ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.4K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ዚክር አራት
"ተሥቢሕ"
"ሡብሓን" سُبْحَٰن የሚለው ቃል "ሠብበሐ" سَبَّحَ ማለትም "አመሰገነ" ወይም "አከበረ" "አጠራ" "አወደሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማህሌት" "ውዳሴ" "ስብሐት" ማለት ነው፦
30፥17 አላህንም በምታመሹ ጊዜ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት"*፡፡ فَسُبْحَانَ اللَّهِ حِينَ تُمْسُونَ وَحِينَ تُصْبِحُونَ

"አጥሩ" ለሚለው ቃል የገባው "ሡብሓነ" سُبْحَانَ ሲሆን "ተሥቢሕ" تَسْبِيح ማለት ደግሞ "ተስብሖት" ማለት ነው። ለአላህ የምራቀርበት ስብሐት ከላይ አንቀጹ ላይ እንደተቀመጠው "ሡብሓነ አላህ" سُبْحَانَ اللَّه ነው፦
15፥98 *ጌታህንም "ከማመስገን ጋር "አጥራው" ከሰጋጆቹም ኹን*፡፡ فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ
103፥3 *ጌታህን ከማመስገን ጋር "አጥራው"፡፡ ምሕረትንም ለምነው፡፡ እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና*፡፡ فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَاسْتَغْفِرْهُ ۚ إِنَّهُ كَانَ تَوَّابًا

ዚክር አምስት
"ተምጂድ"
"መጅድ" مَجْد የሚለው ቃል "መጀደ" مَجَدَ ማለትም "አከበረ" "ከፍ አረገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ክብር" "ከፍታ" ማለት ነው። በቁርኣን ከተጠቀሱ የአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-መጂድ” الْمَّجِيد ሲሆን “እጅግ በጣም የተከበረ” ማለት ነው፦
11፥73 «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን *እርሱ አላህ ምስጉን ክቡር ነውና*» አሉ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 48
አቡ ሑመይድ አሥ-ሣዒዲይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *”ሰዎች፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በእርሶ ላይ እንዴት ሰለዋት እናውርድ? አሉ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ሆይ! ሰለዋትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ፥ ሰለዋትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በረካትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ ልክ በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ፤ አንተ የተመሰገንክ እና የተከበርክ ነህ*። أَخْبَرَنِي أَبُو حُمَيْدٍ السَّاعِدِيُّ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُمْ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ قُولُوا اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ‏”‌‏.‏

ይህ አላህ በአምልኮ ከፍ ከፍ ማድረግ "ተምጂድ" تَمْجِيد ወይም "ሐውቀላህ" حَوْقَلَة ይባላል። ይህም ተዝኪራ "ላ ሀውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢልሏህ" لا حَوْلَ وَلا قُوَّةَ إِلا بالله ነው። "ላ ሀውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢልሏህ" ማለት "ከአላህ በስተቀር ብልሃት ሆነ ኃይል የለም" ማለት ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 170
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ *"ከጀነት ሃብት አንዱን ሃብት ልጠቁምህን? አሉኝ። እኔም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አዎ" አልኩኝ። እርሳቸውም፦ "ከአላህ በስተቀር ብልሃት ሆነ ኃይል የለም" ነው፥ አሉ"*። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ قَالَ لِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ أَلاَ أَدُلُّكَ عَلَى كَنْزٍ مِنْ كُنُوزِ الْجَنَّةِ ‏"‏ ‏.‏ قُلْتُ بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ ‏.‏ قَالَ ‏"‏ لاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ ‏

ኢንሻላህ የተቀሩትን ስለ ኢሥቲግፋር፣ ኢሥቲዓዛህ፣ በስመሏህ፣ ሐስበላህ በክፍል ሦስት እናጠቃልላለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዚክር

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥35 *"አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል"*፡፡ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

ዚክር ስድስት
"ኢሥቲግፋር"
በቁርኣን ከተጠቀሱ የአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-ገፋር” الغَفَّار ወይም “አል-ገፉር” الغَفُور ሲሆን “ይቅርባዩ” ማለት ነው። “መግፊራህ” مَّغْفِرَة ማለት “ይቅርታ” ማለት ሲሆን የእርሱ ባሕርይ ነው፦
15፥49 *”ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
49፥5 ወደ እነርሱም እስክትወጣ ድረስ እነርሱ በታገሱ ኖሮ ለእነርሱ በላጭ በኾነ ነበር፡፡ *”አላህም እጅግ ይቅርባይ መሓሪ ነው”*፡፡ وَلَوْ أَنَّهُمْ صَبَرُوا۟ حَتَّىٰ تَخْرُجَ إِلَيْهِمْ لَكَانَ خَيْرًۭا لَّهُمْ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ

"ኢሥቲግፋር" اِسْتِغْفار የሚለው ቃል "ኢሥተግፈረ" اِسْتَغْفَرَ ማለትም "ይቅርታ ጠየቀ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "ይቅርታ መጠየቅ" ማለት ነው። ይህም ተዚኪራ "አሥተግፊሩሏህ" أَسْتَغْفِرُ اللّٰه‎ ነው። አሥተግፊሩሏህ" ማለት "አላህን ይቅርታ እጠይቃለው" ማለት ነው፦
11፥3 *"ጌታችሁንም ይቅርታን ጠይቁት"*፡፡ وَأَنِ ٱسْتَغْفِرُوا۟ رَبَّكُمْ

"ይቅርታን ጠይቁ" ለሚለው ቃል የገባው "ኢሥተግፊሩ" ٱسْتَغْفِرُوا۟ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። የአላህ የይቅርታው ጥልቀትና ስፋት፥ ምጥቀትና ልቀት የሚያጅብ ነው።

ዚክር ሰባት
"ኢሥቲዓዛህ"
"ኢሥቲዓዛህ" إِسْتِعَاذَة የሚለው ቃል "ኢሥተዓዘ" اِسْتَعَاذَ ማለትም "ተጠበቀ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "መጠበቅ" ማለት ነው። ይህም ተዚኪራ "አዑዙ ቢሏሂ ሚነሽ ሸይጧኒር ረጂም" أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ ነው። "አዑዙ ቢሏሂ ሚነሽ ሸይጧኒር ረጂም" ማለት "እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ እጠበቃለው" ማለት ነው፦
16፥98 *"ቁርኣንንም ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ"*፡፡ فَإِذَا قَرَأْتَ الْقُرْآنَ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተጠበቅ" ለሚለው ቃል የገባው "ኢሥተዒዝ" اسْتَعِذْ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የባህርይ ስም እንጂ የተፀውኦ ስም አይደለም፤ ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
ዚክር ስምንት
"በስመሏህ"
አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ብሎ አዟቸዋል፦
96፥1 *”አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም”*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

ቁርኣን ሲጀምር የሚነበበው “ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም” ነው፥ ከአንድ ሱራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሱራህ ሲጀምር “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው” በሚል ነው። አንድ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ቃል ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሱራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}

"በስመሏህ" بَسْمَلَة የሚለው ቃል "በሥመለ" بَسْمَلَ‎ ማለትም "ጠራ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "የአላህን ስም መጥራት" ማለት ነው። ይህም ተዝኪራ "ቢሥሚል ሏሂር ረሕማኒር ረሒም" بِسْمِ اللهِ الرَّحْمٰنِ الرَّحِيْمِ ነው። "ቢሥሚል ሏሂር ረሕማኒር ረሒም" ማለት "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" ማለት ነው፦
1፥1 *"በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው"*፡፡ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم

ዚክር ዘጠኝ
"ሐስበላህ"
በቁርኣን ከተጠቀሱት የአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-ወኪል” الْوَكِيل ሲሆን “መመኪያ” “መጠጊያ” “መሸሸጊያ” ማለት ነው፦
39፥9 እርሱም የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ *”ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው”*፡፡ رَّبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا

በአላህ ላይ መመካት “ተወኩል” تَوَكُّل‎ ይባላል። ሰይጧን በእነዚያ ባመኑት እና በአላህ ላይ በሚመኩት ላይ ስልጣን የለውም፦
16፥99 *”እርሱ በእነዚያ ባመኑት እና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና”*፡፡ إِنَّهُ لَيْسَ لَهُ سُلْطَانٌ عَلَى الَّذِينَ آمَنُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

“በሚጠጉት” ለሚለው ቃል የገባው “የተወከሉነ” يَتَوَكَّلُونَ ሲሆን ቁርጥ ሐሳብም ባደረጉ ጊዜ አላህ በቂዬ ነው ብለው በአላህ ላይ ሙሉ ለሙሉ የተወከሉ ባሮቹ ደግሞ “ሙተወከሉን” مُتَوَكِّلُون ይባላል፦
39፥38 *«አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ»* በል፡፡ قُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ ۖ عَلَيْهِ يَتَوَكَّلُ الْمُتَوَكِّلُونَ
6፥159 *”ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ፡፡ አላህ በእርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና”*፡፡ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَوَكِّلِينَ

ይህ አላህን በቂ ማድረግ "ሐስበላህ" حَسْبَلَة ይባላል። አላህ መጠጊያ ስናደርግ “ሐሥቡነል ሏህ ወኒዕመል ወኪል” حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيل እንላለን፥ "ሐሥቡነል ሏህ ወኒዕመል" ማለት “በቂያችንም አላህ ነው፥ ምን ያምርም መጠጊያ” ማለት ነው፦
3፥173 እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ ጦርን አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» ይሉዋቸውና ይህም እምነትን የጨመረላቸው *«በቂያችንም አላህ ነው፥ ምን ያምርም መጠጊያ!»* ያሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4564
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ኢብራሂም በእሳት ውስጥ እያለ የመጨረሻ ንግግሩ፦ *”በቂያችንም አላህ ነው፥ ምን ያምርም መጠጊያ”* የሚል ነበር”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ آخِرَ قَوْلِ إِبْرَاهِيمَ حِينَ أُلْقِيَ فِي النَّارِ حَسْبِيَ اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ‏

ከላይ የዘረዘርናቸው የዚክር አይነቶች ትሩፋትና ምንዳ፥ ወሮታና አጸፌታ በዱንያህ ቀልብ ማርጠብ ነው። ዚክር የሞተ ቀልብን ሕያው ማድረጊያ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 80, ሐዲስ 102
አቢ ሙሣ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጌታውን የሚዘክር እና የማይዘክር ምሳሌ፥ ልክ እንደ ሕያው እና እንደ ሙታን ነው"*። عَنْ أَبِي مُوسَى ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَثَلُ الَّذِي يَذْكُرُ رَبَّهُ وَالَّذِي لاَ يَذْكُرُ مَثَلُ الْحَىِّ وَالْمَيِّتِ

አላህ የሚዘክር ደግሞ በአኺራ አላህ ስሙን ይዘክርለታል፦
2፥152 *አስታውሱኝም፥ አስታውሳችኋለሁና"*። ለእኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡ فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ وَاشْكُرُوا لِي وَلَا تَكْفُرُونِ
ኢማም ሙስሊም, መጽሐፍ 55, ሐዲስ 22
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አላህ እንዲህ ይላል አሉ፦ *“እኔን እንደረሳኸኝ እረሳካለው”* فَيَقُولُ فَإِنِّي أَنْسَاكَ كَمَا نَسِيتَنِي

አላህን የሚያስታውሱ ወንድ ባሮቹ በነጠላ "ዛኪር" ذَاكِر‎ በብዜት "ዛኪሪን" ذَّاكِرِين ሲባሉ፥ አላህን የሚያስታውሱ ሴት ባሮቹ ደግሞ በነጠላ "ዛኪራህ" ذَاكِرَة በብዜት "ዛኪራት" ذَّاكِرَات ይባላሉ። አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፦
33፥35 *"አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል"*፡፡ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

ምንኛ የታደሉ ናቸው? አላህ ዛኪሪን እና ዛኪራት ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ስግደት በኢሥላም

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥15 *"በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ"*። وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا

“ሡጁድ” سُّجُود የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ታዘዘ” “ተገዛ” ለሚለው መስደር ሲሆን “መታዘዝ” “መገዛት” ማለት ነው። በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም ለአላህ የታዘዙ ናቸው፦
13፥15 *"በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ"*። وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا

“ይሰግዳሉ” ለሚለው ቃል የገባው የግስ መደብ “የሥጁዱ” يَسْجُدُ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ" የሚለው "በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይታዘዛሉ" በሚል መጥቷል፦
3፥83 *”በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም “ለእርሱ የታዘዙ” ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?”* أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ “በግዴታ ይሰግዳሉ” ማለት “ሙጅመል” مُجّمَل ማለትም “ጥቅላዊ መታዘዝን”general prostration” ያሳያል። በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ “በውዴታ ይሰግዳሉ” ማለት ደግሞ “ሙፈሰል” مُفَصَّل ማለትም “በተናጥል መታዘዝን”particular prostration” ያሳያል። ከዚህ አንቀጽ የምንረዳው ፍጥረት በሁለት መልኩ ለአላህ ይታዘዛል፥ አንዱ በግድ ሲሆን ይህ የግዴታ መታዘዝ “አሥ-ሡጁዱ አት-ተክውኒይ” السُّجُود التَكْو۟نِي ይባላል። ሁለተኛው ደግሞ በውድ ሲሆን ይህ የውዴታ መታዘዝ “አሥ-ሡጁዱ አት-ተሽሪዒይ” السُّجُود التَشْرِعِي ይባላል። ይህንን ነጥብ በነጥብ ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
“አሥ-ሡጁዱ አት-ተክውኒይ”
“ተክውኒይ” تَكْو۟نِي ማለት “ኹነት” ማለት ሲሆን የሚሆን ማንኛውም ፍጥረት ያለ ምርጫው ለአላህ በግዴታ ይሰግዳል። ሰማይና ምድርም፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ተራራዎችም፣ ለአላህ ይሰግዳሉ፦
22፥18 *አላህ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ፣ ፀሐይ እና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም ከሰዎች ብዙዎችም ለእርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን?"* أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَسْجُدُ لَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ وَالنُّجُومُ وَالْجِبَالُ وَالشَّجَرُ وَالدَّوَابُّ وَكَثِيرٌ مِّنَ النَّاس

ለአላህ ይሰግዳሉ ማለት በትእዛዙ የተገሩ ናቸው ማለት ነው፦
7፥54 *ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም “በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ” ፈጠራቸው፡፡ ንቁ! “መፍጠር እና ማዘዝ” የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ ክብሩ ላቀ*፡፡ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ ۗ أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ

ፀሐይ እና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾች ይሰግዳሉ ሲባል "ሡጁድ" ማለት በወገብ "ማጎንበስ" እና በግንባር "መደፋት" ብቻ ነው ብለን ስለተረዳነው ነው።
"ኸር" خَرّ የሚለው ቃል "ኸረ" خَرَّ ማለትም "ተደፋ" ለሚለው መስደር ሲሆን "መደፋት" ማለት ነው።
"ሩኩዕ" رُكُوع የሚለው ቃል "ረከዐ" رَكَعَ ማለትም "አጎነበሰ" ለሚለው መስደር ሲሆን "ማጎንበስ" ማለት ነው።
ዐቅል የሌለው ፍጥረት "ኸር" እና "ሩኩዕ" ላያደርግ ይችላል። ነገር ግን አላህ ላስቀመጠው የተፈጥሮ ሕግ ይታዘዛሉ። እንዴት እንደሚታዘዙ ላናውቅ እንችላለን፥ ተሥቢሕ ሲያረገሩ እንደማናውቀው ሁሉ እንዴት እንደሚታዘዙም ዐናውቅም፦
4፥44 *"ሰባቱ ሰማያት እና ምድርም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያጠራሉ፡፡ ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም፡፡ ግን ማጥራታቸውን ዐታውቁትም"*፡፡ እርሱ ታጋሽ መሓሪ ነው፡፡ تُسَبِّحُ لَهُ السَّمَاوَاتُ السَّبْعُ وَالْأَرْضُ وَمَن فِيهِنَّ ۚ وَإِن مِّن شَيْءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمْدِهِ وَلَـٰكِن لَّا تَفْقَهُونَ تَسْبِيحَهُمْ ۗ إِنَّهُ كَانَ حَلِيمًا غَفُورًا
ነጥብ ሁለት
“አሥ-ሡጁዱ አት-ተሽሪዒይ”
“ተሽሪዒይ” تَشْرِعِي ማለት “ሕግጋት” ማለት ሲሆን ከአላህ ወደ ነቢያቱ የሚወርድ መመሪያ፣ መርሕ፣ ሥርዓት ነው። ወደ ነቢያት የሚወርደው ተሽሪዒይ በውዴታ ላይ የተመሰረተ መገዛት ነው፦
64፥12 *"አላህንም ተገዙ፤ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትዞሩም መልክተኛውን አትጎዱም፤ በመልክተኛውም ላይ ያለበት ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው"*፡፡ وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ ۚ فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَإِنَّمَا عَلَىٰ رَسُولِنَا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ

“አሥ-ሡጁዱ አት-ተሽሪዒይ” ለሁለት ይከፈላል፥ እርሱም “ሡጁዱል ዒባዳህ” سُّجُود العِبَادَة ማለትም "የአምልኮ ስግደት" እና "ሡጁዱ አ-ተሒያህ" سُّجُود التَحِيَّة ማለትም "የአክብሮት ስግደት" ነው።
“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው። ይህም የአምልኮ ስግደት ለአንዱ አምላክ ለአላህ ብቻ የተገባ ነው፦
41፥37 *"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

"ተሒያህ" تَحِيَّة የሚለው ቃል "ሐያ" حَيَّا ማለትም "አከበረ" "እጅ ነሳ" "ሰላምታ ሰጠ" ለሚለው መስደር ሲሆን "አክብሮት" "እጅ መንሳት" "ሰላምታ" ማለት ነው። ለምሳሌ መላእክት ለአደም፥ የዩሱፍ ቤተሰብ ለዩሱፍ የሰገዱት አክብሮትን የሚገልጽ ብቻ ነው፦
18፥50 *"ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡ ወዲያውም ሰገዱ"*። وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا
12፥4 *ዩሱፍ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም በሕልሜ አየሁ፡፡ :ለእኔ ሰጋጆች ሆነው" አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ إِنِّي رَأَيْتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوْكَبًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ رَأَيْتُهُمْ لِي سَاجِدِينَ
12፥100 *ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው፡፡ "ለእርሱም ሰጋጆች ኾነው" ወረዱለት፡፡ እርሱም፦ «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት» አለ*፡፡ وَرَفَعَ أَبَوَيْهِ عَلَى الْعَرْشِ وَخَرُّوا لَهُ سُجَّدًا ۖ وَقَالَ يَا أَبَتِ هَـٰذَا تَأْوِيلُ رُؤْيَايَ مِن قَبْلُ قَدْ جَعَلَهَا رَبِّي حَقًّا

ይህ የአክብሮት ስግደት ከአምልኮ ስግደት የሚለየው በኒያህ ነው፥ "ኒያህ" نِيَّة የሚለው ቃል "ነዋ" نَوَى ማለትም "ወጠነ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "ውጥን"intention" ማለት ነው። ነገር ግን ይህ የአክብሮት ስግደት አቅጣጫውን ቀይሮ አምልኮ እየሆነ ስላለ፥ በነቢያችን”ﷺ” ጊዜ ተከልክሏል፦
41፥37 *"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون
ሡነን ኢብኑ ማጀህ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 1926:
ዐብደላህ ኢብኑ አቢ ዐውፋ እንደተረከው፦ *"ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ከሻም ምድር በተመለሰ ጊዜ ለነቢዩ”ﷺ” ሰገደ፥ እሳቸውም፦ “ሙዓዝ ሆይ! ምንድነው ይህ?” አሉት፤ እርሱም፦ “ሻም ምድር ሄጄ ነበር፣ ለኤጲስ ቆጶሳቶቻቸው እና ለጳጳሳቶቻቸው ሲሰግዱ ተመለከትኩኝ፥ ይህንን ለእርሶ ልንሰራው ተመኘሁ” አለ። የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ይህንን በፍጹም እንዳትሰሩ!"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي أَوْفَى، قَالَ لَمَّا قَدِمَ مُعَاذٌ مِنَ الشَّامِ سَجَدَ لِلنَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ مَا هَذَا يَا مُعَاذُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَتَيْتُ الشَّامَ فَوَافَقْتُهُمْ يَسْجُدُونَ لأَسَاقِفَتِهِمْ وَبَطَارِقَتِهِمْ فَوَدِدْتُ فِي نَفْسِي أَنْ نَفْعَلَ ذَلِكَ بِكَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ فَلاَ تَفْعَلُوا

ስግደት በኢሥላም በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል። ኢንሻላህ ስግደት በክርስትና ያለውን ምልከታ በክፍል ሁለት ይቀጥላል.......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ስግደት በክርስትና

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 *"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

“ስግደት” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሻኻህ” שָׁחָה ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ፕሩስኩኔኦ” προσκυνέω ይባላል፥ ይህም ስግደት ለተለያየ ምንነት ሆነ ማንነት በውጥን”intention” የሚቀርብ አምልኮን”Adoration” ለማመልከት ወይም አክብሮትን”prostration” ለማመልከት በባይብል ተጠቅሞበታል። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ለተቀረጸ ምስል አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም" ተብሏል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን *”ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ”* ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *የማናቸውንም ምሳሌ፥ "የተቀረጸውንም ምስል" ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም*።
ራዕይ 19፥10 *”ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ”*። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ *”ለእግዚአብሔር ስገድ”*፤ …አለኝ።

ለማንም ለምን “አትስገድ” ከተባለ ለምንድን ነው ሰዎች ለሰዎች የሰገዱት?፦
ዘፍጥረት 23፥7 አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ *”ለኬጢ ልጆች ሰገደ”* ።
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም *”ይስገዱልህ”*፤ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ *”የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ”*፤
ዘፍጥረት 37፥9 ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እንዲህም አለ። እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፤ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ አሥራ አንድ ከዋክብትም *”ሲሰግዱልኝ”* አየሁ።
ዘፍጥረት 42፥6 ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ፥ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ *”በግምባራቸው ሰገዱለት”*።
ዘፍጥረት 43፥26 ዮሴፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእጃቸው ያለውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀረቡለት፥ *”ወደ ምድርም ወድቀው ሰገዱለት”*።
ዘፍጥረት 43፥28 እነርሱም አሉት። ባሪያህ አባታችን ደኅና ነው፤ ገና በሕይወት አለ። *”አጐንብሰውም ሰገዱለት”*።
1ኛ ዜና 29፥20 ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ። አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔር እና *”ለንጉሡ ሰገዱ”*።
ቁርኣን መላእክት ለአደም፥ የዩሱፍ ቤተሰብ ለዩሱፍ መስገዳቸው መግለጹን ስትቃወሙ ባብይል ላይ ቅዱሳን ሰዎች ለሰዎች መስገዳቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ምን ይህ ብቻ ኢየሱስ ሲመጣ ኢአማንያንን መጥተው በአማንያን እግር ፊት ይሰግዱ ዘንድ ማድረጉ ይደንቃል፦
ራእይ 3:9 እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው *”በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ”* προσκυνήσουσιν ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።

ዮሐንስ ሊሰግድለት በእግሩ ፊት ሲደፋ “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ! ባሪያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ” ብሎት እያለ ኢየሱስ ኢአማንያንን መጥተው በአማንያን እግር ፊት ይሰግዱ ዘንድ ማድረጉ አግባብ ነው ወይ? ስንል ፦አይ መልአኩ ለዮሐንስ "አትስገድ" ያለው “የአምልኮት ስግደት” ሲሆን ኢየሱስ "የሚያሰግደው ደግሞ “የአክብሮት ስግደት” ነው። የአምልኮት ስግደት በባሕርይ የአንድ አምላክ ሐቅና ገንዘብ ሲሆን የአክብሮት ስግደት ደግሞ በፀጋ ለቅዱሳን ማክበን ያመለክታል” ይሉናል። እንግዲያውስ የቁርኣኑንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉሃል እንደዚህ ነው፥ በተጨማሪም ፍጥረታት ሁሉ ለአዳም እንደሰገዱ በአሁን ጊዜ ጥንት ከሚባሉት እደ-ክታባት አንዱ በሆነው በአሌክሳድሪየስ ኮዴክስ በሚገኘው በሮሙ ክሌመንት ማለትም በቀለሚንጦስ ተገልጿል፦
ክሌመንት 1፥41 አራዊት፣ እንስሳት ወፎች *እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ ወደ አዳም ተሰበሰቡ ከፊቱ ቁመው ራሳቸውን አዘነበሉ፤ ለአዳምም ሰገዱ"*።

በተጨማሪም በመቃብያን ላይ ዲያቢሎስ የወደቀበት ለአደም አልሰግድ በማለቱ እንደሆነ ተገልጿል፦
3ኛ መቃብያን 1፥6 *የሚጠፉ በኔም የሚስቱ ሰዎች ፈጽመው ይበዙ ዘንድ የአዳምም ልጆች ይጠፉ ዘንድ ይህንን በተናገሩ ጊዜ እኔ ደስ ይለኛል። ለሚዋረድልኝ "ለአዳም አልሰግድም በማለቴ" እግዚአብሔር ስለአባታቸው ስለአዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና*።

የዐበይት ክርስትና ማለትም የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክ እና የአንግሊካን ስግደት ግን ከባይብሉ ይለያል። ሰዎች እና መላእክት በሌሉበት መስገድ ይህ እራሱ የአምልኮ ስግደት ነው፥ ምክንያቱም ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉንም ነገር ማየት፣ መስማት የሚችልና ሁሉንም ነገር ማወቅ የሚችል አንድ አምላክ ብቻ ነው። ሲቀጥል ለተቀረጸ ምስል ለስዕል እና ለመስቀል የጸጋ ስግደት ይሰግዳሉ፦
የዘወትር መቅድም ቁጥር 35-36 ገጽ 7
ግዕዙ፦
*ወቅድመ ስዕላ ስግዱ! ዘኢሰገደ ላቲ ይደምስስ እምቅዋሙ ወኢይትዐወቅ ዝግረ ስሙ። ወይበሉ መላእክተ ሰማይ ኲሎሙ አሜን*።

ትርጉም፦
*በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ። በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ*።

መልክአ ሥዕል ዘበዓለ ሃምሳ አርኬ 20
“ወእሰግድ ካዕበ ለድንግልናኪ ክልኤ፤ *”ወእሰግድ ሠልሰ ለስዕልኪ ቅድመ ጉባዔ፤ ዘኢሰገድ ለስዕልኪ አስሪጾ ምማኤ በሥጋሁ ወበነፍሱ ኢይርከብ ትንሳኤ*”።

ትርጉም፦
:በሁለት በኩል ድንግል ነሽና እሰግድልሻለው፤ *ለስዕልሽም በጉባኤ ፊት ሥስት ጊዜ እሰግዳለሁ፤ ለስዕልሽ ከመስገድ ወደ ኋላ ያለ በነፍሱም በስጋውም ትንሳኤ አያግኝ”*።

የዘወትር ፀሎት ላይ እንዲህ ይነበባል፦
ግዕዙ፦
*“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”*

ትርጉም፦
*“ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው”*

"ለተቀረጸ ምስል አትስገድ" እያለ ለወረቀት ስዕል፣ ለእንጨት መስቀል እና ለድንጋይ ሃውልት ይሰግዳሉ። ይህንን የማይናገርና የማይጋገር፥ የማይሰማና የማይለማ ግዑዝ ነገር ሲሰግዱለት ያሳዝናሉ። ዛሬ ክርስቲያኖች ይህንን መልእክት ከሰሙበት ጀምሮ ውስጣቸውን የሚረብሻቸው እሳቦት ነው፥ ሙሥሊሞች ይህንን እውነታ ለሁሉም አዳርሱ! ምናልባት ለሂዳያህ ሰበብ ይሆናቸዋል። ይህንን መጣጥፍ ለምታነቡ ክርስቲያኖች ጥሪያችን ለፍጡርራን መስገድ ትታችሁ ፍጡራንን የፈጠረውን አላህ በብቸኝነት እያመለካችሁት እንድትሰግዱለት ነው፦
41፥37 *"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተዝኪያህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

91፥9 *"ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ"*፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا

"ነፍሥ" نَفْس ማለት "እራስነት"own self" ማለት ነው፥ የነፍሥ ብዙ ቁጥር "ኑፉሥ" نُفُوس‎ ወይም "አንፉሥ" أَنْفُس‎ ነው። "ነፍሢ" نَفْسِي ስል "እራሴ"my self" ማለቴ ነው፣ "ነፍሢከ" نَفْسِكَ ስል "እራስክ"your self" ማለቴ ነው፣ "ነፍሢሂ" نَفْسِهِ ስል "እራሱ"him self" ማለቴ ነው። ነፍሥ በሰዋስው "ደሚሩ አን-ነፍሢያህ" ضَمِير الْنَفْسِيَّة‎ ማለትም "ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun” ነው። በነፍሥ ውስጥ ያለው ዝንባሌ ደግሞ "ነፍሢያህ" نَفْسِيَّة‎ ይባላል፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

“አህዋእ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” ማለት ነው። ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው "ዝንባሌ" ነው። ዝንባሌ ደግሞ ቦታ ከተሰጠው ሊመለክ የሚችል ክፉ አዛዥ ነው፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ሸይጧን ለአላህ አልታዘዝም ብሎ ያመጸው ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ ስለያዘ ነው፥ የሸይጧንን እርምጃ የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ፦
24፥21 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ وَمَن يَتَّبِعْ خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ

በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት። ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ፥ በኀጢኣት የሸፈናትም በእውነት አፈረ፦
79፥40 *በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ* وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 *ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ
91፥9 *"ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ"*፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا
91፥10 *"በኀጢኣት የሸፈናትም በእውነት አፈረ"*፡፡ وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّىٰهَا

"አፍለሐ" أَفْلَحَ የሚለው አላፊ ግስ ሲሆን "ትድኑ ዘንድ" ለሚለው "ቱፍሊሑነ" تُفْلِحُونَ በሚል መጥቷል፦
24፥31 *”ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ”* وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
5፥35 *”ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ”*። وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

ነፍስን ከዝንባሌዋ ማጥራት "ተዝኪያህ” ይባላል፥ “ተዝኪያህ” تَزكِية የሚለው ቃል “ዘካ” زَكَىٰ ማለትም “ጠራ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መጥራራት" ማለት ነው፦
2፥151 በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን *በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁ እና “የሚያጠራችሁ”፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ*፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ

“የሚያጠራችሁ” ለሚለው ቃል የገባው “ዩዘኪኩም” يُزَكِّيكُمْ መሆኑ ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያረገ ነው። ተዝኪያህ ሦስት ደረጃዎች አሉት፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ተዕሊም” تَعْلِيم‎ ማለትም “ትምህርት”
2ኛ. “ተርቢያህ” تَرْبِيَة ማለትም “እድገት”
3ኛ. “ተዕዲል” تَعْدِيل‎ ማለትም “ግብረገብ” ነው።
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 273
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“እኔ የተላኩትን መልካም ሥነ-ምግባርን ላሟላ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ صَالِحَ الأَخْلاق

ተዝኪያህ ከራሳችን ዝንባሌ ጋር የሚደረግ ጂሃድ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 3
ፈዷላህ ኢብኑ ዑበይድ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"ከራሱ ነፍስ ጋር የታገለ ሙጃሂድ ነው"*። فَضَالَةَ بْنَ عُبَيْدٍ، وَسَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ الْمُجَاهِدُ مَنْ جَاهَدَ نَفْسَهُ

እዚህ ሐዲስ ላይ "የታገለ" ለሚለው የገባው ቃል "ጃሀደ" جَاهَدَ መሆኑን ልብ አድርግ። “ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَاهَدَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ማለት ነው፥ እውነትን ለማንገስ ሐሰትን ለማርከስ፥ ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ በአላህ መንገድ በልቡ፣ በምላሱ እና በእጁ የሚታገል ሙጃሂድ” ْمُجَاهِد ይባላል። ነፍስን ለማጥራት ተዝኪያህ ማድረግም “ጁሁድ” جُهْد ነው፥ ሸይኩል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ ስለ ጂሃዱ አን-ነፍሥ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦
ረውደቱል ሙሒቢን 1/478
*"ከነፍስ እና ከስሜት ጋር የሚደረግ ጂሃድ ከኩፋር እና ከሙናፊቂ ጋር ለሚደረግ ጂሃድ መሠረት ነው። እርሱ(ሙሥሊም) እነርሱን ከመታገሉ በፊት ቅድሚያ ነፍሱና ስሜቱን መታገል ይቀድማልና"*። جِهَادُ النَّفْسِ وَالْهَوَى أَصْلُ جِهَادِ الْكُفَّارِ وَالْمُنَافِقِينَ فَإِنَّهُ لَا يَقْدِرُ عَلَى جِهَادِهِمْ حَتَّى يُجَاهِدَ نَفْسَهُ وَهَوَاهُ أَوَّلًا حَتَّى يَخْرُجَ إلَيْهِمْ

እንግዲህ ከነፍስ ጋር ጂሃድ ማድረግ ውስጣዊ ትግል ሲሆን ከዲኑ ጠላቶች ጋር ጂሃድ ማድረግ ውጫዊ ትግል ነው። አላህ በእርሱ መንገድ ከራሳችን ጋር የምንታገል ሙጃሂድ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሰው ሰይጣን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ

ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የግብር ስም እንጂ የተፀውዖ አሊያም የባሕርይ ስም አይደለም። ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

"የሰው ሰይጣን" አለ ስንል ሚሽነሪዎች ቧልትና ፌዝ ውስጥ መግባታቸው የራሳቸውን መጽሐፍ ጠንቅቀው ካለማወቅ የመጣ ዕውር ድንብር ጸለምተኛ ሙግት ነው። ሰይጣን የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ሳታን" שָּׂטָ֖ן ሲሆን "ጠላት" ማለት ነው፥ ይህ ስም ለሰው ሰይጣን አገልግሎት ላይ ውሏል፦
1ኛ. ነገሥት 11፥14 እግዚአብሔርም ከኤዶምያስ ነገሥታት ዘር የኤዶምያስን ሰው ሃዳድን *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן አድርጎ በሰሎሞን ላይ አስነሣው።
1ኛ. ነገሥት 11፥23 እግዚአብሔርም ደግሞ ከጌታው ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር የኰበለለውን የኤልያዳን ልጅ ሬዞንን *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן አድርጎ አስነሣበት።
1ኛ. ነገሥት 11፥25 ሃዳድም ካደረገው ክፋት ሌላ በሰሎሞን ዘመን ሁሉ የእስራኤል *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן ነበረ።
2ኛ. ሳሙኤል 19፥22 ዳዊትም፦ እናንተ የጽሩያ ልጆች፥ እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ዛሬ ስለ ምን *ሰይጣናት* לְשָׂטָ֑ן ትሆኑብኛላችሁ?
1ኛ. ሳሙኤል 29፥4 የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን ተቆጥተው። ይህ ሰው ባስቀመጥኸው ስፍራ ይቀመጥ ዘንድ ይመለስ በሰልፉ ውስጥ *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቍረጥ አይደለምን?

በዐማርኛችን ላይ "ጠላት" ተብሎ የተቀመጠው የዕብራይስጥ ቃል "ሰይጣን" ነው የሚለው። አንዳንድ ባይብልን አገላብጠው ያላዩ ሚሽነሪዎች፦ "ሰይጣን" በኢ-አመልካች መስተአምር "ሳታን" שָּׂטָ֖ן ሲሆን ለሰው፥ በአመልካች መስተአምር "ሀ-ሳታን" הַשָּׂטָ֖ן ሲሆን ደግሞ "ለዲያብሎስ ነው" ይላሉ። ይህ እሳቤ ስህተት ነው። ምክንያቱም የሰው ሰይጣንን ለማመልከት "ሀ-ሳታን" הַשָּׂטָ֖ן በሚል አመልካች መስተአምር ገብቷል፦
1ኛ. ሳሙኤል 29፥4 የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን ተቆጥተው። ይህ ሰው ባስቀመጥኸው ስፍራ ይቀመጥ ዘንድ ይመለስ በሰልፉ ውስጥ *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቍረጥ አይደለምን?

በኢ-አመልካች መስተአምር "ሳታን" שָּׂטָ֖ן ለዲያብሎስ ጥቅም ላይ ውሏል፦
1 ዜና 21፥1 *ሰይጣንም* שָׂטָ֖ן በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አንቀሳቀሰው።

አመልካች መስተአምር ኖረ አልኖረ አንዳች ለውጥ ከሌለው የሰው ሰይጧን እንዳለ አያችሁልኝን? ምነው ጴጥሮስ ሰይጣን ተብሎ የለምን? አዎ! ተብሏል፦
ማቴዎስ 16፥23 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ *ሰይጣን* የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል፡ አለው።

ስለዚህ ቁርኣን ላይ ሰይጣን የሰውም የጂንም አለ ሲባል እዛ ሰፈር አቧራ አታስነሱ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዋው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ስለ "ዋው" و ተስተምህሮ ለማሳያነት ይህንን አንቀጽ እንመልከት፦
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ ይከፈታሉ*፡፡ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

የጀሃነም ደጆች “ይከፈታሉ” የሚለው ቃል ላይ “ፉቲሐት” فُتِحَتْ ሲሆን መነሻው ላይ “ወ” و የሚል ቃል የለውም፤ ግን የጀነት ደጆች “የተከፈቱ” የሚለው ቃል ግን “ወፉቲሐት” وَفُتِحَتْ ሲሆን “ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ “ወ” የሚል መነሻ ቅጥያ አለ፦
39፥73 እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ “የተከፈቱ”* ሲኾኑ፤ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ رَبَّهُمْ إِلَى ٱلْجَنَّةِ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا وَفُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

እስቲ ይህ “ዋው” و የሚለው ቃል”ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ የሌለበትን ምክንያት እናስተንትን፤ ገሃነም ሰባት ደጆች አሏት፦
15፥43-44 «ገሀነምም ለእርሱና ለተከተሉት ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوْعِدُهُمْ أَجْمَعِينَ «ለእርሷ *ሰባት ደጃፎች* አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡ لَهَا سَبْعَةُ أَبْوَٰبٍۢ لِّكُلِّ بَابٍۢ مِّنْهُمْ جُزْءٌۭ مَّقْسُومٌ
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ* ይከፈታሉ፡፡ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

ቀጥሎ “ዋው” و የሚለው ቃል”ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ ያለበትን ምክንያት እናስተንትን፤ ጀነት ስምንት ደጆች አሏት፦
7፥40 እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ *የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም*፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ *ገነትን አይገቡም*፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسْتَكْبَرُوا۟ عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلْجَمَلُ فِى سَمِّ ٱلْخِيَاطِ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُجْرِمِينَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 67:
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጀነት ስምንት ደጃፎች አሏል*፤ ከእነርሱ አንዷ ስሟ አር-ረይያን ፆመኛ እንጂ ሌላ አይገባባትም። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ فِي الْجَنَّةِ ثَمَانِيَةُ أَبْوَابٍ، فِيهَا باب يُسَمَّى الرَّيَّانَ لاَ يَدْخُلُهُ إِلاَّ الصَّائِمُونَ ‏”‌‏

ነጥቡ ያለው እዚህ ጋር ነው፤ ቁርአን ላይ ሰባት ቁጥር ተነግሮ ስምንት ቁጥር ከመጣ ሰባት ላይ ዋው የለውም ግን ስምንት ላይ ዋው አለ፤ ምሳሌ አንድ፦
18፥22 በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው በጥርጣሬ «ሦስት ናቸው፤ አራተኛቸው ውሻቸው ነው» ይላሉ፡፡ «አምስት ናቸው፤ ስድስተኛቸው ውሻቸው ነውም» ይላሉ፡፡ «ሰባት ናቸው፤ *ስምንተኛቸውም* ውሻቸው ነው» ይላሉም፡፡ سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٌۭ رَّابِعُهُمْ كَلْبُهُمْ وَيَقُولُونَ خَمْسَةٌۭ سَادِسُهُمْ كَلْبُهُمْ رَجْمًۢا بِٱلْغَيْبِ ۖ وَيَقُولُونَ سَبْعَةٌۭ وَثَامِنُهُمْ كَلْبُهُمْ ۚ

“ወ” የሚል ቃል “ሳሚን” ثَامِن ማለትም “ስምንተኛ” በሚል ቃል ላይ መጥቷል፤ “*ወ*ሳሚኑሁም” وَثَامِنُهُمْ ። ነገር ግን “ሠብዐቱን” سَبْعَةٌ ማለትም “ሰባተኛ” በሚለው ቃል ላይ ግን አልመጣም፤ ምሳሌ ሁለት፦
69፥7 ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶች *እና ስምንት* መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ سَخَّرَهَا عَلَيْهِمْ سَبْعَ لَيَالٍۢ وَثَمَٰنِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومًۭا فَتَرَى ٱلْقَوْمَ فِيهَا صَرْعَىٰ كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ خَاوِيَةٍۢ

“ወ” የሚል “ሰማኒን” ثَمَٰنِين ማለትም “ስምንት” በሚል ቃል ላይ መጥቷል፤ “ወሰማኒየታህ” وَثَمَانِيَةَ ። ነገር ግን “ሠብዐ” سَبْعَ ማለትም “ሰባት” በሚለው ቃል ላይ ግን አልመጣም። “ዋው” እዚህ ጋር አርፉል አጥፍ ሳይሆን ዋው ሙተና ነው፤ ዋው ሁልጊዜ መነሻ ቅጥያ ላይ ሆኖ ሲመጣ አያያዥ መስተጻምር ነው ተብሎ አይደመደምም፤ ለምሳሌ “ወላሂ” وَٱللّٰهِ እንላለን፤ እዚህ ጋር “ወ” و የሚለው “ቢ” بِا በሚል ሲመጣ “ቢላህ” بِالله “በአላህ” እንደማለት ነው። አንድ ቃል ሁልጊዜ አንድ ትርጉም ይኖረዋል ማለት አይደለም፤ ለምሳሌ “ለው” َلَوْ ማለት “ቢሆን”if” ሲሆን “ኢን” إِن በሚል ይመጣል። ለናሙና ያክል ሌላ ሰዋስው ከቁርኣን ብንመለከት ለምሳሌ “ላ” َلَا የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም ይኖረዋል፦
1ኛ. “ላ” የሚለው ቃል ለቀድ” َلَقَدْ ማለትም “እርግጥ” የሚል ሆና ትመጣለች፤ ለምሳሌ፦
70፥40 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ فَلَآ أُقْسِمُ بِرَبِّ ٱلْمَشَٰرِقِ وَٱلْمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ

2ኛ. “ላ” የሚለው ቃል “ማ” مَا ማለትም “አፍራሽ ቃል” ሆና ትመጣለች፤ ለምሳሌ፦
4፥71 «ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ

ስለዚህ ዋው መጀመሪያ ስለ ጀሃነም በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ አለመኖሩ እና ሁለተኛው ስለ ጀነት በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ መኖሩ ያለው ጥበብ በአጋጣቢ የሆነ ሳይሆን አላህ የጀሃነም ደጆች ያላቸው ውርደት የሚያመለክ ሲሆን የጀነት ደጆች ደግሞ ያላቸውን ክብር ያሳያል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አላህ ቅርብ ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥186 *"ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ "እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ*"፡፡ ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

"ዱዓእ" دُعَآء ማለት "ደዓ" دَعَا‎ ማለትም "ለመነ" "ተማጸነ" "ጸለየ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልመና" "ተማጽንዖ" "ጸሎት" ማለት ነው። አምላካችን አላህ የሚለምኑትን ልመና ይቀበላል፦
2፥186 *"ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ "እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ*"፡፡ ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

"እኔ" ለሚለው ተውላጠ-ስም የገባው "ኢኒ" إِنِّي ሲሆን ማንነትን ያሳያል፥ ወደ አላህ ዱዓእ ስናደርግ በማንነቱ ለእኛ ቅርብ ነው። ዱዓእን በመስማት ቅርብ ነው፥ ይቅርታ ለጠየቁት ይቅርታ በማድረግ ቅርብ ነው፦
34፥50 «ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው፡፡ ብመራም ጌታዬ ወደ እኔ በሚያወርደው ነው፡፡ *እርሱ ሰሚ፥ ቅርብ ነውና»* በላቸው፡፡ قُلْ إِن ضَلَلْتُ فَإِنَّمَا أَضِلُّ عَلَىٰ نَفْسِي ۖ وَإِنِ اهْتَدَيْتُ فَبِمَا يُوحِي إِلَيَّ رَبِّي ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ قَرِيبٌ
11፥ 61 ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ፡፡ *"ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደ እርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ፥ ለለመነው ተቀባይ ነውና»* አላቸው፡፡ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ

በአንድ ጊዜ የሁሉንም ጸሎት የሚሰማው እርሱ ብቻ ነው። እርሱ በተለይ በሶላቱል ለይል ጊዜ የእኛ ዱዓእ ለመስማት ቅርብ ነው፦
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 210
ዐምር ኢብኑ ዐበሣህ እንደተረከው፦ "አቡ ኡማማህ ሰምቶ ለእኔ እንደነገረኝ ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጌታ ወደ ባሪያው በሌሊቱ መገባደጃ ቀራቢ ነው፥ ስለዚህ በዚያ ሰአት አላህን ከሚዘክሩት ከሆንክ ያኔ ኹን"*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا أُمَامَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ يَقُولُ حَدَّثَنِي عَمْرُو بْنُ عَبَسَةَ، أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ أَقْرَبُ مَا يَكُونُ الرَّبُّ مِنَ الْعَبْدِ فِي جَوْفِ اللَّيْلِ الآخِرِ فَإِنِ اسْتَطَعْتَ أَنْ تَكُونَ مِمَّنْ يَذْكُرُ اللَّهَ فِي تِلْكَ السَّاعَةِ فَكُنْ ‏

"አቅረብ" أَقْرَب ማለትም "ቀራቢ" የሚለው በሌላ ሐዲስ "የንዚሉ" يَنْزِلُ ማለትም "ይወርዳል" በሚል መጥቷል። "ዱንያ" دُّنْيَا ማለት "ቅርብ" ማለት ነው፥ እኛን ወዳቀፈው ሰማይ አምላካችን አላህ ይወርድና፦ "ማነው የሚለምነኝ እኔም የምቀበለው? ማነው የሚጠይቀኝ እኔም የምሰጠው? ማነው ይቅርታ የሚለኝ እኔም ይቅር የምለው? ይላል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6 ሐዲስ 201
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህም መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፡- *"ክብሩ ከፍ ያለውና የላቀው ጌታችን የሌሊቱ መገባደጃ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል፡፡ ከዛም፡- "ማነው የሚለምነኝ፥ እኔም የምቀበለው? ማነው የሚጠይቀኝ፥ እኔም የምሰጠው? ማነው ይቅርታ የሚለኝ፥ እኔም ይቅር የምለው? ይላል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ يَنْزِلُ رَبُّنَا تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا حِينَ يَبْقَى ثُلُثُ اللَّيْلِ الآخِرُ فَيَقُولُ مَنْ يَدْعُونِي فَأَسْتَجِيبَ لَهُ وَمَنْ يَسْأَلُنِي فَأُعْطِيَهُ وَمَنْ يَسْتَغْفِرُنِي فَأَغْفِرَ لَهُ
አላህ በምንነቱ ከዐርሽ በላይ ነው። በማንነቱ ደግሞ ወደ እኛ ይቀርብና ዱዓችንን ይቀበላል። አላህ ሁሉን ማድረግ ይችላል፥ በአንድ ጊዜ የሁሉንም ጸሎት መስማት ይችላል። በቀንና ሌሊት ውስንነት ያለብን እኛ ነን፥ እርሱ እንደ እኛ አይደለም፥ እኛ ከፎቅ ላይ ከወረድን ፎቅ ላይ የለንም። ምንነታችን በጊዜና በቦታ ውስን ስለሆነ። እርሱ ግን ለእልቅናው በሚገባው በማንነቱ ይወርዳል፥ ይቀርባል። የእርሱ አወራረድና አቀራረብ "ከይፊያህ" كَيْفِيَّة ማለትም "እንዴትነት"howness" ዐይታወቅም።
እኛ በዱዓእ ወደ አላህ በስንዝር ብንመጣ እርሱ ወደ እኛ በክንድ ይመጣል፥ እኛ በዱዓእ ወደ እርሱ በክንድ ብንመጣ እርሱ ወደ እኛ በሁለት ክንድ ይመጣል። በእርምጃ ወደ እርሱ ብንመጣ እርሱ በሩጫ ወደ እኛ ይመጣል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 34
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፡- *"የላቀው አላህ እንዲህ አለ፦ "ባሪያዬ ለእርሱ እደማደርግለት እንደሚያስበኝ ነኝ። ቢዘክረኝ እኔ ከእርሱ ጋር ነኝ፥ በራሱ ቢዘክረኝ እኔም እንዲሁ በራሴ እንዘክረዋለው። በብዙኃን ቢዘክረኝ እኔም ከእነርሱ በበለጠ በብዙኃን እንዘክረዋለው። እርሱ ወደ እኔ በስንዝር ቢመጣ እኔ ወደ እርሱ በክንድ እመጣለው፥ እርሱ ወደ እኔ በክንድ ቢመጣ እኔ ወደ እርሱ በሁለት ክንድ እመጣለው። በእርምጃ ወደ እኔ ቢመጣ እኔ በሩጫ ወደ እርሱ እመጣለው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يَقُولُ اللَّهُ تَعَالَى أَنَا عِنْدَ ظَنِّ عَبْدِي بِي، وَأَنَا مَعَهُ إِذَا ذَكَرَنِي، فَإِنْ ذَكَرَنِي فِي نَفْسِهِ ذَكَرْتُهُ فِي نَفْسِي، وَإِنْ ذَكَرَنِي فِي مَلأٍ ذَكَرْتُهُ فِي مَلأٍ خَيْرٍ مِنْهُمْ، وَإِنْ تَقَرَّبَ إِلَىَّ بِشِبْرٍ تَقَرَّبْتُ إِلَيْهِ ذِرَاعًا، وَإِنْ تَقَرَّبَ إِلَىَّ ذِرَاعًا تَقَرَّبْتُ إِلَيْهِ بَاعًا، وَإِنْ أَتَانِي يَمْشِي أَتَيْتُهُ هَرْوَلَةً

መቅረብ፣ መውረድ፣ አብሮ መሆን፣ በእርምጃ መምጣት፣ በሩጫ መምጣት የማንነት ጉዳይ ነው። እኛ ወደ አላህ በስንዝር፣ በክንድ፣ በእርምጃ፣ በሩጫ መቅረባችን ምንነታዊ ሳይሆን ማንነታዊ እውነታ ነው። ይህ ሁሉ ሲገርመን አላህ ከራሳችን ይልቅ ለራሳችን ቅርብ ነው፦
50፥16 ሰውንም ነፍሱ በሐሳቡ የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፥ *እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደ እርሱ ቅርብ ነን*፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ ۖ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ

ይህ የሚያሳየው የአላህ ሁሉቻይነት፣ ሁሉን ሰሚነት፣ ሁሉን ተመልካችነት፣ ሁሉን ዐዋቂነት ነው። እኛ ወደ እርሱ በዱዓእ፣ በዚክር፣ በሶላት ስንቀርብ ሙቀረብ" مُقَرَّب ማለትም "ባለሟል" ወይም በብዜት "ሙቀረቡን" مُقَرَّبُون ይባላል፦
56፥11 *እነዚያ "ባለሟሎቹ" ናቸው*፡፡ أُولَـٰئِكَ الْمُقَرَّبُونَ
83፥21 *"ባለሟልዎቹ ይጣዱታል"*፡፡ يَشْهَدُهُ الْمُقَرَّبُونَ

ወደ እርሱ መቃረቢያ የምናደርገው አምልኮ "ቁርባን" قُرْبَان ይባላል፦
5፥35 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ *"ወደ እርሱም መቃረቢያን ፈልጉ*፡፡ ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መቃረቢያ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ወሢላህ" وَسِيلَة ሲሆን መልካም ሥራ ሁሉ "ተወሡል" تَوَسُّل ነው። አምላካችን አላህ ሙቀረቡን ከሚላቸው ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጣዖት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥36 *በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ

"ጧጉት" طَّٰغُوت የሚለው ቃል "ጠጋ" طَغَىٰ ማለትም "ወሰን አለፈ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "በአላህ ሐቅ ላይ ወሰን ማለፍ" ማለት ነው፦
79፥17 ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡ اذْهَبْ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُ طَغَىٰ
79፥24 አለም፡- *«እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡»* فَقَالَ أَنَا رَبُّكُمُ الْأَعْلَىٰ

"ወሰን አልፏል" ለሚለው አላፊ ግስ የገባው ቃል "ጠጋ" طَغَىٰ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ፊርዐውን በአላህ ሐቅ ላይ ወሰን ያለፈው፦ "እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ" በማለት ነው። ስለዚህ በአላህ ሐቅ ላይ ያለፈ ማንነት ሆነ ምንነት "ጣዖት" ይባላል።
ሌላው የጣዖት አይነት አውሳን እና አስናም ናቸው፥ “አውሳን” أَوْثَٰن ማለት ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ የሚቀርብላቸው ምንነት ናቸው፦
29፥25 ኢብራሂም አለም፦ *ከአላህ ሌላ ጣዖታትን አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው*። وَقَالَ إِنَّمَا ٱتَّخَذْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ أَوْثَٰنًۭا مَّوَدَّةَ بَيْنِكُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا

“አስናም” أَصْنَام ማለት ደግሞ ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሰርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ምንነት ናቸው፦
26፥70 *ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ታመልካላችሁ?*» ባለ ጊዜ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ
26፥71 *ጣዖታትን እናመልካለን፤ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًۭا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ

ሌላው ጣዖት ሊሆን የሚችለው በራሳችን ውስጥ ያለችው "ነፍሢያህ" نَفْسِيَّة‎ ናት፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

“አህዋእ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” ማለት ነው፥ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው "ዝንባሌ" ነው። ታዲያ ስንጋደል በምን መንገድ ይሆን? አላህን ብቻ አምላክ አርገን ይዘን የእርሱን ውዴታ ለመፈለግ ወይስ ዝንባሌ አምላክ አርገን ይዘን ለዘረኝነት፣ ለጎጠኝነት፣ ለጠርዘኝነት፣ ለቡድንተኝነት? ልቡንም አላህ ከማስታወስ የዘነጋውን፣ ፍላጎቱንም የተከተለውን፣ ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው መታዘዝ የለብንም፦
18፥28 *"ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውን፣ ፍላጎቱንም የተከተለውን፣ ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ"*፡፡ وَلَا تُطِعْ مَنْ أَغْفَلْنَا قَلْبَهُ عَن ذِكْرِنَا وَاتَّبَعَ هَوَاهُ وَكَانَ أَمْرُهُ فُرُطًا

እንደዚህ አይነት ሰው የሚጋደለው በልቡ ላለው ጣዖት ለዝንባሌው ነው። እነዚያ ያመኑት ሰዎች በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፥ እነዚያ የካዱትም በጣዖት መንገድ ይጋደላሉ፦
4፥76 *"እነዚያ ያመኑት ሰዎች በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፡፡ እነዚያ የካዱትም በጣዖት መንገድ ይጋደላሉ፡፡ የሰይጣንንም ጭፍሮች ተጋደሉ፡፡ የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና"*፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ الطَّاغُوتِ فَقَاتِلُوا أَوْلِيَاءَ الشَّيْطَانِ ۖ إِنَّ كَيْدَ الشَّيْطَانِ كَانَ ضَعِيفًا
“ላ ኢላሀ ኢልለሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ስልን “አምላክ የለም፥ ከአሏህ በስተቀር” እያልን በጣዖት ከንቱነት እየካድን በአላህ አምላክነት እያመንን ነው፦
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ *በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

በጣዖት ስንክድ፥ ጣዖትን አምላክ የለምን ስንል ዝንባሌን አምላክ አርገን ለዘረኝነት፣ ለጎጠኝነት፣ ለጠርዘኝነት፣ ለቡድንተኝነት መጋደል ትተን ይሆን? ወይስ ምላስ ላይ ብቻ ነው? አዎ እነዚያ የካዱትም በጣዖት መንገድ ይጋደላሉ። እነዚያ ያመኑት ሰዎች በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፥ ነቢያት በአላህ መንገድ የሚጋደሉ ነበሩ። የመልእክታቸው ጭብጥ፦ "አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ" የሚል ነው፦
16፥36 *በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ

ከነቢያት አንዱ እና አውራ ኢብራሂም ወደ ጌታውን የመጣው ልቡን ለጌታው ታዛዥ አርጎ ነው፥ የትንሳኤ ቀን እፍረት የሌለው ልቡን ለጌታው ታዛዥ ያደረገው እንደሆነ ተናግሯል፦
37፥84 *ወደ ጌታው "በቅን ልብ" በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ*፡፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
26፥89 *ወደ አላህ "በንጹህ ልብ" የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ*፡፡» إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيم

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ቅን" ወይም "ንጹህ" ለሚለው ቃል የገባው "ሠሊም" سَلِيم ሲሆን ይህም ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተገዢ" "ታዛዥ" የሚለውንም ያስይዛል።
“ኢኽላስ” إِخْلَاص የሚለው ቃል "ኸለሰ" خَلَصَ‎ ማለትም "ጠራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ "ማጥራት" ማለት ነው። የአላህን ውዴታ ለመፈለግ፥ እውነትን ለማንገሥና ሐሰትን ለማርከስ ሲል በኢኽላስ የሚታገል “ሙኽሊስ” مُخْلِص ይባላል፦
40፥14 *አላህንም ከሓዲዎች ቢጠሉም ሃይማኖትን ለእርሱ “አጥሪዎች” ኾናችሁ ተገዙት*፡፡ فَادْعُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُون

አምላካችን አላህ ዝንባሌአችንን አምላክ አድገን ከመያዝ ይጠብቀን፥ ሙኽሊሲን ከሚላቸው ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በደል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥82 *እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው*፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው። ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ

"ዙልም" ظُلْم የሚለው ቃል "ዞለመ" ظَلَمَ ማለትም "በደለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "በደል" ማለት ነው። "ዟሊም" ﻇَﺎﻟِﻢ ማለት ደግሞ "በዳይ" ማለት ነው። የበደል ተቃራኒ “ዐድል” عَدْل ማለትም "ፍትሕ" ነው፦
5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

“ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا ተብሎ የተቀመጠው የግስ መደብ ሲሆን የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ነው፦
16፥90 *አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ማስተካከል” ለሚለው ቃል የገባው “ዐድል” عَدْل መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ የፍትሕ ተቃራኒ "በደል" ሦስት አይነት ነው፥ እርሱም፦
1ኛ. አላህን መበደል
2ኛ. ሰውን መበደል
3ኛ. እራስን መበደል

ነጥብ አንድ
"አላህን መበደል"
አላህን መበደል በእርሱ ሐቅ ላይ ሌላ ማንነትንና ምንነትን ማጋራት ነው። አላህ በደለኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በእሳት ውስጥ ይተዋቸዋል፦
19፥72 ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን*፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا
31፥13 ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! *በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና* ያለውን አስታውስ። وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ

ሺርክ በአላህ ላይ የሚደረግ ትልቅ በደል ነው። “አምን” أَمْن ማለት “ጸጥታ” ማለት ሲሆን አላህን በማንነት ሆነ በምንነት "አንድ ነው" ብሎ በማመንና በብቸኝነት በማምለክ በቀልብ ላይ የሚመጣ “ጸጥታ” “መረጋጋት” እና “ሰላም” ነው፦
6፥82 *እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው*፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው። ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ዙልም” ظُلْم ማለት “በደል” ማለት ሲሆን በአላህ ላይ ማጋራት ለማመልከት የገባ ነው። ሱረቱል አንዓም 6፥82 አንቀጽ በወረደ እና በተነበበ ጊዜ “ዙልም” የተባለው ሺርክን መሆኑን በዚህ ሐዲስ ላይ ተገልጿል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65 , ሐዲስ 4776:
“እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው” የሚለው አንቀፅ በወረደ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ባልደረቦች የሆኑት ቃሉ ከባድ ስለነበር እነርሱም፦ *“ከእኛ ውስጥ በደለኛ ያልሆነ ማን አለ?” ብለው ሲጠይቁ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሉቅማን ለልጁ፡- በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት “ታላቅ በደል” ያለውን አልሰማችሁምን? ብለው ተናገሩ*። حَدَّثَنَا قُتَيْبَةُ بْنُ سَعِيدٍ، حَدَّثَنَا جَرِيرٌ، عَنِ الأَعْمَشِ، عَنْ إِبْرَاهِيمَ، عَنْ عَلْقَمَةَ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ‏}‏ شَقَّ ذَلِكَ عَلَى أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَقَالُوا أَيُّنَا لَمْ يَلْبِسْ إِيمَانَهُ بِظُلْمٍ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّهُ لَيْسَ بِذَاكَ، أَلاَ تَسْمَعُ إِلَى قَوْلِ لُقْمَانَ لاِبْنِهِ ‏{‏إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ‏}‌‏”‏
ነጥብ ሁለት
"ሰውን መበደል"
የሰው ሐቅን መንካት እራሱ በደል ነው። ሰውን መዝረፍ፣ ማማት፣ መስደብ፣ መማታት፣ መግደል "ሰውን መበደል" ነው። ይህ በደል ማንኛውም ሰው ሌላው ላይ የሚያደርሰው በደል ነው፦
14፥42 *አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው*፡፡ وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَار

የሰው ሐቅ የሚመለሰው በካሳ ወይም በይቅርታ ብቻ ነው። "ከፋራህ" كَفّارَة ማለትም "ካሳ" መክፈል ወይም "ዐፉው" عَفُوّ ማለትም "ይቅርታ" ካልተባለ የትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ ያስጠይቀናል።

ነጥብ ሦስት
"እራስን መበደል"
ኸምር መጠጣት፣ የእርያ ስጋ መብላት፣ ዚና ውስጥ መግባት ሌላው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ቢኖረውም እራስን የሚጎዳ ነው። የእራሳችን ሐቅ ስንነካ እራሳችንን እንበድላለን፦
10፥44 *"አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች እራሳቸውን ይበድላሉ"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَظْلِمُ النَّاسَ شَيْئًا وَلَـٰكِنَّ النَّاسَ أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

እንግዲህ በደል ይህ ያህል ከባድ ወንጀል ነው። ፍትሕ ግን ከራስ፣ ከወላጅ እና ከቅርብ ዘመድ በላይ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ፣ ከዝንባሌ የጸዳ፣ ሀብታም ወይም ድኻ ሳይባል፣ አላህ ውስጠ ዐዋቂ ነው ብሎ በትክክል መቆም ነው፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

አምላካችን አላህ ከማንኛውም ዙልም ይጠብቀን፥ የማንንም ሐቅ የምንወጣ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሒሣሢይ እና መዕነዊይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥50 *«ዕውር እና ዓይናማ ይስተካከላሉን? አታስተነትኑምን?»* በላቸው፡፡ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ

የውጪ ዓይናችን ከፍጥረታዊ ብርሃን ጋር ግንኙነት ያረግና ያያል፥ ይህ ውጪአዊ ዓይን እና ፍጥረታዊ ብርሃን "ሒሣሢይ" حَسَّاسِيّ ማለት "እማሬአዊ"literal" ይባላል። የውስጥ ዓይን ከመለኮታዊ ብርሃን ጋር ግንኙነት ያደርግና ያያል፥ ይህ ውስጣዊ ዓይን እና መለኮታዊ ብርሃን "መዕነዊይ" مَعْنَوِيّ ማለት "ፍካሬአዊ"allegorical" ይባላል። ሒሣሢይ በሌላ አቀማመጥ "ኻሪጂይ" خَارِجِيّ ማለትም "ውጫዊ" ነው። መዕነዊይ ደግሞ "ዳኺሊይ" دَاخِلِيّ ማለትም "ውስጣዊ" ነው። የውስጥ ዓይን ልብ ነው፥ ይህ ልብ ዕውቀት ካላገኘ በመሃይምነት ይታወራል፦
22፥46 *"ለእነርሱም በእነርሱ "የሚያውቁባቸው ልቦች" ወይም በእነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮች ይኖሯቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? እነሆ ዓይኖች አይታወሩም ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ*፡፡ أَفَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَتَكُونَ لَهُمْ قُلُوبٌۭ يَعْقِلُونَ بِهَآ أَوْ ءَاذَانٌۭ يَسْمَعُونَ بِهَا ۖ فَإِنَّهَا لَا تَعْمَى ٱلْأَبْصَٰرُ وَلَٰكِن تَعْمَى ٱلْقُلُوبُ ٱلَّتِى فِى ٱلصُّدُورِ

የውጪ ዓይኖች በመሃይምነት አይታወሩም፥ ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ባለማወቅ ይታወራሉ። ማናቸውም የሚያውቁባቸው ልቦች አሏቸው። ማወቅ ማየት ነው፥ አለማወቅ አለማየት ነው፦
6፥50 *«ዕውር እና ዓይናማ ይስተካከላሉን? አታስተነትኑምን?»* በላቸው፡፡ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
39፥9 *«እነዚያ የሚያውቁ እና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?»* በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ

እነዚህ አናቅጽ ላይ ዕውር አለማወቅን ዓይናማ ማወቅን ለማመልከት ተለዋዋጭ ሆኖ መጥቷል። "ዐሊም" عَالِم‎ ማለት "ዐዋቂ" ማለት ሲሆን "ጃሂል" جَاهِل‎ ማለት ደግሞ "መሃይም" ማለት ነው። ቁርኣን ለልብ ዓይን ብርሃን ሆኖ ከአላህ ዘንድ ወደ ሰዎች ወርዷል፦
4፥174 እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥ አስረጅ መጣላችሁ፤ *ወደ እናንተም ገላጭ የኾነን ብርሃን አወረድን*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَكُم بُرْهَٰنٌۭ مِّن رَّبِّكُمْ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ نُورًۭا مُّبِينًۭا
45፥20 ይህ ቁርኣን *ለሰዎች ብርሃን ነው*፡፡ ለሚያረጋግጡም ሕዝቦች መሪና እዝነት ነው፡፡ هَٰذَا بَصَٰٓئِرُ لِلنَّاسِ وَهُدًۭى وَرَحْمَةٌۭ لِّقَوْمٍۢ يُوقِنُونَ
6፥104 *«ከጌታችሁ ዘንድ ብርሃን በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ "የተመለከተም ሰው" ጥቅሙ ለራሱ ብቻ ነው፡፡ "የታወረም ሰው" ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው፥ እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም» በላቸው*፡፡ قَدْ جَآءَكُم بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَنْ أَبْصَرَ فَلِنَفْسِهِۦ ۖ وَمَنْ عَمِىَ فَعَلَيْهَا ۚ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيْكُم بِحَفِيظٍۢ

"ጃአ" جَآءَ ማለት በነጠላ "መጣ" ማለት ነው፥ ይህንን ቁርኣን የተመለከተም ሰው ጥቅሙ ለራሱ ብቻ ነው፥ የታወረም ሰው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው። ልብ አድርግ መመልከት እና መታወር ውሳጣዊ እንጂ ውጫዊ አይደለም። ነቢያችን”ﷺ” ከአላህ የተላኩት ሰዎችን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጡ ዘንድ ወደ እርሳቸው ቁርኣን ብርሃን ሆኖ ወርዷል፦
14፥1 አሊፍ ላም ራ፥ *ይህ ቁርአን ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወደ አንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው*፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ لِتُخْرِجَ النَّاسَ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ بِإِذْنِ رَبِّهِمْ إِلَىٰ صِرَاطِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ
እዚህ አንቀጽ ላይ የተጠቀሱት ብርሃን እና ጨለማ ሒሣሢይ ሳይሆን መዕነዊይ መሆናቸው አንባቢ ልብ ይለዋል። "ዒልም" عِلْم‎ ማለትም "ዕውቀት" ሲሆን "ጀህል" جَهْل ማለት ደግሞ "መሃይምነት" ማለት ነው። ዕውቀት ብርሃን ነው፥ መሃይምነት ጨለማ ነው። ልብ የቁርኣን ዚክር ካገኘ ሕያው ይሆናል፥ በተቃራኒው ከቁርኣን ከራቀ ይሞታል፦
30:52 አንተም *”ሙታንን” አታሰማም፤ ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ" ጥሪን አታሰማም*። فَإِنَّكَ لَا تُسْمِعُ ٱلْمَوْتَىٰ وَلَا تُسْمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوْا۟ مُدْبِرِينَ
27:80 አንተ *”ሙታንን”* አታሰማም፤ *ደንቆሮችንም* የሚተው ሆነው *በዞሩ ጊዜ* ጥሪን አታሰማም። إِنَّكَ لَا تُسْمِعُ ٱلْمَوْتَىٰ وَلَا تُسْمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوْا۟ مُدْبِرِينَ
35፥22 *ሕያዋን እና ሙታንም አይስተካከሉም*፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ያሰማል፡፡ *አንተም በመቃብር ውስጥ ያሉትን አሰሚ አይደለህም*፡፡ وَمَا يَسْتَوِى ٱلْأَحْيَآءُ وَلَا ٱلْأَمْوَٰتُ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُسْمِعُ مَن يَشَآءُ ۖ وَمَآ أَنتَ بِمُسْمِعٍۢ مَّن فِى ٱلْقُبُورِ

"ቀብር" قَبْر የሚለው ቃል "ቀበረ" قَبَرَ ማለትም "ቀበረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መቃብር" ማለት ነው፥ የቀብር ብዙ ቁጥር "ቁቡር" قُبُور ወይም "መቃቢር" مَقَابِر ነው። እነዚ አናቀጽ ላይ መቃብር የተባለው ቀልባቸው የሞተ በጨለማ ውስጥ የሚኖሩ የኢ-አማንያን ሁኔታና ኩነት ነው፦
6፥122 *ሙት የነበረና ሕያው ያደረግነው ለእርሱም በሰዎች መካከል በእርሱ የሚኼድበትን ብርሃን ያደረግንለት ሰው በጨለማዎች ውስጥ ከእርሷ የማይወጣ ኾኖ እንዳለ ሰው ብጤ ነውን?* እንደዚሁ ለከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩት ነገር ተጌጠላቸው፡፡ أَوَمَن كَانَ مَيْتًۭا فَأَحْيَيْنَٰهُ وَجَعَلْنَا لَهُۥ نُورًۭا يَمْشِى بِهِۦ فِى ٱلنَّاسِ كَمَن مَّثَلُهُۥ فِى ٱلظُّلُمَٰتِ لَيْسَ بِخَارِجٍۢ مِّنْهَا ۚ كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلْكَٰفِرِينَ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

ልብ አድርግ የዚህ አንቀጽ ሰበቡ አን-ኑዙል ዐማር ኢብኑ ያሢር ነው፥ እርሱ በኩፍር ሕይወቱ ሙታን እና በጨለማ ውስጥ የሚኖር ሲሆን ብርሃን ሲያገኝ ግን ሕያው ሆነ። "ሙታን" እና "ሕያዋን" እማሬአዊ ሳይሆን ፍካሬአዊ ነው። አካል በምግብ ከውጪው ነገር ጋር ግንኙነት ሲኖረው ሕያው እንደሆነ፥ በተቃራኒው ምግብ ካጣ ከውጪው ነገር ጋር ተለያይቶ ሙት እንደሚሆን ሁሉ ልብም በዚክር ከአላህ ጋር ግኑኝነት ሲኖረው ሕያው ነው፥ በተቃራኒው ዚክር ካላረገ ከአላህ ተለያይቶ ሙት ይሆናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 80, ሐዲስ 102
አቢ ሙሣ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ጌታውን የሚዘክር እና የማይዘክር ምሳሌ፥ ልክ እንደ ሕያው እና እንደ ሙታን ነው”*። عَنْ أَبِي مُوسَى ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَثَلُ الَّذِي يَذْكُرُ رَبَّهُ وَالَّذِي لاَ يَذْكُرُ مَثَلُ الْحَىِّ وَالْمَيِّتِ

አላህ ከጨለማ፣ ከዕውርነት፣ ከሙታንነት ይጠብቀን፥ በብርሃኑ ልባችንን አብርቶ ሕያው ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሂጅራህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥100 *በአላህም መንገድ የሚሰደድ ሰው በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል፡፡ ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም ስደተኛ ኾኖ ከቤቱ የሚወጣ ከዚያም በመንገድ ሞት የሚያገኘው ሰው ምንዳው በእርግጥ አላህ ዘንድ ተረጋገጠ*፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ وَمَن يُهَاجِرْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يَجِدْ فِي الْأَرْضِ مُرَاغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً ۚ وَمَن يَخْرُجْ مِن بَيْتِهِ مُهَاجِرًا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ يُدْرِكْهُ الْمَوْتُ فَقَدْ وَقَعَ أَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

ነቢያችን"ﷺ" ለመጀመሪያ ጊዜ ወሕይ ማለትም "ግልጠተ-መለኮት" የመጣላቸው በ 610 ድህረ-ልደት"AD" ነው፤ ከዚያም በ 613 ድህረ-ልደት የወሕይ ጭብጥ የሆነው ተህሊል ለመካ ሰዎች አወጁ፤ ይህንን አዋጅ ያልተቀበሉት መካውያን የነቢያችንን"ﷺ" ባልደረቦች በማሳደዳቸው የመጀመሪያው ስደት በ 615 ድህረ-ልደት ወደ ሃበሻ ምድር ወደ ኢትዮጵያ ሆኗል። አምላካችን አላህ በእርሱ መንገድ ስለሚሰደዱት ስደተኞች እንዲህ ይለናል፦
4፥100 *በአላህም መንገድ የሚሰደድ ሰው በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል፡፡ ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም ስደተኛ ኾኖ ከቤቱ የሚወጣ ከዚያም በመንገድ ሞት የሚያገኘው ሰው ምንዳው በእርግጥ አላህ ዘንድ ተረጋገጠ*፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ وَمَن يُهَاجِرْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يَجِدْ فِي الْأَرْضِ مُرَاغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً ۚ وَمَن يَخْرُجْ مِن بَيْتِهِ مُهَاجِرًا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ يُدْرِكْهُ الْمَوْتُ فَقَدْ وَقَعَ أَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
2፥218 *እነዚያ ያመኑትና እነዚያም ከአገራቸው የተሰደዱት በአላህም መንገድ ላይ የተጋደሉት እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ*፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أُولَـٰئِكَ يَرْجُونَ رَحْمَتَ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

"ሂጅራህ" هِجْرَة የሚለው ቃል "ሃጀረ" هَاجَرَ ማለትም "ተሰደደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስደት" ማለት ነው። ነቢያችን"ﷺ" እና ባልደረቦቻቸው ከሚኖሩበት ቀዬ ከመካ ወደ መዲና በ 622 ድህረ-ልደት ተሰደዋል፦
16፥41 *እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ መንገድ ላይ የተሰደዱት በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው*፡፡ ከሓዲዎች ቢያውቁ ኖሮ በተከተሏቸው ነበር፡፡ وَالَّذِينَ هَاجَرُوا فِي اللَّهِ مِن بَعْدِ مَا ظُلِمُوا لَنُبَوِّئَنَّهُمْ فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً ۖ وَلَأَجْرُ الْآخِرَةِ أَكْبَرُ ۚ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ
9፥20 *እነዚያ ያመኑት፣ ከአገራቸውም የተሰደዱት፣ በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው*፡፡ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ أَعْظَمُ دَرَجَةً عِندَ اللَّهِ ۚ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْفَائِزُونَ

"የተሰደዱ" ለሚለው ቃል የገባው "ሃጀሩ" هَاجَرُوا ሲሆን "ሃጀረ" هَاجَرَ ከሚለው ሥርወ-ቃል መምጣቱ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ "ሙሃጂር" مُهَاجِر ማለት ደግሞ "ስደተኛ" ማለት ሲሆን ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱትን መካውያን ሰሃባዎችን ያመለክታል፤ መዲና ላይ ከመካ የተሰደዱትን እረድተው የተቀበሉ "ነሲር" نَصِير ማለትም "ረዳት" ይባላሉ፦
8፥74 *እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉ እና የረዱ እነዚያ እነርሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ
9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

"ረዳቶች" ለሚለው ቃል የገባው "አንሷር" أَنْصَار ሲሆን "ነሲር" نَصِير ለሚለው ቃል ብዜት ነው፤ ይህም ስም መዲናውያን ሰሃባዎችን ያመልክታል፦
8፥72 *እነዚያ ያመኑና የተሰደዱ፡፡ በአላህም መንገድ ላይ በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸው የታገሉ፡፡ እነዚያም ስደተኞቹን ያስጠጉና የረዱ፡፡ እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ
622 ድህረ-ልደት በነቢያችን"ﷺ" ላይ የወረደው ወሕይ በነጻነት የተላለፈበት እና የአምልኮ ነጻነት የሆነበት ቀን ነው፤ በዚህ ዓመት በመዲና ውስጥ የቁባ መስጊድ የተገነባበት ነው፦
9፥108 በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ፡፡ *ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው የቁባ መስጊድ በውስጡ ልትሰግድበት ይልቅ የተገባው ነው*፡፡ በእሱ ውስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አሉ፡፡ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል፡፡ لَا تَقُمْ فِيهِ أَبَدًا ۚ لَّمَسْجِدٌ أُسِّسَ عَلَى التَّقْوَىٰ مِنْ أَوَّلِ يَوْمٍ أَحَقُّ أَن تَقُومَ فِيهِ ۚ فِيهِ رِجَالٌ يُحِبُّونَ أَن يَتَطَهَّرُوا ۚ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُطَّهِّرِينَ

በዚህ አንቀጽ ላይ "ከመጀመሪያ ቀን" የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ይህ ቀን መጀመሪያነቱ በአንጻዊ ደረጃ ሂጅራህን ያመለክታል። በዚህ ቀን የቁባ መስጊድ የተገነባበት ነው፤ በነቢያችን"ﷺ" በኩል የመጣው ግህደተ-መለኮት የቀን አቆጣጠሩም የሚጀምረው ከዚህ ቀን ጀምሮ ነው፤ ይህም የዘመን ቀመር"calendar" በኢስላም "አት-ተቅዊሙል ሂጅሪይ" التقويم الهجري ይባላል።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሁለት ዒዶችን በዓመት በዓመት እናከብራለን፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *“አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን”* አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፦ *የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

እነዚህን በዓላት ከሂጅራ ጀምሮ እስከ አሁን ስናከብር ለ 1440 ጊዜ ነው። ኢሥላም ዐቂደቱል ረባኒያ እንጂ ሰው ሰራሽ ሕግና ሥርዓት የለውም። ሱመ አል-ሐምዱ ሊሏህ!

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም