መቼም ሰማይና ምድር ልደት አለው ሲባል ፈጣሪ በእማሬአዊ ወለደው ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ መፍጠሩን የሚያሳይ ስለሆነ ግዕዙ፦ “ፍጥረተ ሰማይ ወምድር” ማለትም “የሰማይና የምድር ፍጥረት” ይለዋል። “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ”? ተራራ እንደተወለደ ይናገራል፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4፥13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90፥2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
psalms 90፥2 πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,

ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግሥ የመጣ ነው። ፈጣሪ ኢየሱስን፣ አማኞችን፣ እስራኤላውያንን፣ ተራራን፣ ሰማይና ምድር ሳይቀር ወለደ ማለት ፈጠረ ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው? ሃይማኖተ-አበው ላይ የቂሳሪያው ባስልዮስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው ብሎ እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ ነግሮናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦
*”ወለደኒ ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ ፈጠረኒ በእንተ ትስብእቱ”*
ትርጉም፦
*”ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለትም ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል”*

ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል" ማለትም "ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ" ወይም "አምላክ ዘእም-አምላክ" ማለትም "ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የእግዚአብሔር ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ክርስቲያኖች ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ነው ይላሉ፤ “ልጅ” ማለት ምን ማለት ነው? ስንላቸው፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ” ይሉናል። እረ ከሰማናቸው፦ “አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ይሉናል። ይህ ኑባሬአዊ እሳቤ”ontological sense” ነው፤ ከእዚህ እሳቤ ቁርኣን በተቃራኒው፦ “አላህ ወለደ” ያሉ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፤ እንደውም አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ይህንን የቁርኣን እሳቤ ካየን ዘንዳ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አባት መባሉ “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” በሚል ፍካሬአዊ እሳቤ “ideological sense” መጥቷል፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ለምሳሌ መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስቱ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠራቸው እንደሆነ ቅቡል ነው፤ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል፦
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።

አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል? ከማርያም ተጸንሶ የተወለደው ሰው መሆኑን አንርሳ፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ ደግሞ *ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።
ገላትያ 4 ፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ*፤
ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ሰው ብቻ ነው፤ ያም ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መባሉ ፈጣሪ ያለ አባት ከእርሷ መፍጠሩን ያሳያል። አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል፤ ሲቀጥል እዚህ ጥቅስ ላይ እግዚአብሔር ኢየሱስን፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ብሏል ተብሏል፤ ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ “አንተ” ብሎ ካናገረው እግዚአብሔር የተለየ መሆኑን ያሳያል፣ እግዚአብሔር ለኢየሱስ “አባት እሆነዋለው” ኢየሱስ ለእግዚአብሔር “ልጅ ይሆነኛል” ብሏል ተብሏል” ሲሰልስ “ወልጄሃለሁ” የሚለው ቃል “ጌኔካ” γεγέννηκά ሲሆን “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በፍካሬአዊ ትርጉም “ፈጠረ” ሲሆን አይሁዳውያን አምላክ ፆታ ስለሌለውን “መወለድ” ማለት “መፈጠር” ነው ብለው ያምናሉ፤ ምክንያቱን ተራራ እንደተወለደ ስለሚናገር፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4:13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90:2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥ בְּטֶרֶם, הָרִים יֻלָּדו
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,
በዕብራይስጡ “ዩላዱ” יֻלָּדו ማለት “ሳይወለዱ” ማለት ነው። “ሳይወለዱ” የሚለው ፍካሬአዊ ቃል በእማሬያዊ ቃል “ሳይፈጠሩ” ማለት ነው። ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ ደግሞ በተመሳሳይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፤ “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ” ? አይ ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በእማሬአዊ ቃል ወለደ ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ ቃል ፈጠረ ለማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። መወለድ መፈጠር ባይሆን ኖሮ ሰማይንና ምድር ፍጥረት ሆኖ ሳለ “ልደት” ባልተባለ ነበር፤ ስለ ሰማይንና ምድር አፈጣጠር የሚናገረው መጽሐፍ “ዘፍጥረት” ይባላል፤ “ፍጥረት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ’ አያያዥ መስተዋድድ “የ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት” ማለት ነው፤ በግዕዙ አርስት ላይ “ዘልደት” ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ *”የሰማይና የምድር ልደት”* ይህ ነው።
ግዕዙ፦
ዝንቱ *”ፍጥረተ ሰማይ ወምድር”* ዘምአመ ኮነት ዕለት አንተ ባቲ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ።
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς, ὅτε ἐγένετο· ᾗ ἡμέρᾳ ἐποίησε Κύριος ὁ Θεὸς τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν

“ጀነሲዋስ” γενέσεως ማለት “ልደት” ማለት ነው፤ “Genesis” የሚለው የኢንግሊዝኛው ስያሜ “ጀነሲስ” γένεσις ከሚለው ከግሪኩ ቃል የመጣ ነው፤ መቼም ሰማይና ምድር ልደት አለው ሲባል ፈጣሪ ወለደው ማለት ሳይሆን መፍጠሩን የሚያሳይ ስለሆነ ግዕዙ፦ “ፍጥረተ ሰማይ ወምድር” ማለት “የሰማይና የምድር ፍጥረት” ማለት ነው፤ “ልደት” ማለት “ፍጥረት” ማለት ስለሆነ “አዲስ ፍጥረት” የሚለውን ተክቶ “አዲስ ልደት” ተብሏል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት”* ነው።
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን *”ለአዲስ ልደት”* γένεσις በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥

ታዲያ ኢየሱስ ልደት አልነበረውምን? ልደቱ ግን ከመንፈስ ቅዱስ በመጸነስ ነው፤ ፈጣሪ ያለ ወንድ ዘር ስለፈጠረው ልደት አለው፤ ዓለም ሳይፈጠር በነበረው የቀድሞ ዕቅዱ ከድንግል ማርያም ማህጸን ፈጠረው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም *”ልደት”* γένεσις እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
መዝሙር 110፥3 ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ *”ከማህጸን ወለድሁህ”*። μετὰ σοῦ ἡ ἀρχὴ ἐν ἡμέρᾳ τῆς δυνάμεώς σου ἐν ταῖς λαμπρότησι τῶν ἁγίων σου· ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.

የተወለደው በኃይሉ ቀን ነው፤ የቅዱሳን ብርሃን በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ነው፤ ይህ የግሪክ ሰፕቱጀንት እንጂ የማሶሬቲኩ ላይ ቃላቱ የለም። ከማርያም ማህጸን “ወለድሁህ” ማለት “ፈጠርኩ” ማለት ካልሆነ ችግር ይፈጠራል። ሃይማኖተ-አበው ላይ የቂሳሪያው ባስልዮስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው ብሎ ፍርጥ አድርጎ ነግሮናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦
*”ወለደኒ ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ ፈጠረኒ በእንተ ትስብእቱ”*
ትርጉም፦
*”ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለትም ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል”*

አንዳንድ ቂሎች “መወለድ” ከአብ “መውጣት” ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ “መውጣት” ማለት “መስረጽ” ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ። ካልሆነ ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ፤ አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ይህ የኡስታዝ አቡ ዩሥራ የሃይማኖት ንጽጽር ፔጅ ነው፥ ላይክ እና ሼር በማድረግ የትምህርቱን ተደራሽነት ያስፉ!
https://www.facebook.com/Abucomparative/
ፈጣሪ ፍጡር አይደለም!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥16 *አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው*፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ

አምላካችን አላህ የሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው፥ አላህ በፈጣሪነቱ ላይ ፍጡርነት የሚባል የነውር እና የጎደሎ ባሕርይ የለውም። አላህ ሁለመናው ፈጣሪ ነው፥ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
13፥16 *አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፥ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው”* በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ፈጣሪ እና ፍጡር ሁለት ተቃራኒ ባሕርይ ናቸው፥ “ኢየሱስ ማህጸን ውስጥ የተፈጠረ ፍጡር ነው” ስንላቸው፥ እነርሱም ቅብል አርገው፦ “አዎ! ኢየሱስ ፍጡርም ፈጣሪም ነው” ይሉናል፦
ሃይማኖተ-አበው ስምዓት 124:19
ቄርሎስም አለ፦
“ለሊሁ ፍጡር ወለሊሁ ፈጣሪ”

ትርጉም፦
“እርሱ ፍጡር ነው እርሱ ፈጣሪ ነው”

ይህንን ስብጥር እሳቤ አዕምሮአችሁ ይቀበለዋልን? “እርሱ ፍጡር ነው እርሱ ፈጣሪ ነው” ምን ማለት ነው? ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የማይችል፥ ሁሉን ዐዋቂ እና ሁሉን የማያውቅ” ሁለት ባሕርይ እንዴት አንድ ላይ ይዋሕዳል? “አይ ፈጣሪ ፍጡር ሆነ” ብለውን አረፉት፦
ሃይማኖተ-አበው ዘአክርስቶዶሎስ 112:31
አክርስቶዶሎስም አለ፦
“ወፈጣሪ ኮነ ፍጡረ እንተ ይእቲ እምህላዌነ ድንግል ዘበአማን ማርያም”

ትርጉም፦
“ፈጣሪ ከእኛ ባሕረይ ከተገኘች በእውነት ድንግል ከምትሆን ከማርያም ፍጡር ሆነ”

እሰይ! ይቀጥሉና፦ “ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን መስሎና አህሎ ከአብ ማንነትና ምንነት የተገኘ ነው” ይሉናል። አብ ማለት “አስገኚ” ሲሆን ወልድ ደግሞ “ግኝት” ነው። በ 325 ድኅረ-ልደት”AD” የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤም፦
ግሪኩ፦ Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,

ግዕዙ “ብርሃን ዘምብርሃን፤ አምላክ ዘምአምላክ”

ትርጉም፦
“ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ብሎታል።

አምላክ አምላክን ካስገኘ ሁለት አምላክ አይሆንም ወይ? አምላክ ተገኘ የሚለው ሲያስገርም አምላክ ተፈጠረ ደግሞ ያስደምማል፦
አማርኛ፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)

ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”

ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)

ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.

ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።

የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረክ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር “የገዛህ አባትህ” መባሉ “አባት” ማለት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያስረዳል።
እንግዲህ “መገኘት” እና “መፈጠር” ተለዋዋጭ ቃል ከሆነ ኢየሱስ ፍጡር እና ግኝት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን ጥቅስ ተሃድሶና እና ፕሮቴስታት ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሽምጥጥ አርገው ቢክዱም፤ ቀደምት ኦርቶዶክስ፣ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የኒቂያ ጉባኤ ስለ ኢየሱስ ፍጥረት ሳይፈጠር መወለዱን ያሳያል ይላሉ፤ በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ አርዮስንና አትናቲዎስ ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ክርክራቸው ይህ ጥቅስ ነበር፤ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያንም ይህ ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሊያቅማሙ ሲሞክሩ አንድምታው ሆነ ሃይማኖተ-አበው አጋልጧቸዋል፤ ቄርሎስ በሃይማኖተ-አበው ላይ ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:12
ቄርሎስም አለ፦
“ተፈጥረ ጥበብ ዘውእቱ ቃል”

ትርጉም፦
*“ጥበብ ተፈጠረ ይኸውም ቃል ነው”*

ቄርሎስም አለ፦
“ወይእዜኒ ጥበብ ትቤ ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”

ትርጉም፦
*“ከፍጥረት አስቀድሞ የነበርኩኝ በቀድሞ ተግባሩ ጌታ ፈጠረኝ አለች”*

የመቃብያን ጸሐፊም ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ፦ “ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ” ማለቱን ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 4፥18 ሰሎሞን ፦ *“ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ”* ብሎ ተናገረ፤

እንግዲህ አባት ማለት “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” መሆኑን እንዲሁ ልጅ ማለት “ተገኚ” ወይም “ፍጡር” መሆኑን ካየን ዘንዳ ኢየሱስ በየትኛው መልኩ ፍጡር ነው።
የዓለማቱ ጌታ አላህ ጌታችሁ ነው፥ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ እርሱን በብቸኝነት አምልኩት፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና፦
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም