ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
እንኩዋን ለታላላቁ ቅዱሳን #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት:
#ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ እና #ቅዱስ_ቶማስ_ዘመርዓስ
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ቅዱስ #ተክለ_ሃይማኖት ሐዋርያዊ "*+ #ልደት
መልካም ዛፍ
መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: #
ጸጋ_ዘአብ ካህኑና #እግዚእ_ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ:
እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ
ፍሬን ሰጥቷቸዋል:: +በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ
ቢደርስባቸው #ቅዱስ_ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ
ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል::
በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል:: +አቡነ ተክለ
ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24, በ1206 (1196) ሲሆን
የተወለዱት ታሕሳስ 24, በ1207 (1197) ዓ/ም ነው::
በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም
በበረከት ሞልቷል:: #ዕድገት =>የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው
"#ፍሥሃ_ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ
ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን
(ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ
አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ #አባ_
ጌርሎስ ተቀብለዋል:: #መጠራት =>አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን
ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ
ተሰማ:: የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አእላፍ
መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::
+የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ: "ከዛሬ ጀምሮ
ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: አራዊትን
ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ
በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ
ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ
ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ:: #አገልግሎት
=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል
አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (#
ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው
አጠመቁ:: ያንጊዜ #ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት:: 1.ዮዲት
(ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ
አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ
አምልኮ ተጠምዷል:: 2.ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት
ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር:: +ግማሹ ሃገር በጨለመበት
ወቅት የደረሱት #ሐዲስ_ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት
ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ::
ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን
(ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል:: #ገዳማዊ ሕይወት =>ቅዱስ
ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው
ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ
የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::
+እነዚህም በአቡነ #በጸሎተ_ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት:
በአቡነ #ኢየሱስ_ሞዐ_ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ
ዳሞ ከአቡነ #ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26
ዓመታት አገልግለዋል:: +በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ
በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ #ዞረሬ ተመልሰው በአንዲት በዓት
ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም
6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል:: #
ስድስት ክንፍ =>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ
ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት
መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ #እሥራኤል የገቡት
በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ
ነበር:: +የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት #አባ_ሚካኤል ጋርም
ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ
በሁዋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ
ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ
እንባቸው ይፈስ ነበር:: +ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው
ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
¤በቤተ መቅደስ ብስራቱን ¤በቤተ ልሔም ልደቱን ¤በቤተ ዮሴፍ
ግዝረቱን ¤በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን ¤በቤተ አልዓዛር
ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር:: +የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል
ወደሆነው #ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ
ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን
ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ:: በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ
#እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን
ወደሰማይ አሳረገቻቸው:: +በዚያም:- ¤የብርሃን ዐይን
ተቀብለው ¤6 ክንፍ አብቅለው ¤የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
¤ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው ¤ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም
ተደምረው ¤ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
¤"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ
ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል:: #ተአምራት
=>የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል *ድውያንን ፈውሰዋል *አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል *በክንፍ በረዋል *ደመናን ዙፋን
አድርገዋል:: +ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን
መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት
አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና:: #ዕረፍት
=>ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን
ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: አእላፍ ፍሬን አፍርተው:
በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24,
በ1306 (1296) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና
ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ
የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::
#ቅዱስ_ቂርቆስ_ገዳማዊ
ቅዱሱ የ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቅ ሲሆን በዓለም ከመናፍቃን: በገዳም ደግሞ ከአጋንንት ብዙ መከራን ተቀብሏል:: በወቅቱ መለካውያን (የአሁኖቹ ካቶሊኮችና ምስራቅ ኦርቶዶክሶች) የተዋሕዶ አባቶችን ያሳድዱ ነበር:: ልክ #9ኙ_ቅዱሳን በዚህ ምክንያት ወደ #ኢትዮዽያ እንደመጡት ቅዱስ ቂርቆስም ወደ ግብጽ በርሃ ተሰደደ::
በበርሃው ውሃም ሆነ ዛፍ ባለመኖሩ በረሃብና በጥም በመሰቃየቱ ወደ ፈጣሪ ለመነ:: ጌታም አንዲት አጋዘን ልኮለት ከእርሷ ወተትን አልቦ ጠጣ:: እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም ምግቡ ይሔው የአጋዘን ወተት ነበር:: በዚህ ምክንያት ይሔው ዛሬም ድረስ "ቅዱስ ቂርቆስ ገዳማዊ ዘሲሳዩ ሐሊበ ቶራ" እየተባለ ይጠራል::
በበርሃው ውስጥ በኖረባቸው ዘመናትም አንድም ሰው አይቶ ካለማወቁ ባለፈ አጋንንት በገሃድ እየመጡ ያሰቃዩት ነበር:: ቅዱሱ ግን በትእግስት ኑሮ በዚህች ቀን ሲያርፍ ብዙ ተአምራት በበዓቱ ውስጥ ተገልጠዋል:: ይህንን ያዩት ደግሞ ከዻዻሱ ዘንድ ተልከው የቀበሩት አበው ናቸው::