ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.1K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ሥነ-ሰብእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

51፥21 *በራሳችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ፥ ታዲያ አትመለከቱምን?* وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ سورت الذاريات ?

"ሰብእ" ማለት "ሰው" ማለት ነው፥ "ግለ-ሰብእ" ማለት "ግላዊ ሰው" ማለት ነው፣ "ቤተ-ሰብእ" ማለት "የሰው ቤት" ማለት ነው፣ "ኅብረተ-ሰብእ" ማለት "የሰው ኅብረት" ማለት ነው፣ "ማኅበረ-ሰብእ" ማለት "የሰው ማኅበር" ማለት ነው። ስለ ሰው ጥናት በመስኩ ምሁራን ዘንድ "አንትሮፖሎጂ"anthropology" ይሉታል፥ ይህም ቃል "አንትሮፖስ" ἄνθρωπος ማለትም "ሰው" እና "ሎጂአ" λογία ማለትም "ጥናት" ከሚል ሁለት የግሪክ ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "ሥነ-ሰብእ ጥናት" ማለት ነው። በቁርኣን "ኢንሣን" إِنسَٰن ማለት "ሰው" ማለት ሲሆን ይህም ቃል በነጠላ የተጠቀሰው 65 ጊዜ ብቻ ነው፥ ሰው የተፈጠረው ደግሞ ከአፈር፣ ከፍትወት ጠብታ፣ ከረጋ ደም፣ ከቁራጭ ስጋ፣ ከአጥንት እና ከጡንጫ ስጋ ነው፦
23፥12 *በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው*፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن سُلَالَةٍ مِّن طِينٍ
23፥13 *ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው*፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ
23፥14 *ከዚያም ጠብታዋን የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ مَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

ሰው የአፈር፣ የፍትወት ጠብታ፣ የረጋ ደም፣ የቁራጭ ስጋ፣ የአጥንት እና የጡንጫ ስጋ ሁሉ ድምር ነው፥ ይህንን በዝርዝር ማየት እንችላለን፦
1. "ቱራብ" تُرَاب "አፈር" የሚለው ቃል 17 ጊዜ
2. "ኑጥፋህ" نُّطْفَة "የፍትወት ጠብታ" የሚለው ቃል 12 ጊዜ
3. "ዐለቃህ" عَلَقَة “የረጋ ደም” የሚለው ቃል 6 ጊዜ
4. "ሙድጋህ" مُضْغَة "ቁራጭ ስጋ" የሚለው ቃል 3 ጊዜ
5. "ዐዝም" عَظْم "አጥንት" የሚለው ቃል 15 ጊዜ
6. "ለሕም" لَحْم "ስጋ" የሚለው ቃል 12 ጊዜ ተጠቅስዋል።
---------------
በድምሩ = 65= ይሆናል። ይህም "ኢንሣን" إِنسَٰن "ሰው" የሚለው ቃል 65 ጊዜ መጠቀሱ ያለምክንያት አልነበረም፥ አላህ ነገር ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ስለሆነ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና *ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን*፥ የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል፡፡ لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዲን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

42፥13 *ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ! በእርሱም አትለያዩ። شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ

“ዲን” دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ፈረደ" "በየነ" "አመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሃይማኖት” “ፍትሕ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርሕ”Doctrine” ማለት ነው፥ ዲን በግሪክ “ዶግማ” δόγμα ይባላል። ዲን የእምነት እሴት እና የሥነ-ምግባር መርሖ ያቀፈ ሥርወ-እምነት ነው፥ “ሃይማኖት” የሚለው የግዕዝ ቃልም “ሀይመነ” ማለትም “አመነ” ወይም “ታመነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመን” ወይም “መታመን” ማለት ነው። እምነት በዕውቀት እያደገ የሚመጣ ሲሆን ሃይማኖት ግን የእምነት ተቋም ያለው አቋም ነው፥ ዲን ያለው ሰው "ሙተዲን" مُتَدَيِّن ይባላል። ዲኑል ኢሥላም ነቢያትን ወንድማማች ያደረገ ዐቂዳህ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 113
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ። ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው፤ እናቶቻቸው ይለያያሉ፤ ነገር ግን ሃይማኖታቸው አንድ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ أَنَا أَوْلَى النَّاسِ بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ، وَالأَنْبِيَاءُ إِخْوَةٌ لِعَلاَّتٍ، أُمَّهَاتُهُمْ شَتَّى، وَدِينُهُمْ وَاحِدٌ ‏

“እናቶቻቸው ይለያያሉ” ማለት በተላኩበት ዘመን ያለውን “ሸሪዓህ” እንደየ ማኅበረሰቡ የእድገት እና የአስተሳሰብ ደረጃ ይለያያል ማለት ነው፥ ዲናቸው ግን አንድ ነው። “ዲን” ደግሞ ሦስት ደረጃ አሉት፥ እነርሱም፦
1. “ኢሥላም” إِسْلَٰم
2. “ኢማን” إِيمَٰن
3. “ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው።

ነጥብ አንድ
“ኢሥላም”
“ኢሥላም” إِسْلَام‎ የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መታዘዝ” “ማምለክ” ማለት ነው። “አርካን” أَرْكَان ማለት “ምሰሶ” ማለት ነው። አርካኑል ኢሥላም አምስት ናቸው፥ እነርሱም፦ ሸሃደተይን፣ ሶላት፣ ዘካህ፣ ሰውም እና ሐጅ ናቸው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፥ እነርሱም፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው” በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ በይት በመጎብኘት”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ

ነጥብ ሁለት
“ኢማን”
“ኢማን” إِيمَٰن የሚለው ቃል “አሚነ” أَمِنَ ማለትም “አመነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እምነት” ነው፥ “እምነት” በግል እና በዕውቀት እንደገባህ እና እንደተረዳከው የሚያድግ አሊያ የሚቀንስ ነው። አርካኑል ኢማን ስድስት ሲሆኑ፥ እነርሱም፦ በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በቀደር ማመን ናቸው። ይህ በሐዲሱል ጂብሪል ተገልጿል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 5
ዑመር ኢብኑ ኽጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፤ ወደ ነብዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ኢማን ምንድን ነው? እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ*። ‏ قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَجَاءَ رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَلْزَقَ رُكْبَتَهُ بِرُكْبَتِهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ مَا الإِيمَانُ قَالَ ‏”‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ
ነጥብ ሦስት
"ኢሕሣን”
“ኢሕሣን” إِحْسَٰن የሚለው ቃል “አሕሠነ” أَحْسَنَ ማለትም “አስዋበ” “አሳመረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስዋብ” “ማሳመር” ማለት ነው፥ ኢሕሣን የዲን ማሳመሪያና ማስዋቢያ ነው። ኢሕሣን “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ” ማለት ነው፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 47 , ሐዲስ 6
ዑመር ኢብኑ ኸጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፣ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፥ ወደ ነቢዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ስለ ኢሥላም ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው” የሚል ምስክርነት፣ ሶላትን መቆም፣ ዘካህን መስጠት፣ ረመዷንን መፆም እና ለመጓዝ አቅም ካለህ የአላህን ቤት መጎብኘት ነው” አሉ። እርሱም፦ “እውነት ተናገርክ” አለ፥ እኛም በሚጠይቃቸው ነገር ተገረምን። ከዚያም ስለ ኢማን ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ። እርሱም፦ “እውነት ተናገርክ” አለ፥ ከዚያም ስለ ኢሕሣን ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ ነው” አሉ”*። قَالَ حَدَّثَنِي عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ، قَالَ بَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى جَلَسَ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إِلَى رُكْبَتَيْهِ وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخِذَيْهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ أَخْبِرْنِي عَنِ الإِسْلاَمِ قَالَ ‏”‏ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَتُقِيمَ الصَّلاَةَ وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ وَتَصُومَ رَمَضَانَ وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلاً ‏”‏ ‏.‏ قَالَ صَدَقْتَ ‏.‏ فَعَجِبْنَا إِلَيْهِ يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ ثُمَّ قَالَ أَخْبِرْنِي عَنِ الإِيمَانِ قَالَ ‏”‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ كُلِّهِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ صَدَقْتَ ‏.‏ قَالَ فَأَخْبِرْنِي عَنِ الإِحْسَانِ قَالَ ‏”‏ أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ

አንድ ሰው በኢስላም “ሙሥሊም” مُسْلِم ሲባል፣ በኢማን “ሙእሚን” مُؤْمِن ሲባል፣ በኢሕሣን ደግሞ “ሙሕሢን” مُحْسِن ይባላል። አምላካችን አላህ ለነቢያችን”ﷺ” እና ለተከታዮቻቸው ያዘዘው ዲን ኑሕን፣ ኢብራሂምን፣ ሙሳን እና ዒሳንም ያዘዘበት ዲን ይህ ነው፦
42፥13 *ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ! በእርሱም አትለያዩ። شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የዘካህ ገንዘብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥219 *”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”*፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ

ዘካህ ከካፒታል ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5% ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 5፥2=2.5 ይሆናል፦
2፥219 *”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”*፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”*። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

በዚህ ሐዲስ መሠረት የአንድ ሰው ካፒታል 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ዘካህ ይወጅበታል፥ በሸሪዓህ የዘካህ አነስተኛ የክፍያ መጠን “ኒሷብ” نِصاب ይባላል፥ ይህም ኒሷብ የሚለካው 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ነው። “ዲናር” دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ማለት ሲሆን “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ማለት ደግሞ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው። ይህ በጥንት “የኮሞዲቲ ገንዘብ”commodity money” ይባላል።
“ዲናር” እና “ዲርሀም” የሚለኩት በሚስቃል ነው፥ “ሚስቃል” مِثْقَال የሚለው ቃል “ሰቀለ” ثَقَلَ ማለትም “ከበደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክብደት” ማለት ነው።
1 ሚስቃል ወርቅ 4.25 ግራም ነው፥ 20 ሚስቃል ወርቅ ደግሞ 4,25x 20 = 85 ግራም ወርቅ ይሆናል ማለት ነው።
1 ሚስቃል ብር 2.975 ግራም ነው፥ 200 ሚስቃል ብር ደግሞ 2.975x 200= 595 ግራም ብር ይሆናል ማለት ነው።

በዘካህ ላይ የሚወጅበው ኒሷብ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ነው።
አንድ ሙሥሊም ያለው ካፒታል በዓመት ውስጥ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ያክል ከሆነ ዘካህ ማውጣት ግዴታው ነው። ይህ ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ”Fiat money” ለመቀየር ወርቅን ዛሬ ባለው በ 24 ካራት የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል፦
1. በስውዲን አንድ ግራም ወርቅ 396 ክራውን ነው፥ 396×85= 33,660 ክራውን ይሆናል።
2. በኢትዮጵያ አንድ ግራም ወርቅ 1,181 ብር ነው፥ 1,181×85= 100,385 ብር ይሆናል።
3. በአሜሪካ አንድ ግራም ወርቅ 41.30 ዶላር ነው፥ 41.30×85= 3,510.30 ዶላር ይሆናል።

ስለዚህ አንድ ሙሥሊም ያለው ካፒታል በገንዘብ ሲተመን በስውዲን 33,660 ክራውን፣ በኢትዮጵያ 100,385 ብር፣ በአሜሪካ 3,510.30 ዶላር ወዘተ ከሆነ ከዚያ ወዲህ ዘካህ ማውጣቱ ፈርድ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው በኢትዮ 100,385 ሺ ብር ካለው ከ 100,385 ሺ ብር ላይ 2.5% ዘካ ያወጣል፥ ያ ማለት የዘካው ብር 100,385×2.5÷100= ውጤቱ 2,509 ብር ይሆናል ማለት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእግዚአብሔር ወይስ የክርስቶስ ደም?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

በክርስትና ስልታዊ ሥነ-መለኮት ውስጥ “ኢየሱስ አምላክ ነው” ብለው ድምዳሜ ላይ ካደረሳቸው አናቅጽ መካከል ይህ ጥቅስ ይጠቀሳል፦
የሐዋርያት ሥራ 20፥28 *በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን* ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። προσέχετε ἑαυτοῖς καὶ παντὶ τῷ ποιμνίῳ, ἐν ᾧ ὑμᾶς τὸ Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ἔθετο ἐπισκόπους, ποιμαίνειν τὴν ἐκκλησίαν τοῦ Θεοῦ, ἣν περιεποιήσατο διὰ τοῦ αἵματος τοῦ ἰδίου.

ቅድሚያ እንደ ባይብሉ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ መንፈስ ስጋ እና አጥንት የለውም፦
ዮሐንስ 4፥24 *እግዚአብሔር “መንፈስ” ነው*።
ሉቃስ 24፥39 *“መንፈስ ሥጋ እና አጥንት የለውምና”*።

እግዚአብሔር ስጋ ከሌለው የስጋ ደም በስጋ ውስጥ ስላለ እግዚአብሔር ደም የለውም፦
ዘሌዋውያን 17፥11 *"የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና"*።

ይህ የሥነ-አመክንዮ ሙግት ነው። ሲቀጥል እንደ ባይብሉ ደም አለው የተባለው እግዚአብሔር ሳይሆን ልጁ ነው፦
ዕብራውያን 9፥14 ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ *"ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም"*

"ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም" ማለት ደሙ የክርስቶስ እንጂ የእግዚአብሔር አለመሆኑን ያሳያል። የደሙ ባለቤት እራሱ አምላክ አለው። አምላኩ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፦
ራእይ 1፥5-6 ለወደደን ከኃጢአታችንም *በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም ለአምላኩ እና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ*።
ዕብራውያን 13፥12 ስለዚህ *ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ* ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ።
1ኛ ዮሐንስ 1፥7 *የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም* ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።

ልጁ የማን ልጅ? የእግዚአብሔር ልጅ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ደሙ የልጁ እንጂ የእግዚአብሔር አይደለም፦
1ኛ ዮሐንስ 5፥12 *ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም*።

"ሢሠልስ "ኢድኦስ" ἴδιος ማለት "ገዛ"own" ማለት ሲሆን ገላጭ ቅጽል ነው። "በገዛ" ምን? "የገዛ ልጁ" የሚል ጥሩ የተዛማች ሙግት አለ፦
ሮሜ 8፥32 *ለ-"ገዛ" ἰδίου ልጁ ያልራራለት*።
ሮሜ 8፥3 *እግዚአብሔር የገዛ ልጁን* በኃጢአተኛ *ሥጋ* ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና።

"ስጋ" የሚለው ይሰመርበት። ስጋ ያለው ልጁ ሲሆን አባቱ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፥ "የገዛ" በሚለው ቃል ውስጥ "ልጁ" የሚለው ቃል ተደብቆ የመጣ ነው። ለምሳሌ እነዚህ አናቅጽ ላይ "የገዛ" ብለን ብንተወው ትርጉም አይሰጥም፦
ዮሐንስ 1፥11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ *"የገዛ" ἴδιοι ወገኖቹም* አልተቀበሉትም።
ዮሐንስ 13፥1 "የገዛ" ἰδίους "ወገኖቹን" የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።
የሐዋርያት ሥራ 4፥23 ተፈትተውም ወደ *"ገዛ" ἰδίους "ወገኖቻቸው" መጡ።

"ወገን" የሚለው የግሪኩ ቃል "ሰገኒአ" συγγένεια ሲሆን ሦስቱም አናቅጽ ላይ የለም። ታዲያ "የገዛ አልተቀበሉትም" "የገዛ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው" "ወደ ገዛ መጡ" ትርጉም ይሰጣልን? አይ "የገዛ" በሚለው ቃል ውስጥ "ወገን" የሚለው ቃል ተደብቆ የመጣ ነው። ሌላ ናሙና፦
ዮሐንስ 19፥27 ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ *ወደ "ገዛ" ἴδια "ቤቱ" ወሰዳት*።

"ቤት" የሚለው የግሪኩ ቃል "ኡኪአ" οἰκία ሲሆን እዚህ አንቀጽ ላይ የለም። ታዲያ ወደ "ገዛ" ወሰዳት" ትርጉም ይሰጣልን? አይ "የገዛ" በሚለው ቃል ውስጥ "ቤት" የሚለው ቃል ተደብቆ የመጣ ነው። ታዲያ "ወገን" እና "ቤት" የሚለው ስለሚመጣ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ "የገዛ" በሚለው ቃል ውስጥ "ልጁ" የሚለው ቃል ተደብቆ ስለሚመጣ የሥላሴ አማንያን ሳይቀሩ "በገዛ "ልጁ" ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ" ብለው ተርጉመውታል፦
1. "the blood of his own Son."
(NET) New English Translation- 2005
2. "the blood of his own Son."
(NRSV) New Revised Standard Version – 1989
3. "the blood of his own Son."
(RSV) Revised Standard Version - 1946
4. "the death of his own Son."
(CEB) Common English Bible – 2011
5. "the blood of his own."
(DARBY) J.N.Darby – 1890
6. "his own Son’s blood."
(CJB) Complete Jewish Bible – 1998
7. "the blood of his own Son."
(CEV) Contemporary English Version – 1995
8. "the blood of his own (Son); or with his own blood."
(EXB) Expanded Bible – 2011
9. "the blood of his Son."
(GNT) Good News Translation – 1992
10. "the blood of his own Son."
(LEB) Lexham English Bible – 2010
11. "the ho blood haima of ho his own idios Son."
(MOUNCE) Mounce Reverse-Interlinear New Testament – 2011
13. "the death of his own son."
(NCV) New Century Version – 2005
13. "the blood of His own Son."
(VOICE) The Voice Bible Translation – 2011

እነዚህ 13 ስመጥርና ዝነኛ ትርጉማን እንዳልተሳሳቱ የምናውቀው የአዲሱ ዓለም ዓቀፍ ትርጉም"the New International Version(NIV) እራሱ በግርጌ ማስታወሻው፦ "ወይም በገዛ ልጁ ደሙ"Or with the blood of his own Son” መባል እንደሚችል አስፍሯል። "ገዛ"own" ገላጭ ቅጽል ስለሆነ የሚፈታው ሌላ ጥቅስ ላይ ባለው ቃል ነው፥ ለምሳሌ፦
ኤፌሶን 1፥6 *በውድ ልጁም* እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።

"ልጁ" የሚል ግሪኩ ላይ የለም። ግን "ውድ" የሚለውን ገላጭ ቅጽል ሌላ ቦታ "ውድ ልጄ" በሚለው ይፈታል፦
ማቴዎስ 3፥17 *ውድ ልጄ ይህ ነው"* አለ።

ኤፌሶን 1፥6 ላይ ልጁ የሚለውን ካላስገቡ ደሙ የአብ ሆኖ ያርፋል፦
ኤፌሶን 1፥7 *በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ* የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።
"ልጁ" የሚል ግሪኩ ላይ የለም። ዐውዱ ስለ አብ ስለሚናገር አንደኛችሁን እንደ ቄስ ተክለ-ማርያም ገዛኸኝ ደሙ የአብ ነው ብላችሁ እረፉት። "ውድ" የሚለውን "በውድ ልጁ" በሚል እንደተረዳችሁት፥ "ገዛ" የሚለውን "በገዛ ልጁ" በሚል ተረዱት።
ሲያረብብ የሐዋርያት ሥራ "ሄን" ἣν ማለትም "እርሱ" የሚለው አንጻራዊ ተውላጠ-ስም "ክርስቶስ" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፦
1 ጴጥሮስ 1፥19 *በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ*።

አየህ "በገዛ ደሙ የዋጃትን" የሚለውን "በክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ" በሚለው ይፈታል፥ በቀላሉ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በገዛ ደሙ መዋጀቱን ያሳያል። ክርስቶስ ደግሞ እግዚአብሔር ሳይሆን የእግዚአብሔር ነው፥ እግዚአብሔር ለክርስቶስ ራስ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ*።

ጳውሎስ፦ "አንድ እግዚአብሔር አለ፥ በእግዚአብሔር እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" ብሎናል፥ ደሙ የእግዚአብሔር ሳይሆን በመካከለኛ ያለው የሰው ደም ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 2፥5 *አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔር እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*።
ዕብራውያን 12፥23 *የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት "ደም" ደርሳችኋል*።

የሚገርመው እኮ "ቴኦዩ" Θεοῦ ማለትም "የእግዚአብሔርን" ቤተክርስቲያን የሚል የግሪክ እደ-ክታባት እንዳለ ሁሉ "ኩርዮዩ" Κυρίοῦ ማለትም "የጌታን" ቤተክርስቲያን የሚል አለ። American Standard Version በበኩሉ በገዛ ደሙ የዋጃትን የጌታን ቤተ ክርስቲያን" ብለው ተርጉመውታል፦
Acts 20:28 (ASV) The church of the *Lord* which he purchased with his own blood.

የ 1980 አዲስ ትርጉም፦ "ጌታ በገዛ ደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ" ብለው ተርጉመውታል፦
የሐዋርያት ሥራ 20፥28 *ጌታ በገዛ ደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ*።

አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ ላይም ፦ "ብዙ የጥንት ቅጆች የጌታን" እንዳሉት እና "በገዛ ልጁ ደም ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፥ የገዛ የሚለው ቃል ተወዳጅነትን ለመግለጽ የገባ ቃል ነው። ይህም ልጁን ያመለክታል" ብሎ ተናግሯል። ይህ የትርጉም ሥራ ሢሠራ ከተሳተፉት መካከል ምራቅ የዋጠ ተወያይ የሚባለው ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ሲሆን፥ ግን እርሱ፦ "በገዛ ደሙ የዋጃትን የጌታን ቤተ ክርስቲያን" እና "በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን የእግዚአብሔ ቤተ ክርስቲያን" የሚል የለም" ሲል ቀጥፏል። ብዙ ጊዜ ይዋሻል፥ ወትሮም አባይ መዋሸት ልምዱ ነው።
በጥቅሉ የጳውሎስ ንግግር ላይ "የልጅ ደም" ወይም "መዋጀት" አሊያም "ልጅ" የእኛ የሙሥሊሞች እሳቤ አይደለም። ዋናው ነጥብ የሐዋርያት ሥራ 20፥28 ላይ ጳውሎስ "እግዚአብሔር ደም አለው" አላለም የሚል ነው። ፈጣሪ የፍጡር ደም ጥገኝነት አይጠይቅም፥ ፍጡሩን ኢየሱስ ፈጣሪ ነው ማለት ክህደት ነው፦
5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሊቃውንት እና መነኮሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

9፥31 *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፥ እንዲሁ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው*፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ሚሽነሪዎች፦ "እኛ ሊቃውንቶቻችንን እና መነኮሳቶቻችንን አማልክት አድርገን አልያዝን፥ እነርሱን አምልከንም አናውቅም። ስለዚህ ቁርኣን ያቀረበብን ክስ አግባብ አይደለም" ይላሉ። በኢሥላም ያሉ የመስኩ ሊሒቃን፦ “ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ” ይላሉና እኛም ከሥሩ ይህንን ተጻራሪ ምልከታ እንመልከት።
"ሐብር" حَبْر ወይም "ሒብር" حِبْر ማለት "ምሁር" "ሊቅ" "ዐዋቂ" ማለት ነው፥ የሐብር ወይም የሒብር ብዙ ቁጥር ደግሞ "አሕባር" أَحْبَار ሲሆን "ምሁራን" "ሊቃውንት" "ሊሒቃን" ማለት ነው። እነዚህም ምሁራን የአይሁዳውያን ምሁራን ናቸው፦
26፥197 *የእስራኤል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መኾኑ ለእነርሱ(ለመካ ከሓዲዎች) ምልክት አይኾናቸውምን?* أَوَلَمْ يَكُن لَّهُمْ آيَةً أَن يَعْلَمَهُ عُلَمَاءُ بَنِي إِسْرَائِيلَ

"ዐሊም" عَلِيم ማለት "ዐዋቂ" ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ የተቀመጠው የዐሊም ብዙ ቁጥር "ዑለማእ" عُلَمَاء ሲሆን "ሊቃውንት" ማለት ነው።
"ራሂብ" رَاهِب ማለት "መነኩሴ" ማለት ነው፥ የራሂብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሩህባን" رُهْبَان ሲሆን "መነኮሳት" ማለት ነው። እነዚህም መነኮሳት የክርስቲያን መነኮሳት ናቸው፦
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውሰጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፡፡ *”አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም*”፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ وَجَعَلْنَا فِي قُلُوبِ الَّذِينَ اتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا ۖ فَآتَيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَاسِقُونَ

ክርስቲያኖች አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አላህ በእነርሱ ላይ አልደነገገም፥ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት።
እዚህ ድረስ ከተግባባን ድንጋጌ ውስጥ አምስት ሕግጋት አሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فَرْد‎ ማለትም “የታዘዘ” ግዴታ ነው።
2ኛ. “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ሡናህ ነው።
3ኛ. “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ ማለትም “የተፈቀደ” ሐላል ነው።
4ኛ. “መክሩህ” مَكْرُوه‎ ማለትም “የተጠላ” ድርጊት ነው።
5ኛ. “ሐራም” حَرَام ማለትም “የተከለከለ” ድርጊት ነው።
አንድን ነገር ፈድር፣ ሙስተሐብ፣ ሙባሕ፣ መክሩህ፣ እና ሐራም ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ሆኖ ሳለ የአይሁዳውያን ሊቃውንት እና የክርስትና መነኮሳት ሐላሉን ሐራም፥ ሐራሙን ሐላል በማድረግ ሕግጋትን ከገዛ ዝንባሌአቸው ደነገጉ፦
9፥31 *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፥ እንዲሁ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው*፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር "አማልክት አድርገው ያዙ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ በዚህ ሐዲስ ፈሥሮታል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3378
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው፦ *"ወደ ነቢዩም”ﷺ” ስመጣ በአንገቴ ዙሪያ የወርቅ መስቀል ነበረኝ፥ እርሳቸውም፦ "ይህንን ጣዖት ከአንተ አስወግድ" አሉ። ሱረቱል በራኣህ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" የሚለው ሲነበብ ሰማዋቸው። እርሳቸውም፦ ለእነርሱ አያመልኳቸውም፥ ነገር ግን ሐላል ባደረጉላቸው ጊዜ ሐላል አርገው ይቀበሉታል። ሐራም ባደረጉላቸው ጊዜ ሐራም አርገው ይቀበሉታል" አሉ*። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، قَالَ أَتَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَفِي عُنُقِي صَلِيبٌ مِنْ ذَهَبٍ ‏.‏ فَقَالَ ‏"‏ يَا عَدِيُّ اطْرَحْ عَنْكَ هَذَا الْوَثَنَ ‏"‏ ‏.‏ وَسَمِعْتُهُ يَقْرَأُ فِي سُورَةِ بَرَاءَةََ ‏:‏ ‏(‏ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ ‏)‏ قَالَ ‏"‏ أَمَا إِنَّهُمْ لَمْ يَكُونُوا يَعْبُدُونَهُمْ وَلَكِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا أَحَلُّوا لَهُمْ شَيْئًا اسْتَحَلُّوهُ وَإِذَا حَرَّمُوا عَلَيْهِمْ شَيْئًا حَرَّمُوهُ
መስቀል በአንገት ላይ ማድረግ ከመነኮሳት የመጣ ትእዛዝ እንጂ ከአላህ ዘንድ አይደለም። ሲጀመር "ረብ" رَبّ የሚለው ቃል "ረበ" رَبَّ ማለትም "አዘዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጌታ" ወይም "አዛዥ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አርባብ" أَرْبَاب ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። "አላህ ብቻውን ትእዛዝ አውጪ ነው" ብሎ አላህ ከፍጡራን መነጠል "ተውሒደ አር-ሩቡቢያህ" تَوْحِيد الرُبُوبِيّة ነው፥ "ሩቡቢያህ" رُبُوبِيّة ማለት በራሱ "ጌትነት" ማለት ነው። "ያልታዘዙ ሲኾኑ" የሚለው ይህንኑ ነው፥ ነቢያችን"ﷺ" ሆኑ አሚሮቻችን አላህ ባዘዘው ያዛሉ፥ በከለከለው ይከለክላሉ እንጂ የእራሳቸው ድንጋጌ አያወጡም። ነገር ግን አይሁዳውያን ሊቃውንቶቻቸውን ክርስቲያኖች መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ ድንጋጌ በመቀበል ጌቶች አድርገው ያዙ። "አያመልኳቸውም" የሚለው ይሰመርበት፥ አላህ በአምልኮ ከፍጡራን መነጠል "ተውሒደል ኡሉሂያህ" تَوْحِيد الأُلُوهِيَّة ነው፥ "ኡሉሂያህ" أُلُوهِيَّة ማለት በራሱ "አምላክነት" ማለት ነው። ተውሒድ ትክክለኛ የሆነች ቃል ናት፥ ተውሒደል ኡሉሂያህ "አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ" ነው፣ ተውሒደ አር-ሩቡቢያህ "ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርጎ ላይዝ" ነው፦
3፥64 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርጎ ላይዝ ነው"* በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ

ነገር ግን መደንገግ የሚችለው አላህ ብቻ ሆኖ ሳለ ሌላ ማንነት የደነገገውን ድንጋጌ ማድረግ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ ሕግን የሚደነግግልን አርባብ አድርጎ መያዝ ነው፥ ይህ በአላህ ጌትነት ላይ ማሻረክ ነው፦
42፥21 ከሃይማኖት *አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?* أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

"ሸሪክ" شَرِيك ማለት "ተጋሪ" ማለት ነው፥ የሸሪክ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሹረካእ" شُرَكَاء ሲሆን "ተጋሪዎች" ማለት ነው፥ አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ነገር ሐላል ማድረግ ለእነርሱ የደነገጉ በአላህ ሐቅ ላይ ተጋሪዎች አሏቸው። ለዚህ ነው "ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው" ነው ያለው፥ ስለዚህ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን በአላህ ላይ በማጋራት ጌቶች አድርገው ያዙ ማለት በዚህ ስሌት እንረዳዋለን።
ሲቀጥል "ጌቶች" የሚለው "አማልክት" ተብሎ ቢቀመጥም "አምላክ አድርጎ መያዝ" ማለት ያንን ማንነት ሆነ ምንነት በቀጥታ ማምለክ ብቻ አይደለም። ምክንያቱም ለአላህ የሚገባውን ሐቅ ለዝንባሌ መስጠት በራሱ አምላክ አድርጎ መያዝ ከሆነ ለአላህ የሚገባውን ሐቅ ለሊቃውንቶቻቸውን እና ለመነኮሳታቸውን መስጠት አምላክ አድርጎ መያዝ ነው፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

መቼም ዝንባሌውን በቀጥታ "አምላኬ" እያለ የሚያመልክ ፍጡር የለም። ዝንባሌ ከነፍሢያችን ነው፥ ነፍሢያህ አላህ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በሐራም ነገር በእርግጥ አዛዥ ናት። ነፍሢያህ ሐራሙን በማዘዟ ዝንባሌን አምላክ አድርጎ እንደሚያዝ ሁሉ እነርሱም ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን በሐራም በመታዘዝ፥ በሐላል በመከልከል አምላክ አድርገው ይዘዋል። ከላይ የቀረበው ተጻራሪ ምልከታ በዚህ የሙግት አግባብ ሐቁን አውጥተናል፥ ባጢል በሐቅ ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ፀሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል፦
17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

የዐሊማችን የሼኽ ኢብራሂም ሲራጅ ከዱንያ መለየት የተሰማን ጥንቅ ሀዘን በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ይህ ጥልቅ ሀዘን ሲነካን፦ "ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُون ብለናል፦
2፥156 እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን» የሚሉትን አብስር፡፡ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

አምላካችን አላህ ለቤተሰባቸው፣ ለተማሪዎቻቸው እና ለሚወዷቸው ሁሉ ጽናቱን፣ መጽናናቱን እና ትእግስቱ ይስጠን። ሃዘናችንን አጅር የምናገኝበት ያርግልን። እርሳቸውንም ጀነቱል ፊርደውሥ ይወፍቃቸው! አሚን።
ተስዊር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

59፥24 *እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ አስገኚው፣ "ቅርፅን አሳማሪው" ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ

አምላካችን አላህ በማኅፀን ውስጥ እንደሚሻ አርጎ የሚቀርፀን እርሱ ነው፥ እርሱ በሚሻው መንገድ ስለሚቀርፀን "አል-ሙሶዊር" الْمُصَوِّرُ የሚል ስም አለው፦
59፥24 *እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ አስገኚው፣ "ቅርፅን አሳማሪው" ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
3፥6 *እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርፃችሁ ነው*፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
64፥3 ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ፡፡ *ቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም አሳመረ*፡፡ መመለሻችሁም ወደ እርሱ ነው፡፡ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ ۖ وَإِلَيْهِ الْمَصِيرُ
82፥8 *በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ*፡፡ فِي أَيِّ صُورَةٍ مَّا شَاءَ رَكَّبَكَ

"ሙሶዊር" مُصَوِّر የሚለው ቃል "ሶወረ" صَوَّرَ ማለትም "ቀረፀ" "ሳለ" "ሠራ" "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቀራፅ" "ሰዓሊ" "ሠሪ" "ፈጣሪ" ማለት ነው። አላህ አደምን በሚሻው ቅርፅ ፈጥሮታል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"አላህ አደምን በቅርጹ ፈጠረ፥ ስፋቱ ስድሳ ይዘት ነበር። በፈጠረው ጊዜ፦ ሒድና እዚያ የተቀመጡትን የመላእክት ቡድን ሰላም በል! ሰላምታህን ምን ብለው እንደሚመልሱ ስማቸው! ሰላምታህም የአንተና የዝርያህ ሰላምታ ትሆናለች" አለው። አደምም፦ "አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም" አለ፥ እነርሱም፦ "አሥ-ሠላሙ ዐለይከ ወራሕመቱሏህ" አሉ፥ እነርሱ፦ "ወራሕመቱሏህ" ጨበሩለት። ነቢዩም"ﷺ"፦ *"ማንም ጀነት የሚገባው በአደም ቅርፅ ነው" አሉ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ، طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا، فَلَمَّا خَلَقَهُ قَالَ اذْهَبْ فَسَلِّمْ عَلَى أُولَئِكَ النَّفَرِ مِنَ الْمَلاَئِكَةِ جُلُوسٌ، فَاسْتَمِعْ مَا يُحَيُّونَكَ، فَإِنَّهَا تَحِيَّتُكَ وَتَحِيَّةُ ذُرِّيَّتِكَ‏.‏ فَقَالَ السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ‏.‏ فَقَالُوا السَّلاَمُ عَلَيْكَ وَرَحْمَةُ اللَّهِ‏.‏ فَزَادُوهُ وَرَحْمَةُ اللَّهِ، فَكُلُّ مَنْ يَدْخُلُ الْجَنَّةَ عَلَى صُورَةِ آدَمَ

"ሱራህ" صُورَة‎ በሚለው ቃል መድረሻ ላይ ያለው "ሂ" هِ የሚለው አገናዛቢ ተውላጠ ስም "አደም" آدَم የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፥ ምክንያቱም "ሱራቲ-አደም" صُورَةِ آدَمَ የሚለው "ሱራቲ-ሂ" صُورَتِهِ ለሚለው ተለዋዋጭ ነው። "ሱራቲ-ሂ" صُورَتِهِ የሚለው ወደ አላህ የሚጠጋ ነው" የሚሉ ምሁራን አሉ። ይህንን ለመረዳት ስለ ኢዷፋህ እሳቤው ሊኖረን ይገባል። "ኢዷፋህ" إِضَافَة የሚለው ቃል "አዷፈ" أَضَافَ‎ ማለትም "አገናዘበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አገናዛቢ"possessive" ማለት ነው፥ የኢዷፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኢዷፋት" إِضَافَات‎ ነው። ኢዷፋህ በሁለት ዐብይ ክፍል ይከፈላሉ፥ እነርሱም "ኢዷፈቱ አሽ-ሸሪፋህ" إِضَافَة الشَرِيفَة እና "ኢዷፈቱ አስ-ሲፋህ" إِضَافَة الصِفَة ናቸው።

ነጥብ አንድ
"ኢዷፈቱ አሽ-ሸሪፋህ"
"ሸሪፋህ" شَرِيفَة የሚለው ቃል "ሸሩፈ" شَرُفَ ማለትም "ላቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እልቅና" ማለት ነው፥ የሸሪፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሸሪፋት" شَرِيفَات‎ ነው። ነቢያችን"ﷺ" የአደምን ቅርፅ ወደ አላህ በማስጠጋት በአገናዛቢ "ቅርፁ" ማለታቸው እልቅናን ያመለክታል፥ ልክ የአላህ ቤት፣ የአላህ ግመል፣ የአላህ ምድር ተብሎ በቁርኣን እደተቀመጠው ማለት ነው፦
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም *ቤቴን* ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ
11፥64 ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን *የአላህ ግመል ናት*፡፡ ተውዋትም፡፡ *በአላህ ምድር* ውስጥ ትብላ፡፡ በክፉም አትንኳት፡፡ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና» አላቸው፡፡ وَيَا قَوْمِ هَـٰذِهِ نَاقَةُ اللَّهِ لَكُمْ آيَةً فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِي أَرْضِ اللَّهِ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ قَرِيبٌ

ቤት፣ ግመል፣ ምድር የአላህ ባሕርይ ሳይሆኑ እልቅና ለመስጠት እንደሆኑ ሁሉ "የአደም ቅርፅ" ወደ አላህ በማስጠጋት እልቅና ሰቶቷል። ይህ አንዱ የምሁራን እይታ ነው።

ነጥብ ሁለት
"ኢዷፈቱ አስ-ሲፋህ"
"ሲፋህ" صِفَة የሚለው ቃል "ወሰፈ" وَصَفَ‎ ማለትም "ገጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መገለጫ" ወይም "ባሕርይ" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሲፋት" صِفَات‎ ነው። "ሱራህ" صُورَة‎ የሚለው ቃል "መልክ" በሚል ከመጣ ባሕርይን ታሳቢ ያደረገ ነው፥ የአላህ ዕውቀት፣ የአላህ ቻይነት፣ የአላህ እይታ፣ የአላህ መስማት፣ የአላህ እጅ ወዘተ የአላህ ባሕርያት ናቸው። አላህ በባሕርይው አደምን ፈጥሮታል፥ ለምሳሌ በእጆቹ ፈጥሮታል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት* ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

ይህ የምሁራን ሁለተኛ እይታ ነው። ኢንሻላህ ስለ ተስዊር በክፍል ሁለት እንዳስሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተኩላ እና አህያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَابٍ مُّنِيرٍ

ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላ እና አህያ፦ "የሳር ቀለም እንዲህ ነው እንዲያ ነው" በሚል ክርክር ውስጥ ገቡ። አህያ፦ “የሳር ቀለም ቢጫማ ነው” አለ። ተኩላ፦ "በፍፁም ! አረንጓዴ ነው” አለ።
ክርክራቸው እየጦፈ መጣ፤ ሊያስማማ የሚችል ነጥብ ላይ መድረስ አልቻሉም። በመጫረሻም የጫካ ንጉሥ ከሆነው አንበሳ ዘንድ ቀርበው መሸማገል እንዳለባቸው ወሰኑ። ሽምግልናው ተጀመረ፥ ሁለቱም የመከራከሪያ አሳባቸውን አቀረቡ። አንበሳም የሁለቱን የመከራከያ ነጥብ በጥሞና አዳመጠ፥ የፍርድ ሒደቱን ለመከታተል የታደሙት እንስሳት በሙሉ ውሳኔውን ለመስማት ጆሯቸውን ጣል አደረጉ። አንበሳው ታዳሚውንም ሆነ ተኩላውን ቅር የሚያሰኝ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ፥ ተኩላው በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ ሲወሰንበት፤ አህያው ደግሞ በነፃ ተሰናበተ።

በፍርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ተኩላ እንዲህ በሚል ስሞታ አቀረበ፦ "ክቡር አንበሳ ሆይ! የሳር ቀለም አረንጓዴ አይደለምን? አንበሳም፦ "አዎ! በርግጥ አረንጓዴ ነው” በማለት መለሰ። ተኩላውም፦ "ታዲያ በየትኛው ጥፋቴ ነው ለአንድ ወር ያክል ዘብጥያ እንድወርድ የወሰንክብኝ? አንበሳውም፦ “ትክክል ነህ! በአመለካከትህ ቅንጣት ስህተት አላስተዋልኩም። ጥፋትህ በዚህ ጉዳይ ከአህያ ጋር ክርክር ውስጥ መግባትህ ነው። ነገሮችን በጥልቀት መረዳት እና መገንዘብ ከማይችል አካል ጋር መከራከር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዘን አንደሚችል የአንድ ወር እስራት የወሰንኩብህ ትምህርት ትቀስም ዘንድ ብየ ነው” አለው።
ከተኩላ እና ከአህያው የምንማረው ቁምነገር ቢኖር ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም ከሚከራከር ሰው ጋር ጊዜን፣ ጉልበትን፣ ዕውቀትን አለማባከንን ነው፦
22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَابٍ مُّنِيرٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተስዊር

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

"ሙሶዊር" مُصَوِّر ማለት "ቀራፅ" "ሰዓሊ" "ሠሪ" "ፈጣሪ" ማለት እንደሆነ አይተን ነበር፥ የሙሶዊር ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሙሶዊሩን" مُصَوِّرُون ወይም "ሙሶዊሪን" مُصَوِّرِين ሲሆን "ቀራፆች" "ሰዓሊዎች" ማለት ነው፦
23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

"ሰዓሊዎች" ለሚለው ቃል የገባው "ኻሊቂን" خَالِقِين ሲሆን "ሙሶዊሪን" مُصَوِّرِين ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 150
ዐብደላህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ከሰዎች በጣም ተቀጪ ሰዓሊዎች ናቸው"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ أَشَدَّ النَّاسِ عَذَابًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ الْمُصَوِّرُونَ ‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 182
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የስዕላት ባለቤት በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፥ ለእነርሱም፦ "የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ" ይባላሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ

ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው። ነቢያችን”ﷺ” በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው፥ ይህም “ጀዋሚዓል ከሊም” ነው። “ጀዋሚዓል ከሊም” جَوَامِعَ الْكَلِم ማለት “አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ትርጉም ያለው” ማለት ነው። "ሱራህ" صُورَة‎ ማለት ብዙ አውራ ትርጉም ያለው ሲሆን "ስዕል" "ቅርፅ" "መልክ" "ፎቶ" ማለት ነው፥ "ሱወር" صُوَر ደግሞ የሱራህ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ስዕላት" "ቅርፃት" ማለት ነው። "የፈጠራችሁትን" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቅቱም" خَلَقْتُمْ ሲሆን ስዕሉን ስለሳሉት እና ቅርፁን ስለቀረፁት እንጂ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተውት አይደለም፥ ይህ "ኢሕቲራዕ" اِخْتِرَاع ማለትም "ፈጠራ" ነው። በእጃቸው የፈጠሩትን ላይ እንደ አላህ ሩሕ ማድረግ አይችሉም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 77, ሐዲስ 179
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"በዚህ ዓለም ቅርፅ የቀረፀ በትንሳኤ ቀን በውስጡ ሩሕ እንዲነፋበት ይጠየቃል፥ ግን መንፋት አይችልም"*። فَقَالَ سَمِعْتُ مُحَمَّدًا صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ مَنْ صَوَّرَ صُورَةً فِي الدُّنْيَا كُلِّفَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنْ يَنْفُخَ فِيهَا الرُّوحَ، وَلَيْسَ بِنَافِخٍ

እዚህ ሐዲስ "ሶወረ" صَوَّرَ ማለት "ቀረፀ" "ሳለ" "ሠራ" ማለት ነው። "ኸልቅ" خَلْق የሚለው ቃል "ተስዊር" تَصْوِير ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ እንደገባ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ይህ የቋንቋ ሙግት ታሳቢ ያደረገ ነው። ነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦቻቸውን ወደ ሐበሻህ ሲልኳቸው ከሔዱት መካከል በአክሱም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስዕላትን አይተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 77
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"ኡሙ ሐቢባህ እና ኡሙ ሠለማህ በሐበሻህ ስላዩአት በውስጧ ስዕሎች ስለነበሩባት ቤተክርስቲያን ዘክረዋል፥ ስለዚህ ለነቢዩም"ﷺ"ዘክረዋል። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "በእነዚያ ሰዎች መካከል የትኛውም ሷሊሕ ሰው ቢሞት በመቃብሩ ላይ የአምልኮ ስፍራ ቢገነቡ እና እነዚህን ስዕላት ቢያደርጉ፥ በትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው"*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ أُمَّ حَبِيبَةَ، وَأُمَّ سَلَمَةَ ذَكَرَتَا كَنِيسَةً رَأَيْنَهَا بِالْحَبَشَةِ فِيهَا تَصَاوِيرُ، فَذَكَرَتَا لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّ أُولَئِكَ إِذَا كَانَ فِيهِمُ الرَّجُلُ الصَّالِحُ فَمَاتَ بَنَوْا عَلَى قَبْرِهِ مَسْجِدًا، وَصَوَّرُوا فِيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ، فَأُولَئِكَ شِرَارُ الْخَلْقِ عِنْدَ اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ

"ተስዊራህ" تَصْوِيرَة ማለት "ስዕል" ማለት ነው፥ የተስዊራህ ብዙ ቁጥር "ተሷዊር" تَصَاوِير ማለት ሲሆን "ስዕላት" ማለት ነው። ስዕል በአምልኮ ውስጥ ምንም ሚና መኖር የለበትም፥ የሥላሴ፣ የኢየሱስ፣ የማርያም፣ የመላእክት እና የቅዱሳን ሰዎች ስዕል ስሎ በፊታቸው መለማመን ባዕድ አምልኮ ነው። በተመሳሳይ ቁረይሾች የአላህ ቤት ውስጥ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በእጆቻቸው አዝላም የያዙ አስመስለው ስዕላት ስለው ነበር፥ "አዝላም" أَزْلاَم ማለት "የጥንቆላ ቀስት" ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" በአላህ ቤት ስዕላት በተመለከቱ ጊዜ ባልደረቦቻቸው እንዲያጠፉ እንኪያዙ ድረስ ወደ እዚያ አልገቡም። ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል"ሠላም በእነርሱ ላይ ይሁን! በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ነበሩ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "አላህ ይርገማቸው(ቁረይሾችን)! ወሏሂ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በአዝላም አይለማመዱም"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم لَمَّا رَأَى الصُّوَرَ فِي الْبَيْتِ لَمْ يَدْخُلْ، حَتَّى أَمَرَ بِهَا فَمُحِيَتْ، وَرَأَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ ـ عَلَيْهِمَا السَّلاَمُ ـ بِأَيْدِيهِمَا الأَزْلاَمُ فَقَالَ ‏ "‏ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ، وَاللَّهِ إِنِ اسْتَقْسَمَا بِالأَزْلاَمِ قَطُّ
የኢብራሂም አባት እና የኢብራሂም ሕዝቦች ቅርጻ ቅርጽ የሆነ አስናምን ያመልኩ ነበር፥ “አስናም” أَصْنَام ማለት ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሠርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ናቸው፦
26፥70 *ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ታመልካላችሁ?*» ባለ ጊዜ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ
26፥71 *አስናምን እናመልካለን፥ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًۭا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
21፥52 ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ «ይህቺ *"ቅርጻ ቅርጽ"* ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَا هَـٰذِهِ التَّمَاثِيلُ الَّتِي أَنتُمْ لَهَا عَاكِفُونَ

"ቲምሳል" تِمْثَال ማለት "ምስል" "ቅርጽ" ማለት ነው፥ የቲምሳል ብዙ ቁጥር ደግሞ "ተማሲል" تَمَاثِيل ሲሆን "ምስሎች" "ቅርጻ ቅርጽ" ማለት ነው። የአምልኮ ይዘት ያላቸው ማንኛውም ምስል ሆነ ስዕል ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 156
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ምስሎች ወይም ስዕሎች ያለበት ቤት አይገቡም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ تَمَاثِيلُ أَوْ تَصَاوِيرُ

ስለ ሱራህ በመስኩ ምሁራን ዘንድ ያለው እይታ በአራት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. ለምንም ነገር ሱራህ መጠቀም ሐራም ነው፣
2ኛ. በእጅ የተሠራ እንጂ ልክ እንደ መስታዎት እራሳችንን የሚያሳዩ በካሜራ እና በፊልም የሚታዩ ነገሮች ችግር የላቸውም፣
3ኛ. ለፓስፓርት፣ ለመታወቂያ እና ለሰርተፍኬት ብቻ መጠቀም ይቻላል፣
4ኛ. ለአምልኮ አንጠቀም እንጂ ስዕል እና ቅርጻ ቅርጽ በራሱ ሥነ-ጥበብ"art" ነው" የሚሉ ናቸው።
አራተኛውን እይታ ለማስደገፍ፦ "ሡለይማን በቤተ-መንግሥቱ ምስሎች አድርጓል፥ እነዚህ ምስሎች ስዕሎች ነበሩ" ይላሉ፦
34፥13 *ከምኩራቦች፣ "ከምስሎችም"፣ እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል*፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ ۚ اعْمَلُوا آلَ دَاوُودَ شُكْرًا ۚ وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِيَ الشَّكُورُ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 34፥13
ወሱዲይ ከወድሐክን፣ ዐጢይል ዐውፊይ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ *"ምስሎች ማለት ስዕሎች ናቸው"*። فقال عطية العوفي ، والضحاك والسدي : التماثيل : الصور

በሱራህ እሳቤ ዙሪያ "አንጡራ መረጃ አላገኘንም" ካላችሁ በአካባቢያችሁ ወደሚገኙት ምሁራን እና ሊሒቃን ጎራ ብላችሁ ጠይቁ! አሏሁ አዕለም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መካህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

90፥1 *"በዚህ አገር እምላለሁ"*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِهَـٰذَا الْبَلَدِ

"መካህ" مَـكَّـة‎ ማለት "የተመጠመጠ" ማለት ሲሆን "በካህ" بَكَّة ማለት ደግሞ የመካህ ተለዋዋጭ ቃል ነው። ልክ አንድ ሕጻን ልጅ የእናቱን ጡት ምጥጥ እንደሚያደርግ ሁሉ ስፍራው ውኃ ምጥጥ የሚያረግ ስለሆነ ይህንን ስም ተሰየመ። ይህ አገር አላህ የማለበት እና ነቢያችን"ﷺ" የሰፈሩበት አገር ነው፥ አላህም የዚህ አገር ጌታ ተብሏል፦
90፥1 *"በዚህ አገር እምላለሁ"*፡፡ لَا أُقْسِمُ بِهَـٰذَا الْبَلَدِ
90፥2 *"አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን"*፡፡ وَأَنتَ حِلٌّ بِهَـٰذَا الْبَلَدِ
27፥91 *"የታዘዝኩት የዚህችን አገር ጌታ ያንን ክልል ያደረጋትን እንዳመልክ ብቻ ነው"*፡፡ ነገሩንም ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ከሙስሊሞችም እንድኾን ታዝዣለሁ" በላቸው፡፡ إِنَّمَا أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ رَبَّ هَـٰذِهِ الْبَلْدَةِ الَّذِي حَرَّمَهَا وَلَهُ كُلُّ شَيْءٍ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِين

ይህ አገር ጸጥተኛ አገር ነው፥ ኢብራሂም በዱዓው ይህ አገር ጸጥተኛ እንዲሆን እና እርሱና ልጆቹንም ጣዖታትን ከማምለክ እንዲያርቅ አላህን የለመነበት አገር ነው፦
95፥3 *"በዚህ በጸጥተኛው አገርም እምላለሁ"*፡፡ وَهَـٰذَا الْبَلَدِ الْأَمِينِ
2፥126 ኢብራሂም ባለ ጊዜ አስታውስ፦ "ጌታዬ ሆይ! *"ይህንን ጸጥተኛ አገር አድርግ"*፡፡ وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ اجْعَلْ هَـٰذَا بَلَدًا آمِنًا
14፥35 ኢብራሂምም ባለ ጊዜ አስታውስ፦ «ጌታዬ ሆይ! *"ይህንን አገር ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከማምለክ አርቀን"*፡፡ وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ اجْعَلْ هَـٰذَا الْبَلَدَ آمِنًا وَاجْنُبْنِي وَبَنِيَّ أَن نَّعْبُدَ الْأَصْنَامَ

አምላካችን አላህ በዚህ አገር በሚገኘው ጥንታዊ ቤት አጽንዖት ለመስጠት ምሏል፥ እልቅና እና ክብር በመስጠት ወደ ራሱ በማስጠጋት “በይቲይ” بَيْتِىَ ማለትም “ቤቴ” በማለት ይናገራል፦
52፥4 *"በደመቀው ቤትም እምላለው"*፡፡ وَالْبَيْتِ الْمَعْمُورِ
22፥26 ለኢብራሂምም፦ *”የቤቱን” ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በእኔ ምንንም አታጋራ! ”ቤቴንም” ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ”ባልነው ጊዜ አስታውስ”*። وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ

"ሚዞሩት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጧዒፊን” طَّائِفِين መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ጦዋፍ” طَواف የሚለው ቃል “ጧፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዙረት” ማለት ነው። ቤቱን በመጎብኘት ሰባት ጊዜ መዞር አምላካችን አላህ ለኢብራሂም የሰጠው ትእዛዝ ነው፦
22፥29 ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይሙሉ፤ *በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ*፡፡ ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ

“ይዙሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጠወፉ” يَطَّوَّفُوا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቤቱን የሚዞሩት ዘዋሪዎች ደግሞ “ጧዒፍ” طَآئِف ይባላሉ፥ ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት በዚህ አገር ውስጥ ይገኛል፦
3፥96 *"ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው"*፡፡ إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ

የዚህን ቤት መሠረት የጣለው ኢብራሂም ነው፥ መካህን የቀደሰውም እርሱ ነው። ነቢያችን"ﷺ" መዲናን ለመሥጂድ እንደቀደሱት ኢብራሂም መካህን ለመስጂደል ሐረም ቀድሶታል፦
2፥127 *ኢብራሂምና ኢስማኢልም* «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ *"ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 15, ሐዲስ 521
ጃቢር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ኢብራሂም መካን ቀድሷል፥ እኔም መዲናን ቀድሻለው"*። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ حَرَّمَ مَكَّةَ وَإِنِّي حَرَّمْتُ الْمَدِينَةَ

"ሐረምቱ" حَرَّمْتُ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። "ሐረመ" حَرَّمَ ማለት "ቀደሰ" ወይም "አከበረ" ማለት ነው፥ ይህ መካህ የሚገኘው ቤት እራሱ "በይተል ሐረም” ْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ ማለትም “የተቀደሰው ቤት” ወይም "የተከበረው ቤት" ይባላል፦
14፥37 «ጌታችን ሆይ! እኔ *"አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ፡፡ ጌታችን ሆይ! ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ አስቀመጥኳቸው"*፡፡ ከሰዎችም ልቦችን ወደ እነርሱ የሚናፍቁ አድርግ፡፡ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው፡፡ رَّبَّنَا إِنِّي أَسْكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِي بِوَادٍ غَيْرِ ذِي زَرْعٍ عِندَ بَيْتِكَ الْمُحَرَّمِ رَبَّنَا لِيُقِيمُوا الصَّلَاةَ فَاجْعَلْ أَفْئِدَةً مِّنَ النَّاسِ تَهْوِي إِلَيْهِمْ وَارْزُقْهُم مِّنَ الثَّمَرَاتِ لَعَلَّهُمْ يَشْكُرُون

ኢብራሂም በተከበረው ቤት አጠገብ ከዘሮቼምቹ ሶላትን ያቋቁሙ ዘንድ አስቀምጧል፥ ከዘሮቹም አዘውትረው ለአላህ የሚሰግዱ እና የሚታዘዙ እንዲሆኑ ዱዓ አርጓል፦
10፥40 «ጌታዬ ሆይ! *ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም አድርግ*፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ። رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ
2፥128 «ጌታችን ሆይ! *"ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ"*፡፡ ሕግጋታችንንም አሳውቀን፡፡ በእኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና፡፡» رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ
"ሙሥሊመይኒ" مُسْلِمَيْنِ ሙሰና ሲሆን ለሁለቱ ማለትም ለኢብራሂም እና ለኢሥማዒል የገባ ቃል ነው፥ "ለአንተ ታዛዦችም አድርገን" ማለቱ ይህንን ያሳያል። "ሙሥሊማህ" مُّسْلِمَة ደግሞ "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው አንስታይ መደብ ሲሆን አምላካችን አላህ የኢሥላምን አስኳል የተውሒድን ቃል በዝርዮቹም ውስጥ ቀሪ ቃል አርጓታል፦
43፥28 *”በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ ቀሪ ቃል አደረጋት”*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةً بَاقِيَةً فِي عَقِبِهِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ኢብራሂም፦ "ከዘሮቼ" አለ እንጂ "ዘሮቼ" አላለም። "ዘሮቼ" በሚለው ቃል መነሻ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ መኖሩ ሁሉም ዘሮቹ ሁሉ አማንያን እንዳልሆኑ እንደውም ከእነዚህ በተቃራኒው በክደት ጣዖታውያን የሆኑ አሉ፥ ከእነርሱ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን፣ መጽሐፍን እና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን እና ከክህደት የሚያጠራቸውን መልእክተኛ አላህ ልኳል፦
2፥129 «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከእነርሱ የኾነን መልክተኛ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍን እና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን *"ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክ"*፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» የሚሉም ሲኾኑ፡፡ رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
2፥151 በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁ እና *"ከክህደትም የሚያጠራችሁ*፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُون

ይህ መልእክተኛ"ﷺ" ሲመጣ ከክህደትም የሚያጠራችሁ ነው። ይህም ክህደት በአላህ ላይ ጣዖታትን ማጋራት ነው። በኢብራሂም ተገንብቶ የነበረው ቤት ቁረይሾች በማዛባት ገንብተው ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 69
የነቢዩ"ﷺ" ባልተቤት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ለእርሷ፦ *"የአንቺ ሕዝብ(ቁረይሽ) ከዕባህን ሲገነቡ በኢብራሂም በተመሠረተው እንዳልገነቧት ታውቂያለሽም? አሏት። እርሷም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለምን በኢብራሂም በተመሠረተውን ተመልሰው አይገነቧትም? አለች። እርሳቸውም፦ "የአንቺ ሕዝብ በኩፍር ባይከስቱት ኖሮ አደርገው ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنهم ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ لَهَا ‏"‏ أَلَمْ تَرَىْ أَنَّ قَوْمَكِ لَمَّا بَنَوُا الْكَعْبَةَ اقْتَصَرُوا عَنْ قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ ‏"‌‏.‏ فَقُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَلاَ تَرُدُّهَا عَلَى قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ‏.‏ قَالَ ‏"‏ لَوْلاَ حِدْثَانُ قَوْمِكِ بِالْكُفْرِ لَفَعَلْتُ ‏

ቁረይሾች በአላህ ቤት ዙሪያ ሦስት መቶ ስድሳ ኑሱብ እና በአላህ ቤት ውስጥ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ሠርተው ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 64, ሐዲስ 320
ዐብደላህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" በመክፈት ቀን ወደ መካህ በገቡ ጊዜ ሦስት መቶ ስድሳ ኑሱብ በአላህ ቤት ዙሪያ ነበሩ። እርሳቸውም እነርሱን በእጃቸው መምቻ በመምታት ሲጀምሩ፦ "እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና" አሉ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ دَخَلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم مَكَّةَ يَوْمَ الْفَتْحِ وَحَوْلَ الْبَيْتِ سِتُّونَ وَثَلاَثُمِائَةِ نُصُبٍ، فَجَعَلَ يَطْعُنُهَا بِعُودٍ فِي يَدِهِ وَيَقُولُ ‏ "‏ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ، جَاءَ الْحَقُّ، وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ ‏"‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” በአላህ ቤት ስዕላት በተመለከቱ ጊዜ ባልደረቦቻቸው እንዲያጠፉ እንኪያዙ ድረስ ወደ እዚያ አልገቡም። ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል”ሠላም በእነርሱ ላይ ይሁን! በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ነበሩ። እርሳቸውም፦ “አላህ ይርገማቸው(ቁረይሾችን)! ወሏሂ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በአዝላም አይለማመዱም” አሉ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم لَمَّا رَأَى الصُّوَرَ فِي الْبَيْتِ لَمْ يَدْخُلْ، حَتَّى أَمَرَ بِهَا فَمُحِيَتْ، وَرَأَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ ـ عَلَيْهِمَا السَّلاَمُ ـ بِأَيْدِيهِمَا الأَزْلاَمُ فَقَالَ ‏ “‏ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ، وَاللَّهِ إِنِ اسْتَقْسَمَا بِالأَزْلاَمِ قَطُّ

"ኑስብ" نُصْب ማለት "ሐውልት" ማለት ሲሆን የኑስብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኑሱብ" نُصُب ወይም "አንሷብ" أَنْصَاب ነው፥ “አዝላም” أَزْلاَم ማለት ደግሞ “የጥንቆላ ቀስት” ማለት ነው። አንሷብም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፦
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም *"አንሷብም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው"*፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
ነቢያችን"ﷺ" ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው አንሷብን እና አዝላምን ካስወገዱ በኃላ ከዕባን አድሰዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 68
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ" ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ *"ከዕባህ በሚገነባ ጊዜ ነቢዩ"ﷺ" እና ዐባሥ ለግንባታ ድንጋዮች ለማምጣት ሔዱ። ዐባሥ ለነቢዩ"ﷺ"፦ "የወገቦትን መታጠቂያ አንገቶት ላይ ያድርጉ" አለ"*። قَالَ سَمِعْتُ جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ لَمَّا بُنِيَتِ الْكَعْبَةُ ذَهَبَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَعَبَّاسٌ يَنْقُلاَنِ الْحِجَارَةَ فَقَالَ الْعَبَّاسُ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم اجْعَلْ إِزَارَكَ عَلَى رَقَبَتِك

ይህ ቤት ንድፉ ርዝመት፣ ስፋት፣ ቁመት ያለው ባለ ሦስት ቅጥ ስለሆነ “ከዕባህ” ተብሏል፥ “ከዕባህ” كَعْبَة ማለት “አንኳር“The Cube” ማለት ነው። ሁላችንም ቂብላችን ወደዚህ ቤት ነው፥ “ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ ማለትም “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው። የትም ቦታ ሆነን ለአንድነት ለአላህ የምንሰግደው ወደ ከዕባህ ነው፦
2፥149 *ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አግጣጫ አዙር*፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

“መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው። ይህ የመጀመሪያው መሥጂድ ነው። እንግዲህ በመላው ዓለም የሚገኙ ሙሥሊሞች በሕይወት ዘመናቸው አንዴ በመካህ የሚገኘው የአላህን ቤት መጎብኘት ፈርድ ነው። “ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት” ማለት ነው። “ሐጅ” حَجّ መደበኛ ዐብይ ጉብኝት ሲሆን “ዑምራ” عُمْرَة ደግሞ መደበኛ ያልሆነ ንዑስ ጉብኝት ነው፦
2፥196 *ሐጅን እና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ*፡፡ وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّه
3፥97 በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደ እርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ *ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው*፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡ فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَّقَامُ إِبْرَاهِيمَ ۖ وَمَن دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا ۗ وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا ۚ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
2፥158 *ሶፋና መርዋ ከአላህ ምልክቶች ናቸው፤ “ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ” ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም*፡፡ إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِن شَعَائِرِ اللَّهِ ۖ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَا

“የጎበኘ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐጀ” حَجَّ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። የአላህ ቤት የሚጎበኝ ተባዕት "ሓጅ" حَاجّ ሲባል፥ የአላህ ቤት የሚምትጎበኝ እንስት ደግሞ "ሓጃህ" حَاجَّة‎ ትባላለች። የሓጅ ወይም የሓጃህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሑጇጅ" حُجَّاج‎ ይባላሉ። አምላካችን አላህ በቅድስት አገር የሚገኘውን ቤቱን ከሚጎበኙት ሑጇጅ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሰው ሩሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥85 *ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا

“ሩሕ” رُّوح ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን አንድን አካል ሕያው የሚሆንበት ንጥረ-ነገር ነው። “ዐን” عَنِ ማለት “ስለ”about” ማለት ነው፦
17፥85 *ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ “ነገር” ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3433 
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ቁራይሾች ለአይሁዳውያን፦ “ይህንን ሰው ስለ ሆነ ነገር የምንጠይቀው ጥያቄ ስጡን” አሉ። የሁዲም፦ “ስለ ሩሕ ጠይቁት” አለ፥ እነርሱም ስለ ሩሕ ጠየቁት። አላህም፦ “ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው” የሚለውን አንቀጽ አወረደ”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَتْ قُرَيْشٌ لِيَهُودَ اعْطُونَا شَيْئًا نَسْأَلُ عَنْهُ هَذَا الرَّجُلَ فَقَالَ سَلُوهُ عَنِ الرُّوحِ قَالَ فَسَأَلُوهُ عَنِ الرُّوحِ فَأَنْزَلَ اللَّهُ ‏:‏ ‏(‏ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُمْ مِنَ الْعِلْمِ إِلاَّ قَلِيلاً ‏)‏

ሩሕ “ነገር” ከሆነ ደግሞ ነገር አላህ የፈጠረው ነው፥ አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ሙሶዊር” مُصَوِّر ማለት “ቀራፅ” “ሰዓሊ” “ሠሪ” ማለት ነው፥ የሙሶዊር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሙሶዊሩን” مُصَوِّرُون ወይም “ሙሶዊሪን” مُصَوِّرِين ሲሆን “ቀራፆች” “ሰዓሊዎች” ማለት ነው። የስዕላት ባለቤትን በትንሳኤ ቀን የፈጠሩትን ሩሕ በመንፋት ሕያው እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፥ ግን አይችሉም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 182
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የስዕላት ባለቤት በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፥ ለእነርሱም፦ “የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ” ይባላሉ”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 77, ሐዲስ 179
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *”በዚህ ዓለም ቅርፅ የቀረፀ በትንሳኤ ቀን በውስጡ ሩሕ እንዲነፋበት ይጠየቃል፥ ግን መንፋት አይችልም”*። فَقَالَ سَمِعْتُ مُحَمَّدًا صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ صَوَّرَ صُورَةً فِي الدُّنْيَا كُلِّفَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنْ يَنْفُخَ فِيهَا الرُّوحَ، وَلَيْسَ بِنَافِخٍ

“የፈጠራችሁትን” ለሚለው የገባው ቃል “ኸለቅቱም” خَلَقْتُمْ ሲሆን ስዕሉን ስለሳሉት እና ቅርፁን ስለቀረፁት እንጂ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተውት አይደለም፥ ሩሕ ከአላህ ነገር ስለሆነ በእጃቸው የፈጠሩትን ላይ ሩሕ ማድረግ አይችሉም። አምላካችን አላህ አደምን ከአፈር ፈጥሮ ያንን የፈጠረውን አካል ሩሕ በማድረግ ሕያው አድርጎታል፦
38፥72 *ፍጥረቱንም ባስተካከልኩ እና በእርሱ ውስጥ “ከ-መንፈሴ” በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» አልኩ*፡፡ فَإِذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُوا لَهُ سَاجِدِينَ

“ሩሕ” رُوح በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ አለ፥ ይህ የሚያሳየው “ሩሕ” አካል ህያው የሚሆንበት ንጥረ-ነገር መሆኑን ነው። ለምሳሌ አላህ ምድርን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “አርዲ” أَرْضِي ማለትም “ምድሬ” በማለት ይናገራል፦
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ*፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! *ምድሬ* በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ፡፡ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ

“አርድ” أَرْض በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ አለ፥ ይህ የሚያሳየው “አርድ” አካል የተሠራበት ነገር መሆኑን ነው። አምላካችን አላህ የሰውን አካል ከምድር ፈጥሮ የፈጠረበትን ምድር ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “ምድሬ” እንዳለ ሁሉ የሰውን መንፈስ ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “መንፈሴ” ብሏል። ልክ እንደዚሁ የዒሣ አፈጣጠርም ከአደም አፈጣጠር ጋር ይመሳሰላል፦
3፥59 አላህ ዘንድ *የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
አምላካችን አላህ አደምን ከአፈር ፈጥሮ ከሩሕ በመንፋት ሕያው እንዳደረገው ሁሉ መርየም ማሕፀን ውስጥ ዒሣን ፈጥሮ ከሩሕ በመንፋት ሕያው አድርጎታል፦
21፥91 ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን *”በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን”* እርሷንም ልጅዋንም ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ፡፡ وَالَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ

ለአደም ሲሆን “ፊ-ሂ” فِيهِ ማለትም “በ-እርሱ ውስጥ” ብሏል፥ “እርሱ” የተባለው የአደም አካል ነው። በአደም አካል ውስጥ ሩሕ እንደነፋበት ያሳያል። በተመሳሳይ ለመርየም ሲሆን “ፊ-ሃ” فِيهَا ማለትም “በ-እርሷ ውስጥ” ብሏል፥ “እርሷ” የተባለችው የዒሣ እናት መርየም ናት። በመርየም ማሕፀን ውስጥ ሩሕ እንደነፋባት ያሳያል። ስለዚህ የዒሣ አካል ሕያው የሆነበት ሩሕ ከአላህ የሆነ ነው፦
4፥171 እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ! የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ብቻ ነው። ወደ መርየም የጣላት የይኹን ቃሉም ነው። *”ከ-እርሱ” የሆነ መንፈስ ነው*። يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ

“ከ” የሚለው መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ያለው “እርሱ” የሚለው ተውላጠ-ስም “አላህ” የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። “ሚን-ሁ” مِنْهُ የሚለው አካሉ ከመርየም ሩሑ ከአላህ መሆን የሚያሳይ ነው፥ አንድ ተመሳሳይ የሰዋስው ሙግት እንይ፦
45፥13 ለእናንተም *በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ “ከ-እርሱ” ሲኾን የገራላችሁ ነው*፡፡ በዚህ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ተዓምራት አልለበት፡፡ وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

“በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ ከእርሱ ነው” የሚለው ይሰመርበት። “ሚን-ሁ” مِنْهُ ማለትም “ከ-እርሱ” የሚለው ፍጥረት ከአላህ መሆኑን እንደሚያሳይ ሁሉ የዒሣም ሩሕ ከአላህ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ የሰው መንፈስ ሁሉ ከአላህ የሆነ ነገር ነው፦
17፥85 *ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا

“ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ስለዚህ የሁላችንም ሩሕ ከአፈር ሳይሆን ከጌታዬ ነገር ነው። አምላካችን አላህ ሩሕ በፅንስ ላይ ሲነፋበት ሕያው ይሆናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 1
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “እውነተኛ ታማኝ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”የእያንዳንዳቹህ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ሂደቱ በአርባ ቀናት ይሰበሰባል። ከዚያም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ያ ዐለቃህ ይሆናል፣ ከዚያም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ያ ሙድጋህ ይሆናል። *ከዚያም መልአክ ወደ እርሱ ይላካል እና በእርሱ ሩሕ ይነፋል*። እርሱም አራት ነገሮችን ሲሳዩን፣ ፍጻሜውን፣ ሥራውን እና ሐዘኑን ወይም ደስታው እንዲጽፍ ይታዘዛል። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ حَدَّثَنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَهُوَ الصَّادِقُ الْمَصْدُوقُ “‏ إِنَّ أَحَدَكُمْ يُجْمَعُ خَلْقُهُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا ثُمَّ يَكُونُ فِي ذَلِكَ عَلَقَةً مِثْلَ ذَلِكَ ثُمَّ يَكُونُ فِي ذَلِكَ مُضْغَةً مِثْلَ ذَلِكَ ثُمَّ يُرْسَلُ الْمَلَكُ فَيَنْفُخُ فِيهِ الرُّوحَ وَيُؤْمَرُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ بِكَتْبِ رِزْقِهِ وَأَجَلِهِ وَعَمَلِهِ وَشَقِيٌّ أَوْ سَعِيدٌ

ስለ ሰው ሩሕ የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ስለሆነ “ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም” ብሎናል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ሡራህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፥ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا

አምላካችን አላህ ቁርኣንን ወደ ነቢያችን"ﷺ" በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነው ያነቡት ዘንድ ከፋፍሎ ቀስ በቀስ አወረደው፦
17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፥ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا

"ከፋፈልነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ቁርኣን በሱራህ የተከፋፈለ ነው፥ ሡራዎች የሚለያዩት በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" በሚል በሥመላህ ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሡራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}

“ሡራህ” سُورَة ማለት “ምዕራፍ” ወይም “ክፍል” አሊያም “ደረጃ” ማለት ነው። የሡራህ ብዙ ቁጥር "ሡወር" سُوَر‎ ነው። አምላካችን አላህ ቁርኣንን በሡራህ መከፋፈሉን ለማመልከት ብዙ አናቅጽ ላይ "ሡራህ" እያለ ይናገራል፦
24፥1 *"ይህች ያወረድናት እና የደነገግናት "ሡራህ" ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል"*፡፡ سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
9፥64 መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው *"ሡራህ" በእነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ*፡፡ «አላግጡ አላህ የምትፈሩትን ሁሉ ገላጭ ነው» በላቸው፡፡ يَحْذَرُ الْمُنَافِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيْهِمْ سُورَةٌ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِي قُلُوبِهِمْ ۚ قُلِ اسْتَهْزِئُوا إِنَّ اللَّهَ مُخْرِجٌ مَّا تَحْذَرُونَ

ስለዚህ የቁርኣን ሡራህ ሡራህ የተባለው ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ ነው። 114 ሡራዎች ወደ ነቢያችን”ﷺ” ልብ በጨረቃ አቆጣጠር ከ 610 ድኅረ-ልደት እስከ 632 ድኅረ-ልደት ለ 23 ዓመት ቀስ በቀስ ወረደ። ለ 13 ዓመት 86 ሡራዎች በመካ ሲወርዱ፥ ለ 10 ዓመት ደግሞ 28 ሡራዎች የወረዱት በመዲና ነው። ነቢያችን”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ጀምሮ እስከ 63 ዓመታቸው ወሕይ ቀስ በቀስ በሒደት ወረደ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 128
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ወሕይ መቀበል ጀመሩ፥ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ቆይተው በ 63 ዓመታቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ بُعِثَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَرْبَعِينَ سَنَةً، فَمَكُثَ بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ سَنَةً يُوحَى إِلَيْهِ، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ فَهَاجَرَ عَشْرَ سِنِينَ، وَمَاتَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ‏.‏

በዚህም በመካ የወረዱት 86 ሡራዎች "መኪያህ" مَكِّيَّة ሲባሉ፥ በመዲና የወረዱት 28 ሡራዎች ደግሞ "መደኒያህ" مَدَنِيَّة ይባላሉ። የሡራዎችን ቅድመ-ተከተል እና ስም ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በተናገሩት መሠረት የተቀመጠ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3366
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"ለዑስማን ኢብኑ ዐፋን፦ "ሡረቱል አንፋልን ከመቶ በታች የሆነችበት፣ ሡረቱል በራኣህ(ተውባህ) ከመቶ በላይ የሆነችበት፣ በመካከላቸውም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ያልተጻፈበት(ሱረቱል በራኣህ) እና ባለ ሰባት አናቅጽ(ሡረቱል ፋቲሓህ) የሆችበት ምክንያታችሁ ምንድን ነው? አልኩኝ። ዑስማን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አንዳች የቁርኣን ክፍል በሚወርድላቸው ጊዜ ከጸሐፊዎቹ አንዱን በመጥራት፦ "ይህንን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት" ይሉ ነበር። አሁንም በድጋሚ የተወሰኑ የቁርኣን አንቀጾች ሲወርድላቸው፦ "እነዚህን አንቀጾች እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት" ይሉ ነበር"*። حَدَّثَنَا ابْنُ عَبَّاسٍ، قَالَ قُلْتُ لِعُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ مَا حَمَلَكُمْ أَنْ عَمَدْتُمْ، إِلَى الأَنْفَالِ وَهِيَ مِنَ الْمَثَانِي وَإِلَى بَرَاءَةَ وَهِيَ مِنَ الْمِئِينَ فَقَرَنْتُمْ بَيْنَهُمَا وَلَمْ تَكْتُبُوا بَيْنَهُمَا سَطْرَ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ وَوَضَعْتُمُوهُمَا فِي السَّبْعِ الطُّوَلِ مَا حَمَلَكُمْ عَلَى ذَلِكَ فَقَالَ عُثْمَانُ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِمَّا يَأْتِي عَلَيْهِ الزَّمَانُ وَهُوَ تَنْزِلُ عَلَيْهِ السُّوَرُ ذَوَاتُ الْعَدَدِ فَكَانَ إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ الشَّىْءُ دَعَا بَعْضَ مَنْ كَانَ يَكْتُبُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَؤُلاَءِ الآيَاتِ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا وَكَذَا وَإِذَا نَزَلَتْ عَلَيْهِ الآيَةُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَذِهِ الآيَةَ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا
ይህ ሐዲስ የሚያሳየው የሡራው ቅድመ-ተከተል እና እከሌ የሚለው ስም በአላህ ነቢይ የታዘዘ መሆኑን ነው። እርሳቸውም በንግግራቸው ሡረቱል በቀራህ፣ ሡረቱል አለ ዒምራን፣ ሡረቱል ከህፍ፣ ሡረቱል ያሢን ወዘተ እያሉ መናገራቸው በራሱ በእርሳቸው መሰየሙን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ የሚያስረዳ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 64
አቢ መሥዑድ አል-አንሷሪይ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሌሊት ከሡረቱል በቀራህ ከመጨረሻው ሁለት አናቅጽ ከቀራ በቂው ነው"*። عَنْ أَبِي مَسْعُودٍ الأَنْصَارِيِّ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الآيَتَانِ مِنْ آخِرِ سُورَةِ الْبَقَرَةِ مَنْ قَرَأَ بِهِمَا فِي لَيْلَةٍ كَفَتَاهُ ‏
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 45, ሐዲስ 3125
ነዋሥ ኢብኑ ሠምዓን እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ቁርኣን በዱኒያ ውስጥ በሚሠሩበት ባለቤቶቹ ላይ የትንሳኤ ቀን ይመጣል። ሡረቱል በቀራህ እና ሡረቱል አለ ዒምራን በፊቱ ይሆናሉ"*። عَنْ نَوَّاسِ بْنِ سَمْعَانَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ يَأْتِي الْقُرْآنُ وَأَهْلُهُ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ بِهِ فِي الدُّنْيَا تَقْدُمُهُ سُورَةُ الْبَقَرَةِ وَآلُ عِمْرَانَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 311
አቢ አድ-ደርዳእ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ከሡረቱል ከህፍ መጀመሪያ አሥር አናቅጽ ያፈዘ ከደጃል ይጠበቃል"*። عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ حَفِظَ عَشْرَ آيَاتٍ مِنْ أَوَّلِ سُورَةِ الْكَهْفِ عُصِمَ مِنَ الدَّجَّالِ ‏
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 33
መዕቂል ኢብኑ የሣር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሡረቱል ያሢን በሙታናችሁ ላይ ቅሩ!"*። عَنْ مَعْقِلِ بْنِ يَسَارٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اقْرَءُوا ‏{‏ يس ‏}‏ عَلَى مَوْتَاكُمْ

ከሦስት ሡራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሡራህ ስማቸው በውስጣቸው አለ። እነዚህም ስማቸው በውስጣቸው ያልተጠቀሱ ሦስት ሡራዎች ሡረቱል ፋቲሓህ፣ ሡረቱል አንቢያህ እና ሡረቱል ኢኽላስ ናቸው። በተረፈ ሁሉም ስማቸው በውስጣቸው አለ፥ ለምሳሌ "በቀራህ" بَقَرَة ማለት "ጊደር" ማለት ሲሆን ስለ ጊደሯ የሚናገር ሡራህ ነው፦
2፥68 «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች ዕድሜዋን ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች *"ጊደር"* ናት ይላችኋል፥ የታዘዛችሁትንም ሥሩ» አላቸው፡፡ قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا هِيَ ۚ قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَّا فَارِضٌ وَلَا بِكْرٌ عَوَانٌ بَيْنَ ذَٰلِكَ ۖ فَافْعَلُوا مَا تُؤْمَرُونَ

ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም