ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ቅዱስ_ቂርቆስ_ገዳማዊ
ቅዱሱ የ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቅ ሲሆን በዓለም ከመናፍቃን: በገዳም ደግሞ ከአጋንንት ብዙ መከራን ተቀብሏል:: በወቅቱ መለካውያን (የአሁኖቹ ካቶሊኮችና ምስራቅ ኦርቶዶክሶች) የተዋሕዶ አባቶችን ያሳድዱ ነበር:: ልክ #9ኙ_ቅዱሳን በዚህ ምክንያት ወደ #ኢትዮዽያ እንደመጡት ቅዱስ ቂርቆስም ወደ ግብጽ በርሃ ተሰደደ::
በበርሃው ውሃም ሆነ ዛፍ ባለመኖሩ በረሃብና በጥም በመሰቃየቱ ወደ ፈጣሪ ለመነ:: ጌታም አንዲት አጋዘን ልኮለት ከእርሷ ወተትን አልቦ ጠጣ:: እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም ምግቡ ይሔው የአጋዘን ወተት ነበር:: በዚህ ምክንያት ይሔው ዛሬም ድረስ "ቅዱስ ቂርቆስ ገዳማዊ ዘሲሳዩ ሐሊበ ቶራ" እየተባለ ይጠራል::
በበርሃው ውስጥ በኖረባቸው ዘመናትም አንድም ሰው አይቶ ካለማወቁ ባለፈ አጋንንት በገሃድ እየመጡ ያሰቃዩት ነበር:: ቅዱሱ ግን በትእግስት ኑሮ በዚህች ቀን ሲያርፍ ብዙ ተአምራት በበዓቱ ውስጥ ተገልጠዋል:: ይህንን ያዩት ደግሞ ከዻዻሱ ዘንድ ተልከው የቀበሩት አበው ናቸው::