ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ከገነት በተሰደደ ጊዜ #የአዳም ተስፋ አንቺ ነሽ፡፡ በግፍ የተገደለ #የአቤል የውሃቱ አንቺ
ነሽ፡፡ #የሴት ቸርነት አንቺ ነሽ፡፡ #የሄኖክ ሥራዎቹ ከክፉ ጥፋት የዳነባት #የኖህ መርከብ
#የሴም ቡራኬው ዕድል ፈንታውም አንቺ ነሽ፡፡
# የአብርሃም እንግድነት #የይስሃቅ መዓዛ #የያዕቆብም መሰላል አንቺ ነሽ፡፡
#ዮሴፍንም የምታረጋጊው አንቺ ነሽ፡፡
#የሙሴ ጽላት #ጳጦስ የተባለች የሲና ዕፅ በካህን #አሮን ልብስ የነበረች ጸናጽል
ዳግመኛም የበቀለች እና ያበበች ያፈራችም በትር አንቺ ነሽ፡፡ #የኢያሱ የምስክሩ ሐወልት
#የጌድዮን ፀምር #የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይ እና የዘይት ቀንድ አንቺ
ነሽ፡፡ የተመካባት #የዕሴይ ሥር #የአሚናዳብ ሠረገላ #የዳዊት መሰንቆ #የሰሎሞንም
አክሊል አንቺ ነሽ፡፡ የታጠረች ተክል የተዘጋች የውሃ ምንጭ አንቺ ነሽ፡፡ #የኤልያስ የወርቅ
መሶብ #የኤልሳዕ ጋን አንቺ ነሽ፡፡ #ኢሳይያስ ፅንስን ከድንግልና ጋር የተናገረልሽ #ዳንኤልም ያለሩካቤ መውለድን የተናገረልሽ አንቺ ነሽ፡፡ #ፋራን የምትባል #የዕንባቆም
ተራራ የተዘጋች #የሕዝቅኤል ምስራቅ የቤቴ-ልሔም ሕግ መውጫ #ኤፍራታ የምትባል
ምድር አንቺ ነሽ፡፡ #የሲሎንዲስ ዕፀ ሕይወት #የናሆምንም ቁስል የምታድን #የዘካርያስ
ደስታው #የሚልክያስ ንፅሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ፡፡
#ቅዱስ_ሚክያስ
ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ.ል. ክርስቶስ በ800 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ
ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው::
አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ 14 ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ
ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::
ሚክያስ ትውልዱ ከነገደ ሲሆን አባቱ ሞራት (ሞሬት)
ይባላል:: #ሚክያስ ማለት " #መኑ_ከመ_አምላክ - እንደ
እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!" ማለት ነው:: አንድም "መልአከ
እግዚአብሔር" ማለት ነው:: የአባቶቻችን ሁሉ ስማቸው
እግዚአብሔርን የሚሰብክ ነው::
ቅዱሱ ነቢይ ገና ልጅ እያለ #መላእክት ያነጋግሩት ነበር::
በዚህ ምክንያት ከሰው አይቀርብም:: ትክ ብለው ሲያዩት በፊቱ ላይ ብርሃን ቦግ ቦግ እያለ ይታይ ነበር:: በወጣትነት ዘመኑ
#እግዚአብሔር ለትንቢት ሲጠራው በእሺታ ታዘዘ:: በ3ቱ
ነገሥታት (በኢዮአታም: አካዝና ሕዝቅያስ) ዘመንም ትንቢቶችን
ተናግሯል:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን አስተምሮ
ገስጿል::
አንድ ቀን በቤተ ልሔም ሲያልፍ #የዳዊት_ከተማ ፈት ሁና:
ዳዋ በቅሎባት ቢመለከት አዘነ:: ወዲያውም ትንቢት
ተናገረላት::
"ወአንቲኒ #ቤተ_ልሔም ምድረ # ኤፍራታ : ኢትቴሐቲ
እምነገሥተ #ይሁዳ: እስመ እምኔኪ ይወጽዕ ንጉሥ:
ዘይርዕዮሙ ለሕዝብየ እሥራኤል::"
"አንቺም የኤፍራታ ምድር ቤተ ልሔም: የይሁዳ ነገሥታት
ከነገሡባቸው ከተሞች ከቶ አታንሺም:: ወገኖቼን እሥራኤልን
የሚጠብቃቸው ንጉሥ (መስፍን) ካንቺ ዘንድ ይወጣልና" አለ::
ይኸውም አልቀረ ለጊዜው ከሚጠት በሁዋላ ደጉ #ዘሩባቤል
ነግሦባታል:: በፍጻሜው ግን የባሕርይ ንጉሠ ነግሥት #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከንጽሕት #ድንግል_ማርያም ተወልዶባታል::
ቅዱስ ሚክያስ ወገኖቹን ሲያስተምርና ሲመራ ኑሮ: 7
ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ተናግሮ: በመልካም ሽምግልና:
በንጉሡ #ሕዝቅያስ ዘመን ዐርፏል:: ወገኖቹ ቀብረውታል::
ጌታም በክብረ ነቢያት ከልሎታል::
✿ቸር አምላከ ነቢያት የነቢያቱን መከራ አስቦ ከመከራ:
በእንባቸውም ከእንባ ይሰውረን:: ከተረፈ በረከታቸውም
አያጉድለን::