ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
+#አባ_አብርሃም_ክቡር ገዳማዊ +
ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ
ከዋክብት አንዱ ነው:: #ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ
ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው
ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው::
ሠርግ ተደግሶ: #ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር
አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ
በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን
እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ10 ዓመታት ተቀመጠ::
+በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር
አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ
ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ::
በቤት ውስጥ ከ6 ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም
የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው::
አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ
ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን (6 ዓመቷ ነበር) ለቤተ ዘመድ
አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን
በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና
ጸሎት ተወስኖ ለ10 ዓመታት ቆየ::
ተጋድሎ በጀመረ በ20 ዓመቱ #እግዚአብሔር ለሌላ
አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ #አባ_አብርሃምን
አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው::
ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት
ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው::
ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን
የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ #አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ
ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው
ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ
ውጪም ጣሉት::
እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን
መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ
ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ
ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው
እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት::
ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ
አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን
አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ
እነሱ እየጸለየ 10 ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ
አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት::
የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር
በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት
የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ (ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ) ወደ ጻድቁ
መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን
በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም
ለመኑት::
ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም
#በስመ_ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ
ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና
ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ ( #ስብሐት_ብጡል
) መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው
ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ::
+እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ #ማርያ ያስብ ነበርና
አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ
መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት
ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ::
ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት
ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ::
በዚህ ተስፋ ቆርጠው 2ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ::
ይልቁኑ እርሷ (ማርያ) ሴተኛ አዳሪ ሆነች::
በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ
አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ
መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና
ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ::
ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት::
ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ
ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ
አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ::
በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: #ማርያም
ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ
እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ
አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ
ኑሯል::
በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን
ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና
ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ
ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ
ተቀብሯል::
✞✞✞ እንኩዋን ለካህኑ #ሰማዕት_አባ_ኦሪ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ኦሪ_ቀሲስ "
ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ
(በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) #ክርስቲያን መሆን ብቻውን
ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው
ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ #እረኛ_ካህን ሆኖ
መገኘት በጣም ከባድ ነበር::
ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና
በሊቀ ዻዻሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም
እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም::
በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ
የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ::
ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል:
ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም::
በጊዜው ( #በዘመነ_ሰማዕታት ) የነበሩ ካህናት የቤት
ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት
በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት
ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ::
ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ
ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ
#ስጥኑፍ (የግብጽ አውራጃ ናት) መጻሕፍትን የተማሩ:
ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ::
አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ
ጥሪት (ምናኔ) ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ
ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን"
ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ::
ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር:
በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል:: ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ #ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም
ከበው ይነጋገሯቸው ነበር::
#ሥጋውን_ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት
አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ
( #ሰማዕትነት ) በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው
በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ #ቤተ_እግዚአብሔር
ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና
ከቤተ ክርስቲያን ወጡ::
በቀጥታ የሔዱትም ወደ #ዐውደ_ስምዕ (የምሥክርነት
አደባባይ) ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "#ክርስቶስ
አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን
ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው" ሲሉ
በድፍረት ተናገሩ:: መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ
#አባ_ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በሁዋላም ወደ ጨለማ እሥር
ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ:: ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ
ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል::
በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል:: ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በሁዋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን
አግኝተዋል:: #በአክሊለ_ጽድቅ ላይ #አክሊለ_ካህናትን :
#በአክሊለ_ካህናትም ላይ #አክሊለ_ሰማዕታትን
ደርበዋል::
#አምላከ_ቅዱሳን_በአባቶቻችን_ጽናት_ያጽናን::_ጸጋ_በረከታቸውንም_ይክፈለን::
💚💛 #ቅድስት_አትናስያ 💛❤️
የዚህች ቅድስት ሕይወት በብዛት የእግዚአብሔርን ቸርነትና የንስሃን ፍጹምነት የሚያሳይ ነው:: ጥንተ ነገሩስ.እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ቅድስት አትናስያ ግብፃዊት ስትሆን የነበረችውም #መኑፍ
በሚባል አውራጃ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ይህ ዘመን
"ዘመነ ከዋክብት" ይባል ነበር:: ከቁጥር የበዙ ቅዱሳንም በዘመኑ ነበሩ:: ቅድስት አትናስያም ከክርስቲያን ወላጆች ተወልዳ:
እንደሚገባ አድጋ: ገና በወጣትነቷ ሁለቱም ወላጆቿ ሞቱባት:: ነገር ግን ብዙ ሃብት ትተውላታልና ምን
እንደምታደርገው ሃሳብ ሆናት:: #መንፈስ_ቅዱስ ግን
መልካሙን ሕሊና አደላትና አብርሃማዊ ሥራን ለመሥራት
ቆረጠች:: መጀመሪያ አገልጋዮችን አዘጋጀች:: እንደየ ወገኑ
ለእንግዶችና ለነዳያን ቤትን ሠራች:: በጐውን እድል
መርጣለችና ለብዙ ዓመታት ለነዳያን በማድላት: እንግዶችን
በመቀበል ተጠመደች:: በዚህ ሥራዋም እግዚአብሔርንም
ሰውንም ደስ አሰኘች::
ግብሯ እንዲህ ነው:: በሌሊት ጸሎት: በመዓልት ግን
እንግዶችን መቀበል: እግር ማጠብ: ማስትናገድ: ማስተኛት:
ስንቅ አሰንቆ መስደድ ነው:: በዚህ ግብሯ ከምንም በላይ የወቅቱን ጻድቃን አስደስታለች:: በዚያው ልክ ግን ዲያብሎስ ተቆጥቶ ይከተላት ጀመር::
በብዙ ጐዳና አልሳካልህ ቢለውም በክፉ ጐረቤቶቿ አማካኝነት ግን ተሳካለት:: የአካባቢዋ ሰወች ወደ እርሷ ተሰብስበው በብዙ ማታለል ከቅድስና ሕይወቷ ፈቀቅ
እንድትል አደረጉ:: እነርሱ መልካም ሥራዋን ያስተዋት በመልክ ቆንጆ ነበረችና
ይህንን ተጠቅመው ነው:: "ውበትና ሀብትሽን አታባክኚ"
ብለው ከጐዳና አስወጧት:: መጽሐፍ ክፉ ባልንጀርነትን
የሚቃወመው ለዛ ነው:: መልካም #ክርስቲያን ማለት
ባልንጀራውን የሚመርጥ ነው::
+የሚገርመው ያን ያህል እንግዳ ተቀብላበት ያላለቀ ገንዘብ
አሁን ግን ተመናመነ:: ክፉዎቹ ምክራቸውን ቀጠሉ:: አካሏን
እንድትሸጥ አሳምነው ሴተኛ አዳሪ አደረጉዋት:: ባንዴ ከዚያ
የቅድስና ከፍታ ወርዳ አካሏን ለዝሙት የምትሸጥ ሆነች::
+ነገሩን የሰሙ ገዳማውያን ሁሉ አዘኑ: አለቀሱላት:: ይልቁኑ
ለእነሱ የእናት ያህል ደግ ነበረችና ከዲያብሎስ ሴራ
ሊታደጉዋት ቆረጡ:: ከመካከላቸውም #ቅዱስ_ዮሐንስ_
ሐጺርን ለዚህ ተግባር መረጡ:: እርሱ በአጋንንት ላይ ስልጣን
ያለው ሰው ነውና::
እነርሱ ሱባ዗ ይዘውላት አባ ዮሐንስ ሐጺር ወደ መኑፍ
ከተማ ሔደ: ወደ ቤቷም ደረሰ:: ጠባቂዋን አስፈቅዶ ሲገባ
ለረከሰው ድርጊት የመጣ ሰው መስሏት ተዘጋጅታ ነበር:: አባ
ዮሐንስ ሐጺር ግን አጋንንትን ያርቅ ዘንድ እየዘመረ ገባ::
"እመኒ ሖርኩ ማዕከለ ጽላሎተ ሞት . . . በሞት ጥላ ሥር
እንኩዋ ብሔድ አንተ ከኔ ጋር ነሕና ክፉን አልፈራም" እያለ
ቀረባት:: (መዝ. 22)
ፈጠን ብሎ ከጐኗ ተቀምጦ ቅዱሱ ምርር ብሎ አለቀሰ::
አትናስያ ደንግጣ "ምነው?" አለችው:: "የአጋንንት ሠራዊት
በራስሽ ላይ ሆነው እየጨፈሩኮ ነው" አላት:: አስከትሎም
አጋንንቱን በጸሎቱ ቢያርቅላት በአንዴ ወደ ልቧ ተመለሰች::
ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው የሠራችውን ሁሉ ማመን
አቃታት:: ተስፋም ቆረጠች:: ቅዱስ ዮሐንስ ግን
"ግዴለሽም: ንስሃ ግቢ:: ፈጣሪ ይምርሻል" ብሎ
አሳመናት:: "እሺ አባቴ" ብላ ከቀደመው ዘመን ሥርዓት
ያለውን አንዱን ቀሚስ ለብሳ: ጫማ ሳትጫማ: ሌላ ልብስ
ሳትደርብ: ምንም ነገር ሳትይዝ ከቤት ወጣች::
ቤቷን አልዘጋችም:: ዘወር ብላ ወደ ሁዋላም አልተመለከተችም:: ቅዱሱን ተከትላ ጉዞ ወደ በርሃ ሆነ:: ያበእንክብካቤ የኖረ አካል እሾህና እንቅፋት: ብርድና ፀሐይ
ጐበኘው:: ሲመሽ እጅግ ደክሟታልና "እረፊ" ብሏት ሊጸልይ
ፈቀቅ አለ:: መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ #መላእክት ከሰማይ የብርሃን
ዓምድ ዘርግተው አንዲትን ነፍስ በዝማሬ ሲያሳርጉ አየ::
"የማን ነፍስ ትሆን" ብሎ ወደ #አትናስያ ሲሔድ መሬት ላይ
ዘንበል ብላ ዐርፋ አገኛት:: ቅዱሱም "ጌታ ሆይ! ምነው
ለንስሃ እንኩዋ ብታበቃት?" ብሎ አለቀሰ:: ፈጣሪ ከሰማይ ተናገረ:- "ገና ከቤቷ ተጸጽታ ስትወጣ ነው
ይቅር ያልኩዋትና ደስ ይበላችሁ" አለው:: ይህንን የአምላክ
ቃል ሁሉም ገዳማውያን ሰምተው እጅግ ደስ አላቸው:: "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: 7 ጊዜ ይነሳል::"
@dn yordanos
✞✞✞ እንኩዋን ለካህኑ #ሰማዕት_አባ_ኦሪ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ኦሪ_ቀሲስ "
ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ
(በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) #ክርስቲያን መሆን ብቻውን
ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው
ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ #እረኛ_ካህን ሆኖ
መገኘት በጣም ከባድ ነበር::
ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና
በሊቀ ዻዻሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም
እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም::
በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ
የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ::
ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል:
ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም::
በጊዜው ( #በዘመነ_ሰማዕታት ) የነበሩ ካህናት የቤት
ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት
በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት
ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ::
ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ
ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ
#ስጥኑፍ (የግብጽ አውራጃ ናት) መጻሕፍትን የተማሩ:
ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ::
አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ
ጥሪት (ምናኔ) ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ
ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን"
ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ::
ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር:
በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል:: ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ #ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም
ከበው ይነጋገሯቸው ነበር::
#ሥጋውን_ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት
አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ
( #ሰማዕትነት ) በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው
በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ #ቤተ_እግዚአብሔር
ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና
ከቤተ ክርስቲያን ወጡ::
በቀጥታ የሔዱትም ወደ #ዐውደ_ስምዕ (የምሥክርነት
አደባባይ) ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "#ክርስቶስ
አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን
ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው" ሲሉ
በድፍረት ተናገሩ:: መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ
#አባ_ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በሁዋላም ወደ ጨለማ እሥር
ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ:: ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ
ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል::
በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል:: ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በሁዋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን
አግኝተዋል:: #በአክሊለ_ጽድቅ ላይ #አክሊለ_ካህናትን :
#በአክሊለ_ካህናትም ላይ #አክሊለ_ሰማዕታትን
ደርበዋል::
#አምላከ_ቅዱሳን_በአባቶቻችን_ጽናት_ያጽናን::_ጸጋ_በረከታቸውንም_ይክፈለን::