ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.4K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አላህ ምንድን ነው? ሲባል የምንነት ጥያቄ ስለሆነ የምንነቱ መታወቂያ የሆኑትን ባሕርያት የተሰየሙበትን ስም በመጥቀስ፦
1. "አል-ኻሊቅ" الْخَالِق ማለትም "ፈጣሪ" ነው፦
29፥24 *እርሱ አላህ "ፈጣሪው"፥ ከኢምንት አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ

2. "አስ-ሰመድ" الصَّمَد ማለትም "የሁሉ መጠጊያ" ነው፦
112፥2 *አላህ "የሁሉ መጠጊያ" ነው*፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ

3. "አል-ገኒይ" الْغَنِيّ ማለትም "ተብቃቂ" ነው፦
35፥15 እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ *አላህም እርሱ "ተብቃቂው" ምስጉኑ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

4. "አል-ለጢፍ" اللَّطِيف ማለትም "ረቂቅ" ነው፦
6፥103 ዓይኖች አያገኙትም፥ እርሱም ዓይኖችን ያያል፡፡ *እርሱም "ረቂቁ"፥ ውስጠ ዐዋቂው ነው*፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ

እያልን እንዘረዝራለን። እርሱ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያስገኘ ፈጣሪ፣ ፍጥረታት በእርሱ ላይ ጥገኛ የሆኑ የሁሉ መጠጊያ፣ ከፍጥረቱ ምንም የማይገጅል ተብቃቂ፣ የፍጡራም አእምሮ መርምሮ የማይደርስበት ረቂቅ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ችግኝ መትከል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥2 *በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

አውሮፓ ላይ ያለው የበረዶ ግግር እየቀለጠ ነው፥ ይህ በረዶ በዚህ ከቀጠለ አውሮፓን ጎርፍ ያጠቃትና ያጠፋታል የሚል ስጋት አለ። ይህ የሆነበት ምክንያት ደኖች በመመንጠራቸው የበረሓ መስፋፋት እየተከሰተ ስላለ ነው። በስፋቱም ከአውሮፓ የማይተናነሰው የሰሐራ በረሓ በፕላኔታችን ላይ የሙቀት መጨመር እያመጣ ነው።
የመሬት ከባቢ አየር በመሬት ዙሪያ የሚገኝ የጋዝ ክምችት ሲሆን የዚህ የከባቢ አየር የላይኛው ክፍል ማለትም ስትራቶስፌር ወደ ምድር ከሚመጣው አልትራቫዮሌት ጨረር ውስጥ 99% የሚሆነውን ውጦ የሚያስቀረውን “ኦዞን”ozone (O3) የተባለ የኦክስጅን ቅንብር ይዟል። ይህ ኦዞን እየሳሳ ያለው በምድሪቱ በረሓ ግለት እና ከሰው ሠራሽ ከሚመጡ የጋዝ ብክለት ነው። ምን ይሆን መፍትሔው?
አምላካችን አላህ”ﷻ” ከምድር የፈጠረን በውስጧ እንድናለማት ነው፦
11፥61ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን አምልኩ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ *እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም "አደረጋችሁ"*፡፡ ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ ለለመነው ተቀባይ ነውና» አላቸው፡፡ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيب

ከተፈጠርንበት ንዑስ አላማ አንዱ ምድርን እንድናለማ ነው። አንድ ሙሥሊም በመሠረተ-ልማት"infrastructure" ውስጥ ያለው ተሳትፎ ጉልህ ሚና አለው። ከሰዎች ጋር በሚኖረው ማኅበራዊ እሴት አምላካችን አላህ”ﷻ” በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አይሁን እንጂ በበጎ ነገር እና እርሱን በመፍራት እንድንረዳዳ አዞናል፦
5፥2 *በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

"በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ " የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ምድሪቱን ማልማት በጎ ነገር ነው። ምድሪቱን ከምናለማበት ነገሮች አንዱ ችግኝ መትከት ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "ማንም ሙሥሊም አንድ ተክል ተክሎ ሰው ሆነ እንስሳ አሊያም አእዋፍ ቢበላው ሰደቃህ ይሆንለታል" ብለውናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 43
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ሙሥሊም የለም አንድ ተክል ተክሎ ሰው ሆነ እንስሳ ቢበላው ሰደቃህ ቢሆንለት እንጂ"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَا مِنْ مُسْلِمٍ غَرَسَ غَرْسًا فَأَكَلَ مِنْهُ إِنْسَانٌ أَوْ دَابَّةٌ إِلاَّ كَانَ لَهُ صَدَقَة
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 63
አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ማንም ሙሥሊም የለም አንድ ተክል ወይም አዝዕርት ዘርቶ ሰው ሆነ አእዋፍ ቢበላው ሰደቃህ ቢሆንለት እንጂ"*። عَنْ أَنَسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَغْرِسُ غَرْسًا أَوْ يَزْرَعُ زَرْعًا فَيَأْكُلُ مِنْهُ إِنْسَانٌ أَوْ طَيْرٌ أَوْ بَهِيمَةٌ إِلاَّ كَانَتْ لَهُ صَدَقَة

ይህንን ሰደቃ ከአላህ ዘንድ ለማግኘት የችግኝ ተከላው እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ይቀጥላል፦
ሙሥነድ አሕመድ ሐዲስ 12491
አነሥ እብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ከእናንተ ውስጥ ችግኝ በእጁ የያዘ የትንሳኤ ቀን ቢደርስበትም ይትከላት"*። ﻋَﻦْ ﺃَﻧَﺲِ ﺑْﻦِ ﻣَﺎﻟِﻚٍ ﻗَﺎﻝَ ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺇِﻥْ ﻗَﺎﻣَﺖْ ﻋَﻠَﻰ ﺃَﺣَﺪِﻛُﻢْ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣَﺔُ ﻭَﻓِﻲ ﻳَﺪِﻩِ ﻓَﺴْﻠَﺔٌ ﻓَﻠْﻴَﻐْﺮِﺳْﻬَﺎ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የነቢያችን”ﷺ” ነቢይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥45 *አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪ እና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا

"ነቢይ" نَبِيّ የሚለው ቃል "ነበአ" نَبَّأَ ማለትም "የሩቅ ወሬን አወራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሩቅ ወሬ አውሪ" ማለት ነው። የሚወርድለት "የሩቅ ወሬ" ደግሞ "ነበእ" نَبَأ ይባላል፥ ይህንን የሩቅ ወሬ ለአንድ ነቢይ ከሦስት መንገድ በአንዱ ይወርድለታል፦
42፥51 *ለሰው አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም"*፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

አንደኛው መንገድ አላህ በራእይ የሚያናግረው ነው፥ “ሩዕያ” رُّءْيَا ማለት “ራዕይ” ማለት ሲሆን ይህም ራዕይ ያ ነቢይ በሰመመን ወይም በተመስጦ ውስጥ ሆኖ አላህ የሚያናግርበት መንገድ ነው።
ሁለተኛው መንገድ አላህ በቀጥታ የሚያናግረው ነው፥ “ተክሊም” تَكْلِيم ማለት በሁለት ማንነት መካከል የሚደረግ “ምልልስ”conversation” ሲሆን አላህ ያለ ራዕይ ወይም ያለ መልአክ ሳይታይ ከግርዶ ወዲያ ሆኖ የሚያናግርበት መንገድ ነው።
ሦስተኛው መንገድ አላህ በመልአክ የሚያናግረው ነው፥ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው።

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አላህ ይህንን የሩቅ ወሬ ለአንድ ሰው ሲያሳውቀው ያ ሰው ነቢይ ይባላል። አምላካችን አላህ"ﷻ" ነቢያችንን"ﷺ" በሦስተኛ መንገድ በመልአኩ ጂብሪል አናግሯቸዋል። አላህ ወደ እርሳቸው ያወረደላቸው ቁርኣን ደግሞ "አል-ገይብ" ነው። "አል-ገይብ" ٱلْغَيْبِ ማለት "የሩቅ ወሬ" "የሩቅ ሚስጥር" ማለት ሲሆን ከህዋስ ባሻገር ጥንት የተከሰተ፣ አሁን እየተከሰተ ያለ እና ወደ ፊት የሚከሰት ዕውቀት ነው፥ አላህ የሰማያትን እና የምድርን የሩቅ ሚስጥር ያውቃል። ይህንን የሩቅ ሚስጥር ለማንም ዐያሳውቅም፥ ለሚፈልገው መልእክተኛ ቢሆን እንጂ፦
49፥18 *"አላህ የሰማያትንና የምድርን "ሩቅ ሚስጥር" ያውቃል"*። إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ
72፥26 *«እርሱ ”የሩቅ ሚስጥር” ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»* عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
72፥27 *ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም*፡፡ إِلَّا مَنِ ٱرْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍۢ

"አል-ገይብ" በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦ አል-ገይቡል ማዲ፣ አል-ገይቡል ሙዷሪዕ እና አል-ገይቡል ሙሥተቅበል ነው። ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"አል-ገይቡል ማዲ"
"አል-ገይቡል ማዲ" ٱلْغَيْب الْمَاضِي ማለት "ኀላፊያት የሩቅ ወሬ" ማለት ነው፥ ድርጊቱ ከዚህ በፊት አላፊ የሆነ ክስተት ነው። ይህንን የሩቅ ወሬ አምላካችን አላህ ለነቢያችን”ﷺ” “ኑሒሂ ዒለይከ” نُوحِيهِ إِلَيْكَ ማለትም “ወደ አንተ እናወርዳታለን” ወይም “ነቁሱ ዐለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ይናገራል፦
12፥102 *"ይህ ወደ አንተ የምናወርደው ሲኾን ከሩቅ ወሬዎች ነው፡፡ አንተም እነርሱ በእርሱ ላይ የሚመክሩ ኾነው ነገራቸውን በቆረጡ ጊዜ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም"*፡፡ ذَٰلِكَ مِنْ أَنبَاءِ الْغَيْبِ نُوحِيهِ إِلَيْكَ ۖ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ أَجْمَعُوا أَمْرَهُمْ وَهُمْ يَمْكُرُونَ
20፥99 *"እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች በአንተ ላይ እንተርካለን"*፡፡ كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ مَا قَدْ سَبَقَ

"ወሬዎች" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አንባእ" أَنبَاء ሲሆን የነበእ ብዙ ቁጥር ነው። ነቢያችን"ﷺ" ከእርሳቸው በፊት ያለው ክስተት ሲከሰት ስላልተፈጠሩ በቦታው የሉም። ነገር ግን በጊዜና በቦታ ዕውቀቱ የማይገደበው አላህ "አስታውስ" በማለት ተርኮላቸዋል፦
38፥71 ጌታህ *«ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» አስታውስ*፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ
ነጥብ ሁለት
"አል-ገይቡል ሙዷሪዕ"
"አል-ገይቡል ሙዷሪዕ" ٱلْغَيْب ٱلْمُضَارِع ማለት "አሁናት የሩቅ ወሬ" ማለት ነው፥ ቁርኣን ሲወርድ ከህዋስ ባሻገት እየተፈጸመ ያለ ክስተት ነው። ለምሳሌ ነቢያችን”ﷺ” ከባለቤታቸው አንዷ ለሆነችው ለሃፍሳ”ረ.ዐ.”፦ "ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዐ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በፍጹም አልጠጣም” ብለው ይህ ወሬ በሚስጥር በመሰጠሯት ጊዜ ሄዳ ለዓኢሻ”ረ.ዐ.” ተናገረች። ነብይ ማለት የሩቅ ዕውቀት የሚገለጥለት ነውና ለዓኢሻ”ረ.ዐ.” በተናገረች ጊዜ የተናገረችውን ከፊሉን ዐሳውቀዋት ከፊሉን ችላ ብለው ሲተዉት፥ በዚያ በነገሯት ነገር ሃፍሳ”ረ.ዐ.”፦ ይህን ማን ነገረህ? ብላ አለቻቸው፤ ነቢያችንም”ﷺ”፦ «ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አሏት። ይህንን ጉዳይ አምላካችን አላህ እንዲህ ይነግረናል፦
66፥3 *"ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ፡፡ እርሱንም በነገረች እና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ፥ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት"*። وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًۭا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍۢ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን መልሱ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ማለትም “ነገረኝ” ማለት ነው። "አንበአከ” أَنْبَأَكَْ ሆነ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ የሁለቱም ግስ ርቢ "ነበአ" نَبَّأَ ነው። ስለዚህ "ነቢይ" ማለት ሁሉን ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው። ከዚያም ባሻገር መመሪያው እራሱ በራሱ የነቢይነት መደብ ውስጥ ነው፦
15፥49 *”ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

"ንገራቸው" نَبِّئْ ለሚለው አሁንም "ነበእ" نَبِّئْ ሲሆን "ነበአ" نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። 66፥3 ላይ "ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ" ማለቱ የሚያጅብ ነው፥ በሁለተኛ መደብ "አስታውስ" እያለ በሦስተኛ መደብ ለራሳቸው "በመሰጠርክ ጊዜ" ሳይሆን "በመሰጠረ ጊዜ" ይላል። ሁሉን ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር ስለሚያውቅ አወረደው፦
25፥6 *«ያ "በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር" የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው*፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

ነጥብ ሦስት
"አል-ገይቡል ሙሥተቅበል"
"አል-ገይቡል ሙሥተቅበል" ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ማለት "መጻእያት የሩቅ ወሬ" ማለት ነው፥ መጪው ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ገና ያልተፈጸመ ወደፊት የሚከሰት ነው። ለምሳሌ ስለ ጀነት እና ጀሃነም ያለው የሩቅ ወሬ ነው፦
3፥15 *«ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው"*፡፡ እርሱም «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ ሚስቶችም፣ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው፡፡ አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው፡፡» قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ ۚ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ
22፥72 *«ከዚህ ይልቅ የከፋን ነገር ልንገራችሁን» በላቸው"*፡፡ «እርሱም እሳት ናት፡፡ አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች ቀጥሯታል፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» قُلْ أَفَأُنَبِّئُكُم بِشَرٍّ مِّن ذَٰلِكُمُ ۗ النَّارُ وَعَدَهَا اللَّهُ الَّذِينَ كَفَرُوا ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ

"ልንገራችሁ" ለሚለው ቃል የገባው "ነበኡኩም" نَبِّئُكُم ሲሆን "ነበአ" نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። ይህንን እንዲናገሩ አላህ "ቁል" قُلْ የሚል ትእዛዝ ያወርዳል። ቁርኣን ላይ ብዙ ቦታ በትንሳኤ ቀን ምን እንደሚከሰት ለማሳወቅ "አስታውስ" እያለ ይናገራል፦
54፥6 *"ከእነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ"*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ

ይህንን ትንቢት አምላካችን አላህ፦ "በእርግጥ ከጊዜ በኋላ ወደፊትም ታውቁታላችሁ" ይለናል፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ
“ኢዝ” إِذْ በሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ ውስጥ “ፈዘከር” فَذَكِّرْ ማለትም “አስታውስ” የሚል ትእዛዝ አለ፥ አላህ ያለፈውን፣ ያሁኑን እና የሚመጣውን የሩቅ ወሬ እየነገራቸው "አስታውስ" ይላቸዋል። ነቢያችን”ﷺ” ደግሞ “ሙዘከር” مُذَكِّرٌ ማለትም “አስታዋሽ” ናቸው። ነቢያችን”ﷺ” የሚያሳታውሱት በተወረዳቸው “ዚክር” ብቻ ነው፥ ይህም "ዚክር" ذِكْر ማለትም "ማስታወሻ" ቁርኣን ነው፦
88፥21 *አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና*፡፡ فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ
21፥50 *ይህም ያወረድነው የኾነ ብሩክ “ዚክር” ነው*፡፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲዎች ናችሁን? وَهَـٰذَا ذِكْرٌ مُّبَارَكٌ أَنزَلْنَاهُ ۚ أَفَأَنتُمْ لَهُ مُنكِرُونَ
50፥45 ስለዚህ ዛቻዬን የሚፈራን ሰው *በቁርኣን አስታውስ*፡፡ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ

አምላካችን አላህ"ﷻ" ነቢያችንን"ﷺ"
በሁለተኛ መደብ፦ "አንተ ነቢዩ ሆይ" በማለት እራሱ እንደላከ ለማመልከት "ላክንህ" በማለት "ለሰዎች ሁሉ" እንደተላኩ ይናገራል፦
33፥45 *አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪ እና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا
4፥79 *"ለሰዎችም ሁሉ መልክተኛ ኾነህ ላክንህ"፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ*፡፡ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا
45፥6 *እነዚህ በአንተ ላይ በውነት የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከአላህ እና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?* تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَ اللَّهِ وَآيَاتِهِ يُؤْمِنُونَ

መስካሪም በአላህ በቃ። ከላይ የተጠቀሱት አናቅጽ አላህ በነቢያችን"ﷺ" ላይ ያወረዳቸው የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፥ ከአላህ እና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ? ይህንን የሩቅ ሚስጥር ከተረዱ በኃላ እኚህን ነቢይ ማስተባበል ይቻል ይሆን? አላህ ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እንስሳት እና ነፍሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥26 *"አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

አምላካችን አላህ እኛም ለማስተማር የቤት እንስሳትን፣ የዱር እንስሳትን በራሪ ፍጥረትን፣ ነፍሳትን በቅዱስ ቃሉ አውስቷል። ከትንሿ ትንኝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ዝሆን ድረስ ምሳሌ እያደረገ አውስቷል፦
2፥26 *አላህ ማንኛውንም ነገር "ትንኝንም" ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

ሀ. የቤት እንስሳት

1. ፈረስ
38፥32 አለም «እኔ ፀሐይ በግርዶ እስከ ተደበቀች ድረስ ከጌታዬ ማስታወስ ፋንታ *ፈረስን*! መውደድን መረጥኩ፡፡» فَقَالَ إِنِّي أَحْبَبْتُ حُبَّ الْخَيْرِ عَن ذِكْرِ رَبِّي حَتَّىٰ تَوَارَتْ بِالْحِجَابِ

2. አህያ
62፥5 የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት ያልሠሩባት ሰዎች ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም *አህያ* ብጤ ነው፡፡ የእነዚያ በአላህ አንቀጾች ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ከፋ፡፡ አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ حُمِّلُوا التَّوْرَاةَ ثُمَّ لَمْ يَحْمِلُوهَا كَمَثَلِ الْحِمَارِ يَحْمِلُ أَسْفَارًا ۚ بِئْسَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

3. በቅሎ
16፥8 ፈረሶችንም፣ *በቅሎዎችንም*፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል፡፡ وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

4. ላም
2፥69 «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ መልኳ ምን እንደኾነ ለኛ ይግለጽልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳለቻ *ላም* ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡ قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا لَوْنُهَا ۚ قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ صَفْرَاءُ فَاقِعٌ لَّوْنُهَا تَسُرُّ النَّاظِرِينَ

5. ግመል
88፥17 ከሓዲዎች አይመለከቱምን? ወደ *ግመል* እንዴት እነደተፈጠረች! أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ

6. ከብት(በሬ)
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ *የከብት*፣ የበግና የፍየል እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

7. በግ
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ የከብት፣ *የበግ* እና የፍየል እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

8. ፍየል
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ የከብት፣ የበግና *የፍየል* እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

9. ውሻ
7፥176 በሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ *ውሻ* ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡ وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَاهُ بِهَا وَلَـٰكِنَّهُ أَخْلَدَ إِلَى الْأَرْضِ وَاتَّبَعَ هَوَاهُ ۚ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ الْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ۚ ذَّٰلِكَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۚ فَاقْصُصِ الْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ
ለ. የዱር እንስሳት

1. ዝሆን
105፥1 *በዝሆኑ* ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን? أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَابِ الْفِيلِ

2. አንበሳ
74፥51 *ከአንበሳ* የሸሹ፡፡ فَرَّتْ مِن قَسْوَرَةٍ

3. ተኩላ
12፥13 «እኔ እርሱን ዩሱፍን ይዛችሁ መሌዳችሁ በእርግጥ ያሳዝነኛል፡፡ እናንተም ከእርሱ ዘንጊዎች ስትሆኑ *ተኩላ* ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ» አላቸው፡፡ قَالَ إِنِّي لَيَحْزُنُنِي أَن تَذْهَبُوا بِهِ وَأَخَافُ أَن يَأْكُلَهُ الذِّئْبُ وَأَنتُمْ عَنْهُ غَافِلُون

4. የሜዳ አህያ
74፥50 እነርሱ ልክ ደንባሪዎች *የሜዳ አህዮች* ይመስላሉ፡፡ كَأَنَّهُمْ حُمُرٌ مُّسْتَنفِرَةٌ

5. እባብ
7፥107 በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ *እባብ* ኾነች፡፡ فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ

6. ዝንጀሮ
7፥166 ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወረዶች *ዝንጀሮች* ኹኑ አልን፤» ኾኑም፡፡ فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ

7. አሳማ
16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ *የአሳማንም* ስጋ፣ ያንንም በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ አመጸኛም ወሰን አላፊም ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ ۖ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

8. አሳ
37፥142 እርሱም ተወቃሽ ሲሆን *አሳው* ዋጠው፡፡ فَالْتَقَمَهُ الْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ
ሐ. በራሪ ፍጥረት

1. ሁድሁድ
27፥20 በራሪዎቹንም ተመለከተ፤ አለም *«ሁድሁድን* ለምን አላየውም! በእውነቱ ከራቁት ነበርን፡፡ وَتَفَقَّدَ الطَّيْرَ فَقَالَ مَا لِيَ لَا أَرَى الْهُدْهُدَ أَمْ كَانَ مِنَ الْغَائِبِينَ

2. ወፍ
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ *ወፍ* ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡» وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

3. ቁራ
5፥31 የወንድሙንም ሬሳ እንዴት እንደሚሸሽግ ያሳየው ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር *ቁራን* ላከለት፡፡ «ወይ እኔ የወንድሜን ሬሳ እሸሽግ ዘንድ እንደዚህ ቁራ ብጤ መኾን አቃተኝን» አለ፡፡ ከጸጸተኞችም ኾነ፡፡ فَبَعَثَ اللَّهُ غُرَابًا يَبْحَثُ فِي الْأَرْضِ لِيُرِيَهُ كَيْفَ يُوَارِي سَوْءَةَ أَخِيهِ ۚ قَالَ يَا وَيْلَتَىٰ أَعَجَزْتُ أَنْ أَكُونَ مِثْلَ هَـٰذَا الْغُرَابِ فَأُوَارِيَ سَوْءَةَ أَخِي ۖ فَأَصْبَحَ مِنَ النَّادِمِينَ

4. ቢራቢሮ
101፥4 ሰዎች እንደ ተበታተነ *ቢራቢሮ* በሚኾኑበት ቀን። يَوْمَ يَكُونُ النَّاسُ كَالْفَرَاشِ الْمَبْثُوث

5. ንብ
16፥68 ጌታህም ወደ *ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

6. ዝንብ
22፥73 እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ ለእርሱም አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው ጣዖታት *ዝንብን* ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡ እርሱን ለመፍጠር ቢሰበሰቡም እንኳን አይችሉም፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَن يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِن يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ

7. አንበጣ
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ *አንበጣንም* ነቀዝንም እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

8. ትንኝ
2፥26 አላህ ማንኛውንም ነገር *ትንኝንም* ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

መ. ነፍሳት

1. ነቀዝ
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም *ነቀዝንም* እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

2. ሸረሪት
29፥41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን ጣዖታትን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች *ሸረሪት* ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

3. ጉንዳን
27፥18 በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ *ጉንዳኖች* ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች፡፡ حَتَّىٰ إِذَا أَتَوْا عَلَىٰ وَادِ النَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَانُ وَجُنُودُهُ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

4. እንቁራሪት
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም ነቀዝንም *እንቁራሪቶችንም* ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ


ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom


ወሠላሙ ዐለይኩም
መገለጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ

“ወሕይ” وَحْي የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት” አሊያም "መለኮታዊ ራእይ"Revelation” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ለነቢያት ግልጠት ይገልጥላቸዋል፦
4፥163 *"እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም "አወረድን"፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም "አወረድን"*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا

"አወረድን" ለሚለው ቃል የገባው "አውሐይና" أَوْحَيْنَا ሲሆን "አውሓ” أَوْحَىٰٓ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ገለጥን" ማለት ነው። አላህ ለነቢያት ስለራሱ ማንነት የሚገልጠው፦ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" የሚል ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ” በማለት ወደ እርሱ ”የምናወርድለት” ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም*፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

"የምናወርድለት" ለሚለው ቃል የገባው "ኑሒ" نُوحِىٓ ሲሆን "አውሓ” أَوْحَىٰٓ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የምንገልጽለት" ማለት ነው። "መገለጥ" ማለት "መታየት" ማለት ሳይሆን "መታወቅ" ማለት ነው። አላህ ለንብ እና ለምድር ዐሳውቋል፦
16፥68 *ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል "አስታወቀ" «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ*፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ
99፥5 *ጌታህ ለእርሷ "በማሳወቁ" ምክንያት*፡፡ بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا

"አስታወቀ" ለሚለው የገባው ቃል "አውሓ" أَوْحَىٰ መሆኑ ልብ በል። ስለዚህ አላህ የራሱን ማንነት "እኔ" በማለት፥ የራሱን ምንነት "አምላክ ነኝ" በማለት ለነቢያቱ ያሳውቃል፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
21፥108 *«ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለት ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُون

"የሚወርደው" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሓ" يُوحَىٰ ሲሆን "የሚገለጠው" ማለት ነው። ወደ ነቢያችን"ﷺ" የተገለጠው ይህም መገለጥ፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" የሚል ነው። አላህ ለተራራው ተገልጿል፦
7፥143 *"ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው"*፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወደ አንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ

ልብ አድርግ "በተገለጸ ጊዜ" አለ እንጂ "በታየ ጊዜ" አላለም። ተራራ ከመነሻው መቼ ዐይን ኖረውና ነው የሚያየው? "ታየ" ለመባል የሚታይለት "ዐይን" ሊኖረው ይገባል። "ታየ" ለማለት የምንጠቀምበት ቃል "ተረኣ" تَرَءَا ሲሆን "ተገለጠ" ለሚለው ቃል ግን የተጠቀመበት "ተጀላ" تَجَلَّىٰ ነው፥ ይህ ቃል የጸሐይን ክብር ለመግለጽ ተጠቅሞበታል፦
92፥2 *በቀኑም "በተገለጸ" ጊዜ*፡፡ وَٱلنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ
91፥3 *በቀኑም ፀሐይን "በገለጻት" ጊዜ*። وَٱلنَّهَارِ إِذَا جَلَّىٰهَا

መቼም የጸሐይን ኑባሬ የሆነውን ሃይድሮጅን እና ሂልየም ማንም ማየት እንደማይችል እና በፀዳሏ እንደምትገለጥ ሁሉ አላህም በህላዌ ማንም በፊቱ እንደማይቆም ኢብኑ ዐባሥ እንደተናገረው የጣት ጥፍር ያክል ክብሩ ለተራራው ሲገለጥ እንኩትኩት አለ። መታየት ዓይን ላለው ነገር ነው። ዓይኖች ደግሞ አያዩትም፦
6፥103 *"ዓይኖች አያዩትም፡፡ እርሱም ዓይኖችን ያያል"፡፡ እርሱም ረቂቁ ውስጠ ዐዋቂው ነው*፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ ٱلْأَبْصَٰرُ وَهُوَ يُدْرِكُ ٱلْأَبْصَٰرَ ۖ وَهُوَ ٱللَّطِيفُ ٱلْخَبِيرُ
በባይብል ቢሆን "መገለጥ" ማለት "መታወቅ" ማለት እንጂ "መታየት" ማለት አይደለም፦
መሣፍንት 16፥17 እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ ብሎ *"የልቡን ሁሉ ገለጠላት"*።

ሶምሶም ለደሊላ "የልቡን ሁሉ ገለጠላት" ማለት "የልቡን ሁሉ አሳወቃት" ማለት እንጂ ሌላ ማለት አይደለም። ምክንያቱም ልብ ውስጥ በዓይን ሊታይ የሚችሉ ነገሮች ስለሌሉ። በተመሳሳይ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ተገለጠ ማለት እራሱን በተለያየ መንገድ ያስታውቃቸው ነበር ማለት እንጂ በዓይናቸው ያዩት ነበር ማለት አይደለም፦
1 ሳሙኤል 3፥21 *እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ፥ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥ ነበር*።

እግዚአብሔር የሚገለጠው በቃሉ ከሆነ ቃሉ ዕውቀት ነው። እግዚአብሔር ለአብርሃም "ተገለጠለት" ማለት እራሱ አስተዋወቀው ማለት እንጂ ኑባሬውን አየው ማለት አይደለም፦
ዘፍጥረት 17፥1 *አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም "ተገለጠለት" እና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን" አለው*።

በምንም ጊዜ ውስጥ በስጋ አይኑ እግዚአብሔር ያየ ማንም የለም። “መቼም” ማለትም “በየትኛውም ጊዜ”at any time” ማለት ነው። እግዚአብሔርን "ማንም" ማለትም አንድስ እንኳን ሰው አላየውም። ብቻውን አምላክ የሚሆነው እግዚአብሔር የማይታይ ነው፦
ዮሐንስ 1:18 *መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም*፤
1ኛ ዮሐንስ 4:12 *እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም*፤
1ኛ ጢሞቴዎስ 1:17 *”ብቻውን አምላክ ለሚሆን”* ለማይጠፋው *”ለማይታየውም”* ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
ዘጸአት 33:20 ደግሞም። *”ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም”* አለ።”

ይህ ማንም ያላየው ብቻውን አምላክ የሚሆን እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፥ ይህ አንድ አምላክ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፥ የዘላለም ኃይሉ እና አምላክነቱ የማይታይ ባሕርይው ነው፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 6:16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ *”ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም”*።
ሮሜ 1፥20 *የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና"*

ምን ትፈልጋለህ? በተፈጠሩት ፍጥረት በመታወቅ ይገለጻል እንጂ እርሱ ማንም አላየውም። ስለዚህ አላህ ለምን አልታየም? ብሎ እንቧ ከረዮ፣ እሪ ከረዮ፣ ያዙኝ ልቀቁኝ፣ አሸሼ ገዳጌ እዚህ ጋር ያበቃል። ፊሽካው ተነፍቷል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢሥቲሥላም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥83 *"በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም "ለእርሱ የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?"* أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

"ኢሥቲሥላም" اِسْتِسْلَام የሚለው ቃል "ኢሥተሥለመ" اِسْتَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" ለሚለው መስደር ሲሆን “መታዘዝ” “መገዛት” ማለት ነው። በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም ለአላህ የታዘዙ ናቸው፦
3፥83 *"በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም "ለእርሱ የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?"* أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

"የታዘዙ" ለሚለው ቃል የገባው የግስ መደብ “አሥለመ” أَسْلَمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ፍጥረት በሁለት መልኩ ለአላህ ይታዘዛል፥ አንዱ በግድ ሲሆን ይህ የግዴታ መታዘዝ "አል-ኢሥላሙ አት-ተክውኒይ" الإِسْلَٰم التَكْو۟نِي ይባላል። ሁለተኛው ደግሞ በውድ ሲሆን ይህ የውዴታ መታዘዝ "አል-ኢሥላሙ አት-ተሽሪዒይ" الإِسْلَٰم التَشْرِعِي ይባላል። ይህንን ነጥብ በነጥብ ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
"አል-ኢሥላሙ አት-ተክውኒይ"
"ተክውኒይ" تَكْو۟نِي ማለት "ኹነት" ማለት ሲሆን የሚሆን ማንኛውም ፍጥረት ያለ ምርጫው ለአላህ ይታዘዛል፥ ይገዛል። ሰማይና ምድርም፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት ወዘተ በትእዛዙ የተገሩ ናቸው፦
30፥25 *"ሰማይና ምድርም ያለምሰሶ በትእዛዙ መቆማቸው"*፣ ከዚያም መልአኩ ለትንሣኤ ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَن تَقُومَ السَّمَاءُ وَالْأَرْضُ بِأَمْرِهِ ۚ ثُمَّ إِذَا دَعَاكُمْ دَعْوَةً مِّنَ الْأَرْضِ إِذَا أَنتُمْ تَخْرُجُونَ
7፥54 *ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም "በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ" ፈጠራቸው፡፡ ንቁ! "መፍጠር እና ማዘዝ" የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ ክብሩ ላቀ*፡፡ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ ۗ أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ

በሰማያት ያሉ መላእክት ለአላህ ይገዛሉ፦
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት *"እርሱን ከመገዛት አይኮሩም"*፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
7፥206 እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላእክት *"እርሱን ከመገዛት አይኮሩም"*፡፡ ያወድሱታልም፡፡ ለእርሱም ይሰግዳሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُون

በምድር ያሉ ሰው፣ እንስሳት ወዘተ እርሱ ላቀመጠው የተፈጥሮ ሕግ ይገዛሉ። መፈጠር፣ መወለድ፣ መሞት፣ ማስነጠስ፣ ማዛጋት፣ መተኛት፣ መመገብ፣ የተመገቡትን ማስወገድ አላህ ያገራው ትእዛዝ ነው። ሰው ለዚህ ትእዛዝ በግድ ይገዛል። ለዚህ ነው ኢሥላም የተፈጥሮ ሃይማኖት ነው የምንለው፥ አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ኢሥላም ናት፦
30፥30 ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን *”አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት”*፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًۭا ۚ فِطْرَتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى فَطَرَ ٱلنَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ ٱللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
ኢማም ቡኻርይ መፅሐፍ 23, ሐዲስ 138
ከአቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተላለፈው ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- *“ማንም የሚወለድ ሰው “በአል-ፊጥራ በኢሥላም ላይ ሆኖ እንጂ አይወለድም”። ወላጆቹ ግን አይሁዳዊ ያደርጉታል ወይም ክርስቲያን ያደርጉታል አሊያም ዞሮስተርያን ያደርጉታል እንጂ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ كُلُّ مَوْلُودٍ يُولَدُ عَلَى الْفِطْرَةِ، فَأَبَوَاهُ يُهَوِّدَانِهِ أَوْ يُنَصِّرَانِهِ أَوْ يُمَجِّسَانِهِ

"አል-ፊጥራህ" الْفِطْرَةِ ማለት "ተፈጥሮ" ማለት ነው። አንድ ሰው ከካፊር ቤተሰብ ተወልዶ ወላጆቹ እስከሚያከፍሩት ወይም በአንደበቱ እኔ የዚህ እምነት ተከታይ ነኝ እስከሚል ድረስ በኢሥላም ሥር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 38
አቢ ሙዓዊያህ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ማንም የሚወለድ ሰው በአል-ፊጥራ በኢሥላም ላይ ሆኖ እንጂ አይወለድም፥ በአንደበቱ እስከሚል ድረስ"*። لَيْسَ مِنْ مَوْلُودٍ يُولَدُ إِلاَّ عَلَى هَذِهِ الْفِطْرَةِ حَتَّى يُعَبِّرَ عَنْهُ لِسَانُهُ

ይህ በተፈጥሮ መታዘዝ የሚታዘዘው ሰው "ሙሥተሥሊም" مُسْتَسْلِم ወይም "ሙሥተሥለም" مُسْتَسْلَم‎ ይባላል።
ነጥብ ሁለት
"አል-ኢሥላሙ አት-ተሽሪዒይ"
"ተሽሪዒይ" تَشْرِعِي ማለት "ሕግጋት" ማለት ሲሆን ከአላህ ወደ ነቢያቱ የሚወርድ መመሪያ፣ መርሕ፣ ሥርዓት ነው። ሰው የተፈጠረበት ዓላማ አላህ በብቸኝነት እንዲያመልክ ነው። ወደ ነቢያት የሚወርደው ተሽሪዒይ ደግሞ፦ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

"ከእኔ ሌላ አምላክ የለም" ብሎ የተናገረውን አንዱን አምላክ በብቸኝነት ስናመልክ "ሙሥሊም" مُسْلِم እንባላለን፥ የሙሥሊም ብዙ ቁጥር "ሙሥሊሙን" مُّسْلِمُون ሲሆን "ታዛዦች" በሚል መጥቷል፦
21፥108 *«ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለት ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُون
22፥34 *አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ "ለእርሱም ብቻ ታዘዙ"*፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

“ታዘዙ” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “አሥሊሙ” أَسْلِمُوا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰው ለአል-ኢሥላሙ አት-ተሽሪዒይ በውዴታ ወዶና ፈቅዶ ይታዘዛል አሊያም ያምጻል። በፈቃዱ የማመን ወይም የመክዳት ነጻ ምርጫ ስላለው በዓለማችን ላይ ከሓዲ አለ፥ አማኝም አለ፦
18፥29 «እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ *የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ*» በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ
64፥2 እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፡፡ *ከእናንተም ከሓዲ አለ፡፡ ከእናንተም አማኝ አለ*፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ فَمِنكُمْ كَافِرٌ وَمِنكُم مُّؤْمِنٌ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

ይህ በፈቃደኝነት መታዘዝ የሚታዘዘው ሰው "ሙሥሊም" مُسْلِم‎ ወይም "ሙሥለም" مُسْلَم‎ ይባላል።
ስለዚህ ከላይ የተነሳው ጥያቄ፦ "ፍጥረት እንዴት በግድ እና በውድ ይታዘዛል? ለሚለው፥ መልሳችን፦
1. "በግዴታ ይታዘዛሉ" ማለት "ሙጅመል" مُجّمَل ማለትም "ጥቅላዊ መታዘዝን"general submission" ያሳያል።
2. "በውዴታ ይታዘዛሉ" ማለት ደግሞ “ሙፈሰል” مُفَصَّل ማለትም "በተናጥል መታዘዝን"particular submission" ያሳያል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የወሕይ መልአክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥51 *ለሰው አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም”*፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

“ነቢይ” نَبِيّ የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “የሩቅ ወሬን አወራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሩቅ ወሬ አውሪ” ማለት ነው። የሚወርድለት “የሩቅ ወሬ” ደግሞ “ነበእ” نَبَأ ይባላል፥ ይህንን የሩቅ ወሬ ለአንድ ነቢይ ከሦስት መንገድ በአንዱ ይወርድለታል፦
42፥51 *ለሰው አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም”*፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

አንደኛው መንገድ አላህ በራእይ የሚያናግረው ነው፥ “ሩዕያ” رُّءْيَا ማለት “ራዕይ” ማለት ሲሆን ይህም ራዕይ ያ ነቢይ በሰመመን ወይም በተመስጦ ውስጥ ሆኖ አላህ የሚያናግርበት መንገድ ነው።
ሁለተኛው መንገድ አላህ በቀጥታ የሚያናግረው ነው፥ “ተክሊም” تَكْلِيم ማለት በሁለት ማንነት መካከል የሚደረግ “ምልልስ”conversation” ሲሆን አላህ ያለ ራዕይ ወይም ያለ መልአክ ሳይታይ ከግርዶ ወዲያ ሆኖ የሚያናግርበት መንገድ ነው።
ሦስተኛው መንገድ አላህ በመልአክ የሚያናግረው ነው፥ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው።

በዚህ ሦስተኛው መንገድ አላህ ለባሪያው መልእክተኛ መልአክ በመላክ ወሕይ ያወርዳል፦
16፥2 *"ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል"*፥ ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ الْمَلَائِكَةَ بِالرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ أَنْ أَنذِرُوا أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاتَّقُونِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መላእክት" የተባሉት ከአላህ ወሕይ ለነቢያት የሚያደርሱት መላእክት ናቸው፦
77፥5 *"መገሠጫን ወደ ነቢያት ጣይዎች በኾኑትም እምላለው"*። فَالْمُلْقِيَاتِ ذِكْرًا
37፥3 *"መገሠጫን በሚያነቡት እምላለሁ"*፡፡ فَالتَّالِيَاتِ ذِكْرًا

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ዚክራ" ذِكْرًا የተባለው ቁርኣን እና የቀደሙት መጽሐፍት ነው። የቁርኣን ጭብጥ እና ከነቢያችን"ﷺ" በፊት የነበሩት ጭብጥ ተውሒድ ነው፦
21፥24 ይልቁንም ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? «ማስረጃችሁን አምጡ፡፡ *ይህ መገሰጫ እኔ ዘንድ ያለው እና ከእኔ በፊትም የነበረ መገሰጫ ነው* በላቸው፡፡ أَمِ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ آلِهَةً ۖ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ ۖ هَـٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِيَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِي ۗ

"ይህ መገሰጫ እኔ ዘንድ ያለው እና ከእኔ በፊትም የነበረ መገሰጫ ነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። መገሰጫ የተባለውን ቁርኣን ወደ ነቢያችን"ﷺ" የሚያስተላልፈው ጂብሪል ሆኖ ሳለ በነጠላ ቁጥር "በሚያነበው" በማለት ፋንታ በብዙ ቁጥር "በሚያነቡት" የተባለበት ልክ እንደ ጂብሪል ሌሎችም መላእክት ለነቢያት መገሰጫ ስለሚያስተላልፉ ጂብሪል ማስተላለፉ ሌሎች እንዳስተላለፉ ይቆጠራል። ለምሳሌ በኑሕ ዘመን የተላከው መልእክተኛ ኑሕ ብቻ ነው፥ የኑሕ ሕዝቦች ኑሕን ሲያስተባብሉ "የኑሕን ሰዎችም መልክተኞችን ባስተባበሉ ጊዜ አሰጠምናቸው" ተብሏል፦
25፥37 *"የኑሕን ሰዎችም መልክተኞችን ባስተባበሉ ጊዜ አሰጠምናቸው"*፡፡ وَقَوْمَ نُوحٍ لَّمَّا كَذَّبُوا الرُّسُلَ أَغْرَقْنَاهُمْ

አይ ኑሕ ሆነ ከእርሱ በኃላ ያሉት መልእክተኞች የመልእክታቸው ጭብጥ ተውሒድ ስለሆነ ኑሕን ማስተባበል የተቀሩትን መልእክተኞች እንደማስተባለል ነው ከተባለ እንግዲያውስ ቁርኣን ሆነ የቀደሙት መጽሐፍት መገሰጫ ስለሆኑ ጂብሪል አነበበ ማለት ሌሎችም መላእክት አነበቡ ማለት ነው። "ዚክራ" ذِكْرًا ወደ ነቢያት የሚወርድ ወሕይ ነው። ይህንን ወሕይ ከአላህ ወደ ነቢያት ለማንበብ የሚላኩ መልእክተኞች እነዚህ የወሕ መላእክት ናቸው፦
22፥75 *"አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል"*፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا

ለምሳሌ መላእክት ከአላህ ዘንድ ወደ ኢብራሂም እና ወደ ሉጥ ተልከው መጥተዋል፦
11፥69 *"መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በልጅ ብስራት በእርግጥ መጡለት"*፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡ وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ
11፥77 *"መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡለት ጊዜ"* በእነርሱ ምክንያት አዘነ፡፡ ልቡም በነሱ ተጨነቀ፡፡ «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا لُوطًا سِيءَ بِهِمْ وَضَاقَ بِهِمْ ذَرْعًا وَقَالَ هَـٰذَا يَوْمٌ عَصِيب

ወደ ነቢያችን"ﷺ" ወሕይ የሚያወርድ የነበረው መልእክተኛ መልአክ ግን ደግሞ ጂብሪል ነው፦
2፥97 *"ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና"*፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

"በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና" የሚለው ኃይለ-ቃል ከላይ ከተጠቀሰው "መልክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን የሚያወርድለት" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አቀራረብ ነው፥ "ቢኢዝኒሂ" بِإِذْنِهِۦ እና "ቢኢዝኒሏህ" بِإِذْنِ اللَّه ተመሳሳይ ነጥብ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሥጂድ ፈረሰ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደኾናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

በምድር ላይ ያሉት መስጊዶች ሁሉ የአላህ ብቻ ናቸው። በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አንገዛም፤ ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ እናወድሰዋለን፥ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ እናጠራለን። መስጊዶች በውስጣቸው የአላህ ስሙ እንዳይወሳ የሚከለክሉ እና መስጊዶች በማፈራረስ እንዳይገነባ ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፥ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፦
2፥114 *”የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው?”* እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ

መሥጂድ ሲያፈራርሱ እጃችሁን አጣምራችሁ እዩ አልተልተባለም። ነገር ግን ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *”ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው”*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

አንቀጹ ይቀጥልና ሲበደሉ ፍትሕ የሚያስተካክሉ አካላት ከሌሉ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም ይፈርሳሉ፥ ይለናል፦
22፥40 ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ፡፡ *”አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር*”፡፡ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

ስለዚህ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና መስጊዶች ማፍረስ ወሰን ማለፍ ነው። “አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። አንደኛው በሌላኛ ፍትሕ ለማስከበር መገፍተሩ ማለትም መጋደል ከሌለ ወሰን አላፊዎች ምድሩቱን ያበላሻሉ። የታከለ ኡማ አስተዳደር የመሥጂድ ማፍረስ መንስኤ ፍትሕ ያለመኖር፥ በነሲብ፣ በስሜት፣ በጭፍን ከማሰብ፣ ከመናገር፣ ከመተግበር የመጣ ነው። ከዛ ይልቅ የሙሥሊሙ ደም በመካከለኛው ምስራቅ እንደ ጎርፍ ሲፈስ እየታየ ነው። ችግሩ ያለው ግን እኛ ጋርም ነው ባይ ነኝ። ምክንያቱም አምላካችን አላህ እውነቱን ቀድሞውኑ ነግሮናል፦
3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደኾናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

"ማበላሸትን አይገቱላችሁም" ማለት እኛን ለማጥፋት አያንቀላፉም። "ጉዳታችሁን ይወዳሉ" ማለት ኢሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ ሲሉ እያየን ነው። "ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች" ማለት እንደነ ዘመድኩን በቀለ ያሉ በሚድያ ላጫቸውንና ቅርሻታቸውን የሚያዝረከርኩ አሉ። ከእነሱ ይልቅ ሙሥሊሙ እንደሚወዱ አፈ ቅቤ፤ ልበ ጬቤ ሰዎች ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እሥልምና ዶግ አመድ ቢሆንላቸው የልባቸው ምኞች ነው። የኢሥላም እድገት፥ የሙሥሊሙ ጥንካሬ ያስከፋቸዋል። የሙሥሊሙ ውድቀት ደስታቸው ነው፦
3፥120 ደግ ነገር ብትነካችሁ ታስከፋቸዋለች፡፡ መጥፎም ነገር ብታገኛችሁ በእርሷ ይደሰታሉ፡፡ ብትታገሱና ብትጠነቀቁም ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም፡፡ አላህ በሚሠሩት ሁሉ በዕውቀቱ ከባቢ ነውና፡፡ إِن تَمْسَسْكُمْ حَسَنَةٌ تَسُؤْهُمْ وَإِن تُصِبْكُمْ سَيِّئَةٌ يَفْرَحُوا بِهَا ۖ وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا لَا يَضُرُّكُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئًا ۗ إِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطٌ

አላህ በሚሠሩት ሁሉ በዕውቀቱ ከባቢ ነውና ብንታገስና ብንጠነቅ ቅቤ አንጓችና አስብቶ አራጅ ተንኮላቸው ምንም አይጎዳንም፡፡ "ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ" ተብለናል። አለመዝረክረክ ነው። አላህ ጥንቁቆች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሠለፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

"ሠለፍ" سَلَف የሚለው በሰፊው የሚነገር ቃል "ሠለፈ" سَلَفَ ማለትም "ቀደመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቀደምት" ማለት ሲሆን "ሠለፊይ" سَلَفِيّ ማለት ደግሞ "ቀዳማይ" ማለት ነው። የሠለፊይ ብዙ ቁጥር "ሠለፊዩን" سَلَفِيُّون‎ ሲሆን "ቀዳማውያን" ማለት ነው። አምላካችን አላህ ስለ ቀዳማውያን እንዲህ ይናገራል፦
9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ "የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች" እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

"የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። እነዚህም "ሰሓቢይ" صَحَابِيّ ሲባሉ የነቢያችን”ﷺ” ውድ “ባልደረባ”companion” ናቸው። እነዚህ ባልደረቦች በሁለት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦ “ሙሃጂር” እና “ነሲር” ናቸው። “ሙሃጂር” مُهَاجِر ማለት “ስደተኛ” ማለት ሲሆን የሙሃጂር ብዙ ቁጥር "ሙሃጂሩን" مُهَاجِرُون ነው፥ ሙሃጂሩን ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱትን መካውያን ሰሓባዎችን ያመለክታል። መዲና ላይ ከመካ የተሰደዱትን እረድተው የተቀበሉ ሰሓባዎች “ነሲር” نَصِير ማለትም “ረዳት” በብዜት “አንሷር” أَنْصَار ይባላሉ፦
8፥74 *እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉ እና የረዱ እነዚያ እነርሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

"የተሰደዱ" የተባሉት ሙሃጂሩን ሰሓቢይ ሲሆኑ "የረዱ" የተባሉት ደግሞ አንሷር ሰሓቢይ ናቸው፥ እነዚህ የመጀመሪያው ትውልድ ናቸው። "የተከተሏቸው" የተባሉት ሁለተኛው ትውልድ "ታቢዒይ" تَابِعِيّ እና ሦስተኛው ትውልድ "ታቢዑ አት-ታቢዒን" تَابِع التَابِعِين ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ ሠለፍይ ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72
ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው”*። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم

የመጀመሪያው ትውልድ ሰሓቢይ ነው፣ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ታቢዒይ ነው፣ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ታቢዑ አት-ታቢዒን ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ "አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን" ٱلسَلَف ٱلصَالِحُون ማለትም "መልካሞቹ ቀደምት" ሲሆኑ የእነርሱ መንሀጅ ጂሃድ ነው። “መንሀጅ” مَنْهَج ማለት "ፍኖት" "ፋና" "መንገድ" ማለት ነው። "በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَٰهَدَ ማለትም “ታገለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ማለት ነው። “ጁሁድ” جُهْد ማለት “መታገል” ነው፥ ጂሃድ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በሐቅ እና በባጢል መካከል የሚደረግ ትግል ነው። እውነትን ለማንገስ ሐሰትን ለማርከስ፥ ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ በአላህ መንገድ የሚታገል፣ የሚጥርና የሚጋደል በነጠላ “ሙጃሂድ” مُجَٰهِد ይባላል፥ በብዜት ደግሞ “ሙጃሂዱን” مُجَاهِدُون ይባላሉ፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ

ምእምናን ማለት በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፥ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 28
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በንብረታችሁ፣ በነፍሶቻችሁ እና በአንደበታችሁ ሙሽሪኮችን ታገሉ”*። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏:‏ ‏ “‏ جَاهِدُوا الْمُشْرِكِينَ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنْفُسِكُمْ وَأَلْسِنَتِكُمْ ‏

እኩይ ድርጊት ለመታገል ሦስት ምርጫ አለን፥ እርሱም፦
1. በእጅ መታገል፣
2. በአንደበት መታገል፣
3. በልብ መታገል ነው፦
ሪያዱ አስ-ሳሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ *“ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”*። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ "‏من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان
ስለዚህ ሠለፍይ ማለት ከላይ የተጠቀሱት ሦስቱ ትውልድ ሲሆኑ ሠለፍ ማለት የሦስቱ ትውልድ መንሀጅ ነው፥ የሦስቱ ትውልድ መንሀጅ ደግሞ ጂሃድ ነው። እኛ ደግሞ የእነርሱን ፈለግ መከተል ያለብን ሙዕሚን ነን። ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ተሹሞ መጨረሻው እሳት ነው፦
4፥115 ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا

አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን የተረዱበትን እና የተገበሩበትን መንሀጅ ለመረዳትና ለመተግበር ያብቃን፥ አላህ በአሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን መንሀጅ የምንመራ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም!

ለመላው ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እህቶቼ፦ "እንኳን የዒዱል አድሓ በዓል በሠላም አደረሳችሁ" ብያለው።

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፤ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፤ ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

በዓሉ ዘርፈ ብዙ የአምልኮ መርሃ-ግብር ያዘለ እንደመሆኑ ረገድ አላህ በኢኽላስ ይቀበለን። በዓሉን የደስታ፣ የፍቅር፣ የመከባበር፣ የብልጽግና ያርግልን! አሚን። ተቀበለሏህ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል፥ ዒድ ሙባረክ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዚክር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥28 *"እነርሱም እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ"*፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

ኢሥላም አጠቃላይ የሕይወት ዘይቤ አቅፏል፥ ይህም መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ(ሥ-መንግሥት) ይዘት ነው። መንፈሳዊ ማለት "አምልኮታዊ" ይዘት ነው፥ ከአምልኮ መካከል አንዱ ደግሞ ዚክር ነው። "ዚክር" ذِكْر የሚለው ቃል “ዘከረ” ذَكَرَ ማለትም “አስታወሰ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አላህ ማስታወስ” ማለት ነው፥ ዚክር በሌላ ስሙ "ኢሥቲዝካር" اِسْتِذْكَار "ተዝኪር" تَذْكِير "ተዝኪራ" تَذْكِرَة "ተዝካር" تَذْكَار "ቲዝካር" تِذْكَار ይባላል። "አዝካር" أَذْكَار የዚኪር ብዙ ቁጥር ነው።
አምላካችን አላህን በሶላት ማስታወስ በዋነኝነት የአምልኮ ክፍል ነው፦
20፥14 «እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ *"ሶላትንም እኔን ለማውሳት ስገድ"*፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
62፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ*፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
29፥45 ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ *ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው"*፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ ۖ إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ

ሶላት በኢማን፣ በኢኽላስ እና በኢቲባዕ ከተሰገደ ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ይከለክላል፥ አላህን ማውሳት ግን ከሶላት ውጪም ስለሚደረግ ከሁሉ ነገር በላጭ ነው። ጠዋትና ማታ የሚዘከረው የዓለማቱ ጌታ የአሏህ ስም ነው፦
7፥205 ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል *በጧትም በማታም አውሳው*፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡ وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ
76፥25 *"የጌታህንም ስም በጧትና ከቀትር በላይ አውሳ"*፡፡ وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
73፥8 *"የጌታህንም ስም አውሳ፥ ወደ እርሱም መገዛትን ተገዛ"*፡፡ وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ وَتَبَتَّلْ إِلَيْهِ تَبْتِيلًا

"ተበተል" تَبَتَّلْ ማለት "ተገዛ" ማለት ሲሆን ትእዛዝ ነው፥ "ተብቲል" تَبْتِيل ማለት ደግሞ "መገዛት" ማለት ነው። አላህን ብዙ በማውሳት መገዛት ልብ ያረካል፥ ልብም ይረጥባል። ልቦችን ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ግን ወዮልን፦
33፥41 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا
13፥28 *"እነርሱም እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ"*፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ
39፥22 *ልቦቻቸውም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው"*፡፡ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው፡፡ فَوَيْلٌ لِّلْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكْرِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ

ከዚክር የራቀ ሰው ወዮ ያስባለው ጉዳይ ምን ይሆን? አዎ ሸያጢን የሚጸናወጡት ከዚኪር የራቀው ሰው ነው፥ ከዚክር የሚርቀውን ሰው ሸይጧን “ቀሪን” قَرِين ማለት “ጓደኛ” ይሆነዋል። ሸይጧን ደግሞ ብዙ አጀንዳ አለው፥ ከአጀንዳዎቹ መካከል በሚያሰክር መጠጥ፣ በቁማር፣ በመካከላችን ጠብንና ጥላቻን ማድረግ ነው፦
43፥36 *ከአልረሕማን ዚክር የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን፡፡ ስለዚህ እርሱ ለእርሱ ቁራኛ ነው*፡፡ وَمَن يَعْشُ عَن ذِكْرِ الرَّحْمَـٰنِ نُقَيِّضْ لَهُ شَيْطَانًا فَهُوَ لَهُ قَرِين
5፥91 *ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል አላህን ከማውሳት እና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው"*፡፡ ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ተከልካዮች ናችሁን? ተከልከሉ፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُوقِعَ بَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ فِي الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ وَيَصُدَّكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَعَنِ الصَّلَاةِ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّنتَهُونَ
ቁርኣን "ዚክር" ذِكْر ነው፥ በውስጡ አያቱል ሩቀያህ ይዟል። ከቁርኣን ስንርቅ ዘፈን ማዳመጥ ይጀመራል፣ ዘፈን ከተደመጠ ደግሞ መዝሙር ይደመጣል፣ ከዚያ በኩፍር ውስዋስ "ከፈርኩኝ" ይባላል። ሌላው ሸይጧን አላህን ማስታወስ የሚያስረሳን ባለን ሃብት እና በልጆቻችን መሽጉል በማድረግ ነው፦
58፥19 በእነርሱ ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው፡፡ *አላህንም ማስታወስን አስረሳቸው፡፡ እነዚያ የሰይጣን ጭፍሮች ናቸው"*፡፡ ንቁ! የሰይጣን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُون
63፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ገንዘቦቻችሁ እና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታሉዋችሁ፡፡ ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ

"ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ከዚክር መራቅ ኪሳራ ከሆነ እንግዲህ ዚክር ይህንን ያህን አንገብጋቢ ጉዳይ ነው ማለት ነው። የአዝካር አይነቶች ደግሞ ብዙ ናቸው፥ እነርሱም፦ ተሕሊል፣ ተክቢር፣ ተሕሚድ፣ ተሥቢሕ፣ ተምጂድ፣ ኢሥቲግፋር፣ ኢሥቲዓዛህ፣ በስመሏህ፣ ሐስበላህ ናቸው። እነዚህን ጥርስ እና ምላሳቸውን እየነቀስን ጥልልና ጥንፍፍ አርገን በሚቀጥሉት ክፍሎች ኢንሻላህ እናያለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዚክር

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥152 *"አስታውሱኝም፥ አስታውሳችኋለሁና"*። ለእኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡ فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ وَاشْكُرُوا لِي وَلَا تَكْفُرُونِ

ዚክር አንድ
"ተሕሊል"
"ተሕሊል" تَحْلِيل የሚለው ቃል "ሐልለለ" حَلَّلَ ማለትም "አወጀ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "አዋጅ" ማለት ነው። ይህም አዋጅ "ላ ኢላሀ ኢልለሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ነው፥ "ላ ኢላሀ ኢልለሏህ" ማለት "አምላክ የለም፥ ከአሏህ በስተቀር" ማለት ነው። ይህ ተሕሊል ሁለት ማዕዘናት አሉት፥ እነርሱም፦ "ነፍይ" እና "ኢስባት" ናቸው።
1ኛ. "ነፍይ" نَفْي የሚለው ቃል "ነፋ" نَفَى‎ ማለትም "አፈረሰ" ለሚለው ሥርወ-ቃል መስደር ሲሆን "ማፍረስ" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ" لَا إِلٰهَ ማለት "አምላክ የለም" በማለት ጣዖታትን የምራፈራርስበት አዋጅ ነው።
2ኛ. "ኢስባት" إِثْبَات የሚለው ቃል "አስበተ" أَثْبَتَ‎ ማለትም "ጸደቀ" ለሚለው ሥርወ-ቃል መስደር ሲሆን "ማፅደቅ" ማለት ነው። إِلَّا اللّٰه "ኢልለሏህ" ማለት "ከአሏህ በስተቀር" በማለት አምላክነቱን የምናጸድቅበት አዋጅ ነው።

የሚያጅበው ነገር ከንፈር እና ከንፈር ሳይነካካ በምላስ የሚዘከር ዚክር ቢኖር "ላ ኢላሀ ኢልለሏህ" ነው። አምላካችን አላህ በሦስተኛ መደብ፦ "ላ ኢላሀ ኢልለሏህን ዕወቅ" ይለናል፥ ነቢያችንም"ﷺ"፦ *"በላጩ ዚክር ላ ኢላሀ ኢልለሏህን ነው" ብለውናል፦
47፥19 *እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ*፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 14
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ" ሰምቶ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"በላጩ ዚክር ላ ኢላሀ ኢልለሏህን ነው፥ በላጩ ዱዓእ አልሓምዱ ሊላህ ነው"*። قَالَ سَمِعْتُ جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ، رضى الله عنهما يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ أَفْضَلُ الذِّكْرِ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَفْضَلُ الدُّعَاءِ الْحَمْدُ لِلَّهِ ‏

የኢማን ትልቁ ቅርንጫፍ ከሊመቱል-ዐቂዳህ የሆነው “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፤ ትልቁ ቅርንጫፍ “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ማለት ነው፥ ትንሹ ደግሞ ከመንገድ ላይ እንቅፋት ማስወገድ ነው። ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏

ዚክር ሁለት
"ተክቢር"
"ተክቢር" تَكْبِير የሚለው ቃል "ከብበረ" كَبَّرَ‎ ማለትም "አተለቀ" ወይም "አከበረ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "ማክበር" ወይም "ማተለቅ" ማለት ነው። ይህም ተክቢራ "አሏሁ አክበር" اللّٰهُ أَكْبَر ነው፥ "አሏሁ አክበር" ማለት "አሏህ ታላቅ ነው" ወይም "አሏህ ክቡር ነው" ማለት ነው፦
23፥10 እነዚያ የካዱት ሰዎች «ወደ እምነት በምትጠሩ እና በምትክዱ ጊዜ *አላህ እናንተን መጥላቱ እራሳችሁን ዛሬ ከመጥላታችሁ የበለጠ ታላቅ ነው*» በማለት ይጠራሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا يُنَادَوْنَ لَمَقْتُ اللَّهِ أَكْبَرُ مِن مَّقْتِكُمْ أَنفُسَكُمْ إِذْ تُدْعَوْنَ إِلَى الْإِيمَانِ فَتَكْفُرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አሏሁ አክበር" اللَّهِ أَكْبَر የሚል ኃይለ-ቃል አለ። አላህን "አሏሁ አክበር" በማለት እናከብረዋለን፥ "ተክቢራ" تَكْبِيرًا ማለት የተክቢር ተለዋዋጭ ቃል ነው፦
17፥111 «ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዘው፣ ለእርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው፣ ለእርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይገባው በልም፡፡ *"ማክበርንም አክብረው"*፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي لَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُن لَّهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَلَمْ يَكُن لَّهُ وَلِيٌّ مِّنَ الذُّلِّ ۖ وَكَبِّرْهُ تَكْبِيرًا

ዚክር ሦስት
"ተሕሚድ"
“ሐምድ” حَمْد ማለት “ሐሚደ” حَمِدَ ማለትም “አመሰገነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምስጋና” ማለት ነው፥ ሐምድ የአምልኮ አይነት ነው፤ በቁርኣን ከተጠቀሱ የአላህ ስሞች መካከል “አል-ሐሚድ” الْحَمِيد ሲሆን “እጅግ በጣም የተመሰገነ” ማለት ነው፦
31፥26 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ *አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው*፡፡ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

አላህ አምላኪዎች “ሓሚዱን” حَٰمِدُون ማለትም “አመስጋኞች” ይባላሉ፦
9፥112 እነርሱ ተጸጻቺዎች፣ ተገዢዎች፣ *”አመስጋኞች”*፣ ጿሚዎች፣ አጎንባሾች፣ በግንባር ተደፊዎች፣ በበጎ ሥራ አዛዦች ከክፉም ከልካዮች፣ የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው ምእምናንንም አብስር፡፡ التَّائِبُونَ الْعَابِدُونَ الْحَامِدُونَ السَّائِحُونَ الرَّاكِعُونَ السَّاجِدُونَ الْآمِرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَالنَّاهُونَ عَنِ الْمُنكَرِ وَالْحَافِظُونَ لِحُدُودِ اللَّهِ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِين

"ተሕሚድ" تَحْمِيد የሚለው ቃል "ሐምመደ" حَمَّدَ ማለትም "ተመሰገነ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "ማመስገን" ማለት ነው። ይህም ተዝኪራ "አልሓምዱ ሊላህ" ٱلْحَمْدُ لِلَّه ነው፥ "አልሓምዱ ሊላህ" ማለት "ምስጋና ለአላህ ይገባው" ማለት ነው፦
1፥2 *"ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው"*። ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ