+♥#አባ_አብርሃም_ክቡር ገዳማዊ ♥+
ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ
ከዋክብት አንዱ ነው:: #ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ
ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው
ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው::
ሠርግ ተደግሶ: #ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር
አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ
በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን
እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ10 ዓመታት ተቀመጠ::
+በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር
አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ
ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ::
በቤት ውስጥ ከ6 ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም
የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው::
አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ
ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን (6 ዓመቷ ነበር) ለቤተ ዘመድ
አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን
በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና
ጸሎት ተወስኖ ለ10 ዓመታት ቆየ::
ተጋድሎ በጀመረ በ20 ዓመቱ #እግዚአብሔር ለሌላ
አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ #አባ_አብርሃምን
አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው::
ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት
ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው::
ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን
የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ #አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ
ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው
ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ
ውጪም ጣሉት::
እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን
መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ
ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ
ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው
እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት::
ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ
አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን
አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ
እነሱ እየጸለየ 10 ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ
አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት::
የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር
በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት
የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ (ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ) ወደ ጻድቁ
መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን
በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም
ለመኑት::
ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም
#በስመ_ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ
ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና
ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ ( #ስብሐት_ብጡል
) መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው
ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ::
+እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ #ማርያ ያስብ ነበርና
አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ
መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት
ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ::
ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት
ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ::
በዚህ ተስፋ ቆርጠው 2ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ::
ይልቁኑ እርሷ (ማርያ) ሴተኛ አዳሪ ሆነች::
በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ
አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ
መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና
ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ::
ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት::
ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ
ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ
አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ::
በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: #ማርያም
ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ
እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ
አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ
ኑሯል::
በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን
ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና
ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ
ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ
ተቀብሯል::
ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ
ከዋክብት አንዱ ነው:: #ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ
ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው
ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው::
ሠርግ ተደግሶ: #ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር
አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ
በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን
እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ10 ዓመታት ተቀመጠ::
+በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር
አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ
ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ::
በቤት ውስጥ ከ6 ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም
የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው::
አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ
ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን (6 ዓመቷ ነበር) ለቤተ ዘመድ
አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን
በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና
ጸሎት ተወስኖ ለ10 ዓመታት ቆየ::
ተጋድሎ በጀመረ በ20 ዓመቱ #እግዚአብሔር ለሌላ
አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ #አባ_አብርሃምን
አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው::
ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት
ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው::
ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን
የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ #አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ
ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው
ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ
ውጪም ጣሉት::
እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን
መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ
ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ
ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው
እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት::
ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ
አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን
አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ
እነሱ እየጸለየ 10 ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ
አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት::
የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር
በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት
የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ (ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ) ወደ ጻድቁ
መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን
በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም
ለመኑት::
ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም
#በስመ_ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ
ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና
ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ ( #ስብሐት_ብጡል
) መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው
ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ::
+እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ #ማርያ ያስብ ነበርና
አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ
መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት
ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ::
ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት
ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ::
በዚህ ተስፋ ቆርጠው 2ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ::
ይልቁኑ እርሷ (ማርያ) ሴተኛ አዳሪ ሆነች::
በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ
አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ
መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና
ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ::
ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት::
ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ
ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ
አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ::
በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: #ማርያም
ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ
እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ
አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ
ኑሯል::
በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን
ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና
ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ
ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ
ተቀብሯል::