ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ይሄድልናል ወይስ ይሄድላቸዋል?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ

"ሰፕቱጀንት" ወይም "ሰፕቱአጀንት"Ἑβδομήκοντα" ማለት "ሰባ" ማለት ሲሆን በ 280 ቅድመ-ልደት በአሌክሳንድያ ይኖሩ የነበሩ የግሪክ አይሁዳውያን 70 ምሁራን ስም ነው፥ በሮማውያን ቁጥር ምልክት"LXX" ይባላል። እነዚህ ምሁራን 72 ነበሩ፥ ሁለቱ ሲሞቱ ሰባው ሊቃናት የዕብራይስጡን ቅዱሳን ጽሑፎች ወደ ሄለናዊ ግሪክ ኮይኔ ተርጉመውታል። እዚህ ትርጉም ላይ ለዚህ ሕዝብ ማንስ ይሄድላቸዋል? የሚል ኃይለ-ቃል አለ፦
ኢሳይያስ 6፥8 *የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ለዚህ ሕዝብ ማንስ ይሄድላቸዋል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ" አልሁ"*። καὶ ἤκουσα τῆς φωνῆς Κυρίου λέγοντος· τίνα ἀποστείλω, καὶ τίς πορεύσεται πρὸς τὸν λαὸν τοῦτον; καὶ εἶπα· ἰδοὺ ἐγώ εἰμι· ἀπόστειλόν με.

ልብ አድርግ የሚለው "ይሄድላቸዋል" ነው። ለማን ሲባል "ለዚህ ሕዝብ" ኢሳይያስም በብዜት "እኔን ላኩኝ" ሳይሆን በነጠላ "እኔን ላከኝ" ብሏል፥ ጌታም፦ "ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም" በላቸው" አለ፦
ኢሳይያስ 6፥9 *"እርሱም፦ ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም" በላቸው"*።

ነገር ግን ከግሪክ ሰፕቱጀት 100 ዓመት በኃላ 875 ድኅረ-ልደት የተዘጋጀው ማሶሬቲክ እደ-ክታብ ላይ በተቃራኒው ማንስ ይሄድልናል? የሚል ኃይለ-ቃል አለ፦
ኢሳይያስ 6፥8 *የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ" አልሁ"*። וָאֶשְׁמַ֞ע אֶת־קֹ֤ול אֲדֹנָי֙ אֹמֵ֔ר אֶת־מִ֥י אֶשְׁלַ֖ח וּמִ֣י יֵֽלֶךְ־לָ֑נוּ וָאֹמַ֖ר הִנְנִ֥י שְׁלָחֵֽנִ

ትክክሉ የቱ ነው? ይሄድላቸዋል የሚለው የግሪክ ሰፕቱጀንት ወይስ ይሄድልናል የማሶሬቲክ እደ-ክታብ? ሁለቱን ለመዳኘት ከግሪክ ሰፕቱጀንት በፊት የነበረውን የነቢያት ፓሌዎ ዕብራይስጥ ጽሑሮች ጠፍተዋል፥ ግን ከደኃራይ ማሶሬቲክ ይልቅ ቀዳማይ ሰፕቱጀንት ሚዛን ይደፋል። ሙግቱን እናጥብብ እና "ይሄድልናል" ቢባልስ ሥላሴን ያሳያልን? በፍጹም። ምክንያቱን አንድ ማንነት ብዜት ተሳቢ ተውላጠ-ስም ተጠቀመ ማለት ያ ማንነት ሥላሴ ነበር ማለት አይደለም፥ "ኒ" נִי የነበረው ነጠላ ተሳቢ ተውላጠ-ስም በብዜት "ኑ" נוּ በሚል መጥቷል፦
ዕዝራ 4፥7 *"በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤል ተባባሪዎቹም ለፋርስ ንጉሥ ለአርጤክስስ ጻፉ"*።
ዕዝራ 4፥18 ሰላም! *"አሁንም "ወደ እኛ" עֲלֶ֑ינָא የላካችሁት ደብዳቤ በፊቴ ተተርጕሞ ተነበበ"*።

ልብ አድርግ "አርጤክስስ" የሚለው ቃላ ላይ መነሻ ቅጥያ ያለው "ለ" የሚለው መስተዋድድ ለንጉሡ ብቻ የተላከ ደብዳቤ ነው። ንጉሡ ግን በዐረማይክ "ና" נָא ብሎ በብዜት ተጠቅሟል፥ ግን ንጉሡ አንድም ሦስትም ሆኖ አይደለም፦
ዳንኤል 2፥25 *የዚያን ጊዜም አርዮክ ዳንኤልን ፈጥኖ ወደ ንጉሡ አስገባውና፦ "ከይሁዳ ምርኮኞች ያለውን ለንጉሡ ፍቺውን የሚያስታውቀውን ሰው አግኝቼአለሁ" አለው*።
ዳንኤል 2፥36 ሕልሙ ይህ ነው፥ *"አሁንም ፍቺውን በንጉሡ ፊት እንናገራለን" נֵאמַ֥ר *።

"አማር" אֲמַר በሚል ግስ ላይ "ኔ" נֵ የሚል "ባለቤት ተውላጠ-ስም አለ። አርዮክ ወደ ንጉሡ ያስገባው ዳንኤልን ብቻ ሆኖ ሳለ ዳንኤን በብዜት "እንናገራለን" ብሏል፥ ግን ዳንኤል አንድም ሦስትም ሆኖ አይደለም። ሙግቱን አሁንም እናጥብበውና "ይሄድልናል" የሚለው ከአንድ በላይ ላሉ ማንነቶች ነው ነው ብንል እንኳን አሁንም ሥላሴን በፍጹም አያሳይም። ዐውዱ ላይ መላእክት አሉ፥ ኢሳይያስ ሲናገር ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እርሱ መጥቶ፦ "እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ" አለው፦
ኢሳይያስ 6፥2 *"ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር"*።
ኢሳይያስ 6፥5-7 *"እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ*። ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ። አፌንም ዳሰሰበትና፦ እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ፡ አለኝ*።

እንደ ባይብሉ እግዚአብሔር የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው አሉ፥ ያዕቆብ ከእግዚአብሔር እና ከመልአኩ ጋር ስለተነጋገረ " ከእኛ ጋር ተነጋገረ" ብሏል፦
1ኛ ነገሥት 22፥19 *"እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ*።
ሆሴዕ 12፥4 ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ *"በዚያም "ከ-እኛ" ጋር עִמָּֽנוּ ተነጋገረ"*።

አየክ "ኑ" נוּ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ከመላእክት ጋር እንዳገለገለ? በምንም ሒሳብ ሥላሴን አያመለከትም። በተረፈ አንዱ አምላክ አንድ ማንነት ኖሮት ለግነት እኛነት ሲጠቀም በውስጡ ሦስት አባላት አሉት ብሎ ሌሎችን ማንነቶችን በማንነቱ ላይ ማጋራት ሺርክ ነው። እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ፦
6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ከእኛ እንደ አንዱ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

14፥52 *ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት እና የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው*፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ቁርኣን ከወረደበት አንዱ ፈጣሪ አላህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት ነው፦
14፥52 *ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት እና የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው*፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ይህ የአንድ አምላክ እሳቤ በመለኮታዊ ቅሪት እንዲህ ተቀምጧል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው*። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.

ያህዌህ አንድ ያህዌህ ሲሆን እርሱ ሌሎችን ማንነቶችን ጨምሮ፦ “ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” ብሏል፦
ዘፍጥረት 3፥22 *ያህዌህ አምላክም አለ፦ *እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ*፤ וַיֹּאמֶר יְהוָה אֱלֹהִים, הֵן הָאָדָם הָיָה כְּאַחַד מִמֶּנּוּ, לָדַעַת, טוֹב וָרָע; וְעַתָּה פֶּן-

“እንደ አንዱ” እና “እኛ” ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ነጥብ በነጥብ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እናየዋለን፦

ነጥብ አንድ
“እንደ አንዱ”
“ከ-አሐድ” כְּאַחַ֣ד ማለት “እንደ አንዱ”as one of” ማለት ነው፤ ያ ማለት በከፊል መመሳሰልን ያሳያል፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥36 *እኔ ባሪያህ “አንበሳ እና ድብ” መታሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ የሕያውን አምላክ ጭፍሮች ተገዳድሮአልና “ከእነርሱ እንደ አንዱ” ይሆናል*። גַּם אֶת-הָאֲרִי גַּם-הַדֹּב, הִכָּה עַבְדֶּךָ; וְהָיָה הַפְּלִשְׁתִּי הֶעָרֵל הַזֶּה, כְּאַחַד מֵהֶם, כִּי חֵרֵף, מַעַרְכֹת אֱלֹהִים חַיִּים.

“ከ-አሐድ ሜሄም” כְּאַחַד מֵהֶם ማለት “ከእነርሱ እንደ አንዱ”as one of them” ማለት ሲሆን ፍልስጥኤማዊ ጎልያድ በዳዊት በመገደል ደረጃ “እንደ አንበሳ እና ድብ” ይሆናል ማለት ነው እንጂ ጎልያድ አውሬ ይሆናል ማለት አይደለም፣ “እንደ” የሚለው ተውሳከ-ግስ የተወሰነን መመሳሰል ለማመልከት የሚገባ ነው፣ ልክ እንደዚሁ አደም መልካምና ክፉ በማወቅ እንደ እንደ እነርሱ ሆኗል፤ ለዛ ነው “ከ-አሐድ ሜንሁ” כְּאַחַ֣ד מִמֶּ֔נּוּ ማለትም “ከእኛ እንደ አንዱ”as one of us” የሚለው፤ ያህዌህ ታዲያ ማንን ጨምሮ ነው “እኛ” የሚለው?

ነጥብ ሁለት
“እኛ”
ያህዌህ “እኛ” የሚለው ማንን ጨምሮ ነው የሚለው ለመረዳት እዚሁ ዐውድ ላይ አዳም ከእኛዎቹ እንደ አንዱ የሚሆነው “መልካምንና ክፉን ለማወቅ” እንደሆነ ይሰመርበት፤ እዛው ዐውድ ላይ አዳም ቢበላ “እንደ አማልክትም መልካምንና ክፉን የሚያውቁ” እንደሆነ ተነግሯል፦
ዘፍጥረት 3፥5 ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ *“እንደ አማልክትም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ”* ያህዌህ ስለሚያውቅ ነው እንጂ። כִּי, יֹדֵעַ אֱלֹהִים, כִּי בְּיוֹם אֲכָלְכֶם מִמֶּנּוּ, וְנִפְקְחוּ עֵינֵיכֶם; וִהְיִיתֶם, כֵּאלֹהִים, יֹדְעֵי, טוֹב וָרָע.

የግዕዙ ዕትም፦
ዘፍጥረት 3፥5 *“ዘይቤ ከመ ኢትኩኑ አማልክተ ወኢታምሩ ሠናየ ወእኩየ”*

የኢንግሊሹ ዕትም፦
For God doth know that in the day ye eat thereof, then your eyes shall be opened, and *ye shall be as gods, knowing good and evil*.(KJV)

የግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX”፦
ዘፍጥረት 3፥5 ᾔδει γὰρ ὁ Θεός, ὅτι ᾗ ἂν ἡμέρᾳ φάγητε ἀπ᾿ αὐτοῦ, διανοιχθήσονται ὑμῶν οἱ ὀφθαλμοὶ καὶ ἔσεσθε ὡς *θεοί*, γινώσκοντες καλὸν καὶ πονηρόν.

የግዕዙ ዕትም ላይ “አማልክት” ብሎ እንዳስቀመጠው አስተውል፤ “ኤሎሂም” כֵּֽאלֹהִ֔ים ማለት “አማልክት” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ለነጠላ ማንነት ወይንም ለብዙ ማንነት ይውላል፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ለብዙ መባሉን በግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ “ቶኢ” θεοί ማለትም “አማልክት” ብሎ በብዙ ቁጥር አስቀምጦታል፤ ልብ አድርግ የቴኦ ነጠላ “ቴኦስ” Θεὸς ነው፤ “ቴኦስ” ብሎ በነጠላ አለማስቀመጡ ለብዙ ማንነቶች መሆኑን ያሳያል፤ በኢንግሊሹም ደግሞ በብዙ ቁጥር “gods” መባሉን አስተውል። በብሉይ ደግሞ ብዙ ቦታ አማልክት የተባሉት መላእክት ናቸው፦
መዝሙር 97፥7 *”አማልክትም” כֵּֽאלֹהִ֔ים ሁሉ ስገዱለት*።
መዝሙር 104፥4 *“አማልክትን” כֵּֽאלֹהִ֔ים መንፈስ የሚያደርግ፥*
መዝሙር 8፥5 *“ከአማልክትን” כֵּֽאלֹהִ֔ים እጅግ ጥቂት አሳነስኸው*፤
መዝሙር 103፥20 የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ *“አማልክቱ” כֵּֽאלֹהִ֔ים ሁሉ ያህዌህን ባርኩ*።
መዝሙር 138፥1 *”በአማልክት כֵּֽאלֹהִ֔ים ፊት እዘምርልሃለሁ*።

ስለዚህ አዳም ዛፉን ሲበላ መልካም እና ክፉውን በማወቅ እንደ መላእክት ከሆነ ያህዌህ ደግሞ መልካምና ክፉ ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ የሚለው እነዚህን አማልክት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፦
ሆሴዕ 12፥4 *በጕልማስነቱም ጊዜ “ከአምላክ” ጋር ታገለ፤ “ከመልአኩም” ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም “ከእኛ” ጋር ተነጋገረ*።

ያዕቆብ የተነጋገረው ከመልአኩ ጋር እና ከያህዌህ ጋር ነው፤ ያህዌህ መልአኩን ጨምሮ “ከእኛ” እንዳለ አንባቢ ልብ ይለዋል። አይ ያህዌህ እኛ የሚለው ሥላሴን ያሳየል ከተባለ ዕውዱ ላይ ስለ ሥላሴ የሚያሳይ ሃይለ-ቃል ፈልቅቆ ማሳየት ይጠበቅባችኃል፤ ወይም ይህ አንቀጽ ስለ ሥላሴ ያወራል ብሎ የተናገረ ነብይ ወይም ሐዋርያ ጠቅሳችሁና አጣቅሳችሁ መሞገትና መሟገት ይጠበቅባችኃል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ይህ ያውቁ ኖሯል?
በዓለም ላይ 23 ሺ የክርስትና ዓይነት አለ። ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ፦
1.ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
2. ኦርቶዶክስ ቅባት
3. ኦርቶዶክስ ጸጋ
4. ኦርቶዶክስ ተሃድሶ
5. ካቶሊክ
6. ፕሮቴስታንት
7. የይሆዋ ምስክር
8. ኦንልይ ጂሰስ
9. አድቬንቲስት
10. ዴቪድያን
11. የእግዚአብሔር መንግሥት(የካሳ ኬርጋ)
12. ሞርሞን
13. ኒው ኤጅ ሙቭመንት
14. ቢብሊካል ዩኒታሪያን
15. ናዝራዊያን አሉ።

ለዛሬ ይህ በቂ ነው። ለበለጠ ትምህርት በዚህ ተከታተሉ፦ https://tttttt.me/Wahidcom
እንፍጠር ወይስ ልፍጠር?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

አምላካችን አላህ ለመላእክት የተናገረው፦ “እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ” የሚል ነው እንጂ “እንፍጠር” አላላቸውም፦
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- *«እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፤ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً
38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

“እንፍጠር” የሚባለው መፍጠር ለሚችል ማንነትና ምንነት ብቻ ነው፤ በባይብልም ከሄድን ያህዌህ ለመላእክት ያለው፦ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለው” የሚል ነው፦

1ኛ. ዕብራይስጡ፦
ዘፍጥረት 2፥18 וַיֹּאמֶר יְהוָה אֱלֹהִים, לֹא-טוֹב הֱיוֹת הָאָדָם לְבַדּוֹ; אֶעֱשֶׂה-לּוֹ עֵזֶר, כְּנֶגְדּוֹ.

2ኛ. ኢንግሊሹ፦
Genesis 2፥18 The LORD God said, “It is not good for the man to be alone. I will make a helper suitable for him.” NIV

3ኛ. አዲሱ መደበኛ ትርጉም፦
ዘፍጥረት 2፥18 ያህዌህ ኤሎሂም፦ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት *አበጅለታለው”* አለ።

4ኛ. 1879 አማርኛ እትም፦
ዘፍጥረት 2፥18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም፤ የምትረዳውን፣ በአገቡ የምትሆን፣ የምትስማማውን *ልፍጠርለት*።

የዕብራይስጡ ላይ “ኤሴህ” אֶֽעֱשֶׂהּ ማለትም “ልፍጠር” አለ እንጂ “እንፍጠር” አላለም፤ እንግሊዘኞቹም፦ “I will make” ብለው አስቀምጠውታል። ታዲያ “እንፍጠር” ከየት መጣ? አዎ ግሪክ ሰፕቱአጀን”LXX” እና ግዕዙ ላይ “እንፍጠር” የሚል አለ፦

1ኛ. ግሪክ ሰፕቱአጀን፦
Καὶ εἶπε Κύριος ὁ Θεός· οὐ καλὸν εἶναι τὸν ἄνθρωπον μόνον· ποιήσωμεν αὐτῷ βοηθὸν κατ᾿ αὐτόν.

2ኛ. ግዕዙ፦
ወይቤ እግዚአብሔር ኢኮነ ሠናይ ለእጓለ እመሕያው ይንበር ባሕቲቱ *ንግበር* ሎቱ ቢጸ ዘይረድኦ።

3ኛ. አማርኛ 1954 እትም፦
ዘፍጥረት 2፥18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት *እንፍጠርለት*።

የግሪክ ሰፕቱአጀን ላይ “ፓኢሴሜን” ποιήσωμεν ማለት “እንፍጠር” ብሎ አስቀምጦታል፤ ግዕዙም፦ “ንግበር” ማለትም “እንፍጠር” ብሎ አስቀምጠውታል። ታዲያ “እንፍጠር” ያለውም ለማን ነው? ስንል ኩፋሌ ላይ ደግሞ ለፍጡራን እንዳለ ይናገራል፦

1ኛ. ግዕዙ፦
ኩፋሌ 4፥4 *ወይቤለነ እግዚአብሔር ለነ*፤ አኮ ሰናይ የሀሉ ብእሲ ባሕቲቱ፤ አላ *ንግበር* ሎቱ መርድአ ዘከማሁ፤ መወየደ *እግዚአብሔር አምላክነ* ሕድመተ ላዕሌሁ ወኖመ”

2ኛ. አማርኛው፦
ኩፋሌ 4፥4 *ፈጣሪያችን* እግዚአብሔር ለእኛ *እንዲህ አለን*፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት *”እንፍጠርለት”*።

“ፈጣሪያችን” የሚል ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ እግዚአብሔር እንፍጠር ያለው ለፈጠራቸው መሆኑን ለማሳየት እዛው አንቀጽ ላይ፦ “እንዲህ አለን” ይላሉ፤ ያላቸውም፦ “እንፍጠርለት” ነው፤ እነዚህ ማንነቶች እነማን ናቸው? ብለን ስንሞግት “መላእክት ናቸው” ይሉናል፤ አንቀጹ ላይ መላእክት ስለመሆናቸው ምንም ሽታው እንኳን የለም። ነገር ግን ኩፋሌ 1፥25 ኩፋሌ 2፥1 ኩፋሌ 2፥4 ኩፋሌ 4፥1 ለሙሴ የፊቱ መልአክ እየተናገረ ነው በሚል መላእክት ናቸው እንበልና ሙግቱን እናጥበው፤ መላእክት ይፈጥራሉ እንዴ? እኔ “እንብላ” ብዬ ብል የሚበላ ማንነትን እያናገርኩኝ ነው፤ የማይበላ ከሆነ “ልብላ” ብዬ ነው የምለው እንጂ “እንብላ” አልለውም፤ የማይፈጥር ማንነት እንፍጠር ወይስ ልፍጠር? የቱ ነው ስሜት የሚሰጠው?
የባሰው ደግሞ በክሌመንት ላይ፦ “እግዚአብሔር አብ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ እንፍጠር” አላቸው ይለናል፦

1ኛ. ግዕዙ፦
ቀለሚንጦስ 1፥33 *ወይቤሎሙ እግዚአብሔር አብ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ ንዑ ንግበር ሰብእ በአርአያነ ወበአምሳሊነ*።

2ኛ. አማርኛው፦
ቀለሚንጦስ 1፥33 *እግዚአብሔር አብ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ በአርአያችንና በአምሳላችን ሰውን እንፍጠር አላቸው*።

ታዲያ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ፍጡር ናቸውን? ምክንያቱም ኩፋሌ ላይ “ፈጣሪያችን” ብለዋልና። እሺ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ “ፈጣሪ” ወይስ “ፈጣሪዎች” ? መልክአ ሥላሴ ላይ ሥላሴ “ፈጣሪዎች” ተብለዋል፦
መልክአ ሥላሴ ቁጥር 39
*”ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! የአደምና የሔዋን “ፈጣሪዎቻቸው” እንደመሆናችሁ”*።

ሥላሴን “ፈጣሪዎች” ከተባሉ ሦስት ፈጣሪ መሆናቸው ነው። ይህንን የሥላሴ ውዝግብና ትርምስ የሚፈታው የዐለማቱ ጌታ አላህ ለመላእክት ምን ብሎ እንደነበር በሚናገርበት አንቀጽ ነው፦
38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

ቁርኣን ከወረደበት ግብና አላማ፣ ፋይዳና ሚና አንዱ ከእነርሱ ጋር ያለውን መለኮታዊ እውነት ለማረጋገጥ እና ቀጥፈው የጨመሩትን ሐሰት ሊያርም ነው፤ ከእነርሱ ጋር ያለውን እውነትን ስለሚያረጋግጥ “ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا ማለትም “አረጋጋጭ” ሲባል፤ የሰዎች ንግግር የገቡበትን በማረሙ ደግሞ “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا ማለትም “አራሚ” correcter” ወይም “ተቆጣጣሪ”supervisor” የሚል ስም አለው፦
5፥48 *ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ እና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን*። وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የብረት ጥሩር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

34፥11 *"ሰፋፊዎችን "ጥሩሮች" ሥራ! በአሠራርዋም መጥን! መልካምንም ሥራ ሥሩ*፡፡ እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና" አልነው፡፡ أَنِ اعْمَلْ سَابِغَاتٍ وَقَدِّرْ فِي السَّرْدِ ۖ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

የታሪክ ተመራማሪዎች ለታሪክ ምንጭ ሁለት መረጃዎች አሏቸው፥ አንደኛው ትውፊት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሥነ-ቁፋሮ ጥናት ነው። የታሪክ ተመራማሪዎች ያለፈውን ክስተት ሲፈጸም በቦታው ስላልነበሩ ከትውፊት እና ከሥነ-ቁፋሮ ግኝት በስተቀር ሙሉ ዕውቀት የላቸውም፥ አንድ ያለፈ ክስተት እነርሱ አላገኙትም ማለት ክስተቱ አልተከሰተም ማለት አይደለም። የክርስትናው ዐቃቤ እምነት አንቶንይ ሮጀርስ፦ "በዳዊት ዘመን የብረት ጥሩር ስለሌለ በቁርኣን በዳዊት ጊዜ ስለ ብረት ጥሩር የተገለጸው ገለጻ ስህተት ነው" ይለናል፦
34፥11 *"ሰፋፊዎችን "ጥሩሮች" ሥራ! በአሠራርዋም መጥን! መልካምንም ሥራ ሥሩ*፡፡ እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና" አልነው፡፡ أَنِ اعْمَلْ سَابِغَاتٍ وَقَدِّرْ فِي السَّرْدِ ۖ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

"ሣቢጋት" سَٰبِغَٰت የሚለው ቃል "አሥበገ" أَسْبَغَ ማለትም "አገራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተገራ" ማለት ነው። አላህ ለዳውድ ሐዲድን ማግራቱን የሚያሳይ ነው፦
34፥10 ለዳውድም ከእኛ የኾነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው፡፡ «ተራራዎች ሆይ! ከእርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ» አልን። በራሪዎችንም ገራንለት፡፡ *ብረትንም ለእርሱ አለዘብንለት"*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا دَاوُودَ مِنَّا فَضْلًا ۖ يَا جِبَالُ أَوِّبِي مَعَهُ وَالطَّيْرَ ۖ وَأَلَنَّا لَهُ الْحَدِيدَ

የታሪክ ተመራማሪዎች የብረት ጥሩር በሦስተኛ ክፍለ ዘመን አገኙ ማለት ከዚያ በፊት ላለመኖሩ ማስረጃ መሆን አይችልም፥ ይህ ሙግት ሥነ-አመክንዮን ታሳቢና ዋቢ ያላደረገ ስሑት ሙግት ነው። ለምሳሌ በዳዊት ዘመን የነበሩ ሰዎች ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት አሥር ሺህ “ዳሪክ” እንደሰጡ የዜና መዋዕል ጸሐፊ ይነግረናል፦
1ኛ ዜና 29፥7 ለ*"እግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት *አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና አሥር ሺህ “ዳሪክ”፥ አሥር ሺህም መክሊት ብር፥ አሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ*።

ዳሪክ ደግሞ መገበያያነቱ የተጀመረው በ 521-486 ቅድመ-ልደት በፐርሺያን ንጉሥ በዳሪዮስ ዘመነ-መንግሥት እንደሆነ የታሪክ ተመራማሪዎች ያትታሉ። ታዲያ በዳዊትና በዳሪዮስ መካከል የ 400 ዓመት ልዩነት ካለ፥ ታሪክ ስላላገኘው ትርክቱ ትክክል አይደለም ብሎ በአራት ነጥብ መደምደም ይቻላልን?
"ጥሩር" በዕብራይስጥ "ተህራ" תַחְרָ֛א ወይም "ሲሪዩን" שִׁרְיוֹן ነው፥ "ጥሩር" ከዳዊት በፊት በሙሴ ዘመን እና በዳዊትም ጊዜ ነበር፦
ዘጸአት 28፥32 *ከላይም በመካከል አንገትጌ ይሁንበት እንዳይቀደድም እንደ "ጥሩር" תַחְרָ֛א የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ይሁንበት።
ዘጸአት 39፥23 በቀሚሱም መካከል አንገትጌ ነበረ፤ እንዳይቀደድም እንደ "ጥሩር" שִׁרְיוֹן תַחְרָ֛א የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ነበረ*።
1ኛ ሳሙኤል 17፥5 *በራሱም የናስ ቍር ደፍቶ ነበር፥ "ጥሩርም" שִׁרְיוֹן ለብሶ ነበር፤ የጥሩሩም ሚዛን አምስት ሺህ ሰቅል ናስ ነበረ"*።
1ኛ ሳሙኤል 17፥38 *"ሳኦልም ዳዊትን የገዛ ራሱን ልብስ አለበሰው፥ በራሱም ላይ የናስ ቍር ደፋለት፥ ጥሩርም አለበሰው"*።

የታሪክ ተመራማሪዎች የብረት ጥሩር በሦስተኛ ክፍለ ዘመን ስላገኙ ባይብል "ጥሩር ከዳዊት በፊት በሙሴ ዘመን እና በዳዊትም ጊዜ ነበር" የሚለው ገለጻ ስህተት ነው ብሎ ተብሎ መደምደም ይቻላል። ግን ቅሉና ጥቅሉ "አንድ ያለፈ ክስተት የታሪክ ተመራማሪዎች አላገኙትም ማለት ክስተቱ አልተከሰተም ማለት አይደለም" የሚል ነው፥ የቁርኣኑንን ትርክትም በዚህ ልክና መልክ ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ርኅሩኅ እና አዛኝ ነቢይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥128 *"ከራሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ላይ ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ"*፡፡ لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ

አምላካችን አላህ በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው፥ እርሱ ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው፦
16፥47 ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚይዛቸው መኾኑን አይፈሩምን? *"ጌታችሁም በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው"*፡፡ أَوْ يَأْخُذَهُمْ عَلَىٰ تَخَوُّفٍ فَإِنَّ رَبَّكُمْ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ
21፥83 አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ፥ *"አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ»* ሲል በተጣራ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

"ረሒም" رَّحِيم በነጠላ "አዛኝ" ማለት ሲሆን "ራሒሚን" رَّاحِمِين ደግሞ በብዜት "አዛኞች" ማለት ነው። ከአዛኞች መካከል አንዱ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ናቸው፥ እርሳቸው በምእምናን ላይ ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ ናቸው፦
9፥128 *"ከራሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ላይ ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ"*፡፡ لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 164
ሙሐመድ ኢብኑ ጁበይር ኢብኑ ሙጥዒም ከአባቱ ሰምቶ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“እኔ ሙሐመድ ነኝ፣ እኔ አሕመድ ነኝ፣ እኔ አላህ በእኔ ሰበብ ክህደትን የሚደመስስብኝ አል-ማሒ ነኝ፣ እኔ ያ ሰዎች ከእርሱ ኋላ ተከትለውት የሚቀሰቀሱበት አል-ሓሺር ነኝ፣ ከዚህ በኃላ ነብይ የለምና እኔ ዓቂብ(መጨረሻ) ነኝ። በእርግጥም አላህ ርኅሩኅ አዛኝ ብሎ የጠራው ነኝ"*። عَنْ مُحَمَّدِ بْنِ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ، عَنْ أَبِيهِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ لِي أَسْمَاءً أَنَا مُحَمَّدٌ وَأَنَا أَحْمَدُ وَأَنَا الْمَاحِي الَّذِي يَمْحُو اللَّهُ بِيَ الْكُفْرَ وَأَنَا الْحَاشِرُ الَّذِي يُحْشَرُ النَّاسُ عَلَى قَدَمَىَّ وَأَنَا الْعَاقِبُ الَّذِي لَيْسَ بَعْدَهُ أَحَدٌ ‏"‏ ‏.‏ وَقَدْ سَمَّاهُ اللَّهُ رَءُوفًا رَحِيمًا

እኛ ክርስቲያኖችን፦ "ኢየሱስ ፍጡር ሆኖ ሳለ ለምን ታመልኩታላችሁ" ብለን ስንጠይቅ፥ እከክልኝ ልከክልህ በሚል ስሜት፦ "ጌታችሁም በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው፥ ያም ርኅሩኅ አዛኝ በምእምናን ላይ ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ ነው። ስለዚህ ነቢያችሁ ጌታችሁ ነው" ብለው አረፉት። ይህ ቁርኣንን አገላብጦ ካለማንበብና ካለመረዳት የሚመጣ የተውረገረገ፣ የተንሸዋረረ፣ የተሳከረ፣ የደፈረሰ መረዳት ነው። አምላካችን አላህ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፥ እርሱ ሰሚ ተመልካች ነው፦
42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ *"እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው"*፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ሰውም አላህ በምንም አይመስልም፥ ግን ሰውም ሰሚ ተመልካች ነው፦
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ *ሰሚ ተመልካችም አደረግነው*፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

አላህ የሚመስለው ምንም ነገር ስለሌለ አላህ ሰሚ እና ተመልካች የተባለው ሰው ሰሚ እና ተመልካች በተባለበት ስሌትና ቀመር እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው። አምላካችን አላህ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፥ እርሱ አመስጋኝ ታጋሽ ነው፦
64፥17 ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ ምንዳውን ለእናንተ ይደራርበዋል፥ ለእናንተም ይምራል። *"አላህም አመስጋኝ ታጋሽ ነው"*፡፡ إِن تُقْرِضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا يُضَاعِفْهُ لَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۚ وَاللَّهُ شَكُورٌ حَلِيمٌ

ሰውም አላህ በምንም አይመስልም፥ ግን ሰውም ታጋሽና አመስጋኝ ተብሏል፦
42፥33 ቢሻ ነፋሱን የረጋ ያደርገዋል፡፡ በባሕሩም ጀርባ ላይ ረጊዎች ይኾናሉ፡፡ *"በዚህ ውሰጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለኾነ ሁሉ በእርግጥ ምልክቶች አሉ"*፡፡ إِن يَشَأْ يُسْكِنِ الرِّيحَ فَيَظْلَلْنَ رَوَاكِدَ عَلَىٰ ظَهْرِهِ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّكُلِّ صَبَّارٍ شَكُورٍ

አላህ የሚመስለው ምንም ነገር ስለሌለ አላህ አመስጋኝ እና ታጋሽ የተባለው ሰው አመስጋኝ እና ታጋሽ በተባለበት ስሌትና ቀመር እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው። አምላካችን አላህ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፥ እርሱ ርኅሩኅ ታጋሽ ነው፦
2፥225 *"አላህም በጣም ርኅሩኅ ታጋሽ ነው"*፡፡ وَاللَّهُ غَفُورٌ حَلِيمٌ

ሰውም አላህ በምንም አይመስልም፥ ለምሳሌ ኢብራሂም ርኅሩኅ ታጋሽ ተብሏል፦
9፥114 *"ኢብራሂም በእርግጥ በጣም ርኅሩኅ ታጋሽ ነውና"*፡፡ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ لَأَوَّاهٌ حَلِيمٌ
አላህ የሚመስለው ምንም ነገር ስለሌለ አላህ ርኅሩኅ እና ታጋሽ የተባለው ኢብራሂም ርኅሩኅ እና ታጋሽ በተባለበት ስሌትና ቀመር እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው። እስቲ ለናሙና ያክል ከባይብል በንጽጽር እንይ! እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው። ሰይጣን ፈታኝ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ *”እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው”*፥
ማቴዎስ 4፥3 *”ፈታኝም”* ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።

እግዚአብሔር ፈታኝ ሰይጣን ነውን? ማነው ፈታኝ? እግዚአብሔር ወይስ ሰይጣን? እግዚአብሔር አጥፊ ተብሏል። ሰይጣንም አጥፊ ተብሏል፦
ዘጸአት 12፥12 እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፥ *”በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ”*።
ዕብራውያን 11፥28 *”አጥፊው”* የበኵሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨትን በእምነት አደረገ።
ራእይ 9፥11 *”በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል”*።

በዕብራይስጥ “አብዶን” ማለት እና በግሪክ “አጶልዮን” ማለት ትርጉሙ “አጥፊ” ማለት ነው። እግዚአብሔር የጥልቁ መልአክ ሰይጣን ነውን? ማነው አጥፊ? እግዚአብሔር ወይስ ሰይጣን? እንዲህ ማነጻጸር ይቻላል። "እረ ወሒድ ምን ነካህ? እግዚአብሔር ፈታኝና አጥፊ የተባለው ሰይጧን ፈታኝና አጥፊ በተባለበት ሒሳብ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አብርሃም ቤት የገቡት ሦስት ሰዎች መላእክት እንጂ ሥላሴ አለመሆናቸው ድርሳነ ሚካኤል እንዲህ ይናገራል፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘሚያዝያ ቁጥር 11
ግዕዙ፦
*ወካዕበ መጽኡ መላእክት ወበጽሑ ኀበ አብርሃም ወነገርዎ ከመ ይትወለድ ይስሐቅ*።
አማርኛው፦
*ዳግመኛ መላእክት ወደ አብርሃም ዘንድ መጥተው ይስሐቅን እንደሚወልድ ነገሩት*።
ሦስቱ መላእክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥31 *መልእክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا إِنَّا مُهْلِكُو أَهْلِ هَـٰذِهِ الْقَرْيَةِ ۖ إِنَّ أَهْلَهَا كَانُوا ظَالِمِينَ

ኦሪት ዘፍጥረት ላይ አብርሃም ቤት ሦስት ሰዎች በእንግድነት እንደተስተናገዱ ይናገራል፤ ዐበይት ክርስቲያኖች፦ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና አንግሊካን እነዚህ ሦስት ሰዎች ሥላሴ ናቸው ይላሉ፤ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 220 ድህረ-ልደት”AD” ቱርቱሊያም ይህንን አንቀጽ ይዞ የሥላሴን ቶኦሎጅይ ቴኦሌጃይዝ ያደረገው፤ በአገራችንም በየወሩ በሰባተኛው ቀን የአብርሃሙ ሦላሴ እየተባለ ይዘከራል፤ እውን ይህ አንቀጽ ለሥላሴ ተስተምህሮት መደላለል ይሆናልን? እስቲ ጥንልልና ጥንፍፍ አርገን እናስተንትነው፦
ዘፍጥረት 18፥1-2 በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ *እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት*። ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ *ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ*፤

እዚህ ጥቅስ ላይ ስለ ሥላሴ ምንም ሽታው እንኳን የለም። እነዚህ ሦስት ሰዎች አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸው የሚል ዐውዱ ላይ ምንም አናገኝም። ይህንን አንቀጽ ለሥላሴ የተጠቀመ ነብይም ሆነ ሃዋርያ የለም፤ እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው ታዲያ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለዐውደ ንባቡ ቦታውን እንልቀቅ፦
ዘፍጥረት 18፥16 *ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ* አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ።
ዘፍጥረት 18፥22 *ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ* አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።

እነዚህ ሰዎች ከአብርሃም ቤት ወደ ሰዶም አቀኑ፣ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ ከዚያስ? በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፦
ዘፍጥረት 19፥1 *ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ*፤

እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ሲነጋገር የነበረው በሦስት ሰዎች ነው፤ ሁለቱ ሰዎች ሲሄዱ ግን “አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር” ይላል፤ እግዚአብሔር በአንዱ ሰው ሲነጋገር ሁለቱ ሰዎች ሎጥ ቤት ገብተዋል፦
ዘፍጥረት 19፥10 *ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት*።
ዘፍጥረት 19፥12 *ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት*።
ዘፍጥረት 19፥13 *እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል*።

“ሁለቱ ሰዎች” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ምን ትፈልጋለህ? ከአብርሃም ቤት ወጥተው ወደ ሎጥ ቤት የገቡት ሰዎች በቁጥር ሁለት መሆናቸውን እና ሁለት መላእክት መሆናቸውን ተገልጻል፤ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ በአንድ ሰው ይናገራል፤ ይህም ሰው መልአክ ተብሏል፤ ለምሳሌ ያዕቆብ ሲታገለው የነበረው መልአክ ሰው ተብሏል፦
ዘፍጥረት 32፥28 አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ *ከእግዚአብሔር እና ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና*።
ሆሴዕ 12፥3-4 በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ *ከአምላክ ጋር ታገለ፤ ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ*፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም *ከእኛ ጋር ተነጋገረ*።

“ከእኛ ጋር ተነጋገረ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ እግዚአብሔር እዚህ አንቀጽ ላይ፦ “እኛ” የሚለው መልአኩን ጨምሮ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ምነው ገብርኤል ሰው ተብሎ የለ እንዴ? መላእክት በሰው ቅርጽ ስለሚመጡ ሰው ይባላሉ፦
ዳንኤል 9፥21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው *የነበረው ሰው ገብርኤል* እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።

እግዚአብሔር ግን ሰው አይደለም፤ አይበላም አይጠጣምም፦
ሆሴዕ 11፥9 *እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና*፥
መዝሙር 50፥12 *ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና። የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?*

ፈጣሪ፦ እበላለሁን? እጠጣለሁን? ሲል በምጸታዊ አነጋገር አልበላም አልጠጣም እያለ ነው፤ አንዳንድ ቂሎች፦ “አብርሃም ቤት የገቡት ሰዎች ምግብ በልተዋል፤ መላእክት እንዴት ይበላሉ? ብለው ይጠይቃሉ፤ የቱ ይቀላል መጋቢ ፈጣሪ መብላቱ ወይስ ፍጡር የሆኑት መላእክት መብላታቸው? አዎ መላእክቱ በልተዋል ይለናል፦
ዘፍጥረት 18፥8 እርጎና ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፥ በፊታቸውም አቀረበው እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር፥ *እነርሱም በሉ*።
ዘፍጥረት 19፥3 እጅግም ዘበዘባቸው ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ *እነርሱም በሉ*።

ሎጥ ቤት የበሉት መላእክት ሥላሴ ናቸው ብላችሁ እንዳታርፉት፤ የዕብራውያን ጸሐፊ፦ “አንዳንዶች በእንግድነት መላእክትን ተቀብለዋል” በማለት አብርሃምን እና ሎጥን ያስታውሰናል፦
ዕብራውያን 13፥2 *እንግዶችን መቀበል አትርሱ*፤ በዚህ አንዳንዶች *ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና*።
ሎጥ ቤት የበሉት መላእክት ሥላሴ ናቸው ብላችሁ እንዳታርፉት፤ የዕብራውያን ጸሐፊ፦ “አንዳንዶች በእንግድነት መላእክትን ተቀብለዋል” በማለት አብርሃምን እና ሎጥን   ያስታውሰናል፦
ዕብራውያን 13፥2 *እንግዶችን መቀበል አትርሱ*፤ በዚህ አንዳንዶች *ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና*።

ከሎጥ ሌላ በእንግድነት እግር አጥቦና ጋብዞ እንግዳ የተቀበለ አብርሃም ነው። ደግሞም ድርሳነ ሚካኤል አብርሃም ቤት ገብተው አብርሃምን ያበሰሩት መላእክት እንደሆኑ ይናገራል፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘሚያዝያ ቁጥር 11
ግዕዙ፦
*ወካዕበ መጽኡ መላእክት ወበጽሑ ኀበ አብርሃም ወነገርዎ ከመ ይትወለድ ይስሐቅ*።
አማርኛው፦
*ዳግመኛ መላእክት ወደ አብርሃም ዘንድ መጥተው ይስሐቅን እንደሚወልድ ነገሩት*።

አምላካችን አላህ ወደ ኢብራሂም ቤት በብስራት የመጡት መልእክተኞቹ እንደሆኑና እነዚህም መላእክትም ወደ ሉጥ ቤት እንደገቡ ይናገራል፦
29፥31 *መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا إِنَّا مُهْلِكُو أَهْلِ هَـٰذِهِ الْقَرْيَةِ ۖ إِنَّ أَهْلَهَا كَانُوا ظَالِمِينَ
11፥77 *መልእክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በእነርሱ ምክንያት አዘነ፡፡ ልቡም በነሱ ተጨነቀ፡፡ «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا لُوطًا سِيءَ بِهِمْ وَضَاقَ بِهِمْ ذَرْعًا وَقَالَ هَـٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌ

እነዚህ መላእክት የቁጥራቸው መጠን ቁርኣን ላይ በእርግጥ አልተገለጸም፤ እንዲሁ ቁርኣን እነዚህ መላእክት በሉ አይልም፤ ኢብራሂም የተጠበሰን የወይፈን ስጋ ሲያመጣላቸው እጆቻቸውም ወደ ምግቡ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፤ ምግብ የማይበሉ መሆናቸውን ሲረዳ ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው፦
11፥69 *መልእክተኞቻችንም ኢብራሂምን በልጅ ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ*፡፡ وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ
11፥70 *እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት*፡፡ فَلَمَّا رَأَىٰ أَيْدِيَهُمْ لَا تَصِلُ إِلَيْهِ نَكِرَهُمْ وَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۚ قَالُوا لَا تَخَفْ إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَىٰ قَوْمِ لُوطٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እንፍጠር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥102 *"ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፥ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው"*፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ከአንድ አይሁዳዊ ምሁር ጋር እየተጨዋወትን ቀበል አርጌ፦ "ኤሎሂም እነማንን ነው እንፍጠር ያለው? ብዬ ጠየኩት፥ እርሱ፦ "በዚህ አንቀጽ ላይ በአይሁድ ጥንታዊ ምሁራን እና ዘመናዊ ምሁራን ዘንድ የተለያየ መልስ ተሰቶበታል" አለኝ። ከተሰጡት መልሶች መካከል፦
1ኛ. ኤሎሂም ከመላእክት ጋር እየተነጋገረ ነው፣
2ኛ. ከምድር ጋር እየተነጋገረ ነው፣
3ኛ. እራሱ ለግነት የብዜት ግስ እየተጠቀመ ነው፣
4ኛ. እራሱ ከራሱ ባሕርያት ጋር በዜቢያዊ አነጋገር እየተናገረ ነው" የሚል ነው፦
ዘፍጥረት 1፥26 ኤሎሂምም አለ፦ *"ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር"*።

አራተኛው ሰምቼ የማላውቀው ስለሆነ ትኩረቴ ሳበው። አንዱ አምላክ ብቻውን ሁሉን ነገር ፈጥሯል፥ ሰውንም የፈጠረ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? *"አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?"*

አንዱ አምላክ ያህዌህ ኤሎሂም ሰውን ከምድር አፈር በእጆቹ ፈጠረው፦
ዘፍጥረት 2፥7 ያህዌህ ኤሎሂም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው"*።
ኢዮብ 33፥6 *"እኔ ደግሞ ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ"*።
መዝሙር 119፥73 *”እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም”*።

ኤሎሂም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ ኤሎሂም እንፍጠር ያለው መፍጠር ለሚችሉ ለእጆቹ ነው። ዳዊት፦ "እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም" ሲል ሰውን ያበጃጁት እጆቹ ከሆኑ፥ ኤሎሂም እጆቹ የራሱ ባሕርያት እንጂ ከኤሎሂም ውጪ ያሉ አካላት አይደለም። ታዲያ አንድ ማንነት ከራሱ ባሕርያት ጋር እንዴት ይነጋገራል? ከተባለ ዳዊት ለራሱ ነፍስ እና አጥንቶች፦ "ነፍሴ ሆይ፥ ያህዌህን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን ባርኩ" ብሏል፦
መዝሙር 103፥1 *"ነፍሴ ሆይ፥ ያህዌህን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን"*።

ዳዊት በሁለተኛ መደብ በትእዛዛዊ ግስ የራሱን ነፍስ እና አጥንቶች "ባርኩ" ካለ፥ የራሱን ነፍስ ነፍሴ ሆይ! ባርኪ፣ አመስግኚ፣ ታመኚ፣ አትርሺ፣ ተመለሺ ካለ ኤሎሂም ሰውን የሚሠሩትንና የሚያበጁትን የራሱን እጆች "እንፍጠር" ቢል ምን ይደንቃል? ፈጣሪ ብቻውን ሰማያትን እና ምድርን እንደፈጠረ እሙን እና ቅቡል ነው፦
ኢሳይያስ 44፥24 *"ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ ያህዌህ እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ”*?

ከእኔ ጋር "ምን" ነበረ? ሳይሆን "ከእኔ ጋር "ማን" ነበረ? ነው ያለው። ከዚህ ከአንድ እኔነት ጋር አብረው የፈጠሩ ማንነቶች እንደሌሉ ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ይህ ሆኖ ሳለ ሰማያት እና ምድርን የፈጠሩ አሉ፥ እነርሱም እጁ፣ ቀኙ፣ ጣቶቹ ወዘተ ናቸው፦
ኢሳይያስ 48:13 *”እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች”*።
መዝሙር 8፥3 *”የጣቶችህን ሥራ” ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ"*።

እነዚህን ባሕርያት ሸንሽነን ማንነት ሰጥተን ከሦስቱ ሥላሴ በላይ ስንት አካላት ልናረጋቸው ነው? ያህዌህ በጥበቡ፣ በማስተዋሉ፣ በኃይሉ ሰማያትን እና ምድርን ፈጥሯል፦
ምሳሌ 3፥19 *"ያህዌህ በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና”*።
ኤርምያስ 10፥12 *"ምድርን ”በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ” እርሱ ነው"*።

ጥበቡ፣ ማስተዋሉ፣ ኃይሉ የራሱ ባሕርያት እንጂ የሚያማክሩት አካላት በፍጹም አይደሉም። እርሱ ራሱ እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንጂ ከራሱ ውጪ የሆኑ አካላትን እንፍጠር እያለ እየተመካከረ የሚሠራ በፍጹም አይደለም፦
ኤፌሶን 1፥11 *"እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ"*።

ከላይ ያለው አራተኛው እይታ ከሥነ-አመክንዮ አንጻር ድንቅ እይታ ነው። በቁርኣን ከሄድን ነገርን ሁሉ የፈጠረ ፈጣሪ ጌታችን አላህ ነው፥ ነገርን ሁሉ ብቻውን ፈጥሯል። ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፥ እርሱን ብቻ በብቸኝነት እናመልካለን፦
6፥102 *"ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፥ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው"*፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ምድር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፦ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥12 *"አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን ፈጥሮአል"*። اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ

"አርድ”أَرْض ማለት "ምድር" ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ምድርንም መፍጠሩ ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፥ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦
30፥22 *"ሰማያትን እና "ምድርንም" መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ

"አርድ"أَرْض የሚለው ቃል "ምድርን" "መሬትን" "አህጉርን" "አገርን" ለማመልከት ይመጣል። ለምሳሌ አላህ ዐረብ አገርን "አርድ"أَرْض ይለዋል፦
17፥76 *"ከምድሪቱም ያወጡህ ዘንድ ሊያሸብሩህ በእርግጥ ተቃረቡ"*፡፡ وَإِن كَادُوا لَيَسْتَفِزُّونَكَ مِنَ الْأَرْضِ لِيُخْرِجُوكَ مِنْهَا ۖ
8፥30 እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም "ከመካ ሊያወጡህ" በአንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ

በተመሳሳይም የሻም አገርን "አርድ"أَرْض ይለዋል፦
21፥81 *"ለሱለይማንም ነፋስን በኀይል የምትነፍስ በትዕዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት "ምድር" የምትፈስ ስትኾን ገራንለት"*፡፡ وَلِسُلَيْمَانَ الرِّيحَ عَاصِفَةً تَجْرِي بِأَمْرِهِ إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا
34፥18 *"በእነርሱ እና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት "አገር" መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን፡፡ وَجَعَلْنَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ الْقُرَى الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا قُرًى ظَاهِرَةً وَقَدَّرْنَا فِيهَا السَّيْرَ

"የሞተችው አገር" የሚለው "የሞተችው ምድር" በሚለው መምጣቱ በራሱ "አርድ"أَرْض የሚለው ቃል አንድ "አገርን" ለማመልከት እንደሚመጣ አመላካች ነው፦
43፥11 ያም ከሰማያ ውሃን በልክ ያወረደላችሁ ነው፡፡ *"በእርሱም የሞተችውን አገር ሕያው አደረግን"*፡፡ እንደዚሁ ትውወጣላችሁ፡፡ وَالَّذِي نَزَّلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً بِقَدَرٍ فَأَنشَرْنَا بِهِ بَلْدَةً مَّيْتًا ۚ كَذَٰلِكَ تُخْرَجُونَ
36፥33 *"የሞተችውም ምድር ለእነርሱ ምልክት ናት! ሕያው አደረግናት"*፡፡ ከእርሷም ፍሬን አወጣን፥ ከእርሱም ይበላሉ፡፡ وَآيَةٌ لَّهُمُ الْأَرْضُ الْمَيْتَةُ أَحْيَيْنَاهَا وَأَخْرَجْنَا مِنْهَا حَبًّا فَمِنْهُ يَأْكُلُونَ

"አርድ"أَرْض የሚለው ቃል የወከለውን አሳብ እዚህ ድረስ ከተግባባን አላህ ሰባትን ሰማያት እና ከምድርም መሰላቸውን ፈጥሮአል፥ የሰባት ሰማያት ቁጥር መሰላቸው ሰባት ከምድር ላይ ያሉ ሰባት የተዘረጉ ምድሮች ናቸው፦
65፥12 *"አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን ፈጥሮአል"*። اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ 65፥12 *"አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው" ማለት አንዱ ሰማይ በሌላው ሰማይ ልክ እንደ ጉልላልት ነው፥ "ከምድርም መሰላቸውን ፈጥሮአል" ማለት ሰባት ንጣፍ ናቸው"*። { ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ } بعضها فوق بعض مثل القبة { وَمِنَ ٱلأَرْضِ مِثْلَهُنَّ } سبعاً ولكنها منبسطة

"ሠማዋት" سَمَاوَات በብዜት "ሰማያት" ተብሎ ሲቀመጥ "አርድ"أَرْض ግን በነጠላ "ምድር" ተብሎ ተቀምጧል። ምድር ላይ ሰባት ንጣፎች ሰባቱ የመሬት ክፍሎች ናቸው፥ ይህ አንደኛው እይታ ነው። "በለድ" بَلَد በነጠላ "አገር" ማለት ሲሆን "አቃሊም" أَقالِيم ደግሞ በብዜት "አህጉር" ማለት ነው። ከምድር በውቂያኖስ የተከፋፈሉ ለሰዎች መኖሪያ ሰባት የተዘረጉ አህጉራት አሉ፥ እነርሱም፦
1. ኤሲያ 44,579,000 km²
2. አፍሪካ 30,370,000 km²
3. ሰሜን አሜሪካ 24,709,000 km²
4. ደቡብ አሜሪካ 17,840,000 km²
5. አንታርክቲካ 14,000,000 km²
6. አውሮፓ 10,180,000 km²
7. አውስትራሊያ 8,600,000 km² ናቸው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 22, Hadith 171
ሠዒድ ኢብኑ ዘይድ ኢብኑ ዐምሪው ኢብኑ ኑፈይል እንደዘገበው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ከምድር ያለ አግባብ የወሰደ አላህ በትንሳኤ ቀን ከሰባት መሬታትን በአንገቱ ዙሪያ እንዲሸከም ያደርገዋል"*። عَنْ سَعِيدِ بْنِ زَيْدِ بْنِ عَمْرِو بْنِ نُفَيْلٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنِ اقْتَطَعَ شِبْرًا مِنَ الأَرْضِ ظُلْمًا طَوَّقَهُ اللَّهُ إِيَّاهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ مِنْ سَبْعِ أَرَضِينَ ‏"‏

በተረፈ በጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3611 ላይ፦ "የሰባቱ መሬቶች በመካከላቸው ያለው እርቀት 500 ዓመት ነው" የሚለው ዘገባ ዶዒይፍ ነው፥ "ዶዒይፍ" ضَعِيْف ማለት “ደካማ”weak” ማለት ሲሆን "መቅቡል" مَقْبُول ሳይሆን "መርዱድ" مَردُود ነው። ኢንሻላህ ስለ ምድርን ንጣፍ፣ ሹረት እና ቅርጽ ነጥብ በነጥብ እንመለከታለን፦
ነጥብ አንድ
"የምድር ንጣፍ"
አምላካችን አላህ ምድርን ለእኛ ፍራሽ አድርጎ ዘርግቷታል፦
2፥22 *"እርሱ ያ ለእናንተ ምድርን "ምንጣፍ" ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው"*። الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ فِرَاشًا وَالسَّمَاءَ بِنَاءً

"ምንጣፍ" ለሚለው ቃል የገባው "ፊራሽ" فِرَاش ሲሆን "ፍራሽ" ማለት ነው፥ አንሶላና ብድር ልብስ ያለ ፍራሽ አይደላም። ምድር ለመኖሪያ የተመቻቸች ድሎት እና ማረፊያ ናት፥ የምንተኛበት አልጋ እራሱ "ፊራሽ" فِرَاش ይባላል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 85, ሐዲስ 27
አቢ ሁረይራህ ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ልጅ ለአልጋ ባለቤት ነው"*። أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ الْوَلَدُ لِصَاحِبِ الْفِرَاشِ ‏"‌‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 85, ሐዲስ 27
ሑደይፋህ እንደተረከው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" ወደ አልጋቸው በሄዱ ጊዜ፦ "አሏሁማ! ቢሥሚከ አሕያ ወአሙት" ይሉ ነበር"*። عَنْ حُذَيْفَةَ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا أَوَى إِلَى فِرَاشِهِ قَالَ ‏"‏ اللَّهُمَّ بِاسْمِكَ أَحْيَا وَأَمُوتُ ‏"‌‏

ሁለቱም ሐዲሳት ላይ "አልጋ" ለሚለው የገባው ቃል "ፊራሽ" فِرَاش መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አምላካችን አላህ ምድርን ለእኛ ማመቻቸቱን በግስ መደብ "ፈረሽናሃ" فَرَشْنَاهَا በማለት ይናገራል፦
51፥48 *"ምድርንም ዘረጋናት፡፡ ምን ያማርንም ዘርጊዎች ነን!"* وَالْأَرْضَ فَرَشْنَاهَا فَنِعْمَ الْمَاهِدُونَ

"ዘረጋን" ለሚለው የገባው "ፈረሽና" فَرَشْنَا ነው። "ዘርጊዎች" ለሚለው ደግሞ "ማሂዱን" مَٰهِدُون ሲሆን "አልጋ" እራሱ "መህድ" مَهْد ነው። ምድር ለእኛ ልክ እንደ አልጋ ምቹ መኖሪያ ናት፦
43፥10 *"እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በእርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው"*፡፡ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ مَهْدًا وَجَعَلَ لَكُمْ فِيهَا سُبُلًا لَّعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ምንጣፍ" ለሚለው ቃል የገባው "መህድ" مَهْد ሲሆን "አልጋ" ማለት ነው። "ለኩም" لَكُم ማለት "ለእናንተ" ማለት ነው። የምድር የላይኛው ቅርፊት"crust” በአብዛኛው ከተለያዩ የቋጥኝ አይነቶች የተገነባ ሲሆን፥ ሕይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ የሚኖሩት በዚህኛው የመሬት ክፍል ላይ ነው። ይህንን ክፍል አላህ "ለእኛ" እንደ ፍራሽና አልጋ ንጣፍ አርጎ ፈጥሮታል፥ መዘርጋት ከእኛ እይታ አንጻር ነው። ምክንያቱ "በእርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው" ይለናል፥ በምድር የላይኛው ቅርፊት ላይ መኪና ስንነዳ መንገዶች ሁሉ የሚታዩን ዝርግ ሆነው ነው። አጠቃላይ የምድር ሹረት እና ቅርፅ ምን ይመስላል? ኢንሻላህ በሚቀጥለው ጊዜ እናያለን.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ምድር

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፦ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

39፥5 ሰማያትንና ምድርን በእወነት ፈጠረ፡፡ *"ሌሊትን በቀን ላይ ይጠቀልላል፡፡ ቀንንም በሌሊት ላይ ይጠቀልላል"*። خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ ۖ يُكَوِّرُ اللَّيْلَ عَلَى النَّهَارِ وَيُكَوِّرُ النَّهَارَ عَلَى اللَّيْلِ

ነጥብ ሁለት
“የምድር ሹረት”
የሥነ-ፈለክ ጥናት ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናጠና እና ስንቃኝ በጥንት ጊዜ ያሉ ሰዎች፦ “ምድር የሥርዓተ-ፈለክ እምብርት”geocentric” ናት" ብለው ያምኑ ነበር። ነገር ግን በ1533 ድኅረ-ልደት ኒክላስ ኮፐርኒኮስ ምድር ሳትሆን ፀሐይ የሥርዓተ-ፈለክ እምብርት”heliocentric” መሆኗን ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለማችን አበረከተ። ምድር በፀሐይ ዛቢያ ስትሽከረከር 365 ቀናት ይፈጃል፥ የዚህ ውጤቱም ክረምት፣ በጋ፣ ፀደይ እና መከር የተባሉ አራት ወቅቶች ይፈራረቃሉ። ምድር በደቡብና በሰሜን በሚገኙት ዋልታዎ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ በራሷ ዛቢያ በ 360 ድግሪ ስትሽከረከር መዓልት እና ሌሊት ይፈራረቃል፥ ይህ ሂደት በአማካኝ 24 ሰዓት ይፈጃል። ይህን ሂደት የሥነ-ፈለክ ምሁራን “ሹረት”rotation” ይሉታል። ምድር ጠፍጣፍ ብትሆን ኖሮ ሌሊት ሲሆን ሁሉም የምድር ይዞታ ላይ ጨለማ ይኖር ነበር፥ እንዲሁ መዓልት ሲሆን ደግሞ ሁሉም የምድር ይዞታ ላይ ብርሃን ይሆን ነበር። ቅሉ ግን ምድር በራሷ ዛቢያ ስለምትሽከረከር መዓልት እና ሌሊት በአንድ ጊዜ እየተደራረቡ ይፈራረቃሉ፦
39፥5 ሰማያትንና ምድርን በእወነት ፈጠረ፡፡ *"ሌሊትን በቀን ላይ ይጠቀልላል፡፡ ቀንንም በሌሊት ላይ ይጠቀልላል"*። خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ ۖ يُكَوِّرُ اللَّيْلَ عَلَى النَّهَارِ وَيُكَوِّرُ النَّهَارَ عَلَى اللَّيْلِ

"ይጠቀልላል" ለሚለው የገባው ቃል "ዩከወሩ" يُكَوِّرُ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ከወረ" كَوَّرَ ማለት "ጠቀለለ" "ደረበ" ማለት ነው፥ አንድን ነገር በሌላ ነገር መደረብ"overlap" እራሱ "ከወረ" كَوَّرَ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ብርሃን ሆኖ መአልት ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ አሜሪካ ጨለማ ሆኖ ሌሊት ይሆናል፥ አሜሪካ ብርሃን ሆኖ መአልት ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ኢትዮጵያ ጨለማ ሆኖ ሌሊት ይሆናል። በእኩል ጊዜ መዓልት እና ሌሊት እየተደራረቡ ይፈራረቃሉ፥ ምድር የማትንቀሳቀስ እና ጠፍጣፋ ብትሆን ኖሮ ሁሉም ጋር ሌሊት ወይም ሁሉም ጋር መዓልት ይሆኖ ነበር። ቅሉ ግን መሬት ትንቀሳቀሳለች፥ ቅርጿም የሰጎን እንቁላል ቅርፅ እንጂ ጠፍጣፋ አይደለም።
የሚያጅበው አእዋፍ ሰማይ ላይ ክንፎቻቸውን ዘርግተው ተንሳፋፊዎች ሆነው ባየር ላይ ሲበሩ እንዳይወድቁ የሚይዛቸው ኤሮዳይናሚክ"Aerodynamics" ሕግ አለ፥ በዚህ ሕግ እንዳይወድቁ የሚይዛቸው አላህ ነው፦
67፥19 *"ወደ አእዋፍ ከበላያቸው ክንፎቻቸውን ዘርግተው ተንሳፋፊዎች የሚሰበሰቡም ሲኾኑ አላዩምን? ከአልረሕማን በቀር ባየር ላይ የሚይዛቸው የለም"*፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا إِلَى الطَّيْرِ فَوْقَهُمْ صَافَّاتٍ وَيَقْبِضْنَ ۚ مَا يُمْسِكُهُنَّ إِلَّا الرَّحْمَـٰنُ

በተመሳሳይም ምድር በራሷ ዛቢያ ስትዞር የማትወድቀው አንዱ በአንዱ ባለው የመሳሳብ”Gravity” ሕግ ነው፥ ይህንን ሕግ አርቅቆ እንዳትወድቅ የያዛት አላህ ነው። ምድርም ያለምሰሶ በትዕዛዙ እንዳትወድቅ መቆሟ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፦
35፥41 *"አላህ ሰማያትንና ምድርን እንዳይወገዱ ይይዛቸዋል፡፡ ቢወገዱም ከእርሱ ሌላ አንድም የሚይዛቸው የለም*፡፡ እነሆ እርሱ ታጋሽ መሓሪ ነውና፡፡ إِنَّ اللَّهَ يُمْسِكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ أَن تَزُولَا ۚ وَلَئِن زَالَتَا إِنْ أَمْسَكَهُمَا مِنْ أَحَدٍ مِّن بَعْدِهِ ۚ إِنَّهُ كَانَ حَلِيمًا غَفُورًا
30፥25 *"ሰማይ እና ምድርም ያለምሰሶ በትዕዛዙ መቆማቸው፥ ከዚያም ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَن تَقُومَ السَّمَاءُ وَالْأَرْضُ بِأَمْرِهِ ۚ ثُمَّ إِذَا دَعَاكُمْ دَعْوَةً مِّنَ الْأَرْضِ إِذَا أَنتُمْ تَخْرُجُونَ
ነጥብ ሦስት
“የምድር ቅርጽ”
አላህ ለሰማይ እና ለምድር "ኑ" ሲላቸው ታዛዦች ሆነው መምጣታቸው በራሱ ምድር እንደምትንቀሳቀስ ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል፦
41፥11 *"ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ"*፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

ሰማያትና ምድርን፣ ሌሊትንና ቀን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፥ ሁሉም በፈለካቸው ውስጥ ይዞራሉ፦
39፥5 *"ሰማያትንና ምድርን በእወነት ፈጠረ፡፡ ሌሊትን በቀን ላይ ይጠቀልላል፡፡ ቀንንም በሌሊት ላይ ይጠቀልላል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፡፡ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ"*፡፡ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ ۖ يُكَوِّرُ اللَّيْلَ عَلَى النَّهَارِ وَيُكَوِّرُ النَّهَارَ عَلَى اللَّيْلِ ۖ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ يَجْرِي لِأَجَلٍ مُّسَمًّى
21፥33 እርሱም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው፡፡ *"ሁሉም በፈለካቸው ውስጥ ይዋኛሉ"*፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ فِي فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

"ይሮጣሉ" ለሚለው ቃል የገባው "የጅሪይ" تَجْرِي ሲሆን "ይዞራሉ" ማለት ነው፥ "ይዋኛሉ" ለሚለው ቃል የገባው ደግሞ "የሥበሑነ" يَسْبَحُونَ ሲሆን "ይዞራሉ" ማለት ነው። ሁሉም አላህ በወሰነላቸው የጊዜ ቀመር በምህዋራቸው ይዞራሉ፥ “ፈለክ” فَلَك የሚለው ቃል “ምህዋር”orbit” ማለት ሲሆን ምድር በፀሐይ ዛቢያ ስትሽከረከር ወቅቶች ይፈራረቃሉ፥ ይህ ሁሉ የሚሆነው ምድር ሞላላ ሆና ስትገኝ ነው። አላህ ምድር ሞላላ መሆኗን ይናገራል፦
79፥30 *"ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት"*፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ዘረጋት” ለሚለው የገባው ቃል "ደሓሃ" دَحَاهَا መሆኑን ልብ በል። "ደሕያህ" دِّحْيَة የሚለው ቃል “ደሓ” دَحَىٰ ማለትም "የሰጎን እንቁላል ቅርጽ አደረገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሰጎን እንቁላል" ማለት ነው። ስለዚህ ምድር እንደ ሰጎን እንቁላል ሞላላ”ellipse” መሆኗን ሰዎች በዚህ ዘመን ከማስተንተናቸው በፊት አላህ ቀድሞ በቁርኣን ተናግሯል። የተለያዩ በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ የቁርኣን ትርጉማት፦ "”He made the earth egg-shaped” ብለው አስቀምጠውታል፦
Dr. Kamal Omar Translation፣
Ali Unal Translation፣
Shabbir Ahmed Translation ተመልከት።

"ደሕያህ" دِّحْيَة የሚለው ቃል “ደሓ” دَحَىٰ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ መሆኑን ዋቢ የዐረቢኛ ሙዳየ-ቃላት ይመልከቱ፦
1. Lisan Al-Arab dictionary , Book 7, Page 456:
2. Lisan Al-Arab dictionary , Book 2, Page 790.
3. Al-Mawrid dictionary Arabic-English section 4, Page 1132.
4. Al-Mawrid dictionary English-Arabic section 4, Page 227.

"አቅጧር" أَقْطَار ማለት "ክልል" "አጽናፍ" "አድማስ" "ቀበሌ"zone" ማለት ነው፥ ዛሬ በዘመናችን የሥነ-ፈለክ ተመራማሪዎች ከሰማያትና ከምድር አጽናፍ ወጥተው የምድርን አቀማመጥ፣ ሹረት እና ቅርጽ ከሞላ ጎደልና ከብዙ በጥቂቱ ዐውቀዋል፦
55፥33 የጂን እና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በሥልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ إِنِ اسْتَطَعْتُمْ أَن تَنفُذُوا مِنْ أَقْطَارِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ فَانفُذُوا ۚ لَا تَنفُذُونَ إِلَّا بِسُلْطَانٍ

"ሡልጧን" سُلْطَان ማለት "ኃይል" "ሥልጣን" "ፈቃድ" ማለት ነው፥ የሰው ጭፍሮች በአላህ ኃይል፣ ሥልጣን፣ ፈቃድ በህዋ ጠፈር ላይ ወጥተዋል። እንግዲህ ስለ መሬት በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቀኝ እና ግራ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፦ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

50፥17 *ሁለቱ ቃል ተቀባዮች መላእክት ከቀኝ እና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ

“ኪራመን ካቲቢን” كِرَامًا كَاتِبِين ማለት “የተከበሩ ጸሐፊዎች” ማለት ነው፥ እነዚህ ጸሐፊዎች የምንሠራውን እና የምንናገረውን ይጽፋሉ። እነርሱም በእያንዳንዱ ሰው ቀኝ እና ግራ ያሉ ሁለት መላእክት ናቸው። በቀኝ ያለው ሰናይ ተግባራትን ይመዘግባል፥ በግራ ያለው ደግሞ እኩይ ተግባራትን ይመዘግባል፦
50፥17 *ሁለቱ ቃል ተቀባዮች መላእክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ
10፥21 *አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው*፡፡ قُلِ اللَّهُ أَسْرَعُ مَكْرًا ۚ إِنَّ رُسُلَنَا يَكْتُبُونَ مَا تَمْكُرُونَ
43፥80 ወይም እኛ ምስጢራቸውን እና ውይይታቸውን የማንሰማ መኾናችንን ያስባሉን? አይደለም፤ *መልክተኞቻችንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ*፡፡ أَمْ يَحْسَبُونَ أَنَّا لَا نَسْمَعُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَاهُم ۚ بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيْهِمْ يَكْتُبُونَ

የምእምናን መጽሐፍ በእርግጥ በዒሊዮን ውስጥ ነው፥ “ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ማለት ነው፦
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ
83፥19 *ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?* وَمَا أَدْرَاكَ مَا عِلِّيُّونَ
83፥20 *"የታተመ መጽሐፍ ነው"*፡፡ كِتَابٌ مَّرْقُومٌ

የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፥ “ሢጂን” سِجِّين “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ
83፥8 *ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?* وَمَا أَدْرَاكَ مَا سِجِّينٌ
83፥9 *"የታተመ መጽሐፍ ነው"*፡፡ كِتَابٌ مَّرْقُومٌ

በዒሊዮን ውስጥ ያለው የምእምናን መጽሐፍ ለአማንያን በቀኙ ይሰጠዋል፥ በተቃራኒው በሲጂን ውስጥ ያለው የከሓዲዎቹ መጽሐፍ ለከሃድያን በግራው ይሰጠዋል፦
69፥19 *መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ ለጓደኞቹ «እንኩ! መጽሐፌን አንብቡ» ይላል*፡፡ فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ فَيَقُولُ هَاؤُمُ اقْرَءُوا كِتَابِيَهْ
69፥25 *መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል*፡፡ وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِشِمَالِهِ فَيَقُولُ يَا لَيْتَنِي لَمْ أُوتَ كِتَابِيَهْ

“አሽ-ሸማል” الشِّمَال ማለትም “ግራ” ማለት ሲሆን “አል-የሚን” الْيَمِين ማለትም “ቀኝ” ማለት ነው፥ ቀኝ እና ግራ መጽሐፉን ከሚቀበለው ሰው አንጻር ነው። በቀኝ የተቀበለው የጀነት ባለቤት “አስሓቡል የሚን” أَصْحَابُ الْيَمِين ማለትም "የቀኝ ጓድ" ሲባል፥ በተቃራኒው በግራ የተቀበለው የእሳት ባለቤት ደግሞ “አስሓቡ አሽ-ሸማል” أَصْحَابُ الشِّمَال ማለትም "የእሳት ጓድ" ይባላል፦
56፥27 *የቀኝም ጓዶች ምንኛ የከበሩ የቀኝ ጓዶች! ናቸው?*። وَأَصْحَابُ الْيَمِينِ مَا أَصْحَابُ الْيَمِين
56፥41 *የግራ ጓደኞችም ምንኛ የተዋረዱ የግራ ጓዶች! ናቸው?*፡፡ وَأَصْحَابُ الشِّمَالِ مَا أَصْحَابُ الشِّمَالِ

"አሏሁ አዕለም" اَللّٰهُ أَعْلَم‎

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጨረቃ አቆጣጠር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥189 *ከለጋ ጨረቃዎች ይጠየቁሃል፥ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج

የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው 9ኛው ወር ረመዷን በመጣ ቁጥር የጨረቃ መታየት እና አለመታየት በፆም መጀመር እና መጨረስ ላይ የሚኖረውም አውንታዊ ተፅዖኖ ብዙ የክርስትና ዘላፊያን ሆኑ ኀያሲያን እንደ በቀቀን እየደጋገሙ መዝለፍና ኂስ መስጠታቸው አይቀሬ ነው። ይህንን ታሳቢና ዋቢ ባደረገ መልኩ ይህንን መጣጥፍ ለዚያ ምላሽ አቅርቤአለው። ግብጻውያን፣ ባቢሎናውያን፣ ሰመርያን፣ ሄለናውያን(ግሪኮች)፣ ሮማውያን፣ ዞራስተሪያን፣ ሂንዱ የየራሳቸው “የዘመን አቆጣጠር”calendar” ነበራቸው።
ይህ አቆጣጠራቸው ምንጩ “አል-ቀመርያ” ማለትም “የጨረቃ አቆጣጠር”lunar calender” እና “አሽ-ሸምሲያህ” ማለትም “የፀሐይ አቆጣጠር”solar calended” ናቸው። አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ ፀሐይን እና ጨረቃን ለሰው ልጆች የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን መቁጠሪያ እንዳደረገ ይናገራል፦
6፥96 እርሱም ጎህን ከሌሊት ጨለማ ፈልቃቂ ሌሊትንም ማረፊያ *”ፀሐይንና ጨረቃንም ለጊዜ መቁጠሪያ አድራጊ ነው”*፡፡ فَالِقُ الْإِصْبَاحِ وَجَعَلَ اللَّيْلَ سَكَنًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ حُسْبَانًا ۚ ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ
10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ *የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው*፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ ۚ مَا خَلَقَ اللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

የሥነ-ተረት ጥናት”mythology” እንደሚያትተው በተለይ በባቢሎናውያን “ሲን” የተባለው የጨረቃ አምላክ እና “ሻም” የተባለው የፀሐይ አምላክ ባልና ሚስት ተደርገው ይመለኩ ነው፤ “ሲን” ማለት “ጨረቃ” ማለት ሲሆን “ሻም” ደግሞ “ፀሐይ” ማለት ነው። ይህንን እሳቤ ቁርአን መንግሎ ይጥለዋል፤ መመለክ የሚገባው ፀሐይና ጨረቃን የፈጠራቸው አላህ ብቻ ነው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም፣ *”ጸሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፤ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ሰገዱ፤ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደሆናችሁ ለሌላ አትስገዱ”*። وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

የዘመናችን የሥነ-ፈለክ ጥናት እንደሚያትተው የጨረቃ ፈለክ ምድራችንን በ 384,408 km በሆነ ዑደት”Revolution” ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ 27 ቀናት ነው። አምላካችን አላህም በቁርኣን “ቀመር” قَمَر ማለትም “ጨረቃ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው “27” ጊዜ ብቻ ነው። ጨረቃ ፕላኔታችንን በምእራባዊ አቅጣጭ 360 ድግሪ ለመዞር 19 ዓመት ይፈጅባታል።
የሚያስደምመው ነገር “ዓመት” የሚለው ቃል የተጠቀሰው “ሢኒን” سِنِين በብዜት 12 ጊዜ ወይም “ሠናህ” سَنَة በነጠላ 7 ጊዜ በጥቅሉ “19” ጊዜ ብቻ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የዓለማቱ ጌታ ነገርን ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ስለሆነ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀቱ የከበበ እና * ነገሩንም ሁሉ “በቁጥር” ያጠቃለለ ሲሆን”* የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል። لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

የእኛ አቆጣጠር የጨረቃ አቆጣጠር ነው፦
2፥189 *ከለጋ ጨረቃዎች ይጠየቁሃል፥ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج

የለጋ ጨረቃ መታየት የጊዜ ማወቂያ ምልክት ነው። ነቢያችን”ﷺ” የአላህ ነብይ ስለሆኑ በዐቂዳህ እና በፊቅህ ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ወሕይ ስለሆነ ስለ ጨረቃ እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 2378
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መቼም ቢሆን ለጋ ጨረቃ በረመዳን ወር ስታዩ ፆምን ጀምሩ፤ የሸዋል ለጋ ጨረቃ ስታዩ ፆማችሁን ጨርሱ፤ ሰማይ ደመናማ ሲሆንላችሁ ፆም ሰላሳ ቀን መሆኑን አጢኑ”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، – رضى الله عنه – قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِذَا رَأَيْتُمُ الْهِلاَلَ فَصُومُوا وَإِذَا رَأَيْتُمُوهُ فَأَفْطِرُوا فَإِنْ غُمَّ عَلَيْكُمْ فَصُومُوا ثَلاَثِينَ يَوْمًا ‏”
የጨረቃ አቆጣጠር በኢሥላም በግርድፉና በሌጣው ይህ ያክል ካየን ዘንዳ የጨረቃ አቆጣጠር በባይብልና በትውፊት እናያለን፥ የጨረቃ መታየት ለጊዜ ማወቂያ እንደሆነ መዝሙረኛው ይናገራል፦
መዝሙረ ዳዊት 104፥19 *”ጨረቃን ለጊዜዎች አደረገ”* ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።

በተለይ አይሁዳውያን የወር መባቻ ጠብቀው በዓላቸውን የሚያውቁበት ነው፥ የወር መባቻ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “ቆደሽ” חֹ֫דֶשׁ ሲሆን ትርጉሙ “አዲስ ጨረቃ” ማለት ነው። ይህም ቃል በባይብል 28 ጊዜ ተወስቷል፥ ዕብራውያን ወራቸውን ሆነ ዓመታቸውን የሚጀምሩ በለጋ ጨረቃ መታየት ነው፦
ዘኍልቍ 10፥10 ደግሞ በደስታችሁ ቀን፥ በበዓላታችሁም ዘመን፥ *”በአዲስ ጨረቃ” חָדְשֵׁיכֶם֒ ፥”* በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በደኅንነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶቹን ንፉ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት ለመታሰቢያ ይሆኑላችኋል እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። NIV Bible
መዝሙር 81፥3 *”በአዲስ ጨረቃ” חָדְשֵׁיכֶם֒ ቀን”* በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ NIV Bible

በክርስትና ቀዳማይ የዘመን አቆጣጠር ከ 180 –222 ድኅረ-ልደት”A.D” ድረስ ለ 42 ዓመት የአሌክሳንድርያ ፓትርያርክ የነበረው ድሜጥሮስ የቀመረው ነው። ይህም የዘመን ቀመር “አቡሻኽር” ወይም “ባሕረ-ሐሳብ” ይባላል። “ባሕር” ማለት “ዘመን” ማለት ሲሆን “ሐሳብ” ማለት ደግሞ “ሒሳብ” “ቁጥር” “ኍልቅ” ማለት ነው። በዚህ የዘመን ቀመር ላይ ስለ “አዕዋዳት” ይናገራል፥ “አዕዋድ” ማለት “ዖደ” ማለትም “ዞረ” ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን “ዙረት” ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው።
ዓውደ-ወርኅ በፀሐይ 30 ቀናት ሲሆን በጨረቃ 29 እና 30 ነው። ዓውደ-ዓመት በፀሐይ 365 ቀናት ሲሆን በጨረቃ 354 ቀናት ነው፦
ዘፍጥረት 1፥14 እግዚአብሔርም አለ፦ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ *”ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ*፤
ዘፍጥረት 1፥16 እግዚአብሔርም *”ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን”*፤ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
መዝሙር 136፥8-9 *”ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው”*፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን ፀሐይን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን ጨረቃን በሌሊት እንዲሰለጥን አደረገ። በተጨማሪም መጽሐፈ ሲራክ ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ፣ ለዓለም ሁሉ ምልክት እና የበዓላት ምልክት እንደሆነች ይናገራል፦
መጽሐፈ ሲራክ 43÷6-7 *”ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ ናት፤ ለዓለም ሁሉ ምልክት ናት፤ በእርሷም ቀን ይለያል፤ በጨረቃም የበዓላት ምልክት ይታወቃል”*።

ታዲያ ጨረቃን ጠብቆ ፆም መያዝና መፍታት እንዲሁ በዓልን ማክበር ለምን ኂስ ይሰጥበታል? ተዉ እንጂ እግር እራስን ያካል እንዴ? ወርቁ ቢጠፋስ ሚዛኑ ጠፋ እንዴ? እውነቱ ቢጠፋባችሁስ ህሊናችሁ ጠፋባችሁ እንዴ? የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ ወይም ቅቤ አንጣሪዋ እያለሽ ጎመን ቀቃይዋን ምች መታት ይላል የአገሬ ሰው። ቅድሚያ እሥልምናን ለመዝለፍ ባይብላችሁን እና ትውፊታችሁን ጠንቅቃችሁ ዕወቁ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም